ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ @zerihungemechu Channel on Telegram

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

@zerihungemechu


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ (Amharic)

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ የቴሌግራም ክትባቶችን ለሀገራት እንዴት ለመከታተለዉ እና ለመጠቀም እንደምትችል እና መዝባራት ይጠቀሙ። የሚከበሩት ቴሌግራሞችን በራሱ የበቃላት መቈየር ብናደር እና ሀገር በሚመለከተው የእናትና አባት ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ይኖራል። ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ባለቤታማ መጠቀምና ሃገርን በልመሉ የተምታችሁት ቴሌግራሞችን ሲርቁን እና ሲፈልግን በማዋቀር እና መደራራዉን ይጠቀሙ። ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ በጣም ቨእምነት ቢሆን ዘሪሁን ስለሚመጣው ሰው ሁኔታ ወደ ቴሌግራሞች እና ለቴሌግራሞች አስተካክል ሽህልና እና ችግሮችን ብናፍርኦን ይሰጡ።

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

13 Nov, 07:30


በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ‹‹በእውነት እምቢ ብትለን ምንድነው የምናደርገው?›ወ.ሮ ስንዱ በተሰበረ ድምፅ ባላቸውን ጠየቁ፡፡
አቶ ኃይለልኡልም እጅ በሰጠ ድምፅ‹‹አንተ ምን ብናደርግ ትመክረናለህ?››ሲሉ እሱኑ መልሰው ጠየቁት፡፡
‹‹ይሄውላችሁ እንደእኔ እንደእኔ በፀሎት ወደቤት መመለስ ያለባት በእናንተ ላይ የነበራት ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ…ሁሉን ነገር በራሷ መንገድ አረጋግጣና ፈቅዳ…ደስ ብሎት ነው
…ይሄውላችሁ አሁን አብዛኛውን አስቸጋሪ የነበረውን መንገድ ተጉዛችኃላ …እስኪ አስቡት ከአስራአምስተ ቀን በፊት ወደቢሾፍቱ ስንሄድ አንድ መኪና ውስጥ መቀመጥ እራሱ የሚቀፋችሁ ሰዎች ነበራችሁ፣ትዝ ይላችኃላ ጋሼ ገቢና ነበር የተቀመጥከው…አሁንስ ይሄው በደስታ ጎን ለጎን በራሳችሁ ፍቃድ ተቀምጣችሁ እርስ በርስ ተጣብቃችሁ የደስታ ወሬ እያወራችሁ ትሳሳቃላችሁ..ከባዱ ነገር እናንተን እዚህ ስሜት ላይ ማድረስ ነበር…ከአሁን ወዲህ ያለው ይሄንን ግንኙነት መሰረት እንዲይዝና ስር እንዲሰድ ማድረግ ብቻ ነው… ያ ደግሞ ቀላል ነው…ቢያንስ 15 ቀን መታገስ ያቅታችኃላ….?፡፡››
‹‹እና ባለችበት ትቀመጥ እያልክ ነው…?ያለችበት ሁኔታ… እቤቱ የሰዎቹ ኑሮ ምኑም አይመቻትም እኮ…››
ከቀናት በፊት ስላለችበት ቤት ሲጠይቃት ያለችው ነገር ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡

‹‹እውነቴን ነው..እርግጥ ሽማግሌው በጣም ጥሩና ደግ ሰው ናቸው….ቢሆንም ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው..ልጄ ከቤት ስትወጣም ደህና ብር እንኳን ይዛ አልወጣችም››
‹‹አይዞችሁ እስከዛሬ ድምጻን አጥፍታ ኖረች ማለት በጣም ቢመቻት ነው….ደግሞ እንዳላችሁ ባይመቻትም ለ15 ቀን ምንም አትሆንም፡፡አለመመቸትን ማጣጣም በቀጣይ ለሚመጣ መመቸት መደላደል መፍጠር ነው፡፡››
‹‹እሺ ቢያንስ እንሄድና ከሩቅም ቢሆንም እንያት››
‹‹እንደእሱ ይቻላል››አላና ያጠፋውን የመኪና ሞተር አስነሳው፡፡
ሰለሞን መኪናውን ነዳና ከተካ መኪናው ፊት ለፊት አቆመ….ተካ መኪናውን ከፊቷ ወጣን ወደእነሱ መጣ ..ሰለሞን የገቢናው በራፍ ከፈተለት ……ገባና ቁጭ አለ››
ወደኃላ ዞረና…..‹‹አሁንም ውስጥ ነች…እንዴት ነው ምናደረገው? ››
‹‹ቆይ እስኪ ተረጋጋ ስትወጣ እንያት….››ሁሉም አይናቸውን የግቢው መውጫ መግቢያ ላይ ተከሉ….በርከት ያሉ ሴቶች ሲወጡ ሲገቡ ይታያል፣››
‹‹ምንድነው ብዙ ሰዎች ይታያሉ… ችግር አለ እንዴ?››አቶ ኃይለ ልኡል ጠየቁ፡፡
‹‹አይ ጌታዬ ችግር የለም… እኔም በመጀመሪያ ግራ ገብቶኝ ነበር…ስጠይቅ ግን ፣ሰዎቹ ነገ የማሪያም ፅዋ ማህበር አለባቸው ..የድግሱ ስራ ለማገዝ የመጡ ጎራቤቶች ናቸው››
‹‹እ …እንደዛ ነው….››በፀሎት ወጥታ ከሩቅ ለማየት ከአንድ ሰዓት በላይ በትዕግስት መጠበቅ ነበረባቸው….ግቢ ውስጥ ካለ የማንጎ ዛፍ ስር ቆማ ከአቶ ለሜቻ ጋር እየተሳሳቀች ስታወራ ነበር የተመለከቱት…ሁለቱም ወላጆች ሄደው ልጃቸው ላይ ለመጠምጠም የሚተናነቃቸውን ስሜት በመከራ ነበር የተቆጠጠሩት፡፡ሁለቱም ስሜታዊ ሆነው እንባ አውጥተው እስከማልቀስ ደርሰው ነበር፡፡
‹‹አሁን በቃ ይበቃናል…ከዚህ በላይ እዚህ ከቆየን ራሳችንን ማጋለጥ ይሆናል…ድንገት እዚህ እንዳለች እንደደረስንባት ካወቀች….ቦታ ለመቀየር ታስብና ዳግመኛ አድራሻዋን ትሰውርብን ይሆናል፡፡››ሰለሞን ነው የተናገረው፡፡
‹‹አዎ ትክክለ ነህ….እንዴት ነው ምናደርገው ታዲያ? እሱ እዚሁ ይጠብቃት አይደል…?››.

‹‹አይ ምንም ጠባቂ አያስፈልግም…ባይሆን በየቀኑ እየመጣ ለተወሰነ ደቂቃ ሰላም መሆኗን ብቻ ካረጋገጠ ይበቃል፣አሁን ሁላችንም ነን አካባቢውን መልቀቅ ያለብን፡፡››ሰለሞን ቁርጥ ያለ ውሳኔውን አስተላለፈ…የተቃወመው ወይም የተከራከረው አልነበረም፡፡
‹‹እሺ ይሁን …..በቃ ተካ አንተም ወደቤትህ ሄደህ እረፍ …ነገ ደውልልሀለው››ብለው አሰናበቱት…‹‹እሺ ጌታዬ እንዳሉ››ብሎ ገቢናውን ለቆ ወረደና ወደአቆማት መኪና ተንቀሳቀሰ…..ሰለሞንም ባልና ሚስቱን ይዞ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተፈተለከ…..
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

13 Nov, 07:30


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሀያአንድ
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ተካ አቶ ኃይለልኡል ባዘዙት መሰረት ሽጉጡን ሙሉ ጥይት ሞልቶ ወገቡ ላይ ከሸጎጠ በኃላ አጉሊ መሳሪያ ያዘና ማንን ሳያስከትል ቀጥታ መኪና ውስጥ ገብቶ ወደ ቃሊቲ ነዳው….የሰውዬውን ጥርጣሬ ምንም አልተዋጠለትም…‹‹ልጅቷ ስንት አማራጭ እያላት እንዴት እዛ ጭንቁርቁስ ቤት ከጭርቁስቁስ ሰዎች ጋር ለመቆየት ታስባለች? ››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ሊዋጥለት አልቻም…፡፡

በፀሎት ከጠፋችበት ቀን አንስቶ በመላ ሀገሪቱ ፍላጋ የተሰማሩትን በመቶ የሚቆጠሩ ግለሰቦችን የሚመራው ..መረጃ የሚቀበለው አዲስ ቦታ ስምሪት የሚሰጠው እሱ ነው፡፡እና የእሱ እቅድ የሆነ ቦታ መኖሯን በሆነ መንገድ ቀድሞ ቢደርስበት እንደምንም ብሎ የራሱ ሰው በሚስጥር እንዲያገኛት አድርጎ በእጅ አዙር 5 ሚሊዬኑን የሽልማት ገንዘብ ለመቀባበል አቅዶ ከልቡ እየሰራ ነበር...እርግጥ እንደዚህ እያደረገ መሆኑን ቀድመው ቢደርሱበት ያለምንም ማቅማማት ግንባሩን በጥይት እንደሚነድሉት እርግጠኛ ነው…ግን በህይወት የተሻለ ነገር ማግኘት ሪስክ መውሰድ የግድ እንደሆነ የሚያምን ስለሆነ ነገሩን ልክ እንደቁማር ነው ያየው..‹‹ወይ በላለሁ..ወይ ደግሞ እበላለው››ብሎ ነበር ውሳኔ ላይ ደርሶ በተግባር ሲንቀሳቀስ የከረመው፡፡…አሁን ሰውዬው እንደሚሉት ልጅቷ የገመቱት ቦታ የምትገኝ ከሆነ ያ ሁ እቅዱ ውሀ በላው ማለት ነው፡፡ቦታውን ራሳቸው ቀድመው አውቀው ስለነገሩት ሽልማት የሚሰጡበት ምንም ምክንያት የለም….መኪናውን ወደእዛ ሲያሽከረክር በውስጡ በፀሎት የተባለው ቤት በፍፅም እንዳትገኝ እየፀለየ ነበር፡፡እንደደረሰ ከመንገድ ማዶ አስፓልት ጠርዝ ላይ መኪናውን ፓርክ አደረገና የመኪናው መስኮት በከፊል ከፍቶ ማጊሊያ መነፅሩን ወደእነ አቶ ለሜቻ ግቢ አነጣጠረና ገቢ ወጪውን መመልከትና በመሀከልም የተለየ ነገር ያገኘ ሲመስለው በሞባይሉ ፎቶ ማንሳት ጀመረ…
ስራ የጀመረው ከጥዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ቢሆንም እሰከ 10 ሰዓት ሁለት ሶስት ጊዜ አሮጊት ሴት ስትወጣ ስትገባ ከማየት ውጭ በግቢው ውስጥ አይን የሚስብ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም…ሰዓቱ እየረዘመ ሲሄድ ተስፋ እየቆረጠና እየተሰላቸ መጣ…ለዛሬ ይበቃኛል ብሎ 11 ሰዓት ላይ አካባቢውን ለቆ ወደቤቱ ሄደ ..
በማግስቱ በጥዋት ማለዳ አንድ ሰዓት ላይ ነበር የመጣው፣እና ሁለት ሰዓት ላይ የሚፈልገውን አገኘ ..ደጋግሞ ፎቶ አነሳው…በቤቱ አንድ ሴት ልጅ ብቻ እንዳላቸው አጣርቷል ..አሁን እየገቡ እየወጡ ያሉት ግን በተቀራራቢ እድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ወጣቶች ናቸው፡፡አንደኛዋ የቤቱ ልጅ እንደሆነች እርግጠኛ ነው…ሁለተኛዋ ግን የሚፈልጋት የባለፀጋው ቅምጥል ልጅ ትሁን አትሁን መለየት አልቻለም…የለበሰችው ልብስ የተለመደ አይነት ነው..በዛ ላይ ፊቷን ጭንቅላቷን ጭምር በሻርፕ ሸፍናለች…ዝም ብሎ ከመኪናው በመውረድና በእግሩ ወደ አጥሩ በመጠጋት ከቅርብ ርቀት በርከት ያለ ፎቶ አነሳና ለአቶ ኃይለ ልኡል ላከላቸው፡፡

አቶ ኃይለልኡል በዚህ ጊዜ ከባለቤታቸው ጋር በሰለሞን በሚሾፈር መኪና ከቢሾፍቱ ወደአዲስ አበባ እየተመለሱ ነበር፡፡ስልካቸው ድምፅ ሲያሰማ ከኪሳቸው አወጡና ተመለከቱት..መልዕክት መሆኑን ሲያዩ ከፈቱት…አይናቸው ተጉረጠረጠ….
‹‹እራሷ ነች ..ልጄ እራሷ ነች….ከጎናቸው ያለችው ሚሳታቸው ላይ ተጠመጠሙና ጉንጮቾን አገላብጠው ይስሙ ጀመር››
‹‹እንዴ ኃይሌ ምን ተፈጠረ..?ምን ተገኘ..አረ ንገረኝ?››
‹‹ይሄውልሽ..እንቺ እይው..ፊቷን ብትሸፋፈንም እራሷ ነች፡፡››ወይዘሮ ስንዱ ስልኩን ከባላቸው እጅ ተቀበሉና አፍጥጠው ተመለከቱ…..ከባላቸው በበለጠ በመደነቅ ኡኡ.አሉ…መኪናዋን በእልልታ አደባላለቁት…ሰለሞን የነገሩ ውል ስላልገባው መሪውን ጠመዘዘና የመንገዱን ዳር አስይዞ መኪናዋን አቆማት…በራፉን ከፍተው ወረዱ….እሱም ተከትሏቸው ወረደ‹‹አረ ለእኔም ንገሩኝ ምንድነው? እንዲህ የሚያስፈነጥዝ ደስታ፡፡››
‹‹ልጃችን የት እንዳለች አወቅን..እያት ተመልከት››ስልኩን ከሚስታቸው ተቀበሉና ለሰለሞን አቀበሉት..አንድ ፊቷ በቅጡ የማይታይ ወጣት ፎቶ ነው…ግን በፀሎት እንደሆነች ወዲያው ነው ያወቃት..ሙሉ ፊቷን ሳያይ እሷ እንደሆነች አንዴት እንዳወቀ አልገባውም…››
‹‹አየህ …ልጃችን እራሷ ነች…ሰው እንዳይለያት ነው ፊቷን የሸፋፈነችው……››
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለችው?››ጠየቀ ሰሎሞን፡፡
‹‹የት እዳለች ቆይ ነግራችኃላው››ብለው ስልኩን ተቀበሉና ደወሉ
‹‹ሄሎ….ፎቶው ደርሶኛል፡፡››
‹‹አዎ ሳስበው እሷ ትመስለኛለች››
‹‹አዎ እሷ እራሷነች…ከቦታው እንዳትንቀሳቀስ..እዛው ጠብቀን…ከቢሾፍቱ እየተመለስን ስለሆነ ከ15 ደቂቃ በኃላ ያለህበት እንደርሳለን››
‹‹ወጥታ ከሄደችስ…?ላስቁማት››
‹‹አይ..ልጄን ቀጥታ እኔው ነኝ የማገኛት..እንዳታስቆማት ትደነግጥብኛለች…ከቤት ከወጣች ዝም ብለህ በርቀት እየተከታተልክ ያለችበትን ታሳውቀኛለህ፡››

‹‹እሺ..ጌታዬ እንዳሉት አደርጋለው››
‹‹ጎበዝ ..እንዳስደሰትከኝ አስደስትሀለው…ቆንጆ ጉርሻ ይጠብቅሀል ››
‹‹እሺ ጌታዬ››ስልኩን ዘጉና‹‹በሉ ጊዜ አናባክን ..ግቡና እንሂድ››
‹‹እንዴ የት አንዳለች ንገረን እንጂ……?››ወ.ሮ ስንዱ ጠየቁ
‹‹ስንድ ልጃችን ሰዎቹ ጋር ነው ያለችው….››
‹‹የትኞቹ ሰዎች››
‹‹እነአቶ ለሜቻ ጋር..ማለቴ የልብ ለጋሾ ቤተሰብ ጋር ነው ያለችው››
‹‹ወይ ጉዴ….አሁን ምንድነው የምናደርገው?››እያሉ ወደመኪናው ገቡ፡፡ አቶ ኃይለልኡልም ተከትለዋቸው ገቡ….ሰለሞን በሰማው ያልተጠበቀ ነገር ግራ እንደተጋባና ምን ማድረግ እንዳለበት እያሰላሰለ ገቢና ገባ፡፡ መኪናውን አንቀሳቀሳት…ባልና ሚስቶቹ በደስታ ሰክረው እሱን ከቁብ ሳይቆጥሩት እርስ በርስ በፈንጠዝያ ሲጎሻሸምና ሲሳሳሙ እሱ ምን ማድረግ እንዳለበትና ይሄንን ያለጊዜው ያጋጠመውን ነገር እንዴት እንደሚፈታ እያሰላሰለ ነበር የሚነዳው….
አቃቂ አቶ ለሜቻ ቤት ለመድረስ 500 ሜትር ያህል ሲቀራቸው የመኪናውን መሪ ወደግራ ጠመዘዘና ፊት ለፊት ከሚታየው ሆቴል ይዞቸው ገባ..ባልና ሚስቶቹ በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሰለሞን…ምን እያደረክ ነው?››አቶ ኃይለልኡል ጠየቁ፡፡
‹መነጋገር አለብን››
‹‹ስለምን?››
‹‹አሁን ልጃቹህ ጋር ከመሄዳችሁ በፊት አረፍ ብለን መነጋገር አለብን››
‹‹ምን መነጋገር ያስፈልጋል…?በቃ እኔና እናቷ ሄደን ልጃችንን ወደቤት ይዘን እንሄዳለን….እንደምታየው አሁን ሁሉ ነገር ውብ እና የተስተካለከለ ነው..አይዞህ

አታስብ…ከንተጋር ያለንን ነገር እንቀጥላለን..ከሶስት ቀን በኃላም ወደአልከው ቦታ ትወስደናለህ››
መኪናውን አቆመና ሞተሩን አጥፍቶ ወደኃላ ዞረ..ፊት ለፊት እያያቸው‹‹ይሄ ነገር እንደምታስብት ቀላል ይመስላችኃላ?››
‹‹ማለት?››
‹‹አሁን ያለችበት ቤት ሄደችሁ በማንኳኳት..ነይ ልጄ በቃ አግኝተንሻል አሁን ወደቤትሽ ተመለሺ ብትሏት ..እሺ ብላ በደስታ ዘላ የምትጠመጠምባችሁ ይመስላችኃላ…እምቢ መሄድ አልፈልግም ብትል ምን ታደርጋላችሁ ?በግድ በጎረምሳ አሳዝላችሁ መኪና ውስጥ በመክተት ወደቤት ትወስዷታላችሁ….?ከዛስ..?አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፋችሁባት በራፍ ላይ ሁለት ጠብደል ጠባቂ ታቆማላችሁ?እስኪ ንገሩኝ ምንድነው የምደርጉት?››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

12 Nov, 06:42


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሀያ
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
‹‹አግብተሀል እንዴ?››
ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡
‹‹ለምን መሰለህ የጠየቅኩህ..?እንዲሁ ሳስበው አንተን ያገባች ሴት በጣም እድለኛ ትመስለኛለች….፡፡››
‹‹ምን አልባት ልትሆን ትችላለች ..እስከአሁን ግን አለገባሁምም አረ እንደውም ፍቅረኛም የለኝም››
ፈገግ አሉ….‹‹ሸክላ ሰሪ በገል ይበላልል›› አሉ…ብዙ ማወቅም እኮ መጥፎ ነው››
‹‹እንዴት?››
‹‹የምትፈልገውን ሁሉ የምታሟላ ሴት ለማግኘት በጣም ይከብድሀላ…ሁሉን ነገር አሟልታ ጥንቅቅ ያለች ሴት አታገኝም..በዛ እርግጠኛ ሆኜ ልነግርህ እችላለው…ግን ምትወድህና ምትወዳት ልጅ ሆና እራሷን ለመለወጥና ለማሻሻል የምትጥር ከሆነ በቂ ነው…አንተ ጎበዝ አንደበተ ርትኡ ባለሞያ ስለሆንክ መስመር ታስይዛታለህ››
እንዴት ብሎ መምከሩን ትቶ ተመካሪ እንደሆነ አልገባውም፡፡‹‹እሺ…የእናንተን ጉዳይ ከዳር ካደረስኩ በኃላ አስብበታለው….ምን አልባት እናንተ ትሆናላችሁ የምትድሩኝ…››
‹‹ለዛውም ድል ባለ ድግስ ነዋ››

‹‹እሺ..አሁን ይበቃናል…የምሳ ሰዓት ስለደረሰ ወደሳሎን እንሂድ››
‹‹አዎ ..ይበቃናል..ይሄኔ ኃይሌ ብቻውን ደብሮታል››
ፈገግ እለ ….. ከመቀመጫው ተነሳና ወደውጭ መራመድ ጀመረ…ወ.ሮ ስንዱም ተከተሉት፡፡


ከሳምንት በኃላ……..
በቢሾፍቱ ቆይታቸው በባልና ሚስቶቹ መካከል አስገራሚ የሚባል ለውጥ ነው የታየው፡፡ቢያንስ እረስ በርስ በመሀከላቸው ያለ ንግግር የጥሩ ጓደኛሞች መምሰል ከጀመረ ሰነባብቷል…ይሄ ለውጥ ሰለሞንን ይበልጥ እንዲበረታታ እና ሙሉ ኃይሉን ስራው ላይ እንዲያውል አግዞታል፡፡
‹‹እንግዲህ ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው ነገ ወደአዲስአባ እንመለሳለን…ሶስት ቀን እረፍት እንወስድና ምን አልባትም ለመጨረሻ ጊዜ ለሌላ 15 ቀን ወደሌላ መዝናኛ ቦታ እንሄዳለን፡፡በቀጣይ የምንሄድበት ከዚህ የተለየ ነው…ሌሎች ሰዎች ማለቴ ጎብኚዎች የሚኖሩበት ቦታ ነው…እዛ ምንሄደው ነፃ ሆናችሁ እንድትዝናኑ ነው..እኔም አብሬያችሁ ኖራለው ግን ነፃ ናችሁ…እዚህ እንዳለው ብዙ ማዕቀብና እገዳ የለም…ስልካችሁን እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ.ሰሻል ሚዲያ ቴሌቪዝን ማየት ትችላላችሁ …ከሰው መተዋወቅና መገባበዝ ትችላላችሁ..አንድ ማትችሉት ነገር መለያየት ብቻ ነው….ለ15 ቀን የምታደርጉትን ሁሉ አብራችሁ ታደርጋላችሁ..››
‹‹ገባን ..ያልከው 15 ቀን የመጨረሻችን ይመስለኛል››
አዎ እኔም እንደዛ ነው የማስበው..በእውነት እዚህ ባሳለፍነው 15 ቀን ሁለታችሁም ካሰብኩት በላይ ከፍተኛ ጥረት አድርጋችኃል …እናም ትልቅ ለውጥ እንዳመጣችሁም ይሰማኛል…እናንሰትስ ምን ይሰማችኃል…?አቶ ኃይለልኡል እስኪ ከእርሶ ልጀምር፡፡

‹‹እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ…እስከዛሬ ሚሲቴን ብቻ የምበድል መስሎ ነበር የሚሰማኝ ለካ ልጄንም ራሴንም ጭምር ነበር እያሰቃየው የነበረው….እውነት አንተና ልጄ የእድሜ ልክ ባለውለታዎቼ ናችሁ››
ፊቱን ወደወ.ሮ ስንዱ ዞረና ተመሳሳዩን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
‹‹አዎ…ኃይሌ እንዳለው ደስተኛ ነን…በፊት ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ገዳም ገብቼ መመልኮስ ነበር ምኞቴ ..ምክንያቱም ህይወት አስጠልታኝ ነበር…ቤቴም ኑሮዬም ይቀፈኝ ነበር…ጨለማ የሆነ ሀዘን ውስጥ ገብቼ ነበር..አንድ ያለችኝ አስደሳች ነገር ልጄ ብቼ ነበረች
..እሷም ከጠፋች በኃላ ደግሞ ነገሮች ለእኔ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው…አሁን ግን እንደዛ አይደለም የሚሰማኝ….ደግመኛ እንደመወለድ አይነት የመታደስ ስሜት እየተሰማኝ ነው…የመከራና የሀዘን ቆዳዬን ከላዬ ገፍፌ ጥዬ በአዲስ ተስፋና ፍቅር ተወልጄለሁ..አሁን ቤቴም ባሌም ይናፍቁኛል….ሃይሌን ከዚህ በፊት ለሆነው ሁሉ ይቅር ባዬዋለሁ.. እሱም ይቅር እንደለኝ ገምታለው፡፡››
ኃይለልኡል ተፈናጥረው ከመቀመጫቸው ተነሱና ሚስታቸው ላይ ተጠመጠሙ…ሁለቱም ተቃቅፈው መላቀስ ሲጀምሩ….ሰለሞንንም ስሜታዊ አደረጉት፡፡ተላቀው ወደቦታቸው ለመመለስ..ከ10 ደቂቃ በላይ ፈጅቶባቸዋል፡፡
ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ‹‹ጥሩ እንግዲህ… እዚህ ደረጃ ላይ ከደረስን አንዳንድ አጠቃላይ ስለሆኑ ነገሮች እናውራ፡፡ያው እናንተ በጋብቻ ውስጥ ረጅም እድሜ ስለአሰለፋችሁ ከእኔ የበለጠ ልምድ እንዳላችሁ አውቃለሁ....አሁን የማወራው የምታውቁትን ነገር ነው…ላሳውቃችሁ ሳይሆን ላስታውሳችሁ ፈልጌ ነው››
‹‹ጥሩ እየሰማንህ ነው ….ቀጥል››
‹‹እንግዲህ እቤት የባል ብቻ አይደለም፣የሚስትም ብቻ አይደለም፣ እቤት የልጆችም ጭምር ነው።በዚህ ምክንያት ለሁሉም ኑዎሪዎች እኩል ምቹ መሆን አለበት።እናንተ ከአሁን ወዲያ በቤታችሁ የሚዘረጋው ስርአት ህግና የአኗኗር ዘየ..ሶስታችሁን በእኩል ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡ሌላው ንብረታችሁን በተመለከተ የእኔ የሚለውን ቃል ከመጠቀም የእኛ የሚለውን የጋራ ቃል መጠቀም የተሻለ ነው።የእኛ ቲቪ..የእኛ ቤት...የእኛ ጊቢ የእኛ ፋብሪካ፣ብሎ የመናገር ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።እያንዳንድ የቤተሰብ አባል የእዛ ቤተሠብ

የአክሰዬን ባለድርሻ ናቸው።ያንን ደግሞ በተግባርም በስነ-ልቦናም መረጋገጥ አለበት።በቤተሰብ ቢዝነስ ውስጥ ስለሚፈጠር ዋና ዋና ክስተት ስለትርፍም ሆነ ኪሳራ ሁሉም ሰው በተገቢው መጠን መረጃ ሊኖረው ይገባል….ሁሉንም ኃላፊነት አንዱ አካል ብቻ ጠቅልሎ መውሰድ የለበትም…እዚህ ላይ በተለይ አቶ ኃይለልኡል ብዙ ነገር ማስተካከል የሚጠበቅቦት ይመስለኛል››
‹‹ገብቶኛል..እሺ…አስተካክላለው፡፡››

‹‹ሌላውና ወሳኙ … የተለየ ችግር ከሌለ በስተቀር ባልና ሚስት መኝታ ክፍላቸውንም ሆነ አልጋቸውን መለየት የለበቸውም…በተጨማሪም ባልና ሚስት በምንም አይነት ሁኔታ ወደመኝታቸው ሲሄድ አኩርፈውና በውስጣቸው ተበሳጭተው ወይ ቂም ይዘው መሆን የለበትም።መኝታ ክፍል ለባለትዳሮች እንደቤተመቅደስ ነው መሆን ያለበት ። የሚሳሳሙበት... የሚተቃቀፉበት.... የሚዋደድበትና የሚፋቀሩበት ….ስለጋብቻቸው እና ስለልጆቻቸው ደህንነትና ሰላም የሚማከሩበትና የሚፀልዩበት የገመና መክተቻ ቦታቸው ነው መሆን ያለበት ። ስለዚህ ... ቅያሜያቸውን ሆነ ቅሬታቸውን ሳሎን ጨርሰው ለጭቅጭቃቸው መፍትሄ አበጅተውለት እና ይቅር ተባብለው ነው በሳቅና በፈገግታ ወደመኝታቸው መሄድ ያለባቸው። አዎ ወደመኝታ ክፍላቸው ሲያመሩ በፍፁም ሰላምና ፍቅርና መሆን አለበት...የበለጠ ለመፍቀር...የበለጠ ለማረፍና ..የበለጠ ለመታደስ ።ይሄ ሁለታችሁንም በእኩል ደረጃ የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡››
ሁቱም አንገታቸውን እላይ እታች በማነቃነቅ መስማማታቸውን ገለፁ

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

12 Nov, 06:42


‹‹ሌላው በቤት ውስጥ አንደኛው ሌለኛውን ማገልገል አለበት...ማገልገል ማለት በፍፅም ፍቃደኝነትና ፍላጎት አንደኛው ሌላኛውን መርዳት ማለት ነው።ባል የቤቱ ንጉስ ከሆነ ሚስት ደግሞ ንግስት ነች ማለት ነው ልጆች ደግሞ ልኡላን ናቸው።ማንም ከማንም የበለጠ አስፈላጊ አይደለም...ማንም ከሌላኛው ያነሰ አይደለም።ለቤቱ ሙሉነትና ፍፁምነት ሁሉም የየራሱ ኃላፊነትና ድርሻ አለው።በፍቅርና በጋብቻ ህይወት ውስጥ እርስ በርስ ያለ መከባበር በጣም ወሳኝ ነው።አንድ ለሌላዎ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሲኖሩት በትህትና እና ክብር በተሞላ ሁኔታ ጥያቄውን ማቅረብ አለብት።እርስ በርስ ያለ ግንኙነት የማስመስል መሆን የለበትም...እንግዳ ሲኖር የሚደረግ አርቴፊሻል የማስመሰል እንክብክቤ እና አክብሮት

ጥቅም አልባ ነው። ለፍቅረኛ ወይም ለትዳር አጋር የሚኖር አክብሮት ጥልቅና ሩቅ መሆን አለበት። ከልብ የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነፍስም የተጨለፈ መሆን አለበት።ሚስት ለባሏ ሚስት ብቻ አይደለችም..የሴት ጓደኛ…የእናት ምትክ ዘመድ ጭምር መሆን አለባት..ባልም ለሚስቱ ወንድ ጓደኛ..ከዛም አልፎ የአባት ምትክ ዘመድ መሆን አለበት፡፡የማወራው ግልፅ ነው አይደል?››
‹‹አዎ ..በጣም ግልፅ ነው..ቀጥል››

ትንፋሽ ወስዶ ከንፈሩን በምራቁ አረጠበና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ‹‹…ከቤት ወጥታችሁ ስትለያዩ የሚኖር ሽኝት እና ከውጭ ውላችሁ ስትመለሱ እርስ በርስ የሚኖር የሞቀ አቀበል በጣም ወሳኝ ኩነት ነው።ተሳሳሞ ደህና ዋል..ደህና ዋይ ተባብሎ መለያየት እና ሲገናኙ እንዴት ዋልሽ…?እንዴት ዋልክ? ተባብሎ በናፍቆት መሳሳም በመሀከል ያለን ግንኙነት ያደረጃል ፍቅርም ግለቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ያግዛል።በመጨረሻው ሚቻላችሁ ከሆነ እቤት ከገባችሁ በኃላ ለተወሰነ ሰዓት ስልክ የሚጠፋበት እና ቲቨ የሚዘጋበት ልዩ የሆነ የቤተሠብ የጋራ የመጫወቻና የመወያያ ሰአት ቢኖር እንደቤተሠብ ለሚኖር መስተጋብር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
‹እና ሌላው ልጃችሁ ላይ ያላችሁ አቋም ትልቅ ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹በፀሎት ነገሮች ተስተካክለው ወደቤት ስትመለስ..ለምሳሌ ስትወጣ ስትገባ በጋርድ እንድትጠበቅና እንድታጀብ ማድረግ አይገባችሁም..እንደማንኛውም ሰው በነፃነት ከፈለገችው ሰው ጋር ወጥታ ከፈለገችው ጋር የመመለስ መብት ሊኖራት ይገባል፡፡››
‹‹ሰለሞን እዚህ ላይ አንድ ያልገባህ ነገር አለ…እኔ እኮ ልጄን በጋርድ ማስጠብቀው ወድጄ አይደለም…..ልጄ ልብ በሽተኛ ነኝ..የልብ ንቅለ ተከላ ተደርጎላታል …በጣም ጥንቃቄ የምትፈልግ ልጅ ነች..ድንገት መንገድ ላይ ወድቃ አጉል እንዳትሆንብኝ ስለምሰጋ ነው ዘወትር ሰዎች በዙሪያዋ እንዲሆኑ የማደርገው፡፡››ሲሉ ተቃውሞቸውን ያሰሙት አቶ ኃይለልኡል ናቸው

‹‹ቢሆንም ለዛ መፍትሄው ያ አይደለም….ይሄ የልጅቷን ነፃነት ከመንፈጉም በላይ በራስ የመተማመን ችሎታዋን በጣም ይጎዳዋል…በየሄደችበት በሰው መጠበቅ የመታፈን ስሜት እንዲሰማት ነው የሚያደርጋት፣እና የእዛ ውጤት ደግሞ እንዲህ አሁን እንዳደረገችው ራሷን ነፃ ለማውጣት አላስፈላጊ ጣጣ ውስጥ እንድትገባ ትገደዳለች››
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን ያው ነፃ ትሁን… ብቻዋን ትንቀሳቀስ ብዬ ከፈቀድኩላት አንዳንድ አላስፈላጊ ቦታዎች ትሄድና የማይሆን ነገር ትሰራለች፡፡››
‹‹ለምሳሌ የት?››
‹‹ይሄውልህ የልብ ንቅለ ተከላ ሲደረግላት ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦች እዚሁ አዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ ነው የሚኖሩት ..ልጄ አሁን አሁን ተወች እንጂ በፊት ሰሞን ቀንና ሌት እዛ ካልወሰድከኝ እያለች ታስቸግረኝ ነበር፣..እኛ ደግሞ ከልጅቷ አባት ጋር ስንስማማ በምንም አይነት ከእኛ በአካል መገናኘት እንደማይፈልጉ ነው ያነገሩን..እሷ ቤታቸው ሄዳ ቢያገኟት ልጃቸውን ስልምታስታውሳቸው ሀዘናቸውን ክፉኛ ትቀሰቅሳባቸዋለች.. እንደዛ አይነት ውለታ የዋሉልኝን ሰውዬ ደግሞ የማይፈልጉትን ነገር ማድረግ ላሳዝናቸው አልፈልግም..አንድ ለዛ ነው የማስጠብቃት››ንግግራቸውን እየተናገሩ ሳለ የሆነ እስከዛሬ ያላሰብት ገራሚ ሀሳብ በአእምሯቸው ብልጭ አለ….እንዴት እሰከዛሬ ትዝ ሊላቸው እንዳልቻለ ግራ ገባቸው‹‹ልጄ እነሱ ጋር ሄዳ ቢሆንስ?››ሀሳቡን በውስጣቸው አፍነው ያዙት፡፡
‹‹የልጃችሁን ደስተኝነትና ሳቅ የምትፈልጉ ከሆነ ለችግሮች ሁሉ ሌላ መፍትሄ አበጁላቸው..ደግሞ ለበፀሎት በግልፅ ነገሮችን ቢያስረዶት ይገባታል…ብስልና አስተዋይ የ22 ዓመት ወጣት ነች….ይልቅ እናንተ በመሀከላችሁ ያለውን ችግር ፈታችሁ ሰላም ከሆናችሁና ስትወጣ ስትገባ የሚከታተላት ሰው መመደብ ካቆማችሁ የልጃችሁን ደስታና ሳቅ መመለስ ብቻ ሳይሆን መቼም መልሳችሁ አታጦትም››
ወ.ሮ ስንዱ መለሱ ‹‹እሺ እንዳልክ እናደርጋለን….ኃይሌ እንዲህ ማድረግ ያቅተናል እንዴ?››
‹‹አረ አያቅተንም..ችግር የለውም ሁሉን ነገር እኔ አስተካክለዋልው..አሁን ከፈቀድክልኝ ወደካማፓኒው አንድ አጭር ስልክ መደወል አለብኝ..ከባድ የስራ ጉዳይ ነበረ ..ምን እንዳደረሱት ልጠይቃቸው፡፡››

‹‹ችግር የለም..በቃ ጨርሰናል..አሁን ለጥዋት ጉዙ እቃችንን መሸካከፍ መጀመር እንችላለን፡፡››
‹‹ጥሩ…››ብለው ቀድመው ከመቀመጫቸው ተነሱና ወደክፍላቸው በመሄድ ስልካቸውን ካስቀመጡበት አንስትው በጀርባ በኩል ባለው በር ከቤት ወጡ…. ስልክ ደወሉ…
‹‹ስማ አቃቂ ለልጄ ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦችን ታውቃቸወላህ አይደል..?››
‹‹አዎ አውቀዋለው››
‹‹አሁኑኑ እዛ ሂድና ቀስ ብለህ ማንም ሳያይህ ወደቤታቸው የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው ተከታተል…ከተቻለህ ሁሉንም ፎቶ አንሳ››
‹‹እሺ….ግን በቀጥታ ምን ለማጣራት ነው የምንፈልገው…?ነገሩን ማወቄ ስራዬን ያቀልልኛል››
‹‹አዎ….ምን መሰለህ..ለማንም እንዳትናገር..ልጄ ምን አልባት እዛ ቤት ተደብቃ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል…እና ከአሁኑ ጀምረህ በቃ እስክልህ ደረስ እንዳልኩህ ተከታተለልኝ…እሷን በተመለከተ የሆነ ትንሽም ቢሆን ፍንጭ ካገኘህ ወዲያው አሳውቀኝ፡፡››
‹‹ስልኩን ዘጉና ኪሳቸው ውስጥ ከተው ወደውስጥ ተመለሱ …ወ.ሮ ስንዱ አልጋቸው ላይ አረፍ ብለው አገኞቸው ፡፡በራፉን ዘጉን የራሳቸውን አልጋ ትተው ወደባለቤታቸው ሄዱና ከጎናቸው ተቀመጡ፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

11 Nov, 07:08


በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራችን ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ጋና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት መነጋገር ነው፡፡ለዘሬው ይበቃናል…አሁን ወደመናፈሻው እንሂድና ትንሽ ዘና እያልን ብና እንጠጣ››
‹‹ጥሩ….እንሄድ››ብለው ሶስቱም ከተቀመጡበት ተነሱና እቤቱን ለቀው ወጡ


////




በማግስቱ…….
ሰሎሞን ባለትዳሮችን ቢሾፍቱ ይዞ ከከተመ አራተኛ ቀኑ ነው፡፡የዛሬው ፕሮግራም ሁለቱን በተናጠል ማነጋገር ስለሆነ አሁን ከወ.ሮ ስንዱ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻ ፊት ለፊት ቁጭ ብለው እያወሩ ናቸው፡፡
‹‹ወ.ሮ ስንዱ አሁን ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››
‹‹እድሜ ላንተ …ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው…ከስንት ዓመት በኃላ ከኃይሌ አንደበት መልካም ነገር መውጣት ጀምሯል››
‹‹ጥሩ እንግዲህ ሰው ምን ጊዜም ከስህተት ጋር ሚኖር ፍጡር ነው፡፡ከሰው ጋር ስንኖር ስህተት ፈላጊ ከሆን በማንኛውም ሰው ላይ ከመጠን ያለፈ ስህተቶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን…..ያ ደግሞ ከሰው ጋር አያኖኑረንም…አንዳችን የሌላችንን ክፍተት ለመድፈን መፈጠራችንን እስካላሰብን ድረስ ምንም ነገር ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡››

‹‹ትክክል ነህ..በህይወት ዘመናችን አውቀንም ሆነ ሳናውቅ…እርስ በርስ በጣም ተጎዳድተናል…በእልህም በጥፋት ላይ ጥፋት እየደረብን የሁለታችንንም ጣር ስናበዛው ነበር››
‹‹ያለፈው አፏል..አሁን ማሰብ ለነገው ነው፡፡የትናንቱን ጥፋት እያነሳን የምንመረምረው ከልባችን ይቅር እንድትባባሉ እንዲያግዛችሁ እና ዳግመኛው ተመሳሳይ አይነት ስህተት በህይወታችሁ እንዳትሰሩ ነው፡፡››
‹‹ገብቶኛል ልጄ በጣም ገብተኛል..ግን ምን መሰለህ ሀይሌ አንዳንዴ እንዲህ እንደምታየው አይምሰልህ… ህፃን ሆኖ የህፃን ስራ ሲሰራ ታገኘዋለህ ››
‹‹ውቃለው ይሄ የእሷቸው ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰዎች ባህሪ ነው….ሰባ አመት ቢሞላን እንኳን ሁላችንም ውስጥ ሳያድግ ህፃን እንደሆነ የሚቀር ማንነት አለ…ሁሌ ውስጣችን ሆኖ ስነልቦናችንን የሚያናውፀው…እናታችን ጉያ ውስጥ እንድንወሻቅ የሚያስመኘን …አባታችን ጭንቅላታችንን እንዲዳብሰንና አይዞህ እንዲለን የሚያስናፍቀን…..አያጂቦ የሚያስፈራን ጭራቅ በህልማችን የሚመጣብን… አዎ ሳያድግ በጮርቃነት የቀረ ማንነት አለን….ለዛ ነው ልጅነት ላይ በሆነ ጎኑ የተሰበረ ሰው አድጎም በቀላሉ ጤነኛ መሆን የማይችለው….ለዛ ነው ጉዳቱ የሚያሳድደው..ለዛነው አንዳንድ ጉድለተችና የህይወት ሽንቁሮች የእድሜ ልክ ህመም ሆነው የሚቀሩት..ልጅነታችን ላይ ተጠጣብቀን እንድንቀር የሚያስገድደን፡፡››
እንግዲህ እኔ አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቼ ከእሱ ለመስማማት ነው የምፈልገው…ግን ሰላማችን ምን ያሕል ይቆያል ?የሚለውን በእርግጠኛ ሆኜ ለማንም ማስተማመኛ መስጠት አልችልም››
‹‹ይገባኛል…የእርሶ ግምት ወደፊት በግንኙነታችሁ እንቅፋት ሊሆነ ይችላል ብለው የሚያስብት ወይም የሚያሰጋዎት ነገር ምንድነው?››
‹‹ይሄማ ግልፅ ነው…እንደምታየኝ እኔ እድሜዬ አምሳ ሞልቷል….ልክ እንደሀያ አመት ወጣት ላስደስተውና ፍላጎቱን ሁሉ በሚፈልገው መልክ ላሟላለት አልችልም..እሱ ደግሞ ከእንቡጦች ጋር መቅበጥና መዳራት ለምዶል፡፡››
‹‹ይሄውሎት ወ.ሮ ስንዱ ..ወሲብ ብቻውን ለወንድ ልጅ በቂ አይደለም፣አንድ ሚስት ለባለቤቷ ሌላ ማንኛውም ሴት ልትሰጠው የምትችለውን ነገር ሊኖራት ያስፈልጋል።ወንድ

በወሲብ ስለተመቸችው ብቻ ከአንድ ሴት ጋር ለዘላለም አብሯት አይኖርም። ወንድ ልጅ ሚስቱ ክብር እንድትሰጠው ይፈልጋል።››
‹‹አዎ ..እሱስ ትክክል ነህ …በዚህ በዚህ ብዙ ጥፋት አለብኝ..ሁልጊዜ እሱን መከራከርና ንግግሩን ሁሉ በመቃረን ማሸማቀቅ ሆነ ብዬ የማደረገው የዘወትር ድርጊቴ ነው፡፡››
‹‹አዎ…ወንድ ልጅ አንድ ገበያ ህዝብ ቢንቀው መታገስ ይችል ይሆናል ..የምታፈቅረውን ሴት ወይም የባለቤቱ ንቀት እና ችላ ባይነት የሚቋቋምበት ምንም አይነት ፅናት የለውም።‹ሴት የላከው ሞት አይፈራም› የሚባለው ለምን ይመስሎታል…አንድ ሴት የምታፈቅረውን ወንድ አክብራ አበረታታ በትህትና ምንም ነገር እዲያደርግላት ብትጠይቀው አይኑን ሳያሽ
ያደርገዋል ለማለት ተፈልጎ ነው››
‹‹ገባኝ ልጄ ይሄ የእኔ ትልቁ ስህተት ነው..እንደማርመው ቃል ገባልሀለው››
‹‹ጥሩ…እንግዲህ ቅድም እንዳሉት ወሲብ ላይ ያሎትን ነገር ብዙም አይጨናነቁበት …በመሀከል ያለ ጥልና ጭቅጭቅ ሲወገድ..ፍቅርና መተሳሰብ በቦታው ሲተካ የወሲብ ችሎታውም ሆነ አምሮቱ አብሮ ይመጣል…ደግሞ ያው ሁላችንም እንደምናውቀው ወሲብ እርካሽና ገንዘብ ያለው ሁሉ ሊገዛው የሚችል ነገር ነው።አንድ ሚስት ስብዕናዋን ከወሲብ በላይ በሆኑ ነገሮች መገንባትና ማነፅ አለባት። ወንድ ልጅ እራሷን በሜካፕ ዲኮር ከምታደርግ ሴት ይልቅ ለችግሮች መፍትሄ የማመንጨት ብልሀት ባላት ሴት ይሳባል።አንድ ሴት ወንዶች የሚፈልጉትን ነገር ሳይሆን ሁል ጊዜ ባሏ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ አለባት፡፡" በፍቅር የተሠራ ኃጢአት ፍቅር ከሌለበት አምልኮ ይበልጣል›ይባላል፡፡››
‹‹አልገባኝም ይህ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹ይህ ማለት ወንዶች ሁሉ ወንድ በመሆናቸው ብቻ አንድ አይነት አይደሉም ለማለት ነው…አንድ ሚስት የባለቤቷን ልዩ ባህሪዎች ጥንቅቅ አድርጋ ማወቅ አለባት…ምን ይወዳል..?ምን ይጠላል…?ምን አይነት ምግቦች ይመቹታል…?ምንአይነት መጠጥ ያስደስተዋል…?ሚስቱ ምን አይነት ልብስ ስትለብስ ፊቱ ይፈካል…?የመሳሰሉትን ዝርዝር ባህሪዎችኑ ማወቅና ያንን ታሳቢ አድርጎ መንቀሳቀስ ይጠበቅባታል…ይሄ ለወንዱም ይሰራል፡፡ አንድ ሚስት እሷ ሴት ስለሆንች ባለቤቷም ሌላ ሴት እንደሆነ ማሰብ የለባትም።በሁለቱ መሀከል የማይካድ የጻታ ልዩነት አለ፡፡የፃታ ልዩነት ማለት ደግሞ የባህሪ እና የፍላጎትም ልዩነትም ጭምር ማለት ነው።

‹‹አዎ ..እሱስ እውነትህን ነው››
‹‹አዎ..ለምሳሌ ባሎች ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ሚስታቸው በቀጥታ በእጆቾ ያበሰለችውን ምግብ መመገብ በጣም ያስደስታቸዋል… ሌላው ሁል ጊዜ ችግር እያወራች
ከምታማርር እና ሁሉን የውጭ ስራዎች ባሏ እንዲሰራቸው ከምትጠብቅ ሴት ይልቅ ጀግና እና ችግርን ፊት ለፊት ለምትጋፈጥ ሴት ክብር አለው። ››
‹‹አሁን ምን እንደተረዳሁ ታውቃለህ..አንዳንድ ጥቃቅን ናቸው ብለን ትኩረት የማንሳጣቸው ነገሮች በህይወታችን ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍሉን ነው፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ብለዋል››
‹‹አግብተሀል እንዴ?››
ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

11 Nov, 07:08


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራዘጠኝ
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ሰሎሞን ሁለቱን ባለትዳሮች ፊት ለፊት አስቀምጦ እያወራ ነው፡፡‹‹የፈለገ ጥረት ብናደርግ ለእያንዳንዱ ብሎን የራሱን ትክክለኛ መፍቻ ካልተጠቀምን ልንፈታው አንችልም!! በህይወታችንም ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን ተረጋግተን ለችግሩ ትክክለኛ የመፍትሄ ሀሳብ ማስቀመጥና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ካልቻልን እንዲሁ ስንባክን እና በችግሩ ውስጥ ስንዳክር ነው የምንኖረው፡፡ይሄንን በስራ አለም በትክክል እየተገበራችሁ ውጤታማ እንደሆናችሁ አውቃለው…በትዳር ህይወታችሁስ?ዋናው ጥያቄ እሱ ነው፡፡››
አቶ ኃይለልኡል ተቀበሉት‹‹ገብቶናል…እንደምንም ብለን በመሀከላችንን የተፈጠረውን ክፍተት በማስወገድ እና ፍቅራችንን መመለስ እንዳለብን በደንብ ተረድተናል…አዎ እንደምታየውም ጥሩ መሻሻል እያሳየን ይመስለኛል፡፡››
ሰለሞን ቀጠለ‹‹ጥሩ ግን ፍቅር ብቻውን በሰላም ለመኖር በቂ አይደለም፡፡በመሀከላችው ምንም አይነት ጥል የሌለ ጥንዶች በመሀከላቸው ፍቅር እንዳለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም…እንደዛውም ዘወትር በነጋ በጣባ የሚጣሉና የሚጨቃጨቁ ጥንዶችም በመሀከላቸው ያለው ፍቅር አልቋል ወይም ቀዝቅዞል ማለት አይደለም….ከዛ ይልቅ እንዴት እርስ በርስ እንደሚግባቡ እና አንዱ የአንዱን ፍላጎት እንዴት እንደሚረዳ አልገባቸውም ማለት ነው፡፡ስለዚህ አሁን መልሳችሁ ማደስ የሚገባችሁ ፍቅራችሁን ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችሁንም ጭምር ነው፡፡አንዳችሁ ሌላችሁን በጥልቀት ለመረዳት እስከምን ድረስ ለመጓዝ ትፈቅዳላችሁ?ይሄ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡››

ወ.ሮ ስንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገሩ‹‹ትክክል ነህ ልጄ… ለፍቀራችን መበላሸት ዋናው ምክንያት እንደውም እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችን ስለተበላሸ ነው….እሱም እኔን እኔም እሱን ለመረዳት ምንም የምናደርገው ጥረት አልነበረም…ሁለታችንም እርስ በርስ እንከን ነበር የምፈላለገው….ያንን በደንብ ተረድቼለው፡፡››
‹‹አዎ ይሄ ችግር የእናንተ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ባለትዳር ችግር ነው…አንድ ሰው በፍቅር ሲወድቅ በመጀመሪያ ስለራሱ ምቾና ደስታ እንጂ ስላፈቀረው ሰው ደህንነት አይደለም የሚጨነቀው…ሁለቱም ተጣማሪዎች በጋብቻ ጥምረት ውስጥ ለእነሱ የሚመች ሰፋ ያለ ግዛት ቶሎ ብሎ ለመያዝ ይጣጣራሉ…ሁለቱም ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው ፍትጊያ ይፈጠራል…አንዱ የሌለኛውን ድምበር ማለፍ…ይሄኛው የዛኛውን ቀይ መስመር መደፍጠጥ ይጀምራል……ከሁለት አንዱ በፍጥነት ነቅቶ ወደኃላ በመመለስ መረጋጋት ውስጥ ካልገባ ችግሩ መስመር ይስታል፡፡
እኔ 25፡50፡25 የሚል ፕሪንስፕል አለኝ፡፡በትዳር ውስጥ እሷ(ሚስትዬው) እሱ(ባልዬው) እና እነሱ (ባልና ሚስቶቹ)አሉ፡፡እና ስሜታቸው፤ፍላጎታቸው፤የህይወት አላማቸው ወ.ዘ.ተ ተጠቅልሎ መቶ ፐርሰን ቢሰጠው፡፡እሷ የግሏ ፍላጎት በግሏ የሚያስደስታት ነገር፤ መዝናኛ ቦታ፤ጓደኞች፤ 25 ፐርሰንት ትይዛለች….እሱም ለብቻው 25 ፐርሰንት ይይዛል፡፡50 ፐርሰንቱ ግን የጋራቸው ነው፡፡በጋራ የሚያቅዱበት፤በጋራ የሚሰሩበትና የሚለፉበት ቤት መስራት፤ልጆች መውለድና ማሳደግ…ወዘተ፡፡ሁል ግዜ ተሰፍሮ 25፤50፤25 ላይሆን ይችላል፡፡በተለይ ሴቶች ከእነሱ 25ፐርሰንት 10ሩን ወይም 15 ቱን ቆርሰው ለጋራቸው ያውሉታል…ወንዶች ደግሞ ከሞላ ጎደል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከጋራቸው ላይ ቆረስ አደርገው የእነሱን 25 ፐርሰንት 30 እና 40 አንዳንዴም ከ50 በላይ ያደርሱታል..የዛን ጊዜ የጋብቻው ባላንስ ይናጋል፡፡ምሰሶው መነቃነቅ ይጀምራል..እርማት ካልተደረገለት ጋብቸውን እያከሳ ይሄድና መጨረሻ ያከትምለታል፡፡…የምናገረው ግልፅ ነው አይደል››
‹‹አዎ..በጣም ግልፅ ነው፡፡››
‹‹በምሳሌ ይበልጥ ለማስረዳት አንድ ገጠር የምትኖር አክስቴ ከአስር በላይ ባሎች አግብታለች፡፡ግማሹን እነሱ ናቸው የፈቷት ግማሾቹን እራሷ ነች ያደረገችው፡፡ከሁሉም ግን የሳበኝን አንደኛውን ልንገራችሁ፡፡አገባሁት አለች..በጣም ሰላማዊ ..ምንም አይነት ክፉ ነገር ማይናገር…የጠየቅኩትን ሁሉ የሚያሞላልኝ ሰላማዊ ሰው ነበር አለች፡፡በፊት ከለመደቻቸው ተደባባዳቢ እና ተጨቃጫቂ ባሎች ጋር የትኛውም ፀባዩ የሚገጥም

አልነበረም፡፡ግን ብዙም ሳይቆይ ሰለቻት….ሁሉ ነገር ዝም እና ጭጭ ያለ ሆነባት…በቃ ግንኙነታቸው ውስጥ ነፍስ አጣችበት ፡፡አንድ ቀን በለሊት ተነሳና በሬዎቹንና ሞፈር ቀንበሩን ይዞ ወደማሳ ወጣ …ሲሄድ ቁርስም አልሰጠችውም..ምሳም ይዛ መሄድ ቢገባትም አልወሰደችለትም..ጭራሽም አልሰራችም…በጣም የባሰው ነገር ደግሞ የቤቱን እቃ ብረትድስት ፤ሰሀን ፤ብርጭቆ አንድም ሳታስቀር ከቤት ጀምራ የቤቱን መግቢያ ደጃፍ…ወለሉን ጠቅላላ አዝረክርካ እና ሞልታ ኩርሲ ላይ ቀጭ ብላ ትጠብቀው ጀመር ፡፡.
ከዛ መጣ…ከውጭ ጀምሮ ያዝረከረከችውን እቃ አንድ በአንድ ጎንበስ ብሎ እየለቀመ…‹‹እታዋቡ …ሰላም ነሽ….?ምንም አልሆንሺብኝም አይደል….?››እያለ ሁሉንም እቃ ወደመደርደሪያ መልሶ ስሯ ቁጭ ብሎ በልምምጥ ጭንቅላቷን መዳበስ ጀመረ..
ከዛ ይህቺ አክስቴ ምን ብታደርግ ጥሩ ነው‹‹ ብድግ አለችና ሻንጣዋን ይዛ‹‹እንዴት ቁርስ አላበላሁህ ..ምሳ አለመጣሁልህ….ቤቱን እዲህ አዝረክርኬ ነው የጠበቅኩህ..ምን እስካደርግህ ነው የምትጠብቀው…?ምንም አይነት የወንድነት ወኔ የለህም እንዴ…?ሁለት ሴት አንድ ቤት አይኖርም… ነውር ነው››ብላ ጥላው ወጣች..በዛው ፈታችው ፡፡አያችሁ ትዳር በጣም ውስብስብ ግንኙነት ነው፡፡የበዛ ጭቅጭና ጥል ብቻ ሳይሆን የበዛ ሰላምና ፀጥታም ሊያፈርሰው ይችላል፡፡፡ዋናው በሁሉም ነገር ሚዛን ጠብቆ መጓዝን መልመድ ነው፡፡››
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደና ፊትለፊቱ ካለ የታሸገ ውሀ በማንሳት አንዴ ተጎንጭቶለት ከንፈሩን አረጣጠበና ንግግሩን ቀጠለ፣እነሱም ልክ በቅርብ ፈተና እንደደረሰበት ቸካይ ታማሪ በጥሞናና በትኩረት እየተከታተሉት ነው‹‹አሁን ልብ በሉ፣ ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደለም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቅ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው.. በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ነገር ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር ለብንም፡፡እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

09 Nov, 06:21


‹‹አይ እነሱ ሳይሆኑ እኔ ነኝ እድለኛ….ምንም ባላደርግላቸው እንኳን ማንም ፊት በኩራት አባዬ ብለው ይጠሩኛል፡፡በቀደም ለሊሴ ይሄ ፌስቡክ ነው ምን በምትሉት ነገር ላይ በተንዠረገገ ፂሜንና በጎፈረ ፀጉሬ የተነሳሁትን የተጎሳቆለ ፎቶ ለጥፋ አባዬ መልካም

የአባቶች ቀን ..እወድሀለው… ዘላለም ኑርልኝ› ብላ የለጠፈችውን ሰው አሳየኝ…አየሽ እኔ ጎስቆላ አባቷን አለም ፊት በአደባባይ ይዛ ለመውጣት አልተሳቀቀችም..እንደውም በኩራት ነበር ያደረገችው…..ከአራት አመት በፊት ምን ሆነ መሰለሽ..እኔ አባትሽ የተቀደደና ያደፈ ቱታ ለብሼ አንድቤት ጣሪያላይ ወጥቼ ቆርቆር እየጠገንኩ ነበር…ስራዬን ጨርሼ ከጣሪያው በመሰላል በመውረድ ላይ እያለሁ እታች ትላልቅ ሱፍ ለባሽ ሰዎች ቤቱን እየተመለከቱት ነው…ከመሀከላቸው ልጄ በሬዱ ነበረችበት…ለካ ያ ቤት የባንክ እዳ ኖሮበት ጫረታ ላይ ሊያወጡት ከባንክ የመጡ የስራ ኃላፊዎች ነበሩ ..የልጄ ሀለቃዎች…ልክ ልጄን እንዳየኋት ተመልሼ ወደላይ መውጣት ጀመርኩ..ለካ ልጄም በዛው ቅፅበት አይታኝ ኖሮ‹‹…አባዬ
..አባዬ ና አንዴ ውረድ››ስትል የት ልግባ….ምርጫ ስላልነበረኝ ወደታች ወረድኩ…ቆሻሻዬን ሳትጠየፍ ጉስቁልናዬን ከቁም ነገር ሳጥቆጥር አገላብጣ እየሳመች ወደሀለቆቾ ይዛኝ ሄደችና…‹‹አባቴ ነው ..ተዋወቁት ብላ አስተዋወቀችኝ…አክብራ አስከበረችኝ››እነሱን ከሸኘሁ በኃላ ለብቻዬ ገለል ብዬ እንደህፃን ልጅ አለቀስኩ…እና ምን ልልሽ ነው እኔ ነኝ እድለኛው፡፡››
‹‹አይ ጋሼ…እኔ አንተ አባቴ ብትሆን በጀርባዬ አዝዬ ድፍን አዲስአበባን እዞር ነበር….››
‹‹አይ አንቺ…አሁንም አባትሽ ነኝ ..አይደል እንዴ?››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው ..አንተ ያደረክልኝ…ግማሹን አባቴ አድርጎልኝ አያውቅም፡፡ማለቴ አሁን እየተነፈስኩ ያለሁት ባንተ ደግነት ነው››
‹‹አይ አንቺ ልጅ….››
‹‹ጋሼ››
‹‹አቤት ልጄ››
‹‹አንድ ነገር ልጠይቅህ ነበረ.. ግን ፈራሁ››
‹‹እንዴ ..እኔ እኮ አባትሽ ነኝ ምን ያስፈራሻል?››
‹‹እንተን.ማለቴ ያው በህመሜ ምክንያት ረጅም ጊዜ ስተኛና ከቤት ሳልወጣ ስለቆየሁ ተጨናንቄያለው…ለተወሰነ ቀን ከለሊሴ ጋር ላንጋኖ ወይም የሆነ ቦታ ሄደን ትንሽ ተዝናንተን ብንመጣ ብዬ ነበር››
‹‹ከለሊሴ ጋር ስራዋስ ልጄ?››

‹‹አልሰማህም እንዴ….ሀለቃዋ እኮ ለስራ ሌላ ሀገር ለአንድ ወር ስለሄደ ፍቃድ ሰጥቶታል፡፡››
‹‹እንደዛ ነው››፣አሉና መልስ ሳይሰጡ ወደትካዜ ውስጥ ገቡ…ምን ብለው ሁለት የደረሱ ሴቶችን እንደሚፈቅዱላቸው ምን ብለውስ እንደሚከለክሎቸው ግራ ገባቸው››
‹‹በፀሎትም መልሱን ለመስማት አፏን ከፍታ በጉጉት መጠበቋን ቀጠለች››
‹‹የእኔ ልጅ ያልሽው ትክክል ነሽ..አየር መቀየርና ትንሽም ዘና ማለት አለብሽ…ግን ሁለታችሁም ሴቶች ናችሁ …ለምን ወንጪ አትሄዱም››
‹‹እንዴ ጋሼ..ደስ ይለኛል….ቦታው አሪፍ ይመስለኛል››
‹‹አዎ ቦታውማ ገነት በይው..ግን ከቦታውም በላይ ትውልድ አካባቢዬ ነው..አሁንም ዘመዶቼ እዛ አሉ..ወንድሞቼ እህቶቼ ብዙ ናቸው..ለሊሴም ቦታውን በደንብ ታውቀዋለች..እዛ ከሄዳችሁ እኔ አባታችሁ ምንም አላስብም….የፈለጋችሁትን ያህል ቀን መቆየት ትችላላችሁ..ግን የእናትሽ የጽዋ ማህበር የዛሬ ሳምንት ነው..ከዛ በፊት እንድትሄዱ አትፈቅድላችሁም››
‹‹አመሰግናለው ጋሼ..››ከመቀመጫዋ ተነሳችና አቅፋቸው ግንባራቸውን ሳመቻቸው፡፡››
‹‹ልጄ አመሰግናለው››
‹‹እኔ ነኝ እንጂ ማመሰግነው››
‹‹አይ አመሰግናለው ያልኩሽ ሁል ጊዜ በድርጊቶችሽ ልጄ በሬዱን ስለምታስታዊሺን ነው..አፈሩን ገለባ ያድርግላትና እሷም እንደእዚህ አንደአንቺ የሆነ ነገር ጠይቃኝ እሺ ካልኳት አቅፋ ትስመኝ ነበር….››
‹‹ይቅርታ ጋሼ እሷን እንድታስታውስ ስላደረኩ››
‹‹አይ…እንዳስታውሳት ስለምታደርጊኝ ሚከፋኝ መሰለሽ….?ልጄን መቼም መርሳት አልፈልግም…ደግሞ የምትረሳም ልጅ አይደለችም…የእኔ በሬዱ ቶሎ ተወልዳ በፍጥነት አድጋ…በጮርቃነቷ በስላ..በችኮላ ጥሩጥሩ ነገሮችን ሰርታ እኔ አባቷን አስደስታ የሞተች ድንቅ ልጅ ነች.…በይ የሆነች ለቅሶ ቢጤ አለችብኝ፣ደረስ ብዬ ልምጣ..እስከዛ ከእናትሽ ጋር

ተጫወቺ…››አሉና የሚተናነቃቸውን እንባ እንደምንም ተቆጣጥረው ወደውስጣቸው በመመለስ ከመቀመጫቸው ተነሱ፡፡
‹‹እሺ ጋሼ…እንዳትቆይ››
‹‹አልቆይም ልጄ..››አሉና ኮፍያቸውን ከጠረጴዛ ላይ አንስተው ጭንቅላተቸው ላይ አስተካከለው እያደረጉ ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡
ሰኞ ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

09 Nov, 06:21


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራስምንት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ሰለሞንና በፀሎት በስልክ እያወሩ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለሽው?››ሲል ጠየቃት
‹‹ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ..እንዲሁ ደህንነትሽ አሳስቦኝ ነው….ምን አልባት የማይመች ቦታ ካለሽ ልረዳሽ እችላለው፡፡››
‹‹ምነው ወደቤትህ ወስደህ ደብቀህ ልታኖረኝ አሰብክ››

‹‹ምነው ..ችግር አለው.?.የእውነት የማይመች ቦታ ካለሽ ንገሪኝ››
‹‹አሁን ካለሁበት ቦታ የተሻለ ሊመቸኝ የሚችለው ምን አልባት ገነት ነው….እሱንም ደግሞ ስላላየሁት እርግጠኛ አይደለሁም››
‹‹እንዴ…ከእናትና አባትሽም ቤት የተሻለ ቦታ ነኝ ነው የምትይኝ…ይሄንን ማመን አልችልም፡ ››
‹‹ነገርኩህ እኮ…››
‹‹‹እ ..ገባኝ››
‹‹ምኑ ነው የገባህ?››
‹‹ከእናትና አባት ቤት በበለጠ የሚመች ቦታ የፍቅረኛ ቤት ነው››
‹‹በጣም ተሳስተሀል..አዲስ ቤተሰብ አግኝቼለሁ…አራት ናቸው..ሽማግሌ አባትና እናት፣አንድ ዋንድ ሴትና ወንድ ልጅ አላቸው..ሀለት ክፍል ሰርቢስ ውስጥ ነው የሚኖሩት፣ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው… ፍቅራቸው ግን ሞልቶ የፈሰሰ ነው….ለዘላለም ልጃቸው አድርገው ተቀብለውኛል…ከአሁን ወዲህ ባለው ህይወቴ ሙሉ አነሱ ወላጆቼ እና ቤተሰቦቼ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ ምንም ነገር አደርጋለው››
‹‹የሚገርም ነው….እናትና አባትሽ ይሄንን ንግግርሽን ቢሰሙ ልባቸው የሚሰበር ይመስለኛል፡፡››
‹‹እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም…በእነሱ ስህተት ነው ከቤት የወጣሁትና እነሱን ያገኘሁት…አሁን አግኝቼ በደንብ አጣጥሜቸዋለው…እና ወደቤት ብመለስ እንኳን ወላጆቼን ከእነሱ ጋር ነው ማነፃፅራቸው…እና ለእነሱ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም››
‹‹….ለመሆኑ ማንነትሽን ያውቃሉ?›
‹‹አይ አያውቁም.. እኔ ለእነሱ እናቷ የሞተችባት እና የእንጀራ አባቷ ሰክሮ በለሊት ሊደፍራት ሲል አምልጣ የወጣች ሚስኪን ሴት ነኝ››
‹‹ይሄንን ታሪክ አንቺ ነሽ የፈጠርሽው?››

‹‹አዎ…..››
‹‹የምትገርሚ ልጅ ነሽ ..እኔጋም መጥተሸ ተመሳሳይ ታሪክ ብትነግሪኝ አምኜ ልረዳሽ መሞከሬ አይቀርም ነበር››
‹‹የእነሱ እኮ መርዳት አይደለም….እናትና አባት መሆን ነው…..እንደልጃቸው መቀበል››
‹‹ የእውነት አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እኔ እራሱ ለመተዋወቅ ጓጓሁ› ›
‹‹መጓጓትህ ትክክል ነህ››
‹‹ነገሮች ከተስተካከሉ በኃላ ታስዋውቂኛለሽ ብዬ ገምታለው››
‹‹መጀመሪያ እስኪ እኛ ለመተዋወቅ ያብቃን››
‹‹እንዴ እኛኮ በደንብ ተዋወቅን፣ለአመታት የማውቅሽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..ያው አካል ለአካል አልተገናኘንም ብዬ ነው፡፡››
‹‹ባክሽ የስልኬ ጋላሪ ባንቺ ፎቶዎ ተጨናንቆል ››ብሎ ያልጠበቀችውን አስደንጋጭ ነገር ነገራት፡፡
‹‹እንዴ በምን ምክንያት?››
‹‹እንዴ ..ደንበኛዬ አይደለሽ?››
‹‹እና የሁሉንም ደንበኞችህን ፎቶ ትሰበስባለህ ማለት ነው?››
‹‹ቆንጆ እና የተለየ የሆኑትን ..አዎ››
‹‹በቻይንኛ ቆንጆ ነሽ እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹እ..ምነው አይደለሽም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ….ለማንኛውም ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ አድርገሀል…እና እኔስ የአንተን ፎቶ የማግኘት መብት ያለኝ አይመስልህም?››

‹‹አይ..አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እንድምታስተዋውቂኝ ቃል ካልገባሽ የምታገኚ አይመስለኝም››
‹‹አዲሶቹን ቤተሰቦቼን….እኔ እንጃ ..ስለምሰስታቸው የማደርገው አይመስለኝም››
‹‹‹ትገርሚያለሽ…፣ዋናዎቹን ቤተሰቦችሽን እኮ ተቆጣጥሬቸዋለው…..ለማንኛውም ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስላገኘሽ ደስ ብሎኛል….ይሄውልሽ በህይወት ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ፡፡ቅጠል የሆኑ ሰዎች… ቅርንጫፍ የሆኑ ሰዎችእና… ስር የሆኑ ሰዎች።ቅጠል የሆኑ ሰዎች ወቅትንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ወደ ህይወትሽ የሚገብ ናቸው።ደካሞች ስለሆኑ በእነሱ ተፅዕኖ ስር ፈፅሞ እንዳትወድቂ። ከአንቺ የሚፈልጉትን የሆነ ነገር ስላለ ነው ወደህይወትሽ የሚመጡት... የመከራ ንፍስ በህይወት ዙሪያ ሲነፍስ መርገፍ ይጀምራሉ።እነዚህ ሰዎች አንቺን ማፍቀር የሚቀጥሉት በዙሪያሽ ያሉ ነገሮች ጥሩ እስከሆኑ ጊዜ ብቻ ነው።ንፋስ እንደመታው የወየበ ቅጠል ከላይሽ ላይ ተዘንጥለው ይረግፋሉ። ቅርንጫፍ ሰዎች ደግሞ በአንፃራዊነት ጠንካሮች ናቸው ግን ልትጠነቀቂያቸው ይገባል።ህይወት ጨከን ስትል መገንጠላቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጠንከር ያለ የህይወት ጫና የመሸከም አቅም የላቸውም።ነገሮች ጨለምለም ሲሉ እና ተስፋም የሌላቸው ሲመስሉ ጥለውሽ ዞር ለማለት አያመነቱም። ሌሎቹ ልክ እንደአንቺ አዲሶቹ ቤተሰቦች ስር የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ በህይወትሽ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው።ለመታየት ብለው የሚሰሩት ስራ የለም።በመከራሽም በደስታሽም ጊዜ አብረውሽ ናቸው።አስከሞት የታመኑሽ ናቸው።ሲያፈቅሩሽ በነፃ ምንም መልስ ካንቺ ሳይጠብቁ ነው፣እንደዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰው ከጎንሽ ማግኘት የህይወት ዘመን ሽልማት ነው፡፡
‹‹ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣አንተም ለእኔ ስር ነህ…በቃ ቸው…ነገ እንደዋወላለን፡፡››
‹‹ቸው …..ደህና ሆኚ››ብሎ ስልኩን ከዘጋ በኃላ …ባለበት ቆሞ ትካዜ ውስጥ ገባ..ይህቺን ልጅ በተመለከተ የተለየ አይነት ኬሚስትሪ በሰውነቱ እየተረጨ ነው….ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡

በማግስቱ……
በፀሎት ከሞላ ጎደል ጤንነቷ እየተመለሰ ነው…አረ እንደውም ድናለች ማለት ይቻላል..የእግሯ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ በደንብ መራመድ ችላለች..የፊቷ ቁስለትም ሙሉ በሙሉ ጠጓል..አሁን ብቸኛ ችግሯ ፊቷ ላይ ተሸነታትሮ የሚገኘው ጠባሳ ብቻ ነው….እንግዲህ ግማሽ ፊቷን ባደረሰው በተበታተነው ጠባሳ ውስጥ ምን ያህሉ እንድሚጠፋና ከበፊት ቆዳዋ በቦታው እንደሚመለስ ምን ያህሉ ደግሞ እንዳዛው እንደሚቀር ምንም የምታውቀው ነገር የለም…ያንን ለማወቅ በርከት ያሉ ተጨማሪ የማገገሚያ ቀኖች ያስፈልጋታል…ከዛ በኃላ የቆዳ ስፔሻሊስቶች ጋር ሔዳ ሰርጀሪ መሰራትም የግድ ያስፈልጋት ይሆናል….ለጊዜው ያ እያሳሰባት አይደለም…‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ወደቤት ከተመለስኩ በኃላ አስብበታለው››ብላ ወስናለች….አሁን ከጎኗ አቶ ለሜቻ ቁጭ ብለው እያጫወቷት ነው፡፡
‹‹ለልጆቾህ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል››
‹‹አይ ልጄ ሁሉም ወላጆች እኮ ልጆቻቸውን አብዝተው ይወዳሉ…››በትህትና መለሱላት፡፡
‹‹እሱን ማለቴ አይደለም..የእናንተ የተለየ ነው…አይኖችህ ከልጆቾህ ላይ አይነቀሉም….ሙሉ ትኩረትህ ልጆቾህ ላይ ነው..ስለእለት ውሏቸው ታውቃለህ….ጥዋትና ማታ አብረሀቸው ባንድ መሶብ ቀርበህ ሁለቱንም እያጎረስክ ነው የምትበላው፣ብዙ ብዙ ነገር…››
‹‹ልጄ ወድጄ አይደለም እኮ…. እንደምትይው እኔ አባትሽ በብዛት ተትረፍርፎ ያለኝ ፍቅር ነው…ገንዘብ ኖሮኝ ይሄን ስሩ ብዬ መቋቋሚያ..ወይም መነገጃ ጥሪት አልሰጣቸው….ሁል ጊዜ ታዲያ ይሄንን ነገር በምንድነው የማካክሰው ብዬ ሳስብ አንድ የማገኘው መልስ…ጊዜዬንና ፍቅሬን ሳልሰስት መስጠት ነው..አዎ ቢያንስ በዛ ነው ልክሳቸው የምችለው፡››
‹‹ግን እንሱ ምን ያህል እድለኞች መሆናቸውን ያውቃሉ?››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

08 Nov, 06:49


ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

08 Nov, 06:49


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራ ሰባት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ይዘውት የሄዱት ቦታ ከቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሀይቅ አካባቢ ከከተማው ወጣ ብሎ የሚገኝ ቪላ ነው፡፡ይህ ቪላ ቤተሰቡ ከውጥረት ረገብ ለማለት ሲፈልግ የሚገለገልበት ስፋራ ነው፡፡ለአለፉት አንድ አመት ከግማሽ ማንም ዝር ብሎበት አያውቅም ነበር፡፡ሰለሞን ስፍራውን ሲያይ ከውበትም ሆነ ከፀጥታ አንፃር ሲታይ ሙሉ በሙሉ እሱ እንደሚፈልገው አይነት ሆኖ ነው ያገኘው፡፡አንድ ሺ ካሬ ሜትር በላይ የሚሆን ቅፅር ግቢ ነው፡፡መሀከል ላይ ግዙፍና ባለግርማ ሞገስ ጥንታዊ ግን ደግሞ ጥሩ ይዞታ ላይ ያለ ግዙፍ ቪላ ቤት አለበት…ግቢው ውስጥ እድሜ ጠገብ ግዙፍ ባለግርማ ሞገስ የባህር ዛፍና የጥድ ዛፎች ስብስባ ላይ እንደተቀመጠ ታዳሚ እዚህም አዛም ዙሪያውን ተሰራጭተው ይታያሉ…ገና ግቢውስጥ ገብተው እንዳቆሙ የቤት ጠባቂዎች በልና ሚስቶች በፍጥነት መጥታው መኪናዋ አጠገቡ ቆሙ፡፡መኪናዋን ሲነዳ የነበረው እራሱ ሰሎሞን ስለነበረ….ሞተሩን

አጠፋና ቀድሞ ወረደ…አቶ ኃይለመለኮትን ወ.ሮ ስንዱም ወረዱና ከጠባቂዎቹ ጋር ሰላምታ መለዋወጥ ጀመሩ…ከዛ ቀጥታ ወደ ቤት ነው የገቡት….ቀድመው ደውለው ስለነበር..እቤቱ ምሉ በሙሉ ፀድቶና የእነሱም መኝታ ክፍል ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው….
ታፈሰ ‹‹ጋሼ ባዘዙኝ መሰረት ሶስት ክፍል ለመኝታ አዘጋጅቼያለው…ይሄው እርሶ እዚህ ግቡ….እትዬ ደግሞ ቀጥሎ ያለው …ወንድም አንተ ደግሞ የፊት ለፊተኛው ክፍል…..ድንገት ስለሆነብን ሁሉንም ነገር ማዘጋጀት አልቻልንም….የጎደለውን ንገሩኝና ከተማ ወጣ ብዬ ገዝቼ አሟላላሁ››
አቶ ሃይለመለኮት ወደሰለሞን እያመለከቱ‹‹ተፈሰ…ይሄውልህ እዚህ 15 ቀን ነው የምንቆየው….በዚህ 15 ቀናት ውስጥ የእኛም ሆነ የአንተ ሀለቃ እሱ ነው….ምንም ነገር ቢያዝህ እሱ ያለውን ነው የምታደርገው…እኛም እንደዛው››ሲሉ መመሪያ አስተላለፉ፡፡
ታፈሰ…የአቶ ኃይለልዕልን ንግግር ከበፊት ቆፍጣና ባህሪያቸው ጋር አልሄድ ስላለው ..ግራ በመጋባት አፍጥጦ ያያቸው ጀመር…እሱ እንደሚየውቀው እኚ ግዙፍ አዛውንት ለሰው ምንም ሊሰጡ ይችላሉ የአዛዥነት ቦታቸውን ግን ፈፅሞ ሸርፈው እንኳን ለሌላ ሰው ይሰጣሉ ብሎ ማመን ይከብደዋል፡፡
‹‹ታፈሰ ..ሰምተኸኛል…የሁሉ ነገር አዛዣችን እሱ ነው››ደገሙለት፡፡
‹‹አዎ ..ገባኝ ጌታዬ…እንዳሉት ይደረጋል››
‹‹አሁን ሁላችንም ወደክፍላችን እንግባና ትንሽ አረፍ እንበል ..አይደል?››ወ.ሮ ስንዱ የሰለሞንን አይኖች በልምምጥ እያዩ ጠየቁ፡፡
ቆይ አንዴ ክፍላችሁን ልይ ብሎ..ለአቶ ኃይለልኡል የተመደበውን ከፍቶ አየው፡፡ቀጥሎ የወ.ሮ ስዱን ከፈተና አየው፡፡‹‹ጥሩ በቃ ግቡና እረፉ››
ሁለቱም ገቡና የየራሳቸውን ክፍል ዘጉ
‹‹አንተም ወደክፍልህ ግባ ጌታዬ..እኔ ደግሞ እቃችሁን ከመኪና ላውርድ››
‹‹ቆይ አብሬህ ልምጣ››ብሎ ተከተለው፡፡የታፈሰ ባለቤት ለእንግዶቹ ምግብ እያበሰለች ስለነበር ታፈሰ እቃዎቹን ማለት ይዘው የመጡትን አስቤዛ እና ሻንጣዎች ሲያወርድና ወደቤት ሲያስገባ ሰሎሞን አገዘው፡፡እንደጨረሱ፡፡‹‹ተለቅ ያለ ክፍል የለም?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ምን አይነት ክፍል…ማለቴ ለምን የሚሆን?››
‹‹ለመኝታ ቤት የሚሆን ..ሁለት አልጋ የሚያዘረጋ››
‹‹ቆይ ..ኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ያለው ክፍል ሰፋ ይላል››
‹‹ማየት እችላለሁ?››
‹‹አዎ ይቻላል….››ብሎ ይዞት ሄደና ከፈተለት…ሰለሞን ወደውስጥ ዘልቆ ሳይገባ በራፉ ላይ በመቆም አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ተመለከተው….አቦራ የጠጣና ለብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቢሆንም የሚፈልገው አይነት ክፍል ነው፡፡››
‹‹ታፈሰ ይሄንን ክፍል በአስቸኳይ ልታስፀዳልኝ ትችላለህ….?››
‹‹እችላለሁ..አፀዳዋለው››
‹‹አይ ብቻህን ይከብድሀል..ሰው ቅጠርና በፍጥነት ወለሉም ግድግዳውም ይፅዳ….ውስጥ ያሉት እቃዎችም ወደሌላ ክፍል ይዘዋወሩ››
‹‹እሺ››
ተሰናብቶት ንፁህ አየር ሊቀበልና እግረመመንገዱን አካባቢውን ለመቃኘት ወጥቶ ሄደ፡፡
///
በማግስቱ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ሁለቱንም የማይጣጣሙ ባለትዳሮችን አንድ ክፍል ጎን ለጎን እንዲቀመጡ አደረገና እሱ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ..ጉሮሮውን አፀዳዳና የመግቢያ ንግግሩን ጀመረ
‹‹በሰዎች መካከል ለተለያየ አለማ ተብለው የሚደረጉ የእርስ በርስ ጉድኝቶችና ቁርኝቶች አሉ፡፡ከነዛ መካከል ግን በጣም ውስብስቡ የጠበቀውና የጠለቀው ግንኙነት በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የሚፈጠር የጋብቻ ጉድኝት ነው፡፡በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁሉ ጊዜ ቀላል የተባለ መንገድ አይገኝም….አንዱ ጋብቻ ውስጥ የሚፈጠረው ችግር ከሌላው ጋብቻ ችግር በአይነትም በይዘትም ፍፁም የተለየ በመሆን ችግሩን ለማስተካከል የሚወሰደውም እርምጃ የዛኑ ያህል የተለያ ነው፡፡በዛ ላይ ሁሉም ችግሮች እዲፈቱ በጥንዶቹ መካከል ስክነት፣ ትዕግስትን፣ጥረትን እና እራስ መግዛትን

ይጠይቃል፡፡አሁን ልብ በሉ ፣ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደልም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቃችሁ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር የለብንም፡፡
እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራች ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ገና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም ..አዎ አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት መነጋገር ነው፡፡ሌላው በምንም አይነት ሁኔታ ንግግራችሁ ሰው ፊት አይሁን፡፡የምንወደው ሰው ላይ ያለንን ቅሬታ ብቻውን በሆነበት ጊዜ ነው መናገር ያለብን…እንደዛ ሲሆን ነው ውጤታማና ጥፈቱን ለማረም ፍቃደኛ የሚሆነው…ወቀሳው..ሰው ፊት ሲሆን ግን ሰውዬው የበለጠ በእኛ ቅሬታ እንዲያድርበት መንገድ ያመቻቻል፡፡
‹‹እንግዲ ሁላተችሁም እንደምታውቁት አሁን ለእኛ እዚህ መገኘት ዋናዋ ምክንያት በፀሎት ነች፡፡እኔ በስራ በተለይ ከሀገር ውጭ በነበርኩበት ጊዜ በጣም ብዙ ባለትዳሮችን አማክሬያለሁ ትዳራችውም መካከል ያለውን ችግር በመተጋገዝ ለመፍታት ችያለሁ....በብዙዎችም ረክቼለው..ከብዙ ቤተሰቦች ጋርም እቤተሰብ ለመሆን ችያለው….ግን እመኑኝ እንዲህ እንደእናነተ የተለየ ጉዳይ ገጥሞኝ አያውቅም››
‹‹የተለየ ስትል?››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

08 Nov, 06:49


‹‹እስከአሁን ወደእኔ መጥተው የሚያናግሩኝ ከሁለት አንዱ ማለቴ ባልዬው ወይም ሚስትዬው ናቸው….የእናንተ ግን ልጃችሁ ነች ያናገረችኝም የቀጠረችኝም፡፡››
‹‹አዎ እሱስ ትክክል ነህ››
‹‹ስለዚህ አሁን ስራችንን ስንጀምር እሷን እያሰብን መሆን አለበት ፡፡በፍቅር የታነፀ ትዳር ውስጥ ያላደጉ ልጆች በመጨረሻ በስነ-ልቦናም ሆነ አካላዊ በሽታ እንደማያጣቸው የተረጋገጠ ነው። ልጅ ስናሳድግ ጥሩ ልብስ ፣ጥሩምግብና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኙ መጣር ብቻ ሳይሆን የተሞላ ፍቅርም እየመገብን ማሳደግ እንዳለበት እንደወላጅ ግንዛቤው ሊኖረን ይገባል።የመፈቀር እና የመፈለግ ስሜት ማጣት በከፍተኛ ሁኔታ የልጆችን በራስ የመተማመን ችሎታን ከመሸርሸሩም በላይ ለአእምሮ ውጥረትና ድብርትም እንዲዳረጉ ያደርጋቸዋል።ለልጆች በፍቅርና በእንክብካቤ ማደረግ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር ብቻ ሳይሆን ጤነኛም ሆኖ ለመኖር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።በወላጆቹ የሚወደድ እና ወላጆቹም የሚወድት ልጆች በጣም ደስተኛ ናቸው።በፍቅር ውስጥ መኖር ጤነኛ ሆኖ ለመኖር እና የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ለመጨመር እንደሚያግዝ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።ስለዚህ ልጆቻችን በፍቅር ታንፀው የመፈለግና የመወደድ ስነልቦና ኖሮቸው ማደግ አለባቸው፡፡ለዚህም ወላጆች ሁሉ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው፡፡፡ እንደውም እናንተ እድለኛ ናችሁ፡
‹‹እድለኛ ናችሁ ስትል?››
‹‹እንዴ በፀሎት እኮ በጣም የምትገርም ብስልና በቀላሉ የማትሰበር ልጅ ነች፣አብዛኞቹ በእሷ እድሜ ያሉ ልጆች በእንደዚህ አይነት ችግሮች ውስጥ ሲያልፉ ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ይገቡና ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣሉ ..ከዛም አልፈው በህይወት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገቡና እራሳቸውን ወደማጥፋት ይሄዳሉ….በፀሎት ግን ያደረገችው ከውጥረቱ ራሷን ዞር አድርጋ እናንተን ለመርዳትና ወደመስመር ለመመለስ መጣር ላይ ነው ያተኮረችው››
‹‹አዎ እውነትህን ነው …በልጄ ታላቅ ኩራት ተሰምቶኛል….ምንም ጭረት ሳይነካት ወደቤቷ እንድትመለስ ማድረግ ያለብኝን አደርጋለሁ..ማለት ሁለታችንም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን አይደል ስንዱ?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…ለዛም አይደል እዚህ የተገኘነው››

‹‹እንግዲያው ጀመርን …ከአሁን በኃላ የምናወራውና የምንናገረው ሁሉ እየተቀዳ ነው.››.ብሎ አይፓዱን አስተካክሎ ተጫነውና ቦታውን ይዞ ተቀመጠ…››
ለሶስት ሰዓት ቀጠለ…..በመጀመሪያ ወ.ሮ ስንዱ አቶ ኃይለመለኮት ላይ ያላቸውን ቅሬታ እስከአሁን በደሉኝ የሚሉትን ነገር እንዲያወሩና አቶ ኃይለመለኮት ደግሞ ለደቂቃ እንኳን ሳያቆርጡ እንዲሰሙ አደረገ…በቀጣዩ ሰዓት ደግሞ አቶ ኃይለልኡል በተራቸው ሚስታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በዝርዝር እንዲናገሩ አደረገ……..ቀጣዩን አንድ ሰዓት ደግሞ እራሱ ሰሎሞን ጥያቄ እየጠየቃቸው ሁለቱም ተራ በተራ እዲመልሱ ተደረገና የጥዋቱ ክፍለጊዜ አለቀና ሶስቱም ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ ..ምሳው በስርአት ተዘጋጅቶ ስለጠበቃችው ሶስቱንም ጠረጴዛውን ከበው ፀጥታ በተጫነው ና እርስ በርስ በተፈራራ በሚመስል ሁኔታ ምሳቸው ተበልጦቶ አለቀ..ብና ተፈልቶ ስለነበረ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ንፋስ እየተቀበሉ ጠጡ
‹‹አሁን ለአንድ ሰዓት ያህል መኝታ ክፍላችሁ ገብታችሁ አረፍ በሉ….ሰዓት ሲደርስ እኔ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››
እሺ ብለው ሁለቱም ከመቀመጫቸው ተነሱ..ሰለሞን ከኃላ ተከተላቸው….››መኝታ ቤታቸው እንደደረሱ ሊከፍቱ ሲታገሉ‹‹ይቅርታ ሳልነግራችሁ መኝታ ቤታችሁ ተቀይሮል..ተከተሉኝ››ብሎ ቀደማቸው፡፡
‹‹የማ…? የእኔም ነው የተቀየረው?››
‹‹አዎ ወ.ሮ ስንዱ….ሁለታችሁም ተከተሉኝ..››
ግራ በማገባት ሁለቱም በዝምታ ከኃላው ተከተሉት …የኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ካለው በራፍ ሲደርስ ቆመና ከፈተው….‹‹ግቡ ››
‹‹ማ እኔ ነኝ እሷ?››
‹‹ሁለታችሁም››
እርስ በርስ ተያዩ…ቀጥሎ በጋራ እሱ ላይ አፈጠጡበት…አንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከተኙ አስር አመት አልፏቸዋል..አሁን በአንዴ እንዴት….?ጉዳዩ ሁለቱንም እኩል ነው ያስበረጋጋቸው፡፡

ጫን ባለ የአዛዥነት ቃና‹‹እባካችሁ ግቡ››አላቸው
ምርጫ ስላልነበራቸው አቶ ኃይለልኡል ቀድመው ገቡ…ወ.ሮ ስንዱ ተከተሏቸው….ሁለቱም ጎን ለጎን ቆመው ክፍሉን ዙሪያ ጋባ ቃኙት …ሻንጣቸው ሆነ ጠቅላላ እቃቸው በየቦታው ተቀምጦል…ሁለት አልጋ ማዶ ለማዶ ግድግዳ ተጠግቶ ይታያል…፡፡
ያው ..ሁለት አልጋ አለ …ተነጋገሩና አንዳንደ አንድ ተካፈሉ …በቃ መልካም እረፍት..ሰዓቱ ሲደርስ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››አለና ከክፍሉ ወጥቶ በራፉን መልሶ ዘግቶላቸው ወደገዛ ክፍሉ ሄደ፡፡
///
የሁለት ሰዓት የረፍት ጊዜ ከሰጣቸው በኃላ በጥዋቱ ጊዜ ባለው ፕሮግራም የቀረጸውን ወደኮምፒተሩ ገለበጠና ይዞ ወደእነሱ ክፍል አመራ…በስሱ ቆረቆረ…ወዲያውን ነበር የተከፈተለት፡፡
‹‹መጣህ ..?እየጠበቅንህ ነበር››
‹‹አዎ መጥቻለው››
‹‹ስንዱ ተነሽ..እንሂድ››አቶ ኃይለልኡል ተናገሩ፡፡
‹‹አይ ቆይ መሄድ አያስፈልግም ….እዚሁ እናድረግው››
‹‹ይሻላል ..እሺ ግባ..››ብለው በራፉን ለቀቁለትና ወደውስጥ በመመለስ አልጋቸው ጠርዝ ላይ ተቀመጡ ፡፡ወ.ሮ ስንዱም የራሳቸው አልጋ ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡
ወንበር ሳባና ከሁለቱ መካከል ተቀመጠና ኮምፒተሩን ጠረጳዛ ላይ አስቀመጠው፡፡
‹‹ይሄውላችሁ በትዳር ውስጥ ችግር መፈጠርና አለመስማማት የእናንተ ብቻ ሳይሆን የሚሊዬን ጥንዶች ችግር ነው..እመኑኝ ያልተስማማንበት ነገር ይህ ነው ያ ነው ብላችሁ ቀኑን ሙሉ ስትዘረዘሩ ብትውሉ የእናንተ ከሌላው ትዳር ውስጥ ከተፈጠረው ችግር የተለየ ሊሆን ይችላል እንጂ የባሰ ግን አይደለም፡፡ስሙኝ አብዛኛውን ጊዜ በትዳር ውስጥ ችግር ሲከሰት በትዳር ውስጥ ችግር የፈጠረውን ነገር ከማየት ይልቅ እራሱ ትዳርን እንደችግር የመውሰድ አዝማሚያ ይታያል።ያ ደግሞ ከትዳራቸው ውስጥ ሾልኮ ስለመውጣት

ስለመፋታት እንዲያስብ ያደርጋቸዋል።እንደሀሳባቸው ትዳራቸውን ፈተው የተሻለ ወዳሉት ወደሌላ ትዳር መሸጋገር ቢችሉም ችግሩም አብሯቸው ነው ወደአዲሱ ትዳራቸው የሚሸጋገረው።
መፍትሄው ትዳሩን እንደችግር ወስዶ ያልሆነ ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ይልቅ ትዳሩ ውስጥ የተከሰቱ ችግሮች ምን ምን ናቸው ብለው በመለየት እነሱን ለማስወገድ መጣር እና በዛ ሂደት የጋብቻውን ህልውና ማስቀጠል ይበጃል።ምክንያቱም የመኪናህ ጓማ ቢያልቅ ጎማውን ትቀይራለህ እንጂ መኪናዋን ሙሉ በሙሉ አታስወግድም።አይደለም ጎማ ሞተሩ ቢነክስ እንኳን ሞተር አስወርደህ ከእንደገና ተፈቶና ተበታትኖ ችግሩ ተለይቶ ከተወገደ በኃላ መልሶ ይገጣጠምና መኪናው እንደነበረ ይቀጥላል... ጋብቻም እንደዛ ነው የሚደረገው።እና አሁን እያደረግን ያለነው በመሀከላችሁ ያለውን ችግር የመቃቃራችሁን መንሴ መለየት ነው፡፡አሁን በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ ሁለታችሁም የተናገራችሁትን እዚህ ኮምፒተር ላይ ከፍትላችኃላው በጋራ አብራችሁ ታዩታላችሁ…ይሄ መልሳችሁ የተናገራችሁትን እንድታዳምጡና የትኛው ትክክል ነው..የትኛው ንግግራችሁ ተጋኗል የሚለውን መልሳችሁ እንድታስበቡበት ይረዳችኃላ…በቃ አሁን ቀጥታ ወደማዳመጡ እንግባ ››አለና ኮምፒተሩን ከፈተና ለ.ወሮ ስንዱ አቀበላት…አቶ ኃይለልኡል ያለምንም ንግግር ከተቀመጠበት የራሱ አልጋ ተነሳና ሄዶ ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ላይ ከጎኗቸው ተቀመጠና በኮምፒተር የሚታየውን የራሳቸውን ንግግር ለማደመጥ ዝግጁ ሆነ…ሰለሞን በፀጥታ ከተቀመጠበት ተነሳና ክፍልን ለቆ በራፍን ዘጋላቸውና ወጥቶ ሄደ…
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

07 Nov, 07:32


….ከሶስት ቀን በኃላ
አቶ ለሜቻ ነገሮችን ተቀብለው….ቱታቸውን ለብሰውና ሌሎች ሁለት ሰዎችን ቀጥረው ቀጥታ ቤቱን ወደመገንባት ስራ ገቡ..ይሔ ሁኔታ የቤቱን ሰው ሁሉ በጣም ሲያስደስት በፀሎትን ደግሞ በይበልጥ አስፈነጠዛት፡፡ቢያንስ አንድ ነገር ልታደርግላቸው በመቻሏ የውስጥ እርካታ ተሰማት….ማንነቷን በሚያቁበት ቀን መልሰው ብስጭት እና ቁጭት ውስጥ እንደሚገቡ እርግጠኛ ነች..ቢሆንም ግን ምርጫ ያላትም…በዚህ ጉዳይ ላይ እሷቸው ትክክል ናቸው ብላ አታስብም…ሰው እርስ በርሱ መረዳዳትና አንዱ የሌላውን ኑሮ ማቃናት ያለና የነበረ ተግባር

ነው….እሷቸው ይሄንን ጉዳይ ከክብር አንፃር ማየታቸው የእሷቸውን ኑሮ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ የቤተሰቡ ኑሮ እየጎዳ ያለው፡፡
ስራውን ከጀመሩት በኃላ እንደፊቱ አልከበዳቸውም..እንደውም ይበልጥ ጉጉት አሳደረባቸውና ከወር በኃላ ለሚከበረው ከልጃቸው የ3ተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ ቀን በፊት ጥንቅቅ አድርገው መጨረስ አቅደው ቀን ከሌት መስራት ጀምረዋል፡፡አዎ ልጃቸው በህይወት ብትኖር ኖሮ እሰከዛሬ ይሄንን ቤት ሰርታ እንደምትጨርስ ያምኑ ነበር…አሁንም የሙት አመት መታሰቢያዋን ሲደግሱ የሙት መንፈሷ ሊያያቸው እንደሚመጣ እርግጠኛ ናቸው… ታዲያ ያንን ጊዜ ለእነሱ ቤት መስራት ህልሞ ስለነበረ ተሰርቶ ስታየው በጣም ደስ ብሏት እንደምትመለስ እርግጠኛ ናቸው…፡፡
እንደ ወትሮ መሽቶ ቤተሰቡ ሁሉ ተሰብስበው በሳቅና በጫወታ እራታቸውን በልተው ቡና ተፈልቶ ተጠጥቶ ከተጠናቀቀ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ ሁሉም ሰው ወደመኝታው ሄደ…ፊራኦልም የውስጡን በውስጡ ይዞ ልክ እንደወትሮ እንደተኛ ሰው ሆኖ አደፈጠ…..በጨለማ ውስጥ አፍጥጦ እስከሰባት ሰዓት ድረስ በሀሳብ ሲባትት ነበር…ልክ ሰባት ሰዓት ሲሆን ቀስ ብሎ ከተኛበት ሶፋ ላይ ተነሳና መብራቱን አበራ ..የቤቱን ዙሪያ ገባ ቃኘ….በፀሎትና ለሊሴ ተዘረጋግተው እንደተኙ ነው፡፡ከወላጆቹ ክፍልም ምንም የሚሰማ እንቅስቃሴ የለም…..ቀስ ብሎ ወደሴቶቹ መኝታ ተጠጋ… ሁለቱም አይናቸውን ጨፍነው ጥልቅ የሚባል እንቅልፍ ውስጥ ናቸው፡፡ይሄኔ ህልም እያለሙ እንደሚሆን ገመተ…ቀስ አለና በፀሎት በተኛችበት በኩል ዞሮ ከራስጌዋ ጎን ካለ መቀመጫ ላይ ተቀመጠ…ቁልቁል አዘቅቆ አያት…ቀስ ብሎ እጁን ዘረጋና ፊቷ ላይ የተጠቀለለውን ሻርፕ ጫፍ ይዞ ጎተተው…ቀስ በቀስ ከፊል ፊቷ እየታየው መጣ …ሻርፑን ሙሉ በሙሉ ከፊቷ አስወገደእና በትኩረት ይመለከታት ጀመር…..ድንገት ተገላበጠችን በጀርባዋ ተንጋለለች ..በዛን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ለእይታው ተጋለጠች….አሁን እርግጠኛ ሆነ…ምንም እንኳን የተወሰነ መጓሳቆል ቢታይባትም …ምንም እንኳን ቀኝ የፊቷ ክፈል ላይ ብዛት ያላቸው ጭረቶችና ጠባሳዎች ቢኖሩም እራሷ ነች…ለአመታት በድብቅ ከሩቅ ሲያያት የነበረችው..የእህቱን ውድ ልብ በውስጧ የተሸከመችው ልጅ….
‹‹እሺ አሁን ምንድነው የማደርው?››እራሱን ጠየቀ…ቀስ ብሎ ሻርፑን መልሶ ፊቷን ሸፈነና ከተቀመጠበት ተነስቶ መብራቱን አጠፋና ወደ መኝታው ተመለሰ….ሙሉ ለሊቱን እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም…..
አሁን ያወቀውን ነገር ባያውቅ ምኞቱ ነበር….አንዳንድ ማወቆች ሸክማቸው ያጎብጣል..አውቆ የሆነ ነገር ማድረግም አለማድረግም እዲህ አስቸጋሪ ሲሆን ምነው ምንም ነገር ባላወቅኩ ኖሮ ያስብላል፡፡ይህቺን ልጅ አፍቅሯት ነበር…የሞች እህቱን ልብ የተሸከመችው ልጅ መሆኗን ሳያውቅ በፊት ከእሷ ፍቅር ይዞት ነበር..ለእሷም ሆነ ለማንም ይሄንን ስሜቱን ተናግሮ አያውቅም….ግን እሱ በፍቅር እንደተነደፈ እርግጠኛ ነበር‹‹እሺ አሁን ምንድነው የማደርገው….?››እራሱን ጠየቀ…ብዙ ጊዜ ስለፍቅር ና ውበት ሲያወራ እርዕስ የምትቀይረውና ወሬውን የምትገፋው ለምን እንደሆነ አሁን ገባው…‹‹ይህቺ ልጅ ተአምረኛ ነች››ሲል አሰበ‹‹እራሷን በበሬዱ ቦታ ለመተካት እየጣረች ነው…አዎ ወደቤታችን የመጣችው ድንገት በአጋጣሚ ሳይሆን ሆነ ብላ አስባና አቅዳበት ነው… አንተ ወንድሜ ነህ ስትለኝ እንዲሁ ለአባባል ብቻ የምትጠቀምበት ይመስለኝ ነበር..ለካ እሷ ከአንጀቷ ነው፡፡››ሲል አሰበና በድቅድቅ ጨለማው ፈገግ አለ….‹‹ይሄን ጉድ ወላጆቹ ሲሰሙ ምን አይነት ምላሽ እንደሚሰጡ አሰበ…..ለመገመት አንኳን አልቻለም፡፡በተለይ አባቱ በበሬድ ጉዳይ ስሜተ ስስ እንደሆነ ያውቃል….ፈራ …በጣም ፈራ…. ‹‹ግን እሷስ እስለመቼ እንዲህ ከወላጆቾም ተሰውራ እውነቱን ከእኛም ደብቃ ትዘልቃዋለች..?እቅዷ ምንድነው?››ሊገባው አልቻለም፡፡

ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

07 Nov, 07:32


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራስድስት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
በፀሎት ግቢው ውስጥ ባለ የዛፍ ጥላ ስር ወንበር አውጥታ ቁጭ ብላለች…ፊራኦል ግንዱን ተደግፎ እሷን በትኩረት እያያት እያወሩ ነው፡፡ ወሬው ስለሟች እህቱ ስለበሬድ ነው፡፡በእሷ ሞት ምክንያት ምን ያህል እንደተጎዳና የእሱ ብቻ ሳይሆን የቤተሱም ኑሮ እንደተመሰቃቀለ እየነገራት ነው፡፡
‹‹ሀዘንንም ጨመሮ ሁሉም ነገር ጊዜያዊ መሆኑን አውቀህ ከክስተቶች ጋር እራስን አታጣብቅ…ከነገሮች ጋር እራስህን አስማምተህ ፍሰስ..እናም እራስህን ደስተኛ ለማድረግ ሞክር..ጊዜ የማይፈውሰው ህመም የለም››ብላ ልታፅናናው ሞከረች፡፡

‹‹ጊዜ ሁሉንም ህመሞች እኩል አይፈውስም….አንዳንድ ህመሞች በዕድሜያችን ልክ ተሰፍረው የተሰጡን ናቸው..አንዳንድ ስብራቷች የዘላለም ናቸው፡፡እህቴ ከሞተች ሁለት አመቷ አልፎ ሶስተኛውን ልናገባድድ ነው…ግን አሁንም ድረስ አባዬ እህህ እንዳለ ነው….እማዬን እደምታያት አይኗን እንዲህ የደከመው ከእድሜ የመጣ ህመም ወይም ጭስ አይደለም…የዘወትር ለቅሶ ነው….አየሽ አንዳንድ ስንጥቆች እንዲህ በቀላሉ ጊዜ ስላለፈ ብቻ አይደፈኑም…››
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን መሞከሩ አይከፋም…››
‹‹.በይ አሁን ወጣ ብዬ ልምጣ፡፡››
‹‹ሩቅ ካልሆነ ለምን እኔንም ይዘኸኝ አትወጣም?››
‹‹አይ ይሄንን ሻርፕሽን ከላይሽ ላይ ካልጣልሽ ከእኔ ጋር ከእዚህ ጊቢ መውጣት አትችይም..ጓደኞቼ እኮ ያቺ ሊንጃ ዘመድህ እያሉ ፉገራቸውን አልቻልኩትም››
‹‹እንዲሁ …ከአንቺ ጋር መታየቱ ይደብረኛል አትልም››
‹‹አይ… ያ እውነት እንዳልሆነ አንቺም ታውቂያለሽ…ለማንኛውም ቀላል ነገር ነው የጠየቅኩሽ…ሻርፕሽን ከላይሽ ላይ አንሺና አብረን እንሂድ››
‹‹አንተ ባለጣባሳዋ ዘመድህ ከሚሉህ ሊንጃዋ ቢሉህ አይሻልህም?፡፡››
‹‹አይ ግድ የለም..ባለ ጠባሳዋ ቢሉኝ ይሸለኛል…››
‹‹እንግዲያው ቀረብህ ሂድ በቃ››
‹‹አንቺም ቀረብሽ…ቸው››ብሏት ወጣ……ፊራኦል ሆነ ብሎ በአላማ ነው እንደዚህ የሚያደርጋት፡፡በፀሎትን መጠራጠር ከጀመረ ቀናቶች አልፈዋል…የምትለውን አይነት ልጅ እንዳልሆነች ውስጡ እየነገረው ነው….ምን አልባት የተጠራጠረው እውነት ከሆ ምን እንደሚያደረግ ግራ ገብቷታል….አጋልጦና አሳልፎ ይሰጣታል? ለአባቱ ይናገራል…?ለወላጆቾ አሳውቆ ለሽልት ያቀረብትን 5 ሚሊዬን ይቀበላል…?እንደዛ ካደረገ በእርግጠኝነት አባቱን ለዘላለም እንደሚያጣ እርግጠኛ ነው…ማጣት ምን እንደሆነ ደግሞ በእህቱ ሞት በደንብ ስለተማረ አባቱን ደግሞ ካጣ ከዛ በኃላ ሰው እንደማይሆን እርግጠኛ ነው…ብቻ የተወሳሰብ ነገር ውስጥ እንደገባ እርግጠኛ ነው….አንዳንዴ ነገሮችን በጥልቀት ከመቆፈር እራሱን ማገድ

