Ethio Fm 107.8

@ethiofm107dot8


በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 14:03


በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት  መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ እንሚያሳውቅም አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 13:01


የነገ የጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 11:43


በ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የእግድ ውሳኔ ተላለፈ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ቦርዱ በተለያዩ ጊዜ በአስራ አንድ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

የዕግድ ውሳኔ የተሰጣባቸው ፓርቲዎች የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ናቸው ።

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ውጤት ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለጊዜው ፓርቲዎችን ከማናቸውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 10:45


የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያዉ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ገለጸ፡፡

ቦርዱ አዲስ የሚመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ‹‹የሙሉ ዕዉቅና›› ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረዉን 2 መቶ ብር ወደ 30 ሺህ ከፍ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አዲስ የሚመሠረቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ እውቅናን ለማግኘት ይከፍሉ የነበረውን 1መቶ ብር ወደ 15 ሺህ ብር ከፍ አድርጎታል፡፡

በአዲሱ የምርጫ ቦርድ የዋጋ ማሻሻያ አዲስ የሚቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ እና ሙሉ የዕውቅና ምስክር ወረቀቶችን ለማግኘት በድምሩ 45 ሺህ ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከትናንት ሰኞ ጥቅምት 11 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው ይህ የዋጋ ማሻሻያ ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጣቸው ሦስት አገልግሎቶች ላይ ነው።

በዚህም ሌላኛዉ ጭማሪ የተደረገበት አገልግሎት ደግሞ የተመዘገቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸዉን በጉባዔ አሻሽለዉ ሲያቀርቡ ይከፍሉት የነበረዉ ክፍያ ነዉ፡፡

ይህን አገልግሎት ለማግኘት 30 ብር ይከፍሉ የነበሩ የተመዘገቡ ፓርቲዎች አሁን ላይ አገልግሎቱን ለማግኘት 5ሺህ ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸዉ ቦርዱ አስታዉቋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ እንዲሁም የመከታተል እና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚጠይቀው ክፍያ ተመን ላይ ጭማሪ ማድረጉን ያስታወቀው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 12/2017 ዓ.ም. ነው።

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 10:14


አሸዋ ቴክኖሎጂ ከ500 በላይ የዌብሳይት ቴፕሌት አበልፃጊዎችን አወዳድሬ ልሸልም ነው አለ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየዉን የቴክኖሎጂ ዉጤት ከ500 በላይ አበልፃጊዎችን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበረታታት ፕሮጀክት ቀርፆ መንቀሰቀስ መጀመሩን በዛሬዉ ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እቶ ዳንኤል በቀለ ይሀንን የፈጠራ ዉድድር በ90 ቀን ዘመቻ ወደስራ ስናስገባ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን የቴክሎሎጂ እድገት ካለበት ደረጃ በአጭር ጊዜ የከፍታ ማማ ላይ ለማድረስ አልመን ነዉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በውድድሩ ለሚሳተፉ ሰዎች በቅድሚያ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንደሚካሄድ እና ምዝገባዉም እስከ ጥቅምት 30 እንደሚቆይ ገልፀዋል።

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተማሪዎችን እንዲሁም በዘርፉ በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ከ500 በላይ ዌብሳይት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም እና ለወጣቶች የስራ ፈጠራ ሀሳባቸዉን ይዞ መምጣቱንም አንስተዋል።

ፕሮጀክቱ ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር፤ ለአገር ዉስጥ የምጣኔ ሀብት እድገትና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችል ተጠቁሟል ።

ዉድድሩ በአምስት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄድ እንደሆነና የዌብ ዲዛይነሮች ይህ እድል ሳያመልጣቸዉ እንዲመዘገቡ የሚል ጥሪያቸውን ሀላፊው አስተላልፈዋል ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ዘመኑን የዋጁ ድንቅ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማቅረብ በአጭር ጊዜ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።

ሐመረ ፍሬዉ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 10:10


የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ

የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት ክብረበዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሂዷል

ዛሬ ጥቅምት 12 የክብረበአሉን ማጠቃለያ መርሀ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲያካሂድ ላለፉት አስርት አመታት ያስመዘገባቸዉን ስኬቶችን በመዘከር አክብሮል ፡፡

ክብረ በዓል ተከታታይነት ያላቸው በርካታ ሁነቶችን በማከናወን ሲከበር የቆየ ሲሆን ድርጅቱ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ የድርጅቱ ደጋፊዎችና ሰራተኞች እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

ሲያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎችም ድጋፍ ለማሰባሰብ ስራዉን ለማስተዋወቅ
በሚያበረታታ መልኩ የተቀረጹ ናቸው ተብሏል።

ድርጅቱ ከተመሰረተበት ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ነው።

አቤል እስጢፋኖስ

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 08:55


የዛሬ የጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን

Ethio Fm 107.8

22 Oct, 08:47


ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ ካዛን መግባታቸው ተገለጸ

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በብሪክስ (BRICS) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ መግባታቸውን የአዘጋጇ የሩሲያዋ ታታርስታን ግዛት ፐሬዝዳንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

"የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በ BRICS የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ካዛን ገብተዋል፤ በካዛን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግዛቷ ፕሬዝዳንት ሩስታም ሚኒካኖቭ አቀባበል አድርገውላቸዋል" ሲል መግለጫው አትቷል።

በካዛን በሚካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ከ30 ሀገራት በላይ ተወካዮች ይታደማሉ መባሉን ከሩሲያ የዜና አገልግሎት ታስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬቱ ፕሬዝዳንት ቢን ዛይድ፣ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን፣ የህንዱ ፕሬዝዳንት ናሬንድራ ሞዲ በካዛን ከተገኙ መሪዎች ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ ላይ ቡድኑን በይፋ መቀላቀሏ ይታወቃል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም