መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase) @mezgebe_kidase Channel on Telegram

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

@mezgebe_kidase


ትክክለኛውን የቅዳሴ ስርዓት በደብረ ዓባይ ጣዕመ ዜማ ከነ ሥነ-ስርዓቱ እግዚአብሔር እንደፈቀደ ምስክር ባላቸው መምህራን የሚቀርብበት ቻናል።

@Mezgebe_Kidase

ለማንኛውም አስተያየት @Yishak_41 ይጠቁሙን።

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase) (Amharic)

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase) በደብረ ዓባይ ጣዕመ ዜማ ከነ ሥነ-ስርዓቱ እግዚአብሔር እንደፈቀደ ምስክር ባላቸው መምህራን የሚቀርብበት ቻናል ነው። ይህ ቻናል በቅዳሴ እና በበቃ ደብረ ዓባይ ጣዕመ ዜማን በሚያንኳኳ በሰለጠነው የእንቅስቃሴ መልዕክት እና በበጋዝ መምህር ለሚሆን ስርጭት እና በድርጅቱ ስጦታው ልብሽን ነው። በተንኮል እና በእንቁጣጣሽ መቆም ለሚያስቻል እና ለሚቀርበው ሌሎች በተመለከተ ሰዓት ስሙ ቤተልሔምን ጋብዙ። እስኪሞክሩ እና እንዲህም መተከል የሚገባውን ቻናል በማሳተፍ ሀሳብ የሚገባቸውን መልዕክት ለመበተን እና ለጨዋታ እንዲሁም ስልኩን የማየት ካለ፤ ሌላን አሰልጣኞችን ከሚገልጹ አስተያየቶቻቸውን ነገሮችን እና ፈጣን ጉዳዩቻቸውን ዥንጀራ እና እንስማ የማሳያ መተግበሪያ ለማቀራረብ ይህ ቻናል ኃላፊነቱ በሚስቅ አለበት። @mezgebe_kidase ከሌሎች ቻናሎች አካባቢ ለመቀነስ እና ለመግደል በቁጥር እንደገና በረከት እንዲሆኑ እና እንዲወስድ ማመልከቱን ለማቅረብ ይህ ቻናል በማድረግ አድርገዋል።

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

26 Jul, 10:00


“ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?”
ዕብራውያን 1፥14

እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስን እና ቅድስት ኢየሉጣን ላዳነበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደርሳችሁ!

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

06 Nov, 19:07


እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን መልካም ክብረ በዓል።

ካራ ቆሬ ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

03 Nov, 07:11


✔️🔔ማሳሰቢያ

ሰሞኑን ብዙ ሰው የቴሌግራም አካውንቱን እየተዘረፈ ነው።

በተለያዩ የቴሌ ግራም ቻናል ሲዘዋወሩ የምናያቸው አጫጭር ሊንኮች የቴሌግራም አካውንታችሁን ለማበላሸት ስለሚዳርጉት ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ እንኳን ቢሆን ሊንኮቹ የተላኩት የሚልኩላችሁ እነርሱ አይደሉምና የሚላከውን ሊንክ አትንኩት።

ምንክያቱም ሊንኮቹን ስትነኩ እናንተ የምታስተዳድሯቸውን
አካውንቶቻችሁን
ግሩፖቻችሁን
ቻናላችሁን
በተጨማሪም ከሰዎች ጋር Text ያደረጋችሁትን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፉት እና እንደ አዲስ የቴሌግራም አካውንት እንድትከፍቱ ትዕዛዝ ሊሰጣችሁ ይችላል። 

ስለዚህ ከእነዚህን ጠላፊዎች/ሃከሮች ሴራ ለመዳን የሚላክላችሁን ሊንክ አለመንካት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው።

በተጨማሪም ከጠላፊዎች  አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት PASSWORD ከቴሌግራም ሴቲንግ ውስጥ "TWO STEP VERIFICATION" የሚለውን ON  አድርጋችሁ አካውንታችሁን ጠብቁ።

https//t.me/Gamel_Media

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

14 Oct, 17:18


" ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።

ከቅዱስነታቸው መልዕክት የተወሰደ ፦

" ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን ።

ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል።

ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም። የተሰዉት ልጆቻችን በሕይወተ ሥጋ ኖረው ቢሆን ብዙ ታሪክ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም እነዚህ የቤተሰብና የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ተስፋዎች በእሸት በመቅረታቸው በኀዘን በተሰበረ ልብ ሁነን ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን።

በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን፡፡

በምድር ላይ ስንኖር ማንም ለራሱ መከራን አያቅድምና የታቀዱ ቀኖችንም ለማለፍ ሕገ ተፈጥሮ አይፈቅድልንምና በሆነውና በሚሆነው ነገር ሁሉ ' እንደ ፈቃድህ ይሁን ' እያሉ ልብን ማሳረፍ ይገባል በማለት እንመክራለን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@Gamel_Media

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

03 Sep, 02:53


የረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እሑድ ነሐሴ 28 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ያከብራል።

እርስዎም የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የምስረታ በዓል አብረውን ያከብሩ ዘንድ ተጋብዘዋል።

አድራሻ: - አዲስ አበባ, ካራ ቆሬ, በረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት እና ስብከተ ወንጌል ሁለገብ አዳራሽ።

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

21 Aug, 19:12


+++እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ+++

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ፡፡

ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር፡፡

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው፡፡

ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ዘንድ ተቀምጦ አየው፡፡ የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡

ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት፤ የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ፡፡

ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፅዋት ሁሉም አዘነበሉ፤ መላእክት፤ የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት፡፡

አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወረቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት፡፡

በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኃላ በልጆችዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች፡፡

ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ፤ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንዳሳረጓት ነገራቸው፡፡

ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ፡፡

ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር የአንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ፡፡ እነሆ እኔ እርስዋን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው፡፡ ይህንንም ብሎ ከእርሳቸው ዘንድ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሳየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በጾም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን፡፡

በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ፤ የነሐሴ ወር እንደዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት፡፡ እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው፡፡

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዔ ካህን ሆነ፡፡ እስጢፋኖስም አዘጋጀ፤ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ፡፡ ሁሉም ሐዋርያት በመሰዊያው ዙሪያ ቆሙ፤ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡

ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው፡፡

ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን  እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት፡፡ በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰበኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው፡፡ መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ፡፡ የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለቸው ልጄ ሆይ እነሆ በዓይኖቻቸውም አዩ፤ በጆሮዎቻቸውም ሰሙ፤ በእጆቻቸው ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ድንቆች ሥራዎችን አዩ፡፡

እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል፡፡ እርሷ ስለ እኛ ወደተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለች፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን፡፡ በረከቷም ሐዋርያት በሰበሰበዋት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን፡፡

ምንጭ፡-ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

18 Aug, 11:57


ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል?  ሙልሙል ለምን ይታደላል?  በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል  ?

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ ብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል
https://t.me/Gamel_Tube

ጅራፍ

  በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል
   https://t.me/Gamel_Tube

    ችቦ

     ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና 
https://t.me/Gamel_Tube

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና

ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል  ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው
https://t.me/Gamel_Tube

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

05 Aug, 18:15


#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን በይቅርታውና በምሕረቱ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ::
“ወእምኵሉስ ዘይቀድም ተፋቀሩ በበይናቲክሙ በምልአ ልብክሙ እስመ ተፋቅሮ' ይደፍኖን ወይደመስሶን ለኵሎን ኃጣውእ!" (ከሁሉ አስቀድሞ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ፣ መፋቀር ሁሉንም ዓይነተ ኃጢአት ይሸፍናልና ይደመስሳልምና (፩ ጴጥ.፬-፰)

