TIKVAH-SPORT

@tikvahethsport


TIKVAH-SPORT (English)

Are you a sports enthusiast looking for a community to share your passion with? Look no further than TIKVAH-SPORT! This Telegram channel is dedicated to all things sports-related, from the latest game updates to insightful analysis and discussions. Whether you're a fan of football, basketball, tennis, or any other sport, you'll find like-minded individuals to connect with here. TIKVAH-SPORT provides a platform for sports lovers to interact, share news, and engage in friendly debates. Stay updated on the latest scores, player transfers, and tournament schedules with the help of our dedicated team of moderators. Join TIKVAH-SPORT today and be a part of a vibrant sports community that celebrates the thrill of the game!

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 14:59


ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአመቱ የመጀመርያ ድሉን አሳካ !

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከባህርዳር ከተማ ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ የድል ግብ አቤል ሀብታሙ ከመረብ አሳርፏል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በውድድር አመቱ የመጀመርያ ድሉን ሲያሳካ የጣና ሞገዶቹ በአንፃሩ ሁለተኛ የሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

3⃣ ባህርዳር ከተማ - 6 ነጥብ

9⃣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ - 5 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ?

ቅዳሜ - አርባ ምንጭ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ

እሁድ - ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 14:10


አርሰናል ለሳሊባ ቀይ ካርድ ይግባኝ ይጠይቃል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ ባሳለፍነው እሁድ ቡድኑ ከቦርንማውዝ ጋር ባደረገው ጨዋታ የቀይ ካርድ መመልከቱ ይታወቃል።

ሆኖም መድፈኞቹ የዳኛ ውሳኔውን በመቃወም ለእንግሊዝ ኤፍኤ ይግባኝ ላለመጠየቅ መወሰናቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ዊሊያም ሳሊባ አርሰናል በሚቀጥለው እሁድ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርገው ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብር የሚያመልጠው ይሆናል።

@Tikvahethsport          @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 13:58


" የባርሴሎና አምበል መሆን የተለየ ስሜት አለው " ራፊንሀ

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራፊንሀ ባርሴሎናን በአምበልነት መምራት የተለየ ስሜት እንዳለው ገልጿል።

" የባርሴሎና አምበል መሆን ልዩ ስሜት አለው " የሚለው ራፊንሀ " ይህን ሀላፊነት እየተወጣሁ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።" ሲል ተናግሯል።

ተጨዋቹ የውድድር ዘመኑ ለእሱ ጥሩ መሆኑን በመግለፅ " አሰልጣኙ እና የቡድን አጋሮቼ በአስቸጋሪ ጊዜያት የጣሉብኝ እምነት አሁን ላይ ላለሁበት ደረጃ ትልቅ ድርሻ እለው" ብሏል።

ራፊንሀ አያይዞም የነገው ተጋጣሚያቸው ባየር ሙኒክ ጠንካራ ቡድን መሆኑን ጠቅሶ " ጨዋታውን ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን " ሲል ተደምጧል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 13:35


ጀማል ሙሲያላ ወደ ባርሴሎና ይጓዛል !

ጀርመናዊው የባየር ሙኒክ አማካይ ጀማል ሙሲያላ
ቡድኑ ነገ ከባርሴሎና ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ የመሰለፍ እድል እንዳለው ተገልጿል።

በጉዳት ከሜዳ ርቆ የነበረው ጀማል ሙሲያላ በትላንትናው ዕለት የቡድን ልምምድ መጀመሩ ይታወሳል።

የክለቡ ዋና ዳይሬክተር ክሪስቶፍ ፍሪዩድ በሰጡት አስተያየት ተጨዋቹ ወደ ባርሴሎና በሚያቀናው የቡድኑ ስብስብ እንደሚካተት አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም " ጀማል ሙሲያላ ከቡድኑ ጋር ወደ ባርሴሎና ያቀናል ነገር ግን ለምን ያህል ደቂቃዎች እንደሚጫወት አናውቅም " ብለዋል።

@Tikvahethsport            @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 12:56


" ባየር ሙኒክ ለእኔ የተለየ ክለብ ነው " ሀንሲ ፍሊክ

የባርሴሎናው ዋና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ቡድናቸው ነገ ከባየር ሙኒክ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኙ በቆይታቸው ምን አሉ ?

