የእግዚአብሔር ወንጌል @gospel_of_god Channel on Telegram

የእግዚአብሔር ወንጌል

@gospel_of_god


የእግዚአብሔር ወንጌል (Amharic)

የእግዚአብሔር ወንጌል የእምነትን እንቅስቃሴን መስሎት ነገሩን ለመግባት እና በደስታ የሰጠን ባህርያት ተወካዮችን በመስራት ለመደጋገም የሚጠየቁ የቴሌግራም አፕናሽናል መሳሪያ ነው። ይህ አፕናሽንን በማስታወቂያ ያስተላለፉን ወንጌላችንን በመደጋገም እና በመረጃ እንዲወስዱ ያስቻሉ። ይህን አቅርቦት ዋጋ።

የእግዚአብሔር ወንጌል

23 Nov, 02:09


በኃጢአት የወደቀ ሰው ልበ ስውር ነው። ሰይጣን ልቡን የሚቆጣጠረው ነው። (የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። 2ቆሮ 4V4) በጉልበት፣ በዘዴ፣ በትምህርት በመሄድ መላቀቅ አይቻልም። የመገለጥ ብርሃን እስካላገኘ ድረስ በውርቅ ብታሽቆጠቁጠው፣ በድንቅ ነገሮች ብትከበው፣ [ሁሉም ቦታ] ብትወስደው፣ የዓለምን [ድንቃ ድንቅ] ነገሮች ብታስረክበው ምንም ነው፤ በጨለማ የተያዘ ሰው የታሰረ ነው።
ነገርግን "በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፡” ያለ እግዚአብሔር ነውና። (2ቆሮ 4V6)
እግዚአብሔር ራሱ በሰው ልብ ይበራል!!

     __ሰለሞን አበበ ገብረመድህን

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

06 Nov, 01:21


ኢየሱስ የኖረውም የሞተውም ለታሰሩት ነፃ መውጣትን፣ ለዕውሮች ማየትን፣ ለተሰበሩት መፈወስን፣ ለኃጢአተኞች  መዳንን ልሰጥ ነው።

      —Alistair Begg

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

28 Oct, 12:58


ለክርስቶሱ ያልተኖረች ነፍሴ ረብ የለሽ ናት።
ለእግዚአብሔር መንግሥት ያልፈሰሰ ጉልበቴ የባከነ ነው።
ለእግዚአብሔር ክብር ያልተኖረ ዕድሜዬ ከንቱ ነው።
ወንጌለ መለኮትን የማይሰብክ እስትንፋሴ ቃና ቢስ ጩኸት ነው።
ለኢየሱስ ጌታነት ያልታመነ ኑሮ ሊኖር ያልተገባው ነው።
እጅግ አስፈላጊው ደግሞም አንገብጋቢው ጉዳይ በምንኖራት አንዲት ሕይወት በፍርድ ቀን የማናፍርበት ምልልስ ይኖረን ዘንድ ወደ ፍጽምና በእምነት ኃይል መጓዝ ነው። ዝለት፣ ሞኝነት እና ክፋት ሲከብበን በኑዛዜ መንገድ ኅብረትን በማደስ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኘው ጎዳና መገስገስ ነው። በዚህች እንደ ዕንፋሎት በምትተንን ሕይወት ልናደርገው የምንችል ዘላለማዊ ፋይዳ ያለው ነገር ይህ ብቻ ነው።

__Tesfatsion Alemayehu

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

27 Oct, 10:18


"ስለ ሥጋ ማሰብ" አእምሯችን ግራ በሚያጋባ ሐሳቦች ይሞላል፤ ፍርሃት፣ ሀሳብ፣ ጭንቀት፣ ምኞት ደግሞ ወደ ሁከት፣ ጨለማና ግራ መጋባት ውሰጥ ይጥሉናል። “ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና” (ሮሜ 8V6)። ነገር ግን አሳባችን በኢየሱስ ላይ ስናደርግ ልባችን የተቀደሰ፣ የተረጋጋ ይሆናል። አእምሯችንና ልባችን በእግዚአብሔር ሰላም ይጠበቃል። “ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።” (ሮሜ 8V6)

       —Alistair Begg

#መልካም_ሰንበት!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

15 Oct, 03:55


እግዚአብሔር በሁሉም ነፃ ምርጫዎቻችን፣ ውሳኔዎቻችን እና በሁሉም ኃላፊነት በምንወስዳቸው ነገሮች ውስጥ በመግቦቱ እየሰራ ነው።

__Alistair Begg

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

09 Oct, 07:50


እያንዳንዱ የትላንት ጊዜ፣ የአሁኑ ጊዜ እና የወደፊት ጊዜ የምንለው የጊዜ ሰሌዳ የራሱ የሆነ ምስጢር አለው። እያንዳንዱ የጊዜ ሰሌዳ የራሱ በቂ ጭንቀት አለው። ደግሞ እያንዳንዱ የጊዜ ቀመር፥ በሕይወት ውስጥ መነሳት ወዳለበት የመጀመሪያም የመጨረሻም ወደሆነ ጥያቄ ይመራናል። እና ለዚህ ጥያቄ አንድ መልስ ብቻ አለ! ዘለዓለማዊው እርሱ!
ጊዜን ሁሉ ጠቅልሎ የሚውጠውን ኋይል የሚልቅ ኋይል አለ! ዘለዓለማዊው እርሱ! የነበረውና ያለው፣ የሚመጣውም መጀመሪያውና መጨረሻ የሆነ! እርሱ ለትላንትናችን ይቅርታ ይሰጠናል፣ እርሱ ለሚመጣው ድፍረት ይሰጠናል። እርሱ
በዘላለም መገኝቱ ውስጥ ዕረፍትን ይሰጠናል።

__ማንደፍሮ ማሩ (የሕላዌ እንቆቅልሽ)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

21 Sep, 02:54


ድነት ለጻድቅ የምሰጥ ሽልማት ሳይሆ፣ ለኃጢአተኛ የምሰጥ ስጦታ ነው።

    __Steven Lawson

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

20 Sep, 09:38


የእግዚአብሔር ጸጋ ከኃጢአታችን ከፍ ያለ፣ ከርኩሰታችንም የጠለቀ፣ ከቅብዝብዝነታችን የሰፋ፣ ከዘላለም የረዘመ ነው።

   __Steven Lawson

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

10 Sep, 11:38


ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን። ሰላማችንን  የሚጠብቅ አስታራቂ አለን። ሰላምን የሚገዛ፣ የሰላም ሁሉ አለቃ እርሱ ነው።
   እርሱም ሰላማችን ነው!!

     __R.C. Sproul

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

25 Aug, 03:45


የወንጌል ዓላማ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ማምጣት እና ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ ነው። ቤተክርስቲያንን መሙላት አይደለም! ጥሩ የአባላት ስታቲስቲክስ ማኖርም አይደለም!
የወንጌል ዋና ልቡ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ማድረግና ከሚመጣው ቁጣ ማዳን ነው።

     __Martyn Lloyd Jones

#መልካም_ሠንበት!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

21 Aug, 15:59


የትኛውም እውነተኛ አማኝ በመንፈሳዊ ሕይወት እድገቱ ሙሉ በሙሉ አይረካም። በመንፈስ ቅዱስ አብርሆት በቅድስና እግዚአብሔር ለመምሰል መጥራት እና መገሰጽ ያለባቸው ጉዳዮች በሕይወቱ እንዳለ ያውቃል። ይበልጥ በመንፈሳዊ ሕይወት በበሰለ መጠን በልቡ ውስጥ ያለውን ስውር ኃጢአት ማየት ይጨምራል።

    __ጆን ማክአርተር

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

20 Aug, 04:35


አማኞች ኢየሱስ በከፈለው ዋጋ ለዘላለም ተፈውሰዋል። ይህ እውነታ በምሉዕነት የሚከናወነው ግን በዘመን ፍጻሜ መደምደሚያ መሆኑ ግን ግልጽ ነው።
የአዲስ ኪዳን ነገረ ፍጻሜ ትኩረቱ በመሥኡ አማካኝነት የእግዚአብሔር መንግስት መገለጥ ላይ አደላድሎ ቆሟል። መንግስቱ በክርስቶስ ፊተኛ መምጣት ተመርቃ ተከፍታለች። የተሟላ ፍጻሜዋ እስከሚከናወን ግን እኛ አሁን በውጥረት አለን። ... እምባ ከሌለበት፣ ሕመም ከማይታወቅበት፣ ለቅሶና ዋይታ በፍጹም ከተወገዱበት፣ ሞት ከተሻረበት አዲስቷ እየሩሳሌም ጋር ለመገናኘት አስቀድሞ ብንገባም ሙሉ በሙሉ ለመቀዳጀት ገና እየቃተትን አለን። ይኸውም ከአዲስ ሰማይና ምድር የመታደስ ቀዳማዊ ባርኮቶች ብንቀምስም በምልአተ ለመድረስ ግን በመጠባበቅ በዚህ ድንኳን ያለን ከብዶን እንቃትታለን። በጎትጓች ትግሎች ውስጥ እያለፍን ነው። ከዚህ የተነሳ በአሁኑ ሕይወት ከመከራና ከስብራት ጋር እንታገላለን።
   ነገርግን አንድ ነገር እናውቃለን እግዚአብሔር በመከራችን አይተወንም!!

     __ሰለሞን አበበ ገብረመድህን

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

18 Aug, 09:01


ኢየሱስ ሁል ጊዜ ይሰብክ የነበረው ስለ ንስሐ ፣ እምነት እና ስለ መታዘዝ ሕይወት ነበር።

__ጆን ማክአርተር

#መልካም_ሠንበት

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

16 Aug, 09:53


ዘመናችን በእግዚአብሔር እጅ ነው። ይሄ ከምንም በላይ ምቾት የሚሰጥ ነው። አማኞች ለባለጠግነትን፣ ረጅም ዕድሜ ስለመኖር፣ ወይም ፈተና አልባ ሕይወት ስለመኖር አንቋምጥም። ምንም ነገር ብሆን ለበጎ ነገር ይታዘዛሉና። በፈተናም ውስጥ የአዕምሮ እርጋታ እና የልብ ጽናት የጠንካራ እምነት ፍሬ ነው። ከኢዮብ ታሪክ የምናስተውለው ይህን ነው።

     __Matthew Henry

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

03 Aug, 16:23


በምንኖርባት ዓለም ምንም ይሁን ምን፣ እንደ እንፋሎት ለጥቂት ጊዜ ብቅ ብለን የምንጠፋ ነን። [እዚህ ዘላለም ኗርዎች አይደለንም።] ያለን በጣም አጭር ጊዜ ነው። እናም ፍቅራችንን፣ ትኩረታችንን ከላይ (ሰማይ) ባሉት ነገሮች ላይ ማድረግ አለብን።
  "እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።" (ቆላስይስ 3V1&2)

__ጆን ማክአርተር

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

31 Jul, 12:01


ሰው ክርስቶስን ካልያዘ፣ ሰማይንና ምድርን ቢያውቅ እንኳ ጥበቡ ሞኝነት ነው። 
ሰማያዊው የጥበብ መዝገብ ሁሉ በክርስቶስ ውስጥ ይገኛልና።

__John Calvin

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

21 Jul, 10:42


"የሰው ልጆች ታሪክ ከእግዚአብሔር ውጪ ሌላ ደስታን ለማግኘት የሚሞክሩበት ረጅም እና አስከፊ ታሪክ ነው"

    __C.S. Lewis

#መልካም_ሠንበት!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

20 Jul, 14:10


እግዚአብሔር ሁሉንም “ጭንቀቶቻችንን” ከአእምሮአችን አውጥተን “በጸሎት ዝርዝራችን” ላይ እንድናስቀምጥ ይፈልጋል።

    __H.B. Charles Jr

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

16 Jul, 14:14


⨳ኑ የመስቀሉን ድሎች እዩ፡
      • ቁስሎቹ ፈውስ፣
      • ጭንቀቱ እረት፣
      • ስቃዩ ድል መንሳት፣
      • ማቃሰቱ የድል መዝሙሮች፣
      • ህመሙ ምቾት፣
      • እፍረቱ ክብር፣
      • ሞቱ ህይወት፣
      • መከራው ደህንነታችን ናቸው።

   __Matthew Henry

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

የእግዚአብሔር ወንጌል

14 Jul, 16:28


ጸጋ የኃጢአተኛው የመጨረሻና ብቸኛ ተስፋ ነው። በጸጋ ከልዳና በሌላ በምንም  በፍጹም አይድንም።

   __A.W Pink

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

2,812

subscribers

42

photos

60

videos