Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏 @ethomunzuma Channel on Telegram

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

@ethomunzuma


Kedir Al Hadra@Islamic items

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida (English)

Are you looking for a channel that brings you the best Islamic items, Menzuma, and Neshida? Look no further than Kedir Al Hadra Official! This channel, run by Kedir himself, is dedicated to providing high-quality content related to Islamic teachings and culture. From beautiful recitations of Menzuma and Neshida to informative posts about Islamic items, this channel has it all.nnWho is Kedir Al Hadra? Kedir is a talented individual who has a deep passion for spreading the beauty of Islamic teachings. Through his channel, he aims to educate and inspire his followers to connect with their faith on a deeper level.nnWhat is Kedir Al Hadra Official all about? This channel is your one-stop destination for all things related to Islamic items, Menzuma, and Neshida. Whether you're looking to listen to calming recitations or learn more about the significance of Islamic items, Kedir Al Hadra Official has something for everyone.nnJoin Kedir Al Hadra Official today and immerse yourself in the rich world of Islamic culture and teachings. Stay updated with the latest content and connect with like-minded individuals who share your love for Islam. With Kedir Al Hadra Official, you'll not only be entertained but also enlightened on your spiritual journey. Don't miss out on this incredible opportunity to expand your knowledge and deepen your connection to your faith. Join now and experience the beauty of Islamic items, Menzuma, and Neshida with Kedir Al Hadra Official!

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

07 Sep, 15:46


https://youtube.com/watch?v=BNpEbeivXZA

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

02 Aug, 16:41


#2024 ተለቋል
በዚህ ሊንክ ይከታተሉ
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/rLu5-aaw0O0?si=_GzGGUz2uf3tp3jj

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

15 Jul, 08:09


#የዓሹራእ ፆም
__
  ያለንበትን(የሙሐረምን)ወር አስረኛ ቀን(ዓሹራእ)መፆም የተወደደና የላቀ ምንዳ እንደሚያስገኝ እንዲሁም ያለፈውን የአንድ አመት ወንጀል እንደሚያስምር ጠንካራ በሆኑ በነብያዊ ሀዲሶች ተገልፀዋል።
ኢብኑ አባስ(ረዐ)የአላህ መልእክተኛ(ሰዐወ)መዲና ሀገር በመጡበት ሰዓት አይሁዶች የአሹራእን ፆም ሲፆሙ ተመለከቷቸውና ለምን እንደሚፆሙ ሲጠይቋቸው:ይህ ቀን በጎ ቀን ነው:አላህ(ሱወ)የኢስራኢል ልጆችን ከጠላቶቻቸው ያዳነበት ቀን ነው:ነብዩላህ ሙሳም ይፆሙት እንደነበረ ተናገሩ:በዚህ ጊዜ ነብዩ(ሰዐወ)እንደዛማ ከሆነ ከናንተ የበለጠ እኔ ለዚ የተገባሁ ነኝ በማለት:እሳቸውም ፆሙት:ሰዎችንም አዘዙ"።
ይህ ቀን አላህ(ሱወ)ብዙ ተዓምራቶችን ያሳየበት ቀን ነው:አንባገነኑ ፊርዐውን ከነ ወታደሩ የሰጠመበት:የነብዩላህ ኑህ(ዐሰ) መርከብ ከዛ ከባድ ማዕበል በዃላ የተረጋጋችበት ቀን ነው:ስለዚህ ይህን ቀን በመፆም ምስጋናችንን እንግለፅ:ለኛም በዚ ሰዐት የናፈቀንን ፍቅር ሰላም አንድነትን እንዲሰጠንና:አዛ ያረገንን ጥላቻና ዘረኝነትን እንዲያነሳልን አስበን እንፁም.......ወዳጆቼ የምንም አይነት ችግር መፍትሄ ሚገኘው ከአላህዬ ነው:ወደሱ በመቅረብ:እሱን በማስደሰት ችግራቸን ይወገዳል:አልገራ ያለው ይገራል።
      ይህን ቀን መፆም ሌላውና ትልቁ ትሩፋት ባሳለፍነው አመት ሰይጣንም ይሁን ነፍሳችን አሳስቶን የሰራናቸውን ወንጀሎች እንዲታበሱልን ያደርጋል:ይህን ታላቅ ብስራት ነብያችን(ሰዐወ)በሀዲሳቸው ገልፀውልናል።
  በዚሁ አጋጣሚ ዘጠነኛውንም ቀን(ታሱዐእ) አያይዘን መፆም ይወደዳል:ነብዩ(ሰዐወ)እስከሚቀጥለው አመት አላህ ካቆየኝ ዘጠነኛውንም እፆማለው ብለው ነገር ግን በመሀል ሚቀጥለው አመት ሳይደርሱ ወደ አኼራ ሄዱ።
   ኢማሙ ነወዊ(ረዐ)ዘጠነኛውን ቀን የምንፆምበት ምክንያቶች ሲጠቅሱ በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ዋና ምክንያት ያስቀመጡት ከአይሁዶች ጋር ላለመመሳሰል ነው:እነሱ አስረኛውን ብቻ ነጥለው ስለሚፆሙ ማለት ነው።

