Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

@housinginaddisababa


The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates. This page is not a gov't page.

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች (Amharic)

የአዲስ አበባ ቤቶች ስለተመሳሳይ መረጃዎች (40/60 & 20/80) እና ሌሎች አገሮችን በማንኛውም ደረጃ ጥናት አስተካክል ማንበብ የሚሞላባቸውን ሕንጻ እንቅስቃሴ ይጠቀሙ። ይህ ገጽ አሰዳሽ አይሰሩም።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

22 Oct, 04:37


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባቸው ቤቶች ለጨረታ አቅርቧል፤

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 13:05


አዲስ አበባ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 13:01


የዚህን ሰአት ባትሪ ድንጋይ የት ነው የሚገኘው?
🙈

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 12:55


ማስታወቂያ

የማህበር ቤት ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና ቀደም ሲል ስም ዝርዝራችሁ ተገልፆ ቅጽ 01 አስሞልታችሁ የመመለሻ ቀን የተራዘመባችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ።

ቅፁን እና አስፈላጊውን  መረጃዎች ይዛችሁ ከጥቅምት 13/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ ተቅምት 19/2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ብቻ ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ህንፃ 6ኛ ፎቅ የቤት ማህበራት ዳይሬክቶሬት በመገኘት መረጃችሁን እንድታስገቡ እናሳወቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:12


በኤርፖርት ያሉ እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሲነሱ አንዳንዶች በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚያያይዙት ቢሆንም የኤርፖርት ጥበቃ እና ፍተሻ የሚከናወነው በአየር መንገዱ ሳይሆን በሌሎች የመንግት የደህንነት እና የፅጥታ አካላት መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
መሰረት ሚዲያ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:10


ወደ ደቡብ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎች ቦሌ ኤርፖርት ላይ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር ጉቦ እየተጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ።

በርካታ ጥቆማ ሰጪዎች በሰጡን መረጃ መሠረት በተለይ ወደ ብራዚል የሚጓዙ ዜጎች ለጉዞ ማድረግ ያለባቸውን ፕሮሰስ ሁሉ ጨርሰው እና ከብራዚል ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው በበረራ ሰአታቸው ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ "በዛው ልትጠፉ ነው፣ ስለዚህ እንድትሄዱ እንድንፈቅድላችሁ 500 ሺህ ብር አምጡ እየተባልን ነው" ብለዋል።

አንድ ጥቆማ ሰጪ ደግሞ ወደ አንድ የአየር ማረፊያው ቢሮ ሀላፊ በመግባት ሁኔታውን ሲያስረዳ "እዛው ጨርስ" እንደተባለ ተናግሯል።

በቦሌ አየር ማረፊያ ላይ በርካታ የመብት ጥሰቶች እና ሙስና እንደሚፈፀም ከዚህ በፊት ተደጋግሞ መነሳቱ ይታወሳል። ይሁንና በአየር ማረፊያው የፍተሻ እና ጥበቃ አካላት አንድ ተጓዥ ላይ በየካቲት 2016 ዓ/ም ዝርፊያ እና እንግልት ከተፈፀመ በኋላ ጉዳዩ ወደ ማህበራዊ ሚድያ በመምጣቱ መንግስት ምላሽ ሰጥቶበት ነበር።

በወቅቱ አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ግለሰብ በፍተሻ ወቅት "ሻንጣሽን ከፍተሽ አሳዪን፣ ማሽኑ የሆነ ነገር ያሳየናል" በማለት ሻንጣዎቿን አስከፍተዋት በዚህ ወቅት የያዘችውን የግል መገልገያ ጌጣጌጥ እና በህጋዊ መንገድ የያዘችውን ዶላር አካፍዪን ማለታቸው ይታወሳል።

ይህን መረጃ ተንተርሶ በተደረገ ማጣራት ድርጊቱን ፈፃሚዎች በካሜራ ክትትል ተይዘው ለእስር ተዳርገው ነበር።

እንዲህ አይነት ኤርፖርት ላይ በፀጥታ እና ኢሚግሬሽን ሰራተኞች የሚፈፀም ድርጊት በተለይ ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ዜጎች የበረታ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

መሰረት ሚዲያ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:05


#AddisAbaba #ኮንዶሚኒየም

🔵 " ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " - አቶ አበበ አካሉ

" የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ


ከአዲስ አበባ የኮሪደር ስራ ጋር በተያየዘ በርካቶች በልማት ተነሺነት ከኖሩበት አካባቢ ተነስተው ወደ ተለያዩ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲገቡ እየተደረገ ነው።

