የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU @amharaattorney Channel on Telegram

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

@amharaattorney


የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU (Amharic)

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU የአስተዳደር ባለስልጣን ሚኒስቴር አስተዳደርነት መምሪያ ድርጊት እና ሕጎች ምንም ይተጉለዋል ፡፡ ይህ የተጠቃሚዎችን ለማስፋፊያ እና አከባቢያለው ለድርጊት አካባቢ እየተሞላች መጠቀም ያስፈልጋል። ከተጠቃሚዎች ለምን?

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

12 Nov, 09:46


https://www.youtube.com/watch?v=gnwUGalHoG8&list=PL84RdiRVL3M8u32VfybYSK31maoYsJhiX&index=31

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

12 Nov, 09:45


https://youtu.be/4ma-evuQNpE?si=XGZ8nEXtRCFsWscc

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

05 Nov, 07:54


https://www.youtube.com/watch?v=ZGo0liSW09A&list=PL84RdiRVL3M8u32VfybYSK31maoYsJhiX&index=29

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

25 Oct, 03:09


የፍትህ ሚኒስቴር ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር ‹‹ንቃተ ህግ›› በሚል ርዕስ ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 5:30-6:00 ሰአት በፋና ሬድዮ 98.1 ኤፍ ኤም የሚያቀርበውን ፕሮግራም ትከታተሉ ዘንድ ተጋብዛችኋል። https://www.youtube.com/watch?v=lKBI8exnZtU

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

21 Oct, 13:51


https://www.youtube.com/watch?v=xkGB6co_A0s&list=PL84RdiRVL3M8u32VfybYSK31maoYsJhiX&index=25

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

19 Oct, 16:27


https://www.youtube.com/watch?v=I-YpN9v1H1k&list=PL84RdiRVL3M8u32VfybYSK31maoYsJhiX&index=26

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

16 Oct, 02:35


የአቶ ሙሉጌታ ከበደ አጭር የህይወት ታሪክ

አቶ ሙሉጌታ ከበደ ከአባታቸው ከአቶ ከበደ ተሰማና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ወርቅየ ከበደ ግንቦት 19 ቀን 1982 ዓ.ም በደሴ ከተማ ተወለደ።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ካቤ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደሴ ቅዳሜ ገበያና ካቶሊክ ትምህርት ቤቶች የመሠናዶ ትምህርቱን በመምህር አካለ ወልድ ትምህርት ቤት ተምሮ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግራውን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪውን በቢዝነስ ሎው ተምሮ በ2013 ዓ.ም የተመረቀ ሲሆን  በስራ ህይወቱ ከአብክመ ፍትህ ባለሙያዎች የህግ ምርምር ኢንስቲትውት የቅድመ ስራ ስልጠና ወስዶ በማጠናቀቅ ሰኔ 22/2008 ዓ.ም በደላንታ ወረዳ ፍርድ ቤት በረዳት ዳኝነት ጀምሮ በዚያው ፍርድ ቤት በዳኝነት ፣ በስራ ሂደት አስተባባሪነትና በሰብሳቢ ዳኝነት ከአምስት አመት በላይ ያገለገለ ሲሆን ከነሐሴ 16/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆኖ አገልግሏል።
አቶ ሙሉጌታ ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሀያት አልታሰብ ሁለት ልጆችን አፍርተዋል።
ሙሉጌታ በስራው ታታሪ ፣ ከሰዎች ጋር በቀላሉ መግባባት የሚችል፣ ሠው አክባሪና በተመደበበት የኃላፊነት ቦታዎች ሁሉ ብቁ የመምራት አቅም ያለው መሆኑን ያስመሰከረ አርቆ አሳቢና ብዙ ህልሞች የነበሩት ወጣት ነበር።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ እና የምድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች፣ በተዋረድ የሚገኙ የዞን ፍትሕ መምሪያዎች፣የወረዳ እና ንዑስ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤቶች የምንሰራ ዐቃቤያነ ሕግና የአስተዳደር ሠራተኞች በአቶ ሙሉጌታ ከበደ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ፣ለጓደኞቹ ፣ለስራ ባልደረቦቹና ለወዳጆቹ ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን።

