ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች❤ @mirtyefkrtarikoch Channel on Telegram

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

@mirtyefkrtarikoch


ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች❤🇹 (Amharic)

የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች❤🇹 የቴሌግራም ክፍል ነው በእርስዋ ሚሊዮች ላይ የፍቅርን ታሪኩን እና አባባሎችን ማስታወቅ ማለት ነው፡፡ ይህ እትም በወርሃዊ ሁኔታ ለመመልከት ለሚያስፈልጋችሁ የፍቅርም እና አባባሎችም መምሪያ መንፈሳዊ ሆኖ አስቀመጠችው፡፡ ከዚህ በፊት ተጨማሪ ክሊክ፣ በረሌ፣ በድምፅ፣ በመርህ፣ በዘረባና በሕያዋን ታሪኮችን ለማስወገድ እጅግ ሆኖ መመልከት የሚገባውን የፍቅር ታሪኮቹን በቴሌግራሙ እና አባባሙ ለመደምም አዲሱ መተግበስ እንደምንሰጥህ በመጠቀም ይህን ክፍልን ቀጣሪ አስወግድ፡፡

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

30 Jan, 22:05


ትዝ ሲለኝ ሚስቴን ሳልስማት ነው የወጣውት
.
.
.
.
ልስማት ከተመለስኩ በኋላ ትዝ ሲለኝ ሚስት የለኝም😏😏😂
በነገራችን ላይ ትዳር ማለት Work Shop ነው
.
.
.
.
ባል Work ያደርጋል ሚስት ደሞ Shop ታደርጋለች😏😏😂

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

29 Jan, 21:45


ባል እና ሚስ በተጋቡ የመጀመሪያው ቀን ፣ ማንም እቤታቸው ቢመጣ በራቸውን ላለመክፈት ይስማማሉ ። ከዛ በመጀመሪያ ቀን ፣ የባል ወላጆች እነሱን ለማየት መጡ ። ባል ፣ ሚስት ተያዩ ባል ፣ በሩን መክፈት ፈለገ ፣ ግን በስምምነታቸው መሰረት
በሩን ሳይከፍት ቀረ ፣ ወላጆቹም ተመልሰው ሄዱ ። ከተወሰነ ቀን በኋላ የሚስት ወላጆች እዛው ቤት ፣ ተከሰቱ ። ሚስት ፣ ባል ተያዩ ፣ ምንም እንኳ ስምምነት ቢኖራቸውም ፣ ሚስት ስምምነቱን ጥሳ እያለቀሰች ፣ ለባል ቀስ ብላ ቦጆሮው ፣ እንዲህ አለች ፣ ወላጆቼ ላይ ይሄን ማድረግ አልቻልኩም ፣ ብላ በሩን ከፈተች ፣ ባል ምንም አልተገረመም ከብዙ አመታት በኋላ ባል እና ሚስት- 4 - ወንድ ልጆችን እና አምስተኛዋ ሴት ልጅ ነበረች ። አባት :- አምስተኛዋ ሴት ልጅ ስትወለድ ትልቅ ድግስ አዘጋጅቶ ፣ ሰው ጠርቶ ጋበዘ ፣ ሚስትም በድግሱ ተገርማ ፣ ባልን አዲስ ስለተወለደችው ህፃኗ ልጅ ለምን እንደዚህ እንደደገሰ ጠየቀችው ? ባልም እንዲህ ሲል መለሰላት ፣ በር የምትከፍትልኝ ሴት ልጅ እሷ ነች አላት ። ሴት ልጅ ክቡር ናት😭