ምንም እንኳን ተነሺዎቹ መግባታቸው ላይ ቅሬታ ባይፈጥርም ከ97 አንስቶ ሲቆጥቡ የኖሩ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸው እና አሁን ላይ አስተዳደሩ ቤት የተሰጠ መሆኑ ቅሬታ አሳድሯል።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተካሄደ የኮሪደር ስራውን በሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ይኸው ቅሬታና ጥያቄ ተነስቷል።

ጥያቄውን ካነሱት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

" ሲቆጥቡ የኖሩ ሰዎች ጉዳይ ምን ደረሰ ? አሁን ማህበረሰቡ ምን ያማል ከተማ አስተዳደሩን ' እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው የልማት ተናሺዎችን እያሰፈረ ያለው ' የሚል ሮሮ አለ።

ለዚህ ምንድነው ምላሻችሁ ?

ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" የኮንዶሚኒየም ቤት እስኪ ከየት አምጥታችሁ ነው በዚህ ደረጃ ያላችሁ ኃላፊዎች ' በቆጡት ገንዘብ ነው የሚሰራው ' የምትሉት።

እነ ንግድ ባንክ ናቸው ብሩን የሚያቀርቡት እስቲ እንነጋገር ትንሽ ወደ መረጃው ጠጋ ብላችሁ ብናወራ ምናለበት።

ኮንዶሚኒየም በብድር ነው የሚሰራው። የከተማ አስተዳደሩ በጀቱን አስይዞ ነው የሚበደረው።

ለምንድነው የሚቆጥቡት ? ከተባለ ዕጣ የደረሳቸው ዕለት የሚከፍሉትን እንዳያጡ ነው። እንጂ ቤቱን መገንቢያ አይደለም። ልክ ቤቱ ሲገነባ ብሩን ይከፍሉታል።

ሁለተኛ እንዴት ነው እኛ ብቻችንን የምንጠየቅበት ? ቤት ባልተዘጋጀበት በሚሊዮኖች መዝግቦ ቆጥቡ ብሎ ኃላፊነት ወስዶ የሰራ አካል እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

ቤት ሳያዘጋጅ ዜጎችን ልክ እንደ ማታለያ በሚሊየን መዝግቦ የበተነ እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

የኮንዶሚኒየም ቤት አጠቃላይ አንድ ቦታ እጅብ ብሎ ስለተሰራ ብዙ ይመስላችኋል እንጂ እስካሁን እስካጠናቀቅነው ያለው 300,000 ነው። የተመዘገበው በሚሊዮን ነው። በየጊዜው ተስፋ ቆርጦ፣ ተጣርቶ ተጣርቶ እኛ የደረስንበት 600,000 ነው። አክተቭ ይቆጥብ የነበረው። ግን ቤት ማግኘት እንዳለባቸው እናምናለን። ቤት ማግኘት አለባቸው።

ካለቁት ኮንዶሚኒየሞች ብራቸው ተዘርፎ፣ ቀድሞ ተከፍሎ ያልተሰራ 80 ህንጻ ብር ተከፍሎበት ጥለው ሄደዋል። በብዙ ውጣውረድ ነው 139,000 ቤቶችን የጨረስነው። የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ብቻ።

አሁንም ቢሆን ግን የከተማችን ነዋሪዎች ቤት ማግኘት አለባቸው። ለዚህም በኮንዶሚኒየም ብቻ አይደለም እንደ ቀድሞ በሚፈለገው ደረጃ ብድር ማግኘት አልቻልንም ከባንክ። ኮንዶሚኒየም መጥፎ ስለሆነ አላቆምነውም።

ከተማ አስተዳደሩ ዕዳ እየከፈለ ነው። ንግድ ባንክ የሚያበድረው የባለሃብትን ገንዘብ ነው አይደል ? 56 ቢሊዮን የኮንዶሚኒየም ዕዳ ነው የተረከብነው ዋስትና የሚሰጠው ከተማ አስተዳደሩ ስለሆነ ክፈሉ ተባልን ተገደድን በለውጥ ዘመኑ 30 ቢሊዮን ከፍለናል የኮንዶሚኒየም ዕዳ።

ይህ ሁሉ ዕዳ አንደኛ በከፍተኛ ሰብሲዲ ስለሚሰራ ነው ፤ ሌላው ያልተሰሩ ቤቶች የተከፈለባቸው አሉ። ሳይከፍሉ ሲሸጡ በተለያየ መንገድ ሲተላለፉ የነበሩ ቤት ውስጥ ያገኘናቸው ሰዎች ከግለሰብ የገዙ ናቸው፤ ሊገደዱ አይችሉም የኮንዶሚኒየም ክፈሉ ተብለው። አጣርተን እኮ በሚዲያ ነግረናችኋል ፤ ያጋጠመንን።

