ጡሩንባ ሚዲያ @tiruba_media Channel on Telegram

ጡሩንባ ሚዲያ

@tiruba_media


ጡሩንባ ሚዲያ (Amharic)

ጡሩንባ ሚዲያ ከኃምሌ እምነት እና እኩል እጅግ ጋር በሚፈልገው የህይወት ነጋዴዎች የሚኖረው የኢትዮጵያ ገጽ የበለጠ መረጃ። ይህ በትምህርቱ ያለ ስራ ሰጭና መንገድ አዲስ ሰልፍ የሚል ነኝ። የጡሩንባ ሚዲያ ሊያሳይ የሚገባውን የትምህርት ዝግጅት እና ኢትዮጵያዊውን መረጃ አዳምጠው ተሳታፊ እንዳለ የታዘዙበትን ወረቀት ያቀርቡ እንወስዳለን። ከህብረት የቆጣሁበት አባባሎች ተለዋዋጮላ ፊሻሡን ካናገደው እራሱ ትፈቺ።

ጡሩንባ ሚዲያ

19 Nov, 06:09


የድል መረጃ!!


መነሻውን ከአለፋ ወረዳ አፀደ ማርያም ከተማ በማድረግ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ሃይል ላይ በተደረገው ጥቃት አስደናቂ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ፋኖ በጎንደር የአድዋ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ተስፋ ጌታሁን ገለፀ።

በአርበኛ ሳሙኤል ባለድል የሚመራው የአድዋ ክፍለጦር በቀጠናው በስፋት በመንቀሳቀስ እየወሰደ ባለው የመልሶ ማጥቃት ኦፕሬሽን የጠላትን አከርካሪ መምታቱ ተነግሯል።

በዚህም በዛሬው ትናንትናው የአገዛዙ ሃይል በቀጠናው በምትገኘው አፀደ ማርያም ከተማ ተነስቶ በመንቀሳቀስ የንጋት ጮራ ብርጌድ ሻለቃ አንድን ለማፈን ሙከራ ቢያደርግም የአፀፋ ምላሽ በማድረግ ዋጋውን ሰጥተውታል ብሏል ቃል አቀባዩ::

ጡሩንባ ሚዲያ

18 Nov, 10:41


የድሉ ዜና | የአማራ ፋኖ በጎንደር #fano #amhara @Tirunba1
https://youtube.com/watch?v=UhWe1Inae8c&si=KkA1H_1hFJxnsHvE

ጡሩንባ ሚዲያ

15 Nov, 04:44


የአማራ ሕዝብ ትግል መሠረቱን በፅኑ አለት ላይ ገምብቷል።

ትግሉ አማራዊ ማንነቱን አሳልፎ ላለመስጠት የሚደረግ የአትግደሉኝና ዘርፈ ብዙ ሕልውናን የማስጠበቅ ንጡህና የተቀደሰ የነጻነት የትግል
መስመር ነው።

ይህ ትግል ሲያሻህ የምትገባበት ሳይመችህ
የምትወጣበት አይደለም። ትግሉ በቃ የመኖርና ያለመኖር ዕንቁም መርገምትም የሆነ ነው።
ይህንን ዕድል ከተጠቀምንበት አማራ የአባቶቹን የአሸናፊነት መንገድ የሚደግምበት፤ ዕድሉን ካልተጠቀምንበት ደግሞ ዘልአለማዊ ባርነትን በፀጋ የምንቀበልበት መርገምታዊ ዕሳቤ ነው።

ነገር ግን ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር ትግላችን በማሸነፍ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው።
አማራም አንድ ሆኖ ይህንን ነውረኛና ጨካኝ አገዛዝ፣ ሆዳም አማራ፣ ፊደላዊ ነኝ ባይ ጸረ ፊደል አማራ፣ መሬት ላይ ከፋፋይነትን የሚተነፍሱ ፅንፍ የሄዱ ጎጠኞችን ማምበርከክ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው።  አዲሱ ግዮናዊ የአማራ ትውልድ ጭምብል ላጠለቁ ሁሉ ምንም አይነት ይሉኝታ ሳይሰማው ዝቅታዬ አማራነት ብቻ ነው ሲል ለማሳወቅ ይሰራል።

የጠላትን አጀንዳ ይዘው ለመጡ ሆዳም አማሮች ከጠላት እኩል ይፈርጃቸዋል። ሆዳም አማሮች ያላቸውን የመጨረሻ ዕድል አማራ በመሆን ቢጠቀሙበት ሰናይ ነው። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በትግል ስም የፖለቲካ ንግድን እናጧጡፋለን የሚል አካል ካለ ከርኩሳዊ መንገዱ ቢታቀብ ይጠቅመዋል።

44 ጊዜ አስረግጠን የምንናገረው ይህንን ትግል አማራ በአሸናፊነት እንደሚወጣ ለናኖ ሰከንድ አንጠራጠርም። ሥለሆነም የአማራ ሆዳሞች የሚያጠፋችሁን መንገድ ትታችሁ የሚያድናችሁንና ከታሪክ ተጠናቂነት ነጻ የሚያደርጋችሁን ሰናይ መንገድ ብትመርጡ የተሻለ ነው።

አማራ በልጆቹ የተባበረ ክንድ ጠላቱን ያምበረክካል
፩ አምሐራ


©Hakealew Alebachew

ጡሩንባ ሚዲያ

15 Nov, 04:43


"የኢትዮጵያ ሕዝብ የዐማራ ሕዝብ ዕንባ [እና ደም] በዋንጫ ቢሰጣቸዉ የማይጎፈንናቸዉን የብልጽግና ሥርዓት ቁንጮዎች በቃችሁ ሊላቸዉ ይገባል።"


ዶ/ር ወንድወሠን አሰፋ

ዛሬ በፍርድ ቤት የቀረበበትን የፈጠራ ክስ ሲቃወም የተናገረው።

ጡሩንባ ሚዲያ

14 Nov, 15:23


ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ


ዛሬ በፍርድ ቤት ያደረገው ታሪካዊ ንግግር

ከዚህ በመቀጠል በተከሰስኩበት ክስ የእምነት ክህደት ቃሌን እሰጣለሁ።
በቀዳሚነት የተከሰስኩት ጉዳይ የአማራ ህዝብ እኩል ከሌሎች ብሄሮችና ህዝቦች ጋር የአገር ባለቤት ሆኖ እያለ አገር ተወስዶበታል ብሎ ተናግሯል የሚል ነዉ።ክሴ ይሄን የሚል በመሆኑ አሁን ለፍርድ የቀረበዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ነዉ ማለት ነዉ።

የአማራ ህዝብ ላለፉት ሰላሳ አራት አመታት ፀረ አማራ ሀይሎች ተደራጅተው እና ተቀናጅተው ስልታዊ እና መንግስታዊ ጥቃት እያደረሱበት ያሉ ህዝብ ነዉ።
የአማራ ህዝብ የአገር ባለቤትነቱንበግልፅ በአደባባይ የተነጠቀዉ በ1983 ዓ.ም አማራ ጠል ሀይሎች የመንግስት ስልጣንን ተቆጣጥረዉ ባደረጉት የ ሰኔ 1983ቱ የቻርተሩ ጉባኤ ነበር።
ጉባኤው ያለምንም የአማራ ህዝብ ዉክልና የተካሄደ መሆኑን የስርአቱ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በአደባባይ የመሰከረው ሀቅ ነዉ።በዚህ የቻርተር ጉባኤ የተመሰረተው የሽግግር መንግስት  ባደረገው የክልል አከላለል ዉስጥ ምንም አይነት የአማራ ህዝብ ዉክልና  ያልነበረው ሲሆን በዚህ የሽግግር መንግስት ዘመን የተዘጋጀው ህገመንግስትም የአማራን ህዝብ በማዉገዝ ተጀምሮ በማዉገዝ ያለቀ መሆኑን የቻርተሩ ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ,የሽግግር ም/ቤቱ ቃለጉባኤዎች,የህገመንግስት ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ዘላለማዊ ምስክር በመሆኑ ያስረዳሉ ።
በዘመኑ ትህነግ/ኢህአዴግ በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙት አድሏዊ ድርጊቶች ,መፈናቀሎች,የንብረት ዉድመት,የዘር ፍጅትእና አገር አልባነት ልለፈዉና የዛ ስርአት ቀጥተኛ ወራሽ የሆነውን የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመዉን እና እየፈጸመ ያለዉን በደል ልግለፅ።

የብልግና መንግስት በአማራ ህዝብ ተጋድሎ ወደ ስልጣን የመጣ ቢሆነም ህገመንግስታዊ ማሻሻያን ጨምሮ ፀረ አማራ የሆኑትን የመንግስት ፖሊሲዎች አስተካክላለሁ ብሎ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተግባር ግን አማራ ጠል መሆኑን ያስመሰከረዉ ጊዜ ሳይወስድ ነበር።
የብልፅግና መንግስት ከ ትህነግ ኢህአዴግ የወረሰውን የፌደራል እና የክልል ህገመንግስቶች ,ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ይዞ ቀጥሏል።ከ 50 በላይ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም ፀረ አማራነትን የሚቀሰቅሱ መፃህፍት አሳትሟል ።በምርምር መፅሄቶች ስም አማራ ጠልነትን ሰብኳል።በመንግስትነቱ በሚያስተዳድራቸው በኦሮምያ ቱሪዝም ቢሮ,በኦሮምያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት,በኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅቱ ስር በሚታተሙ መፅሄትና ጋዜጦቹ በአማራ ህዝብ ላይ ለአመታት የቆየ የጥላቻ ዘመቻ አካሂዷል ።ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፀረ አማረ ንግግሮች እና ትንኮሳዎች ተደርገዋል።

በተጨማሪም የብልፅግና መንግስት የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ዉክልና እንዳይኖረው በማድረግ ዛሬ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ዉክልና የለዉም ።

ከመንግሥት የስራ ሀላፊነት ጠርጎ በማዉጣት አድሎአዊ አሰራርን በማስፈን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በማፈናቀል ፣ በቢሊዮኖች የሚገመት የአማራን ህዝብ ሀብትና ንብረት በማውደም እንዲሁም ዘግናኝ የሆነ እንኳን ሊያዩት ሊሰሙት እንኳ የሚከብድ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም አድርጓል ። ይህ የዘር ፍጅትበመላው ኢትዮጵያ በሶማሌ ፣ በኦሮሚያ ፣ በትግራይ ፣ በሲዳማ ፣ በቀድሞ የደቡብ ክልል ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች የተፈፀመ ነው ።
ለዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአይን ምስክሮች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ ጥምረት እንዲሁም አለም አቀፍ የሆኑት የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የሂውማን ራይትዎችን ዘገባዎች በማየት መረዳት ይቻላል ።
  ጉዳዩን ሊከታተል ይችላል ተብሎ ይታሰብ የነበረው የብልፅግናው የአማራ ክልል መንግሥት ደግሞ እንኳን የአማራን ህዝብ ሊታደግ የገዛ ስልጣኑን የማያውቅ ፣ የፖለቲካ ነፃነቱን አሳልፎ የሰጠ እንዲሁም ከውሳኔ ሰጪነት ወደ ፈፃሚነት የወረደ ነው ። (ከክልሉ ውጪ ያሉ አማራዎች እንታገላቸዋለን እንጂ አንታገልላቸውም)ከማለት የደረሰ ሎሌ ነዉ።

   በተደጋጋሚ ባጋጠሙ ጉዳዮችም ተፈትኖ የወደቀ ለምሳሌ በአማራ ልዩ ሃይል መፍረስ ፣ በፕሪቶሪያ ድርድር ፣ በሱዳን ወረራ ፣ በአጣዬ እና ሸዋሮቢት ፍጅት የአማራን ህዝብ መብት ማስከበር ያልቻለ ለተፈናቃይ ዱላ ለዘር ፈጂዎች ግን ካባ የሚሸልም ስብስብ ነው ።

     የፌደራል መንግሥቱ ደግሞ ያለምንም እፍረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ፣ አቃቢ ህጉ ፣ መርማሪው ፣ ደህንነቱ ፣ የፍርድ ቤት አስተዳደር በአጠቃላይ የአንድ ብሔር/ሀይማኖት አባላት በመሆን ህግን የማጥቂያ መሣሪያ በማድረግ የአማርን ሕዝብ ልጆች ያጠቃል ።
   የአማራ ሕዝብ ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያት የሀገር ባለቤትነቱ የተወሰደበት ፣ ሀገሩን የተቀማ በመሆኑ ፣ ድርጊቱም ሥርአታዊና መንግሥታዊ ለመሆኑ የሚመሠክሩ በርካታ ማስረጃዎች ያሉ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ከዚህ የህልውና አደጋ ለመውጣት መንቃት ፣ መደራጀትና እራስን ከጥቃቶች መከላከል ይገባዋል የሚል የፀና አቋም ያለኝ በመሆኑ ይሄንን ዘረኛ እና ነውረኛ አንባገነን ሥርዓት ለመጣል ትግል እንደሚያስፈልግ እምነቴ ነው ።

በጭብጦቹም ላይ

   * የሸዋ ፋኖን በማደራጀት በኩል የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ
  *የአማራ ፋኖን ወደ አንድነት ለማምጣት ሲባል የተመሠረተው አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኜ ሠርቻለሁ
  *የአማራ ፋኖ ምክርቤት እንዲመሠረት የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ

  * አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችና የብልፅግና መንግሥት እመራበታለሁ በሚለው ህገመንግስት በሰፈሩት ሰብአዊና እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹን መሰረት በማድረግ የህዝቤን ግፍ እና በደል ለማስቆም በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ ታግያለሁ።

*የሰራሁት በሙሉ በግልጽ በአደባባይ የተፈፀመ እንጂ ምንም አይነት ህቡዕ ድርጅት አቋቁሜ አልሰራሁ።

*በህቡዕ አደረጃጀት ተፈፀሙ የሚሉትን ተግባራት አላዉቅም።አልፈፀምኩም

የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ በደል በደንብ ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ "የአማራ ህዝብ እንባ በዋንጫ"ቢሰጣቸዉ የማይጎፈንናቸዉን የብልፅግና ስርአት ቁንጮዎች በቃችሁ ሊላቸዉ ይገባል።

በተጨማሪም የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ለነፃነት ለእኩልነትና ለፍትህ የሚደረግ ትግል እንጅ ጠላቶቻችን እንደሚያወሩት ሌላዉን ለመጨፍለቅ የሚደረግ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ደግፎ እንዲቆም እጠይቃለሁ።

አለማቀፉ ማህበረሰብም የአማራ ህዝብ እየተፈፀመበት ያለዉን የዘር ፍጅትና መፈናቀል ቸል በማለቱ በጣም እያዘንኩ ለአምባገነኑ መንግስት ጅምላ ጨራሽ ድሮዎኖች እና ተተኳሾችን የሚያቀብሉ አገራት ታሪክና እና እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣችኋል እላለሁ።

አመሰግናለሁ ።
ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ

ጡሩንባ ሚዲያ

11 Nov, 07:25


ዓለም በር

የአማራ ፋኖ በጎንደር በተመሥገን ውባንተ የሚመራው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና በሻምበል አምሣሉ የሚመራው ጉና ክፍለ ጦር እንዲሁም ፀዳሉ ደሴ የሚመራው የጎንደር ዕዙ  ጀነራል ነጋ ተገኝ ክፍለ ጦር ዓለም በር ላይ በአንድ የአማራነት ሥሜትና መተማመን የአራዊት ሠራዊቱን ወታደር ለሠዓታት የፈጀን ውጊያ ፈጽመውበታል።

