መረጃ 24 ሰአት @qonjowochu Channel on Telegram

መረጃ 24 ሰአት

@qonjowochu


ቶሎ ቶሎ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶት ላይክ እና ሼር አርጉ ፈጠን ፈጠን ብለን መረጃን አንለቃለን ላይክ ያርጉ ፈጠን በሉ

መረጃ 24 ሰአት (Amharic)

መረጃ 24 ሰአት የብስክሌት የድምፅ ትምህርት ከምንነት ጋር ሼር አርጉ ፈጠን እና ያላው ባለቅብ መረጃ ማጉርጉር እንዲሆን ከሚሰማበት መረጃ የተከበረ ጊዜ ነው። ይህ መረጃ የተለያዩ ሼር ያሉትን መረጃዎችን አስተማሪ የሆነውን ያደረገ መረጃ ነው። qonjowochu ድምጾም መረጃን እና ለሚሆን ጊዜዎች ገና የብስክሌትን እና የድምጽነትን ማድረግ እንዲመኖር ያለንን መረጃ ባወቅን መሰረት ነው።

መረጃ 24 ሰአት

09 Feb, 18:49


የቡና ባንክ ጥበቃ ሰራተኞች ጋፋት ላይ ክስ አቀረቡ

በቡና ባንክ ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች፣ በአሰሪ ድርጅታቸው "ጋፋት" ላይ ከባድ ክስ አቀረቡ። ሰራተኞቹ፣ ድርጅቱ ለዓመታት ሲያቀርብላቸው የነበረውን የአገልግሎት ውል በመጣስ፣ ያለአመት እረፍት፣ የጡረታ እና ሌሎች መሰረታዊ ጥቅማጥቅሞች ሳይሰጥ እንደተዋቸው ይናገራሉ።

"ለዓመታት ስንሰራ ቆይተናል፣ አሁን ግን ምንም አይነት መብታችን ሳይጠበቅልን ተጥለናል" ሲሉ ሰራተኞቹ #ለዜና_ኢትዮጵያ  በምሬት ተናግረዋል። "ይህ ድርጊት ፍጹም ኢፍትሐዊነት ነው። የብዙ ዓመታት ልፋታችን ዋጋ የሌለው ሆኗል።" ሲሉ ተናግረዋል

ሰራተኞቹ አክለውም፣ ጋፋት ድርጅት ምንም አይነት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እንደዘጋውና አሁን ባሉበት ሁኔታ ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጡ ገልጸዋል። "ቤተሰቦቻችንን እንዴት እንደምንመግብ አናውቅም። የወደፊት ህይወታችን አደጋ ላይ ነው" ሲሉ በምሬት  ተናግረዋል።

የቡና ባንክ ጥበቃ ሰራተኞች ጉዳዩን ወደሚመለከተው አካል ለማቅረብ እየተዘጋጁ ሲሆን፣ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ለዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጡና ፍትህ እንዲሰፍን ጠይቀዋል።

''ይህ ክስተት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የግል ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች መብት ምን ያህል እየተጣሰ እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው። መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ሰራተኞች መብታቸውን እንዲጠብቁና ፍትህ እንዲሰፍን ማድረግ አለባቸው ''ሲሉ አክለው ተናግረዋል

via:ዜና ETHIOPA

መረጃ 24 ሰአት

09 Feb, 16:56


7 ሺህ 831 ሊትር ሕገ-ወጥ ቤንዚን ተያዘ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ በጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ሲዘዋወር የነበረ 7 ሺህ 831 ሊትር ሕገ-ወጥ ቤንዚን ተይዟል።

ሕገ ወጥ ቤንዚኑ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ከአንፎ አደባባይ ወደ ጦርሀይሎች በሚወስደው መንገድ በአይሱዙ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲዘዋወር በፖሊስ መያዙ ተጠቅሷል።

የተያዘውን ቤንዚን በአቅራቢያ በሚገኝ ማደያ እንዲሸጥ በማድረግ 794 ሺህ 611 ብር ከ57 ሳንቲም በፋይናንስ ዝግ አካውንት እንዲገባ መደረጉን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተመሳሳይ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር እንዲቻል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃ 24 ሰአት

09 Feb, 07:39


ትራምፕ ካናዳን ወደ አሜሪካ መጠቅለል የሚሹት ከልባቸው ነው - ጀስቲን ትሩዶ

ተሰናባቹ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፤ ትራምፕ ካናዳን ወደ አሜሪካ ስለመጠቅለል የሰጡት አስተያየት ለፌዝ እንዳልነበረ ተናግረዋል።

ትሩዶ ይህን ያሉት የትልልቅ ኩባንያ መሪዎችን ቶሮንቶ ላይ ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

"ትራምፕ ካናዳን የአሜሪካ 51ኛዋ ግዛት ማድረግ ይፈልጋል፤ ይህን የሚፈልገው ደግሞ ከልቡ ነው" ብለዋል።

ይህም ፍላጎት የመነጨው ካናዳ ውድ የተፈጥሮ ሃብት ስለታደለች ነው ብለዋል።

"ትራምፕ ይህን ሃብት ለመቀራመት አቋራጩ መንገድ ካናዳን የአሜሪካ ግዛት ማድረግ አንደሆነ በመረዳቱ ነው" ሲሉም ትሩዶ ጨምረው ገልጸዋል።

ምንም እንኳ ጉባኤው ለሚዲያ ዝግ የነበረ ቢሆንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድምጽ ተቀድቶ ወጥቶ በአንዳንድ የካናዳ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

ትራምፕ "ለካናዳ የሚሻላት የአሜሪካ 51ኛው ግዛት መሆን ነው" የሚለውን አስተያየታቸውን በተደጋጋሚ ተናግረውታል።

መረጃ 24 ሰአት

09 Feb, 05:54


የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ 101 ሚሊዮን ብር ደረሰ

በሚያስደንቅ ፍጥነት እየተከናወነ የሚገኘው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ 101 ሚሊዮን ብር፣ በዜልና ካሻ-አኘ የገንዘብ ማስተላለፊያ 275,000 ዶላር፣ እንዲሁም በጎፈንድ ሚ ደግሞ 111, 003 ሺ  ዶላር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን በመርሃ ግብሩ በርካታ ልብ የሚነኩ ስጦታዎች እየተደረጉ ነው።
Via dagu

መረጃ 24 ሰአት

09 Feb, 05:54


ኢትዮጲያውያን አትሌቶች ድል ተቀናጅተዋል

በፈረንሳይ ሜዝ በተካሄደ የ800 ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ውድድር እትሌት ፅጌ ዱጉማ አሸንፋለች፡፡

አትሌት ፅጌ 1 :58.97 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።አትሌቷ ያስመዘገበችው የቦታው ክብረ-ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በሴቶች የ1500 ሜትር ውድድር አትሌት ሳሮን በርሀ 4:04.51 በመግባት በቀዳሚነት አሸንፋለች፡፡

በተያያዘ ዜና በወንዶች  የ3000 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ኩማ ግርማ 7:31.78 በመግባት የግሉን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ በአንደኝነት አሸንፏል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

08 Feb, 11:12


'ብርጌድ ንሐመዱ' የተሰኘዉ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አገዛዝ ተቃዋሚ ቡድን አዲስአበባ ላይ ቢሮ ሊከፍት ነዉ ተባለ

በውጭ አገራት የተመሠረተው 'ብርጌድ ንሐመዱ' የተሠኘው የኤርትራ ተቃዋሚዎች ስብስብ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ቢሮ ሊከፍት መኾኑን መስማቱን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘግቧል።

'ብርጌድ ንሐመዱ' ወይም 'የሰማያዊ አብዮት ንቅናቄ' የተሰኘው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ስብስብ፣ ከአንድ ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ማካሄዱን ዳጉ ጆርናል የጀርመን ድምፅ ራዲዮን ዘገባ ዋቢ በማድረግ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል።

በዚኹ ስብሰባ ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወከሉ የንቅናቄው አባላት እንደተሳተፉ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።

ንቅናቄው በውጭ አገር የተመሠረተው ከኹለት ዓመት በፊት ሲኾን፣ በተለያዩ የምዕራቡ ዓለም አገራት የኤርትራ ኢምባሲዎችና የመንግሥት ደጋፊዎች ያካሄዷቸውን የባሕል ፌስቲቫሎች በማወክና በማስተጓጎል ይታወቃል።

መረጃ 24 ሰአት

07 Feb, 10:45


የሸማ ተራ ቃጠሎ መንስኤ ታወቀ

በ 6 ወራት ውስጥ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ቃጠሎ  ተፈፅሟል

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል ።

1.  በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ምክንያት የደረሰ 50 ቃጠሎ፤
2.  በመካኒካል ችግር ምክንያት የደረሰ 11 ቃጠሎ፤
3.  ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ቃጠሎ፣
4.  በቸልተኝነት የደረሰ 17 እና
5.  በሌሎች ምክንያቶች የደረሰ 15  ቃጠሎ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ ሰባት በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤም በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን በፎረንሲክ ምርመራ ማጣራት ችያለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ።

በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣  በስድስት ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስድስት ወር ሪፖርት አመላክቷል።

ኅብረተሰቡ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ማስረጃዎች ሳይነካኩ መጠበቅና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት እንዲሁም የቃጠሎ መንስኤዎች በሙያዊ ምርመራ እስካልተረጋገጡ ድረስ አስተያየት መስጠትና መፈረጅ ፍትሕን  እንደሚያዛባ ተገንዝቦ ለፍትሕ መረጋገጥ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃ 24 ሰአት

07 Feb, 09:25


በጋምቤላ ክልል የመንግስት የሥራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል።

ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የሥራ ሰዓት ለውጥ በሙቀት መጨመር ሳቢያ ነው ተብሏል።

በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለሥራ ምቹ ባለመሆኑ ነገ የሚጀምረው የሥራ ሰዓት ለውጥ ለ3 ወራት ይቆያል።

በዚህ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 6 ፡30 የነበረው ከ1፡00 እስከ 5፡30 ይሆናል።

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 9፡00 እስከ 11፡30 የነበረው ከ10፡00 እስከ 12፡30 እንዲሆን የክልሉ አስተዳደር ወስኗል።

የሥራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ተጠቁሟል።

መረጃ 24 ሰአት

07 Feb, 07:59


"መርካቶ ሸማ ተራ የተቃጠለው በኤሌክትሪክ ምክንያት ነው"ፌደራል ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል ።

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ዲፓርትመንት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ዘመኑ ያፈራቸውን ዘመናዊ የላብራቶሪ መሣሪያዎችን በመጠቀም ከሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የቀረቡለትን  የእሳት አደጋ ቃጠሎ መንስኤዎችን በማጣራት የደረሰበትን የፎረንሲክ ምርመራ  ውጤት እንደሚከተለው አቅርቧል።
1.  በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ምክንያት የደረሰ 50 ቃጠሎ፤
2.  በመካኒካል ችግር ምክንያት የደረሰ 11 ቃጠሎ፤
3.  ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ቃጠሎ፣
4.  በቸልተኝነት የደረሰ 17 እና
5.  በሌሎች ምክንያቶች የደረሰ 15  ቃጠሎ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ ሰባት በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤም በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን በፎረንሲክ ምርመራ ማጣራት ችያለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ።

በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣  በስድስት ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስድስት ወር ሪፖርት አመላክቷል።

ኅብረተሰቡ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ማስረጃዎች ሳይነካኩ መጠበቅና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት እንዲሁም የቃጠሎ መንስኤዎች በሙያዊ ምርመራ እስካልተረጋገጡ ድረስ አስተያየት መስጠትና መፈረጅ ፍትሕን  እንደሚያዛባ ተገንዝቦ ለፍትሕ መረጋገጥ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል

መረጃ 24 ሰአት

07 Feb, 07:57


አሜሪካ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድቤት ላይ ማዕቀብ ጣለች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።

ትራምፕ "በአሜሪካ እና የቅርብ አጋሯ እስራኤል ላይ ቅቡለነት እና መሠረት የሌለው ተግባር እየፈጸመ ነው" ሲሉ የከሰሱት ዓለም አቀፉ የጦር የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ላይ ማዕቀብ የጣሉበት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ላይ ፈርመዋል።

ትራምፕ አይሲሲ ላይ የጣሉት ዕቀባ እና ቪዛን የሚያጠቃልል ነው።

የቪዛ ዕቀባው የአሜሪካ ወይም የአጋሯቿ ዜጎች ላይ ምርመራ የሚያደረጉትንና የሚረዱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻችን ዒላማ ያደረገ ነው።

ታራምፕ ይህንን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የፈረሙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ዋሽንግተንን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው።

ባለፈው ጥቅምት ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ኔታኒያሁ በጋዛ ፈጽመውታል ባለው የጦር ወንጀል ምክንያት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ይህንን ክስ እስራኤል አትቀበለውም፤ በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ የሐማስ የጦር አዛዥ ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል።

አሜሪካ የዚህ ዓለም አቀፍ ተቋም አባል አይደለችም፤ በተደጋጋሚም በአሜሪካ ዜጎች ላይ በፍርድ ቤቱ የሚተላለፍ ውሳኔዎችን ውድቅ አድርጋለች።

አይሲሲ እስራኤል ራሷን የመካለከል መብቷ ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ኢራን እና ጸረ እስራኤል የሆኑ በድኖችን ችላ ብሏል ሲል ዋይት ኃውስ ገልጿል።

መረጃ 24 ሰአት

07 Feb, 06:42


የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የኤምፔሳ ደንበኞች ብዛት ባለፈው ዓመት በሦስት እጥፍ መጨመሩን የኬንያው ቢዝነስ ደይሊ ጋዜጣ አስነብቧል።

ባለፈው ዓመት ታኅሳስ ወር የኩባንያው የኤምፔሳ ደንበኞች ብዛት 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን የነበረ ሲኾን፣ በዘንድሮው ታኅሳስ ግን ቁጥሩ ወደ 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል።

የኩባንያው የኤምፔሳ ደንበኞች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ የጨመረው፣ የአየር ሰዓት እና ዳታ በኤምፔሳ አማካኝነት የሚገዙ ተጠቃሚዎች ቁጥር በመጨመሩ እንዲሁም ኩባንያው በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ድንበር ዘለል የገንዘብ የኤምፔሳ አገልግሎት በመጀመሩ እንደኾነ ከኩባንያው ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ ጋዜጣው ዘግቧል።

መረጃ 24 ሰአት

07 Feb, 05:22


በUSAID እርዳታ ስራ የተቀጠሩ ብዙሃኑ በጤናው ዘርፍ ላይ ያሉ ከ40 ሺህ በላይ ኬንያውያን ስራ አጥ ሊሆኑ ነው።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ አስተዳደር ከUSAID ጋር በተገናኘ እርዳታ እንዲቆም ውሳኔ ማሳላፋቸውን ተከትሎ በተለይ በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በአሜሪካ እርዳታ የተቀጠሩ ሰራተኞች ስራ አጥ ይሆናሉ።

ከነዚህ ሀገራት መካከል ጎረቤታችን ኬንያ አንዷ ናት።

በሀገሪቱ በአሜሪካ መንግሥት እርዳታ ስራቸውን የሚሰሩ ከ40,000 በላይ ሰራተኞች  ስራ አጥ ይሆናሉ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በጤናው ዘርፍ ላይ ያሉ መሆናቸውን ከሲቲዝን ቴሌቪዥን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ ከUSAID እና CDC ጋር በተገናኘ ድጋፍ በጤና ዘርፍ ስራ እየሰሩ ያሉ ከ5,000 በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ ጤና ሚኒስቴር ትዕዛዝ መሰጠቱን ነግረናችሁ ነበር።

ይህ በጤና ሚኒስቴር ብቻ የታዘዘው ነው።

ሌሎች በUSAID እርዳታ የሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ልብ በሉ።

መረጃ 24 ሰአት

06 Feb, 12:32


ሜክሲኮ 10 ሺህ ወታደሮቿን በአሜሪካ አዋሳኝ ድንበር ላይ አሰማራች

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ዛቻን ተከትሎ ሜክሲኮ 10 ሺህ ወታደሮችን በዩናይትድ ስቴትስ አዋሳኝ ድንበር ላይ ማሰማራቷን አስታወቀች፡፡

የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሼንቦም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተክትሎ የሀገሪቱ ብሄራዊ ጦር አባላት ከአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት ጋር በሚዋሰኑት ሱዳድ ጁዋሬዝና ኢል ፓሶ በተሰኙ አካባቢዎች መስፈራቸው ተገልጿል፡፡

ዛሬ ጠዋት ላይም ጭንበል የለበሱና የታጠቁ ከ1 ሺህ 650 በላይ የሜክሲኮ ብሄራዊ ጦር አባላት በድንብር አካባቢ በመስፈር በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ መታየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሜክሲኮ ወታደሮቿን ለማስፈር የወሰነችው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሜክሲኮ ምርቶች ላይ ከበደ ያለ ታሪፍ እንደሚጥሉ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ወታደሮቹ በዋናነት በሜክሲኮ እና አሜሪካ ድንበር የሚደረጉ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚቆጣጠሩ ሲሆን÷ በተጓዳኝ ከአሜሪካ መንግስት የሚሰነዘርባቸውን ማንኛውም ጫና ለመመከት እንደሚሰሩ መጠቀሱን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል

መረጃ 24 ሰአት

06 Feb, 12:29


የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እርዳታ ማቋረጡ ኢትዮጵያ በኤች አይ ቪ ላይ የምታደርገውን ትግል አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ

ከሩብ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የቫይረሱ ተጠቃሚዎችን ለአደጋ ያጋልጣል ሲል አስጠንቅቋል

ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ድጋፍና እርዳታ መቋረጥ በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ270 ሺ በላይ ለሚሆኑ የቫይረሱ መከላከያ መድሃኒት ተጠቃሚዎችን ህይወት ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም አስጠንቀቀ።

በርካቶች ኤች አይቪን ጨምሮ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚውል ኮንዶም ከአሁን በኋላ አይደርሳቸውም ብሏል።

በተጨማሪም የገንዘብ ድጋፍ መቋረጡ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ አቅም ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንዳያደናቅፈው ስጋት እንዳለው አስታውቋል፤ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡት ስልጠና ላይ ተፅዕኖ በማሳደር በኢትዮጵያ የኤችአይቪ በሽታ መከላከል ሂደት ላይ እየተመዘገበ ያለውን እድገት ያዘገየዋል ሲል አመልክቷል።

መረጃ 24 ሰአት

06 Feb, 09:26


መረጃ ‼️

አሜሪካ፣ ግብጽ የጋዛ ነዋሪዎችን ተቀብላ እንድታሠፍር ለማግባባት የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመችበት መኾኑን ከዲፕሎማቲክ ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ኒው ዓረብ ድረገጽ ዘግቧል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ልዑካን ሰሞኑን ወደ ካይሮ ባቀኑበት ወቅት፣ ከግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደር አብደላቲና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋር በዚኹ ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተው እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። የሕዳሴው ግድብ ውዝግብን ለመፍታት አሜሪካ ገንቢ ሚና እንድትጫወት ከተፈለገ፣ ግብጽ የጋዛ ነዋሪዎችን ተቀብላ ማስፈር እንዳለባት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለግብጽ አቻዎቻቸው ነግረዋቸዋል ተብሏል። ግብጽ ግን ከፊል የጋዛ ነዋሪዎችን እንድታሠፍር ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን ሃሳብ ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው ዙር የሥልጣን ዘመናቸው፣ የግድቡን ውዝግብ ለመፍታት ያቀረቡትን አስገዳጅ የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ኢትዮጵያ ውድቅ ማድረጓ አይዘነጋም።

መረጃ 24 ሰአት

06 Feb, 05:14


መቄዶንያ 5 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ገለፀ

መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በአዲስ አበባ እና በክልል የጀመረዉን ስራዉን ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር እንደሚስፈልገው አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ዋናዉ ማዕከል የሚገነባዉን ባለ 15 ወለል የአረጋውያን መኖሪያና ዘመናዊ ሆስፒታል ለመጨረስና ተረጂዎችን ከጎዳና አንስቶ ህንፃውን ወደ ስራ በማስገባት ለማጠናቀቅ 4.3 ቢሊየን ብር ያስፈልገኛል ብሏል፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማሳካትም የፊታችን የካቲት 1 ጀምሮ ሀገራዊ የገቢ ማሰባሰቢያ በseifu on ebs tube ላይ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታዉቋል፡፡

ከየካቲት 01 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሰይፉ በኢቢኤስ ዩቱዩብ ቻናል በሚደረገዉ የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብያ መርሀግብር ላይ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚሰበሰው ገንዘብም በአዲስ አበባ ዋናው ማዕከል እና ከ15 በላይ ቅርንጫፎች ላይ የተጀመሩ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ የሚሆን ነው ተብሏል።

መቄዶንያ በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ሻሸመኔ፣ ዓድዋ፣ ባህርዳር እና ሌሎችንም ጨምሮ በአጠቃላይ በ44 ከተሞች ቅርንጫፍ በመክፈት ስራውን በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡

በቀጣይም በወሊሶ፣ ሱልልታ፣ ሰበታ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሆሳዕና፣ ዲላ፣ ጂግጂጋ፣ እና በሌሎች ከተሞች ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታዉቋል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

27 Jan, 12:57


የዶርሚተሪ አይነት ቤቶችን በብዛት ለመገንባት እቅድ ተይዟል.... መንግስት


ከኮንዶሚኒየም ያነሱ ቤቶችን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህረሰብ ክፍሎች  ለማቅረብ እየተሰራ ነው ተባለ

የቤቶች ልማት ኮርፖሮሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ፤  የቤት ችግርን ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁ ሲሆን በተለይም በከተሞች ያለውን የቤት እጥረት ለመቅረፍ ከኮንዶሚኒየም ያነሱ ቤቶች ለመስራት መታቀዱን አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በተነሳው  ኮንዶሚኒየም ዝቅተኛው የቤት ደረጃ  መሆን የለበትም የሚለውን ሀሳብ በመያዝ ከኮንዶሚኒየም ያነሱ እንደ ዶርምተሪ አይነት ቤቶችን በብዛት ለመገንባት ጥናቶች መኳሄዳቸውን አንስተዋል።

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ6 ወር ውስጥ 20 ሺ 7 መቶ 54  ቤቶች በመንግስት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆ መንገድ  መገንባታቸውን በመግለፅ   በቤት ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን አመላካች ነው ብለዋል።

አቶ ፀጋዬ  ከኮንዶሚኒየም ያነሱት  ቤቶች  ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለመንግስት ሰራተኞች በቀላሉ በኪራይ የሚያገኙበትን መንገድ ነው በጥናት ተቀርፆ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በሀገሪቱ 35 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች የሚገነቡት በመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበራት ነው የሚሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው፤  በክልሎች ደግሞ ይህ ስራ በስፋት እየተሰራበት መሆኑን አንስተዋል።

ኮርፖሬሽኑ ቤቶችን እንደልብ ለመገንባት የመሬት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር አንዱ  እና ዋነኛው መሆኑንም ገልፀዋል።

በዚህም እንደ መፍትሄ የቀረበው በቅርቡ በሚወጣው የሊዝ አዋጅ ላይ ከሚቀርበው መሬት በአስገዳጅ ሁኔታ  30 በመቶውን ለቤት ልማት እንዲውል ማድረግ መሆኑንም አቶ ፀጋዬ አስረድተዋል።

መረጃ 24 ሰአት

27 Jan, 12:54


በአማራ ክልል ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ

የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች በሰሜኑ ጦርነት እና አሁን ላይ በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በመውደማቸው በርካቶች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸው ይታወቃል።

በመሆኑም የክልሉ ትምህርት ቢሮ  ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር  እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እና በሰሜኑ ጦርነት በርካታ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውን የቢሮው ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር ዘመነ አበጀ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት ለመመለስ 112 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

ቢሮው አስጠናሁት ባለው ጥናት መሠረት ይህ ገንዘብ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባትና ከመጠገን በተጨማሪም ተጓዳኝ የትምህርት ሥራዎችን ለማከናወን የሚውል ነው ብሏል።
መረጃው አማራ ኮምኒኬሽን ቢሮ ነው።