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

13 Oct, 06:57


በ2016 በጀት አመት ከ79 ሽህ በላይ መዛግብት እልባት አግኝተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የዐቃቢያን ህግ ተከራክሮ አጥፊዎችን የማስቀጣት አቅም ከ92 በመቶ በላይ ማደጉን የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታውቋል።

ደሴ፣ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም
የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት አጀማመር መርሃ ግብር የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ምድብ ችሎት ጋር በጋራ በደሴ ከተማ አካሂደዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወካይ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ትዕግስት ዳኛቸው በ2016 ዓ.ም ከቀረቡት ከ82 ሽህ በላይ መዛግብት ከ79 ሽህ በላይ ለሚሆኑት እልባት ተሰጥቷል ብለዋል።

ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም የተገለጸ ሲሆን የውሳኔ ጥራትም እንደተሻሻለ ተመላክቷል።

በ2017 ዓ.ም የዳኝነት አገልግሎቱን በጥራትና በቅልጥፍና ለማሻሻል መታሰቡንም ነግረውናል። ባለፉት ሁለት ወራት የዳኝነት አገልግሎቱ በከፊል ሲሰጥ እንደነበር ያነሱት ወ/ሮ ትዕግስት ከጥቅምት 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ የዳኝነት አገልግሎቱ የጀመረ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ከ3 ሽህ 800 በላይ መዛግብት ቀርበው 99 በመቶ የሚሆነውን መርምሮ በማጥራት መወሰኑን የጠቆሙት የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ሞላ ናቸው።

በችሎት ክስ በሚቀርብባቸው ጉዳዮች ተከራክሮ በማሸነፍ አጥፊዎችን የማስቀጣት አቅም ከ92 በመቶ በላይ ማደጉ ተብራርቷል።

ከ1ሽህ 600 በላይ መዛግብት በፍታብሄር ቀርቦ ሙሉ በሙሉ መርምሮ መወሰን እንደተቻለ መምሪያ ኃላፊው አብራርተዋል። በዚህም በከሳሽነት ሙሉ በሙሉ በተከሳሽነት ደግሞ 89 በመቶ በላይ ተከራክሮ የማሸነፍ አቅም ማደጉን አቶ አብርሃም ዘርዝረዋል።
ይህም በመሆኑ መንግስት ተከሶበት በነበረው ዐቃቢያን ህግ ተከራክረው በማሸነፋቸው 180 ሚሊዮን ብር ማዳን ተችሏል። 540 ሄክታር መሬት ወደ መንግስት መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉንም አክለዋል አቶ አብርሃም። በውልና ማስረጃ የተቀላጠፈ አገልግሎት 541 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደተገኘም ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎት አስተባባሪ ወ/ሮ ደብረወርቅ ገብሬ እንዳሉት ደግሞ ሪፎርሙ ተግባራዊ በመደረጉ ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ደረጃውን የጠበቀ ሕንጻ በመገንባት በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎት እንደተሰጠም ጠቁመዋል። በ2017 ዓ.ም አገልግሎቱን የበለጠ በማዘመንና በማቀላጠፍ የማኅበረሰቡን እርካታ ለመፍጠር እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

13 Oct, 01:05


የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎትና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ.ም የችሎት ስራዎች የማስጀመሪያ መድረክ በፍርድ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።
የቋሚ ምድብ ችሎት አስተባባሪ ወ/ሮ ደብረወርቅ ገ/ህይወት ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ተወካይ ፕሬዝዳንት ወሮ ትዕግስት ዳኛቸውን ጨምሮ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ደሴ ምድብ አስተባባሪ አቶ ድልባንተ ደባሹና የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሀም ሞላ በመድረኩ ለተገኙ የምድብ ችሎቱና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሰራተኞች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሀላፊ ተወካዮች የደሴ ከተማና የደሴ ዙርያ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችና የዋና የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ተገኝተዋል። መድረኩ በዝህብ ግንኙነት ስራ ሂደት " አዎ ዳኛ ስትሆን " በሚል ርዕሰ በቀረበ ግጥምና በቡና ስነስርአት ታጅቦ በቀጣይ በዞኑ ካሉ ሁሉም የፍትህ ተቋማት ጋር ተባብሮ በመስራት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎች ላይ ወይይት ተደርጐ በሁሉም ዳኞች ፣ ሰራተኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች ቃል የመግባት ስነስርአት ተጠናቋል።የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዝብግንኙነት