እኔ እና አንተ እናንቀላፋለን ማንቀላፋት ደግሞ በዐረበኛ ቋንቋ (السنة) ይባላል ፤ እንደዚሁ እኔ እና አንተ እንተኛለን ፤ አሏህ ደግሞ በኪታቡ እንዲህ ብሏል፡
{{لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ}} سورة البقرة- آية (255)
{{ማንቀላፋት እና መተኛት አይዘውም}} ሱረቱል በቀራህ- አንቀፅ (255)
እንደዚሁ አሏህ እንዲህ ይላል፡
{{لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ}} سورة الشورى- آية (11)
{{አሏህ ከፍጡሮች ውስጥ አንዱንም በማንኛውም መልኩ አይመስልም እሱም ሰሚ እና ተመልካች ነው}} ሱረቱ ሹራ- አንቀፅ (11)
በጥቅሉ፦ የትኛውም ፍጡር የሚገለፅበትን ባህሪ ሁሉ ፈጣሪያችንን አሏሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አንገልፅበትም።
እኔ እና አንተ በቦታ ነው የምነንኖረው አሏሁ ተዓላ ግን በየትኛውም ቦታ የሚኖር አይደለም ይልቁንም አሏህ ያለ ቦታ ያለ ነው።
ይህንን ቃል ሸምድደህ ለምታየው ሁሉ አስተምረው ለምታውቀውም ሁሉ ላከው ምናልባት በዚህ ስራ ምክኒያት ከሳት ነፃ ትደረግ ይሆናል