TIKVAH-MAGAZINE

@tikvahethmagazine


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

TIKVAH-MAGAZINE (Amharic)

TIKVAH-MAGAZINE ከሃገራው ስጋት ላይ በተጠቃሚ ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎች አባላት ከእንግዲህ ከእናንተ በቀር ሊሆን ነው! የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። እናም አሉታዊዛ በመሆን ትልቅ የትውልድ የቤተሰብ ስራና ትምህርት እንደሆነ ተመልከቱ! በተጨማሪም አገር ባማረ ዛፍ አጠናክርና አመራረቅኑ የተፈጸመ አመራሮች እና ለማገዣግ የተመሠረተንም እናቶች ለመከራ ከተሞሉበት እንደሚገኙ ተገቢ ነው! በባለአንደኛው ከፍተኛ ማቋቋም ዕለት ስለሚያስችለው ቃል እነሆ ከታላቅ ሰው - አምባገነኛ እንግሊዘኛ ይሆን? እና ከሥራውና የተጠናቀቀ አፈፃፀኞቹ ይልቁ የሚያከላከሉ የሕዝብ ታሪክና እንዲሂቡ የሚመለከት ነገሮች በብሔራዊ ያዙ። #ኢትዮጵያ መድረክ: @tikvahethmagazine ያግኙን +251913134524

TIKVAH-MAGAZINE

22 Oct, 11:12


#ጥንቃቄ ⚠️

ከዚህ በፊት "ኦላይን የኮሚሽን ሥራ" እንዲሰሩ የሚያስችል ድረ-ገጽ አማካኝነት ገንዘባቸውን የተጭበረበሩ በርካታ ሰዎች እንዳሉ በተደጋጋሚ ገልጸን ነበር።

ይህ አይነቱ ሥራ አሁንም በተለያዩ አይነት መንገዶች፤ በተለያዩ ስሞች እየተቀያየረ ብዙ ሰዎችን እያታለለ ይገኛል።

ShopAmz, kenmall TESCO በሚሉ ዌብሳይቶች አማካኝነት በርካቶች ተጭበርብረዋል። አሁን ደግሞ Grace Farm / Grean Ranch በሚል ገንዘባቸውን የተጭበረበሩ ሰዎች ጥቆማ እየሰጡ ነው።

የሚሰሩበት መንገድም እንደሌሎቹ ተመሳሳይ ሲሆን በቅድሚያ ለምታስገቡት አነስ ያለ ብር ኮሚሽን ይከፍሏችሁና እንድታምኗቸው ያደርጋሉ።

ከዚያም መሸወዳችሁን እስክታውቁ ድረስ በዚሁ ገንዘባችሁን ይቀበሏችኋል። ተበዳዮች የሚልኩት ገንዘብ በሙሉ ገቢ የሚሆነው በኢትዮጵያ በሚገኙ ባንኮች ቢሆንም ገንዘቡ የሚገባው በተለያዩ ቁጥሮች እና ግለሰቦች አካውንት በመጠቀም ነው።

ከዚህ ቀደም እንደገለጽነው የተለያየ የባንክ አካውንት የሚጠቀሙት ክሪብቶ የሚሸጡ ኢትዮጲያውያንን የባንክ አካውንት ተቀብለው ነው። ስለዚህ ገንዘቡ እነሱ ጋር የሚደርሰው በክሪብቶ (በዲጂታል ገንዘብ) አማካኝነት ነው።

እንዲህ አይነት ማጭበርበሮችን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም አይቻልም። ማድረግ የሚቻለውና አዋጭ የሚሆነው የማኅበረሰቡን ንቃተ ህሊና መጨመር ነው።

ምን ብንሰራ በዚህ ጉዳይ የሚጭበረበሩ ሰዎችን መታደግ እንዲሁም የዲጂታል ግንዛቤያቸውን ማሳደግ እንችላለን?