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

28 Jan, 18:49


በፍቅር ታሪኬ የደረሰብኝ ፈተና እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አይደለም፡፡ ዕድሜዬ 21 ነው፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ አንድ ሰው ተዋውቄ በአጭር ጊዜ በፍቅር ከነፍን፡፡ ሰው ጉድ እስኪል ፍቅራችን የሰፈር መነጋገሪያ ርዕስ ሆነ፡፡ ቤተሰቦቼ ግን አርፌ ትምህርቴ ላይ እንዳተኩር ስለፈለጉ ከእሱ ጋር እንዳልታይ አስጠነቀቁኝ፡፡ እኔ ግን እሺ አላልኩም፡፡ በኋላ ብዙ ታሪክ ተፈጥሮ ቤተሰቦቼን ትቼ ከፍቅረኛዬ ጋር ቤት ተከራይተን መኖር ጀመርን፡፡ ከቤተሰቦቼ ጋር ተቆራረጥኩ፡፡ አንድ ዓመት ቆይቶ ግን ፍቅራችን እንደመጀመሪያው አልሆን ብሎ መጋጨት አበዛን፡፡ በኋላም ሌላ የማልጠብቀው ነገር በማድረጉ ጥዬው ወጣሁ፡፡ ያኔ አማራጭ ስላልነበረኝ ወደ ቤተሰቦቼ ፊቴን አዞርኩ፡፡ እናም ከአድካሚ የቅርብ ዘመዶቼ ሽምግልና በኋላ ወደ ቤተሰቦቼ ተመለስኩ፡፡ ታዲያ ከወራት በኋላ ይኸው ፍቅረኛዬ እንድንመለስ እየጠየቀኝ ነው፡፡ በጣም ስለምወድው እንቢ ማለት አቅቶኛል፡፡ ቤተሰቦቼ ፈፅሞ እንዳላገኘው ቢያስጠነቅቁኝም አልፎ አልፎ ተደብቄ አገኘዋለሁ፡፡ ህይወቴን ዳግም የሚያመሰቃቅል ጉዳይ እየመሰለኝ መቀጠል እፈራለሁ፡፡ ፍቅሩ ደግሞ ሊወጣልኝ አልቻለም፡፡ ቤተሰቦቼን ማሳመኑ ደግሞ የሚታሰብ ነገር አይደለም፡፡ ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ፡፡
ምን ላድርግ?

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

27 Jan, 18:29


አንድ አጭር የፍቅር ታሪክ ልጋብዛቹ!

በአንድ ወቅት ሁለት እጅግ የሚዋደዱ ፍቅረኛማቾች💃 ነበሩ፡፡ በፍቅራቸው ሙሉ አካባቢው ይቀናባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ግን በአንድ ሆቴል ልጆቷ በድንገት ከሌላ ወንድ ጋር ትታያለች፡፡ በዚህ ሰአት የሆነ ሰው ደውሎ "ና የፍቅረኛህን ቅሌት ተመልከት" ብሎ ይነግረዋል፡፡ ልጁም ካለበት በፍጥነት ሲመጣ ክፍል ይዘው ገብተዋል፡፡ ገቡ ወደተባለበት ክፍል ቀርቦ ሲያዳምጥ ከውስጥ ይሳሳቃሉ፡፡ እስከመጨረሻው የመታገስ አቅም አልነበረውም፡፡
በኔ ላይ ሌላ ወንድ ? ሲል ይናደዳል😡፡፡ በዚህ ግዜ የሷ ጉዋደኛ የሆነች ልታፅናናው ትቀርበዋለች፡፡ እሱም አጋጣሚውን በመጠቀም እንደውም ላስቀናት በሚል እሷ በምታየው ቦታ ጓደኛዋን እየወሰደ ያዝናናታል እንደፍቅረኛ አድርጎ ለሰው ያወራል፡፡
ከ ወር ቡሀላ ፍቅረኛው ሞተች፡፡ በዚህ ግዜ በእናቷ በኩል አንድ ደብዳቤ አስቀምጣለት ነበር፡፡ እሱ የኔ ግፍ ነው ብሎ በቀብር ስርአቱ ላይ እንኳን አልተገኘም፡፡ እናትየዋ ባለበት ሄዳ የልጇ አደራ የሆነውን ደብዳቤውን ሰጠችው፡፡ ደብዳቤው ይህን ይላል፡፡
😍😍 "ውዴ የኔ ፍቅር አንተ አዝነክብኛል እኔ ግን ተደስቻለው፡፡ ያን ቀን ሆቴል ደውዬ እንድትመጣ ያደረኩት እኔ ነኝ፡፡ በዛ ክፍል ውስጥ ምንም አልተፈጠረም፡፡ አንተ በኔ ተናደክ ወደሌላ ሴት እንድትሄድ የሰራውት ድራማ ነበር፡፡ በሀዘንህ ሰአት ያፅናናችክ ጉዋደኛዬ እኔ ነኝ የላኳት፡፡ እሷ በጣም ትወድካለች ፡፡ እንዳትተዋት፡፡ አንተ እኔን ለማስቀናት ፍቅር ስትሰጣት ሳይ እኔ እደሰት ነበር፡፡ ያንን ፍቅር ከልብህ አድርገው፡፡ ደስታህን አይቼ በመሞቴ እድለኛ ነኝ፡፡ ቢያንስ ብቻክን አልተውኩህም፡፡ ይሄንን ያደረኩት ለመሞት 30ቀን ብቻ እንደቀረኝ ሳውቅ ነው፡፡"

