ጥቅምት 29/2017 (አዲስ ዋልታ) የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ከተመራጩ የአሜሪካ ሪፐብሊካን ፕሬዝዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ናት ሲሉ ገለጹ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ምርጫ በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ትራምፕ ከዚህ ቀደም ስለ ዩክሬን የሰጡት አስተያየት እና ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ ትኩረት የሚሻ ነው ማለታቸው በፑቲን የተወደደ ሀሳብ ሆኗል።
የሩስያው ፕሬዝዳንት በደስታ መግለጫ መልዕክታቸው ሞስኮ ከተመራጩ ሪፐብሊካን ፕሬዝዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከምርጫ በፊት ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በተወያዩበት ወቅት ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት በሰዓታት ውስጥ ማስቆም እንደሚችሉ ገልፀው አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን እርዳታ ደጋግመው መተቸታቸው ይታወሳል።