EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow


Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Promotional Article for EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) (English)

Are you looking for a reliable source of news and information from Ethiopia? Look no further than EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) Telegram channel! With the username 'ebcnewsnow,' this channel provides up-to-date news, current affairs, and in-depth analysis of events happening in Ethiopia and around the world. EBC, short for Ethiopian Broadcasting Corporation, is the oldest and most trusted public broadcaster in Ethiopia. Established in 1960, EBC has been at the forefront of providing news and entertainment to the Ethiopian people for over six decades. With a team of experienced journalists and reporters, EBC delivers accurate and unbiased news coverage on a wide range of topics, including politics, economy, culture, and sports. Whether you are a resident of Ethiopia, a member of the Ethiopian diaspora, or simply someone interested in staying informed about the latest developments in the country, EBC's Telegram channel is the perfect source for you. From breaking news alerts to in-depth feature stories, EBC covers it all, ensuring that you are always in the know about what's happening in Ethiopia. By joining EBC's Telegram channel, you will have access to a wealth of information at your fingertips. Stay updated on the latest political developments, economic trends, and social issues facing Ethiopia and its people. Get exclusive interviews with key figures in Ethiopian society, as well as live coverage of major events and press conferences. In addition to news coverage, EBC's Telegram channel also features entertaining and informative content, including cultural shows, educational programs, and sports highlights. Whether you are interested in learning more about Ethiopian traditions and customs or keeping up with the latest sports scores, EBC has something for everyone. Don't miss out on the opportunity to stay informed and connected with EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) through their Telegram channel. Join 'ebcnewsnow' today and start receiving the latest news and updates from one of Ethiopia's most trusted news sources. Stay ahead of the curve and be the first to know about the stories that matter to you. Subscribe now and experience the power of reliable news and information at your fingertips!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 14:16


ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ
***********************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ ጋር በአርባምንጭ ከተማ ተወያይተዋል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ ውይይቱ ክልሉ ከአገልግሎቱ ጋር በቅንጅት ለመስራት እና ክፍተቶችን ለይቶ ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስንቀናጅ እና ስንደመር የህብረተሰቡን ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፤ አገልግሎቱ ቃል የተገባላቸው የገጠር ቀበሌዎች መብራት እንዲያገኙ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ለዚህም የክልሉ መንግስት አስፋላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ በበኩላቸው፤ አገልግሎቱ አዲስ የሪፎርም ሥራ በመጀመር ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

በህብረተሰቡ ለሚነሱ የመብራት ተደራሽነት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እና የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋትም የተለያዩ ሥራዎች መጀመራቸውን ማስረዳታቸውን ከርዕሰ መሥተዳድሩ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 14:02


በወልዲያ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን ተገላገለች
******************
በወልዲያ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም መገላገሏን የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገለጸ።
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚድዋይፍሪ ባለሞያ የሆኑት ወጋየው ገብሬ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር እንደገለጹት፤ሰላማዊት ደርቤ የተባለች የ31 ዓመት እናት በትናትናው እለት ንጋት ላይ 4 ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ በሰላም ተገላግላለች፡፡
ከተወለዱት ሕጻናት መካከል የሁለቱ ክብደት ከመጠን በታች በመሆኑ በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ አራቱ ልጆች እና እናታቸው በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
የሕጻናቱ ወላጅ እናት ከዚህ ቀደም አንድ ልጅ እንዳላትም ጠቁመዋል፡፡
በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም 3 ልጆችን የወለደች እናት መኖሯን አስታውሰው፤ይህ ክስተት ግን ለሆስፒታሉም ሆነ ለአከባቢው አዲስ ነው ብለዋል፡፡
በሜሮን ንብረት
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0YMaT3j1CLe3UFir2Rvya2PX9R7gM1T1arv1XTVjqVpfEHj1xyPWtJ7bL4UD9vRHJl

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 13:40


በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመርኩ ነው - የአዲስ አበባ ፖሊስ
*************************

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከል እና በአካባቢው በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁሟል፡፡

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ላይ ቀላል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱንም አመላክቷል፡፡

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍ እና ተባባሪነትም ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረሰው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደ ፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጿል፡፡

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 13:30


የዓለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ሽኝት ተደረገላቸው
*******************

የዓለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ለፕሬዚዳንቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በትላንትናው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፣ የካፍ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ፣ የፊፋ ዋና ፀሐፊ ማትያስ ግራፍስትሮም፣ የካፍ አባል ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች፣ የቀጣናዊ እግር ኳስ ማኀበራት ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 12:59


አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኢሉባቦር ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው
************************

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኢሉባቦር ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዞኑ ሀሉ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ የሻይ ቅጠል እና ሌሎች ልማቶችን በመመልከት ላይ ናቸው።

በክልሉ የአርሶ አደሩን እና የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋግጣሉ ተብለው ተስፋ ከተጣለባቸው መስኮች አንዱ የሻይ ቅጠል ልማት ሲሆን፤ በኢሉባቦር ዞንም ስራውን በአርሶ አደሮች ዘንድ ለማስፋፋት እየተሰራ ይገኛል።

የክልሉ መንግስት የሻይ ቅጠል ልማትን ጨምሮ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ የግብርና ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየተገበረ መሆኑ ይታወሳል።

በኢሉባቦር ዞንም የሻይ ቅጠልን ጨምሮ ሩዝ፣ ስንዴ፣ ማር እና የቡና ልማት ኢንሼቲቮች በዋናነት እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡

የኢሉባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቻላቸው አዱኛ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት በዞኑ በጉመሮ ሻይ ቅጠል ልማት ድርጅት ብቻ ሲካሄድ የቆየውን የሻይ ቅጠል ልማት ወደ አርሶ አደሮች የማስፋፋት ሥራ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።

እየተደረገ ባለው ጥረትም በአሁኑ ወቅት በዞኑ 2 ሺህ 475 ሔክታር መሬት ላይ የሻይ ቅጠል ልማት በአርሶ አደሮች እየተካሄደ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 12:51


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ
******************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አግዷል፡፡

ቦርዱ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዳስታወቀው የታገዱት ፓርቲዎች የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ናቸው።

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ለጊዜው ከማንኛውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ ነው።

በመሆኑም ቦርዱ የሰጠውን የዕግድ ውሳኔ እስከሚያነሳ ድረስ ከላይ የተገለጹት ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በሚያዘጋጃቸው ጉባዔዎች ላይ ሊገኙ፣ ሊመርጡም ሆነ ሊመረጡ እንዲሁም በኮሚቴ አባልነት ሊያገለግሉ አይችሉም ተብሏል።

የጋራ ምክር ቤቱ የዕግድ ውሳኔ የተላለፈባቸውን ፓርቲዎች ከማንኛውም የምክር ቤቱ ሥራዎች እና እንቅስቃሴዎች እንዳይካፈሉ እንዲያደርግም ቦርዱ አሳስቧል።

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 11:55


የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅነት ጥያቄ በካፍ የአሰራር ስርዓት ይታያል - የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ
**********************

የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅነት ጥያቄ በካፍ የአሰራር ስርዓት እንደሚታይ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ተናግረዋል፡፡

የካፍ መስራች አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ሚና እንዳላትም አውስተዋል፡፡

ለአፍሪካ ነጻነት ትልቅ አቅም የነበረችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ በትክክለኛ ጊዜ ለካፍ ጥያቄ ማቅረቧንም አንስተዋል፡፡

“ኢትዮጵያውያን ለእግር ኳስ ያላቸውን ከፍ ያለ ስሜት እረዳለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ እግር ኳስን ህዝባዊ አንድነትን ለመፍጠር መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስጎበኟቸው በግንባታ ላይ ባሉ ስታዲየሞች እና የስፖርት መሰረተ ልማቶችም መደሰታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ በካፍ የአሠራር ሂደት እንደሚታይም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 11:30


ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ ከተመድ ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ
**********************

ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መካከል ያለውን ቀጣናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም የባለብዙ ወገን ትብብርን በይበልጥ ማጠናከር እና ማሳደግ እንደሚገባ መምከራቸውን ከፕሬዚዳንቱ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

22 Oct, 10:58


ኢትዮጵያ እያካሄደች ላለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ገለጸ
*******************

ኢትዮጵያ እያካሄደች ላለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጄቫ ገልጸዋል።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን፤ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጄቫ እና ከአይኤምኤፍ የአፍሪካ ዲፓርትመንት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ እያካሄደች ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በቀጣይ የትብብር መስኮች ዙሪያ ተወያይቷል።

በውይይቱ አቶ አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ ያስቀመጠቻቸውን የለውጥ አጀንዳዎች ከግብ ለማድረስ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0QwcjWayPWLDMaJBYkkRMN3sDEDZ3sJLw7YnxM6MGY5HfjWuvKHpSAjgMuaqLmct3l