Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ @muleritsolutions2 Channel on Telegram

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

@muleritsolutions2


👉👉 አዳዲስና ትኩስ የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችንና፣ ሞያ አዘል ፅሁፎችን፣ ጥያቄና መልሶችን፣የኮምፒውተርና የዲሽ ሪሲቨር ሶፍትዌሮችን፣ ጠቃሚ የሞባይል አፖችን ከተለያዩ የ Hacking እና Technical Trick ና ቲፖች የሚገኙበት ምርጥ ቻናል:: ለማንኛውም ጥያቄ @mulerjolly ን ወይም @mulerjolly3 ን ይጠቀሙ!! ወይም በ 0938020816 ወይም 0918711801 ይደውሉ። Share

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ (Amharic)

የMuler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ ቴክኖሎጂ ነክ መርጃዎችንና ሞያ አዘል ፅሁፎችን፣ ጥያቄና መልሶችን፣ ኮምፒውተርና ዲሽ ሪሲቨር ሶፍትዌሮችን፣ ጠቃሚ የሞባይል አፖችን ከተለያዩ የ Hacking እና Technical Trick ና ቲፖች የሚገኙበት ምርጥ ቻናል:: ይህን መረጃዎችን ለመረጃ፣ ለጥያቄ ብለውን ተመልከቱ። በመላክም የሞባይል አፕሊኬሽን እናወራለሁ። በመቀጠለ ባለፈው ስም @mulerjolly ወይም @mulerjolly3 እባኮት በመደውሉ። ስለመተላለፍ ላይ ለቀጣይ ቁጥር 0938020816 ወይም 0918711801 እባኮት ለመመደብ። ከእናንተ ጋር ለማየት ስለተለያዩ መጠቀም ማስቻለት። ከአካላትም ያሉ ባትሪክ መረጃዎችን በእንግሊዝ ይመልከቱ። Share ለማየት።

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

19 Nov, 19:12


በሞባይል ከሌላ ሰው ጋር እያወራችሁ ባለበት ሰአት ተደርቦ ሌላ ሰው እንዲደውልና የደወለው ሰው በሚስኮል መልክ እንዲያሳያችሁ ከፈለጋችሁና ከሌላ ሰው ጋር በምታወሩበት ሰአት የሚደውለውን ሰው እንዲታያችሁ ከፈለጋችሁ ከታች ያለውን USSD ኮዶችን ይጠቀሙ።

1. Enable Call Waiting:  *43# ኮል ዌቲንግ እንዲሰራላችሁ ይህንን ኮድን በመደወል ይጠቀሙ።

2. Disable Call Waiting: Dial #43# ኮል ዌቲንግ እንዳይሰራላችሁ ከፈለጋችሁ ይህንን ኮድ ይጠቀሙ።

3. Check Call Waiting Status: Dial *#43# ኮል ዌቲንግ አክቲቭ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ይህንን ኮድ ይጠቀሙ።

🔰 @muleritsolutions2

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

18 Nov, 18:48


🔵 አስደሳች ዜና ለሞባይል ጥገና ቴክኒሻኖች

የኢንፊኒክስና ቴክኖ አዳዲስና ነባር ሞዴል ስልኮችን MDM Lock bypass በማድረግ የሚከፍት አዲስ በነፃ የሚሰራ ቱል ለቀንላችኋል አውርዳችሁ ተጠቀሙበት።

🔰 Offline ነው የሚሰራው

➡️ አንዴ MDM Bypass ያደረጉትን ስልክ በፍፁም Hard Reset አያድርጉት MDM ተመልሶ ሊመጣ ስለሚችል

💜 Features of This Tool

ADB MODE
AUTO DISABLE UPDATE   
AUTO FIX MDM                
—————————————
Software in beta testing maybe have some errors