ቢችል ይመኛል…ምንም ትሁን ማንም ችላ ብሎ ሊተዋት ይወስንና ውሳኔውን ለረጅም ጊዜ አፅንቶ ማቆየት አይችልም….‹‹ውይ በፀሎት….ምን አይነት ልጅ ነሽ?››እንደጀማሪ እብድ ብቻውን መንገድ ላይ እየለፈለፈ እየሄደ ነው፡፡
ከሄደ በሃላ ግን እሷ ከፍተኛ ትካዜ ውስጥ ነው የገባችው፡፡ይሄ ልጅ ሙሉ ፊቷን እንድታሳየው ወጥሮ ይዞታል…አውጥተው አይናገሩ እንጂ የቤቱ ሰው ሁሉ ቀንና ለሊታ ፊቷን ጠቅላላ አልብሶ በአንገቷ ዙሪያ ተጠፍሮ ታስሮ የሚውለውን ሻርፖን ከዛሬ ነገ ለምን አይነሳም? የሚሉ ጥያቄ በውስጣቸው እየተጉላላ እንዳለ እርግጠኛ ነች….ይሄንን ማድረግ አትችልም…ቀኑ ከመድረሱ በፊት እራሷን ማጋለጥና ማንናቷን ማሳወቅ ሁሉን ነገር ነው ትርምስምስ የሚያደርግባት፡፡ከመቀመጫዋ ተነሳችና ከሻንጣዋ ውስጥ ስልኳን በማውጣት ወደጓሮ ሄደች …ወደእሷ ሰው ከመጣ በግልጽ ለማየት የሚቻላትን ቦታ መርጣ ተቀመጠችና የጠፋውን ስልክ አበራችው…..ሰሎሞን ጋር ደወለች፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነህ?››
‹‹ሰላም ነኝ..አንቺ ደህና ነሽ….ከአሁን አሁን በደወለች እያልኩ በማስብበት ጊዜ ነው የደወለሽው››
‹‹ምነው አዲስ ነገር አለ?››
‹‹አዎ …ዛሬ አባትሽ ቤት አስጠርተውኝ ነበር››
‹‹አትለኝም!! ታዲያ እንዴት ሆነልህ?››
‹‹ሁሉ ነገር አንቺ እዳልሽው ነው የሆነው…ስለእኔ በድንብ ሲያጠኑ ነበር የከረሙት..የስልክ ልውውጣችንንም አግኝተው አዳምጠውታል…..በአጠቃላይ እውነቱን እንደተናገርኩ ተረድተዋል››
‹‹እና መጠጨረሻው ምን ሆነ?››በጉጉት ጠየቀች
‹‹ምን ይሆናል..?ያው አሁን ቁጭ ብዬ ዝርዝር እቅድ እያወጣሁ ነው….ሁለቱም ነገሮችን መስመር ለማስዝ ያልኳቸውን እንደሚያደርጉ ውሳኔያቸውን አሳውቀውኛል፡፡››
‹‹በጣም ደስ ይላል….በዚህ ፍጥነት ይስማማሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር››

‹‹እኔም ከአንቺ በላይ ፈርቼ ነበር…ግን አንቺን በጣም ስለሚወዱሽ ምንም ምርጫ የላቸውም…እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም ጋብቻቸውን ስለማዳንና ፍቅራቸውን ስለማደስ ደንታም የላቸውም…ግን ደግሞ በምንም ብለው በምንም አንቺን መልሰው እጃቸው ለማሰገባት ከልብ ይፈልጋሉ..ለዛ ነው በፍጥነት የተስማሙት፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…እሷን ለማግኘት እርስ በርስ ተገዳደሉ ብተላቸው በተሻለ ቀሏቸው አሁን ከፈጠኑት በላይ ፈጥነው ያደርጉት ነበር፡፡››
‹‹እንዴ ..አንቺ ደግሞ አጋነንሺው…እርስ በርስ ከተገዳደሉ እንዴት ብለው ነው አንቺን የሚያገኙሽ…ለማንኛውም ስራው ስለተጀመረ ስልክሽን ባትዘጊው ጥሩ ነው…ምክንያቱም ስለእነሱ አነሱን ጠይቄ ማወቅ የማልችለውን መረጃ አንቺ ነሽ ልትነግሪኝ የምትችይው…ለዛ ደግሞ የግድ በፈለኩሽ ግዜ ማግኘት አለብኝ፡፡››
‹‹በስልኬ ተከታትለው ከደረሱብኝስ?››
‹‹ስልኩን አዲስ ቁጥር ነው…ማንም አያውቀውም ያልሺኝ መስሎኝ?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ አዲስ ነው…አሁን ግን አንተ ታውቀዋለህ››
‹‹እኔ ለእነሱም ሆነ ለሌላ ለማንም ሰው አልሰጥም…ለአንቺ ስል ሳይሆን ለራሴ ስል….ሁለተኛ አሁን አንቺን መፈለጉን እርግፍ አድርገው ትተው ጋብቻቸውን ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ አጥብቄ ነግሬያቸዋለሁ እነሱም ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል››
‹‹እና መቼ ልትጀምሩ ነው?፡፡››
‹‹እንደነገርሺኝ በፍጥነት ወደቤትሽ መመለስ ትፈልጊያለሽ..ስለዚህ ምንም ጊዜ ማባከን አያስፈልግም…ነገ ስራ እንጀምራለን…ለሚቀጥሉት 15 ቀን ቢሾፍቱ ወዳለው ቤታችሁ እንሄዳለን ፡፡ከዛ በኃላ ደግሞ ውጤቱን እናይና ወደአንዱ ጋር እንሄዳለን፡፡;;
‹‹እንዴ ሁለቱም ለመሄድ ተስማሙ››
‹‹አዎ…በደንብ ተስማምተዋል..ነገ ሶስት ሰዓት አዲስአበባን ለቀን እንወጣለን››
‹‹ይገርማል….በዚህ ፍጥነት ከከተማው ይዘኸቸው ትወጣለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››

‹‹አየሽ ነገሩ ለአመታት የተከማቸና ስር የሰደደ ስለሆነ …..ሙሉ ትኩረት ይፈልጋል….አዲስአባባ ተቀምጦ ደግሞ በሙሉ ትኩረት እንዲህ አይነት ነገር ለመከወን ምቹ አይደለም….ለዛ ነው ከከተማው ላርቃቸው የፈለኩት››
‹‹በጣም እያስደስትከኝ ነው…››
‹‹ተይ እንጂ….ገና ምኑም ሳይያዝ ምስጋና ከጀመርሽ በኃላ ጥሩ አይመጣም››
‹‹አያያዝህን አየሁት …እንደምታሳከው በጣም ነው ምተማመንብህ››
‹‹አመሰግናለሁ›››
‹‹እሺ.. በቃ ቸው››
‹‹ቆይ…የስልኩን ነገር ምን አልሺኝ?››
‹‹እሺ…አልዘጋውም…ግን ቀጥታ አትደውልልኝ….ለማውራት ስትፈልግ መልእክት ላክልኝ..ከዛ ሁኔታዎችን አመቻችቼ በተቻለኝ ፍጥነት ደውልልሀለው››
‹‹ተስማምተናል..በይ ቸው››
‹‹ስልኩ ተዘጋ….በጣም ደስ አላት…ነገሮች ሁሉ ባሰበቻው መንገድ እንዲህ መስመር ስለያዙላት ወደላይ አንጋጣ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

06 Nov, 07:17


‹‹በጣም ጥሩ…በቃ ሁለታችሁም ጋብቻችሁን ለማዳንና በመሀከላችሁ ያለውን መቃቃር ለማስወገድ ከእኔ ጋር አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ ከሆናችሁ ሌላው ነገር እኮ ቀላል ነው…ቃል እገባላችኃላው እንወጣዋለን……በፀሎት በደስታ ወደቤቷ እንድትመለስ እናደርጋለን፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነህ…ግን የእኔ ሀሳብ ምን መሰለህ….አሁን ስትደውልልህ ወደ ቤቷ እድትመለስ አሳምናት ..በቃ እኛ ተስማማን አይደል…ከነገ ጀምሮ ከፈለክ ከአሁን ጀምሮ ማድረግ ያለብንን ነገሮች ንገረን እና ማድረግ እንጀምራለን..እሷ ግን ዛሬ ነገ ሳትል ወደቤቷ ትመለስ..እሷ እዚሁ እቤቷ እያለች እኛ ችግራችንን መፍታት እንችላለን››
‹‹ይቅርታ ይሄ መንገድ የሚሰራ አይመስለኝም››አለ ሰለሞን
‹‹ብሩን እኮ እንከፍልኃለን..ማለቴ አምስት ሚሊዬኑን እንከፍልሀለን..አይደል ኃይሌ..?››.ወ.ሮ ስንዱ ለዘመናት አድርገው በማያውቁት መንገድ ባልዬውን በአይናቸውም በቃላቸውም እየተለማመጡ ጠየቁ፡፡
‹‹አዎ..ትክክል ነች…ከፈለክ አሁኑኑ የ5 ሚሊዬኑን ቼክ ልፅፍልህ እችላለው…አዎ››
‹‹ይቅርታ እኔ ያልሰራሁበትን ገንዘብ የምቀበል አይነት ሰው አይደለሁም…በዛ ላይ 5 ሚሊዬኑን ከፍልሀለው አለች እንጂ እኔ ስራዬን እሷ ባለችው መንገድ እንኳን በውጤት ባጠናቅቅ…ይሄንን ብር እቀበላለሁ አላልኩም..እኔ ለሰራሁት ስረ የሚገባኝን ብር ብቻ ነው እንዲከፈለኝ ምፈለገው..እኔ እናንተን ብሆን ግን ሁሉን ነገር ልጃችሁ ባለችው መንገድ እንዲከናወን ጊዜ ሳላባክን እንቀሳቀስ ነበር….ቢያንስ እኮ እነዚህን እናንተ የምትሉትን ነገር ለልጃችሁ አቅርቤ የምትለውን ለመስማት የተወሰነ ቀናቶች ሞክረን እናንተ ግንኙነታችሁን ለማሻሻል የምታደርጉትን ጥረት አይተን ጥረቱ ፍሬ እያፈራ መሆንኑ መመዘን አለብን…እኔ ባለሞያ ነኝ..በፀሎት ደግሞ ዋና ቀጣሪዬ ነች..ታማኝነቴ ለእሷ ነው….እሷ ባለችው መንገድ ለመጓዝ ስትወስኑ ደውሉልኝ..አሁን ልሂድ..ብሎ ከመቀመጫው ሲነሳ ሁሉቱም በድንጋጤ ከተቀመጡበት ተስፈንጥረው ተነሱና ግራና ቀኝ ትከሸውን ይዘው መልሰው አስቀመጡት..
‹‹እሺ በቃ እንዳልክ ይሁን..አሁን ማድረግ ያለብንን ንገረን..ምንም ጊዜ ሳናባክን ወደተግባር መግባት አለብን፡፡ለመሆኑ ምን ያህል ጊዜ የሚፈጅ ይመስልሀል?፡፡››
‹‹ወር ..ሁለት ወር..ወይም ሶስት ወር..ወይም አመት››
‹‹አልገባኝም?››አቶ ኃይለልኡል ኮስተር ብለው ጠየቁ
‹‹ጊዜውን ምታረዝሙትም ምታሳጥሩትም እናንተው ናችሁ፡፡የጋብቻ አማካሪ ውጤታማ የሚሆነው ሁለቱ የጋብቻ ተጣማሪዎች በመሀከላቸው ያለውን ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ በሆኑበት መጠን ነው…እኔ እገዛ ነው የማደርግላችሁ..ትልቁን ስራ የምትሰሩት እናንተው

ናቸሁ…ምን ያህል ፍቃዳኛ ናችሁ ?ቁርጠኝነታችሁስ…?ችግሩን ለመፍታት ምን ያህል ርቀት ድረስ ትጓዛላችሁ?››
‹‹ነገርንህ እኮ …ልጄ እንድትመለስ እንኳን ከባሌ ጋር ሰላም ማውረድ ይቅርና ከዳቢሎስ ጋርም ተስማሚ ብባል አደርገዋለው…››
‹‹የእኔም አቋም ከእሷ የተለየ አይደለም››
‹‹እንደዛ ከሆነ እንጀምር…ከዚህ ከተማ ለቀንናት እንወጣለን…የፈለጋችሁበት ቦታ መምረጥ ትችላላችሁ ..ላንጋኖ ሰዳሬ ወይም ሌላ ቦታ ከተማና …ግርግር ያለበት ቦታ ግን አይሆንም››
‹‹እሺ..ሌላስ?››
‹‹ስልክ ሁለታችሁም በቀን ለአንድ ሰዓት ያህል ብቻ ነው የምትጠቀሙት…ከምትፈልጉትሰ ሰው ጋር የምትደዋወሉት በዛ በተፈቀደላችሁ ሰዓት ብቻ ነው….››
‹‹ይሁን እሺ…››
‹‹በቃ ከአሁን ጀምሮ ተዘጋጁ ..ነገ ሶስት ሰዓት አንንቀሳቀሳለን..ቀድሜ ደውልላችኃላው፡፡››
‹‹እሺ..ተስማምተናል፡፡››
‹‹በቃ ደህና ዋሉ…››መቀመጫውን ለቆ ተነሳ…ደስ እያለው እቤቱንም ሰፈሩንም ለቆ ሄደ…
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

06 Nov, 07:17


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራአምስት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
‹‹ለማንኛውም ተመልሼ መጣለሁ..ና ወደቢሮ እንመለስ …››ብለው ሰለሞንን አስከትለው ወደቢሯቸው ተመለሱ፡፡
‹‹በል አሁን ንገረኝ ልጄ እንዴት ናት?››
‹‹እኔ እንጃ እንዴት እንደሆነች አለውቅም?››

‹‹ማለት ደብዳቤውን ስትሰጥህ አይተሀት የለ..?ከስታለች…እንዴት ነች ተጎሳቁላለች?ልቧስ እንዴት ነው…?ታውቃለህ አይደል የልብ በሽተኛ ነች››
‹‹ደብዳቤውን በአካል መጥታ አይደለም የሰጠችኝ..ማለቴ ቢሮዬ በሚገኝበት ህንፃ መታጠቢያ ቤት አስቀምጣ ስልክ ደወለችና እንድወስድ አዘዘችኝ..ስልኬን ከየት እንዳገኘች አላውቅም…ሁሉን ነገር የተነጋገርነው በስልክ ነው…በወላጆቼ ትዳር መካከል አለመግባባት አለና እርዳቸው ብላ መቶ ሺ ብር በደብተሬ አስገብታለች….መልሼ ስልኳን ብደውልላት አይሰራም…እራሴ ስፈልግህ መልሼ አገኝሀለው ነው ያለችኝ..እኔ የማውቀው ይሄኑን ነው፡፡››
ኪሱ ገባና ቢዝነስ ካርዱን አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠ‹‹ይሄው አድረሻዬ …ቢሮዬ ሜኪሲኮ ኬኬር ህንፃ ላይ ነው….ዝግጁ ስትሆኑ ደውሉልኝ….ካልሆነም ይንገሩኝ ገንዘቡን ተመላሽ አደርጋለው፡፡አሁን ልሂድ፡፡››
‹‹እሺ በቃ…አመሰግናለው..አሁን ተረጋግቼ ማሰብ አለብኝ..ደውልልሀለው፣ልጆቹ ይሸኙሀል››አሉት፡፡
እሱም ሌላ ምንም ተጨማሪ ቃላት ሳይናገር ቦርሳውን ያዘና ሹልክ ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
በሁለተኛው ቀን የሚጠብቀው ቁጥር ተደወለ…የልብ ምቱ ፍጥነት እንደጨመረ እየታወቀው ነው…እንደምንም ለመረጋጋት ሞከረና አነሳው፡፡
‹‹አቤት …..››
‹‹ሃይለ ልኡል ነኝ….››
‹‹አወቅኮት፣ ሰላም ኖት ?››
‹‹ደህና ነኝ….እቤት ብቅ ብትል ይመችሀል?››ሰከን ባለና በተረጋጋ የድምፅ ቅላፄ ጠየቁት፡፡
‹‹መቼ…አሁን››
‹‹አዎ አሁን ብትመጣና ..በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ብናወራ ደስ ይለኛል››
‹‹እሺ….ከአንድ ሰዓት በኃላ እደርሳለሁ..››
‹‹አመሰግናለሁ….ከባለቤቴ ጋ ሆነን እንጠብቅሀለን››

‹‹ጥሩ በቃ መጣሁ….››ስልኩን ዘጋና ቀጥታ ቦርሳውን ይዞ ከመቀመጫው ተነሳ….ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ሲገባ ለሊሴ ፊትለፊቷ ያለውን ኮምፒተር ከፍታ አፍጥጣ ነበር….
‹‹ልወጣ ነው…ዘሬ ተመልሼ የምመጣ አይመስለኝም››
‹‹እሺ በቃ..ባለጉዳይ ከመጣ…ለነገ ቀጠሮ ይዤላቸዋለው››አለችው፡፡
‹‹ጥሩ እንደዛ አድርጊ….መልካም ውሎ››ብሏት ቢሮውን ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጣ፡፡
መኪናውን እራሱ እያሽከረከረ….አእምሮውም በሀሳብ እየተሸከረከረ ቀጥታ ወደአቶ ኃይል ልኡል ቤት ነዳው…ምን እንደሚጠብቀው አያውቅም..እርግጥ ና ብለው ሲጠሩት በጣም በተረጋጋ እና በተለሳለሰ ድምፅ ነው…ግን ያንን ያደረጉት ሁሉ ነገር ሰላም ነው ብሎ በማመን በገዛ እጁ ሄዶ እጅ እንዲሰጣቸው አስበው ከሆነስ? ይሄ የእቅዳቸው አንዱ አካል ቢሆንስ?››እራሱን ደጋግሞ ጠየቀ…በሀሳብ ከመብሰልሰል ለደቂቃ እንኳን ሳያነጥብ ሰፈራቸው ደረሰ …መኪናውን ከሩቅ አቆመና ደወለ፣ስልኩ ተነሳ››
‹‹ኪያ እንዴት ነሽ?››
‹‹ሰልም ነኝ….አንተስ?››
‹‹አለው…እዛ የነገርኩሽ ቦታ ጠርተውኝ እየሄድኩ ነው››
‹‹የት?››
‹‹አንቺ ደግሞ …የጠፋችው ልጅ ወላጆች ጋር ነዋ››
‹‹ና ብለው ጠሩህ?››
‹‹አባትዬው አሁን ጠርተውኝ በራፋቸው ጋር ደርሼ ወደውስጥ ዘልቄ ከመግባቴ በፊት መኪናዬን አቁሜ ነው የምደውልልሽ››
‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››
‹‹አይ ለምን ፈራለሁ….ማለቴ ከገባሁ በኃላ በፀጥታ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ስልኬን ስለማጠፋ ድንገት ደውለሽ ስልኬ ካልሰራልሽ እንዳታስቢ ብዬ ነው››
‹‹አይ ጥሩ አደረክ…ለማንኛውም እንደወጣህ ደውልልኝ››

‹‹እሺ….ኪያ …ቸው››ስልኩን ዘጋ፡፡ቀለል አለው፡፡‹‹ቢያንስ አሁን እዛው በገባሁበት ከቀረሁ በቀላሉ አድርሻዬን ታገኘዋለች፡፡››ብሎ አሰበና መኪናውን አንቀሳቀሰ….የውጭ በራፍ ጋር ደረሰና ክላክሱን አንጣረረ….ወዲያው በራፉ ተከፈተና…ጠብደል ጥቁር ሱፍ የለበሰ ጠባቂ ወደእሱ መጣና …ማንነቱን ጠየቀው‹‹አዎ አንተን እየጠበቁሀ ነው››ብሎት መልሶ ሄደና በራሀፍን ከፈተለት ….ወደውስጥ ዘልቆ ገባና ከአራት መኪና በላይ ወደቆመበት ገራዥ በመሄድ ክፍት ቦታ ፈልጎ መኪናውን አቆመና ሞተሩን አጥፍቶ ወረደ…..ጠባቂው እየመራ ሳሎን በራፍ ድረስ ወሰደውና ወደኃላ ተመለሰ…
እራሳቸው አቶ ኃይለልኡል ነበሩ በራፍ ድረስ መጥተው በወዳጅነት አቀባበል አቅፈው የተቀበሉት….ወደሳሎን ይዘውት ዘለቁ…መጀመሪያ ምግብ እንብላ…‹‹እስከአሁን ቁርስ ሳንበላ እየጠበቅንህ ነው››አሉት፡፡
‹‹ዝም ብላችሁ ተቸገራችሁ….እኔ እኮ በልቼ ነበር የመጣሁት››
‹‹ቢሆንም…ና ቁጭ በል….››ቀድመው ተቀመጡና የሚቀመጥበትን ቦታ አሳዩት…ተቀመጠ
‹‹ልጇች..ስንዱን ጥሯት››
ሰራተኞቹ ግራ የገባቸው ይመስል ዝም ብለው ሰውዬው ላይ አፈጠጡ፡፡
‹‹ምን አፍጥጣችሁ ታዩኛላችሁ…ክፍሏ ነች…አንዳችሁ ሂዱና እንግዳው መጥቷል ነይ በሏት…የተቀራችሁ ቁርሱን አቅርቡ››
ሁሉም ትዛዙን ሰምተው ተበታተኑ
‹‹እንዴት ነው …ወ.ሮ ስንዱ ተሸላቸው?፡፡››ሰለሞን ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ…እድሜ ላንተ የልጃችንን ሰላም መሆን ዜና ካሰማሀን በኃላ ተሸሏታል…የተሳሰረ የነበረ እግሯቾም ታምራዊ በሆነ ፍጥነት ተላቀውላት አሁን በራሷ መራመድ ችላለች፡፡››
‹‹በእውነት በጣም እስደሳች ዜና ነው…ያልኳችሁን ስላመናችሁኝ ደስ ብሎኛል››
‹‹አይ እሱ እንኳን በቀላሉ አላመንህም…ስላአንተ ለሁለት ቀን ሳስጠና ነበር…በዛ ላይ ከእሷ ጋር የተደዋወላችሁትን የስልክ ልውውጥ አግኝቼ አዳምጬዋለው…የልጄን ድምፅ ሰምቼያለው…በሰላምና በጤና መኖሯን ያረጋገጥኩት ከዛ በኃላ ነው…በቀላሉ ላምንህ

ሳላልቻልኩ ይቅርታ….ደግነቱ እንዲህ በቀላሉ እንደማላምንህ ልጄ አስቀድማ ነግራሀለች…ይገርማል ይሄን ያህል ጠልቃ ምታውቀኝ አይመስለኝም ነበር››
‹‹ልጆት አይደለች…ልጆች እኮ ወላጆች የሚያደርጉትን እያንደንዱን ድርጊት በጥልቀት ያስተውላሉ ፣በአእምሮቸውም ይመዘግባሉ…ስለወላጆቻቸው በጥልቀት ነው የሚያውቁት››
‹‹ትክክል ነህ ..››ንግግራቸውን በወ.ሮ ስንዱ መምጣት ምክንያት አቆረጡ….ሰሎሞን ከመቀመጫው ተነስቶ በትህትና ሰላምታ ተቀበላቸው….ወንበር ስበው ተቀመጡ..ቁርስ ቀረበ….ጠረጴዛው ሙሉ ቢሆንም ያን ያህል አፒታይት የነበረው ሰው አልነበረም….ቁርሱ እንደተጠናቀቀ ከወንበራቸውን ተነስተው አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የአቶ ኃይለልኡል ቢሮ ተያይዘው ሄዱ.. ወደሶፋው ሄዱና ተቀመጡ..፡፡
‹‹እንግዲህ አሁን መነጋገር እንችላለን››አቶ ኃይለልኡል ጀመሩ
ወ.ሮ ስንዱ ተቀበሏቸው‹‹ልጄ እንደው አባክ እርዳን ..ልጃችን ወደቤቷ እንድትመለስ አሳምናት››ከመቀመጫቸው ተነስተው እግሩ ላይ ሊደፉ ሲሉ በአየር ላይ ትከሻቸውን ያዘና መልሶ አስቀመጣቸው፡፡
‹‹አይገባም..እኔ እዚህ ያለሁት እኮ ልረዳችሁ ነው..የእኔም ምኞትና ፍላጎት ያ ነው››
‹‹እኮ አድርገዋ….ያለችበትን እንድትነግርህ አሳምናት›››
‹‹አይ በእንደዛ አይነት ሁኔታ እንኳን ምትስማማ አይመስለኝም..እሷ ወደቤቷ ምትመለስበትን አንድና ብቸኛ መንገድ በግልጽ ተናግራለች…ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ደስተኛ ሆና ወደቤቷ እንድትመለሰ ያለችውን አድርጎ ማሳየት ብቻ ነው ያለብን፡፡››
‹‹ይሄውልህ ልጄ…ልጃችን ያለችውን ለማድረግ እኔም ባለቤቴም ተስማምተናል…..ለዛ ቃል እንገባለን..አንተ ትረዳናለህ እኛም በመሀከላችን ያለውን ችግር እንፈታዋለን..››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

05 Nov, 06:39


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራአራት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ሰላሞን የሆነ ሰው እየተጫወተበት እንደሆነ ነው የተረዳው‹‹ግን ማን ነው እንዲህ ያለ ጫወታ ከእኔ ጋር ለመጫወት የሚደፍረው?››በዙሪያው ያሉ ሰዎችን እያሰበ እራሱን እስኪያመው ቢያስጨንቅ በዙሪያው ካሉ ሰዎች እንዲህ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀልድ ከእሱ ጋር ለመቃለድ የሚሞከር ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡
ነገሩ ቀልድ እንዳልሆነ የተረዳው ልክ በተነገረው መሰረት ከሶስት ቀን በኃላ ተመሳሳይ ስልክ ሲደወልለት ነው፡፡በጉጉት አነሳው፡፡‹‹ሄሎ..አወቅከኝ?››
‹‹መሰለኝ… አደናጋሪዋ ልጅ ነሽ አይደል?››
‹‹መሰለኝ….የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ?››
‹‹ምን ለማድረግ?››
‹‹በተነጋገርነው መሰረት ስራ ማስጀመሪያ መቶ ሺ ብሩን እንድልክልህ ነዋ››
‹‹እንዴ? ስራው ምን እንደሆነ ሳላውቅ…ልስራው አልስራው መወሰን የምችለው እኮ ስራውን ሳውቅ ነው…መጀመሪያ በአካል ተገናኝነተን ስለስራው ማውራት አለብን››
‹‹ለጊዜው በአካል ላገኝህ አልችልም…ስራው በአባትና እናቴ መካከል ያለውን ችግር መቅረፍ ነው…እናትና አባቴ ያለፉትን 28 አመታት በጋብቻ አሳልፈዋል….እኔ ሀያ አንድ አመቴን ጨርሼ 22 ዓመት ውስጥ ነኝ…በእድሜዬ አንድም ቀን ሰላም ሆነው አይቻቸው አላውቅም…መኝታ ለይተው በየራሳቸው መኝታ ቤት ነው የሚያድሩት….ሁል ጊዜ

እንደተጣሉና እንደተጨቃጨቁ ነው.ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድም እስከመፈለግ የሚያደርስ ጥላቻ በመካከላቸው አለ..ወይ አይፋቱ ወይ እንደሰው የእውነት አብረው አይኖሩ፣….እና የፈለኩህ ይሄንን የሻገተና የበሰበሰ ጋብቻ የበሰበሰውን ቅጠል ከላዩ አራግፈህ የደረቀውን የጋብቻ ግንድ ቆርጠህ ከስር አዲስ የፍቅር ቅርንጫፍ እንዲያቆጠቁጥ እንድታደርግ ነው…ቢያንስ እንደባለትዳር መልሰው መተቃቀፍ ባይችሉ እራሱ እንደጓደኛሞች እንዲጨባበጡ ማድረግ እንድትችል ነው፡፡ይሄ ጉዳይ የእኔ የህይወቴ ትልቁ አላማ ነው…እባክህ ይሄንን ጉዳይ እንደጉዳይህ ልትይዘው ትችላለህ….?›››
‹‹በእውነቱ ከጠበቅኩት በተቃራኒ የሆነ መሳጭ ነገር እየነገርሺን ስለሆነ ቀልቤን ገዝተሸዋል…የምትይውን በደንብ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡፡ለመሆኑ እኔን የምታናግሪው አባትሽ ወክለሽ ነው ወይስ እናትሽን…..?ማለት እኔን ለስራው እንድታናግሪኝ የጠየቀሽ ማን ነው?፡፡››
‹‹በእውነቱ ሁለቱም ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር የለም….››
‹‹ይሄ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደርገዋል..እሺ ቆይ ለመሆኑ እኔን ለምን…?እንዴት እኔን መረጥሽ?››
‹‹ለጊዜው ማንነቱን ልነግርህ የማልችለው አንድ አንተን የሚያውቅ ሰው ነው ሰለአንተ በሆነ ጉዳይ አንስተን ስንጨዋወት በጋብቻ ጉዳይ ላይ እንደምትሰራና በጉብዝናህም እንደሚተማመንብህ የነገረኝ..እንዳአጋጣ ሚ ሆኖ ደግሞ ያንን ሰው እኔ አምነዋለው…እሱ ጎበዝ ነህ ካለህ ጎበዝ ነህ ማለት ነው…ተመለሰልህ?፡››
‹‹በከፊል አዎ…ግን እንደነገርሺኝ በወላጆችሽ መካከል ያለው ችግር ለረጅም አመት የተከማቸ የተወሳሰበና ዘርፈ ብዙም ነው፡፡››
‹‹በትክክል ገልፀኸዋል››
‹‹ችግሩ ምን መሰለሽ..በቀደም እንደነገርኩሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በጋብቻ መካከል የተፈጠረ ችግርን ለመፍታት የሚችለው ሁለቱም ተጋቢዎች በመሀከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ያንን ለማስተካከል ከአማካሪው ጋር ለመተባበር ሙሉ ፍቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው…አሁን ያንቺን ጉዳይ ስንመለከት ወላጆችሽ ጉዳዩን እንኳን አያውቁትም..ቢያውቁትም ፈፅሞ ከእኔ ጋር ለመስራት ላይቀበሉት ይችላሉ.››.

‹‹እሱን ለእኔ ተወውና አሁን የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ… ገንዘቡን ትራንስፈር ላድርግልህ››
‹‹ይሄውልሽ ፣እኔ በነገርሺን ታሪክ በጣም ተስቤያለሁ…አንድ ወጣት ሴት በወላጆቾ ግንኙነት ተረብሻ እንዲህ ነገሮችን ለማስተካከል ስትጥር እኔም የበኩሌን እገዛ ለማድረግ ፍጽም ፍቃደኛ ነኝ..እዚህ ላይ ዋናው ገንዘብ አይደለም.. እሱ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው…አሁን መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ወላጆችሽን ከቻልሽ አንድ ላይ አስቀምጠሸ ካልሆነም ለየብቻ ያሰብሽውን ንገሪያቸውና ለማሳመን ሞክሪ..እነሱ ፍቃደኛ ከሆኑ በኃላ ደውይልኝ..ከዛ ፕሮግራም እናወጣና ያለውን ችግር እያየን ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡››
‹‹እነሱን በቀጥታ ማናገር አልችልም››
‹‹ለምን?››
‹‹ስሜ በፀሎት ኃይለልኡል ይባላል››
‹‹እሺ በፀሎት…ለምንድነው ወላጆችሽን ማናገር የማትችይው..?እነሱን ማናገር የማትቺይ ከሆነ እንዴት አድርጌ ነው ወላጆችሽን መርዳት የምችለው?››
‹‹ማለት ስሜን የነገርኩህ ስለእኔ የተወሰነ መረጃ እንዲኖርህ ነው..በፀሎት ኃይለልኡል በልና ድህረገፆች ላይ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈልግ ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መልሼ ደውልልሀለው፡፡››አለችና ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችበት፡፡
ስልኩ ቢዘጋም እሱ ግን ስልኩ ላይ እንዳፈጠጠ ነው…የገባው የመሰለው የልጅቷ ሁኔታ መልሶ እየተበታተነበት ነው‹‹…ድህረ-ገፅ ላይ ስለእሷ ምን…?ታዋቂ ሰው ነች ማለት ነው…?››
ጎግል ከፍቶ ››በፀሎት ኃይለመለኮት››ብሎ ሰርች መድረግ ጀመረ..በርካታ መረጃዎች ተዘረገፉ….እውነትም ይህቺ ልጅ ታዋቂ ነች መሰለኝ..ብሎ የመጀመሪያውን ሲያነብ
‹‹የታዋቂ ቢሊዬነሩ የኃይለመለኮት ብቸኛ ወራሽ በውድቅት ለሊት ከቤት ወጥታ ከጠፋች 14 ቀን አልፏታል፡፡››
‹‹ታዋቂው ቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ በፀሎት ለምን ከቤቷ ጠፋች?››
‹‹በጸሎት ኃይለመለኮትን ያለችበትን የጠቆመ የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት እንደሚሸልሙ አባቷ ለፋና ቴልቨዥን በሰጡት መግለጫ አሳወቁ››
በሚያነበው ዜና ሁሉ ደነዘዘ…..ማንበቡን አቆመና..ደወለላት
‹‹ሄሎ ..››
‹‹አሁን በመጠኑ ገባህ?››
‹‹ማለት አሁንም እንደጠፋሽ አይደለሽም አይደል…..?ማለቴ ወደቤት ተመልሰሻል?››
‹‹አይ አልተመለስኩም…ወደቤት እንድመለስም እንደወጣው በዛው እንድቀርም የምታደርገኝ አንተ ነህ፡፡››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ከእቤት የጠፋሁት የወላጆቼ ጭቅጭቅና የእርስ በርስ ጥላቻ ምርር ብሎኝ ነው….እኔ የእነሱን ሀብታቸውንም ሆነ ውርሳቸውን አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅራቸውን ነው..ቢያንስ የሁለት ጓደኛሞችን አይነት እርስ በርስ የመግባባት እና የመረዳዳት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ወደዛ ቤት አልመለስም…እና እቅዴ ምን መሰለህ..ለእነሱ ደብዳቤ ፅፌ ልክልሀለው….በዛ ደብዳቤ ላይ ግልፅ የሆነ ፍላጎቴን አሰፍራለሁ…ማለቴ በግልፅ ከአንተ ጋር ሰርተው በማሀከላቸው ያለውን ግንኙነት ካስተካከሉ…እናም ያንን አንተ ካረጋገጥክልኝ ወደቤት እመለሳለው..ካለበለዚያ በቃ እኔም እነሱን እረሳለው አነሱም እኔን ይረሱኛል ማለት ነው፡፡››
‹‹በተሰቀለው..ነገሩ ካሰብኩት በላይ የተወሳሰበና ..አደገኛም ጭምር ነው፡፡››
‹‹ለዚህ እኮ ነው አምስት ሚሊዬን ብር እንድታገኝ የማደርግህ..ግብቷሀል አይደል አባቴ እኔን ላገኘ ወይም ያለሁበትን ለጠቆመ ሰው የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል ..ያ ማለት ነገሮች እንደተሳኩ እርግጠኛ በሆንኩ ጊዜ አንተ እንድታገኘኝና ለቤተሰቦቼ እንድታስረክበኝ አደርጋለሁ…እናም ለሽልማት የተዘጋጀውን ብር ከአባቴ ተቀብዬ ለአንተ አስረክብሀለው፡፡››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

05 Nov, 06:39


‹‹ገባኝ..አሁን እኔን ያሳሰበኝ የብር ጉዳይ አይደለም..አስበሽዋል ግን በጠቅላላ በሀገሪቱ ጉራንጉር እየተፈለግሽ ነው…በጥቂቱ እንደተረዳሁት አባትሽ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪና የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው ነው…እንዳልሽው ለእነሱ የፃፍሺውን ደብዳቤ ይዤ እቤት

ድረስ ስሄድ አሜን ብሎ የሚቀበልለኝ ይመስልሻል?ያለሽበትን ቦታ በትክክል የማውቅ ነው የሚመስለው…ሊያሳስረኝም ሆነ ሌላ ነገር ሊያደርገኝ ይችላል….ያንን አስበሽዋል?፡፡››
‹‹አይ አባቴን አውቀዋለው..እንደዛ አያደርግም…መጀመሪያ እርግጠኛ ለመሆን ያሰልልሀል..ስትገባ ስትወጣ ከማን ጋር እንደምትገናኝ ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ያጣራል
፣ስልክህን ያስጠልፋል…ይሄንን የተነጋገርነውን ሁሉ ከቴሌ አስወጥቶ ያዳምጣል…ከዛ እኔ ልጅ በዚህ ነገር እንዴት እንደቆረጥኩ እርግጠኛ ይሆንና ከአንተ ጋር ይተባበራል..ወይም እኔን ልጁን እስከወደያኛው ይሰናበታኛል፡፡››
‹‹ገባኝ…በእውነቱ ሁኔታዎች በጣም ቢያስፈሩኝም …ግን እምቢ ልልሽ አልችልም….ተስማምቼለው፡፡››
‹‹ጥሩ በቃ ያልኩህን አድርግ..የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ…ደብዳቤውን ነገ እንዲደርስህ አደርጋለው…ከዛ ሁኔታዎችን አመቻችና እናትንና አባቴን አግኛቸው……….ከዛ በኃላ ያሉትን ነገሮች እንነጋገራለን፡፡››
‹ጥሩ እንዳልሽ…ስፈልግሽ በዚህ ቁጥር ነው የማገኝሽ?››
‹‹አይ አንተ ልታገኘን አትችልም..እኔ ነኝ የማገኝህ…ቸው››ስልኩ ተዘጋ፡፡
አሁንም እንደደነዘዘ ነው፡፡የባንክ ሂሳብ ቁጥሩን ላከላት…ከአንድ ሰዓት በኃላ እንዳለችው 100 ሺ ብር እንደተላከለት በስልክ ቁጥሩ ሚሴጅ መጣለት…አሁን የበለጠ ብርድ ብርድ አለው…
‹‹ሠሎሞን ምን አይነት ነገር ውስጥ እራስህን እያስገባህ ነው?፡፡››ጠየቀ…መልሶ ድህረ ገፅ ላይ ገባና የበፀሎትን የተለያ ፎቶዎችን ዳውንሎድ አደረገ ፣እንዲህ አይነት የተሰወሳሰበ ነገሮችን አስባ ለመከወን የምትንቀሳቀስ ሳይሆን ቢነግሯት እንኳን የማዳመጥ ትግስት ያላት አትመስልም፡፡እያንዳንዱን ፎቶ በየተራ እየገለጠ ተመለከት...ወርቃማ ፀጎሯን..ጥቋቁር አይኖቾን ..አፍንጫዋንና የሚያጎጉ ብስል እንጆሪ መሳይ ከንፈሮቹን አንድ በአንድ ነጥሎ ለየብቻ አጠናቸው…ይሄንን ጉዳይ ብቻውን አመንዥጎ ሊወጣው ስለማይችል አስቴር ጋር ደወለ….ቤት ነኝ ስትለው….ጃኬቱን ከተሰቀለበት አንስቶ በእጁ እንዳንጠለጠለ ሄደ፡፡

///
በማግስቱ
በፍራቻ እንደተሸበብ የሆንኩትን ልሁን በሚል ስሜት የውስጥ ፍራቻውን እና ስጋቱን በላይ ገፅታው መኮሳተር ሸፍኖት የአቶ ኃየለ መለኮትን ቤተመንግስት መሰል ግዙፍ ህንፃ መጥሪያ ተጫነ….ብዙም ሳይቆይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጋርድ የሚመስል ሙሉ ጥቁር ሱፍ የለበሰ ጠብደል ወጣት በራፍን ከፈተና‹‹አቤት ጌታዬ ምንድነበር?››አለው፡፡
ከስር እስከ ላይ አየውና ሁኔታውን ገመገመ..ይሄን የመሰለ ዘናጭ መለሎ የዚህ ቤት ዘበኛ እንዳይሆን ብቻ ሲል አሰላሰለ…ከላይ ወደታች አፍጥጦ እያየው እንደሆነ ሲገባው ወደቀልቡ ተመለሰና ‹‹አቶ ኃይለመለኮትን ወይም ባለቤታቸውን ፈልጌ ነበር››
‹‹ቀጠሮ አላህ?››
‹‹አይ የለኝም››
‹‹ይቅርታ ጌታዬ …እንደዛ ከሆነ ልታገኛቸው አትችልም…አሁን ባሉበት ሁኔታ ምንም አይነት እንግዳ አያስተናግዱም››
‹‹ይገባኛል..የእኔ ጉዳይ ግን የተለየ ነው፡››
‹‹ጌታዬ የተግባባን አይመስለኝም….መልዕክት ካለህ ስጠኝና ላድርስልህ..አስፈላጊ ከሆነ እራሳቸው ደውለው ያገኙሀል..ከዛ ውጭ አዝናለሁ ልረዳህ አልችልም››ብሎ ከእሱ መልስ ሳይጠብቅ የከፈተውን በራፍ መልሶ ሊጠረቅምበት ሲል እጁን በፍጥነት ዘረጋና አስቆመው…
ዘበኛው‹‹ይበልጥ በንዴት አፈጠጠበት››
‹‹አልተረዳሀኝም..ጉዳዬ ከበፀሎት ጋር የተገናኘ ነው..ምን መሰለህ..››
ንግግሩን ሳይጨርስ እጁን ጨመደደና ወደውስጥ ጎትቶ በማስገባት በራፉን ቀረቀረው፡፡
‹‹በጸሎት ምን..?ያለችበትን ታውቃለህ..?የት ነች..?››
‹‹ቀጥታ አባቷን ወይ እናቷን ነው ማናገር የምፈልገው››

‹‹እሺ ና ግባ›› እየተሸቆጠቆጠ ፊት ለፊት እየመራ ወደግዙፉ ሳሎን ይዞት ገባ…እቤቱ ግዝፈትና ሰው አልባ ስለሆነ ያስፈራል…‹‹እባክህ እዚህ ሶፋ ላይ አረፍ በል …ጋሼን አናግሬያቸው መጣሁ…፡፡››ብሎ መልስ ሳይጠብቅ የፎቁን መወጣጫ የሩጫ ያህል እየተራመደ ወደላይ ወጣ….እዛው በቆመበት የቤቱን ዙሪያ ገባ እየጎበኘ በመደነቅ ላይ ሳለ ነበር ልጁ ተመልሶ የመጣው
‹‹ተከተለኝ ጋሼ ቢሯቸው ናቸው..አስገባው ብለዋል..እየጠበቁህ ነው››
በፍጥነት ደራጃውን ወጣና ደረሰበት፡፡ የመጀመሪያውን ፎቅ እንደወጡ ወደግራ ታጠፈና በኮሪደሩ የተወሰነ ከተራመዱ በኃላ በግራ በኩላ ካለው ገርበብ ያለ ክፍል እንዲገባ በእጁ ጠቆመውና እሱ ወደኃላ ዞሩ የመልስ ጉዞ ማድረግ ጀመረ..ሰለሞን ወደ ክፍሉ ተጠጋና በእጁ ቆረቆረ…አሁንም ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ እንደሆነ ይሰማዋል..ወዲያው በራፉ ተከፈተና አንድ ባለግርማ ሞገሳም ግዙፍ አዛውንት ፊት ለፊቱ ቆመው እጃቸውን ለሰላምታ ሲዘረጉለት አገኘ…በደመነፍስ እጁን ዘረጋና ጨበጣቸው …
‹‹ግባ ›› አሉን እጁን እንደያዙ ወደውስጥ ይዘውት ዘለቁ…ከጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ካለው ሶፋ ቅድመው ተቀመጡና ፊትለፊታቸው እንዲቀመጥ በእጃቸው ጠቆሙት...
ቦርሳውን ከትከሻው ላይ አወርዶ ፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና… ተቀመጠ፡፡
‹‹እሺ፣ስለ በፀሎት የምታውቀው ነገር እንዳለ ነበር የተነገረኝ ..?››
‹‹ትክክል››
በመርማሪ አይናቸው ከስር እስከላይ እየገመገሙት‹‹ለመሆኑ ልጄን የት ነው ምታውቃት?››ሲሉ ጠየቁት
‹‹አላውቃትም››
‹‹አልገባኝም..እሺ ያለችበትን ታውቃለህ?››
‹‹አይ አላውቅም፡፡››
‹‹ሰውዬ እኔ አሁን ቀልድ ላይ ያለው ይመስልሀል?››እንደቆሰለ ነብር ተቆጡ፡፡

‹‹ይረጋጉ፣እሷን ለማግኘት የሚጠቅሞትን ነገር ነው ይዤሎት የመጣሁት››አለና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቦርሳውን ወደራሱ ስቦ በመክፈት ከውስጡ ሁለት የታሸገ ፖስታ አወጣና አቀበላቸው..አገላብጠው አዩት ፣ለአባዬ እና ለእማዬ ይላል..የልጃቸው የእጅ ፅሁፍ ነው፡፡ከመቀመጫቸው በደስታ ብድግ አሉ ፣ ወዲያው ፖስታውን ሸርክተው ቀደዱትና ውስጡ ያለውን ደብዳቤ አውጥታው እዛ ክፍል ውስጥ ከውዲህ አዲያ እየተሸከረከሩ አነበቡት
‹‹ወይኔ ፈጣሪ…ልጄ በህይወት አለች….ልጄ በህይወት አለች..ወደሰሎሞን ተንደረሩን ከተቀመጠበት ጎትተው አቆመትና እያገላበጡ ጉንጩን ሳሙት፤ ጨምቀው አቀፉትና ከግራ ወደቀኝ ወዘወዙት፣‹‹ቆይ አንዴት ናት? ››እጁን ያዙትና የጎተቱ ከክፍሉ ወጡ… ግራ ገባው፡፡ ብዙ ክፍሎችን አልፈው የሆነ ክፍል ከፈቱን ይዘውት ገቡ…ግዙፍ መኝታ ቤት ነው..ፊት ለፊት ያለው ግዙፍ አልጋ ላይ ተዘርረው የተኙ ግዙፍ ሴትዬ አሉ፡፡
‹‹ስንዱ ልጃችን በህይወት አለች..ልጃችን ደብደቤ ላከችልን…እይ .. ተመልከቺ፡፡‹‹በእጃቸውን ያንከረፈፉትን ደብዳቤ አቀበሏቸው….ሴትዬዋ የበፀሎት እናት እንደሆነች ገባው…ይሄን ቤተሰብ ከገባበት እንዲህ አይነት የተረማመሰ ህይወት እንዴት አድርጎ ሊታደግ እንደሚችል ሲያስብ ገና ካሁኑ ደከመው…ሴትዬዋ በተዳከመ አይናቸው በተጋደሙበት የልጃቸውን ደብዳቤ በእንባ ታጅበው አንብበው ጨረሱ፡፡
‹‹ወይኔ …አየህ ልጃችንን ለዚህ ያበቃናት እኛው ነን..እኔና አንተ ነን ጥፋተኞቹ…እኔና አንተ ለአንድ ልጃችን እንኳን መሆን የማንችል ከንቱዋች ነን››
‹‹እንግዲህ ጀመረሽ…አይገባሽም እንዴ ..?ልጃችን ምንም አይነት አደጋ አልደረሰባትም…አልታገተችም..ሆስፒታልም አልገባችም….ይሄ በቂ አይደለም፡፡››
‹‹አይደለም…ይህ በፍፁም በቂ አይደለም….ልጄን አምጣልኝ…ልጄን በአካል እፈልጋለው››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

05 Nov, 06:39


‹‹ለማንኛውም ተመልሼ መጣለሁ..ና ወደቢሮ እንመለስ …››ብለው ሰለሞንን አስከትለው ወደቢሯቸው ተመለሱ፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

04 Nov, 06:37


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራ ሶስት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
እለቱ እሁድ ነው፡፡ከፊራኦል ጋር ለመውጣት ስለተነጋገሩ እየተዘጋጀች ነው፡፡ለሊሴ እየረዳቻት ነው፡፡
ሰው ከለገመ ከሻማ በላይ በቀላሉ ቀልጦ የሚጠፋ ከጠነከረ ደግሞ ከአልማዝም በላይ ማይቆረጥና ማይሸረፋ ተአምራዊ ፍጡር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡በፀሎትም የማያልፍ የመሰላት አሰቃይ ህመም በጥቂት ቀናት ውስጥ ጥሏት ሄዶ ንፅህና ጤነኛ ልጅ ሆናለች፡፡የእግሯን ስብራት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ድኗል…የፊቷ ቁስል ግን ምንም እንኳን ቢድንም ጣባሳውና ቁስለቱ አሁንም በግልጽ ፊቷ ላይ ይታያል… በዚህ ምክንያት አሳባ ከፊል ፊቷን ሁሌ በሻርፕ እንደሸፈነችው ነው፡፡ዋና ምክንያቷ ግን ማንነቷ በቀላሉ እንዳይለይ በማሰብ ነው፡፡አሁንም ተመሳሳይ አለባበስ አድርጋ በዛ ላይ ጥቁር መነፅር አይኗ ላይ ሰክታ ዝግጁ ሆነች፡፡
‹‹ግን እህቴ ለምንድነው እኔን የማታስከትሉት?››ለሊሴ ተነጫነጨች፡፡
‹‹አይ …መጀመሪያ ከወንድሜ ጋር የምንሄድበት ቦታ አለ…ባይሆን ከዛ ቶሎ ከጨረስን እንደውልልሽና ትቀላቀይናለሽ››
‹‹ይሁንላች ግን ታበሳጭቼባችኋለሁ››
በታክሲ ከሰፈር ሁለት ፌርማታ ያህል ርቀው ከሄዱ በኃላ ‹‹ደርሰናል እንውረድ›› አላት፡፡ያን ያህል ቅርብ ይሆናል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡እንደወረዱ ቀጥታ ፊት ለፊት የሚገኝ በፅድና በባህርዛፍ አፅድ የደመቀ ሰፊ መናፈሻ ውስጥ ነው ይዞት የገባው…ቀጥታ ከሰው ነጠል ያለ ቦታ ይዞት ሄደና ቁጭ እንድትል መቀመጫ አመቻችቶላት ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ‹‹እሺ ምን ትጠቀሚያለሽ?››
‹‹ቆይ እስኪ… ምን አስቸኮለህ…መጀመሪያ ትምጣ››
‹‹ማን?››
‹‹ምን ….ማንን ልናገኝ ነው የመጣነው…?ፍቅረኛህ ነቻ…በል ደውልላት፡፡››
‹‹ስልክ የላትም››
‹‹ታዲያ እንዴት ነው የምታገኘን››
‹‹የልቤን ምት አዳምጣ ትመጣለች››
‹‹ጥሩ ትቀልዳለህ….ይሄ የተለመደ መገናኛ ቦታችሁ ነው ማለት ነው…ገባኝ›› አስተናጋጁ መጣችና‹‹ምን ልታዘዝ ?››ብላ ጠየቀች፡፡
በፀሎት ቀደም ብላ‹‹ሰው እየጠበቅን ነው….››ብላ ለአስተናጋጆ መለሰችላት
‹‹አይ አሷን እንጠብቅም..ቆንጆ ፒዛ አሰሪልን…ፒዛው እስኪደርስ እሷም ትደርሳለች››

አስተናጋጆ ትዕዛዙን ተቀብላ ሄደች፡፡
ፊራኦል ወደእሷ አትኩሮ እያያት…..‹‹እስኪ ሻርፑን አንሺው››በማለት ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት
‹‹እንዴ ለምን?››
‹‹ሙሉ ፊትሽን ለማየት ፈልጌ››
‹‹ኖ ዌይ…..›
‹‹ምን ችግር አለው?››
‹‹እኔ እራሴ ሙሉ በሙሉ ፊቴ እንደዳነ እና እንደማያስጠላ እርግጠኛ ስሆን እገልጠዋለው፡፡››
‹አንቺ እንዴት ልታስጠይ ትችያለሽ…ውብ እኮ ነሽ››
‹‹ሙሉ ፊቴን ሳታይ ውብ መሆኔን በምን አወቅክ…?››ኮስተር ብላ በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ ውብ እንደሆንሽ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡››
መልስ ልትሰጠው አፏን ስትከፍት አስተናጋጇ የታዘዘውን ፒዛ ይዛ ፊታቸው ስታስቀምጥ አፏን ያለምንም ንግግር ከደነች፡፡
‹‹‹ለእኔ እስፕራይት አምጪልኝ…..ላንቺስ ?››
‹‹እንዴ ልጅቷ ሳትመጣ….?››
‹‹ባክሽ የሆነ ነገር እዘዢ እሷ ስትመጣ የራሷን ነገር ታዛለች››
ግራ እየገባት አዘዘች …ፒዛውን ቆርሶ መብላት ሲጀምር ፣ በገረሜታ ተከተለችው… በልተው ጨርሰው እንኳን ልጅቷ አልመጣችም››
‹‹እንደዛ ቅኔ ምትቀኝላት ልጅ እስከአሁን ካልመጣች ከአሁን ወዲያም የምትመጣ አይመስለኝም፡፡››

‹‹መጣችእኮ››
‹‹የታለች?››
‹‹ይህቹት ፊት ለፊቴ ቁጭ ብላ እያወራቺኝ ነው፡፡››
‹‹እየቀለድክብኝ ነው እንዴ?››
‹‹እሺ አትበሳጪ..እኔ ምንም አይነት ፍቅረኛ የለኝም….አንቺን ወጣ አድርጌ ማዝናናት ስለፈለኩ ነው እንደዛ ያልኩሽ››
‹‹አንተ ውሸታም……..ቆይ ምንም ፍቅረኛ ሳይኖርህ ነው እንደዛ ፈዘህ በውድቅት ለሊት ቅኔ ስትዘርፍ የነበረው››
‹‹በተጨባጭ ፍቅረኛ የለኝም አልኩሽ እንጂ በምናቤ ስዬ የማስባት ሴት የለችም አላልኩሽም…..እንደዛ አወራ የነበረው በልቤ ውስጥ ተንሰራፍታ የተቀመጠችውን ልክ እንደአንቺ ውብ የሆነችውን ልጅ እያሰብኩ ነበር››
‹‹ምን አይነት አዝግ ልጅ ነህ….?እኔ ደግሞ እንዴት አይነት ቆንጆ ልጅ ትሆን እያልኩ ለሊቱን ሙሉ ሳስብና ስጓጓ ማደሬ››
‹‹ምን ያጓጓሻል…የፈለገ ውብ ብትሆን ካንቺ አትበልጥ…አንቺ እኮ ሁለመናሽ ውብ ነው…ማለት ስብዕናሽ ፖስቸርሽ..እርግጠኛ ነኝ መልክሽም ውብ ነው..ፍቅረኛዬ ልክ አንቺን ካልመሰለች ልቤን ማሸነፍ አትችልም››ፊራኦል ቀጥታ መንገር ፈርቶ ነው እንጂ ከበፀሎት ፍቅር ከያዘው ሰነባብቷል…ስሩ ሆና እራሱ ትናፍቀው ከጀመረች ቆይታለች..ለዛ ነው ሙሉ ፊቷን ማየት በጣም የናፈቀው…ቆንጆና ውብ ፊት ነው በምናቡ የሳለው…
‹‹ጥሩ ..ግን ስለውበትና ቁንጅና እኮ በእህትና በወንድም መካከል የሚወራ ኮንሰፕት አይደለም…..ባምርም ባስጠላም እንደእህትህ ነኝ…ለውጥ አያመጣም፡፡››
‹‹እንደእህት እና እህት ግን ይለያያል››
ለዚህ ንግግሩ ምን ብላ መልስ ልትሰጠው እንደምትችል ሊመጣላት አልቻለም…‹‹.እኔ የእህትህን ልብ በውስጤ የተሸከምኩ ሴት መሆኔን ብታውቅ ይሄን ሁሉ ርቀት ለመጓዝ አይዳዳህም ነበር››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች

//////

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

04 Nov, 06:37


በማግስቱ-----
እቤት ውስጥ ማንም የለም..ሌንሳ ብቻ ከበፀሎት ጎን ቁጭ ብላ እያወራቻት ነው፡፡
እህቴ ስራ በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ሆኜያለው….ይገርምሻል ፀሀፊ ሆናለው ብዬ አንድም ቀን ኣስቤ አላውቅም ነበር…››
‹‹ላንቺ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል… ስራውን ግን እንዴት ነው..እየለመድሽው ነው? ››
‹‹አሪፍ ነው ..ተመችቶኛል፡፡››
‹‹የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው ያልሽው?››
‹‹አዎ እህቴ …ብታይ ሰውዬው ማለቴ አለቃዬ በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡››
‹‹ለምንድነው የሚያሰዝነው? እሱም ፍቅር ይዞታል እንዴ?፡፡››
‹‹አይ እሱን አላውቅም … ያሳዝናል ያልኩሽ…ምንም ደንበኛ የለውም….ዝም ብለን እኔና እሱ ቢሮ ውስጥ ተፋጠን ነው የምንውለው…››ለምን ያሳዝናል እንዳለች ታስረዳት ጀመር፡፡
‹‹ምነው በስራው ጎበዝ አይደለም እንዴ?››
‹‹አረ በቅርብ ነው ከውጭ የመጣው..በሞያው ኤክስፐርት ነው…እንደነገረኝ ከሆነ አሜሪካ እያለ በሞያው ከሶስት አመት በላይ ሰርቶ በጣም ብዙ ሰዎችን ረዳቷል …እዚህ መጥቶ የራሱን ድርጅት ቢከፍትም እንዳሰበው አልሆነለትም….እንደምታውቂው የእኛ ሰው ድብቅ ነው …ባለትዳሮችም ቢሆኑ እዛው ቤታቸው ውስጥ ሲቋሰሉ ይኖራታል እንጂ ገበናቸውን ወደአደባባይ ማውጣት አያስብትም ..ባስ ቢልባቸው እንኳን እዛው የሰፈር ሽማጊሌ ጠርተው በምስክር ፊት ይጨቃጨቃሉ እንጂ ወደባለሞያ አይሄዱም፡፡ለዚህ ጉዳይ ባለሞያም እንዳለው የሚያውቅ የማህበረሰብ ክፍል አንድ ፐርሰንት የሚሞላ አይመስለኝም፡
‹‹ታዲያ እኮ የሰፈር ሽምግልናው ቀላል ነገር አይምሰለሽ…ሁለቱም ለእኛ ጥሩ ያስባል እና ያስማማናል የሚሉትን ሰው በማሀከላቸው አስቀምጠው ችግራቸውን በግልፅ በመነጋገር

ለመፍታት መሞከር ትልቅ ዋጋ ያለው ማህበራዊ እሴታችን ነው፡፡በዚህም መንገድ በጣም በርካታ ሺ ትዳሮች በየአመቱ ስንጥቃቸው ይደፈናል ስብራታቸው ይጠገናል፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ እህቴ… ቢሆንም ግን.. አልፏ አልፏም ቢሆን ባለሞያ መጠቀም ብንለምድ ደግሞ ተጨማሪ ማህረሰባዊ ጥቅም እናገኝበታለን…አንዳንድ ችግሮች ከሽማግሌ አቅም በላይ ይሆናሉ..ዕውቀት የሚጣይቁ.. የባለሞያ ክትትልና መመሪያ የሚፈልጉ በጋብቻ ውስጥ ሚፈጠሩ ችግሮች አሉ፡፡››
‹‹በዛ እስማማለው….ግን የእውነት ሀለቃሽ ጎበዝ ነው?››
‹‹በጣም…. በጉብዝናውና በእውቀቱ ምንም ጥርጣሬ የለኝም፡፡››
‹‹እሺ ጥሩ››
‹‹በቃ ተጫወቺ ኩሽና ሄጄ እማዬን ላግዛት፡፡››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡
‹‹እሺ ሂጂ …ግን ስልክሽን መጠቀም እችላለሁ?››
‹‹አረ ችግር የለውም…..››አለችና ከጃኬት ኪሷ አውጥታ እጇ ላይ አስይዛት ሄደች….በፀሎት ስልኩን ከፈተችና መፈለግ ጀመረች …..ሪሰንት ኮል ውስት ገብታ ስትፈልግ ሰሎሞን ቦስ የሚል አገኘችና ቁጥሩን በቃሏ ሸመደደች፡፡
በማግስቱ ፊራኦልን ለመደወል የምትገለገልበት ቀላል ስልክና በማይታወቅ ሰው ስም የወጣ ሲም ካርድ እንዲፈልግላት ጠየቀችው…..ያለችውን በግማሽ ቀን ውስጥ አሰረከባት፡፡እና ለብቻዋ የምትሆንበትን ሰዓት አመቻቸችና ከቤቱ ራቅ ብላ ወደጓሮ በመሄድ ደወችለት፡፡
‹‹ሄሎ ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነው፡፡››
‹‹እባክህ እገዛህን ፈልጌ ነበር ››
‹‹ችግር የለውም …ቁጥር ልክልሻለሁ… ፀሀፊዬ ጋር ደውይና ቀጠሮ ያዢ››የሚል ምክረሀሳብ አቀረበላት፡፡
ቆፍጠን ብላ‹‹እንደዛ ማድረግ አልችልም››አለችው፡፡

‹‹ማለት?››በንግግሯ ግራ እንደተጋባ ያስታውቃል፡፡
‹‹በጣም ሚስጥራዊ ስራ ነው እንድትሰራልኝ የምፈልገው…››
‹‹የእኔ እህት ንግግርሽ ምንም አልገባኝም..ምን አይነት ሚስጥራዊ ስራ…ለማንኛውም ቢሮ ብቅ በይና በአካል ተገኛኝተን እናውራ››
‹‹አይ እንደዛ ማድረግ አልችልም..ቢያንስ ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አልችልም….››
‹‹ታዲያ እንዴት ማድረግ ነው የምትችይው….?፡፡›››ከመገረም ውስጥ ሣይወጣ ጠየቃት፡፡
‹‹ስራው የአምስት ሚሊዬን ብር ስራ ነው…ቅድሚያ ክፍያ መቶ ሺብር እከፍልሀለው…ብሩ እንደደረሰህ ስራውን ትጀምራለህ…..ስራው በስኬት ማጠናቀቅ ከቻልክ እንዳልኩህ 5 ሚሊዬን ብር ታገኛልህ …ይመችሀል፡?››
‹‹ማነሽ…የተሳሳተ ቦታ የደወልሽ መሰለኝ…አምስት ሚሊዬን ብር የምትከፍይኝ ምን እንዳደርግልሽ ብትፈልጊ ነው…?አውቀሻል..እኔ ፍቅርና ጋብቻን በተመለከተ የምክር አገልግሎት የምሰጥ ባለሞያ ነኝ፡፡››ምን አልባት የተሳሳተ ቦታ ደውላ የእሱንም ሆነ የራሷን ጊዜ እያቃጠለች ነው ብሎ ስለገመተ ሊያብራራላት ሞከረ…
‹‹በጣም የተወሳሰበና በነገሮች የተቆሳሰሉ የጋብቻ ተጣማሪዎችን ማገዝ ትችላለህ..?እንደምንም ችግራቸውን ቀርፈውና ይቅር ተባብለው ወደሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ማድረግ ትችላለህ?፡፡››
‹‹እንደማስበው …ማለቴ ከድምፅሽ እንደምረዳው ገና ወጣት ነሽ….ይሄውልሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በስራው ውጤታማ መሆን የሚችለው ሁለቱ ተጣማሪዎች በመጀመሪያ በመካከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ..ከዛም ሁለቱም ለችግሩ በጋራ ኃላፊነቱን ወስደው ለመለወጥ ፍፅም ፍቃደኛ ሲሆኑና ባለሞያው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ምክር ከቁም ነገር ወስደው ተግባራዊ ሲያደርጉ ነው….አዎ አንቺና የትዳር አጋርሽ ለመለወጥና ትዳራችሁን ለመታደግ ፍላጎቱ ኖሮችሁ ፍጽም ተባባሪ የምትሆኑ ከሆነ አዎ እኔ ጋብቻችሁን ወደቦታው ልመልሰው እችላለው፡፡በዛ ቃል ልገባልሽ እችላለው››
‹‹ጥሩ ..መቶ ሺ ብሩን አዘጋጅቼ ከሶስት ቀን በኃላ ደውልልሀለው››

‹‹ይሄውልሽ….እኔ የማስከፍለው ክፍያ አንቺ ከጠራሽው ብር ጋር ፈጽሞ አይቀራረብም…ቀብድ ያልሽው ብር እራሱ በጣም ይበዛል፡፡››
‹‹አይ ክፍያውን አንተ ሳትሆን እኔ ነኝ የምወስነው….ይሄውልህ እደግመዋለው..ቅድሚያ ክፍያ 100 ሺ ብር ከፍልሀለው…ስኬታማ ሆነህ ጋብቻውን ማከም ከቻልክ የ 5 ሚሊዬን ብር ቼክ ከታላቅ ምስጋና ጋር እጅህ ይገባል…ካልተሳካልህ ደግሞ ከ100 ሺ ብሩ ውጭ ምንም ተጨማሪ ክፍያ አይኖርም፣ገባህ…..?ይሄ ማለት ሌሎች ስራዎችህን በሙሉ ሰርዘህ ወይም ወደሌላ ጊዜ አዘዋውረህ ሙሉ ትኩረትህን የእኔ ጉዳይ ላይ እንድታደርግ ስለምፈልግ ነው..አንድ ወርም ፈጀብህ ስድስት ወር አላውቅም…እስኪሳካልህ ወይም ተስፋ እስክትቆርጥ ሙሉ ትኩረትህን እፈልጋለው…በል ቸው፡፡››ሰልኩን ዘጋችው
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

02 Nov, 07:29


ካንቺ ልኖር ..በፍቅር አስሮኛል ዛሬ ባንቺ ….በጣም ረክቼያለሁ ነገም አብረን ….ሰላም አገኛለው፡፡
በህይወቷ ብዙ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ተካፍላ ታውቃለች…በአባቷ ቤት ሳለች በተለያዩ ጊዜ ትላልቅ የተባሉ የሀገሪቱ ዘፋኞች እቤታቸው ድረስ መጥተው ሲዘፍኑ ምቹ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ አድምጣ ታውቃላች…በተለያየ ጊዜ ከሀገር ውጭ ለመዝናናት በሄደችበት ጊዜ አለም አቀፍ አርቲስቶች ባዘጋጁት ውድ ኮንሰርት ላይ ታድማ ታውቃለች..እንዲህ እንደአሁኑ ግን ምቹ ባልሆነ ደረቅ ወንበር ላይ በውድቅት ለሊት ብርድ እያንዘፈዘፋት እየሠማችው እንዳለ ሙዚቃ በተመስጦ እያንዳንዱን ቃላት በደስታ አድምጣና አጣጥማ አታውቅም…
‹‹ፍቅረኛህ በጣም የታደለች መሆኗን ታውቃለች?፡፡››
‹‹ታውቃለች..የእኔ ፍቅር እኔን ከእነድምፄ ከመላ እኔነቴ ጋር በጣም ታፈቅረኛለች..በጣም በጣም..››
‹‹አንተስ?››
‹‹እኔማ አፈቅራታለሁ ብል..ቃላቱ የውስጤን ስሜት አይገልፅልኝም….ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው…እሷ ስትናፍቀኝ እኮ መተንፈስ እራሱ ከባድ ይሆንብኛል…ምስሏ እናቴ ደግነት ላይ አየዋለሁ…የአዲስ አበባ ከንቲባ ብሆን የከተማዋን ዋና ዋና መንገድ ሁሉ ለስሟ መጠሪያ እንዲሆን አደርግ ነበር….አረ አንጦጦ ታራራ ጫፍ ላይ ቤተመቅደስ ባንፅላት ሁሉ

ደስ ይለኛል…..እና ለእሷ ያለኝ ፍቅር እንዲህ አይነት እብደትና ጅልነት በአንድ ላይ የተቀየጠበት ስሜት ነው፡፡ አንዳንዴ ልብሴን አወላልቄ እርቃኔን ሰው በሚርመሰመስበት መርካቶና ፒያሳ እየተሸከረከርኩ….እኔ እሷን አፈቅራታለው..በጣም አፈቅራታለው..እያልኩ ስጮህ ብውል ደስ ይለኛል..አዎ እንደዛ አድርግ የሚል ስሜት ይተናነቀኛል…ግን ከጃኬቴ ውጭ የተቀረውን ለማውለቅ ወኔ አላገኝም፡፡
‹‹እንዴ..አንተ ለካ ድምፃዊ ብቻ ሳትሆን እብድ የሆንክ አፍቃሪ ነህ….በል በል ነገ እሁድ አይደል..ይህቺን እንደእብድ የምታፈቅራትን ልጅ ታስተዋውቀኛለህ፡፡
‹‹ማንን ፍቅረኛዬን?፡፡››
‹‹አዎ››
‹‹ባስተዋውቅሽ ደስ ይለኝ ነበር…ግን እሷ እዚህ መምጣት አትችለም?››
‹‹ለምን..እ ..ገባኝ..አማቾቻን ትፈራለች ማለት ነው?››
አልመለሰላትም….ዝምታውን ‹‹ትክክል ነሽ ››የሚል መልስ እንደሰጣት አድርጋ ወሰደች፡፡
‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ እኔም ውጩ ናፍቆኛል …በኮንትራት ታክሲ ያለችበት ድረስ ትወስደኛለህ፡፡
‹‹እርግጠኛ ነሽ?››
‹‹አዎ እርግጠኛ ነኝ››አለችው..ግን ውስጧ የእርግጠኝነት እና የደስታ ስሜት አይደለም እየተሰማት ያለው….ፊራኦል እንዲህ የሚያሳብድ አይነት ፍቅር ውስጥ መሆኑንና
…እንደዛም ያሳበደችውን ሴት ፊት ለፊት አግኝታ ልትተዋወቃት መሆኑን ስታስብ ደስታ ሳይሆን ፍራቻ ነው የተሰማት…‹‹ግን ለምንድነው የፈራሁት….?በምን ምክንያት ነው ቅር ያለኝ?››ስትል እራሷን ጠየቀችና አማተበች፡፡
ሁኔታዋን በትኩረት ሲከታተል የነበረው ፊራኦል ‹‹ ….ምነው አማተብሽ ሰይጣን አየሽ እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ውስጤ ሲገላበጥ ስለተሰማኝ ነው?››
‹‹ማ ሰይጣን?››

‹‹አዎ ሰይጣን እኮ ሌላ ምንም ሳይሆን የልባችን ክፋት ነው፡፡ሰይጣን ቅናታችንና ተንኮላችን ነው፡፡››
‹‹እና እንደዛ ከሆነ እኮ በአንቺ ልብ ውስጥ መቼም ሊገባ አይችልም…››
‹‹እንዴት? እኔ ጥሩ ሰው ነኝ አንዴ?››
‹‹እኔ በዚህ እድሜዬ ሶስት በጣም ደግና ቅን ሰዎችና አውቃለሁ››
‹‹እሺ እነማን ናቸው?››
‹‹አንቺንና አባቴን እና …
‹‹ማን…ፍቅረኛህን?››
‹‹አይ አይደለም….ሞች እህቴ በሬዱ…ብታይ የአባቷ ልጅ ነበረች…በጣም ቅን ደግና ሁሌ ለሰው የምትኖር ነበረች…እዚህ መንደር አይደለም በቀበሌው ውስጥ ጦሪ የሌላቸው አቅመ ደካሞችን በየቤታቸው እየሄደች ልብሳቸውን ታጥባለች ..ታበስልላቸዋለች…..የታመሙትን ታስታምማለች…የሆነ ነገረ ሰርታ ብር ካገኘች በማግስቱ እጇላይ የለም…ቸገረኝ ላላት ሁሉ አድላ ባዶዋን ስትቀር ትንሽ እንኳን ቅር አይላትም፡፡ትንሽ ትልቁ እንደመረቃት ነበር፣ዳሩ ምን ዋጋ አለው?››
‹‹ማለት….?››
‹‹ምርቃት እህቴን ከመኪና አደጋ ከለላት…?ምርቃት በወጣትነቷ እንዳትቀሰፍ እረዳት
?አረዳትም…በመዝረፋና ማጅራት በመምታት ሰውን ሲያስለቅሱ የሚውሉ ድርዬና ወሮበሎች እንቅፋት እንኳን ሳይነካቸው በሳለም ህይታቸውን ያጣጥማሉ ፃድቋ የእኔ እህት ግን ገና ምኑንም ሳትይዘው ተቀጠፈች….››
‹‹አይ እንዲህማ አታስብ…እግዚያብሄር እሷን በጊዜ የጠራበት የራሱ የሆነ ምክንያት ይኖረዋል….ምን ይታወቃል የረዘመ ህይወት ብትኖር እንዲህ ንፁህና ቅዱስ እንደሆነች እንደማትቀጥል ስለሚያውቅ ይሆናል በጊዜ የሰበሰባት..ወይንም ህይወቷ በመከራ የተሞላ ሊሆን ይችል ይሆናል…ወይንም ደግሞ በማይድን በሽታ ተይዛ የአልጋ ቁራኛ ሆና ለዘመናት የምትማቅቅ ሊሆን ይችላል….እግዚያብሄር ከደግነቷ አንፃር አይቶ ከክፉ ነገሮች ሊከልላት አስቦ ይሆናል በጊዜ የወሰዳት፣ደግሞ ልብ በል እግዚያብሄር አይሳሳትም…በዛ ላይ እደነገርከኝ እህትህ ሙሉ በሙሉ ሞታ አልሞተችም….አሁንም በሌላ ሰው አካል ውስጥ ከፊል አካሎ ህያው ሆኖ እየኖረ ነው…ሞታ እንኳን ደግነቷን ማስቀጠል ችላለች፡፡››
‹‹ጥሩ አፅናኚ ነሽ…ግን በአቋሜ አንደፀናሁ ነው….ደግነት ይከፍላል በሚሉት ብሂል አላምንም..እንደውም ደግነት ሲከፍል ሳይሆን ሲያስከፍል ነው ያየሁት..እናም አንቺንም ምመክርሽ ደግነትሽን በልክ አድርጊው ብዬ ነው፡፡››
ክትከት ብላ ሳቀች …ሳቋ በገደል ማሚቱ እስተጋብቶ ጆሮ እየተመሰገ ነው ‹‹..ምን
አይነት መመሳሰል ነው››
‹‹ምን አልከኝ?››
‹‹‹አይ ምንም››
‹‹ይሄውልህ አባትህ ማለት የሰው መልአክ ናቸው፡፡ሙሉ ስብዕና የተላበሱ ቅዱስ ሰው፡፡አንዳንድ ሰው እኮ አንደበቱ ጣፋጭና መልካም ሆኖ ምግባሩ የተበላሸ ይሆናል…ወይም ደግም በምግባሩ አስደናቂና መልካም ሆኖ በአንደመበቱ ያቆስልሀል፡፡አባትህ ግን አንደበታቸው ከምግባራቸው በፍፁም ስምም የሆነላቸው ድንቅ ሰው ናቸው..እንደነገርከኝ እህትህም የአባትህ ቢጤ ነች….እኔ ግን ..አረ ተወኝ በዚህ ሰዓት በእኔ ምክንያት ስንት ሰው እያለቀሰ እና እየተሰቃየ መሆኑን ብታውቅ ከአባት እና እህትህ ጋር ልታነፃፅረኝ አይዳዳህም ነበር፡፡
‹‹ኸረ ተይ አንቺ ሰውን ልታስቀይሚና ልታስጭንቂ ..የማይሆነውን››
ሰኞ….ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

02 Nov, 07:29


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራሁለት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡
‹‹ልጄ ይቅር የምልህ..እያንዳንዱን የገዘኸውን ዕቃ ወይ በየገዛበት መልሰህ ካልሆነም ለሌላ በመሸጥ ገንዘቡን አንድም ሳታጎድል ለልጅቷ ስትመልስ ነው፡፡››
‹‹እሺ አባዬ እንዳልክ አደርጋለው፡፡››
‹‹እኮ ተነስና አድርግ››
‹‹አሁን እኮ መሽቷል….ነገ በጥዋት ተነስቼ እንዳልከው አደርጋለው››
‹‹እስከዛው ላይህ አልፈልግም፣ወይ ቤቱን ለቀህ ውጣ ወይ እኔ ልልቀቅልህ››
‹‹አረ አባዬ… አንተ ምን በወጣህ እኔ ወጣለሁ….››ብሎ ከተቀመጠበት ሲነሳ በፀሎት ከተቀመጠችበት ሆና ጣልቃ ገባች…ጋሼ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ሀሳብ ነው….ቆርቆሮውም..ሲሚንቶውም ሁሉም የተገዛው በእኔ ሀሳብ ነው፡፡በወቅቱ እሱ እንደማይሆን ነገሮኝ ተቃውሞኝ ነበር..እኔ ነኝ ያስገደድኩት…ስለዚህ ወቀሳውም ቅጣቱም የሚገባው ለእኔ ነው…ለሊሴ ታክሲ ልትጠሪልኝ ትችያለሽ?››
ጥያቄዋ ሁሉንም ሰው አስደነገጠ፡፡
‹‹እንዴ ታክሲ ምን ሊያደርግልሽ?››ለሊሴ ጠየቀች፡፡
‹‹የጋሼን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ነዋ…ሆቴል ድረስ የሚወስደኝ ታክሲ ጥሪልኝ…ከቤት መባረር ያለብኝ እኔ ነኝ››
‹‹ተይ እንጂ ልጄ..ለምን ጡር ውስጥ ታስገቢኛለሽ?››አቶ ለሜቻ ለዘብ ብለው ተናገሩ
‹‹ጋሼ ..ይሄ ምንም ጡር አይደለም…ይሄንን እቃ ያስገዛሁት ለራሴ ስል ነው….ያው እንደምታዩት በዚህ አያያዜ ለመዳን ሁለትና ሶስት ወር ይፈጅብኛል ..ከዳንኩ በኃላም ቶሎ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ከእናንተ ጋር ቢያንስ ስድስት ወር ኖራለው..ስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እንዲህ የለሊሴን መኝታ አስለቅቄ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ከባድ ስለሆነ ነው

ሀሳብን ያመጣሁት..እኔ እንደውም ቤቱን ተረባርበን በአንድ ወር ውስጥ አልቆ እኔ ከእነለሊሴ ጋር እኖርበታለው ብዬ ነው››ስትል አብራራች፡፡
‹‹ልጄ ቢሆንም አግባብ አይለም..በእኛ ላይ ይሄን ሁሉ ብር መከስከስ እኛም አሜን ብለን መቀበል ነውር ነው…ሰውን ተይው …እግዚያብሄሩስ ምን ይለናል?››
‹‹አሁን ልጅህ ለሊሴ ብር አግኝታ እንዲህ ብታደርግ ይሄን ያህል ትበሳጭባታለህ?›› ዝም አሉ
‹‹ገባኝ አትበሳጭባትም….እኔንም እንደልጅህ አድርገህ ከምር ብትቀበለኝ ኖሮ ይሄን ያህል ቅር አትሰኝም ነበር..በቃ ለሊሴ ደውለሽ ታክሲውን ጥሪልኝ››
ለሊሴ ፈራ ተባ እለች… ስልኳን ከተቀመጠበት አነሳችና ለመደወል ስትዘጋጅ ጋሽ ለሜቻ‹‹ልጄ ስልኩን አስቀምጪው..እስኪ ሁላችሁም ተቀመጡና እንረጋጋ…››
‹‹አዎ ልጆች ሁላችሁም ተቀምጡ….ለሊሴ እስኪ ሲኒውን አቀራርቢና ብና እናፍላ››እናትዬው ውጥረቱ ረገብ ስላለ ተደስተው የተናገሩት ነበር፡፡
////
በማግስቱ

‹‹…አየሩ በጥላቻ ጥላሼት ጠቁሯል፡፡ከፍቅር ዕጦት በሚመጣ የፍራቻ ግንብ ተከልያለው….በንዴቴ አጥር ስር ተሸሽጌ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡ይበርደኛል..አዎ በጠራራ ፀሀይ ይበርደኛል…ይርበኛል..እየበላው ሁሉ ይረበኛል….፡፡ጉሮሮዬ በጥማት ተሰነጣጥቆል….ግን ከዛ ከጥማቴ የሚፈውሰኝ ውሀም ሆነ ምድራዊ ወይን የለም፡፡››በፀሎት ነች የምታወራው…ፊራኦል ግን ምንም አልገባውም
‹‹አንዳንዴ እንደፈላስፋ ነው የምታወሪው?››
‹‹እንደእኔ ህይወትህን ሙሉ በብቸኝነት በራፍ ዘግተህ ለብዙ ሰዓታት በትካዜና በቁዘማ የምታሳልፍ ከሆነ ወደፈላስፋነት መቀየርህ የግድ ነው፡፡ከሞት ደጃፍ ደርሶ..በቃ አበቃልኝ ብሎ ተስፋ ከቆረጠ በኃላ ወደህይወት ተመልሶ ሁለተኛ እድል የተሰጠው እደእኔ አይነት ሰው ነገሮችን በተለየ መልክ ባያይ ነው የሚገርመው፡፡›››

‹‹አልገባኝም የሞት አፋፍ ላይ መድረስ ስትይ?››
ደነገጠች..አንደበቷን አንሸራቷት ሚስጥር ልታወጣ በመድረሶ እራሷን ወቀሰችና‹‹ማለቴ በዛ ለሊት በሞተሬ ከእዚህ በራፍ ጋር ስለ መጋጨቴ እያወራው ነው…የሞትኩ ማስሎኝ ነበር እኮ››
‹‹እ..እሱ እንኳን እውነትሽን ነው….ግን አሁን ፊትሽ ቁስሉ ደርቆል እኮ …ለምን ቀንና ለሊት በሻርፕ ትሸፍኚዋለሽ…››
‹‹እርግጥ እንዳልከው ድኗል ግን ጠባሳው ያስጠላል..እንዲህ ሆኜ ሰው እንዲያየኝ አልፈልግም ..በተለይ ወንዶች ››
ፈገግ አለ….‹‹ዝም ብለሽ እያካበድሽው ነው እንጂ እርግጠኛ ነኝ ከነጠባሳሽ በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ…እንደውም እንዲሁ አቋምሽን ሳየው የት እንደሆነ የማውቃት አርቲስት ወይም ሞዴል ነገር እየመሰልሽኝ ደነግጣለው፡፡››
‹‹አየህ አንደውም ለዚህ ነው ፊቴን ዘወትር በሻርፕ ምጆብነው››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ሙሉ በሙሉ ገልጬልህ ፊቴን በደንብ ካየኸው የትኛዋ ሞዴል ወይ አርቲስት እንደሆንኩ ወዲያው ስለምትለየኝ፣እንደዛ እንዳይሆን ስለፈለኩ ነው››
‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››
‹‹ምን ላድርግ ብለህ ነው….በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እንደእኔ አይነት ሰው ባይቀልድ ነው የሚገርመው››
‹‹እስኪ እርእሱን እንቀይር ፣ሌላው ስለአንቺ የሚገርመኝ እስከአሁን ሞባይል ይዘሽ አለማየቴ ነው››
‹‹የለኝም…..ማለቴ ከቤቴ ስወጣ ይዤ መውጣት አልቻልኩም፡፡››
‹‹ታዲያ ልግዛልሽ…ማለቴ በራስሽው ብር የምትፈልጊውን አይነት ስልክ ልገዛልሽ እችላለሁ፡፡››

ፈገግ አለችና‹‹በራስህ ብር ብትገዛልኝ አይሻልም?››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር..ግን አቅሜ ላንቺ የሚመጥን ስልክ ለመግዛት በቂ አይመስለኝም…››
‹‹የእኔ አቅም ምን ያህል ነው..?በምንስ ሚዛን ለካሀው…?ለማንኛውም ለጊዜው አያስፈልገኝም…ስፈልግ ግን ነግርሀለው፡፡››
‹‹ይገርማል… በአንቺ እድሜ ያለች ሴት ስልክ አያስፈልገኝም ስትል አጃኢብ ነው፡፡››
‹‹ምኑ ይገርማል..?ለጊዜው ማንም ጋር ለመደወል እቅድ የለኝም..››
‹‹ሶሻል ሚዲያስ….እንዴት ያስችልሻል፡፡››
‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ስልክና ላፕቶፕ ላይ አረ አንቺ ልጅ አይንሽ ይጠፋል እየተባልኩ እስክሪን ላይ አፍጥቼ ነው የኖርኩት…ሶሻል ሚዲያ ከጨለማ ሀሳቦቼ እና ከድብርቶቼ መሸሺጊያ እና መደበቂያ ዋሻዬ ነበር…አሁን ግን ችግሮቼን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው የምፈልገው
….እስከአሁን ከኖሩኩት ህይወት በተቃራኒ ነው መኖር የምፈልገው፡፡ይልቅ ከቻልክ ነገ መፅሀፎች ገዝተህልኝ ትመጣለህ፡፡››
‹‹እሺ ምን ምን መፅሀፍ እንደምትፈልጊ ትንግሪኝና ገዝቼልሽ መጣለው፡፡››
‹‹ጥሩ አሁን ደግሞ ምርጥ አንድ ሙዚቃ ብትጋብዘኝ በጣም ደስተኛ እሆናለው…››
‹‹ጥሩ …አለና ከአጠገቡ ያለውን ክራር አንስቶ ክሮቹን በእጁ እያጠበቀ እና እያላላ ቅኝቱን አስተካከለና‹‹ምን አይነት ዘፈን ይሁንልሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹መቼስ በዚህ ውድቅት ለሊት ስለሀገር ዝፈንልኝ አልልህም…የፍቅር ዘፈን ይሁንልኝ፡፡›› እንደማሰብ አለና ክራሩን መገዝገዝ ጀመረ ..አፏን ከፍታ ነበር የምታዳምጠው…
የነገን ማወቅ ፈለኩኝ … መጪውን አሁን ናፈቅኩኝ.. የፍቅር ምርጫዬ አንቺ ነሽ…ልቤንም መንፈሴን የገዛሽ ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ፣አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ

በፍቅር ህይወቴን ላኖረው..ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰው የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሺኝ
ካንቺ ደስታ ፣እኔን እያስቀደምሺልኝ ፍቅር ለካ ለራስ …ማለት እንዳልሆነ ስታደርጊው አይቶ… ልቤ በቃ አመነ ከነገርሽ…. ባህሪሽ ማርኮኛል…

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

01 Nov, 08:48


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራ አንድ
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታት…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር…
‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?››
‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡››
‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››
‹‹አዎ ጎበዝ ልጅ ትመስላለች››
‹‹ጎበዝ?››
‹‹አዎ ምነው?››
‹‹አይ በአንድ ቀን እንዴት ጎበዝ መሆኗን አወቅክ ?ብዬ ገርሞኝ ነዋ››
‹‹ማለቴ እንዲሁ ሳያት ተግባቢና ቀልጣፍ ነገር ነች ልልሽ ነው››
‹‹ወንድሜ ፍቅር እንዳይዝህና እንዳትጎዳብኝ…ልጅቷ ፍቀረኛ አላት››
‹‹አይዞሽ አታስቢ አውቃለው፣በዛ ላይ እኔ ማፈቀሪያ ጭንቅላቴ የተበላሸብኝ ሰው ነኝ….››
‹‹ምኑ ነው ምታውቀው?››
‹‹እንዳላት ነዋ››
‹‹ከምኔው?››
‹‹ውይ ኪያ ደግሞ ….በቃ ቸው ማታ ቤት እንገናኝ››
‹‹እሺ ቸው ወንድሜ››በተንከትካች ሳቅ አጅባ ስልኩን ዘጋችው፡፡


////
ወላጇቾ ብቻ ሳይሆኑ ያደገችበትና የእድሜዋን ግማሽ የኖረችበት እቤቷም ጭምር ናፈቃት‹‹ ቤት ማለት..ግን ምን ማለት ነው?ስትል እራሷን ጠየቀችና መልሱን ከአእምሮዋ ውስጥ በርብራ ለማግኘት አይኖቾን ጨፍና ማሰላሰል ጀመረች
‹‹አዎ እቤት ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የሚታነፅ የሰው ልጅ መጠለያ ነው።ያንን ህንፃ ከመጠለያነት ወደ ቤትነት የሚቀይረው ግን የታነፀበት ማቴሪያል ጥራትና ውበት አይደለም...ውስጡ ያሉት ዘመናዊ የቤት እቃዎች እና ውድነትም አይደለም። ህንፃው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነትና የፍቅር ትስስር መጠን ነው ህንፃውን እቤት የሚያደርገው።ለዚህ ነው ከኖርኩበት የተንጣለለ ቪላ ይልቅ አሁን እየኖርኩበት ያለሁት ባለ ሁለት ክፍል ጎስቋላ ቤት የተሻለ የሞሚሞቀውና የሚደምቀው
››መልሱን ለራሷ ሰጠች፡፡ ቀኑን እንዲሁ በሀሳብና በትካዜ ጊዜውን ብታሳልፍም ሲመሽ ግን ሁሉ ነገር የተለየ ሆነ፡፡
ማታ የቤተሰቡ አባል ጠቅላላ ተሰብስበው በሞቅ ደስታ ከወትሮ በተለየ ድግስ መሰል እራት ቀርቦ በመጎራረስ ከበሉና ቡናም ተጠጥቶ ከተነሳ በኃላ በፀሎት ሽንት ቤት ለመሄድ እንድምትፈልግ ለለሊሴ ነገረቻት…ያሰበችው እሷ ደግፋ እንድትወስዳት ነበር…በተቀራራቢ እድሜ ስለሚገኙ እቤት ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ እሷን ማዘዝ ወይም ትብብር መጠየቅ ቀላል ይላታል፡ ….ለሊሴ ግን እንዳሰበችው አላደረገችም….
‹‹ወንድሜ በፀሎትን ሽንት ቤት ትወስዳታላህ?››ብላ ስትጠይቀው ክው ነበር ያለችው….እሱ አንደበት አውጥቶ ፍቃደኝነቱን ሳይናገር በቀጥታ ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳና ወደእሷ በመሄድ ልክ ትናንት ለሊት እንዳደረገው ከስር ሰቅስቆ ልክ እንደህፃን ልጅ አቀፋት….እንዲህ አይነት ሁኔታ በህይወቷ ገጥሞት ስለማያውቅ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እፍረትም ተሰማት…‹‹.ወላጆቹ እንዲህ ሲያቅፈኝ ምን ይላሉ ?››የሚለው ሀሳብ አእምሮዋ ተሰነቀረና ያንን ለማጣራት እይታዋን በቤቱ ዙሪያ ስትሽከረከር ሁሉም በራሳቸው ጫወታ ተመስጠው እርስ በርስ እያወሩ እየተሳሳቁ ነው……አንከብክቦ እንዳቀፋት ይዟት ወጣ
..ቀጥታ ሽንት ቤት ወሰዳና ወደውስጥ አስገብቶ አቆማት…ልክ እንደሌሊቱ ውሀ በሀይላንድ ከቧንቧው ቀድቶ አመጣላትና የሽንት ቤቱን መጋረጃ ወደታች መልሶ ‹‹ስትጨርሺ ጥሪኝ
››ብሎ ከአካባቢው ዞር አለ፡፡

የሽንት ቤት ጣጣዋን ከጨረሰች በኃላ ቀጥታ ወደቤት አይደለም ይዞት የገባው፡፡ልክ እንደለሊቱ ወንበር አመቻችቶ ስለነበር ተሸክሞ ወስዶ አስቀመጣት….‹‹ቀኑን ሙሉ ተኝተሸ ስለዋልሽ አሁን ትንሽ ንፍስ ይንካሽ››
‹‹አዎ ትክክል ነህ፣በዛ ላይ ጨረቃዋም ናፍቃኝ ነበር፡፡››
እሱም ለራሱ መቀመጫ አምቻችቶ ከፊት ለፊቷ እየተቀመጠ‹‹ከጨራቃዋ ጋር ወዳጅ ናችሁ እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ ለዛውም የእድሜ ልክ››
‹‹ያን ያህል ብቸኛ ነሽ ማለት ነው?››
‹‹እንዴት ከጨረቃ ጋር ለመወዳጀጀት ብቸኛ መሆን የግድ ነው እንዴ?››
‹‹አይ የግድ ባይሆንም ከልምዴ ስነሳ ብዙውን ጊዜ ከጨረቃዋ ጋር ለረጅም ጊዜ የማውጋት ልምድ ያላችው እንቅልፍ አልባ ብቸኛ ሰዎች ናቸው……በተለይ በፍቅር የተሰበሩ››
‹‹እንዴ በፍቅር የተሰበሩ ነው ያልከው..አይ እንደዛ እንኳን አይደለም…..ባይሆን እንዳልከው ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ብቸኝነት ብንለው የተሻለ ነው..የፍቅር ጉዳይማ ቢሆን በምን እድሌ..ፍቅር እኮ በጣም ምርጥ ነገር ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ… ፍቅር በጣም ወሳኝ ስሜት ነው….አንድ ሰው ሩሚን ‹‹ፍቅር ምንድነው?››ብሎ ጠየቀ።ሩሚም ..‹‹ፍቅር ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጉሙን ልታውቅ የምትችለው ውስጡ መጥፋት ስትችል ነው።›› ብሎ መለሰለት…..፡፡
‹‹አዎ ትክክለኛ አባባል ይመስለኛል….ፍቅር የምትተነትነውና የምታወራው ነገር አይደለም፣ፍቅር ኖረህ የምታጣጥመው የተቀደሰ ስሜት ነው….በፍቅር መጥፋት ጥሩ አባባል ነው››
‹‹አይ ጥሩ…ለማንኛውም ለደቂቃም ቢሆን እስቲ ከጨረቃዋ ጋር ብቻችሁን ልተዋችሁ…. መጣሁ›› ብሎ ተነስቶ ወደቤት ገባ..እሷ አይኖቾን ወደላይ አንጋጠጠች…ሰማዩ ጥርት ብሎ ይታያል ፡፡ጨረቃዋ ሙሉ ክብ ሆና ደፍናለች..ዙሪያዋን የተበተኑና ከዋክብቶች ብልጭ ድርግም እያሉ ይታያሉ…አናትና አባቷ ትዝ አሏት..ይሄኔ የእሷን መጥፋት ምክንያት በማድረግ የመጨረሻውን ጥል እየተጣሉና የመጨረሻ የተባለውን አንጀት በጣሽ ስድብ

እየተደሰዳደብ እንደሆነ በምናቧ አሰበችና ሙሉ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለባት..ሰውነቷ ሲሸማቀቅ ደግሞ የእግሯ ሆነ የፊቷ ጥዝጣዜ ህመም ተቀሰቀሰባት….
ድንገት የሰማችው ድምፅ ነው ከሀሳቧ ያባነናት…..ያልገመተችውን ነገር ነው እያየች ያለችው..ፊራኦል ፊት ለፊቷ ቅድም የነበረበት ቦታ ቁጭ ብሎ ክራር እየከረከረ የሙሀመድ አህመድን የትዝታ ሙዚቃ ያንቆረቁራል….ፍዝዝ ብላ በፍፁም ተመስጦ ታዳምጠው ጀመር፡፡
ስንቱን አስታወስኩት…ስንቱን አስብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
አንዴ በመከራ …አንዴ በደስታዬ ስንቱን ያሳየኛል ..ይሄ ትዝታዬ በድምፁ ድንዝዝ ብላ ጠፋች………… የትናንቱ ፍቅር ….ጣሙ ቁም ነገሩ ምነው ያስተዋሉት ያዩት በነገሩ
ሁሉም እንደገና ኑሮን ቢያሰላስል አይገኝም ጊዜ ያኔን የሚመስል፡፡
ዘፈኑን ሲጨርስ‹‹አንተ..አንድ ሺ አመት በዚህ ምድር ላይ ኖረህ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ያለውን ጊዜ ናፍቀህ የምትተክዝ እድሜ ጠገብ አዛውንት ነው የምትመስለው፡፡››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡
‹‹ያን ያህል?››
‹‹አዎ …ድምፅህ በጣም ግሩም ነው….ሙዚቃ ትሰራለህ እንዴ?››
‹‹አይ ያን ያህል እንኳን ሰራለሁ ማለት አልችልም …በፊት በፊት ቀበሌ ኪነት ከጓደኞቼ ጋር እሞክር ነበር አሁን ከህይወት ሩጫ ጋር አብሮ እልሄድ አለኝና ተውኩት፣እንዲህ አንደዛሬው ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን እንዲህ እቀመጥና ለእሷ አዜምለታለው፡፡››

‹‹እንዴ..ለእኔ የዘፈንክልኝ መስሎኝ ውስጤ በደስታ ተፍነክንኮ ነበር ..ለካ ለጨረቃዋ የተዘፈነውን ዘፈን ነው ሳይፈቀድልኝ የሰማሁት…..››
‹‹አይ እንደዛ አንኳን ለማለት አልችልም…የዛሬው ዘፈን ቀጥታ ላንቺ ነው..ምስጋናና ይቅርታ ለመጠየቅ፡ ብዬ ነው የዘፈንኩት፡፡››
‹‹አልገባኝም..ይቅርታውስ ለምን ?ምስጋናውስ?፡፡››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

01 Nov, 08:48


‹‹ይቅርታው ገና ስትመጪ ጀምሮ በሙሉ ልቤ ስላልተቀበልኩሽና ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ እንደሸክም ስለቆጠርኩሽ…ምስጋናው ዛሬ እናቴንም ሆና መላ ቤተሰብን አንበሽብሸሽ በማስደሰትሽ…..››
‹‹ተው ተው..አሁን ከዚህ ውብ እና አስደሳች ሙዚቃ በኃላ እንዲህ አይነት ንግግር አስፈላጊ ነው…?ይሄውልህ ምን አልባ አንተ ፍቅር በሚፈስበት ቤት ውስጥ በስስት በሚተያዩ ወላጆች እቅፍ ውስጥ ያደክና እስካሁንም እየኖርክ ያለህ ሰው ስለሆንክ ስለመገፋትና ጥላቻ ያለህ እውቀት አናሳ ይመስለኛል….አዎ እንዳልከው ከልብህ በደስታ አልተቀበልከኝም ይሆናል…ግን ደሜን ሲጠርጉ አብረህ ጠርገሀል….በህመም ስጮህ አዝነህ ስትሸማቀቅ ነበር…በእኩለ ለሊት እንደህፃን ተሸክመህ ሀኪም ቤት ወስደሀኛል…. ሽንት ቤትም ስታመላልሰኝ ነበር፡፡ …አእምሮህ የተወሰኑ ክፉ ነገሮችን አሰቦ ቢፈታተንህም ልብህ ግን መልካምና በፍቅር የተሞላ ስለሆነ ድርጊቶች በአጣቃላይ መልካምና ውብ ነበረ….በዚህም ምስጋናዬ ለዘላለም ነው…፡፡ደግሞ አደረግሽ ላልከኝ ..ምንም ያደረኩት ነገር የለም..እኔ እራሴ የምጠቀምበትን ዕቃዎችና የምበላቸውን ምግቦች ነው የተገዛበት፣ይልቅ አንድ ነገር ላስቸግርህ አስቤያለው፡፡››
‹‹ምንድነው..ምችለው ከሆነ ችግር የለውም… ጠይቂኝ››
‹‹በእኔ እና አንተ መካከል በሚስጥር የሚያዝ ነው››
‹‹እኮ ልስማው››
‹‹ትናንት ለሊት የነገርከኝ ትዝ ይልሀል አባትህ ዕቁብ የገባበትን ምክንያት››
‹‹አዎ ትዝ ይለኛል፡፡››
‹‹እንደነገርከኝ ከሆነ ከእዚህ ቤት ቀጥሎ አንድ ሰርቢስ ሊሰራ ነው….››

‹‹አዎ ይሄ የተቆለለው ብሎኬት ለዛ የተገዛ ነው፡፡ነፍሷን ይማርና እህቴ ነበር የገዛችው…ይሄም አሻዋ እንደዛው፡፡››
‹‹ጥሩ ….ስለዚህ ቀሪ የሚያስፈልገው ነገር ምን ምን ይመስልሀል?››
‹‹ያው ሀያ ቆርቆሮ ..ሚስማር ሲሚንቶ….በራፍ መስኮት..በዋናነት እነዚህ ናቸው የሚያስፈልጉት..ከዛ አባዬ እራሱ ግንበኛም ሀናጢም ስለሆነ የባለሞያ ወጪ የለበትም››
‹‹ስንት ብር የሚፈጅ ይመስልሀል?››
የጥያቄው መአት ውሉ ስላልገባው‹‹ምን አስበሽ ነው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ንገረኝ ስንት ይፈጃል?››
‹‹ለማሰቢያ የሚሆኑትን 5 ደቂቃ ካባከነ በኃላ ብዙ ነው እስከ50 ሺብር የሚፈጅ ይመስለኛል…››
‹‹ጥሩ አንድ ሀሰብ አለኝ..ሁለት ክፍል ቢሆን ግን ጥሩ ነው››
በጭለማ ውስጥ አፍጥጦ አያት..ይህቺ ልጅ ጭንቅላቷን የተመቻችው ከቆይታ በኃላ ተናግቶ አሁን እያቃዣት ይሆን እንዴ ?››ስል አሰበ፡፡
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹አንዱ ክፍል የሚቀጥለው እናንተ ጎረምሶቹ እንድታድሩበት አይደል.?››
‹አዎ ትክክል ነሽ…››
አንዱ አነስ ያለ ክፍል ደግሞ እንዲህ ወደ ዋናው መንገድ ጠጋ ብሎ ቢሰራና በውጭ በኩል በራፍ ቢወጣለት ጥሩ አይደል…?››
‹‹ለምኑ ነው ጥሩ የሚሆነው?››
‹‹አንተ ደግሞ አይገባህም እንዴ ?ለለሊሴ ፀጉር ቤት እንድትከፍትበት ነዋ…ሞያ አላት
….የራሷን አነስተኛ ፀጉር ቤት ብትከፍት እኮ በጣም ድንቅ ነው፡፡››
‹‹በጣም ድንቅ ነው..ግን አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹አዎ ሰላም ነኝ…..ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹ይሄ ሁሉ የምታወሪው የሟች እህቴ እቅድ ነበር..አሁን አንቺ በማይጨበጥ ሀሳብ እንድቃዥ እያደረግሺኝ ነዋ፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይደለም…ነገ ስራ መቅረት ወይም ማስፈቀድ ትችላለህ? ››
‹‹እችላለው…ግን ለምን?››
‹‹100 ሺ ብር እሰጥሀለው..ያልኩህን ሁለት ክፍል ቤት ለመስራት የሚያስፈልግጉትን እቃዎችን በሙሉ ትገዛና አምጥተህ ግቢውስጥ ትዘረግፈዋለህ…ከዛ ጋሼ ትንሽ ይቆጣል ግን ምንም ማድረግ ስለማይችል ቤቱን ወደመስራት ይገባል፡፡››
‹‹እየቀለድሽ አይደለም አይደል፡?››
‹‹እኔ በቤተሰብ ጉዳይ አልቀልድም?››
‹‹መቶ ሺ ብር ብዙ ነው እኮ..?ከየት ታመጫለሽ..?››
‹‹ከዛ የበለጠ ብር አለኝ…እና ደግሞ ካልበቃም…ጌጣ ገጦቼን ብዙ ብር እንደሚያወጡ የነገርከኝ አንተው ነህ…..ቤቱ እንዳለቀ እሱን እንሸጥና የፀጉር ቤት ዕቃዎችንና ማሽኖችን እንገዛበታለን ለሊሴን ሰርፕራይዝ እናደርጋታለን፡፡በዛውም እግረመንገዳችንን የሞች እህትህን ምኞት እውን እናደርግና ነፍሷ ባለችበት አፀደገነት እንድትደሰት እናደርጋለን….ግን እስከዛው ጉዳዩ በእኔ እና በአንተ መካከል ሚስጥር ነው….በል አሁን እግሬን እየጠዘጠዘኝ ነው ወደውስጥ መልሰኝ፡፡››አለችው፡፡
‹‹እሺ..ግን እወቂ በቁሚ እንድቃዥ እያደረግሺኝ ነው…እህቴ በሬዱ ከሞት ተነስታ እያወራች ያለ እየመሰለኝ ነው፡፡››አለና እንዳመጣት አንከብክቦ አቅፎ ወደውስጥ ይዞት ገባ፡፡እሷም ‹‹አዎ ..አሁን እያወራች ያለች እህትህ ነች ..የእሷ ልብ ባይቀይረኝ እኔ እንዲህ አይነት ለሰው አሳቢና ተጨናቂ ሰው አልነበርኩም››ስትል በውስጦ አብሰለሰለች፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

31 Oct, 06:30


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስር
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም …
‹‹ይሄን ያህል ምን ቢመስጥህ ነው?››
‹‹ባክሽ የድሮ መስሪያ ቤቴ..ማለቴ ቆርቆሮ ፋብሪካ ምናምን ብዬ አውርቼሽ ነበር አይደል?››
‹‹እ..ስለምትናፍቅህ ልጅ እያወራኸኝ ነው?››
‹‹አዎ ..ትክክክል?››
‹‹እና እሷ ምን ሆነች?››

‹‹እባክሽ ጠፋች…አንድ ብቸኛ ልጃቸው ጠፋችባቸው…ከዛሬ ነገ አገኛታለሁ ብዬ ስቃትት የእህቴንም ልብ ይዛ ጠፋች››
‹‹ጠፋች ማለት?››
‹‹እኔ እንጃ ..ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ ስለእሷ ነው የሚያወራው››
‹‹ስለጠፋች ብቻ?››
‹‹አዎ አባትዬው ያለችበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዬን ብር በሽልማት መልክ እክፍላለሁ ብሎ ስላሳወጀ ምድረ ድርዬ ጠቅላላ መንገድ ላይ ያገኞትን ወጣት ሴት ሁሉ እያስቆሙ ከእሷ ፎቶ ጋር ማስተያያት ጀመረዋል፡፡››
‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት?››
‹‹እውነቴን ነው…አታይውም እንዴ..?››ብሎ ስልኩን አቀበላት… ማህበራዊ ሚዲያውን የተቆጣጠረውን ሁለት ሶስት ፎቶዋን አየች…ውስጧን በረዳት…ግማሽ ፊቷ በፋሻ የተሸፈነ ቢሆንም አስተውሎ ያያት ሰው ሊለያት ይችላል…ፊቷ የተቀመጠው ፊራኦል እስከአሁን እንዴት እንዳለያት ተደንቃለች፡፡
ስልኩን መለሰችለት‹‹ምን ሆና ይሆን …..?የሀብታም ልጅ ነገር ይሄኔ ቀብጣ ሊሆን ይችላል?››ስትል አፏ ላይ እንደመጠላት ተናገረች፡፡
‹‹አይ እንደዛ እንኳን ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም…እሷ የሀብታም ልጅ ስለሆነች ነገሩ ጮኸ እንጂ በየቀኑ እኳ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚህም እዛም ከያሉበት ተወስደው የሚጠለፉበት…በሰው ሚሊዬን ብር የሚጠየቅበት ሀገር ነው እኮ ያለነው….ስንቶች የተጠለፈባቸውን ልጃቸውን ወይም ባላቸውን ለማስመለስ ቤታቸውን ሸጠዋል…?ስንቶች የመኪናቸውን ሊቭሬ አስይዘው አራጣ ተበድረዋል….?.ንብረቱን አሟጦ ሸጦ ከከፈለስ በኃላ ስንቱ ሬሳ ተልኮለታለል…….እዚህ አገር በዚህ ጊዜ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች እንኳን ለማውራት ለማሰብም ይከብዳ…እና ይህቺ ልጅ ምን እንደገጠማት ማንም የሚያውቅ የለም….፡፡››
‹‹እንዲህ አይነት ነገር መኖሩን አላውቅም››

‹‹እንዴ!! ሀገር ውስጥ እየኖርሽ አልነበረም እንዴ…..?ክፍለሀገር ያለች የእናቱን ሞት ሰምቶ ሄዶ መቅበር ያልቻለ ስንት አለ….?ዘመድ ከዘመድ ከተቆራረጠ እኮ ቆየ፣ስንቱ የትውልድ አካባቢውን ሄዶ ለማየት ልክ እንደአውሮፓና አሜሪካ እንደመሄድ ከባድና የማይቻል ሆኖበታል…እና የዚህች ልጅ ቤተሰብ ጭንቀታቸውን ተመልከቺ…ስንቱን ያስባሉ… እህቴ ብትሆንስ ብዬ ሳስብ ዝግንን ይለኛል…እንደውም በቀደም የሰማሁትን ታሪክ ላጫውትሽ…››
በጉጉት ትኩረቷን ወደእሱ አቅንታ‹‹እሺ እየሰማሁህ ነው..››አለች ፡፡
ከአስር ወራት በፊት አዳማ አካባቢ ካለ አንድ የጠበል ቦታ ታጣቂዎቹ ድንገት ይመጡና የተወሰኑ ሰዎች አፍነው ይወስዳሉ፡፡ከተወሰዱት ውስጥ አንዱ ከአርሲ አካባቢ ነው የመጣው…የተጠየቀውን ብር ወላጆቹ በቀላሉ ማሟላት አይችሉም ቢሆንም ተለምኖና ከየሰው ተለቃቅሞ ከተጠየቀው ሩቡን ያህል ብር ለታጣቂዎች ይላክና የልጁ መለቀቅ ይጠበቃል..ግን ከዛሬ ነገ ይመጣል ሲባል ወራቶች ያልፋሉ፣..እናት እንቅልፍ ታጣለች…ቀንና ለሊት ማልቀስ ይሆናል ስራዋ…ልጇ ይኑር ይሙት የምትጠይቀው ሰውና የምታጣራበት መንገድ አልነበራትም…በመጨረሻ ሰው መፍትሔ ያለውን ይነግሯታል…የሞተ ሰው ነፍስ ጠርተው የሚያናግሩ ሰዎች ጋር ይዘዋት ይሄዳሉ…እንደተባለውም የልጇ ነፍስ ሲጠራ ይመጣል..‹‹አዎ እማዬ እኔ ልጅሽ ከሞትኩ 6 ወር አልፎኛል….እርምሽን አውጪ ይላታል››እናትም ወደቤቷ ተመልሳ ድንኳን ጥላ የልጇን እርም ታወጣለች…ዘመድ አዝማድ ሁሉ ለቅሶ ደርሶ እርማቸውን ያወጣሉ..በጣም የሚገርመው ምፀት ደግሞ ምን መሰለሽ እሷን ለቅሶ ለመድረስ ከሚመጡት የቅርብ ዘመዶቾ ውስጥ ሶስቱ ዳግመኛ በታጣቂዎች ተጠልፈው አረፉት፡፡››
ንግግሩ ይበልጥ ሆድ እንዲብሳት አደረጋት..እንባዋን ሊዘረገፍ ሲተናነቃት ተሰማት..
እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹አባዬ ይሄንን ባይሰማ ደስ ይለኛል…ከሰማ በጣም ነው የሚያዝነው….እሷን ሰፈራቸው ድረስ እየሄደ ከመኪና ስትወርድና ከቤት ስትወጣ እንደሚያያት አውቃለው…ልጄን በውስጧ ይዛለች..እሷን ሳያት ልጄ በከፊልም ቢሆን በህይወት እንዳለች ይሰማኝና እፅናናለው ይላል…ይገርምሻል እኔ እራሱ እንዲዚህ እንዳስብ ተፃዕኖ ያደረገብኝ እሱ ነው››

‹‹ይገርማል ….ግን ጋሼ ምን በሩቅ አሳያቸው ማለቴ እቤት ገብተው ቢያዮት እኮ ሰዎቹ የሚቃወሙ አይመስለኝም፡››
አዎ እንዳልሽው አይቃሙም ይሆናል..ግን አባዬ እኛን ፊት ለፊታቸው ካዩ ይሳቀቃሉ…ልጅቷ ፊት ከቀረብን ማልቀሳችን አይቀርም.. እሷ ፊት ማልቀስ ማለት ደግሞ ልጅቷ ልክ በሌላ ሰው ህይወት እንደምትኖር እንድታስብ ማድረግና ልጅቷን መጉዳት ነው….ሁላችንም ከእሷም ሆነ ከቤተሰቡ በስህተት እንኳን መገናኘት የለብንም ብሎ ቁርጥ ያለ ትዕዛዝ ለሁሉም አስተላልፏል…እኔንም ከዛ ፋብሪካ ስራዬን ጥዬ እንድወጣ ያስገደደኝ በዛ ምክንያት ነው፡፡አሁን አሁን ግን ያንን የእሱን ትዕዛዝ ለመጠበቅ እየተቸገርኩ ባለሁበት ሰዓት ነው…ይሄው አንደምታይው ልጅቷ የጠፋችው…››
‹‹‹በቃ ደከመኝ መሰለኝ ትንሽ ልተኛ ››ብላ አልጋ ልብሱን ወደላይ ሳበችና ሙሉ በሙሉ ተሸፈነችና ..በፀጥታ እንባዋን ዘረገፈች…አባትና እናቷ አሳዘኗት….ቢሆንም ለአመታ ያበሳጮትን ብስጭት ልትረሳላቸው አልቻለችም….በውሳኔዋ ፀንታ እስከመጨረሻው መቆየት እንዳለባት ዳግመኛ ወሰነች፡፡‹‹አዎ አሁን እያዩት ያሉት ስቃይ ይገባቸዋል››በማለት በረጅሙ ተነፈሰች፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

31 Oct, 06:30


////
ሰለሞን በሶስተኛው ቀን አርፍዶ ሶስት ሰዓት አካባቢ ወደቢሮ እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ…የማያውቀው አዲስ ቁጥር ነው…አነሳው፡፡
‹‹ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው፡፡››ድርጅቱን ኪያ ብሎ የሰየመው አስቴርን ለማስደሰት ስለፈለገ ነበር…አስቴር እናቷ ከመሞታቸው በፊት ‹‹ኪያ ›› እያሉ ነበር የሚጠሯት እሱም አልፎ አልፎ ይሄንን ስም ይጠቀማል…ድርጅት ለመመስረት ሲያስብ ግን ወዲያው በምናብ የመጣለት ስም ይህ ኪያ የሚለው ስም ነው፡፡እንደምንም ብሎ አግብቶ ከእሷ ጋር አንድ ቤት መኖር ሲጀምሩ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በወጥነት ኪያ የሚለውን ስም ይጠቃማል..ሚስቱም ሆነ ድርጅቱ በአንድ ስም ይጠራሉ…ይህ ነው እቅዱ፡፡

ሴሎቹ ሁሉ ተነቃቁ…‹‹በስተመጨረሻ ተሳካ…በስተመጨረሻ የመጀመሪያ ደንበኛዬን አገኘሁ….‹‹ሰሎሞን ጀግና ነህ፣›››ብሎ ተደሰተና ድምፁን ጎርነንና ሻከር አድርጎ፡፡‹‹አዎ ትክክል ኖት..ምን ልታዘዝ?፡፡››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እባኮት የቢሮዎትን ትክክለኛ አድርሻ ላስቸግሮት…?››
‹‹ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 3ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 ፡››
‹‹አመሰግናለው ..ከ15 ደቂቃ በኃላ ደርሳለሁ›› ስልኩ ተዘጋ፡፡
እሱ ደግሞ ቢሮ ለመደርረስ 5 ደቂቃ ብቻ ነው የሚቀረው.. ‹‹ቢያንስ የመዘጋጃ 10 ደቂቃ ይኖረኛል›› ሲል አሰበ…‹‹ ደንበኛዬ መጀመሪያ የምትፈልገውን ምክር ሆነ ማንኛውንም አገልግሎት በነፃ ነው የምሰጣት ..ክፍያ አልቀበልም….››ሲል ወሰነ ፡፡መልሶ ደግሞ ሀሳቡን ቀየረ‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም….የእኛ ሰው ላልከፈለበት ነገር የሚሰጠው ዋጋ ትንሽ ነው….ምክሬን ከልቧ ሰምታ ተግባራዊ ለማድረግ የምትሞክረው ገንዘብ ካወጣችበት ብቻ ነው….ስለዚህ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያማ ላስከፍላት የግድ ነው…አዎ የተወሰነ አስከፍላታለው.፡፡››ሲል ውሳኔውን አሻሻለ፡፡.ቢሮው ደረስና ከፍቶ ገባ….፡፡የተዝረከረኩ ነገሮችና የተቀዳደቁ ወረቀቶችን አነሳሳና አስተካከለ…ቢሮው ሁለት ክፍል ሲሆን የመጀመሪያውን የፊት ለፊቱን በመተው ወደ ውስጠኛው አለፈና ወንበሩ ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠ፣ሌላ ነገር ለማሰብ ከመጀመሩ በፊት በራፉ ተቆረቆረ…..ድምፀን ከፍ አድርጎ ከመቀመጫው እየተነሳ ወደፊት ለፊቱ በራፍ እየተራመደ ‹‹ይግቡ ››አለ.. በራፉ በስሱ ተከፈተና አንድ አንገተ መቃ ጠይም ወጣት ታየችው….ሙሉ በሙሉ ከፍታ ወደውስጥ ገባች….፡፡ስሯ ደረስና እጁን ለሰላምታ ዘረጋ፡፡
‹‹ሰለሞን ገብረየስ›› እባላሁ፡፡
‹‹ለሊሴ ለሜቻ ›› ስሟን አስተዋወቀችውኝ፡፡
‹‹ግቢ ››አለና ወደ ውስጠተኛው ክፍል እመራ.. ዞሮ ወንበሩ ላይ ተቀመጠና ከፊት ለፊቱ እንድትቀመጠ ጋበዛት..ተቀመጠች፡፡

‹‹እሺ ምን ልታዘዘዝ…?እዚህ ቤት ውስጥ ያለነው እኔና አንቺ ብቻ ነን..እዚህ የምንነጋገርነው ነገር እስከመጨረሻው በእኔና አንቺ መካከል ሚስጥር ሆኖ ተቀብሮ የሚቀር ስለሆነ ሁሉንም ነገር ያለምንም መሳቀቅና ይሉኝታ ንገሪኝ …ከዛ መፍትሄ እንፈልጋለን….››
የልጅቷ አይኖች ፈጠጡ….ግራ በመጋባት ..‹‹‹ይቅርታ….እህትህ ነች የላከችኝ፡፡››አለችው
‹‹እህትህ የእኔ ?ለምን፡፡››ግራ መጋባቱ የእሱ ተራ ሆነ.፡፡
‹‹ፀሀፊ ይፈልጋል ብላኝ ነው››
‹‹ኦ……ገባኝ››የንዴት ሳቅ ሳቀ፡፡
ባልጠበቀችው ሁኔታ ቀጥታ ወደገደለው ገባላት‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ ጥሩ፣ስራ መች መጀመር ትችያለሽ?››
‹‹ነገ››
‹‹ጥሩ በቃ››
‹‹በቃ…ማለቴ ሌላ የምትጠይቀኝ ነገር የለም?››
‹‹እኔ እንጃ ምን እጠይቅሻለው…..?አንቺ የምትጠይቂኝ ጥያቄ አለሽ?››
‹‹አዎ… ስንት ትከፍለኛለህ?››
‹‹ስንት እንድከፍልሽ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አራት ወይም አምስት ሺ ብትከፍለኝ ደስ ይለኛል፡፡››
‹‹ለመጀመሪያ የሶስት ወር የሙከራ ጊዜ አራት ሺ ብር ከፍልሻለው…ከዛ በኃላ ደግሞ አብረን እናየለን….ሌላ ይያቄ አለሽ …?››
‹‹የለኝም፡፡››
ኪሱ ገባና ቁልፍ መያዣውን አውጥቶ ከውስጡ የቢሮውን ትርፍ ቁልፍ አወጣ‹‹.ይሄው የቢሮ ቁልፍ..የስራ መግቢያ ሰዓት 2.30 ነው….ነገ ስመጣ ቢሮ ከፍቶ መግት አይጠበቅብኝም ማለት ነው?፡፡››አላት፡፡

‹‹አዎ ትክክል ››አለችና ቁልፉን ይዛ ለመሄድ ተነሳች፡፡
‹‹ይቅርታ ነገ ሰራተኛ ሆኜ ስራ ከመጀመሬ በፊት ዛሬ እንደ ደምበኛ አገልግሎት ማግኘት እችላለሁ…?.››
ጥያቄዎ አስደምሞት በትኩረት አያት፡፡‹‹ቁጭ በይ›› አላት፡፡ተመልሳ ቁጭ አለች፡፡
‹‹እሺ እየሰማሁሽ ነው፡፡››
‹‹የጋብቻ ጉዳይ ሳይሆን የፍቅር ጉዳይ ነበር››
‹‹ገባኝ››
‹‹ሁለት አፈቀርንሽ ብለው እንዳገባቸው እየጨቀጨቁኝ ያሉ ወንዶች አሉ…ከሁለቱም ጋር ከሁለት አመት በላይ እውቂያ አለኝ፡፡አንዱ የተማረ እስማርት የሚባል የመንግስት ሰራተኛ ነው…የመንግስት ሰራተኛ ነው ስልህ ያው ይገባሀል አይደል…ከወር እስከ ወር ያለውን ወጪ ለመሸፈን የሚቸገር አይነት ሰው ነው..ሁለተኛው ነጋዴ ነው…ደህና ድርጅት አለው
….ሁለቱም እንዳገባቸው ጠይቀውኛል ..የትኛውን እሺ ማለት እንዳለብኝ ግራ ተጋብቻለው…..እንዴትና በምን አይነት መስፈርት ነው መምረጥ የምችለው?››
‹‹የትኛውን ይበልጥ የምትወጂው ይመስለኛል…?››
‹‹እኔ እንጃ ከመንግስት ሰራተኛው ገር ስሆን በጣም ዘና እላለሁ..ቀልዶቹ ያስቁኛል
….ነጋዴው ደግሞ የፈለኩት ቦታ ወስዶ ያዝናናኛል..ጥሩ ጥሩ ስጦታ በመስጠት ያስደስተኛል….ግን ንግግሩ ደረቅና የጠነዛ ነገር ነው…ግራ ተጋብቻለው…አንዳንዴ ሁለቱ ተጨፍለቀው አንድ ሰው ቢሆኑና እሺ ብያቸው በተገላገልኩ እላለው፡፡››
ለተወሰነ ደቂቃ አሰበና መናገር ጀመረ‹‹እንግዲህ ይህንን ችግርሽን ለመፍታት ሶስት ወር የተከፋፈለ የቤት ስራ እስጠሸለሁ፡፡
‹‹ሶስት ወር ሙሉ አልበዛም?››
አይ አልበዛም…ለእድሜ ልክሽ አብሮች የሚኖረውን ሰው እኮ ነው የምትመርጪው
….ፍቅረኛ ብቻ ሳይሆን የዕድሜ ልክ ባልሽን ነው የምትመርጪው… ጓደኞችሽ እና

ወዳጆችሽ ፊት ይዘሽው ምትሄጂውን ሳይሆን ከቤተሰቦችሽ ወስደሽ ምትቀላቀይውን ሰው ነው የምትመርጪው….እና ደግሞ ያንቺን ባል ብቻ ሳይሆን ነገ ለምትወልጃቸው ልጆችም አባት የሚሆነውን ሰው ነው እየመረጥሽ ያለሽው፣እና እዚህ ጉዳይ ላይ ሶስት ወር አይደለም ሶስት አመትም ብታሳልፊ እንደብክነት የሚቆጠር አይደለም…..ግን እንዲህ ስልሽ ይሄን ሁሉ አድርገንም ይንን ሁሉ ጊዜ አባክነንም ፍፅም ትክክለኛውን ሰው መምረጥ እንችላለን ለማለት አይደለም….የፍቅር ጓደኛ በመምረጥ ሂደት ውሥጥ ፍጽም ትክክል የሚባል ምርጫ የለም…ግን በብዙ መስፈርት ሲለካ የተሻለውን መምረጥ እንችላለን..እና ለዛ ሶስት ወር አይበዛም፡፡
‹‹አሳምነሀኛል…የማደርገውን ንገረኝ፡፡››አለችው፡፡
በመጀመሪያ ወር አንደኛውን ምረጪና ከእሱ ጋር ብቻ ተገናኚ…ሌላውን የሆነ ምክንያት ስጪውና ሙሉ በሙሉ ግንኙነት አቋርጪ…. በስልክም ቢሆን አታግኚው፣ፎቶውንም ቢሆን እንዳትመለከቺ ….ሙሉ ትኩረትሽን አንደኛው ላይ ብቻ አድርጊ….ልክ ወሩ ሲያልቅ ይሄኛውን በተመሳሳይ ከግንኙነት ውጭ አድርጊውና ከሌለኛው ጋር ተገናኚ…በሶስተኛው ወር ደግሞ ሁለቱንም ሳታገኚ ለብቻሽ አሳልፊ፣ስለሁለቱም በጽሞና አስቢ …ከዛ አብረን እናወራበታለን፡፡››
‹‹ጥሩ ይመስላል ..አዎ እንዳልከኝ አደርጋለሁ…..አዎ እንደዛ ባደርግ ጥሩ ይመስለኛል….ግን በጣም የተቸገረች ጓደኛዬ ነበረች..ምን የመሰለ ትዳሯ ሊፈርስባት ነው…እባክህ እርዳት ቆይ እንደውም ልደውልላለት..››አለችን ስልኳን አንስታ እየደወለች መቀመጫዋን ለቃ ወደውጭ ወጣች፡፡
ሰሎሞን‹‹ዋው የመጀመሪያ ኢትዬጵያዊት ደንበኛዬን ኢንፕረስ አደረኳት ማለት ነው…››ሲል አሰበና .ደስ አለው ..፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

31 Oct, 06:30


ስልክን አናግራ ተመልሳ መጣች…‹‹ጓደኛዬ ነገ መምጣት ትችላለች..?እባክ ችግሯ በጣም አጣዳፊ ስለሆነ እንደምንም ጊዜህን አሸጋሽገህ አግኛት፡፡››ተለማመጠችው፡፡
‹‹ነገ ምንም ደንበኛ የለኝም በፈለግሽው ሰዓት ቅጠሪያት››
‹‹አመሰግናለው…አራት ሰዓት ትመጣለች..በቃ ቸው..ጥዋት እንገኛን ››ብላ ለመሄድ መንገድ ከጀመረች በኃላ ወደኃላ ዞራ..‹‹ይቅርታ ክፍያውን ዛሬ ስላላያዝኩ ነው…..ነገ ይዤ መጣለው››
‹‹ችግር የለውም…ሲሳካ ምሳ ትጋብዢኛለሽ ››አላት

‹‹አመሰግናለው››ብላ በደስታ እየሳቀች ወጥታ ሄደች፡፡

ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

30 Oct, 07:18


ጋር እየተጋገዙ ወደውስጥ አስገቡ….ከገዛችው ዕቃዎች ውስጥ ለበፀሎት አዲስ አንሶላዎች
…ምቾት ያለው ብርድልብስ ፣ቢጃማ ..ሸበጥ ጫማ..ቅባት…ፓንቶች..ብቻ ያስፈልጋታል ያለችውን እና በእይታዋ የገባላትን ዕቃ ሁሉ ገዝታ ነበር..ከዛ የቤት አስቤዛ አትክልቱን..ፍራፍሬውን..ፓስታ ..መኮሮኒ..ስጋና የመሳሰሉትን እልክ የታጋባች ይመስል ቤቱን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በቁሳቁስ ሞላችው…፡፡
አቶ ለሜቻ ዶክተሩን ሸኝተው ሲመለሱ ትተው የሄዱት ሳሎን ሌላ መልክ ይዞ ሲጠብቃቸው ከመደንገጣችው ብዛት ባሉበት ደርቀው ቆሙ….
‹‹ሊሊሴ ምንድነው ይሄ ሁሉ?››
‹‹አየህ አባዬ አንሶላው አያምርም… ብርድ.ልብሱስ….?.የሄው ቢጃማም ገዛሁላት…››
‹‹ጥሩ አደረግሽ…ብሩን ከየት አመጣሽው?››
‹‹እኔማ ከየት አመጣለው….እራሶ ሰጥታኝ ነው፡››አለች ወደበፀሎት እየጠቆመች፡፡
‹‹ይሄንን ካሮት፤ ቆስጣ ፤ስጋ ፤መኮሮን ይሄን ሁሉ በእሷብር ነው የጋዛሽው ››
‹‹አዎ አባዬ››
‹‹እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ለሊሴ…?ችግር ላይ ካለች ልጅ እንዴት? ››
‹‹ጋሼ እኔ አስገድጄያት ነው…..ያው ለእኔው እኮ ነው… ደህና ደህና ምግብ ካልተመገብኩ ከስብራቴ ቶሎ አልድንም..ውጌሻዋ ያለችውን አልሰማህም፡፡››
‹‹ቢሆንም ..ይሄው እኔ እኮ ለአስቤዛ የሚሆን ብር ይዤ መጥቼለው ››አሉና እጃቸውን በወደኪሳቸው ሰዳው የተወሰኑ ድፍን ብሮችን አውጥተው ዘረጉ
በፀሎት እንባዋ ካለፍቃዶ ዘረገፈች…ይገርማል ወላጆቾ ቤት እያለች ዘወትር የምታለቅሰው በእነሱ ጥል እና ጭቅጭቅ በመበሳጨት ነበር..እዚህ ቤት እግሯ ከረገጠ ጀምሮ ግን እንባዋ የሚረግፈው በመሀከላቸው በምታየው ፍቅርና ለእሷ በሚያደርጉላት እንክብካቤ ስሜቷ እየተነካ ነው…ሰው ለሀዘንም ለደስታም እንዴት ተመሳሳይ ምላሽ ይሰጣል..?‹‹ጋሼ እኔ በጣም ብዙ ብር አለኝ …ችግሬ ብር አይደለም..ከእናንተ የምፈልገው ፍቅር ብቻ ነው……››

‹‹ይሁን እስኪ ..ግን እንዲህ መሆን አልነበረበትም.››.እያሉ ከቆሙበት ተንቀሳቀሱና ወደውስጥ ዘልቀው ፊት ለፊት ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጡ፡፡ወ.ሮ እልፍነሽና ለሊሴ አስቤዛውን ተጋግዘው ወደ ጓዲያ ወሰዱት፡፡
አቶ ለሜቻ ማውራት ጀመሩ…‹‹ምንም ነገር ከፈለግሽ ለእኔ ለአባትሽ ንገሪኝ..በስልክ እድንጠራልሽ የምትፍጊው ሰው ካለም…..ችግር የለው››
‹‹ጋሼ ሙሉ በሙሉ እስከምድን ድረስ ከማንም ሰው ጋር መገናኘት አልፈልግም..ደግሞ እመነኝ እኔ በመጥፋቴ ማንም የሚያስብ ሆነ የሚጨነቅ ሰው አይኖርም….እንደውም ጠፍታለች ሳይሆን ለሆነ ስራ የሆነ ሀገር እንደሄድኩ ነው የሚያስቡት..ከዚህ በፊትም ሁለት ሶስቴ አድርጌዋለው››
ከመቼ ወዲህ እንዲህ ውሸታም እንደሆነች ለራሷም ግራ ገባት ፡፡አሁን የት ሄደሽ ነበር ቢሏት የት ልትል ነው?፡፡ለመዝናናት ካልሆነ ለመኖር ወይም ለተወሰነ ጊዜ ቆይት ከአዲስአባባ ውጭ እግሯን አንስታ አታውቅም…ስለየትኛውም ሌላ ከተማ የጠለቀ እውቂያ የላትም..ብቻ ከቤሰተቦችሽ ተገናኚ እያሉ እንዳያጨናንቋት ማድረግ ያለባት እንደዚህ እንደሆነ በውስጧ አምናለች፡፡
‹‹ይሁን..እንግዲያው …እኛ አለንልሽ..አይዞሽ…ግን እንዲህ ብርሽን አታባክኚ… ስትድኚ በጣም ያስፈልግሻል ››
‹‹አይ ጋሼ..ስለእኔ አታስብ..እናቴ ብዙ ብር ጥላልኝ ነው የሞተችው…ባንክ በቂ ብር አለኝ፡፡››
‹‹ይሁን ልጄ..ብር ግን አያያዙን ካላወቁበት ስር የለውም..ሲታይ ብዙ የመሰለ ብር ከእጅ በኖ ሲጠፋ ቀናት አይፈጅበትም ››
‹‹ገባኝ….፡፡››
‹‹እሺ በቃ… አሁን አረፍ በይ..ሰፈር አንዲት ለቅሶ አለች… ደረስ ብዬ መጣሁ››
‹‹እሺ ጋሼ››
ወጥተው…ሄዱ…እሷም ወደትካዜዋ ገባች፡፡

ድንገት በቀኝ በኩል ወደአለው ግድግዳ ቀና ብላ አይኗን ስትተክል ግዙፍ ፎቶ ላይ ፈዛ ቀረች…የበሬዱ እንደሆነ እርግጠኛ ነች….
ከንፈሯቾ በፀደይ ወራት ለመበላት እንደደረሰ የጎመራ ብርቱካን ይመስላሉ…ስስ ነው በጣም ስስ..የሚገመጥ ሳይሆን የሚመጠጥ አይነት እና ደግሞ ጠባብ ነው ጠባብ የሚስጥር በር መሳይ ጠባብ፡፡አይኖቾ ብርሀናቸውን ከከዋከብት የተዋሱት ይመስላል
…አፍንጫዋ ዝንፈት በሌለው የሂሳብ ስሌትና ትንግርት በሚያበስር የስነ.ከዋክብት ትንቢታዊ ጥበብ እንደተሰራ የግብፃችን ፕራሚድ አይነት ነው፡፡ፀጉሯ ምድረ አራዊት ሁሉ ተሰብስበው የሚኖሩበትና አማዞን ደን መሰል ነው፡፡እንዲህ ፎቶዋ ሲታይ ይሄ ቢሰተከካከል ብሎ ምንም እንከን ወይም ጉድለት ሊገኝበት የማይችል አይነት ነው፡፡
‹‹ሞት ግን ምንድነው?›› እራሷን ጠየቀች….ሞት በቀላሉ ጭሩሱኑ ባይኖር ብለን የምናማርረው ነገር አይደለም…ሞት ባይኖር ምድር የበለጠ የምትሰለች አስቸጋሪና አስጨናቂ ስፍራ ትሆን ነበር…ስለዚህ ሞት የህይወትን ያህል እጅግ አስፈላጊ የአምላክ ስጦታ እንደሆነ ታምናለች ይሁን እንጂ ሰው ደግሞ የህይወትን ጫፍ እንኳን ሳያይ እንዲህ በጨቅላ እና በለጋ ህይወቱ ሲቀጠፍ ያሳዝናል..‹‹በተለይ ለወላጆቾ እና ለሚያፈቅሯት ሰዎች ይሄንን እውነት መቀበል በጣም ከባድ ነው፡፡››ስትል አሰበች
‹‹አንቺ ሞተሸ አልሞትሽም ዋናው አንቺነትሽ ለእኔ ህይወት ሰጥቶኛል….የአንቺ ልብ ከእኔ ማንነት ጋር ከተዋሀደ በኃላ ቀይሮኛል፡፡››ስትል በውስጧ አጉረመረመች፡፡ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም …
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

30 Oct, 07:18


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ዘጠኝ
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
አቶ ኃይለ መለኮት እቤታቸው ባለ የገዛ ቢሯቸው ውስጥ ተሸከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠዋል…በቀኝ እጃቸው የሚያብረቀርቅ ማካሮብ ሽጉጣቸውን ይዘው ፊታለፊታቸው ያሉት ሶስት ግለሰቦች ላይ በየተራ እያነጣጠሩ ምላጩን በስሱ እየዳበሱ ይናገራሉ
‹‹በመጀመሪያ ማንን ልግደል?››
‹‹ጌታዬ ይቅር ይበሉን…አጥፍተናል….››

‹‹አጥፍተናል….ጥፋት እኮ በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ስህተት የሆነ ድርጊት ስታደርግ ነው፡፡ለምሳሌ እዚህ መኖሪያ ቤቴ ላይ ጋዝ አርከፍክፈህ ክብሪት በመለኮስ ግማሹን ህንፃ ብታወድመው ጥፋት አጥፍተሀል ብዬ የጠየቅከውን ይቅርታ ልቀበልህ እችላለው፡፡ ምክንያቱም እቤቱን አሁን ካለበት ይዘት ይበልጥ አስውቤ ከእንደገና ላስገነባው እችላለሁ…ወይም ከፋብሪካዎቼ ትልቁን መርጠህ ሙሉ በሙሉ ብታወድመው እንደጥፋት ቆጥሬ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው…ወይንም ሽጉጥህ ባርቆብህ ቀኝ እጄን ብትመታኝና በዛ የተነሳ እጄ ቢቆረጥ አዎ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው፡፡ግን አሁን ምንም አላስቀረህልኝም፡፡ልጄ ሁለ ነገሬ ነች…ምንም መተኪያ ምንም ማካካሻ የላትም…ያ ማለት ይቅርታ ላደርግላችሁ ፈፅሞ አልችልም.››
‹‹ጌታዬ ይገባናል፣ አንተ ትክክል ነህ..ግን ቢያንስ በፍለጋው ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው….የሆነ ትንሽ ቀን ጨምርልንና አቅማችንን አሟጠን እንፈልጋት… የሆነ ያህል ጊዜ ስጠን… ካልተሳካልን ያሰብከኸውን ታደርጋለህ፡፡››
‹‹አዎ እሱማ አደርጋለው….ዋጋማ ትከፍላላችሁ….አሁን የምናደርገው…..››ንግግራቸውን ሳያጠናቅቁ ስልካቸው ጠራ…የደቀኑትን ሽጉጥ ሳያወርድ ስልኩን አንስተው ማውራት ጀመሩ፡፡
‹‹እሺ…ጥሩ …ሶስቱም ነው እይደል… በጥንቃቄ ጠብቋቸው››
ስልኩን ከዘጉ በኃላ ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹ስልኩ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ…?የእናንተ የሁለታችሁን አንዳንድ ልጃችሁን ያንተን ደግሞ ምትወዳትን ሚስትህን አሳግቼቸዋለው…ልጄ በሚቀጥሉት ሶስት ቀን ውስጥ ተገኝታ ወደቤቷ ካልተመለሰች ያው የምወዳትን ልጄን ስላሳጣችሁኝ ለዛ ክፍያ የምትወዱትን ሰው ታጣላችሁ ማለት ነው፡፡››ሲል ሰቅጣጭ መርዶ አረዷቸው፡፡
ሶስቱም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ ሲኦላዊ ነበር፡፡፡አቶ ኃይለልኡል ሰዎቹን ከቢሮቸው አሰናብተው ሽጉጡን ወደመሳቢያው ውስጥ መልሰው በማስቀመጥ ቆለፉበትና ወጥታው ወደ ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ መኝታ ቤት ሄዱ ….ሚስታቸው አልጋው ላይ ተሰትረው ጉልኮስ ክንዳቸው ላይ ተሰክቶ እህህ እያሉ ነው..ለዘመናት ወደዋቸው የማያውቁት ባላቸውን ድምፅ ሲሰሙ የከደኑትን አይን ገለጡ እና በመከራም ቢሆን ከንፈራቸውን አነቃነቀው ማውራት ጀመሩ

‹‹ኃይሌ…ልጃችን አልተገኘችም?››
‹‹አይዞሽ አታስቢ ..ትገኛለች….አንቺ ምንም አትጨነቂ››ሊያፅናኗቸው ሞከሩ፡፡
‹‹እንዴት አልጨነቅ…?በዚህ አለም ላይ ያለቺኝ እሷ ብቻ ነች..በህይወቴ ሙሉ የበደልከኝን በደል እንድረሳልህ…የሰራህብኝን ስራ ይቅር እንድልህ ከፈለክ ልጄን አግኝልኝ….ልጄን ካገኘህልኝ ያልከኸውን ሁሉ አደርግልሀለው….እንደውም ምንም ሀብት ሳልካፈልህ እፈታሀለው…እፈታህና ገዳም እገባለው..አዎ ልጄ ሰላም መሆኗን ካረጋገጥኩ ከህይወትህ ዞር እልልሀለው››
‹‹አረ ተይ …ለእኔም ልጄ እኮ ነች…እሷን ለማግኘትና ወደቤቷ ለመመለስ ከአንቺ ጋር ይሄንን አድርጊልኝ እያልኩ የምደራደር ጭራቅ ነገር እመስልሻለው….?ተይ እንጂ..አሁን ወጣ ብዬ ፖሊሶቹ ምን ላይ እንደደረሱ መጠየቅ አለብኝ..ሀኪሞቹ ሚሉሽን ስሚና ጤናሽን ተነክባከቢ..ልጃችን ስትመጣ እንደዚህ ሆነሽ እንደታገኚሽ አልፈልግም…እናቴ በእኔ ምክንያት ሽባ ሆነች ብለ መፀፀት የለባትም››ብሎ ወጥቶ ሄደ…..
///
በፀሎት ከእንቅልፏ የባነነችው በቤቱ ውስጥ ግርግር እና የብዙ ሰው ድምፅ ስትሰማ ነበር..አይኖቾን ስትገልጥ ግን ያሰበችውን ያህል ብዙ ሰው አልነበረም ነበር…ወ.ሮ እልፌ
፤አቶ ለሜቻና አንድ ሙሉ ሱፍ የለበሰ ጎልማሳ ሰው ነበር በቤቱ ያሉት….ግን ያ ጎልማሳ ሰው ሲያወራ ድምጹ መመጠኛው እንደተበላሸበት ማይክራፎን ከጣሪያ በላይ ይጮኸ ስለነበረ የብዙ ሰው ድምጽ ይመስላል….
አይኗን ስትገልጥ አየና ወደእሷ ተጠጋ.‹‹ልጄ ተነሳሽ..?ጥሩ …ይሄ ዶክተር ታፈሰ ይባላል..የጓደኛዬ ልጅ ነው….አንቺን እንዲያይልኝ አስቸግሬው ነው፡፡›››አቶ ለሜቻ ናቸው ተናጋሪው፡፡
‹‹አባቴ ዝም ብለህ ነው እኮ የተቸገርከው..ደህና ነኝ እኮ››
ከወ.ሮ እልፍነሽ ጋር በተስማማችው መሰረት ቢሻክራትም አንቱታውን በአንተ ቀይራ ማውራት ጀመረች…
‹‹ደህና መሆንሽና አለመሆንሽን እኔ ሀኪሙ አይቼ ብወስን አይሻልም›› ዝም አለችው….
ወደእሷ ተጠጋና አያት…ግንባሯና ከፊል ፊቷ በስነስርአት መታሸጉን አረጋገጠና ..አንድ መርፌ በክንዷ ወግቷት መድሀኒት አዘዘላት…
‹‹በቃ ጋሼ..የወንድሞት ልጅ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች..ቁስሉ ጊዜውን ጠብቆ ፋሻው ተነስቶ በደንብ ፀድቶ ከእንደገና መታሸግ አለበት…›››
‹‹ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም እያልከኝ ነው?››
‹‹አይ የለም ሰላም ትሆናለች..ግን ምን አልባት ፊቷ ላይ ጠባሳ ሊሆንባት ይችላል፡፡››
‹‹ያንን ማስቀረት አይቻልም?››አቶ ለሜቻ ጠየቁ፡፡
‹‹ያው የቆዳ ስፔሻሊስቶች ያስተካከሉታል..በአሁኑ ጊዜ ብር ካለ የማይስተካከል ነገር የለም..ዋናው በህይወት መትረፏና አካለ ጎዶሎ አለመሆኗ ነው…የጠባሳው ነገር የገንዘብ ጉዳይ ነው… ይስተካከላል፡፡››
‹‹ይሁን እንግዲህ…….አንተንም አስቸገርኩህ››
‹‹አረ ጋሼ…ለርሶ ባልታዘዝ አባቴ አያናግረኝም….በማንኛውም ሰዓት ካመማት ደውሉልኝ..አሁን ልሂድ….፡፡እግዜር ይማርሽ እህቴ››
‹‹አመሰግናለው ዶ/ር፡፡››
‹‹ዶ/ር አቶ ለሜቻን አስከትሎ ቤቱን ለቆ ወጣ ..ክፍል ውስጥ ወ.ሮ.እልፍነሽና በፀሎት ብቻ ቀሩ፡፡
‹‹ጋሼ ዝም ብሎ እኮ ነው የሚጨነቀው?››
‹‹እሱ..እንዲሁ ነው….ታያለሽ ነገ ደግሞ ሌላ ዶክተር ለምኖ ይዞ ይመጣል..እስክትድኚ እረፍት አይኖረውም››
አቶ ለሜቻ ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት ለሊሴ ከሄደችበት ተመልሳ መጣች፡፡ ይዛ የመጣችው ዕቃ ግን የሳሎኑን ግማሽ የሸፈነ ነበር….ከአምስት በላይ ፔስታል ከባለታክሲው

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

29 Oct, 07:00


youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

29 Oct, 07:00


‹‹ያው የተገኘውን ነዋ….ከሁለት አመት በፊት ነው ከተግባረእድ በፀጉር ስራ የተመረቀችው…..አፈሩን ገለባ ያድርግላትና ሁለት አመት ከፍላ ያስተማረቻት ሟች እህቷ ነበረች…የሆነ ቤት ተቀጥራ ለአንድ አመት ሰርታ ነበር ፡፡አልተስማማችም መሰለኝ ሰሞኑን ለቀቀች ….አሁን ሌላ ቦታ እየፈለገች ነው፡፡ አንድ ወዳጇ ፀሀፊነት አግኝቼልሻለው ብላት ያንን ለማረጋገጥ ነው የሄደችው፡፡››
የሞቿ ስም ሲጠራ እንደተለመደው የበፀሎት ሰውነት ሽምቅቅ አለ‹‹ግን እቤታችሁ ፊት ለፊት ነው….የሆነች ትንሽ ክፍል ቢኖር እኮ የራሷን ስራ ብትሰራ ጥሩ ነበር››

‹‹እሱማ እንዳልሽው ጥሩ ነበር …ልጄ ግን ቀላል ይመስልሻል…?ለእኛ ያንን ማድረግ ከባድ ነው፡፡እህቷ ልክ አሁን አንቺ እንዳልሺው አይነት እቅድ ነበራት…ተምረሽ ስትጨርሺ ከምሰራበት ባንክ ተበድሬም ቢሆን የራስሽን ፀጉር ቤት ከፍትልሸለሁ ብላ ቃል ገብታላት ነበር…ልጄ ቃሏን የምታጥፍ ሰው አልነበረችም……››እንባቸው በአይናቸው ግጥም ብሎ ረገፈ….አብራ አለቀሰች…እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከሩ ንግግራቸውን ካቆሙበት ቀጠሉ‹‹እንዳልሺው…እንደምንም እቤቱን ብንሰራላት እንኳን ማሽኑን ከየት መጥቶ ይገዛል…..እንዳልሽው ግን አንድ ቀን እንደዛ ማድረጋችን አይቀርም…››በትካዜ መለሱላት፡፡
‹‹እማዬ››
‹‹አቤት ልጄ››
‹‹የሆነ ቦርሳ ነበረኝ አይደል..?››
‹‹አዎ አለሽ ..ላምጣልሽ?››
‹‹አዎ ካላስቸገርኮት››
‹‹የምን መቸገር አመጣሽብኝ..አመጣልሻለሁ››አሉና የበላችበትን እቃ ከተቀመጠበት አንስተው ወደውስጥ በመግባት ከደቂቃዎች በኃላ ቦርሳውን አንጠልጥለው አመጡና ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላት፡፡
ዚፑን ከፈተችና ከላይ ያሉትን ሁለት ጅንስ ሱሪ…ሁለት ቲሸርቶች አወጣችና አልጋ ላይ አስቀመጠች….ከዛ በኃላ ያለውን እስር እስር ባለሁለት መቶ ኖት ብር ነው…ስንት ብር እንደሆነ አታውቅም …በተለያየ ጊዜ ዝም ብላ ቁም ሳጥኗ ውስጥ እየወረወረች ያጠራቀመችው ገንዘብ ነው..ምን አልባ ሶስት ወይም አራት መቶ ሺ ብር ይሆናል፡፡አንዱን እስር አወጣችና ልብሱን መልሳ ከታ.. ዚ..ፑን ዘጋችና ከራስጌዋ አስቀመጠችው…
‹‹እማዬ..››
አቀርቅረው ሲኒ እያጠቡ ነበረ ..ስትጠራቸው ቀና አሉና‹‹አቤት ልጄ.. ጠራሺኝ?››አሉ
‹‹እንኩ ይሄንን ብር››
ለደቂቃዎች ያህል ክው ብለው አዮት…‹‹ምን እያልሽ ነው ልጄ?››

‹‹ለቤት አንዳንድነገር ይግዙበት….››
‹‹እንዴ ይሄን ሁሉ ብር?››
‹‹ትንሽ እኮ ነው…ሀያ ሺ ብር ነች››
ፈገግ ብለው ‹‹አይ ልጄ… ሀያ ሺ ብር እኮ በአንድ ጊዜ እንዲህ ከነክብሩ እዚህ ቤት ገብቶ አያውቅም..በይ መልሺው…..ከህመምሽ ስታገግሚ ያስፈልግሻል፡፡››
‹‹አይ አያስፈልገኝም…››
‹‹አይ ልቀበልሽ አልችልም….ለሜቻስ ዝም ሚለኝ ይመስለሻል?››
ከጎኗ ያስቀመጠችውን ሻንጣ መልሳ ሳበችና ዚፕን እስከመጨረሻው በመክፈት.. ከነልብሱ ዘቅዛቃ ፍራሹ ላይ ዘረገፈችው….
ወ.ሮ እልፍነሽ በህልማቸው እንኳን አይተው የማያውቁት አይነት የብር ቁልል እየተመከቱ ነው..ያለፍቃዳቸው የተከፈተውን አፋቸውን መልሰው መክደን አቃታቸው፡፡
‹‹አዩ አይደለ….ይሄ ሁሉ ብር አለኝ….ደግሞ አዩት ይሄንን ሀብልና የጆሮ ጌጥ ብዙ መቶ ሺ ብር የሚያወጣ ነው..ከቸገረኝ እሸጠዋለው….እና ይሄንን ብር ይቀበሉኝና እቤት ውስጥ የጎደለውን ነገር ያሟሉበት….ደግሞ እናንተ ማለት እግዚያብሄር ለእኔ የሰጣችሁ ስጦታዎቼ ናችሁ …እንኳን ብሬን ህይወቴን እሰጣችኃላው፡፡የተገለበጥኩት መንገድ ላይ ወይም ሌላ ሰው ጊቢ ቢሆን አኮ…እንኳን ብሬን ህይወቴን እንኳን ማትረፍ አልችልም ነበር…እዛው ሳጣጥር ገድለው ቀብረውኝ ..ገንዘቡን በሙሉ ይወስዱት ነበር፡፡››
‹‹በስመአብ በይ ልጄ ….ተይ ተይ…››
‹‹እውነቴን ነው….እናንተ ሻንጣውን እንኳን ምን እንዳለበት ከፍታችሁ አላያችሁትም››
‹‹የሰው ዕቃ ያለፍቃድ እንዴት ይታያል …?.ነውር አይደለ እንዴ?››
‹‹እኮ እኔም ለማለት የፈለኩት ያንን ነው..በዚህ ዘመን ነውር የሚባል ነገር ጠፍቷል…ሰው ቁስአምላኪ ሆኗል….እምነት ..ሀቀኝነት ..ክብር …እውነት ….የሚባሉ ቦዶ ቃላት ሆነዋል››
‹‹ካልሽ እሺ ልጄ……ለሜቻ ግን ምን ብዬ እንደማስረዳው አላውቅም››

‹‹ግድ የሏትም ጋሼን እኔ አሳምናቸዋለሁ፡፡››
ብሩን ተቀበሏትና..‹‹ልጄ እቤቴን እንዲህ እንደሞላሽው ላንቺም የሞላ ህይወት ይስጥሽ..››አይናቸውን ግድግዳው ላይ ወደተሰቀለው የሞች ልጃቸው ፎቶ ላኩና ፍዝዝ ብለው‹‹ልጄ እንዲህ ድንገት መጥታ መአት ብር እጄ ላይ በማስቀመጥ ..እማዬ የሚያስፈልግሽን ነገር ግዢበት ..እቤት የጎደለ ነገር ካለ አሟይ…ትለኝ ነበር….አንድ ቀን የራሷን ኑሮ ሳትኖር እንደጓደኞቾ ጌጣጌጥና መዘነጥ ሳያምራት ቤተሰቦቾን እንዳገለገለች ሞተች….አሁን ሳስበው ልጅ ከጊዜዋ ቀድማ እንደዛ በስላ ትልቅ ሰው የሆነችውና በደግነትና ቤተሰቦቾን በማገልገል ብኩን የሆነችው ምን አልባት ቶሎ እንደምትሄድ አውቃ ይሆን እንዴ
?እላለሁ..ብቻ ተይው…..አንቺን እግዜር ይባርክሽ››
‹‹አሜን እማዬ››
‹‹ልጄ››
‹‹ወይ እማዬ››
‹‹እማዬ ማለትሽ ካልቀረ …አንቱታውን ተይው…ልጆቼ አንቺ ነው የሚሉኝ
…..አባታቸውንም አንተ ነው የሚሉት…እንግዲህ አንቺም ልጃችን ሆነሽ የለ….ከአነሱ ለምን ትለያለሽ..አንቱታውን ተይው››
‹‹አመሰግናለው እማዬ…..በጣም ነው ማመሰግነው..አሁን ትንሽ ልተኛ፡፡››
‹‹ተኚ ልጄ.. ተኚ››አሉና ወደጓዲያቸው ገብተው…አሮጌ ሞባይላቸውን ፈለጉና ለልጃቸው ለለሊሴ ደወሉና ስራ ፍለጋውን ጥላ ወደቤት እንድትመጣ ነገሯት….
እንደመጣች ወደጓዲያ ወስደው ብሩን እያሳዩ የሆነውን ሲነግሯት ከመደንገጧ የተነሳ አፏ እንደኩበት ደረቀና ምላሶን ምታረጥብበት ምራቅ አጣች…ይህቺ ልጅ ለ በቤቱ መከራ ወይ መዘዝ አስከትላ ትመጣለች የሚል ከፍተኛ ፍራቻ በውስጦ ሲገላበጥ ነበር..ተቃውሞዋን እንደወንድሟ አውጥታ አታንጸባርቀው እንጂ በውስጧ ለመቶኛ ጊዜ ደጋግማ አስባበታለች…አሁን ግን እናቷ እየነገሯት ያሉት ተቃራኒውን ነው…መአት ሳይሆን በረከት ነው እጃቸው ላይ ያለው…በዛ ላይ ጥሩ ገድ አላት…ለወር ስራ ፍለጋ ስትኳትን ነበር..አሁን ግን የተሻለ የተባለ ስራ ባልጠበቀችው መንገድ ለዛውም በቀላሉ

አግኝታለች፡፡ፀሀፊነት፡፡ስራውን ያገኘችላት..በፊት ትሰራበት የነበረ ፀጉር ቤት በደንብኝነት ታውቃት በነበረች አስቴር በምትባል ሴትዬ አማካይነት ነው፡፡
‹‹እማዬ በቃ እሷንም ሆስፒታል ወስደን ማሳከም እንችላለን ..ብዙ ብር ነው፡፡››
‹አዎ እንደዛ ብያት ነበር..ግን ቦርሳዋ ውስጥ ብዙ ብር አለ ….ይሄንን ለቤት የጎደለ ነገር ግዙበት መታከም ከፈለኩ በዚህ እታከማለው አለችኝ…››አብራሩላት
‹‹ውይ እማዬ እንደዛ ከሆነ ደስ ይላል..አሁን ምን እናድርገው››
‹‹እኔ እንጃ የጠራሁሽ ለዛ ነው…አንቺ ያስፈልጋል የምትይውን ነገር ለቤቱም ለእሷም ገዝተሸ ነይ፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ እማዬ ››አለችና ብሩን ከእጃቸው ላይ ተቀብላ ግማሹን ገመሰችና‹‹..ይሄንን አስቀምጪው..በዚህ የሚያስፈልገንን ነገር ገዝቼ መጣለሁ...ዝም ብለን ብሩን ታቅፈን ከጠበቅነው አባዬ ሁንም ተቀብሎን ነው የሚመልስላት››ስትል ስጋቷን ነገረቻቸው፡፡
‹‹አዎ ልጄ… እሱ እንደዛ ነው የሚያደርገው››
‹‹በይ አታስቢ…ብላ ብሩን ቦርሰዋ ውስጥ ከታ እንዳመጣጡ ጓዲያውን ለቃ ወጣችን ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ያለችውን በፀሎትን እስከአሁ አይታት በማታውቀው መንገድ በስስት አይን እያየቻት እቤቱን ለቃ ወጣች፡፡
ይቀጥላል

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

29 Oct, 07:00


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ስምንት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//

ሰለሞን ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው
‹‹ምንድነው መስራት ያለብኝ?ምን አይነት ዕውቀት ነው ያለኝ?ምን አይነት ጥሪትስ አለኝ?ህብረተሠብስ ምን አይነት ሸቀጥ ወይም አገልግሎት ነው መግዛት የሚፈልገው?። መልሶቹ ቀላል አልነበሩም...ወደ አእምሮው የሚመጣው መልስ ወደግል ስራ የሚያስገባው ሳይሆን እንደውም በተቃራኒው የሚያርቀ ነው የሆነበት።
1/ይሄ የምኖርበት ህብረተሠብ በዚህ ሰአት ግዙፍ ችግሩ ምንድነው...?ወረቀትና እስኪሪብቶ ያዘና ዘርዝሮ መፅፍ ጀመረ
1/ኑሮ ውድነት
2/የሠላም እጦት
3/የፍቅር እጦት
4/ቴክኖሎጂ ቅኝ ግዛት
5/...!!የአየር ፀባይ መዛባት
የፃፈውን መለስ ብሎ አየው ...ለደቂቃዎች ብቻውን ተንከትክቶ ሳቅ ። ዝርዝሩን አንድ አነስተኛ የግል ቢዝነስ ለመክፈት ሳይሆን አዲስ ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ ተሹሞ በሀገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጡ የፓሊሲ አማራጮችን ለማርቀቅ መነሻ ሀሳቧችን እያሰላ ያለ ፓለቲከኛ ነው የሚመስለው።
‹‹እስቲ የህብረተሠብም የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ምን አይነት ቢዝነስ ነው የሚኖረው...?ኑሮ ውድነቱ እንኳን ግለሠብ መንግስትስ ለማስተካከል አቅም አለው...?የመለኮት ጣልቃ ገብነት ከሌለስ መፍትሄ ይኖረዋል?።››ሲል አሰበና በራሱ ድርጊት ዳግመኛ ሳቀ፡፡ ከዘረዘራቸው ሀሳቦች የ3 ተኛው ሀሳቡን ገዛው።‹‹ፍቅር እጦት የእኔም የማህበረሰብም የጋራ ችግር ነው።የፍቅር እጦት ደግሞ የሌሎች ችግሮች ሁሉ መነሻ ምክንያት ነው።ደግሞ በሙሉ አቅሜ መስራት የምችለው ስራ እሱን ነው …ሞያዬም ችሎታዬም እሱ ላይ ነው››ሲል አሰበና ወሰነ፡፡

አሜሪካ እያለ ተቀጥሮ የሚሰረባትን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ድርጅት እዚህ ሀገሩ መሀል አዲስ አበባ ላይ በራሱ ለመክፍት ወሰነ…‹‹የራስህን ቢዝነስ ጀምር›› ብላ ስትጨቀጭቀው ለነበረችው አስቴር ነገራት፡፡፡አንገቱ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመች በሀሳብ በጣም መደሰቷንና በማንኛውም ነገር ከጓኑ እንደሆነች አበሰረችው…እሷ የተደሰተችበት ነገር ደግሞ በእሱ ህይወት ትልቅ ቦታ ስላለው ወዲያውኑ በደስታ ወደእንቅስቃሴ ገባ……ፍቃድ ለማውጣት ቢሮ ለመከራየትና አስፈላጊ የቢሮ እቃዎችን አሞልቶ ለመክፈት 40- ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወር ያህል በሰአት ቢሮ እየገባ በሰዓት ቢወጣም አንድም ደንበኛ ማግኘት አልቻለም…ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ የሆነበት፡፡ግራ ጋባው ፣በመጀመሪያውም ዝግና ድብቅ ባህል ባለበት ሀገር የጋብቻና የፍቅር አማካሪ ድርጅት ከፍቶ ውጤታማ ሆናለው ብሎ በማሰብ በራሱ ጅልነት ተበሳጨ…የስድስት ወር የቢሮ ኪራይ ባይከፍልና ለፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎችን ለማሟላት ከመቶ ሺ ብሮች በላይ ባያወጣ ኖሮ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ዘጋግቶ ሌላ የቅጥር ስራ ይፈልግ ነበር..ግን ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አይችልም…‹‹አዎ ለአስቴር ምን እላታለሁ….?እንድታፍርብኝማ አላደርግም…እሷ ከምታፍርብኝ አለም ጠቅላላ ብትገለባበጥ እመርጣለሁ….ስለዚህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››በማለት ወሰነና ቀኑን ሙሉ ሲያሰላስል ዋለ… የሆነ ነገር ብልጭ አለለት፡ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡
ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ወንድሜ….›››የሚል ድምፅ በስልኩ እስፒከር አቆርጦ ጆሮው ውስጥ ተሰነቀረ…
‹‹አለሁልሽ››
‹‹ምነው ድምፅህ?››
‹‹ደህና ነኝ….የሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር?››
‹‹ይቻላል..ግን ስራ አሪፍ ነው እንዴ?….››
‹‹አሪፍ ነው …አሁን አንድ ደምበኛዬን ወደትዳር ከመግባቷ በፊት ማድረግ ስለሚገባት ቅድመ ዝግጅት ማወቅ ፈልጋ ነበር.. እሷን እንደሸኘሁ ነው የደወልኩልሽ››ዋሻት፡፡
‹‹ደስ ይላል ወንድሜ …ህልምህን መኖር ጀምረሀል ማለት ነው….››
‹‹አንቺ ከጎኔ ሆነሽ እስከደገፍሺኝ ድረስ ምንም ማላሳከው ነገር የለም…..አሁን ለምን መሰለሽ የደወልኩልሽ…ፀሀፊ ብቀጥር ብዬ አሰብኩ…››ያሰበውን ነገራት፡፡
‹‹አዎ አንተ ….እስከዛሬ እንዴት አላሰብንበትም…?ለፕሮቶኮሉ እራሱ አስፈጊ ነው…ባለጉዳዬች እንደመጡ አንተን ማግኘት የለባቸውም በፀሀፊህ በኩል ቀጠሮ ይዘውና ተገቢውን ቅድመ ማሟላት ያለባቸውን ነገር አሟልተው መሆን አለነበት…አሪፍ ነው…››
‹‹እና እንዴት ላደርርግ ?ማስታወቂያ ላውጣ….?››
‹‹አይ እኔ በሶስት ቀን ውስጥ ምርጥ ፀሀፊህ ቀጥርልሀለው….አንተ በዚህ ጉዳይ ምንም አትጨነቅ…..ሶስት ቀን ብቻ ስጠኝ››
‹‹እሺ ማታ እቤት እንገናኝ››
‹‹እሺ ቸው ..ወንድሜ››
‹‹ቸው..››
ወንድሜ የሚለው ቀል ከአንደበቷ በወጣ ቁጥር በአንገቱ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት ነው የሚታየው….ሆነ ብላ እሱን ለማጥቃት አስባ ከአንደበቷ የምታወጣው ነው የሚመስለው….‹‹አደራ እኔ እህትህ ባልሆንም ልክ እንደእህትህ ነኝና ሌላ ነገር በአእምሮህ እንዳይበቅል››የሚል ማስጠንቀቂያ ነው የሚመስለው፡፡
የእናትና አባቱ ልጆች የሆኑት እህቱ ወንድሜ የሚለውን ስም በአመት አንዴ እንኳን ሲጠቀሙ አልሰማም….ትዝም የሚላቸው አይመስለውም…እሷ ግን ልክ እንደዘወትር ፀሎት እንደውዳሴ ማርዬም ነው በየእለቱ የምትደግመው፡፡
///
በፀሎት ጥዋት ከእንቅልፏ ስትባንን እቤት ውስጥ ከወ.ሮ እልፍነሽ በስተቀር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም፡፡
‹‹እማዬ ሰው ሁሉ የት ሄደ?››እማዬ ብላ መጣራቷን ለራሷም እየገረማት ነው…ደግሞ አፏ ላይ አልከበዳትም…ወላጅ እናቷ…ሌላ ሴት እናቴ እያለች መጥራት መጀመሯን ብትሰማ ልብ ድካም ይዟት ፀጥ እንደምትል እርግጠኛ ነች፡፡
‹‹ወይ ልጄ… ነቃሽ…ልቀስቅሳት ወይስ ትንሽ ትተኛ እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ነበር፡፡ በረሀብ ሞትሽ እኮ››ብለው ወደ ጓዲያ ገብና የእጅ ማስታጠቢያ ይዘው መጥተው

ሊያስታጥቦት ጎንበስ አሉ…እንደምንም ከአንገቷ ቀና ብላ ተነሳችና ‹‹ያስቀምጡት እኔ እታጠባለው››
‹‹አረ ችግር የለውም ልጄ ..ችግር የለውም››
‹‹ግድ የሎትም….››.
‹‹እንግዲያው ታጠቢ …ቁርስሽን ላቅርብ ›› ብለው ማስታጠቢያው ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላትና ተመልሰው ወደ ጓዲያ ሔድ …….እግሯ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ጥዝጣዜው ነፍሶ ድረስ ይሰማታል…..ፊቷ ላይ አሁንም ተራራ የሚያህል ቁስል የተሸከመች እየመሰላት ነው…እንደምንም ተንፏቀቀችና እጇን ታጥባ የሚመጣላትን ቁርስ መጠበቅ ጀመረች…ጩኮ ከእርጎ ጋር ነበር የመጣላት…ጩኮ መች በልታ እንደምታውቅ አታስታውስም….ቤቷ ቁርስ ሲቀርብ አስር …አስራአምስት አይነት ምግብ ጠረጴዛ ሞልቶ ነው….ከዛ ውስጥ ሶስት ወይም አራት አይነቱን አፕታይቷ የፈቀደላትን መርጣ በልታ ሌላውን ትተዋለች..አሁን የቀረበላት ምግብን ያህል ግን አስደሳች አልነበረም…….እርቧት ስለነበረ እየተስገበገበች በላች…
ያጋባችውን ሰሀንና ብርጭቆ መልሳ…እጇን ታጠበችና…..‹‹እማዬ ማንም የለም እንዴ?››ስትል ደግማ ጠየቀች፡፡
‹‹ልጄ ለሊሴ ስራ ፍለጋ ብላ ወጥታለች…ፊራኦል ስራ ነው ..አባትሽም እንደዛው››መለሱላት፡፡
‹‹ለሊሴ ምን አይነት ስራ ነው የምትፈልገው?››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

28 Oct, 11:59


እናትና አባቱም እሷን በዳሩ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነው ተከታትለው የሞቱባቸው……‹‹አሁን ምክንያት አይኖራትም››ብሎ ወስኗል፡፡
ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

28 Oct, 11:59


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሰባት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ስራው "የፍቅርና የጋብቻ አማካሪነት ነው።የተማረው ፍልስፍና ነው።ሁለተኛ ዲግሪውን ግን አሜሪካ ሄዶ በስነልቦና መስራት ችሏል፡፡በፍቅርና ጋብቻ አማካሪነት የሰራውም አዛው አሜሪካ ነው….ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኃላ ሶስት አመት ተቀጥሮ ሰርቶል፡፡አሜሪካዊያኑ በፍቅርና በጋብቻ ጉዳይ ችግር ሲያጋጥማቸው ባለሞያ ጋር መሄድና ድጋፍ ማግኘት ባህላቸው ነው፡፡በመጀመሪያ ወደትዳር ከመግባታቸው በፊት ማድረግ ስለሚገባቸው ስነልቦናዊ ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ ባለሞያው ጋር ይሄዳሉ..ትዳር ውስጥ ገብተው ችግር ሲያጋጥማቸው…እርስ በርስ ያለው ተግባቦታቸው አመርቂ ካልሆነ…የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት የሚያጨቃጭቃቸው ከሆነ…የወሲብ አለመጣጣም በመሀከላቸው ካለ ብቻ ማንኛውንም ችግር በመሀከላቸው ከተፈጠረ ወደጋብቻ አማካሪ ሄዶ ሞያዊ ምክር መጠየቅና ከዛም የሚሰጣቸውን ምክርና ትዕዛዝ ለየብቻም ሆነ አንድላይ በመተግበር ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት ያስቀናል፤ሌላው ይቅር ጋብቻቸው እንደማይሰራ እርግጠኛ ከሆኑ እንኳን ጤናማና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መለያየትና ጓደኛሞች ሆኖ መቀጠል እንደሚችሉ ምክር ለማግኘት ተያይዘው ወደ ጋብቻ አማካሪ ቢሮ ይሄዳሉ..ይህ ጉዳይ በጣም ነበር የሚያስገርመው፡፡በተለይ በመሀከላቸው ልጆች ካሉ ለየብቻ ሆነው እራሱ
የልጆቻቸውን ስነልቦና ጠብቀው እንዴት ተግባባተው ማሳደግ እንዳለባቸው ዝርዝር መመሪያ ከአማካሪዎች በመስማት ያንን ሳያዛንፉ በመተግበር የልጆቻቸውን ደስታ ሆነ የእነሱን ሰላም ይጠብቃሉ፡፡ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳን በስራው በጣም ደስተኛና ጥሩ ገቢ የሚያገኝበት ቢሆንም ከአምስት አመት በኃላ ጠቅልሎ ወደሀገሩ ተመለሰ….ሲሄድ መቼም ላይመለስ ነበር…..ሀገር ቤት ባሉ ነገሮች ጠቅላላ ተስፋ ቆርጦ ነበር…ግን እንዲመለስ የሚያስገድደው ቁራጭ ምክንያት አገኘ……እና ተመለሰ፡፡
ሰለሞን ወደሀገር ቤት እንደተመለሰ መጀመሪያ ተቀጥሮ ለመስራት ስራ ለማፈላለግ ሞክሮ ነበር….።አስቴር ግን የራሱን ስራ መጀመር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ ግፊት ስታደርግበት እራሱን ከተበታተንበት ሰበሰበና እና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ በላዩ ላይ ዘጋና ስብሰባ ተቀመጠ።አስቴር የልጅነት ጓደኛው እናም ደግሞ ፍቅሩ ነች…ወጣት ሲሆኑ ደግሞ እህቱ ሆነች…እስከአሁንም እህቱ ሆና ቀረች..እሱ በልቡ ተመልሳ ፍቅሩ እንድትሆን ነው የሚመኘው….አላማውም እቅዱም ያ ነው..እሷ ግን ያንንን መስመር ጠርቅማ ዘግታበት አባቱን አባቷ እናቱን እናቷ አድርጋ ለእሱ ደግሞ እህቱ ሆናለች፡፡
ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የሚያውቃት፡፡ ገና ሰባት ወይ ስምንት አመቱ ላይ…የእናቷን ጠርዙ የነተበ የቀሚስ ጫፍ በትናንሽና ለስላሳ እጆቾ ጨምድዳ ይዛ ስርስሯ ኩስ ኩስ እያለች ስትመጣ ነበር የሚያውቃት…የዛን ጊዜውን የልጅነት መልኳን አሁንም በአእምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ ተስሎ ይገኛል..በአጭሩ ተቆርጦ እርስ በርሱ ተጠቅልሎ የተንጨፈረረ ወርቃማ ፀጉር…ጎላ ጎላ ብላው በፍርሀት የሚንካባለሉ አይኖች…በእንባና በአቧራ ብራብሬ የሆነ አሳዛኝ ፊት….ልክ የግቢው አጥር ተከፍቶላቸው የፊትለፊቱን ትልቁን የሳሎን በራፍ አልፈው ወደጓሮ ሲዞሩ ከኃላ ተከትሎቸው ይሄዳል…እናትዬውን ተከትላ ማድቤት ስትገባ ተከትሏቸው ይገባል…
‹‹የእኔ ልጅ፣ እስኪ እኔ ስራዬን ልስራበት አንቺ ከሰሎሞን ጋር አብራችሁ ተጫወቱ››እያለች እናትዬው ታባብላታለች…እሷም የእናትዬውን ልመና ተቀብላ ከእሱ ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ እንድትሆን በአይኖቹ ጭምር ይለማመጣታል….የተቋጠረ ግንባሯን ሳትፈታ በቀሰስተኛ እርምጃ ወደእሱ ትጠጋለች…በደስታ አጇን አፈፍ አድርጎ ይይዛትና እየጎተተ ወደትልቁ ቤት ይዞት ይሄዳል…ከታላቅ እህቱ ጋር በጋራ ወደሚኖርበት መኝታ ክፍላችው ይዞት ይገባል፣..ያሉትን መጫወቻዎች ሁሉ ከየመደርደሪያዎቹን ከየአልጋ ስሩ እየጎተተ ያወጣና ፊት ለፊቷ ወለሉ ላይ ይቆልላል፣ለእሱ የሰለቹትን መጫወቻዎች ለእሷ ብርቆ
ነበሩ….እናትዬው እነሱ ቤት በተመላላሽነት በሳምንት ሶስት ቀን ትሰራለች፡፡እና እነዛን ሶስት ቀናት በናፍቆትና በፍቅር ነበር የሚወዳቸው… ሳምንቱን ሙሉ ለምን እንዳማይመጡ ይገርመው ነበር..ከዛ አባቱ እሱን አንደኛ ክፍል አስመዝግቦ ትምህርት ሲያስጀምረው ለእሷም እንደዛው ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ እሱ የሚማርበት ትምህርት ቤት እናቷ እንድታስመዘግባት አደረገ…አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል መማር ጀመሩ…ይሄ ደግሞ የሚገናኙበትን የቀን ብዛትና አጋጣሚ አሰፋው…..ጓደኝነታቸው አብሮ ዕቃ ዕቃ ከመጫወት የተጀመረ ….ከዛ ኤለመንተሪ ጀምረው እስከ ሀይ እስኩል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ነው የተማሩት።የተወሰኑ ክፍሎችን አንድ ክፍል ጥቂት ክፍሎችን ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይም አብረው ተቀምጠው የመማር አጋጣሚዋች ነበሯቸው።ስለዚህ እሷ ልክ አብረውት እንደተወለድ ወንድሞቹ እና እህቱ እድሜ ልኩን ነው የሚያውቃት፡፡
ፍቅር የጀመሩት 8ተኛ ክፍል ሲማሩ ነው።በወቅቱ እሱ 8ተኛ ቢ ሲማር እሷ ደግሞ 8ተኛ ኤፍ ክፍል ነበረች።ግን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ወደት/ቤት ሲሄድና ወደሰፈር ሲመለሱ ተጠራርተውና ተጠባብቀው ነበር።እና አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጡ እየጠበቀችው ነበር።አብረው ወደቤት መመለስ ቢጀምሩም ግን አንደበቷ እንደተቆለፈና እንደተበሳጨች ነበር...ምን እንደሆነች ቢጠይቃትም በቀላሉ ልትነግረው አልቻለችም..በኃላ በስንት ጭቅጭቅ ከባርሳዋ አንድ ወረቀት አውጥታ ሰጠችው።ምንድነው? ብሎ በጉጉት ተቀብሎ አነበበው።
አስቴርዬ የእኔ ቆንጆ..የፍቅርሽ ፍላፃ ልቤ ላይ ነው የተሰካው….እስካሁን ሰንኮፉን
አልነቀልኩትም…ያልነቀልኩት ሲሰካብኝ ከነበረው ጊዜ በላይ ስነቅለው ያመኝ ይሁን በሚል ስጋት ነው…….ምን አልባት አንቺው በትንፋሽሽ አዘናግተሸ በልስልስ እጆችሽ ቀስ ብለሽ ብትነቅይልኝ መልካም ይሆን ይመስለኛል፡፡፡አንቺ እኮ ከአለም ሴቶች ጭምር ተወዳዳሪ
የሌለሽ ውብ ነሽ።እኔ አፍቃሪሽ በአንቺ ፍቅር መንገላታት ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል።ግን እስከዛሬ ስቃዬን በውስጤ አፍኜ ህመሜን የቻልኩት ከጓደኛዬ ከሰለሞን ጋር ግንኙነት ያላችሁ ስለሚመስለኝ ነበር።ግን በቀደም ወኔዬን አሰባስቤ ስጠይቀው ጓደኛሞች ብቻ እንደሆናችሁ ነገረኝና ነፍሴን በሀሴት አስጨፈራት።እና ውዴ አንቺስ ምን ትያለሽ...
?መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ... የአንቺው አፍቃሪ መስፍን ጋዲሳ›› ይል ነበር።
አነበበውና ግራ የመጋባትና የመደነጋገር ስሜት ተሠማው..በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው በቀደም በብዙ ጓደኞቻቸው መካከል ስለፍቅር አንስተው ሲያወሩ መስፍን እንደቀልድ ‹‹አስቴርና ሰለሞን ፍቅረኛሞች ናቸው›› አለ ወዲያው ሰለሞን ከአፉ ተቀበለና
‹‹እውነት አይደለም እኔና አስቴር ፍቅረኛሞች ሳንሆን ጓደኛሞች ነን ››ብሎ መልስ ሰጠ
።ነገሩ በዚህ ተደመደመ።ደብዳቤውን ባነበበበት ወቅት ግን መሠፍን ሆነ ብሎ ለገዛ የግል ጥቅሙ ጥያቄውን ጠይቆት እንደነበረና እሱንም ማኖ እንዳስነካው ገባውና በጅልነቱ ተበሳጨ።
ግን ደግሞ የአስቴር ወቅታዊ ኩርፊያ አልገባውም ነበር።‹‹መስፍን ደብዳቤ ለፃፈላት እኔን ለምን ልታኮርፈኝ ቻለች?››እራሱን ጠየቀ
"እና እኔ ምን አጠፋው..የምታኮርፊኝ?"ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

28 Oct, 11:59


"አይ አንተማ ምንም አላጠፋህ …እኔ ነኝ እንጂ ዘላለም በብላሽ ከአንተጋር የምንዘላዘለው..ነው ወይስ እናቴ የቤታችሁ አገልጋይ ስለሆነች አትመጥነኝም ብለህ አስበህ ነው?"አለቸው።እና እየተመናጨቀች ተለይታው ወደቤቷ አመራች።
ሰለሞንም ደንዝዞ ወደቤቱ ገባና በመጨረሻ ስትለየው የተናገረችውን ዓ.ነገር ሲያሰላስል አደረ።"....እኔ ነኝ እንጂ ዘላለም በብላሽ ከአንተጋር የምንዘላዘለው... ‹‹ምን ለማለት ፈልጋ ነው?ታፈቅረኛለች ማለት ነው?እኔስ አፈቅራታለሁ እንዴ? መስፋን የፃፈላትን ደብዳቤ ሳነብ ለምን ቅር አለኝ,,,?ቀንቼ ነው እንዴ?ፍቅር ሲይዝ እንዴት ነው የሚያደርገው?ስምንተኛ ክፍል ሆኖ ፍቅረኛ መያዝ ይቻላል እንዴ?››እነዚህንና መሰል ጥያቄዎች ባልጠና እና ለጋ ጭንቅላቱ ሲያወርድና ሲያወጣ እንዲሁ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነጋ...፡፡ከዛን በኃላ በማግስቱ አናገራት ….እንደሚያፈቅራትና እሷ ፍቃደኛ ከሆነች ፍቅረኛው እንድትሆን እንደሚፈልግ ነገራት..እሷም በደስታ ፈንጥዛ እላዩ ላይ ተጠመጠመችበት….ከዛ የታዳጊነት ፍቅራቸው እስከ አስረኛ ክፍል ቀጠሉ…የበለጠ ጊዜ በሄደ መጠን በእነሱም መካከል ያለ ፍቅር እየደረጀና ስር እየሰደደ መጣ፡፡አስረኛ ክፍል በጀመሩ በሶስተኛው ወር አንድ ቀን ጥዋት የትምህርት ቤት ሰዓት ደርሶ ቀድሞ ወጥቶ ቢጠብቃት ልትመጣ አልቻለችም...ተማሪ ሁሉ ሄዶ ማለቁንና ሰዓቱ መርፈድንም ከግንዛቤ በማስገባት በለሊት ቀድማ መሄዶን ጠረጠረና በሩጫ ወደትምህርት ቤት...በረፍት ሰዓት ክፍሏ ሄዶ ቢያያት እንዳልመጣች ጓደኞቾ ነገሩት።ግራ ተገባ።
አስቴር ከትምህርት ቤት በቀላሉ የምትቀር አይነት ልጅ አይደለችም። ለትምህርቷ የምትሰጠው ትኩረት ቀላል የሚባል አንዳልሆነ ያውቃል…ታዲያ እንዴት?።እናም ያለ መምጣቷ ዜና አልተዋጠለትምና እሱም እንዳመመው በመናገር አስፈቅዶ ወደቤት ሄደ…ወደቤት የሄደበት ዋና ምክንያት የአስቴር እናት እንጀራ ልትጋግር ወይም ሌላ ስራ
ለመስራት ወደእነሱ ቤት የምትመጣበት ቀን ስለሆነ አስቴር ለምን እንደቀረች ሊጠይቃት ነበር እቅዱ፡፡እቤት ሲደርስ ግን ማንም አልነበረም..የአስቴር እናትም እንዳልመጣች በኩሽናው መቆለፍ አረጋገጠና ደብተሩን አስቀምጦ ወጣና ወደ እነአስቴር ቤት አመራ… ሰፈራቸው ሲደርስ እቤታቸው ፊት ለፊት ድንኳን ተተክሎ ነጠላ ያዘቀዘቁ ሴቶችና ጋቢ የደረብ ወንዶች ሲተረማመሱ ከሩቅ አየ...ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ ነው የደነገጠው፡፡
‹‹አስቱካ ምን ሆነች?››በሩጫ ነበር ተንደርድሮ ድንኳኑ መሀከል የተገኘው...አስቴር በአራት በሚበልጡ ሴቶች ግራና ቀኝ ተደግፋ ‹‹ወይኔ እናቴ እያለች›› ስትንፈራፈር ተመለከታት"ተመስገን"አለና ትንፋሹን ወደውስጥ እየሳበ ለመረጋጋት ሞከረ።‹‹ተመስገን
››ያለው እናቷ ስለሞቱ አይደለም...በፍፁም ።ይልቅ እሷ በህይወት ስላለችልለት ተደስቶ ነው።እንጂማ እናቷ ከህፃንነቱ ጀመሮ ከገዛ እናቱ በመቀጠል ያሳደጉት ያዘሉትና የመገብት ሴት ናቸው…….የእሳቸውም ሞት በጣም አስደንግጦታልም አሳዝኖታልም…
ከዛ ከሀዘን ቤት እስክትወጣም ሆነ ከዛ በኃላ ከስሯ አልተለየም።ግን እሷን ማፅናናት እና ወደ ህይወቷ እንድትመለስ ለማድረግ ቀላል አልሆነለትም።ምክንያቱም ለአስቴር እናቷን ማጣት እናትን ብቻ ሳይሆን መላ ዘር ማንዘሯን ማጣት ማለት ነበር።ምክንያቱም አባቷን ጭራሹኑ እሷ እንደተፀነሰች የሞተ እና ዘመዶቹንም የማታውቅ ሲሆን በተመሳሳይ እናቷም የረባ የቅርብ ዘመድ ያልነበራት ብቻዋን ወልዳ ብቻዋን ያሳደገቻት ነበረች እና እሷም ስትሞትባት ሌላ አይዞሽ የሚላትና የሚያፅናናት አንድም የቅርብ ዘመድ አልነበራትም።በኃላ የእናትና አባቱ ተማከሩና አስቴርን እንደልጃቸው አድረገው ወደቤታቸው አመጧት፡፡
ትዝ ይለዋል የአስራ አምስት አመት ልጅ እና የአስረኛ ክፍል ተማሪ እያለ ነበር…አስቴር የቤተሰቡ አባል ሆና የተቀላቀለች፡፡አዎ እሷ ስትመጣ እሱ ከእህቱ ጋር ከሚጋራው ክፍል ተፈናቀለና ሌላ ትልቁ ወንድሙ ለቆ ዩኒቨርሲቲ በገባበት ክፍል ከአመፀኛው ወንድሙ ጋር ደባል ሆኖ ገባ…
እድሜውን ሙሉ የኖረበትን ክፍልና የተኛበትን አልጋ እንዳለ ለአስቴር አስረከበ….እንደዛ በመሆኑ አልከፋውም….፡፡ለሌላ ሰው ልቀቅ የተባለ ቢሆን ኖሮ ከፍተኛ አብዬት ያስነሳ እንደነበር እርግጠኛ ነው….ለአስቴር ስለሆነ ግን እንደውም ደስ ያለው ይመስላል…እርግጥ እሱ ከመኝታው ሳይፈናቀል በእሱ ምትክ እህቱ እንድትለቅላት ቢደረግ ወይንም ሌላ ሶስተኛ አልጋ ወደክፍሉ እንዲገባ ተደርጎ እሷ እንድትተኛ ቢደረግ በጣም ደስተኛ ይሆን እንደነበር እርግጠኛ ነው..ግን ለምን ተብሎ ሊጠየቅ የማይችለው አባቱ ኮስተር ብሎ የወሰነው ውሳኔ ስለሆነ ያለምንም ማቅማማት ነው ተግባራዊ የሆነው፡፡
አስቴር ከእሱ በአንድ አመት ስትበልጥ ከእህቱ ስህን ደግሞ በሁለት አመት ታንሳለች…..ስለዚህ የሁለቱንም ጓደኛ ነች፡፡
ይሄ ውሳኔ በደስታ እንዲፈነጥዝ እና በወላጆቹም እንዲኮራ አደረገው።እና እህቱም ጓደኛውም ሆነች...።የነካኩት የፍቅር ጉዳይ ግን እንደተዳፈነ ቀረ...።
አስቴር ‹‹ እቤታቸውንም ልባቸውንም ከፍተው እንደገዛ ልጃቸው የተቀበሉኝን ሰዎች ልጃቸው ጋር ባልጌ አላሳዝናቸውም…እኔ እና አንተ ከአሁን በኃላ እህትና ወንድም እንጂ ፍቅረኛሞች መሆን አንችልም›› ብላ ቁርጥ ያለ ውሳኔዋን ነገረችው፡፡እሱ በቀላሉ ውሳኔውን ሊቀበል አልቻለም፡፡ይበልጥ ሊያጣት እንደሆነ ባወቀ ቁጥር ውስጡ የንዴት እሳት እየነደደ ይለበልበው ጀመር፡፡
እና ውሳኔዋን እንድትቀይርና እንድታስተካክል በወጣች በገባች ቁጥር ሲያስቸግራት እሷም እሱን ተስፋ ለማስቆረጥ እርምጃ ወሰደች…ስምንተኛ ክፍል ሆነው ደብዳቤ የፀፈላትን መስፍንን 11 ክፍል ፍቅረኛ አድርጋ ተቀበለችው፡፡
ከዛሬ ነገ እሱን ትታ ወደእኔ ትመለሳለች ብሎ በትእግስ ሲጠብቅ ሁለቱም 12ተኛ ክፍል ማትሪክ ተቀበሉና ዩኒቨርሲቲ ገቡ…ልክ በተመረቁ በ3ተኛ ወሯ መስፍን እነ ሰለሞን ቤተሰቦች ጋር አስቴርን ለማግባት ሽማጊሌ ላከ…ወዲያው ቀለበት አሰሩና ከሶስት ወር በኃላ ተጋቡ፡፡
በዚህን ጊዜ ሰለሞን ሁሉ ነገር አስጠላው…ሁሉን ነገር ጣጥሎ በትምህርት አሳቦ ወደውጭ የተሰደደበት ዋና ምክንያት የእሷ ማግባት ነበር…ለአመስት አመት እዛው ኖረና ድንገት ለመመለስ ወሰነ…ይሄንን ወደሀገር የመመለሱን ውሳኔ የወሰነበት ዋናው ምክንያትም አስቴር ከ5 አመት የጋብቻ ቆይታ እና አንድ ልጅ ከወለዱ በኃላ ተፋተው እሱም ልክ እንደእሱ አገር ጥሎ እንደተሰደዱ ስለሰማ ምን አልባት ከአመት በፊት የተነጠቅኩትን ፍቅሬን መልሼ የማግኘት እድል ይኖራኛል በሚል ተስፋ ነበር የተመለሰው፡፡ከልጅነት እስከጎልማሳነት የዘለቀ እንቅፋት የበዛበት ውስብስብ ፍቅር…እና ሁሉ ጊዜ ስለራሱና ስለፍቅሩ ሲያስብ ‹‹ጠንቆይ ለራሱ አያውቅም እያለ ››ይተርታል..፡፡
እሱ ለላፉት ሶስትና አራት አመታት ለብዙ ሺ ጥንዶች እንዴት ያፈቀሩትን ሰው ማሳመንና የራሳቸው ማድረግ እንዳለባቸው..ፍቅራቸውን እንዴት መንከባከብ እንደሚገባቸው ውጤታማ ምክር እየሰጠ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ሲጫናቸውና ደከም ያሉትንም ሲበሳጭባቸው ከርሞል..ግን የራሱን ከልጅነቱ ጀምሮ ሲያበቅለውና እየተንከባከበ ሲያሳድገው የነበረውን ፍቅር የሆነ ዘዴ ፈጥሮ ፍሬውን ለመብላት ፈፅሞ አልቻለም፣አሁን ግን ቆርጦ ነው የመጣው አዎ
…አስቴርን ከአነልጇ ያገባታል ..የልቡም የቤቱም ንገስት ያደርጋታል››ሰው ምን ያላል እቤተሰብ ምን ይላሉ አሁን አይሰራም ..እስከዛሬ እሷ እንደምክንያት የምታቀርባቸው

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

26 Oct, 07:30


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ስድስት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ማታ አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡
ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ እንደምታውቂው ቀኑ ገና 18 ነው….በ18 ደግሞ ደሞዝ የለም…ስለዚህ ሙዙ ላንቺ አይደለም››ሲል መለሰላት፡፡
ለሊሴ ግራ ገብቷት‹‹ እና››ስትል አይኖቾን በማፍጠጥ ጠየቀችው፡፡
‹‹ለበሽተኛዋ ማለቴ… ለእንግዳዋ ነው››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት፡፡
‹‹እ ነው…እሺ…››አለችና ፔስታሉን ወደበፀሎት ወስዳ ስሯ አስቀመጠችላት…፡፡

በሳቅና በጫወታ በደመቀ ምሽታ እራት ተበላ… ቡና ተፈልቶ ተጠጣ….ከጓዲያ የተጠቀለለ የጥጥ ፍራሽ ወጣና ወንበሮቹ ተሰብስበው ከእሷ ጎን ተነጠፈ…ለሊሴ ከጎኗ በተነጠፈው የጥጥ ፍራሽ ላይ ስትተኛ ፊራኦል ደግሞ ከእነሱ ራቅ ብሎ ግድግዳውን ተደግፎ ካለ አሮጌ ሶፋ ላይ አንድ አልጋ ልብስ ተከናንቦ ተኛ…
‹‹ለሊሴ ታዲያ ስትበራገጂ እግሯን እንድትነኪባት››
‹‹አረ አታስቢ እማዬ …እጠነቀቃለሁ፡፡››
ለሊሴ በፀሎትን ‹‹ለሊት የሆነ ነገር ከፈለግሽ ቀስቅሺኝ››አለችትና የለበሰችውን አልጋ ልብስ ተከናነበች፡፡
‹‹እሺ ቀሰቅስሻለሁ..ደህና እደሩ ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ደህና እደሪ….ወንድሜ ደህና እደር››
‹‹ምኑን ደህና አደርኩት ….ዛሬ ደግሞ ምን አልባት ሴኖ ትራክ ይሆናል ቤታችን ላይ የሚወጣው…. ››
‹‹ወንድሜ ደግሞ.. አሽሙራም ነገር ነህ››
‹‹እሺ መብራቱን ላጥፋው?››ፊራኦል ጠየቀ፡፡
‹‹አጥፋው››በፀሎት መለሰች፡፡
መብራቱ ጠፋ፡፡ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ሁሉም ፀጥ ያለና በእንቅልፍ የተዋጠ ይመስል ነበር..በፀሎት ግን ፈፅሞ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም...ጨለማው ውስጥ አይኗን አፍጥጣ በጭንቀት እያሰላሰለች ነበር..ይሄኔ የአባቷ ቅጥረኞች ድፍን አዲስ አበባን እየገለባበጦት እንደሚሆን እርግጠኛ ነች..
‹‹የፈለገ ቢገለባብጡ የፈለገ ያህል ቢሞክሩ አያገኙኝም….››ስትል እርግጠኛ ሆነች፡፡ስልኳን ከቤት ይዛ አለመውጣቷ አሁን ነው ያስደሰታት….እንደዛ ባታደርግ ኖሮ ያንን ተከትለው ያለችበትን ለማግኘት ይሞክሩ ነበር አሁን ግ ምንም እድል የላቸውም…አዎ አሁን ባልና ሚስቶቹ እየተናቆሩም ቢሆን እሷን በመፈለጉ አንድ ላይ ለማውራትና ለመተባበር ይገደዳሉ…ምን አልትም ወደቀልባቸው እንዲመለሱ ምክንያት ሊሆናቸው ይችል

ይሆናል…ይሄ የእሷ ምኞት ነው፡፡ካለበለዚያም ይለይላቸውና እርስ በርስ ይገዳደሉ ይሆናል፡፡‹‹እንደዛ ከሆነ እስከወዲያኛው እገላገላቸዋለው››አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ እንዲሁ ስትገላበጥና ስትተክዝ እኩለ ለሊት ሆነ፡፡ በአእምሮዋ የሚጉላላው ሀሳብ ብቻ አይደለም እቅልፍ የነሳት… የእግሯም ጥዝጣዜ ጭምር ነው ፡፡በዛ ላይ ሽንቷን ወጥሯታል….‹‹እንዴት ነው የማደርገው.?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡.እንደምንም ተቆጣጥራው እስከንጊት ለማቆየት ብትጥርም አልቻለችም..አምልጧት ከመዋረዷ በፊት ከጎኗ ድብን ያለ እንቅል የተኛችውን ሊሊሴን መጣራት ጀመረች‹፡፡
‹‹ሌሊሴ….ሌሊሴ››
ያልጠበቀችው ሻካራ ድምጽ መልስ ሰጣት..‹‹አትልፊ እህቴን እንኳን በጥሪ በመድፍም ልትቀሰቅሻት አትችይም››
ግራ ተጋብታ ምን እንደምትመልስ እያሰላሰለች ሳለ መብርቱ በራ…በቁምጣና በጃፖኒ ቲሸርት ውጥርጥር ያለ ሰውነቱን በከፊል አጋልጦ ካለችበት በሶስት እርምጃ ርቀት ቆሟል…
‹‹ምን ልስጥሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ..ሽንት ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር››ፈራ ተባ እያለች መለሰችለት፡፡
‹‹ምን ፖፖ ላምጣልሽ?››
ፖፖ ቢያመጣላት እዚህ እፍንፍን ያለ ቤት ይሄ ሁሉ ሰው ባለበት እንዴት አድርጋ እንደምትሸና አሰበችና‹‹ አይ ሽንት ቤት ነው መሄድ የፈለኩት››በማለት መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲያው እሺ›› አለና ወደበራፍ በመሄድ የተቀረቀረውን በራፍ ወለል አድርጎ ከፈተና ተመልሶ ወደእሷ መጣ …ምን ሊያደርግ ነው ብላ አፍጥጣ እያየችው ሳለ በርከክ ብሎ ስሯ ተቀመጠና የለበሰችውን ብርድ ልብስ ከላዮ ላይ ገፈፈ፡፡ እጆችን በትከሻዋና በእጆቾ መካከል አሰቅስቆ አስገባ..
‹‹ምን እያደረክ ነው?››ግራ በተጋባ ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹መቼስ እንዲህ ተሰባብረሽ ልራመድ አትይም….እንደፈረደብኝ አቅፌ ሽንት ቤት እየወሰድኩሽ ነው››

‹‹አረ ተው ..እነጋሼ ብያዩን ምን ይሉናል?››
‹‹አይዞሽ እነጋሼ ልጃቸው ምን አይነት ልጅ እንደሆነና እንዴት አድርገው እንዳሳደጉት ስለሚያውቁ ምንም አይሉም…..ምን አልባት ግን ይመርቁኝ ይሆናል››አለና አንከብክቦ አቅፎ ከቤት ይዟት ወጣ፡፡የልጁ ድርጊት ፍጽም ያልጠበቀችው ስለሆን በጣም ነው የተደመመችው፡፡እንደተሸከማት ከሰርቢስ ቤቱ ጫፍ በኩል ክፍቱን ካለ አንድ ክፍል ወስዶ ወደውስጥ ደፉን አሳለፈና ደግፎ አቆማት…ከዛ ቀኝ እጁን ዘረጋና በቀይ የኤሌክትርክ ገመድ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለውን ማብሪያ ማጥፊያ ሲጫናው የሽንት ቤቱ መብራት ቦግ ብሎ በራና በክፍሉና በአካባቢው ያለው እይታ ወለል ብሎ አንዲታየ አደረገ …
ደረቱ ላይ ተደግፋ እንደቆመች ሽንት ቤቱን ቃኘችው..ስፋቱ ሁለት ካሬ እንኳን አይሞላም
…በዛ ላይ ከለመደችው አይነት መፀዳጃ ቤት ፍፅም የተለየና የማይነፃፀር አይነት ነው….ይህን መሰል አይነት ሽንት ቤት በምስል አንኳን አይታው የማታውቀው አይነት ነው፡፡እርግጥ ፅዳቱ የተጠበቀ በመሆን ዝግንን የሚል የመቅፈፍ አይነት ስሜት እንዲሰማት የሚያደርግ አይነት አይደለም…ቢሆንም በምቾት ዘና ብላ የምትቀመጥበት አይነት አይደለም…‹‹በቃ እንደምንም ግድግዳውን ተደግፈሽ ቁሚ..››ትዕዛዙን ስትሰማ እንደምንም የተበታተነ ሀሳቧን ሰበሰበች፡፡
እስከአሁን ደረቱን ተደግፋ መቆሟን ትዝ ሲላት እንደመደንገጥ አለችና ግራና ቀኝ እጇን የሽንት ቤቱን በራፍ ግራና ቀኝ ጉበን ይዛ ቆመች…ትቷት ወደኃላ ሸሸና መራመድ ሲጀምር
በመደንገጥና በመገረም ስሜት‹‹እንዴ? ጥለኸኝ ልትሄድ እንዳይሆን?››ስትል ጠየቀችው፡፡
እርምጃውን ሳያቋርጥ ‹‹መጣሁ..››አለና ከበራፉ አካባቢ አንድ ባዶ ሀይላንድ ላስቲክ ይዞ ወደ ቧንቧው በመሄድ ውሀ ቀድቶ ከሞላበት በኃላ ..ወደእሷ ተመለሰና እጁን አንጠራርቶ ከሽንት ቤቱ ቀዳዳ አጠገብ አስቀመጠላትና …‹‹..ግቢና እንደምንም ተቀመጪ››አላት፡፡
ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹በራፍ የለውም እንዴ?››ሌላ ያስጨነቃትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይዞሽ….ምንም አትሆኚም››አለና ወደላይ ተሰብስቦ የተጠቀለለ ጨርቅ ነገር አላቀቀና እንደመጋራጃ ወደታች ለቆ ጋረደላት…..የእግሯን ጥዝጣዞ እንደምንም ችላ በአንድ አይኗ አጨንቁራ በማየትና ነገሮችን በመቆጣጠር እደምንም ተቀምጣ ለመተንፈስ ቻለች..ጨርሳ ስትወጣ ተንደርድሮ ከበራፍ ተቀበላትን ሰቅስቆ አቀፋት፡፡

‹‹ካላስቸገርኩህ ጨረቃዋ ደስ ትላለች ..ትንሽ ውጭ መቀመጥ እንችላለን?››ስትል በልመና ቃና ጠየቀችው፡፡
‹‹እንደፈለግሽ.. ››አለና ግድግዳውን አስደግፎ አቆማትና ትቷት ወደውስጥ ሊገባ መራመድ ጀመረ…
‹‹እንዴ ብቻዬን ልቆይ እኮ አይደለም ያልኩህ ..አንተ ምትገባ ከሆነማ እኔ ብቻዬን ፈራለሁ››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

26 Oct, 07:30


‹‹በለሊት ሞተር ስትጋልቢ እንዴት ሳትፈሪ…?ለማንኛውም ወንበር ላመጣልሽ ነው››አለና ወደቤት ገባና አንድ ባለመደገፊያ ወንበር በማምጣት አደላድሎ ወስዶ አስቀመጣትና ከጎኗ ጠፍጣፋ ድንጋይ አስቀምጦ ተቀመጠ፡፡
‹‹ስምህ ፊራኦል ነው አይደል ምን ማለት ነው?፡፡››
‹‹በትክል የስሙ ትርጉምን ለማወቅ ፈልጋ ሳይሆን እንዲሁ ወደጫወታ እንዴት እንደምትገባ ግራ ስለገባት የሰነዘረችው ጥያቄ ነበር ‹‹ከዘመድ ሁሉ በላይ ነህ..ወይም ከዘመድ ሁሉ በላይ ሁን ማለት መሰለኝ....እኔ ግን ከዘመድ ሁሉ እኩል እንጂ በላይ መሆን አልፈልግም፡፡››
‹‹ሶሻሊስት ነገር ነህ ማለት ነው?››
‹‹በይው..እንዳንቺ አይነት ካፒታሊስት በበዛበት አለም ሶሻሊስት መሆን ከባድ ቢሆንም አዎ ሳሻሊስታዊ ነኝ፡፡››
‹‹እኔ ካፒታሊስታዊ መሆኔን በምን አወቅክ?››
‹‹በወዝሽ››
ከቀናት በኃላ ከት ብላ ሳቀች‹‹እንዴ እንዲህ ቆሳስዬ እና ግማሽ ፊት በባንዴጅ ታሽጎ ወዜን እንዴት ማወቅ ቻልክ?፡፡››
‹‹ወዝሽ እኮ ፊትሽ ላይ ብቻ አይደለም ያለው…የቆዳሽ ልስላሴ እኮ የሰው አይመስልም…ጌጣጌጦችሽም አንዱ ምስክር ናቸው…››
‹‹እንዴ አርቴ እኮ ነው፡››

‹‹አይ ቤተሰቦቼ..ማለቴ እህቴ አርቴ ነው ብላ ስታወራ ሰምቼለሁ....እኔ ግን ስለጌጣጌጥ የተወሰነ እውቀቱ አለኝ …አርቴ እዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹ጎበዝ ነህ!!››
የተወሰነ ደቂቃ በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ ‹‹ምንድነው የምትሰራው?››ስትል ድንገት ጠየቀችው..ጥያቄዋ እንዲሁ በመሀከላቸው የተጀመረውን ጫወታ ለማራዘም ብላ እንጂ ምንም ይስራ ምንም የሚያስጨንቃት አይነት ሆኖ አይደለም፡፡
‹‹ገንዘብ ያስገኝ እንጂ ያገኘሁትን ሁሉ ሰራለሁ››
‹‹ማለት…?››
‹‹ማለትማ ማርኬቲንግ ነው የተመረቅኩት…ሱፐር ማርኬት ውስጥ ሰርቼ አውቃለሁ…የጅውስ ማከፋፈያ ፋብሪካም ተቀጥሬ ሰርቼ አውቃለው…..ቆርቆሮ ፋብሪካም ሰርቼ ነበር..አሁን ግን አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ነው እየሰራሁ ያለሁት፡፡››ሲል አብራራላት
‹‹አኸ…ስለጌጣጌጤ የተናገርከው ከዛ ልምድ በመነሳት ነዋ››
‹‹ይሆናል››
‹‹ግን ቆርቆሮ ፋብሪካ የትኛው ቆርቆሮ ፋብሪካ ነው የሰራኸው?››
‹‹በፀሎት ቆርቆሮ ፋብሪካ…እዛ ሁለት አመት ሰርቼው›› ከድንጋጤዋ የተነሳ ..ትን አላት…ደንግጦ ተነሳና ጀርባዋን ደገፋት
‹‹ደህና ነኝ ደህና ነኝ››
‹‹ምነው ..ያልሆነ ነገር ተናግሬ አስደነገጥኩሽ እንዴ?››
‹‹አይ በፀሎት የሚባል ቆርቆሮ ፋብሪካ መኖሩን አላውቅም ነበር…››
‹‹እንግዲህ ቆርቆሮን በተመለከተ ምንም እውቀት የለሽም ማለት ነው…..በፀሎት እኮ አገሪቱ ውስጥ ካሉ ትላልቆቹ ቆርቆሮ አማራቾች መካከል አንዱ ነው…ባለቤትነቱ የቢሊዬነሩ ባለሀብት የአቶ ኃይለመለኮት ነው…..በፀሎት የልጃቸው ስም ነው፡፡›

‹‹አይገርምም..የእኔም ስም በፀሎት በመሆኑ እኮ በእኔ ስም የሚጠራ ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለማወቄ ተደንቄ ነው...ሰውዬውን ማለቴ ባለቤቱን ታውቃቸዋለህ?››
‹‹አዎ …አውቃቸዋለው…ማለቴ በመጠኑ .. ሁለት ወይም ሶስት ቀን እሷቸውን የማናገር እድል ነበረኝ››
‹‹ልጃቸውንስ?››
‹‹እሷን የፋብሪካው በራፍ ላይ በትልቁ ቢልቦርድ ላይ የተለጠፈው ምስሏ ለአመታት ሳየው ነበር ….ይሄኔ እሷ በስሟ ወላጆቼ ፋብሪካ እንዳላቸው ሁሉ አታውቅም ይሆናል..ግን ይገርምሻል አሁን በጣም ትናፍቀኛለች…ብዙ ቀን ላገኛት ሞክሬ ነበር ግን አውሬ መሳይ ጋርዶቾ ሊያስጠጉኝ አልቻሉም….ግን በቅርብ እንደማገኛትና እንዲህ እንደእኔና እንዳንቺ ፊትለፊት ተቀምጠን ብዙ ብዙ ነገር እንደምናወራ እርግጠኛ ነኝ…በሆነ መንገድ የግድ ማግኘት አለብኝ››
ንግግሩን ስትሰማ በተቀመጠችበት ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥና የልብ ምቷ ሲጨምር ታወቃት…
‹‹ትናፍቀኛለች ነው ያልከው…..ግራ አጋቢ ነገር ነው››ይብልጥ እንዲያወራ የሚያበረታታ ዓ.ነገር ጣል አደረገች፡፡
‹‹ግራ አትጋቢ…አብራራልሻለሁ …ቆይ እንደውም…››አለና ኪሱ ገባና የገንዘብ ቦርሳውን አወጣ ….ምን ሊያደርግ ነው ብላ ስትጠብቅ….ከፈተውን አንድ ጉርድ ፎቶ አወጣና አቀበላት…‹‹አየሻት…በፀሎት ማለት ይህቺ ነች…››ብሎ መች እንደተነሳች የማታውቀውን የገዛ ፎቶዋን እጇ ላይ አስቀመጠላት…ለተወሰነ ጊዜ ድንዝዝ አለች፡፡
‹‹ፎቶዬን እንዴት…..?››
‹‹ምን አልሺኝ?››
በመዘባረቋ ደንግጣ‹‹ማለቴ ..የልጅቷን ፎቶ አንተ ጋር ምን ይሰራል….?››
‹‹…ስለምትናፍቀኝ እልኩሽ እኮ…እርግጥ ቀጥታ እሷ አይደለም የምትናፍቀኝ ….እህቴ በሬዱ ነች…አወሳሰብኩብሽ አይደል፡፡ታላቅ እህቴ በሬድ ከሁለት አመት በፊት ነው በአደጋ ምክንያት የሞተችው…ታላቄ ነበረች..የሁለት አመት ታላቄ..የቤቱ እጅግ ተወዳጅ ልጅ ነበረች….ባንክ ነበር የምትሰራው…የቤታችንን ወጪ ግማሹን እሷ ነበረች

የምትሸፍነው…ግን ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደረሰባትና ሆስፒታል ገባች፣የዛን ጊዜ እኔ የነበፀሎት ቆርቆሮ ፋብሪካ ነበር የምሰራው….እና እህቴ ክሪትካል ኬዝ ላይ ደረሰችና ጭንቅላቷ በጣም ተጎድቷ ስለነበረ ወደውጭ ሄዳ ብትታከም ጥሩ እንደሆነ ሀኪሞቹ ምክር ሰጡ ..እኛ አቅማችን አይችልም ነበር…በአጋጣሚ በዛን ጊዜ በፀሎት የልብ በሽታዋ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደውጭ ለህክምና ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበረች…እኔ እህቴን ለማሳከሚያ የእርዳታ ብር ለመሰብሰብ እላይ እታች በመሯሯጥ ላይ ነበርኩ ….ከመስሪያ ቤት ሰራተኞች እየተሰበሰበ ሳለ አቶ ኃይለመለኮት ድንገት ፋብሪካውን ለመጎብኘት ይመጣሉ..እና እያለቀስኩ እርዳታ ከሰራተኞች ስሰበስብ አይተውኝ ወደመኪናቸው ይዘውኝ ገቡና ምን እንደሆንኩ ጠየቁኝ…እያለቀስኩ በቤተሰባችን የደረሰውን መከራ ነገርኮቸው………
‹‹በቃ እርዳታ መሰብሰቡን አቁም እኔ እህትህን አሳክምልሀለው››አሉኝ በፍፅም እውነት አልመሰለኝም ነበር…ግን ከምራቸው ነበር..‹‹ከአስር ቀን በኃላ ልጄን ለልብ ህክምና ወደታይላንድ ይዤት ስለምሄድ እህትህንም እዛ ሔዳ መታከም ትችላለች..የህክምና ማስረጃውን ጨርሱ የጉዞ ሰነድችን የእኔ ሰዎች ያመቻቻሉ››ብለው አስፈነጠዙኝ፡፡
ቃላቸውን ጠብቀው እህቴን ከአባቴ እና ከገዛ ልጃቸው ጋር ይዘው ታይላንድ ሄዱ…እህቴ ታይላንድ በገባች በአስራ ሶስተኛው ቀን ህይወቷ አረፈ….….በዛን ጊዜ ደግሞ በተመሳሳይ ቀን የፀሎት ልቧ ፌል አድርጎ በህይትና በሞት መካከል ስታጣጥር ነበረ…ብቻ ፕሮሰሱ ብዙ ነው…በስተመጨረሻ አባቴ ልጄ ሙሉ በሙሉ እንዳትሞት ልቧን መለገስ እፈልጋለው አለና ፍቃደኛ ሆኖ እዛው የእህቴ የበሬድ ልብ ለበፀሎት ተገጠመላትና..አባቴ የእህቴን ሬሳ ጭኖ መጣ እልሻለው፡፡፡››
‹‹በጣም የሚገርም ልብ ሰባሪ ታሪክ ነው የነገርከኝ››
‹‹አዎ በጣም ልብ ሰባሪ ነው…አይገርምም የአንዱ ቤት ደስታ በሌላው ቤት ሀዘን ላይ መብቀሉ…አንዱ እንዲስቅ ሌላው ማልቀስ አለበት…ህይወት እንዲህ ኢፍትሀዊ መሆኗን ከዛ በፊት አላውቅም ነበር››
‹‹በቃ አትበሳጭ ..እናውራ ብዬ ..አስደበርኩህ አይደል?››
‹‹አረ በፍጽም..››ብሎ ሊያብራራት ሲል የሰርቢሱ በራፍ ተከፈተ… ሁለቱ ፊታቸውን ሲያዞር አቶ ለሜቻ ነበሩ፡፡

‹‹እንዴ ልጄ አመመሽ እንዴ… ?ፊራኦል ለምን ሳትቀሰቀኝ?››ልጃቸውን ተቆጡት
‹‹አይ አባዬ …አላመማትም..እንቅልፍ እምቢ ሳላላትና እቤቱ ስለሞቃት ነው ውጭ የወጣነው፡፡››
‹‹አዎ አበባ ..ደህና ነኝ…እንቅልፍ እምቢ ስላለኝ ነው፡፡››እንዳላመማት አረጋገጠችላቸው፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

26 Oct, 07:30


ስሯ ቀረቡና ከጀርባዋ ቆመው ግንባሯን እያሻሹ..‹‹ልጄ …ሀሳብ ስታበዢ እኮ ነው እንቅልፍ የሚነሳሽ…..ከህመምሽ በፍጥነት ለማገገም ደግሞ የምግብን ያህል እንቅልፍም ወሳኝ ነገር ነው….አይዞሽ አልኩሽ እኮ..እኔ አባትሽ እያለሁልሽ ምንም አትሆኚ… በዛ ላይ እሱም ወንድምሽ..ለሊሴም እህትሽ ነች..፡፡.››
እንባዋ ከአይኖቾ ያለፍቃዷ ረገፈ…
‹‹አመሰግናለው ጋሼ..በእውነት በጣም አመሰግናለው፡፡››
‹‹ልጅ አባት አያመሰግንም..ዝም ብሎ ብቻ ይወደዳል….በቃ በእኛ መካከል ፍቅር ብቻ ነው ያለው..በሉ ብርዱን ብዙም አትዳፈሩት….››አሉና እንደአመጣጣቸው ወደውስጥ ተመልሰው ገብ፡፡
ስሯ የተቀመጠውን ፊራኦልን በጭለማ ውስጥ አፍጥጣ እያየችው ‹‹ታድለህ››አለችው
‹‹ማለት?››
‹‹እኚን የመሰለ ..የተባረከ እና ፍቅር የሆነ አባት ስላለህ ››
‹‹አዎ አባዬ የእኔ ብቻ ሳይሆን የሀገር ምድሩ አባት ነው…ለሰው ሁሉ ያለው ፍቅር የሚገርም ነው..አንዳንዴ እንደውም ስለሚያበዛው እበሳጭበታለው››
‹‹ጥላቻ እንጂ ፍቅር ሲበዛ እኮ አያበሳጭም››
‹‹አይ ያበሳጫል..ልጅ ሆነን ለእኛ ገዝቶ የመጣውን ሙዝ መንገድ ላይ ላገኛቸው ልጆች ሁሉ አንድ አንድ እየመዘዘ ሲያድል እቤት ሲደርስ ባዶ ፔስታል ብቻ ይቀራል…አባዬ እንደዛ ነው….ቢሆንም ግን በጣም ደሀ ግን በጣም ተወዳጅ አባት ስላለኝ አመስጋኝ ነኝ ››
‹‹አይ አባትህማ ደሀ ተብለው የሚገለፁ አይደሉም…ግርማቸውና ርህራሄያቸው ቢሊዬን ብር ያወጣል….እመነኝ ምነው የእኔም አባት በሆኑ ብዬ ቅናት እያንገበገበኝ ነው፡፡››

