የመዳም ቅመም እንደወጣች ቀረች
<<በአሰሪዎቿ ለደረሰባት ጉዳት መጠኑ ከፍ ያለ ገንዘብ በፍርድ ቤት ተወሰኖላታል።ግን ጠፋች>>ከዱባይ የደረሰኝ መረጃ ነው
ይህንን መረጃ በደንብ ተመልከቱትና በግሩፖቻችሁ ሼር አድርጉት
በፓስፖርት ምስሉ ላይ የምትታየው ዘምዘም መሐመድ አሊ ትባላለች።ከአመታት በፊት(2004ዓ.ም)የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሰው ቤት ስትሰራ በአሰሪዎቿ ጉዳት ደርሶባት ነበር በማለት ጥቆማውን ያመጡት ወዳጆች አስረድተዋል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠበቃ ቀጥሮላት ጉዳዩ በህግ እንዲያዝ ተደርጎ እሷ ወደ ሀገሯ ተላከች።የፍ/ቤት ክርክሩ በተጎጅዋ ጠበቃ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ለእሷም ጉዳቷን ታሳቢ ያደረገ ጥሩ ገንዘብ ተወሰነላት።አሁን አድራሻዋ ጠፋ።ፓስፖርት ያወጣችው ደሴ ከተማ ኢሚግሬሽን ስለነበር ኤምባሲው ሰነዷን አስፈልጎ በጊዜው ሁሉም ዲጅታል ስላልነበር በሀርድ ኮፒ የተቀመጠው በሰሜኑ ጦርነት ጠፍቷል።በዚህም ምክንያት አድራሻዋን ማግኘት አልተቻለም ሲሉ ወዳጆቼ ነግረውኛል።
ለተጎጅዋ ዘምዘም መሐመድ አሊ በፍርድ ቤት የተወሰነላትን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በፊት መወሰድ አለበት።በህይወት ካለች ራሷ ከሌለች እናትና አባት ከህጋዊ አካል የወላጅነታቸውንና በህይወት አለመኖሯን የሚያስረዳ መረጃ ይዘው መውሰድ እንደሚችሉ እነኝሁ ኢትዮጵያዊያን ነግረውኛል።ስለትክክለኛ ወላጅነታቸው የዘረመል(DNA) ምርመራ ይደረጋል ያሉት ወዳጆቼ መልዕክቱንም ፅፌ በማስተላለፍ እንዲተባበራቸው ጠይቀውኛል።ይሄው አስተናግጃለሁ።እናንተ ደግሞ ሼር በማድረግ ለሌሎችም አድርሱት🙏
👇👇👇👇
👉Abronet tube
👉አብሮነት ቲዩብ