🔑 Zip Password = FLX

➡️ መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ Share ማድረግ አይዘንጉ።

🔰 @muleritsolutions2

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

15 Nov, 10:54


🥊🥊 Who do you think is gonna win? Jake Paul vs. Mike Tyson

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

14 Nov, 14:45


🔵HUAWEI E5785-320a 4G LTE Mobile WiFi Hotspot/ Huawei Mobile Wifi 3

💵 ዋጋ እና ሙሉ Product Description👇 @africaelectronicsshop

➡️ ለመግዛት በቴሌግራም @africustomercare ያዋሩን ወይም በስልክ ቁጥር 📲 0938020816 ሃሎ ይበሉ

🔰@africaelectronicsshop

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

07 Nov, 13:51


🔵 TECNO BATTERY MONSTER 4G LTE Portable WiFi / Tecno 4G WiFi Router

💵 ዋጋ እና ሙሉ Product Description👇 @africaelectronicsshop

➡️ ለመግዛት በቴሌግራም @africustomercare ያዋሩን ወይም በስልክ ቁጥር 📲 0938020816 ሃሎ ይበሉ

🔰@africaelectronicsshop

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

05 Nov, 15:16


👌 XCRUISER 4K Andriod TV Box

💵 ዋጋ እና ሙሉ Product Description👇 @africaelectronicsshop

➡️ ለመግዛት በቴሌግራም @africustomercare ያዋሩን ወይም በስልክ ቁጥር 📲 0938020816 ሃሎ ይበሉ

🔰@africaelectronicsshop

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

01 Nov, 17:44


🔵 ሁዋዊ አዲስ ስማርት 4G Omni WiFi አንቴና እና WiFi AC 1300 ራውተር በአንድ ላይ

🔵 Huawei Smart 4G Omni WiFi Antenna + Huawei Smart 4G LTE WiFi Router

➡️ Model AF78
➡️ ከፍተኛ የሆነ የ 4G LTE ኔትዎርክ የመሳብ ፍጥነት ያለው
➡️ ውሃ የማያስገባ ፀሀይና ሙቀት የሚቋቋም
➡️ ቤት ውስጥ የሚገባውን የኢንተርኔት ፍጥነት መጠን በከፍተኛ የሚጨምር
➡️ እስከ 1 ኬሎ ሜትር ድረስ በመጓዝ ከ telecom ኔትዎርክ ማማው ፈጣን ኔትዎርክ የሚስብ
➡️ 5 ሜትር የሚረዝም ወደ ዋናው ራውተር የሚሰካ የራሱ ኬብል ያለው
➡️ 360 ዲግሪ በሁሉም አቅጣጫ ሞገድ መሳብ የሚችል
➡️ ለመግጠም ምቹ የሆነ
➡️ ለቤትውስጥና ከቤት ውጪ አገልግሎት የሚውል
➡️ ከሀሉም አይነት CPE ራውተሮች ጋር የሚስማማ

➡️ Model AC1300 (4G CPE3)
➡️ ማንኛውንም አይነት ሲምካርድ የሚቀበል
➡️ እስከ 300Mbps የኢንተርኔት ዳታ ፍጥነት የማስተላለፍና ማስተናገድ አቅም ያለው
➡️ ለቤትና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል
➡️ እስከ 64 ዲቫይሶችን በአንዴ ማስተናገድ የሚችል
➡️ አራት Gigabit Ethernet Port
➡️ በ 2.4 GHZ እና 5 GHZ Band ሞገዶች የሚሰራ
➡️ ተጨማሪ Guest WiFi Feature ያለው
➡️ የራሱ የሆነ መቆጣጠሪያ አፕሊኬሽን ያለው
➡️ የደህንነት መቆጣጠሪያው ጠንካራና አስተማማኝ የሆነ
➡️ ተጨማሪ (ከላይ የተጠቀሰውን) አንቴና መቀበል የሚችል
➡️ በአይየቱ CPE ከሚባሉት ራውተሮች የሚመደብ ምርጥ ራውተር።

💵 ዋጋ 👇 @africaelectronicsshop

➡️ ለመግዛት በቴሌግራም @africustomercare ያዋሩን ወይም በስልክ ቁጥር 📲 0938020816 ሃሎ ይበሉ

🔰@africaelectronicsshop

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

31 Oct, 16:15


🔵 If you can't beat them then join them. 😀😀

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

29 Oct, 12:03


🔵 ለዛሬ አንዳንድ የሞባይልና ተያያዥ አከሰሰሪወች አጠቃቀም ስህተት በተመለከተ ከታዘብኳቸው መካከል የተወሰኑትን የማደርሳችሁ ይሆናል።

1, ኤርፎን መጎንጎን(እንደ ፀጉር ስሬት) :— መጎንጎን በኤርፎኑ ኬብል ውስጥ ያሉት ድምፅ አስተላላፊ የሆኑት ቀጫጭን ገመዶች እንዲሰባበሩ በማድረግ ኤርፎኑ ስራውን እንዲያቆም ይሆናል።

2, ቻርጀርን አዳብተር ላይ ሁሌም ቻርጅ የሚደረግ ሞባይል ሳይኖር እንደተሰካ እዛው ላይ መተው የቻርጀሩን እድሜ ስለሚያሳጥረው ይህን መጥፎ ልማድ ማስወገድ ይኖርብናል።

3, ስማርት ስልክን ያለሴፍቲ ከቨርና ግላስ መጠቀም ለአደጋ ተጋላጭ ስለሚያደርገው በተለይ ውድና መለዋወጫቸው ሀገር ውስጥ እንደልብ የማይገኙ ስልኮችን ተጠንቅቆ መያዝ መተኪያ የሌለው አማራጭ ይሆናል።

4,ውሀ የገባን ስልክ ወዲያው አስነስቶ ለመጠቀም መሞከር ስልኩን ለበለጠ ጉዳት ስለሚዳርግ፤ባትሪውን አውጥተን ፀሀይ ላይ ማስጣትና አሊያም ሩዝ ውስጥ ማስገባት ጊዚያዊ መፍትሄ ይሆናል። የበለጠው አማራጭ ግን ወደ ባለሞያ መውሰዱ በተራዘመ ጊዜ ለሚመጣ የተባባሰን ብልሽት ማስቀረት ይቻላል። ሌላው ደግሞ ባትሪው የማይወጣ ስልክ ከሆነ ስልኩን ማጥፋት(switched off) ማድረግ ቀዳሚ እርምጃ መሆን ይኖርበታል። በመቀጠልም
ፀሀይ ማስመታና ሩዝ ውስጥ ማስገባት ጊዚያዊ አንዳንዴም ዘላቂ መፍትሄን ሊያመጣ ይችላል።
በተለይ ስልኩ በደንብ ውሀ ላይ የቆየ ከሆነ ብዙ ውሀ ከገባበት በቀጥታ ወዲያውኑ ወደ ባለሞያ መውሰዱ መተኪያ የሌለው አማራጭ ይሆናል።

5,ጥቅማቸው እዚህ ግባ የማይባሉ መተግበሪያወችን መጫን ስልኩን የማጨናነቅና ሶፍተዌሩን እስከማዛባት ስለሚያደርሱ አለመጫን ይመረጣል። ለምሳሌ የስልክ ጥሪ ማሳመሪያ የተለያዩ ዌልፔፔሮችና የመሳሰሉት ቢቀሩ ይመረጣል። በተረፈ አፖችን ከጎግል ፕሌይ ስቶር ማውረድ ከቫይረስ ነፃ የሆነ አፕ እንዲኖረን ያደርጋል።

6,ያለምንም ምክንያት ብሉቱዝና ዋይፈይን ከፍቶ መተው ባትሪያችን ቶሎ እንዲያልቅ ስለሚያደርግ ተጠቅመን ከጨረስን በሗላ ወዲያውኑ መዝጋት የተሻለ ነው።

7, ባትሪ በምላስ መንካት:— ብዙ ሰወች ስልክ አልነሳ ሲላቸው ባትሪውን አውጥተው በምላስ ቀምሰው ባትሪው ቻርጅ እንዳለውና እንደሌለው ለመለየት ይሞክራሉ፤ ችግሩ በምላስ መቅመሱ ሳይሆን ከቀመሱት በሗላ ማበስና እርጥበቱን ማዳረቅ ይዘነጉታል።ስለሆነም በጊዜ ሂደት ባትሪውንም ሆነ የባትሪ ኮኔክተር ላይ ዝገት(እርጅኖ) በመፍጠር ስልኩ ተገቢውን ስራ እንዳይሰራ ያደርጋል። ይህ ልምድ ያለችሁ ሰወች ያለምንም ምክንያት ስልካችሁ አልነሳ ካለ የባትሪው አይኖች ላይና የባትሪው ኮኔክተር ላይ ዝገት ካለ እሱን በደንብ መፋቅና ማፅዳት የመጀመሪያ ቀዳሚ እርምጃዎ እንዲሆን እመክራለሁ።

