Federal TVET institute official students group @federal_tvet_students_group Channel on Telegram

Federal TVET institute official students group

@federal_tvet_students_group


Sharing knowledge and information for TVET students

Federal TVET Institute Official Students Group (English)

Are you a student at the Federal TVET Institute looking to connect with fellow classmates and share knowledge and information? Look no further than the Federal TVET Institute Official Students Group on Telegram! Dedicated to providing a platform for students to exchange ideas, ask questions, and support each other throughout their educational journey, this group is the perfect place to network with like-minded individuals. Whether you're seeking study tips, project ideas, or simply want to stay updated on the latest news and events at the institute, the Federal TVET Institute Official Students Group has got you covered. Join today and become part of a community that is passionate about learning and growing together. Don't miss out on this opportunity to enhance your educational experience and make new friends along the way. We can't wait to welcome you to our group!

Federal TVET institute official students group

24 Aug, 22:42


ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,851 የላብራቶሪ ምርመራ 1,472 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 267 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 42,143 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 692 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 15,262 ደርሷል።

@MinistryOfHealth_Ethiopia

Federal TVET institute official students group

01 Aug, 01:17


ለመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!🕌

Federal TVET institute official students group

15 Jun, 06:28


ፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአረንጓዴ አሻራ ቀን፡ ሰኔ 8ቀን 2012 ዓ.ም
።።።።

ክቡር ጠ/ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ ቀን በይፋ ባስጀመሩበት ዕለት እንደገለጹት በያዝነው ዓመት አገራችን ኢትዮጵያ 5ቢሊየን ችግኞችን የመትከል እቅድ ይዛለች።

ይህ እቅዷ እንዲሰምር ሁላችንም ዜጎቿ ኃላፊነት አለብን። ከተባበርን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ከመከላከል ጎን ለጎን በጥንቃቄ እቅዱን ማሳካት እንችላለን።

አገራችንን አረንጓዴ ለማልበስ የሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ የ2012 መርሃግብር ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ ችግኞችን በመትከል ላይ የሚገኙት የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋሞቻችን ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ምን “የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና የአረንጓዴ አሻራ ቀን” በሚል ስያሜ የተለያዩ ተግባራትን ያከናወናሉ፡፡

#በዕለቱ
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን እንተክላለን፣
ለወገኖቻችን ማዕድ እናጋራለን፣
በመቶዎች የሚቆጠሩ የደም ዩኒቶች እንለግሳለን።

የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብና አዳዲስ ችግኞችን በመትከል፣ ለተቸገሩ ማዕድ በማጋራትና ደም በመለገስ ከጎናችን ሆናችሁ የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

Federal TVET institute official students group

24 May, 11:45


👍👍👍 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1441ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ኢድ ሙባረክ!

Federal TVET institute official students group

21 May, 13:59


የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የፈጠራ ስራዎቻቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናዎችን ማስቀጠል በሚቻልባቸው፣ የተቋማቱን የፈጠራ አቅም ማሳደግ እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን አጠናክሮ ማስኬድ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከፌዴራልና ከክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲዎችና ቢሮዎች እንዲሁም ከፌዴራልና ከክልል የብቃትና ምዘና ማዕከላት ጋር የቨርቹዋል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም በሀገሪቱ አጠቃላይ 1681 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት መኖራቸውን ገልፀው ወቅቱ ለፈጠራ ሥራዎች አመቺ በመሆኑ ተቋማቱ አቅማቸውን በማሳደግ የፈጠራ ስራዎቻቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉበት እንደሚገባና የማህበረሰብ አገልግሎትንም አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

በየጊዜው እየጨመረ የሚመጣውን የተማሪዎች እና የሠልጣኞች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የመማር-ማስተማር እና ሥልጠናው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ቀደም ተብሎ በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ የተካተተ እና በፖሊሲ የተቀመጠ መሆኑን ጠቁመው ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልባቸው መንገዶች ገምግሞ ማመቻቸት እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