‹‹ምንም መቅናት አያስፈልግሽም…በቃ አሁን ልጄ ነሽ ብሎሻል አይደል……ለእሱ ከእኔ የተለየሽ አትሆኚም ፣ላጋንን አይደለም…ታይዋለሽ…..ቅድም ካንድ ጓደኛው ጋር በስልክ ሲከራከር ነበር››
‹‹ለምን?››ለማወቅ ጓጉታ ጠየቀችው፡፡
‹‹የፊታችን እሁድ ማለት ከሶስት ቀን በኃላ የሚወጣል እቁብ አለው…ስምንት ሺ ብር አካባቢ መሰለኝ፡፡እና የወንድሜ ልጅ ታማብኝ ማሳከሚያ ቸግሮኛል …ወይ እቁብን ሰጡኝ ወይ ደግሞ ከወጣለት ሰው እንድገዛ አመቻቹልኝ እያለ ሲለምናቸው ነበር…እኔ ደግሞ ለራሱ ጉዳይ ቸግሮት አንቺን እንደሰበብ እየተጠቀመ መስሎኝ‹‹‹አባ ብሩን ለምን ፍልገህ ነው?››ብለው፡፡
‹‹ይህቺን ልጅ ደህና ሆስፒታል ወስጄ ማሳከም አለብኝ..ከዚህ ሁሉ ሺ ቤቶች የእኔን ቤት ጋር መታ የተላተመችው ያለምክንያት አይደለም..እግዜር እኔን ሊፈትን ይሆናል የላካት…ደግሞስ እንዲህ ተጎድታ የተኛችው ለሊሴ ብትሆን ወይም አንተ ብትሆን እንዲህ ዝም እል ነበር?ልጄ በሬዱ አደጋ ባጋጠማት ጊዜ ቶሎ በፍጥነት አንስቶ ሆስፒታል ሚወስዳት ሰው ብታገኝ ኖሮ በለጋነቷ አትቀጠፍብኝም ነበር…..ከሁለት ሰዓት በላይ መኪና ውስጥ ተቀርቅራ ደሟ ሲንዠቀዠቅ……›› አለኝ…አባዬ የልጁ የበሬዱ ሞት ብቻ ሳይሆን አሟሟቷም ሁል ጊዜ እንደረበሻቸው ነው፡፡
በፀሎት የምትሰማው ነገር ከአእምሮዋ በላይ እየሆነባት ነው፡፡
‹‹ታዲያ አባትህ እንደዛ ሲሉህ አንተ ምን አልካቸው?››
‹‹እውነቱን መስማት ነው የምትፈልጊው?››
‹‹አዎ እውነቱን››
‹‹እንግዲያው እኔ አባቴ ያንን እቁብ እንዴት አድርጎ እንዴት ተቸግሮ በየሳምንቱ በመጣል ያጠራቀመው ብር እንደሆነ ስለማውቅ ተቃውሞ ነው ያሰማሁት..ታያለሽ አይደል ያን የተከመረውን ብሎኬት እንዲህ ከተደረደረ ሶስት አመት አለፈው…እህቴ በሬዱ ነበረች ከመሟተዋ በፊት የገዛችው….ቤተሰብ አሁን ባለው አኗኗር እየተጨናነቀ ስለሆነ አባቴ አንድ ክፍል ቤት ቀጥሎ እንዲሰራ አቅዳ ነበር፣ግን ያው ሞት ቀደማት ….እና አባቴ ከእቁቡ የሚገኘው ብር ለዚህ አዲስ ተቀጥሎ ለሚሰራው ክፍል ቆርቆሮና ምስማር መግዣ ነበር ያሰበው…አላማው ቤቱን መስራት ብቻ ሳይሆን የእህቴንም እቅድ ተግባራዊ ማድረግ
የአእምሮ ሰላም ማግኘት ነበር…በዚህ ምክንያት በቀላሉ ልስማማ አልቻልኩም…በእኔ አመለካከት እስከአሁን ላንቺ ያደረግነው ትብብር በቂ ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡እና የቤተሰቦችሽን ስልክ ፈልገን ደውለንላቸው እንዲወስዱሽ ነበር ሀሳብ ያቀረብኩለት፡፡››
‹‹እና ታዲያ አባትህ ምን አሉ?››
‹‹የከፋት ልጅ ነች…በራሷ ውሳኔ እንደዛ ካላደረገች እኔ እንደዛ እንድታደርግ አልገፋትም…የእኛ ሀላፊነት የቻልነውን ማድረግ ነው..ሌላው የእሷ ውሳኔ ነው..ልጄ በየቤቱ ወጣቱ እራሱን የሚያጠፋውና ህይወቱን የሚያበላሸው እንዲህ የሚያዳምጠው አጥቶ ያም ያም ሲገፋውና ሲያሳድደው ነው…የቻልነውን እናደርጋለን.››አለኝ፡፡
‹‹አሁን እንግባ በቃኝ››አለችው፡፡
ከተቀመጠበት ተነሳና ሰቅስቆ አቀፋት..ወደውስጥ ይዞት ገባና ቀስ ብሎ ቦታዋን አስተካክሎ አስተኛትና….በራፉን በትክክል ዘግቶ ወደሶፋው በመሄድ ተኛ…እሱ ወዲያው እንቅልፍ ቢወስደውም እሷ ግን እስኪነጋጋ ድረስ እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም ነበር….ጥዋት ግን ሁሉም ሲነሱ እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ነበር፡፡
ሰኞ…ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

25 Oct, 06:09


ምትመልሰውን መልስ ማሰላሰል ጀመረች….በአእምሮዋ አስልታ ከመወሰኗ በፊት ከአንደበቷ ሾልኮ ወጣ…..‹‹ሰክሮ መጥቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፡፡››ስትል አፈረጠችው፡፡፡
እቤቱ ሁሉ በድንጋጤ ፀጥ አለ….ሁለቱ አዛውንት ወላጆች ስቅጥጥ አላቸው፡፡እሷ እራሷ በተናገረችው ውሸት እራሷ ደነገጠች…በመደንገጧ ደግሞ የማተቆጣጠረው እንባ በጉንጮቾ ላይ እንዲረግፍ አደረገ…አቶ ለሜቻ በቀኝ ወይዘሮ እልፍነሽ በግራ አቅፈዋት እያሻት ያባብሏት ጀመር‹‹ልጄ አይዞሽ..ከዛሬ ጀምሮ እኔ እናትሽ ነኝ….እሷቸውም አባት ይሆንሻል፡፡››ቃል ኪዳን ገቡላት፡፡
‹‹በቃ ልጄ ምንም አታስቢ… እኛ ቤተሰቦች ነን…አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገሽ እርሺና እራስሽን አስታሚ …በደንብ ከዳንሽ በኃላ ..የሚሆነውን እናደርጋለን.፡፡.ልትከሺውም ከፈለግሽ..ወይም ሌላ ነገር ካሰብሽ በማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነን..አሁን ግን ስለምንም ነገር አትጨነቂ በሽታሽን ላይ ብቻ አተኩሪ …እንደምታይው ኑሮችን ደከም ያለ ነው …ትልቅ ሆስፒታል ወስደን ልናሳክምሽ አንችልም….ግን ደግሞ ውጌሻው የማያሽልሽ ከሆነ

የመንግስት ሆስፒታልም ቢሆን አመላልሰን እናሳክምሻለን..ምንም አታስቢ፡፡››የአቶ ለሜቻ ማበረታቻ ቃል ነበር፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለው…..በእውነት በህይወቴ እንደእናንተ የወደደኝ ሰው የለም……ሰው ሰውን እንዲሁ በነፃ በዚህ መጠን መውደድ እንደሚችል አላውቅም ነበር…በጣም አመሰግናለው..››አለችና ሸርተት ብላ ተኛች…አይኗን ጨፈነች፡፡
ወ.ሮ እልፍነሽም‹‹ልጄ..ሲያዩሽ እኮ መልዐክ ነው የምትመስይው፡፡ አንቺን ምን አይነት ሰው ነው ላይወድሽ የሚችለው?››ብለው አልጋ ልብሱን ወደላይ ስበው አለበሶትና ከስሯ ዞር አሉ….
ስለዋሸቻቸው ፀፀታት..ግን ምርጫ የላትም..እንዲህ ካላደረገች ከቤተሰቦችሽ እናገናኝሽ ብለው ያስቸግሯታል..እሷ ደግሞ ወደእዛ ምድራዊ ሶኦል ወደሆነ ና ፍቅር ወደነጠፈበት ቤት እንዲ በቅርብና በቀላሉ የመመለስ ምንም አይነት እቅድ ያላትም….፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

25 Oct, 06:09


ወ.ሮ እልፍነሽ ጥያቄው መደናገር ውስጥ አስገባቸው‹‹ለምን ጠየቁኝ?››
‹‹አይ እንዲሁ ነው..ይህቺ የወንድሙ ልጅ እጅግ የሀብታም ልጅ እንደሆነች ያስታውቃል››
‹‹እንዴት ነው ሚያስታውቀው…?ያደረገችውን ልብስና የደረገችውን አርቴፊሻል ጌጥ ተመልክተው ነው?››
‹‹አይ ፍፅም እነሱን አይቼ አይደለም…ሰውነቷን አይቼ ነው…ልስላሴው እኮ ከሀር ጨርቅ በላይ ነው…..እጅግ ቅንጡ አስተዳደግ ያደገች የንጉስ ልጅ ነው የምትመስለው…አዎ በደንብ ያስታውቃል፡፡››አሉ እርግጠኛ በመሆን፡፡
ወ.ሮ እልፍነሽ‹‹ይሆናል››ብለው በድፍኑ መልስ ሰጡ፡፡

‹‹እንግዲ..ከሶስት ቀን በኃላ መጥቼ አያታለው…ሾርባ ነገር እያደረጋችሁ በደንብ ተንከባከቧት …ትድናለች……በሉ›› ብለው ሲወጡ አቶ ለሜቻ ወደውስጥ ገቡና ወደባለቤታቸው በመቅረብ….‹‹የእኔ አለም….ለውጌሻዋ የሚከፈል ብር አለሽ አንዴ?››ሲሉ ልብን በሚሰረስር ትህትና ጠየቁ፡፡
‹‹ስንት ይሆን….?››
‹‹ሁለት መቶ ብር ነው..እኔ ጋር መቶ ብር አለ፡፡››
በፀሎት በወገባቸው ዙሪያ የተጠመጠመ መቀነታቸውን ሲፈቱ አጨንቁራ እያየቻቸው ነው..ከቋጠሮ ውስጥ ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጡና ለባለቤታቸው ሰጦቸው….
‹‹መቶ ብሩን አትሰጪኝም…?››
‹‹ኪስህማ ባዶ መሆን የለበትም…ግድ የለህም ሂድ ውጌሻዋን ሸኛት ››
አቶ ለሜቻ የተሰጣቸውን ብር በእጃቸው እያሻሹ ወደ ውጭ ወጡ…ወ/ሮ እልፍነሽ ወደጓዲያ ገብና በጓድጓዳ ሰሀን ምግብ እና በብርጭቆ ውሀ ይዘው በመምጣት ስሯ ቁጭ አሉ ፡፡
የተኛች መስሎቸው ቀስ ብለው ትከሻዋን ያዙና ‹‹የእኔ ልጅ ..የእኔ ልጅ››ሲሉ ሊቀሰቅሷት ሞከሩ… ቀስ ብላ አይኗን ስትገልጥ እንጀራ የጠቀለለ እጃቸው አፏ አካባቢ ደርሶል….‹‹በ…ቃኝ…እማ….ማ››
‹‹አይ….በቃኝ አይሰራም…ካልበለሽ አትድኚም…እንደምንም ባይጣፍጥሽም ታግለሽ መብላት አለብሽ››ኮስተር አሉባት፡፡
አሳዘኗት…‹‹ቆይ ማንነቴን አያውቁ ለምንድነው እንዲህ እየረዱኝ ያሉት….?ነው ወይስ የልጃቸውን ልብ የተሸከምኩ መሆኔን ደመነፍሳቸው ነግሯቸው ይሆን?››መልስ በቀላሉ ልታገኝለት ያልቻለችው ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡፡
ለእሳቸው ስትል እንደምንም አፏ ከፈተች…አፏ ውስጥ ከተቱት…በመከራ አላመጠችና ዋጠች..እንቁላል ፍርፍር ነው…በመከራ አምስት ጉርሻ ያህል አጎረሶትና ወደላይ ደግፈው ውሀ እንድትጠጣ ካደረጉ በኃላ አስተኟት…፡፡ከዛ አቶ ለሜቻም ውጌሻዋን ሸኝተው ስለተመለሱ ለቤተሰቡ ጠቅላላ ቁርስ ቀረበና ተሰብስበው እየተጎራረሱ ሲበሉ አየች….ያ

ደግሞ ይበልጥ ስለወላጆቾ ቤት እንድታስብና ልቧ እንዲሰበር አደረገ ..ለእሷ እንቁልል ጠብሰው ያባሏት ሴትዬ ለቤተሰቡ ደረቅ ዳቦ በሻይ ነው ማቅረብ የቻሉት፡፡የገረማት ደግሞ እሱንም በፍቅር እየተሳሳቁ ይጎራረሳሉ፡፡
እሷ ቤት በየቀኑ ጠረጴዛ ሙሉ ለአይን እራሱ የሚያታክት ምግብ ይቀርባል፡፡ የሚበላው ግን አስር ፐርሰንትም አይሞላም…ከዛ የተረፈው ምን እንደሚደረግ አታውቅም..ምን አልባት እዛ ጊቢ ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ይታደል ይሆናል… ወይም ደግሞ ተበላሽቶ ገንዳ ውስጥ ሊደፋም ይችል ይሆናል…..እዚህ ግን እቤቱ ያፈራውን ምርጥ ምግብ ለማያውቁት እንግዳ ሰው አብልተው እነሱ ደረቅ ዳቦ ይቆረጥማሉ..ለዛውም በጫወታ የደመቀ በደስታ የታጀበ ቁርስ ነው እየበሉ ያሉት…እነሱ ቤት ግን በኩርፊያ የታጀበ ቁርስ ነው የሚሆነው..ወሬ ካለውም በአሽሙርና በነቆራ የታጀበ በሚያስጠላ ጥል የሚገባደድ ነው የሚሆነው፡፡
ይበልጥ ሆድ ባሳት….‹‹በምንም አይነት ወደእዛ ቤት በቀላሉ አልመለስም››ለራሷ ዳግመኛ ቃል ገባችና አይኗን ጨፈነች..ደክሞት ስለነበረ ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት፡፡
‹‹የእኔ ልጅ ተነሽ….›› የሚል ድምጽ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት..ምን ያህል እንደተኛች አታውቅም፡፡ ብቻ አይኖቾን ስትገልጥ ልክ እንደቅዱሙ ያች ደግ እናት ምግብ በሰሀን ይዛ ልክ እንደህፃን ልጅ ልታጎርሳት ስሯ ቁጭ ብላለች፡፡
‹‹እማማ…አራበኝም እኮ ..አሁን አይደል እንዴ የበላሁት?››
‹‹አይ አሁን እኮ ሰባት ሰዓት ሆኗል…አባትሽ ላንቺ ሲል ነው ስጋ ገዝቶ የመጣው… እኔ እናትሽ ደግሞ ቆንጆ አድርጌ ሰርቼሻለሁ››
‹‹በሰማችው ነገር አንባዋ በአይኗ ግጥም አለ….››
‹‹ነይ እስኪ ለሊሴ ትንሽ ቀና ትበል ትራስ ደርቢላት›ለሊሴ መጣችና ደግፋ ቀና አድርጋ ትራስ ደረበችላትና ወደቦታዋ ተመለሰች …ቡና እያፈላች ነው..አቶ ለሜቻ ከለሊሴ ፊት ለፊት ባለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው በፀጥታ እየተመለከቷት ነው፡፡
‹‹እንጀራውን ጠቅልለው ወደ አፏ ዘረጉት…አፏን ከፍታ ተቀበለቻቸው…አላምጣ ከወጣች በኃላ…

‹‹እናንተስ አትበሉም?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹አዬ ልጄ …አኛማ በልተን ጨርሰን ቡና ስንጠብቅ አታይንም..አንቺ ብይ››አቶ ለሜቻ መለሱላት፡፡ወይዘሮ እልፍነሽ አብልተዋት ከጨረሱ በኃላ አቶ ለሜቻ ከተቀመጡበት ተነስተው ወደእሷ ተጠጉና ፍራሹ ጫፍ ላይ ተቀመጡ…የሆነ ነገር ሊጠይቋት እንደሆነ ገብቷት ዝግጁ ሆነች፡፡
‹‹ስምሽ ማነው ልጄ?››እስከአሁን ስሟን እና ማንናቷን እንኳን ሳያውቁ ይሄን ሁሉ እገዛና እንክብካቤ ሲያደርጉላት እንደቆዩ ስታስተውል ግርም አላት፡፡‹‹በፀሎት እባላለሁ››
‹‹እኔ አባትሽ..ለሜቻ እባላለሁ..እናትሽ ደግሞ እልፍነሽ ነው ስሟ….የመጀመሪያ ወንዱ ልጄ ፍራኦል..እሷ ደግሞ የእሱ ተከታይ ለሊሴ ትባላለች..፡፡››የቤተሰቡን አባላት ሁሉ በስማቸው እየጠሩ አንድ በአንድ አስተዋወቋት…በፅሞና እያዳመጠቻቸው መሆኑን ከተገነዘቡ በኃላ ንግግራቸውን አራዘሙ‹‹በእውነት በዛ ውድቅት ለሊት በዛ ሞተር ሆነሽ ከቤታችን ጋር ተጋጭተሸ ስትወድቂ በህይወት የምትተርፊ መስሎ አልተሰማኝም ነበር… ሁላችንም በጣም ፈርተን ነበር..ግን አምላክ ደግ ነው እና አጋልጦ አልሰጠንም…ተርፈሻል….ይመስገነው››
አሁን እሷቸው ሲናገሩ ሞተሩና ቦርሳዋ ትዝ አላት….ሞተሩ ምንም ቢሆን ግድ የላትም ቦርሳዋ ግን ያስፈልጋታል…
‹‹ወይኔ አባባ የሆነ ቦርሳ ይዤ ነበር …ጣልኩት እንዴ?››እሰከዛን ሰዓት ድረስ እንዴት ትዝ እንዳላላት ለራሷም ገረማት.፡፡፡
‹‹…አይ ልጄ አልጣልሺውም… ቦርሳውም ሞተሩም ጓዲያ ተቀምጦልሻል…ሞተሩን ወደውስጥ ያስገባነው ምን አልባት ችግር ላይ ሆነሽ ከፖሊስ እየሸሸሽ ወይም ከሆነ ሰው እየተደበቅሽ ከሆነ እንዳትጋለጪ ብለን ነው…››
‹‹አይ አባባ…እምልሎታለው የነገርኳችሁ እውነቴን ነው..ከፖሊስ ጋር የሚያገኛኘኝ ምን ነገር የለም…ከእንጀራ አባቴ ጋር ተጣልቼ ነበር …በለሊት ከቤት ወጥቼ በንዴት ስነዳ የነበረው››
‹‹አዎ እኔም ጠርጥሬለው…የቤተሰብ ችግር እንደሆነ ታውቆኝ ነበር››

‹‹ውይ ልጄ ይሄኔ እናትሽ በጭንቀት ልትፈነዳ ደርሳለች››ወ.ዘሮ እልፍነሽ በእናትነት አንጀታቸው የተሰማቸውን ተናገሩ ….ስለራሳቸው ልጆች እያሰቡ ስለነበር ነው ስሜቱ የተጋባባቸው፡፡
በፀሎት‹‹አይ እናቴ አትጨነቅም››ፍርጥም ብላ መለሰች፡፡
‹‹ምን ማለትሽ ነው ልጄ …?በጣም ነው እንጂ የምትጨነቀው..እናንተ ልጆች የእናትን አንጀት እስክትወልዱ ድረስ አይገባችሁም…ይሄኔ በየፖሊስ ጣቢያው እና በየሆስፒታሉ አንቺን ፍለጋ እየተንከራተተች ነው፡፡››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠንካራ እምነታቸውን በድጋሜ ገለፁ፡፡
‹‹እይ እደዛ ማለቴ አይደለም ..እናቴ ከሁለት ወር በፊት ነው የሞተችው›››
‹‹ውይ ታዲያ እንጀራ አባትሽ እናት የሞተባትን ልጅ ምን አድርጊ ነው የሚልሽ….?ሌሎች እህትና ወንድም የለሽም›?›
‹‹የለኝም እኔ ብቻ ነኝ››
‹‹ታዲያ በውድቅት ለሊት ምን አጣላችሁ?››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

24 Oct, 07:06


አባዬ ልጅ ሆኜ እርግቤ እያልክ ነበር የምትጠራኝ..እርግቤ ስትልኝ እንዴት እንደምደሰት አታውቅም ፡፡የእውነትም ያንተ ነጭ እርግብ ሆኜ አድማሱን ሰንጥቄ በሰማይ መብረር የምችልና ጨረቃ ጋር ደርሼ ከዋክብቶችን ጨብጬ ምጫወትባቸው ይመስለኝ ነበር…ባቃ ትንሽ መልአክ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ነበር የምታደርገው..ግን አባዬ አንተ ያልተረዳኸውነ ነገር እኔ ከ19 ዓመቴ በኃላ ማለቴ የሌላ ሴት ከሰውነቴ ካወሀድኩ ጀምሮ እኔ እኔን አይደለሁም…..ትዝ ይልሀል እርግቤ አትበለኝ በስሜ ጥራኝ ብዬ ያስተውኩህ እራሴው ነኝ..ለምን ብለህ ጠይቀኸኝ ግን አታውቅም..ምን አልባት ዝም ብዬ እርግቤ የሚለው ሰም ደስ ስለማይለኝ መስሎህ ሊሆን ይችላል እንደዛ ግን አይደለም….ከልብ ነቅለ-ተከላ ከተደረገልኝ በኃላ ክንፏ የተሰበረባት መብረር የማትችል እና በየጓሮ የምትንፏቀቅ እርግብ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ስለመጣ ነው ያስቆምኩህ..ለአንድ ልጅ እኮ በሰማይ እንዳሻት እንድትበር የሚያደርጋት የአባቷ ፍቅር ቀኝ ክንፍ እና የእናቷ ፍቅር ግራ ክንፍ ሲሆናት ነው….የወላጆቾ ፍቅር ነው እንድትበር የሚያደርጋት….ያ እንደሌለኝ ስረዳ ነው ስሙ ያስጠላኝ፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም ከድሮዬ በተለየ ፍቅር ይርበኛል፡፡
አባዬ እንደነፍስህ የምትወዳቸው ሁለት የአንተ አንደኛ ሰዎች አንድ ቤት እየኖሩ እንደጠላት ሲታያዩ ከማየት የበለጠ የሚያስጣላና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም….አሁን አሁን ሳድግ ተስፋ ቆርጬ ተውኩ እንጂ በፊት እናትና አባቴ ግራና ቀኝ እጄን ይዘው እርስ በርስ እያወሩና እየተሳሳቁ ወደ መዝናኛ ቦታ ወይም ዘመድ ቤት ይዘውኝ ሲሄዱ አልም ነበር..ሁሌ የማየው ህልም እንደዚህ አይነት ነበር…ያን ህልም ግን አንድም ቀን እውን ሆኖልኝ አያውቅም….ከቤት ውጭ ከሁለታችሁም ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የትም ሄጄ ሆና የትም ቦታ ተገኝቼ አላውቅም……ወይ አንተ ትጎድላለህ ወይ ደግሞ እማዬ ትጎድላለች…ይሄ ምን ያህል ልቤን እንዳቆሰለው አታውቅም….ደግሞ ታውቃለህ በውስጤ

የተሸከምኩት የሌላ ሰው ልብ ነው…ያንን ልብ በአደራ ነው የተረከብኩት ….ላሰቃየውና ላጨናንቀው መብት የለኝም…. እንደአለመታደል ሆኖ ግን በፍቅር የተሰጠኝን ልብ በስርአቱ ተንከባክቤ እንድይዘው እናንተ እየፈቀዳችሁልኝ አይደለም፡፡
አባዬ ይገርምሀል ..ሁል ጊዜ ስለአንተእና ስለእማዬ ሳስብ ‹‹ ቆይ ሁል ጊዜ እንዲህ እየተጠላሉ..ለምን ባልና ሚስት ተብለው አንድ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ? ብዬ በተደጋጋሚ እራሴን ጠይቅ ነበር…፡፡አሁን ግን ለምን እንደሆነ መገመት እችላለው…አንድም እኔ እንቅፋት ሆኜባችሁ ነው…እንደውም ብዙ ጊዜ አንቺን በስለት ነው የወለድንሽ ብላችሁ በየአመቱ መደገሳችሁ ለበጣ ይመስለኛል..ተፈልጋ ለዛውም በስለትና በፀሎት ተወለዳ በጸሎት የሚል ስም የወጣላት አንድ ብቸኛ ልጅ ያላቸው ጥንዶች እንዴት እንዲህ ሊጠላሉ ይችላሉ..?እንዴት ልጃቸውን በፍቅር እጦት ሊያሳቃዩና ሊያሰቅቁ ይችላሉ…? ይሄ የሚያመለክተው ለእኔ ያላችሁ ፍቅር የውሸት እንደሆነ ነው፡፡ፈፅሞ ሁለታችሁም ትወዱኛላችሁ ብዬ አላስብም ፡፡ምን አልባት ከእኔ በላይ ሀብታችሁን አምርራችሁ ትወዱ ይሆናል፣ሁለታችሁም ላለመለያየትና በዛአይነት ጥላቻ ውስጥ ሆናችሁም ቢሆን በአንድ ጣሪያ ስር መኖር መቀጠሉን የመረጣችሁት ሀብታችሁን ላለመበታተን ሰስታችሁ ይመስለኛል፡፡እና ለዚህ ስል ሄጄያለው…ከእናንተ በጣም እርቄ ሔጄያለው፡፡አንድ ቀን ግን ተመልሼ መጣለሁ፡፡ መች እንደምመጣ አላውቅም፡፡ እሱ የእናንተ ውሳኔ ነው…እንድመለስ ከፈለጋችሁ በዚህም ብላችሁ በዛ ህይወታችሁን አስተካክሉ…፡፡ወይ በቃን ብላችሁ ተለያዩና የየራሳችሁን ህይወት መኖር ቀጥሉ፣ቢያንስ በዚህ ውሳኔ ከሁለት አንዳችሁ በቀሪ ህይወታችሁ ደስተኛ የመሆን እድል ይኖራችኋል…ካለበለዘያም ቁጭ ብላችሁ ተነጋገሩና ይቅር ተባብላችሁ ያለፈ ህይወታችሁን ጨለማ ታሪከ ዘግታችሁ ለራሳችሁ እንደባልና ሚስት ለእኔም ደግሞ እንደወላጅ ለመሆን ተዘጋጁ…..እስከዛው ልትፈልጉኝ እንዳትሞክሩ ልታገኙን አትችሉም…ብታገኙኝም ወደቤት ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆንም….ግን ባለሁበት ሆኜ በራሴ መንገድ እከታተላችኃላው….በእናንተ ዙሪያ መኖር ለእኔ ምቹ ነው ብዬ ባመንኩበት ሰዓት እመጣለሁ..ካልሆነም ከእናንተ እንደራቅኩ የራሴን ህይወት እኖራለሁ..፡፡አባዬ አይዞህ ስለበሽታዬ አትጨነቅ…አትጨነቅ የምልህ በእኔ ጥንካሬ ስለምተማመን አይደለም..በውስጤ ያለው የልጅቷ ልብ እጅግ ጠንካራ ስለሆነ ነው፡፡ ያንን ደግሞ ያወቅኩት የእኛን ቤት ያንን ሁሉ ጥላቻና ጥል ተቋቁሜ እስከአሁን በህይወት የኖርኩት እና ኮላፕስ ያላደረኩበት ብቸኛ ምክንያት የተሸከምኩት ልብ ጥንካሬ ነው፡፡በል ቸው አባዬ… ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ …በጣም እወድሀለው፡፡

ይላል ደብዳቤው፡፡አቶ ሃይለመለኮት ደነዘዙ፡፡ምን ማድረግና ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው እየገባቸው አይደለም፡፡ልጃቸው በእሷቸውም ሆነ በሚስታቸው ይሄን ያህል መጎዳቷ እና መማረሯን ፈፅሞ ልብ ብለውት አያውቁም ነበር፣በዚህም በራሳቸው አፈሩ…. ደብዳቤውን ደረት ኪሳቸው ውስጥ ከተቱና ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

24 Oct, 07:06


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አራት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
በፀሎት ከጠፋች ከአንድ ሰዓት በኃላ ነበር አባትዬው ዜናውን የሰሙት፡፡በመጀመሪያ የቤቱ ሰው ሁሉ ያሰበው የተለመደው የልብ በሽተዋ ተነስቷባት ተዝለፍልፋ የሆነ ቦታ ወድቃ ይሆናል ተብሎ ነበር ፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ጋርዶቹ ፤ ዘበኞቹና አስተናጋጆቹ ሳይቀር የቤቱ ጥጋጥግ ከ50 በላይ ክፍሎች አንድ በአንድ እየከፈቱ አንድም ቦታ ሳይቀር ፈልገው ጅባት ካሉ በኃላ ነበር የጋርዶቹ ሀላቃ ፈራ ተባ እያለ የአቶ ኃይለመለኮትን መኝታ ቤት ያንኳኳው….በለሊት ልብሳቸው ሆነው የልጃቸውን የልደት በዓል ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታቸውን አልጋ ላይ አሳርፈው ገና እንቅልፍ እንዳሸለባቸው ነበር በራፋቸው የተንኳኳው…በመጀመሪያ በህልማቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በኃላ ግን የምርም ክፍላቸው እየተንኳኳ መኆኑን ገባቸውና እየተነጫነጩ አልጋቸውን ለቀው በንዴት ውስጥ ሆነው በራፉ ሊከፍቱ እየሄዱ ባሉበት ቅፅበት ከመኝታ ቤታቸው ቀጥሎ ካለው ከፍል ውስጥ ያሉት ወ.ሮ ስንዱ ድምፅ ሰምተውና ደንግጠው ክፍላቸውን ከፍተው እየወጡ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እያንኳኳ ያለው ጋርድ ላይ አፈጠጡበት፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››

‹‹ጋሼ..እንዴት እንደሆነ አናውቅም…..ልጆቹ እየተከታተሏት ነበር….››ለማስረዳት አስቦ መንተባተብ ጀመረ..፡፡
‹‹ምን እያወራህ ነው?››
‹‹በፀሎት..››
‹‹በፀሎት ..ልጄ ምን ሆነች..?አመማት እንዴ…?የልብ ህመሟ ተቀሰቀሰባት?››እናትዬው በመርበትበት በጥያቄ አጣደፉት፡፡
‹‹አይ አላመማትም…ላለፉት አንድ ሰዓት ውስጥ ስንፈልጋት ነበር…የለችም…››
‹‹የለችም ማለት…….?››
‹‹ጓደኞቾ ደብቀው ይዘዋት ሄደው መሰለኝ…. ግቢው ውስጥ የለችም፡፡››
‹‹እንዴ ..ይሄ ምን ማለት ነው..?ያን ሁሉ ጠብደል ጎረምሳ በጠባቂነት የቀጠርኩት እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት ነው እንዴ…?ሰውዬ የእያንዳንዳችሁን ግንባር በሽጉጥ ሳልነድልላችሁ ልጄን ካለችበት ፈልጉና አስረክቡኝ…፡፡››በመራር ንግግር ቀድሞም የደነገጠውን ሰውዬ ይበልጥ ፍርሀት ለቀቁበት፡፡
‹‹እሺ ጌታዬ… ሁሉም ሰው እየፈለጋት ነው፣ይሄንን ነገር እርሶም በሰዓቱ መስማት አለቦት ብዬ ነው ቀድሜ ያሳወቅኳት…››
‹‹ወይኔ ልጄን..ይሄ የእነሱ ሳይሆን ያንተ ጥፋት ነው…››እናትዬው ቁጣቸውን ወደባላቸው አዞሩት፡፡
‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?››ባልና ሚስቶች የተለመደውን ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ፡፡
‹‹ልጄን እንደከብት እረኛ ቀጥረህባት ስታጨናንቃት ነው ለዚህ ያበቃችው፡፡››
‹‹ሴትዬ እስኪ አሁን ተይኝ….እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ.››አሉን ፊት ለፊት እየሄደ ያለውን ጋርድ ተከትለው ኮሪደሩን አቆርጠው መሄድ ጀመሩ..፡፡ወ.ሮ ስንዱም ማጉረምረማቸውን በለቅሶ አጅበው የለበሱትን ቢጃማ እንኳን ሳይቀይሩ ከኃላ መከተል ጀመሩ…፡፡በፀሎት ግን ለሊቱን ሙሉ ብትፈለግ ..በየወዳጅ ዘመድ ቤት ቢደወል…በከተማ አውራ ጎዳናዎች ከሰላሳ በላይ መኪኖችን ተሰማርቶ ብትፈለግ ድካዋን ለማግኘት አልተቻለም…
በስተመጨረሻ የግቢው ካሜራ ቅጂ ለሁለተኛ ጊዜ በዝግታ ሲታይ ነው እራሷን በአለባበሶ ቀይራ ብቻዋን በሞተር ሳይክል ግቢውን ለቃ እንደወጣች የታወቀው፡፡ይሄ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ የነበረውን ድንጋጤና ፍራቻ ይበልጥ አናረው..ምክንቱም አወጣጧ አስባባት መሆኑን ስለተረዱ….፡፡ከዛ አባትዬው አቶ ኃይለመለኮት ያላቸውን ተሰሚነትና ከመንግስት ሰዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በመጠቀም ለእያንዳንዱ ፖሊስና ትራፊክ ፖሊስ ፎቶዋና የሞተር አይነትና ታርጋ ቁጥሩ ተበትኖ እንድትፈለግ መመሪያ እንዲተላለፍ ተደረገ ፡፡
በማግስቱም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ በመንጋቱ እቤቱ ሁሉ በወዳጅ ዘመድ ተጨናነቀ፡፡..ወላጆቹ በስጋትና ፍራቻ ብቻ ሳይሆን በሰው ትንፋሽም መፈናፈኛ አጣ…አቶ ኃይለመለኮት ሲጨንቃቸው ከአጀቡ ተነጥለው ቀጥታ ወደልጃቸው መኝታ ቤት ገብና ከውስጥ ዘግታው አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብለው ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ግዙፍ የልጃቸውን ፎቶ እየተመለከቱ በትካዜ መንሳፈፍ ጀመሩ....እንባቸው መቆጣጠር አልተቻላቸውም…እንደህፃን ልጅ ነው ተንሰቅስቀው ያለቀሱት….በህይወታቸው እንዲህ አይነት ለቅሶ መቼ እንዳለቀሱ ፍጽም ትዝ አይላቸውም….አዎ ልጃቸው የልብ ንቅለተከላ በተደረገላት ጊዜ በህይወታቸው በጣም ያዘኑበትና የተጨናነቁበት ጊዜ ነበር…በቀሪ ህይወታቸውም መቼም ተመሳሳይ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ የሚል ግምት አልነበራቸውም….ግን ተሳስተው ነበረ..አሁን ያሉበት ጭንቀትና ስጋት ከዛን ጊዜም ከፍ ያለ ነው…. ፡፡ልጃቸው አንድ ነገር ብትሆን ምን እንደሚሆኑ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም..፡፡ግን በእርግጠኝነት ሌላ ኃይለመለኮት እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው..ምን አልባት አብደው ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችሉ ይሆናል...ወይንም ንዴታምና አውሬ አይነት ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ….ልባቸው ፍስስ እያለባቸው ነው….አይናቸውን ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከሩ የልጃቸውን እቃዎች በስስት ሲቃኙ አይናቸው አንድ ፖስታ ላይ አረፈ..በድንጋጤ ተነሱና ወደእዛው ተራመድ፡፡ አነሱት… ሁለት ነው…፡፡ከላዩ ላይ የተፀፈውን አነበቡት..፣አንደኛው ለአባዬ ይላል…ሁለተኛውን አዩት ለእማዬ ይላል…እሱን ጠረጴዛው ላይ መልሰው አስቀመጡና ለእሷቸው የተጻፈውን ይዘው ወደአልጋ ጠርዝ ተመላሱና ፖስታውን ቀደው ወረቀቱን በማውጣት ማንበብ ጀመሩ፡፡
አባዬ….እንዴት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል? በጣም ነው የምወድህ..ግን ሁሌ ትናፍቀኛለህ…፡፡ሁሌ እሩቅ ውጭ ሀገር ያለህ ነው የሚመስለኝ….እቤት እያለህ እራሱ የሌለህ መስሎ ነው የሚሰማኝ…እርግጥ አንተ ሁሉ ነገር ተሟልቶልኝ በቅምጥል የምኖር ደስተኛ

ልጅ ነው የምመስልህ…እየቀያየርኩ ምነዳችወ ከሶስት በላይ ዘማናዊ መኪናዎች አሉኝ፣በወር ከመቶ ሺ ብር በላይ በእጄ ይሰጠኛል….በየሄድኩበት እየሄዱ የሚጠብቁኝ ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ጋርዶች አሉኝ……በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የፈለኩትን ውጭ ሀገር ሄጂ እዝናናለሁ…በአጠቃላይ ኑሮዬ ለአብዛኛው ኢትዬጵያዊ በተረት አለም እንኳን ሰምቶት የማያውቀው የህልም አለም አይነት ነው…ግን እኔ በእድሜዬ እናትና አባቴ ሲሳሳሙ አይቼ የማላውቅ ልጅ እንደሆኑክ ማንም አያውቅም..አረ መሳሳሙ ይቅር አንድ መኝታ ቤት ውስጥ አብረው ሲያድሩ አይቼ አላውቅም… አይገርምም…..፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

23 Oct, 06:21


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሶስት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
በፀሎት የልብ ንቅለ ተከላ ካደረገች በኃላ ልክ እንደዛሬው አይነት በህይወቷ ወሳኝ የሆኑ ትላልቅ ውሳኔዎችን አሳልፋለች….አንዳንዴ‹‹ በእውነት እንዲህ እያሰብኩና እያደረኩ ያለሁት እኔው ነኝ?››ብላ በራሷ እስክትደመም ድረስ ነበር ለውጦ፡፡

‹‹አሁን የሌላ ሰው ለዛውም የሞች ንፅህ ልብን በሰውነቴ ተሸክሜ ርካሽ የሆነ ስራ ፈፅሞ አልሰራም››የሚል አቋም ላይ ደርሳ በዛ መሰረት ነው የምትንቀሳቀሰው…ትንሽ ለስሜቷ የማይመችና የሚቆረቁር ነገር ሲያጋጥማት እንደድሮው ‹‹ቆይ እስኪ ልሞክረው›› ብላ ዘላ አትገባበትም….ጊዜ ወስዳና ተረጋግታ ታስብበታለች..ነገሩን ትመዝንና እሷንም ሆነ ሌላውን ሰው የሚያሳዝንና የሚያስከፋ መስሎ ከተሰማት ወዲያው መንገዷን ታስተካክላለች….ይሄ በብዙ ነገሮች ጠቅሟታል…ግን ደግሞ ቤተሰቦቾን በተመለከተ እንደበፊቱ ነገሮችን አይታ እንዳላየች እንድታልፍ አላደረጋትም…እያንዳንዱ በመሀከላቸው ያለው ጥላቻና ጥል በጣም ያስጨንቃትና እረፍት ይነሳት ጀመር…ለምን ብላ እንድትጠይቅ..ጥፋቱ የማንኛቸው ይሆን እያለች እንድትመረምርና ፣እንዴት ሊስማሙና ትክክለኛ ባልና ሚስት ሆነው ለእሷም መቼ እንደ ትክክለኛ ወላጅ የምትፈልገውን ፍቅር ሊለግሶት እንደሚችሉ ማለምና መተከዝ የጀመረችው ከበርካታ ወራቶች በፊት ነው፡፡
በፀሎት ጨረቃ በነገሰችበትና ከዋክብቷች ሰማዩ ላይ ተበትነው በሚንሸራሸሩበት በዛ ውድቅት ለሊት እቤቷን ጥላ ..ከእናትና አባቷ ርቃ …ከጋደርዶቾ አምልጣ መሄዷን እንጂ ወዴት እንደምትሄድ ለምን ያህል ሰዓት መንዳት እንዳለባትና የመንገዷ ማዳረሻ የት እንደሆነ ምንም የምታውቀው ነገር የለም፡፡ዝም ብላ ብቻ በዛ ውድቅት ለሊት የአስፓልቱን መሀከል ይዛ በመድሀንያለም ቤተክርስቲያንን አጠር ተኮ በሚገኘው መንገድ ወደፊት በመውጣት ዋናውን አስፓልት ገባችና ቀጥታ ወደ ስቴዲዬም ሚወስደውን መንገድ ያዘች….መስቀል አደባባዩን እንደጨረሰች ወደግራ ታጠፈችና ወደላንቻ የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ ያዘች..
ከትራፊክ መጨናነቅ ነፃ የሆነውን መንገድ በፍጥነት መጋለብን ተያያዘችው…ምንም ሳታውቀው ለአንድ ሰዓት ያህል ከነዳች በኃላ አቃቂ ድልድይ ጋር ስትደርስ ወደቀኝ ተጠማዘዘችና ወደአቃቂ የሚወስደውን መንገድ ገባች ፣…መንዳቷን ቀጠለች…ድንገት ተረጋጋችና ሞተሩን አቀዝቅዛ አቆመችና አካባቢውን ስታስተውል የምታውቀው ሰፈር ሆኖ በማግኘቷ ደነገጠችም.. ተገረመችም….እዚህ ሰፈርና እዚህ ቦታ ለመምጣት ባለፈው ሁለት አመት ስትመኝ ነበር….ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በህልሟ እዚህ አካባቢ መጥታ ስትዳክር ነው የምታየው..ግን መጥታ የምትፈልገውን ነገር ለማድረግ አባቷ ሊፈቅድላት አልቻለም..ለጠባቂዎችም በጥብቅ ስለተነገራቸው እንኳን አሁን ያለችበት ሰፈር ይቅርና ክፍለከተማው ውስጥም ዝር እንድትል እንዳይፈቅዱላትም ፤ከዚህ ቀደም ምንአልባትም ከአመት በፊት ሰፈሩንና እቤቱን ለአንድ ጊዜ በስንት ጭቅጭቅ ያሳያት እራሱ አባቷ ነበር፡፡

በጊዜው መኪናዋን አሁን ሞተሯን ያቆመችበትን ቦታ አቁሞ…የቤቱን በራፍ በጥቁሩ የመኪና መስታወት ወደውጭ እየጠቆመ…‹‹አየሽ የልጅቷ ቤተሰቦች የሚኖሩት እዚህ ነው..እኛ አሁን የሚገቡት አባቷ ናቸው…አብሯቸው ያለው ደግሞ ልጃቸው ነው….እናትና እህቷም አሉ››እያለ ነበር ያብራራላት፡፡
‹‹አባዬ እንዲት እንዲህ ጭንቁርቁስ ያለ ቤት እንዲኖሩ ትፈቅዳለህ..?እየው እስኪ አጥሩን..እቤታቸውን ተመልከተው››በምሬት አባቷን መጠየቋን ታስታውሳለች፡፡
‹‹ልጄ ምን ላድርግ ?በግድ በወታደር አስገድጄ ሌላ ቤት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አልችል››
‹‹ማለት…?››
‹‹ነግሬሻለሁ እኮ …ቤተሰቡ ከእኛ አምስት ሳንቲምእንደማይቀበሉ ምለው ነው የነገሩን››
‹‹አባዬ ይሄ ምንም ሊገባኝ አልቻለም…የተሸከምኩት እኮ የልጃቸውን ልብ ነው….በልጃቸው ሞት እኮ ነው አሁን እኔ በህይወት መኖር የቻልኩት…አልገባህም አባዬ …ለምን እሷ ሞታ እኔ ኖርኩ..?እግዚያብሄር ይሄን እንዴት ፈቀደ…?.አባዬ በየቀኑ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ነው…እየተሰቃየሁልህ ነው…››
‹‹አውቃለው ልጄ…እነሱ ፍቃደኛ ቢሆኑ እኔ የሀብቴን ግማሽ እንኳን ብሰጣቸውና
..ላደረጉልኝ ነገር ምስጋና ባቀርብ ደስ ይለኝ ነበር…ግን ተቀባይ ከሌላ መስጠት ስለፈለግሽ ብቻ አይሳካልሽም፡፡››
‹‹ቢሆንም አባ ..እኔ ልቧን ሰጥታኝ ህይወቴን እንዲራዘም ያደረገቺኝን ልጅ ቤተሰቦች እንዲህ በጉስቁልና እንዲኖሩ አልፈልግም…..ልጃቸው በህይወት ኖራ ቢሆን ትጦራቸው ነበር…የሆነ የሆነ ነገር ታደርግላቸው ነበር….ብቻ አላውቅም የሆነ ዘዴ ፍጠርና እርዳቸው፡፡››
‹‹አይ ልጄ አልገባሽም እንዴ…ልጃቸው ላንቺ ልብ ከመስጠቷ ከአመታት በፊት በእኛ ፋብሪካ የሚሰራውን ወንድ ልጃቸውን እራሱ ስራ እንዲለቅ አድርገውታል…..ለማንኛውም የተቻለኝን እሞክራለው..አሁን ይሄን ያህል ካየሻቸው ይበቃሻል… አንሂዱ ››ብሎ ነበር ከአካባቢው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለቀቁት፡፡

ከዛ ወዲህ ግን ፍፅም ወደአካባቢው እንድትጠጋና ከቤተሰቡ ጋርም በምንም አይነት መንገድ ተገኛኝታ እንዳትተዋወቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ተሳክቶላቸዋል…አሁን ግን ይሄው በደመ ነፍሷ ከቤቱ ፊት ለፊት አስፓልቱ ጠርዝ ላይ ሞተሯን አቁማ ቁልቁል አዘቅዝቃ እያየችው ነው፡፡
‹‹ወደእዚህ መምጣት በአእምሮዬ ስሌት ውስጥ አልነበረም….ሳስበው ግን የልጃችሁ ልብ ነው እየመራ እዚህ ድረስ ያመጣኝ››ስትል አጉረመረመች፡፡ድንገት ስሜታዊ ሆነችና ነዳጁን ረገጠችና ጨምቃ የያዘዘችውን ፍሬን ለቀቀች…አስፓልቱ ን ለቃ ቀጥታ ወደቤቱ አቅጣጫ መንዳት ጀመረች …የሞተሩ ፍሬን ድንገት እምቢ አላት… ያ ደግሞ ጠቅላላ ሰውነቷ በፍራቻ እንዲቀዘቅዝ ነው ያደረጋት…ሞተሩ ከቁጥጥሯ ውጭ እየወጣ ነው.. መንገድን ሰታ ወደቀኝ እየተጓዘች ነው…›የተውሸለሸለ የእንጨት አጥር ቤት ጥሳ ገባች…. የቆርቆሮ በር ካለው ሰርቢስ ቤት በራፍ ጋር ተላትማ በአየር ላይ ተንሳፈፈችና መሬት ላይ ጧ…ጧጧ ብላ ወደቀች....ሞተሩ አጥሩን ጥሶ ሲገባና ከቆርቆሮ በራፉ ሲጋጭ የፈጠረው ድምፅ የፍንዳታ አይነት ነው….እሷ ወዲያው ነው ጭልም እያለባት የሄደው…እንዲህ ባለ ሁኔታ እራሷን አደጋ ላይ የመጣል እቅድ አልነበራትም…….ከቤት ውስጥ ግን ቡዙ ጫጫታና ትርምስ ተሰማ…
‹‹አማዬ ምንድነው……?››
‹‹.ልጆቼን ..››
‹‹ልጆቼን ››
‹‹አባዬ ሰላም ነህ?››
የሶስት ወይም የአምስት ሰዎች ድምጽ እየተሰማት ነው….እያንዳንዱ ድምፃ ልቧ ላይ እየተንጠባጠ እያቀለጣት ያለ ነው የመሰላት፡፡‹‹ምን ሆኜ ነው …?ምን ተፈጠረ…?ይሄን እያሰበች ሳለ ጭልም እያለባት ሄደ ፣እንደምንም ላለመጥፋት ብትሞክርም አልቻለችም
…እራሷን ሙሉ በሙሉ ሳተች….፡፡እቤቱ ውስጥ ያለ አንድ ጎረምሳ እና አንድ ወጣት ሴት… እናት አባት በዛ ውድቅት ለሊት ፈጣሪ ምን አይነት መብረቅ እንደላከባቸው ለማወቅ በሀይለኛ ድንጋጤ እንደተመቱ የተተራማመሱ የቤታቸውን በራፍ እንደምንም ተራ በተራ እየተጋፉ ወደውጭ ወጡ….የውጭ መብራት አብርተው ሲመለከቱ ..ከበራፉ በሶስት ሜትር ርቀት መሬት ላይ የተዘረጋ ጥቁር እና ነጭ ቀለም የተቀባ ዘመናዊ ሞተር ሳይክል

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

23 Oct, 06:21


ይታያል...ከሳይክሉ ሁለት ሜትር ርቀት አንድ ሄሌሜት ያደረገ ባለመካከለኛ ቁመት ሰው እጥፍጥፍ ብሎ ወድቆ ይታያል....ሁሉም በቃል ሰይነጋገሩ እየሮጡ ሰውዬውን ከበቡት…
‹‹አባዬ…ይሄ ነገር በእኛ እንዳይሳበብ…ከመነካካታችን በፊት ለፖሊስ ደውለን እናሳውቅ፡፡››ወንዱ ልጅ ስጋቱን ለአባቱ ተናገረ፡፡
‹‹ልጄ ገና ለገና እንጠየቃለን ብለን በሰው ህይወት ላይ እንፈርዳለን….?አይ እንደዛ ማድረግ አልችልም›› በማለት…ሰውዬው ተጠጋና ቀስ ብሎ ሄልሜቱን ፈቶ አወለቀው….ረጅምና ዞማ ፀጉሯ ዝንፍል ብሎ መሬቱን ሞላው፡፡ፊቷ በደም ተሸፍኗል፡፡
‹‹በጌታ ሴት ነች››እናትዬው ተናገሩ፡፡
አባትዬው እጁን ወደ ልጅቷ አንገት ላከና በህይወት መኖሯን አለመኖሯን ለማረጋገጥ ሞከረ፡፡‹‹ተመስገን አለች፣ትተነፋሳለች….ቀስ ብለን ወደቤት እናስገባት…››
‹‹እንዴ አባዬ ለፖሊስ እንደውልና እነሱ ሀኪም ቤት ይውሰዷት››ወንዱ ልጅ ስጋቱን መለሶ አስተጋባ፡፡
‹‹አይ…አይሆንም ፡፡በዚህን ሰዓት እንደዚህ አይነት አለባበስ ለብሳ እንዲህ አይነት ሞተር የምትነዳ ሴት የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እርግጠኛ ነኝ፣…ምን ላይ እንዳለች ሳናውቅ ለፖሊስ በመደወል አሳልፈን አንሰጣትም…አይሆንም..ይልቅ ና ከታች ቀስ ብለህ ያዛት
…ወደቤት እናሳገባት….››አባትዬው ጠንከር ባለ ንግግር ውሳኔያቸውን አሳወቁ፡፡
ወጣቱ ሳይመስለው አባትዬው እንዳለው አደረገ ….ወስደው ጠባቧ ሳሎን ከተዘረጋው ልጆቹ ተኝተውበት ከነበረ ባለሜትር ከ20 ፍራሽ ላይ አስተኟት፡፡እናትዬው ቦርሳውን አንጠልጥላ በማስጋበት ወደ ጓዲያ ወስደው አስቀመጡት፡፡ ….ከላይ የለበሰችው ልብስ አወለቁላትና የቆሰለ ወይም የደማ ቦታ እንዳለ መፈለግ ጀመሩ ግንባሯ ላይ ከጀርባ በኩል የሚፈስ ደም አለ ግማሽ ፊቷ ቆዳዋ ተገሽልጦ በደም ተሸፍኗል፡፡ ሌላ ቦታ ሰላም ትመስላለች፣ቢያንስ ለጊዜ የሚታይ ቦታ የለም፡፡
‹‹ምን እናርግ..ፊቷ እኮ በጣም ተጎድቷል…ደሟም እየፈሰሰ ነው..የግድ ህክምና ማግኘት አለባት፡፡››

ሴቷ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረች‹‹እዚህ ከጀርባችን ያለው ኪሊኒክ ለምን አንወስዳትም?››
‹‹በሊሊት ይሰራሉ እንዴ?››
‹‹አዎ ተረኞች አሉ…፡፡››
ወደኪሊኒክ በመውሰዱ ሁሉም ተስማሙ…ወጣቱ ልጅ እና አባትዬው ተራ በተራ እያዘሉ ከቤታቸው ግማሽ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ኪሊኒክ ወሰዷት…ሀኪሞቹ ቁስሏን አፅድተው ግንባሯ ላይ የለውን ስንጥቅ ሰፍተውና ግማሽ ፊቷን በፋሻ ሸፍነው ህክምናቸውን ጨረሱ…ለማንኛውም ሆስፒታል ወስደው ሙሉ ምርመራ እንድታደርግ እንዲያደርጉ አዛው… ሸኞቸው፡፡
እነሱ ግን ቀጥታ ወደቤት ነበር የመለሶት፡፡….እሷ ያ ሁሉ ሲሆን ከገባችበት ከፊል ሰመመን አልነቃችም ነበር፡፡….ከዛ አቶ ለሜቻ ከልጃቸው ከፊራኦል ጋር እየተረዳዱ በማዘል ወደበት ከመለሷት እና መልሰው ካስተኞት በኃላ በዛ ውድቅት ለሊት በሞተሩ የተጣሰውን የውጭ አጥር ወደነበረበት መለሱና ሞተሩን ተጋግዘው ወደውስጥ በማስገባት ጎዲያ ውስጥ አስገብት፡፡
ፊራኦል‹‹አባዬ ምን እያደረክ እንዳለ ምንም አልገባኝም?››ሲል አባትዬውን የጠየቀው
‹‹ልጄ እንደምታያት ልጅቷ ሴት ነች..ወጣት ሴት…..እንዴትም አድርጌ ባስበው በዚህ እድሜ ያለች ሴት ልጅ በሰላም ሆና በዚህ ውድቅት ለሊት ሞተር አትነዳም…ልጅቷ የሆነ ችግር ላይ ነች….››
‹‹እኮ እኔም እኮ ምለው እንደዛ ነው..ችግር ላይ ነች..እኛንም አብራ ችግር ውስጥ ትከተናለች እያልኩህ ነው፡፡››
‹‹ልጄ ስጋትህ ይገባኛል …ትክክልም ነህ፡፡እኔ ግን አባት ነኝ…እንደእሷ ልጆች አሉኝ..ነገ እንሱም የሆነ ችግር ውስጥ ሊገቡ እና እንዲህ የማያውቁት ቦታ በማያውቁት ሰው እጅ ሊወድቁ ይችላሉ ..ለልጆቼ ጡር አላቆይም…ይህቺ ልጅ ከገባችበት ሰመመን ነቅታና ከህመሟ አገግማ የሆነችውን ከነገረችን በኃላ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወስናለን..እስከዛ ግን አይሆንም››
‹‹ከረፈደብንስ?›››