የወገንን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ወታደር ወደ ደብረ ታቦርና ወረታ እግሬ አውጭኝ ብሏል። በዚህ ግምባር የገባው የጠላት ጦር አብረውት ሲንከራተቱ የነበሩ ጓዶቹን አስከሬን ይዞ መውጣት አልቻለም። የጠላት ጦር የመዋጋት ሥነ ልቦናውን ተሰልቧል። ጠላት በአካልም በቁሥም ኪሣራ ላይ ወድቋል።

እሥቴ

በዚ ዕለት ከእሥቴ ወጥቶ ወደ ምክሬ፣ ፀዶዬና የተለያዩ ከተማዎችን መግባት ያለመው የጠላት ጦር በጉና ክፍለ ጦር ምክትል ወታደራዊ አዛዣ አርበኛ ቢራራ ደምሤ እየተመራ ሾለክትና ደንጎልት ላይ ውጊያ ሢያደርግ ውሏል።

በዚህ አውደ ውጊማ ድል የግላቸው የሆኑት እሥቴ ዴንሳ ብርጌዶች ከእልህ አሥጨራሽ ውጊያ በኋላ ጠላትን ከደንጎልትና ሾለክት ወደ መካነ እየሱስ ከተማ ከትተውታል።

መተማ

የምዕራብ ጎንደሯ መተማ በአማራ ፋኖ በጎንደር አጣናው ዋሤ ክፍለ ጦር በባሻ ጥጋቡ መንፈሥ ተበረታትተው የአቢይ ሸኔን ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት ሲያሳድዱት ውለዋል።

 የአቢይ አሕመድ አራዊት ሠራዊት በቀጠናው ላይ በብዛት ከገባ ሣምንታት ተቆጥረዋል። ጠላት የመጨረሻ አማራጬ ያለውን የምድርና የአዬር ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል። ነገር ግን ትግሉን በፍትሕ መሠረት ላይ ያጸናው የአማራ ፋኖ ብርታትና ጥንካሬን እንጅ ድክመትን አላሥተናገደም። ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝምና የአማራ ፋኖ ከወገን ጠላት ራሱን እየጠበቀና የለዬለት ፋሽሥት አገዛዙን እያብረከረከ ይገኛል። ጠላት ያሰበውና የደረሰበት ውጤት የውቅያኖሥና የኩሬ ልዩነት አለው።

ጠላት አሉኝ ያላቸውን ዘመናዊ ሠላዮችና መረጃዎች በገፍ አሰማርቷል። ነገር ግን ይህ ሁሉ የጠላት አካሄድ ከአማራ ፋኖ ዓይን የተሰወረ አልሆነም።
ድላችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን



አማራ ፋኖ በጎንደር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ

አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

10 Nov, 16:46


ሰበር ዜና!


ሁለቱ ዕዞች አስደናቂ ድል አስመዘገቡ!

የአማራ ፋኖ በጎንደር ሜጄር ጀነራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሻለቃ ተመስገን ውባንተ አባተ የሚመሩት እና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የጀነራል ነጋ ተገኝ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሻለቃ ፀዳሉ ደሴ ሁለቱ ክፍለጦሮች ከሃሙስ እለት ጀምሮ እያደረገው ባለው የመደበኛ ውጊያ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ኪሳራን እያደረሰ ነው።

ሆኖም እንደሚያወቀው ሃሙስ እለት በተደረገው የደፈጣ ጥቃት 13 የፖሊስ አባላትና 7 ሚኒሻዎች በዕለቱ ግባዓተ መሬታቸው ተፈፅሟል። እስከዛሬው ቀን ድረስ የመከላከያው እና የአድማ ብተና አስከሬኖችንም በፓትሮል እያጓጎዘ እንደሚገኝ ኢትዮ 251 ሚዲያ ለማወቅ ችላለች።

የአገዛዙ ሰራዊት ሳያስበው ወደጫካው በፋኖወቹ ተስቦ የገባው የመሐመድ ተሰማ ሰራዊት ከክንደ ብርቱው የአማራ ፋኖ ጎንጀር ዕዝ ስልጠና መምሪያ ኃላፊና በጀነራል ነጋ ክፍለጦር አዛዥ ሻለቃ ፀዳሉ ደሴ እጅ አምልጦ መፈርጠጥ እንዳልቻለ ተገልጿል።

የጀግናው ሜጀር ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር አናብስት ልጆች ጋር በጥምረት እየተካሄደ ባለው በዚህ ታሪካዊ ተጋድሎ ከአምስት በላይ ዲሽቃ በማሰለፍ መሬት ላይም በተቀበረ ፈንጂ እንዲሁም በሞርታር የታገዘው ውጊያ ለማድረግ ቢሞክርም አገዛዙ ጠላትን ማርበድበድ ተችሏል፤
በዚህም ውጊያ ከእግሬኛ ተዋጊ ውጭ  ከአራት በላይ የዲሽቃ ተኳሾችን አንድ የአስር አለቃ አዛዥን እስከመጨረሻው  መሸኘት ተችሏል፤ አሁንም የብልጽግና ሰራዊት ተከቦ እየተቀጠቀጠ ይገኛል።

 የጠላትን አስከሬንም ገበሬው በሃዘኔታ እያነሱ በክብር መቅበራቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።



አማራ ፋኖ በጎንደር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ጡሩንባ ሚዲያ

10 Nov, 00:26


ደጎማ

የብርሐኑ ጁላ ጦር ወታደራዊ መቀመጫውን ደጎማ ላይ አድርጎ ወደ አርባያ፣ጉኋላ፣ ማክሰኝት፣ ሚካኤል ደብር፣ ኪንፋዝ በገላና አምባ ጊዎርጊሥ እየተወረወረ ወገንን ለማጥቃት ይሞክራል።

👉በጥቅምት 29/2017ዓ.ም ጠላት ሌሊት ላይ ከደጎማ ተነሥቶ ወደ አርባያ በለሣ መንቀሳቀሱን የሰሙት የአማራ ፋኖዎቹ የሀብቴ ወልዴና የባዬ ቀናው ልጆች ወረሃላ ላይ ደፈጣ አድርገውበታል። የመጣው የጠላት ጦር አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።

የመጣው ኃይል ከተመታ በኋላ ተጨማሪ ኃይል ከደጎማ ሢመጣ የደፈጣው ውጊያ ከደፈጣ ወደ መደበኛ ውጊያ ተቀይሯል። በዚህ አውደ ውጊያ የተለያዩ ዕዞች አንድነትን ፈጥረዋል። መዳኛውም አማራዊ አንድነት ብቻ እንደሆነ አውቀዋል።

በዚህ ውጊያ የተሳተፉ፦
1.በሻለቃ አንተነህ ብርሐን የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር ጥቁር አምበሳ ብርጌድ
2.የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካላት በአርበኛ ሚናሥ አለማየሁ የሚመራው ዳግማዊ ቴዎድሮሥ ብርጌድና በሻምበል ሙሉሰው የሚመራው ነብዩ አሣምነው ብርጌድ የሆኑት ጎንደር ዕዞች ናቸው።

👉በጥቅምት 30/2017ዓ.ም በሻለቃ አንተነህ ብርሃን የሚመራው ጥቁር አምበሳ ብርጌድ ከደጎማ ወደ አርባያ እንዲሁም ከአርበያ ደጎማና ወደተለያዩ የአርባያ በለሣ የገጠር ወረዳዎች ለመንቀሳቀሥ የወጣውን የጠላት ጦር የባዬ ቀናው ልጆች በተጠና አውደ ውጊያ ያሰበውን እንዳይፈጽም አድርገውታል።

አለፋ

የብርሐኑ ጁላ ጦር ከአለፋዋ ዋና ከተማ ሻውራ ከተማ ከሌሊቱ 7:00 ተነሥቶ ወደፋኖዎች መጃረሻ ተንቀሳቅሷል። የአማራ ፋኖ በየትኛውም ጋዜና ሁኔታ ሠረጃው ሁሉ ከጠላት በላይ ሆኗል።

ወገን ልብ በል ጠላት እየተንቀሳቀሰ ያለው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ዕንቁ ሥጦታ የሆነው አርበኛ ሣሙኤል ባለዕድል ወዳለበት ነው። አድዋ ክፍለ ጦር ዋና ወታደራዊ አዛዡ አርበኛ ሣሙኤል ባለዕድል ነው። ሣሚ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ወታደራዊ አዛዥና ምክትል ሰብሳቢም ነው። ሣሚ በየትኛውም መንገድ ዕይታው ንሥራዊና አማራዊ ነው። አማራነት ማንን ይመሥላል ከተባለ ተጠየቁ ሣሙኤል ባለዕድልን ነው መልሱ።

እንግዲህ ጠላት የተንቀሳቀሰው የአድዋ ክፍለ ጦር አንዲት ሻለቃ ወዳለችበት መዳረሻ ነው። ጠላት የተንቀሳቀሰው አፀደ ማርያም ያለችውን የንጋት ጮራ ብርጌድ አካል የሆነችውን አንዲት ሻለቃ ለማፈን ነበር። ነገር ግን የአማራ ፋኖ መረጃው ደርሶታል። ጠላት አገር አማን ብሎ ሢከንፍ ሌሊት 10:00 ላይ በደፈጣ ርምጃ ተወሰደበት። ውጊያው ጠዋት ላይ ከደፈጣ ወደ መደበኛ ውጊያ ተቀይሯል።

የደነገጠው የጁላ ጦር አጋዥ ኃይል ከሻውራ ወደ አፀደ ላከ። አሁንም ንስሮቹ ጠላትን ሢያደባዩ ሌሎች 2 ሻለቃዎች ወደ ወረዳዋ መቀመጫ ሻውራ ገብተዋል። ከባባድ የሚባሉትን ምሽጓች ሰባብረዋል። ከተሰበሩት ከባባድ ምሽጎች መካከል ማንዴላ ሠፈር፣ ማርያም፣ ኬላና አቦዬ ይገኙበታል። ከአፀደ ማርያሙ ውጊያ ተገርፎ ወደ ሻውራ የተመለሰው የጠላት ጦር ሻውራ ላይም ሢመለሥ ከፍተኛ ርምጃ ተወሥዶበታል።

