ስብከተ ወንጌል ። @sebeketwongel Channel on Telegram

ስብከተ ወንጌል ።

@sebeketwongel


" በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።"
(1ኛ ቆሮንቶስ 9:23)

ስብከተ ወንጌል ። (Amharic)

ስብከተ ወንጌል ። በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።" (1ኛ ቆሮንቶስ 9:23)nnይህ ቦታ የሚለው ለእናቶቻችን የቀረላቸው እና ጥንቃቄ ገና ነው። ይህ ሥራ ስኬት ለመስራትና የህዝብና የቅርብ ምንጭ ምከራና መሳሪያ ያስፈልጋል። ስለዚህ የዚፎውን እርምጃ ለማቀናበር እኚህን ይጫኑ።nnበሚመገበው ጊዜ ድምጽህን በአክሥሮት የመለያዎችን መዝለልና ተጨባጭ ሼርክ ያድምጠሃል። እናቶችዎች እርምጃዎች እና ምከራነቶችን እንደ ግንኙነቶች ውስጥ አወዳድሪን እንደ ሥራዎች ዝቅ አለቅሳል።

ስብከተ ወንጌል ።

07 Nov, 14:30


ጥያቄ ።የአንዳንድ አባቶቼን ስህተት በሚዲያ ስሰማ ከነሱማ እሻላለሁ የሚል ፈተና አለብኝ እንዴት ላሻሽለው ?
መልስ። መምህር ብርሃኑ አድማስ

ስብከተ ወንጌል ።

26 Oct, 16:19


❤️ከእግዚአብሔር ጋር መስራት
በመምህር ብርሃኑ አድማስ
ቢሰሙት ያተርፋሉ ።
ሌሎች እንዲሰሙት ከፈለጉ ደሞ  
(share )  share
👇👇👇👇👇
@sebeketwongel
@sebeketwongel
@sebeketwongel

ስብከተ ወንጌል ።

26 Oct, 13:41


ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ "ሃይማኖትን የተሞላ እስጢፋኖስ መረጡ" የሐዋ ሥራ 6፥5 በሚል ርእስ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ በንግሡ በዓል ላይ ያስተማሩት ድንቅ ትምህርት።

ስብከተ ወንጌል ።

21 Sep, 22:42


በጎ ዘመን ለማየት የሚወድ
በመምህር ብርሃን አድማስ
ቢሰሙት ያተርፋሉ ።
ሌሎች እንዲሰሙት ከፈለጉ ደሞ  
(share )  share
👇👇👇👇👇
@sebeketwongel
@sebeketwongel
@sebeketwongel

ስብከተ ወንጌል ።

13 Sep, 05:33


“በአባ ቢሾይ ገዳም ከአባቶች መነኰሳት ጋር ተገናኘሁ። በዚያም የቦታውን መንፈሳዊነትም ሆነ የእንግዳ ተቀባይነታቸውን ነገር፣ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተግባራቸውንና ትምህርታቸውን ተመለከትሁ፤ ሆኖም ግን ካየሁት ሁሉ አንዱንም እንኳ እንደሚገባ አድርጌ አሟልቼ ልገልጸው አልችልም። ሆኖም የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት በታሪካችን ውስጥ የነበረውን ሚና መዘንጋት ለእያንዳንዱ ዐረብ ታላቅ ኪሳራ የመሆኑ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ለራሴ ተረድቻለሁ። በእ*ስልምና ሃይማኖት ውስጥ ምንኲስናና ገዳማዊ ሕይወት የሚባል ነገር አለመኖሩን ማሰብ ውስጥን የሚረብሽና የሚያሳዝን ነገር ነው።”

መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው።

ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም።

ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!

ስብከተ ወንጌል ።

13 Sep, 05:33


ከዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ወደ ላይ አያዳልጣችሁ!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አንድ ጨዋነት የራቀው ሰው ሰደባቸው አሉ። በኋላ ግን ጸጽቶት እግራቸው ላይ ወድቆ “ይማሩኝ፣ አጥፍቻለሁ፣ አድጦኝ ነው” ሲላቸው፣ እርሳቸውም “ታዲያ ወደ ታች ያድጣል እንጂ ወደ ላይ ያድጣል እንዴ?” አሉት ይባላል።

ወደ ላይ የሚያድጣቸውን ብዙ ሰዎች እያየን ነው። ሰሞኑን ዘነበ ወላ የተባለ ግለሰብ፣ ሊነቅፈው ቀርቶ ሊረዳውና ሊያደንቀው እንኳ እጅግ የሚበዛበትን የምናኔ ሕይወት ለመንቀፍ ሲሞክር ሰምተናል (የተነገረው በሕንድኛ ወይም በታይ ቋንቋ አይደለም!)። ይህን የመሰሉ እናውቃለን ከሚሉ አላዋቂዎች ወይም ጭፍን ጥላቻ ካሳወራቸው ሰዎች በኦርቶዶክሳዊነት ላይ በተለያየ መንገድ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየበዙ መምጣታቸው ጉዳዩን እንደ ቀላል ለማለፍ የማይቻል ያደርገዋል። ዛሬ ካለው የተከማቸ ኦርቶዶክስ-ጠልነት ያደረሱን ከ20ኛው መ/ዓ መጀመሪያ ጀምሮ ኦርቶዶክስ ጠል በነበሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ይሰነዘሩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮችና ጽሑፎች መሆናቸውን ልብ ይሏል።

ምናኔያዊ ሕይወት፣ ከትንሣኤ በኋላ የምናገኘውን እንደ መላእክት የመሆንን ሕይወት፣ በዚህ ዐለም ገንዘብ የማድረግ ሕይወት ነው። “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” እንዳለ ጌታችን። ማቴ. 22፡30 መላእክት በተፈጥሯቸው እንደማያገቡና እንደማይጋቡ ሁሉ፣ ከትንሣኤ በኋላ ደግሞ ለሰዎችም ማግባትና መጋባት እንደማይኖር ሁሉ፣ መላእክት ዛሬ የሚኖሩትን፣ የሰው ልጆች ደግሞ ከሞት በኋላ የሚያገኙትን ሕይወት መናንያን ገዳማውያን በአሁኑ ሕይወት ይኖሩታል። እንደዚሁም ምናኔያዊ ሕይወት አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ሕይወት ምን ይመስል እንደ ነበረ በመስታወት የሚያሳይ ነው፣ ጌታችን የሰጠውን ሕይወት በምልዓት የሚያሳይ ነው።

ምናኔያዊ ሕይወት በክርስትና ውስጥ ያለውን እጅግ የገዘፈና ዘርፈ-ብዙ የሆነ ነገረ-ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ለጊዜው ብናቆየው እንኳ፣ ክርስቲያናዊ ገዳማት ለሰው ልጆች ያበረከቷቸው ኢኮኖሚያዊ፣ እውቀታዊና ታሪካዊ ጠቀሜታዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ጥቂቶቹን እንኳ ብናስታውስ፤ ዩኒቨርሲቲዎችና አዳሪ ት/ቤቶች በዋናነት የተቀዱት ከገዳማት ነው። የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሲመረቁ የሚለብሱት ጋዋንና የሚደፉት ቆብ የገዳማትን ቀሚስና ሞጣህት እንዲሁም ቆብ የሚመስለው በአጋጣሚ አይደለም።