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

22 Oct, 11:12


አስደሳች ዜና ለመኖሪያ ቤትና የንግድ  ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ ከቴምር ፕሮፐርቲስ
* 25% ቅናሽ ቅናሹን ተጠቅመው ከ1,000,000  እስከ  4,000,000 ብር ያትርፉ!!!
💫ሊሴ ገብረማርያም ት/ት ቤት ጀርባ💫
መሰርታዊ አገልግሎት  የተሟላለት  በተንጣለለ የ ሪል እስቴት መንደር ውስጥ በተለያዩ የካሬ ስፋት እና
ምቹ የክፍያ አማራጮች ከልዩ ቅናሽ ጋር ለሽያጭ አቅርበናል።
በ10% ቅድመ ክፍያ  ከ483,000 ብር
ከስቱዱዮ_ባለ ሶስት መኝታ

ልብ ይበሉ ቤትዎን የሚገዙት በኢትዮጵያ ብር ነው ከፋለው እስከሚጨርሱ ድረስ ምንም አይነት የዋጋ ለውጥ የሌለው።

ለበለጠ መረጃ እና ሳይት ለመጎብኘት
በ 0941443188 ወይም 0916807333
ሀሎ ይበሉን ።

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 18:37


ግብፅ ከወባ ነጻ ሀገር መሆኗ በይፋ ተነገረ።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ግብፅ ከወባ ነጻ ሀገር መሆኗን ይፋ አውጇል። ይህን አስመልክቶ የተናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም "የወባ በሽታ እንደ ግብጽ ስልጣኔ የቆየ ነው አሁን ግን ከሀገሪቱ ተወግዷል" ሲሉ ነው የገለጹት።

ግብፅ ወባን ለማስወገድ መስራት የጀመረችው የዛሬ 100 ዓመት ገደማ ነበር። አሁን ላይ በሽታውን ካስወገዱ 44 ሀገራት ተርታ ተመድባለች።

አንድ ሀገር ከወባ ነጻ ለመባል ቢያንስ ለ3 ዓመታት በአካባቢው ምንም አይነት የበሽታው ስርጭት እንዳልተከሰተ ማሳየት አለበት።

በወባ በሽታ በየዓመቱ ከ600,000 በላይ ሰዎች ለሞት ይዳረጋሉ። በአብዛኛው የሞት መጠን በአፍሪካ ውስጥ ይገኛል።

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 18:05


#ወባ

የወባን ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር እየተካሄደ ያለውን ወባን የማጥፋት ፕሮግራም አስመልክቶ በበይነ መረብ ሣምንታዊ የግምገማ ስብሰባ መደረጉን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታውቋል።

በዚህ ስብሰባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ ተሳትፈው ነበር።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለህብረተሰቡ በሚገባ ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር አስፈላጊ በሆኑት የሚዲያ አግባቦች ሁሉ ተደራሽ ለማድረግ የሚዲያ ንቅናቄ መደረግ እንዳለበት ገልጸዋል።

በተጨማሪም፥ መድኃኒት ብሎም የግብዓት አቅርቦት ላይ ያለውን ስርጭት በተመለከተም ተገቢው ቁጥጥር መድረግ እንዳለበት፤ ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን መናበብ በመፍጠር አፋጣኝ እና ቀልጣፋ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች መስራት እንዳለባቸው መመሪያ ሰጥተዋል ተብሏል፡፡

ዶ/ር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው በአካባቢው የሚገኙ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰሱና የማድረቁ ስራ በዘመቻ መልክ ተግባራዊ መደረግ እንደሚገባቸው እና አስፈላጊና ተገቢ የሆኑ የመከላከል ስራዎች  በአስቸኳይ ተግባራዊ መድረግ እንደላባቸው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

በስብሰባው የክልል ጤና ቢሮዎችና ክላስተሮች ወረርሽኙን ከመከላከልና ከመቆጣጣር አንጻር የተሰሩ ሥራዎችን ሪፖርት አቅርበዋል።

የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች ከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የተለያዩ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 16:43


#FireAlert 🔥

መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው መድረሳቸውንና እሳቱን ለማጥፋት በጥረት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ዝርዝሩን በ @tikvahethiopia ይከታተሉ