አሁን በግልና በመንግሥት አጋርነት ወደ 100,000 ቤቶች አስጀምረናል። የቁጠባ ቤቶችንም እየሰራን እያከራየን ነው። በሪስልቴትም በግል የሚሰሩትን እንደ ከተማው ፕሮጀክት ጠጋ ብለን እያገዝን ቶሎ እንዲጨርሱ እያደረግን ነው።

እስካሁን የቆጠቡትን አሁን በግልና መንግሥት ትብብር ከምንሰራው  ውስጥ ቅድሚያ ሊያገኙ የሚችሉበትን አግባብ እየተከተልን ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተደራጅተው በማህበር እንዲሰሩ ...እስካሁን ለተደራጁት መሬት አስረክበናል።

መነገጃ አታድርጉት፤ ከእውነታው ውጭ መነጋጃ ማድረጉ አይጠቅምም።

የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል። ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ 97 አክቲቭ ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል።

እነሱ ከወጣላቸው በኃላ ዲአክቲቬት ያደረገውን አካውን አክቲቬት ያደረገ ካለ እሱ ስለቆጠበ ቤት ስለሚፈልግ ለሚቀጥለው ጊዜ ሊታይ ይገባል ፤ እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ የለበትም " ሲሉ መልሰዋል
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:01


ወርልዶሜትር ባወጣው የተባበሩት መንግስታት የቅርብ ጊዜ መረጃ1 መሰረት አሁን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 133,084,331 ነው፡፡
እ.ኤ.አ. October 20 ቀን 2024

-The current population of Ethiopia is 133,084,331 as of Sunday, October 20, 2024, based on Worldometer's elaboration of the latest United Nations data1.

-Ethiopia 2024 population is estimated at 132,059,767 people at mid year.

-Ethiopia population is equivalent to 1.62% of the total world population.

-Ethiopia ranks number 10 in the list of countries (and dependencies) by population
.
-The population density in Ethiopia is 132 per Km2 (342 people per mi2).

-The total land area is 1,000,000 Km2 (386,102 sq. miles).

22.1 % of the population is urban (29,204,015 people in 2024).

-The median age in Ethiopia is 18.9 years.

https://www.worldometers.info/world-population/ethiopia-population/

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 03:38


#AddisAbaba

ለምን የልማት ተነሺዎችን እዛው ቦታቸው ላይ ቤት ሰርቶ ማስገባት አልተቻለም ?

በአዲስ አበባ ከሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ ነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ከኖሩባቸው ሰፈሮች እንዲነሱ እየተደረገ ነው።

አስተያየት ሰጪዎች ፤  " ይሄ ነገር ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመሃል ለማስወጣት ፤ የማህበራዊ ትስስሩንም ለመበጣጠስና ፤ ነባሩን ነዋሪ ለመበታተን ፤ የልማት ተነሺ ቦታዎችንም ለሚፈልጉት ባለሃብት ለመስጠት ነው ፤ እውነት ልማት ከሆነ ለምን ባሉበት በኖሩበት ቦታ የጋራ መኖሪያ ቤት አይሰራላቸው ? " ሲሉ ይጠይቃሉ።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች በተገኙበት ከዚሁ ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዘ የውይይት መድረክ ላይ ፤ " ለምን የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ከተገነባ በኃላ ከለማ በኃላ በነበሩበት ቦታ መኖር አይችሉም ? ልክ እንደ አዋሬ ለምን አልተደረገም ? እዛው እንዲኖሩ ለምን ማድረግ አልተቻለም ? " የሚል ጥያቄ ተስቷል።

እንዲሁም ረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ነዋሪዎች ፦
- ከእድራቸው
- ከእቁባቸው
- ከሰንበቴያቸው ፤ በእስልምናም በኩል ያሉት የማህበረሰቡ መገናኛዎች እንዲበተኑ እየተደረጉ ነው የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" እዛው አካባቢ ላይ ብታለሙ አይሻልም ወይ ? እውነት ነው ይሻላል እንላለን። በነበሩበት አካባቢ ቢሆን የበለጠ ቅድሚያ የሰጠዋል።

አዋሬ እንደዛ ነው የለማው። አዋሬ ብቻ ሳይሆን 70 ደረጃ የገነባናቸው ቤቶች እዛው ሰፈራቸው ነው። በተመሳሳይ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ የበጎነት መንደር ብለን የሰራነው እዛው ነው። ለሚኩራም ሎውኮስት ሀውስ የተሰሩት እዛው ነው፣ ጉለሌ፣  አየር ጤና ሁሉንም መዘርዘር ይቻላል።

