AASTU Muslims union

@aastumuslims


ይህ የቴሌግራም ቻናል ሁሉንም የ አአሳቴዩ ሙስሊም ተማሪዎች የሚመለከት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ የተለያዩ ዳእዋና ሙሃደራዎች እንዲሁም ጀመዓውን የሚመለከቱ መልእክቶች ይለቀቁበታል። ከዚህ ውጪ ሌላ ቻናል የሌለን መሆኑን እና የትኛውም ከዚህ ቻናል ውጪ የሚለቀቅ ነገር እኛን እንደማይወክል እናሳስባለን።

ለማንኛውም አስተያየት

@ab097ab097
@abduw99

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:27


ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች

ክፋል ሁለት

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ለዘር ተኮር ቀልዶች ጥርስህን አታሳይ። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ ራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

ይቀጥላል...

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:26


Today we will have خلاصة نور اليقين kitab program inshallah

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:26


💫💫Welcome program invitation 💫💫

ነገ እሮብ 13/02/2017 በአልነጃሺ መስጂድ ለአዲስ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ይኖራል::
ፕሮግራሙ ላይም አዝናኝ እና አስተማሪ ትምህርቶች ይቀርባሉ::ሁላችሁም ፕሮግራሙ ላይ እንድትገኙ ስንጋብዝ በታላቅ ደስታ ነው::
 
💎ቦታ :አል ነጃሺ መሰጂድ
ሰዐት : ከ 8:00 -12 :00

Tomorrow, Wednesday,October 23/2024, there will be a welcome program for new students at Alnejashi Mesjid . In the program joyful and educative lessons will be presented.It is with great pleasure that we invite you all to attend the program.

💎Place : al-nejashi msjid
Time : 8:00 to 12:00

Nb. Please be on time; being late can lead to feelings of regret

https://t.me/aastumuslims

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:25


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته.
በኘሮግራማችን መሠረት ዛሬ በአላህ ፈቃድ በአል ነጃሺ መስጂድ ከመግሪብ ሰላት በኋላ የاصول الإيمان
ኪታብ ቂርአት ይኖረናል።

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:24


ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
ክፋል አንድ
~
ትምህርት እየተጀመረ ነው። ፈተና ሲደርስ መደናበር ወይም የአመቱ መጨረሻ ላይ ውጤትን ጭንቅ ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቁንም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከቀን አንድ ጀምረው በቁም ነገር መዘጋጀት ነው የሚያዋጣው። ከልቡ የተዘጋጀ ሰው በአላህ ፈቃድ የልፋቱን አያጣም። ጥሮ ግሮ ውጤት ባይመጣ እንኳ ሰበብ ያደረሰ ሰው የሚጠበቅበትን ተወጥቷል።
ይህን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ለተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ስብእና እንዲኖራቸው ያግዛሉ ያልኳቸውን የተወሰኑ ነጥቦት እንደሚከተለው አስፍሬያለሁና በማሰራጨት ብታግዙኝ ደስ ይለኛል።

① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ  ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚጎድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የኮፒ፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።

ይቀጥላል....

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:23


AASTU Muslims union pinned «السلام عليكم والرحمة الله وبركاته ውድ የAASTU የሙስሊም ተማሪዎች እነሆ የAASTU የሙስሊም ተማሪዎች ጀምአ የዳእዋ እና ኢርሻድ ክፍል ጋር በመተባበር በዘንድሮ በ2017አ.አ ልዪ ልዩ የቂርአት ፕሮግራሞችን ቀርፆ አላህ ካለ የፊታችን ሰኞ 11 /02 /2017 ወደ ቂርአት የሚገባ ይሆናል። በዘንድሮ አመት በቁርአን እና በኪታብ ዘርፎች በተለያዩ ሁኔታዎች ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቆ…»

