💔 ስነ ልቦና 💆‍♀ @love_therapist Channel on Telegram

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

@love_therapist


ስለ
ጤና
ስነ ልቦና
ቤተሰብ
ጓደኝነት
የፍቅርና ወሲብ ጉዳዮች ላይ እንመካከራለን ።

የግለሰብ ችግር የማህበረሰብ ችግር ነው

የግለሰብ ጥያቄ የማህበረሰብ ጥያቄ ነው

ስለዚህ ጥያቄዎን ይዘው ይምጡና ለብዙሀን መልስ እና ማስተማሪያ ይሁኑ


ለማንኛውም ጥያቄ @therapist_100

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀ (Amharic)

ስነ ልቦና 💆‍♀ ለፍቅርና ወሲብ ጉዳዮች ላይ የፍቅርና ሥራዎችን የሚፈልጉት ነሐሴ ሳይንስቶች እና ምላሽ ጥያቄዎችን እና ማህበረሰብን ፕሮፌሰንን ማካፈል ያለብን መረጃዎች አሁንም የሚሰራ ነው። ውጤቶችን የሚለይበትን ይሸከማል። እኛም የምንወዳቸውን እርምጃዎች ማስተማር እና መልስ ይሁኑ። በተጨማሪም ጥያቄ @therapist_100

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

01 Nov, 07:37


#ማስታወቂያ

የውጪ ሀገር የስራ ዕድል

🇹🇭 ታይላንድ
🇬🇧 እንግሊዘኛ ቋንቋ እና የኮምፒውተር እውቀት

ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የለውም

የበረራ ትኬትና የፕሮሰስ ክፍያ ብቻ በራሳችሁ ትሸፍናላችሁ

ቅድሚያ የOnline ፈተና ይኖራል

ምግብ ማደሪያ ከድርጅቱ

ደሞዝ : 1200 dollar

ለበለጠ መረጃ : @cannada_1 ላይ አናግሩኝ


@cannada_1

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

30 Sep, 10:55


🥅 አላማ

መቼም ሰዉ የሚያስበዉ ሃሳብ ወይ አላማ ይኖረዋል፡፡ ያልማል...ይህን በዚህ አድርጌ ይህን በዛ አግብቼ አዉጥቼ ወዘተ... እያለ

አላማና ሃሳብ ጎን ለጎን ሲሄዱ ይጥማል፡፡አላማህ ከሃሳብህ ስር ሆኖ ‘ወደፊት!’ እያለ ሲነዳ ይጥማል፡፡አላማህ ቆራጥ መሆንን የሚጠይቅ ስርአት ነዉ፡፡አላማ ቀለል ያለ በማንኛዉም ጊዜና ስፍራ ልትፈፅመዉ እንደምትችል የምትገነዘበብበት ድራማ አይደለም፡፡

አላማ ዋጋ ያስከፍላል፣ከብዙ ሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት አላማህን ለማስፈፀም ደፋ ቀና ስትል ትጋጫለህ፣ትቆስላለህ፡፡ታዝናለህ፣ትናደዳለህ...

ሃሳብህ የአላማህ ደጋፊ እንዲሆን ሁሌም መስመር አስይዘዉ፡፡ ነገር ግን ላገኘኸዉ ሰዉና “አላማህ ምንድነዉ?” ብሎ ለጠየቀህ ሁሉ መናገር አግባብ አይደለም በተለይ አብሮህ ሊቀጥል የሚችልና ረጅም ጉዞ ያለዉ መንገድ እንደምትጓዝ ከተገነዘብክ ዝምታን ምረጥ

ዝም ብሎ ስራን መስራት፣ዝም ብሎ አላማን ማሳካት፣ዝም ብሎ ወደፊት! ፍሬ ስታፈራና ነገሮች ሲሳኩ የሚከቡህ ሰዎች እንደአሸን እንደሚበዙት ሁሉ 'ፍሬህ ሲደርቅና ስትከስር' እንደሳር ይደርቃሉ፡፡አንተ ግን ሁሌም ፊትህን ወደ ኣላማህ!

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

17 Sep, 06:48


🥰 ሰውን ከማስደሰት ፣ በተቻለው አቅም ከመርዳት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ ? 😍

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

13 Aug, 03:47


💸 ቢዝነስ

$ እንደ ጥንቃቄ

ብር ለምታምኑትም ለማታምኑትም ሰው አታበድሩ:: በዚህ ዘመን ብድር የሚመልስ ሰው ማለት ሐዋሪያዊነት የተቀባ ነው:: ግን ማን ይታመናል? ሰው በተፈጥሮው አጭበርባሪ ሆኖ ሳይሆን ያለንበት የኑሮ መዋቅር ገንዘብ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ብሩ ወዲያው ይጠፋል:: መተካት ስለማይችል ከጭንቀት ብዛት መካድና እናንተን ማራቅ ይመርጣል::

$ መነሻ ላይ

የኢንቨስትመንት ወጭ እና ኪሳራ በፍጹም እንዳትፈሩ:: እንደ ወጪ እንዳትቆጥሩት:: ከከሰረም ካተረፈም አይመለከታችሁም:: በሁለቱም ትምህርት አለ:: ላለመክሰር ጥረት ማድረግ ነው:: ትርፍ ማለት በምንወስደው ሪስክ መጠን ነው:: ሪስክን ከፈራን ትርፍም አያጓጓን የሚሉ ኢንቨስተሮች እንዳሉ ሁሉ ሪስክን መዳፈር የእቅድና የመረጃ ትንተና አናሳነት ነው የሚሉም አሉ:: በሁለቱም በኩል የተሳካላቸው ቢሊኒየሮች ምልከታ ነው:: ኤለን መስክ ሪስክን ሲዳፈር ዋረን ቡፌት ግን ተንትኖ ይገባል:: በእርግጥ አሜሪካውያን ለእኛ ምሳሌ ባይሆኑም ሆነዋል::

$ የመጀመሪያዎቹ ዐመታት ላይ ለሥራው ሙቱለት:: ድከሙለት:: እናንተም ሥራውን ዕወቁት:: ሥራውም እናንተን ይወቃችሁ:: ከዚያ አከፋፍላችሁ ታሸጋግሩታላችሁ::

$ በግል እንጂ በቡድን ባትንቀሳቀሱ
የካፒታሊዝም ዘመን ማለት የግለኝነት እና ገንዘብ የመነጣጠቅ ዘመን ነው:: በግላችሁ ከባንክ ወይም አበዳሪ ተቋማት ጋር ብትሠሩ ይመከራል:: ካፒታል ማግኛ እነኮላተራል አዳብሩ:: ተበደሩ:: ከዚያ ቅጠሩ/አባሩ:: ትርፍ ገንዘብ ሲኖራችሁ የጀመራችሁትን ሥራ የማያደናቅፍ ዓይነት ብር አስተማማኝ አክሲዮኖች ላይ ብቻ ኢንቨስት አድርጉና እርሱት:: አክሲዮን ማለት እኮ የቡድን ሥራ ሆኖ በቦርድ የሚተዳደር ነው:: እናንተ ሳትሆኑ ብራችሁ ይሠራና ዲቪደንድ ታገኛላችሁ:: ብሩም ከግሽበት ይጠበቃል:
©Hasen injamo

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

25 Jun, 14:49


🤨 ምኞቴ

ልጅ እያለሁ ትልቅ መሆን እመኝ ነበር እናም 'ልክ 30 አመት ሲሞላኝ በእርግጠኝነት እነዚህ ነገሮች ይኖሩኛል..!' ብዬ አስብ ነበር

• በወር 60 ሺህ ብር እየተከፈለኝ መስራት
• ጂ+2 ቤት እስከነ መዋኛዉ
• ሜርሴዲስና ኢነፊኒቲ መኪና
• በጣም የምታምር ሚስት እስከነ ዉብ ባህሪዋ

አሁን ላይ ያቀድኩትን ህልም ወደኋላ ሳየዉ አንድ ነገር ብቻ በትክክል አሳክቻለሁ!...' ትልቅ ሰው ሆኛለሁ 30 አመት ከደፈንኩ!'

ዋናዉ ቁም ነገሩ በአቅምህ ልክ ጠንክረህ ስራ፣ ጤንነትህን ጠብቅ ከዛ ደስተኛ ሁን አለቀ! ህይወትን እንጂ ከህይወት ጋር የሚከተሉ እቃዎች ላይ ብቻ በማለም እድሜህን አትጨርስ፡፡

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

15 Jun, 04:18


🤔ኑሮክ

አንዳንድ ጊዜ አጠገብህ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን በቀላሉ ሲያገኙና በትምህርት፣ በሥራ በትዳር... ቶሎ ስኬትን ሲጨብጡ ታያለህ። አንተ ግን አንድ ቦታ ቆመሃል። ወቅቱ የእነርሱ ነውና ከመቅናት ይልቅ ባገኙት ስኬት የደስታቸው ተካፋይ ሁን። ለእነርሱ ያደረገ አምላክ ላንተም እንደሚያደርግልህ እመን። ይሀውልህ፤ የማንጎ ዛፍ የቡርቱካን ዛፍ ከርሱ ወቅት ቀድሞ ምርትን ስለሚሰጥ አይጨነቅም። ሆቴል ውስጥ ያለ ምግብ ተቀምጬ ብታየኝ ልታዝንልኝ አይገባም፣ ያዘዝኩት እስኪደርስ እየጠበኩ ነውና።

ስኬት፣ በወቅት የሚታጨድ መኸር ነው። ወቅትህ ሲሆን ምንም ነገር ከመንገድህ ሊቆም አይችልም። የአንበሳ በዝግታ መራመድ ስንፍናን ወይንም ድካምን አያመለክትም፤ ያለመውን አደን በእጁ ለማስገባት እርምጃውን እያሰላ እንጂ። የሰዎች ፈጥነው መራመድ አያውክህ። በቃ! የራህን ኑር!፤ ፈጣሪህን ታመን። ልብ በል፤ ቤትህን በፍጥነት ሠርተህ መጨረስህ ሳይሆን ንፋስና ጎርፍን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አድርገህ መሥራትህ ነው ቁምነገሩ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። የእውቀት ሰውና ጠንካራ ሠራተኛም ሁን!

ደግሞ ሁሉንም አታገኝም!

አንተ የተሳፈርክበት አውሮፕላን መሬት ሲያርፍ፣ ከዛ መሬት የሚነሣ አውሮፕላን አለ፤ ሌሎች ደግሞ ለመነሳት በሂደት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም መዳረሻቸው የተለያየ ነው፤ ምናልባትም ወዳንተ መነሻ ሊሆን ይችላል። አየህ ህይወት እንዲ ናት፤ "ደረስኩ" ብለህ ስታስብ ሌሎች ያንን ሥፍራ "ጥለው" ሲነሱ ታገኛቸዋለህ። አንዳንዶቹ አንተ ወደ ተነሳህበት፣ ሌሎቹም ወደ ሌላ።

በልጅ ማጣት ምክንያት ቀን ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዳሉ በልጆቻቸው ምክንያት ቀንና ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች አሉ። ባለማግባታቸው የሚጨነቁ ሰዎች እንደገጠሙኝ ሁሉ በማግባታቸው የሚጨነቁም ሰዎች ገጥመውኛል። በሥራ እጥረት ምክንያት የታመሙ እንዳሉ በሥራ ብዛት ምክንያት የሚታመሙ አሉ። ልጆቻቸው ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡላቸው የሚጨነቁ እንዳሉ፣ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲገቡላቸው የሚጨነቁ አሉ።

ህይወት እንዲህ ነው፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም!፣ ንፋስን አባሮ እንደመያዝ ነውና። ሁሉንም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ እንደሚያሸጋግርህም ፈጣሪህን ታመን።
ሁልጊዜም በአምላክህ ደስ ይበልህ!
በእምነትም ኑር!

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

19 May, 06:33


👧 ትክክለኛዋ ሴት

ማንኛዋንም ሴት ጓደኛህ ለማድረግ ካሰብክ ትችላለህ፡፡ ትክክለኛና ያንተን ባህሪይ የምታዉቅ ጓደኛ ማግኘት ግን ይከብዳል!

ስለዚህ ትክክለኛዋን ለማግኘት በሳል ነች ብለህ ከገመትካት ሴት ጋር ግንኙነት ጀምር...ከዛ በጊዜ ሂደት ማን ምን እንደሆነ ትደርስበታለህ፡፡

እዚህ ጋር ግን ሴቶችን በአንዴ አዉቀህ የምትጨርሳቸዉ እንዳልሆኑና ሁሉንም በአንድ ጎራ መጨፍለቅ እንደሌለብህ ነዉ፡፡

ትክክለኛዋ የሴት ጓደኛ ማለት:

•ስሜትህ በተረበሸበት ሰአት ከጎንህ የምትሆን (ምንም አይነት ምክንያት ቢኖራትም)

•ቢኖርህም ባይኖርህም አንተነትህ ብቻ የሚበቃት

•ከሁኔታዎች መዘበራረቅና መሳካት ጋር ግኑኝነታችሁን ከፍና ዝቅ ለማድረግ ሀሞቱ የሌላት

•ስትጋጩ ያልተገባና ዉስጥህን ሊሰብር የሚችል ንግግር ሊወጣት የማትደፍር

•ስሜትህና ማንነትህ በተደበላለቁብህ ጊዜ...ስሜትህን ወደስሜቱ ማንነትህን ደግሞ ወደማንነቱ የምትመልስ ዉብ ሴት ነች፡፡

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

05 May, 02:01


“አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ" ማርቆስ 16:6

እንኳን አደረሳችሁ!

@love_therapist @love_therapist

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

25 Apr, 05:27


📖 ትምህርት እና ፍቅር

‘በትምህርት ቆይታህ ፍቅር መጀመሩ ጥሩ ነዉ ወይስ ይጎዳል?’ ለሚለዉ ጥያቄ ሰዎች የተለያየ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡ እኔ ከህይወት ልምድ እንደተረዳሁት ግን ላጤ ሆኖ መኖር የበለጠ ሰላም እንዳለዉ ነዉ፡፡

ትምህርቱን፣ የፍቅር ግንኙነቱንና ሌላዉንም ነገር ባላንስ አድርገዉ የሚሄዱ ሰዎች ከስንት አንዴ እንዳሉ ብረዳም የኖርማል ሰዉ ህይወት ግን ከዚህ የወረደ መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡ አእምሮአችን አንድ ነገር ላይ ብቻ አተኩሮ የመስራት ባህሪይ ስላለዉ በአንድ ጊዜ ስናበዛበትና ስንንቀሳቀስ ይዝላል፣ እንደሚገባዉ ለመስራትም ይቸገራል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ትምህርት የጀመረ ሰዉ እራሱን ትምህርቱ ዉስጥ አስጥሞ በብቃት ለመጨረስ ‘ብቻዉን’ መንቀሳቀሱ የበለጠ ዉጤታማ ያደርገዋል፡፡ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ እራሱን እምርሮ የገባን ተማሪ በብዙ አይነት ጭንቀት ተወጥሮ ማየት የተለመደ የእለት ተእለት ህይወት ነዉ፡፡

✓ስልክ ስደዉል ለምን አላነሳህም?

✓አሞኛል ና!

✓ የት ነህ!

✓ማጥናት አልቻልኩም!

✓አብረን ወክ እንድርግ

✓ዛሬ ክላስ ቅጣዉና የሆነ ቦታ እወስድሃለሁ

✓ብሩን ላክልኝ!

✓F አምጥቻለሁ...

✓አሁንስ ተስፋ ቆረጥኩ ና የምታደርገዉን አድርግ!

✓ እንዳታናግረኝ!

✓ ከክላሴ ልጅ ጋር ምን እያልካት ነበር?


አስበዉ! ከላይ ከተዘረዘሩት 'ቫይረሶች' ተመርምረህ ነፃ መሆን አላማረህም ?

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

24 Mar, 12:52


🤗 መልካም ባህሪ

• ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

• አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር

• ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ

• ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

• ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

• ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

• ፀዳ በል፡፡ በደንም ልበስ፣ ፏ በል!

• ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

• አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

• በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

• ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ መዝናቸዉ

• የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናር

• ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

• ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

• ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

• የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

• ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

23 Mar, 05:08


😎 ከሃዘን ለመውጣት ...

የሆነ ቀን አዝኜ ነበር ... ከዛ

እኔ፡ ይሄ ቢጫ ቀሚስሽ በጣም ያምራል!

ፍቅረኛዬ፡ እዉነት?

እኔ፡ እዉነቴን ነዉ!

ፍቅረኛዬ፡ የምትጠላዉ ይመስለኝ ነበር፡፡

እኔ፡ እንደዉም ይሄን በጣም እወደዋለሁ!

ፍቅረኛዬ፡ አመሰግናለሁ ዉዴ!

ፍቅረኛዬ ፊቷ ላይ ደስ የሚል ስሜት ተሰማት፡፡ እኔንም ደስ አለኝ

ደስታ የሚመነጨዉ ሌሎችን ሰዎች ደስ ለማሰኘት ስትሞክር ነዉ፡፡ ለዚህ ነዉ ሰዎች ደስታ ይጋባል የሚሉት ።

ስለዚህ ... ከሃዘን ለመውጣት ... ሌላ ሰው አስደስት

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

17 Mar, 13:54


😑 ትዕግሥት

ትንሽ ትግስት ስላለህ ብቻ ምን ያህል ችግር ተቋቁመህ እንዳለፍክ እስኪ ወደኋላ ዞር ብለህ ተመልከት፡፡

ሰዎች የሆነ ነገር ለመግዛት ሲፈልጉ አቅሙ እስኪኖራቸዉ ድረስ ታግሰዉ ቢቀመጡ ስንት የእዳ ክምር እንደሚቀንሱ ታዉቃለህ?

ትግስት የህይወት እንዱ ቅመም ነዉ፡፡ የማይመቹ መንገዶች ህይወትህን ቢሞሉትም ትንሽ ታገስ...ነገሮች ይለዋወጣሉ: የዛኔ መታገስህ ለመልካም እንጂ ለክፉ እንዳልሆነ ታዉቃለህ

ትግስት አይታለፉም የተባሉ ክፉ ጊዜያትን እንድታልፍ ያደርግሃል፡፡አምላክህን ትእግስት እንዲሰጥህ እየጠየቅክ ነገሮችን ዝቅ ብሎ ማሳለፉ ለነገ ወሳኝ ሚና ይጫወታል

ትግስት አጥቶ ስንቱ ሰዉ አላማዉን እንዳይነሳ አድርጎ ገደለዉ?ተስፋዉን እንዳይለመልም አድርጎ ቆረጠዉ!

አንተም ከማይታገሱት ጎራ እንዳትሆን እራስህን መልካም ፍሬ ባለበት በትእግስት ሰፈር አሳርፍ!

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

16 Mar, 12:00


🔅 ነገ

የነገዉን ማሰብ በራሱ ምንም ክፋት የለዉም፡፡ ነገ መጥፎም ይሁን ደግ ነገን አልሞ መነሳቱ እንከን የማይወጣለት ነገር ነዉ፡፡ በተለይ በኛ ሀገር ባለዉ ነባራዊ የህብረተሰባችን አኗኗርና የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ነገን ማሰብ ያልተለመደ ነዉ፡፡

አሁን ባለሁበት ሁኔታ የምኖር ከሆነ ነገን እንዴት አልፋለሁ ብሎ ማሰብ እግዚአብሄርን እንደማቆስጣት እናየዋን፡፡ አዎ ነገን ሁሉን ለሚችለዉና በእጆቹ ለሰራዉ ፈጣሪ አሳልፈን መስጠት ብልህነት እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ነገን እሱ ስለሚያዉቅ ከኛ መላምት ፍፁም በማይገናኝ መልኩ የእሱ ቸርነት ያስፈልገናል፡፡ ተስፋችንም እሱ ነዉ፡፡

ግን አልመን መነሳታችንና ማቀዳችን አምላክ በሰጠን አእምሮ መጠቀማችን ጥቅሙ እንጂ ጉዳቱ አያመዝንም፡፡ ዛሬ እያየን ያለናቸዉ የራሳችን የህይወት ዉጥንቅጥ እንዳናስተዉል የሚገፋፉን ቢሆንም ወደፊት በተስፋና በሙሉ ቆራጥነት መገስጉ እጅግ ይጠቅመናል፡፡

ነገን ‘የራሱ ጉዳይ!’ ብለን ያገኘናትን የምንበትን ከሆነ፣ ‘ልሙት ልኑር የት አዉቃለዉ?’ ብለን 'ዛሬን ቸባ!' እያልን የምንደልቅና የምናስደልቅ፣ ዛሬን በቀልድና በዝባዝንኬ አሳልፈን ነገን በቁጭት ከመኖር እስኪ ቆፍጠን ብለን ህልማችንን፣ ሃሳባችንን ስጋ አልብሰን ለማየት እንነሳ!

ወሬዉ፣ ቀልዱ፣ ጭፈራዉ ሁሉ ከስራ ሲቀድሙ ይዘዉን ገደል ይከቱናል...አሁንም እየከተቱን እያየን ነዉ፡፡ ምክንያት ለመፍጠር ቅንጣት ያህል ሰበብ ብቻ በሚኖርበት በዚህ ሀገር፣ የግል ህልማችንን ለማነፅ መሄድ እንደቀረ ፋሽን ሊያስመስለን ቢሞክርም በቃ እንነሳ... የሌላዉ አጨብጫቢ ሆኖ መኖር ይበቃናል!

“ፓ እንትናን አየሃት!” እያልን የጎረቤት የሃብት ምጥቀትን እንደቃና ቲቪ ፊልም አሳምረን ከምንተርክ እንኑረዉ...ተራኪ መሆን ያማል፣ መጨረሻዉ አምስት ሳንቲም የሌለዉ ማንነት ይዞ መቅረት ነዉና ዳይ ወደስራ!!

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

14 Mar, 13:34


🕶 ሃላፊነት አለመዉሰድ-በህይወትህ 100 ፐርሰንት ኃላፊነት እራስህ ዉሰድ፡፡

ይሄ ማለት የሆነ አስደንጋጭ ሲደርስብህ እንዴትና ምን እንደምታደርግ የምትወስነዉ 100 ፐርሰንት እራስህ የምትፈፅመዉ ነዉ፡፡

  • የምትፈልገዉን ነገር አለመጠየቅ - ስኬታማ ሰዎች እንደሚናገሩት የምትፈልገዉን ነገር በአጭሩን ግልፅ በሆነ መንገድ ካልጠየቅክ ማንም ዉስጥህን ሊያነብልህ አይችልም፡፡

ለምሳሌ የምትወዳት ሴት ካለች እንደምትወዳት ካልገለፅክላትና 'ይገባታል' ብለህ ለረዥም ጊዜ ዝም ማለት እንድታጣት ሊያደርግህ ይችላል፡፡

በሌላ መንገድ ደግሞ አለቃህን የደረጃ እድገት እንዲያደርግልህ ከመጠየቅ ይልቅ ‘ይገባዋል’ ብለህ ዝም ብትል፡ ነገሮች ይለዋወጡና ምንም ነገር ሳይፈጠር ይረፍድብሃል፡፡ ስለዚህ ዉስጥህ ያለዉን ነገር ለሚመለከተዉ ሰዉ ብቻ ቀጥተኛ ሆነህ በድፍረት መናገር ያስፈልጋል

• ‘አይሆንም ወይም አልችልም’ አለማለት- ሰዎችን ለማስደሰት መሄዱ ይብቃህ፡፡ የማትፈልገዉ ነገር ላይ ያለመሳተፍ መብት እንዳለህ ወስነህ አትሳተፍ!

የሆነ ሰዉ ካንተ ፍላጎትና ሃሳብ ዉጪ የሆነ ነገር ፈፅምልኝ ቢልህ ጓደኛህን ለማስደሰት ብለህ አታድርግ! መጨረሻ ላይ አልችልም በማለትህ ሃሳቡን ያመጣዉ ጓደኛህ እንኳን ሳይቀር እንዲያከብርህ ያደርገዋል፡፡

• ስራን ወደነገ ማስተላለፍ- ነገ እሰራዋለሁ ማለት የስኬታማ ህይወት ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ማነቆ ነዉ፡፡ ጉዳይ ማለቅ እንዳለበት ካሰብክ ለምን መጨረስ እንደፈለክ ምክንያቶችህን መዝናቸዉ፡፡

ስራዉን በሰአቱ ሰርተህ መጨረስህ ትልቅ ሽልማት እንደሚያስገኝልህ አምነህ ዛሬን በትክክል ተጠቀም፡፡ ዛሬን ያባከንከዉን ጊዜ፣ ጉልበትና አቅም 'ነገ እተካዋለሁ' ብለህ አታስብ... ነገ ሌላ ቀን ነዉ!

• ካጠርከዉ የምቾት አጥር አለመዉጣት- ከምታስባቸዉ ምቾቶችህ ወጥተህ የህይወትን አስቸጋሪ ተራራ ለመዉጣት ካልቆረጥክ ነገን የማየት እድልህ እየመነመነ ይመጣል፡፡

  • የምትወደዉን ስራ መምረጥ-አሁን የማትወደዉን ስራ የምትሰራ እንኳን ቢሆን የምትወደዉን እስክታገኝ መስራትህን አታቁም፡፡ የያዝከዉን እንደድልድይ ትጠቀምበታለህ፡፡

ነገር ግን ህይወት በጣም አጭር ነች...ወደምትወደዉ ስራ ለመግባት መተኛት የለብህም በፍፁም! ለነገ ካልቀረብክ ነገ ቤትህ ድረስ መጥቶ እንደሎተሪ ሊያድልህ አይችልም፡፡ ጊዜህን አታባክነዉ...መስራት ባለብህ ነገር ተነስተህ ስራ!

  • ለጥል ሌላ እድል መስጠት - ሰዉ ይጣላል...ስትጣላ ነገሮች እንደዚህ መገለባበጣቸዉ ያሳዝንሃል፡፡ ያስቆጣህማል!

ይሁን እንጂ የተጣላህን ሰዉ ወደለየለት ጦርነት ዉስጥ መግባት ያለዉን አቅም ይሟጥጠዋል፡፡ ከዛ ሰዉ ዘወር በማለት ያቆምከዉን ስራ መቀጠሉ ይበጃል፡፡

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

13 Mar, 15:35


👗 የሴቶች ሳይኮሎጂ
⛔️( ቁም ነገር አይደለም )

👉 ድሮ

ሳይኮሎጂ-ሴቶች በተፈጥሯቸዉ በራሱ የሚተማመን ወንድ ይወዳሉ፡፡ እራሱን የሚጠብቅና ለራሱ ዋጋ የሚሰጥ ወንድ አንደኛ ምርጫቸዉ ነዉ፡፡ ሴቶች የሚያስቃቸዉን ሰዉ በጣም ይወዳሉ

👉 ዘንድሮ

የድሮዎቹ በ'ሳይኮሎጂና በሳይንስ' ሲጠቃለሉ ያሁኖቹ ደግሞ በ'ሂሳብ አያያዝና በገንዘብ አሰባሰብ፣ አነዳደፍ፣ አቀፋፈል እንዲሁም በብር ጤና አጠባበቅ' የተካኑ ዶክተሮች ናቸዉ፡፡

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

12 Mar, 12:46


🥹 ጓደኛ / ጉደኛ

አንድ ጊዜ ከጓደኞቼ ጋር አብረን እየተዝናናን የሚያናድድ አይነት ቀልድ አወራሁ፡፡ ሁሉም እያዩኝ ዝም ዝም አሉ...

ግን ባያስቅም የዉስጣቸዉን እንዳላዉቀዉ ፈገግ ነገር አሉ፡፡ እኔ ይህንን ያደረኩት አዉቄ ነበር...'እስኪ ስለኔ ምን እንደሚሉ እሰማለሁ!'አልኩና ቀስ ብዬ ሞባይሌን ሪከርደር ላይ አድርጌ ስልኬን እዛዉ አስቀምጬ ሽንት ቤት ደርሼ ልምጣ አልኩና ተነስቼ ሄድኩ፡፡

ስልኬ ከሄድኩ ጀምሮ የሚሉትን በሙሉ እየቀዳቸዉ ነበር፡፡ ከዛ መጣሁና ሪከርደሩን አቆምኩት...ምንም እንዳልተፈጠረ በመምሰል ወሬያቸዉን ተቀላቀልኩ፡፡

ከተለያየን በኋላ ቤት ገብቼ የስልኬን ሪከርደር ከፈትኩት...አቤት! ያልሰደቡኝ ስድብ አልነበረም!

“ይሄ ሰገጤ፣ ፋራ እኮ ነዉ ከፋራ ጋር ተቀምጠን፣ ጥርስህን አሳይተኸዉ ሌላ ቀን ሲደዉል ላሽ ማለት ነዉ...” በዛ ሰአት የተሰማኝ ስሜት እንዲህ ነዉ ብዬ ለመግለፅ እንኳን ቃላት ያጥረኛል፡፡

አሪፍ መስለዉ የሚታዩህ ሰዎች ልክ ዞር ስትል ስላንተ ክፉ ነገር ያስባሉ፣ ይረማመዱብሃል፡፡ የዛኔ እዉነተኛ ማንነታቸዉን ታዉቃለህ!

እስኪ አንድ ቀን ስልክህን ሪከርደር ላይ አድርገህ የሰዉን የልብ ምት አዳምጥ...

አደራ ዉስጥህ ሊደማ ስለሚችል እራስህን በተቻለህ መጠን አረጋግተህ ማን ምን እንደሆነ ፈትሸዉ!

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

07 Nov, 21:00


🤩 1⃣0⃣0⃣0⃣ ቀናቶች 🦋

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

24 Oct, 06:46


ክፍል -2-

👉 አምነክ ተቀበል

አንዳንድ ጊዜ ህመም እንኳን እንዳልተሻለህ እያሰብክ ከሆነ ጤናህ መዛባቱን አያቆምም ስለዚህ የማይሆን ነገር እንደሆነ እያወክ ተመልሳ ትመጣለች ብለህ ተስፋ ማድረግ የህመምህን ጊዜ ማራዘም እና የራስህንም የሷንም ሰላም በራስ እጅ መንሳት እንደሆነ አውቀህ አጉል ተስፈኝነትህን ገታ አድርግ ።

👉 ሌሎች ሰዎች ላይ አተኩር

መለያየት ሌሎች ጊዜ የነፈካቸው ሰዎች ።  ወደ አዲስ የፍቅር ግንኙነት መጣደፍ ጥሩ ሀሳብ ባይሆንም ፣ በቤተሰብ ፣በጓደኞች እና በስራህ ላይ ማተኮር ቆንጆ ነገር ነው ።

ከፍቅረኛ ጋር ከተለያየህ በኋላ ብቸኝነት ማዘውተር ፈፅሞ አይመከርም ስለዚህ ከሌሎች ሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ እና መዝናናት ተመራጭ አድርግ ።


👉 ራስህን ተንከባከብ

መለያየት ከራስህ ጊዜ እና ትኩረት እንድትሰጥ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልሃል ።

ራስህን በብዙ ነገር ስትበድለው እንደነበር እና መካስ እንዳለብህ ሊሰማህ ይገባል ፣ጋር ስለዚህ ሰውነትህን እና ስሜትህን በደንብ ተንከባከብ ።

ቅድሚያ መስጠት ያለብህን ነገሮች ላይ ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለመወሰን ቆንጆ አጋጣሚ ስለሆነ ተጠቀምበት ፣ በቂ እንቅልፍ ፣ የፈለከውን ምግብ ፣ የአካል እንቅስቃሴ እንዲሁም መሄድ ምትፈልጋቸው ቦታዎችን እና መረግ ምትፈልጋቸውን ተግባራት ሁሉ ፈፅም ።

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

21 Oct, 11:18


💔 ከፍቅረኛ ጋር ከተለያየን በኋላ ...

ክፍል -1-

አንድ ሰው ምን አለ " የፍቅር ግንኙነት ተቋረጠ ማለት መጥፎ ግንኙነት ነበር ማለት ስለዚህ መደሰት እንጂ ማዘን አያስፈልግም "

መለያየት ፣ ፍቺ እና ለጊዜው መጣለት እንኳን በጣም የሚያሠቃዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ ፣ ለኛ የማይሆን ሰው እንደነበር እና ወደ ተሻለ ሁኔታ እና ጥሩ ግንኙነት ሊመራን እንደሆነ እያወቅን ራሱ ያንን ጥሩ ያልነበረ ግንኙነት ካቋረጥን በኋላ ሀዘናችንን መቋቋም ሊያቅተን ይችላል ።

ስለዚህ ከእንደዚህ አይነት ሃዘን ለመራቅ እነዚህን ነጥቦች ፈፅሞ መዘንጋት የለብንም ።

👉 የፍቅር ግንኙነት ተቋረጠ ማለት የአለም ፍፃሜ ነው ማለት አይደለም ።

ምንም አይነት ፍቅር ቢኖርብህ እንኳን ተፋታችሁ ማለት ፣ ህይወትህ አብቅቷል ማለት አይደለም ። ይልቁንም፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘት እና አዲስ ግንኙነቶችን ለመመስረት ጥሩ አጋጣሚ  ሊሆን ይችላል። መጀመሪያ አከባቢ ሌላ ሰው ለማየት ከባድ ሊሆን ቢችልም ስለ ወደፊቱ ጥሩና የተሻለ እድል እየመጣ እንደሆነ ማመንና መጠበቅ አለብህ ።

👉 እራስህን በፍፁም እንዳትወቅስ

ግንኙነት አብዛኛውን ጊዜ ሁለት ሰዎችን የሚመለከት ጉዳይ ነው ስለዚህ ለተፈጠረው ጉዳይ የተወሰነ ሃላፊነት ብቻ ነው ሊኖርህ የሚችልው ።

እራስህን ስትወቅስ በተሳሳትካቸው ነገሮች ወይም እንዲህ ማረግ ነበረብኝ ብለህ ልትፀፀት ትችላለህ በዚህ መሃል ራስህን ከመንከባከብና ስለወደፊቱ ከማሰብ ይልቅ ራስህን ልትጎዳና በጥፋተኝነት ስሜት ልትሰቃይ ትችላለህ ።

ላጠፋከው ነገር ሃላፊነት መውሰድ ፣ ራስህን እና አጋርሀን ይቅርታ መጠየቅ እና ለሌላ ጊዜ ትምርት እንዲሆንክ አለመዘንጋት ቆንጆ ነገር ቢሆነም ነገሩን አስሬ እያሰላሰሉ መኖር ምንም ጥቅም ስለሌለው ገንቢ የሆኑ ሃሳቦች ላይ ብቻ ትኩረት አድርግ ።

ይቀጥላል ...

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

20 Oct, 12:37


🤗 ሃብታም ነህ

በስራ ፣ በገንዘብ እና ብዙ ነገር በሚያምርህ በዚህ ወቅት ሃብታም ነህ ስልህ እየሰደብኩህ ያለሁ ይመስልሃል ፣ እየቀለድኩብህ ይመስልሃል ... ልክ ነህ ግን አንዴ ብቻ ስማኝ 

የሰው ልጆች ዋና ሃብት የሚባሉት
👉 ጤና
👉 እውቀት / ክህሎት / ችሎታ
👉 የደስተኝነት ስሜት ናቸው

ገንዘብ ፣ ንብረት ፣ ኢንቨስትመንቶች ያለ እነዚህ ዋና ሃብቶች ከየትም አይመጡም ።

ጤነኛ ስለሆንክ ፈጣሪን አመስግን ፣ ባለህ እውቀትና ችሎታ ራስህንም ሌሎችም ሳትታክት አገልግል ፣ በዙሪያክ ላሉ ለምትወዳቸውና ለሚወዱክ ሰዎች ስትል ደስተኛ ሆነህ ለነሱም የደስታ ምንጭ ሁን ፣ ሌላው በጊዜው ይደርሳል ።

እናስ ሃብታም አይደለህም  ???

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

20 Oct, 09:48


🥛 ደግነት ይከፍላል

በአንዲት አነስተኛ ከተማ የሚኖር ምስኪን ልጅ የትምህርት ቤት ክፍያውን ለመክፈል ቤት ለ ቤት እቃዎችን እየሸጠ ይኖር ነበር ።

አንድ ቀን ምንም ሳይሸጥ ውሎ በጣም ራበው በሚቀጥለው ቤት ምግብ ለመጠየቅ ወሰነ ።

ከዛም ሲደርስ አንዲት ልጅ ሴት በር ስትከፍት አፈረና ከምግብ ይልቅ ውሃ ብቻ እንድትሰጠው ጠየቀቃት ። እሷ ግን እንደተራበ ገብቷት ነበርና በአንድ ትልቅ ብርጭቆ ወተት አመጣችለት።

ደስ ብሎት ቁጭ ብሎ ጠጣው እና “ምን ያህል እዳ አለብኝ?” ሲል ጠየቃት።

“ምንም ዕዳ የለብህም” ፣ "እናቴ ለደግነት ክፍያ ፈጽሞ እንዳልቀበል አስተምራኛለች." ብላ መለሰች ።

እሱም “ ከልቤ አመሰግንሃለሁ” ብሎ ተሰናበታት።

ከዛ ቤት ሲወጣ፣ አካላዊ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም በረታ በእግዚአብሔር እና በሰው ላይ ያለው እምነትም ጠነከረ ።

ትምህርቱን ለማቆም እና በከንቱ እንደሚለፋ ተሰምቶት የነበረው ስንፍናና ተስፋ መቁረጥ ሁሉ በአዲስ መንፈስ ተሞላና ሳይታክት ጠንክሮ መስራት እና መማር ቀጠለ ።

ከዓመታት በኋላ ያቺ ወጣት ሴት በጠና ታመመች። የአካባቢው ዶክተሮች በበሽታዋ ግራ ተጋቡ ። በመጨረሻ ወደ ትልቁ ከተማ ላኳት፤ እዚያም ስፔሻሊስቶች ተጠርተው በሽታዋን መመርመር ጀመሩ ።

አንድ ዶክተር ግን የመጣችበትን ከተማ ስም ሲሰማ ትኩረቱን ሳበው  ወዲያው ወደ ተኛችበት ክፍል ሄደ።

ወዲያውኑ ለዚህ ደረጃ ያደረሰችሁ ያች ደግ ልጅ እንደሆነች አወቃት። ህይወቷን ለማዳን የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጦ ልዩ ክትትል ያደርግላት ጀመር ።

ከብዙ ትግል በኋላ አገገመች ፣ ተሽሏት የመውጫዋ ቀንም ደረሰ  ፣ ዶክተሩም ወደ ሂሳብ ክፍሎች ደውሎ የክፍያ ደብዳቤውን ሳይሰጧት በፊት እንዲልኩለት ጠየቀ እንደደረሰውም ተመለከተውና ጫፉ ላይ የሆነ ነገር ፃፎ ሂሳቡ ወደ ክፍሏ ተላከ።

ለመክፈት ፈራች, ምክንያቱም ውድ እንደሚሆን እና ሙሉውን ለመክፈል ቀሪ ህይወቷን  እንደሚፈጅ እርግጠኛ ነበረች ።

በመጨረሻም ከፈተችው ፣ እናም የተፃፈው ነገር ግራ አጋቢ ሆነባት ። እንዲህ ይላል ...

“ሙሉ ሂሳብሽ በአንድ ብርጭቆ ወተት ተከፍሏል።

💌 ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ💌
         @therapist_100
        @therapist_group
    ሼር @love_therapist ሼር

2,855

subscribers

17

photos

5

videos