Sewasew - ሰዋስው @ye_sewasew Channel on Telegram

Sewasew - ሰዋስው

@ye_sewasew


The indigenous knowledge platform — https://www.sewasew.com

Sewasew - ሰዋስው (Amharic)

ሰዋስው - Sewasew ለሁሉም አዳዲስ ምሽትና ገጽ የሚሰራ ረቂቅ ቴሌግራም ቻናል ነፃ የሆነ ነው። ስለሆነ ይህ ቴሌግራም ቻናል ሚዲያዎችን እና ቴሌግራሞችን ለመከባበር እና ምክንያት እንዴት ላያመልጣል። ማንኛውንም ውርስ እና አስካሎን እና መረጃ የቅናሽ ፎቶዎችንም ለማነጋገር እንዴት ነው እንግዳ። ምስል በተጨማሪ መለያ ሊጠቀም፣ በሳህን በሆነ እና በሁሉም ቅናሽ ተጭነጠቅ ሰኞ እና አርብ ከምሽት 6-8 ሰዓት እንዲሰጥ ቻናል በተገናኘ ሁኔታዎች ላይታ ቀረብ ።

Sewasew - ሰዋስው

25 Aug, 07:46


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የ2020 የጆርጂያ ግዛት ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ አሲረዋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ተከትሎ በጆርጂያ፣ አትላንታ ታሰሩ.

Sewasew - ሰዋስው

23 Aug, 08:40


የጺም መላጫ ማሽን (beard trimmer) እንዴት እንምረጥ?
ለወንድ ልጅ ጺም ውበት ነው። በአግባቡ ከተያዘ እና ከተስተካከለ ነው ታዲያ! በተለይ አሁን አሁን ጺምን ማሳደግ እና በተለያየ ቅርጽ መፈሸን ፋሽን ሆኗል። በዚህም ምክንያት ብዙዎች የጺም ማስተካከያ ማሽን በየቤታቸው እንዲኖራቸው ግድ እያላቸው ነው።

ጺም ወደድንም አልወደድንም (ሙልጭ አድርጎ ለመላጨት) ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ጺማችንን ማስተካከል እንዳለብን የውበት ባለሞያዎች ይመክራሉ። ይህን ለማድረግ ታዲያ ትክክለኛ እና ለኛ ተስማሚ የሆነውን ጥሩ የጺም መላጫ ማሽን ለይተን መግዛት ይጠበቅብናል።
ምን ምን ነገሮችን ማስተዋል አለብን?

🪒ምላጩ/ the blade🪒

የጺም መላጫ ማሽን ስንገዛ በመጀመሪያ ማስተዋል ያለብን ምላጩን ነው። ምላጩ ከቆዳችን ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነገር በመሆኑ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ጥሩ ያልሆነ የጺም መላጫ ማሽን ምላጭ ፊታችን ላይ የተለያየ እንደ ብጉር ያሉ ምልክቶች እና ቆዳችን እንዲንደበደብ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የዚህም ዋነኛ ምክንያት ምላጩ የሚሰራበት ጥሬ እቃ ነው። ስለዚህ የጺም መላጫ ማሽን ስንገዛ ምንጊዜም ቢሆን ምላጩ ከማይዝግ ብረት የተሰራ (stainless steel) ወይም ከ ቲታኒየም (titanium) የተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

መለዋወጫ/ Accessories / Features

ሌላው የጺም መላጫዎችን ተመራጭ የሚያደርጋቸው መለዋወጫቸው እና የሚሰጡት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ነው። የምንገዛው የጺም መላጫ በተለያየ መጠን ጺማችንን ሊቀንሱልን የሚችሉ የቁጥር መለዋወጫ ቢኖሩት ይመከራል። ይህም በፈለግነው መጠን እና ልክ ጺማችንን ለመቀነስ እና ለመላጨት ያስችለናል። ማሽኑ የራሱ ተለዋጭ ምላጭ ያለው ቢሆን ደግሞ ተመራጭ ነው።

🔋ባትሪ/battery🔋

የጸጉር ማሽኖች ሌላው የጥራት መለያ ነጥብ ባትሪ ነው። አንዴ ቻርጅ ተደርገው ምንያክል ሊያገለግሉን ይችላሉ? ይሄ በተለይ ብዙ ጊዜ በስራ ሁኔታ ከቦታ ቦታ ለሚንቀሳቀስ ሰው እና መብራት በተደጋጋሚ ለሚቋረጥበት ወሳኝ ነጥብ ነው። ስለዚህ ጥሩ የ lithium-ion battery ያላቸውን እና ማሽኑ ምን ያክል የባትሪ መጠን እንደቀረው የሚያሳይ ዲጂታል ዲስፕሌይ ያለው ማሽን ብንገዛ ይመከራል።

