ኢትዮ ሊቨርፑል™ @ethioliverpool143 Channel on Telegram

ኢትዮ ሊቨርፑል

@ethioliverpool143


➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ቻናል በደህና መጡ።

➠ በቻናላችን ስለ ሊቨርፑል:-

🔴|| ዝውውሮች

🔴|| ውጤቶች

🔴|| የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴|| የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳዎችና

🔴|| ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ለማስታወቂያ ስራ 👇

➟ @NATI_YNWA
➟ @atsbaha12

❷⓪❷❹ ኢትዮ ሊቨርፑል

ኢትዮ ሊቨርፑል™ (Amharic)

ኢትዮ ሊቨርፑል™ በአማርኛ እና በቋንቋዎ የሚገኝ ቻናል ነው። ይህ ቻናል ለሊቨርፑል ያሉ ፕሮግራሞችን እና እንግዳዎችን እንዲሁም ከጨዋታ አገልግሎት የሚገኙ ሰዎችን ለማግኘት ሲስብም። ከናቲ ወደለተ በመጫን እና ጫካ ቻናል የሚገኙበትን በሚል የሊቨርፑል ስራን ለመስበር ጥቅም ፡፡ የሚለውን ያግኙ ፡፡

ኢትዮ ሊቨርፑል

21 Nov, 12:27


🔻 I ሊቨርፑል የበርንማዉዙን ግራ መስመር ተከላካይ ሚሎስ ከርኬዝን በቅርበት እየተከታተሉት ነዉ። ክለቡ የተጨዋቹ አድናቂ ነዉ።

ምንጭ፦ ፋብሪዚዮ ሮማኖ🎖

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

21 Nov, 12:18


🎙| ቨርጅል ቫንዳይክ ስለ አርነ ስሎት !

"ከአዲሱ አሰልጣኛችን አርነ ስሎት ትንሽ ለየት ያሉ ነገሮችን እንድሰራ እየተጠየኩ ነው ፣ በእርግጥ እኔ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ተጫዋቾች ጭምር ነው የተጠየቁት ፣ በዚህ ውስጥ ትልቅ ሚና አለኝ ፣ እና ወድጄዋለሁ ፣ እናም አሰልጣኙ እዚህ በጣም የተደሰቱ ይመስለኛል።"

"እኔ አሁን በምን አይነት ሁኔታ መጫወት አለብኝ የሚለውን እንደጨዋታው ይለያያል ፣ ለምሳሌ የተጋጣሚ ቡድኖች እንዴት ጫናዎችን እንደሚፈጥሩ ታያለህ እና በአንድ አጥቂ ነው ፣ ወይስ በሁለት ወይስ በሶስት የሚለውን ማወቅ አለብህ ፣ የኀላ መስመራቸው ጠንካራ ነው አይደለም ፣ በሁለት 8 ቁጥር ነው የሚጫወቱት ወይስ በ1 ነው የሚለውን እነዚህን ሁሉ የተጋጣሚ ቡድን መረጃን ማወቅ ያስፈልጋል እና በእያንዳንዱ ጨዋታ የተለያዩ አማራጮች መጠቀም ያስፈልጋል።"

“ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ስለዚህ ጉዳይ ከአሰልጣኙ ጋር እየተነጋገርኩ ነበር ፣ የተለያዩ ምስሎች ይዘን ስንመለከት ነበር ፣ ከዚያ በኋላ የነበረው የተግባር ስራ ጥሩ ነበር እና በዚህ አርነ በጣም ተደስቷል።"

"ባለፈው የውድድር አመት ከአርሰናል እና ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ለሊጉ ሻምፒዮንነት እስከ መጨረሻው አምስት ጨዋታዎች ድረስ ስንታገል እንደነበር ማስታወስ አለብን።"

"አርነ ጥሩ ቡድንን ወርሷል እሱም ጥሩ እና ጎበዝ አሰልጣኝ ነው።"

@EthioLiverpool143
@EthioLiverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

21 Nov, 11:43


ዝክረ ሬን ብረስተር!

የቀድሞ ተጨዋቻችን ሬን ብረስተር ማን ነው?

ብረስተር በአንድ ወቅት ብዙ ተስፋ ከተጣለባቸው ወጣት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የነበረና በጥሩ ይንቀሳቀሱ ከነበሩ ባለ ተሰጦ ወጣት ተጨዋቾች ውስጥም አንዱ ነበር።

ሬን ብስተር የት ይገኛል?