"ፍቅር ማለት አብረው ላሉት ብቻ ሳይሆን ትተውት ለሚሄዱትም ደስታ መጨነቅ ነው፡፡"
💞 መልካም_ጊዜ

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

24 Jan, 10:21


ፍቅረኛዬ የሚኖረው ውጭ ሃገር ነው፡፡ የተዋወቅነው የዛሬ ዓመት ለእረፍት አዲስ አበባ መጥቶ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ያህል ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን ወደ መጣበት ከተመለሰ በኋላ ዕድሜ ለቴክኖሎጂ በየቀኑ ማውራት ቀጠልን፡፡ ጥሩ ተግባባን፡፡ ከዚያም በሄደ በስድስት ወሩ ተመልሶ አብረን የተወሰነ ጊዜ አሳለፍን፡፡ ሁለተኛው ቆይታው እሱን በተሻለ እንዳውቀው አድርጎኛል፡፡ በስልክ ማውራት በአካል የመገናኘትን ያህል እንዳልሆነ የተረዳሁበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ብዙ የማያግባቡን ነገሮች እንዳሉ እየተሰማኝ መጣ፡፡ በዚህ መሃል ደግሞ የቫለንታይንስ ቀን ሲከበር በጣም የተለየ ዝግጅት አድርጎ ሰርፕራይዝ አደረገኝ፡፡ ተንበርክኮ የአግቢኝ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ ምንም እንኳ ጥያቄዎች እየተመላለሱብኝ የነበሩ ቢሆንም እምቢ ማለት የምችልበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ የነበሩት እንግዶች ብዛትና አጠቃላይ ነገሩ ያንን ማድረግ አላስቻለኝም፡፡ ይሄ እንዳለፈ ደግሞ ሽማግሌ ስለመላክ ማውራት ጀመረ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ አይሆንም ከማለት ብዬ ሰበብ እየፈጠርኩ አዘገየሁት፡፡ አሁን እዛ ሆኖ ወሬው ስለሚላከው ሽምግልና ነው፡፡ በበኩሌ አይሆነኝም ብዬ ባልወስንም ተጨማሪ ጊዜ መገናኘትና አብረን ማሳለፍ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ በግልፅ እንቆይ ብለው ግንኙነቱን ሊያቆምና ላይመጣም ይችላል ብዬ እፈራለሁ፡፡ በዚያ ላይ ዕድሜዬ እየሄደ ስለሆነ ቤተሰብ እንዳገባ ጫና ያደርግብኛል፡፡ እኔም ማግባቱን እፈልገዋለሁ፡፡ ግን ያልሆነ ነገር ውስጥ መግባት አልፈለግኩም፡፡ ግራ ገብቶኛል፡፡ ምን ልወስን?