‹‹ከረፈደብን ስትል….?››
‹‹ምን አልባት ባትነቃስ?››
‹‹ተው ልጄ ..እንደዛ አይሆንም….አምላክማ እንዳዛ አሳልፎ አይሰጠኝም፣በል አሁን ተነስ ከብርድ ላይ እንግባ፡፡››
አካባቢው ትኩረት የሚስብ ነገር አለመኖሩን ካረጋገጡ በኃላ ከለሊቱ 10 አካባቢ ለመተኛት ወደውስጥ ተያይዘው ገቡ…እናትዬው እና ለሊሴ የለሌት እንግዳዋን በግራና በየቀኝ አጅበው በድንጋጤ እንዳፈጠጡ ቁጭ ብለዋል….፡፡
እናትዬው ወ.ሮ እልፍነሽ አንዴ ጓዳ ፤ሌላ ጊዜ ሳሎን ይመላለሳሉ…መልሰው ደግሞ ከጎኗ ቁጭ ይላሉ… በፍራቻና ግራ በመጋባት እህህ እያሉ ያጉረመርማሉ‹‹ይሄኔ እናቷ አላየቻት፣ወይ የሰው ልጅ፣አሁን እሺ ባትነቃስ?››ብቻቸውን ይለፈልፋሉ፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

22 Oct, 08:14


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሁለት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
በፀሎት በእንባዋ እና ሜካፕ ቅልቅል የተበላሸውን ፊቷን በሳሙና ታጠበችና አፀዳችው….መልሶ ሜካፕ መጠቀም ሳያስፈልጋት ቀጥታ ወደሳሎን ሄደች፡፡ከላይ ከአንደኛ ፎቅ እስቴሩን ተጠቅማ ወደታች ስትወርድ በመጀመሪያ አይኗ የገቡት እናትና አባቷ ነበሩ… ጎን ለጎን ተጣብቀውና እጅ ለእጅ ተቆላልፈው…በየመቀመጫው እየተዞዞሩ እንግዶቹን ያዋራሉ፡፡‹‹እንኳን ሰላም መጣችሁ›› እያሉ የውሸት የተጠና ሳቅ ይስቃሉ፡፡ከአስር ደቂቃ በፊት እንደዛ በፀያፍ ቃላት ሲጠዛጠዙ ላያቸው ሰው አሁን በእንደዚህ አይነት ቅርበት መጣበቅ ይችላል ብሎ ማንም ሊያስብ አይችልም፡፡
‹‹ሰላም ተስፋዬ እና ሰላሞን ቦጋለ እንኳን የእናንተን ገፀ ባህሪ ቢሰጣቸው በዚህ ልክ አስመስለው መጫወት መቻላቸውን በጣም እጠራጠራለሁ፡፡››እያለች ወደታች ወርዳ መድረኩ ላይ ወደተዘጋጀላት የክብር ቦታ ሄዳ ተቀመጠች፡፡ወዲያው እሷን ብለው የመጡ የሰፈርና የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቾ ዙሪያዋን ከበቧት..እሷም ወላጆቾን እንደአርአያ ወስዳ የውስጧን ብስጭትና ንዴት በሆዷ ቀብራ አንድ ልደቷ እየተከበራላት እንዳለ ደስተኛ ቀበጥ የሞጃ ልጅ በፈንጠዝያና በፌሽታ ልደቷን ማክበሩ ላይ ትኩረቷን አደረገች….፡፡
ከመቀመጫዋ ተነሳችና ከእናቷ ጋር ደነሰች…ከዛ ከአባቷም ጋር ደነሰች…እናም በሁለቱ መሀከል ሆና ለሶስት ሆነው እንዲደነስ አደረገች….ይሄ እንቅስቃሴያቸው እያንዳንዱ ዳንሳቸውና የእርስ በርስ መተቃቀፋቸው በፕሮፌሽናል ቪዲዬ ማን እየተቀረፀና ፎቶም እየተነሳ መሆኑን ታውቃለች….ለዛም ነው እንደዛ እያደረገች ያለችው‹‹ልጄ እስከዛሬ ከነበረው ልደትሽ ሁሉ ይሄ ልዩ ነው…ይሄው ሀያ አንድ አመት ሙሉ ያንቺን ልደት ሳከብር አንድ ቀን አብሬሽ እንድደንስ ጋብዘሺን አታውቂም ነበር….ዛሬ ግን…››ለሶስት ሆነው እጅ ለእጅ ተያይዘው በመደነስ ላይ ሳሉ ነበር አባቷ ስሜታዊ ሆኖ የተናገረው፡፡
እናትዬውም ወዲያው ነበር የራሷን ሀሳብ ያስቀመጠችው‹‹አባትሽ እውነቱን ነው….እኔም ብሆን ከልጄ ጋር የመደነሱን እድል ሳገኝ ይሄ የመጀመሪያ ቀኔ ነው…በጣም ደስ ብሎኛል፡፡››
‹‹እርስ በርሳችሁስ?››ስትል ሁለቱንም ያስደነገጠ ጥያቄ ጠየቀቻችው፡፡
‹‹ማለ…ት?››እናትዬው በተለጠጠ ንግግር ጠየቀቻት፡፡
‹‹አንቺና አባዬ እንዲህ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ከደነሳችሁ ምን ያህል አመት ሆናችሁ?››ጥያቄውን አፍታታ ደገመችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ ልጄ እኔ አላስታውሰውም…..ምን አልባት አንቺ ከመወለድሽ በፊት ይመስለኛል››አባትዬው መለሰ፡፡
‹‹አያችሁ..ልጅ ወላጆቹ የሚያወሩትን ሳይሆን የሚያደርጉትን ነው ኮርጆ ደግሞ የሚያደርገው..እናንተ በዚህ መልክ ስትደንሱ አይቼ ስለማላውቅ ነው እኔም ላደርገው ያልቻልኩት…ፍቅርን በተመለከተ ጥሩ አርአያዎቼ አልነበራችሁም ማለት ነው..አዎ እውነቱ እንደዛ መሰለኝ፡፡››
‹‹አይ ያ እውነት አይደለም፡፡ልጄ እኛ በጣም እኮ ነው የምንወድሽ፡፡››
‹‹እሱ አይደለም ጥያቄው..እናንተስ እርስ በርስ እንዴት ናችሁ…..?ከመሀከላችሁ ማንኛችሁ ናችሁ የታመማችሁት….?ምናችሁን ነው የሚያማችሁ….?እንዴት ነው ይሄን ሁሉ አመታት እርስ በርስ መጠላላት የማይደክማችሁ…..?እንዴት አንዳችሁ እንኳን አትሸነፉም….?ለማንኛውም እኔ ማውራቱ ደከመኝ …ይብቃን…..ከአሁን ወዲህ ልደት ብዬ ስለማልደግስ የዛሬው የመጨረሻችን ነው፡፡››
‹‹የመጨረሻ ማለት?››አሁንም ልጃቸሁን እንደአምስት አመት ህጻን የሚያዩት አባቷ ኮስተር ብለው ጠየቁ፡፡
‹‹አባዬ አትኮሳተር ፡፡አሁን ሀያ አንድ አመት ሞላኝ…እራሴን ችዬ ከቤት መውጪያ ጊዜዬ ከመድረሱም በላይ እያለፈብኝ ነው…በእናነተ ላይ መንጠልጠልና መደገፍ ይበቃኛል…ከነገ ጀምሮ ጋርዶችህ እንዲከተሉኝ አልፈልግም….በሹፌርም አልንቀሳቀስም…..በአጠቃላይ እንደምርኮኛ ወፍ ለዘመናት ካስቀመጥከኝ ጎጆ በሩን ሰብሬ ወጣላሁ ..ክንፌን በሰፊው ዘርግቼ በሰፊው ሰማይ ላይ ባሻኝ አቅጣጫ በራለሁ..አንተም ልታስቆመኝ ያለህ ኃይል በሙሉ በቂ አይሆንም፡፡››
ይሄ ንግግር በሁለቱም ወላጆች ላይ መብረቃዊ ድንጋጤ ነው ያስከተለው‹‹ልጄ እንዲህ አይነት ቀልድ ከመቼ ወዲህ ነው መቃላለድ የጀመርነው..?ይሄ እቤት ዘመንሽን ሁሉ የምትኖሪበት ያንቺ የእድሜ ልክ ቤተመንግስት ነው…እዚሁ አግብተሸ እዚሁ ወልደሽ እዚሁ ነው የምታረጂው..ይሄን ምን ጊዜም ከአእምሮሽ እንዳታወጪው፡፡››
‹‹አባዬ… እናንተም መቼም ቢሆን ይህቺን ቀን ከአእምሮችሁ አታውጧት….››

‹‹እሺ ልጄ አሁን ለእንዲህ አይነት ጭቅጭቅ ጊዜው አይደለም… በድጋሚ መልካም ልደት..››
‹‹አመሰግናለው ..››ብላ ሁለቱንም በየተራ ጉንጫቸውን ሳመችና ልርገፍ እያለ የሚታናነቃትን እንባዋን እንደምንም ከትራ ወደመቀመጫዋ ተመሰችና ከጓደኞቾ ጋር ተቀላቀለች፡፡፡

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

22 Oct, 08:14


የልደት ዝግጅቱ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የጀመረ ሲሆን እሰከአራት ሰዓት ያለው ዝግጅት ለሁሉም የሚሆን ሰከን ያለ ሙዚቃ ያለበት የምግብና የመጠት መስተንግዶ ጨምሮ… የተረጋጋ የእርስ በርስ ጫወታ… የኬክ ቆረሳና.. የሻማ ማጥፋት ስርአት …የስጦታ ዝግጅት የተደረገበትና የተለመደ አይነት ነበር…ከአራት ሰዓት በኃላ ግን ጠና ጠና ያሉት ሰዎች አባትና እናቷንም ጨምሮ ግዙፍንና የተንጣለለውን ሳሎን ለወጣቶቹ ለቀው በመሰናበት ሄዱ፡፡የዝግጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ተቀየረ..ሙዚቃዎቹ የፈጠኑና የሚያስጨፍሩ ሆኑ፤ መጠጡ የጠነከረና አስካሪ እየሆነ ሄደ….ይሄም ሆኖ ግን በፀሎትን የሚጠብቁ ሁለት ጋርዶች የሳሎንን የግራና ቀኝ በራፍ ይዘው በተጠንቀቅ እንደቆሙ ነው፡፡እሷም በአይነ ቁራኛ እያየቻቸው ነው…በየሆነ ደቂቃ ልዩነት መጠጥ እንዲወስዱላቸው ለአስተናጋጆቹ መልዕክት ማስተላፏን ፈፅሞ አትረሳም…..መጀመሪያ ስራ ላይ ስለሆኑ መጠጥ እንደማይጠጡ በመናገር መልሰው ነበር..በኃላ ግን እራሷ ሄዳ ‹‹በልደቴ ቀንማ ቢያንስ አንድ ጠርሙስ መጠጣት አለባችሁ ››ብላ እንዲቀበል አስገደደቻቸውና ተቀበሏት…በአንድ ብቻ ግን አላቆሙም፤ አራትና አምስት መደጋገም ቻሉ..፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት አልፎ ሰባት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ሰክሮ ሚለፋደደው በዛ….በፀሎት ግን ከመጀመሪያም ጀምሮ እየጠጣች አልነበረም ….ዛሬ የምትጠጣበት ቀን እንዳልሆነ ከመጀመሪያውኑ ነው የወሰነችው…እንደምንም ጋርዶቹን በጥንቃቄ እያየች…እየተሹለከለከች የፎቁን ደረጃ ተያያዘችውና ወደላይ ወደመኝታ ቤቷ አመራች…ከፍታ ገባች እና መልሳ ከውስጥ ቆለፈችው፡፡

የለበሰችውን ቀሚስ በፍጥነት አወለቀችና ቅድም አዘጋጅታ የነበረውን ጅንስ ሱሪ ለበሰች…፡፡ወርቃማ አርቴፊሻል ፀጉሯን አወለቀችና ጥቁር ሆኖ ከኃላ ረጅም ከፊት አጭር ሆኖ ከፊል ግንባሯን ሚሸፍን ሌላ ፀጉር አጠለቀችና ከላይ ኮፍያ ያለው ጥቁር ጃኬት ደረበችበት፡፡ አይኗ ላይ ጥቁር መነፅር ሰካችና መስኮቱን ከፈተች…፡፡
…መለስተኛ የቆዳ ሻንጣዋን ከአልጋዋ ላይ አነሳችና በጀርባዋ አንጠለጠለችው… አዎ በጀርባ የሚገኘውን የአደጋ ጊዜ መውጫ ተጠቅማ ወደ ምድር መውረድ ጀመረች፡፡ይሄንን መወጣጫ ልጅ እያለች ጀምሮ በጣም ትፈራዋለች፡፡ መጀመሪያ ቀኝ እግሯን አስቀደመች
…….ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት..የሆነ ስህተት ፈጥራ እግሯ አዳልጦት ከመወጣጫው ላይ ተንሸራታ ብትፈጠፈጥ ሁሉ ነገር እንደሚያበቃለትና የአሰበችውን አንዱንም ሳታሳካ እግረ ሰባራና አካለ ጎዶሎ ሆና ለሌላ ስቃይ እደምትዳረግ አሰበችና ዝግንን አላት…በአእምሮዋ የተፈጠረው ክፉ ሀሳብ እዳይፈጠር እየጸለየች..በጥንቃቄ ወደታች መውረዷን ተያያዘችው…ምንም እንኳን ያን የአደጋ ጊዜ ጠባብ መወጣጫ ተጠቅሞ ወደታች መውረድ ሊወስድ ከሚገባው የጊዜ ስሌት በላይ የወሰደባት ቢሆንም ግን ደግሞ ምንም ክፉ ነገር ሳይከሰትባት ሻንጣዋን እንዳዘለች መውረድ ቻለች…ከዛ በግቢው ውስጥ ባሉ የጽድ ዛፎች እየተከለለች፣ከጀርባ ወደሚገኘው ገራዥ አመራች..የአባቷ ታናሽ ወንድም አልፎ አልፎ የሚጠቀምባት ሞተር ሳይክል ወደ ቆመበት ስፍራ አመራችና ቀድማ ሄልሜቱን አንስታ ጭንቅላቷ ላይ ከሰካች በኃላ መተሩን አስነስታ ቀጥታ ወደመውጫው በራፍ አስፈነጠረች፡፡…ወጪ ገቢ ስላለ የውጪ በራፍ አንደኛው ተካፋች ወለል ብሎ እንደተከፈተ ነው፡፡
ዘበኛው ሞተሩን ቢያውቃትም ማን እየነዳት እንደሆነ መለየት አቅቶት ላስቁም ወይስ ልፍቀድ…? በሚል ግራ መጋባት ውስጥ ሳለ ምንም እንዲል እድል ሳትሰጠው አስፈንጥራ የግቢውን ድንበር ጥሳ ዋናው አስፓልት ላይ ወጣች፡፡ ዘበኛው የፈለገ ቢገምት የቤቱ ቅምጥል ልጅ ትሆናለች ብሎ ሊገምት እንደማይችል እርግጠኛ ነች…ዘበኛው ሞተርም እንደምትነዳ እንኳን አያውቅም…
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

21 Oct, 06:34


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አንድ
22 አመቷ ነው፡፡እንዲሁ ከውጭ ለሚመለከታት ሰው ሁሉ የተሟላላት እንከን አልባ ውበት ይዛ እንከን አልባ ኑሮ እየኖረች በእንከን አልባ ደስታ የምትሰቃይ ቅምጥልጥል እድለኛ ነው የምትመስለው፡፡ ግን ቀርቦ ህይወቷን በጥልቀት ላጠና እህ ብሎ የውስጧን ላደማጠ ምን ያህል የማይደረስበት ሽንቁር በህይወቷ እንዳለ በቀላሉ ይረዳል…ግን ያንን እሷን የመቅረብን እድል የሚያገኝ ሰው ጥቂት ነው ..ወይም ጭሩሱኑ የለም……እንዴት ተደርጎ..፡፡
አባቷ በሀገሪቱ ከሚገኙ ጥቂት ቢሊዬነሮች አንድ ናቸው፡፡ቢሊዬን ብር ያላቸው ሰውዬ የወለድት አንድ ልጅ ብቻ ነው…አንድ ብቸኛ ሴት ልጅ፡፡በዛ የተነሳ የበዛ እንክብካቤ፤ ለከቱን ያለፈ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገባት ያለች ልጅ ነች፡፡እርግጥ ቁጥጥሩ ከጊዜ በኃላ የመጣ ነው፡፡እስከ15 ዓመቷ ድረስ በነፃነት ነፃ ሆና ያደገች ልጅ ነበረች…ከ15 ዓመቷ በኃላ ግን ከጤንነቷ ጋር በተያያዘ ነገሮች የተለየ መልክ ያዙ….፡፡
በፀሎት የልብ ህመምተኛ መሆኗ የታወቀው ከ15 ዓመቷ በኃላ ነበር ፡፡ አ17 ዓመት ከሞላት በኃላ ግን ነገሮቸ ፈር ለቀቁና ህመሟ ከፍተኛ ደረጃ ደረሰ…በየሄደችበት ቦታ የተለየ ነገር ገጥሟት ትንሽ ስትጨናነቅ መውደቅና እራሷን መሳት ስትጀምር…24 ሰዓት በክትትል ስር እንድትሆንና ጠባቂዎች ከአጠገቧ እንዳይለዩና በመንገዷ ሆነ በማንኛውም እንቅስቃሴዋ ምንም አይነት እንከን እንዳያጋጥማትና ካጋጠማትም በፍጥነት አፋፍሰው ሆስፒታል እንዲወስዷት የታቀደ የጥንቃቄ እርምጃ በአባቷ ተወሰደ ..በዚህ ውሳኔ መሰረት ሳትወድ በግዷ ነፃነቷም ተነጠቀ፡፡
በፀሎት በአስተዳደጓ ምክንያት ገና የታዳጊነት ህይወቷን ሳታገባድድ ነው ህይወት ስልችት ያለቻት፡፡ አቶ ኃይለ መለኮት ስጦታው ሀብታቸውን ተከትሎ ባለዝና እና ታዋቂ ከመሆናቸውም በላይ የተናገሩት የሚደመጥላቸው፤ ያዘዙት የሚፈፀምላቸው ተፈሪ ሰው ናቸው፡ወይዘሮ ስንዱ መሸሻ የአቶ ኃይለ መለኮት የትዳር አጋር ናቸው..አብረው በጋብቻ 28

ዓመት አሳልፈዋል፡፡ከዚህ ውስጥ በዚህ ትዳር ውስጥ ፍቅር አብሯቸው የነበረው ለስምንት ዓመት ያህል ብቻ ነበር፡፡ከዛ በኃላ አንድ ቤት በጋራ ተጋርተው ከሚኖሩ ዳባሎች የተለየ ትርጉም ያለው ትዳር አልነበረም..አንደውም እርስ በርስ በእየእለቱ እያደገ የሚሄድ ጥላቻ…አንዱ ሌለኛውን ለማበሳጨትና ደስታ ለመንጠቅ የሚደረግ ተንኳልና አሻጥር እናም ደግሞ ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድ እስከመመኘት የሚደረስ የበቀል ስሜት …..በቃ በጋብቻቸው ውስጥ ያለው ነገር ይሄ ነው፡፡አዎ ሁለቱም ወላጆቾ በመረረ የእርስ በርስ ጥላቻ ነፍሳቸው የበከተ..አንደኛው የሌለኛውን ጉዳት ብቻ ሳይሆን ሞትም ጭምር አምርሮ የሚመኝ.. አንድ ህንፃ ውስጥ በሚገኝ ሁለት ክፍል ውስጥ ተነጣጥለው የሚተኙ….የጋራ ጣሪያና የጋራ ሳሎን ስለሚጠቀሙ የሚቀፋቸው…..የሁለት አለም ሰዎች ናቸው..ወላጆቾ፡፡ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ሁለቱም በእኩል ደረጃ ከልባቸው የሚያፈቅሩት አንድ ነገር አለ..ልጃቸውን፡፡ብቸኛ ልጃቸው በፀሎት…፡፡ ከተጋቡ ከስድስት አመት በኃላ በስንት ስለትና የህክምና እርዳታ ነው የወለዷት..ስሟንም በፀሎት ያሏት በፀሎት አገኘንሽ ለማለት ፈልገው ነው፡፡ከእሷ በፊትም ሆነ ከእሷ በኃላ ሁለቱም ሌላ ልጅ አልወለዱም….ሳይፈልጉ ቀርቶ አይደለም…እንዴትስ ላይፈልጉ ይችላሉ?፡፡ የዚህን ሁሉ ሀብት ወራሽ ሚሆን ስድስት ሰባት ልጆች ቢኖራቸው ምን አልባት በመሀከላቸው ያለው መራራቅና ጥላቻ የዚህን ያህል ሊንቦረቀቅ አይችልም ነበር ብላው ብዛዎች ያወራሉ….…ያም ሆነ ይህ አሁን በዚህ ወቅት ከ28 ዓመት የጋብቻ ቀይታ በኃላ ሆድ ከጀርባ በሆነ ግንኙነት የ22 ዓመት ልጃቸው የልደት በዓል በጋራ በአማረ እና በሸበረቀ ሁኔታ ለመክበር ሽርጉድ እያሉ ነው፡፡
አዎ በፀሎት ዛሬ የልደቷ ቀኗ ነው ፡፡ የ22 ዓመት የልደት በዓሏ፡፡በዚህም ምክንያት ቦሌ ከመድኃንያለም ቤተክርስቴያን ጀርባ ሁለተኛ መንገድ ላይ በሚገኘው ቤታቸው ድል ያለ የልደት ዝግጅት አዘጋጅተው ከ100 በላይ ሰዎች ተጠርተዋል፡፡እርግጥ ይሄን የልደት ዝግጅት ቀደም ብላ አልፈለገችውም ነበር፡፡አቧቷ ነው ችክ ብሎ ካልተደገሰ ያለው፡፡በኃላ እሷም በዝግጅቱ ደስተኛ ሆነች፡፡በዝግጅቱ ላይ ከታደሙት መካከል ግማሽ ያህሉ የእሷ የዩኒቨርሲት ጎደኞቾ እና መሰል እኩዬቾ ናቸው፡፡ቀሪዎቹ ደግሞ የሁለት ተፃራሪ ፓርቲ የጋራ ስብሰባ ላይ የታደሙ የሚመስለው የእናቷ እና የአባቷ የቅርብ ሰዎችና የስራ ባለደረቦች ናቸው፡፡
የድግሱን መስተንግዶ ሆነ የመጠጥና የምግብን ዝግጅት በሀላፊነት ወስዶ እያዘጋጀ ያለው በከማው አሉ ከተባሉት ሆቴሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ዲጄ ከመቀጠሩም በላይ የራሱ ባንድ ያለው አንድ ታዋቂ ድምፃዊ በዝግጅቱ ላይ ተገኝቶ ዘፈኑን እንዲያቀርብ ተደርጎል፡፡ለአንድ

የ21 አመት ቀንበጥ ወጣት ልደት 3 ሚሊዬን ብር ወጪ ሆኗል ቢባል ማን ያምናል…?ግን የሆነው እንደዛ ነው፡፡
በጸሎት ለልደት በዓሏ በልዩ ትዕዛዝ በሀገሪቱ አለች በተባለች ዲዛይነር የተዘጋጀላትን ውብ ቀሚስ ለብሳ ብዙም ያልደመቀ የተወሰነ ሚካፕ ነካ ነካ አድርጋ የምትወደውን ከፈረንሳይ የተላከለላትን ሽቶ ነስነስ አድርጋ አጠር በለፀጉሯ ላይ 50 ሺ ብር የተገዛ ዘንፋላ ባለ ወርቃማ ቀለም የኢጣልያን ፀጉር ደርባበት በከፊል የተለወጠና የተቀየረ መልኳን ይዛ ከክፍሏ ወጣች..አንደኛ ፎቅ ላይ ካለ መኝታ ቤቷ ቀጥታ የልደት ዝግጅቱ ወደሚካሄድበት ምድር ቤት ወደሚገኘው ግዙፉ ሳሎን ከመሄዷ በፊት ወላጆቾ ወደታች መውረድ አለመውረዳቸውን ለማረጋገጥ ከእሷ መኝታ ቤት በተቃራኒው ኮርነር ጎን ለጎን ወደሚገኘው የወላጆቾ መኝታ ቤት አመራች፡፡መጀመሪያ የሚገኘው የእናቷ መኝታ ቤት ስለሆነ በቀስታ ቆረቆረች..ከውስጥ መልስ እየጠበቀች ሳለች ቀጥሎ ካለው የአባቷ መኝታ ቤት የእናቷን ድምፅ ሰማች…፡፡…ግራ ገባት››
‹‹ወይ..ዛሬ ሰላም ሰፍኗል ማለት ነው… እንደዛ ባይሆን እማዬ አባዬ መኝታ ቤት አትገባም ነበር››ብላ አሰበችና በደስታ ፈገግ ብላ ወላጆቾን ላለመረበሽ ፊቷን አዙራ ልትመለስ ስታስብ በጆሮዋ ሾልኮ የገባው ጠንከር ያለ የእናትዬው ንግግር ከእርምጃዋ ገታት፡፡
ቆም አለች ….ጥርት ብሎ እየተሰማት አይደለም..ፊቷን መለሰችና ወደአባቷ መኝታ ቤት ቀረበች..ጆሮዋን በራፉ ላይ ለጠፈች….ሰቅጣጭ ንግግር እየተመላለሱ ነው፡፡
‹‹እስኪ ከውሽሞችህ መካከል አንዷን እንኳን መርጠህ ብትጠራ ምን አለበት…? ሶስት ውሽሞችህን በአንድ ቤት፣እኔን እሺ ግድ የለም ለእነሱ ስሜት አትጨነቅም…ነው እርስ በርስ አይተዋወቁም..?››
‹‹አሁን ለምንድነው የምትነዘንዢኝ…….?ከፈለግሽ አንቺም ውሽሞችሽን መጥራት ትቺያለሽ››
‹‹በእውነት እንዴት ደግ ነህ እባክህ…..እንኳን ውሽማዬን ወንድ ጓደኞቼን መጥራት እንደማልችል አንተም እኔም እናውቀዋለን››
‹‹ለምን ?ምን ችግር አለው..?ድግሱ እንደሆነ የተትረፈረፈ ነው!!››በሹፈት ቃና የታሸውን የአባትዬውን መልስ ሰማች፡፡

‹‹አዎ የተትረፈረፈ ነው…ግን ውሽማ የለኝም እንጂ ቢኖረኝም ላንተ ስለማስብ አልጠራውም››
‹‹ለምን ?››
‹‹ሌላ የሰው ነፍስ በእጅ እንዲጠፋ አልፈልግም....ምን አይነት ቀናተኛና በሽተኛ እንደሆንክ እኔም አንተም እናውቃለን…እስከዛሬ ገና ለገና ከአንቺ ጋር አወሩ ብለህ ስንት ወዳጆቼን አስገደልክ?፡፡››
‹‹ወዳጆችሽን ወይስ ውሽሞችሽን…?ለማንኛውም..ያለመረጃ ሰውን አትወንጅይ››

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

21 Oct, 06:34


‹‹እኔ እኮ ነኝ ..ምን ያህል ጨካኝና ነፍሰ ገዳይ እንደሆንክ በደንብ አውቃለሁ….እርግጥ ቀጥታ ቃታ ስበህ ሰውን አትገድልም…ውሾችህ ግን የጠላሀውን ሰው ሁሉ ሄደው ቦጫጭቀው እንዲገድሉት በአንድ ቃል ታዛቸዋለህ..እነሱም በየጊዜው ለምትጥልላቸው አጥንት ሲሉ አድርጉ ያልካቸውን ያለማቅማማት ይደርጉታል…››
‹‹እሺ አሁን ቢበቃሽ አይሻልም..?ሳሎን ሙሉ እንግዶችን ሞልተን እኔና አንቺ እዚህ በማይረባ ነገር አንጨቃጨቅ..ግድ የለም..ስድብና ዘለፋሽን ነገ ካቆምሺበት ትቀጥይዋለሽ…የት እሄድብሻለው?››
‹‹አሹፍብኝ…..አንድ ቀን ትክክለኛው ቀን መጥቶ እኔም በተራዬ አሾፍብህ ይሆናል!››
በፀሎት ከዚህ በላይ የወላጆቾን ጆሮ የሚበጥስ ሰቅጣጭ ጭቅጭቅ ማዳመጥ አልፈለገችም…እንባዋን እያንጠባጠበች በሩጫ ወደክፍሏ ተመለሰች፡፡
‹‹በቃኝ…..ለእነዚህ ሰዎች እኔ አልገባቸውም….በቃኝ…..››ቀኝ እጆን አነሳችና ልቧ ላይ አስቀመጠች…የሆነ ሸክም ነገር ልቧ ላይ እንደተጫነባት እየተሰማት ነው፡፡‹‹አልችልም…በእናንተ ምክንያት ባደራ የተቀበልኩትን የሰው ልብ ማበላሸት አልፈልግም…..››ከቁም ሳጥኗ በላይ የተሰቀለውን ሻንጣ ወንበር ላይ ቆማ አወረደች..ኮመዲኖዋን ከፈተችና በተለያየ ጊዜ ለተለያዩ ወጪዎች ከወላጆቾ የሚሰጣትን ስፍር ቁጥር ከሌለው ገንዘብ ውስጥ እየተረፋት እንደቀልድ ወርወር እያደረገች ያከማቸችውን ብር እየዛቀች ሙሉ በሙሉ ወደሻንጣው ከተተች…ከዛ ሁለት ሱሪ ፤ ሁለት ቲሸርት የተወሰኑ ፓንቶችን ጨመረችና ፣ዚፑን ዘጋች..፡፡ከዛ ሌላ ጅንስ ሱሪ ቲሸርትና ባለኮፍያ ጠቆር ያለ ጃኬት መረጠችና አልጋው ላይ ዝግጁ አድርጋ በማስቀመጥ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች…፡፡
ነገ ይቀጥላል……

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

17 Oct, 14:41


🐯ርዕስ-ጉዞ በፀሎት
🐯ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
👍ረጅም ልብ ወለድ
የሚቀርበው- ከመጪው ስኞ ጀምሮ በየቀኑ ከእሁድ በስተቀር
🤝በፍቅር እና በጋብቻ ስነ-ልቦና ላይ ያተኳረ ስራ ስለሆነ በግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶች ቢያነብት በህይወታቸው የሚመነዝሩት የሆነ ጠቃሚ ሀሳብ እንደሚያገኙበት እርግጠኛ ነኝ።
👍አመሰግናለሁ...የስኞ ስው ይበለን

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

16 Oct, 10:37


🤙በፍፁም እናንተ ሰዎች የሚሏችውን አይደላችሁም!!!

በአምፖል የፈጠራ ውጤቱ የምናውቀው ቶማስ አልቫ ኤድሰን አንድ ቀን ከትምህርት ቤቱ ወደ ቤት የተመለሰው መምህሩ የሰጠውን ወረቀት ይዞ ነበር፡፡ እናም ኤድሰን
ለእናቱ እንዲህ አላት “መምህሬ ይሄን ወረቀት ለእናትህ ብቻ ስጣት ብሎ ሰጠኝ” በማለት ወረቀቱን አቀበላት፡፡
እናት እንባ በአይኖቿ ሞልቶ በወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ሀሳብ ለልጇ አነበበችለት፡፡ ያነበበችለት ሀሳብም ይህ ነበር “ልጅሽ በአስተሳሰቡ ምጡቅ (ጀኒየስ) ነው፡፡ ይሄ ትምህርት ቤት ለእሱ አይመጥነውም ፡፡ ለእሱ ብቁ የሆኑ መምህራኖችም ትምህርት ቤቱ የሌለው በመሆኑ እባክሽ አንቸው አስተምሪው ይላል” በማለት እንባዋን እየጠራረገች ወረቀቱን አጣጥፋ መሳቢያ ውስጥ
ከተተችው፡፡
-
እናቱ ካረፈች ከብዙ ዓመታት በኋላ ኤድሰን በክፈለ ዘመኑ ካሉ የፈጠራ ውጤት ባለቤቶች አንዱና ቀዳሚው ከሆነ በኋላ አንድ ቀን እናቱ እቃዎቿን የምታስቀምጥበትን መሳቢያ ማገላበጥ ጀመረ፡፡ ባጋጣሚ የተጣጠፈች ወረቀት ከመሳቢያው ጠርዝ አካባቢ ተሰክታ ይመለከትና
አንስቶ ከፈታት፡፡ ወረቁ ልጅ እያለ ከመምህሩ ለእናቱ ብቻ እንዲሰጥ ታዞ የተሰጠው ወረቀት እንደነበር አውቋል፡፡ ከፍቶ ሲያነበውም ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ሀሳብ እንዲህ ይላል “ልጅሽ የአእምሮ ችግር ያለበትና ዘገምተኛ ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ወደ ትምህርት ቤቱ እንዲመጣ አንፈቅድለትም” ይላል፡፡
-
ኤድሰን ለሰዓታት ካለቀሰ በኋላ ደያሪውን ከፍቶ እዲህ ሲል ጻፈ “ቶማስ አልቫ ኤድሰን አእምሮው ዘገምተኛ የተባለ ልጅ ነበር፡፡ ነገር ግን በጀግናዋና በልዩዋ እናቴ የምእተ ዓመቱ ጂኔስ ሁኛለሁ፡፡” እናትን መግለጽ እጅግ አዳጋች ነው፡፡በፊደል ገልጸው ሊያስቀምጡት የሚያዳግት ተፈጥሯዊ ጸጋ እናትነት ይመስለኛል፡፡ እጅ አትስጡ፤ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ በራሳችሁ ተማመኑ፣ ማንኛውንም ትግል ሁለት ጊዜ ነው። የምናሸንፈው ቀዳሚውም በአእምሮ ውስጥ የሚያልቀው ነው ይለናል ቶማስ ኤድሰን፡፡ እኔ በሙከራዬ አልወደኩም፤ የማይሰሩ አስር ሽህ መንገዶችን ለይቻለሁ እንጅ ይላል ተስፋ ላለመቁረጥ በአይነተኛ ተምሳሌትነት ቀድሞ ሊጠቀስ የሚችለው ቶማስ አልቫ ኤድሰን፡፡

via-#ራስን መለወጥ

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

12 Oct, 04:54


📌📌ትርምስ እና ስርአት (Chaos and order)

📍ትርምስ(chaos) በራሱ ያለማወቅ ጎራ ነው ። ያልተገለጠ ግዛት እንግዳ ነገር ነው። ትርምስ ማለት የት እንዳለን በማናወቅበት ጊዜ ያለንበት ቦታ ነው።

📍ስርአት(order) ደግሞ የተገለጠው ግዛት ነው። ስርአት የማህበረሰብ መዋቅር፣ የረገጥነው መሬት እና ለቀናችን ያለን እቅድ ነው። ስርአት ይሞቃል! ብርሃን የሞላበት ህጻናት በደስታ የሚጫወቱበት ደህነነቱ የተጠበቀ ሳሎን ነው። ስርአት የሃገር ባንዲራ ፣ሃይማኖት፣ ቤት እና ሃገር ነው።

📍 ስርአት የአለም ባህሪ ከምንጠብቀው እና ከመኞታችን ጋር የሚገጥሙበት ቦታ ነው።

የምንትንሸራተቱበት በረዶ ጠጣር ሁኖ ሲያንሽራትታችሁ የምትወዱት ጓደኛችሁ ሲታመናችሁ ስርአት ወስጥ ናችሁ። በረዶው ተሰብሮ ሲያሰምጣችሁ ያው ጓደኛችሁ ሲክዳችሁ ትርምሱ ይጀመራል።

🧷 ስርአት በቂ አይደለም።ዝም ብላችሁ ባላችሁበት ሳትቀየሩ መቆየት አትችሉም ምክነያቱም አሁንም ከህይወት የምትማሯቸው ብዙ ጠቃሚ ነገሮች አሉ።

🧷 ትርምስም ደግሞ ሊበዛ ይችላል። ጫናውን መቋቋም መታገስ አትችሉም። መማር ያለባችሁን እየተማራችሁ ቢሆንም ከአቅማችሁ በላይ መጨነቅ አትችሉም።

ስለዚህ አንድ እግራችሁን በተካናችሁበት በምትረዱት ቦታ ሌላኛውን ደግሞ አሁን ለማወቅ እና ለመቻል በምትፈልጉበት ቦታ መትከል አለባችሁ። ከዛ እራሳችሁን የመኖር ሽብር በቁጥጥራችሁ ወስጥ በሆነበት እና ደህነነታችሁ በተጠበቀበት ነገር ግን ለነገሮች ንቁ እና ተሳታፊ በምትሆኑበት ቦታ አስተካከላችሁ ማለት ነው። እዚህ ቦታ ነው ትርጉም የሚገኘው።

Jordan peterson 12 rules of life, Chaos and order(ከዚሁ መንደር የተገኘ)

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

23 Sep, 19:56


✍️ የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው!

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው ፡፡ አንዱ ክንፍ እውቀት ነው፡፡ ሌላኛው ተግባር ነው፡፡ሰዎች ለመለወጥ የሚቸገሩበት አንደኛው ምክንያት ከእውቀት እጦት የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም በማታውቀው ነገር ዙሪያ እንዴት ትለወጣለህ? ይሄ ቦታ አልተመቸንም ብንል የት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ሄደን ምን ያጋጥመናል? ካላልን አስቸጋሪ ነው፡፡

ሁሉ እውቀት ኖሮን ደግሞ ባለንበት ቁጭ ብንል ተለወጥን ማለት አይደለም። አሁን እንደውም ትልቁ ሽወዳ ያለው አንዳንዴ ብዙ ስለለውጥ ስናውቅ የተለወጥን ይመስለናል፡፡ ከእሱ ደግሞ አለማወቅ ሁሉ ይሻላል፡፡

እውቀት ብርሀን ነው፡፡ ካወክ በራልህ ማለት ነው ፡፡ ቤት ውስጥ መብራት ባይኖር ምንም ማድረግ አትችል ይሆናል፡፡ ግን ቤት ውስጥ መብራት ቢኖር ስቶቩን ለኩሶ፣ እቃውን አውጥቶ፣ ድስቱን ጥዶ ምግብ አብስሎ አያበላህም፡፡ ነገር ግን አንተ እንድትሰራ በር ይከፍትልሀል፡፡

ስለዚህ እውቀትን እና ተግባርን ማቀናጀት ነው ለውጥ የሚፈጥረው! ምንድን ነው መለወጥ የምንፈልገው? እሱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እሱንም መለየት እና ማድረግ ነው፡፡ ጓሮህን ከሆነ መለወጥ የምትፈልገው እንዴት መለወጥ እንደምትችል ማወቅ አለብህ፡፡ ከዛ እጅህን ሰብስበህ መነሳት አለብህ፡፡ ጓሮህ ተቀየረ ማለት ነው፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ
ጥበብ እና ፍልስፍና

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

21 Sep, 11:33


ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን ማስወገድ ተማር!!

ጥበብ ሕይወትን የምንቀዝፍባቸው ክህሎቶች መለኪያ ነው። ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከተፈጠሩ በኋላ ከመፍታት የተሻለ ጥበብን ይጠይቃል፡፡እውነታው ሕይወት ከባድ መሆኗ ነው፡፡ ችግሮች በሁሉም አቅጣጫ በየጊዜው ይተኮሱብሃል፡፡ እጣ ፈንታ መርገጫህ ስር ጉድጓዶችን ልትቆፍርብህ ወይም መሿለኪያዎችህን ልትዘጋብህ ትችላለች። ይህንን መቀየር አትችልም፡፡ አስቀድሞ አደጋ ያለው የት ጋር እንደሆነ ከተረዳህ ግን ወዳንተ እንዳይመጣ ለማጠር እድል ይኖርሃል፡፡ በዚህ መንገድ መሰናክሎችን ሁሉ ማስወገድ ትችላለህ፡፡ ይህንን ሀሳብ አልበርት አንስታይን እንዲህ ያስቀምጠዋል፡፡ “ጎበዝ ሰው ችግሮችን ይፈታል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ችግሮችን ያስወግዳል፡፡”

ችግሩ ችግሮችን ማስወገድም የሚወደስ ነገር አለመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ፊልሞችን አስብ፡፡
1.በመጀመሪያው ፊልም ውስጥ አንድ መርከብ ከበረዶ ክምር ጋር መጠነኛ ግጭት ይገጥመዋል፡፡ መርከቡም ይሰምጣል። በዚህ ጊዜ የመርከቧ ካፒቴን ራስ ወዳድነት በሌለበት መልኩ ራሱን አበርትቶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ ከመስመጥ ይታደጋቸዋል፡፡ መርከቧ ለዘለዓለሙ ከመሰወሯ ከደቂቃዎች በፊት ሁሉንም ተጓዦች በማዳን ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሕይወት አድኑ ቦቴ ውስጥ በመግባት የመጨረሻው ሰው ነበር።

2.በሁለተኛው ፊልም ውስጥ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ መርከበኛው መርከቧ ከበረዶ ክምሩ ጋር ከመጋጨቷ በፊት አስተውሎ በቂ ርቀት ላይ እንድትቆም አደረጋት፡፡

የትኛውን ፊልም ለማየት የበለጠ ትከፍላለህ?በእርግጠኝነት የመጀመሪያውን ፊልም፡፡ ሌላ ጥያቄ ደግሞ ላንሳልህ፡፡ አንተ በመርከቧ ውስጥ ተጓዥ ብትሆን ኖሮ በየትኛው ፊልም ሁኔታ ውስጥ መሆንን ትመርጣለህ? ያለ ምንም ጥርጥር ሁለተኛው ፊልምን።

እነዚህ ምሳሌዎች እውነተኛ ገጠመኞች ናቸው ብለን እናስብ፡፡ ቀጥሎ ምን ይፈጠራል? የመጀመሪያው ፊልም ውስጥ ያለው ካፒቴን የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ይጋበዛል። ምናልባት መርከበኛነቱን ትቶ አነቃቂ ንግግሮችን እያደረገ ሕይወቱን መምራት ሊጀምር ይችላል። መንገድም በስሙ ሊሰየምለት ይችላል፡፡ ልጆቹም (ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ) በአባታቸው ይኮራሉ፡፡ የሁለተኛው ፊልም ውስጥ የሳልነው ካፒቴንስ? ከስራው በጡረታ እስኪገለል ድረስ ችግሮች እንዳይከሰቱ በቅድመ ጥንቃቄ የመርከበኝነት ስራውን ይሰራል። መርሁም “ከ20 ጫማ እርቀት ላይ ልታልፈው የምትፈራውን ነገር በ500 ጫማ እርቀህ እለፈው” የሚለው የቻርሊ ሙገር የሕይወት መርህ ይሆናል፡፡

እንግዲህ ተመልከት፡- የሁለተኛው ፊልም ካፒቴን ከመጀመሪያው ፊልም ካፒቴን በሚታይ መልኩ የሚሻል ቢሆንም እኛ የምናከብረውና የምናደንቀው ግን የመጀመሪያውን ፊልም ካፒቴን ነው፡፡ ለምን? በቅድመ ጥንቃቄ የሚመጣ ስኬት ለውጪው ዓለም እይታ የሚጋለጥ አይሆንም፡፡

ጋዜጠኞች አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳይመጡ ካረጉ በሳል ሰዎች ይልቅ ችገሮችን የቀለበሱ የሥራ መሪዎችን ነው የሚያሞካሹት ።የቅድመ ጥንቃቄ ስኬቶች ለውጪው ዓለም የማይታዩ ባለመሆናቸው ምክንያት ሳይታዩና ሳይወደሱ ይኖራሉ፡፡ የእንደዚህ አይነት ስኬቶት ባለቤቶችን ጥበብ የሚያውቁት በእሱ ዙሪያ ያሉ የቡድኑ አባላት ብቻ ናቸው። እነሱም ቢሆን በተወሰኑ መልኩ ቢያውቁት ነው፡፡

የአንተስ ሕይወት? አመንክም አላመንክም ከስኬቶችህ ሁሉ 50% የሚሆኑት የቅድመ መከላከል ጥንቃቄህ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደምናደርገው ሁሉ አንተም አንዳንድ ነገሮችን በንዝህላልነት ልታደርግ ትችላለህ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖም ግን ስህተቶችን ላለመስራት ሁልጊዜም ትጠነቀቃለህ፡፡ በአርቆ · አሳቢነት ያስወገድካቸውን በስራህ፣ በትዳርህ፣ በትምህርትህ ወይም በሌላ የሕይወትህ ዘርፍ ሊገጥሙህ የነበሩ ችግሮችን አስብ፡፡

ጥንቃቄ (prevention) ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ በባህሪው ቀድሞ ማየት (imagination) ይጠይቃል ቀድሞ መረዳትና የሚመጣውን መገመት ደግሞ ብዙውን ጊዜ አዛብተን የምንረዳቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ አዲስ ሀሳብ አያመጣልንም፡፡ በዓይነ ህሊና ማየት (imagination) ማለት የመጨረሻው ፍትሃዊ ነገር ሆኖ እስክናይ ድረስ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ውጤቶችና የመፈጠር እድላቸውን ሁሉ እንዲያስብ አዕምሯችንን ማሰራት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም አስቀድሞ ማየትና መገመት ከባድ ስራ ነው።

በተለይ ጉዳዩ ስለአደገኛ ችግሮች ሲሆን ደግሞ ቀድሞ የመገመት ሥራ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ ሊመጡ እድል ባላቸው ችግሮች ላይ ሁሉ እየተጠነቀቅክ መኖር ይጠበቅብሃል? ይህስ ሁልጊዜ የተጨናነቀ ሰው ሆነህ እንድትኖር አያደርግህም? ተሞክሮዎች የሚያሳዩት እንደዚያ እንዳልሆነ ነው፡፡ ቻርሊ ሙገር እንዲህ ይላል “በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሚመጠብኝን አደጋዎች ስገምት ኖሬያለሁ፡፡ ሁልጊዜ ይሄንን እያሰብኩ፣ አደጋዎች ከመጡም እንዴት መመከት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ መኖሬ ደስተኛ እንዳልሆን አላደረገኝም፡፡”

ሮልፍ ዶልቢ
The art of good life
via-እስማኤል ኢብራሂም

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

10 Sep, 10:05


https://youtu.be/aT0O9uKJ1WI

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

10 Sep, 10:04


https://youtu.be/1VKvFHVDagA

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

08 Sep, 14:49


-❤️ በስውር ላደረጉልኝ በአደባባይ ማመስገን እፈልጋለሁ ፡፡
****
🥦አዲሱን አመት ልንቀበል ሁለት ቀን ነው የቀረን፡፡ሁሌ አዲስ አመት ሲመጣ አሮጌ የተባለውን አመት እንዴት እንዳሳለፍን ኦዲት ማድረግና በመጪው አዲስ አመት የምንከውናቸውን ነገሮች እቅድ ማውጣት ለምዶብናል፡፡እኔም በዚህ ስሌት አመቱን ከህይወት ውጣ ውረዴ አንፃር መዝኜ በምስጋና መዝጋት ፈለኩ፡፡እናም ደግሞ በዚህ ሰዓት በፍፅም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ ይህን ለሚያነብ ሰው የሆነች የተስፋ ብርሀን ይረጭለት ይሆናል በሚል እምነት ነው፡፡
////
🤡-ልክ አምና በዚህ ጊዜ የህይወቴ በጣም አስቀያሚው ወቅት ላይ ነበርኩ፡፡ህመሜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ አልጋ ላይ የወደቅኩበት ፤ህመሙን ተከትሎ የተፈጠረብኝ ስቃይ ፤ድባቴና እራስንም ሆነ ዓለምን እንድጠላ እና እንድፀየፍ የተገደድኩበት ሁኔታ ላይ ነበርኩ፡፡እና በዛ ሁኔታ ላይ ሆኜ ስለአዲስ አመት ሲወራ እኔ እንዴት በሰላም እንደማርፍ ነበር ማስበው…መኖር ፍፁም ደክሞኝ ነበር….ፈጽሞ አመት ሙሉ ቆይቼ ይሄኛውን አዲስ አመት ለመቀበል የሚያስችል ትግስቱም ሆነ ፍላጎቱ አልነበረኝም፡፡
🤡ግን ድንገት የድሮ ወዳጆቼ በህይወቴ ተመልሰው መጡ …ከአልጋዬ አንስተው ወደህክምና ወሰዱኝ ..ገንዘባቸውን ያለስስት ከስክሰው እያመላለሱ አሳከሙኝ…እንሆ አሁን ከበሽታዬ ባልድንም ስቃይም ሆነ ድባቴ የለብኝም…በሽታዬ የሚያስከትልብኝን ህመም በመድሀኒት እገዛ እንዴት መቋቋም እንደምችል ተለማምጄ የህይወቴ አንዱ ክፍል እንደሆነ ተቀብዬዋለው….እንደዛም በማድረጌ በፈገግታና በምስጋና እየኖርኩ ነው፡፡ይሄ ሁሉ የሆነው በሚወዱኝ ቤተሰቦቼና በወዳጆቼ እገዛ ነው፡፡
🤡እና የቤተሰቦቼን ላቆየውና ለዚህ ዋና ባለድርሻ የሆኑትን
1/የጀስቲስ ህንፃ ተቋራጭ ባለቤት…ኢንጂነር ዩሱፍ መሀመድ….(ከነቤተሰቡ)
2/ደረጄ ታምራት………….(ከነቤተሰቡ)…..
እንሆ ላለፉት 9 ወራት ለህክምና ለመድሀኒት …እና ተያያዝዥ ወጪዎች እነሱ ሳይሰስቱ በሰጡኝ ብር ነው ያለሀሳብ ስጠቀም የቆየሁት….ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በስውር ሰጥተውኛልና በአደባባይ መመስገን ይገባቸዋል ብዬ አስባለው፡፡…እናም ከልቤ አመስግናለው፡፡
ሌላው
🤡እኔን ለማዳን ለበርካታ ወራት የተቻላችሁን ሁሉ በማድረግ ከልባችሁ ለጣራችሁ ገላዬ ሸዋንግዛው እና ባለቤቱ ህይወት መኮንን(የእናንተን ምስጋና በአጭሩ ያደረኩት የአንድ ቤተሰብ አባል ስለሆን ብዬ ነው..ቢሆንም ያደረጋችሁልኝን መቼም አረሳውም)
👌-ሌላው….
በፍላጎታቸውና በፍቅራቸው በየአጋጣሚው ቀዳዳዬን ለመድፈን ለሞከሩት እና ዘወትር አይዞህ እያሉ ብርታት ለሆኑኝ ጓደኞቼ
1/የሲፍለን ኢንጂነሪን ባለቤት..ኢንጂነር ሞሲሳ ታከለ
2/ ተስፋዬ አሰፋ (ከነቤተሰቡ)
3/ኢንጂነር..ግሩም ተፈራ
4/ ›› …ሽመልስ መኮንን
5/››………..ዬሴፍ …..ሌሎችም
6/- የጀስቲስ ህንፃ ተቋራጭ የስራ ባለደረቦቼ የነበራችሁ በአጠቃላይ…..ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ፡፡
👉በድጋሚ
ደረጄ ታምራት…ጓደኛዬ ብቻ አይደለም ..ከወንድምም በላይ ነው…..ከላይ ያመስገንኩት ለእኔ ህክምና ላወጣው ብር ነው፡፡ግን በገንዘብ ብቻ አላቆመም….በየሶስት ቀኑ ያለማቆረጥ ይደውልልኛል…ትንሽ ሲያመኝ መኪናውን አስነስቶ ቢሾፍቱ ይመጣና ይዞኝ አዲስ አበባ ይሄዳል….ስራውን ጥሎ ያሳክመኝና ወደቤቱ ይወስደኛል…ከዛ መላአክ የሆነች ባለቤቱ እመቤት ጉልማ በቃኝ ወደቤቴ መልሱኝ እስክል እንደንጉስ ታስተናግደኛለች..ይሄ አንዴ ሁለቴ የሆነ አይደለም..አመቱን ሙሉ ያልተለየኝ እንክብካቤያቸው ለእኔ የህልም ያህል አስደናቂ ነው ….እነዚህን ባልና ሚስቶች ታዲያ ምን ብዬ ማመስገን እችላለሁ….ፅድቅና ኩነኔ የሚኖር ከሆነ … በእኔ ምክንያት ብቻ ይፀድቃሉ፡፡ ወንድሜ በጣም አመሰግናለው፡፡
👌ሌላው
ያለሁበት ሁኔታ ከባድ እንዳይሆንብኝ እቤት ሆኜ ስራ እንድሰራ እና ገንዘብ እንዳገኝ ሁኔታውን ያመቻቸህልኝ ወዳጄ ጋዜጠኛ ፀጋዬ አብራር…..አንተንም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
👉ሌላው
የዚሁ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ…መታመሜን በሰማችሁ ጊዜ ያቅማችሁን ላደረጋችሁልኝና ከጎኔ ሆናችሁ ብርታት ለሆናችሁኝ ..አቤት ድረስ መጥታሁ ለጠየቃችሁኝ
1/መሀመድ እንድሪስ ካሳ…..ሙስታጅብ….ሀመር ውቢት….ታደለች ግብሩ…እሌኒ አሮን… ቴድሮስ ሲሳየ…መሲ ነፍጠኛዋ…ያለምዘርፍ ወሌ ..መስፍን ተሰማ….መቅደስ ኃይሌ..ሌሎችም ስማችሁን ለጊዜው ማስታወስ ለተሳነኝ በአጠቃላይ …አመሰግናለው፡፡
መጪው አዲስ አመት ለሁላችሁም …ሰላም የሰፈነበት…በረከት የሚታጨድበት…ፍቅር የሚዘመርበት…የምቾትና የተድላ ይሆንላችሁ ዘንድ ከልብ እመኛለሁ፡፡በድጋሜ አመሰግናለሁ፡፡

1,663

subscribers

281

photos

3

videos