Minster Of Education MoE @tvneaea Channel on Telegram

Minster Of Education MoE

@tvneaea


╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
OFFICA


Minster Of Education MoE (English)

Are you looking for a platform where you can stay updated on all the latest news and developments in the field of education? Look no further than the Minster Of Education MoE Telegram channel! This channel, with the username @tvneaea, is your go-to source for all things education-related.

The Minster Of Education MoE channel provides its subscribers with valuable information on educational policies, school updates, upcoming events, and much more. Whether you are a teacher, student, parent, or education enthusiast, this channel has something for everyone.

Stay informed and connected with the Minster Of Education MoE channel. Join us today and be a part of our growing community of education enthusiasts! OFFICA ☞

Minster Of Education MoE

21 Feb, 08:01


#NationalExam

" ፈተናው ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት እየተዘጋጀ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ " የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ብሏል።

" ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ሲል ገልጿል።

በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም  የሚፈተኑ እንዳሉም ጠቁሟል።

በዚህም " የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።

የፈተና ዝግጅቱ፡-

1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣

2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ እንደሆነ ተገልጿል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ እንደሆነ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎት መ/ቤቱ አሳስቧል።

ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል።

የዘንድሮ ሀገር አቀፉ የ12ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም።

Minster Of Education MoE

14 Feb, 17:34


" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት እስከ ነገ ይለቀቃል " - ትምህርት ሚኒስቴር

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት እስካሁን አልተለቀቀም።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ውጤቱ ለምን ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እኩል አልተለቀቀም ? ስንል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞችን ክፍያ የሚፈፅሙት ተቋማቱ መሆናቸውን አመራሩ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ተቋማቱ ክፍያውን ባለመፈፀማቸው ውጤት መለቀቅ ላይ መዘግየት እንዳጋጠመ ኃላፊው ተናግረዋል።

አሁን ላይ ብዙዎቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክፍያውን እየፈፀሙ በመሆናቸው የተፈታኞቹ ውጤት እስከ ነገ ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኃላፊው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

የመውጫ ፈተናውን በግል የወሰዱ ድጋሜ ተፈታኞች ውጤትም ወደየተፈተኑበት ተቋማት ይላካል ብለዋል።

Minster Of Education MoE

27 Jan, 11:50


ይህ የእጅ ፅሁፍ የአለማችን ምርጡ የእጅ ፅሁፍ ፣ በሚል ዕውቅና ተሰጥቶታል ፣ የፅሁፉ ባለቤት ኔፓላዊቷ ልጅ " Prakriti Malla" ትባላለች የ 8ተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ስትፅፍ እድሜዋ 16 ነበር።

Minster Of Education MoE

27 Jan, 10:00


የመውጫ ፈተና ከጥር 26 እስከ  ጥር 30 ይሰጣል።

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Minster Of Education MoE

29 Dec, 11:54


በመሬት መንቀጥቀጡ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደረሰባቸው

በጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ አስገድዷል፡፡

በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ  ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸው እና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

Minster Of Education MoE

25 Dec, 19:23


የሰላማዊ ሰልፉን ምክንያት በተመለከተ በሰጠን ማብራሪያ ኀብረቱ፣ “ አዲስ የወጣውን የምግብ ፓሊሲ እንቀበላለን አንቀበልም በሚል ነው ” ብሏል።

ቅሬታ የተነሳበትን የምግብ ሜኑውን በተመለከተ ከትምህር ሚኒስቴር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያዬት ቀጠሮ እንደያዘም ኅብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲው፣ የመቐለው አሁን ተረጋግቷል። ኮንሰርኑ ግን የ100 ብሯ ጉዳይ  ነው ” ሲልም ገልጿል።

ቅሬታው በሌሎችም ዩኒቨርቲዎች መሆኑን ኀብረቱ በገለጸው መሠረት ቅሬታ አለበት የተባለውን ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን የጠየቅን ሲሆን፣ የአዲሱ ሜኑ ጉዳይ ለእርሱም ጥያቄ  እንደሆነበት

Minster Of Education MoE

25 Dec, 19:23


#Update

“ መቐለ ብቻ አይደለም። ትላንት ደብረ ብርሃንም ፣ ደባርቅም ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተነስቷል ቅሬታው ” - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት

🚨 " የታሰሩ ተማሪዎች ተፈተዋል !! "

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ በጀት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

በዚህም ትምህርት ሚኒስቴር አጠናሁት ባለው ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ጥናት መሠረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ በጀት ከታኀሳስ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በቀን 100 ብር እንዲሆን መወሰኑ አይዘነጋም።