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

23 Jan, 20:57


በፍቅር ስድስት ዓመታት ቆይተናል፡፡ ነገር ግን ግንኙነታችን ጥል የበዛበት ነው፡፡ ከአስር ጊዜ በላይ ተጣልተን ታርቀናል፡፡ አሁን ደግሞ ለመጋባት ወስነን ሽር ጉድ ላይ ነን፡፡ የእንጋባ ጥያቄውን ያቀረበው እሱ ነበር፡፡ እኔም ተቀብዬ ሽማግሌ ተልኮ ቀን ቆርጠናል፡፡ አሁንም ታዲያ መጣላታችን አልቆመም፡፡ በተለይ እሱ በሰርጉ ዝግጅት ላይ የሚያሳየውን ቸልተኝነት ሳይ በጣም እየተናደድኩ ነው፡፡ ወደፊትም አብረን ስንሆን የሚጠብቀን ኑሮ በፈተና የተሞላ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡ ቢሆንም ሁኔታዎችን እያየሁ ግን ማቆም ወይም ማስተካከል አልቻልኩም፡፡ ዝም ብዬ በደመነፍስ ወደ ትዳር እየገባሁ ነው፡፡ ችግራችንን እንዴት እንደምንፈታ አላውቅም፡፡ መለያየት ይሻላል ብንል እንኳ ለእሱም መንገዱ ጠፍቶብኛል፡፡ ምን ላድርግ?

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

23 Jan, 14:50


ድንግል ነኝ ብላኝ አጣሁት
😭😭🤔

ሰላም ቤተሰብ ምክር ፈልጌ ነበር ፍቅረኛ አለችኝ እና አንድ ነገር ላይ አልተማመንም ፣
ከአንተ በፊት በፍፁም ከሌላ ጋር ግንኙነት አላደረኩም አለችኝ ፣
እኔ ደግሞ የመጀሪያሽ ከሆንኩ ድንግልናሸን የት ሄደ ስላት መልስ ታጣለች : ልታምን አልቻለችም መጀመሪያ ስቀርባት ድንግልና አላት ብየ ሳይሆን ልጂቷን ስለምወዳት ነበር በመሐል እሷ ግንኙነት ሳንጀመር ድንግል ነኝ አለችኝ : እኔ ደግሞ ከሌላ ጋር ግንኙነት ማድረግሽን እመኝ ካመንሽ እንቀጥላለን ካላመንሽ ግን አብረን አንቀጥልም እያልኳት ነው አስካሁን እሷ አላመነችም :ጭራሽ ብዙ አይነት ድንግል አለ ከፈለክ ጠይቅ ትለኛለች ፣
ቆይ የማይገኝ ድንግል አለ እንዴ?
ስለ ቀና ምክራችሁ አመሰግናለሁ።

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

22 Jan, 20:03


ሃሳብ ስጡ

ባለትዳር ነኝ ካገባሁ አመት ሆኖኛል፡፡ባለቤቴን በጣም እወደዋለሁ፡፡አብረን በምንኖርበት ጊዜ እህቴ ብዙ ጊዜ እኔ ቤት እየመጣች ታድራለች፡፡ከባለቤቴ ጋር በጣም ይቀራረባሉ፡፡የላፋሉ ይሳሳቃሉ እኔ ፈጽሞ በሌላ ነገር ተርጉሜው አላቅም ነበር፡፡ነገሩ ግን እየበዛ እኔን ችላ እያለ ከእሀቴ ጋር ያለው ነገር እየጎላ መጣ፡፡እኔ እሱ ቤት ውስጥ ስንሆን ደስተኛ አይሆንም፡፡እህቴ ለምን እንዳልመጣች ይጠየቀኛል፡፡እኔ ቤት በማልኖርበት ጊዜ ራሱ ቤት ውስጠ አንድ ላይ ይሆናሉ፡፡መጠራጠር ጀመርኩ ሰውም እህቴና ባለቤቴ የተለየ ግንኙነት እንዳላቸው ነገሩኝ፡፡በጣም ደንግጬ ባለቤቴን ስጠይቀው እና ምን የጠበስ ብሎኘ ቁጭ፡፡ምን ማለት ነው ስለው እንዴት የሰው ወሬ ታምኛለሽ ብሎ ጭራሽ እኔን መቆጣት ጀመረ፡፡እህቴን እያለቀስኩ ስጠየቃት ከሱ ጋር ግኑኝነት ከጀመረች እንደቆየች እና ይቅር በይኘ ብላ ጉልበቴ ላይ ወደቀች፡፡አሁን ምን ማረግ እንዳለብኘ ግራ ገብቶኛል፡፡ምን ላድርግ?

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

22 Jan, 14:52


ትዳር ውስጥ የገባሁት በጣም በጥድፊያ ነው። በሚገባ የምንተዋወቅበትን በቂ ጊዜ ያለማሳለፋችንን ጉዳት ያየነው ገና በመጀመሪያዎቹ የትዳር ወራት ነው። በዚህ መሃል ከምንኖርበት ኮንዶሚኒየም ጎረቤት ከሆነ ሰው ጋር በጣም መግባባት ጀመርኩ። ሳናስበው ፍቅር ውስጥ ገባን። ባለቤቴ ምንም ባያውቅም የሰፈር ሰዎች ግን የሚጠረጥሩ ይመስለኛል። ስህተት እየሰራሁ እንደሆነ ባውቅም ማቆም ግን አልቻልኩም። አሁንማ ጎረቤቶችን መፍራት ሁሉ ትቼያለሁ። የመጣው ይምጣ ባይ ሆኜያለሁ። ትዳሩን ትቼ ከዚህ ሰው ጋር መሆን እፈልጋለሁ። ግን ደግሞ እሱ ደግሞ ስለሁለታችን የወደፊት ሁኔታ እንዲነሳ አይፈልግም። በማሳልፈው ድብቅ የፍቅር ጊዜ በጣም ደስተኛ ብሆንም አጠቃላይ ሁኔታው ግን ግራ ያጋባል። ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገሩኝ? አርፈሽ ትዳርሽን አጥብቂ ብቻ አትበሉኝ።

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች

21 Jan, 19:45


የተዋወቅነው ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ በጣም ደስ የሚል ፍቅር ውስጥ ነበርን፡፡ ከተዋወቅን ከስድስት ወር ገደማ በኋላ አብረን እንድንተኛ ብገፋፋትም ድንግል እንደሆነችና ትንሽ እንድንቆይ ጠየቀቺኝ፡፡ ሽማግሌ ልኬ መጋባት እንዳለብንም ነገረቺኝ፤ ነገር ግን ያንን ሳላደርግ ቆየሁ፡፡ የዛሬ ዓመት አካባቢ ለሥራ ጉዳይ ካለሁበት ከተማ ወደ ሌላ ቦታ ሄጄ አራት ወራት ቆይቼ ተመለስኩ፡፡ እንደመጣሁ ሰሞን ተነፋፍቀን ስለነበር እኔ ቤት አድራ ለመጀመሪያ ጊዜ ግንኙነት ስንፈፅም ግን ድንግል አለመሆኗን ተረዳሁ፡፡ ምክንያቱን ስጠይቃት እኔ ባልነበርኩበት ሰሞን አንድ የወንድሟ ጓደኛ በመጠጥ አታሎ ጉድ እንዳደረጋት ምላ ተገዝታ ነገረቺኝ፡፡ ሁኔታዋ ስላላሳመነኝ ፍቅራችን እንዲቆም አደረግኩ፡፡ እሷ ግን ልትለቀኝ አልቻለችም፡፡ ስህተት እንደሆነና ከእኔ ጋር መሆን እንደምትፈልግ እየነገረች መግቢያ መውጫ አሳጣቺኝ፡፡ በእርግጥ እኔም እወዳታለሁ፡፡ ግን አምኖ መቀበል ከበደኝ፡፡ አብሬያት ለመሆን እወስንና መልሼ እየፈራሁ እተወዋለሁ፡፡ ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ፡፡ መላ ስጡኝ፡፡