(ዓሹራእ) ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ማለት ነው፤ነገር ግን አስቀድሞ ከ9 ኛው አልያ አስከትሎ ከ 11ኛው ቀን ጋር መፆም ይወደዳል
____
# ለሌሎች አስታውሱ !
ማስታወስ ለምእመናን ይጠቅማል !

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

02 Jul, 05:07


በተሳሳትንባቸው ወይም አዳልጦን በወደቅንባቸው ጉዳዮች ላይ ሁሉም ፈላስፋ ይሆናል። ሀሳብ ያነሳብሃል ሀሳብ ይጥልብሃል፣ ይኮንንሃል ይዘባበትብሃል። እራሱን አንተ የነበርክበት ቦታ ላይ አስቀምጦ ሊረዳህ የሚፈልግ ሰው እምብዛም ነው። በግላጭ ካገኘህ አይደለም ለሹማምንቶቹ ለተመላላሽ መንደርተኛ ሁሉ ያሰጣሃል። ከዙሁር በኋላ ያለው የቡና ማጣጫ ያደርጉሃል😁። "አይይይ እርሱ ልጅኮ" ይባልልሃል። ለዚህም ነው “ሁሉም ባልደረሰበት መከራ ውስጥ ምሁር ነው” የሚለው ግብፃዊው አሰላሳይ መህሙድ ዓቃድ። የስህተትም የችግርም መከራ ካገኘህ አንዳንድ አንደበቶችና አይኖች ለጉድ ናቸው። ዞሮ ዞሮ ግን… ህይወትህን፣ አላማህን፣ ሙከራህንና የተጋፈጥካቸውን ነገሮች የሚያውቅ ማንም የለም። እና… እስቲ ጎዳናውን እንሂደው… ከአላህ ጋር… እስክንደርስ!!

ከ fuad kheyredin የ fb ገፅ የተወሰደ

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

28 Jun, 05:41


https://youtu.be/FF3THTTkXXY

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

28 Jun, 05:41


🟢 ሰሉو ዐለ ረ፟ሱوል ﷺ
___
አንድ ሰው ነበረ ጭንቀት የበዛበት
ከጋራ የከፋ መከራ ያደረበት
መራመድ ያቃተው መውጣት ያን ዐቀበት
የኡሑድን ወዳጅ ነቢን ቢጠራበት
አብዝቶ ቢያወርድ በርስዎ ላይ ሰለዋት
ጭንቀቱ ተነሳ ሸክሙ ቀለለት
ለአባቶ የሆኑ ለልጆ አይሳኖት !!!
____
{ وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ ۚ  }
{ በውስጣችሁም የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ፡፡}
[ ሱረቱ አል-ሁጁራት - 7 ]

  ሰለዋት ከሰዪዳችን ጋር ያለህን አብሮነትን ምታደረጅበት፣የፍቅርን ሲቃ፣የናፍቆትን ሮሮ የምታሰማበት፣ተሐድራዎ አዳራሽ የምትገባበት፣በእርሳቸው ላይ አውርደህ፣አንተ ምትልቅበት ሚዕራጅህ ነው !!!

