በአቪዬሽን ዘርፍ የሚደረጉ የጋራ የምርምር ስራዎችን በአቅም ግንባታ፣ በሰው ሀይል ልማትና መሰል ጉዳዮች ላይ ኢንዱስትሪው እየገጠመው ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል ብሔራዊ የሲቪል አቪዬሽን ፕሮግራም መቀረፁን ተከትሎ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ሲሆን አጥኚ ቡድኑ የመጀመሪያ የሆነውን ሪፖርቱን ( inception report) አቀረበ፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ውይይት አጥኚው ቡድን ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጠቃሚ ግብዓቶችን ተቀብሏል፡፡
ብሔራዊ የሲቪል አቪዬሽን ፕሮግራም ነሀሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በይፋ ስራ መጀመሩን ካስታወቀ ጀምሮ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን ከመሀከለኛ የተቋሙ አመራር አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀቱ፣ የፕሮግራሙ ዋና ፈፃሚ ከሆነው የተቋሙ ሰራተኞች ጋር የተደረገው ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ፣ ራሱን የቻለ ብሔራዊ የትራንስፎርሜሽን ቢሮ መቋቋሙና የትራንስፎርሜሽን ቲም መዋቀሩ ከተሰሩት ስራዎች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በውይይቱ ላይ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ሪሰርች ቡድን አባላት፣ ምሁራን፣ የግል ኦፐሬተሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