ብዙ ተጠብቆ እንደተጠበቀው መሆን ያልቻለው ሬን 2015 ክረምት ላይ ከቼልሲ የወጣቶች ቡድን በነፃ ዝውውር ክለባችን የተቀላቀለ ሲሆን በክለባችን ሊቨርፑል በቆየባቸው (5) አመታት ከቅድመ ውድድር ጨዋታዎችና ከአንዳንድ የሀገር ውስጥ ውድድሮች በቀር ለሊቨርፑል ዋናው ቡድን ውስጥ የመጫወት እድሉን አላገኘም።

በ5 አመታት ቆይታ ውስጥ ለክለባችን ከ18 አመት በታች ወጣቶች ቡድን ውስጥ ለ2 አመታት ያገለገለ ሲሆን 2019 ላይ የሻምፒዮን ሺፑን ክለብ ስዋንሲ ሲቲን በውሰት መቀላቀል ችሏል።

በዛው አመትም የውሰት ውሉን ካጠናቀቀ በኻላ በሊቨርፑል ቤት ውል የነበረው ብረስተር 2020 ላይ በቋሚ ውል በ26ሚ$ ሼፊልድ ዩናይትድን መቀላቀል ችሏል።

አሁን ላይም በሻንፒዮን ሺፑ ክለብ ሼፊልድ ዩናይትድ እየተጫወተ ይገኛል።

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

21 Nov, 09:01


"በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለናንተ በሊጉ ምርጥ አሰልጣኝ ማነው ?"

🗣️ ሚካኤል ኦወን፡ "ስሎት"

🗣️ ቲም ሼርሮድ፡ "ስሎት"

🗣️ ካረን ካርኒ፡ "ስሎት"

🗣️ ዶን ሁቺሰን፡ "ስሎት"

🗣️ ሊዮን ኦስማን፡ "ስሎት"

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

21 Nov, 03:39


እንዴት አደራችሁ ሊቨርፑላዊያንስ ❤️ መልካም ቀን ይሁንላቹ 👌

@ethioliverpool143
@ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 19:55


🔻 | ከርቲስ በይፋዊ የኢንስታግራም ገፁ ላይ ያጋራው ስቶሪ 📲...........

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 19:40


🎙 I የቀድሞ የክሪስታል ፓላስ ፣ ሉተን ታዉን ፣ ቶትንሀም እና ኤቨርተን ተጨዋች የነበረዉ በአሁን ሰዓት ለቱርኩ ክለብ አንታሊያስፖር የሚጫወተዉ እንግሊዝያዊዉ አንድሮስ ታዉንሴንድ ስለ ቤን ዶክ፦

🗣 I "አብዛኛዉ ክንፍ ተጨዋቾች የሚያስቸግራቸዉ አንድ ደካማ እግር አላቸዉ ነገር ግን እንደ ቤን ዶክ ሁለቱንም እግር ተጠቅሞ ተጋጣሚን አታሎ ያለፈ ተጨዋች አይቼ አላዉቅም።"

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 19:33


ክለባችን በ12ተኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከሳውዝሀምፕተን ጋር በሚኖረው መርሀግብር ላይ የጨዋታው የመሀል ዳኛ ተረጋግጧል እርሱም ሳሙኤል ባሮት ነው !

በአጠቃላይ :

የመሀል ዳኛ :ሳሙኤል ባሮት ነው
የመስመር ዳኞች :ሊይ ቤትስ እና ዌድ ስሚዝ
የጨዋታ 4ተኛ ዳኛ : ማት ዶንሆው
የቫር ዳኞች : ማይክል ኦሊቨር እና ማት ዋትኪንስ ናቸው

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 19:01


🎙 I የቼልሲ ተከላካይ ሌቪ ኮልዊል ስለ ቨርጂል ቫን ዳይክ፦

🗣 I "ማዕዘን ምት በሚመታበት ጊዜ ቫን ዳይክን አጥብቄ ይዤዉ ነበረ እና እኔን ለማደነባበር የሆነ ነገር እያለኝ ነበረ ፣ እኔም 'አፍህን ዝጋ' አልኩት ከዛን ዞር ብሎ አየኝ እና 'ማነዉ ይሄ ትንሹ ልጅ?' አለኝ።

ቨርጂል የኔ አርአያ ነዉ ፣ እንዲሁ ዝምብዬ ሳየዉ እራሱ እሱን መሆን እፈልጋለሁ ወይም ደግሞ እድሜዬ ሲጨመር ከእሱ የበለጠ የተሻልኩኝ መሆን እፈልጋለሁ።"

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 18:44


የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ምርጥ 11 ውስጥ ዶማኒክ ሶቦዝላይ መካተት ችሏል!

[Who Scored]

@ethioliverpool
@ethioliverpool

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 18:11


የሀንጋሪው ግብ ጠባቂ ዴኒስ ዴቡስ ሶቦዝላይ ስላስቆጠራት የመጨረሻ ደቂቃ ግብ :

"በነዛ ሰዓታት ውስጥ የጨዋታው የመሀል ዳኛ የፍፁም ቅጣት ምቷን እንደሚሰጡን እርግጠኛ ነበርኩኝ፤ከዛን በኋላ ግን በውስጤ ምን አይነት ጥያቄ አላነሳሁም ምክንያቱም የፍፁም ቅጣት ምቷን ሊመታ ከኳሷ ፊት የነበረው ሶቦዝላይ ስለነበር ....!

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 17:20


ፎቶ ግብዣ 📸

@Ethioliverpool143 @Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 16:55


🗣️ || ሞ ሳላህ ስለ ማርሙሽ፦

“ነገሮች ለሱ ቀላል እንዲሆኑ ሰዎች እኔና እሱን ማወዳደር እንዲያቆሙ እፈልጋለሁ። ሰዎች አዲሱ ሳላህ ነው እናም እሱ ያደረገውንና ከሱ በላይ ያደርጋል ይላሉ። ይህ እሱን ምንም ካለመጥቀሙ አልፎ ጫና ውስጥ ይከተዋል። እሱ ለራሱ በራሱ የጀመረውን ነገር በደስታ እንዲቀጥል ፍቀዱለት። ማወዳደር ለሱ አይጠቅመውም። ከኔ የእግር ኳስ ህይወት ለየት ባለ በራሱ መንገድ አዳዲስ ነገሮችን እንዲሰራ ፍቀዱለት።”

Mo 🫡❤️

@ethioliverpool143 @ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 15:11


🔻 I ክለባችን ሊቨርፑል በስሙ ያስመዘገቡ ሪከርዶችን በጥቂቱ ላስጎብኛቹ፦

▪️በሀገረ እንግሊዝ ዉስጥ ብዙ አዉሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ማሸነፍ የቻለ ክለብ ነዉ። [6] በቅርቡ ሌሎችም ይመጣሉ።

▪️በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳዉ በተከታታይ ብዙ ጨዋታዎችን 100% ማሸነፍ የቻለ ቡድን ነዉ። [ከየካቲት 12/2011 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 4/2012 ዓ.ም]

▪️በአንድ የዉድድር አመት ዉስጥ ከሜዳ ዉጭ ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ክለብ ነዉ። [2013/2014 48 ጎል]

▪️በዋንጫ ፍፃሜ ላይ ብዙ ከ21 አመት በታች ተጨዋቾችን ማጫወት የቻለ ክለብ ነዉ። [6]

▪️በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብዙ ነጥብ ሰብስቦ ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ ያልቻለ ክለብ ነዉ። [2018/2019 97 ነጥብ]💔

▪️በተከታታይ ዉድድር አመት ዉስጥ ቢያንስ በ1 ጨዋታ ዉስጥ ከ4 ጎል በላይ ማስቆጠር የቻለ ክለብ ነዉ። [1913 እስከ አሁኑ ድረስ]

▪️በአንድ የዉድድር አመት ዉስጥ ብዙ ጨዋታዎችን መጫወት የቻለ ክለብ ነዉ። [1983/1984 67 ጨዋታዎች]

▪️በ1965/1966 ዉድድር አመት ላይ ሙሉ ወድድሩ አመት ዉስጥ 14 ተጨዋቾችን ብቻ ነዉ የተጠቀመዉ። አብዛኛዉ ቡድን ከሁለት ጨዋታ ብቻ ነዉ ከ14 በላይ ተጨዋቾችን የሚጠቀሙት😳

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 14:33


እግሩ ላይ ባጋጠመው የስብራት ጉዳት ምክንያት ከክለባችን ስብስብ ውጪ እርቆ የነበረው ሀርቬይ ኤልየት ቀስ በቀስ በግሉ ልምምዶችን ከማከናወን አንስቶ ሌሎች ተጨዋቾቻችንም በሀገራዊ ግዳጅ ላይ በነበሩት ወቅት ከክለባችን የ21 ዓመት በታችን ቡድን ጋር ልምምድን ያከናወነው ሀርቬይ ኤልየት በዚህ ሳምንት ዋና ቡድኑ በሚያደርገው የልምምድ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚሳተፍ ተገልጿል !

ከሳውዝሀምፕተን ጋር ለሚኖረን የ12ተኛ ሳምንት ጨዋታ ይደርሳል ተብሎ ባይታሰብም ነገር ግን ወደ ዋና ቡድኑ ልምምድ የሚመለስ ይሆናል !

ምንጭ : ጄምስ ፒርስ 🏅

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 11:58


ይሄ የጎዳና ላይ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት ኔዘርላንድ ውስጥ አምስተርዳም ከተማ ላይም ከዚህ በፊት ታይቶ እንደነበረ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል ይህ ፎቶ ማድሪድ ላይ መታየቱ ከትሬንት ዝውውር ጋር ምንም የሚያገናኘው ጭብጥ እንደሌለም ነው የተነገረው።

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 11:40


አዲስ የትሬንት የማስታወቂያ ሰሌዳ በማድሪድ ከተማ 👀

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool14

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 11:28


Iconic

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143

ኢትዮ ሊቨርፑል

20 Nov, 10:57


በ ዘንድሮው UEFA ኔሽንስ ሊግ ብዙ ቁልፍ ኳሶችን ያቃበሉ ተጫዋቾች ፡-

◎ 27 - ዶሚኒክ ሶቦዝላይ
◎ 27 - ዴጃን ኩሉሴቭስኪ
◎ 19 - ሮማኖ ሽሚድ
◎ 19 - አርዳ ጉለር
◎ 19 - ቪክቶር ዮከርስ

@Ethioliverpool143
@Ethioliverpool143