በተለይ ዘርፉ ለሀገር ብልጽግና ትልቅ አቅም በመሆኑ የዲጅታል ላይብራሪ፣ የኢንተርኔት ፕላትፎርም ተዘጋጅቶ በንድፈኃሳብ የሚማሯቸውን ትምህርቶች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ፕሮፌሰር ሂሩት ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ የስራ ኃላፊዎቹ በቴክኒክና ሙያ ትምህትና ስልጠና ተቋማትን የተሰሩ ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ በተለይ ወቅቱን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ ፈጠራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአንድ አከባቢ የተሰሩ ስራዎችን እንደምርጥ ተሞክሮ ወስዶ በሌሎች አከባቢዎች ማስፋፋት እንደሚገባና በተለይ በፕሮቶታይፕ መልክ ተሰርተው የተቀመጡ ፈጠራዎችን ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችም ሳይዘናጉ ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አቶ ጌታቸው ነጋሽ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ አሳስበዋል፡፡

በማጠቃለያው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ እንዳሉት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋሞች ከመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በየከተማ አስተዳደርና ክልሎች ካሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች፣ ጤና ቢሮዎችና የምርምር ተቋማት ጋር ተናብበውና ተባብረው ትስስር ፈጥረው እንዲሰሩና የጀመሩትንም በማጠናከር ይበልጥ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአንድ አገር የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር ናቸው ብለዋል፡፡ አያይዘውም በኮቪድ 19 ምክንያት እጃችን ላይ ያለውን ችግር ለመቀነስ ተጠናክሮ መስራትና የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ይበልጥ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ውጤቶችን ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ዘርፉ አምራች እንደመሆኑ መማር ማስተማሩን እና ስልጠናውን ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መስራት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

Federal TVET institute official students group

13 May, 20:37


Federal TVET Agency
# ኮሮናን_ለመከላከል_የጀርመን_መንግስት_ለሳይንስና
_ከፍተኛ_ትምህርት_ሚንስቴር_ድጋፍ_አደረገ ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ድጋፉን
ከጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነር ትላንት ተረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሮፌሰር ሂሩት እንደገለፁት የጀርመን መንግስት
ለረጅም ዓመታት የኢትዮጵያን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና ከፍተኛ
ትምህርት ዘርፉን ሲደግፍ ቆይቷል፡፡
አምባሳደር ብሪታ በበኩላቸው ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ከ50 ዓመታት በላይ
የዘለቀ የትብብር ስምምነት እንዳለው እና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና
ስልጠና ዘርፍ ድጋፍ በማድረግ የ25 ዓመታት የትብብር ድጋፍ ግንኙነት
እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡
የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት
ለመቀነስ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰራቸውን ተግባራት የሚደግፉ
ቁሰቁሶችን ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡
ከንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎች፣ ሰራተኞች ቤት ሆነው እንዲሰሩ
ለማስቻል የሚያግዙ 75 የኢንተርኔት ዋይፋይ ዶንግሎችና 200 ሺህ የእጅ
መታጠቢያ ሳሙናዎችን እንዲሁም 50 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች በድጋፍ
ከቀረቡት መካከል መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም ድጋፋቸውን አጠናክረው
እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡
ጀርመን ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ፣ ትምህርት፣ ጤና እና
የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ሰራተኞችን ለመደገፍ የሚያስችል የ120 ሚሊየን ዩሮ
ማዘጋጀቱንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ሂሩት ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው በተለይ ቴርሞሜትሮቹ የለይቶ
ማቆያና ማገገሚያ ማዕከላት በመሆን ለሚያገለግሉ ዩኒቨርስቲዎች
ጠቃሚዎች ናቸው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ ባስተላለፉት መልዕክትም ተማሪዎች ሳይዘናጉ ከትምህርታው ጋር
ተያያዥ የሆኑ ንባቦችን እንዲያደርጉና ራሳቸውን ከቫይረሱ በመከላከል ሌሎች
ወገኖቻቸውም እንዲጠነቀቁ እንዲያስተምሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
@FTA