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

01 Jan, 10:31


ባልና ሚስት ይጣሉና ሽማግሌ ይሰበሰባል። ከዚያም ሁለቱም ችግራችሁን ተናገሩ ሲባሉ ...
ባል፦ "እኔ ከስራ ደክሞኝ ስመለስ ማረፍ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ልጆችን እያንጫጫች አያሳርፉኝም" አለ
ሽማግሌዎቹም "ሌላስ?" ይሉታል
"እኔ ከስራ ስመለስ ልጅ ያዝ ትለኝና ወጥ ትሰራለች። የልጅ ወተት ታፈላለች። ምናለ ሳልመጣ ጨርሳ ብጠብቀኝ ተቀምጣ እየዋለች" ይላል በንዴት።

ሚስትም በሰዎቹ ፊት "ከዚህ በኃላ በፍፁም አንረብሸውም" ብላ ይቅርታ ስለጠየቀች ሽማግሌዎቹ ትተዋቸው ይሄዳሉ።

በነጋታውም ሚስት ልጆቿን ይዛ እናቷ ቤት ሄደች። ከስራ ሲመጣ ቤቱ ተቆልፏል። ልክ ከፍቶ ሲገባ ቤቱ እጅግ ይቀዘቅዛል። ከሰል ለማቀጣጠል ቢሞክር እምቢ አለው። ልብሱን ደራርቦ ሚስት ሰርታ የነበረውን
ጠራርጎ በላ። ዝምታው ሲጨንቀው ቴሌቪዥን ከፍቶ ለማየት ሞከረ ግን የለመደው የልጆቹ ድምፅ ናፈቀው እና እየከፋው ተኛ።

ጠዋት ሲነሳ ያ የሚጣፍጠው ቁርስና የሚወደው የሚስቱ ፈገግታ የለም። ከፋው። ፊቱን ታጥቦ ወደ ስራው ሄደ። ቁርሱንም ውጪ በላ ግን አላረካውም። ቀኑ እንደከበደው ዋለ። ስልኩን ቢያይም አትደውልለትም። ውሎ ሲመለስ ራቱን ውጭ በልቶ ከጓደኞቹ ጋር ቢያመሽም በመጨረሻ ያ ባዶ ቤት ጠበቀው። ለቅሶ ቤት ይመስል መግባት አስጠላው። ዞር ብሎ ሲያስብ ለካ ያለ ሚስቱ ጎዶሎ ነው።
ለካ ልጆቹ ረባሾቹ ሳይሆኑ አጫዋቾቹና የመንፈስ እርካታው ናቸው።

ከዚያ በኃላ "በእጅ የያዙት ወርቅ ሆናችሁብኝ ጥቅማችሁን ስላልተረዳሁ በጣም በድያችኃለሁ። እባክሽ ይቅር በይኝ ውዷ ሚስቴ!" ብሎ በሽማግሌ ታረቃትና በሰላም ኖሩ።
***
መልዕክቱ፦ ሚስቶች ሸክሞች ሳይሆኑ የቤቱ ተሸካሚዎች፣ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች ናቸው። ልጆች የቤቱ ሁከት ፈጣሪዎች ሳይሆኑ ደስታና ሙቀት ፈጣሪዎች ናቸው።
ስለዚህ ደስታ የሚሰጠንን ነገር ከማጣታችን በፊት ቀድመን ለይተን አውቀነው ተገቢውን ቦታ እንስጠው ለማለት ነው።

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

31 Dec, 21:15


ያልወደቅነው የሚጥል ነገር ስለሌለ ሳይሆን:
በማይጥለው ጌታ እጅ ስለተያዝን ብቻ ነው!!!

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

29 Dec, 15:32


ሀገረ መንግስት ማለት ምን ማለት ነው ?
ሀገረ መንግስት ማለት ፦ የሚታወቅ ወሰን ያለው ፣ ህዝብ ያለው ፣ ሉዓላዊነት ያለው ፣ መንግስት ያለውና አለማቀፋዊ እውቅና ያለው ማለት ነው።
እነዚህን አምስቱን ነጥቦች ያላሟላ ሀገረ መንግስት ሊባል አይችልም።
መንግስታት ሊቀያየሩ ይችላሉ ፤ ሀገረ መንግስት ግን አይቀየርም ። ፀንቶ ይኖራል እንጂ ።
ነገር ግን ከኛ አንፃር ስናየው መንግስታት ሲቀየሩ ሀገረ መንግስት የሚቀየር የሚመስላቸው ዜጎች በርካታ ናቸው።
ይህ የሚያሳየው በሀገረ መንግስት ግንባታ/ state building / በኩል አለመስራታችንና ይባስ ብሎ ከአንድነቶቻችን ይልቅ በልዩነቶቻችን ላይ ያተኮረ
የከፋፍለህ ግዛው አይነት ፓለቲካ ውስጥ መኖራችን ነው።
ይሁን እንጂ የሀገር ሉዓላዊነት ( ክብር) ፣ የህዝቦች ጥቅምና የዜጎች ክብር ፣የሀገር ሰንደቅ ዓላማ ጉዳዮች ላይ አንድ አይነት የጋራ እሳቤ ሲኖረን ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት እንችላለን።

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

06 Nov, 03:13


😃

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

27 Sep, 22:45


ምርጥ ምርጥ አባባሎች ከሀገራት።።።

🌷 ያለሰዓቱ የሚጮኽ ዶሮ መንጋቱን ሳይሆን መታረዱን
ያውጃል። (( #ኢትዮጵያዊያን ))

🌹 በችግር ጊዜ ብልህ ሰው ድልድይ ሲገነባ፤ ሞኝ ደግሞ
ግድብ ይገድባል። (( #ናይጄሪያዊያን ))

🌹 ብዙ በተናገርን ቁጥር ስህተት ለመናገር እየተዘጋጀን
መሆኑን አንርሳ፡፡ (( #የበርማውያን ተረት ))

እውነቱን ላለማየት ዓይናችንን የምንጨፍን ከሆነ ልንማር የምንችለው
ከአደጋ ብቻ ይሆናል። (( #ኬንያዊያን ))

በአንበጣዎች መካከል የሚደረግ ፀብ ለከብቶች መዝናኛ
ነው።" (( #ቦትስዋናዊያን))

አይጥ በድመት ከሳቀች አጠገቧ ጉድጓድ አለ ማለት ነው።
(( #ናይጀሪያን))

ክፉ ታሪክ ለማወቅ እንጅ ለመድገም አይነበብም። (#የሱዳኖች
አባባል)

ራሷን ከፍ ከፍ የምታደርግ ማሽላ አንድም ለወፍ አልያም ለወንጭፍ።
(( #ኢትዮጵያውያን))

በረሮ ዶሮዎችን የመምራት ሐሳብ ካለው፤ ቀበሮን ጠባቂው አድርጎ
መቅጠር ይኖርበታል።" (( #ሴራሊዮናዊያን))

የተኩላ እራት መሆን ካላማረህ በግ አትሁን፡፡ (( #ሩስያኖች ))

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

09 Sep, 11:52


ሀይ ቤተሰብ
አዲስ ዩቱብ ከፍቻለሁ ገብታቹህ ሰብስክራይብ አድርጉ🙏

https://youtube.com/@ikramahmadyoutube2707?si=iKA6xwLeOmAwOP3S

ምርጥ የፍቅር ታሪኮች እና አባባሎች🇹

30 Jul, 20:27


በህይወትህ ውስጥ ለማሸነፍ 5 ህጎችን ተግብር

1ኛ: እቅድህን ለሰዎች መናገር አቁም
2ኛ: እምቢኝ ማለትን ልመድ
3ኛ: መወላወልህን አቁመህ ወስን
4ኛ: ለስኬትህ በሚጠቅሙህ ሰዎች መሃል ሁን
5ኛ: ጊዚያዊ ደስታን ከሚሰጡህ ነገሮች ራቅ