የአማራ ፋኖ ከዕለት ዕለት ሥነልቦናው የጠነከረ፣ ትጥቁ የተሟላ፣ ወታደራዊ ጥበብን እየተማረ፤ የፖለቲካ ሴረኞችን እየለዬ፣ አንድ አማራነትን እየተገበረ ጎጠኞችን ለሕዝብ እየገለጠ ሕዝባዊነቱን በተጨባጭ ለወገንም ለጠላትም እያሳዬ ነው።


አማራ ፋኖ በጎንደር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ

አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

08 Nov, 18:07


ሥሜን በጌምድር ጠቅላይ ግዛት
ጥቅምት 29/2017ዓ.ም

ዓለም በር

በፀዳሉ ደሤ የሚመራው የጎንደር ዕዙ  ጀነራል ነጋ ተገኝ ክፍለ ጦር እና በአማራ ፋኖ በጎንደር (በተመሥገን ውባንተ የሚመራው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርና በሻምበል አምሣሉ የሚመራው ጉና ክፍለ ጦር ዓለም በር ላይ በአንድ የአማራነት ሥሜትና መተማመን የአራዊት ሠራዊቱን ወታደር ለሠዓታት የፈጀን ውጊያ ፈጽመውበታል።
የወገንን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ወታደር ወደ ደብረ ታቦርና ወረታ እግሬ አውጭኝ ብሏል። በዚህ ግምባር የገባው የጠላት ጦር አብረውት ሢንከራተቱ የነበሩ ጓዶቹን አሥከሬን ይዞ መውጣት አልቻለም። የጠላት ጦር የመዋጋት ሥነ ልቦናውን ተሰልቧል። ጠላት በአካልም በቁሥም ኪሣራ ላይ ወድቋል።

እሥቴ

በዚ ዕለት ከእሥቴ ወጥቶ ወደ ምክሬ፣ ፀዶዬና የተለያዩ ከተማዎችን መግባት ያለመው የጠላት ጦር በጉና ክፍለ ጦር ምክትል ወታደራዊ አዛዣ አርበኛ ቢራራ ደምሤ እየተመራ ሾለክትና ደንጎልት ላይ ውጊያ ሢያደርግ ውሏል። በዚህ አውደ ውጊማ ድል የግላቸው የሆኑት እሥቴ ዴንሳ ብርጌዶች ከእልህ አሥጨራሽ ውጊያ በኋላ ጠላትን ከደንጎልትና ሾለክት ወደ መካነ ኢዬሡሥ ከተማ ከትተውታል።

የምዕራብ ጎንደሯ መተማ በቁርጠኛ ልጆቿ አጣናው ዋሤ ክፍለ ጦር በባሻ ጥጋቡ መንፈሥ ተበረታትተው የአቢይ ሸኔን ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት ሢያሣድዱት ውለዋል።

        የአቢይ አሕመድ አራዊት ሠራዊት በቀጠናው ላይ በብዛት ከገባ ሣምንታት ተቆጥረዋል። ጠላት የመጨረሻ አማራጬ ያለውን የምድርና የአዬር ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል። ነገር ግን ትግሉን በፍትሕ መሠረት ላይ ያጸናው የአማራ ፋኖ ብርታትና ጥንካሬን እንጅ ድክመትን አላሥተናገደም። ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝምና የአማራ ፋኖ ከወገን ጠላት ራሱን እየጠበቀና የለዬለት ፋሽሥት አገዛዙን እያብረከረከ ይገኛል። ጠላት ያሰበውና የደረሰበት ውጤት የውቅያኖሥና የኩሬ ልዩነት አለው። ጠላት አሉኝ ያላቸውን ዘመናዊ ሠላዮችና መረጃዎች በገፍ አሰማርቷል። ነገር ግን ይህ ሁሉ የጠላት አካሄድ ከአማራ ፋኖ ዓይን የተሰወረ አልሆነም።

ድላችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን

አማራ ፋኖ በጎንደር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ

አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

03 Nov, 22:15


በዛሬው ዕለት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም

ከባንዳነት ተግባሩ አልመለስ ያለው የሚሊሻ አድማ ብተናና መከላከያ ጥምር ጦር በጠገዴ ረመጦች ተደመሰሰ።

የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ ተከዜ ክ/ጦር በጠገዴ ወረዳ ግጨው ከተማ ላይ የመሸገውን ጥምር ጦር ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀሩ 67 ያህሉን እስከ ወዲያኛው ሸኝተው፣ 43 ያህሉን ቁስለኛ፣ አድርገው ቀሪው ፈርጥጦ ብትንትኑ መውጣቱን ማረጋገጥ ተችሏል። በአርበኛ አበባው አማረ የሚመራው የተከዜ ክ/ጦር ነበልባሎች ከሌሊት 10:00 የጀመረ  በሠራው አስደናቂ ኦፕሬሽን ግጨው ከተማን በቁጥጥር ሥር በማድረግ የጠላትን ቅስም መስበር ተችሏል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

27 Oct, 16:14


#ጎንደር❗️

የሜጀር ጀነራል ዉባአንተ አባተ ልጆች ዛሬም ለሀቅ እንደቆሙ ነው። ጀግና መሪን ተክቶ ያልፋል። ዛሬ በጎንደር ሲማዳ የሰሩት ታሪክ ለዘላለም ተመዝግቧል። ከዉስጣችን የተሰገሰጉ ጥቁር አማራዎችን ማስወገድ አስፈላጊ ነው።
ዛሬ ታሪክ ተሰርቷል💪💪💪
17/2/17 ዓ.ም


ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

ጡሩንባ ሚዲያ

27 Oct, 16:02


#የአርበኛው ባዬ ቀናው  ልጆች ጠላትን እስክስ እያስባሉት ነው‼️

በጎንደር ደብረ ታቦር በአገዛዙ ሀይልና በህዝብ ልጅ ፋኖ  ከፍተኛ ውጊያ እየተካሔደ መሆኑ ተሰምቷል።

የአማራ ጠሉ አገዛዝ ሰራዊት   ዙ-23 ጨምሮ ሌሎች የቡድን መሳሪያዎችን እየተጠቀመ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን  ጠላት ተጨማሪ ሀይል ወደ ቦታው እያስጠጋ መሆኑ ተገለጿል።

ድል ለህዝብ ልጆች!!
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!


የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

24 Oct, 21:00


🔥ወልቃይት ጠገዴ ሠቲት ሑመራ ዞን እርጎዬ ከተማ (ከሶሮቃ ወደ አብራጅራ የሚወሥደው መንገድ ላይ) ልዩ ሥሙ 5 ቁጥር የተባለ ቦታ ላይ በሻለቃ አበባው አማረ የሚመራው ተከዜ ክፍለ ጦር በነጻነት ብርጌድ  በወሰደው ልዩ የደፈጣ ውጊያ ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ተደምስሷል። በቁሥና በአካል ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።

  በተመሣሣይ በዚሁ ዕለት ጎቤ ከተማን ለመያዝ የመጣው የአገዛዙ ጥምር ጦር  በተከዜ ክ/ጦር ሥር የሚገኘው ጎይቶም ርሥቀይ ብርጌድና በሶተኛው አበበ ካሤ ብርጌድ በሕብረት በሰሩት ኦፕሬሽን ወርቃማ ድል ተገኝቷል። የአገዛዙ ወምበር አርዛሚ ቡድንም ሽንፈትን ቀምሶ ለመመለስ ተገድዷል።

  ሰሜን ጎንደር ላይ ራሥ ደጀን ክፍለ ጦር ለአገዛዙ  የእግር እሣት ሆኗል። የአገዛዙ ወምበር ጠባቂ ወታደር ከገደብዬ ከተማ ተነሥቶ ቅኝት በሚያደርግበት ጊዜ ከወቅን ከተማ አለፍ ብላ ከምትገኘው ፍኖተ ሠላም መዳረሻ  ላይ ደፈጣ የጣለው  የቢትወደድ አዳነ መኮንን አባ ደፋር ብርጌድ ትልቅ  ድልን ተቀዳጅቷል።



ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

24 Oct, 15:38


ትግሉ የህዝብ ሁኖአል።የፋኖ ብቻ አይደለም የአማራ ፋኖ በጎንደር ተከዜ ክፍለጦር #አማራ_ፋኖ #amhara @Tir...
https://youtube.com/watch?v=v2jgA6PCK70&si=f9Dn56wQiLtp-ikL

ጡሩንባ ሚዲያ

20 Oct, 17:06


ደብረታቦር/አለም በር
ጥቅምት 10/2017ዓ.ም

የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ተጨማሪ ኃይል ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ለመግባት  በምድር ዙ- 23፣ BM-107፣ ዲሽቃና ሞርታርን እንዲሁም በሠማይ በሄሊኮፍተር የታገዘ ጉዞን ሢያደርግ ውሏል። በተመሣሣይ ከባሕር ዳር የተነሳውን ጦር ለመቀበል ከደብረ ታቦር ወደ አለም በር  የአገዛዙ ጦር በከባድ መሣሪያ ታግዞ ዘምቷል።

ድልን እሥትንፋሳቸው ያደረጉ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጥምረት የአገዛዙን ጦር የተለያዬ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለውበታል። በደፈጣ የታጨደው የአገዛዙ ጦር ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እግሬ አውጭኝ ካለ በኋላ ራሱን አደራጅቶ ተመልሷል።

ድንጋጤን መለያው ያደረገው የአቢይ ጦር በምድር ውጊያ እንደተሸነፈ ሢያረጋግጥ በሠማይ በሄሊኮፍተር ታግዞ ከእንደገና ውጊያን አድርጓል። ነገር ግን አሸናፊነት ከአባቶቻቸው የወረሱት፣ ሥነ ልቦናቸው በዕውነት የጸናው፣ ትግላቸው ሕልውናን ማሥቀጠል እንደሆነ ያመኑት የአሥቻለው ደሤ ቀኝ እጆች፣ የውባንተ አባተ ልጆችና የናሁሰናይ ወንድሞች በአገዛዙ የጦር ጋጋታ አልተረበሹም።

የአማራ ፋኖ በአለም በር ላይ የልብ ትጥቅን በደምብ ታጥቆ በውሥን ጦር አገዛዙን ሢለበልብ ውሏል። አለም በርና ዙሪያ ገባው ላይ በነበረው ውጊያ የአገዛዙ አመራሮችም ጭምር ሢደመሰሱ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በዚህ ሠዓት በአገዛዙ ቁሥለኞች ተሞልቷል። የአገዛዙ ከፍተኛ የጦር መሪም እንደቆሰለና ታቦር ሆሥፒታል እንደገባ አረጋግጠናል።


ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
አርበኛ ባዬ ቀናው

ጡሩንባ ሚዲያ

19 Oct, 07:31


በዛሬው ዕለት ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም

ጎንደር የገባው አራዊት ሠራዊት እየተቀጠቀጠ ይገኛል። ዛሬ ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ አጣናው ዋሴ ክ/ጦር ከመተማ ዮሐንስ ወደ ድል በር በመገስገስ ላይ የነበረን ጨፍጫፊ ሠራዊት ከ5 በላይ ደፈጣዎችን በመጣል አሳሩን ሲያሳዩት ውለዋል።

በአምስት ኦራልና በአንድ ፓትሮል ዙ23 እና ዲሽቃ ይዞ ባልተጠበቀ ሰዓት ፋኖን አጠቃለሁ ብሎ ቢንቀሳቀስም ቀድመው መረጃ የደረሳቸው የአጣናው ዋሴ ክ/ጦር ነበልባሎች ገዥ የደፈጣ ቦታዎችን በመያዝ ሲበትኑት ውለዋል። በዚህ አስደናቂ ደፈጣ አንዱ ኦራል ሙሉ ለሙሉ ተደምስሶ በመጣበት እግሩ ፈርጥጦ መተማ ለመግባት ተገዷል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
አርበኛ ባዬ ቀናው

https://t.me/fanozgonder

ጡሩንባ ሚዲያ

17 Oct, 19:09


ከአማራ ፋኖ በጎንደር ለመላው የትግል ጓዳችን የቀረበ የትግል ጥሪ

የጀመርነው የኅልውና ትግል መራር ሃዘንን እየተጋፈጥን፣ በጀግንነትም የሥርዓቱን አከርካሪ እየሰበርን በአሸናፊነት መስመር ላይ እየተጓዝን
መሆኑ ይታወቃል። ለትግላችን የውስጥ መጓተቶች፣ የሥርዓቱ ስንኩል ፖለቲካዊ ሴራዎ፣የእርስ በእርስ መጠላለፎች ክፉ መርገሞች ናቸው።
እንዲህ ያለው ስሁት እሳቤ ወለድ አካሄድ ከትግላችን ዓላማና ግብም ጋር የሚጻረር ለሕዝባችን ዘለቄታዊ ኅልውና የማይበጅ ኮተት
እንደሆነም በጽኑ እናምናለን።

ትናንት በጀግንነት፣ በሐቅ፣ በቅንነትና በታማኝነት ለአማራ ሕዝብ ኅልውና ሕይወታቸውን ለውጠው የመነኑት የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ ንሥር
በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ሳለአምላክ ነጋሽ እንዲሁም ም/አዛዥ አርበኛ ጉልላት ፀጋዬ እና አጃቢዎቻቸው ለግዳጅ
እንቅስቃሴ ላይ በነበሩበት ሰዓት በድሮን ጥቃት ሕይወታቸው በማለፉ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን በተቋማችን ስም መግለጽ እንወዳለን።
አርበኞቻችን የምሥራቅና ምዕራብ በለሳን ወጣት በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ ለትግል በማሠማራት፣ በማታገል እንዲሁም ለማኅበረሰቡ
ፍትሕ ርትዕ በመስጠት ለአማራ ሕዝብ የሚችሉትን ሁሉ በማበርከት የድርሻቸውን አበርክተው በጀግንነትና በአርበኝነት ተሰውተዋል።

የትግል ምልክቶቻችንና አርበኞቻችን ደመላሻዊ የትግል ጥሪ "ዘመቻ ሳለአምላክ እና ጉልላት" በሚል መሪር የቁጭት መፈክር ከዛሬ ጥቅምት
08/2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የትግል ጥሪ እናቀርባለን። ስለሆነም የአርበኞቹን ደም የምንበቀልበት፣ ይህ የትግል ጥሪ በመላው
ጎንደር ተግባራዊ እንዲደርግ በጀግንነት በተሰው ጓዶቻችን ስም እንጠይቃለን።

ፈጣሪ የአርበኞቻችንን ስም በአጸደ ገነት ያሳርፍልን!!!

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አርበኛ ባዬ ቀናው

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና አዛዥ

ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም

https://t.me/fanozgonder

ጡሩንባ ሚዲያ

17 Oct, 18:44


https://t.me/fanozgonder

ጡሩንባ ሚዲያ

17 Oct, 16:41


አዲሱ ክፍለ ጦር ተመሰረተ!! አማራ ፋኖ በጎንደር አጣናዉ ዋሴ ክፍለጦር #fano ##amhara #amharafano...
https://youtube.com/watch?v=nSHnnuQzpJ8&si=WjNnLJTGF9hGu-qC