መረጃ 24 ሰአት

27 Jan, 12:52


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኤምባሲዎችን የመሬት ጥያቄን የሚመልስ ውሳኔ አሳልፊያለሁ ሲል ገለጸ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታወቀ።ካቢኔው ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከልም የሀገሪቱን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን ማስተናገድ የሚለው እንደሚገኝበት አመላክቷል።

ካቢኔው የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን የሚመልስ ውሳኔ አሳልፊያለሁ ቢልም መሬት የጠየቁትን ኤምባሲዎች በዝርዝር አላሳወቀም።ከኤምባሲዎች በተጨማሪም የዉጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን ምላሽ የሚሰጥ ውሳኔ አሳልፊያለሁ ብሏል።

የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ ተቋማትም መሬት ለመስጠት የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ከአስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

መረጃ 24 ሰአት

26 Jan, 07:46


ፑቲን የትራምፕን ስልክ እየጠበቁ ነዉ ተባለ

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት  ቭላድሚር ፑቲን  ከአሜሪካ አቻቸዉ ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸዉን ክሪሚሊን አስታዉቋል፡፡

የክሪሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ  በእኛ በኩል  ዝግጅት ጨርሰናል ብለዋል፡፡

በቀጣዮቹ ቀናት  ሁለቱ መሪዎች  እንደሚገናኙም  ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ነገሮች  እዉን ሲሆኑ   ይፋ እንደሚያደርጉም ፔስኮቭ መናገራቸዉን  አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር  በቅርብ እንደሚገናኙ መናገራቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

መረጃ 24 ሰአት

26 Jan, 05:02


ህውሃት ተከለከለ

ህወሀት ለነገ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከለ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በፃፈው ደብዳቤ ህወሀት ያካሄደውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተከትሎ በኮንፈረንሱ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለመደገፍ በሚል ነገ ጥር 18 ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል፡፡

ለዚህ ሰልፍም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥያቄ ማቅረቡንም አስረድቷል፡፡ በጥያቄው ላይ የክሉሉ ፖለስ ኮሚሽን ባለድርሻ አካላት ማለትም የትግራይ የፀጥታ ሀይሎችና ሚሊሻ ፅህፈት ቤት በጋራ ለመስራት ምክክር ማድረጋቸውን የጠቀሰው ደብዳቤው እነዚህ አካላት የተደራረበ ስራ እንዳላቸው መታወቁን አስረድቷል፡፡ በመሆኑም አሁን ባለው ሁኔታ ነገ ጥር 18 የፀጥታ ሽፋን መስጠት ስለማይቻል ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላለፉት ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

25 Jan, 10:25


የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር፣ የግል የጦር መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች ከመደበኛ ጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ጸጥታ ተደራጅተው እንዲጠብቁ እንደፈቀደ ዋዜማ ሰምታለች።

ነዋሪዎቹ የሚይዙት የግል ጦር መሳሪያ፣ ሕጋዊ መኾኑን ለማሳወቅ ኩፖን ይዘው መንቀሳቀስ አለባቸው መባሉን ምንጮች ተናግረዋል።

ኾኖም በራሳቸው ጦር መሳሪያ ሰላም የሚያስብሩ ነዋሪዎች፣ ከራሳቸው ቀበሌ ወደ ሌላ ቀበሌ ወይም ወረዳ መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም ተብሏል።

የክልሉ መንግሥትም፣ በኹሉም አካባቢዎች ጦር መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲያስጠብቁ የመፍቀድ ሃሳብ እንዳለው አንድ የዋዜማ ምንጭ ተናግረዋል።

መረጃ 24 ሰአት

25 Jan, 06:32


በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ 359 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 359 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እንደቀጠለ ሲሆን÷ በሳምንቱ 156 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 143ቱ ሴቶች፣13ቱ ጨቅላ ህፃናት እንዲሁም 18ቱ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ በሳምንቱ 203 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን÷ከተመላሾች መካከል 4ቱ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል።

መረጃ 24 ሰአት

25 Jan, 05:08


ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀ ሆቴል 300 ሺህ ብር ተቀጣ‼️

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተርናሽናል ሆቴል 300 ሺህ ብር መቀጣቱን እና ቦታውን እንዲያጸዳ መደረጉን የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በከተማዋ ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶች እና ግንባታ ገንቢዎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

23 Jan, 09:45


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ አቅራቢያ አዲስ ሰደድ እሳት ተቀሰቀሰ!

በአሜሪካ ካፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ሎስ አንጀለስ ከተማ ሰሜናዊ ክፍል ትናንት አዲስ የሰደድ እሳት መቀስቀሱ ተነግሯል።

በሰዓታት ውስጥ ከ3 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት የሸፈነው ይህ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ስፍራቸው እያፈናቀለ መሆምኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎም 31 ሺህ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ለ23 ሺህ ሰዎች ደግሞ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ደረቅ አየርና አደገኛ ንፋስ ለሰደድ እሳቱን መዛመት ምክንያት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋም ተሰግቷል።

በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ሰደድ እሳት ለማስቆምም በርካታ የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል። በሎስ አንጀለስ ከተማ እና አካባቢው ከ16 ቀናት በፊት ከተቀሰቀሰው እሳት ውስጥ ከባድ የተባሉት የኢቶንና ፓላሲደስ እሳቶች አሁንም እየነደዱ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

መረጃ 24 ሰአት

23 Jan, 09:22


በእሳት እና በመኪና አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ

በደብረ ብርሀን ከተማ በደረሰ የእሳት እንዲሁም በሐረር ከተማ እና በስልጤ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ አደጋው ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 በወረዳው ሌፎ በሚባል አካባቢ ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ደርሷል።

በአደጋው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል የወረዳው መረጃ ያመላክታል፡፡

የእሳት አደጋው በደብረብርሀን ከተማ አየር ሀይል ቀበሌ ትናንት ምሽት 2፡30 የደረሰ ሲሆን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ የትራፊክና  መረጃ ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ኪዳኔ በቀለ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የእሳት አደጋው የተነሳው ከመኖሪያ ቤት መሆኑንና በቤት ውስጥ ቤንዚን መኖሩ አደጋውን አባብሶ ለመቆጣጠር አዳጋች እንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡

በእሳት አደጋው ጉዳት የደረሰበት አንድ ግለሰብ በደብረ ብርሀን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ መሆኑ መገለጹን ሪፖርተራችን አላዩ ገረመው ዘግቧል።

በሌላ በኩል በሐረር ከተማ ዛሬ ሌሊት 8፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ጣሰው ቻለው እንደገለጹት፤ አደጋው የደረሰው በሬ የጫነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪን ለማዳን ሲሞክር በመገልበጡ ነው፡፡

በአደጋውም በአይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንና  በአይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ ከተጫኑት 15 በሬዎች መካከልም ሶስቱ መሞታቸውንም ገልጸዋል።

የአይሱዙ አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩን ጠቁመው፤ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

መረጃ 24 ሰአት

23 Jan, 09:15


በሰሜን ሸዋ ዞን በፍርድ ቤት ዳኞች ላይ በተፈጸመ ድብደባ እና ማስፈራሪያ የፍርድ ቤት አገልግሎት ተቋረጠ!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በፍርድ ቤት ዳኞች ላይ በተፈጸመ ድብደባ እና ዛቻ ምክንያት የወረዳው ፍርድ ቤት አገልግሎት መስጠት ማቆሙን የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ገለፁ።

ድብደባ እና ዛቻው የደረሰባቸው ጄኔኑስ ነጋሳ የተባሉ ዳኛ “ስድስት ሰዎች ሆነው መሬት ላይ ጥለውኝ የቻሉትን ያህል መላ ሰውነቴን ራጋገጡን። በብረት ቀበቶ ፊቴን ሲገርፉኝም ነበር።ትንፋሽ ሲያጥረኝ አንስተው ወደ ክፍል መለሱኝ” ሲሉ ወደ ወታደራዊ ካምፕ ተወድሰው የደረሰባቸውን ጥቃት  ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በያያ ጉለሌ የፍርድ ቤት ዳኛ በሆኑት ጄኔኑስ ነጋሳ ላይ የተፈጸመውን ድብደባ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጾ ከተፈጸመው ድርጊት ጋር በተያያዘ ምርመራ እንዲደረግ ለዞኑ መመሪያ ተላልፎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል

መረጃ 24 ሰአት

23 Jan, 05:37


መረጃ ‼️

የደቡብ ሱዳን መንግሥት፣ ሱዳን ውስጥ የተገደሉ ደቡብ ሱዳናዊያን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ሥርጭት ለመግታት ኹሉንም የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከዛሬ ጀምሮ ለ30 ቀናት እንዲዘጉ አዟል።

የሱዳን ጦር ሠራዊት ከሳምንት በፊት የአልጀዚራ ግዛት ዋና ከተማ ዋድ ማዳኒን ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል ሲያስለቅቅ፣ በከተማዋ የሚኖሩ በርካታ ደቡብ ሱዳናዊያን ተገድለዋል።

ይህንኑ ተከትሎ ጁባ ውስጥ በሱዳናዊያን ላይ የበቀል ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲኾን፣ ጥቃቱን ለመከላከልም መንግሥት በተያዘው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሰዓት እላፊ አውጇል።

ደቡብ ሱዳናዊያን ሱዳን ግድያ የተፈጸመባቸው፣ ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋር ወግነው የሚዋጉ በርካታ ደቡብ ሱዳናዊያን ቅጥረኛ ተዋጊዎች ስለመኖራቸው ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው።

መረጃ 24 ሰአት

22 Jan, 10:23


ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ቦንቡ የፈነዳው ዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ አሳሊ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ዱቤ 02 ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት መንደር ነው።

የደቡብ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፓሊስ እንደገለፀው ትናንት ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በደረሰ በዚህም ፍንዳታ በስድስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በተርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት የአደጋው መነሻ ምክንያቱ የአንድ ግለሰብ አሮጌ መኖሪያ ቤት አፍርሶ በአዲስ ለመስራት በአከባቢው አጠራር ዳጉዋ (በደቦ) ሥራ ላይ የነበሩ ስምንት ሰዎች በቁፋሮ ወቅት ያገኙትን F1 የተባለ የእጅ ቦንብ ባለማወቅ በድንጋይና በመዶሻ በመቀጥቀጣቸው ፍንዳታው መከሰቱን ፓሊስ አስረድቷል፡፡
መረጃው የቲክቫህ መጋዚን ነው።

መረጃ 24 ሰአት

01 Jan, 07:37


"ኢትዮጵያዊያን ከእንግልትና ካላስፈላጊ ወጪ ያድናል" የተባለለት የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ጸደቀ

   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዜጎች አዳዲስና ዘመኑን የሚመጥን የጤና አገልግሎት ፍለጋ ወደ ሌሎች ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያስቀር አዋጅ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር)፥ በተለያዩ ሕጎች በተበታተነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የሚገኙ የጤና አገልግሎቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በአንድ ማእቀፍ ሕግ እንዲወጣ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የተነሳ አዋጁ እንዲሻሻል ምክንያት የሆነው ብለዋል።

ከነዚህ ድንጋጌዎች በተጨማሪም አሁን ወቅቱ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ የተጣጠመ አዳዲስ የጤና አገልግሎት ድንጋጌዎችን በማካተት እና በስራ ላይ የነበሩት ድንጋጌዎችን በማሻሻል ወጥ የሆነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የሕግ ማእቀፍ በማስፈለጉ የተዘገጀ ረቂቅ አዋጅ ነውም ብለዋል።

አዋጁ የጤና አገልግሎት ፍትሃዊነት፣ ተደራሽነትና ጥራት፣ ቅልጥፍና  እንዲሁም የህዝብ ጥቅም፣ ባህልና ሃይማኖትን በጥንቃቄና በጥልቀት በመመልከት አልፎም የጤና ባለሙያዎችን መብት የሚያስከብር ነው ተብሏል።

እንደዚሁም ከዘረ መል መራባት  እና ጥቅም ላይ ማዋል ጋር  የሚሰጡ አገልግሎችን ከማህበረሰብ እሴት ባህልና ከኢትዮጵያ ህግ ጋር በማጣጣም የተዘጋጀ መሆኑ ነው የተገለጸው።

አዋጁ ዜጎች አዳዲስና ዘመኑን የሚመጥን የጤና አገልግሎት ፍለጋ ወደ ሌሎች ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያስቀር መሆኑን የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

መረጃ 24 ሰአት

01 Jan, 06:36


የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት

🔥የእሳተ ገሞራ ከመከሰቱ በፊት መወሰድ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ከተፈጠረና በፍንዳታው ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች ሰዎችን ለማዳን ከመኖሪያቸው ማስወጣት አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ሁኔታ ቤት መልቀቅ ሊኖር ስለሚችል ከመንግስት አካላት የሚሰጡ ትዕዛዞችን እና መልዕክቶችን በትጋት መከታተል ይገባል።

ከሚመለከታቸው አካላት ከቤት ልቀቁ ከተባለ የሚከተሉትን እቃዎች ቀድመው ያዘጋጁ:-

👉🏽ደረቅ ምግቦችና የመጠጥ ውሃ
👉🏽ማስኮች
👉🏽አስፈላጊ መድሃኒቶች
👉🏽ፊት መሸፈኛ ሻርፖች
👉🏽 ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍኑ ልብሶች
👉🏽 ስልክ መረጃ ለመለዋወጥ
👉🏽 የእጅ ባትሪዎች
👉🏽 የመጀመሪያ እርዳታ መሳሪያ ኪቶች
👉🏽 መነጽሮች
👉🏽 ሬድዮ
👉🏽 የጤና ባለሙያዎች ስልክ ቁጥር መያዝ

☝️የእሳተ ገሞራ ከተከሰተ በኋላ መደረግ  የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የእሳተ ገሞራው ጭስ የሚደርስበት አካባቢ ከሆኑ ጭሱ የተለያዩ ጎጂ ጋዞችን የያዘ በመሆኑ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ:-

🏡በቤት ውስጥ ከሆኑ 

👉🏽 ጭሱ እንዳይገባ መስኮቶችን እና በሮችን በመዝጋት ቤት ውስጥ መቀመጥ
👉🏽 የመጠጥ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ውሃዎችን በደንብ መክደንእንስሳቶችም በጭሱ ምክንያት አደጋ ሊደርስባችው ስለሚችል በቤት ውስጥ በርና መስኮት ዘግቶ ማስቀመጥ
👉🏽ተዐማኒ ከሆኑ የመረጃ ሰጪ ተቋማት የሚሰጡ መረጃዎችን በንቃት መከታተል
👉🏽 የአየር ማቀዝቀዣ ፋኖችን ማጥፋት
👉🏽 በቤት ውስጥ ከሰል አለማቀጣጠል

🌆ከቤት ውጪ ከሆኑ

👉🏽 ወዳገኙት መጠለያ በመግባት መጠለል
👉🏽 በጋዙ ምክንያት የአይን፣ የአፍንጫ፣ የጉሮሮ ማቃጠል ካጋጠሞት ጭሱ ካለበት ቦታ ወደቤት በመግባት እራስዎን ያርቁ። ( ማቃጠሉ ካላቆመ ለህክምና ባለሙያ ደውለው ማሳወቅ)
👉🏽 የተቃጠለ አካል ካለ ወዲያውኑ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ
👉🏽 ቅልጥ አለቱ ሊፈስ ወደሚችልበት ቁልቁለታማ ወደ ሆኑ ቦታዎች አለመሄድ
👉🏽 ፊትን እና የተገለጠ የሰውነት ከፍሎችን መሸፈን፣ መነጽሮችንና የመተንፈሻ ማስኮችን ማድረግ
👉🏽 የመኪና ሞተር ማጥፋት
👉🏽 አቅመ ደካማ እና ህጻናትን መርዳት

መረጃ 24 ሰአት

31 Dec, 22:31


🎚🌟🎚 2⃣0⃣2⃣5⃣ 🏍🏍

✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️

🎆🎆 2️⃣0️⃣2️⃣5️⃣ 🎆🎆

🔠🔠🔠🔠🔠 🔠🔠🔠 🔠🔠🔠🔠

Share🙏🙏🙏🙏🫴🫴🫴🫴

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Dec, 20:19


ዛሬ ምሽት  ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ  በአዋሽ ፈንታሌ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።

በተለይም ደግሞ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። ጠንከር ያለ እንደነበረም ጠቁመዋል።

ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ጣፎ ... ሌሎችም አካባቢዎች በተለይ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች  ገልፀዋል።

via_ticvah

መረጃ 24 ሰአት

31 Dec, 07:16


በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ያውቃሉ?

በአዋሽ ፈንታሌ በሬክተር ስኬል የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ከታች የተዘረዘሩትን ጥንቃቄዎች መተግበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡

📌 በተለያየ ምክንያት ከቤት ውጭ ከሆኑ፦  ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌክትሪክ ምሦሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መሆን ይመከራል፡፡

📌 በቤት ውስጥ ከሆኑ፦ በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ እንዲሁም ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች ፣ ከመስኮት አካባቢ መራቅ እና የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

📌 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

📌 መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ፦ የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሦሶዎች፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌክትሪክ መስመር ምሦሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እና መሰል የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ መክሯል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

31 Dec, 07:15


የመሬት መንቀጥቀጡ 47 ቤቶችን አፍርሷል።ከ2,500 በላይ አባዋራ አፈናቅሏል።

📌ትናንት ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም ለሊቱን ከእስከ ዛሬው ከፍተኛ የተባለ(5.2 በሬክተር ስኬል) ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

📌 የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የተሰማባቸው ሰዓታት
4:30  5:29   5:33   5:58
6:22   7:13    9:02 ናቸው።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ መነሻው አፋር ክልል ሲሆን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ ባይኖርም በገቢ ረሱ ዞን 47 መኖሪያ ቤቶችን ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል።30ዎቹ ቤቶት ከትናንት በፊት ሲሆን 17ቱ ትናንት ምሽት  ጉዳት ደርሶባቸው አጠቃላይ ከ2500 በላይ አባዎራ ተፈናቅሏል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዋሽ አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀለ በሚገኝበት ወቅት ፣በርካታ ህንፃዎች፣ የመኖርያ ቤቶች እና መንገድ ጭምር እየተሰነጣጠቀ ባለበት ሰዓት፣አዳዲስ እሳት ገሞራ እየተፈጠረ(ፈንታሌ) ባለበት ሰዓት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕ/ር አታላይ አየለ ከሰሞኑ ህዝቡን እየረበሸ እና እያሳሰበ በሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ ዙርያ ለቲክቫህ በሰጡት አስተያየት "መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም" የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተው ተመልክተናል።

መረጃ 24 ሰአት

30 Dec, 20:55


ቦሌ አከባቢ ፣ ሀና ማርያም ሰፈራን ጨምሮ ፣ ሾጎሌ ፣ ኮዬ ፈጬ ፣ አዲስ ዩኒቨርስቲ አከባቢዎች ይሄን ከወትሮ በተለየ ከበድ ያለ ንዝረት እንደነበረ የተላከልኝ መረጃ ያሳያል።

እኔ በበኩሌ ኳስ እያየሁበት በነበረ ቅፅበት ይሄን በከፍተኛው ተሰምቷል። እስከአሁን ምንም የደረሰ አደጋ የለም። ነገር ግን ለተከታታይ ቀናት በመሆኑ መውሰድ ያለብን ጥንቃቄዎች መውሰድ ተገቢ ነው።

መረጃ 24 ሰአት

30 Dec, 18:37


''ከንቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል 'የትኛውን ከንቲባ' ተብዬ እየጠየቃለሁ'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡

''በሕወሃት ፓርቲ መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት ህዝቡ እየተንገላታ ነው'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተናግሯል፡፡በሕወሃት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከተሞች ሁለት ከንቲባ እና አስተዳደሪ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ይህም ተገልጋዩ ለእንግልት ዳርጓል ብሏል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ፡፡

የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ እና አዲግራትን ጨምሮ በክልሉ ያሉ አንዳንድ ወረዳዎች በጊዜአዊ አስተዳደሩም እና በእነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) በሚመራው ህወሃትም ከንቲባ እና አስተዳዳሪ ይሾምላቸዋል ሲሉ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ አንባዬ አስታውሰዋል፡፡

ይህም አንዱ ለአንዱ ስለማይታዘዝ ተገልጋዩ ጉዳዩን የሚፈጽምለት አጥቶ ተቸግሮ ነው ያለው ሲሉ አቶ ጸሃዬ እንባዬ አስረድተዋል፡፡በተመሳሳይ ወረዳ እና ከፍለ ከተማ ላይ ያሉ የስራ ሃላፊዎች  አንዱ የመራውን ደብዳቤ ሌላኛው እኔ የእገሌን ትዕዛዝ አልፈጽምም ይላሉ ሲሉ አቶ ጸሃዬ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ራሱ የህዝብን አቤቱታ ለማስፈፀም መቸገሩን ነገሮናል፡፡በሕወሃት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ከንቲባውን ፈልገን ስልክ ስንደውል እንኳን 'የትኛውን ከንቲባ' እየተባልን እየተጠየቅን ጉዳይ ለማስፈፀም ተቸግረናል ብሏል፡፡

Via Sheger

መረጃ 24 ሰአት

30 Dec, 11:32


ቡሩንዲ በሶማሊያ በአዲስ ተልዕኮ ከሚሰማራው የሰላም አስከባሪ ጦር መውጣቷን በይፋ አስታወቀች

በሶማሊያ አዲስ ተልዕኮ ተሰጥቶት ከቀናት በኋላ ስራ በሚጀምረው የሰላም አስከባሪ ጦር ከሚያዋጡ ሀገራት መካከል መሆኗ ተገልጾ የነበረው ብሩንዲ ጦሯን እንደማታዋጣ አስታወቀች።

ሀገሪቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በሶማሊያ ለቀጣዩ ተልእኮ በምታሰማራቸው ወታደሮች ብዛት ላይ አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ነው።

ቡሩንዲ ለተልዕኮው ሁለት ሺ ወታደሮችን ለማዋጣት ብትፈልግም፣ ሱማሊያ ለቡሩንዲ የፈቀደችላት የወታደር ብዛት ግን አንድ ሺሕ 41 ብቻ መሆኑ ተነግሯል።

ቡሩንዲ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ሂደት  ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካደረጉ ሀገራት መካከል አንዷ እንደመሆኗ ከተተኪው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ መልቀቋ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ተመላክቷል።

“ሶማሊያ ውስጥ ከአልሸባብ ጋር በምናደርገው ጦርነት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈልን ቢሆንም ከሶማሊያ ባለስልጣናት በኩል ክህደት እና ውለታ ቢስነትን ታዝበናል” ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቡሩንዲ ባለስልጣን አስተያየታቸውን እንደሰጡት ቺምፕ ሪፖርት ጋዜጣ በድረገጹ አስነብቧል።

በተጨማሪም "በሶማሊያ በኩል እንድናሰማራ የተጠየቅነው አነስተኛ የወታደር ቁጥር የአሰራር ደህንነታችንን አደጋ ላይ ይጥላል" ማለታቸውን ዘገባው አካቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ከቀናት በፊት ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ተግባር ተሰማርቶ በቆየው አትሚስ አተካክ ረቂቅ ውሳኔ ላይ ውሳኔ ማሳለፉን መዘገባችን ይታወሳል።

አትሚስን በመተካት ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቶ ለሚሰፍረው የሰላም አስከባሪ ጦር ይሁንታ መስጠቱን፤ የቆይታ ግዜውም 12 ወራት እንዲሆን መፍቀዱን በዘገባው ተካቷል።

መረጃ 24 ሰአት

30 Dec, 06:51


ለሊት ላይ  ከደብረ ሲና 52 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

- በቅርብ ቀናት ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል

ለሊት 7:20 ላይ የተከሰተው ይህ ርዕደ መሬት 5.1 ሆኖ በሬክተር ስኬል እንደተመዘገበ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል፣ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ንዝረቱ እንደተሰማቸው እየጠቆሙ ይገኛሉ።