በተጨማሪም ጺማችንን ስንላጭ ጸጉር መብነኑ አይቀርም ። ነገር ግን አንዳንድ የጺም መላጫ ማሽኖች ከፊታችን ላይ የሚወገደውን ጸጉር ወደ ውስጥ የሚሰበስብ ሳጥን አላቸው። ታዲያ ጺማችንን ለመስተካከል የምንመርጠው ቦታ የጸጉር ብናኝ እንዳይወድቅበት የሚፈለግ ከሆን ይህን አይነቱን ማሽን መግዛቱ ይመከራል።

Sewasew - ሰዋስው

14 Aug, 08:03


የቡና ዓለም አቀፍ መግባቢያ ቋንቋ ለምን ጣሊያንኛ ሆነ/Why Italian Is the International Language of Coffee?
☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️
ዬትም የዓለም ክፍል ላይ ብንኖር አንድ ብዙዎቻችንን ሊያመሳስል የሚችል ልምድ አለን። ጥዋታችንን በቡና መጀመር! ግን ቡና ቀመስ መጠጦች ስማቸው የጣሊያነኛ ቋንቋ መሆኑን ልብ ብለን እናውቅ ይሆን? ላቴ፣ ማኪያቶ፣ ኢስፕሬሶ፣ ወዘተ። ጣሊያን ከቡና መሰረት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌላት ሁኔታ ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ ልምዱስ ከዬት መጣ? እንደሚታወቀው የቡና መሰረት ኢትዮጵያ ናት። ያገኘውም ካልዲ የሚባል እረኛ መሆኑ በታሪክ የሚነገር ጉዳይ ነው።
☕️☕️☕️☕️☕️
ነገሩ እንዲህ ነው…ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ምድር እንዲሁም ደቾች ቡናን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስፋፋት ስማቸው ይወሳ እንጂ ቡና ላይ እሴት በመጨመር ጣሊያንን የሚያክል የለም። በተለይም የኢስፕሬሶ (espresso) ማሽን ግኝት በዚህ ዘርፍ ጫወታ ቀያሪ መሆኑ ይነገርለታል።

Sewasew - ሰዋስው

07 Aug, 06:22


ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች እንኳን ለጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም የጾም ወቅት ይሁንላችሁ!

Sewasew - ሰዋስው

02 Aug, 08:00


😭🛫አይረሴው የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን የአውሮፕላን አደጋ🛫😭😭

#ሰዋስው_ስፖርት

በቅጥል ስማቸው ቺፖሎፖሎ (Chipolopolo) የሚባሉት የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ለ1994ቱ የዓለም ዋንጫ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመድረስ ጫፍ ላይ ደርሶ ነበር። ምን ዋጋ አለው ለዓለም ዋንጫው ማጣሪያ ከሴኔጋል ጋር ዳካር ላይ ለነበረበት ጫወታ የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድንን አሳፍሮ ከሉሳካ ዛምቢያ የተነሳው አውሮፕላን ካለመበት ሳይደርስ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ሰምጦ ቀረ። ያ የዛምቢያ ወርቃማ የእግር ኳስ ትውልድ በአንስ ቅጽበት አለቀ። 25 የብሔራዊ ቡድኑ አባላት እና 5 የበረራ ቡድን አባላት በአደጋው እስከወዲያኛው አሸለቡ። ⚰️⚰️

ሉሳካ በሀዘን አንገቷን ደፋች!😭😭 የወቅቱ የዛምቢያ የእግር ኳስ ፈርጥ ካሉሻ ቡዋሊያ ግን በአጋጣሚ በረራው ላይ አልነበረም ። ካሉሻ ቡዋሊያ ሀዘኑን ዋጥ አድርጎ ለሞቱ ጓዶቹ መታሰቢያ የሚሆን ታሪክ ለመስራት አዲስ ብሔራዊ ቡድን አቋቋመ። በአስደናቂ ሁኔታ አዲስ የተቋቋመው ቡድን ሞሮኮን በማጣሪያው በማሸነፍ ታሪክ ሰራ።💪