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:23


በአል-ነጃሺ መስጂድ ወንዶችና ሴቶችን አሳታፊ የሆነ ሳምንታዊ የደርስ ኘሮግራም

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:23


السلام عليكم والرحمة الله وبركاته
ውድ የAASTU የሙስሊም ተማሪዎች እነሆ የAASTU የሙስሊም ተማሪዎች ጀምአ የዳእዋ እና ኢርሻድ ክፍል ጋር በመተባበር በዘንድሮ በ2017አ.አ ልዪ ልዩ የቂርአት ፕሮግራሞችን ቀርፆ አላህ ካለ የፊታችን ሰኞ 11 /02 /2017 ወደ ቂርአት የሚገባ ይሆናል። በዘንድሮ አመት በቁርአን እና በኪታብ ዘርፎች በተለያዩ ሁኔታዎች ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነው።
በቁርአን ፕሮግራም ላይ በሂፍዝ እና በነዘር ከቃኢደተ ኑራኒያ ጀምሮ እስከ 30 ጁዝ ቁርአን በተጅዊድ ለማስቀራት ፕሮግራሞችን ነድፏል። ቁርአንን ከመጀመሪያ እስከ ሂፍዝ ድረስ በካምፓስ ቆይታችን በህይወታችን ላይ ጥሩ ነገር አስቀምጠን  እንድንወጣ የሚያስችል ልዩ ዝግጅት ነው ።

በሌላ በኩል በኪታብ ዘርፋ በተለያዩ ፕሮግራሞች እና በብዙ አይነት ፈኖች ብቅ ብሏል።እነደ ጀምአችን የምንቀራቸው ኪታቦች አም(ሁሉን አካታች) እና ለሙብተዲእ (ለጀማሪዎች) ብለን ማህበረሰብ አካታች በሆነ መልኩ  በሁለት ከፋለን አዘጋጅተናል።

⚙️ለጀማሪዎች የተዘጋጁ ኘሮግራሞች የኪታብ ቂርአት ላልጀሙሩ እና ወደ ኪታብ እውቀት እንዲገቡ የሚያደርግ ከዚህም ባሻገር ጎን ለጎን ቁርአንን ላልጀመሩ ፣ ከዚህ በፊት ቀርተውም አሁን ላይ ተጅዊድን ጠብቀው አሳምረው መቅራት ለሚፈልጉ ሁሉ ያዘጋጀነው ኘሮግራምም አለ። ኘሮግራሙንም ለየት የሚያደረገው ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ ከተማሪዎች አልፎ ማህበረብንም ከግምት በማስገባት አካታች በሆነ መልኩ ተዘጋጅቷል። ይህም ሊሰጥ የታሰበው በቂሊንጦ መውጫ በር ፊት ለፊት በሚገኘው መድረሳ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ባለው ጊዜ ላይ ነው።
ሰኞ፣ረቡዕ እና ጁምኣ .... የቃኢደቱ ኑራንያ እና የነዘር ኘሮግራም ሲሆን ማክሰኞ እና ሀሙስ የ ሹሩጡ ሰላት (شروط الصلاة) ኪታብ የሚሰጥ ይሆናል።


⚙️ሁሉንም አጠቃላይ የሆኑት ኪታቦች(አም ኪታቦች) ደግሞ በተለያዩ ፈኖች ተዘጋጅተዋል።
🛑 ቂርአቶቹም ሁሉንም የጀምአው አባላት የሚያሳትፍ ሲሆን የሚሰጡትም ከዚህ በፊት እንደነበረው በአል-ነጃሺ መስጂድ  ይሆናል።
እነሱም፤
▪️1-በአቂዳ ፈን(علم العقيدة)
👉የሚቀራው ኪታብ፡ኡሱል አል-ኢማን (الأصول الإيمان)
የተሰኘው መሰረታዊ የእምነት ህጎችን በውስጡ አካቶ የያዘ ድንቅ መጽሐፍ ነው። በውስጡ የሰው ልጅ የመኖራቸውን ትርጉም ፤የሚኖሩለትን አላማ፤ ስለጌታቸው ማወቅ ያለባቸውን ነገር፤ የህይወታቸውን ስኬት፤ስለ ትክክለኛ አምልኮ፤የመጨረሻው ሀገር ስኬት፤የዘመኑ የጠመሙ እና የተለያዩ ሰዎች ብዥታቸው እና መልሶቹ  ምን ይህ ብቻ ብዙ ተዘርዝረው ማያልቁ የእምነት(የአቂዳ) እውቀቶችን የያዘ ኪታብ ተዘጋጅቷል።
🕐ጊዜው፥ዘውትር ስኞ ከመግሪብ እስከ ኢሻ
▪️2-የሲራ ፈን(علم السرة النبوية )
👉የሚቀራው ኪታብ፡ኹላሰቱ ኑረል የቂን (كتاب خلاصة النور اليقين)
ይህ ድንቅ የነብዩን የህይወት ታሪክ ከነብይነት በፊት ጀምሮ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ሙሉ የህይወታቸው ክስተት ሚዳስስ፤ለእስልምና የከፈሉት ዋጋ እና እንዴት ትክክለኛ እስልምና መኖር እንደሚቻል ጭምር እኛም ያለንበት ህይወት እንዴት መኖር እንዳለብን አቅጣጫ ሚሰጥ ኪታብ ከድንቅ ማብራሪያ ጋር ተዘጋጅቷል።
🕐ሰአት፥ዘውትር ማክሰኞ ከመግሪብ እስከ ኢሻ
▪️3-በሉጋ(በናህው)ፈን(علم النحو)
👉የሚቀራው ኪታብ፡መትን አጅሩሚያ(كتاب متن الأجروميا)
ይህ ኪታብ ብዙዎቻችን እንደምናቀው የአረበኛ ሰዋሰው ህግን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ልዩ ኪታብ ነው። ነህው እውቀት መማር ለእውቀት ፈላጊዎች እጅጉን አንገብጋቢ እና አሳሳቢ ነው። ምላስን ከትልቅ ስህተት ይጠብቃል።
በአጠቃላይ ይህንን እውቀት ማግኘት በየቦታው በጣም ከባድ ነው። እኛ ካምፓስ ላይ ግን  ዘውትር ማክሰኞ እና ሀሙስ ቀን ላይ ከ10፡30-11፡30🕐 ድረስ ተዘጋጅቷል። ይህንን እድል መጠቀም የኛ ሀላፍትና ነው
▪️4-በሙስጠልሀል ሀዲስ ፈን (علم مصطلح الحديث)
👉የሚቀራው ኪታብ፡መትኑ አል-በይቁኒያህ (متن البيقونية)
ይህ ኪታብ የሀዲስ አዘጋገብ እና የሀዲስ አመጣጥ ላይ ያለው ሁኔታዎች እና ሀዲሱ ከምን አንፃር ሰሂህ፤ደኢፍ፤ሀሰን እንደሚሆን የሚቃኝ እና የሚዳስስ ኪታብ ሲሆን የሀዲስ ውስጣዊ ሚስጥሩን እጅግ ፍንትው አድርጎ ሚያስረዳ መሳጭ ኪታብ ነው።
🕐ጊዜው ዘውትር ረቡእ ከመግሪብ እስከ ኢሻ
▪️5-የተጅዊድ ፈን(علم التجويد)
👉የሚቀራው ኪታብ፡......
ይህ ኪታብ ቁርአንን አሳምሮ እና አስውቦ መኻሪጅን በጠበቀ መልኩ ለመቅርአት እጅግ ወሳኝ ኪታብ ነው።በአጠቃላይ ቁርአንን ማንበብ ብቻ ሳይሆን በትክክል እንድናነበው ሳንሳሳት አቀራሩን ጠብቀን የሚያስችለን እውቀት ያስጨብጠናል።
🕐የሚሰጥበት ቀን፡ዘውትር ጁምአ እና ቅዳሜ ከመግሪብ እስከ ኢሻ
▪️6-የፊቅሂ ፈን علم الفقه
👉የሚሰጠው ኪታብ መትን ሰፊነቱ ነጃ
( متن سفينة النجاة)
በዚህንኛው ኪታብ ውስጥ ደግሞ መሰርታዊ የሆኑ የሰው ልጅ የእለት ተአለት እንቅስቃሴዎች የሚመለከቱ ነጥቦችንን ያዘለ። በአጠቃላይ እንዴት መኖር እንዳለብን ሚገልፅ ኪታብ ነው። ውስጥ ብዙ ተወርተው ማያልቁ ቁምነገሮችንን ይዟል።
🕐ጊዜው ዘውትር ሀሙስ ከመግሪብ እስከ ኢሻ

በሴቶች በኩል አዲስም ይሁን ነባር ተማራዎችን  ባማከለ መልኩ  የደርስ ኘሮግራም አዘጋጅተውላቹሀል። ከኘሮግራሙ ጋር በተያያዘ መረጃ የምትፈልጉ እህቶች ከታች ባለው username መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

@ab097ab097

🛑 በአጠቃላይ እነዚህ ኪታቦች ሁሉንም ያማከለ ኪታብ መቅራት ላልጀመረ እና ኪታብ መቅራት ስለማልችል ሚባል ሳይሆን እንደ ጠቅላላ እውቀት ብዙ እውቀቶችን የሚያስጨብጡ። የህይወት እንቅስቃሴዎቻችን ሚነካ መቅራት ለጀመሩት በሁሉም ደረጃ ላይ ለሚገኙት አስፈላጊ የሆኑ ኪታቦች በዚህ አመት ተዘጋጅተዋል። ሁላችንንም አካታች እና ሁላችንም ሚጠራ ልዩ ዝግጅት ላይ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በቀን 11-02-2017አ.አ በአላህ ፈቃድ ወደተግባር የሚገባ ይሆናል።

ዳእዋ እና ኢርሻድ ዘርፍ

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:20


﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ۝﴾

قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً»
በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል
اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمدﷺ 🍃🍂
ሱረቱል ካህፋንም መቅራት አንርሳ

መልካም ጁምኣ

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:20



      እኛ የት ነበርን??

  ሁለት ጓደኛሞች አብረው ከተማ ውስጥ እየዞሩ ናቸው። እና አንደኛው ወደ ትላልቅ ህንፃዎች ተመለከተና ለጓደኛው እንዲህ ብሎ ጠየቀው

"ይህንን ሁሉ ሀብት ሲታደል እኛ የት ነበርን?" አለው

  ጓደኛውም "ና" ብሎ እጁን ይዞ ወደ ሆስፒታል አስገባውና
  "ይህንን ሁሉ በሽታ ሲታደል እኛ የት ነበርን?" ብሎ ጠየቀው።


👌የተሰጠን ብናውቅ የተከለከልነው የለም!!


منقول

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:17


ጀግናና አሸናፊ ማነው

ታላቁ አሸናፊነት ስሜትን ማሸነፍ ነው።
የሽንፈት ሁሉ ሽንፈት ለጊዜያዊ ደስታ ብሎ የኣኺራን ደስታ የሚያሳጣ ወይም የሚቀንስ ነገር ማድረግ ነው።
منقول

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:17


«አኼራ እየመጣች ነው፣ዱንያ ላትመለስ እየሄደች ነው።የአኼራ ልጆች ሁኑ። የዱንያ ልጆች አትሁኑ። ዛሬ ሥራ እንጂ ሂሳብ የለም። ነገ ሂሳብ እንጂ ሥራ የለም።»

ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:17


إِنَّا ِلِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ !

የጀመኣችን አባል የሆነች እህታችን እናቷ ወደ አኼራ ስለሄደች ሁላችንም ዱኣ እንድናደርግላቸው  አደራ ብለዋል ። አላህ ቀብሯን የጀነት ጨፌ ያድርግላት በጀነተል - ፊርደውስም ያኑራት። ለእህታችንም አላህ ሰብሩን ይስጣት።

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:12


በ2017 አ.አ ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ  አዲስ ተማሪዎች
=======================================================================================
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ጥቅምት 03 እና 04 /2017 ዓ.ም  አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡ በመሆኑም ከተለያዩ ቦታዎች ለምትመጡ ተማሪዎቻችን ሁለት ቦታዎች ላይ ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያዘጋጀ ስለሆነ ይህን የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቅማችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መምጣት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት ጣቢያዎች
•  መገናኛ እና ቃሊቲ
  # እሁድ 5፡00 ሰዓት
  # ሰኞ 4፡00 ሰዓት  በተጠቀሱ ጣቢያዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:10


Here’s AASTU Muslim Union's
Al- nejashi masjid on the map 👇👇👇

https://maps.app.goo.gl/hRfVw2fCL4RJWTK17?g_st=it

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:10


ማስታወቂያ

ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና  ወስዳችሁ ምርጫችሁን አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖዎሎጂ ዩኒቨርሲቲ(AASTU) በማድረግ እኛን 🔜 ለመቀላቀል በመጠባበቅ ላይ ላላችሁ በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ስናስተላልፍ በታላቅ ደስታ ነው::በመቀጠልም የዩኒቨርስቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር 03/02/2017 (እሁድ) እና 04/02/2017 (ሰኞ) ስለሆነ በእለቱ የAASTU 🕌 ሙስሊም ተማሪዎች ህብረትም ደማቅ አቀባበል የሚያደርግላችሁ ይሆናል :: እናንተም ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ማንነታችሁን(ሙስሊም መሆናችሁን) ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን::

Beeksiisa
🧑‍💻Barana Qormaata intraansi fudhattani filanno keessan yunivarsiiti saayinsii fi teknolojii Addis Ababa taasisudhaan nu waliin 🔜 makamuf qophii irraa jirtan Hundaaf dhaamsa baga gammaddan yeroo isinif dabarsinu gammachu guddaa nutti dhagahama .Itti ansudhaan sagantaan simannaa barattootaa yunivarsiiti keenya Oct 13 -2024 (sun) and 14 - 2024 (mon) waan ta’ef guyyaa sanitti gamtaan barattoota 🕌 musliimaa yunivarsiiti AASTU simannaa ho’aa kan isinif taasisu ta’a. Isinis , jaalatamoo barattoota harawaa enyummaa (musliima ta’u keessan) beksiisudhaaf eeyyamamaa akka nuf taatan kabajaan isiin beeksifnaa.

Announcement
🪴we would like to convey a message of congratulations to all of you who are took the entrance exam this year and waiting to join us by choosing Addis Ababa Science and Technology University (AASTU) .Next, since our university's student admission program is on Oct 13 -2024 (sun) and 14 - 2024 (mon) on that day the AASTU 🕌Muslim Students Union will welcome you warmly , Dear 🧳 new students, we respectfully ask for your sincere cooperation to inform us of your identity (being a Muslim).

💴 For any support and general info call at

📞 +251979037273 Abduselam

📞 +251928988230 Faruk

For those who enter in tuludimtu gate use the following numbers

📞 +251944748863  Reyan

📞 +251955370783 Abdurzak

For those who enter in klinto(main) gate use the following numbers

📞 +251913010328 Ilyas

📞 +251910208461 Anwar

For Somali use                          +251947488427 Abdurzak,
For oromifa use
  📞  +251903604206 awol,
For seltegna use
📞 +251910208461 Anwar

To find female students' representative Address please call at

+251979037273

💥Join our telegram channels

AASTU Muslim union's Official channel link.             👇👇
https://t.me/aastumuslims

AASTU Muslim union's qirat channel link.              👇👇
https://t.me/+OMuThh9HOC40Yjk0

AASTU Muslim union's Academic
channel link   👇👇

https://t.me/+U0uC3sukqiRmMGFk

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:10


💡 የጁምአ ሰላት "ራቲባህ" ማለትም፤ ከፊት የሚሰገድ የተደነገገ ሱና የለውም። ነገር ግን ጁምዓ ቀን ፀሀይ ወደ መጥለቂያዋ ከመዘንበሏ በፊት ሱና ሰላት መስገድ ሙስተሀብ ነው።
ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-
(በጁምዓ ቀን የታጠበ ሰው፣ በቻለው ልክ ራሱን ያጠራ፣( ንፀህናውን/ ፅዳቱን የጠበቀ) ከዚያም ቅባት ወይም ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ወደ መስጂድ የሄደ፣ ሁለት ሰዎችን በተቀመጡበት ሳይለያይ( በመሀላቸው ገብቶ ሳይቀመጥ)፣ ለርሱ የተደነገገውን  ያህል የሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ ወደ ሚንበር ሲወጣ በዝምታ ኹጥባውን ያደመጠ፣  በዚህኛው ጁምዓ እና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል ምህረት ይደረግለታል። )
እንዲሁም ፀሀይ ከተዘነበለችበት ሰአት አንስቶ ኢማሙ  ወደ ሚንበር እስኪወጣ ሱና ሰላት መስገድ የተወደደ ነው።

📚 የፊቅህ ኢንሳይክሎፒዲያ/ዱረር አስ-ሱንኒያ ድህረ ገጽ

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:10


ከቀናቶች በላጬ የጁምአ ቀን ነው።

ረሱልም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾
“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531

AASTU Muslims union

21 Jan, 00:09


ለሰላት ስትመጡ መታወቂያ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