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 16:27


ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ 4 ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈ።

በተለያዩ ጊዜያት አሽከርካሪዎችን ራቅ ወዳለ ስፍራ እየወሰዱ በመግደል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር  ስር ውለው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በአዲስ አበባ ገላን፣ በሳሪስ እንዲሁም በቢሾፍቱ ከተማ መኖሪያቸውን ያደረጉት ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና እዩኤል ቴዎድሮስ እንዲሁም በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ የተባሉት ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ በመመላለስ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር ነው የተገለጸው። 

የሸገር ከተማ አስተዳደር  ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ ስለወንጀሎቹ ተከታዩን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

#ወንጀል_1

ቴዎድሮስ እና እዮኤል የተባሉት ተከሳሾች   ሰለሞን አሊ የተባለ የጭነት ተሽከርካሪ   አይሱዚ አሽከርካሪን ከዱከም ከተማ እንጨት ትጭንልናለህ  በማለት በኮንትራት ዋጋ  ተስማምተው ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ያቀናሉ።

በመቀጠል ወደ ሰንዳፋ  መስመር እንዲሄድ በጦር መሳሪያ በማስገደድ ጨፌዶሳ የተባለ ቦታ  ሲደርስ በሽጉጥ በመምታት ጥለውት ተሽከርካሪውን  ይዘው ተሰውረው ቆይተው እንደሸጡት ተገልጿል።

#ወንጀል_2

ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ የተባሉት የወንጀል ቡድን አባላት ደግሞ አቶ  ከበደ በለው የተባሉ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ የሆኑ እና ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ  ሚኒባስ ከአዲስ አበባ አሰላ በማሽከርከር የሚተዳደሩ ግለሰብ ላይ ግድያ ፈጽመዋል።

ይህም ሞችን ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ  ሰው እናመጣለን በማለት ከወሰዷቸው በኋላ በመሳሪያ በማስገደድ ወደ ገላን ከተማ በመውሰድ በገመድ አንቀው መግደላቸውንና ከዚያም ተሽከርካሪውን በጎሮ በኩል ገላን ከተማ በመውሰድ አንዶዴ የተባለው ቦታ  አስከሬኑን ጥለው መሰወራቸውን ነው የገለጹት።

#ወንጀል_3

የሜትር ታክሲ አሽከርካሪው ሚኪያስ ተስፋዬ የተባለ የ28 ዓመት ወጣት እዩኤል ቴዎድሮስ የተባለው ማታ ላይ ደውሎለት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የምንቀበለው  እንግዳ አለ  በማለት ምሽት ላይ ቢሾፍቱ ከተማ በተከራዩበት ቤት በመውሰድ በሽጉጥ ገድለውታል።

የፖሊስ ክትትል . . .

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ቴዎድሮስ ብርሃኔ  እና  እዮኤል ቴዎድሮስ በቁጥጥር  ስር  በማዋል  የምርመራ ሂደቱ ሲያጣራ ቆይቷል።

በዚህም ሰለሞን የተባለው አሽከርሪውን ገለው ጫካ ውስጥ መጣላቸውን የጭነት ተሽከርካሪውን በ700ሺህ ብር መሸጣቸውን  ለፖሊስ መርተው  አሳይተዋል።

በመቀጠል ሚኪያስ ተስፋየ የተባለውን አሽከርካሪ ገድለው እንደጣሉት እና ኮሮላ ተሽከርካሪውን የደበቁበትን ቦታ ለፖሊስ ይጠቁማሉ።

ፖሊስ ምርመራውን በመቀጠል የአቶ ከበደ ገዳዮችን ለመያዝ ባደረገው  ክትትል አዲስ አበባ ሳሪስ  ዶሮ ተራ ከሚባል ስፍራ በመያዝ  በሁለቱም ግለሰቦች ላይ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ ሃይሩፍ ተሽከርካሪውን እንዲፈታታ በማድረግ ለመሸጥ ሲሞክሩ በቁጥጥር  ስር ለማዋል ተችሏል። 

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በማጠናቀቅ  ለዓቃቢ ህግ ይልካል። ዓቃቢ ህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ  በመመልከት  ተከሳሾች በመደራጀት የጦር መሳሪያ  በመታጠቅ በአሰቃቂ ሁኔታ  የሰው መግደል ወንጀል  መፈጸማቸውን በመጥቀስ  በወንጀል ህግ 530 መሰረት ክስ መስርቷል።

የፍርድ ቤት ውሳኔ . . .

በዓቃቢ ህግ የተመሰረተውን  ክስ የተመለከተው የሸገር  ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራቱም ተከሳሾች  የፈጸሙት የወንጀል ድርጊት በመመልከት  ከባድ እና አደገኛ በመሆኑ የቅጣት ማክበጃ በመጥቀስ በአራቱም ተከሳሾች ላይ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።

በተጨማሪም ተሽከርካሪዎች የደበቁ አራት ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል።

Credit : Bisrat Fm

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 09:56


ከአንዲት የአዕምሮ ታማሚ የተለያዩ ባዕድ ነገሮች በቀዶ ጥገና መውጣቱ ተነግሯል

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ከአንዲት የ23 ዓመት የአዕምሮ ህመም ታካሚ ከነበረች ወጣት ላይ በተደረገ የቀዶ ጥገና የተለያዩ ባዕድ ነገሮች መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ስለጉዳዩም ቀዶ ጥገናውን የመሩትን ዶ/ር ሲያስበው ማሞን (በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የደረት ልብ ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስትና የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) ጠይቀናል።

ዶ/ር ሲያስበው ወጧቷ የአዕምሮ ህክምና ክትትል የነበራት በመሆኗ የዋጠችው ነገር እንዳለ ለመረዳት የቻሉት ከቤተሰቦቿ መሆኑን ነግረውናል።

"ወደ ሆስፒታሉ እንደመጣች ሲቲ ስካንን ጨምሮ የተለያዩ የራሳችን ተጨማሪ ምርመራ ተደርጎላት በውስጧ ባእድ ነገር መኖሩ በመረጋገጡ ባጠቃላይ 3 ሰዓት ከ30 የፈጀ የተሳካ ቀዶ ጥገና የተደረገላት ሲሆን ጉሮሮዋ ውስጥ ያለው ባዕድ ነገር በኢንዶስኮፒ ማሽን በመታገዝ እየተለቀመ ወጥቷል አንጀቷ እና ጨጓራዋ ላይ ያለው ደግሞ በቀዶ ጥገና ወጥቷል" ሲሉ አብራርተዋል።

ለመሆኑ ምን አይነት ባዕድ ነገሮች ወጡ?

መስታወት፣ የሀይላንድ ክዳን፣ ቆርኪ፣ አጥንት፣ እርሳስ፣ እስክሪፕቶ፣ ሚስማር፣ የትራማዶል ብልቃጥ እና ጌጣጌጥ በተደረገው ህክምና ሊወጣ መቻሉን ብለውናል።

ዶ/ር ይታሰበው ስለታካሚዋ ጤንነት ሲያስረዱም "ታካሚዋ ከቀዶ ጥገና በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ ትገኛለች፣ እየተንቀሳቀሰች ነው ፈሳሽም እየተጠቀመች ትገኛለች" ያሉን ሲሆን በቀጣይም በሆስፒታላችን የአዕምሮ ህክምናዋን እንድትከታተል እና እዚህ ክትትል የማድረጉ ስራ እንዲሰራ መወሰናችውን" ገልጸውልናል።

"ጥናቶችን ለማየት ሞክረን ነበር መሰል አጋጣሚዎች በጣም ጥቂት ናቸው እንደ እኛ ሆስፒታልም የመጀመሪያው ነው እሷንም ያለባት የሳይካትሪክ ችግር ነው ሊዚህ ያጋለጣት ያሉን ሲሆን ብዙ ጊዜ ህጻናቶች ወይም አዋቂዎች አንድ ነገር ብቻ ውጠው ሲመጡ ነው ሚገጥመን፤ ይህ ነገር በተለይ የአዕምሮ ህክምና ሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሚውሉበትን ቦታ መምረጥና ንጹህ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያስተምራል" ብለውናል በመልዕክታቸው።

በቀዶ ጥገናው  ዶ/ር ሲያስበው እና ዶ/ር ዘረሰናይ (አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም)፣ ዶ/ር ብሩክ፣ ዶ/ር አብዱላሂ፣ ዶ/ር ኤርሚያስ እና ዶ/ር ሮባ፣ ጣሂር (አንስቴዥያ) እና ሲ/ር የሺ እና ህይወት(ነርሶች) ተሳትፈዋል።

Photo: Hakim Page

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 09:54


#ይህንአድርሱልን

"ይህ የምትመለከቱት መንገድ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን መንገሺ ወረዳ ካቦ ኬላ የሚገኝ ሲሆን ዝናብ ሲጥል ተሽከርካሪ ማለፍ አይችልም። እግረኛ በውሃ ውስጥ ነው የሚያልፈው። ሞተር ማለፍ ስለማይችል 200 ብር ነድተው ለሚያሳልፉ ይከፍላል። ህዝብ በእንግልት ይገኛል።"

via @tikvahmagbot

@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 09:54


መልካም ዜና 12ኛ ክፍል ላጠናቀቃችሁ በሙሉ

🚴‍♀️ ብስክሌት
🏍 ሞተር
🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል

💰 በተጨማሪም 🚲ብስክሌት🚲 ለሌላቸው እና ይሄን ስራ መስራት የሚፈልጉ ሰዎችን በቅናሽ ዋጋ አመቻችቶ ብስክሌት በመስጠት ኑ አብረን እንስራ ይላችኋል።

የት/ት ደረጃ ፡ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ

የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-


ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://t.me/DriversRegistration_bot

☎️ +251923344444 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።

TIKVAH-MAGAZINE

21 Oct, 09:54


አስደሳች ዜና ለመኖሪያ ቤትና የንግድ  ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ ከቴምር ፕሮፐርቲስ
* 25% ቅናሽ ቅናሹን ተጠቅመው ከ1,000,000  እስከ  4,000,000 ብር ያትርፉ!!!
💫ሊሴ ገብረማርያም ት/ት ቤት ጀርባ💫
መሰርታዊ አገልግሎት  የተሟላለት  በተንጣለለ የ ሪል እስቴት መንደር ውስጥ በተለያዩ የካሬ ስፋት እና
ምቹ የክፍያ አማራጮች ከልዩ ቅናሽ ጋር ለሽያጭ አቅርበናል።
በ10% ቅድመ ክፍያ  ከ483,000 ብር
ከስቱዱዮ_ባለ ሶስት መኝታ

ልብ ይበሉ ቤትዎን የሚገዙት በኢትዮጵያ ብር ነው ከፋለው እስከሚጨርሱ ድረስ ምንም አይነት የዋጋ ለውጥ የሌለው።

ለበለጠ መረጃ እና ሳይት ለመጎብኘት
በ 0941443188 ወይም 0916807333
ሀሎ ይበሉን ።

TIKVAH-MAGAZINE

19 Oct, 19:33


በሶማሌ ክልል ጥቃት ሊፈፅሙ የነበሩ የአልሻባብ አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ ቅጣት ተላለፈ

በሶማሌ ክልል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም በተንቀሳቀሱ 60 የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ የፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

በሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 60 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው በ10 የምርመራ መዝገብ ተከሰው እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የፍርድ ቤት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ፖሊስ በ60 የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ በቂ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃ በማቅረብ በሽብር ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለፍትህ ሚኒስቴር በመላክ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ተዘዋዋሪ ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም 56 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፎአቸው ከ6 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአልሸባብ የሽብር ቡድን አባልነት የተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንደተፈረደባቸው ተነግሯል።

@tikvahethmagazine