ምንም እንኳን ቺፖሎፖሎዎቹ ለ1994ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ባይችሉም ከአውሮፕላን አደጋው ከአንድ አመት ብኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ በመድረስ ዓለምን ጉድ አሰኝተዋል። በዋንጫው ጫወታ ናይጄሪያ ሁለት ለአንድ በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆናለች።🏆🏆

ምንጭ፡ https://www.reuters.com/.../thirty-years-zambia-mourns.../

Sewasew - ሰዋስው

01 Aug, 11:55


ከሳምሰንግ ወደ አይፎን በቀላሉ ፋይል ትራንስፈር ማድረግ

ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች በተለያዩ ምክንያቶች ከሳምሰንግ ስልክ ተጠቃሚነት ወደ አይፎን ወይንም ከአይፎን ወደ ሳምሰንግ ስልካችንን ልንቀይር እንችላለን፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ኮንታክት፣ ሜሴጅ፣ ፎቶ፣ ቪዲዮ የመሳሰሉ ፋይሎችን በቀላሉ ከአንደኛው ወደሌላኛው ስልክ ለማስተላለፍ ልንቸገር እንችላለን፡፡

እኛም ለዛሬ ከሳምሰንግ ስልክ ወደ አይፎን ፋይሎቻችንን በቀላሉ እንደምናዘዋውር ከሚያስችሉ ዘዴዎች መካከል አንዱን እንነግራችኋለን፡፡ በነገራችን ላይ አሁን እምንነግራችሁ ዘዴ አይፎናችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ እያስተካከላችሁ(Setup) ከሆነ ብቻ የሚሰራ መሆኑን ልብ በሉ፡፡

📌ልክ አይፎናችሁን እያስጀመራችሁ በምትሄዱበት ጊዜ Quick Start የሚል ገጽ ታገኛላችሁ በዚህ ጊዜ Setup Manually የሚለውን ምርጫ ትመርጣላችሁ

📌በመቀጠል ደግሞ ከአንድሮይድ ስልካችሁ ፋይሎችን አዘዋውሩ (Move data from Android) የሚል ምርጫ ይመጣላችኋል፡፡

📌 አሁን አይፎናችሁ ባለ 6 ዲጂት ሚስጥራዊ ቁጥር ይሰጣችኋል፡፡ እዚህ ላይ አይፎናችሁን ታስቀምጡትና ወደ ሳምሰንግ ስልካችሁ ትሄዳላችሁ

📌ከፕለይ ስቶር ውስጥ Move to iOS የሚባለ አፕሊኬሽን ዳውሎድ ታደርጋላችሁ

📌አፕልኬሽኑ ዳውሎድ አድርጎ እንደጨረሰ 6 ዲጂት ቁጥር እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል፡፡ ይሄኔ ቅድም ከአይፎኑ ያገኛችሁትን 6 ዲጂት ቁጥር ታስገባላችሁ፡፡

📌አሁን አይፎናችሁ ጊዜአዊ የዋይፋይ ግንኙነት ይፈጥራል፡፡ Connect የሚለውን ምርጫ ትጫናላችሁ፡፡

📌በመጨረሻም ከሚመጡላችሁ ዝርዝሮች መካከል ማዘዋወር የምትፈልጉትን ትመርጡና Continue የሚለውን ቁልፍ ትጫናላችሁ፡፡

እንደምታዘዋውሩት ፋይል ብዛት ሂደቱ የሚፈጀው ጊዜ እንደሚወሰን ልብ ይሏል፡፡ በነገራችን ላይ ሳምሰንግ ስልካችሁ ላይ የተጫኑ ነፃ አፕሊኬሽኖች አፕስቶር ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ይህ የትራንስፈር ማድረጊያ ዘዴ አብሮ ዳውሎድ እንደሚያደርጋቸው ማስታወስ እንፈልጋለን፡፡

Sewasew - ሰዋስው

31 Jul, 10:38


የስልክ ኔትወርኮች በምንድን ነው የሚለያዩት?
ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች መቼም ስለኔትወርክ ሲወራ ስልኩ 1G የኔትወርክ ስርአት ነው የሚቀበለው፣ የተዘረጋው የኔትወርክ ስርአት 2G ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችለው፣ ከ3G እስከ 5G ድረስ ያሉ ኔትወርኮች የሚያቀርቡትን አገልግሎት በዚህ ዲቫይስ መጠቀም ይቻላል ሲባል ሳትሰሙ አትቀሩም፡፡ ታዲያ አንዳንዴ እነዚህ ስያሜዎች ቴክኒካዊ ስለሆኑ በሁሉም ዘንድ እኩል መረዳት ላይኖር ይችላልና የሚከተለውን ልንነግራችሁ ወደድን፣


