የሸገር ልጅ ነኝ @yeshegerlij_negn Channel on Telegram

የሸገር ልጅ ነኝ

@yeshegerlij_negn


Subscribe our youtube channel

የሸገር ልጅ ነኝ (Amharic)

የሸገር ልጅ ነኝ (Yeshegerlij Negn) is a vibrant and engaging Telegram channel that focuses on showcasing the talents and creativity of young Ethiopians. From aspiring singers and dancers to talented artists and entrepreneurs, this channel is a platform for the youth to shine and share their work with the world. If you are looking for inspiring content that celebrates the next generation of Ethiopian talent, then look no further than Yeshegerlij Negn. Subscribe now and be part of a community that supports and uplifts the youth of Ethiopia. Don't miss out on the opportunity to discover the next big stars and innovators in the country. Subscribe our youtube channel to stay updated on the latest videos and highlights from the talented individuals featured on Yeshegerlij Negn.

የሸገር ልጅ ነኝ

12 Feb, 09:45


ከትላንት እስከ ዛሬ ከነውሩ ፈቀቅ የማይል ይህ የሀገር ጉድፍ ሰምታችሁታል። ትላንት 95 ሚሊየን ለ5 ሚሊየን እንዴት ያስቸግራል ብሎ በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ሲቀሰቅስ ነበር ዛሬ ደሞ አንድ ብሄር ከ83 ብሄር ጋር ተጣልቶ እንዴት ይሆናል የሚል በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሌላ የፍጅት መርዝ በሚዲያው እንዲሰራጭ እያደረገ ይገኛል።

እነዚህ ሰዎች አንዱን ህዝብ በአንድ ህዝብ ላይ እንዲነሳ እያደረጉ ሀገር ከማተራመስ ውጪ ሌላ አላማ የላቸውም ሀገሪቷ ምን እንደበደለቻቸው አላቅም። የፖለቲካ እና የባለስልጣናትን ነውር ወደ ህዝብ መውሰድ ቆሻሻ አስተሳሰብ መላበስ ነው ወገን በጋራ ሊከላከለው ይገባል እነዚህ ማንንም የሚወክሉ አይደሉም።

የሸገር ልጅ ነኝ

11 Feb, 16:53


ወዲ ረዳ👌

ሽምግልናው እንዲሳካ በቅን ልብ እያደረከው ስላለው ጥረት ትልቅ አክብሮት አለኝ። ለትግራይ ህዝብ ዘላቂ ሰላም አንድነትና ህብረት የሚያስፈልገው በጋራ መቆም ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

10 Feb, 19:31


ለመረጃ እንዲሆናችሁ ነው🤔
አንድ የኤርትራ ናቅፋ 8 የኢትዮጵያ ብር ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

10 Feb, 19:00


አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ሀገሩ እንዳይመለስ ክልከላ እንደተደረገበት ተናግሯል። ይህ እጅግ ገራሚና አስደናቂ ነገር ነው ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሀገሩ እንዳይገባ የተደረገ አስገራሚ ታሪክ ነው። ብልፅግና ገና ብዙ ያሰማናል።

የሸገር ልጅ ነኝ

10 Feb, 06:42


ሻዕቢያ ጠላት እንጂ ወዳጅ መሆን ፈፅሞ አይችልም ቢፈልግም አፈጣጠሩ አይፈቅድለትም። ከእሱ ጋር ህብረት መፍጠር አይደለም ማሰብ ኩነኔ ነው። በተለይ በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረገውን ፀያፍ ነውር ከተመለከትኩ በኃላ እጅግ አድርጌ ነው የተፀየፍኩት ይህ ድርጅት የጎረቤት መዥገር ነው።

አሁን አሁን ከወደ ትግራይ ከእዚህ ነውረኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው አሉ ሚባል ወሬ እሰማለሁ ግን ላምን አልችልም ከዚህ ትግራውያንን ከበላ አውሬ ድርጅት ጋር ህብረት ፈጥሬ የትግራይን መብት አስጠብቃለሁ ሰላሟን አረጋግጣለሁ የሚል ይኖራል ብዬ አላስብም ካለም ከአንገት በላይ ህክምና ያስፈልገዋል።

የሸገር ልጅ ነኝ

09 Feb, 07:25


ምን እየሆኑ ነው ጎበዝ🤔

በትግራይ ፖለቲከኞች መሀል እርቅ ለመፍጠር ውይይት ተጀምሯል ሽማግሌዎቹ ጥሩ ተስፋ እንዳለ እያመላከቱ ነው የሚል ወሬ ሲሰራጭ ተጋሩ ሆነው በትግረኛ እየፃፉ ሚበሳጩት ሰዎች ምን ነክቷቸው ነው።

ገና ምንም ባልተባለበትና ባልወጣ መረጃ የሸር ሽምግልና ምንትስ እያሉ እየተደረገ ያለው ውይይት አልመች ብሏቸው የሚቁነጠነጡ ሰዎች ምን እየሆኑ ነው ሁከቱና ግርግሩ ተመችቷቸው ነው ወይስ እንደተባለው የብልፅግና ረብጣ ገንዘብ በአካውንታቸው ታጭቆ አልገባህ ስላለኝ ነው።

ትግራዋይ ሆኖ የተፈጠረው ግርግር በሰላም ሊፈታ ነው ሲባል የሚበሳጭ ይኖራል ብዬ አላሳብም። አብዛኛው ትግራዋይ የሚፈልገው ሰላም ነው ሌላ ግርግርና ኮሽታ አቅለሽልሾታል ይህ የተጀመረው ሽምግልና ገና ውጤቱ ሳይታወቅ የምትቁነጠነጡ ሰዎች በርቱ ህዝብ ፍላጎታችሁ እየተረዳው ይሄዳል።

የሸገር ልጅ ነኝ

08 Feb, 19:26


እውነት ሆኖ አይቼም ሰላም ሆኖ ተመልክቼው🙏 ወገኖቼ አሸማጋዮች በሁለቱም ወገን መልካም የሆነን እሺታ አግኝተዋል ሂደቱ ጥሩ እየተጓዘ ነው ለመነጋገርና ችግሮቻቸውን በጠረንቤዛ ለመፍታት ሙሉ ስምምነት እንደተደረሰ ተሰምቷል።

ለትግራይ እና ህዝቧ የሚጠቅመው ይህ ብቻ ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

08 Feb, 18:12


እውነቱን ልንገርህ አንተማ ልዩ ሌባ ነህ!

ብንያም ሆይ:- ሌባ ነኝ ስትል ሰማሁህ? እውነት አለህ። አልተሳሳትክም።

የኹሉንም ዓይነት ሰዎች ልብ የወሰድክ አንተማ የለየልህ አገር ያወቀህ ሌባ ነህ። ፈቅደው ፈልገው ልባቸውን ከፍተው እጃቸውን ዘርግተው የሚሰጡህ ሌባ። የሌቦች አናት ዲያብሎስን ያራቆትህ ባለ ልዩ ችሎታ ሌባ። ሰርቆ ያሠራቸውን የምታስፈታ ሌባ!

እጅ ከፍንጅ እንዳትያዝ ስትሰርቅ አትታይም አትገኝምም። አትሰርቅም እንጅ ሌባ ነህ።

የማትሰርቅ ሌባ!

የሸገር ልጅ ነኝ

08 Feb, 16:22


"ህወሓት" ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ ስትራቴጂክ አመራር የሚሰጠው አጦ የወቅቱን ፖለቲካ በሚገባ እየተረዳ አሸናፊ በአብዛኛው ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሃሳብ ማመንጨት ተስኖታል።

ይሄን ደሞ በራሳቸው ግምገማ አረጋግጠዋል አሁን ጥያቄው ህወሓት እውነት ስትራቴጂክ አመራር የሚሰጥ ሰው አጣ ነው ወይስ እድሉን ለወጣቶች የመስጠት ፍላጎት ማጣት ነው?

በእርግጥ አቶ መለስ ዜናዊ ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ለአፍሪካም እጅግ ወሳኝ አመራር የሚሰጡ በዓለም ላይ ድንቅ ብቃታቸው አረጋግጠው ባለ ምጡቅ አይምሮ ባለቤት ከሚባሉት ተርታ የተመደቡ የአፍሪካ መመኪያ የነበሩ መሪ ናቸው።

የሸገር ልጅ ነኝ

08 Feb, 13:36


ተጋሩ አስተውሉ?

የትግራይ ህዝብ አንድነት ምርጫ ሆኖ የሚቀርብ አይደለም የህልውና ጉዳይ ነው። ተጋሩ አንድ መሆን ካልቻለ እጅግ አስቸጋሩ ፈተና ይገጥመዋል የትግራይን ህዝብ አንድነት የሚፈታተን የውስጥ ይሁን የውጪ ሀይል በጋራ ክንድ ሊረታ ይገባል።

የትግራይ ፖለቲከኞች ለተጋሩ አንድነት ለሰላም ለልማት የማይተጉ ከሆነ በቃቹ ሊባሉ ይገባል። ማንም ከትግራይ ህዝብ ሰላምና አንድነት በላይ ሊሆን ፈፅሞ አይችልም።

ሁሉም ተጋሩ ሊያስተውል ይገባል መጓተት ሁሉንም ይጎዳል በመጓተት መሀል ሁሉም ተጠቃሚነቱን ከሚነጠቅ ሻም ብሎ አስቦና አስተውሎ በጋራና በህብረት ሊቆም ይገባል በጋራ ቆሞ ችግሩን በመፍታት የትግራይ ዘላቂ ሰላም ሊያረጋግጥ ይችላል።

የሸገር ልጅ ነኝ

07 Feb, 13:50


"አብይ ሚኒልክ" እያሉ ያዜሙ ሰልፈኞች መቼም ከህሊናዬ አይጠፉም የትግራይ ህዝብ ላይ ጦሩን በማዝመቱ ብቻ አብይን ሚኒልክ አዳነችን ጣይቱ ያሉ ቡድኖችና ሰልፈኞች ዛሬ የት ናቸው ዛሬስ ማን ይሉት ይሆን እንድል ያስገድደኛል። በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ ሰልፍ አካሄደው ነው ወይስ ማሊያ የቀየሩ ሰልፈኞች ተከስተው? በዚህ ጥንቅር ላይ የተጠቀሱ ዝርዝር ነገሮችን ይመልከቱ። https://youtu.be/s-cQbPNgGXg?si=zkTj0SRQ4I9d6rAE

