የቴሌቲቪ መተግበሪያን ለማስተዋወቅ ባለመው የቲክቶክ ቻሌንጅ ላይ ተሳትፈው ላሸነፉ ቲክቶከሮች ሽልማት ተበርክቷል።
ከሐምሌ 26 ጀምሮ በተደረገው ቻሌንጅ ላይ በርካቶች ተሳታፊ ሲሆኑ ከፍተኛ ዕይታ እና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኙ ተሳታፊዎች ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።
በ3.4 ሚሊዮን ዕይታ እና 145.7 ተወዳጅነት አንደኛ በመውጣት ነፃነት ታምራት የአይፎን ፕሮማክስ 15 ተሸላሚ ሆናለች።
ያቤፅ በላይ እና ዳዊት ፀጋዬ በተመሳሳይ የ2.1 ሚሊዮን ዕይታ እና በተወዳጅነት ቁጥር ተበላልጠው የ2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በቀጣይም የቴሌቲቪ መተግበሪያ የተለያዩ መሰል ቻሌንጆችን በሚዘጋጀት ይፋ እንደሚያደርግ የቴሌቲቪ መስራች እና ባለቤት አቶ በሱፍቃድ ጌታቸው ተናግረዋል።
ኢግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት ባቀረበው የቴሌቲቪ መተግበሪያ እስከአሁን ድረስ ስምንት ፊልሞችን ተደራሽ በማድረግ ተወዳጅነትን አትርፏል።
#ደቦ_ሚዲያ