ውሳኔው ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአዲሱ የምግብ ሜኑ ቅሬታ እንዳላቸው እየገለጹ ይገኛሉ።

በመቐለ ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደባርቅና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ትላንት ቅሬታቸውን በአደባባይ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በነበረው በዚሁ ሂደት በተማሪዎቹ ድብደባ እስራት እንደደረሰ፣ ንብረት እንወደመም ተመልክቷል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትላንት በተፈጠረው ግርግር የታሰሩ ተማሪዎች ተፈቱ ? ምን ያህል ተማሪዎች ናቸው የታሰሩት ? ስንል የጠየቅነው ኀብረቱ፣ “ 27 አካባቢ ተማሪዎች ነበሩ የታሰሩት ” ሲል መልሷል።

ኀብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣“ ታስረው የነበሩት ሁሉም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተፈተትተዋል። አሁን እዛ እየወጣን ነው ” ሲል አረጋግጧል።

“ ሁሉም ነገር ተረጋግቷል። ተቋሙ የራሳቸው በመሆኑ ተማሪዎች መጠበቅ እንዳለባቸው፣ የወደመው ንብረትም በጋራ መስተካከል ያለበት እንዲስተካከል ማሰሰቢያ ተሰጥቶ ሁሉንም አስፈትተናቸዋል ” ነው ያለው።

“ ተማሪዎቹ ታስረው የነበረው ቀዳማዊ ወያኔ እና ኣደ ሓቂ ነበር። ግማሾቹ ከቁኑ ስምንት ሰዓት ገደማ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ነው የፈቱት ” ብሏል።

በተማሪዎች ላይ ድብደባ ደርሷል የተባለውን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ “ ተማሪ ላይ ድብደባ ደርሷል። ጉዳትም ደርሷል ” ነው ያለው።

የአዲሱ የምግብ ሜኑ ውሳኔ ቅሬታ ያሳደረው በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚገኙ ተማሪዎች ብቻ እንዳልሆነ ኅብረቱ ገልጿል።

ኅብረቱ “ መቐለ ብቻ አይደለም። ትላንት ደብረ ብርሃን፣ ደባርቅም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተነስቷል ” ሲል ነው ያስረዳው።

“ በይበልጥ የመቐለው ፓለቲሳይዝ ስለሆነ ነው እንጂ በሌሎችም እኮ አለ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡበት በዚሁ በሜኑ ጉዳይ። ጉዳዩ አገራዊ ነው እየሆነ ያለው ” ሲልም አክሏል።

Minster Of Education MoE

15 Nov, 17:56


" ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏል።

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ  ከቀኑ  8:00  ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ " አልወርድም " በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ፦
- ጎፋ ዞን፣
- አሪ ዞን፣
- ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

Minster Of Education MoE

11 Nov, 17:21


#AddisAbaba

" ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል።

ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ዘመቻ ሲባል ፦
- ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣
- ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድረግ፣
- ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ማስቻልን ያካትታል።

የቁጥጥር ስራው በተለይም በገበያ ሞሎች ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም አንዳንድ ነጋዴዎች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ " ንብረት ለመውረስ እና ሱቆችንም ለመዝጋት ነው " በሚል ሱቃቸውን ዘግተዋል ንብረትም ወደ ሌላ ቦታ አዙረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ በመርካቶ አካባቢ የሚሰሩ ነጋዴዎሽ  " ከምንም በፊት ያሉትን ችግሮች ማወቅ ይገባል። ቸርቻሪውን ማነጋገር ያስፈልጋል። ችግሮቹን ለመቅረፍ መሰራት አለበት። " ብለዋል።

" ነጋዴው ከአስመጪ እቃ ሲገዛ አስመጪው ከዋጋው በታች ደርሰኝ ይሰጣል አልያም ጭራሽ ላይሰጥም ይችላል ፤ ምንም  አይነት የግዢ ደረሰኝ ባላገኘበት ' ነጋዴው ሱቅ ውስጥ ያለዉን ንብረት እንወርሳለን ' ማለት ትክክል አይደለም " ሲሉ አክለዋል።

" መንግሥት ታች ያለው ነጋዴ ላይ ጣቱን ከመቀሰር አስመጪዎቹን ደረሰኝ እንዲሰጡ ማድረግ እና ቸርቻሪውን ማወያየት ያስፈልጋል " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አንዳንድ የራሳቸው የገቢዎች ሰዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ቸርቻሪዶችን ማስጨነቅ እንደሚቀናቸው ቃላቸውን የሰጡ አንዳንድ ነጋዴዎች ጠቁመዋል።