አላ፟ሁመ፝ ሰሊ፟ ወሰሊ፟ም ዐላ ሰዪ፟ዲና ሙሐመድ ﷺ

ሰለዋት ወደርሳቸው ልከህ አንተ ምትደርስበት ድንቅ ሐብለል–ዊሳል ነው፤ሰለዋት ሰዪዳችንን ምታስደሳበት ስጦታ ነው፣ሰለዋት አውርደህ እንዳሻህ ተወሰልባቸው፣ይሆናል ምት፟ሻው፣ይቀርባል የራቀው፣ይፈታ፟ል ቋጠሮው ……………

እስቲ የዛሬውን ለይል የምታደምቁበት፣የእውቁን ወሊይ፣ዓሪፍ ሰዪዲ አሕመደ–ደ፟ርዲ_ሪይን (የሰለዋት ኪታብ)
« አል–ሰ፟ለዋቱ–ደ፟ርዲ_ሪያ፟ » ልጀባችሁ።የ pdf እና mp3 ፋይሉን በቴሌግራም ቻናሌ ላይ አስፍሬያለው 🙏

   ቢሲሪ፟ ሰዪዲነል–በሺ_ር፣የታመመው እንዲሽር፣ሓጃችንም እንዲሆን ገር በገር፣ብለን ያ ረብ የሲ፟ር፣ነየትን ከቀዲ_ር፤በነቢ ካሉትማ እርሱም አያሳፍር !!!!
👇
t.me/hamidabuhamid

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

27 Jun, 05:43


# ከዝንጉዎች አትሁን
__
የጭንቀት፣የድብርት፣የድባቴ … ዋነኛ መንስኤ ወንጀል ነው፤
የ ኃጢአት ዋነኛ ምክንያት ዝንጋኤ (ጘፍላ) ነው፣የጘፍላ ማጥፊያው ደግሞ የዚክር ኑር ነው።

በተለይ ደግሞ ሙሪد ያለዊርድ መሪض ነው፤ወደ መንፈስ ከፍታ የሚወ፟ጣጣበት ዊርድ የሌለው፣ከአላህ ዘንድ የሚወርድለት መደድ አይኖርም፤የዋሪዳ ዝናብ እንዲዘንብልህ፣የዊርድን እንፋሎት አትንን !!!

ዊርድ እራሳችንን ከሰይጣንና ነፍሲይያ ሸር የምንጠብቅበት ምሽግ፣ከጠላትና ከክፉ ሰዎች የምንከለልበት አጥር ነው!!!

ቀደምት ትላልቅ ሊቃውንትም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የተለያዩ አዝካሮችን የያዙ የዊርድ ኪታቦችን በተለያየ ይዘት ያዘጋጁ ሲሆን፣ከነዛ ውስጥ ለናንተ የመረጥኩትን ከተለያዩ ቁርኣናዊ አንቀፆችና፣ነቢያዊ ሐዲሶች የተወጣጡ አዝካሮችን ያዘለ እጥር ምጥን ያለ ምርጥ ኪታብ ልጀባችሁ !!!

ኪታቡም
“ ሰፊነቱን–ነጃ ሊመን ኢለላ፟ሂ– ልተጃ” ወይም “አል–ወዚፈቱ–ዘ፟ሩ፟ቂያ፟ህ ” ይባላል

የታላቁ ዓሊምና፣ዓሪፍ ኢማም አሕመድ ዘሩ፟ቀል–ፋሲ_ (ቀደሰላሁ ሲረ፟ህ) ኪታብ ሲሆን፣ዘወትር ከፈጅርና ከዐሱር ሰላት በዃላ የሚነበቡ ውዳሴዎችን፣ከቅንጭብ የግር ጌ ትንታኔዎችና አስረጂዎች ጋር የያዘ ነው !!!

