ye allah baroche @yealahbarochh Channel on Telegram

ye allah baroche

@yealahbarochh


ወደ አላህ ከትጠራና መልካምንም ከሰራ፣ <<እኔ ከሙስሊሞች ነኝ >> ካለም ሰው ይበለጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

ye allah baroche (Amharic)

የአላህ ባሮች (ye allah baroche) በትጠራላቸውና በመልካም መገናኛዎቻቸው ላይ እየሆነ በመሆኑ የተገኙበት ቻናል ነው። የትጠራቸው አላህን እና በመገናኛዎቻቸው የሚከታተለውን መስራት እንዴት መንክር ይችላሉ። በእነዚህ ትጠራቸውና መልካም መገናኛዎቻቸው እንዴት በአላህ የተጠናቀቀ ወንጀላዊ ተመሳሳይ እና ተናጋሪ የነበረውን መረጃ ይበልጣል። ለምሳሌ የባሮች በምስሊሞች መካከል ታሳልፈዋል። እስካሁን የትጠራና መልካም መገናኛዎች ጠንካሮች ያልተሞሉትን ቦታዎች ማሳካት ይጠቀሙ። በምሳሌ ስለ ያማር የመስህት ግንባታ እና ሰነዳዎች ስንት ጊዜ እንልካለን? ለትጠርም ካልተጠናቀቀበት በኋላ ወሬ ዓለም ዋና ህይወቴ የማይቆም እለመዳለሁ። ከእረኛ እና ከነበረው ወንጀላ ወገንዋ u2013 በአላህ ባሮች!

ye allah baroche

21 Nov, 19:22


ለይል ሶላት ላይ ነፍስህን ስትዳከም ካየህ
ፊርደውሰል አእላ የሚገኘው ብዙ ሱጁድ ባደረገ መሆኑን ንገራት
የለይል ሶላትህ በጨለማው ቀብርህ ላይ ብርሀን ነው ። አላህ በዛ ሰዓት ወደ ምድር ይወርድና ዱዓህን ይሰማሀል ይቀበልሀል እድሉን ተጠቀምበት!

ye allah baroche

21 Nov, 19:21


አላሁመ ባወኩህ ልክ ወደድኩህ
ያረብ እኔን  በቸርነትህ ልክ ውደደኝ
ከማይቀንሰው ንግስናህ  ከሀብትህ ላይ ሪዝቅ ስጠኝ
ትግስት ማድረግ ባልቻልኩት ነገር ላይ ትግስት አርጌለሁና ከደም ስሮቼና ከአለም በላይ ለኔ ቅርብ ነህና ልቤ የሚያስፈልገውን ስጠኝ

አንተም "ጠይቁኝ እሰጣቹሀለሁ "ብለህ የለ!

ye allah baroche

21 Nov, 19:20


አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ካልፈቀደልህ በስተቀር
እሱን ማስታወስ እንደማትችል ታቃላህ ወይ?

ራስህን አላህ እያስታወስክ ከተመለከትከው
ከባሪያወቹ አንተን እንደመረጠህ
ባንተ ላይ የማይዘጋብህን በር እንደከፈተልህ እወቅ ። አላህን አመስግነህ እድሉን ተጠቀምበት አላህም እሱን ብቻ እንድታስታውሰው አላደረገም ፊልመለኢል አእላ ያስታውስሀል ።

ye allah baroche

21 Nov, 17:22


አላህ ጋር ብቻህን ስትሆን
አይኖችህ በእንባ ሞልተው ቢፈሱ ቃሎችህ ቢንተባተብ  አትፈር ።
በአላህ እጆች ስር ደካማ መሆን ክብርና ጥንካሬ ነው ።

ye allah baroche

21 Nov, 17:21


በአላህ እጆች ስር በተቀመጥክ ጊዜ
የህፃናት ባህሪ አሳይ
ህፃን የሆነ ነገር ፈልጎ ካልተሰጠው እስከሚሰጠው ያለቅሳል!😥

ye allah baroche

21 Nov, 17:20


በሁለት ፀጋወች መሀል ነኝ
የትኛው የተሻለ እንደሆነ አላቅም
አላህ የደበቀልኝ ወንጀሎቼ ማንም የማያነውረኝ
በባሪያወቹ ልቦች ላይ ያስገባልኝ ውዴታ ስራወቼ የማይደርሱበት

ye allah baroche

21 Nov, 16:46


መመለሻ ሁሉ ወደ አምላክ ነው

🎙 ኡስታዝ ፈትሒ ዒዘዲን ባሻ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
  ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------

ye allah baroche

21 Nov, 11:04


ኢዝቲግፋር 2

አስኮ ሰላም መስጊድ ኹጥባ

🎙 ሸይኽ ሙሐመድ ሙስጠፋ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------

ye allah baroche

19 Nov, 18:55


አንዷ የባሎን እዝነት ስትገልፅ

የሆነ ጊዜ በጣም አዝኜ በነበረበት ሰአት ባሌን እሱን ማየት እንደማልፈልግ ነገርኩት
ማብራቱን አጠፍና አጠገቤ ቆየ!

ye allah baroche

19 Nov, 17:05


የድብቅ ወንጀሎች ...

ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ

ye allah baroche

19 Nov, 17:05


ነሲሓ ቲቪ እና አፍሪካ ቲቪ በጋራ...


#አፍሪካ_ቲቪ1
#ነሲሓ_ቲቪ

ye allah baroche

19 Nov, 13:21


የሁለት ደካማ ፍጡራንን ሀቅ የማያከብር

🎙 ኡስታዝ ሱለይማን ዓብደላ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------

ye allah baroche

19 Nov, 11:03


☞:::::::ወድሜ ሆይ::::☜

#የሴት ልጅ ሀዘን በጣም
ጥልቅ ነውና‥ የእናትህን ልብ
በጎጂ ንግግሮች አትስበር!
- የሚስትህን ቅስም ችላ በማለት አትስበር!
- የእህትህን ሞራል በቀልድም ቢሆን አትግደል!
- የልጅህን ልብ በቁጣ አታውልቅ!
⇘ ወደነርሱ ቅረብ ላንተ እዝነት ናቸውና!

       

ye allah baroche

19 Nov, 11:02


እነሆ ዛሬም ሌላ እድል፣ እነሆ ሌላ ተጨማሪ የመኖር ተስፋ••• አልሀምዱሊሏህ እልፍ ምሥጋና ይገባሓል።

ምሥጋናህን በሶላት፣ በሱጁድ፣ በኢስቲግፋር... አካበው። አልሀምዱሊሏህ•••

#የፈጅርሶላትን_በመስጂድ

ye allah baroche

19 Nov, 10:21


እነሱን ለመጠየቅ ስንመጣ
እንዲህ ነው የሚመለከቱን...🙌😂

ye allah baroche

19 Nov, 10:19


ከቂያማ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸዉ፦

1 ዝሙት ይስፋፋል

2 ወንዶች ሀር ይለብሳሉ

3 ሙዚቃ እንደሚፈቀድ ይነገራል 

4 ሴቶች ዘፋኞች በአጫዋችነት ይያዛሉ

5 መጥፎ ቃላቶችንመለዋወጥ ይበዛል

6 ዝምድናን መቁረጥ ይበረክታል

7 ታማኝ ሰዉን እንደ ከዳተኛ መቁጠር እና መወንጀል

8 ከዳተኛን ማገዝ እና ማቅረብ

9 ድንገተኛ ሞት መከሰት

10 መስጅድን እንደ መተላለፊያ መንገድ መጠቀም

11 ጥሪያቸዉ ወይም ተልእኮአቸዉ ተመሳሳይ የሆነ ሁለት ቡድኖች ይፋ ጦር ይማዘዛሉ(የአልይ ና የሙአዉያዉጊያን ያመለክታሉ

12 የዘመን መቀራረብ ወይም የጊዜ መፍጠን (በረካ ማጣት)

13 ፈተናዎች ይደራርሳሉ ፣ተንኮል ይስፋፋል

14 ኢልም ከህፃናት ይፈለጋል

15 የመሬት መንቀጥቀጥ

16 ሰዉነታቸዉን አግባብ ባለዉ ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች ይበዛሉ

17 እዉቀት የሌላቸዉ ሰዎች ህዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወስናሉ

18 ሰላምታ በትዉዉቅ ላይ ብቻ ይመሰረታል

19 ዉሸት መናገር ይስፋፋል::

20 የንግድ ቤቶች ተቀራርበዉ ይገነባሉ።

21 ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ግመሎች ና ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ቤቶች ይገነባሉ። ማለትም 1 አንድ ሰዉ ከሚጠቀምባቸዉ ዉጭ ያሉ ግመሎች በስድ ሲለቀቁ ሰይጣን ይጋልባቸዋል። 2 ከመኖሪያ ቤት ዉጭ ያሉ ትርፍ ቤቶች ለረጅም ጊዜ ሰዉ ሳይገባባቸዉ ከቆዩ የሰይጣን መኖሪያ ይሆናል።

22 ሰዎች በመስጊድ ዉበት ይፎካከራሉ_በዉስጡ ይመፃደቃሉ።

23 ሺበታቸዉን በጥቁር ቀለም የሚያጠቁሩ ሰዎች ይመጣሉ። እነዚህ ሰዎች የጀነትን ሽታ እንኮአን አያገኙም።

24 ሰዎች አላህን የመታዘዝ ባህሪያቸዉ ይመነምናል።ለአኬራ መስራትም ይቀንሳል።

25 ስስት ይስፋፋል፣ሁሉም ሰዉ ግለኛ ይሆናል፣አዋቂ እዉቀቱን ለማካፈል ይሳሳል።

26 ሰዎች አላማዉን በማያዉቁት ዉጊያ ዉስጥ ይሳተፋሉ (ይጋደላሉ።)"ነፍሴ በእጁ በሆነዉ ጌታ እምላለሁ በሰዎች ላይ ይህ ዘመን ይመጣል።ገዳይ በምን ምክንያት እንደገደለ አያዉቅም-ተገዳይ በምን ምክንያት እንደተገደለ አያዉቅም።

" 27 የህዝብ ገንዘብ ያለ አግባብ ይመዘበራል።

28 አማና (ታማኝነት) ይጎአደላል።

29 ባል ሚስቱን እየታዘዘ እናቱን ይበድላል።

30 በአባቶች ላይ እየተፌዘ (አባት ሳይከበር) ጎአደኛ ይከበራል።

31 በመስጅድ ዉስጥ ጩሀት ይበራከታል።

32 ተንኮሉ ተፈርቶ ሰዉ ይከበራል-ችሎታና ስነ-ምግር ግን የለዉም።

33 ፖሊስ ይበዛል፤ይህም ማለት ወንጀል መበራከቱን ያመለክታል።

34 አንድ ሰዉ በእዉቀቱ አናሳ ሆኖ እና በባህሪዉም ገና ያልተገራ ሆኖ ሳለ ድምፁ የሚያምር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ሶላት እንዲመራ (እንዲያሰግድ) ይደረጋል።

35 ሚስት ባሏን በንግድ እና በስራ ላይ ትጋራለች።

36 ብእር ይበራከታል፤ድርሰት እና ህትመት ይስፋፋል።

37 ልጅ መመኪያ መሆኑ ቀርቶ መተከዣ እና መቆጫ ይሆናል።

38 የዝናብ እጥረት ይስተዋላል።

39 መኪና ይፈለሰፋል። "ከኡመቶቼ መካከል ወደመጨረሻዉ የሚመጡት 'ሱሩጅ ወይም (መኪና) ላይ ይሳፈራሉ። የመጎጎዣ አይነት ነዉ በመስጅድ በሮች ያቆሙታል (ይወርዳሉ) ሴቶቻቸዉ ግን የለባሽ እርቃን ናቸዉ።

40 ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት።

41 ኢራቅ ማእቀብ ይጣልባታል-ምግብናእርዳታ ትከለከላለች።

42 በመቀጠልም ሻም (ሶሪያ፣ሊባኖስ፣ዩርዳኖስ እና ፍልስጤም) ምግብና እርዳታ ይከለከላሉ ማእቀብ ይጣልባቸዋል።

43 የነብዩ ሙሀመድ (ሶ.አ.ወ) ከዚህ አለም በሞት መለየት እንደ አንድ የቂያማ ቀንመድረስ ምልክት ተወስዷል።

44 በይተል መቅደስ (እየሩሳሌም) በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር መግባት።

45 በጅምላ ጨራሽ በሽታም ሆነ ጦርነት የሰዉ ህይወት መጥፋት።

46 ሙስና፣ማጭበርበር እናየ ዋጋ ንረት እያየለ መምጣት።

47 በአረቦችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ቤት ዉስጥ ጣልቃ ገብነት እና ፊትና (መከራ) ይስተዋላል።

48 በሙስሊሞች እና በሮማዉያን(አዉሮፓ እና አሜሪካ) የጋራ ስምምነት ይፈረማል።

አዉፍ ኢብን ማሊክ (ረ.አ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.አ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ የቂያማ ቀን ከመድረሱ በፊት ስድስት ነገሮች ይከሰታሉ፥

1 የኔሞት።
2 ከዚያም በይተልመቅዲስ ይከፈታል።
3 ከዚያም ሁለት ሞት እዉን ይሆናል።
4 አንድ ሰዉ መቶ ዲናር ቢሰጠዉ እንኳን ምንም አይመስለዉም።
5 ከዚያ በሁላ ደግሞ ፊትና ይከሰታል።

6 ከዚያም በናንተና በነጮች መካከል ስምምነት ይኖራል። ይከዷችሁል ። 80 አላማ ይዘዉ ይመጣሉ እያንዳንዱ አላማ ደግሞ 12 ሺህ (ንኡስ አላማ) አለዉ።

ያአላህ እዘንልን ከምናውቀውም ከማናውቀውም ፊትና ጠብቀን በዲናች አትፈትነን በዲናችን ላይ የመጣውን ፊትና አንሳልን ያረብ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ye allah baroche

19 Nov, 10:18


ታዳጊው ቃሪዕ 😍
ዳኞቹን አጂብ ያስባለ ሴኔጋላዊ ታዳጊ በመሆኑም ሸይኹ በመገረም የዚህን ታዳጊ ጭንቅላት መሳም እፈልጋለሁ በማለት ከመድረኩ ወርደው የህፃኑን ራስ ስመውታል። ሸይኹም “...ሂፍዙ ጠንካራ ሀርፎች የተፍታቱ እና ግልፅ የሆኑ በማለት አሞካሽታውታል።”
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!

ye allah baroche

19 Nov, 06:57


ቆንጆ መሆኗን «በምን አወክ?!»
ሲሉት «ኒቃቢስት» ነች አለ!!

ye allah baroche

18 Nov, 17:57


የሰው ልጅ ልክ እንደ ሳንቲም ሁለት ፊት ሲኖረው በሰዎች ኪስ ውስጥ ከአንዱ ወደ አንዱ እየተገለባበጠ ይኖራል።