የሸገር ልጅ ነኝ

07 Feb, 09:57


ራያ ሰላም ነው።

የብልፅግና አክቲቪስቶች ስራቸውን ጀምረዋል በራያ አካባቢ አርሚ ሚኒቲስ ሰፈረ አንደኛው ቡድን ደሞ አረሚ ወደ መቐለ ተጠራ ገለመኔ የሚል ፅሁፍ ማሰራጨት ጀምረዋል። እንዲህ ያለ ያልተገባ ወሬን በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረግ ሩጫ ሊቆም ይገባል በአሁኑ ሰዓት የተጠራም ሆነ የሰፈረ አርሚ የለም ራያ አካባቢ ሰላም ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

06 Feb, 06:06


እንግዲህ በአዲስ አበባ 11 ክፍለ ከተሞች አሉ በአንዱ ክፍለ ከተማ ብቻ ደሞዝ ተከፋይ አመራር ከ350 በላይ አለ ይህ ሀይል ዋና ካድሬው ሲሆን የሰላም ዘብ ተብሎ የተደራጀው አመራሩ ብቻ በየወረዳው ከ100 በላይ አለ ይሄን በክፍለ ከተማ ስትመታው ከ1ሺ በላይ ነው በድምሩ ከካድሬው ጋር ከ1350 በላይ ይሆናል በ11 ክፍለ ከተማ ስትደምረው ከ13ሺ በላይ ሰው ይገኛል ካልወጣህ አስብበት የተባለው ትግራዋይ አብዛኛው የመጣው ይምጣ ብሎ ተኝቷል።

የተኛው ሰላምን ጠልቶ ሳይሆን የፖለቲካ መጠቀሚያ አልሆንም ብሎ ነው ሰላም እና የሰላም ሰልፈኛው ሁሌም ስለ ሰላም እንዲሰለፍ አበክሮ እንዲጮህ በዚሁ እንዲቀጥል መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን። ከሰልፈኞቹ ይቺ ቫነር ቀልቤን ስባዋለች ለምን ካልከኝ የብልፅግና ጥርነፋ ከባድ ነች ፖለቲካ ከባድ ነው ለማለት ነው።

በነገራችን ላይ "ጥሩ ትግሬ" እየተባሉ የሚጠሩት በየወረዳውና ክፍለ ከተማው በአመራርነት የተመደቡና በየወረዳው ተሳታፊ የሆኑት በሰልፉ ላይ አሉ ትግራዋይ የለም ማለት ሀሰት ነው ሚሆነው ያው ስለሰልፉ ባለው ግልፅ አርገን ፅፈናል።

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Feb, 19:05


የሰማሁትን ላሰማችሁ ይሳካ ይሆን ዘንድ ተመኘሁ ታላቁ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በትግራይ ፖለቲከኞች ላይ የተፈጠረውን ችግር በውይይት እንዲፈታና ችግሩ እንዲቀረፍ ማወያየት እንደጀመሩ ተሰምቷል።

ይህ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ የሚል በሙሉ አጋርነቱን #ሼር በማድረግ ይግለፅ ዶክተር የጀመሩትን አበርትተው እንዲቀጥሉበት ባይጀምሩት እራሱ መልካም እሳቤ ነውና እንዲጀምሩት ሁሉም በትብብር #ሼር ያርግ🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Feb, 18:44


እነዚህ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፋይናስ ፅ/ቤት ቢሮ ውስጥ የተነሱ የብልፅግና አባላት ናቸው እናም የነገው ሰልፍ ለማገዝ የተዘጋጁ ብርቱ ሰልፈኞች ናቸው።

በነገራችን ላይ የነገው የአዲስ አበባ ሰልፍ ላይ "የትግራይ ግዛት አንድነት ይጠበቅ፣ የምዕራብ ትግራይ ህዝብ ወደ መኖሪያው ይመለስ፣ ወራሪዎች ከትግራይ መሬት ይውጡ።" የሚሉ መፈክሮች ይዘው ከወጡ በትክክል የትግራይ ተወላጆች ያካሄዱት ሰልፍ ነው ብሎ ለመናገር ያነሳሳ ይሆናል አለዛ እንዲህ በብልፅግና የወረዳ አባላቶች የተጠረነፈ ለመሆኑ ማረጋገጫ ፎቶ እየለቀምን እንለጥፍላቹሃለን።

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Feb, 10:50


እኔም ትልቁ ጭንቀቴ ይሄ ነው😱😜

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Feb, 08:38


በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ ነገ ሰልፍ እንዲወጣ ቤት ለቤት ጥሪ እየተደረገለት ይገኛል። አንዳንድ ክፍለ ከተሞች ላይ ከለሊቱ 10 ሰዓት አንዳንድ ክፍለ ከተሞች ላይ ደሞ ከለሊቱ 11 ሰዓት እንዲወጡ መልዕክት የተላለፈ ሲሆን መቅረት ብሎ ነገር አይታሰብም የሚቀር ያስብበት ተብሏል።

ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የተባሉ ጉዳዮች "አንድም አማረኛ ተናጋሪ ጋዜጠኛ እንዳይዘግብ" ከሰልፈኛው ትግረኛ አቀላጥፎ የሚናገር ብቻ ሚዲያ ላይ ይውጣ። የሚወጣው ሰልፈኛ እንዳያንስ የመንግስት ሰራተኛ የፀጥታ አባላት ውስጥ የሚሰሩ የትግራይ ተወላጆች አቴንዳስ ተይዞ እንዲወጡ ይደረግ የሚያዙ መፈክሮች ከአንድ መዓከል ይዘጋጃሉ ማንም መፈክር ይዞ እንዳይገኝ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የነገው ሰልፍና ዓላማ ባለፈው ግልፅ አድርገነዋል።

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Feb, 06:32


የመቐለ ከተማ ነዋሪ እስከ አሁን ከንቲባ የለውም የዚችን ከተማ አንድ ወንበር እንኳን ለህዝቡ መልካም አስተዳደርና አገልግሎት ሲባል ተስማምተው መከወን የተሳናቸው ቡድኖች መሆናቸው እጅግ አሳዛኝ ነው።

የህዝብ ድርጅት ማለት ምን ማለት ነው ህዝብ አገልግሎት እያጣ ህዝብ ከመኖሪያው ተሰዶ እየተሰቃየ የምንታገለው ለህዝብ ነው የሚሉት ለየትኛው ህዝብ ነው።

እነዚህ ሀይሎች የህዝብን የመደራደር አቅም አሳጥተው በህዝቦች ጠንካራ ትግል የተገኘውን እድል በመግፋት ስልጣን ፍለጋ አብይ ጋር ሲመላለሱ ነው ነገሩን ያጨቀዩት ለነገሩ ስትራቴጂክ አመራር የለንም ብለው ያመኑ ፖለቲካ ጨርሶ የጠፋባቸው ስብስቦች ከሆኑ ከራርመዋል።

እነዚህ ሀይሎች በአሁኑ ሰዓት ለትግራይ ህዝብ መከታ መሆን ትተው ስጋት እየሆኑ ነው ፈጣን እርምት ካልወሰዱ አደጋው ከፍተኛ ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

04 Feb, 15:29


የትግራይ ሊህቃንና ፖለቲከኛ ዝነኛና አክትቪስት ሁሉም የዚህ ህዝብ መከራና ስደት እንዲያበቃ ነው መስራት ያለባቸው እነዚህ ከ1535 ቀናቶች በላይ በስደትና በመከራ ያሉ ህዝቦች አንዳች ጥፋት የለባቸው ጥፋታቸው ትግራዋይ ሆነው መፈጠራቸው ነው ከሚኖሩበት መንደርና ሰፈር የተፈናቀሉት በማንነታቸው ነው።

በአካባቢው ፖለቲከኞች ባመጡት ጦርነት እሳቱን ፍራቻ ተሰደዱ መኖሪያቸው በወራሪዎች ተያዙ ሀገር ሰላም ሆነ ድርድር ተደረገ ተባለ እንመለሳለን ብለው ቢጠብቁ እስከ አሁን የውሃ ሽታ ሆኖ የመመለስ ተስፋቸው ተመናምኖ በመከራ ውስጥ ሆነው ነገን በተስፋ እየጠበቁ ይገኛሉ።

የሸገር ልጅ ነኝ

03 Feb, 15:37


የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተር ለትግራይ ህዝብ ስለሰላም የፃፉትን ጥሪ አከብራለሁ ነገር ግን ይሄን ፅሁፍ ለመፃፍ ከሚደክሙ በአጭሩ የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲፈፀም ቢተጉ የትግራይ ህዝብ ሰላም በዘላቂነት ይረጋገጥ ነበር።

ነገ በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በየወረዳው ከተጠራ በኃላ ቀኑ ተቀይሯል እንነግራቹሃልን ቢሉም ወደ 29 ሀሙስ መሸጋገሩን ሰምተናል። ሰልፉ የተሸጋገረውም በመጀመሪያ የእሳቸው መግለጫ እንዲብላላ ታስቦ እንደሆነ ታውቋል።

የሸገር ልጅ ነኝ

02 Feb, 19:43


ከመሸ የተከሰትኩት የዚህ ሰውዬ ነገር አስጨንቆኝ ነው ይሄ መምህር መጀመሪያ በአስተሳሰብ ነበር የደሀየው አሁን ደሞ ኢኮኖሚካሊ ተቸገርኩ እርዱኝ እያለ ነውና የቻላችሁትን ጣል ጣል አርጉለት🤔
:
እኔ ቲንሽ ያስከፋኝ የሰጣት ሃሳብ ነች እንጂ ልመናው አይደለም ሰው ከተቸገረ ደጅ ይጠናል እሱ ብዙም አላስገረመኝም ሃሳቧ ግን "ከየትኛውም ፖለቲካ ባለመወገኔ" የተነሳ ያልካት ከዚህ በላይ ወዴት ልትወግን ኑሯል አንድ ህዝብ ላይ በግልፅና በአደባባይ የከረፋ ጥላቻን እየሰበክ እንዲጨፈጨፉ ስንት ስትለፋና ስትደክም ኑረህ ባለመወገኔ ትላለህ እንዴ መለስ ብለህ ቪዲዮችን ተመልከት ከዘነጋሀው ደሞ አለማፈርህ ባይሆን ፀጥ ብለህ እርዱኝ በል ሌላውን ተው🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