Federal TVET institute official students group

13 May, 01:25


ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 1,526፣ ሞት 74፣ ያገገሙ 161

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,256፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 886

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,170፣ ሞት 52 ፣ ያገገሙ 126

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 715፣ ሞት 36 ፣ ያገገሙ 259

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 261 ፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 106

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 194 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 38

Federal TVET institute official students group

12 May, 10:46


"ዘርፈ ብዙ የኮቪድ 19 ምርምር የትኩረት ይዘቶች ለኢትዮጵያ" በሚል በቀረበው የምርምር ግኝት ላይ ውይይት ተካሔደ
።።።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከአማካሪ ምክር ቤቱ እና ከኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ ጋር በመተባበር ከ52 ተቋማት የተወከሉ 283 ኢትዮጵያውያን ምሁራን በኦንላይን የሞሉትን መጠይቅ በማደራጀትና በመተንተን “ዘርፈ ብዙ የኮቪድ 19 ምርምር የትኩረት ይዘቶች ለኢትዮጵያ (Ethiopian National COVID-19 Research Priorities and Alignment፡ Multi-disciplinary Taskforce Report)" የሚል የጥናት ግኝቱን ዛሬ ለ146 የዘርፈብዙ ኮቪድ 19 ምርምር ግብረኃይል አባል ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች ቨርቹዋሊ አቅርቧል፡፡

በውይይቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የውይይቱ ዋና ዓላማ ወረርሽኙን አስመልክቶ እንደ ሀገር የጋራ የጥናትና ምርምር የትኩረት መስክ /thematic area/ በማስፈለጉ መሆኑን ጠቅሰው በምሁራን የተዘጋጀው የጥናት ውጤት ላይ በመወያየት ብሔራዊ የጥናትና ምርምር የፖሊሲ የመነሻ ሰነድ በማድረግ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ፕሮፌሰር አፈወርቅ አክለውም በአለም አቀፍ ደረጃ በአለም የጤና ድርጅት፣ በአፍሪካ ደግሞ በአህጉራዊ የሳይንስ አካዳሚዎች ማህበር የተመላከተው የኮቪድ 19 የቅድሚያ ትኩረት መነሻ በኢትዮጵያ ለተካሄደው ሰርቬይ እንደግብዓት እንዳገለገሉና ኮቪድ-19ን አስመልክቶ ቅድሚያ ቢሰጣቸው የተባሉ በጥናቱ ውጤት ተለይተው መቀመጣቸው ገልጸዋል፡፡

በጥናቱ ውጤት መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ የተጠቀሱትን እውነታዎች እና የሀገራችንን፣ የየአከባቢዎቻችንን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በየተቋማቱ ተመራማሪዎችን ማሳተፍ ይጠበቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ቀደም ተብለው ከባህላዊ የህክምና ምርምሮች ጀምሮ ሲጠኑ የነበሩ እውቀቶችን ታሳቢ ባደረገ እንዲሁም የምርምር ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ የአገራችን የምርምር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች ከሚመለከታቸው ተቋማት እና እርስ በርሳቸው በመናበብ ቶሎ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶክተር ጌትነት ይመር የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢኒሼቲቭ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር
በጥናቱ መሰረት በአጥኚዎቹ ቅድሚያ ቢሰጣቸው ተብለው የተለዩትን አንኳር ነጥቦች (Infection prevention and control, Physical distancing & NP interventions, Clinical management and Biomedical issues, Medical Plants/Vaccine, Economic Analysis, Ethics and Related Issues, Modeling, Community engagement, amAnimal, human & environment interface, Genomics and Strain diversity, Technology, Indigenous knowledge, & Psychosocial assessment) መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጥናቱ የሀገራችን የምርምር ተቋማት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሳይንስ የሙያ ማህበራት እና መንግስታዊ ያልሆኑ የምርምር ስራ የሚሰሩ ወይም የሚደግፉ ተቋማት እንደየተቋሞቻቸዉ ተልዕኮ በጥናቱ ግኝቶች የተመላክቱትን ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸዉ የሚገቡ የኮቭድ-19 የጥናትና ምርምር ርዕሰ ጉዳዮች በመለየት በአስቸኳይ ወደ ስራ ለማስገባትም ያግዛል ተብሏል።

በማጠቃለያው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወረርሽኙ አገራችን ከገባ ጊዜ አንስቶ ግብረ-ኃይል በማቋቋም ከአማካሪ ምክር ቤቱ ጋር ወደ ስራ ገብቶ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አንስተው ተመሳሳይ ውይይቶች ከምሁራን ጋር ሲያደርግ መቆየቱን እና ወደፊት እንደሚቀጥልበጥም ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገልጸዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ውይይቱን በዘጉበት ወቅት እንዳሉት የጥናቱን ውጤት ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ተቋማት ወደ ስራ ሲያስገቡ አስከፊውን ወረርሽኝ በመከላከል ለአገራቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ገልጸው በቶሎ ወደ ስራ በመግባት የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ አደራ ብለዋል። ሲያጠቃልሉም በጥናቱ የተሳተፉትን ሁሉንም አካላትም አመስግነዋል።
ምንጭ፡ MSH

Federal TVET institute official students group

08 May, 20:03


ሳይማር አስተማረን" ለምንለው ወገናችን አገልግሎታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን መሆን ይገባዋል!
፡፡፡፡፡፡
አገራት የሃብት መጠናቸው የቱንም ያህል ቢሆን ዜጎቻቸው የዘመናዊ ትምህርት እንዲቀስሙላቸው የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ዓለም በአዳዲስ ፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ በገባችበት በዚህ ጊዜ ጭራ ሆኖ ከመከተል ወጥቶ መሪ ለመሆን በማለም አገራት መዋዕለ ንዋያቸውን ትምህርት ላይ ያፈስሳሉ፡፡

የአገራችንን ፅኑ ፍላጎት ስናይ በ2012 በጀት ዓመት መንግስት እንደሀገር ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍንና ለዘላቂ ግቦች ማሳኪያ የተፈቀደውን ጨምሮ 386.9 ቢሊየን ብር ገደማ መድቦ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ (ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለ45ቱ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) የተመደበው 48.4 ቢሊየን ብር ሲሆን ከአጠቃላይ የፌደራል በጀት የ20.15% ድርሻን ይይዛል፡፡ ይህም መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡

"ለትምህርትና ስልጠና ብቻ ለምን ይህን ያህል ወጪ ይወጣል" ካልን ትምህርት ለአገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ስለሆነ ነው፡፡ ትምህርት ለሰብአዊ እድገት ፣ ለኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ፣ ለማህበራዊ ደህንነት ፣ ለግላዊ እርካታ እና ዘላቂ የሆነ ፕላኔት እንዲኖር ለማድረግ መሠረት ነው፡፡

መማር አዲስ መረዳትን ፣ ዕውቀትን ፣ ባህሪያትን ፣ ክህሎቶችን ፣ እሴቶችን ፣ እና ምርጫዎችን የማግኘት ሂደት ነው። መማር የአእምሮን አስተሰሳብ ለማስፋት ያግዛል፡፡ ትምህርት የህይወት ተሞክሮ ለማግኘት ይረዳል ፡፡ መማር ብዙ ክህሎቶችን ቀስመን በተግባር የተሻልን ሆነን እንድንወጣ ያመቻቻል፡፡

