PURE GOSPEL @puregospel Channel on Telegram

PURE GOSPEL

@puregospel


"እኛ ግን #ትርፍ ለማግኘት #ብለን የእግዚአብሔር ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት #እንደብዙዎች #አይደለንም"2ኛቆሮ2:17ወንጌል የሰው #እውቀት #ባህል #ትምህርት ያልተቀላቀለበት #ንጽህ መልዕክት ነው።አላማችን #ኢየሱስን መስበክ ብቻ ነው።For more info፦ @Mikipeter

PURE GOSPEL (Amharic)

አስተዋይ ታሪክን ሰጥተው ሁሉ የሚያረጋግጡት ትንሽ አቋም ላይ ያስቀምጡ የዩናይት እና ትምህርት አቅምን ለማለፍ በዚህ ካንሰር ላይ ባላቋምላችሁ ትምህርቶችን በማምጣት የትምህርትን በሚሰሩ እንደዚህ አለምና አላማችን PURE GOSPEL ቺንነሩ ከሚለው አስፈላጊ እና መረጃ የተለያዩ እና የንጽህ መልዕክቶችን ለመቀበል ተደምስሰናል። በዚሁ ካንሰር በመሳሪያዎ ውስጥ ም kikipeter ላ የትምህርት ሃሳቦንን ሊያፈራርሰብን እና ማስታወሻን ለማድረግ ወጣቻችኋል።

PURE GOSPEL

28 Sep, 03:53


ይሄንን ለወዳጆቻችሁ በማጋራት በዚህ ሳምንት 500 እናድርስ።
አሁኑኑ እንጀምር።
እስቲ share የምታደርጉ
❤️ምልክት አሳዩኝ።

PURE GOSPEL

22 Sep, 02:49


በፓስተር በረከት በላይ
ዘጸ 40:34-38 ባለው ታሪክ ምሽቴን የጸለይኩበት፣የልብ ቃጠሎ የሆነ መልዕክት ነው።
ያነበብነውን በመኖር እናውቀው ዘንድ ለራሴ ለቤተክርስቲያን ለእናንተ ለሁላችሁም ቀናሁ ቀናሁ አብራችሀኝ እንድትቀኑ ደመናውን ህልውናውን እንድትራቡ የሚያደርግ መልዕክት ነውና እባካችሁ በማስተዋል በትዕግስት አድምጡት።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
እወዳችኋለሁ ጸጋ ይብዛላችሁ።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
መልካም ዕለተ ሰንበት ዕለተ እሁድ።
🥪ወደቤተክርስቲያን ሂዱ የቃሉን ምዕድ በህብረት ተካፈሉ።
https://t.me/GospelrevivalGRPEM
Join and share it pleas.

PURE GOSPEL

03 Jul, 07:57


ፓስተር በረከት በላይ
ይህ መጋቢያዊ ባርኮቴ ነው።
አማኝ የሆነ ሰው ይህን ከሰማ በኋላ ምስክርነት በህይወቱ ላይ እንደሚሆን አምናለሀ።
ከሰማችሁ በኋላ በራሳችሁ ላይ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ቃሉን አውጁት።
❤️እቀዳችኋለሁ ተባረኩልኝ።
#እውነትን #መግለጥ
join us @puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

01 Jul, 09:09


ፓስተር በረከት በላይ
ከእግዚአብሔር የሚለየን አይኑር ለእግዚአብሔር የምንለየው እንጂ።
   እግዚአብሔር ላልተገባን ለእኛ ባደረገው ስጦታ መደነቅ ይብዛልን።
   ቀናችሁ ሳምንታችሁ በዚህ አጭር ደቂቃ መልዕክት የተዋጀ ይሁን።
መልካም ሳምንት እወዳችኋለሁ።
#እውነትን #መግለጥ
   join us @puregospel
                @puregospel
                @puregospel

PURE GOSPEL

30 Jun, 20:22


ፓስተር በረከት በላይ።
በኢየሱስ በጸጋው ተመርጣችኋል።
ታግሶ የሰማ ሰው የእውነት ይጽናናበታል።
"የትላንት ታሪክ የሌለው ጻድቅ
የነገ ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛ የለም"
#እውነትን #መግለጥ
   join us @puregospel
                @puregospel
                @puregospel

PURE GOSPEL

26 Jun, 07:06


https://t.me/GospelrevivalGRPEM
#ፊቱን_በመፈለግ_መጽናናት አና መበርታት መልካመ ቀን ይሁንላችሁ።

ወዳጆቼ በሕይወታችሁ ብዙ ነገሮችን ለማግኘት ቆፍራችሁ ቧጣችሁ አልተሳኩ ይሆናል። እኔ ብዙ ደክሚያለሁ በእጄ ያልሆነውን፣ በአቅሜ ልፈጽመው የማልችለውን ነገር ለማግኘት በሃሳብም በብዙ ነገርም ተፍጨርጭሪያለሁ እስካሁን አላሳካሁትም። ልክ የተዘጋ በር የመገንጠል ያህል ጥሪያለሁ። አንዳንዴም በእጄ ገባ የምትሉት ነገር እድሜው ያጥርባችኋል ደስታውን ሳታጣጥሙት የጉም ስፍር ይሆንባችኋል እንደ ጤዛ ይበንባችኋል። ግን አይዟችሁ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ ኢየሱስን በልባችሁ አቆዩ። ምንም ነገር አያጓጓችሁ፣ ምንም ነገር በእጃችሁ አይግባ፣ ፕሮሰሳችሁ ይዘግይ፣ ይሳካል ያላችሁት ሲፈልግ ይጨንግፍ ተስፋ እንዳትቆርጡ። ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ከሆነ ቢኖር ባይኖር አያሳስብም፣ ቢገኝ ቢታጣ አያስገርምም። ኢየሱስ በቤታችሁ በልባችሁ ይቆይላችሁ።

                 ወዳጆቼ በሕይወታችሁ ብዙ ነገሮችን ለማግኘት ቆፍራችሁ ቧጣችሁ አልተሳኩ ይሆናል። እኔ ብዙ ደክሚያለሁ በእጄ ያልሆነውን፣ በአቅሜ ልፈጽመው የማልችለውን ነገር ለማግኘት በሃሳብም በብዙ ነገርም ተፍጨርጭሪያለሁ እስካሁን አላሳካሁትም። ልክ የተዘጋ በር የመገንጠል ያህል ጥሪያለሁ። አንዳንዴም በእጄ ገባ የምትሉት ነገር እድሜው ያጥርባችኋል ደስታውን ሳታጣጥሙት የጉም ስፍር ይሆንባችኋል እንደ ጤዛ ይበንባችኋል። ግን አይዟችሁ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ ኢየሱስን በልባችሁ አቆዩ። ምንም ነገር አያጓጓችሁ፣ ምንም ነገር በእጃችሁ አይግባ፣ ፕሮሰሳችሁ ይዘግይ፣ ይሳካል ያላችሁት ሲፈልግ ይጨንግፍ ተስፋ እንዳትቆርጡ። ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ከሆነ ቢኖር ባይኖር አያሳስብም፣ ቢገኝ ቢታጣ አያስገርምም። ኢየሱስ በቤታችሁ በልባችሁ ይቆይላችሁ።

                            https://t.me/GospelrevivalGRPEM
መልካም ብሩህ ፊቱን የመፈለግ ቀን።
 https://t.me/GospelrevivalGRPEM
Join and share ለተጨማሪ ጸሎት ትምህርት ስብከቶች።

PURE GOSPEL

21 Jan, 09:00


ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን፦
"ዮሐንስ ወንጌሉን ለምን ጻፈ?"
ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው #ክርስቶስን እንደ #ማንኛውም #ሰው በታርክ ውስጥ የነበረ የአንድ ተራ #አናጢ ልጅ #በረባሶ የምያደርግ የደፈረሰ #አይን ያለው በኢየሩሳሌም እና አከባቢዋ ይመላለስ የነበረ የሀጢአተኞች ወዳጅ የሆነ በምድር 33 6/12 አመት ኖሮ #የሞተ አርገው #ለሚገምቱ እና #ለምቆጥሩ ሁሉ #እግዚአብሔር #መለኮት #አምላክ እንደሆነ #ከዘላለም በፊት ከእግዚአብሔር #አብ ጋር እንደነበረ የሁሉ #ፈጣሪ እንደሆነ #1 2 3 ተብሎ #እድሜው እንደማይቆጠር #እንዳልጀመረ #እንዳስጀመረ እንደፈጠረ #እንዳልተፈጠረ #እንዳስገኘ #እንዳልተገኘ #ከአብርሃም በፊት እንደነበረ #የዘላለም ህይወት እንደምሰጥ #የዘላለም ህይወት #ራሱ እንደሆነ #ህግ እና ነቢያት የተናገሩለት #በአይናቸው ፊት የሄደው እርሱ እንደሆነ #ከምድር መጀመሪያው ሳይሆን #ከላይ #ከፍጥረት በፊት ከነበረው ማንነቱ አንስቶ #አልፋ እና #ኦሜጋ ብቻ እንዳልሆነ ከአልፋ እና ኦሜጋ #በፊት እንደነበረ #ንጉስ ከመምጣቱ በፊት #አዋጅ ነጋሪ ለንጉስ መንገድ አዘጋጅው እያለ እንደሚመጣ #መጥመቁ ዮሐንስም #ከንጉሱ ኢየሱስ በፊት የመጣ መንገድ ጠራጊ እንደ ነበረ #ኢየሱስ ከተናገራቸው ራሱን #አምላክነቱን በደንብ ከምገልጽሁ #ንግግሮች መካከል 7ቱን #እኔ ነኞች በመጠቅስ እርሱ ካደረጋቸው #በቀጠሮ #በቆይታ ካልሆኑት #ቅጽፐታዊ ከሆኑት ብዙ ከአምዕሮ በላይ ከሆኑት ድንቆች እና ምልክቶች 7ቱን #ስለ 4ቀኑ ሬሳ #ስለ 38 አመቱ የአልጋ #ቁራኛ ውሀን ወደ ወይንጠጅ መቀየሩን...በመጥቀስ #አምላክ እንደሆነ ብነግራቸውም #ቃሉን የሚጠብቅ ለዘላለም #ሞትን እንደማይቀምስ #ቃሉ ህይወት እንደምሰጥ #ቢያስተምራቸውም #ጋኔል አለብህ እንዳሉት እርሱ ግን እንደሌለበት #አላወቁም እንጂ #ጋኔል ያሉቱ #የመላዕክት ፈጣሪ እንኳ #እሱ እንደነበረ የህይወትን #እስትንፋስ እሱ እንደሰጣቸው እርሱ #ለዘላለም የተባረከ #አምላክ እንደሆነ #በ21ምዕራፎች #በ879ቁጥሮች #በ19099ቃላት በጥልቀት በስፋት እና በግልጽ በብዙ ማስረጃ እያስደገፈ #ሊያሳውቅ አብሮት በአካል 3አመት 6/12 #ስለነበረው #በአይኑ ስላየው #በእጆቹ ስለዳሰሰው #ደረቱ ጋር #ተጠግቶ ስላወራው #ሊመሰክር ነው።ይሄ ነበረ የጻፈበት ምክንያቱ እኔ ሳጠና ያገኘሁት
#እውነትን #መግለጥ
join us @puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

30 Aug, 16:24


ብዙ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ #ፍጽምሰውነት ስናነሳ ዘለው ከእግዚአብሔር አብ #ከማነስ ጋር ያገናኙታል ይሄ ስህተት ነው የክርስቶስ ኢየሱስን #ፍጽምሰውነት ስናስብ ማሰብ ያለብን፦
1የፍቅሩን ጥልቀት
2 ራሱን ስለ እኛ መስጠቱን
3 የመታዘዙን ጥግ
4 ከአምላክነቱ ቅንጣት ያህል አለመቀነሱን ነው።
#እውነትን መግለጥ
@puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

25 Aug, 13:32


ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን፦
በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን #በረከት ከሚንቀበልባቸው መንገዶች ፊተኛው እና ቀዳሚዊ እንደራሳችን #ሀሳብ በመሄድ እንደ #ዘመኑ በመሄድ #ያዋጣል ብለን ባሰብነው መንገድ በመሄድ #በብልሀት በመሄድ በሰዎች #ምክር በመሄድ ሳይሆን እግዚአብሔር #እንደነገረን እንደ #ቃሉ #በመሄድ #በመኖር ነው።ዘፍ26 እስራኤል የ40ቀኑ መንገድ የ40 አመት የሆነባቸው እንደነገራቸው እንደ #ቃሉ እንደ #ምሪቱ እንደ #ፈቃድ ባለመሄዳቸው ነው ዛሬም ይሄ አሰራር አልተቀየረም።
#እውነትን #መግለጥ
Join us @puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

28 Jul, 12:13


በዚ ዘመን ትኩረት(focus)ማድረግን የመሰለ ሀብት የለም አዳዲስ የመፍትሔ ሀሳቦች ትኩረት ከሚያደርጉ ሰዎች ይወጣሉ ብዬ አምናለው።በእጅ ስልኮቻችን አማካኝነት ሩቅ የማያስኬደንን የማያደክመንን እጥር ያለ ቶሎ የሚያልቅ ያልተሟላ ቅንጭብጭብ ከፓለቲካው ከመዝናኛው ከሀይማኖቱ ምንም ፈርጅ(category)የሌለውን እንኳ ሳይቀር ወደ አዕምሮዋችን በምንጎሰጉስበት በዚ ዘመን ጤንነታቸው ያልተጠበቀ ያልተመጣጠኑ ለጊዜው ርካታን የሚሰጡ በዘላቂነት ግን ትኩረት የማድረግ አቅማችንን የሚያዳክሙ እና አዕምሮ እንዳያብሰለስል የሚያሰልሉ መረጃዎች በበዙበት በዚ ዘመን የአብዛኛው ሰው አዕምሮ እንዳያተኩር ሆኖ በተቃኘበት በዚ ዘመን አዕምሮዋቸው እንዲያተኩር ራሳቸውን ያስለመድ በሙሉ ትኩረት ከአምላካቸው እግር ስር የማይጠፍ (በፀሎት የሚተጉ ቃሉን የሚበሉ)የብዙ መዛባቶች መፍትሔ ሆነው ይነሳሉ።እግዚአብሔር ብዙ ሚነግረን አለው "ትኩረታችንን" ሙሉ ልባችንን ግን ይፈልጋል።(Samri)
#እውነትን #መግለጥ
join us@puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

21 Jul, 18:27


ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን፦
በይቅርታ ህግ #የበደለ #የተበደለን ወይም በዳይ #ተበዳይን ሰው #ይቅርታ ይጠይቃል ሁላችንም እንደ ባለ አዕምሮ ሰዎች በዚህ #ህግ እንስማማለን #የበደልነውን ሰው #ይቅርታ እንጠይቃለን #ምህረትን እንለምናለን በሰው ልጆች እና #በእግዚአብሔር መካከል በነበረ #ግንኙነት እኛ የሰው ልጆች #እግዚአብሔርን #በድለነዋል #አሳዝነነዋል #ይቅርታ መጠየቅ #እንታረቅ ብለን በፍቱ #መውደቅ የነበረብን #መለመን የነበረብን #እኛ የሰው ልጆች ነበርን ነገር ግን #ከፍቅሩ ብዛት #ከመውደድ ጥልቀት እኛ #በድለነው #አሳዝነነው #ተጣልተነው እርሱ እራሱ #ልጅን ልኮ #በልጅ በኩል #ታረቀን #የበደልነው እያለን #የተበደለው ይቅርታ #ጠየቀን ይህ ነው #የወንጌል አስተምህሮ
#እውነትን #መግለጥ
join us @puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

23 Sep, 19:33


(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 1)
----------
3-5፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።
6-7፤ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።
8-9፤ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
10፤ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤
11፤ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።
12፤ ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
13፤ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
14፤ እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
15-16፤ ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
17፤ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
18-19፤ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።
20-21፤ ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።
22፤ ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
23፤ ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።
24፤ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤
25፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።

PURE GOSPEL

23 Sep, 19:33


ፊልጵስዩስ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ።
¹⁰ ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ፣ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጹሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ፣
¹¹ ለእግዚእብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው።

PURE GOSPEL

23 Sep, 19:31


(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 10)
----------
1፤ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤

2፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤

3፤ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤

4፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።

5፤ እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።

6፤ እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን።

PURE GOSPEL

09 Feb, 18:35


እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ #ተናግሮ ጨርሳል ስንል መናገር #አቁማል እያልን ሳይሆን መናገር #የፈለገውን ሁሉ #በክርስቶስ #ተናግሯል ወይም ደግሞ #አንድ ጊዜ ለዘላለም የሚሆን #እለት እለት የሚደመጥ የህይወት ቃል #ተናግሯል እያልን ነው፤ የቀረ የለም።
#እውነትን #መግለጥ
@Puregospel
@Puregospel
@Puregospel

PURE GOSPEL

08 Feb, 17:14


ብዙ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ #ፍጽምሰውነት ስናነሳ ዘለው ከእግዚአብሔር አብ #ከማነስ ጋር ያገናኙታል ይሄ ስህተት ነው የክርስቶስ ኢየሱስን #ፍጽምሰውነት ስናስብ ማሰብ ያለብን፦
1የፍቅሩን ጥልቀት
2 ራሱን ስለ እኛ መስጠቱን
3 የመታዘዙን ጥግ
4 ከአምላክነቱ ቅንጣት ያህል አለመቀነሱን ነው።
#እውነትን መግለጥ
@puregospel
@puregospel
@puregospel

PURE GOSPEL

10 Sep, 18:19


(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 10)
----------
1፤ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤

2፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤

3፤ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤

4፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።

5፤ እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።

6፤ እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን።

PURE GOSPEL

03 Oct, 11:29


በዓለም ዙርያ ያላቹ የተወደዳቹ እህት ወንድሞቻችን ሰላምታችን በያላቹበት ይድረሳቹ፡፡
ይህ መልዕክት በዓዲግራት መካነ ኢየሱስ ቤ/ክርስቲያን አገልጋይ ለሆነው ለወንድማችን ቄስ አታክልቲ ገ/ስላሴ የፀሎት እና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በትህትና ለመጠየቅ የተዘጋጀ ነው፡፡
ወንድማችን በደረሰበት የጤና እክል ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከስራ ውጪ በመሆናቸው በከባድ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል፡፡ ስለሆንም የኩላሊት ነቅሎ ተከላ በአፋጣኝ ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህም ወደ 700,000.00 ብር ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ደግሞ ከወንድማችን አቅም በላይ ስለሆነ የእርሶ ድጋፍ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ ያለበትን ሁኔታ ክብደት እና ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ተረድተው በሚችሉት ሁሉ እንድትደግፉት በጌታ ፍቅር እንጠይቃቿለን፡፡ ዛሬውኑ ወንድማችንን ለማትረፍ እንነሳ፡፡ የእርሶ ጥቂት ድጋፍ ከሌሎቹ ጋር ተደምሮ ወንድማችንን ይታደግልናል፡፡
ድጋፋቹን በሚከተለው መንገድ ማድረግ ይችላሉ፡፡
Name of bank account holder: EECMY-NAW
Bank account no: 1000012126844
BIC/SWIFT:   CBETETAA
Bank name:   Commercial Bank of Ethiopia
Branch name: Mekelle branch
Bank postal address: P.O. Box  36
Postal code and city: Mekelle city 
Country: Ethiopia 

phone +251912691736, +251914300483
Seyoum Abraha (Coordinator, EECMY-NAWC- Ethiopia)

ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ🙏🙏🙏

PURE GOSPEL

10 Jun, 17:15


ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን፦
ከፍታ ያለው ወንድምን #በማውረድ ውስጥ ሳይሆን እግዚአብሔርን #በማክበር ውስጥ ነው።እግዚአብሔር #የሚያከብረን እሱን #ባከበረነው ልክ እንጂ ወንድማችንን #ባዋረድነው ባጠለሸነው ባንቋሸሽነው በሰደብነው ልክ #አይደለም።
#እውነትን #መግለጥ
Join us @puregospel
@puregospel