ይህ በቅርብ ቀናት ውስጥ በአብዛኛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከተከሰቱት ርዕደ መሬቶች በመጠኑ ከፍተኛው እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ የተጠጋ ሆኖ ተመዝግቧል።

የሰሞኑን ተደጋጋሚ ክስተት ተከትሎ በርካታ የጥንቃቄ መልእክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ።

መረጃ 24 ሰአት

30 Dec, 06:50


በሣቡሬ ቀበሌ በተከታተይ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተሰነጠቀ መሬት ሲሆ በስንጥቁ አንድ ግመል እና ሁለት ከብት መሞቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመረዳት ችለናል።እንዲሁም መኖርያ ቤታቸውን ከቦታው ለማስነሣተ የተገደዱ ቢሆንም ይሻላል ብለው የሚሄዱበት አካባቢ እንደሌለ ነዋሪው ገልፆልናል።

መረጃ 24 ሰአት

29 Dec, 18:04


ለፓርላማ የቀረበው የንብረት ታክስ ረቂቅ ሕግ ‹‹የኅብረተሰቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል ነው›› ተባለ

ከተሞች ለዓመታዊ የልማት ወጪያቸውና ፍላጎታቸው ሀብት እንዲያመነጩበት በሚል ዕሳቤ እንደተዘጋጀ ተገልጾ፣ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ለሕግ አውጭው የላከው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣ የኅብረተሰቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል ነው ተብሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠንካራ ትችት ገጠመው፡፡

ትችቱ የቀረበው የምክር ቤቱ ፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስቴር ጋር በመሆን፣ ታኅሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአባላቱ ጋር በረቂቁ ዙሪያ ሲያወያይ ነው፡፡

ረቂቁን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ  መሐመድ አብዶ (ፕሮፌሰር)፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገባ ሳይታቀዱ የተሠሩ መንገዶች ፈርሰው እንደገና ሲሠሩ መመልከታቸውንና ይህ ዓይነት የልማት ዕሳቤ በሕዝብ ኪሳራ የሚተገበር መሆን የለበትም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ለከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ ምጣኔ እንዲጥሉ ኃላፊነትና ዕድል መስጠት፣ ከተሞች እየተነሱ ፍትሐዊ ያልሆነ ታክስ ሕዝብ ላይ እየጣሉ ለብዝበዛ ይዳርጋሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ እንደተብራራው በሥራ ላይ ያለው የቦታ ኪራይና የቤት ታክስ ሥርዓት በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የከተማ ነዋሪ ሕዝብ፣ የአገልግሎትና የመገልገያ ቦታዎች ፍላጎት፣ በአግባቡ ለማሟላት የሚያስችል ገቢ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማመንጨት ትልም ተይዟል፡፡

በከተማ ቦታ መጠቀሚያ መብት ላይ የሚጣል ታክስ፣ በከተማ ቦታ ላይ በተደረጉ ማሻሻያዎችና በከተማ ቤት ባለቤትነት ላይ የሚጣል በሚል በረቀቁ ተመልክቷል፡፡
ምክር ቤቱ በጠራው ውይይት የተገኙት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ታክስ ማን ላይ ነው እየጣልን ያለነው? ታክስ ፍትሕዊ በሆነ መንገድ ሀብት የምናከፋፍልበት ነው፡፡ ከፍተኛ ገቢ ወይም የሀብት መጠን ካላቸው ዜጎች በመሰብሰብ ደሃውን የምንደጉምበት አሠራር ነው፡፡ ይህንን መርህ መጠበቅ ደግሞ ግድ ይመስለኛል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹በእኛ አገር ግን አብዛኛውን ታክስ የምንጥለው ዝቅተኛ ገቢ ባለው ሰው፣ በአብዛኛው የከተማ ነዋሪና የመንግሥት ሠራተኛው ላይ ነው፡፡ የግብር አሰባሰቡን የምናሻሽለው በእነዚህ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ታክስ በማብዛት ነው ወይ? ይልቁንስ ከፍ ያለ መሬትና ሕንፃ ያላቸው ላይ ከፍ ያለ ታክስ በመጣል ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች መደጎም አይሻልም ወይ?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡....

የሌላ አገር ልምድ በሚል የቀረቡትን የታክስ ምጣኔ ማሳያዎች ሲያብራሩ፣ ‹‹የእኛ ሕዝብ አይችለውም፣ ሌላ ቀውስ ውስጥ በማስገባት ሕዝብንና መንግሥትን የሚያራርቅ ጉዳይ እንዳይፈጠር፤›› ሲሉም ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ወደ ታች ሲወርድ ሌላ ችግር  እንዳያመጣ እሠጋለሁ፤›› ብለዋል፡፡

    ከዚህ ቀደም ኤሌክትሪክ ላይ የተጨመረው ታሪፍ መንግሥት ከጨመረው ደመወዝ ጋር እኩል አይሄድም ብለው፣ ‹‹እኔ 700 ብር ተጨምሮልኛል፣ የመብራት ወጪዬ ግን 1,200 ብር ነው፡፡ ይህ ማለት ከተጨመረው አንፃር ጭማሪው ኔጌቲቭ ውስጥ ገብቷል ማለት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ማኅበረሰቡን እያንገላታው ነው፣ ልናሻሽል ብለን ልናባብስ አዋጅ ማውጣት የለብንም ከሚሉት ውስጥ ነኝ፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

  አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) የተባሉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ተወካይ በበኩላቸው ፣ ‹‹ገንዘብ በመሰብሰብ ብቻ አገር ማሳደግ ይቻላል ወይ? ሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የታክስ ጫና አለ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ደሃ የሚበላው ቢያጣ የሚከፍለው አያጣም የሚለውን መርህ መደበኛ ባልሆነ መንገድም ቢሆን እየተከተለ ይመስለኛል፤›› ብለዋል፡፡ via_ሪፖርተር

መረጃ 24 ሰአት

29 Dec, 04:47


ውብና ማራኪ እሁድ ተመኜን !

[መልካም ቀን]

መረጃ 24 ሰአት

29 Dec, 04:38


የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች

• የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር - ኤላ ትሪክ
• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ
• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi
• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ
• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮንቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ
• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ /Miss Fendisha/
• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ - ጃዝሚን/jazmin_hope1/
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት - ኤላ Review
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ - Baes
• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ
• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ
• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu
• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ - ባዚ
• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ /Elatick/
• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ - I did it በዘነዘና
• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ - አቤል ብርሃኑ
• የዓመቱ ምርጥ ኢንፎርማቲቭ ኮንቴንት አዋርድ- ሙሴ ሰለሞን
• የዓመቱ ምርጥ ኢመርጂንግ ኮንቴንት አዋርድ-ስኬት ቤስት ሾርት ሙቪ ቪዲዮ አዋርድ
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በወንድ አሸናፊ- ከርተንኮል
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በሴት አሸናፊ - ማሂልት ኢብራለም

መረጃ 24 ሰአት

28 Dec, 20:13


"አልሃምዱሊላህ ለዚህ ላበቃኝ አላህ"
                                       ኤላ
''ቲክቶክ ስጀምር እንኳን እዚህ እደርሳለው ብዬ ላስብ ቪዲዮዬ viral ይወጣል ብዬ አላሰብኩም ነበር''
ኤላ የ2024 የቲክቶክ ክሪኤቲቭ አሸናፊ ሆነ!
የ300ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል ።

መረጃ 24 ሰአት

28 Dec, 18:12


በቀናት ውስጥ 3 ፕሬዝደንቶችን የቀያየረችው ደቡብ ኮሪያ

የገንዘብ ሚኒስትሩ ቾይ ሳንግ ሞክ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል
በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው እስያዊቷ ሀገር ደቡብ ኮሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 3 ፕሬዝዳንቶችን ቀይራለች፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዩል ምንም አይነት በቂ ምክንያት ሳይኖር የወታደራዊ አስተዳደር (ማርሻል ሎው) ማወጃቸውን ተከትሎ ከስልጣናቸው በጊዜያዊነት ወርደው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡

ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃን ዳክ-ሶ በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል፡፡

ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ የፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዩል ጉዳይን ለመመልከት በተቋቋመው ህግ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የዳኞች ስያሜ ላይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ነው ከስልጣናቸው ወርደው ምርመራ እንዲደረግባቸው ፓርላማው የወሰነው፡፡

በዚህም የፋይናንስ ሚኒስትሩ ቾይ ሳንግ ሞክ በ15 ቀናት ውስጥ ሶስተኛ ወደ መንበሩ የመጡ ፕሬዝዳንት ሆነው በጊዜያዊነት ተሹመዋል፡፡

የሃን ድንገተኛ ከስልጣን መነሳት በሀገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፤ ኢኮኖሚውም የስጋቱ ተካፋይ ነው፡፡

 ከ2008 የፋይናንስ ቀውስ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ዎን ከዶላር አንጻር የመገዛት አቅሙ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል፡፡(አልዓይን)

መረጃ 24 ሰአት

28 Dec, 08:28


የቅዱስ ገብርዔል ዓመታዊ የንግስ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

ታሕሣሥ 19 የሚከበረው የቁልቢ እና የሐዋሳ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ዓመታዊ ክብረ በዓሉ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ነው በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች  በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በንግስ በዓሉ ለመታደም  ከተለያዩ  የአለም ሀገራት እና የሀገሪቱ ክፍሎች የእምነቱ ተከታዮችና ቱሪስቶች ወደ ስፍራው አቅንተዋል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

28 Dec, 08:27


ድጋሚ ተወሰነባቸው

አቶ አብነት ገብረመስቀል ከቦሌ ታወርስ ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሠናበቱ በፍርድ ቤት በድጋሚ ተወሰነባቸው

    አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሳሽ በነበሩበት የቦሌ ታወርስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል መሕበርን በባለአንድ አክሲዮን ሆኖ እንድጠቀልለው  ይወሰንልኝ ብለው ያቀረቡት ክስን ፍርድ ቤት ሳይቀበለው  ቀርቷል ።

በአቶ አብነት ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ተከሰው የነበሩት አላሙዲ የተከሳሽ ከሳሽ በመሆን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ 5ኛ ንግድ ችሎት ሲከራከሩ ቆይተዋል ።

ጉዳዩን ለወራቶች ሲመለከት የቆየውም ፍርድ ቤቱም መጋቢት 30 ቀን 2016 አም በዋለው ችሎት ፍርድ ሰጥቶ ነበር ።

በወቅቱ ፍርድ ቤቱ በአቶ አብነትእና በሼኽ መሐመድ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ብርቱ በመሆኑ መሐበሩ ከሚፈርስ  ቦሌ ታወርስ ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል መሐበርን ሼኽ መሐመድ እንዲጠቀልሉት ሲል ፍርድ ሰጥቶ ነበር ።

ይህን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም አቶ አብነት ገብረመስቀል ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ችሎት ይግባኝ በማለት ቅሬታ አቅርበው እንደነበር የውሳኔ መዝገቡ ይገልፃል   ።

ይግባኙን ሲመለከት የቆየው ፍ / ቤቱም ማክሰኞ ታህሳስ 15 ቀን 2017 አም በቀረበው ይግባኝ ላይ ውሳኔ ሰጥታል ።

ፍርድ ቤቱ በውሳኔውም አቶ አብነት ገብረመስቀል  የመሐበሩ ስራ አስኪያጅ ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ መሐበሩ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ከ20 አመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ እንደማያውቅ ፣ የመሐበሩን ሒሳብ በወቅቱ እንደማያሰሩ ፣ የመሐበሩ የሒሳብ ሚዛን የኦዲት ሪፖርት የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችና ሌሎች ሰነዶች ለሼኽ መሐመድ ያልሰጡ መሆናቸውና የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች የ15 አመታት የሒሳብ መዝገቦች አና ሰነዶች የየአመቱ ትርፍና ኪሳራ መግለጫ ፣ የየአመቱ የንብረት ዝርዝር ፣ የየአመቱ ሐብትና እዳ መግለጫ ወይም የሒሳብ ሚዛን የሌሉ መሆናቸው ና ፣ የየአመቱ የመሐበሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሰነድ የሌለ መሆኑ ፣ በመሐበሩና በይግባኝ ባይ መካከል ከፍተኛ የጥቅም ግጭት መኖሩን፣ የመሐበሩን ሰነዶች በአግባቡ አለመያዛቸው፣ መሐበሩን በተገቢው ጥንቃቄ እና ትጋት አለመምራታቸው፣ የማህበሩ ይዞታን የሆነ 2000ካ ሬ ሜትር ስመሀብት ወደ መሐበሩ አለመዞሩ ፣የመሐበሩ ካፒታል ከአስር ሚሊዮን ብር ወደ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር ያደገ መሆኑን ቢገልፅም ድርሻው ያደገው ግን ወደ አምስት መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ፣ለማህበሩ ህንፃ ግንባታዎች የተደረጉ ወጪዎች አለመመዝገባቸው ፣ ማህበሩ ከዳሽን ባንክ በሶስት ብድሮች የወሰደው አርባ አምስት ሚሊዮን ብር  እና ከማህበሩ የባንክ ሒሳበሰ የተደረጉ ክፍያዎች፣ በማህበሩ ሒሳብ አለመመዝገባቸው፣ መሐበሩ ሲመሠረት የተከፈለው መዋጮ በመሐበሩ ስም በተከፈተ ዝግ ሒሳብ አሐመቀመጡ ፣ በኦዲት ሪፖርት መረጋገጡ ምክንያትነት በመጥቀስ ነው

ይግባኝ ባይ በማህበሩ ይዞታዎች ወደ ግላቸው ያዛወሩ መሆኑም ተረጋግጧል ።እነዚህ ተግባራት ይግባኝ ባይ  በማህበሩ ጥፋትና ጉዳት ያደረሱ መሆኑ የሚያስረዱ ናቸው ።

እነዚህ የፈፀሟቸው ተግባራት በሁለቱ ባለአክሲዮኖች  አለመተማመን የሚፈጥሩና አብረው መቀጠሉ ማህበሩ አላማውን ያሳካል ተብሎ ስለማይገመት ማህበሩ በቀጣይነት የተመሠረተበትን አላማ እንዲያሳካ ጥፋት የፈፀሙት ባለአክሲዮን አቶ አብነት ገብረመስቀል በመሆናቸው የስር ፍርድ ቤት እነዚህን ጥፋቶች ይግባኝ ባይ ከማህበሩ ለማስወጣት የሚያበቁ በቂ ምክንያት ነው ብሎ ይግባኝ ባይ ከመሐበሩ አባልነት እንዲሰናበቱ ውሳኔ መወሰኑ በማስረጃ ምዘና የፈፀመው ስህተት የለም ሲል ወስናል ።

ውሳኔው ሲቀጥልም አቶ አብነት ገብረመስቀል ከመሐበሩ እንዲሰናበቱ በመወሰኑ አክሲዮን ድርሻቸው በምን አግባብ ተሰልቶ እንደሚከፈላቸው በንግድ ህጉ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚመለከት በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለም ።

ነገር ግን በን /ህ/ቁ 527(1)የን/ህ/ቁ403 ባለ አክሲዮን ከማህበሩ መውጣት በሚመለከት ከሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ ስለደነገገ የስር ፍርድ ቤት አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦሌ ታወርስ በመጨረሻ የሒሳብ አመት የሃብትና እዳ የሒሳብ መግለጫ ውስጥ በተመለከተው የማህበሩ ሐብት ውስጥ አክሲዮናቸው በሚመለከት መጠን ድርሻቸው ታስቦ እንዲከፈላቸው መወሰኑ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም በመሆኑም አቶ አብነት በ29/09/2016 አም በፅሁፍ ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ 5ኛ ንግድ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 01605 በቀን 30/07/2016 ዓም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ ሊነቀፍበት የሚያስችል የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ጉድለት ያልተገኘ በመሆኑ መልስ ሰጪን መጥራት ሳያስፈልግ በፍ/ብ/ስ/ ስ//ህ/ቁ 337 የይግባኝ ባይ አቤቱታን ፍርድ ቤቱ ሰርዟል ሲል ውሳኔ ሰጥቷል ።

መረጃ 24 ሰአት

28 Dec, 08:23


19

እንኳን ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መረጃ 24 ሰአት

27 Dec, 12:27


ዳቦ ለመግዛት የሄደች 5 ዓመት ሕጻንን አስገድደው የደፈሩ ሁለት የዳቦ ቤት ሠራተኞች በ19 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ

በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ሕጻን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት መቀጣታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ተከሳሾች አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ ሁለቱም ግለሰቦች የዳቦ መጋገሪያ ቤት ሠራተኞች ናቸው።

ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን፤ ተበዳይ የ5 ዓመት ሕጻን ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት በሁለት ዳቦ ቤት ሠራተኞች መደፈሯ ተገልጿል።

ይህም ወንጀል መፈጸሙን ክሱ የደረሰው የወናጎ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀረቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጡን አስታውቋል።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ታሕሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን አሐዱ ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ሕጸን ርኆቦት በለጠ ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድ ቤት በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተገልጿል።

መረጃ 24 ሰአት

26 Dec, 10:04


ዩኒቨርስቲዎች ውጤታማ ካልሆኑ ህልውናቸው ሊቀጥል አይችልም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ አስጠነቀቁ

ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በጀት የምመድበው በተማሪዎቻቸው እና በመምህራን ብዛት ሳይሆን ባስመዘገቡት ውጤት ልክ ነው ሲል ገለጸ፤ ዩኒቨርሰሲቲዎች ውጤታማ ካልሆኑ ህልውናቸው ሊቀጥል አይችልም ብሏል።

ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር ይቀራል ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎቹ ውጤታማ ካልሆኑ ወደ ቴክኒክ ማሰልጠኛነት የሚቀየሩበት ኹኔታ ይኖራል ሲሉ አሳስበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴሩ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውጤትን ማዕከል ያደረገ የአፈፃፀም ኮንትራት ስምምነት ትናንት ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርሟል።

ሥራዎቻቸውም በዚሁ ኮንትራት መሰረት እንደሚለካ የገለጹት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደፊት ለዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው በጀት፣ የሥራ አፈፃፀማቸውን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

በተለይም ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና ፋይዳቸው የጎላ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ለማውጣት ጥራት ላይ መስራት ግዴታ መሆኑ በስምምነቱ ተካቷል ብለዋል።

ስምምነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትክክለኛ መንገድ የሚሰሩና ተጠያቂነት ያለባቸው እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይም ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑንም አንስተዋል።

መረጃ 24 ሰአት

26 Dec, 05:53


#NewAlert

አንጋፋው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በመንግስት መታገዱን ዋዜማ ሰምታለች።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ኢሰመጉን ያገደው፣ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል በማለት ነው።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ የቆየው ኢሰመጉ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል።

ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም። [ዋዜማ]

መረጃ 24 ሰአት

25 Dec, 06:37


"..እኛ የጠየቅነው የዩኒፎርማችንን ተመሳሳይ ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንድንማር ነው። ነገር ግን ፀጉራቹሁ ካልታዬ መማር አትችሉም ተባልን" - የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች

በትግራይ ክልል የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃባቸው ምክንያት ትምህርት አቋርጠው ያለመፍትሔ መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

"እኛ ከትምህርት ቤቶቹ ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሀይማኖታችን በሚያዘው መሰረት ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንማር ብለን ነው የጠየቅነው የሚሉት ተማሪዎቹ ነገር ግን ፀጉራቹሁ ካልታየ መማር አትችሉም ተብለን ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለናል" ብለዋል።

የ12ኛ ክፍለ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻ ቀን ነገ ረቡዕ እንደሆነ የገለፁት ተማሪዎች "ሂጃብ ካላወለቃችሁ" በመባሉ ምክንያት አንድም ሙስሊም ተማሪ ፎርሙን አለመሙላቱን ተናግረዋል።

የከተማዋ መጅሊስ በዛሬው ዕለት ከወረዳው የፀጥታ ሀላፊዎች እና ከክልሉ የፀጥታ ቢሮ ተወካዮች ጋር "በከተማዋ አድማ እንዲቀሰቀስ አድርጋችኋል" በሚል ስብሰባ መቀመጣቸውን የተናገሩ ሲሆን "ይህ አድማ አይደለም፣ ሀይማኖታዊ መብታቸውን ነው የጠየቁት" የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ ትምህርት አቋርጠው የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በመጣ ቁጥር በተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

via_ሀሩን ሚዲያ

መረጃ 24 ሰአት

25 Dec, 06:32


ሆሳዕና

ትናንት ሌሊት 8:00 በሆሳዕና ከተማ ለጊዜው መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 15 የንግድ ድርጅቶች እና 2 መኖሪያ ቤቶች ከሙሉ ንብረታቸው ጋር መውደሙን የሀዲያ ፖሊስ መምሪያ ፖሊስ አስታውቋል።ምርመራው እንደተጠናቀቀ ይፋ እንደሚሆን ፖሊስ ጠቁሟል።

መረጃ 24 ሰአት

09 Dec, 07:39


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው የሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ህዳር 30/2017 ዓ/ም ያበቃል።

ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ቀደም ብሎ የተሰጠው ገደብ ጥምቅት 30 የነበረ ቢሆንም ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች ተብሎ እስከ ህዳር 30 ተራዝሞ ነበር።

ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ የጊዜ ገደብ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጾ ነበር። ቀኑ ዛሬ ሰኞ ያበቃል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ ይታወሳል።

የቤት ባለቤቶች ቢፈልጉ ቤታችሁን አድሰው ማከራየት መብታቸው እንደሆነ፤ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ አድሰው እራሳቸው መግባት መብታቸው እንደሆነ፣ #ማከራት እንደሚችሉም ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ሊኖርበት እንደሚገባ ማብራራቱ ይታወሳል።

መረጃ 24 ሰአት

08 Dec, 10:24


ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚፎካከሩት ሦስት ዕጩዎች የምርጫ ክርክር ሊያደርጉ ነው።

ዓለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚፎካከሩት ሦስት ዕጩዎች በቀጣዩ ሳምንት ታኅሳስ 4 በኅብረቱ አዳራሽ የምርጫ ክርክር እንደሚያደርጉ ኅብረቱ አስታውቋል።

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትርና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዱንጋ፣ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሞሐሙድ ዓሊ የሱፍ እና የማዳጋስካሩ የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ ናቸው የምረጡን ክርክር የሚያደርጉት።

እጩዎቹ ቀደም ሲል ወደየአባል ሃገራቱ እየዞሩ ድምፅ የማሰባስብ ተግባር እንደጀመሩ የሚታወቅ ነው።

የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ፤ የሥልጣን ጊዜያቸውን በመጭው ጥር ወር በሚያጠናቅቁት ሙሳ ፋኪ ምትክ ቀጣዩን የኮሚሽኑን ሊቀመንበር የሚመርጠው በየካቲት ወር እንደሆነ ይታወቃል።

መረጃ 24 ሰአት

08 Dec, 10:20


ቢሾፍቱ በሚገኘው ጋፋት የመሳርያ ማምረቻ ኢንደስትሪ ውስጥ የሶስት ሰዎች ህይወት የቀጠፈ ፍንዳታ ተከሰተ

መሰረት ሚድያ ከውስጥ ምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት አደጋው የደረሰው ባሳለፍነው ማክሰኞ ህዳር 24/2017 ዓ/ም ነበር።

ቢሾፍቱ በሚገኘው ጋፋት የመሳርያ ማምረቻ (አርማመንት) የስፔስ ሳይንስ ክፍል ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች እና መከላከያ በአንድ ተወንጫፊ ሮኬት ላይ ምርምር እያረጉ በነበሩበት ወቅት ሮኬቱ ፈንድቶ የሶስት ሰው ህይወት ወዲያው መቅጠፉ ታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሌላ ባልደረባቸው እግሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የህክምና ክትትል እያረገ መሆኑ ታውቋል፣ ፍንዳታው በማምረቻው ላይም ጉዳት አድርሷል ተብሏል።

እስካሁን በጉዳዩ ዙርያ የፖሊስ ምርመራ እንዳልተጀመረ የታወቀ ሲሆን ጉዳዩም ወደ ሚድያ ሳይወጣ እንደቀረ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ( meseret media)

መረጃ 24 ሰአት

07 Dec, 22:03


የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የተደራጀ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያዎች ለማስጀመርና የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች ለማካሄድ የሚያስችሉትን ኹለት ፍቃዶች ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማግኘቱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኹለቱ ፍቃዶቹ፣ እንደ የአክሲዮን የዕዳ ሰነድና በጠረጴዛ ዙሪያ ያሉ የገበያ ዓይነቶችን ጨምሮ የተለያዩ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ አውጪዎች ባለሃብቶችን ፍላጎት ባማከለ መልኩ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያዎች አገልግሎቶችን እንዲያቀርብ እንደሚያስችሉት ኩባንያው ገልጧል።

ኩባንያው፣ ቀደም ሲል ግብይት ለመጀመር የሚያስችለውን ከበቂ በላይ የኾነ መነሻ ካፒታል ያሰባሰበ ሲኾን፣ የስጋት አስተዳደር፣ የሕግ ተገዢነትና የቁጥጥር ሥርዓት መመሪያዎችንም ማውጣቱ ይታወሳል።

የመንግሥትና የግል ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች በሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው አማካኝነት የድርሻና የብድር ሰነዶችን በመሸጥ ካፒታል እንዲሰበስቡ ወይም ድርሻዎችን እንዲገዙ የሚያስችለውን "የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች፣ የተዛማጅ ውሎችና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች የፍቃድ አሰጣጥ፣ የአሠራርና የቁጥጥር መመሪያ በሥራ ላይ ያዋለው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ነበር።

መረጃ 24 ሰአት

07 Dec, 16:50


ልጅ ገድላለች ብለው የቤት ሰራተኛቸውን ተጠያቂ ያደርጉ ግለሰቦች የህፃኗ ገዳይ ሆነው ተገኙ!!