ታዲያ ብዙ የአገር መዋዕለ ንዋይ ፈስሶለት የተማረው ዜጋም ኮቪድ 19ን ለመዋጋት ከኛ ምን ይጠበቃል?
"ሳይማር አስተማረን ህብረተሰብ ማገልገል እፈልጋለሁ" የሚል ፍላጎት ከሁሉም ወገን ይሰማል፡፡ እርግጥ ነው ያንን የምናሳይትጊዜ ላይ ነን! "ሳይማር አስተማረን የምንለውን ህብረተሰብ" የምናገለግልበት ትክክለኛ ጊዜ ዛሬ እና አሁን ነው!
መማር የባህሪ ለውጥ ለማምጣትና አዳዲስ እውቀቶችን ይዞ ለመተግበርም ያግዛልና በመጀመሪያ የኮቪድ 19ን ስርጭት ለመከላከል መተግበር ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ሁሉ እንደ ግለሰብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ከዚያ ራሳችን እየተጠነቀቅን ከወንድም እህቶቻችን፣ ቤተሰቦቻችን ጎረቤቶቻችን ጀምረን በአከባቢያችን ላሉት ወገኖቻችን ሁሉ የቫይረሱን አደገኛነትና የመዛመቻ መንገዶቹን በማስተማር፣ የጥንቃቄ መንገዶችን ሁሉ እንዲተገብሩ ግንዛቤ በመፍጠር፣ ቫይረሱን አስመልክቶ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ በማገዝ፣ በጥንቃቄ መጠናችን ለሌሎች አርአያ ሆነን ወገኖቻችንን ልናነቃ ይገባል፡፡
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡ ቁጥር ከፍተኛ እንደመሆኑ ራሳችን እየተጠነቀቅን ሌሎች እንዲጠነቀቁ በተለያዩ መንገዶች ማስተማር ከቻልን የምናተርፈው ህይወት ብዙ ነው፡፡
በተለይ ወገኖቻችን "እኔ ጋር አይደርስም" ከሚል አስተሳሰብ እንዲወጡ፣ በይሉኝታ ተይዘው ከቀጠሉት ማህበራዊ መስተጋብር ተላቅቀው አካላዊ እርቀታቸውን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
በጋራ ሆነን ስንጠነቀቅ፣ ወገኖቻችንን ተባብረን ስናነቃ ቫይረሱ የሚያደርስብንን ሁለተናዊ ጉዳት በእጅጉ መቀነስ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ራሳችን ቀድመን ነቅተን "ሳይማር አስተማረን የምንለውን ህብረተሰብ" አንቅተን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ድል ለማድረግ ዛሬ፣ አሁን፣ እንነሳ! አንዘናጋ
ምንጭ ministry of science and Higher education

Federal TVET institute official students group

05 May, 01:12


ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተልዕኮዎች አንዱ ሳይንስን በአገር አቀፍ ደረጃ ማስተባበር ነው፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወደአገራችን ከገባበበት ጊዜም አንስቶ ይሔንንኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በወረርሽኙ ዙሪያ የተለያዩ ቅድመ-መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና አካላት እየተካሄዱ ቢሆኑም በችግሩ ዙሪያ ልዩ ሳይንሳዊ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያምናል፡፡ በመሆኑም በወረርሽኙ ዙሪያ ልዩ የሆነ በኮቪድ19 ላይ ያተኮረ ሳይንሳዊ ይዘት ያለው ሳምንታዊ የምሁራን ምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የመጀመሪያው ሳምንት ውይይት “በወረርሽኝና የመቋቋሚያ ስልቶቹ ላይ የኢትዮጵያ ተሞክሮ ከታሪክ እይታ አንፃር” በሚል ርዕስ በ3 ምሁራን ታሪካዊ ዳራ ያለው ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም በኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት ገብተውም ሆነ እዚሁ አገራችን ተከስተው ስለነበሩ ወረርሽኞችና ስላደረሱት ጥፋት የተዳሰሰ ሲሆን ካለፈው ወረርሽኝ ታሪክ በዘመነ ኮቪድ 19 ምን ልንማርበት እንችላለን የሚሉ ጠቃሚ ምክረ ሃሳቦች ተገኝተውበታል፡፡

የፊታችን ረቡዕ ሚያዚያ 28 ቀንም ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚና ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ፤ ያለንበት ነባራዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሀሳቦች” በሚል ርዕስ ቀጣይ የምሁራን ዌቢናር ያካሂዳል፡፡

የሳምንታዊ የምሁራን ውይይቱ ዓላማ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ላይ ሳይንሳዊ መሰረት ያለው ውይይት በማድረግ የጋራ ግንዛቤ መያዝና በወረርሽኙ ዙሪያ የመፍትሔ ሀሳቦችንና አቅጣጫዎችን በመለየት ለትግበራ በማመላከት ሊከሰት የሚችል አደጋን መቀነስና መቆጣጠር እንዲቻል ማገዝ ነዉ፡፡

Federal TVET institute official students group

02 May, 10:47


የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,089፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 642

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 396፣ ሞት 17፣ ያገገሙ 144

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 601፣ ሞት 28፣ ያገገሙ 31

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 375፣ ሞት 28፣ ያገገሙ 32

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 131፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 59

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 35፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

Federal TVET institute official students group

02 May, 10:43


እንኳን ደስ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ❤️❤️❤️🙏🙏🙏

ዛሬ በኢትዮጵያ 2016 ስዎች ተመርምረው ሁሉም ሰዎች ነፃ ናቸው

ኮሮና የያዘው አልተገኘም

ስለዚህ ዛሬ በኢትዮጵያ ኮሮና ያያዘው ስዉ የተመዘገበ የለም

ደስ ሲል ፈጣሪ እንደዚህ መልካም መልካም ዜና ያምጣልን

እስቲ በየግሩፑ በየአካውንቱ ሼር አድርጉት

ጉርሻዎች ደስ ብሏናል

ይሄ ሆነ ብለን መጠንቀቁን ችላ እንዳትሉት እባካችሁ

ተመስገን 🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

Federal TVET institute official students group

30 Apr, 18:56


Federal TVET Agency
#በተቋማት_የተሰሩ_ስራዎች_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭ
ትን_ለመከላከል_ለመቆጣጠርና_የሚያደርሰውን_ጉዳት
_ለመቀነስ_የሚደረገውን_ጥረት_በቴክኖሎጂ_የሚደግ
ፉ_መሆናቸውን_የሲዳማ_ዞን_የቴክኒክና_ሙያ_ትምህ
ርትና_ስልጠና_መምሪያ_አስታወቀ፡፡
የዞኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ አመራሮች ሰሞኑን
ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና
የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየሠሩ ያሉትን ስራ ጎብኝተዋል፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ገቢባ እንደገለፁት በዞኑ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል፣
ለመቆጣጠርና የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች
የተሰሩ ሲሆን ጥራታቸውን በመፈተሽ ወደ ኢንተርፕራይዞች ተሸጋገረው
ለህረተሰቡ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡
ከተሩ ቴክኖሎጂዎች መካከልም ከንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ፣ የአፍና
አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ ለለይቶ ማቆያ የሚሆን አልጋ፣ የህክምና
ባለሙያዎች ጋወን እና በግብይት ወቅት በሻጭና በገዢ መካከል የእጅ ንክክ
እንዳይኖር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይገኙበታል፡፡
የአለታ ወንዶ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ
የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዱጉና እሽኔ በበኩላቸው ተቋሙ የኮሮና ቫይረስ
ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ
በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን ለመወጣት ጥረት በማድረግ ላይ
ናቸው፡፡
እስካሁንም ከ1000 በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ ከንክኪ ነፃ
የሆነ በፔዳል የሚሰራ እንዲሁም በሞተር ሳይል የሚሰራ ተንቀሳቃሽ የእጅ
መታጠቢያ፣ ለለይቶ ማቆያ የሚሆን አልጋ እና የህክምና አልባሳትን በመስራት
ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡

Federal TVET institute official students group

30 Apr, 12:27


ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 31ኛ ላይ ትገኛለች፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ለ17 ሺህ 842 ሰዎች የኮሮና ቫረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ የተገኝባቸው 130 ዜጎች ናቸው። ከነዚህም ውስጥ 59 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን 69 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማከምያ ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስም በኢትዮጵያ በቫይረሱ ሶስት ሰዎች ብቻ ናቸው ሂወታቸው ያለፈው፡፡

በደቡብ አፍሪካ 5 ሺህ 350 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የማቾች ቁጥር ደግሞ 103 ነው፡፡ በአፍሪካ ከፍተኛ ሞት የተስተናገደው በአልጄርያ ሲሆን 444 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡ ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት የተስተናገደባት አፍሪካዊት ሀገር ደግሞ ግብጽ ስትሆን 380 ያህል ዜጎቿን በሞት አጥታለች፡፡ በአፍሪካ ሶስተኛው ከፍተኛ ሞት የተስተናገደው ደግሞ በሞሮኮ ሲሆን 168 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

እስካሁኑ ሰአት ድረስ በአፍሪካ 35 ሺህ 935 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 1 ሺህ 566 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡ 11 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ እንዳገገሙ ነው ከጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ያገኝነው መረጃ የሚጠቁመው፡፡ በአፍሪካ ከሌሴቶ እና ኮሞሮስ ውጪ በሁሉም አገራት የኮሮና ቫይረስ ተሰራጭቷል ።

Federal TVET institute official students group

30 Apr, 12:24


Federal TVET Agency
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና
የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በየደረጃው የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና እና የካይዘን ኢንስቲቲዩት
ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
በመገኘት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡

Federal TVET institute official students group

30 Apr, 02:15


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፥ ገንዘብ ከሰማይ በራቀበት የድሆች ሃገር
ተቀምጠው ሳለ የሚያባክኑት፣ ለቧልት ስራቸው የሚረጩት ገንዘብ ሃይ ሊባል
ይገባል። ተቋማቱ የተሰጣቸውን አካዳሚያዊ ነጻነት እንደምሽግ በመጠቀም
ከውስጥ ሃብታቸው አልፈው መንግስት የዜጎችን ጉረሮ አንቆ የመደበላቸውን
ካፒታል ፕሮጀክቶችን ሳይቀር እያጠፉ ለደራሽ ማህበራዊ ስራዎች
ፊትአውራሪዎች በመምሰል የሚያባክኑት ሃብት በእጅጉ አሳሳቢ ነው።
መንግስት ኮሮናን መሰል ችግር ሲገጥመው የተቋማቱን ሃብት በማእከላዊነት
እያናበበ በመምራት የገጠመውን የሃብት እጥረት ችግር በመጠኑ መቅረፍ
ሲገባው ሁሉም በየፊናው እንዳሻው ሃብት ሲበትን መሃል ቆሞ መመልከቱ
ያለብንን ደካማ የሴክተር መስሪያ ቤቶች አመራር ዘይቤ በግልጽ ያሳየ ነው።
መንግስት ሃብት ፍለጋ ጆንያ አንከርፍፎ ሃገራትን፣ ድርጅቶችንና የኩባንያ
ባለቤት ቱጃሮችን ለማግባባት እና ለመለመን አለምን ከሚዞር፣ የሃገር ውስጥ
ባለሃብቶችን ደጅ ከሚጠና እራሱ የሚያስተዳድራቸው ተቋማት የበጀተላቸውን
ሃብት ወጭ ቆጣቢ እና ተገቢ በመሆነ መንገድ እንዴት እንደሚጠቀሙት
ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ስርዓት ቢዘረጋ
በብዙ መመዘኛ ያተርፋል።