01 Feb, 15:50


ሀገር በቀሉ ብልፅግና የቱ ነው።

መቼም አንድ ሀገር ላይ መንግስት የሆነ ፓርቲ እኔ ምከተለው ሀገር በቀል አስተሳሰብ ነው ካለ ዓለም የማትከተለው ለየት ያለ ፖሊስ ቀርጫለሁ ማለቱ ነው። የእኛ ሀገር ብልፅግና ፓርቲ ደሞ በተደጋጋሚ እኔ ምከተለው ሀገር በቀል ነው ሲል ይደመጣል የቱ ነው ሀገር በቀልነቱ ሲጀመር የሚመራበት ፖሊሲ አለው ወይ ቆይ ምንድን ነው የሚከተለው በጨዋ ደንብ አስረዱኝ?? በጣም ማወቅ እፈልጋለሁ።

የሀገሪቷን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለIMF አስረክቦ ለታላቅ ታሪካዊ ስህተትና ባርነት ከዳረገን በኃላ የምን ሀገር በቀል ነው ሲጀመር ሊበራል አስተሳሰብ ሀገር በቀል ሆነ እንዴ ነው ሰው አይባንንም ብላችሁ ነው🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

29 Jan, 19:47


https://youtu.be/9jBvPtCYTxA?si=2TeGtMwXkF2s7yWc

የሸገር ልጅ ነኝ

29 Jan, 17:45


🕊ሰላም ለትግራይ🕊

በትግራይና በከተሞቿ እየሆነ ያለው አንዳንዴ ሰምተን እንዳልሰማን የምናልፋቸው ነውረኛ ድርጊቶች በጊዜ ሊቆሙ ይገባል ተጋሩም ተከፋፍሎ ለየብቻ ቆሞ መመልከት ስርዓት አልበኝነትን ፈጥሮ እራስን መልሶ ይበላልና በጋራ NO ሊባል ይገባል።

ትግራዋይ ወገኖቼ ልዩነት መስተናገዱ የፖለቲካ አንዱ ባህሪ ቢሆንም ግን ጊዜው አይደለም ትላት ትግራውያንን ለመንከስ የማይስማሙ ዘይትና ውሃ የሆኑ ሀይሎች ልዩነታቸውን ትተው አንድ ሆነው ተሰለፉ ዛሬ እንዴት ተጋሩ የተፈናቀሉ ወገኖቹን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስ ራሱ ላይ ያንዣበበውንም አደጋ ለመከላከል ልዩነቱን አቆይቶ በአንድ መቆም አቃተው።

ተጋሩወይ እናንተ በአንድ ከአልቆማቹ አመራሩን በአንድ አታቆሙትም ለአመራሮቻቹ ልዩነቱን አቆዩትና አስቀድማቹ የትግራይ ግዛት አንድነት አስጠብቁ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አስፈፅሙ በላሏቸው አለዛ ጅማሮው በዚህ ከቀጠለ የከፋ ይሆናል።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

29 Jan, 13:11


🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የምዕራብ ትግራይ ህዝብ እንዳይመለስ የፕሪቶሪያው ስምምነት በአግባቡ እንዳይፈፀም ዋነኛ ተጠያቂው ፌደራል መንግስቱ ሲሆን ሁለተኛው ተጠያቂ ደሞ የህወሓት አመራር ነው ሶስተኛ ተጠያቂው ደሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ነው።

የፌደራል መንግስቱ ሆን ብሎ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዳይተገበር ሲሰራ ቆይቷል። የተከዜ ዘብ ምንትስ የሚባል ሀይል እያደራጀ እያበረታታ ተግባሩን ሲመራው ቆይቷል ለዚህ ተግባሩ ደሞ የህወሓት አመራሮች መከፋፈል ትልቅ አቅምና ጉልበት ሆኖለታል።

የህወሓት አመራሮችም ይሁኑ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተፈናቃይ ህዝቦች መከራና ስደት ይልቅ የራሳቸው ጊዜያዊ ችግር የወንበር ናፍቆት በልጦባቸው ሙሉ ለሙሉ ተግባሩን ትተውታል።

ስለዚህ የፕሪቶሪያ ስምምነት በፌደራል መንግስት በጎ ተግባር የሚከናወን ባለመሆኑ ስምምነቱ የማይተገበር ከሆነ ደሞ አደጋው ለትግራይና ህዝቦቿ ስለሆነ ህዝብ በአንድነት አመራሮቹ ላይ ጫና በመፍጠር ወደ አስቸኳይ ንግግር ገብተው ልዩነታቸውን ለጊዜው በማቆየት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲተገበር ስደተኞች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ሊሰሩ ይገባል።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Jan, 18:03


ጠቅላዩ "በጅማ ከተማ 15ሺ የልማት ተነሺዎች ካሳ አልጠየቁንም ብለው ነበር" ነገር ግን ሌሎች የመንግስት መረጃዎች የሚያሳዩት ደሞ ለልማት ተነሺዎቹ ካሳ መኖሪያ ቤት መንግስት ሰርቶ ማጠናቀቁን ነው።

እዚህ ጋር ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲናገሩ ዋሾ ከሚባሉ "የጅማ ነዋሪ ለልማቱ ካሳ አልጠየቀንም እኛ ግን ቤት ሰርተንለታል " ብለው ቢሰክሱ ይሻላቸው ነበር።

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Jan, 09:54


የትግራይ ወታደራዊ ከፍተኛ አመራር የወሰነው ውሳኔ የቱ ነው ትክክል የቱ ነው ስህተት? ይሄን ሳያውቁ እኔን ለመሳደብ መሯሯጥ በሽታ ነው ህክምና ያስፈልገዋል። ለማንኛውም ግልፅ ላርገው።

የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች ከፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም እና የስደተኞች አመላለስ ጋር ተያይዞ ያወጡት መግለጫ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው። #ይኣክል በሚል ንቅናቄ ህዝቡ የተሰለፈበት አጀንዳን የሚያጠናክር የጊዜያዊ አስተዳደሩም አቋም የሆነን የሚገልፅ ሁሉም ሊግባባት የሚችል አቋም ነው። ይህ በወታደራዊ አመራሩ መነሳት ያለበት ወታደራዊ አመራሩን የሚመለከት ነውና ስህተት ሊሆን አይችልም።

ወታደራዊ አመራሩ በእኔ አተያይ መግባት አልነበረበትም ትክክልም አይደለም ልለው የምችለው በፖለቲካ የምደግፈውን የእነ እከሌን ነው ማለቱን ነው። ለምን ከተባለ TDF የትግራይ ሀይል እንጂ የህወሓት ሀይል አይደለምና ነው። TDF የባይቶናም የአረናም ነው መሆን ያለበት ሲቀጥል ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲስተካከል ፈቅጃለሁ ማለቱም ወታደራዊ አመራሩን ባይገባበት ተመራጭ የሚያደርጉ ናቸው።

የTDF ወታደራዊ አመራር በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ውክልና አለው በዛ ውክልና ውስጥ ሆኖ ተገቢ ናቸው የሚላቸውን አቋሞች እያንፀባረቀ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሄድ ነበረበት ነው እንጂ ያወጣቸው መግለጫዎች በሙሉ ተገቢ አይደለም አይባልም በነገራችን ላይ አቶ ጌታቸው ረዳም በማብራሪያው ላይ ወታደራዊ አመራሩ ያወጣው መግለጫ የሚደገፍ እና እኛም የምንጋራው አቋም አለበት ብሏል።

ይሄ ማለት በሁለቱም ቡድኖች መካከል የጋራ የሆኑ ሚያስማሙ አቋሞች አሉ ማለት ነው ስለዚህ ልዩነቶችን በውይይት እንዲፈቱ ግፊት ማድረግ የእኛ ሀላፊነት ነው የጋራ የሆኑትን አቋሞች ደሞ አጠናክረው እንዲሄዱበት መደገፍ ተገቢ ይሆናል ከዛ ውጪ የተፈጠሩ ልዩነቶችን ማካረር መበሻሸቅ አይጠቅምም ደሞም አይረቤ ነው መሰዳደብም እንደዛው ባልቴትነት ነው።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Jan, 09:09


🕊ሰላም ለትግራይ🕊

አቶ ጌታቸው ረዳ ፌደራል መንግስቱን ስለ "ምዕራብ ትግራይ ስጠይቀው አክሱምን ሳታስተዳደር ስለ ወልቃይት አትጠይቅ?" ብሎ አሾፈብኝ ብሎ ሲናገር ሰማሁት።

አቶ ጌታቸው ይሄን ቃል ለመናገር የፈለገው የእኛ ስምምነት አለመኖር የመደራደር አቅማችንን አዳክሞታል ልዩነታችን በተደራዳሪያችን በኩል ሰነፍ ሆነን እንድንታይ አድርጎናል ለማለት እንደሆነ ቢገባኝም መልሱ ግን እጅግ አናዳጅ እና ንቀት የተሞላበት ነው።

በአሁኑ ሰዓት ትግራይ አቅም እንድታጣ ዋነኛው ድርሻ የበላይ አመራሩ ነው ለዚህ ጌታቸው የድርሻው ይወስዳል። አሁን ተከታታይነት ያለው መድረክ መነጋገር ያስፈልጋል የትግራይ ወታደራዊ አመራር የወሰነው ውሳኔ በአብዛኛው ቅቡልነት ያለው እና የሁሉም አቋም የሆነ አጀንዳ እንዳለው እሙን ነው። ስለዚህ መነጋገሩ የግድ ይላል።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Jan, 05:43


🕊ሰላም ለትግራይ🕊

በሁለቱም ወገን ያሉ ደጋፊዎችም ሆኑ ፖለቲከኞች መፈራረጁን ተያይዘውታል አሁን እሱን ወደ ጎን እንተውና መሆን ስላለበት እንምከር።

አሁን ወጣቱ ለዳግማዊ ጦርነት የሚጋብዝ ማንኛውንም መንገድ አይቀበልም መሆንም የለበትም ትክክልም አይደለም ስለዚህ ቆም ብሎ ጊዜ ወስዶ በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ መምከር ያስፈልጋል ማለት ነው።