የግድያ ወንጀል እንደፈፀመች አምና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረች የቤት ሰራተኛ ላይ በተደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀሉ ተጠርጣሪ አሰሪዋ ሆና እንደተገኘች የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፤ ምርመራው ቀጥሏል፡፡

ህፃን ሰላማዊት አስፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐድያ ዞን ነው ።

በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የአጎቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሴ ለህፃኗ ወላጆቿ እያስተማረች ልታሳድጋት ቃል በመግባት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኖሪያ ቤቷ ይዛት በመምጣት መኖር ትጀምራለች፡፡

መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ሲሆን ለግዜው የፀቡ መነሻ ባልታወቀ ምክንያት ህፃን ሰላማዊት አስፋው ህይወቷ ያልፋል፡፡

ህፃኗን እያስተማረች ልታሳድጋት ያመጣቻች ተጠርጣሪ ታዳጊዋን የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በእንጨት በመደብደብ ከ20 ቦታ በላይ ጉዳት በማድረስ እና አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በህፃኗ ህልፈተ-ህይወት ተጠያቂ ላለመሆን ያሰቡት ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከባለቤቷ ጋር በመነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኝ የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት ተስፋነሽ ጀባኔን ህፃኗን በድንገት እንደገደለቻት ለፖሊስ ቃል እንድትሰጥና ለውለታዋም ደሞዟን በእጥፍ እንደሚጨምሩላት በተለያዩ መደለያዎች በማሳመን߹ በወንጀሉም ጉዳይ ጠበቃ እንደሚቀጥሩላት ካሳመኗት በኋላ ለፖሊስ በሰጠችው ቃል የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመች የሚገልፅ ነበር፡፡

ሆኖም ፖሊስ የተስፋነሽ ጀባኔን ቃል መነሻ በማድረግ የምርመራ ስራውን በማስፋት ሂደት ለጊዜው ተጠርጣሪ የሆነችው የቤት ሰራተኛ እኔ ነኝ የገደልኳት ብትልም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች መኖራቸውን የደረሰበት ፖሊስ ባደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀል ድርጊቱን የቤት ሰራተኛዋ እንዳልፈፀመች እና ልታሳድግ እና ልታስተምራት ባመጣቻት ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ ህፃን ሰላማዊት አሰፋ ህይወቷ እንዳለፈ ይደርስበታል።

የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ተጠርጣሪዋ ግለሰብም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሟን አምና በመኖሪያ ቤቷ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመች መርታ ማሳየቷን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪ ግለሰቧና ባለቤቷ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ፍ/ቤቱ እንዳዘዘ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደማይኖር ያስታወቀው ፖሊስ ንዴትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የወንጀል ድርጊትን መከላከል እንደሚቻል አስታውቆ ከቅድመ መከላከሉ ባሻገር ወንጀል ሲፈፀም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

Via_አ.አ ፖሊስ

መረጃ 24 ሰአት

07 Dec, 15:51


በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

[ዳጉ ጆርናል]

መረጃ 24 ሰአት

07 Dec, 11:49


የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቲክ ቶክ እንዲሸጥ የሚያስገድድ ውሳኔ አሳለፈ!!

የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በቻይና መንግስት ቁጥጥር ሥር እንደሆነ የሚነገረውን የቲክ ቶክ መተግበሪያ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ እንዲሸጥ ወይም እገዳ እንዲጣልበት የሚያስገድድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ውሳኔው ለአሜሪካ የፍትህ ዲፓርትመንት ትልቅ ድል እንደሆነ እና ለመተግበሪያው ባለቤት ባይት ዳንስ ኩባንያ ከባድ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑ ተጠቅሷል።

የባይት ዳንስ ኩባንያ ንብረት የሆነው እና በአሜሪካ 170 ሚሊዮን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክ ቶክ የዜጎችን ግላዊ መረጃዎች ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል ለቀረበበት ክስ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ እንደተደረገበት ነው የተገለፀው፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ የቻይና መንግስት ቲክ ቶክን በመሳርያነት እንዳይጠቀም ለማድረግ ወሳኝ እርምጃ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በአሜሪካ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በበኩሉ፤ ውሳኔው በግልፅ የተካሄደ የንግድ ዘረፋ መሆኑን ገልፆ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን መተማመንና ግንኙነት እንዳይጎዳ አሜሪካ ጉዳዩን በጥንቃቄ መያዝ እንዳለባት አስጠንቅቋል።

በውሳኔው መሰረት ቲክ ቶክ ለአሜሪካ ኩባንያዎች ከመሸጥ ይልቅ መታገድን የሚመርጥ ከሆነ በሚቀጥሉት 6 ሳምንታት ውስጥ በአሜሪካ መስራት ሊያቆም እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በአሜሪካ የፍትህ ዲፓርትመንት የተረታው የባይት ዳንስ ኩባንያ ውሳኔውን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ማቀዱን የዘገበው ሮይተርስ ነው።

መረጃ 24 ሰአት

06 Dec, 18:45


ሼኽ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ፣ አብነት ገብረ መስቀል በፍርድ ቤት የተወሰነባቸውን ከ852 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈል ካልቻሉ፣ በናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኩባንያ ውስጥ ያላቸው የ15 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ተሽጦ እንዲከፈላቸው ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስገቡት ማመልከቻ መጠየቃቸውን ዋዜማ ተረድታለች።

ከኅዳር 27፣ 2014 ዓ፣ም እስከ ኅዳር 12፣ 2017 ዓ፣ም የተሰላውና አብነት እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው የ9 በመቶ ሕጋዊ ወለድ ደሞ፣ 226 ሚሊዮን 968 ሺሕ ብር ነው።

ሼክ አል-አሙዲ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ስለመባሉ እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ በላኩት ማመልከቻ ላይ ጠቅሰዋል። ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 5 የሰጠውን ውሳኔ አብነት የማይፈጽሙበት ምክንያት ካለ፣ ታኅሳስ 18 ቀርበው እንዲያስረዱ ታዘዋል።

ገዥው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከአብነትና ከሚድሮክ ኩባንያ አመራሮች ከፍተኛ የገንዘብ ሥጦታ የተቀበሉት የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት አል-አሙዲን ይመለስልኝ ያሉትን ገንዘብ መቀበላቸውን አምነው፣ ገንዘቡን የተቀበሉባቸውን የባንክ ደረሰኞች ፍርድ ቤቱ ላዘጋጀው ገለልተኛ ኦዲተር ማረጋገጣቸውን ዋዜማ የተመለከተቻቸው የተቋማቱ ደብዳቤዎች አረጋግጠዋል።

መረጃ 24 ሰአት

06 Dec, 09:28


የደቡብ ኮሪያ ገዢው ፓርቲ መሪ የፕሬዝዳንት ዮን ስልጣን እንዲታገድ ጠየቀ

የደቡብ ኮሪያ ገዥ ፓርቲ መሪ የፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል ስልጣን በፍጥነት እንዲታገድ የጠየቁ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ የማርሻል ህግን ማወጃቸውን ተከትሎ የፖለቲካ መሪዎችን ለማሰር እንደፈለጉ "ተአማኒ ማስረጃ" አለ ብለዋል።

ቀደም ሲል ዮንን ለመክሰስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወሙ የገለፁት የፒፕል ፓወር ፓርቲ መሪ ሃን ዶንግ-ሁን “አዲስ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ግን በፕሬዚዳንቱ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን እያሳዩ ይገኛል። ፕሬዚዳንቱ የመከላከያ ኢንተለጀንስ አዛዥ ዋና ዋና የፖለቲካ መሪዎችን እንዲይዝ ፀረ-መንግስት ሃይሎች እንደሆኑ በመግለጽ እና የስለላ ተቋማትን በሂደቱ እንዲያንቀሳቅስ እንዳዘዙ ተረድቻለሁ ሲሉ ሃን ተናግረዋል። ሃን አክለውም “ይህች አገር ወደ ሌላ ትርምስ እንዳትገባ ለመከላከል፣ የክስ መቃወሚያ ሂደት እንዳይቋሩጥ ለማድረግ እሞክራለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ደቡብ ኮሪያን እና ህዝቦቻችንን ለመጠበቅ ፕሬዝዳንት ዩን እንደ ፕሬዝደንት ስልጣናቸውን በፍጥነት እንዳይጠቀሙ ማስቆም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ ብለዋል።

ሃን ፕሬዝዳንት ዩን የማርሻል ህግ መግለጫው ህገወጥ እና ስህተት መሆኑን አምነው መቀበል አልቻሉም ሲሉ አክለዋል። በስልጣን ላይ ከዚህ በላይ ከቆዩ እንደገና ተመሳሳይ ጽንፍ ያለው እርምጃ ሊወስዲ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት አለኝ ሲሉ አክለዋል።ደቡብ ኮሪያ ማክሰኞ ምሽት ላይ ለስድስት ሰአታት ያህል በማርሻል ወይም ወታደራዊ ህግ ስር ወድቃ የነበረች ሲሆን ፕሬዝዳንት ዮን እርምጃው መተግበሩን ለህዝቡ ያሳወቁት በድንገተኛ በቴሌቭዥን ላይ ቀርበው ነው።ለእርምጃው ምክንያት ሲሉ የገለፁት ከ"ፀረ-መንግስት ኃይሎች እና ከሰሜን ኮሪያ ደጋፊዎች የሚሰነዘሩ ዛቻዎችን ጠቅሰዋል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ የዩኑን ትዕዛዝ በ190 ተቃውሞ ያለ አንዳች ድጋፉ በፍጥነት ውሳኔው እንዲሻር አድርገዋል።

ዩን በአሁኑ ወቅት ከስልጣን ከተነሱት የመከላከያ ሚኒስትር ኪም ዮንግ-ህዩን ፣የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ፓርክ አንሱ እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሊ ሳንግ ሚን ጋር በመሆን በሀገር ክህደት ወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የፍትህ ሚኒስትር የሆኑት እና በገዢው ፒ.ፒ.ፒ. ውስጥ የፕሬዝዳንት ዮን ከፍተኛ ተቀናቃኝ አንዱ የሆኑት ሃን ተቃውሞ ገዥው ፓርቲ ለችግሩ የሚሰጠውን ወሳኝ ምላሽ ለውጥ ያሳያል ተብሏል። ተቃዋሚው ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዮንን ለመክሰስ ቅዳሜ ምሽት ድምጽ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ነገር ግን 300 አባላት ባለው የብሄራዊ ምክር ቤት ውስጥ አስፈላጊውን ሁለት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ከገዥው ፓርቲ ቢያንስ ስምንት ድምጽ ያስፈልገዋል።አቤቱታው ከተሳካ፣የደቡብ ኮሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዮንን ከስልጣን እንዲወገዱ ውሳኔ ይሰጣል።እ.ኤ.አ. በ2016 የቀድሞ ፕሬዚደንት ፓርክ ጊዩን ሃይ ከስልጣን መነሳቷን ተከትሎ እንደተከሰችው አሁን ላይ ገዢው ፒፒፒ ፓርቲ የዮንን መከሰስ እንደሚቃወም አንዳንድ ተንታኞች ጠቁመዋል።ፓርክ ባምህረት ከመለቀቋ በፊት በሙስና ወንጀል የ20 አመት እስራት ተፈርዶባት እንደነበር ይታወሳል።ዩን ሳይጨምር፣ በ1980ዎቹ መገባደጃ ላይ ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ ከተሸጋገረችበት ጊዜ አንስቶ ከነበሩት ሰባት ፕሬዚዳንቶች አራቱ በሙስና ተከሰው ወይም በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል።

መረጃ 24 ሰአት

06 Dec, 08:14


እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅማለች በሚል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያቀረበውን ሪፖርት ፍፁም ውሸት ስትል ውድቅ አደረገችው

ፍልስጤማውያንን ከሰው በታች አድርጋለች - አምነስቲ

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመብት ቡድኑን "አሳዛኝ እና አክራሪ ድርጅት" በማለት መግለጫ አውጥቷል፤ በድጋሚ አምነስቲ የፈጠራ ዘገባ በማዘጋጀት እስራኤልን ለማጠልሸት ሞክሯል ሲል ኮንኗል።

የአምነስቲ ዘገባ፣ እንደተመለከትነው፣ እ.ኤ.አ. በ1948 በተደረሰው የዘር ማጥፋት ስምምነት ከተከለከሉት አምስት ድርጊቶች ውስጥ ቢያንስ ሦስቱን የእስራኤል ወታደሮች ፈፅመዋል። እስራኤል የፍልስጤማውያንን የእርዳታ አቅርቦትን በመዝጋት እና በዘፈቀደ እስራት ስትፈጽም ፍልስጤማውያንን ከሰው በታች አድርጋ እያስተናገደች ነው ብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የእስራኤል ቅርንጫፍም ግን የሪፖርቱ ግኝቶችን "አስቀድሞ የተወሰነ" በማለት ሪፖርቱን አልተቀበለም። ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ጋዜጣ ባወጣው መግለጫ አምነስቲ እስራኤል በጋዛ የፈጸመችው ግድያ እና ውድመት መጠን እጅግ አሰቃቂ ደረጃ ላይ መድረሱን አምኗል” ነገር ግን የሪፖርቱን ግኝቶች ላይ ጥያቄ አቅርቧል።

የእስራኤል ድርጊት “የዘር ማጥፋት ወንጀልን መከላከል እና መቅጣት ስምምነት ላይ በተደነገገው መሠረት የዘር ማጥፋትን ፍቺ ያሟላል” የሚል እምነት እንደሌለው አሳውቋል።ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ለስድት ወራት ያካሄደውን ምርመራ አጠናቆ ሀሙስ እለይ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።ግኝቱ "ሰብአዊነትን በሚያጠለሹና የዘር ፍጅትን በሚቀሰቅሱ የእስራኤል መንግስት እና ወታደራዊ አመራሮች ንግግሮች" እንዲሁም የጋዛን ውድመት በሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎችና ከጋዛ በተላለፉ ዘገባዎች ላይ የተመሰረት መሆኑን አምነስቲ ገልጿል።ዮ

ሆን ተብሎ በጅምላ የሚፈጸም ግድያ፣ የአካል እና አዕምሮ ጉዳት ማስከተል እና ጥበቃ በሚያስፈልገው ቡድን ላይ የተቀነባበረ ውድመት ማድረስ በሚሉት ጥፋተኛ ሆና መገኘቱን ሪፖርቱ አመላክቷል።በዚህም እስራኤል በጋዛ የዘር ጭፍጨፋ መፈጸሟን ከድምዳሜ ደርሰናል ያሉት የአምነስቲ ዋና ሃላፊ አንጌስ ካላማርድ፥ የድርጅቱ ድምዳሜ "በቀላል መረጃ የተሰመሰረተና ፖለቲካዊ አላማ" የሌለው መሆኑን አብራርተዋል።እስራኤል በጋዛ ወታደራዊ ግብ እንዳላት እሙን ነው ያሉት ካላማርድ፥ ወታደራዊ ግቡ ግን የዘር ማጥፋት ፍላጎት አለመኖሩን ሊያሳይ አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።በሌላ በኩል የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ጊቪር የእስራኤል ምርኮኞች እስኪፈቱ ድረስ እስራኤል የነዳጅ አቅርቦቶችን ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ማቆም አለባት ብለዋል።

ነዳጅ ለጥቂት ወራት ማቆም አለብን፣ ያንን ስናደር በጉልበታቸው ተንበርክከው ‘ታጋቾቹን ይዛችሁ ሂዱና ነዳጅ አምጡ’ እንደሚሉ አምናለሁ” ማለታቸውን የእስራኤል ጦር ሬዲዮ ተናግሯል። የቀኝ አክራሪው ብሔር ተወላጆች ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዳይገባ ሲጠቁም ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቀጠለው ጦርነት እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገቡትን የነዳጅ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ገድባለች፣ በዚህም የዳቦ መጋገሪያዎች፣ ሆስፒታሎች ሥራቸውን እንዲያቆሙ አድርጓል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል ተጨማሪ ነዳጅ እና ሌሎች እርዳታዎች ወደ ቀጠናው እንዲገባ ደጋግመው አሳስበዋል።

መረጃ 24 ሰአት

06 Dec, 04:52


በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አለመግባባት ምክንያት #የመቀለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ታሽገ!

በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ከንቲባ የተሾመላት የትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀለ፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤቷ መታሸጉ ተገለጸ።በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነትና መከፋፈል እየተባባሰ በመምጣቱ፣ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ላለፉት ሦስት ቀናት "ታሽጓል" የሚል ጽሑፍ እንደተለጠፈበት ተጠቁሟል።

ሁለቱም ቡድኖች "የየራሳቸው ከንቲባ ሾመዋል" በሚል እርስ በእርስ እየተወቃቀሱ ሲሆን ሁለቱም ለከተማዋ ከንቲባ ሾመዋል።በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ዶ/ር ረዳኢ በርኸን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ያሾመ ሲሆን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንተ አቶ ጌታቸው ደግሞ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም አቶ ብርሃነ ገ/እየሱስን ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

ከህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋ የከንቲባ ጽሕፈት ቤቷ መታሸጉን መመልከቱን ቪኦኤ በዘገባው አስታውቋል፣ ሌሎች የከተማዋ አስተዳደር ቢሮዎች ግን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቁሟል።በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለው ልዩነት እየተካረረ ከመምጣቱ ባለፈ እውቅና እስከመነፋፈግ ደርሰዋል።

“ከፕሪቶሪያ ስምምነት አግባብ ውጭ በሆነ መንገድ ጊዚያዊ መስተዳድሩ በግለሰቦች እጅ ወድቋል” ሲሉ በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በሌላ በኩል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በክልሉ ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር እየሰራ ነው ባለው የእነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) “የህወሓት ቡድን ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ” ማስጠንቀቁን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችንም ይታወሳል።

Via Addis Standard

መረጃ 24 ሰአት

05 Dec, 19:31


❗️ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ፣ ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ!

በዛሬው እለት በትግራይ ክልል ያለውን አጠቃላይ የፓለቲካ የአስተዳደር እና የፀጥታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ በክልሉ ያሉ የፓለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ከፌደራል መንግስት አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም ላይ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ምክክር ተደርጓል። በተደረገው ምክክርና ውይይት በተለያዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራት እና የክልሉ ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተለይም ከመኖርያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ፣ ታጣቂዎች ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ሂደትን በትኩረት የሚሰራበት እና የሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ተደርሷል።

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ህጋዊ በሆነ አግባብ የህዝብን እና የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግስት አገልግሎቶች የሚሻሻሉበት እና የህዝብን ፍላጎት የሚመጥኑ እንዲሆኑ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ ተገቢው አቅጣጫ በውይይቱ ተለይቷል።

በመጨረሻም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ክልላዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ያለበትን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተገባዷል።

መረጃ 24 ሰአት

04 Dec, 09:56


ከንቲባዋ ይቅርታ ጠየቁ‼️

የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ በጥራት እና በፍጥነት ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የተገኙ ልምዶችን ቀምረን የጀመርነው 2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች አገልግሎት ክፍት ማድረግ በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት፣ ከኮንትራክተሮች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተወያይተናል።

በውይይታችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከመጀመሪያ ዙር አንጻር ሰፊ እና የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትብብር፣  በተያዘለት ጊዜ፣  በጥራት እና ስታንዳርዱን ጠብቀው  እንዲያጠናቅቁ ተግባብተናል።

በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላታችሁ የከተማችን ነዎሪዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ እንደምንክሳችሁ ቃል ለመግባት እወዳለሁ።

መረጃ 24 ሰአት

02 Dec, 18:40


የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡

የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው፤ 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል፡፡

የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት፤ በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም ሲል አል-ዐይን ዘግቧል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

02 Dec, 18:02


አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑን ባለቤታቸው ሲንትያ አለማየሁ  ተናገሩ።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔውን ያሳለፈው ሰኞ፣ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም በነበረው ችሎት ነው።

ሰበር ሰሚ ችሎት የአቶ ታዬ ደንደአን ዋስትና የፈቀደው የሥር ፍርድ ቤቶች የዋስ ጥያቄያቸው ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው።

ፍርድ ቤቱ አቶ ታዬ ደንደአ በ20ሺህ ብር የዋስትና ገንዘብ በማስያዝ ወይም በዋስ እንዲፈቱ ብያኔ ማሳለፉን ባለቤታቸው ለቢቢሲ ዘጋቢ ገልጸዋል።

አቶ ታዬ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አስፈላጊውን እንዲያሟሉ መጠየቃቸውን ጨምረው ባለቤታቸው ተናግረዋል።

መረጃ 24 ሰአት

02 Dec, 15:55


አዲስ አበባ ከተማ በኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት በአንደኛነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ተባለ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የነበረዉን የኤችይቪ ኤድስ ስርጭት ወደ 0.8 በመቶ መቀነስ እንደተቻለ ቢነገርም ኤች አይቪ/ኤድስ ዛሬም ቢሆን የማህበረሰቡ የጤና ችግር መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ያደታ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የበሽታዉ የስርጭት ምጣኔ ከክልል ክልል ይለያያል።አያይዘውም  በ6 ክልሎች ከአጠቃላዩ ሀገራዊ የስርጭት ምጣኔ በላይ ከፍ ብሎ እንደሚታይ ገልፀዉ  በአሁኑ ወቅት የበሽታዉ ስርጭት ምጣኔ በአዲስ አበባ 3.25 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም  በጋምቤላ ክልል 3.24 በመቶ ፣ በሐረሪ 2.76 በመቶ፣ በድሬዳዋ 2.35 በመቶ፣በትግራይ 1.2 በመቶ እንዲሁም በአማራ ክልል 1.1 በመቶ  ከአጠቃላዩ አገራዊ የስርጭት ምጣኔ በላይ ከፍ ብሎ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ዝቅተኛው የቫይረሱ የስርጭት መጠን የታየው በሶማሌ ክልል  እንደሆነ ተገልጻል።የበሽታዉ ስርጭት ከቦታ ቦታ እንደሚለያይ ያነሱት አቶ ፍቃዱ በከተማ 2.9 በመቶ እንዲሁም በገጠር 0.4 በመቶ ልዩነት እንዳለዉ አቶ ፍቃዱ ጨምረዉ ለጣቢያችን ገልጸዋል።

