FIDEL POST NEWS

@tesfaget55


Fast news about Ethiopia

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 14:14


" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው ፦

" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡

ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡

ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡

ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡

ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡

በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 13:49


በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
          
ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው በአጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት  መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረሰው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ እንሚያሳውቅም አስታውቋል፡፡     

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 13:48


ዛሬ ዓለም አቀፉ የወንድ የነርቭ ሥርዓት በሴቶች ከሚደርስባቸው ጥቃት የመከላከል ቀን ነው።

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 13:25


በመሬት ውስጥ ተቀባሪ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባ:-
👉የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 440 እና 447፣
👉 አርሴማ አካባቢ፣
👉ወጋገን ባንክ ጀርባ፣
👉ሸገር ዳቦ መሸጫ፣
👉 አባዶ መስቀለኛ እና
👉ፒያሳ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል፡፡አገልግሎቱን ለመመለስ እየሰራን በመሆኑ ደንበኞች በትዕግስት ጠብቁኝ ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልፆል።

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 11:44


ኬንያ አራት ቱርካዊ ስደተኞችን አሳልፋ ሰጠች።

ኬንያ አንካራ ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ ያቀረበችባቸውን አራት ቱርካዊ ስደተኞችን አሳልፋ መስጠቷን አስታውቃለች።

ኬንያ ይህን ያደረገችው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቱርካውያኑ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ሊታሰሩ ይችሉ ሲል ያቀረበውን ስጋት ወደ ጎን በመተው ነው።

ኬንያ አሳልፋ እንድትሰጥ የቀረበላትን ጥያቄ የተቀበለችው በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመኖሩ ነው ያለው የውጭ ጉዳይ እና የዲያስፖራ ጉዳይ መግለጫ÷ አራቱ ቱርካውያን በክብር እንደሚያዙ ማረጋገጫ መቀበሉንም ገልጿል።

አምነስቲ ባለፈው ቅዳሜ ስደተኞቹ ተላልፈው የሚሰጡ ከሆነ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሊፈጸምባቸው እንደሚችል እና በኬንያ ውስጥ ያሉ ሁለም ስደተኞች የደህንነት ስጋት መጨመሩን ገልጿል።

የመንግሥታቱ ድርጅትም ኬንያ የቱርክ ስደተኞችን ያለፈቃዳቸው ወደ አገራቸው መመለሷ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡

ኬንያ እንደገለጸችው ያስጠለላቻውን አብዛኞቹ ከሶማሊያ የሆኑ 780 ሺህ ስደተኞችን ለመከላከል ቁርጠኝነት አላት።

መግለጫው ተላልፈው የተሰጡትን ስደተኞች ስም እና ለምን ተላልፈው እንደተጠሱ በዝርዝር አለመግለፁ አል-ዐይን ዘግቧል።

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 11:44


በመዲናዋ 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት ለሊዝ ጨረታ አቅርቧል፡፡የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫውን የሰጡት በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍና የሊዝ ክትትል ዳይሬክተር ጫሊ አብርሀም፤ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታው የቀረቡ መሬቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ አራተኛው ዙር ሲሆን፤ በዚህኛው ዙር ብቻ አጠቃላይ የቀረበው 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ነው ተብሏል።ይህም በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው መሆኑ ተመላክቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 11:42


ቦርዱ በተለያዩ ምክንያቶች በ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ አሳለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ የዕግድ ደብዳቤ ይፋ አድርጓል፡፡

የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄና፣የአገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች ናቸው በቦርዱ እግድ የተጣለባቸው፡፡

ቦርዱ ፓርቲዎቹን ለምን እንዳገደ እስኪያሳውቅ ድረስም ፓርቲዎች ምንም አይነት ህጋዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይችሉም ነው ያስታወቀው፡፡

ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  እግድ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ክትትል እንዲያደርግም አሳስቧል፡፡

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 09:32


🛸📹 ተጨማሪ ዩፎዎች? ያልታወቁ የብርሃን ምንጮች በኮሎምቢያ ሰማይ ላይ ታዩ

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 08:31


የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ የጊዜያዊ ዕውቅና ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረው 100 ብር ከዚህ በኋላ 15ሺ መሆኑ ተገለጸ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጊዜያዊና ሙሉ ዕውቅና ለማግኘት የሚጠበቅባቸው ክፍያ መሻሻሉን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፤ ለጊዜያዊ ዕውቅና 15ሺ፣ ለሙሉ ዕውቅና 30ሺ ነው ብሏል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን ባወጣው መግለጫ ለሀገር አቀፍ እና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፍኬት ለማግኘት 100 ብር ብቻ ያስከፍል እንደነበር አውስቶ ከጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በኋላ ግን ክፍያው 15ሺ ብር መሆኑን እወቁልኝ ብሏል።

በተመሳሳይ የሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ ዕውቅና ለማግኘት እስከ ትላንት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ይከፍሉ የነበረው 200 ብር ብቻ መሆኑን አስታውሶ ከዚህ በኋላ ግን ክፍያው 30ሺ ብር ነው ሲል አስታውቋል።የተመዘገቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር የአገልግሎት ክፍያ ሲያስከፍል እንደነበር ጠቁሞ ከዚህ በኋላ ግን ሰነዶቹን ያሻሻለ ፓርቲ 5ሺ እንዲከፍል ወስኛለሁ ሲል ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ክፍያውን ያሻሻልኩት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ እና የሰነድ ማሻሻያ አገልግሎት ክፍያ መጠኑ በቦርዱ እንዲወስን በአዋጅ ስልጣን ስለተሰጠኝ ነው ብሏል።

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 07:47


🇪🇹 የኢትዮጵያው መሪ ከአውሮፕላን ሲወርዱ በብሔራዊ የታታር ምግብ "ቻክ-ቻክ" ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 07:07


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ዕለታዊ  የነዳጅ አቅርቦት መጠን ከዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ በቢሮው የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም መረጃውን ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኢንስፔክሽንና ሪጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዮሴፍ አሰፋ  እንደገለጹት በከተማዋ 123 የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን  በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋዮችን እንግልት ለመቀነስ እንዲቻል ቢሮው 123   ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙና በየዕለቱ የተራገፈው የነዳጅ መጠንና የጥቆማ ሥርዓቱን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ማጋራት እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በወሩ መጨረሻ ቀናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት የነዳጅ እጥረት ሲያጋጥም ይስተዋላል፡፡ይህም ከነዳጅ አቅርቦት እጥረት ጋር የተያያዘ ነው ሲባል ቆይቷል፡፡

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 07:04


🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ#BRICS2024 የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ካዛን ገቡ

📲👉@sputnik_ethiopia

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 05:01


አሁናዊ ገፅታ መርካቶ ነባር ህንፃ

FIDEL POST NEWS

22 Oct, 03:47


በፔንስልቬንያ ትራምፕ የማክዶናልድ ሰራተኛ በመሆን የሸሚዛቸውን እጄታ ሰብሰብ አርገው ሲሰሩ ታይተዋል።


የድንች ቺብስ አብስለው ለተቋሙ ደንበኞች ሲሰጡ ታይተዋል።

ካማላ ሃሪስ በተማሪነት በማክዶናልድ የትርፍ ሰዓት ስራ እንደምትሰራ ከዚህ ቀደም ተናግራ ነበር።

ትራምፕ ደግሞ ካማላ ማክዶናልድ ስለመስራቷ ምንም ዓይነት መዝገብ ስላልተያዘ ተቀናቃኛቸው እየዋሸች ነው ብለዋል።

FIDEL POST NEWS

21 Oct, 23:23


መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።


በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትና መንስኤዉን በማጣራት ቀጣይ ለህብረተሰቡ የምናሳዉቅ ሲሆን መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እዲደረግ አደራ እላለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።

FIDEL POST NEWS

21 Oct, 19:44


የሰላም አዳር ተመኘን !!!

FIDEL POST NEWS

21 Oct, 19:09


Update

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እስከ አሁን መቆጣጠር ባለመቻሉ በሄሊኮፕተር እየተሞከረ ነ

FIDEL POST NEWS

21 Oct, 19:06


ለ 56 ዓመት በሳምንት አንዴ እየተገናኙ ቢራ የጠጡት እንግሊዝያውያን ጓደኛሞች አነጋጋሪ ሆነዋል

ይህ የእንግሊዝ በ 80 ዎቹ እድሜ ላይ የጡረተኞች ቡድን በፈረንጆቹ ከ 1968 ጀምሮ ጠንካራ ትስስርን አስጠብቆ ቆይቷል፣።

በየሳምንቱ ሐሙስ በየመጠጥ ቤቱ ለ56 ዓመታት እየተሰበሰቡ ተገናኝተዋል።
በኮሮና ጊዜ እና በአንዳንድ በአሎች ላይ ባይገናኙም ረጅሙን አመት ግን ተገናኝተው ተጫውተዋል።
BBC

FIDEL POST NEWS

21 Oct, 18:36


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል።

የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም  ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ ሲሆን አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን ነው። ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ሁላ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ።                                                                                  
ከንቲባ አዳነች አቤቤ