የትኛውንም አይነት የፖለቲካ ቅቡልነት ለማግኘት ሲባል የትግራይን ህዝብ ከጨፈጨፈና ከዘረፈ ሀይል ጋር ህብረት የሚባል ነገር መፈጠር የለበትም! በኢትዮጵያ ካለው ፌደራል መንግስት ጋር እንደ ሀገር አብረህ እስከቀጠልክ ድረስ የራስህን ሀገር እስካልመሰረትክ በሚያስማማህ ጉዳይ እየመከርህ ትቀጥላለህ አንዳንድ ማይስማሙ ነገሮች ቢሮሩ እንኳ ለህዝብ ስትል በሰላም ለመፍታት ትጥራለህ አበደን።

ከዚህ ውጪ ሌላ ወንበዴ ቡድን ፈልገህ የትግራይን ህዝብ ዳግም ጦርነት ውስጥ ሊከት የሚችል መንገድ መምረጥ መታወር ነው ሊታሰብም የሚችል አይሆንም ሃሳብ ካለ ሊቆም የሚገባው ነው ህዘብ መታገል ያለበት ይህን ነው።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

27 Jan, 17:40


🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የትግራይ ህዝብ መከራ ውስጥ በነበረበት ሰዓት ስፅፍ ስሰደብ ስታሰር በትግራይ ጉዳይ አያገባህም ያለኝ ማንም የለም ዛሬ ግን አያገባህም እየተባልኩ ነው መልካም ነው።

ግን እኔ አያገባኝም ልል አልችልም ያ ደግ ያ መልካም ያ ጨዋ ያ ፍቅር ወዳድ የሆነ ህዝብ ደስታና ሰላም እንጂ ሁሌ ጦርነት የሚሰጠው የለም የትግራይ ህዝብ ትጉህ ብርቱ ህዝብ ነው ለኢትዮጵያ ነፃነት ትርፍ መስዋዕትነት የከፈለ ጀግና ህዝብ ነው።

ዛሬን በድጋሚ ወደ መከራ ወደ ስቃይ እንዲገባ አልፈቅድም ሰላሙን መልካሙን እንዲያገኝ አበክሬ እጮሃለው እናንተ ተሳደቡ እኔ ከነገ ጀምሮ አቋሜን አሳውቃለሁ ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

27 Jan, 12:35


🕊ሰላም ለትግራይ🕊

ይህ ህዝብ ይህ ወጣት በመቐለ ሮማናት አደባባይ የተከሰተ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሲንበለበል ውሏል መልዕክቱም አንድ ነው። "ሰላምን እንሻለን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ ይከበር መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ ማናቸውም እንቅስቃሴ አንቀበልም ወዘተ… የሚሉ ናቸው"

የትግራይ ህዝብ ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ይፈልጋል ይሄን ውሳኔ ማክበር ደሞ የሁሉም አመራር ግዴታ ነው።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

27 Jan, 08:09


ሶስት እውነቶችን እንግለፅ👌

እውነት አንድ "ህዝብ በድጋፍም ይሁን በተቋውሞ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሃሳቡን የሚገልፀው በትግራይ ብቻ ነው።"

እውነት ሁለት "በተቋውሞም በድጋፍም ሰልፍ የወጡ ሰልፈኞች የጋራ አቋም የተፈናቀሉት ወደ መኖሪያቸው ይመለሱ #ይኣክል የሚያስማማቸው መሆኑ"

እውነት ሶስት "የትግራይ ወጣት በአብዛኛው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ደጋፊ መሆኑ ነው።"

ይህ ፎቶ ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች ያወጡትን መግለጫ በመቃወም የተካሄደ ሰልፍ ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

26 Jan, 15:37


የትግራይ ወቅታዊ አስገራሚ ሁኔታና የመከላከያ ሰራዊት በስውር የታዘዘው ትዕዛዝ በከተሞች እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች የእናቶች ተማፅኖ ተዳሶበታል። https://youtu.be/up9Q30vU3OA?si=BO4cDeuc5g1mpkeH

የሸገር ልጅ ነኝ

26 Jan, 12:32


ትግራዋይ አስተውል?

በትግራይ ህዝብ መካከል የእርስ በእርስ ጦርነት ቢነሳ ሴቶች በእልልታ ወንዶች በጭብጨባ አመሰግኑ ብሎ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በደስታ እየቦረቀ ሰልፍ የሚወጣ እንደሚኖር ለአፍታም አልጠራጠርም። ዛሬም ተጋሩን ነክሶ ነክሶ ሳይጠግብ የተሰባበረ ጥርስ ዛሬም የተፈጠረው አጋጣሚ ተጥቅሞ ሊናከስ አሰፍስፎ ይገኛል።

እንዲህ አይነት የማይለቅ ጥላቻ እንዴት ሆኖ እንደተፈጠ ባላቅም ተጋሩ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ጮቤ እየረገጡ መች ነው ምትጀምሩት እያሉ የሚናፍቁ እንዳሉ ግን እየተመለከትኩ ነው ትግራዋይ አስተውል?

ተጋሩ አስተውል ስልህ ይሄን ቡድን ፈርተህ መብትህን አሳልፈህ ስጥ ለውጥህን አትሻ እያልኩህ አይደለም አስተውለህ ለሌላው ተጋላጭ ሳትሆን ነገራቶችህን ዲሞክራያዊ በሆነ መልኩ ፍታው ለማለት ነው። አለዛ እንደ ትላንትናው ፀቡን ትቶ ጅብ ለጅብ አብረን እንጓዛለን ብሎ ይሰለፍብሃል።

የሸገር ልጅ ነኝ

25 Jan, 18:30


ደብረፅዮን ይምራ ጌታቸው ይምራ ገብረ ገ/ፃዲቅ ይምራ ማን ይምራ አይመለከተኝም። ዋናው ነጥቤ የትግራይ ህዝብ ሰላም ይሁን የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ መኖሪያቸው ይመለሱ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይሸራረፍ ይፈፀም። ሰላም ሰላም ብቻ ይሁን🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

25 Jan, 14:57


🕊 ሰላም ለትግራይ 🕊

ይህ የትግራይ እናቶች ፀሎት ሁሌም በደጃቸው በአካባቢያቸው የሚያሰሙት ታላቅ እና ግሩም ፀሎት ነው። የአክሱሟ እመቤት ፅዮን ማርያም ፀሎታቸውን ሰምታ ዘላቂ ሰላም ስጋት የሌለበት ህይወት እንድትኖሩ ትርዳችሁ🙏

አዎ በትግራይ ምድር አንድም የጥይት ድምፅ እንዲሰማ አልሻም ዳግም የእናቶችን እንባና ሀዘን መመልከት አልፈቅድም ብዙ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች በድርድር ለሚፈታ ችግር ህይወታቸውን እንዲያጡ እንዲሆን መንገድ አላመቻችም።

🕊ሰላም ለትግራይ🕊

የሸገር ልጅ ነኝ

21 Jan, 05:52


"ሂጃቧንም ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች" በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

የሸገር ልጅ ነኝ

20 Jan, 19:55


https://youtu.be/KdceKIF0YRQ?si=1vcy-9fydPnOa-8-

የሸገር ልጅ ነኝ

20 Jan, 19:33


ታላቋን ቤተክርስቲያን ላይ የሚያላግጡ በዝተዋል ሰው የፈለገውን የማመን መብቱን በሚጋፋ መልኩ እንዲህ ያለውን ነውር የሚፈፅሙ ምዕመኑን የሚያበሳጩና ለተለያየ ፀብ የሚዳርጉ ነውረኞችን የህግ አካሉ አደብ ሊያሲዝ ይገባል።

እንዲህ ያለ ያልተገባ ነገር ወደ አልተፈለገ ጠብ ያመራል ስለዚህ ቤተክርስቲያኒቱ ተከታትላ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ፍርድ እንዲያገኙ ማስደረግ አለባት። አለዛ ይዞት የሚመጣው መዘዝ የከፋ ይሆናል።

የሸገር ልጅ ነኝ

20 Jan, 15:06


ይሄ ወፈፌ ትላንት መምህር ሄኖክን የአእላፍ ዝማሬን የጀመረ ሰሞን ስንት ሲለው ሲዘልፈው ከረመ ዝም ተባለ አሁን ደሞ አኬ የሚባለውን ልጅ ይሰድበው ጀምሯል። በኦርቶዶክስ ቤት ትንሽ ስም ካገኘህና ለየት ያለ ነገር ከፈጠርክ ይንጨረጨራል አንድም እውቀት የለውም አይሞግትህም የስድብ መዓት ነው ሚያወርድብህ እራሱን በእውር ደጋፊዎቹ አግዝፎ ይነጉዳል አይናቸው የተገለጠ ጊዜ የዳንኤል ክብረት እጣ ፈንታ ይደርስሃል።

የሸገር ልጅ ነኝ

19 Jan, 20:11


በጥምቀት በዓል የተለያዩ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ተከናውነዋል ከእነዛ ውስጥ የቃሊቲ ምድርን ያራደ ትዕይንት እጅግ ማራኪ ነበረ። ይህን ገራሚ ትዕይንት ባየንበት ዓይናችንየታቦታቱን ማደሪያ ተነጥቀው ጥቁር ለብሰው እያነቡ ያከበሩ ምዕመናን ስንመለከት ከልብ አዝነናል። https://youtu.be/Ggs5hqA8tTI?si=j2CrbPmWCwz4RO4z

የሸገር ልጅ ነኝ

19 Jan, 16:57


በዓሉ በሰላም ተጠናቋል ተመስገን🙏
:
የዓመት ሰው ይበለን🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

19 Jan, 08:44


እጅግ ያሳዝናል ሁሉም ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። #ሼር

የከተራን እና የጥምቀትን በዓል ሌላው በደስታ ሲያሳልፍ እነሱ ግን ጥቁር ለብሰው ማቅ ነስንሰው በሐዘን እያከበሩ ይገኛሉ።

በሀዲያ ዞን የሚገኙት የጊንብቾ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን
የጥምቀት ማክበርያ ስፍራ ተነፍገው መከራን እየተጋፈጡ ከተራንና የጥምቀት በዓልን እንዲህ ጥቁር ለብሰው ማቅ ነስንሰው አክብረዋል።

በሌሎች አካባቢዎች በዓሉ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ እየተከበረ ያለ ቢሆንም በዚህ አካባቢ ግን እየሆነ ያለው ነገር እጅግ ውስጥ የሚጎዳ ሆኖ እናገኘዋለን እናም መላው ህዝብ ከጎናቸው ቆሞ ችግራቸው እንዲፈታ ሼር በማድረግ እንዲያግዛቸው ስንል በትህትና እንጠይቃለን🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

18 Jan, 18:19


ፈሪ ነህ...እራስህን ግለጥ የሚል ተደጋጋሚ መልዕክት ይደርሰኛል።
.
የውልህ ብራዘር:

አውሬን መፍራት ያለ ነው። ደግሞ ፈርተንም እየተረፈን አይደለም...!