የቫይረሱ ስርጭት በአዲስ አበባ ላይ ከፍ ሊል የቻለበት ምክንያትን አስመልክቶ በቂ ጥናት ባይደረግም  የከተማ ፍልሰት መኖር እንዲሁም ፣ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ለበሽታዉ ሊጋለጡ የሚችሉበት እድል መኖሩ ሁኔታዉን ካባባሱት መካከል ተጠቃሽ ናቸዉ ተብሏል ።ቀደም ሲል በወሲብ ንግድ ሰራተኞች እና ሀገር አቋራጭ ሹሬሮች ላይ የበሽታዉ ስርጭት ጎልቶ ይታይ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ላይ ግን አፍላ ወጣቶችንና ወጣት ሴቶችን  በተለየ ሁኔታ ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል ነዉ የተባለዉ።

በእነዚህና መሰል መንስኤዎች የተነሳ ከጋምቤላ ክልል በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ የነበረችዉ አዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ በሆነ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ምጣኔ የአንደኛነት ደረጃን ልትይዝ ችላለች። ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት የማህበረሰቡን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ፕሮግራሞች በተለያዩ መልኩ ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ቫይረሱ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒትን በአግባቡ መዉሰድ እንዲችሉ እና በውስጣቸዉ ያለዉ የቫይረስ መጠን ልኬት ዝቅተኛ እንዲሆን የሚያስችሉ የመከላከል ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።

መረጃ 24 ሰአት

02 Dec, 08:20


በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት "ህወሓት ፤ ኤርትራ ውስጥ ከ70 በላይ ዒላማዎችን በረዥም ርቀት ሮኬት መትቷል” ሲሉ የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሰሱ

ፕሬዚዳንቱ “ኤርትራ በፍፁም ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ውስጥ ገብታ የማየት ፍላጎት የላትም” ብለዋል

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቅዳሜ ምሽት በመንግሥታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ስለወቅታዊ ጉዳዮች ቃለ-ምልልስ ሰጥተዋል።

ፕሬዝደንቱ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና ሀገራቸው ኤርትራ ስለገቡት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ እንዲሁም ስለአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ስላለው ጉዳይ እና ስለህወሓት

ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ሁልጊዜው “አሁን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት አለመስማማት የመነጨው በአውሮፓውያኑ 1994 ተግባራዊ በሆነው ሕገ-መንግሥት ነው” ብለዋል።

“[ሕገ-መንግሥቱ] ለውጥረት መንስዔ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ግንባታን የሚያስፋፋ አይደለም። ኢትዮጵያ ከራሷ ጋር ሰላም ካልፈጠረች ቀጣናው ለሚያስፈልገው መረጋጋት፣ ትብብር እና መቻቻል አዎንታዊ አስተዋፅዖ አይኖራትም” ሲሉ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ተናግረዋል።

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እንዲሁም ለ20 ዓመታት ያክል በባድመ ምክንያት በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰፍኖ የቆየው ውጥረት “የዚህ ፖሊሲ ውጤት ነው” ብለዋል። አክለው በሁለቱ ሀገራት መካከል ለነበረው የድንበር ግጭት የውጭ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዝደንቱ በቀጣናው እንዲሁም በመላው የአፍሪካ ቀንድ ግጭት እያስፋፉ ነው ያሏቸው የውጭ ኃይሎችን ማንነት በስም አልጠቀሱም።

ኢሳያስ በኢትዮጵያ አዲስ አስተዳደር [የዐቢይ አሕመድ መንግሥት] ከመጣ በኋላ “የተቀሰቀሰውም ጦርነት በዚህ አግባብ ሊታይ ይገባል” ብለዋል።

“ህወሓት በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ አልቀበልም ብሎ ጦርነት ውስጥ በመግባት ኤርትራ ውስጥ ከ70 በላይ ዒላማዎችን በረዥም ርቀት ሮኬት መትቷል” ሲሉ የከሰሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የኤርትራ መንግሥት ህወሓት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ያቀረበው ጥሪ ሰሚ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላም በአማራ ክልል ግጭት መከሰቱን ያነሱት ፕሬዝደንቱ መንግሥታቸው ላይ የሚነሳውን ወቀሳ እንደማይቀበሉት እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ከመግባት ሁሌም እንደሚቆጠቡ አሳውቀዋል።

በጠቅላላው የመንግሥታቸው ዓላማ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን መሆኑን ተናግረው የውጭ ኃይሎች ጣልቃ እንዲገቡ ክፍተት ላለመፈጠር እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ውስጥ ሠራዊታቸው የኢትዮጵያ መንግሥትን ደግፎ መሳተፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ጦርነቱን ካስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ግን በሁለቱ መንግሥታት መካከል የነበረው ግንኙነት መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል።

በተለይ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ መተላለፊያ እንዲሁም ሚና እንዲኖራት ያላትን ፍላጎት ይፋ ካደረገች በኋላ በቀጥታም ባይሆን ኤርትራ ደስተኛ አለመሆኗን ስታሳይ ነበር። በዚህም የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኤርትራ ከሦስት ጊዜ በላይ ጉብኝት አድርገዋል።

በተጨማሪም ሶማሊያ ከግብፅ ጋር የወታደራዊ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ አሥመራ ላይ የተፈረመው የሶስትዮሽ ስምምነት ከኢትዮጵያ አንጻር መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል። ነገር ግን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ይህንን አስተባብለዋል።

ፕሬዝደንት ኢሳያስ “የውጭ ኃይሎች እና አቀንቃኞች በመገናኛ ብዙኃን እና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያሠራጩት የተዛባ መረጃ እና ዘመቻ በቀጣናው ግጭት ያባብሳል” ሲሉ ኮንነዋል።

“ይህ [በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚሠራጨው] የመነጨው ከልብ ለኢትየጵያ ከማሰብ አይደለም” ያሉት ፕሬዝደንቱ በሦስቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት “ዋና ዓላማው በቀጣናው መረጋጋትን ማስፈን” እንደሆነ ተናግረዋል።

የኤርትራ ዋና ፍላጎት “በመላው የአፍሪካ ቀንድ፣ በአባይ ተፋሰስ እና በቀይ ባሕር አጎራባች ሀገራት መረጋጋት እና ትብብር እንዲኖር ነው” ብለዋል ፕሬዝደንቱ።

“ኤርትራ በፍፁም ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ውስጥ ገብታ የማየት ፍላጎት የላትም” ያሉት ኢሳያስ፣ በቀጣናው ሀገራት መካከል የሚደረሱ ስምምነቶች ያለመተማመንን እንዲሚቀርፉ እና ፍሬያማ እንደሆኑ አስምረዋል። (BBC )

መረጃ 24 ሰአት

02 Dec, 08:20


ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለልጃቸው ሀንተር ስልጣናቸውን ተጠቅመው ይቅርታ እንደማያዱርጉ ቢናገሩም ቃላቸውን ሻሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ምህረትን ላለማድረግ ቃል ቢገቡም በፍርድ ቤት በጦር መሳሪያ እና በታክስ ጥፋተኛነት በተፈረደበት በልጃቸው ሀንተር ላይ ይቅርታ አድርገዋል። ባይደን እሁድ እለት እንደተናገሩት ልጄ በቤተሰቡ ግዙፍ ስም ምክንያት “ተለይቷል” እናም "ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ” ተከሷል ሲሉ ተደምጠዋል።ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ ሀንተርን ለመስበር ጥረት ተደርጓል ፤ ለአምስት ዓመት ተኩል በማያቋረጡ ጥቃቶች እና በተመረጡ ክሶች ውስጥ እንዲያልፍ ተደርጓል ብለዋል።

ሀንተርን ለመስበር ሲሞክሩ እኔን ለመስበር ሞክረዋል ፤ እናም እዚህ ጋር ያበቃል ብለን የምናምንበት ምንም ምክንያት የለም ግን በቃ ማለት አለብን ሲሉ ባይደን መናገራቸውን የዋይት ሀውስ መግለጫ አመላክቷል።

እውነቱ ይሄ ነው ያሉት ባይደን እኔ በፍትህ ስርዓቱ አምናለሁ፣ ነገር ግን ከዚህ ጋር ስታገል፣ ፖለቲካም ይህን ሂደት በመበከሉ እና ፍትህ እንዲጓደል አድርጓል ብዬ አምናለሁ። እናም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ይህን ውሳኔ በመወሰን ከዚህ የበለጠ እንዲዘገይ አልፈቀድኩም ሲሉ ተደምጠዋል።

ሃንተር ባይደን በጠመንጃ ምርመራ ወቅት ስለ አደንዛዥ እፅ አጠቃቀሙ የውሸት መግለጫ በመስጠቱ እና ቢያንስ 1.4 ሚሊዮን ዶላር ግብር ካለመክፈል ጋር በተያያዙ ተከታታይ ወንጀሎች ላይ የቅጣት ውሳኔ ከሳምንታት በፊት እንደተላለፈበት ይታወሳል።ይህ የባይደን ውሳኔ ውዝግብ ፈጥሯል።የተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የበኩር ልጅ የባይደን ይቅርታ የሚጠበቅ እርምጃ ነበር ብሏል። ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር “ሁሉም ሰው ይህንን ባይደን እንደሚያደርገው ያውቅ ነበር "ሲል በኤክስ ገፁ ላይ ያጋራውን መልዕክቱን ኤሎን ማስክ ሪፖስት አድርጓል።

ጆ ባይደን በሰኔ ወር ለልጃቸው ይቅርታ እንደማይደረጉለት ወይም ቅጣቱን እንደማይቀንሱለት ተናግረው ነበር። በልጄ ሀንተር በጣም እኮራለሁ። ሱስን አሸንፏል፤ ከማውቃቸው በጣም ብሩህ እና ጨዋ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። "የዳኞች ውሳኔን አከብራለሁ ፣ ያንንም አደርጋለሁ። እናም የፕሬዝዳንትነቴን ስልጣን ተጠቅሜ ይቅር አልለውም" ሲሉ ባይዳን በጣሊያን የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለጋዜጠኞች ተናግረው ነበር። ፕሬዝዳንቱ የሃንተር ባይደንን ቅጣት ለማቃለል እቅድ እንዳላቸው ሲጠየቁ “አይሆንም” ሲሉ ተናግረው ነበር።

መረጃ 24 ሰአት

28 Nov, 10:53


IMF ለኢትዮጵያ የ251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊያፀድቅ ነው!

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመተግበሯ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት በማድነቅ የ251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊፈቅድ መሆኑን ፎርቹን ዘግቧል።IMF ለኢትዮጵያ በአራት አመታት ውስጥ በተራዘመ ብድር ለመስጠት ከፈቀደው የ3.4 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ሁለተኛውን የ251 ሚሊየን ዶላር ብድር ለመልቀቅ መስማማቱ ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ የ IMF ልዑክ መሪ አልቫሮ ፒሪስ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በጥሩ ሁኔታ መሄዱን ቀጥሏል” ብለዋል።ወደ ወለድ መር የገንዘብ ፖሊሲ በሚደረግ ሽግግር ወቅት የዋጋ ግሽበትን ዝቅተኛ ለማድረግ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲዎች መተግበርን መክረዋል።

በባንክ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን የምንዛሪ ተመን ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት መቀነሱ እንደ ስኬት ተጠቅሷል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ባያውለውም የፋይናንስ ሥርዓት ውህደትንና የሒሳብ አያያዝን ለማሻሻል የአገር ውስጥ ባንኮች የገንዘብ ግብይትን ማስጀመሩ ይታወሳል።የIMF ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ሁለተኛውን ግምገማ ሲያጠናቅቅ ብድር በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚለቀቅ ተጠቅሷል።

መረጃ 24 ሰአት

28 Nov, 07:36


" በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶችን እያሰለጠነ ነው" አማኑኤል አሰፋ

በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ  መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው "ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም" ብለዋል።

አቶ አማኑኤል "የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው" ሲሉ ወንጅለዋል።

" የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመት ያለ እቅድ እየተመራ ይገኛል "  በማለትም ገልፀዋል ።(ቲክቫህ)

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 18:29


ግዙፉ የሩሲያ የኒውክሌር ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት መፈጸሙ ተገለጸ

ግፉ የሩሲያ የኒውክሌር ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በኒውክሌር ሳይንስ ልማት ስምምነት መፈጸሙ ተነግሯል፡፡

ሮሳቶም የተባለው ኩባንያ በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር የኒውክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል የአዋጭነት ጥናት ለማካሄድ ከኢትዮጵያ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት መፈጸሙን የሩሲያው አርቲ አስነብቧል፡፡

ኩባንያው በቅርቡ የኑክሌር እና የጨረር ቴክኖሎጂ ከሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ጋር እንዴት መጣጣም እንደሚችል ለማወቅ የኢትዮጵያን ኢነርጂ ዘርፍ መገምገም እንደሚጀምር የሩስያ አቶሚክ ኢነርጂ ባለስልጣን ያወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

የዚህ ግምገማ ውጤት በኑክሌር ሀይል አቅም ላይ የተመሰረተ ለንግድ ምርቶች እና አገልግሎቶች ገበያ መሰረት በመጣል የቴክኖሎጂዎቹ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ የገበያ እድሎችን ለመለየት ያስችላል ነው የተባለው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የኑክሌር ሀይል አቅምን እንድታሳድግ ሮሳቶም የሚኖረውን ሚና በመግለጽ በስምምነቱ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የሮሳቶም ዋና ዳይሬክተር ኢሊያ ቬርጊዛቭ ኩባንያው በአፍሪካ አህጉር ላይ የኒውክሌር ልማትን ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸው፣ "በአፍሪካ አህጉር ላይ የኒውክሌር እና የጨረር ቴክኖሎጂዎችን ለማዳበር በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና የጋራ መፍትሄዎች ላይ ከአለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር እየሰራን ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዳይሬክተር አናቶሊ ባሽኪን በበኩላቸው በአፍሪካ ያለውን የሀይል ፍላጎት ለማሟላት እንዲሁም እያደጉ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሀይል አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሞስኮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአህጉሪቷ ሌሎች ሀገራት ጋር በቅርበት መስራቷን ትቀጥላለች ነው ያሉት፡፡

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 16:43


ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ500 ሄክታር ላይ የተዘራ የደረሰ ሰብልን አወደመ

በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ኅዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ የጣለው ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሶስት ቀበሌዎች ከ500 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳቱ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ የደረሰ ሲሆን ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል።

አርሶ አደሮቹም በአካባቢው ባሕል መሰረት ሰብላቸውን በደቦ ለመሰብሰብ ነገ ዛሬ በሚሉበት ወቅት ድንገት የጣለው በረዶ ሰብላቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳወደመባቸው ተናግረዋል።

አቶ ራራ ደሴ የተባሉ የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ አርሶ አደር በደረሰው ጉዳት በማዘንና በመደናገጥ በርካታ አርሶ አደሮች ለከፋ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውን አንስተዋል።

"ጉዳቱ ያልተጠበቀ ነው፤ እንኳን እኛ እንስሳቱ ራሱ የሚበሉት ድርቆሽ ሳር አልተረፈም" ሲሉ አርሶ አደሩ ማሬ ታረቀኝ ለአሚኮ ተናግረዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያው ጥላሁን ዓለም ለአሚኮ እንደገለጹት ከ600 በላይ አርሶ አደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ሥራ መሠራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የደረሰው ጉዳት ከባድ በመኾኑ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በመሥራት በበጋ መስኖ ሰብል ልማት ምርቱን እንዲያካክሱ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በዕውቀት አየነው ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አርሶ አደሮችን መልሶ በማቋቋም ሥራው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 16:42


መምህር በመሆኔ አዘንኩ” - የኢትዮጵያ መምህራን እሮሮ

በደቡብ ምዕራብ ክልል ካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ለልማት በሚል መምህራን “ያለፈቃዳቸው” የአንድ ወር ደሞዛቸው ለመዋጮ እንደተቆረጣባቸው ገልጸዋል።

መምህራኑ “ለገጠር መንገድ ግንባታ” ይውላል የተባለ እና በአንድ ዓመት የሚቆረጥ የአንድ ወር ደሞዝ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ “በጅምላ” እና “በማን አለብኝነት” መቆረጡን ይናገራሉ።

“ከ50 በመቶ በላይ [የመንግሥት ሠራተኞች] ደገፉት ስለተባለ በጅምላ ይቆረጣል” ተብሎ መወሰኑን የተናገሩ አንድ የአንደኛ ደረጃ መምህር፤ ፈቃደኝነታቸው እና አቅማቸው ውሳኔው ላይ ሚዛን እንዳልደፋ ተናግረዋል።

“መምህራን የልማት ተቋዳሽ አይደሉም ሳይሆን፤ አቅማችን የማይፈቅደውን አትጠይቁን ነው እያልን ያለው” ሲሉ አንድ መምህር ምሬታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

መዋጮው መምህራን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልሆነ የጠቆሙ ሌላ መምህር አነስተኛ ገቢያችንን እና የኑሮ ጫናን አገናዝቦ “በአቅማችን ይሁን” የሚል ሀሳብ እንዳለ ተናግረዋል።

“የአራት ሺህ ብር ደሞዝተኛ ነኝ። አራት ሺህዋን ብር ከምትወስዱብኝ እባካችሁ 1500 ብር በእጄ ልስጣችሁ [ብዬ] ለመንኩ” ብለዋል የወረዳው ባሺ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር።

“እርዳታ ነው፤ አስተዋጽኦ ነው፤ ለልማት አሻራችሁን አሳርፉ ነው የሚባለው። ሰው በቻለው ነው። . . . የሚችል ነው የሚደግፈው” ሲሉ በአቅማቸው ለማዋጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም የወረዳው አስተዳዳሪዎች ግን “የአንድ ወር ደሞዝ ሙሉ ካልሆነ አይቀበሉም” ብለዋል።

የጥቅምት ወር ደሞዝ የተቆረጠባቸው መምህራን አቤቱታ ለማቅረብ ወደ መንግሥት ተቋማት ሲያቀኑ እንግልት እንደደረሳቸው አንድ መምህር ሲናገገሩ፤ ሌላ መምህር ደግሞ “በፖሊስ ታፍነን ነበር” ብለዋል።

“ሰርቆ እንደሄደ ሰው [በፖሊስ] ታጅበን ነው የሄድነው” ሲሉ አንድ መምህር ክስተቱን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በወረዳው ለሁለት ቀናት ያህል ትምህርት ተቋርጦ እንደነበር የተናገሩት መምህራን፣ ከዞኑ አስተዳደር ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው ስለተነገራቸው ማስተማር መጀመራቸውን ተናግረዋል።

“መምህር በመሆኔ በጣም ነው ተቆጨሁት። መምህር ከወር ደሞዝ ውጪ የሚያገኘው አንዳች ነገር የለም። አዲሱ ክልል ከተመሠረተ ወዲህ እስከ 50 ቀን ድረስ ቆይቶ ነው ደሞዛችን የሚከፈለን። ይህን ታግሰን፤ ሆድ እና ጀርባችን ተጣብቆ፣ ስቃይ አይተን ደግሞ ይሄ ደሞዝ ሲቆረጥ፤ መብታችንን ማንም ሳያስከብርልን ሲቀር. . . መምህር በመሆኔ በጣም አዝናለሁ” ሲሉ በምሬት ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 16:42


የቀብር ስፍራዎች መናፈሻ ሊሆኑ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ዘላቂ ማረፊያ የሆኑ የቀብር ስፍራዎች የሚያምር ገፅታ ኖሯቸው መናፈሻ እንዲሆኑ እየተሰራ ቢሆንም ‘’ሙታንን የሚያውኩ ነገሮች’’ በህግ ያስቀጣሉ ተብሏል፡፡

ቀብር የሚፈፀምባቸው ስፍራዎች በአብዛኛው ሰወር ያሉ፣ በደንና ቁጥቋጦዎች የተሞሉ እንደመሆናቸው እነዚህን ስፍራዎች ከነበራቸው አስፈሪ ገፅታ ወደ መናፈሻነት ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ካሉ የቀብር ስፍራዎች መካከል አንዱ የሆነው የቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ድሪባ ገመቹ ነግረውኛል ሲል ሸገር ዘግቧል፡፡

‘’እውነት ነው የቀብር ስፍራዎቹ ለወንጀል ድርጊት የተመቹ ነበሩ፤ አሁን ግን ቦታውን ወደ መናፈሻነት ቀይረነዋል፣ ባሉን 17 የሚደርሱ የጥበቃ ባለሙያዎች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረግን ነው’’ ብለዋል፡፡

አቶ ድሪባ ‘’ምንም አይነት ሙታንን የሚረብሹ ተግባራት’’ በህግ የሚያስጠይቁ መሆኑን በቅርቡ በመቃብር ስፍራው ሲጨፍሩ በመቅረፅ በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ ሰዎችን ጉዳይ በማንሳት አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ አንዳንድ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ መቃብር ስፍራ ላይ በመሄድ ጭፈራ ሲያደርጉበት ነበር የተባለዉ የቀጨኔን መቃብር ስፍራን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ስር የሚተዳደሩ 15 ያህል ዘላቂ ማረፊያዎች አሉ፡፡

በዘላቂ ማረፊያዎቹ መደበኛ የቀብር አገልግሎት፣ የባይተዋር (ቀባሪ የሌላቸው በህመምም ሆነ በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አልፎ ቤተሰቦቻቸው ያልተገኙ፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች ቀብር ማስፈፀም፣ የግብዓተ መሬት ማስረጃ መስጠት፣ የሙታን መረጃ መስጠት፣ 7 ዓመት ሞልቷቸው የሚነሱ አፅሞችን ወደ ዴፖ የማዛወር ስራን በዋነኛነት የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡

ዘላቂ ማረፊያዎቹንም በዘመናዊ መልክ በመስራት ቀብር ለመፈፀም ለሚመጡ ሰዎች ማረፊያ የሚሆኑ ቦታዎችን በማዘጋጀት በአጠቃላይ ደረጃቸውን የጠበቁ የዘላቂ ማረፊያ ስፍራዎችን አስገንብቶ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረጉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

Via ሸገር ራዲዮ

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 08:09


እስራኤል እና የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ትናንት ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፤ ዛሬ ስምምነቱ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ለ13 ወራት የዘለቀውን ውጊያ ለመቋጨት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የእስራኤል የጸጥታ ካቢኔ ትናንት ባደረገው ምክክር ወስኗል፡፡

ይህንን ግጭት ለማቆም ስምምነት ላይ መደረሱን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ያረጋገጡ ሲሆን፤ የተኩስ አቁሙ ግጭትን በዘላቂነት ወደማቆም ስምምነት ለመምራት ያለመ መሆኑን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ነገር ግን በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በስምምነቱ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።

በአሜሪካ አደራዳሪነት አሁን የተደረሰው ስምምነት በሄዝቦላህ እና እስራኤል መካከል በአውሮፓውያኑ 2006 የተከሰተውን ጦርነት የቋጨው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 1701 በተሰኘው ውሳኔን የተሰመረው ድንበር የተመሰረተ እንደሆነም ተገልጿል።

ይህም እስራኤል እና ሊባኖስ ከሚዋሰኑበት ሊታኒ ከተሰኘው ደቡባዊ ሊባኖስ ስፍራ የሄዝቦላህ ተዋጊዎች እንዲርቁ ማድረግን ያካተተ ነው ተብሏል።

እስራኤል፣ ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከጣሰ ወታደራዊ እርምጃ የመውሰድ መብት እንዳላት የገለጸች ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ባይደንም፤ “ከዓለም አቀፍ ህግ ጋር በተጣጠመ መልኩ ራሷን የመከላከል መብት አላት” ማለታቸው ተነግሯል።

በዚህ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት እስራኤል በሚቀጥሉት 60 ቀናት ከወረረቻቸው የሊባኖስ ደቡባዊ ክፍል ቀስ በቀስ ወታደሮቿን ታስወጣለች የተባለ ሲሆን፤ በምትኩም የሊባኖስ መንግሥት ወታደሮች ስፍራውን እንደሚቆጣጠሩት ተመላክቷል።

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 05:00


መረጃ ‼️

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ሺመልስ አብዲሳ ክልሉ ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች በፋኖ ታጣቂዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የመንግሥት ኃይሎች እንዳይከላከሉ በዋናነት እንቅፋት የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አማጺዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው ሲሉ ትላንት በነቀምት ከተማ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ተናግረዋል።

ሽመልስ ከዚህ ቀደም በምሥራቅ ወለጋ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በምሥራቅ ሸዋ እና በቅርቡ ደሞ በሰሜን ሸዋ ዞኖች "ጽንፈኛ" ሲሉ የጠራቸው የፋኖ ታጣቂዎች ለሚፈጽሟቸው ጥቃቶች በዋናነት ኃላፊነቱን የሚወስደው ኦሮሞን ነጻ አወጣለው ብሎ የሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተባሉት ኃይሎች የፋኖ ታጣቂዎች ወደሚገኙባቸው አካባቢዎች አይጠጉም ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ራሱን እንዳይከላከል አስቀድመው ትጥቅ በማስፍታት ለጥቃት ያጋልጡታል በማለት ከሰዋል።

ኹለቱ ኃይሎች የጥፋት ሥራቸውን ተናበው እንደሚሠሩ በመግለጽም፣ መንግሥት አማጺዎቹን ከከልሉ በቅርብ ቀናት በማጥፋት ሰላምን እንደሚያረጋግጥ ቃል ገብተዋል።

መረጃ 24 ሰአት

27 Nov, 05:00


ቅስም ይሰብራል!