ሰፋፊ አካባቢዎችን ስናነሳ አንደኛ የሚገነባበት ቦታ የለም ፤ ካልተነሱ በስተቀር። ሁለተኛ በጥናታችን ሲገነባ የመስረተ ልማቱ የፍሳሽ፣ የጎርፍ መውረጃው የከተማ ልማት የመሬት አጠቃቀሙ የመኖሪያ ቤት መሆን የሌለበት አካባቢ አለ። ተዘግቶ የተገነባበት አለ ጥናቱ በዝርዝር ያስረዳል።

ስለዚህ ሰፋ ወዳለ ቦታ ይሄንን ማህበረሰብ መውሰድ ያስፈልጋል። ቤት ብቻ አይደለም ያየነው። በአካባቢያቸው የሚያስገልጉ ሌሎች መሰረተ ልማቶች አብረው መኖር አለባቸው።

ሌሎች ሀገሮችን እኮ እናውቃለን መኖሪያ ቤቶች መሃል ዋናው ከተማ ላይ ናቸው እንዴ ? ንጹህ አየር ወዳለበት ከተማ ውስጥ ነው ከከተማ አልወጣም። እዚህ ነው የተሻለ ቦታ የተሻለ ሰፋ ያለ ለልጆችም የሚሆን ፤ ብዙ ሰው ሊይዝልን የሚችል ቦታ ላይ ገንብተን አዲስ ቤት መሰረተ ልማት የተሟላለት ቤት አስገብተናል።

ጥያቄ የምታነሱ ወገኖቻችን ኑ አብረን እንሂድና ገላን ጉራን፣ አቃቂን እንመልከት ፣ አቃቂ የቁጠባ ቤቶች ግቢ እንሂድ አብረን ፣ አራብሳ ግቢም የልማት ተነሺዎች የገቡበት አካባቢን እንይ።

አንዳንድ ቦታዎች የተጠቆሙ (የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸው) ካሉ እንደግብዓት እንወስዳለን ህዝባችን እንዲንገላታ አንፈልግም ፤ ህዝባችን እንዲንገላታ ምንም አይነት ፍላጎት የለንም።

ግን እሱም ቢሆን ይኖሩበት ከነበረው ጋር አይወዳደርም።

ከማህበራዊ ትስስራቸው ተበታተኑ የሚለው ፍጹም ውሸት ነው። አልተበታተኑም። የአንድ አካባቢ ሰዎችን አንድ አካባቢ ነው ዕጣ ያስወጣነው። ዕጣውን ለሁሉም ከየአካባቢው ለሚነሱት በጋራ አይደለም ያደረግነው ቀጠናቸውን እንኳን ጠብቀንላቸዋል።

እቁብ፣ እድር፣ ማህበር አላቸው፣ ትስስር አላቸው። ' አይ የቁጠባ ቤት ላይ አንገባም ኮንዶሚኒየም ነው ' ሲሉ የተወሰኑ ሰዎች ኮንዶሚኒየም ሲመርጡ ወደ ሌላ ሄደው ሊሆን ይችላል። ይሄ ለተባለው ግን በቂ ማሳያ አይሆንም።

ባለቤቱ መርጦ ' ይሄ ይሻለኛል በዛው ንብረት ይዛለሁ የጋራ መኖሪያ ቤት ማግኘት ማለት ባለቤት መሆን ነው በቁጠባ እየከፈልኩ ከምኖር ባለቤትነትን እመርጣለሁ ' ካለ ለምንድነው ? ከማህበራዊ ትስስርህ ተነጥለህ ፤ እዚህ እቁብ፣ እድር አለ እዚህ ሰፈር ካልሆነ አትገባም አንለውም። እንደዛ የተባለ ካለ ይዛችሁ ኑ " ብለዋል።
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

20 Oct, 09:24


#ለመረጃ

ጅቡቲ ላይ የተከማቹ የነዳጅ ተሸከርካሪዎች እንዲገቡ ተፈቀደ!


የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡


አዲሱ መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም እንዳይገቡ ታግደው የቆዩ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡


መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ከተለያዩ ኤጀንሲዎችና ከጉምሩክ ኮሚሽን ተውጣጥቶ የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ዝርዝር ግምገማ  ማድረጉን ተከትሎ፣ በጥያቄ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በተገዙበት ቀንና የጉምሩክ ምዝገባ መሰረት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡

መንግሥት በተለይም ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢው ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው መንግሥት ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል (@አዲስ አድማስ)፡፡