በቅድሚያ ከቁጥሮቹ ቀጥሎ የምትገኘው G ፊደል የምታመለክተው የኔትወርኩን እድሜ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ Generation ይሏታል በእነርሱ አጠራር፡፡ የአንደኛው ትውልድ ኔትወርክ፣ የሁለተኛው ትውልድ ኔትወርክ፣ የሶስተኛው ትውልድ ኔትወርክ ወ.ዘ.ተ
እነዚህ ኔትወርኮች በምንድን ነው የሚለያዩት?
1G (የአንደኛው ትውልድ ኔትወርክ)
ይሄኛው የአናሎግ ሲግናልን የሚጠቀምና የመጀመሪያው ትውልድ ሞባይል ወይም የሞባይል ስርአት በአሁኑ ዘመን ለደረስንባቸው የረቀቁ የቴክኖሎጂ ስርአቶች ሁሉ መሰረት የጣለ ሲሆን የተሻለ ጥራት ያለው የድምጽ አገልግሎትንና ደህንነቱ የተጠበቀ የዳታ ጥሪ እንዲያስተናግድ ተደርጎ ነበር የተነደፈው፡፡
2G (የሁለተኛው ትውልድ ኔትወርክ)
በዚህ የኔትወርክ ትውልድ እንደ ዳታ፣ ፋክስ እና አጭር የጽሁፍ መልዕክት የመሳሰሉትን ነገሮች መገልገል እንችላለን፡፡
2.5G (የሁለተኛው እና ግማሽ ትውልድ ኔትወርክ)
ይሄኛው የኔትወርክ ስርአት ሁለተኛው ትውልድ ኔትወርክ ላይ መጠነኛ ለውጥ በማድረግ የተፈጠረ ሲሆን መልቲሚዲያ ሜሴጂንግ አገልግሎትን (MMS) ጨምሮ የተሻሻለ የዳታ ግንኙነት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ኢሜል ለመላክ ለመቀበል እንዲሁም ዌብሳይቶችን ለማሰስ የሚጠቅም እንደ ገመድ አልባ የመተግበሪያ ፕሮቶኮል (WAP) አካቷል፡፡

3G (የሶስተኛው ትውልድ ኔትወርክ)

እ.አ.አ በ1998 ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የተዋወቀው ይህ የኔትወርክ አይነት ከዚያ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ፈጣን የኢንተርኔት ግንኙነት በመፍጠር ሙዚቃና ቪዲዮን በቀላሉ ዳውሎድ ማድረግ አስችሏል፡፡

4G (የአራተኛው ትውልድ ኔትወርክ)

ይሄኛው አሁን በአብዛኛው አለማችን ላይ የሚገኙ ስልኮች የሚጠቀሙት የኔትወርክ አይነት ሲሆን እስከ 300 ሚጋባይት በሰኮንድ የሚደርስ የኢንተርኔት ግንኙነት የመፍጠር ብቃት አለው፡፡

5G (የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ)

ይሄኛው የኔትወርክ አይነት አለማችን በአሁኑ ሰአት የደረሰችበት ፈጣኑን የኢንተርኔት ግንኙነት የሚያቀርብ ኔትወርክ ሲሆን ከአራተኛው ትውልድ ኔትወርክ በ100 እጥፍ የሚበልጥ ፍጥነት አለው፡፡ አሁን አሁን የሚወጡ ስልኮችም ይህን ኔትወርክ የሚያስጠቅሙ ሲም ካርዶችን እንዲያስተናግዱ ተደርገው ነው የተዘጋጁት፡፡

Sewasew - ሰዋስው

31 Jul, 10:38



Sewasew - ሰዋስው

25 Jul, 11:36


ሥርዓተ ምንኵስና እና ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዓርገ ክህነት የሚሰጠው፣ በአብዛኛው፣ ትሩፋትን አገልግሎትን፣ ቅድስናን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ እንደ ጥንቱ ሥርዓት ከኾነ፣ አንድ ምእመን ከገዳም ገብቶ ምንኵስና እንዲፈቀድለት በጠየቀበት ሰዓት፣ ሥርዓተ ምንኵስና አይፈጸምለትም ነበር፡፡ የገዳም አበምኔቶች የምንኵስና ፈላጊውን ምእመን ጥያቄ ብቻ ተቀብለው ሥርዓቱን አያደርሱም፡፡ በቅድሚያ ለምን የምንኵስና ሕይወትን እንደመረጠ ይጠይቁታል፡፡ ምንኵስና የመረጠው

