ህዳር ፡ 12/2017 ዓ.ም
++++++++++++++++++++++++++++++++++
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከዋና ስራዎቹ መማር ማስተማር፤ምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተለያዩ ክፍት ቦታዎችን ወደ ምርታማነት በመቀየር አትክልት ፤ፍራፍሬ እና ጥራጥሬ በማልማት ማህበረሰቡን የሌማት ቱርፋት ተጠቃሚ እንዲሆን ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአንድ በኩል የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ በሌላ በኩል ማህበረሰቡን ከግብርና ምርቶች ተጠቃሚ የሚያደርገው የልማት ትሩፋት አካል የሆነውን በክረምት ወራት የለማውን የስንዴ ምርት እየሰበሰበ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 8 ሄክታር የሚሆን ክፍት ቦታ ስንዴ በማልማት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ምርቱ እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