#ጥላዬ_ያሚ "የእኔም የልቤ ሃሳብ ነው"

የሸገር ልጅ ነኝ

18 Jan, 12:10


ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

17 Jan, 15:15


የተለመደው ክፋት ዛሬም ተደግሟል የዛሬው መራር ነው በእናትና አባቱ ፊት ቤተሰብ እያሳዩ ረሸኑት። ንፁሃንን በህዝብ ፊት መረሸን ምን የሚሉት ጀብደኝነት ነው።

ይህ አረመኔነት እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው ወገኔስ ከእነዚህ ግፈኞች ቀንበር መቼ ነው የሚላቀቀው እኔን ወንድሜ እኔን ወገኔ 😭ከማልቀስ ውጪ አቅም የለኝም😭 ነፍስ ይማር🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

16 Jan, 18:33


አሁን ይሄ ምን ይሉታል "የከሰረ አክቲቪስት" 🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

15 Jan, 07:35


#ይኣክል ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የህዝቦች ድምፅ በሮማናት አደባባይ እያስተጋባ ነው።ሁሉም ሰው #ሼር ያርግ አስተጋባ!!

የሸገር ልጅ ነኝ

14 Jan, 20:45


"ይኣክል" ሁለተኛ ቀኑን የያዘው በእንባ የታጀበው የመቐለው ሰልፍ በሮማናት አደባባይ "ይበቃል" ነገም ይቀጥላል። https://youtu.be/xBlUqO6xv20?si=Wiy0PHhUR-5RnGi5

የሸገር ልጅ ነኝ

14 Jan, 18:17


#ይኣክል #ይበቃል ንቅናቄ ዛሬ 2ኛ ቀኑን ይዞ ምሽት ላይ እንገኛለን። ሰልፈኞቹ አዳራቸው እዚሁ በሮማናት አደባባይ እንደሚሆን እየተናገሩ ነው። በአሁኑ ሰዓት ይህ ብርቱ ሰልፈኛ ድምፁን ለተፈናቃይ ወገኖቹ እያሰማ ይገኛል። አሁን ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ሆንዋል። ነገም ሰልፉ ይቀጥላል። #ሼር #ሼር

የሸገር ልጅ ነኝ

14 Jan, 15:07


እሱ ሞትን አምኜ ነው ምመጣው አለ።
:
እዚህ ሰፈር ግን ረብሽ ተፈጠረ🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

14 Jan, 10:00


#ይኣክል🖐 #ይበቃል🖐 #ሼር

ይህ የፖለቲካ አጀንዳ አይደለም ይህ የህዝቦች መከራና ስቃይ እንዲቆም የሚጠይቅ እንጂ ይህን እውነተኛና ፍትሃዊ ጥያቄ ከጊዜያዊ የፖለቲካ ልዩነት ጋር እያቆራኛችሁ የምትውተረተሩ ሁሉ በስደት በመጠላያ ጣቢያ እየተሰቃዩ ያሉ ህፃናት አረጋውያን ህዝቦች ላይ እንዳላገጣችሁ ቁጠሩት የእናንተ ደረቅ የፖለቲካ ትንታና እዛው ይዛችሁት ተቀመጡ።

ከእናንተ በላይ ነገር መሰንጠቅና ፖለቲካን ማመንዠግ ይቻላል ግን እስከመቼ አሁን ይብቃ ይበቃል በእናንተ መቧደን በእናንተ መከፋፈል መሀል መከረኛው ህዝብ ስቃዩ እየተራዘመነ ነው ለዚህ መከረኛ ህዝብ በአንድነት ቆሞ ችግሩ እንዲፈታ ወደ መኖሪያው እንዲመለስ ቢተጋ ይሻላል።

የሸገር ልጅ ነኝ

14 Jan, 06:20


በትግራይ ክልል 2ኛ ቀኑን የያዘው #ይበቃል የተሰኘው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬም እየተካሄደ ነው። ይህ አጀንዳ የመላው ትግራዋይ አጀንዳ ነው የተፈናቀሉት ወደ መኖሪያቸው ይመለሱ በስደት እያሳለፉት የሚገኘው ስቃይና መከራ ሊያበቃ ይገባል ብለው የተነሱ ሰልፈኞች ዛሬም ጎዳናውን ሞልተውታል።

የሸገር ልጅ ነኝ

22 Dec, 19:23


አይምሮዬን የሚፈታተኑኝ ነገሮች በዝተው በነፃነት እንዳልራመድ ሁኛለው የትላንቱ ጥንካሬዬ ከድቶኛል፣ ደክሞኝ ይሁን ሰልችቶኝ አልተረዳሁትም። በአሁኑ ሰዓት እኔ እኔን መሆን አልቻልኩም አንዳንዴ የገጠሙህን ችግሮች መናገር ሲያቅትህ ለካ ከባድ ነው።

ቤተሰቦች በፀሎት አግዙኝ አሸንፌው እወጣ ዘንድ እሻገረው ዘንድ አብራችሁኝ ሁኑ መልካም የሆን ዘንድ ተመኘሁ🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

22 Dec, 14:40


የተሰበረን ነገር ወደ ነበረበት መመለስ ይቸግራል💔

የሸገር ልጅ ነኝ

21 Dec, 17:53


"ታሪኩ ዲሽታ ጊናን" መምረጥ ሰላምን መምረጥ ነው ትላንት በተሰደበበት የሰላም ስብከቱ ዛሬ እጩ ሆኖ ቀርቦበታል ጊዜ እውነትን ይናገራል ትላንት ባጎነበስክበት ዛሬ ቀና ብለህ ትሄድበታለህ ብቻ አንተ እውነትን ተከተል ታሪኩ ድንቅ ሰው ነው።

ሰላም ወዳድ የሆነ ሁሉ ይምረጠው በዚች ሀገር ሰላምን የሚሰብክ ከፍ እንዲል የፈለገ ድምፅ ይስጠው እሱን መምረጥ የፈለገ ማንኛውም ሰው በመልእክት መላኪያው ላይ BIW10 የሚል ጽሁፍ አስፍሮ ወደ 9355 አጭር መልዕክት ይላክ!

ታሪኩ ዲሽታ ጊና የሰላም አምባሳደር ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

21 Dec, 15:35


#ማዕድ ማጋራት በአፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ አቡጃ ከተማ ለመከወን አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በተለያዩ ቤተክርስቲያናት ውስጥ በማሰባሰብ ለመደገፍ የምግብ እህል እየተሰራጨ በነበረበት ሰዓት በተከሰተ ግጭት 65 ሰዎች ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

ይቺ አፍሪካዊት ሀገር በቅርቡ ነፃ ገበያን ፈቅዳ እንደነበር ይታወሳል። ሀገሪቷ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን በኢኮኖሚ መደገፍ ተስኗት ዜጎቿም እራሳቸውን መመገብ ተስኗቸው ይሀው በአደባባይ እህል ዘረፋ ውስጥ ተሰማርተዋል።

ያሳዝናል💔

የሸገር ልጅ ነኝ

21 Dec, 10:21


የአንከር ሚዲያ ባለቤት መሳይ መኮንን ወደ ኤርትራ ገብቶ ጉብኝት እንዲያደርግ ፍቃድ መሰጠቱን ተከትሎ ብዙዎች ከሀዲ ባንዳ እያሉት ይገኛሉ።

ዛሬ ይሄን ግለሰብ ባንዳ የሚሉት ትላንት ኤርትራ ውስጥ ገብቶ ሀገሪቷን ለማተራመስ ዶላሮችን ተቀብሎ በህዝብ ላይ መርዝ ሲረጭ ጀግና ያሉት ናቸው።

በመሰረቱ ይህ ግለሰብ ለገንዘብ ሲል ምንም ያደርጋል ሲበዛ ሆዳምና ጨካኝ ባንዳ ነው። ዛሬ እባብነቱ አደባባይ ወጦ ፀሀይ እየመታው ይገኛል። ጊዜ ደጉ ብዙ ያሳየናል።

የሸገር ልጅ ነኝ

21 Dec, 06:49


በመግለጫ ጋጋታ የተፈታ ህዝባዊ ችግር የለም እታገልለታለሁ መብቱን አስከብርለታለሁ የምትለው ህዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ ዘርፈ ብዙ መከራዎችን እያሳለፈ አንድም ጠብ የሚል ተግባር መከወን አቅቶትህ ህዝብን በሌላ አጀንዳ ማወራከብና በመግለጫ ጋጋታ ጠንካራ መስሎ መታየት ፋሽኑ ያለፈበት ጉዞ ነው።

መለስ ብሎ ተረጋግቶ ለህዝብ ሲባል ቅራኔን ፈቶ ወደ ተግባር መግባት ነው ብልህነት በመሰረታዊነት ለህዝብ የማትጨነቅ ከሆነ ትንንሽ አጀንዳዎች ከህዝብ መሰረታዊ ችግሮች በላይ አግዝፈህ መመልከት ትጀምራለህ። ይህ መሆን እንደሌለበት በተደጋጋሚ ነግረናል የማይታረም ከሆነ ከህዝብ ችግር የሚበልጥ የለምና ከተቸገሩ ህዝቦች ጎን መሰለፍ ይጀመራል።

የሸገር ልጅ ነኝ

19 Dec, 17:31


"ብልፅግናዎች ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሀገርም ይዘው ሊወድቁ ነው" ጃዋር መሀመድ

ቃለ ምልልሱን ተመለከትኩት ጃዋር እያሟሟቀ ያለ ይመስላል።

የሸገር ልጅ ነኝ

17 Dec, 06:13


ከትግራይ አዋጅ ታውጇል📢 "#ታህሳስን_ለፍሬምናጦስ!!"

መላው የሀገሬ ህዝብ ለወገኑ የሚደርስበት ቀን ታውጇል ኢትዮ ቴሌኮም በታህሳስ ወር በተለያዩ ገፆቹ ላይ ለሚደረጉ #ፎሎው #ሼሮች #ሰብስክራይብ በእያንዳንዳቸው ገንዘብ አዘጋጅቶ ለፍሬምናጦስ ለማዋል ቅድመ ዝግጅቱን አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል።

መላው ወገን በፍሬምናጦስ ያሉ ወገኖቹን ለመርዳት በዚህ ላይ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል። ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ይረባረብ። ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር ሼር ይደረግ አወጁን ተቀላቀሉ።https://www.facebook.com/share/p/14F4nCS3zV/

የሸገር ልጅ ነኝ

16 Dec, 14:23


በዚህ ጊዜ እንዲህ አይነት ሰው አለ ገራሚ ነው። ትላንት እሁድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በሆሣዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሠቢያ ሆስፒታል አንድ ጀግና ዶክተር ታሪክ ሰርቷል።

ታሪኩ እንዲህ ነው:- "ዶክተሩ የሰርግ ፕሮግራም መልስ ላይ ነበር አንዲት ወላድ እናት በሞት አፋፍ ላይ ነበረች ይህን መልዕክት ለሙሽራው ዶክተር ደረሰው የሰማው ነገር መልሱን በሰላም ማካሄድ አላስቻለውም ሙሽሪቷንና አጃቢ እንግዶቹን አስፈቅዶ የመልስ ፕሮግራሙን አቋርጠው ወደ ሆስፒታል ከነፈ።

ሁሉን ትቶ ወደ ሆስፒታሉ ያቀናው ዶክተር በሞት አፋፍ ላይ የነበረችውን ወላድ እናት በፈጣሪ እርዳታ ታግዞ የተሣካ ኦፕሬሽን በማድረግ ህይወት ከነህፃኗ ማትረፍ ችለዋል።

ይህ ታላቅ ግሩም ዶክተር ስሙ ዶ.በየነ አበራ ይባላል ታላቅ ምስጋናም ይገባዋል። እንደሱ ያሉትን ለሙያቸው ክብር የሚሰጡ፣ የሰው ህይወት ለማዳን የገቡትን ቃለ-መሃላ የሚጠብቁ፣ በጎ ህልናና መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው ቅኖችን ፈጣሪ አብዝቶ ይጠብቅልን መልካምነት ውድ ናት።

የሸገር ልጅ ነኝ

16 Dec, 07:08


የትግራይ አመራሮች ነገሮችን በእርጋታ መፍታት ባለመቻላቸው ነገሩ እየተወሳሰበ ይገኛል በመቐለ ከተማ ያለው ውጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው። ነገሮችን እየፃፉ እያስረዱ ከመሄድ ተቆጥበን ቆይተናል አሁን ግን ነገሩ እየተበላሸና ህዝብን ሊጎዱ የሚችሉ አካሄዶች ተመራጭ ሆነዋል አመራሩ ህዝቡን ዘንግቷል ለህዝቡ ረፍት መስጠት አልቻለም።

ይህን ደሞ ታግሶ ቸል ብሎ መመልከት አይቻልም።

የሸገር ልጅ ነኝ

12 Dec, 18:09


በጨቅላ አንደበቷ የምትማፀነው ህፃን ተፈናቃይ ነች ተጋሩ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ እየተንከራተት የራሱን ህይወት ገብሮ መሪዎቹን ያተረፈ ትውልድ ቤተሰቡ ወደ መኖሪያው መመለስ ተስኖት ተማፅኖ እያደረገ መሆኑን ቢያውቅ ምን ይል ይሆን🤔

ያ ክንደ ብርቱ ወጣት የTDF ሀይል የት ገብቶ ነው ዲያስፖራውስ ምን ነክቶት ነው። አይበቃም ዝምታው አልበዛም እስከ መቼ ነው ትዕግስትም ገደብ አለው።

የሸገር ልጅ ነኝ

12 Dec, 05:44


ሰላምን የሚያመጡ ስምምነቶች ሁሉ ተወዳጅና ተመራጭ ናቸው ኢትዮጵያ የተደነቀነባትን አደጋ በሰላም ለመወጣት መጣር አለባት ሁሌም አማራጯ ሰላም ሊሆን ይገባል።

በተለይ እንደ ሻዕቢያ ያሉ መዥገር ጎረቤቶች ሲኖሩህ ዙሪያን በእሾህ ለማጠር ስለሚውተረተሩ ከባቢህን ሰላም ለማድረግ መትጋት ይኖርብሃል ድሮም ቢሆን መንግስት የሄደበት ያልተጠና የፖሊስ ጉዞ ነው እዚህ ቅርቃር ውስጥ የከተተው ዞሮ ዞሮ ግን ጦርነት የሚያስቀር ሰላም መመረጡ ጎሽ የሚያስብል ስራ ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

07 Dec, 17:11


በመላ ሀገሪቷ የመብራት መቋረጥ ተከስቷል ችግሩን ለመፍታት መስራቤቱ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሆነ ገልጿል። በምን ምክንያት እንደሆነ ግን ግልፅ አላደረገም።

የሸገር ልጅ ነኝ

07 Dec, 05:15


የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም! ይህ ማለት ግን ሰላምን የማይሰጡ ደጆችን ሰላም ለማግኘት መውተርተርንም ያካትታል ማለት አይደለም። ሰላም በአንድ ወገን ብቻ ፍላጎት የሚሰምርም አይደለም።

ሁሉም ሰላምን አብዝቶ መፈለግ መውደድ አለበት ለአሻጥር ሳይሆን የምር ገብቶን ሰላምን አብዝተን መውደድ አለብን።

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Dec, 19:56


"በትግራይ ክልል ክልላዊ ምርጫ እስኪካሄድ ባላችሁበት ተደምራችሁ ቀጥሉ!!" ፕሬዝዳንት መቀየር ገለመኔ ሚባል ነገር የለም ህወሓት ፕሬዝዳንት የመቀየር ስልጣን የለውም!! ስለ ተፈናቀለው ህዝባችሁ አስቡ አለ አሉ 7ኛው 👑

አይገርምም🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Dec, 19:26


የእኛ ነገር ግሩም ነው 🤔 አርቲስት ማስተዋል ወንድወሰን የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዘዳንት ሆና ተመረጠች አሉ ⚽️ አሁን ኳሳችን ይመነደጋል🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

05 Dec, 15:13


የትግራይ ህዝብ በኢኮኖሚ እንዲደቅ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ በጎረቤት ጠላት ሀገር ስርዓት እንዲገደል እንዲጨፈጨፍ ዙሪያውን ተከቦ እንዲቀጠቀጥ ከዓለም ተነጥሎ ለ3 ዓመት ተከቦ እንዲሰቃይ ከ1ሚሊየን ህዝብ በላይ እንዲገደል ያደረገ ስርዓትና ዋና መሪ ለትግራይ መፍትሄ ይሰጣታል ብሎ እንደመጠበቅ ሞት ከየትም የለም።

የህወሓት አመራሮች በስነልቦና የተጎዳን ህዝብ በኢኮኖሚ እየተሰቃየ ያለ ማህበረሰብ ከመኖሪያ ቤቱ ተሰዶ እየተንከራተተ ያለ ወገንን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ እንዲህ ወርደው ሹመት ፍለጋ ሲንከራተቱ ማየት ያሳፍራል። ቢያውቁት ከውረደት ሞት ህይወቱን ገብሮ ከፍ ያረጋቸው ህዝቡ ነበር።

በዚህ ደረጃ እነሱን ማየት ያሳፍራል🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

04 Dec, 18:34


የህወሓት አመራሮች ትግራይን መምራት ተስኗቸው መፍትሄ ፍለጋ 4 ኪሎ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ናቸው ወቸው ጉድ ይሁን እስኪ ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል🤔 ብቻ ይህ እልፍ መከራዎችን እያሳለፈ ያለ ህዝብ ሰላም ይሁን እንጂ ስለ ሌላው ብዙ አሁን አያሳስበኝም።

የሸገር ልጅ ነኝ

03 Dec, 14:09


የትግራይ ፀጥታ ሀይል አመራር ከፖለቲካ ውዥንብሩ ውጪ ሆኖ ትግራይና ህዝቧን ማረጋጋት ትልቅ ሀላፊነት አለበት። አመራሩ ማዳመጥ ያለበት በመጀመሪያ የህዝቡን ድምፅ ቀጥሎ የሰራዊቱን ድምፅ ነው።

ፖለቲከኞቹ እንዲህ በአንድ ጊዜ ያሳለፉትን መከራ ረስተው ህዝቡ የከፈለውን ዋጋ እና አሁንም እየከፈለ ያለውን መከራ ዘንግተው ማዶ ለማዶ ቁመው ይነታረካሉ ብሎ ያሰበ የለም ግን ሆኖ አይተነዋል።

ስለዚህ የሰራዊት አመራሩ ድርሻ እና ሀላፊነት በከፍተኛ ደረጃ አስፈላጊ ነው ወደዛ ወደዚህ ሳይወዛወዝ ቆፍጠን ብሎ የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ሰላም ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ መራመድ አለበት።

የሸገር ልጅ ነኝ

03 Dec, 04:42


ወልቃይት ፀገዴ ሰቲት ሑመራ እና ዛላንበሳ ኢሮብ ዓሌተና ባድመ ላይ የሚኖር ህዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ በመከራና ስቃይ እየተጓዘ ባለበት በዚህ ሰዓት በመቐለ መከራከር ተገቢ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ ሰው በዚህ አጀንዳ ተጠምዶ ዋነኛው አጀንዳ እንዲዘነጋ እየተደረገ ያለበት መንገድ መረዳት እንዴት ተሳናችሁ።

ተጋሩ ምን እያሰባችሁ ነው እየሆነ ያለው የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ሰላም የሚያረጋግጥ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ቆም ብሎ መነጋገር መምከር ተገቢ ይመስለኛል።

የሸገር ልጅ ነኝ

01 Dec, 17:57


😭

ጌታቸው ረዳ Vs ዶ/ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 💔🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

30 Nov, 10:10


የመደመር ውጤት "ውታፍ ነቃዩን" በፀሎት ላይ 😜

የሸገር ልጅ ነኝ

30 Nov, 08:26


እንኳን አደረሳችሁ

እንኳን ለዚህ አበቃችሁ፣ ሰላማችሁን ታብዛላችሁ፣ ፀሎታችሁ ትስማላችሁ፣ በቃችሁ ትበለን ታስታርቀን ይቅርም ትበለን🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

29 Nov, 08:47


ታላቋ አክሱም ፅዮን ደጅ ደማቸው እንደ ጎርፍ የፈሰሱ ንፁሃንን በመዘከር ዛሬ የደብሩ ካህናት ምዕመናን በአደባባይ ተገናኝተዋል። ያን ፀያፍ ነውር በወቅቱ የካዱ ጳጳሳትና መነኮሳት ዛሬ ምን ይሰማቸው ይሆን?😡 አላውቅም🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Nov, 17:29


ህዳር 19 በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ በታቦተ ፅዮን ደጅ የተጨፈጨፉ ንፁሃንን ለመዘከር ህዝቡ በነቂስ ወጦ የጧፍ ማብራት ፕሮግራም አካሄዷል። ይህ ነውር እንዳይደገም በነውር ሲታወስ ይኖራል😭🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Nov, 16:58


መቼም አይረሳም አይደገምም😭

የሸገር ልጅ ነኝ

27 Nov, 11:51


ገራሚ ትውልድ ነው። ትላንት የትግራይ ህዝብ ላይ መከራ እንዲቀጥል እንደ ተቋም ሲደግፍ የነበረ ቡድን ዛሬ ተጋሩ ፊት ስለ ከፍታ ሊናገር ቀጠሮ ይዣለሁ ይለናል። በእርግጥ ለስብከት እንዳልሆነ ለሌላ ተልዕኮ እንደተዘጋጁ እሙን ቢሆንም ይጥፋ ብለው በፈረዱበት ህዝብ ፊት ያለ ህፍረት ለመቆም መወሰናቸውን ግን የንቀታቸውን ጥግ ያሳያል😡

የሸገር ልጅ ነኝ

26 Nov, 17:27


ተጀመረ🙏

ትግራዋይ የተለመደ ክቡር እንግዳ ተቀባይነቱን ዛሬም ሳይሸራረፍ መተግበር ጀመረ ለሕዳር ፅዮን በዓል የተገኙ ምዕመናንን የመቐለ ደብረሰላም ቅዱስ ሚካኤል ኣብርሃም ሰ/ት/ቤት አባላት እግር በማጠብ ተቀብለዋል ነገም ከነገ ወዲያም እስከ በዓሉ ክብረ በዓል የሚገኙ ምዕመናንን በዚህ መልኩ አቀባበሉ ይቀጥላል።

የሸገር ልጅ ነኝ

20 Nov, 18:39


ካሳዬ ጨመዳ የጀመረው ነውር ዛሬ አድጎ እዚህ ደርሷል የትግራይን ህዝብ አጋንት ብለው በመፈረጅ በጦርነቱ ወቅት ለገዳዮች ስትተኩሱ ክርስቲያን ከሆናችሁ በስመአብ ሙስሊም ከሆናችሁ ቢስሚላህ ብላችሁ ተኩሱ ብለው በህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ሲያወጁ የነበረው ጭብጨባ ያሳቅቅ ነበር።

ዛሬ ደሞ ጋ* ነው በስመአብ ብለህ እረደው ተብሎ ሲፈፀም አየን አንዳንዱ ይሄን ነውር አሻጥር ነው ብሎ ወገቡን ይዞ ሲከራከር ታያለህ። እንዲህ ያለውን ነውር አስቀድመን ብናወግዘው ኑሮ እዚህም ባልተዳረሰ ነበር።

እዚህ ሀገር ያለው ክፋት ሀይማኖተኛ ነኝ በሚለው ሀይል የሚፈፀም መሆኑ ነው ሀይማኖተኛ በስመአብ ቢስሚላህ እያለ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሚያርድ ከሆነ ነገርየው አብቅቷል ማለት ነው።

እኔ የምፈራው ነገን ነው። ሰዎች እንረጋጋ🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

20 Nov, 02:55


አወይ ግፋችን አወይ ጭካኔአችን አረ ጎበዝ ኡ ኡ እንበል በእውነት በሰላሌ የሆነው ያማል በእርግጥ ላለፉት ዓመታት ካየነው ጭካኔ የተለየ አይደለም እኛ ሀገር ሰው በማንነቱ የተነሳ በቁሙ ከእነህይወቱ በእሳት ተጥሎ ሲቃጠል አይተናል ተዘቅዝቆ ሲሰቀልም ተመልክተናል በድንጋይ ተወግሮ ሲገደልም ታዝበናል ብዙ ግፍ እዚህ ሀገር ተፈፅሟል።

ዛሬ እንደ ትላንቱ ሰው በማንነቱ ምክንያት በስመአብ ተብሎ እንደ በግ ሲታረድ በድጋሚ ተመለከትን😭 እንዲህ ያለ ነውር እንዲህ ያለ ግፍ እራስ በራሳችን ላይ እየፈፀምን እስከመቼ እንዛለቃለን።

ከበደሉ በላይ ይሄን አፀያፊ ተግባር በጋራ አለማውገዛችን የበለጠ ያማል ያኔም ሲፈፀም እሰይ ዛሬም እሰይ ነገ ደሞ ሌላው ላይ ሲፈፀም ሌላው እሰይ እየተባባልን እየተራረድን ልንጓዝ ነው ወይ? አረ ፈጣሪ ሆይ ተመልከተን🙏 በእውነት ያማል😭

የሸገር ልጅ ነኝ

19 Nov, 11:48


ይሁን መልካም ይሁን! የትግራይን ህዝብ ሁሉም ሊያጠፋ ተነስቷል አብዛኛው ተሳታፊ ሆንዋል አንዱ ከአንዱ ፈፅሞ መለየት በማይቻልበት ደረጃ ብዙ ነውር ተከውኗል የሀገሬው አብዛኛው ህዝብ የዚህ ነውር ጥፋት አካል ሆንዋል በአጭር አማርኛ የሁሉም ጭምብል ተገልጧል።

የተፈፀመው ልብ ሰባሪ ተግባር መቼም አይረሳም። አይረሳም ማለት ቂም ቋጥረህ ትኖራለህ ማለት አይደለም የተፈፀመው ነውር እንዳይደገም ስህተትህን አርመህ ጠንካራ ስራዎችን ትሰራለህ። ለህዝብህ መልካም ይሆን ዘንድ ከፊት ለፊትህ ሰላምና ሰላምን ብቻ አስቀድመህ ትወያያለህ ያ መልካም ይሆናል ያ ለህዝብ ጠቃሚ ነው።

የትግራይ ህዝብ እያረገው ያለው ይህን ነው መሆንም ያለበት ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

18 Nov, 10:16


መርካቶ አድማ ላይ ነች🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

18 Nov, 04:16


አክሱም ከፊት ለፊቷ የሚጠብቃት ልዩ በዓል አለ እመቤታችን ፅዩን ማርያም በህዳር 21 በልዩ ሁናቴ በክብር ትነግሳለች እግዶች ከተለያየ ቦታ እዛ ይገኛሉ ህዝቧ እንደተለመደው የእግዶችን እግር እያጠበ በክብር ይቀበላል። ይህ በዓል በታላቅ ድምቀት እንዳይከበር የተለያዩ አቧራዎች በሶሻል ሚዲያው ተነስተዋል።

በመጀመሪያ አባታችን አቡነ ማቲያስ አይሄዱም የሚል ግርግር በመፍጠር ምዕመኑ እንዲቀር ተጀመረ አሁን ደሞ በአክሱም የመሳሪያ ተኩስ አለ ትግራይ ውጥረት ላይ ነች የሚል ወሬ ተነዛ ነገም ሌላ ይቀጥላል ሁሉም ግን ግባቸው አንድ ነው። አክሱም ፅዩን ክብረ በዓል እንዳይደምቅ እንዳይከብር ማረግ ከእሷ ጋር ያላቸው ቅናት ገራሚ ነው ለነገሩ ሰይጣን አድራሻ አይሳሳትም አይደል የሚባለው እውነት ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

16 Nov, 17:23


አይ ፋሲል ትላንት ለሙገሳ ለልገሳ ማንም እንዳይቀድመኝ እያልክ አንበሶችዬ እያልክ ያደለብከው ሀይል እኮ ነው ዛሬ ሽልማት እየተጎናፀፈ ያለው ያንተ የተዛባና የከረፋ ጥላቻ ቅስቀሳ ፍሬ አፍርቶ ነው ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ የደረስነው አሁን እየዬ ብትል የሚሰማህ የለም መቻል ነው ወዳጄ🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

15 Nov, 03:20


ጊዜው አሁን ነው! የአክሱሟ ፅዮንን ይቅርታ የምንጠይቅበት አባቶች ተንብርክከው የሚማፀኑበት ጊዜው አሁን ነው። አንዳንዶች አባታችን አቡነ ማቲያስ ወደ አክሱም አይጓዙም እያሉ በደስታ ሲዘግቡ ተመለከትኩ እኔ ግን ይህ ጉዞ አዋጪ አለመሆኑ ይታየኛል።

በአክሱም ፅዮን ደጅ ብዙ ነውራት ተፈፅመዋል አባቶች በወቅቱ ሃሰት ብለው የተፈፀመውን ነውር ደብቀዋል ግን ከልብ የሆነ ይቅርታ ፀፀት ያሻግራል ቅዱሳን አበው አባቶቻችን ደፍረው እያነቡ በደጇ ተገኝተው ይቅርታን ሊማፀኑ ይገባል ያለ አክሱም ፅዩን ጉዞ የለም በእሷ ደጅ የፈሰሰው የንፁሃን ደም ዋጋ አስከፍሏል እያስከፈለንም ይገኛል።

አሁን ጊዜው ነው ሳይብስ መከራው ሳይራዘም ይቅርታ ልንባባልበት ይገባል አባቶቼ ሆይ ሚስጥሩን እያወቃችሁ ያለ እሷ መባረክ እንደሌለ እየተረዳችሁ አትዘናጉ የመከራውን ጊዜ አታራዝሙ እናታችን ፅዮን ሆይ ማሪን ብላችሁ አስምሩ🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

10 Nov, 17:09


እንኳን ለቤትህ አበቃህ🙏

የአቶ ልደቱ አያሌው መልዕክት:– በጭንቀት ላይ ለሰነበታችሁ ዘመድ ወዳጆቸ እና የትግል አጋሮቸ በሙሉ።ለገጠመኝ የጤና ችግር ከአንድ ቀን በፊት የተካሄደልኝ የቀዶ ጥገና ህክምና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ አሁን ላይ ጤናየ በጥሩ ሁኔታ ስለሚገኝም ከሆስፒታል ወጥቸ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ።

ስለ ደህንነቴ ተጨንቃችሁ በፀሎትና በሀሳብ ስታግዙኝ ለሰነበታችሁ ወዳጅ ዘመዶቸ በሙሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። አሁን ረዥም ጊዜ የፈጀው የህክምናየ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ስለሆነም ወደ አገሬ ተመልሸ ለመሄድ የነበረኝ ከፍተኛ ፍላጐትና ጉጉት ዕውን ሊሆን በመቃረቡ ደስ ብሎኛል።

ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው

የሸገር ልጅ ነኝ

03 Nov, 03:47


ይሄ ልጅ ከደፋሪው በላይ ነው አጠገቡ ያላችሁ ሴቶች ተጠንቀቁት ምን አይነት ዘመን ላይ ነው የደረስነው ጎበዝ እንዴት ይሄን ነውር በአደባባይ ትደግፋለህ??

እናትህ እህት ብታየው ሚስትህ ወይም ፍቅረኛህ ብታነበው ምን ትል ይሆን? የትግራይ ህዝብ ትላንት የመከራ መዓት ስለወረደበት ይቺ አታጋኗት ምን አላት ነው አባባሉ ምንድን ነው።

በነገራችን ላይ እንዲህ ያሉ የወረዱ አስተሳሰቦችን መታገል ካልተቻለ ጥፋቱ ቀጣይነት አለው ይሄም ቀጣይ ገዳይ ሊሆን ይችላል አስቀድሞ መጠንቀቁ አይከፋም።

የሸገር ልጅ ነኝ

02 Nov, 17:43


💔በቃ አሁናዊዋ ኢትዮጵያ ይቺ ናት በትክክል ዜጎቿ የተቸገሩባት የተማሩ ስራ ያጡባት ኢኮኖሚ ያደቀቃቸው የጠወለጉ ፊቶች የሚታዩባት ነች። በቃ ሀገሬ ይቺ ናት💔

የሸገር ልጅ ነኝ

02 Nov, 16:22


ሁሉም ትግራዋይ በአንድ ቋንቋ በአንድ አስተሳሰብ ውስጥ ሆኖ ይሄ ነውር እንዲወገድ ሊተጋ ይገባል። በክልሉ አሁን እጅግ ተባብሰው የወጡ እነዚህ ፀያፍ ተግባራትን በቸልታ ማሳለፍ ፈፅሞ አይኖርበትም።
:
ከሶሻል ሚዲያ የጋራ እንቅስቃሴ በተጨማሪ በከተሞች የሚደረግ መጠነ ሰፊ መድረኮች ንቅናቄዎች ሊፈጠሩ ይገባል። እህቴ በሀገሯ በሰላም የመኖር መብቷ ሊረጋገጥ ሁሉም ከጎኗ ሆነው ሊያሳይዋት የግድ ይላል።
:
ጊዜያዊ አስተዳደር የፍትህ አካላትም በሚዲያ ወጠው ይህን ድርጊ ከማውገዝ ጀምሮ ወንጀለኞችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ፈጣን ተግባር ውስጥ ሊገቡ ይገባል።

የሸገር ልጅ ነኝ

02 Nov, 05:31


በጦርነት ሊያጠፏት ተነሱ አልተቻለም በአውራጃነት ከፋፍለው ህዝቧን አባልተው ሊበታትኗት ሞከሩ እሱም ከሸፈ ዛሬ ደሞ የሀይማኖት ካርድ መዘዋል። እንግዲህ ወዳጅ የሆኗት መች እንደሚቀየሩባት ግራ የምታጋባው ትግራይ የጉዞዋ ጥንካሬ የብዙሃኑን ጭንብል እያስወለቀ ቀጥሏል።

በትግሉ ወቅት የትግራይ ወዳጅ የነበረው ይህ የፖለቲካ አረዳዱ የተሻለ የሚባለው ግለሰብ በዚህ ደረጃ ወርዶ እርቁ ላይ የሙስሊም ተወካይ የለም በማለት ነገርየውን ለማጣጣል የሄደበት ርቀት አግራሞትን ፈጥሮብኛል።

የሸገር ልጅ ነኝ

01 Nov, 14:57


"ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ" የሚለውን መዝሙር አስታወሰኝ። ዛሬ ከመቐለ ሰማይ ስር የተሰማው መልካም ዜና ምቾት ያልሰጣቸው አንዳንድ አካላት ስድቧን እየጀመሯት ነው።

"ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል" ትል ነበር አያቴ እነዚህ ሰዎች በትግራይ ሰላም ሲሰፍን ምቾት አይሰማቸውም ያቁነጠንጣቸዋል። ከእነዚህ መሀል አንዱ ግዕዝ ሚዲያ የሚባለው የእፉኝት ልጅ ነው። ትላንት ጌችዋ ሲል ከርሞ ዛሬ እንካ ቅመስ ለምን ታረቁ እኮ ነው አይገርምም ጎበዝ🤔

የሸገር ልጅ ነኝ

01 Nov, 08:55


ዛሬ በመቐለ መልካም ሆነ🙏

ህዝቡ ሰላም የሚሰጥ መነጋገር ሁሉ መልካም ነው።

የሸገር ልጅ ነኝ

31 Oct, 18:11


#ሼር በማድረግ ወንጀለኛው እንዲያዝ ተባበሩን🙏

ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ እህታችንን ገድሎ ተሰውሯል የተባለው ተጠርጣሪ አዳማ ከተማ አካባቢ ታይቷል የሚባለ መረጃ አለ። እዛ አካባቢ ከታየ ወደ አዲስ አበባ እና አቅራቢያ አካባቢዎች ሊንቀሳቀስ ስለሚችል በተቻለ መጠን ትብብራችሁ አይለየን።

በተለይ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ወጣቶች ማህነረሰብ በሙሉ ይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት ተጠርጣሪ ከተመለከታችሁ ለህግ አካላት በመጠቆም እንድትተባበሩን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን 🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

31 Oct, 13:17


በትግራይ ምድር ሴቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት እጅግ አሳሳቢ ሆንዋል። ይህ ግድያ አፈና ተግባር በቸልታ ሊታይ አይገባም መላው ተጋሩ ሊፈትሸው ሊያየው ሊመለከተው ሊነጋገርበት የሚገባ ጉዳይ ነው።
https://youtu.be/-aTlWCJgnkc?si=D5kslO8qCLg1r_o3

የሸገር ልጅ ነኝ

31 Oct, 06:01


የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት ሻዕቢያ ነው አሁን የተሰማው ዜና ደሞ የሻዕቢያ መንግስት የአየር ክልሉን መዝጋቱ ነው። 🤔

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሏን የኤርትራ እና የሶማሊያ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦችን ሻንጣ ጥሎብናል በሚል ክስ መስርቻለሁ ማለቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ማቆሙ ይታወሳል።

አየር መንገዱ በኤርትራ የሚገኘውን ገንዘቡን ማንቀሳቀስ እንዳይችል መደረጉንም መግለፁ ይታወሳል። ዛሬ ደሞ የአየር ክልሌን ዘግቻለሁ እያለ ይገኛል። በመሰረቱ ሻዕቢያ የኢትዮጵያን እድገት የማይመኝ ቀንደኛ ጠላት መሆኑ ድሮም ይታወቃል።

የሸገር ልጅ ነኝ

29 Oct, 18:02


"ተቀራርቦ መነጋገርን የመሰለ ነገር የለም" ጌታቸው ረዳ

ይሄን ስንሰማ ፎቶውንም ስንመለከት ደስ ብሎናል መጨረሻው ያሳምረው ብለን መርቀናል ምክሩ ተመካከሩ ተስማሙ ህዝቡንም ረፍት ስጡት እንላለን👌

የሸገር ልጅ ነኝ

29 Oct, 15:52


ሰዳቢውም እሱ መካሪውም እሱ 🤔

ከፋፋይ የሆነ ስድብ ትርክት ተረት ሽሙጥ ቧልት እያመጣ ሁሉንም የሀገሬው ሰው የሚቧጭረው እሱ ነው። አንድ እንሁን ብሎ መምህር ሆኖ የቀረበውም እሱ ነው። እንዴት ነው ጎበዝ🙄

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Oct, 17:32


የሀገራችን ፈተና መከራው በዝቷል😭

በድሬደዋ እና ሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን መካከል ተፈጥሮ የነበረውን እሳት መቆጣጠር ቢቻልም የባቡር አገልግሎቱ መቋረጡ ግን ታውቋል። አገልግሎቱን ለማስጀመር ሰፊ ርብብርብ እየተደረገ እንደሆነም ተሰምቷል።

ይቺ ሀገር መከራዋና ምልክቷ በዝቷል ምዕመኑ ልግጫውን ተያይዞታል ወደ ፈጣሪ አቤት የሚል ጠፍቷል🙏🙏

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Oct, 17:18


https://youtu.be/YJqsgTo-Hkw?si=4JJtwucFGUkUuEvE

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Oct, 06:48


የትግራይ ፀጥታ ሀይል መግለጫ ሰጧል።

በመግለጫው በኣሰና ቴሌቭዥን ጣቢያ በሰበር ዜና የተላለፈው ትርኪ ምርኪ ወሬ እርባና ቢስና ትግራይንና የፀጥታ ሀይሉን የማይገልፀ ሀሰተኛ ወሬ ነው። የትግራይ ፀጥታ ሀይል ፖለቲከኞች ውስጣዊ ችግራቸውን በሰላማዊ እና በፖለቲካዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ይሄንንም እንደሚደግፍ ገልፆ።

ከዚህ ውጪ ያሉ ፕሮፖጋንዳዎች በሙሉ ትግራይ ለመረበሽ በተጠናና በታቀደ መልኩ የሚፈፀም የጠላት ወሬ ነው ሲል አሳስቧል። ለትግራይና ለህዝቧ ሰላም የፀጥታ ሀይሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አስምሮበታል።

የሸገር ልጅ ነኝ

28 Oct, 04:54


ከፍተኛ ጉጉት አለ🤔

በትግራይ ምድር ሰበር ዜና ለመስራት ከፍተኛ ጉጉት አለ ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እንዲህ ተደረገ ሆነ ጌታቸው ረዳ እንዲህ ሆነ ተደረገ ብሎ ዜና የመስራት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ስለ ትግራይ ጄነራሎች ወሬ ፍለጋ ሁሉም ይማስናል ጋዜጠኞች ጭምር ቅዠት ጀምረዋል።

ሁሉም ነገር ድፍንፍን ብሎባቸዋል።