ሁላችንም እንደምናውቀው የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ መሠረትና ጣርያ ወለልና ግድግዳ በፍቅርና በፍቅር ብቻ የተገነባ ነው፡ ፍቅር እግዚአብሔር ዓለምን ያዳነበት መድኃኒት ነው፣ ፍቅር የጥላቻና የመለያየት ግንብን ንዶ ይቅርታንና አንድነትን የሚገነባ ጠንካራ ዓለት ነው፣ ፍቅር መጽናናትንና ደስታን የሚያፈራ ጣፋጭ ተክል ነው፤ በፍቅር ለፍቅር የሚደረግ ሁሉ ፍሥሐን እንጂ ጸጸትን አያስከትልም በመሆኑም በሰብአዊ ድክመት ምክንያት ሰዎች ፍቅርን ሙሉ በሙሉ በሚፈለገው ደረጃ ባንጠብቀውም በዓለማዊም ሆነ በመፈንሳዊ ሕይወት ከፍቅር የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም ፍቅር የማይሻርና ለዘላለሙ ጸንቶ የሚኖር እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዘግቦአል፤ ምክንያቱም ፍቅር ከሞት በኋላም ቢሆን በእግዚአብሔር መንግሥት ይቀጥላልና ነው ዛሬ የሚጀመረው የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታም በፍቅር ለፍቅር የተፈጸመ ነው፣ ይኸውም ቅዱሳን
ሐዋርያት የድንግል ማርያምን የማረፊያ ቦታ ለማየት ሲሉ የጾሙት ጾም ነው! ቅዱሳን ሐዋርያት የገለፁት ፍቅረ ድንግል ማርያምን ብቻ ሳይሆን ያረፈችበትንም ቦታ ጭምር ያመለከተ ነበረ፤ ይህ ሊሆን የቻለው ከልብ የሆነ እውነተኛ ፍቅር በሐዋርያት ዘንድ ስለነበረ ነው፡፡ እኛም ዛሬ የምንጾመው ይህንን የማርያም ጾም እንደ አበው ሐዋርያት ፍቅረ ድንግል ማርያም በልባችን ውስጥ ተተክሎ ስላለ ነው፤ እግዚአብሔር በፍቅርና በሃይማኖት የሚቀርብለትን ሁሉ ይቀበላልና የሐዋርያትን ጾምና ጸሎት ተቀበሎ ጥያቄአቸውን መልሶአል።

ዛሬም ይህንን ጾም የምንጾመው እግዚአብሔር ጾማችንን ተቀብሎ የልባችንን መሻት ይፈጽምልናል ብለን ነው ፣ በፍቅርና በሃይማኖት አስክ ጾምን ደግሞ እግዚአብሔር ይቀበለናል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ ፍልሰታ ጾም ሲጾም የበደለ ይቅርታ ጠይቆ፣ ተገቢውንም ካሣ ከፍሎ፣ ቂም በቀሉን አሰርዞ፣ ፍቅርን መሥርቶ ነበረ የተበደለም በበኩሉ ዕርቅን አውርዶ፣ ይቅርታን ሰጥቶ የእእምሮ ማለስለሻና ማስረሻ የሆነውን ካሣውን ተቀብሎ ተሙንና በቀሉን ከአእምሮው አውጥቶና አጽድቶ፤ ለእግዚአብሔር ስል ከልቤ ይቅር ብያለሁ ብሎ፣ ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ በፍቅር ይታረቃል በዚህ ሁኔታ ፍጹምና ልባዊ ፍቅር ተይዞ ሲጾም ሁሉም ዓይነተ : ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ይደመሰስለታል ፤ እግዚአብሔርም ይቅርታ ጠያቂውንም፣ ይቅርታ ሰጪውንም አሸማጋዩንም ይባርካል፤ ማኅበረ ሰቡም በዚህ ቅዱስና ሃይማኖታዊ ባህልና ትውፊት ተጠብቆ ለብዙ ዘመናት አንድነቱንና ሃይማኖቱን ወንድማማችነቱንና ነጻነቱን አስጠብቆ እስከ ዛሬ ደርሶአል | ይህ ለሀገራችን ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር በረከት ነበረ፣ ይህ እውነተኛ በረከት በአሁኑ ጊዜ ቸል በመባሉ ፈተናችን በዝቶአል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሰው በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ጥልና መገዳደል በየትኛውም ጊዜ፤ በየትኛውም ሀገር በየትኛውም ማኅበረ ሰብ ይከሠታል፤ ዛሬም በሀገራችን በተፈጠረው አለመግባባት ከባድ ችግር ተፈጥሮአል የሚያስገርመው ነገር ቢኖር እንዴት እንደባህላችንና እምነታችን በቀላሉ በዕርቅና በይቅርታ ማስተካከል አቃተን የሚለው ነው፡ የዘመናችን ልዩ ነገር ይህ ነው ለዚህም ብዙ የተለያየ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፣ በሃይማኖት ዓይን ሲታይ ግን ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ክብር በእጅጉ ስለተቀነሰ ነው የሚል ሆኖ ይገኛል፣ ይህ ዝንባሌ አሁን ላለውም ሆነ ለሚመጣው ትውልድ አደገኛ ስለሆነ የኦርቶዶክስ ሕዝበ ክርስቲያንም ሆነ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን በጥልቀት ሊያጤኑትና ሊያርሙት ይገባል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናንት | ሽማግሌ የሀገር በረከት ነው፤ አስታራቂ ሽማግሌ የችግር ሐኪምና ፈዋሽ ነው፣ የፍቅርና የተግባቦት መሐንዲስም ነው፤ በእግዚአብሔርም የሚያስታርቁ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው” ተብሎ ውዳሴ ተችሮአቸዋል፣ እነዚህን ሽማግሌዎች ተጠቅመን ችግሮቻችንን መፍታት ጊዜው የሚጠይቀው አስገዳጅ ጉዳይ ሆኖአል፤ ሁሉም ታየ፤ ሁሉም ተሞከረ፣ ዘላቂ መፍትሔ ሲያመጣ ግን አልታየም፤ እንዲያውም ችግሩ ወደ ሃይማኖት ተዛምቶ ቤተ ክርስቲያንም የገፈቱ ቀማሽ ለመሆን ተገዳለች፡፡

በተጨባጭ እንደሚታውቀው ሕዝብንና ሃይማኖትን ነጣጥሎ ሰላምን ማረጋገጥ ከቶውኑ ሊታሰብ አይችልም ምክንያቱም ሕዝብ የሃይማኖቱ ቤተሰብ ነው፤ ሃይማኖቱም በሕዝቡ መንፈስ ውስጥ ነግሦ የሚኖር መለኮታዊ ኃይል ነውና፣ ከዚህ አንጻር “ወልድ ሲነካ አብ ይነካ" እንደሚባለው ሕዝቡ ሲነካ
ሃይማኖቱ ይነካል፣ ሃይማኖቱ ሲነካ ደግሞ ሕዝቡ ይነካል፤ በመሆኑም በተካሄደው ግጭት ብዙ ነገሮች መመሳቀላቸው የማይካድ ቢሆንም ችግሩ በዕርቅና በካሣ
በይቅርታና በመተው ካልተዘጋ ለማንም ስለማይበጅ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለዕርቅ ዝግጁ እንዲሆነ፣ የበደሉም እንዲክሱ የሀገር ሽማግሌዎችም የማስታረቅ ስራን በሐቅ በገለልተኝነትና ዕንባን በሚያደርቅ ስልት እንዲሸመግሉ መንግሥትም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የገጠመንን ፈተና ሁሉ ሊያቀልልንና ሊያስወግድልን የሚችል እግዚአብሔር ስለሆነ፤ በዚህ የጾመ ማርያም ወቅት ምእመናን በተመሥጦና በንሥሐ ሕይወት ለእግዚአብሔር በመንበርከክ ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ፣ ካላቸውም በረከት ለተራቡትና ለተፈናቀሉት እንዲለግሱ ሁሉም ወገኖች በሆነው
በመጨረሻም ነገር ይብቃን ብለው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲቀርቡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን
እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የጾመ ማርያም ሱባዔ ያድርግልን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን !!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም.

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

04 Aug, 17:59


እስከ ዛሬ ድረስ አውቄም ይሁን ሳላውቅ ያስቀየምኳችሁ፣

ከአንገቴ ደፋ ከወገቤ ጎንበስ ብዬ ይቅርታ አልኳችሁ፣

ይቅርታ ማድረግ ትልቅነት ነው ካላችሁ፣

ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት ከንቱ ድካም ነው ብላችሁ፣

ይኸው በ ድንግል ማርያም ስም ማሩኝ ይቅር በሉኝ እባካቹ።
                  🙏🙏🙏

           ይቅርታ
              +
           ይቅርታ
              +
           ይቅርታ
              +
   መልካም የፍልሰታ ጾም ይሁንላቹ፡፡
   ጾሙን # የኃጢአት መደምሰሻ
           # የነፍስ ማደሻ 
           # የዲያብሎስ ድል መንሻ
                ያድርግልን።
                    አሜን!

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

07 Jul, 09:24


ሙሉ ሥርዓተ ቅዳሴ እና ሰዓታት ከነ መመርያው በመምህር ኤፍሬም በደብረ ዓባይ ጣዕመ ዜማ!

መዝገበ ቅዳሴ (Mezgebe Kidase)

26 Apr, 10:31


ለቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ መልእከት ከምእመናን:- አንብበው ካመኑበትና የጉዳዩ አንገብጋቢነት ከገባዎት ይፈርሙ። አጋርተው ያስፈርሙ
https://chng.it/yYqsWxbLhK