በአውሮፓ የውኃ ኃይልን ለወፍጮና ለቆዳ ሥራ መጠቀምንና ማዕድናትን ማውጣትንና መጠቀምን በስፋት ያስተዋወቁት ገዳማውያን ናቸው። የአውሮፓን የእርሻ መሬት፣ ሥነ ጥበብና እውቀት ከጥፋት በመጠበቅና በማበልጸግ ረገድ ገዳማት የተጫወቱት ሚና ምትክ አልባ ነው። አንዳንድ ገዳማት በየዓመቱ የአበምኔቶች መደበኛ ስብሰባ ስለነበራቸው፣ የደረሱባቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ እውቀቶችና ልምዶች ይለዋወጡ ስለነበር በዚህ መንገድ ሥልጣኔ በመላው አውሮፓ እንዲስፋፋ የራሳቸውን ታላቅ ሚና ተጫውተዋል።

ከክርስትና በፊት የጉልበት ሥራ መልካም ክብርና ስም አልነበረውም። በግሪኮች ትምህርት መሠረት የጉልበት ሥራ የዝቅተኞቹ ኅብረተሰብ ክፍል (የድሀውና የባሪያዎች) ሥራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። በሮማውያን ዘንድም ለሥራ የነበረው መንፈስ ተመሳሳይ ነበር። ለጉልበት ሥራ በተለይም ለግብርና ከፍ ያለ ቦታና ከበሬታ የሰጡት ገዳማት ናቸው።

ከዚህም ጋር ገዳማት ለድሆች፣ ለስደተኞች፣ ለወላጅ አልባ ልጆች፣ ለሕሙማንና ለችግረኞች መጠጊያዎች በመሆን አገለግልዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ4ኛው መ/ዓ የነበረው ቅዱስ ባስልዮስ የመሠረታቸው ገዳማት ሐኪም ቤቶች፣ የድሆች መመገቢያዎችና የችግረኞች መርጃ ማዕከሎችም ነበሩ። የዘመናዊ ሆስፒታል ጽንሰ-ሐሳብ መሠረቱ ክርስቲያናዊ ገዳማት ናቸው።

እንደዚሁም ገዳማት የሥነ ጽሑፍና የትምህርት ማዕከላት ነበሩ። ታላላቅ ቤተ መጻሕፍት የነበራቸው ብዙ ገዳማት ነበሩ። ብዙ መጻሕፍት ከእኛ እንዲደርሱ ያደረጉት መጻሕፍትን የሚሰበስቡና ባለሙያዎችን መድበው በእጅ የሚያስገለብጡ ገዳማት ናቸው። ብዙዎቹ መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ከጥፋት ተርፈው ከዛሬ የደረሱት በገዳማት ተደብቀውና ተጠብቀው ስለኖሩ ነው።

ግሪኮች በኦቶማን ቱርክ በተገዙባቸው ወደ 300 የሚደርሱ ዘመናት ውስጥ እምነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና ሥነ ጽሑፋቸውን ሕያው አድርገው የጠበቁት በገዳማት ዋና ማዕከልነት ነበር። ገዳማቱ ለካህናት ብቻ ሳይሆን በቱርኮች ግዛት ሥር ለነበሩ መላው ግሪካውያን ስውር ት/ቤቶች ነበሩ። በአገራችንና በሌሎች አገራትም ብዙ ተመሳሳይ ታሪኮች አሉ። ነጻነትን ለሚወዱና ባርነትን ለሚጸየፉ ሰዎች ሁሉ እነዚህ ትርጉማቸው ጥልቅ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ገዳማትን ትቁር ጥምድ የሚያደርጓቸውም ለዚህ ነው።

መናንያን አባቶችና እናቶች ለሰው ልጅ ሁሉ ምሕረትን ከእግዚአብሔር የሚለምኑ ናቸው። በአስቄጥስ ገዳም ስለ ነበረ አባ ኢሳይያስ ስለ ተባለ አባት በመጽሐፈ ገነት እንዲህ ተብሎ እናገኛለን፡- “በዋዕየ ፀሐይ ላይ ራቁቱን ቁሞ ስለ መላው ዐለም ሲጸልይ ሳለ ከመነኰሳት አንዱ እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማ፡- ‘ከእርሱ ጸሎት የተነሣ ለዐለሙ ሁሉ ምሕረት አድርጌያለሁና ሂድና ለአባ ኢሳይያስ ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብስ ስጠው።’”

ገዳማውያን መናንያን ሌላውን የሚዘርፉና የሚያጠፉ ሳይሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምኑ ናቸው፣ ሰውን የሚያሳድዱ ሳይሆኑ የተሰደዱትን የሚቀበሉ ናቸው። እንኳንስ የሰው ልጅ እንስሳትና አራዊት እንኳ አዳኞች ሲያሳድዷቸው ሸሽተው የሚጠጉባቸው ናቸው። የፍርሃትና የአጎብዳጅነት መንፈስ ያይደለ የእውነትና የጥብዓት መንፈስ ያለው ሁሉ ይህን ይረዳል።

ምንም እንኳ ምናኔያዊ ሕይወት ዓላማው በዚህ ዐለም ሀብት መበልጸግ ባይሆንም፣ በኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ረገድም ቢሆን ገዳማት በየዘመናቱ የነበራቸው ሚና ቀላል አልነበረም። ለአብነት ያህል በዘመናችን የግብፅን የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች በከፍተኛ ድርሻ የሚሸፍኑት ኦርቶዶክሳውያን ገዳማት ናቸው። የአስቄጥስ ገዳም ለግብፅ የአየርና የዐፈር ጠባይ ተስማሚ የእህልና የአትክልት ዝርያዎችን በማምረት የአገሪቱን የምግብ አቅርቦት ችግር በመፍታት ረገድ የተጫወተው ሚና ታላቅ ነው።

በተለይም ደግሞ የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት በሳይንሳዊ ምርምር በግብፅ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ያመረቱት “ፎደር ቢት” (fodder beet) የተሰኘ የስኳር ድንች ዓይነት አዲስ ምርት በእጅጉ ተመስግነውበታል። የአሰቄጥስ ገዳም መነኰሳት በዚህ ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ሙስሊሙ መሪ አንዋር ሳዳት ከታላቅ ምስጋና ጋር ብዙ ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ሌሎቹ የግብፅ ገዳማትም ለበረሃው ተስማሚ የሆኑ የዕፅዋትና አዝዕርት ዓይነቶችን በሳይንሳዊ ምርምር በመፈለግ ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሠሩ ናቸው።

ወደ ግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ተጉዞ የነበረ አህመድ ኤል-ጋማል የተባለ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ጋዜጠኛ November 21, 1988 ላይ በወጣ “Khaleeg” በተባለ ጋዜጣ ላይ “A visit to the Depth of the Desert” በሚል ርዕስ እንዲህ ጽፎ ነበር፡-

ስብከተ ወንጌል ።

11 Sep, 01:17


፣መምህር፣
ቀሲስ ህብረት፣የሺጥላ ለአዲስ ዓመት ያስተማሩት ነው ።
የትምህርቱ ርዕስ ፣
ይቺን ዓመት ተዋት ፣
ቢሰሙት ያተርፋሉ ።
(share ) JOIN
👇👇👇👇👇
@sebeketwongel
@sebeketwongel
@sebeketwongel

ስብከተ ወንጌል ።

12 Jul, 02:33


ተከታታይ ዩመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሰባተኛ ዙር ምዝገባው ለአንድ ሳምንት ተራዝሟል።For students who have just joined today and are not yet registered, please use this link to register.

https://forms.gle/Z8RTNQ3MsoXc3EzDA

ስብከተ ወንጌል ።

11 Jul, 13:29


መምህር ፣ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
የትምህርቱ ርዕስ = ቅዱሳን ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲሰሙት የቴሌግራሙን አድራሻ Share ያድርጉ
👇👇👇👇👇
@sebeketwongel
@sebeketwongel
@sebeketwonge

ስብከተ ወንጌል ።

10 Jul, 02:12


https://us02web.zoom.us/j/81873667259?pwd=R2ZGVWVEamhLZU5aVk1PeXhxcGFrdz09

ስብከተ ወንጌል ።

10 Jul, 02:12


ተጀምሯል ግቡ

ስብከተ ወንጌል ።

05 Jul, 16:27


ከተተረጎመበት ቋንቋ (source language) ጋር ማነጻጸር እና ማጥናት ተገቢ ነው። ይህ በየትም ሀገር የተደረገ እና እየተደረገ ያለ ቢሆንም በተለይም በእኛ ቤተ ክርስትያን ደግሞ የበለጠ ያስፈልጋል። ይህም የሚሆንበት ምክንያት በታሪክ አጋጠመውን የነበሩትን መለያየቶች እና ክርክሮች በትርጉም መጻሕፍት ላይ ያራሳቸውን አሻራ እንዳስቀመጡ የሚታወቅ ነገር ነውና። ስለዚህ ይህም እንደጊዜ ግብሩ ሊከወን ይገባዋል። አሁን ለዚህ ጽሑፍ አያስፈልግም እንጂ መለስተኛ ጥናቶች ካደረጉ ሰዎች እንደሰማሁት አስደናቂ ውጤቶችን አስተማሪ ክስተቶችን ያገኙ አሉ። ስለዚህ ለዚህም ተገቢውን ቦታ መስጠት አስፈላጊ ነው።

ማጠቃለያ

ነገረ-ክርስቶሳዊ ጉዳዮች በቀላል ብያኔ እና ፎርሙላ የሚያልቁ ሳይሆኑ ረቂቅ ምስጢር ያላቸው መሆናቸውን መገንዘብ ይገባል። ይህም ለመረዳት በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ቅጥነተ ህሊናን የሚጠይቁ መሆናቸውን እና ባሕርያችን ስለሚገድበን ዐውቀንም የማንጨርሳቸው ጉዳዮች እንዳሉት መገንዘብ ይገባል። ብያኔዎች እና ፎርሙላዎች በአንድ አቅጣጫ ትክክል ሲሆኑ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ አደናጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ዓውዳቸውን ጠብቆ በቅዱሳት መጻሕፍት በተነገሩበት መንገድ መቀበል ይገባል። በመሆኑም 'ይባላል አይባልም' ከሚል ውዝግብ ወጥቶ የሚባሉበት ዓውድ ምንድር ነው? የማይባሉበትስ? የሚለውን በትልቅ ጥንቃቄ እንደ ቅዱሳን አበው አስተምህሮ መረዳት ይገባል። በዚህም ያልተቀናነሰ እና በፎርሙላዎች ልክ ያልተሰፋ ርቱዕ መረዳትን ማግኘት ይቻላል።በተጨማሪም ንባቦችንም ምንጫቸውን በሚገባ መርምሮ ማጣራት እና ከሌሎች ጥንታውያን ቅጆች ጋር ማመሳከር ይገባል። በርግጥ ይህ ረጅም ጥረትን የሚጠይቅ ስለሆነ ትእግስትን ይጠይቃል።

መሠረታዊ ልዩነት በሌለበት የተለጠጠ ውይይት የምናካሒድ ሰዎችም ብናቆመው መልካም ነው። አሁን የታተመውን የነገረ ክርስቶስ መጽሐፍም በተባለበት ዐውድ ማለትም ከአጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት አንጻር መረዳት ይገባል። አንድን ሊያሰኙ የሚችሉ አገላለጾችን ደግሞ ከላይ እንዳልሁት የበለጠ በማብራራት እና ግልጽ በማድረግ እንደገና ማሳተም ይቻላል። ስለዚህ እርሱንም እየጠቀሱ መወዛገብ ምንም ትርጉም የሌለው ነገር ነው። ስለዚህ ሰከን ብለን ከሚያጠፋ እና ከሚለያይም ውይይት ተጠብቀን በመሠረታዊ ትምህርቶች እና ድኅነት ተኮር ውይይቶች ላይ ብቻ ብናተኩር የምናቀርብበትንም መንገድ በማስተዋል ብናደርገው የተሻለ ይሆናል። ሐሳብህን በአንድ ቃል ግለጸው ብባል ራሴን ዝቅ አድርጌ ንነጽር (እናስተውል) ነው የምለው።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

ስብከተ ወንጌል ።

05 Jul, 16:27


በርግጥ ለብዙ መፈራረጆችም ሆነ ድፍረቶች የጋበዘን ደግሞ በሀገራችን የዲስኮርስ ባሕል አለመኖሩ ሊሆን ይችላል። የተለያዩ እሳቦችን፣ አገላለጾችን፣ (ከመሠረታዊው ዶክትሪን እስካልተቃረን ድረስ) በየትምህርት ቤቱ እና አብያተ ጉባኤያት ቢለመድ ኖሮ እንዲህ በትንሽ በትልቁ ለመወቃቀስ እና ለመፈራረጅ አንበቃም ነበር። በሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያን ስናይም የብሒል ልዩነቶች አሉ። እነዚያን የሚያስተናግዱበት መንገድ ግን ሰላማዊ ነው። የብሒል ልዩነትን የሃይማኖት ልዩነት አድርገው አይመለከቱም። ይሄ ጉዳይ እንዲያውም አንድ ሰው ለተለያዩ ስሑታን ሲመልስ በዚያ አንድ ሰው ላይ እንኳ የመታየት እድል ይኖረዋል። ለምሳሌ አንዳንድ አጥኚዎች ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ለሰማንያ የስሕተት ትምህርቶች መልስ የሰጠበት ፓንርዮን (Panarion) (ታቦተ መድኃኒት፣ ማኅደረ መድኃኒት እንደማለት ነው) በተባለ መጽሐፉ ላይ ያነሱበታል። ይህ የሆነው እንደ ጊዜ ግብሩ የተለያዩ ብሒሎችን አቀራረቦችን ተጠቅሞ እንጂ ራሱን በራሱ ሊቃረን ፈልጎ አይደልም። እንዲህ ያሉትን እየተረዳን የውይይት ባሕላችን እያሳደግን ብንሔድ እንጠቀማለን እንጂ አንጎዳም፤ ሰይጣን ግን በሌላ መንገድ ሥራችንን እንቅፋት ይፈጥረበታል። ይህን ክፍል በዚህ ጉዳይ ልቋጨው።

ለብዙ ሰዎች የሚታወቅ ቢሆንም ሰይጣን ሥራችን የሚያበላሽበትን ብልሃት ጨምሬ ማስታወስ እፈልጋለሁ። ከንባባቼ ደጋግሜ ካገኘሁት ውስጥ ብዙ ቅዱሳን እንደሚሉት ከሆነ ምንም ያህል ጥሩ ነገር ብናደርግ ሰይጣን ጥሩ ነገርን እንዳይጠቅም የሚያደርገው እግዚአብሔር በማይፈቅደው መንገድ እንድንፈጽመው በማድረግ ነው ። ስለዚህ ከድርጊቱ እኩል የምናደርግበትን መንገድ ኦርቶዶክሳዊነት መመርመር እና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ሳንጋጭ ይልቁንም ደግሞ ያለትዕቢትና ሌሎቹን ለማጥቃት ወይም ለመፈረጅ ባለመቸኮል መሆንኑ በልባችን ውስጥ ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ይህን ማድረጋችንንም ለሰዎች ለማስረዳት መሞከር አይጠበቅብንም። በራሳችን ልብ ውስጥ ይህ ችግር እንደሌለ ከንዴት እና ከሰሜት ነጻ ሆኖ ማረጋገጥ እንደምናስበው ቀላል ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም አእምሮአችን ምንጊዜም የራሱን መረዳት ትክክል እንደሆነ ስለሚያሳምነን ችግሩ ሌሎች ጋር እንጂ እኛም ጋር ሊኖር እንደሚችል እንዳንስብ ይዘጋብናል። ብዙ ቅዱሳን እንደሚሉት ይህን ማየት የሚቻለው ነፍሳችን እያለቀሰች መጸለይ ስትችል ነው። ይህ ከሆነ አላስፈላጊ ውይይቶች ፣ ትምህርቶችም ሆኑ ሌሎቹ ነገሮች እንደሚቆሙ ምንም ጥርጥር የለኝም።

4) ችግሮቻችን ለመፍታት ማድረግ የሚገባንን በተመለከተ

ችግሮቻችን ከላይ ካልነውም ሰፋ ሊሉ ይችላሉ። አሁን የተጀመሩም ላይሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ጥልቅ ጥናትና ውይይት ሁሉ ሊፈልጉ ይችላሉ። ሌላው ቀርቶ አሁን የተፈጠረችው ትንሽዬ ልዩነት እንደ በጎ ዕድል ወስደን ከተጠቀምንባት ሌሎች ነባርም ሆኑ ጊዜያዊ ችግሮችን ለመፍታት በር የሚከፍት መንገድ ሊያስገኝልን ይችላል። በተለይ በተለይ ሊቃውንት ጉባኤው እና የተለያዩ ከፍተኛ መንፈሳዊያት የትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳዊ ሥነ ዘዴያቸውን የጠበቁ የጥናት እና የምርምር መንገዶችን በመጠቀም ድርሻቸውን ቢወጡ ብዙ ችግሮችን ማቃለል ይቻላል። ይህ እንኳ ባይሆን ደግሞ ችግሮቻቸን እየፈታን እምነታችን እያጸናን፣ ልዩነቶችን እያጠበብን ለመሔድ የሁላችንም ድርሻ ቀላል አይደለም። በተለያዩ ገድላት፣ ድርሳናት እና ሌሎችም መጻሕፍት ላይ ተቺዎች እና ነቃፊዎች ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች ጀምሮ ሊሎች ጥይቄዎችን መመለስ እና ልዩነቶችን እያስወገዱ ችግሮችን እየፈቱ መሔድ ተገቢ ነው፤ ይቻላልም ብዬ አስባለሁ።

ለዚህ ሁሉ የሚያስፈልገው ደግሞ ከላይ እንደገለጽኩት በትሑት ሰብእና ሆኖ ሌላውን ከመፈረጅ እና ክፍፍል ሊያመጣ ከሚችል መንፈስ መጠበቅ ነው። የሌሎችን ሀሳብ በቅንነት ለመረዳት እየጣርን፣ ያልገባንን በጥያቄ እየመለስን፣ ለማናውቀው ጊዜ እየሰጠን ፣ ከግለሰባዊ መረዳት ይልቅ ለሃይማኖታዊ ምሥጢራት ቦታ እየሰጠን ብንሔድ ብዙ ችግሮ ሊፈቱ ይችላሉ ብዬ አምናለሁ።

አሁን ያለው ሁኔታ ግን በእጂጉ አሳሳቢ ነው። እውነት ለመናገር አሁን ያለውን ውዝግብ፣ መፈራረጅ፣ አለመደማመጥ እና ውዝግቡን ሳየው አንድ ነገር ያስታውሰኛል። ቤዛንታይን ቱርክ ከመሆኗ በፊት በጥንቷ ቁስጥንጥንያ በአሁኗ ኢስታንቡል በክርስቲያኖች ዘንድ ይሆን የነበረውን የጻፈ አንድ ጸሐፊ ላይ የገለጸው ነገር ልክ በዓይኔ እንዳየኋቸው ሁሉ ይመጣብኛል። ጸሐፊው እንደሚለው ገበያ የሚሔደው ተራው ሰው ሁሉ በማያገባው ከመወያየቱ የተነሣ ገበያ እየሔደ እንኳ መንገድ ላይ አብ ይበልጣል ወይስ ወልድ እያለ ይነጋገር ነበር ይላል። ያ እንግዲህ ከመጥፋታቸው በፊት መጥፋት ይገባቸው እንደነበረ ከሚያሳዩ ምልክቶች አንዱ ተደረጎ ስለተወሰደ ነው የተጻፈው። እኔም ያነሣሁት እኛም ጋር ያለውን ሁኔታ ሳየው ያን እየመሰለኝ ስለተቸገርኩ ነው ። ድኅነታችን በማይከለክሉ፣ ቅጥነተ ኅሊና እና እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ወይም ተጋድሎ ከፍጹም ትሕትና ጋር በሚፈልጉ ጉዳዮች እንደፈለጉ እዚያውም በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገር ጥቅሙ አይታየኝም። እንዳልሁት እንዲህ ያለው ነገር ጥፋት ያመጣ እንደሆነ እንጂ ችግር አይፈታም። ችግሮቻችን ለመፍታት መንገዱ በየሚዲያው መወዛገቡ አይመስለኝም። በርግጥ ውይይት የሚያስፈልገውም ነገር ካለ በአግባቡ ተገናኝቶ መወያየት እንጂ ውዝግብ አይጠቅመንምና እናስተውል። በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የምናስተምር ሰዎችም ቢሆን መልካሙንና ጥቀሚውን ተግባር ሰይጣን በማይጠቅም መንገድ እንዳያሠራን በአግባቡ ራስን ጠብቆ ፣ በጸሎት፣ በትዕግሥት እና በማስተዋል አጥር ውስጥ ሆነን ብቻ ልናደርገው ይገባል።

5) ዕቅበተ እምነትን በተመለከተ

የዕቅበተ እምነት ተግባር ቀላል ተግባር አይደለም። ይህን በተመለከተ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጽሑፎች ያነሣኋቸው ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆነው ሁለት ጉዳዮች ላይ ግን ዛሬም አጽንዖት መስጠት እፈልጋለሁ። የመጀመሪያው እቅበተ እምነት በጽሑፍ ወይም በሌላ ከመገለጹ በፊት በሕይወት የሚጠበቅ መሆኑን ደግሜ ማስታወስ እፈልጋለሁ። ይህም ማለት ራዕይና የተለየ መገለጥ መጠበቅ ተገቢና አስፈላጊም ባይሆንም ከእግዚአብሔር የምትገኝ እርዳታን የምትሻ ልቡና እና ወደዚያ የሚያመራ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚጠበቅ መሆኑን መርሳት የማይገባ ይመስለኛል። በአንዳንዶች ያየሁት ግን አሳሳቢም አስፈሪም ነው። ሰዎችን ለመሳደብ ፣ ለመንቀፍ እና ከፍ ዝቅ ለማድረግ የሚደረገው ነገር እንኳን ሃይማኖትን ለመጠበቅ በዚህ ዓለም ለሚደረግ የፖለቲካ ውይይት እንኳ እጂግ ጸያፍ እንደሆነ አምናለሁ። በእንዲህ ዓይነት ሰብእና የሚጠበቅ ሃይማኖት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። እንዲህ ያለውን ድርጊት ዕቅበተ እምነት አድርጎ መውሰድም አይቻልም። እንዲያውም ለእግዚአብሔር እቆረቆራልሁ በሚል ሰበብ ራሱ እግዚአብሔርን ከመሳደብ የሚለይ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ዕቅበተ እምነትም የለም።

ሁለተኛው ደግሞ ምንጭ አጠቃቀማችን የተመለከተ ነው። ይህ ጉዳይ ብዙ ማስተዋል የሚፈልግ ነው። የመጀመሪያው ትልቁ ነገር መጻሕፍትንም ሆነ ሊቃውንትን ከጻፉበት እና ከተናገሩበት ዐውድ አንጻር በአግባቡ ለመረዳት መጣር ተገቢ ነው። እንዲህ ባልሆነበት ቀላሉ ነገር ሊከብድ ይችላል። ሁለተኛው ደግሞ መጻሕፍት ወይም ምንጮቹ ላይ አለመስማማት ካለ በዚያም ላይ ማጥናት ተገቢ መፍትሔ ነው። በተለይ ልዩነት ሲመጣ አንዳንድ ጉዳዮች ጥልቅ ጥናት በማድረግ ከሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያን ካሉ ድርሳናት ይልቁንም መጽሐፉ

ስብከተ ወንጌል ።

05 Jul, 16:27


ስለነበረ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት ለማሳየት በርካታ ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ሁሉ እንደሌሉ ቆጥሮ ከአጠቃላይ ይዘቱ እና ለውይይት የቀረበችውንም ኃይለ ቃል ከዐውዱ አውጥቶ ማየቱ እንደ ድክመት የሚወሰድ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ጠቀሜታም አይኖረውም። ስለዚህ አንድን መጽሐፍ በአጠቃላይ ይዘቱ ማየት ለማንኛውም መጽሐፍ መቼም ሊደረግ የሚገባው መሠረታዊ ነገር ነው ብዬ አምናለሁ። የተለየ ፍላጎት እስከሌለ ድረስም መደበኛው መተቻም ሆነ ማቅኛ መንገድ ይህ እንደሆነ ይሰማኛል።

ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሁለት አነሥተኛ ጉዳዮች ወይም ደጋፊ ጉዳዮች ተነሥተው ሊታይ ይገባል ። የመጀመሪያው ለውይይት በር የከፈተው ኃይለ ቃል የተባለበትን ዐውድ ጠንቅቆ መረዳት ነው። ለምሳሌ በዚህ መጽሐፍ የተነሣው ጉዳይ ለተሐድሶዎች ወቅታዊ ጥያቄዎች በመልስነት የተዘጋጀ ነበር። ሆኖም እንደ ችግር የሚነሣው ጉዳይ የትኛው የውይይት ርእሰ ጉዳይ ላይ እንደነበረ አሁን ላይ አላስታውስም። መጽሐፉን የሚያነብቡ ሰዎች ውይይቱ እንደወረደ በጽሑፍ የቀረበ ከሆነ ግን ይህን ዐውድ ይዘው ማየት ይችላሉ። እስከማስታውሰው ደረስ የውይይታችን ዋና ትኩረቱ በሥጋው አሁንም ይማልዳል ወይም ከቅዱሳን ምልጃ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ይማልዳል የሚል ትምህርት ያላቸው አካላት የሚጠቅሷቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች የተከተለ ነበር። የእኛም የመልስ አቅጣጫ ያን አስተሳሰብ መሞገት እና በተቻለው መልስ መስጠት ነበር።

ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ዐውዱ ይህ ቢሆንም ዳሕጽ አለው ወይም ደግሞ እንዲህ ሊያሰኝ ይችላል የሚባል ጉዳይ ካለው እርሱን ነቅሶ አውጥቶ በተለየ መንገድ ማብራራት ነው። ይህ ቅድመ ኅትመት ቢደረግ ያማረ ይሆን ነበር። ሌላው ቀርቶ አርታኢው ለቪዲዮው ታማኝ ለመሆን ሲል (ተወያዮቹ በቃል ያሉትን ትቶ አርታኢው አዲስ ነገር አመጣ እንዳይባል ፈርቶ) እንዳለ ቢያመጣው እንኳ ማብራሪያውን በግርጌ ማስታወሻ ማድረግ ወይም ተወያዮቹን አነጋግሮ ካስተካከሉ በኋላ በመግቢያው ላይ ይህ መደረጉን ለአንባቢ በማሳወቅ ሊዘጋጅ ይችል ነበር። ይህ ዕድል በርግጥ አምልጧል። ሆኖም ችግሩ ሊያሰኝ ይችላል የሚባል እስከሆነ ደረስ (አሁን እየተባለ ስልሆነ) ይህ መጽሐፍ ወደፊትም ከዚህ የተለየ ተግባር የሚፈልግ ነገር ይኖረዋል ብዬ አላስብም። ማኅበሩ ሊያደርገው የሚገባውም ይህንኑ ነው ብዬ አስባለሁ።

ከዚህ በላይ ጉዳይ ወይም ትኩረት የማይፈልገውን ነገር ወደዚህ ያደረሰው በቲክታክ የሚወያዩ ሰዎች ለሀሳባቸው ድጋፍ ይሆነናል ያሉትን ብቻ ቆርጠው መጠቀማቸው ሊሆን ይችላል። ሆኖም መንገዱን አስተካክለው እንዲጠቀሙ እየረዱ እግረ መንገዱንም ከመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት እና ከተነገረበት ዐውድ አንጻር እያዩ መጠቀም እየተቻለ ወደ ተለጠጠ ክርክር መውሰድ ልጆቹንም በጉድለታቸው መስደብና ማዋረድ ጉዳቱ እንጂ ጥቅሙ አይታየኝም። ሃይማኖት ሁልጊዜም የሚፈልገው በተቻለው መጠን ሁሉ ትክክሉን ማድረግ ብቻ ነው። ጌታ የሳተውን የወደቀውን ለማዳን መጥቷል፤ ይህንም ልታውቅ እፈልጋለሁ የሚል ሰው እንዴት የሚያስት እና የሚያደናቅፍ ነገር ያደርጋል? በነገረ ድኅነት ላይ እየተወያዩ ግብረ ድቀትንስ ማስፋት እንዴት ያለ ተቃርኖ ነው? የወደቀ እንኳ ቢኖር ከቻልን እንደ ደጉ ሳምራዊ የወደቀውን ማንሣት ፤ ካልሆነ ቢያንስ አልፈው ከሔዱት እንኳን አንሰን እንዴት እንገኛለን?

2) የተነሣውን ጉዳይ በተመለከተ

የተነሣውን ጉዳይ ለምን ተነሣ፣ እንዴት ተነሣ ማለት ብዙም ጥቅም ስለሌለው ጉዳዩ ተሳታፊዎች ላይ ባለኝ አስተያየት በአጭሩ አስተያየቴን እሰጥበታለሁ። ስለነገረ ሥጋዌ የጠራ እምነት ሲቻልም ዕውቀት መፈለግ መልካም ነገር ነው። ሆኖም ችግሩ የመጣው በማስተማር ሒደት ላይ ነው። ማስተማር መልካም ቢሆንም ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ ግን አሁን እንደሆነው ያለ መለያየትን ወይም መነቃቀፍን ሊያስከትል ይችላል።

በእኔ እምነት በሁለት ወገን ከሚካሔዱት ተወያዮች ውስጥ እኔ ካየኋቸው መሠረታዊው የተዋሕዶ አስተምህሮ ላይ ልዩነት አላየሁም። ለምሳሌ ቃል የነሣው ሥጋ ከእመቤታችን አይደለም፣ ወይም ፍጡር አይደለም ወይም የሰው አይደለም የሚል አላየሁም። ቃል ከሥጋ ጋር አልተዋሐደም የሚልም አላየሁም። ተዋሕዶው በተዐቅቦ አይደለም የሚልም አልገጠመኝም። አውጣኪያዊም ሆነ ንስጥሮሳዊ ትምህርት አላየሁም። ውላጤም ምንታዌም አላጋጠመኝም። ኅደረትም ሆነ ሌላ አላየሁም። አንዱን የአንዱን ይዘሃል ወደዚያ ታጋድላለህ ከሚለው ፍረጃ በቀር አንድም ሰው እንዲህ ነው ሊያሰኝ የሚችል ነገር ሲገልጽ አላጋጠመኝም። ባይሆን እንዲህ እንዳልባል ብሎ ሲሸሽ ወደሌላው ሔድክ የሚል የተቃራኒ ትችት ግን ይታያል። እንጠነቅቃለን ወይም የሌላውን ስሐተት ተረድተናል ከሚል መልስ እና መገፋፋት የተነሣ ከሚያመልጡ ዳሕጾች ባለፈ መሠረታዊ አዲስ አስተምህሮም ሆነ ችግር ቢያንስ ለእኔ አልታየኝም። አካሔዱ እና ውይይቱ ግን ምንም የሚያንጽ ነገር አላየሁበትም። ያ ደግሞ ከውይይት ባሕላችን እና ከሰብአዊ ድካማችን የሚመነጭ ስለሆነ ወደዚያ ላምራ።

3) ውይይቶችን በተመለከተ

ውይይቶችን ብዙዎቹን (በተለይም በቲክታክ ያሉትን ተቆራርጠው ከተላኩልኝ በቀር) አላየሁም። ከተላኩልኝ እና ከነገሩኝ ሰዎች ተነሥቼ ሳይ ውይይቶቹ ላይ የሚታዩኝ ድክመቶች አሉ። የመጀመሪያው እና ዋናው ችግር ነው ብዬ የማስበው ነገሩን ተጠናቅቆ የማወቅ እና የማስተማር ችሎታ እንዳለ ከሚያምን ልቡና የሚመነጭ ይመስለኛል። ይህ በጣም የማይቻል እና አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን በትክክል እንግለጸው ከተባለም ወደ ትዕቢት የሚወስድ መንገድ የሚከፍት ይመስለኛል። ከዚህም ሁሉ በላይ ውይይቱ በምናደርግበት ወቅት ያለው መንፈስ የማሸነፍ እና ያለመሸነፍ መንፈስ ያየለበት መሆኑ ሰብአዊ ድካማችንን ጉልህ ያደርገዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ነገረ እግዚአብሔርን ነገረ ክርስቶስን ወይም ትምህርተ ሥጋዌን ያህል እጂግ መንፈሳዊ ምሥጢር በእኛ አእምሮ የመረዳት እና የማስረዳት ችሎታ ላይ ወስኖ መናገር ከባዱ ችግር ይመስለኛል። በተለይ ከአንዳንዶቻቸን ደግሞ (መማራችን እና ማንበባችን ያላቸው ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ) በትምህርታችን እና በንባባችን የምንመካበት ሁኔታም እንዳለ ንግግራችን ይጠቁማል። ይህም ችግሩ የትምህርቱ ወይም የንባቡ ሳይሆን የተማረው እና የአንባቢው ማለትም የሰውየው ችግር መሆኑን ያመለክታል። የነገረ ሃይማኖት አስተምህሮዎች እንደ ሳይንስ በግለሰቦች የመረዳት አቅም ላይ የተንጠለጠሉ በአመክንዮቻቸውም ላይ የተመሠረቱ እንዳልሆነ የታወቀ ቢሆንም መሠረታቸው ግን ፍጹም በሆነ ትሕትና ውስጥ ሆኖ ጸጋ እግዚአብሔርን ተደግፎ የሚደርግ ትምህርት ንባብ መሆን ይገባዋል። አሁን የቸገረንም ይህ ይመስላል። በተለይ ጥቂት ወጣቶች ላይ ይህ ጉድለት ጎላ ብሎ የታየኝ መስሎኛል። ሆኖም እይታው የግሌ ስለሆነ ስሕተት ካለበት በተገቢው መንገድ ካሳወቃችሁኝ ሀሳቤን በዚያ መሠረት አስተካክላለሁ። ስለዚህ ውይይቱ በመሠረታዊነት ይህ ችግር ያለበት ይመስለኛል። በብዙ ቅዱሳን ትምህርቶች እና ምክሮች ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ሁልጊዜም ኑፋቄ የሚወለደው ዶክትሪንን በራስ መረዳት ላይ ለማስተማር በሚደረግ ሒደት ነው። ስለዚህ ይህ አሁን የተፈጠረውን ጉዳይ ሰክነን በማየት ብንመለስ እና መንገዱን ብናርመው ለወደፊት ከሚመጣ አደጋ ልንጠበቅ እንችላለን፤ ካልሆነ ግን ዛሬ ባይሆን ነገ በዚህ መንገድ ውድቀት ሊያስከትልብን የምንችል ሰዎች መኖራችን አይቀሬ መስሎ ስለተሰማኝ ነው ያነሣሁት።

ስብከተ ወንጌል ።

05 Jul, 16:27


ከመምህር ብርሃኑ አድማስ


ንነጽር
(ሰሙናዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠች አስተያየት)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክርስቶስ “በሥጋው ፍጡር” ይባላል አይባልም የሚል ክርክር በማኅበራዊ ሚዲያው ውስጥ ሰፋ ያለ ውይይት እየተካሔደበት እንደሆነ ፤ ከዚያም አልፎ አንዱ ወገን ሌላውን ወገን ከቀደሙ እና ከተወገዙ መና*ፍቃን ሀሳብ ጋር እያዛመደ ከዚህ ነህ፣ ከዚያ ነህ፣ እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ በሚል እስከ መፈራረጅ እና መነቃቀፍ የደረሱ ክርክሮች አንዳሉ ሰምቻለሁ፤ ጥቂቶቹንም አይቻለሁ። በቲክታክ የሚደረገውን አካውንትም ስለሌለኝ ማየት አልቻልኩም፣ ደግሞም አልፈልግምም። በአብዛኛው ጊዜ ፌስቡክ ገጼንም ዝግ (deactivated) አድርጌው ስለነበር በፌስ ቡክ ያለውንም አልተከታተልኩም። ሆኖም ጥቂት ወንድሞች በቴሌ ግራም እና በመሴንጀር የላኩልኝን ውስጥ በጣም ጥቂቶቾን በተወሰነ ደረጃ ለማየት ችያለሁ። በዚሁ ላይ ደግሞ ሰሞኑን የእኔም ስም ከአዘጋጆቹ አንዱ እንደሆንኩ በሚገልጸው እና ማኅበረ ቅዱሳን ባሳተመው የነገረ ክርስቶስ መጽሐፍ ላይ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ባላቸው አገላለጾች መነሻነት ክርክሩ እንዳገረሸ እና ያልተገቡ አነጋገሮች እንደበረከቱ አለፍ ብሎም መፈራረጆችን እና መነቃቀፎችን መሠረት ያደረገ የሚመስል የመከፋፈል ጠባይ እየታዬ እንደሆነ የተሰማቸው ወንድሞች ቢያንስ በጉዳዩ ላይ ሀሳቤን እንዳካፍል ከላኳቸው መልእክቶች ተረድቻለሁ። በዚሁ መሠረት እኔም በጉዳዩ ላይ ሊደረግ የሚገባውን በተመለከተ ሀሳቦቼን በቅደም ተከተል እንደሚከተለው ለማስረዳት እሞክራለሁ።

1) የታተመውን መጽሐፍ በተመለከተ

ማኅበረ ቅዱሳን ሰሞኑን አሳትሞ ለኅትመት ያበቃው መጽሐፍ ከጥቂት ዓመታት በፊት በወቅቱ ከተሐድሶዎች በኩል ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ እንዲሆኑ በቀረቡ እና በቴሌቪዥን ከተላለፉ ተከታታይ ውይይቶች ላይ ተወስዶ የተዘጋጀ እንደሆነ የታወቀ ነው። በቃል የተላለፉ ትምህርቶችን በጽሑፍ መልክ አዘጋጅቶ ማሳተምም በተለይ በሌሎች አብያተ ክርስቲያን በጣም የተለመደ ተግባር ነው። በእኛም መጠነኛ ልምምድ ሳይኖር አይቀርም። ሆኖም ንግግሮች ወደ ጽሑፍ ሲቀየሩ ሊደረግ የሚገባው ሒደት እንደየሁኔታው በጣም የተለያየ ነው። ለምሳሌ ያህል ስብከቶችን ለማሳተም የሚፈልግ እና አንድ ጉባኤ ወይም ስብሰባ ላይ የቀረቡ የመግቢያ፣ የማጣቃለያ ወይም ደግሞ ለውይይት የቀረቡ ጽሑፎችን ለማሳተም አርትዖት የሚሠራበት መንገድ አንድ ዓይነት ሊሆን እንደማይችል ለመረዳት አስቸጋሪ አይመስለኝም። እንደታተመው መጽሐፍ ያሉ የውይይት ጉዳዮችም ራሱን የቻለ መንገድ ሊከተሉ ይችላሉ። ክርክሮች ሲሆኑ ደግሞ ፈጽሞ የተለየ መንገድ ሊከተሉ ይችላሉ።

በመሠረቱ አብዬ መንግሥቱ ለማ በትዝታ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ መጽሐፍ መቅድም ‹‹መቼም ሰው እንደ መጽሐፍ አይናገርም፤ እንደ አነጋገሩም መጽሐፍ አይጽፍም፡፡ ለሁለቱም ስልት አለው፡፡›› ሲሉ ጥሩ አድርገው እንደገለጹት ነው። በዚህ ረገድ በማኅበሩ የታተመው ይህ ጽሑፍ ከላይ እንደተገለጸው ከንግግር የተወሰደ ስለሆነ ቁጭ ተብሎ ተመክሮ እንደተጻፈ መጽሐፍ ሊሆን አይችልም። ንግግሩ ወይም ውይይቱም በጉባኤ ውስጥ የሚቀርና ለውስን ሰማዕያን የተዘጋጀ ተዋሥኦም አልነበረም፡፡ ለበርካታ ምዕመናንን ቀለል ባለ ቋንቋ የቀረበና በአቀራረቡም በስብከትና በተዋሥኦ መካከል ሊመደብ የሚችል ነው፡፡ ከዚህ ተነሥቶ የተናጋሪዎችን አቋም መበየንም ሆነ ምስክር ማድረግ ምሉዕ ሥዕል የማይሰጥበት ዕድል እንዳለ ለመረዳት የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ በውስን ሰዓትና ዐውድ የተነገረ ቃላዊ ስብከት/ተዋሥኦ ስለሆነ፡፡

ይህ የታተመው መጽሐፍ በምን ዐይነት መንገድ በጽሑፍ እንደተዘጋጀ አላወቅሁም። በርግጥ መጽሐፍ ሆኖ እንደሚዘጋጅም ሆነ ሲዘጋጅም አላውቅም ነበር። ያወቅሁት ታትሞ ከወጣ በኋላ አሁን ወዳለሁበት ሀገር በምሔድበት ዕለት ነበር። በበረራየ ዕለት አምጣልኝ የተባልኳቸውን መጻሕፍት ለመግዛት የማኅበረ ቅዱሳንን የመጻሕፍት ማከፋፈያ እና ሌሎቹንም ለመመልከት በሔድሁበት ጊዜ አንድ ወንድማችን ጋር ቆም ብዬ በምነጋገርበት ሰዓት የክፍሉ ሓላፊ በዚያ ሲያልፍ ሰላምታ ሰጥቶኝ ወደ ቢሮ ከገባ በኋላ መጽሐፉን አምጥቶ ሲሰጠኝ ብቻ ነው መዘጋጁትን እንኳ ያወቅሁት። እኔም መጽሐፉን ቤቴ ትቼ ማታውን ወደ መንገዴ ስለወጣሁ ይዘቱን ቀርቶ መግቢያውን እና ማውጫውንም አላየሁትም።

መጽሐፍ ሆኖ በመዘጋጀቱ ተቃውሞ የለኝም። የቅጅ መብቱም የማኅበሩ ስለሆነ እኔን ለምን አላሳዩኝም የሚል ቅሬታም የለኝም። ሆኖሞ ቀድሞ ቢያወያዩን ኖሮ ይጥቀምም አይጥቀምም እኔ በግሌ አንዳንድ አስተያየት መስጠቴ አይቀርም ነበር። በርግጥ ቢያሳዩን ወይም ቢያወያዩን ኖሮ አሁን ያለውን ሁኔታ ሊቀይረው ይችል እንደነበር እርግጠኛ ልሆን አልችልም። በይዘቱ ወይም በአቀራረቡ የሆነ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ግን መገመት አያስቸግርም። ይህን ያላደረጉት ግን በተለይ እኔን ባለብኝ ጫና አዝነውልኝ እንደሆነ ይሰማኛል። የሆነው ሆኖ መጽሐፉ ላይ ያሉ አገላለጾች አሁን በሚባለው መንገድ ሊያወያዩ እንደማይችሉ ደግሞ በደንብ እረዳለሁ።

መጽሐፉ ላይ የሚሰጡት አስተያየቶች በዚህ መጠን ሊያወያዩ አይችሉም የምለው በአንድ መሠረታዊ እና በሁለት ደጋፊ ምክንያቶች ነው። አንድ መጽሐፍ የሚተች ወይም ግምገማ የሚያደርግ ሰው መጀመሪያ የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት ምን እንደሆነ፣ ምን ላይ እንዳተኮረ፣ ለምን ጉዳይ እንደተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ይህን በሚያደርግበት ጊዜ መሠረታዊ ይዘቱ ችግር አለበት ብሎ ካሰበ በዚያ መጠን ሊተቸው ይችላል። አጠቃላይ ይዘቱ ትክክል ሆኖ የተሳቱ ነገሮች ካሉ ደግሞ ያም ለምን እንደሆነ ይመረምራል። ምክንያቶቹ ዳሕጽ ናቸው? ከአርትዖት ጉድለት የመጡ ናቸው? ወይስ ዐውዳዊ ይዘት አላቸው የሚለውን እና ሆነ ተብለው በዓላማ የተደረጉ ናቸው የሚለውን ከመጽሐፉ ይዘት ለመረዳት አያስቸግርም ብዬ አምናለሁ።

ለምሳሌ ይህ መጽሐፍ አጠቃላይ ጉዳዩ ነገረ ክርስቶስ የሚመደብ (ስለተባለም) ስለሆነ ብዙ ተወያዮች አሁን የሚያነሷቸው ጉዳዮች (አሁን በዝርዝር ባላስታውስም) ተዳስሰውበታል። ተዋሕዶ በተአቅቦ መሆኑ፣ የነሣው ሥጋ የእኛ የፍጡራን ወይም የሰው መሆኑ፣ ይህም ከእመቤታቻን ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም የነሣው መሆኑ፣ ... የመሳስሉት ብዙዎቹ ነገሮች ተነሥተውበታል፣ ተካትተውበታል። ነገር ግን የቃል ውይይት በመሆኑ ለተወያዮቹ በጊዜው እንደታሰባቸው፣ ያልተነሣ ብለው ያሰቡትን ለማካተት እና ለማጽናትም በሚል ስለሚሆን ቁጭ ተብሎ በማጠቀሻ እንደተጻፈ መጽሐፍ ዓይነት ይዘት ሊኖረው አይችልም። ይህ ማለት ደግሞ መሠረታዊ ይዘቶችን አልያዘም ማለትም አይደለም። ስለዚህ የተባሉትን ነገሮች በመጽሐፉ እንደሌሉ አድርጎ እና መሠረታዊ ይዘቱን ትቶ አንዲት ኃይለ ቃል ላይ ብቻ አተኩሮ ብዙ ማለቱ ተገቢነቱ አይታየኝም። እንዲያውም አንድ ትጉህ ሰው መጽሐፉን አንብቦ የመጽሐፍ ግምገማ ቢጽፍበት መጽሐፉን የሚነቅፉ ሰዎች የሚያነሷቸው ሀሳቦች ብዙዎቹ ምናልባት ሁሉም ሀሳቦች በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚገኙ ጥርጣሬ የለኝም። እስከማስታውሰውም ድረስ የውይይታችን ትኩረት ወደ ነገረ ድኅነት ያደላ ይመስለኛል። ውይይት ስለሆነ ብዙ ነገሮችን መዳሰሱ ባይቀርም ከኩነታዊ ነገር ክርስቶስ ይልቅ ወደ ግብር፣ ይልቁንም ወደ ነገረ ድኅነት ያደላ ነበረ፡፡ በዚያ ሒደት በተሐድሶዎች ዘንድ ክርስቶስን በትሑታን ግብራት የመግለጥና የማዳን ሥራውን ከቅዱሳን ምልጃ ጋር ማነጻጸር ተደጋግሞ ይሰማ

ስብከተ ወንጌል ።

03 Jul, 01:10


ዛሬ DC ሰአት 10:00 pm ለዚህ የሚያጠፉት ጊዜ አይቆጭም።
አምስተኛ ክፍል ትምህርታችንን እንቀጥላለን። ትምህርቱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ላላችሁ ሁሉ ክፍት ነው።


“ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን” ዕብ 1:2


ከታች ባስቀመጥነው የzoom link በመጠቀም ይቀላቀሉን!

https://us02web.zoom.us/j/81873667259?pwd=R2ZGVWVEamhLZU5aVk1PeXhxcGFrdz09

ስብከተ ወንጌል ።

26 Jun, 11:18


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመማር አስበዋል ይህ እድል እንዳያመልጥዎ።
ለሰባተኛ ዙር ምዝገባ ይህንን ማስፈንጠሪያ ( ሊንክ) ይጫኑ ።
https://forms.gle/Z8RTNQ3MsoXc3EzDA

ስብከተ ወንጌል ።

26 Jun, 01:09


ለዚህ የሚያጠፉት ግዜ አይቆጭም
ዛሬ ዘወትር ማክሰኞ በዲሲ 10:00 PM
ረቡዕ ሰኔ 19 አጥቢያ 11 ሰዓት (በኢ/ያ አቆጣጠር) አራተኛ ክፍል ትምህርታችንን እንቀጥላለን። ትምህርቱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ላላችሁ ሁሉ ክፍት ነው።


“ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ” ዕብ 1:1


ከታች ባስቀመጥነው የzoom link በመጠቀም ይቀላቀሉን!

https://us02web.zoom.us/j/81873667259?pwd=R2ZGVWVEamhLZU5aVk1PeXhxcGFrdz09

2,058

subscribers

77

photos

5

videos