- “ ባየር ሙኒክ ለእኔ የተለየ ክለብ ነው ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የባርሴሎና አሰልጣኝ ነኝ ስለዚህ ቡድኔ መልካም እንዲገጥመው እመኛለሁ።

- ባየር ሙኒክ በቪንሴንት ኮምፓኒ ስር ጠንካራ መሆኑን አሳይቷል ጨዋታው ፈታኝ እንደሚሆን ግልፅ ነው በጥሩ ሁኔታ መዘጋጀት ይኖርብናል።

- ከትልልቅ ክለቦች ጋር ስንጫወት ራሳችንን መፈተን እንፈልጋለን ለዚህም የነገው ጨዋታ ጥሩ ፈተና ይሆነናል።

- ደጋፊዎቻችን በነገው ጨዋታ ይበልጥ እንዲያበረታቱን እንፈልጋለን ይህም ጨዋታውን እንድናሸንፍ ያግዘናል።“ ብለዋል።

በጨዋታው የትኞቹ ተጨዋቾች ይመለሳሉ ?

- ፍሬንኪ ዲ ዮንግ እና ጋቪ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

@Tikvahethsport        @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 12:34


" ዋንጫዎችን እያሸነፍን መቀጠል እንፈልጋለን " ፔፕ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የነገው ተጋጣሚያቸው ስፓርታ ብራጋ ጥሩ ቡድን መሆኑን ገልፀዋል።

" ስለ እነሱ ብዙም እውቀቱ የለኝም ነገር ግን ባለፉት ቀናት ባደረግኩት ምልከታ ጥሩ ቡድን መሆናቸውን መረዳት ችያለሁ " ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናገረዋል።

አሰልጣኙ ቡድናቸው ያለ ሮድሪም ጠንካራ መሆኑን በመግለፅ "አሁንም በቡድኔ ደስተኛ ነኝ ከዚህ በላይ ጥሩ ብቃት ማሳየት እንደምንችል እርግጠኞች ነን" ብለዋል።

ፔፕ ከጆን ስቶንስ ጋር ያላቸው ግንኙነት የአባት እና ልጅ መሆኑን በመጠቆም "እርሱ ለቡድናችን እየሰጠ የሚገኘው ጥቅም የሚደንቅ ነው" በማለት ተናግረዋል።

" ዋንጫዎችን እያሸነፍን መቀጠል እንፈልጋለን ለዚህም ሁልጊዜ ጠንክረን እንሰራለን ተጨዋቾቼ እያንዳንዱን ጨዋታ ለማሸነፍ የሚያደርጉት ጥረት የሚያስደንቅ ነው" ፔፕ ጋርዲዮላ

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 12:00


ጃክ ዊልሸር በሀላፊነት ሊሾም ነው !

የቀድሞ እንግሊዛዊ የአርሰናል ተጨዋች ጃክ ዊልሸር የሻምፒዮን ሺፑን ክለብ ኖርዊች ሲቲ በሀላፊነት ሊረከብ መሆኑ ተገልጿል።

የ 32ዓመቱ ጃክ ዊልሸር ኖርዊች ሲቲን ለሚቀጥሉት ሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ጃክ ዊልሸር በአሁን ሰዓት የቀድሞ ክለቡ አርሰናልን ከ 18ዓመት በታች ቡድን በአሰልጣኝነት እየመራ ይገኝ ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 11:52


ሲቲ የተጨዋቾቹን ግልጋሎት አያገኝም !

ቤልጂየማዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ኬቨን ዴብሮይን ከነገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።

“ ዴብሮይን ለምን ያህል ጊዜ ርቆ እንደሚቆይ አላውቅም ነገርግን ለመመለስ ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው “ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

እንግሊዛዊው ተከላካይ ካይል ዎከር በበኩሉ ከጨዋታው ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘውም ኦስካር ቦብ በሚቀጥለው የካቲት ወር ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 11:28


“ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኮርቻለሁ “ ፓትሪስ ሞትሴፔ

“ ኢትዮጵያዊያን እግርኳስ አፍቃሪያን ናቸው “

46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን " ካፍ " ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተካሄዷል።

የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የካፍ ሥራ ሀላፊዎች ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ለተደረገው አቀባበል መደሰታቸውን ያነሱት ፓትሪስ ሞትሴፔ “ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኮርቻለሁ “ በማለት ተናግረዋል።

“ ዶ/ር ዐብይ የእግርኳስ ፍቅር አላቸው “ ያሉት ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን እግርኳስ ለማሳደግ ቁርጠኛ ናቸው ብለዋል።

“ ኢትዮጵያ አፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት በመወሰኗ ኮርቻለሁ ኢትዮጵያዊያን እግርኳስ አፍቃሪያን ናቸው “ ሲሉ ፓትሪስ ሞትሴፔ ገልፀዋል።

ሌሎች የተወሰኑ ሀገራትም የ 2029 አፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንደሚፈልጉ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ “ ውሳኔውን በትክክለኛው ሰዓት የካፍን ህግ ተከትለን እንወስናለን “ ብለዋል።

ሀገራት በሜዳቸው መጫወት አለመቻላቸው እንዳሳዘናቸው የገለፁት ፓትሪስ ሞትሴፔ “ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚያኮራ ታሪክ አለው በሜዳው ነው መጫወት ያለበት “ ብለዋል።

“ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በአለም በትልቅ ደረጃ ሊነሱ የሚችሉ ክለቦች ናቸው በራሳቸው ሜዳ መጫወት አለባቸው “ ሲሉ ፓትሪስ ሞትሴፔ ክለቦቹን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

“ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ታለንት ያላቸው ተጨዋቾች አሉ አቡበከርን መመልከት ይቻላል አደገኛ ተጨዋች ነው ለዛ ነው የሚጎዱት።“ ፓትሪስ ሞትሴፔ

የኢትዮጵያ እግርኳስ የወደፊት ተስፋ ብሩህ መሆኑን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ በሰጡት አስተያየት አክለው ገልፀዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 11:27


🇪🇹⚽️ #ዋናው፣ ከስፖርት ትጥቅም በላይ! 🇪🇹⚽️

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዋናው ስፖርት የተሰራውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያ ለፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በስጦታ አበርክተውላቸዋል።

46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባኤን እያስተናገደች ያለችው ኢትዮጵያ ትናንት ምሽት በብሔራዊ ቤተመንግስት ለእንግዶቿ የራት ግብዣ አድርጋለች።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህ ወቅት ከካፍ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙሴፔ ጋር ለፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በፍሬም ውስጥ የተቀመጠ ዋናው ስፖርት ትጥቅ ብራንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያን በስጦታ አበርክተዋል።

በራስ በተሰራ እና የሀገር ኩራት የሆነ ብራንድ በመገንባታችን ክብር ይሰማናል።

       🌍 Made in Africa 🌍

Contact us!
📞 8289


Instagram | Facebook | TikTok  | X  | Youtube

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 11:27


🏆💥 የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋቾችን የምናይበት የሻምፕዮንስ ሊግ ፍልሚያ ወደ ሜዳ ይመለሳል!

🔥 ድሉ የማን ነው?

👉 ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በSS Premier League ቻናል 223 በሜዳ ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3yBcOHc

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 10:09


ቶኒ ክሩስ ወደ አሰልጣኝነት ይመጣል ?

