አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ “ምርት አቅርቦት ለገበያ ማረጋጋት!” በሚል መሪ ቃል ባለፉት አመታት ለገበያ መረጋጋቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረክቱ አምራችና አቅራቢዎች እንዲሁም ለሴክተር ተቋማት የእዉቅና ሽልማት መድረክ በኢሊሊ ሆቴል በዛሬው ዕለት አከናውኗል።
በፕሮ ግራሙ ላይ እንደተገለፀው ከተማ ግብርና በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የግብርና ምርትና አገልግሎቶችን በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርስ በማድረግ ያበረከተው አሰተዋጽኦ ቀላል አይደለም።
በእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሙ ላይ እንደተገለፀው ንግድ ቢሮ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ ለማገናኘት ባዘጋጃቸው 82 የቅዳሜና እሑድ ገበያዎች ላይ የግብርና ምርቶች ይቀርቡ እንደነበረ ተገልጿል። እየቀረቡም ይገኛል። ኮሚሽናችንም ላበረከተውም አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጥቷል።
በተጠቀሱትም የገበያ ቦታዎች ግብርና እስከአሁን ባከናወናቸው ተግባራት የነዋሪዉን ኑሮ በማቃለል ረገድ ምርት በሰፊዉ በማቅረብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ መሆኑ ተጠቅሷል።
አሁንም በገና ዋዜማ በተሠራዉ ቅንጅታዊ ስራ በየትኛዉም የግብይት ቦታ ምርት በሰፊዉ የገባ በመሆኑ ምንም አይነት የምርት አቅርቦት እጥረት እንደሌለና ሸማቹም በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንደሚችልም ተነስቷል።
"ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚለው መርህ መሰረት አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚ በመሆኑ የከተማ ግብርና ሚናው ቀላል የማይባል ነው።