8,ባትሪ 0% እስኪሆን መጠቀም በተለይ ባትሪያቸው በማይወጡ ስልኮች ላይ ላላስፈላጊ ወጪ ይዳርጋል። ማንኛውንም ስልክ ቢያንስ ከ10% በታች ሳይወርድ ቻርጅ ማድረግን እንደልምድ መውሰድ ተገቢ ነው። በተለይ 2 አመትና ከዛ በላይ ግላጋሎት የሰጠ ሲልድ ስልክ ባትሪው እየደከመ ስለሚሄድ ባትሪ ሳይዘጋ በፊት ተከታትሎ ቻርጅ ማድረግ ይኖርብናል።

9,ሲም ካርድ በምላጭና በመቀስ መቁረጥ:— በጣም ካልቸገርን በቀር ሲም ካርድን በራሱ መቁረጫ ብቻ ያስቆርጡ።

10,ስልክን አፈርና አቧራ ላይ ማስቀመጥ:— በተለይ የስፒከር ማፈኛቸው ከሌለና ወይም ሰፋ ያለ ከሆነ እስፒከር ውስጥ ያለው ማግኔት አፈር ስለሚስብ በቀላሉ አፈር አባራና አሊያም ብናኞች በመገባት እስፒከሩን ያበላሹታል። በተለይ ትናንሽ በተን የሆኑ የኖኪያና የቻይና ስልኮች እንዲሁም ኮፒ ስልኮች ለዚህ ችግር ተጋላጭ ሲሆኑ ይስተዋላሉ። በጠቅላላው ማንኛውም ስልክ ከአፈር፣ከአቧራና ብናኝ በተጨማሪም ከፈሳሽና እርጥበት አካባቢ መራቅ ይኖርበታል።

11,ቫይብሬት:— ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እንደተኛን ስልካችን ትራሳችን ስር ሆኖ በተደጋጋሚ ቫይብሬት በሚያደርግበት ጊዜ በአንጎላችን ውስጥ የሚካሄደው የመልእክት መለዋወጫ የኤልከትሪክ ፍሰትን የማወክ ሀይል እንዳለው ያስረዳሉ፤ስለሆነም ስንተኛ ቫይብሬቱን ማጥፋት ግድ ያላል። በጥቅሉ ቫይብሬትና ጭንቅላታችን ቢራራቁ መልካም ነው።

☑️ @muleritsolutions2

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

29 Oct, 12:02


ለዛሬ አንዳንድ የሞባይልና ተያያዥ አከሰሰሪወች አጠቃቀም ስህተት በተመለከተ ከታዘብኳቸው

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

26 Oct, 21:16


አዲሱ Yacine TV Black
ምንም አይነት External Player አይፈልግም።
ለAndroid TV Android Box እና ስልኮች የሚሆን ነው።

መረጃው ለወዳጅ ዘመድ ይደርስ ዘንድ Share እና Forward በማድረግ ይተባበሩን።

➡️ @muleritsolutions2

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

19 Oct, 19:36


🔵 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 9 የ Android አፖች

🎞 ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም። ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ሞባይል ስልኮን ክኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮን ኤዲት አንዲያደርጉ ያስችሎታል። እኛም 9 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ ያገለግላሉ ያልናቸውን አፖች የዘን ቀርበናል።

1, FilmoraGo በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የ ዓንድሮኢድ ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። የመቁረጥ ፣ ገጽታዎችን መቀየር ፣ ሙዚቃን የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ ሊከናወኑ ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም ለ Youtube ለ Instagram እና ለ Facebook ሚሆኒ ቪዲዮችን መስራት ይችናሉ
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.wondershare.filmorago