ያለ ደረሰኝ ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የገንዘብ ድርድር ሁሉ እንደሚያደርጉና ያሉ ችግሮች ስር የሰደዱ እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ከምንም በላይ ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይኖር ከላይ ጀምሮ መስራት እንደሚገባ ነጋዴው በደረሰኝ ከገዛ በደረሠኝ እንደሚሸጥ ከላይ ግን እጃቸው የረዘመ ሰዎች ስላሉ መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ " አመልክተዋል።

ሁኔታዎችን በመጠቀም በህግ ሰበብ ከነጋዴው ገንዘብ የሚቀበሉና ሙስና የሚሰሩ ህገወጥ ተግባራትንም የሚያባብሱ በገቢዎች አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዲታረሙ መሰራት እንዳለበት አክለዋል።

ሌላ አንድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ የሃሳብ መለዋወጫ መድረክ ሃሳባቸውን ያካፈሉ ዜጋ ፥ አስመጪዎች እና አምራቾች ለጅምላ ነጋዴ እና ቸርቻሪ ያለደረሰኝ ስለሚሸጡ ያለደረሰኝ የተገዙ እቃዎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

" ነጋዴዎች እቃዎቻቸው ሳይወዱ ደረሰኝ ስለሌላቸው እንዳንወረስ ብለው ወደ ሌላ ቦታ ያሸሻሉ ሱቅም ለመዝጋት ይገደዳሉ  " ብለዋል።

" ዋናው ስራ መጀመር ያለበት ከአስመጪዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች መሆን አለበት ፤ እነሱን በሚገባ ከተቆጣጠሩ እና እርምጃ ከወሰዱ በኋላ በተዋረድ ጅምላ ነጋዴዎች እና ቸርቻሪዎችን መቆጣጠር ይገባል " ብለዋል።

" የችግሩ ምንጭ ከሆኑት አስመጭዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ጠበቅ ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት " ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

" በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው " የሚል ውዥንብሮች በመፈጠራቸው አንዳንድ ነጋዴዎችን ግርታ ውስጥ መክተቱ ተናግሯል።

ስለ ጉዳዩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽን አነጋግሯል።

ዳይሬክተሩ ምን መለሱ ?

➡️ " ጠዋት ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል " ተብሎ ተወርቶ በአካል ዞሬ አይቻለሁ የተወሰኑ ሱቆች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጉ የሚመስሉ አሉ ነገር ግን መደበኛ ሥራ ቀጥሏል።

➡️ " በዚህ ደረጃ ተዘግቷል ለማለት እይቻልም ተዘጋ የሚባለው ምን ያህል ሱቅ ሲዘጋ ነው ? አንድ ቤት ሁለት ቤት ተዘግቶ ይሆናል ነገር ግን አብዛኛው እየሰራ ነው።

➡️ ህገ ወጥነትን ማስቀጠል የሚፈልግ አካል  አለ። ሆን ብሎ ' የሆነ ነገር ተሰርቷል፣ ሊሰራ ነው ' የሚል ውዥንብር መፍጠር የሚፈልግ አካል እንዳለ ነው የተረዳሁት።

➡️ ቁጥጥር ሊደረግ ነው በተለይ አስመጪ እና አከፋፋይ ላይ ሲባል ቸርቻሪ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አሉ፣ በትላንትናው ዕለትም የሚሸሹ ነጋዴዎች ገጥመውናል ያለፍቃድ ይነግዱ የነበሩ ናቸው ብንጠየቅ መልስ የለንም በሚል ስጋት ነው። ሱቃቸውን ቢዘጉም እነሱ ናቸው የሚሆኑት።

➡️ ተዘግቷል የሚለውንም እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል በእርግጥ የተዘጋ ነው ወይስ ነጋዴው በsocial ችግር ሱቃቸውን ዘግተው ስለሌሉ ነው የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ስለሆነ የተዘጉ አይደሉም ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስነው።

➡️ ይርጋ ሃይሌ የገበያ ሞል ላይ ከ15 ቀን በፊት ኮንትሮባንድ ስለነበረ ጎምሩኮች በርብረዋል ደረሰኝ የሌለውን ወርሰዋል ደረሰኝ ያለውን ጥለው ወጥተዋል።

➡️ የገበያ ሞሉ ላይ እቃዎችን መለየት አስቸጋሪ ስለነበር እና ሰዎቹም ተባባሪ ስላልነበሩ ለጊዜው ታሽጎ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ሀሉም ተከፍተዋል። የቀረ ካለ በንግድ ቢሮ በኩል ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ በተወሰደ እርምጃ ነው።

➡️ ታሽገው የነበሩ አብዛኛው ሱቆች ተከፍተዋል። እስካሁን ያልተከፈተ ካለ ፈቃድ ስላላወጣ ነው የሚሆነው በተረፈ እቃ የሚወረሰው ኮንትሮባንድ ሲሆን ብቻ ነው።

➡️ ሁሉም ሰው ደረሰኝ ስለማይሰጥ የሚመለከተው ብቻ ነው ደረሰኝ እንዲሰጡ የሚጠበቀው መስጠት የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች ደረሰኝ እየሰጡ ግብይታቸውን ይቀጥሉ።

➡️ " እቃችሁ እየተወረሰ ነው፣ ሊወረስብን ነው" የሚሉ አካላት እቃቸው ምን ስለሆነ ነው የሚወረሰው ? እንደዚህ የሚሉ አካላት ኮንትሮባንድ ስለሆነ ይመስላል።

➡️ ያለደረሰኝ አትግዙ ፣የሚሸጥላችሁን ጠቀሙ እኛ ደግሞ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽምን አካል እንቆጣጠራለን ብለናል የምንከታተላቸውም ለዛ ነው።

➡️ እቃ ለመውረስ የህግ መሰረት ያስፈልጋክ። እቃ የሚወረሰው የታክስ እዳ ማካካሻነት ከተያዘ ብቻ ነው።

➡️ ግብይት ላይ ያለ እቃን የታክስ ማካካሻ ብለን የምንወርስበት ምክንያት የለንም። ክፍተት ያለበትን ነጋዴ ለማወናበድ የሚሮጥ ሌላ ጥላ የሚፈልግ አካል የሚያወራው ወሬ ነው።

➡️ " ያለደረሰኝ አትሽጡ " አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም። ይህም ለነጋዴዎች በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
https://t.me/tvNeaea

Minster Of Education MoE

10 Oct, 15:05


https://t.me/tvNeaea

Minster Of Education MoE

08 Oct, 19:16


#MoE #Placement

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

Minster Of Education MoE

20 Sep, 05:49


💧 ጠዋቱን በአሪፍ ዜና እንጀምረው 💧

Telegram ትልቅ project ይዞ ከች ብሏል ይሄም project ልክ እንደ tik tok እንደ YouTube short አጫጭር video የምንመለከትበት project ነው 👈

በመጀመሪያ በዚህ ሊንክ ግቡ 👉https://t.me/coub/app?startapp=coub__marker_18626398


በመቀጠል 👇
⚡️ task  Section ውስጥ  በመግባት የተለያዩ task በመስራት coub የተሰኘውን coin መሳይ ነገር አግኙ

⚡️በድጋሚ video የማየት task እየሰራችሁ ተጨማሪ cloub ማግኘት ትችላላችሁ
⚡️wallet ደግሞ connect ማድረግ እንዳይረሳ

💧እንደዚህ አይነት ነገሮች ሲመጡ ቀልጣፋ በመሆን ቀድሞ መጀመር ብልህነት ነው👈



https://t.me/coub/app?startapp=coub__marker_18626398

Minster Of Education MoE

19 Sep, 10:12


https://t.me/rocky_rabbit_bot/play?startapp=frId676141491
Rocky Rabbit: Fun and Earnings! 🐰🚀
Play Rocky Rabbit for fun and profit! Join through this link and let’s start our profitable journey together!

Minster Of Education MoE

19 Sep, 07:33


1 kenew biyanse 50dollar teseralchu,5000 birr

Minster Of Education MoE

19 Sep, 07:18


እንዳትቆጩ LAUNCH adrigu ,1 ቀን ነው የቀረው   lost dogs

Minster Of Education MoE

19 Sep, 07:18


https://t.me/rocky_rabbit_bot/play?startapp=frId676141491
Rocky Rabbit: Fun and Earnings! 🐰🚀
Play Rocky Rabbit for fun and profit! Join through this link and let’s start our profitable journey together!

Minster Of Education MoE

16 Sep, 11:42


https://t.me/major/start?startapp=676141491

👑 Join me in @Major game and earn $MAJOR token soon!
⭐️ 750 rating bonus for you.
⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.

Minster Of Education MoE

14 Sep, 18:36


https://t.me/empirebot/game?startapp=hero676141491

Minster Of Education MoE

10 Sep, 17:29


እንዳትቆጩ LAUNCH adrigu ,5 ቀን ነው የቀረው lost dogs

Minster Of Education MoE

10 Sep, 17:29


https://t.me/lost_dogs_bot/lodoapp?startapp=ref-u_676141491

Minster Of Education MoE

10 Sep, 07:22


እንዳትቆጩ LAUNCH adrigu ,19 ቀን ነው የቀረው

Minster Of Education MoE

10 Sep, 07:21


t.me/empirebot/game?startapp=hero676141491
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium