በዝርዝር ስናያቸው እነሆ 👇
❶.አሊፍ ላም ሚም በሚለው ቅርፅ (الٓمٓ) ብቻ የሚጀምሩ ❻ ሱራዎች ናቸው።
እነርሱም፦👇
1- ሱረቱል በቀራህ
2- ሱረቱል አል ኢምራን
3- ሱረቱል አንከቡት
4- ሱረቱ አር'ሩም
5- ሱረቱ አል'ሉቅማን
6- ሱረቱ አስ'ሰጅዳህ
❷.አሊፍ ላም ሚም ሷድ በሚለው ቅርፅ (الٓمٓصٓ) የሚጀምረው አንድ ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱል አዕራፍ ብቻ ነው።
❸.አሊፍ ላም ራ በሚለው ቅርፅ (الٓر) የሚጀምሩ ሱራዎች ❺ ናቸው።
እነርሱም፦ 👇
1-ሱረቱል ዩኑስ
2-ሱረቱል ሁድ
3- ሱረቱል ዩሱፍ
4- ሱረቱል ኢብራሂም
5- ሱረቱል ሒጅር
❹. አሊፍ ላም ሚም ራ በሚለው ቅርፅ (الٓمٓر) የሚጀምረው ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እሱም ሱረቱ አር'ረዕድ ነው።
❺.ካፍ ሐ ያ አይን ሷድ በሚለው ቅርፅ (كٓهيعٓصٓ) የሚጀምረው ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱል መርየም ነው።
❻.ጧ ሃ በሚለው ቅርፅ (طه) የሚጀምረው ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱል ጧሃ ነው።
❼.ጧ ሲን ሚም በሚለው ቅርፅ (طسٓمٓ) የሚጀምሩት ሁለት ሱራዎች ናቸው።
እነርሱም፦👇
1- ሱረቱ አሽ'ሹዓራእ
2- ሱረቱል ቀሶስ
❽.ጧ ሲን በሚለው ቅርፅ (طسٓ) የሚጀምር ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱ አን'ነምል ነው።
❾. ያ ሲን በሚለው ቅርፅ (يسٓ) የሚጀምር ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱል ያሲን ነው።
❿. ሷድ በሚለው ቅርፅ (صٓ) የሚጀምር ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱ አስ'ሷድ ነው።
❶❶. ሀ ሚም በሚለው ቅርፅ (حمٓ) የሚጀምሩ ሱራዎች ስድስት ናቸው።
እነርሱም፦👇
1- ሱረቱል ጋፊር
2- ሱረቱል ፉሲለት
3- ሱረቱ አዝ'ዙህሩፍ
4- ሱረቱ አድ'ዱኻን
5- ሱረቱል ጃሲያህ
6- ሱረቱል አህቃፍ
❶❷. ሀ ሚም አይን ሲን ቃፍ በሚለው ቅርፅ ( حمٓ عٓسٓقٓ) የሚጀምረው ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱ አሽ'ሹራ ነው።
❶❸. ቃፍ በሚለው ቅርፅ (قٓ) የሚጀምር ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱል ቃፍ ነው።
❶❹. ኑን በሚለው ቅርፅ (نٓ) የሚጀምር ሱራ አንድ ብቻ ሲሆን እርሱም ሱረቱል ቀለም ነው።
♦️ በነዚህ የሱራ መክፈቻዎች የመጡ ፊደላቶች መዱል ላዚም ሀርፍይ ተግባራዊ የሚሆንባቸው እነዚህን አራት መስፈርቶች የሚያሟሉት ብቻ ናቸው።
መስፈርቶች
1) በሱራ በክፈቻ ላይ መምጣት አለባቸው።
2) ተበትኖ ሲፃፍ ፊደሉ ከሶስት ፊደላቶች የተቀናበረ መሆን አለበት።
3) ከሶስቱ ፊደላቶች መካከለኛው ፊደል የመድ ፊደል መሆን አለበት።
4) ከሶስቱ ፊደላቶች የመጨረሻው ፊደል ሱኩን መሆን አለበት።
🏝 ✍️ አቡ ሁዘይፋህ ኢብኑ ሙሃመድ
🔷 የሚለቀቀው ትምህርት ለሌሎችም እንድደርስ #ሸር አድርጉት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🌎t.me/Merkezhuzeyfetulyeman