Authority for Civil Society Organization (ACSO)

@authority_for_civil_society


Authority for Civil Society Organization (ACSO)

23 Oct, 13:09


ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ https://ethiocoders.et/

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

23 Oct, 13:03


ተመዝገቡ!! አስመዝግቡ!
የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ መርሃ ግብር
ኢኒሼቲቩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 5 ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ነው፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ መርሃግብር ታላቅ እድል የሚፈጥር እና ሀገር በቀል መፍትሔዎችን የሚሰጥ ነው፡፡
ስለሆነም ማንኛውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሰራተኞች የዚህ ነጻ እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ  ጥሪ እናቀርባለን፡፡
መርሃ ግብሩ በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ ነው።

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

14 Oct, 13:09


17ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል በተቋማችን ተከብሯል፡፡
*********************************************
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባስተላለፉት መልዕክት የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር በአዋጅ መደንገጉን ተናግረው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠትና የማክበር ኃላፈነትና ግዴታ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ተጨማሪም የባንዲራውን ቀለማትና ዓርማ ትርጉም ለብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሰጠውን እኩልነት መረዳት ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ፕሮግራሙም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመርና ቃል በመግባት ተጠናቋል፡፡

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

03 Oct, 07:51


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለተለያዩ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
******************************************
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ትምህርት ፅህፈት ቤት ስር ለሚገኙት አዲስ ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትና በቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ያስረከቡ ሲሆን የወረዳ 5 ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እሸቱ ኢፋ እና የየትምህርት ተቋማቱ ተወካዮች ተቀብለዋል።
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ከ212,784 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች የተደረገ ድጋፍ ነው።

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

02 Oct, 18:26


4ተኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ከዴሴንበር /December  6-8 እንደሚከበር ኮሚቴው አሳውቋል፡፡
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሚዘጋጀው 4ተኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀን አከባበር  ላይ አብይ ኮሚቴው ዛሬ ስብሰባ ያካሄደ ሲሆን በውይይቱም በርካታ ጉዳዬች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ቀኑ ከዴሴንበር /December  6-8 እንደሚከበር ያሳወቀው ኮሚቴው በሁነቱ ፓናል ውይይት፣ኤግዚቪሽን እና የመክፈቻ ስነስርዓት እንደሚኖረው እንዲሁም ከ80 አስከ 100 ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅችም እንደሚሳተፉበት አሳውቋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሣምንት ዓላማ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ላይ ያላቸውን  አስተዋፅዖ ለማሳደግ እና ዘርፉን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።
ኮሚቴው በቀጣይ የሚካሄድበትን ቦታ ጨምሮ  ሌሎች ጉዳዬችን እያሳወቀ እንደሚሄድ ገልጿል፡፡

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

07 Sep, 12:48


ተቋሙ EU-CSF Plus ፕሮግራምን እያስፈጸሙ ከሚገኙ ሶስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር አብሮ በሚያሰሩ ጉዳዮች ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያሉ የጋራ መድረኮች እንዲጠናከሩ ማገዝ ፣ የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን እና በዚህም የአገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል እገዛ ማድረግን ዓላማ ያደረገ የስምምነት ሰነድ ነው፡፡
የስምምነት ሰነዱ የተፈረመው ከጀርመን አግሮ አክሽን፣ Consortium of Self-help group Approach Promoters (CoSAP) እና Development Expertise Center (DEC) ጋር ነው፡፡
ድርጅቶቹ በEU-CSF Plus ፕሮግራም የሃገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አቅም መገንባትና የማብቃት ስራ ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

27 Aug, 14:27


ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ!!
ገዳዩ፡- በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ-ፈቃድ አገልግሎት እና አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሪፖርት እንዲትልኩ ስለማሳወቅ፤
በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፎ ያደረጋችሁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አገር አቀፍ መረጃዎችን እያሰባሰብን ሲሆን ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘው ቅጽ መሰረት ድርጅታቸው ያደረገውን ተሳትፎ በመሙላት እስከ ሀሙስ 23/12/2016 ዓ.ም በባለስልጣኑ ኢሜል ሪፖርት እንዲትልኩ እናሳውቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር!!