በቅርቡ ጫማውን የሰቀለው ጀርመናዊው ኮከብ ቶኒ ክሩስ ወደ አሰልጣኝነት የመምጣት ፍላጎት እንደሌለው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ቶኒ ክሩስ በቀጣይ “ አሰልጣኝ የመሆን እቅድ የለኝም “ ሲል ከዘ አትሌቲክ ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ አረጋግጧል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ምክትል እንዲሆን ከጠየቁት በሀሳብ ማገዝ እንደሚፈልግ ነገርግን በድጋሜ ወደ እግርኳስ የመመለስ አቅድ እንደሌለው ክሩስ ጠቁሟል።

ስኬታማ የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወትን ማሳለፍ የቻለው ቶኒ ክሩስ አሁን ላይ በማድሪድ ከተማ በከፈተው የራሱ አካዳሚ በመስራት ላይ ይገኛል።

@Tikvahethsport         @Kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 09:50


የአርሰናል እና ሊቨርፑልን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን እሁድ የሚጠበቀውን የአርሰናል እና ሊቨርፑል የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ኤምሬትስ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ አንቶኒ ቴለር በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታው እሁድ ምሽት 1:30 በኤምሬተስ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@Tikvahethsport         @Kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 07:38


“ ትልቅ ሳምንታት ትልቅ አቋም ይፈልጋሉ “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በዚህ ሳምንት ላሉበት ጠንካራ ጨዋታዎች በተሻለ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል።

" የበርንማውዙን ጨዋታ ሽንፈት ብስጭታችንን በመውሰድ በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ልንጠቀምበት ይገባል።" ሲሉ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

“ ትልቅ ሳምንታት ትልቅ እንቅስቃሴ ማድረግን ይፈልጋሉ “ የሚሉት ሚኬል አርቴታ አሁን ከፍ የምንልበት ጊዜ ነው በማለት ተናግረዋል።

አርሰናል ዛሬ ምሽት በሻምፒየንስ ሊጉ ሻክታር ዶኔስክን ሲያስተናግድ እሁድ በሊጉ ከሊቨርፑል ጋር ተጠባቂ ጨዋታውን ያደርጋል።

@Tikvahethsport         @Kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 06:22


“ ትልቁ ግባችን ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ ነው “ ሜሪኖ

የመድፈኞቹ አማካይ ሚኬል ሜሪኖ ዋንጫ የማሸነፍ ልምዱን ወደ አርሰናል ቡድን ውስጥ ይዞ መምጣቱን ተናግሯል።

“ ዋንጫ የማሸነፍ ተሞክሮ አለኝ “ የሚለው ሚኬል ሜሪኖ “ በግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ ጨዋታዎች የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንደሚያውቅ ገልጿል።

“ ከበርንማውዝ ጨዋታ የተሻለ መንቀሳቀስ አለብን ከስህተታችን መማር እና ወደ ጥሩ ስሜት መመለስ አለብን “ ሲል ሚኬል ሜሪኖ ጨምሮ ተናግሯል።

“ እዚህ ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ ጥሩ ይሆናል አሁንም ብዙ ርቀት መጓዝ አለብን ይህንን ለማድረግ ፣ አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ አሉን ይህ የመጨረሻው አላማችን ነው።" ሜሪኖ

@Tikvahethsport         @Kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

22 Oct, 06:15


የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

10:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ባሕር ዳር ከተማ

1:00 ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን

1:45 ኤሲ ሚላን ከ ክለብ ብሩጅ

4:00 አርሰናል ከ ሻክታር ዶኔስክ

4:00 አስቶን ቪላ ከ ቦሎኛ

4:00 ጁቬንቱስ ከ ስቱትጋርት

4:00 ፒኤስጂ ከ ፒኤስቪ

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ዶርትመንድ

@Tikvahethsport         @Kidusyoftahe