ከትዳር ለመሸሽ ወይም የሚወደውን ስላጣበመሳሰሉት ሥጋዊ ምክንያቶች ከኾነ ራሱን እንዲመረምር ያደርጉታል፡፡
የምንኵስና ሕይወት፣ ከነዚኽ ነገሮች ለመሸሽ ሳይኾን፣ ዕድሜን በሙሉ ራስን ከክርስቶስ ጋር ሰቅሎ በገድልና በትሩፋት የሚኖሩበት ሕይወት መኾኑን አስረግጠው ይነግሩታል፡፡ የምንኵስና ሕይወት በዓለም ዘንድ መሞት መኾኑን ምእመኑ ከተረዳ በኋላ ምእመኑ በተለያዩ አገልግሎቶች እንዲፈተን ይደረጋል፡፡

በሌላ አነጋገር፣ የአመክሮ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡ በቅድስናቸው የተመሰከረላቸው የበቁ አባቶችና ወንድሞች በጸሎት እንዲያግዙት ይደረጋል፡፡ በአባቶች ጸሎት እየታገዘ በትሩፋት ሥራ ተጠምዶ ካገለገለ በኋላ ለአንድ ምእመን ሥርዓተ ምንኵስና ይፈጸምለታል፡፡ በዚኽ መስመር የሚጓዙ መነኰሳት በአብዛኛው አገልግሎታቸው ሲሠምርላቸው ይታያል፡፡ በስሜት ተነሣስተው ለሚመጡ ሰዎች ግን የቀደሙት መምህራን ገዳማውያን አባቶች ሥርዓተ ምንኵስናን አይፈጽሙም ነበር፡፡
ይህ ትውፊት የተወሰደው ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ነው፡፡ ሐዋርያው ለአዲስ አማኝ የጵጵስና ማዕርግ መስጠት፣ ተሿሚው ገና ቀንበር ያልለመደ በመኾኑ ለፈተና ሊጋለጥ ስለሚችል፣ “አዲስ ክርስቲያን አይኹን”/1ጢሞ.3፥7/ በማለት ከልክሏል፡፡ ሐዋርያው ክልከላውን ያስቀመጠው፣ አዲስ ክርስቲያን ለኤጲስ ቆጶስነት ቢመርጡት፣ ሰይጣን በአመጣው ትዕቢት ተይዞ በዲያቢሎስ ሊወድቅ ስለሚችል ነው፡፡


ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያውን ትምህርት መሠረት በማድረግ ስትሠራበት ትኖራለች፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አባቶች ያኖሩትን ትምህርት በመጣስ፣ አንድ ሰው አምኛለኹ፤ በቅቻለኹ ብሎ ቢቀርብ እንኳ ቤተ ክርስቲያን መሾም የለባትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ማዕርግ በታማኝነት ሊያገለግሏት የሚችሉትን አገልጋዮች በጥንቃቄ መምረጥ አለባት፡፡



የአበውን ትውፊት በመጣስ፣ የዕድሜን የአገልግሎትን ኹኔታ ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ ቢሾሙ፤ በዲያቢሎስ ሽንገላ በትዕቢት እየተነፉ፣ እነርሱም ሳይገለገሉ ቤተ ክርስቲያንንም ሳያገለግሉ የጥፋት መሣርያ ይኾናሉ፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯን መሠረቷን የሚያውቁ፤ በገድል የተቀጠቀጡና በትሩፋት ያጌጡ፤ በአጠቃላይ በቅድስና ሕይወት ጸንተው የኖሩ አባቶችን ከገዳም ጭምር እየፈለገች መሾም ይጠበቅባታል፡፡ በቅድስናቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች መሾም፣ በእውነት ምእመናንን በጸሎታቸው የቅድስና ሕይወታቸው ተካፋይ ያደርጋቸዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያንን በአግባቡ ያላገለገሉ፤ በገዳማዊ ሕይወት ያልተፈተኑ፤ በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድ የወደቁ፤ በፍቅረ ንዋይ ያበዱ፤ የውድቀት ታሪክ ያላቸው ሰዎች ያለምንም መስፈርት ሳይመረመሩ ቢሾሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊመሯት አይችሉም፤ እንሥራ ቢሉም ይጎዷታል፡፡ ስለዚኽ በአገልግሎት ያልተፈተኑ፤ በውጭ ባሉ ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር የሌላቸውን ሰዎች መሾም አደጋው የበዛ መኾኑ ሊስተዋል ይገባል፡፡

ምንጭ፡
https://haratewahido.wordpress.com

Sewasew - ሰዋስው

24 Jul, 10:11


የ online መገበያያ የሆነው አማዞን ሎጎ ከ A ተነስቶ እስከ Z ድረስ የሚሄድ ቀስት አለው፡፡ ይሄም የሚያሳየው ምንም ነገር አማዞን ላይ ተፈልጎ እንደማይታጣ ሲሆን Amazon የሚለው ስም ደግሞ ከ አለማችን ትልቁ ደን እና በርዝመቱ ሁለተኛ ወንዝ ከሆነው ከብራዚሉ Amazon የተወሰደ ሲሆን የድርጅቱን ግዝፈት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡

Sewasew - ሰዋስው

21 Jul, 08:36


በ USB 2.0 እና በ USB 3.0 ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

እንደሚታወቀው እንደ ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ፣ ስልክ፣ ዌብካም፣ ኪቦርድ ያሉ የተለያዩ ዲቫይሶችን ከኮምፒዩተር፣ ከቻርጀር አልያም ከአንዳች ዲቫይስ ጋር በማገናኘት ቻርጅ ለማድረግ ወይም ዳታ ለማስተላለፍና ለማጋራት በአብዛኛው የምንጠቀምበት ኬብል USB ነው፡፡ ታዲያ እዚህ ላይ አንዳንድ ሰዎች ልብ የማይሉት አልያም በትክክል የማያውቁት በእነዚህ የUSB ኬብል ዝርያዎች መካከል ያለውን ልዩነት ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ልዩነት አለማወቅ ደግሞ ስራዎችን በተቀላጠፈ፣ ባስተማማኝና ባጠረ ጊዜ ማከናወን እምንችልባቸውን መንገዶች እንዳናይ ይጋርደናል፡፡

ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች ለአሁኑ እስኪ በUSB 2.0 እና በUSB 3.0 መካከል ያለውን ልዩነት እንንገራችሁ
በመጀመሪያ ደረጃ ዳታ የሚያስተላልፉበትን ፍጥነት በምንመለከትበት ጊዜ በጣም ሰፊ ልዩነት እናገኛለን፡፡ USB 2.0 480 ሚጋቢት በሰኮንድ ብቻ ሲያስተላልፍ USB 3.0 ደግሞ ይህን ፍጥነት በአስር እጥፍ ያሳድገዋል፤ 4800 ሚጋቢት በሰኮንድ፡፡
ሌላው ልዩነት በውስጣቸው የያዟቸው የኬብል ብዛት ነው፡፡ USB 2.0 4 ኬብሎች ሲኖቱት USB 3.0 ደግሞ 8 ኬብሎች አሉት፡፡ እዚህ ላይ ታዲያ የኬብሎቹ መብዛት ከቁጥር ውጭ ምን ልዩነት ያመጣል የሚል ጥያቄ ከተነሳ መልሳችን፣ የUSB 2.0 ኬብሎች በአንድ ጊዜ በአንድ አቅጣጫ የሚሄድን ዳታ ብቻ የሚያስተናግዱ ሲሆን የUSB 3.0 ኬብሎች ግን ባንድዊድዛቸው ሰፋ ያለ ፍጥነታቸውም ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር በተመሳሳይ ሰአት ዳታ መላክም መቀበልም የሚያስችል ብቃት አላቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አማካኝ የሚባለው የ USB 2.0 ኬብል ርዝመት 5 ሜትሮች ሲሆን የ USB 3.0 ደግሞ እስከ 3 ሜትሮች ይደርሳል፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ምንም እንኳን USB 3.0 የተሻለ ፍጥነት ቢኖረውም የኬብል ምርጫችን ኮኔክት እንደምናደርጋቸው ዲቫይሶች ርቀትም ሊወሰን የሚችልበት እድል እንዳለው ልብ ይሏል፡፡

አሁን ደግሞ ስለቻርጅ የማድረግ አቅማቸው እናውራ፡፡ አስተውላችሁ ከሆነ ተመሳሳይ ስልክ በሁለቱ የተለያዩ ቻርጀሮች ሲሰካ በአንደኛው ፈጥኖ ቻርጅ ያደርጋል በሌላኛው ደግሞ በጣም ቀርፋፋ ይሆናል፡፡ ለምን? ይህ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንዱ እነዚህ ኬብሎች የሚያስተላልፉት የኤሌክትሪክ መጠን ነው፡፡ ለምሳሌ USB 2.0 ኬብል ማስተላለፍ የሚችለው 500 ሚሊአምፒር በሰኮንድ ብቻ ሲሆን USB 3.0 ኬብል ደግሞ 900 ሚሊአምር በሰኮንድ ነው፡፡

ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች እንግዲህ እነዚህን ኬብሎች ለመግዛት በምታስቡበት ጊዜ ሌላኛው መለያቸው የቀለም ልዩነት ነው፡፡ የ USB 2.0 ኬብል ፖርት ቀለም ነጭ ወይም ጥቁር ሲሆን የUSB 3.0 ኬብል ፖርት ደግሞ ሰማያዊ መሆኑን ማስታወስ ይገባል፡፡

Sewasew - ሰዋስው

21 Jul, 08:35


በ USB 2.0 እና በ USB 3.0 ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

Sewasew - ሰዋስው

20 Jul, 09:08


የአፍንጫ👃👃 ሰላምታ በኒውዝላንድ

በተለያዩ ባህሎች የለሰላምታው አይነት የተለያየ ነው። በእጅ መጨባበጥ፣መተቃቀፍ አሊያም መሳሳም የተለመዱ የሰላምታ ልውውጥ መንገዶች ናቸው። ይህ እንዳለ ሆኖ በአንዳንድ ማህበረሰቦች ዘንድ ያሉ የሰላምታ ልውውጥ መንገዶች ለብዙዎቻችን እንግዳ ናቸው።
በኒውዝላንድ የሚኖሩት የማኦሪ(Māori) ማህበረሰቦች ለየት ያለ የሰላምታ ልውውጥ መንገድ አላቸው። ሆንጊ(hongi) ይሉታል ይህን ሰላምታቸውን። ሆንጊ ሁለት ሰዎች ሲገናኙ ግንባርና አፍንጫዎቻቸውን በማነካካት የሚደረግ ሰላምታ ነው።

እንደ ማኦሪዎች እምነት ይህ የሰላምታ መንገድ ቀጥታ ከፈጣሪ የተሰጠ ነው። በአፈታሪካቸው እንደሚነገረው ፈጣሪያቸው “ታኔ” በመጀመሪያ ሴትን ልጅ ከምድር አፈር አንስቶ አቡክቶ የሰው ቅርጽ ካስያዛት በኋላ የሰራትን ሴት ከጭቃ የሰራትን ሴት በአፍንጫዋ ሲተነፍስባት ነፍስ ዘራች ይባላል። ይህንን ታሪክ መነሻ በማድረግ እነዚህ ማህበረሰቦች በአፍንጫችን ሰላም ስንባባል የህይወትን እስትንፋስ እየተለዋወጥን ነው ብለው ያምናሉ።

ኒውዝላንዶች ትልልቅ እንግዶችን ሲያስተናግዱ በዚህ መንገድ ሰላምታ በመስጠት ባህላቸውን ያስተዋውቃሉ። በዚህ መንገድ ከተስተናገዱ ታዋቂ ሰዎች መካከል የብሪቲሽ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች፣ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች ይገኙበታል።

Sewasew - ሰዋስው

17 Jul, 10:33


#ሰዋስው_ቴክኖሎጂ

አገራችን ውስጥ ኢ-ሲም የሚያስጠቅሙ ስልኮች የትኞቹ ናቸው?

የጋላከሲ ፒክስል ስልኮች እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ኢ-ሲም የነበራቸው ሲሆን የአፕል ስልኮች ደግሞ ከ2018 ጀምሮ ኢ-ሲም ይዘው መጥተዋል፡፡

ሌላው የሳምሰንግ ስልኮች ኢ-ሲም ካርድ ይቀበላሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም የሳምሰንግ ምርቶች የዚህ ሲም ካርድ አገልግሎትን ይቀበላሉ ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ20 እስከ 22 እንዲሁም ሳምሰንግ ኖት ስልኮች ይህን አገልግሎት ማስተናገድ ይችላሉ፡፡ ሳምሰንግ ጋላክሲ ዜድ ፎልድና ፍሊፕ የተባሉት ታጣፊ ስልኮችም ኢ-ሲም ካርድ ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ከዚያ ውጭ የአፕል ምርት የሆኑ አይፎን ስልኮችም ኢትዮጵያ ውስጥ ኢ-ሲም ለመጠቀም እንደሚያስችሉ ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀ ሲሆን ከአይፎን ኤክስ ጀምሮ እስከ አይፎን 14 ድረስ ያሉ በቅርብ ዓመታት የተመረቱ ስልኮች ካልዎት ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እ.አ.አ በ2022 የተመረተው አይፎን ኤስኢ 3 ስልክም ይህን ኢ-ሲም ይቀበላል፡፡

የዓለም የተንቀሳቃሽ ስልክ ገበያን ከተቆጣጠሩት ሳምሰንግና አይፎን ስልኮች በተጨማሪ ጉግል ፒክስል ስልኮች ሲም ይወስዳሉ፡፡ በነገራችን ላይ ኦፖ የተሰኘው ቻይና የምታመርተው ስልክም ይህን ቴክኖሎጂ የሚያስጠቅም ቢሆንም፣ ጥቂት የኦፖ ምርቶች ናቸው በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ተቀባይነት ያላቸው፡፡ ሁዋዌ ፒ40፣ ፒ40 ፕሮና ሁዋዌ ማቴ 40 እንዲሁም አራት ዓይነት የሞቶሮላ ምርቶች በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡

Sewasew - ሰዋስው

15 Jul, 08:48


#ጤና

ኮፍያ ማድረግ በማብዛቴ ፀጉሬ ይመልጣል
=====
ኮፍያ ማድረግ ከፋሽንነት ባሻገር፣ ፀጉርን፣ የራስ ቅልን እና የፊት ቆዳን ካላስፈላጊ የፀሀይ ጨረር በመከላከል፣ የፀሀይ ጨረርን ተንተርሰው ከሚመጡ የቆዳ ላይ ችግሮች አንዱ መከላከያ መንገድ ነው፡፡

እንግዲህ ኮፍያ በቀጥታ ፀጉርን እንደሚመልጥ የሚያመላክቱ በቂ ጥናቶች ባይኖሩም ንፅህናው የማይጠበቅ፣ የራስ ቅልን አጥብቆ የሚይዝ እና አየር የማያስገባ ኮፍያ ለረጅም ግዜ ማዘውተር ግን የፀጉር እና የራስቅል ቆዳ ላይ የጤና ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡

ሆኖም ግን፣ ራሰ በርሃነት እና የፀጉር መሳሳት፣ ኮፍያ ማድረግን ብቻ ተንተርሰው የሚመጡ ችግሮች ሳይሆኑ፣ ከስር በተዘረዘሩት በተጓዳኝ ችግሮችም ሊከሰቱ ይችላሉ፤

📌በዘር ራሰ በርሀነት ካለ፣
📌የምግብ እጥረት መኖር
📌የደም ማነስ፣
📌ራስ ቅል ላይ በበሽታ አምጪ ተህዋስና በተፈጥሮ የሚመጣ ቁጣ ካለ፣
📌እንዲሁም አንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎች እና፣
📌የራስ ቅል ላይ የሚደርስ የጨረር የኬሚካል እና የሳት አደጋ መኖር፣

እና የመሳሰሉ ምክኒያቶች፣ ለፀጉር መሳሳት፣ መበጣጠስ እና መመለጥ የሚዳርጉ የተወሰኑ ምክኒያቶች ናቸው፡፡

Sewasew - ሰዋስው

13 Jul, 11:20


ውድ የስዋስው ቤተሰቦች የትላንቱ ጥያቄ አሸናፊ ምህረት አናጋው ነው።

Sewasew - ሰዋስው

13 Jul, 08:58


በሱርማዎች ዘንድ 💍 ትዳር በቀላሉ አይገኝም። በቀጭን እና በቀላሉ በማይሰበር ዱላ 🦯🦯 ወገብ እስኪላጥ፣ ሰንበር እስኪወጣ መገራረፍን ይጠይቃል።

ይህ የመገራረፍ ባህል 'ዶንጋ' ተብሎ ይጠራል። በነገራችን ላይ በዚህ ጨዋታ መቁሰል እና መድማቱ እንዳለ ሆኖ እስከሞት ለሚያደርስ ጉዳትም መጋለጥ ያለ ነው። ግን በዶንጋ ቂም የለም!

ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን 👨‍👩‍👧‍👦

Sewasew - ሰዋስው

12 Jul, 17:54


Sewasew - ሰዋስው pinned «🎁🎁የ50 ብር ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ 🎁🎁 ወስከንቢያ ምንድነው? 🙋‍♂️መልሳችሁን ኮሜት ላይ ያስቀምጡልን 🏆🏆 አሸናፊውን ነገ ሐሙስ ቀን 8 ሰዓት ላይ ይፋ እናደርጋለን🏆🏆 ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ»