AAU-Official @aau_official Channel on Telegram

AAU-Official

@aau_official


Addis Ababa University

AAU-Official (English)

Welcome to AAU-Official, the official Telegram channel of Addis Ababa University! If you are a student, alumni, or simply interested in staying up-to-date with the latest news and events from one of Ethiopia's top universities, then this is the channel for you. AAU-Official provides a platform for the university to share important announcements, academic updates, and exciting happenings on campus. Whether you are looking for information on admissions, research opportunities, or upcoming seminars and workshops, you will find it all here. This channel is also a great way to connect with fellow members of the AAU community, sharing experiences and networking with like-minded individuals. Stay informed and engaged with Addis Ababa University by joining AAU-Official today!

AAU-Official

10 Jan, 08:06


Addis Ababa University mourns the loss of Dr. Befekadu Degife, a respected senior faculty member of the Department of Economics. His dedication to AAU spanned over half a century. With deepest sympathies, we extend our condolences to his family, students, and colleagues. Rest in peace.

AAU-Official

07 Jan, 15:57


የማዕድ ማጋራት ስነ-ስርዓት ዛሬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!

እናመስግናለን!

AAU-Official

06 Jan, 12:29


ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ የቀድሞ ምሩቃን አንዲሁም አጋሮች እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ለእናንተ እንዲሁም ለወዳጆቻችሁ በዓሉ የአንድነት፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ፡፡

ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዚደንት

AAU-Official

04 Jan, 15:15


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ህክምና ማዕከል በከፊል አገልግሎት አስጀመረ።
***

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የህክምና ልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ በከፊል ስራ የጀመረው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ማዕከል የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻሽልም ገልጸዋል።

ከዚህ ባሻገር ማዕከሉ ኢትዮጵያን የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትርጉም ያለው ድርሻ እንደሚኖረውም አመልክተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአአዩ ፕሬዚደንት ሳሙኤል ክፍሌን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው በከፊል ማዕከሉ ተመርቆ ስራ የጀመረው።

ማዕከሉን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማስገባት ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያስፈልግ ሲሆን የባለድርሻ አካላት ርብርብም ወሳኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዓመት ከ14ሺህ እስከ 15ሺህ ለሚደርሱ ዜጐች የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ቆይቷል።

ታኅሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

02 Jan, 16:24


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ የመጀመርያውን ዓለማቀፍ የምልክት ቋንቋዎች ምርምር ጉባዔን በመጪው ጥር ወር ያስተናግዳል
***

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደውን 15ኛው ዓለማቀፍ የምልክት ቋንቋዎች ምርምር ጉባዔን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ ሲሆን ኢትዮጵያም ጉባዔውን በማስተናገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ ትሆናለች። በዓለማቀፍ ደረጃ ከ600 በላይ የሚሆኑ ጥናት አቅራቢዎችና ተሳታፊዎች የሚታደሙ ይሆናል።

በምልክት ቋንቋ ዘርፍ ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት የሚሆን የምርምር ውጤት ከጉባዔው የሚጠበቅ ሲሆን በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መስማት የተሳናቸው ዜጐች ተሳትፎን ለማሳደግ በመንግስት የሚሰራው ስራ እንዲጐለብት የሚረዳ ነው። በዚህ ረገድ ፍትሐዊነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ጉባዔውን ማስተናገዱ ኢትዮጵያ የዓለማቀፍ ጉባዔዎች መዳረሻ ለመሆን የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጉባዔውን እንዲያስተናግድ የተመረጠው ላለፉት 15 ዓመታት በዘርፉ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተገምግሞ ነው።

ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

31 Dec, 15:30


አንድ ብር እና ህብረት የገነባው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
***

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተገነባው ከአንድ ብር ጀምሮ በተደረገ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መዋጮ ሲሆን፤ ወዳጅ የውጭ ሀገር ሰዎችም አርዳታ አድርገው እንደነበር ታሪክ ያወሳል፡፡ በአጠቃላይ በመዋጮ የተሰበሰበው የገንዘብ መጠንም 4,891,167.14 ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡

በ1954 ዓ.ም የህዝብን ፈቃደኝነት እና ትብብር አግኝቶ ግንባታው የተጀመረው የያኔው የልዑል መኰንን ኃይለስላሴ መታሰቢያ ሆስፒታል የዛሬው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግል ኖሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 20 ሚሊዮን በሚገመትበት በዚያ ዘመን በተባበረ ከንድ የተሰራው ይህ ሆስፒታል ዛሬ 120 ሚለዮን ለሚገመት ህዝብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ዛሬም በህብረት ሀገራችንን መገንባት እንደምንችል ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቋሚ ምስክር ነው።

ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

26 Dec, 10:32


ለግማሽ ሚሊዮን ዜጎች ፈውስና እንክብካቤ በግማሽ ዓመት
***
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆስፒታል የሆነው ጥቁር አንባሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባለፉት ስድስት ወራት አምስት መቶ ሺህ ለሚጠጉ ህሙማን የህክምና አገልግሎት ሰጠ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስብስብ የቀዶ ህክምና፣ ተመላለሽ ህክምና፣ የተኝቶ ህክምናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽ አድርጓል።

በተጨማሪም ሆስፒታሉ በክረምት የጤና በጎ አገልግሎት ለሶስተኛ ጊዜ "እሺ ለበጎ ተግባር" በሚል መሪ ቃል አገልግሎት ሰጥቷል።

ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

22 Dec, 12:17


Curious minds and bright smiles, Addis Ababa University students shine as they embrace their academic journeys.

#addisababauniversity #ethiopia #ethiopianstudents #education #like #life #university@aau_official

AAU-Official

16 Dec, 16:06


Throwback to a breathtaking moment at the state-of-the-art Ashenafi Kebede Preforming Arts Center.

Andrea Griminelli played morricone, attribute from an exceptional musician Ennio Morricone, one of the most iconic film composers of all time with the participation of Amedeo Salvato🎹

#throwbackfriday@aau_official

AAU-Official

15 Dec, 09:11


https://www.facebook.com/share/v/19X6fesMjz/

AAU-Official

12 Dec, 08:42


6ኛው ልዩ ሴሚናር አሁን በራስ መኮንን አዳራሽ

“አዙሪት፣ ኢትዮጲያ እና ጦርነት ፍቺ የሚያፈስፈልገው ጋብቻ”
#አዲስአበባዩኒቨርሲቲልዩሴሚናር

AAU-Official

10 Dec, 16:19


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 319 የቅድመ-ምረቃና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ሆኑ።

በቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ስኮላርሺፕ ሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት አዲሱ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቹን ሃይ በስራ ዘመናቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ጋር በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን 2ሺህ አንድ መቶ መጽሐፍትና 30 ታብሌት ኮምፒዩተሮችንም አበርክተዋል።

በሌላ በኩል የቻይና መንግስት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ ድጋፉ በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ጠንካራ የትምህርት ዲፕሎማሲ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የብሪክሰ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ህብረት መስራች አባል መሆኑ ይታወሳል።

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

08 Dec, 15:12


በሃገራችን አንድ አጀንዳ ላይ እንመካከር፣ እንምከር

ልዩ ሴሚናር፡ "አዙሪት፣ ኢትዮጵያና ጦርነት፣ ፍቺ የሚያስፈልገው ጋብቻ" በሚል ርዕስ የውይይትና ክርክር መድርክ ተዘጋጅቷል።

በሌ/ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል በተፃፈ መጽሐፍ መነሻነት በዘርፉ ምሁራን በሚቀርብ ሃሳብ ላይ ውይይት የምናደርግ ሲሆን ሁላችሁም በመድረኩ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

👉 ቀን፡ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም.
👉 ሰዓት፡ ጠዋት 3፡00- 6፡00 ሰዓት
👉 ቦታ፡ ራስ መኰንን አዳራሽ

#አዲስአበባዩኒቨርሲቲልዩሴሚናር

AAU-Official

07 Dec, 14:08


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል አርቲስቲክ ዳይሬክተር አበባው አስራት ዕልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ እንወዳለን።

አርቲስት አበባው አስራት በተወዳጅ የዩኒቨርሲቲያችን መዝሙሮች ማለትም እንኳን ደስ አላችሁ፣ ዩኒቨርሲቲ፣ ባዶ ቤት በክረምት፣ ጆኒ ምን እዳ ነው እንዲሁም እማ በጡቶችሽን በመጫወት የሚታወቅ ሲሆን የግጥም መጽሐፍት ደራሲና የባህል ሙዚቃ አልበሞችም ባለቤት ነበር።

ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።

ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

06 Dec, 14:42


ወጣት ቴዎድሮስ ምንዳዬ ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ 27 ደረጃቸውን የጠበቁ ዊልቸሮችን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ።

ሕዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

04 Dec, 06:52


የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- አአዩ/ብግጨ/የሱቅ ኪራይ/06/2016/24
1. የተጫራጭ ስም----------------
2. የተጫራች አድራሻ….አዲስ አበባ ..ክ/ከተማ……. ወረዳ….የቤት ቁጥር……………. ስልክ ቁጥር…………
3. የንግድ ፈቃድ ቁጥር…………
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቁጥር………….
5. ቲን ሰርተፍኬት ቁጥር………………….
6. የስራው አይነት…………………………………
7. የሚጫረቱበት ክፍል ቁጥር……………
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ቫትን ጨምሮ…………


ማሳሰቢያ፡-
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቡነ-ጴጥሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የጋዜጠኝነትና ብዙሀን መገናኛ ህንጻ ለማከራዬት ይፈልጋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ታህሳስ 04 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ ጨረታውን ለያዘው ሰው ማሰረከብ ወይም ለዚህ ጨረታ በዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 04 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡30 ሰአት ይከፈታል::

3. ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ሰርተፍኬት እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት፡፡

4. በአንድ ንግድ ፈቃድ መጫረት የሚቻለው ለአንድ ክፍል ብቻ ነው፡፡

5. በጨረታው ቅድሚያ ክፍያ ለስድስት (6) ወር እና ከዚያ በላይ ቅድሚያ ክፍያ ለሚሰጡ ድርጅቶች ቅድሚያ ይሰጠቸዋል፡፡

6. በጨረታው ለትልልቅ ካሬ ቦታዎች ማህበር ላላቸው ተጫራቾች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

7. የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው፡፡

8. በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን ይህንን ለማድረግ የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

9. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገላፀው አድራሻ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

11. ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትታቸው ዋና የሚከራዩ ቦታዎች ዝርዝር እና የሚከራይ ቦታውን የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል፡፡

12. ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በአገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎት አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡

13. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ዋናው ግቢ የአስተዳደር ህንፃ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 312



ስልክ ቁጥር 251+111249030 ከሠላምታ ጋር
Tel 0111220001/0111243272 P.O.B. 1176

AAU-Official

02 Dec, 15:53


በድጋሚ የወጣ የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-AAU/NCB/pd/02/2017/24

👉 ሎት 1 ያገለገሉ የተሸከርካሪዎች ጎማና ባትሪ ድንጋይ ሽያጭ ጨረታ


👉 ሎት 2 ያገለገሉ የፈርኒቸር እቃዎች ሽያጭ ጨረታ


1. አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከላይ በሎት የተጠቀሱትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

2. እቃዎቹ የሚገኙበት አድራሻ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንብረት አስተዳደር ክፍል ሲሆን ለመግዛት ፍላጎትና ብቃት ያላቸዉ ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡

3. ጨረታዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈፀማል::

4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ሀ/ በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በዩኒቨርስቲዉ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግና ደረሰኙን ይዘዉ በመቅረብ ስለእቃዎቹ ሙሉ ዝርዝር የያዘዉን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ እስከ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እሰከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተዉ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡ ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰዉ አድራሻ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቄጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ወይም በፊት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በፊት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ተጋባዥ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለሎት 1 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዩኒቨርስቲዉ ስም አሰርተዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ በተጨማሪም ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ማንኛዉም ተጫራች ከዉድድሩ ከወጣ የተያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡

7. ሀ/ ሰነዶቹ የሚሸጡበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 313
ለ/ የጨረታዉ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
ሐ/ ጨረታዉ የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200

8. የጨረታ አሸናፊዉ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዉል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለየኒቨረስቲዉ ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውሥጥ ያሸነፈበትን እቃ ማንሳት አለበት፡፡

9. ዩኒቨርሲቲዉ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ
ስልክ ቁጥር 011-122-00 01/011-124-32-72 ፖ.ሣ.ቁ 1176

AAU-Official

29 Nov, 05:46


በአንጋፋዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017  ዓ.ም ለሁለተኛ ሰሚስተር ለድኅረ- ምረቃ ትምህርት አመልካቾች

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም. ለድኅረ - ምረቃ ትምህርት በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለዚህም በዩኒቨርስቲዉ ድረ-ገጽ (www.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡

👉 የአ.አ.ዩ የድኅረ- ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻ ቀናት ከህዳር 23 እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም፤
👉 የድኅረ- ምረቃ መግቢያ ፈተና መፈተኛ ቀናት ታህሣሥ 17 እና ታህሣሥ 18 2017 ዓ.ም
👉 የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች ዉጤታቸዉን እና ምዝገባቸዉን  https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus ማየት እና መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 2 2017 ዓ.ም ለትምህርት ማመልከት ይችላሉ::
👉 በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስገቢያ ቦታ አ.አ.ዩ. ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

አ.አ.ዩ ሬጅስትራር

AAU-Official

27 Nov, 14:14


የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አማካሪ ፕሮፌሰር ኢሪና አብራሞቫ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
***

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አማካሪ ከሆኑት ፕሮፌሰር ኢሪና አብራሞቫ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ላይ የትብብር ማዕቀፍ ሆነው የተቀመጡ ምክረ ሃሳቦች በምን መልኩ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ረገድ የሚጫወተውን ሚና የዳሰሰ ነው።

ዩኒቨርሲቲው የትብብር ማዕቀፉን መሠረት በማድረግ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

በህክምና ሳይንስ፣ በህዋ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ግብርና ልማትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራትም ከስምምነት ደርሷል።

ዩኒቨርሲቲው በእነዚህ ዘርፎች ሀገርን የሚጠቅሙ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ፕሮጀክቶችን ለመስራት እንደሚያግዝ ይታመናል።

የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ በዓለማቀፍ ደረጃ ስመጥር ከሆኑ ግዙፍ የሳይንስ አካዳሚዎች ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚቀመጥ ነው።

ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

27 Nov, 09:13


Vacancy Announcement

AAU-Official

22 Nov, 10:34


Guess what’s up?

AAU’s telegram channel is now officially verified!We know that there are a lot of other channels out there that try to mimic us and some of them even post ads for used cellphones or laptops. But we would like everyone to know that they do not represent our institution. Follow us for more updates!

AAU-Official

21 Nov, 10:00


Did you know that Addis Ababa University has an official instagram page? We started posting on it a little while ago and we’d like to use it to as a platform to boost our community engagement. Go ahead and follow us to stay updated and see all the cool things going around on campus.

https://www.instagram.com/aau_official_?igsh=cHR4OWJocTY2ejN6&utm_source=qr

AAU-Official

16 Nov, 15:30


Join us for a Seminar on BRICS+ in Physical Activity, Health Tourism, and Leisure: Exploring Integration Opportunities between Brazil and Ethiopia

Venue: Ras Mekonnen Hall
Speaker: Professor Ricardo Uvinha
Date: 18 November 2024

AAU-Official

15 Nov, 09:00


📢 Calling all fresh & senior journalism students! 📢

Join us for our J-School_Fresh_welcoming event and kickstart your journey!

🔥 Network with fellow students
🔥 Hear from experienced journalists on a panel
🔥 Learn about PR careers from industry professionals

🗓️ Nov 15, 2024
8:00 LT
📍 IES,MOHAMMED ALAMOUDI BLDG

Don't miss out! #journalism #freshwelcome #networking #PR #students

AAU-Official

13 Nov, 13:20


https://www.facebook.com/share/v/1Ao3YdtWTV/

AAU-Official

08 Nov, 15:33


https://www.facebook.com/share/v/14JVt4tNF1/

AAU-Official

07 Nov, 15:08


https://www.facebook.com/share/v/15bfkENn3f/

AAU-Official

05 Nov, 14:53


https://www.facebook.com/share/v/7rvdbsuoPmHQe9oA/

AAU-Official

30 Oct, 19:11


https://www.facebook.com/share/v/QVXFb9TvsBy7amo7/

AAU-Official

29 Oct, 06:00


የሱቅ ኪራይ ውጤት ስለማሳወቅ
በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፎረም ህንጻ የሱቅ ቦታ ለመከራየት የተሳትፋችሁ ድርጅቶች በሙሉ ከዚህ በታች በተቀመጠው የውጤት ማሳያ መሰረት በአንድ ካሬ በሰጣችሁት የኪራይ ዋጋ መሰረት በተወዳደራችሁበት የሱቅ አይነት ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት ያሸነፋችሁ ድርጅቶች በዩኒቨርሲቲው የግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 312 ቀርባችሁ ውል እንድትፈርሙ እያሳወቅን ሌሎች የተሳተፋችሁ እና ያላሸነፋችሁ ድርጅቶች ስለተሳተፋችሁ እያመሰገን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በሚያቀርበው የሱቅ ኪራይ መሳተፍ እንድትችሉ ከወዲሁ እያሳሰብን፡፡
1. ለEB- 3 ለመከራየት የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ሙሉጌታ መኮንን አትክልት ጁስ………………………………….2,100.00
 እናትትሁን ሲሳይ አማረ…………….…………………………..2,200.00አሸናፊ ሆኗል
 ዴልት ሙዲካል ላብራቶሪ………………………………………2,050.00
 በላይ ሽኩር በላይ……………………………………………….1,350.00
2. ለEB- 4 ለመከራየት የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ዴልት ሜዲካል ላብራቶሪ…………………………………………2,050.00
 ወሊፍ ሄልዝ ኬር አ.ማ…………………………………………..1,500.00
 የራብ አደራው ……….…………………………………………..2,400.00አሸናፊ ሆኗል
 ጆይን በርገር……………………………………………………….2,100.00
 የምስራች አዳሙ………………………………………………….1,200.00
በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ቤዝመንት ላይ ያሉ የተለያዩ ሱቆች የተወዳደሩ ድርጅቶች
1. ለSH- 1 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ዞላ ሴፍ…………………………………………….1,500.00አሸናፊ ሆኗል
 ቤዛውይ የህትመትና ተያያዥ ስራዎች………………1,111.70
2. ለSH- 4 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 እንዳለ ካፌና ሪስቶራንት………………………………….1100.00
 ሂሩት ኑርበዛ…….………………………………………..1,260.00አሸናፊ ሆኗል
 ይከበር ሁነኛው……………………………………………1,251.25
3. ለSH- 8 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ቤዛዊት አረጋይ ………………………………………….1412.50
 ቦንያስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ…………………………….1,500.00አሸናፊ ሆኗል
 ገነት የስቴሽነሪ እቃዎች ማከፋፈያ…………………………1,150.00
 ወርቅዬ ተሾመ ሳህሌ……………………………………….1000.00
 አብርሃም ንጉሴ ፈለቀ………………………………………1250.00
 ረዴትና ረይስ………………………………………………1225.00
 ኤሊያስ ዳሩ የሱፍ………………………………………….1300.00
 ደሊላ የንግድ ስራ……………………………………………1412.60
 ኤም ኤስ አፍ ጠቅላላ ንግድ…………………………………1323.60
4. ለSH- 9 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ጁነይድ ሙስጠፋ ………………………………………….1100.00
 ቅድስት የሽጥላ ብሩ………………………………………..1,560.00አሸናፊ ሆኗል
 ሽቶ ፎቶና ስቴሽነሪ…………………………………………1,200.00
 ብሩክ ዜና ወ/ገብርኤል……………………………………….1351.00
 ሚስጠፋ ካሚል ሙደሲር……………………………………..1,350.00
 ፍፁም ጸጉ የጽህፈት መሳሪያ………………………………….1550.00
5. ለSH- 12 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ጦቢያ ጫማ….. ………………………………………….1700.00
 ኤልሳቤጥ ቱሉ ረታ………………………………………..1,750.00አሸናፊ ሆኗል
 ሳሚ የውበት ሳሎን…………………………………………1,200.00
 ታገል ዘለቀ ጋሸ…………………………………………….1,201.05
6. ለSH- 13 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 መልከአ ስቲዲዮ………………………………………..1600.00አሸናፊ ሆኗል
7. ለSH- 15 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ነጋ ዋሴ…. ……………………………………………..1350.00
 ወርቅነህ መኮንን…………………………………………..1,750.00አሸናፊ ሆኗል
 ሊፕ ሶፍትዊር ……………………………………………1,200.00
 ፅጌ ዳግም የሴቶች የውበት ሳሎን…………………………1151.00
 ዳምጤ ግዛቸው…………………………………………….1,270.90
 ሚኒ ማርኬት………………………………………………1150.00
 እሙ ዲዛይን………………………………………………..1500.00
 ቤዛ እቴሽነሪ…………………………………………………1150.00
 ማህበር ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል………………………..1266.50
 ሄለን በለጠ…………………………………………………..1200.00
 ብሌን ስዩም………………………………………………….1500.00
 ምንተስኖት ብርሃኑ…………………………………………1551.00
8. ለSH- 16 የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ሜሎስ የፅህፈት መሳሪያ………………………………………….1275.00
 ቢኒያም መለሰ…………………………………………………..1550.00 አሸናፊ ሆኗል
 ሰለሞን ዘውዱ ልዑል………………..…………………………….1,211.50
9. ለSH- 2 With coffee shop area የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 መንግስቱ ተክሉ…….…………………………………………..1,019.00
 እየሩሳሌም ፀጋው………………………………………………..1,202.00
 ራሔል ዮሴፍ ሬስቶራንት………………………………………..1,440.67
 ሽመልስ አበበ ንጋቱ……………………………………………1,512.00 አሸናፊ ሆኗል
 ሙሉነህ ግዛው……………………………………………………1,050.84
 አለባቸው ሀይሉ አሰፋ…………………………………………….1,020.00
 ትክክል አሰፋ………………………………………………………1,030.00
 እየሩ ገ/እግዚአብሔር ተምትሜ…………………………………….1,050.00

AAU-Official

25 Oct, 13:56


https://www.facebook.com/share/v/RmHzm2BWQzPZ1rH1/

AAU-Official

25 Oct, 13:07


Did you know that Addis Ababa University has an official instagram page? We started posting on it a little while ago and we’d like to use it to as a platform to boost our community engagement. Go ahead and follow us to stay updated and see all the cool things going around on campus.

https://www.instagram.com/aau_official_?igsh=cHR4OWJocTY2ejN6&utm_source=qr

AAU-Official

22 Oct, 16:10


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፖርቱጋል ውጪ ጉዳይና ትብብር ጋር በትምህርት ዲፕሎማሲ ረገድ አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የፈረሙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ ( ፒ.ኤች.ዲ) እና በፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና ትብብር ዋና ፀሀፊ ክቡር ኑኖ ሳሞፒዮ ናቸው።

ስምምነቱ በትምህርት ዲፕሎማሲው ዘርፈ ብዙ የትብብር መስኮችን ጨምሮ በዓለማችን በአራተኛ ደረጃ ብዙ ተናጋሪ ያለውን የፖርቹጋል ቋንቋን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለማስተማር የሚያስችል ነው፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ፈረንሳይኛን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ ቋንቋዎችን በአጫጭር ኮርስ እንዲሁም በዲግሪ መርሃ ግብሮች በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

21 Oct, 08:00


የሱቅ ጨረታ ውጤት ስለማሳወቅ
አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ በጨረታ ቁጥር አአዩ/ብግጨ/የሱቅ ኪራይ/06/2016/24 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት(ኮሜርስ) አውጥቶት በነበረው የሱቅ ኪራይ ጨረታ ተሳትፋችሁ የነበራችሁ ድርጅቶች በሙሉ ከዚህ በታች በተቀመጠው የውጤት ማሳያ መሰረት በአንድ ካሬ በሰጣችሁት የኪራይ ዋጋ መሰረት በተወዳደራችሁበት የሱቅ አይነት ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት ያሸነፋችሁ ድርጅቶች በዩኒቨርሲቲው የግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 312 ቀርባችሁ ውል እንድትፈርሙ እያሳወቅን ሌሎች በጨረታው የተሳተፋችሁ እና ያላሸነፋችሁ ድርጅቶች ስለተሳተፋችሁ እያመሰገን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በሚያወጣቸው የሱቅ ኪራይ ጨረታ መሳተፍ እንድትችሉ ከወዲሁ እያሳሰብን ከታች የተዘረዘሩት ቦታዎች በንግድ ስራ ት/ቤት ፋሲሊቲ ህንጻ ላይ ያሉ ቦታዎችን ውጤት ብቻ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት(ኮሜርስ) ያሉ የተለያዩ ሱቆች የተወዳደሩ ድርጅቶች
1. ለ studenet launge with separate toilet(SL/ 400.34 ካሬ) የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 መኮንን ጫኔ ጌታሁን……………152.51
 ራሔል ዮሴፍ ሪስቶራንት………….500.00
 ቢቦኒቮ ትሬዲንግ………………875.00
 ሬዲዋንኑረዲን ኤመር………………..585.10
 እንዳላማው እንዳዬሁ………………500.00
 ተባረክ አህመድ ወል…………..1,556.99 አሸናፊ
2. ለ shops with separate store and toilet (SST-5 /73.54 ካሬ ) የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ፎገራ ፋርማሲውቲካል ትሬዲንግ…………………………600.00 ብር
 መኩሪያ ተሾመ የምግብ ምርቶች ንግድ…..1,700.00
 አማን መካ ሙሳ…………………….3,000.00 አሸናፊ
 አንዳርጋቸው እና ቤተሰቡ የትራነዚት አገልግሎት…………………………951.00
 ፈቃዱ ብርጉ ውርጅኝ…………………………..1,101.00
 ቡና ባንክ አ.ማ……………………….1,000.00
 ታጠቅ ኃይለማርያም………………………..1281.05
 አብራር ከሊል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ…………….1223.82
3. ለ shops with separate store and toilet (SST-3/ 60.77 ካሬ ) የተሳተፉ ድርጅቶች ስም ዝርዘር እና ቫትን ጨምሮ በአንድ ካሬ ያስገቡት ዋጋ
 ፅጌ ወይን መውጫ መስፍን……………………… 1,665.00 አሸናፊ
 ዋሲሁን መከተ ደስታ …….. 1,314.00
 በርባኖስ ትሬዲንግ…………………….1,151.84

AAU-Official

15 Oct, 16:21


Freshers' Week is officially underway! We're rolling out the red carpet for our fresh students.
Welcome to AAU!

#AAU #FreshersWeek

AAU-Official

14 Oct, 16:44


ውድ የአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ወደ ቤታችሁ ስለመጣችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቤታችሁ መሆኑን ዳግም ጥሪውን ተቀብላችሁ በመምጣት አረጋገጣችሁ።

ከአመታት በኋላ የናፈቃችሁትን ወዳጅ አገኛችሁ። መምህራኑንም አገኛችሁ፣ የመማሪያ ክፍሎችና ቤተ-መጻሕፍቱን እንዲሁም ዶርሚተሪና ካፌዎችን በትዝታ መንፈስ ጎበኛችሁ። በዚህም አጋጣሚ ያለፈውን ትዝታ ብቻ ሳይሆን አብሮነታችሁን የምታጠናክሩበትን ድልድይ እንዳፀናችሁ እናምናለን።

ሁሌም በመንፈስና በአካል ከተቋማችሁ ጋር እንደምትሆኑ ተስፋ እናደርጋለን። ለዚህም alumni.aau.edu.et ላይ በመግባት ጓደኞቻችሁን እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን ዳግም እናስተላልፋለን።

እናመስግናለን!
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

AAU-Official

13 Oct, 16:11


ትዝታ አያረጅም🥰

#ዛሬ
#ትዝታችን
#ወደቤትዎይምጡ
#aaualumnihomecoming

Please register to join AAU alumni family @ https://alumni.aau.edu.et

AAU-Official

12 Oct, 16:04


https://www.facebook.com/share/v/z8tsfk2wPJkVGd2A/?mibextid=qi2Omg

AAU-Official

12 Oct, 15:48


ኦ ትዝታ 🤔

እንኳን ወደ ቤታችሁ በደህና መጣች🥰
ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#ወደቤትዎይምጡ
#aaualumnihomecoming
Please register to join AAU alumni family @ https://alumni.aau.edu.et

AAU-Official

12 Oct, 15:16


ዛሬ...ትዝታን በታሪካዊው ልደት አዳራሽ🥹🥰

እንኳን ወደ ቤታችሁ በደህና መጣችሁ🥰

#ትዝታችን
#ወደቤትዎይምጡ
#aaualumnihomecoming
Please register to join AAU alumni family @ https://alumni.aau.edu.et

AAU-Official

12 Oct, 13:51


ቤተሰብ❤️

እንኳን ወደ ቤታችሁ በደህና መጣችሁ🥰

ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#ወደቤትዎይምጡ
#aaualumnihomecoming

Please register to join AAU alumni family @ https://alumni.aau.edu.et

AAU-Official

12 Oct, 07:48


Happening now...
AAU premium alumni at Mekonnen hall 🥰

#ወደቤትዎይምጡ
#aaualumnihomecoming

AAU-Official

11 Oct, 17:07


https://www.facebook.com/share/v/4VfQNGSb8N16aZBu/?mibextid=qi2Omg

AAU-Official

10 Oct, 16:39


Please register to join AAU alumni family @ https://alumni.aau.edu.et

Welcome Home🥰
#Be_the_first