2, Adobe Premiere Clip: አዶቤ ፕሪሚየር ክሊፕ ማንኛውንም ቪዲዮ ከእርስዎ የ ስማርት ፎን በፍጥነት እንዲያርትዑ ያስችልዎታል። ለመጠቀም ፈጣን እና አዝናኝ ነው። ስለ ክሊፕ በጣም ጥሩው ባህሪ አውቶማቲክ ቪዲዮ መፍጠር ችሎታ ነው ፣ ማለትም ፣ መተግበሪያው በመረጣቸው ማንኛቸውም ፎቶዎች ወይም ቅንጥቦች አማካኝነት ቪዲዮዎችን በራስ-ሰር ለእርስዎ መፍጠር ይችላል ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.adobe.premiereclip

3, VideoShow ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ ሲሆን በነጻ በ Play Store ውስጥ ለሚገኙት ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። VideoShow ለአጠቃቀም ቀላል እና ለአጠቃቀም ቀላል ነው ፡፡ ከዋና ዋና ተግባራት ፊልተሮችን ፣ ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም ቀጥታ ስርጭትን በማከናወን ቪዲዮዎን ማስዋብ ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.xvideostudio.videoeditor

4, PowerDirector ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ሙሉ ለሙሉ የ አንግሮይድ ቪዲዮ ኤዲተር ነው ፣ ግን ከመቆጣጠሪዎች ጋር ለመግባባት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድዎት ይችላል። ሆኖም ፣ አንዴ በዚህ መተግበሪያ ኤክስ ኤክስፐርት ከሆኑ ባለሙያዎችን መፍጠር እና በሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ምርጥ የሚባሉ ቪዲዮዎችን መስራት ይችላሉ ፡፡ ከቪድዮዎ ውስጥ ለመምረጥ ከ 30 በላይ የተለያዩ የትራንዚሽን ምርጫዎች አሉት ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.cyberlink.powerdirector.DRA140225_01

5, KineMaster ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነገጽ ጋር በመጣመር KineMaster ለ Android ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው። የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ “copy paste” መጠቀም ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር KineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ይረዳል። በቪዲዮ መቁረጥ የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ፣ ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን ብሎግ ማስገባት ይችላሉ
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nexstreaming.app.kinemasterfree

6, Quik እጅግ በጣም ጥሩ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ኩዊክ ሌላ ብልጥ መንገድ ነው ፡፡ ፈጣን እና ነፃ ነው። የራስዎን ታሪኮች በኩዊክ ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ። ስለ ኩዊክ በጣም ጥሩው ነገር አውቶማቲክ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎች ይዞ መምጣቱ መሆኑ ነው ፡፡ ቪዲዮዎችን crop ማድረግ ፣ ማሳመሪያዎችን ፣ ጽሑፎችን መጨመር እና ማንኛውንም Audio መምታት በፍጥነት ማመሳሰል ይችላሉ ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.stupeflix.replay

7, VivaVideo ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት። መተግበሪያው በቀጥታ ከ አንግሮይድዎ ፕሮፌሽናል-የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው። ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ ፡፡ በውስጡ የማይንቀሳቀስ ዘገምተኛ(slow motion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ሰሪ እና የተንሸራታች ማሳያ(slideshow maker) ሰሪ አለው።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.quvideo.xiaoying

8, Funimate video editor በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል። የዕለት ተዕለት አፍታዎችን ወዲያውኑ ወደ የፈጠራ ቪዲዮዎችን መለወጥ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ሜዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት ። አጭር ቪዲዮዎችን ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ ከ 1 በላይ የላቁ አማራጮች አሉት ፡፡
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.avcrbt.funimate

9, Magisto መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው። ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፣ ፎቶግራፎችን ፣ audio ፣ ጽሑፎችን ፣ የቪዲዮ ውጤቶችን እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል ፡፡ አንድ ወይም ከዛ በላይ ቪዲዮ ክሊፕ እና ለድምጽ ማጫወቻው አንድ ዘፈን ይምረጡ እና መተግበሪያው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አውቶማቲካሊ ቪዲዮ ይፈጥራል።
የዳውንሎድ ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.magisto

☑️ @muleritsolutions2