አርብ እለት ፒኮክ መናፈሻ አካባቢ አትክልት በማምረት ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው ቢሮዬ መጡ።'ሰፈሩ ለልማት ሊነሳ ነው እየተባለ ነው።ከወላጆቻችን ዘመን ጀምሮ በአካባቢው ለ73 አመታት ቆይተናል።ድንገት ተነሱ ብንባል ምን ይዋጠን!?'  አሉኝ።

'መጀመሪያ የምትሄዱበትን ቦታ ማመቻቸት የመንግስት ግዴታ ነው።ያ ሳይሆን ለማስነሳት እንቅስቃሴ የሚደረግ ቢሆን ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቤ እግድ እንዲሰጣችሁ አደርጋለሁ!' ብያቸው ተለያየን።ቅዳሜ ጉዳዩ የሚታይበትን አግባብ ሳዘጋጅ ዋልኩ።እሁድ ጠዋት ደወሉልኝ ።ከቤተክርስትያን ስንመለስ ቤታችን እየፈረሰ አገኘነው አሉ። ከባልደረባዬ ጋር ሄድን ።አይዟችሁ ብለን መትረፍ የሚችለውን ለማስቆም እንሞክራለን አልናቸው ።እስከ ማታ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት የህግ አቤቱታዎችን ስናዘጋጅ አመሸን።ሰኞ ጠዋት ኮሚኒቲው ህጋዊ የህብረት ስራ ማህበር ያላቸው በመሆኑ በማህበራቸው ስም ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ኑርጋ ውክልና እንዲሰጡን ተነጋገርን።ትላንት ከሰአት ሊቀመንበሩ  የጠበቃ ውክልና ለመስጠት የማህበሩን የመመስረቻ ጽሁፍ ስላጡት  ለማክሰኞ ጠዋት እንደሚሰጡን  ተነጋገርን ።

ዛሬ ጠዋት አቶ ዱላ ከቤታቸው ሲወጡ የማህበሩ አባላት ሰፈር ውስጥ ለማፍረሻ የመጣ ዶዘር ቆሟል።ሌሎች አባላቶች ለኛ ውክልና ለመስጠት ውልና ማስረጃ እየጠበቋቸው ነው።አብራቸው ከቤት የወጡትን ባለቤታቸውን ' መጣሁ እየሄድሽ ጠብቂኝ !' ብለዋት  ወደ ቤት ተመለሱ።በአንዲት ቀጭን ሲባጎ እራሳቸውን አንጠልጥለው  ተገኘ።

ዛሬ  ጠዋት 3:00 ላይ እኔ አቤቱታዬን ይዤ የአቶ ዱላን ስልክ ስጠብቅ ከሌሎች አባላቶች ተደወለልኝ።ከዛ ወዲህ ያለው ቢነገርም ጥቅም የለውም።

ሰፈሩ መፍረሱ እና  መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰአት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው።

አቶ ዱላ ለ20 አመት በሊቀመንበርነት ያገለገሉትን ከ70 አመት በላይ በአንድ ቦታ የቆየውን ለፍቶ አዳሪ ማህበረሰብ 'ፌይል አደርጌያቸዋለሁ' ብለው እራሳቸውን አጥፍተዋል።እኔም ያንን ኮሚኒቲ ፌይል አድርጌዋለሁ።ትላንት አቤቱታውን ባስገባ ምናልባት ሊቀመንበሩ ከውሳኔው ይቆጠብ ይሆን?!ከጠዋት ጀምሮ በሰቀቀን ውስጥ ነኝ!

ቀብራቸው ነገ ይፈጸማል!
ነብሳቸውን ፈጣሪ ይቀበላት !!

ከጠበቃ አንዱዓለም ቡኬቶ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

Via_dagu

መረጃ 24 ሰአት

26 Nov, 06:42


ወቸዉ ጉድ‼️

ለቃጠሎ ቀርቦ የነበረው አስክሬን ነፍስ ዘራ
የ25 አመቱ ህንዳዊ ወጣት በሀኪሞች መሞቱ ተረጋግጦ አስክሬኑ ለመቀጣል ተራ እየጠበቀ በነበረበት ወደ ህይወት ተመልሷል


የመናገር እና የመስማት የጤና እክል ያለበት ኩማር ባሳለፍነው ሀሙስ የህመሙ ሁኔታ በድንገት በመክፋቱ ወደ ሆስፒታል ይወሰዳል፡፡

የህንድ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በሚጥል በሽታ የሚሰቃየው ወጣት ወደ ሆስፒታል በደረሰበት ወቅት ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነበር፡፡

እንደ መገናኛ ብዙሀኑ ዘገባ ከሆነ ታድያ የኩማር ሰውነት መንቀጥቀጡን ሲያቆም ሀኪሞቹ ተገቢውን ምንም አይነት የአስከሬን ምርመራ ሳይደርጉለት በፍጥነት መሞቱን የሚገልጽ ሪፖርት አዘጋጅተውለታል፡፡

ቀጥሎም አስከሬኑ በህንድ ባህል መሰረት ወደ አስከሬን ማቃጠያ ስፍራ ይዛወራል አስገራሚው ነገር የተፈጠረውም እዚህ ላይ ነው፡፡

እሳቱ ከመቀጣጠሉ በፊት በቦታው የተገኙት ሰዎች ከወጣቱ አካል ላይ ያልተጠበቀ እንቅስቃሴ ሲመለከቱ ወደ አስክሬኑ ተጠግተው የተጠቀለለበትን ጨርቅ ሲከፍቱ እስትፋንስ እንዳለው ማረጋገጣቸውን ተከትሎ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ህይወቱ አልፏል፡፡

አጋጣሚውን ተከትሎ የሆስፒታሉ ባለስልጣና ሦስት ሀኪሞችን ከሥራ አግደው አግደዋል፤ በተጨማሪም ፖሊስ በከፈተው ምርመራ አስከፊ ሁኔታን ሊያስከትል የነበረውን ቸልተኝነት እያጣራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እና ሌሎች የህንድ ሚዲያዎች ጉዳዩን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡

ሚድያዎቹ አጋጣሚው በሆስፒታሎች ውስጥ ያለውን የህክምና ቸልተኝነት አደገኛነት አመላካች ነው በሚል ቁጥጥርን ማጠናከር እና እንደዚህ አይነት ክስተቶች እንዳይደገሙ አስፈላጊው የህክምና ሂደቶችን መከተል እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

መረጃ 24 ሰአት

25 Nov, 14:19


ደጃች ውቤ ሰፈር

ዛሬ ከሰአት 9 ሰአት ገደማ ፒያሳ በተለምዶ 'ቻይና ግቢ' የተከሰተው የእሳት አደጋ እስካሁን(10:54) ሙሉ ለሙሉ አለጠፋም ተብሏል።

የእሳት አደጋው 'ጃንጉሲ ኮንስትራክሽን' በተባለ ድርጅት ውስጥ እንደተነሳ ታውቋል። ከሰሞኑ በተመሳሳይ በመርካቶ በቀናት ልዩነት ሁለት ግዜ ከባድ የእሳት አደጋዎች መከሰታቸው ይታወሳል።

መረጃ 24 ሰአት

25 Nov, 14:18


ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ 340 ሚሳኤሎችን በመተኮስ በአሽዶድ የባህር ኃይል የጦር ሰፈርን ደበደበ

ሄዝቦላህ በደቡባዊ እስራኤል የሚገኘውን አሽዶድ የባህር ሃይል ጦር ሰፈርን ለመጀመሪያ ጊዜ ኢላማ አድርጌያለሁ ያለ ሲሆን በቴል አቪቭ “ወታደራዊ ስፍራ” ላይ የላቁ ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የጦር ኦፕሬሽን ማካሄዱን አስታውቋል። የእስራኤል ጦር የቴል አቪቭ ከተማን ጨምሮ በማዕከላዊ እና በሰሜናዊ አካባቢዎች የአየር ወረራ የማስጠንቀቂያ ሳይረን አሰምቷል። በሰሜን እስራኤል ላይ የተተኮሱትን በርካታ ሚሳኤሎችን መያዙን የገለጸው ወታደራዊ ሃይሉ ከሊባኖስ 250 የሚጠጉ ሚሳኤሎች መተኮሳቸውን ገልጿል።

ከመጀመሪያዋው መግለጫ ዘግይቶ የእስራኤል ጦር ሬድዮ ‘340 ሚሳኤሎች’ ከሊባኖስ ተወንጭፏል ሲል አስታውቋል። በጥቃቶቹ ቢያንስ 11 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ፣ አንድ ሰው በከባድ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ የህክምና ኤጀንሲዎች ገልፀዋል። እስራኤል በማዕከላዊ ቤይሩት ባደረገችው ጥቃት ቢያንስ 29 ሰዎችን ከገደለች ከአንድ ቀን በኋላ ሄዝቦላህ ይህንን እርምጃ ወስዷል። የሊባኖስ የህዝብ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለፀው ቢያንስ 66 ሌሎች ሰዎች በእስራኤል ጥቃት ቆስለዋል ብሏል።

የሊባኖስ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ ጦርነቱን ለማቆም ሁሉንም ጥረቶች እና ቀጣይ ግንኙነቶችን የሚቃወም ቀጥተኛ እና ደም አፋሳሽ መልእክት ያለው ጥቃት በማለት የእስራኤል እርምጃን ያወገዙ ሲሆን በዩናይትድ ስቴትስ መሪነት የሚደረገው የተኩስ አቁም ጥረቶች ላይ የተፈፀመ ጥቃት ሲሉ አውግዘዋል።የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ አንድ የሊባኖስ ወታደር ለገደለው እና 18 ሰዎችን ላቆሰለው ጥቃት ይቅርታ መጠየቁን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

የእስራኤል ጦር “ክስተቱ የተፈፀመው ከሂዝቦላህ ጋር ጦርነት በሚካሄድበት አካባቢ ነው” ብሏል። አክሎን ለወታደራዊው ድርጊቱ ጦሩ ተጸጽቷል እስራኤክ የምትዋጋው ከሊባኖስ ጦር ጋር ሳይሆን ከሂዝቦላህ ጋር ብቻ ነው ሲል ገልጿል።የሊባኖስ ጦር በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል ካለው ግጭት ርቆ ቆይቷል፤ ነገር ግን በመስከረም ወር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ጦርነት ተቀስቅሶ ወደ ሁለንተናዊ ጦርነት ከገባ በኋላ ከ 40 በላይ የሊባኖስ ወታደሮች በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል።

በስምኦን ደረጄ

መረጃ 24 ሰአት

25 Nov, 08:21


 የሩሲያ የሳይበር ደህንነት ግዙፉ ኩባንያ ካስፐርስካይ እና አፍሪፖል የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል ጥምረታቸውን አጠናከሩ

ባለፈው ሳምንት በአልጀርስ የካስፐርስካይ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩጌኔ ካስፐርስካይ እና የአፍሪፖል ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ጃሌል ቼልባ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት የበለጠ ለማጠናከር የሳይበር ወንጀልን ለመከላከልና ለመዋጋት  የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።

ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ስምምነቱ ለኩባንያው እና ለአፍሪካ ህብረት ሕግ አስፈጻሚ ድርጅት የቅርብ ጊዜ የሳይበር ወንጀል እንቅስቃሴን በተመለከተ አስጊ መረጃን ለመለዋወጥ ህጋዊና እና ቀላል ያደርገዋል።

በኩባንያው መግለጫ መሰረት አፍሪካ ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር ካስፐርስካይ ሶሉሽንስ የሳይበር ወንጀሎችን የተከላከለበት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢንዱስትሪያል ቁጥጥር ስርዓቶች የተጫኑባቸው ኮምፒውተሮች አሏት።

💬 “ከአፍሪፖል ጋር ያለንን ትብብር በማሳደግ እና ለሚከሰቱ የሳይበር አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስፈልጉትን መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ለኤጀንሲው በማሟላት፤ ለበለጠ የሳይበር መቋቋም እና ለሁሉም ደህንነቱ የተጠበቀ ሳይበርስፔስን በማጎልበት ረገድ አስተዋፅኦአችንን ለማሳደግ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል ካስፐርስካይ።

መረጃ 24 ሰአት

25 Nov, 07:34


አትሌት ሰውመሆን አንተነህ ''ስፔሻል ዐይን''ተገጠመለት

አትሌት ሰውመሆን አንተነህ ሙሉ ወጪው ተሸፍኖለት ወደሕንድ ሀገር ተጉዞ ''ስፔሻል ዐይን'' ሊገጠምለት እንደሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለፁ ይታወቃል።

የ17 ዓመቱ አትሌት ሰውመሆን ታሪኩ ፔሩ ሊማ በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስት ሺሕ ሜትር ሀገሩን ወክሎ እንዲወዳደር አንደኛ ሆኖ ተመርጦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው ሆቴል ገብቶ በዝግጅት ላይ እያለ ልምምዱን ለመሥራት ወደ ጫካ በወጣበት አንድ ዕለት ፖሊስ ነኝ ካለ አንድ ሰውና ከሁለት ግብራበሮቹ ጋር በተፈጠረ እሰጣ ገባ አንድ ዐይኑን በሽጉጥ ተመትቶ ብርሃኑን እንዳጣ የሚዘነጋ ይታወሳል።

አትሌቱ ከገጠመው ከፍተኛ ጉዳት ለማገገም በዳግማዊ ምኒልክ ስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶ፣ በኋላም ሙሉ ወጪም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተሸፍኖ ለተሻለ ሕክምና ወደሕንድ ሀገር እንደሚጓዝ መነገሩም ይታወሳል።

በወቅቱ በሕንድም በመጀመሪያ ዙር ለሰባት ቀን ሕክምና ተደርጎለት እንደሚመለስና ከሁለት ወር በኋላ ''ስፔሻል ዐይን'' ለማስገጠም ተመልሶ እንደሚሄድ ተገልፆ ነበር።

ከሰሞኑም ለዚህ ሕክምና አትሌቱ ወደሕንድ እንዳቀና የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት ለአትሌት ሰውመሆን ''ስፔሻል ዐይን'' እንዳስገጠመለት የሚጠቁም መረጃ በአትሌቱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገፅ ላይ ተጋርቷል።
አትሌቱም ከአጋራው ፖስት ስር''ተመስገን አምላኬ ሁሉም ታሪክ ሆነ።'' የሚል መልዕክት አስፍሯል።

መረጃ 24 ሰአት

25 Nov, 07:33


ሱዳን የከሸፈች አገር የመሆን ስጋት ላይ ናት ሲሉ የረድዔት ኃላፊ አስጠነቀቁ

በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰችው ያለችው ሱዳን ሌላ የከሸፈች አገር የመሆን ስጋት ላይ ናት ሲሉ አንድ የዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።

በአገሪቱ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ በታጣቂ ኃይሎች እየፈራረሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሱዳን ውስጥ ያሉት ዋነኛ ተፋላሚዎች የጦር ሰራዊቱ እና የፈጣን ደራሽ ኃይሉ እንዲሁም በርካታ አነስተኛ ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋዎችን እየፈጸሙ ነው ሲሉ የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት (ኤንአርሲ) ኃላፊ ጃን ኤጌላንድ ገልጸዋል።

“ታጣቂዎቹ የራሳቸውን እና የህዝባቸውን ቤቶች እያወደሙ ነው። ወገኖቻቸውን እየጨፈጨፉ ነው” ብለዋል።

መረጃ 24 ሰአት

25 Nov, 06:23


መረጃ ‼️


የግብፅ ከፍተኛ የጦር ጀነራሎችና ባለስልጣናት ላለፉት ቀናት በአሰብ ይፋዊ  ያልሆነ ጉብኝት ማድረጋቸው ተሰማ

የኤርትራ መንግስት ለግብፅ በአሰብ የጦር ቤዝ እንድትገነባ ፍቃድ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ ፡፡

ይህ ሁኔታ ከኤርትራ መንግስት ጋር የሻከረ ግንኙነት ያለዉ የፌደራሉ መንግስት የአባይን ግድብ በአንክሮ ከምትመለከተዉ ግብፅ ጋር ያፋጠጠ  ሆኖል ፡፡

በዲፕሎማሲዉ ሜዳ የተዋጣለት አይደለም የሚባለዉ የፌደራሉ መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የገባበት እሰጣ ገባ የኢትዬጲያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚባሉት ሀገራት መጠቀሚያ እንዳያደርጉት ስጋት አለ ሲሉ ዲፕሎማቶች ይናገራሉ ፡፡

መረጃ 24 ሰአት

16 Nov, 09:50


ታላቁ ሩጫ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጥምር የፀጥታ ኃይል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፍፁም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጥምር የፀጥታ ኃይል ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።

ለ24ኛ ጊዜ ከፊታችን እሁድ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ 50 ሺሕ ተሳታፊዎች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በልዩ ልዩ የአደባባይ ኩነቶች ላይ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ በሚያከናውነው ተግባር ከተማችን ፍፁም የተረጋጋ ሠላም እንዲኖራት እና ፀጥታ የሰፈነባት እንድትሆን ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተከናወኑ የአደባባይ ኩነቶች በሠላም እንዲጠናቀቁ የከተማዋ ነዋሪ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው የዘንድሮው የታላቁ ሩጫ ስፖርታዊ ውድድርም በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሩ የከተማችንን መልካም ገፅታ የሚያጎላ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

ከስፖርታዊ ተልዕኮው ውጭ ማንኛውም ዓይነት የተቃረነ መልዕክትን ማስተላለፍ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑንና የፀጥታ ኃይሉም ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቀው ውድድሩ በጨዋነት መንፈስ መካሄድ ይኖርበታል ብለዋል።

መረጃ 24 ሰአት

16 Nov, 09:49


| የቢሾፍቱ ከተማ አብዛኛው ስፍራ ለዱባይ ባለሀብቶች በሊዝ እንደተሸጠ የተነገራቸው ነዋሪዎች በአንድ ሳምንት እንዲነሱ መታዘዛቸውን ተናገሩ

ከተማዋን 'በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል' ለማድረግ እየተሰራ ካለው ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ የከተማው ቦታ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባለሀብቶች ሊሰጥ እንደሆነ በመጀመርያ የተሰማው የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ነበር።

"እስከ 80 ፐርሰንት የሚደርስ የከተማው ቦታ ለኤምሬትስ ኢንቨስተሮች ሊሰጥ ነው የሚል መረጃ አለን፣ በዛ ላይ ትንሽ የቤት እድሳት ለማድረግ እንኳን ስንሞክር በከተማው አስተዳደር 'እዚህ ብዙ ስለማትቆዩ ማደስ አትችሉም' እየተባልን ነው" ብለው ነዋሪዎቹ በወቅቱ ለመሠረት ሚድያ ተናግረው ነበር።

ይህን በተመለከተ መሠረት ሚድያ የቢሾፍቱ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሀላፊ የሆኑትን አቶ ገብሬ ዳቢን አነጋግሮ የነበረ ሲሆም "እኔ የከተማው ኢንቨስትመንት ቦርድ ውስጥ አባል ነኝ፣ ግን በዚህ ደረጃ እንዲህ አይነት ኢንቨስትመንት ይመጣል የሚል መረጃ የለኝም" ብለው ተናግረው ነበር።

ሀላፊው የቤት እድሳት ክልከላውም ምናልባት ከተማው ውስጥ ወጥነት ያለው የቤት አሰራር እንዲሆን ከሚሰራው ስራ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ገልፀው ነበር።

ነዋሪዎቹ ግን ትነሳላችሁ የሚለው ቃል ከመንግስት እስካሁን ባይወጣም ወደፊት ግን ሊነሱ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልፀው ነበር።

አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ደግሞ ከ15 እና 20 አመት በላይ በቢሾፍቱ የኖሩ ነዋሪዎች "ቦታው ለዱባይ ባለሀብት በሊዝ ተሽጧል፣ ስለዚህ በአንድ ሳምንት ውስጥ ልቀቁ ተብለናል" በማለት ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ ለገበሬ ባለይዞታዎች ከሳ መክፈል እንደተጀመረ የታወቀ ሲሆን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው የአየር ካርታ ላላቸው 105 ካሬ መሬት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

በአንድ ሳምንት ውስጥ ልቀቁ የተባሉት እነዚህ ነዋሪዎች የገበሬ ቤት የሆነውን አረንጓዴ ቀለም፣ የሌላውን ህዝብ ደግሞ ቀይ ቀለም እየቀቡ ለይተው እንደጨረሱ ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት እስካሁን በግልፅ ምን ያህል መሬት ለኤምሬትስ ባለሀብቶች እንደሸጡ ይፋ አላደረጉም።

መሠረት ሚዲያ

መረጃ 24 ሰአት

15 Nov, 18:51


እነዶ/ር ደብረፂዮን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ ለባንኮች ደብዳቤ መፃፋቸው ተሰማ

" ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል ሲል በድጋሜ ከሷል።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን " በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች " ህጋዊ ያልሆነ " የስራ ምድባ በማካሄደ የመንግስት ግለበጣ በማካሄድ የቀን ተቀን ስራ የማደናቀፍ ኢ-ህጋዊ ተግባሩ ቀጥሎበታል ሲል ጠቅሰዋል።

" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ህጋዊ ያልሆኑ የስራ ምደባዎች በማካሄድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ከማደናቀፍ አልፎ ስራውን በሚመሩት ላይ አላስፈላጊ ጫና በመፍጠር የመንግስት ስራ እንዲቆም እያደረገ ነው ሲልም ገልጿል።

በየደረጃው የሚገኙ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅሮች ፣ በትግራይ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላት እና ተቋማት ፣ የፌደራል መንግስት እንዲሁም የዓለም ማህበረሰብ " ህጋዊ ባልሆነው መንገድ " የሚመድቡ እና የሚመደቡ በማንኛውም መንግስታዊ ሃላፊነት ስም እንዲንቀሳቀሱ ምንም እውቅና የሌላቸው መሆኑ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አስታውቀዋል። 

" ህጋዊ ባልሆነው ቡድን " የሚመደቡት አካላት የሚያስተዳድሩት ማንኛውም ሃብት የለም ያለ ሲሆን የፀጥታ አካላት ፣ የፍትህ መዋቅር እና ባንኮች ይህንኑ በመገንዘብ ህግ እንዲያስፈፅሙ ሲል አስገንዝበዋል።

የመረጃው ምንጭ ቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳስነበበው ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ሲል በፈረጀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተመደቡ የአስተዳደር አካላት ስም ጠቅሶ ማንኛውም የመንግስት ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ የሚያግድ ደብዳቤ ወደ ባንኮች ፅፏል።

መረጃ 24 ሰአት

15 Nov, 11:12


ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙርያ በተሰጠ አስተያየት ምክንያት የሱዳን አምባሳደርን ጠርታ አነጋገረች!

የሱዳን ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አሊ የሱፍ "በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ውሳኔ ያላገኙ እና ያልተፈቱ ልዩነቶች ወደ ጦርነት ሊያመሩ ይችላሉ" ሲሉ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ኢትዮጵያ የሱዳንን አምባሳደር ረቡዕ ዕለት ጠርታ ማነጋገሯን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

ሚንስትሩ በቅርቡ በቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙርያ የሚደረጉ ድርድሮች የማይሳኩ ከሆነ ሱዳን ከግብፅ ጋር ልትሰለፍ እንደምትችል ገልፀው ጦርነት የሶስቱንም ሀገራት የውሃ ተጠቃሚነት መብት የሚያረጋግጥ አማራጭ መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሱዳን አምባሳደር አልዘይን ኢብራሂም ጋር ባደረገው ውይይት በጉዳዩ ደስ አለመሰኘቱን ገልጾ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል።የሱዳን ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አሊ የሱፍ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሊሰጡ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ እንደሚችሉ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ጠቁመዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ትናንት ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን “የዳበረ እና ስትራቴጂካዊ” ግንኙነት በመጥቀስ የህዳሴ ግድብ ጉዳይን በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።አክለውም ኢትዮጵያ ላለፉት 13 ዓመታት ካካበተችው ልምድ ግድቡ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉዳት እንደሌለው የሚያረጋግጥ መሆኑንና ይልቁኑ ቀጠናዊ ትብብርን እንደሚያጠናክር አጽንኦት ሰጥተዋል።
ViaAddis Standard

መረጃ 24 ሰአት

15 Nov, 07:28


ቀዳማዊ እመቤት ዝናሺ ታያቸዉ "የህብርተሰቡን ችግር አዉቀዋለሁ የህዝብ ልጅ ነኝ" ሲሉ ተናገሩ

ቀዳማዊ እመቤቶ በፅህፈት ቤታቸዉ ስር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዳቦ እና የትምህርት ተቆማትን በማስገንባታቸዉ የሚያመሰግኖቸዉ ወገኖች ካባ እንደሸለሞቸዉ ይታወሳል ፡፡

በሌላ ወገን ፅህፈት ቤታቸዉ ኦዲት የማይደረግ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ አሰራር የሚከተሉ ናቸዉ በማለት ቀደማዊ እመቤቶን የሚወቅሱ አሉ ፡፡

እሳቸዉ ግን "ዳቦ ብሉ ብለን አቅርበናል፣ ሰላም ማፅናት የህዝብ ስራ ነዉ"በሚለዉ ንግግራቸዉ ይታወቃሉ ፡፡

በአንድ ዉይይት መድረክ ላይ በመገኘት የህብርተሰቡን ችግር አዉቀዋለሁ ፡የህዝብ ልጅ ነኝ ፡ ወደ ላይ ሳይሆን ወደ ታችኛዉ የህብረተሰብ ክፍል ማየት ይቀናኛል ሲሉ ቀዳማዊ እመቤቶ ተናግረዋል ፡፡

ይሄን ይበሉ እንጂ አዉቀዋለሁ የሚሉት ህዝብ አብዛኛዉ ኑሮ ዉድነት ከአቅሙ በላይ ሆኖ የእለት ጉርሱን ማሞላት በተቸገረበት ግማሹም ቀዬዉ በታንክ እና በድሮን እየታመሰ ባግዳድ በሆነበት የህዝቡን ችግር ካወቁት ለምን ለመፍታት አልሞከሩም የሚለዉን ጥያቄ አለመመለሳቸዉ አጠያያቂ ያደርገዋል ፡፡

Via አንኳር መረጃ

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

14 Nov, 19:12


ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የወባ ወረርሽኝ በአስጊ ደረጃ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተከስተውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል በተደረገው ርብርብ የሰዎች ሞት ቢቀንስም፤ ወረርሽኙ  በአስጊ ደረጃ  እየጨመረ ስለመምጣቱ ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች  ቋሚ ኮሚቴ በጅማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የወረርሽኙን ሁኔታ አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው በጅማ ዞን በሰቃ ጨቆርሳ፣ በጌራ እና ጎማ ወረዳዎች በተመረጡ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ባደረገው ምልከታ የወባ ወረርሽኙ  በፍጥነት እያደገ መምጣቱን አረጋግጧል ተብሏል።

የቋሚ ኮሚቴው  አባልና የቡድኑ አስተባባሪ ወ/ሮ አሚራ መሀመድ በሦስቱም ወረዳዎች የወባ ወረርሽኙን ለመከላከል የተደረገው ሁለንተናዊ ጥረት የተሻለ ቢሆንም፤  በአንጻሩ የበሽታው ስርጭት እየከፋ መምጣቱን አስረድተዋል። ወረርሽኙን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች  የበለጠ ሊጠናከሩ  እንደሚገባም አሳስበዋል።

የሰቃ ጨቆርሳ  የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሣቢት ጀማል ወረርሽኙን ለመከላከል የደም እና የመድኃኒት አቅርቦቶች ሊሟሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ  እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን እና ከእነዚህም መካከል 1,157 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

 

መረጃ 24 ሰአት

14 Nov, 19:11


የስፖርት ቤት የጂም ባለሙያዎች ሙሉ የስፓርት ቱታ እና የስፓርት ጃፓኒ ሳያስለብስ አገልግሎት የሰጠ ተቋም 50 ሺህ ብር ይቀጣል ተባለ

የጂም የስራ መስክ ባለሙያን ለስፖርት የተፈቀደ አለባበስን ሳያስለብስ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ይመር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ቢሮዉ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 22 ቁጥር 6-13 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዙሪያ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት እየተሸረሸረ በመሆኑ እንዲሁም ወጥ የሆነ አለባበስ እንዲኖር  የወጣዉ የደንብ ረቂቅ ፀድቋል ብለዋል።

በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ስነ-ስርዓት ላይ ቢሮዉ ያወጣዉ የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት እንዲፀድቅ ተደርጓል። በረቂቅ ደንቡ መሰረት የጂም የስራ መስክ ባለሙያ ሆኖ ሙሉ የስፓርት ቱታ ፣ከላይ የስፖርት ጃፓኒ ወይም የስፓርት ቲሸርት ማድረግ እንዳለበት ይህ ደንብ ያስቀምጣል ያሉት ዳይሬክተሯ ሌሎች ክልከላዎችን አካቷል ብለዋል።

አያይዘዉም የጂም ባለሙያ የስፖርት ቁምጣ ወይንም ለስፓርት አገልግሎት የተፈቀደ ጫማ ሳያደርግ አገልግሎት መስጠት እንደማይችል ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።ይህን ደንብ ተላልፎ አገልግሎት የሰጠ ተቋም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ገንዘብ ቅጣትና ከባድ የሚባል እርምጃ ድረስ በረቂቅ ደንቡ ተደንግጓል ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልፀዉ እንደ ጥፋት ደረጃዉ የገንዘብ መቀጮዉ ተወስኗል ብለዋል።

በተደነገገዉ ክልከላ መሰረት በደረጃ ሀ፣ አምሳ ሺህ ብር፣በደረጃ ለ 30 ሺህ ብር፣ በደረጃ ሐ ደግሞ  5 ሺህ ብር  ያስቀጣል። በተጨማሪም ይህን የተደነገገዉን ክልከላ ያላከበረ ተቋም እስከ 1 ሺህ ብር በደረሰ ዝቅተኛ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል። በዚህም መሰረት ይህን ክልከላ ሳይተገብር ጂም  ሲያሰራ የተገኘ የሆቴል ተቋምም ሆነ መሰል አገልግሎት ሰጪ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያቀጣ ወ/ሮ ገነት ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንድ በላይ ጥፋቶችን ያጠፋ ተቋም ለእያንዳንዱ ጥፋት አምሳ ሺህ ብር ተደምሮ ይቀጣል  ሲሉ ዳይሬክተሯ  ጨምረዉ ተናግረዋል።

በቅድስት ደጀኔ

መረጃ 24 ሰአት

13 Nov, 13:13


ቢሊየነሩ መስክ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም መስሪያ ቤት ኃላፊነት ሹመት ተሰጠው!

የተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ የጀርባ አጥንት የሆነው ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም አዲስ መስሪያ ቤት የኃላፊነት ሹመት ተሰጠው።ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለሪፐብሊካን እጩ ፕሬዚዳንትነት ተወዳድረው ከነበሩት ቪቬክ ራምስዋሚ ጋር በጋራ ይህንን መስሪያ ቤት ይመራሉ ብለዋል።

መስሪያ ቤቱ በዋነኝነት የመንግሥት ቢሮክራሲን ለማስወገድ እና ወጪን በመቀነስ ላይ ከመንግሥታዊ ስራ ውጭ ምክር እና መመሪያ ይሰጣል ተብሏል።መስሪያ ቤቱ መንግሥታዊ ሚና የለውም የተባለ ሲሆን ምን አይነት ቅርጽ እንደሚኖረው እስካሁን ግልጽ አልሆነም።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የፎክስ ኒውስ አቅራቢውን ፒት ሄግስትን የመከላከያ ጸሓፊ እንዲሁም ጆን ራትክሊፍን የብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር አድርገው መርጠዋል።ኤለን መስክ በመንግሥት ብቃት እና የበጀት ቅነሳ ላይ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተናግሮ ነበር።

Via_BBC

መረጃ 24 ሰአት

13 Nov, 13:12


ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ለመውጣት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ!

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እየተጠየቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው መጠየቃቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።

የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡ክፍያው በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃገራት ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተቋሙ የውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አዳነ ደበበ ገልጸዋል።

አክለውም ክፍያው የውጭ አገር ዜጎቹ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ በጨመረ ቁጥር ክፍያውም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም አሳስበዋል።
Via_VoA

መረጃ 24 ሰአት

13 Nov, 13:11


ፍራንኮ ቫሉታ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር  ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ተባለ

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር  ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ  ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን እና በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡

መረጃ 24 ሰአት

12 Nov, 17:32


<<በአሰሪዎቿ ለደረሰባት ጉዳት መጠኑ ከፍ ያለ ገንዘብ በፍርድ ቤት ተወሰኖላታል።ግን ጠፋች>>ከዱባይ የደረሰኝ መረጃ ነው

ይህንን መረጃ በደንብ ተመልከቱትና በግሩፖቻችሁ ሼር አድርጉት

በፓስፖርት ምስሉ ላይ የምትታየው ዘምዘም መሐመድ አሊ ትባላለች።ከአመታት በፊት(2004ዓ.ም)የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሰው ቤት ስትሰራ በአሰሪዎቿ ጉዳት ደርሶባት ነበር በማለት ጥቆማውን ያመጡት ወዳጆች አስረድተዋል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠበቃ ቀጥሮላት ጉዳዩ በህግ እንዲያዝ ተደርጎ እሷ ወደ ሀገሯ ተላከች።የፍ/ቤት ክርክሩ በተጎጅዋ ጠበቃ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ለእሷም ጉዳቷን ታሳቢ ያደረገ ጥሩ ገንዘብ ተወሰነላት።አሁን አድራሻዋ ጠፋ።ፓስፖርት ያወጣችው ደሴ ከተማ ኢሚግሬሽን ስለነበር ኤምባሲው ሰነዷን አስፈልጎ በጊዜው ሁሉም ዲጅታል ስላልነበር በሀርድ ኮፒ የተቀመጠው በሰሜኑ ጦርነት ጠፍቷል።በዚህም ምክንያት አድራሻዋን ማግኘት አልተቻለም ሲሉ ወዳጆቼ ነግረውኛል።

ለተጎጅዋ ዘምዘም መሐመድ አሊ በፍርድ ቤት የተወሰነላትን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በፊት መወሰድ አለበት።በህይወት ካለች ራሷ ከሌለች እናትና አባት ከህጋዊ አካል የወላጅነታቸውንና በህይወት አለመኖሯን የሚያስረዳ መረጃ ይዘው መውሰድ እንደሚችሉ እነኝሁ ኢትዮጵያዊያን ነግረውኛል።ስለትክክለኛ ወላጅነታቸው የዘረመል(DNA) ምርመራ ይደረጋል ያሉት ወዳጆቼ መልዕክቱንም ፅፌ በማስተላለፍ እንዲተባበራቸው ጠይቀውኛል።ይሄው አስተናግጃለሁ።እናንተ ደግሞ ሼር በማድረግ ለሌሎችም አድርሱት🙏
Wasu Mohammed

መረጃ 24 ሰአት

12 Nov, 17:30


በወራቤ ባልተለመደ መልኩ የደም ማነስ ህመም መጨመር እየተስተዋለ መሆኑ ተነገረ

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ሶስት ወራት ከ62 ሺ በላይ ዜጎች የህክምና አገልግሎት እንዳገኙ ተነግሯል።

በተቋሙ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ለ62 ሺህ 4 መቶ 51 ዜጎች በተመላላሽ ፣ በድንገተኛና በአስተኝቶ ህክምና አገልግሎት መስጠት መቻሉን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ቡድን መሪ የሆኑት አ/ቶ አብዱልጃበር አብደላ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

የእናቶችና ህፃናት ሞትን ከመቀነስ አንፃር በተለይም ወላድ እናቶችን መንከባከብና ጤናቸውን መጠበቅ የተቻለ ሲሆን ለ1160 እናቶች የወሊድ አገልግሎት እንደተሰጠ ተጠቁሟል ። በተጨማሪም በተቋሙ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት 1 ሺ 5 መቶ 72 የቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠት መቻሉ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የበጀት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ወጪ ለመቆጠብ እንዲያግዝ በሆስፒታሉ እየተመረተ ያለውን የጽዳትና የንጽህና መስጫ ቁሳቁስ በሌሎች ዘርፎችም ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቁሟል ። በሌላ በኩል በተለየ ሁኔታ እየተስተዋለ ያለውን የደም ማነስ ህመም መጨመር በተመለከተ ጥናት ማድረግ ይገባል ተብሏል ።ከዚህ በተጨማሪም ለመድኃኒት አቅርቦት ቅድሚያ በመስጠት የህክምና ክፍሎችን ማስፋፋትና ማሻሻል፣ የህክምና ቁሳቁስና ማሽኖች አቅርቦት ላይ አማራጮችን  መጠቀም እንደሚገባ ተጠቁሟል ።

መረጃ 24 ሰአት

11 Nov, 16:32


አባትን ለመበቀል የ4 ዓመት ህጻን ልጁን የገደሉ አራት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በባሌ ዞን  ሀረናቡልቅ ወረዳ ሁምቢ በተባለ ቀበሌ ውስጥ አራት ግለሰቦች ከሟች ህጻን አባት ጋር ባለቸው አለመግባባት ለመበቀል በማሰብ  የአራት ዓመት ህጻን ልጅ ላይ አሰቃቂ ግድያ የፈጸሙ ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል ።

የባሌ ዞን ፖሊስ  መምሪያ የኮሙኒኬሽን  ጽ/ቤት ባለሙያ ሳጅን ጎሳ ስንታየሁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  እንደገለጹት አንደኛ ተከሳሽ  ሃሎሼ ኢብሮ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ አህመድ ኢብራሂም፣ ሶስተኛ ተከሳሽ አብዱ ኢብራሂም ፣ አራተኛ አደም አህመድ የተባሉት ግለሰቦች ድርጊቱን መፈጸማቸው ተረጋግጧል።ሚያዚያ 3  ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ህጻን ሙሄ መሃመድ የተባለዉን የአራት ዓመት ህጻን በትብብር መግደላቸው በማስረጃ መረጋገጡን ገልጸዋል።

ሶስቱም ተከሳሾች በአንደኛው ተከሳሽ አነሳሽነት፣ ሁለተኛ ፣ ሶስተኛ እና አራተኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 1 ሺህ ብር  በመቀበል ድርጊቱን መፈጸማቸው የዓቃቢ ህግ ማስረጃ አመላክቷል።1ኛ ተከሳሽ ከሟች አባት ጋር በስራ  በነበረው አለመግባባት ጸብ ውስጥ የገባ ሲሆን በዚህም በአራት ዓመቷ ልጅ ላይ  አሰቃቂ ግድያ ለመፈጸም  እንደተነሳሳ በምርመራ ተረጋግጧል ። አራቱም ተከሳሾች  ድርጊቱን ፈጽመው የአራት ዓመቱን ህጻን አስከሬን ወንዝ ውስጥ የጣሉ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ  አስከሬኑን በመመልከት ለጸጥታ አካላት በሰጠው መረጃ  ምርመራው ሊጣራ ችሏል።

1ኛ ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ውሎ በሰጠው ጥቆማ ሶስቱንም መያዝ መቻሉ ተገልጿል፡፡ ፖሊስ አስከሬኑን በማስመርመር የምርመራ መዝገቡን በማጠናከር መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ ልኳል።መዝገቡን ሲመለከት የነበረው   ዓቃቢ ህግ በወንጀል ህግ 539 እና 540 በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ የመሰረተ ሲሆን ክሱን ሲመለከት የነበረው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ  ቤት ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት  1ኛ ተከሳሽ  ሃሎሼ ኢብሮ ፣2ተኛ ተከሳሽ አህመድ ኢብራሂም እና 4ተኛ ተከሳሽ አደም አህመድ  እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ሲወሰን 3ተኛ ተከሳሽ  አብዱ ኢብራሂም በ15 ዓመት እስራት  እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ሳጅን ጎሳ ስንታየሁ  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

መረጃ 24 ሰአት

11 Nov, 11:37


አዲስ አበባ

መርካቶ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ በመደረጉ በዚህ ስጋት ውስጥ የገቡ ሰዎች ሱቃችን ሊታሸግ ወይም እቃችን ሊወሰድብን ይችላል በሚል አልፎ አልፎ ሱቃቸውን እንደዘጉ ተሰምቷል።

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

11 Nov, 11:08


አዲስ ተከታታይ ድራማ

       🤩እናት ነገር 1🤩


Share
https://t.me/Abolduka1
https://t.me/Abolduka1
https://t.me/Abolduka1

መረጃ 24 ሰአት

11 Nov, 11:02


የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አስተዳደር  የመኪና ስጦታ አበረከተ

ባለፈዉ ሳምንት አንድ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስአበባ የገቡት የአቡዳቢዉ መሪ 30 ያህል ጥይት የማይመታቸዉ ዘመናዊ መኪኖች በስጦታ መልክ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ማብርከታቸዉ ተሰምቶል ፡፡

ከዚህ በፊት የብልፅግና መንግስት ወደ መሪነት በመጣ ሰሞን የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መንግስት ቁጥራቸዉ በርከት ያሉ  ኒሳን  V8  መኪኖችን ለጠቅላዩ መስጠታቸዉ የሚታወስ ነዉ ::

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

11 Nov, 11:01


ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይነጋ

ከሰሞኑ በአፍሪካ ምድር መነጋገሪያ የነበረው የጊኒው ሰው ጉዳይ አሁን ደሞ ሌላ ጉድ ከሰውዬው ጓዳ ተሰምቷል።

የጋሽ Balthazar ጉዳይ ሊያልቅ ትንሽ ቀረው ሲባል አሁን ደሞ ባለቤቱም ከሌላ ወንድ ጋር አሸሼ ገዳሜ ስታደርግ ቪዲዮ ወጥቶባታል።

ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው ሰውየው አሸሼ ገዳሜውን እልል ብሎ በማሳጅ ጀምሮታል::

እንዲሁም 1.8 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ የሚኖርባት ኢኳቶሪያል ጊኒ አሸሼ ገደሜ ሲያደርጉ ቪዲዮ ሲቀርፁ ነው ወይ የሚውሉት አስብሏል?

በዚህ መሀል ግን ምንም የማያቁት
6ልጆች ትልቅ ችግር ውስጥ ገብተዋል

በትምህርት ቤት ስነልቦናቸው ሊጎዳ ይችላል እየተባለ ይገኛል::

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

10 Nov, 17:24


🪙Star መግዛት የምፈልጉ⭐️

☑️Premium መግዛት የምፈልጉ 🎁

🤑Ton መግዛት  የምፈልጉ 👛

🐶Dogs መሸጥ የምፈልጉ👛

🐹Hamster መሸጥ የምፈልጉ 😀

💵Usdt ($) መሸጥ መግዛትም የምፈልጉ

🪙  x empire መሸጥ የምፈልጉ 🥇

ታማኝነት መገለጫችን ነው

✉️✉️INBOX ✉️✉️
አሁን Online ነኝ

👇👇👇
@Dadaya345
@Dadaya345

መረጃ 24 ሰአት

10 Nov, 12:32


ተሽከርካሪን በመጠቀም በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል በተለያዩ ቦታዎች ሲፈፅሙ የነበሩ  ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ‼️

ግለሰቦቹ ወንጀሉን ሲፈፅሙ በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አየር ጤና አካባቢ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጥሩነሽ ቤጂንግ  አካባቢ ነው።

በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በተለምዶ አጠራሩ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን የወንጀል አይነት አስቀድሞ ለመከላከል እያከናወነ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5  አየር ጤና አካባቢ በኮድ 3 20947 ኦሮ በሆነ ተሽከርካሪ ሁለት ተጠርጣሪዎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር  ወንጀሉን ሲፈፅሙ  በፖሊስና በአካባቢው ህብረተሰብ ተባባሪነት ከሰረቋቸው 9 ሞባይል ስልኮች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል።

በተመሳሳይ ዜና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማም ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሠዓት ገደማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጥሩነሽ ቤጂንግ አካባቢ የታክሲ ሾፌር፣ ረዳትና  ተጓዥ በመምሰል በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 በሆነ 26019ደሕ ሚኒ ባስ ተሽከርካሪ  አንድ መንገደኛ ሴት ካሳፈሩ  በኋላ የያዘችውን ሳምሰንግ የእጅ ስልክና 20 ሺ ብር በመቀማት በኃይል ገፍትረው በመጣል  ለማምለጥ  ሲሞክሩ በስራ ላይ   በነበሩ የታክሲ ተራ አስከባሪዎችና የፖሊሰ አባላት ከነ ኤግዚቢቱ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውንም የአዲስ አበባ  ፖሊስ አስታውቋል።

በተለምዶ ሿሿ እየተባለ የሚጠራው የማታለል ወንጀል የሚፈፀመው በትራንስፖርት ተሽከርካሪ መሆኑን ያሳሰበው  ፖሊስ ህብረተሰቡ ትራንስፖርት ሲጠቀም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ገልፆል።

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

10 Nov, 11:13


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር መስራች አባል ሆነ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፣ ህንድና ብራዚልን ጨምሮ ከብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን በጣምራ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበርን በመመስረት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ዩኒቨርስቲ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

አራቱ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች የመሰረቱት ማህበር በትምህርት በዲፕሎማሲ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በፈጠራ ስራ በጋራ መሰራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

ዩኒቨርስቲው በአዲሱ የራስ-ገዝ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት አጋርነትና አለማቀፋዊነትን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋልአስታውቋል።

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

10 Nov, 11:12


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለክልሉ መምህራን እንዲከፈል ፌደራል መንግስት የፈቀደውን የአምስት ወር ደመወዝ ለሌላ አላማ አውሎታል በሚል ክስ ተመሰረተበት

የትግራይ ክልል የመምህራን ማህበር በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በፌደራል መንግስቱ ላይ የመሰረተው ክስ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚታየ ተገለጸ።በነሀሴ ወር 2016 ዓ.ም ክሱን የመሰረተው ማህበሩ፣ ሁለቱም አካላት ለ17 ወራት ለክልሉ መምህራን መከፈል የነበረበትን ደመወዝ ባለመክፈላቸው መሆኑ ይታወቃል።የትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቃ የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረሚካኤል ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በፌደራል መንግስት ላይ የቀረበው ክስ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየታየ ነው።

"ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የክልሉ ትምህርት እና ፋይናንስ ቢሮዎች ይገኙበታል፣ ክሱም የፌደራል መንግስት ለመምህራን የላከውን የአምስት ወር ደሞዝ ለሌላ አገልግሎት በማዛወራቸው የተሰጣቸውን ስልጣን ያለአግባብ ተጠቅመዋል” የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።በተጨማሪ የፌዴራል መንግስት ደግሞ “የ12 ወራት ደሞዝ ባለመልቀቁ ነው ክሱ የተመሰረተው" ሲሉ አቶ ዳዊት አስረድተዋል፡፡

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

10 Nov, 11:11


ኳታር የሀማስ ሃላፊዎችን ከሀገሯ ለማስወጣት ተስማማች።

ኳታር በሀገሪቱ የሚኖሩ ከፍተኛ የሀማስ አመራሮችን ለማስወጣት ከአሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏ ተሰማ፡፡

ሀማስ በ2012 በሶርያ የእርስ በእርስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ዋና ቢሮውን ከደማስቆ ወደ ዶሃ አዘዋውሯል፡፡

የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ “ኳታር በተለመደው መንገድ ከቡድኑ ጋር ግንኙነቷን መቀጠል እንደማትችል” ስታስጠነቅቅ ሰንብታለች፡፡

ሀገሪቱ በዶሃ የሚገኘውን የቡድኑን ዋና ቢሮ እንድትዘጋ እና ለሀላፊዎቹ ጥገኝነት ከመስጠት እንድትቆጠብ ጫና ስታደርግ መቆየቷን ሲኤንኤን የአሜሪካ እና ኳታር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ዘገባው ሀማስ ታጋቾችን ለመልቀቅ እና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ የቀረበለትን ተደጋጋሚ ጥያቅ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ፤ መሪዎቹ በማንኛውም የአሜሪካ አጋር ዋና ከተሞች ተቀባይነት ሊያገኙ አይገባም የሚል ሀሳብ በዋሽንግተን በኩል መንጸባረቁን ጠቅሷል፡፡

አሜሪካ ከሁለት ሳምንት በፊት ኳታር መሪዎቹን እንድታስወጣ በጠየቀችው መሰረት ኳታር ከሳምንት በፊት ባለስልጣናቱ ከሀገሪቷ ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ሰጥታለች፡፡

በዚህም መሰረት የሀማስ ወቅታዊ መሪ ካሊድ ማሻልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ ዶሀን ለቀው እንዲወጡ ሊደረግ ይችላል፡፡

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

09 Nov, 15:49


ኳታር የሀማስ አመራሮችን ልታስወጣ ነው

ኳታር በሀገሪቱ የሚኖሩ ከፍተኛ የሀማስ አመራሮችን ለማስወጣት ከአሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏ ተሰማ፡፡

ሀማስ በ2012 በሶርያ የእርስ በእርስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ዋና ቢሮውን ከደማስቆ ወደ ዶሃ አዘዋውሯል፡፡

የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ “ኳታር በተለመደው መንገድ ከቡድኑ ጋር ግንኙነቷን መቀጠል እንደማትችል” ስታስጠነቅቅ ሰንብታለች፡፡ 

ሀገሪቱ በዶሃ የሚገኘውን የቡድኑን ዋና ቢሮ እንድትዘጋ እና ለሀላፊዎቹ ጥገኝነት ከመስጠት እንድትቆጠብ ጫና ስታደርግ መቆየቷን ሲኤንኤን የአሜሪካ እና ኳታር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ዘገባው ሀማስ ታጋቾችን ለመልቀቅ እና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ የቀረበለትን ተደጋጋሚ ጥያቅ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ፤ መሪዎቹ በማንኛውም የአሜሪካ አጋር ዋና ከተሞች ተቀባይነት ሊያገኙ አይገባም የሚል ሀሳብ በዋሽንግተን በኩል መንጸባረቁን ጠቅሷል፡፡(via Alain)

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

09 Nov, 15:34


ፑቲን  ትራምፕ ደፋር ነዉ አሉ‼️

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር  ፑቲን ተመራጩን  የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንኳን ደስ አልዎት ብለዋቸዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕም  ለፑቲን እደዉላለሁ    ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሶቺ ቫልዳይ ጉባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት  ፑቲን  ትራምፕ ደፋር ሰዉ ነዉ  ብለዋል፡፡

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት  የተናገረዉን ሁሉ ማመን ባይቻልም ነገር ግን ከዩክሬን ቀዉስ ጋር ተያይዞ  ያነሳዉን ሀሳብ ትኩረት መስጠት  ይገባል ነዉ ያሉት ፑቲን፡፡

ከዚህ በተጨማሪም  ዶናልድ ትራም ደፋር ነዉ ያስገርመኛል ያሉት ፑቲን  ከፖለቲካ ይልቅ የቢዝነስ  ሰዉ  በመሆኑ ብዙ ስህተቶችን  ከዚህ ቀደም  ይሰራ ነበር ሲሉም  አንስተዋል፡፡

ሞስኮ  ከዋሽንግተን ጋር  ለመነጋገር በሯ  ክፍት  ስለመሆኑም  ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ኔቶን አስመልከተዉ ሲናገሩም  የጦር ጎራዉ  ጊዜዉን የሳተ ስብስብ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡

የትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አስቸኳይ  ስብሰባ የተቀመጡት የአዉሮፓ አገራት መሪዎቸ አደጋ ዉስጥ  ነን እያሉ ነዉ፡፡

አውሮፓ ካማላ ወይም ትራምፕ ስለተመረጡ ሳይሆን የራሱን እጣፈንታ የሚወስንበትን አቅም ሊገነባ ይገባል  ብለዋል፡፡

ይህም በመላው አውሮፓ በሚገኙ ሀጋራት ላይ ከፍ ያለተጽዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ኤፒ ዘግቧል፡፡

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

09 Nov, 11:16


መሀመድ ሳላሀ የተቀናጀ ግብርና ልማት እና ቦርከና የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

ዶሮና የዶሮ ውጤት:-

እንቁላል፤ የስጋ ዶሮዎች፥  የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች እና የተበለተ የዶሮ ስጋ በጥራትና በብዛት ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ እንገኛለን።

የእንስሳት መኖ:-

ለእንቁላል ጣይ፤ ለስጋ ዶሮ፤ ለጫጩት፤ ለቄብና ለታዳጊ ዶሮዎች፤  ለበሬ ማድለቢያ፥  ለወተት ላም ፤ ለፍየልና በግ ማድለቢያ ጥራቱን የጠበቀ የተቀነባበረ መኖ በጥራትና በብዛት አምረተን እናከፋፍላለን

በተጨማሪ ለእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ የሚሆኑ ጥሬ እቃዎች ግብአት እኛ ጋር ይገኛሉ፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በማድለብም ሆነ በማርባት በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት የምርቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡

ይዘዙን የፈለጉትን ምርት በጥራትና በብዛት በፈለጉበት ሰዓት እናመርታለን እናቀርባለን፡ በጥራቱና በዋጋው ይደስታሉ

📌ወኪል ለመሆን የምትፈልጉ ይምጡ አብረን እንስራ አትራፊ ይሆናሉ

አድራሻ፡- ወሎ ኮምቦልቻ ሽህ ሳቢር አየር ማረፊያ በሚያስኬደው አድሱ መንገድ  ድልድይ ሳይሻገሩ በአል-ሂጅራ መስጅድ ወረድ ብሎ ቦርክና ዳር ያገኙናል፡፡

ስልክ ቁጥር :- 0910097080
                        0944125879
                        0919977639
  Email: [email protected]
 
 መሀመድ ሳላሀ የተቀናጀ ግብርና ልማት እና ቦርከና የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪ

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

01 Nov, 12:51


ዛሬ በኮንታ በደረሰ የመሬት መሸራተት አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆን ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

መረጃው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

መረጃ 24 ሰአት

01 Nov, 12:49


ቦሌ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ማርያም ማዞሪያ አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ እሳት አደጋ አጋጥሟል።

ዛሬ ከቀኑ 6:38 ላይ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ከሆኑ መኖሪያ ቤቶች የተነሳው እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ የእሳት እና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ  ተናግረዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር 11 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተዋል ተብሏል።

እሳቱ ከዚህ በኋላ ሊስፋፋ የሚችልበት እድል አለመኖሩን የጠቆሙት አቶ ንጋቱ እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ት/ቤት እንዳለ እና ወደዛ የመስፋፋት እድሉ ዜሮ መሆኑን ነግረውናል።እሳቱ ምክንያት እስካሁን በሰው ላይ ያጋጠመ ጉዳት የለም።
(ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የተወሰደ)

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 17:34


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡

ዛሬ ከቤተክርስቲያኗ በወጣው መግለጫ መሠረት ሲኖዶሱ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ማሳለፉን ተመላክቷል።

1. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

2. በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡

3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

4. የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆነ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ
ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

5. የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣

6. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኀበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት መጠናቀቁን በመግለጫው ተጠቅሷል።

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 17:26


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ አደርገ

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 16:37


የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ስለ ሱዳኑ ጦርነት የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎን ጠይቀው አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ሰሞኑን ከሱዳናዊያን ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

ኢሳያስ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት ድል ማድረግ ለሱዳን ቀጣይነት የጀርባ አጥንት እንደሆነ ተናግረዋል ተብሏል።

የውጭ ተጽዕኖዎች ዋናው ማዕከል ዳርፉር መኾኑን የገለጡት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ሱዳናዊያን እገራቸውን ሊበታትኑ ካቆበቆቡ የውጭ ተጽዕኖዎች መላቀቅ እንዳለባቸው መክረዋል።

ፕሬዝዳንቱ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራ ውስጥ ለሱዳናዊያን ስደተኞች መጠለያዎችን ለማቋቋም ጠይቋቸው እንደነበር ጠቅሰው፣ ኾኖም ሱዳናዊያን ስደተኞች ኤርትራ ውስጥ በነጻነት መኖር እንደሚችሉ በመግለጽ ጥያቄውን ሳይቀበሉት እንደቀሩ ተናግረዋል።

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 09:41


✒️"አሮጌው ቤተ መንግስት ውስጥ  470 ኪግራም ወርቅ አግኝተን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል።"

✒️"አበባዬሆሽና ሆያሆዬ ግጥሙ መቀየር አለበት:ትርክት እፈጠረ ነው"

ጠ/ሚ አብይ


Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 09:17


በኢትዮጵያ 3 ወታደራዊ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 72 ፋብሪካዎች ወደ ሥራ የሚገቡ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ተገኝተው በሰጡበት ማብራሪያ ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ ውስጥ ዘጠኝ የጨርቃ ጨረቅ ፋብሪካ፣ 41 የምግብና መጠጥ ፋብሪካ፣ አራት ኮንስትራክሽንና ኬሚካል ፋብሪካዎች እንዲሁም ትልቅ እምርታ ሊያመጡ ይችሏሉ ያሉት ትልቅ ሦስት የወታደራዊ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡

በዚህም ዓመት ከኢንዱስትሪ 12 ነጥብ 8 ዕድገት እንደሚጠበቅ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉ 12 ነጥብ 3 ዕድገት እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል፡፡

"በዚህ ዓመት ኢንዱስትሪ የተሻለ አፈፃፀም ይኖረዋል ተብሎ የተጠበቀው፤ ከኢትዮጵያ ታምርት በተገኘው የተሻለ ማሳያ በመሆኑ ነው" ብለዋል፡፡

ከኢንዱስትሪ ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በተለይም እንደ መብራት ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የተሻለ ሥራ መሰራቱንም ለምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡

ከመከላከያ ጋር ተያይዞ በርካታ ምርቶች ከውጪ እየተገዙ የቆዩ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ይህ ፋብሪካ ከውጪ የሚገቡ የመካለከያ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ያስችላል" ብለዋል፡፡

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 09:09


#ይፈለጋል

በሓበን የማነ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል የህዝብ እገዛ እፈልጋለው ሲል የመቐለ ከተማ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ

የሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዛሬ ጥቅምት 21 እንደገለፀው ከሆነ በክፍለ ከተማው ዓዲ ሓ ተብሎ በሚታወቅ አከባቢ ሓበን የማነ የተባለች እንስት ግፍ በተሞላት መንገድ ግድያ እንደተፈፀመባት  ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ግድያው በፍቅረኛዋ እንደተፈፀመ ለማወቅ ችያለዉ የሚለው ፖሊስ ግድያውን ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አለመዋሉ በመግለፅ ፖሊስ አረመኔያዊ ሲል የገለፀውን ግድያ የፈፀመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ መረጃ ለፖሊስ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል።
Via_degu


Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 09:08


#ሰይፍ ጠጋኙ ሕጻን…  


ለዘመናት ሲዘርፉና ሲገድሉ የነበሩ ሁለት ወንበዴዎች ከፍተኛ ሽልማት የተጣለባቸው ሁለት ሰዎችን ፍለጋ በረሀ አቋርጠው ፍለጋ ያደርጉ ጀመር፡፡

በስተመጨረሻም በለስ ቀናቸውና ተፈላጊዎቹን ሰዎች አገኟቸው፡፡ ተፈላጊዎቹ ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምና ሔሮድስ የሚያሳድደው ሕጻን ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ጋርም ዘመዷ ሰሎሜና ሽማግሌው ዮሴፍ አብረዋቸው ነበሩ፡፡ ወንበዴዎቹ በዕለተ አርብ በቀኝና በግራው የተሰቀሉት ጥጦስና ዳክርስ ናቸው፡፡


ሰሎሜ ጌታን እንዳይጎዱት አስቀድማ መጎናጸፊያዋን ሰጠቻቸው፡፡ እነርሱ ግን ምንም ሳያስቀሩ ሙልጭ አድርገው ዘረፏቸው፡፡ የጌታችን ሰብአ ሰገል ያመጡለት ስረ ወጥ ቀሚስና የወርቅ ጫማውን ጭምር ወሰዱበት፡፡

ከዚያም ከእነርሱ እልፍ ብለው ጭቅጭቅ ያዙ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ወንበዴ ከዘረፈ በኋላ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ይሸሻል እንጂ መች ቆሞ ይማከራል ልጄን ሊገድሉብኝ ነው እንጂ” ብላ አምርራ አለቀሰች፡፡

በቀኙ ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ጥጦስ “እነዚህ ሰዎች አሳዘኑኝ እንመልስላቸው” የሚል ጥያቄ ማንሳቱና የዳክርስ እምቢታ ነበር የጭቅጭቁ መነሻ፡፡

የዘረፉትን በየተራ ይወስዱ ነበርና ተራው የዳክርስ ስለነበር ብሸጠው ብዙ ገንዘብ ያወጣልኛልና አልመልስም ብሎ ተከራከረው፡፡ በመጨረሻም ጥጦስ ወሰነ “ከገሊላ ጀምሮ እንከዚህ የዘረፍነው ላንተ ይሁንና ይህን እንመልስላቸው” አለው፡፡


ዳክርስ በዚህ ሀሳብ ተስማማና ጥጦስ መጥቶ መለሰላቸው፡፡ በዚህ አላበቃም፤ ጌታችንን አቅፎ ጥቂት መንገድ ሊሸኛቸው ወደደ፡፡ አቅፎት ሲሔድም የሚመረኮዘው ሰይፉ ተሰበረበት፤ ደግ በሰራሁ ክፉ እጣ ገጠመኝ ሲል በጣም አዘነ፡፡ በእናቱ እቅፍ የነበረው ጌታችንም የሰይፉን ስብርባሪዎች አንድ አድርጎ ገጥሞ ሰጠው፡፡


ልባችንን ቅን አድርገን ያለንን ሁሉ ለመስጠት፣ ያም ባይሆን ካለን ላይ ቀንሰን ለመስጠት ምን ያህል ዝግጁ ነን? መስጠት ፍጹማዊ ሲሆን ወንበዴው ጥጦስ እንኳን የዘረፈውን መልሶ መንገድ እስከ መሸኘት ድረስ ተጉዟል፡፡ እኛ በሐቃችን እንኖራለን የምንለው ለመስጠት ምን ያህል ተሰጥተናል፡፡ በተለይ ብዙ የምንፈልግ ከሆነ አብዝተን እንስጥ ክፍያው በብዙ እጥፍ ይልቃልና፡፡


ጌታችን አቅፎት ለሚጓዘው ወንበዴ ጥጦስ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ የተናገረውን “እውነት እልሃለሁ ከአዳም ቀድመህ ገነት ትገባለህ” ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረው፡፡ ጥጦስ በዚህ ተደስቶ ይህ ሕጻን ከነቢያት ወገን ይመስለኛል አለው ለጓደኛው፡፡

ይህን ጊዜ ዳክርስ “አዎ ከነቢያት ወገን ቢሆን አይደል አንተን ወንበዴውን ገነት ትገባለህ የሚልህ” ሲል አሾፈበት፡፡

ታዲያ ተሰናብተዋቸው ከሔዱ በኋላ ጌታን ያቀፈበት ጎኑ የልብሱ መዓዛ ተቀየረ ቢያጥበው ልዩ ሽቱ ሆኖለት በ300 ዲናር ሸጠው፡፡ ያን ሽቱ ነበር ዘማዊቷ ሴት ማርያም እንተ ዕፍረት አምጥታ በራሱ ላይ ያፈሰሰችው፡፡ በቅን ልባችን የምሰጠው መስጠት፣ ገዳማውያንን መርዳትና በዓታቸውን ማጽናት በብዙ እጥፍ ይከፍለናል፡፡ የእመቤታችን የስደቷ በረከት ከኛ ጋር ይሁን፡፡ ከቅድስና ስደት ይመልሰን፡፡          

  

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 08:32


"124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን አዘናል።አዲስ አየር መንገድ ለመገንባት ጥናት ተደርጎ ተጠናቋል" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

"124 አውሮፕላኖችን ማዘዝ ቀላል ነገር አይደለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ትልቅ ስኬት ነው" ሲሉ ገልጸውታል።

እንዲሁም "አየር መንገዱ በዓመት ከ20 እስከ 25 ሚሊየን ተጓዦችን ያስተናግዳል" ሲሉ ለምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል።

አክለውም፤ "በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡" ብለዋል

የተጓዦችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ከ100 ሚሊየን እስከ 130 ሚሊየን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል አየር መንገድ ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተደርጎ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

"ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን፤ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡" ብለዋል።"ይሔ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት አንዱ ማሳያ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

Share🔽🔽🔽🔽

https://t.me/qonjowochu
https://t.me/qonjowochu

መረጃ 24 ሰአት

31 Oct, 08:30


ፓርላማ

" እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ! " - አበባው ደሳለው (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ምንድነው ?

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" በባለፈው ዓመት መጨረሻ የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ሰኔ 28 ወቅት ያነሳናቸው በርካታ ከህዝብ ጥያቄዎች ነበሩ።

ነገር ግን እነዛ ጥያቄዎች ስላልተመለሱ ከዛ ብዙም ለየት ያለ ጥያቄ አይደለም የምንጠይቀው ምክንያቱም ችግሮቹ እየተባባሱ ስለመጡ።

በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጻሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር ፣ እገታ ፣ ጾታዊ ጥቃት ፣ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ ከኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ያኔም ነበረ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ። በተለይ በአማራ ክልል ያለው ችግር ደግሞ አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።

አሁንም ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው ፣ ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ ፣ በአማራ ክልል እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።"

በተጠየቀው ጥያቄ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ምላሽ ተከታትለን እናቀርባለን።

መረጃ 24 ሰአት

30 Oct, 18:24


ዜናዎች

1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ነገ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች በአካል ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ የሚሰጡት፣ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባለፈው ወር መጨረሻ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤተና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ የዓመቱ የሥራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ባቀረቡት የመንግሥት ዕቅድ ዙሪያ ይኾናል፡፡

2፤ የሱማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ፣ ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞና ጫና ቢደርስባት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ለቢቢሲ ሱማሌኛ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ቢሂ፣ በሶማሌላንድና ግብጽ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ግብጽ እንድትገባበት መደረጉን ጠቅሰው፣ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሶማሌላንድ ራሷን የቻለች አገር መኾኗን ከተቀበሉ ንግግር ማድረግ እንደሚቻል ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ የሱማሊያና ግብጽ ወታደራዊ ስምምነት የሶማሌላንድን የሉዓላዊ አገርነት ሂደት ለማስቆም ያለመ ነው በማለት ከሰዋል። ባንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ ይኾናል የተባለው የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን ተግባራዊ ላለመኾኑ፣ የሱማሊያ ተቃውሞ አስተዋጽኦ እንደሌለውም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

3፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል። በአደጋው ከሞቱት መካከል አምስቱ ሴቶች እንደኾኑ የጠቀሰው የዞኑ አስተዳደር፣ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ደሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ብሏል። በኹለቱ ቀበሌዎች የመሬት መንሸራተት አደጋ የተከሰተው፣ ባካባቢው ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ እንደኾነ ተነግሯል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን እና ሌሎች አከባቢዎች ባለፈው ዓመት ክረምት የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፉ ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች እንደደረሱ አይዘነጋም።

4፤ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በከተማዋ በአለባበሳቸው የተነሳ ከአራት ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ባስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለከተማዋ ትምህርት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል። ምክር ቤቱ ካለፉት ኹለት ሳምንታት ወዲህ ባንዳንድ ትምህር ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች "በአለባበሳቸው" እና "በእምነታቸው" ላይ ያነጣጠረ “ጫና እና እንግልት” እየደረሰባቸው ይገኛል ብሏል። የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ያወጣው የተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያ የሙስሊም ተማሪዎችን አለባበስ እንዳልወሰነ የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ የአንዳንድ ትምህርት ቤቶች አመራሮች በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የጣሉት እገዳ ግን "ሕዝበ ሙስሊሙን እና መንግሥትን ለማጋጨት" የሚደረግ ጥረት ነው በማለት ኮንኗል።

5፤ የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በ80 ወረዳዎች የወባ በሽታ መከሰቱን ለፋና ብሮድካስት ተናግሯል። በሽታው በተለይ በጎጃም፣ ጎንደር፣ ዋግኽምራና ሰሜን ወሎ ዞኖች በ40 ወረዳዎች በከፍተኛ ደረጃ እንደተስፋፋ ኢንስቲትዩቱ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። በሽታው በከፍተኛ ደረጃ በተስፋፋባቸው ወረዳዎች በሳምንት ከ70 ሺሕ በላይ የወባ ታማሚዎች ሪፖርት ለኢንስቲትዩቱ እንደሚደርስ ተገልጣል። የወባ በሽታ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ ለማንሠራራቱ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል፣ በሽታውን አስተላላፊዋ የወባ ትንኝ መድሃኒቶችን የመቋቋም አቅም ማዳበሯ፣ በሽታው በሕክምና ምርመራ በቀላሉ የሚገኝበት እድል እየጠበበ መሄዱና ግጭቶች በመድሃኒትና በወባ ትንኝ መከላከያ አጎበሮች ሥርጭት ላይ እክል መፍጠራቸው ይጠቀሳሉ።

6፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ስለ ሱዳኑ ጦርነት የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎን ጠይቀው አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ሰሞኑን ከሱዳናዊያን ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። ኢሳያስ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት ድል ማድረግ ለሱዳን ቀጣይነት የጀርባ አጥንት እንደሆነ ተናግረዋል ተብሏል። የውጭ ተጽዕኖዎች ዋናው ማዕከል ዳርፉር መኾኑን የገለጡት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ሱዳናዊያን እገራቸውን ሊበታትኑ ካቆበቆቡ የውጭ ተጽዕኖዎች መላቀቅ እንዳለባቸው መክረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራ ውስጥ ለሱዳናዊያን ስደተኞች መጠለያዎችን ለማቋቋም ጠይቋቸው እንደነበር ጠቅሰው፣ ኾኖም ሱዳናዊያን ስደተኞች ኤርትራ ውስጥ በነጻነት መኖር እንደሚችሉ በመግለጽ ጥያቄውን ሳይቀበሉት እንደቀሩ ተናግረዋል።
[ዋዜማ]

2,158

subscribers

4,286

photos

49

videos