አጥብቃችሁ ያዙት !!!
በቴሌግራም ቻናሌ ላይ የ mp3 እና pdf ፋይሉን ታገኙታላችሁ 👇👇👇
____
T.me/hamidabuhamid

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

24 Jun, 20:05


"ከመተኛትህ በፊት፣ልብህን ተመልከት
ከጥላቻ ነፃ ከሆነ፣ያኔ ሰላማዊ እንቅልፍ ታገኛለህ ”

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

24 Jun, 20:04


እናመዛዝን

ምንጎዳውም ምናታልለውም እራሳችንን ነው።

እስቲ እነዚህን ቁርኣናዊ ጥቅሶች በጥሞና እናንብብ……

يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ

አላህንና እነዚያን ያመኑትን (ሰዎች) ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ ነፍሶቻቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፡፡
[ አል-በቀራህ - 9 ]
____

وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ وَرَحْمَتُهُ لَهَمَّت طَّائِفَةٌ مِّنْهُمْ أَن يُضِلُّوكَ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ ۖ وَمَا يَضُرُّونَكَ مِن شَيْءٍ ۚ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا

የአላህም ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነሱ የኾኑ ጭፍሮች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር፡፡ ነፍሶቻቸውንም እንጅ ሌላን አያሳስቱም፡፡ በምንም አይጐዱህም፡፡ አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡
[ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 113 ]

ከሰው ልጅ ደካማነት መገለጫ ውስጥ ይህ የብዙኃኖቻችን ባህሪ አንዱ ነው፤ዳሩ እራሳችንን እየሸወድን፣ለኛ የሚመስለን ግን ሌላን ምንሸውድ ነው፤ሌላውን እየጎዳን ይመስለናል፣እውነታው ግን እራሳችንን ነው ምንጎዳው፤የዚህም ዋነኛ መንስኤ ስሜታችን ከዐቅላችን በላይ መሾሙ ነው።

እናም የትኛውንም አቋምና ውሳኔ ከመውሰድ በስተፊት፣ግራና ቀኝን ዞር ብሎ ማሰስ፣ጥቅምና ጉዳቱን ቆም ብሎ ማመዛዘን የዐቅለኛ ሰው መገለጫ፣የአስተዋይ ሰው መለያ ነው 🙏

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

24 Jun, 15:26


ዱዓእ የሙእሚን መሳሪያ
__
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህንን ዱዓእ ያዘወትሩ ነበር

ዐብደላህ ቢን ዑመር(ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት:የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሲያነጉም ሆነ ሲያመሹ እነዚህን ቃላቶች ትተው አያውቁም ነበር፣ይላሉ :–

اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِي وَدُنْيَايَ وَأَهْلِي وَمَالِي، اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَاتِي وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ وَمِنْ خَلْفِي وَعَنْ يَمِينِي وَعَنْ شِمَالِي وَمِنْ فَوْقِي وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ مِنْ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تحتي.
رواه أبو داود.

« አላ፟ሁመ፟ ኢኒ፟ አስአሉከል–ዓፊየተ ፊ ዱ፟ንያ ወል–ኣኺረህ,
አላ፟ሁመ፟ ኢኒ፟ አስአሉከል–ዓፍወ ወል–ዓፊየተ ፊ_ ዲ_ኒ_ ወዱንያየ ወአህሊ_ ፣አላ፟ሁመ፟–ስቱር ዐውራቲ_ ወኣሚን ረውዓረቲ_ ,አላ፟ሁመ፟–ሕፈዝኒ_ ሚን–በይኒ የደየ፟ ወሚን ኸልፊ_ ወዐን የሚ_ኒ_ ወዐን ሺማሊ_ ወሚን ፈውቂ_,ወአዑ°ዙ ቢዐዘመቲከ ሚን አን ኡጝታለ ሚን ተሕቲ_ »

📚 አቡ° ዳውድ

ዐፍው ፡- ኃጢአትን መሰረዝና መሸፈን ሲሆን
ዓፊያ :– ደግሞ፣በዱንያም ሆነ በኣኼራ ከባሪያው ክፉን ነገር በማራቅ ከአደጋና ከችግር በመከላከል መጠበቅ ነው።

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

21 Jun, 05:17


የነቢዩ ﷺ ከተማ (المدينة النبوية)
___
ከከውን ካኢናቱ፣ከሙልክ መለኩቱ ከላቁት ነቢይ ጋር በሙሐባ ተሳስሮ ልሕቀትን ያላገኘ አንድም የለ!!! አላህ ﷺ አክብሮ በዐቅልና በቀልብ ሞሽሮ፣ዓላማና ግብ ቸሮ ከፈጠረው የሰው ልጅ አንስቶ፣ለሰው ልጅ ግልጋሎት እስከተፈጠሩት እንስሳትና እፅዋት፣ተራራና መሬት ድረስ ሰዪዳችንን ወዶ ያልተወደደ፣አክብሮ ያልተከበረ አንድም የለም!!
መዲና ከተማም የዚህን እጣ በሰፊው የተሰጠች፣በብዙ ስጦታዎችና ደረጃዎች ልዩ የተደረገች ከተማ ነች።
የአኹኗ የነቢ ﷺ ከተማ የቀድሞዋም የስሪብ፣ሰዪዳችን ﷺ ከተወለዱባትና ካደጉባት መካ የተሰደዱባት፣ከባልደረቦቻቸው ጋር ወደሷ ከትመው የተሞናደሉባት፣ከሁሉ ቀድሞ እምነት የተደላደለባት፣ኢስላማዊ ኡምማ የተመሰረተባት፣ሰላም፣እርጋታ የከበባት፣ከምንም በላይ የውዱን ነቢይ አካል በምድሯ ስር የተሸከመች ከተማ ናት!!!
ሰዪዳችን ﷺ እጅግ አብዝተው የሚወዷት፣እንደው ለአንድ ጉዳይ ከመዲና ቢወጡ እጅጉን በጣም የሚናፍቋት፣ጉዳያቸውን ሲጨርሱ በፍጥነት እየጓጉ የሚመለሱባት ድንቅ ምድር።
በምድሯ ለሞተ የሰዪዳችንን ﷺ ምልጃ ይታደላል፣
ሰዪዱና ዑመር (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት ዱዓእ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል :–
(اللهمَّ ارزُقني شهادةً في سبيلك, واجعَل موتي في بلدِ رسولك محمّد صلى لله عليه وسلم) [ رواه البخاري: (1890).]
( በመንገድህ ላይ ሰማዓትነትን ለግሰኝ፣ሞቴንም በመልእክተኛህ ሙሐመድ ﷺ ሀገር ላይ አድርግልኝ)
ቡኻሪይ
____
ያ ረብ እኛም ይህንኑ ጠየቅንህ 🤲🤲🤲

የመዲናን ሙሐባ የሚጨምር፣ሸውቁን አብዝቶ የሚጨምር የሆነ፣ በኡስታዝ አስለም(ሐፊዘሁላህ) የቀረበ ዳዕዋ ጋበዝኳችሁ👇👇👇
https://youtu.be/ACWtjBxUilc?si=1T3at0dLNCmRfkLj

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

15 Jun, 17:36


እንኳን ለዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓለ በሠላም አደረሠን!
በዓሉ የኢማን፣ የዓፊያ፣ የሠላም ይሁንልን!

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

11 Jun, 17:32


#እውቀት…የላቀው ስጦታ
____
አላህ ካለ በቅርቡ ለንባብ ከሚበቃው የወንድማችሁ አቡ ሱሀይል መፅሀፍ የተቀነጨበ…
========
« وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا»
« አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡»
[ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 113 ]
ኢማም አል–ቀራፊይ(ረ.ዐ) ይህን የቁርኣን ጥቅስ አያይዘው እንዲህ ይላሉ:–

ዐረቦች በውለታ ገለፃ ዐውድ ላይ፣ይበልጥ የላቀውን ከላቀው የማዘግየት፣የተሻለውን ይበልጥ ከሚሻለው የማስቀደም ልማድ አላቸው፤በዚህ አይነት የአላህ መልእክተኛ ﷺ የዕውቀት ስጦታ፣ነቢይነትንና መልእክተኛነትን ካዘለው ስጦታ የላቀ ነው፤ይህ ትልክ ክብር ነው።
_
ይህ የአላህ ﷻ ቃል፣የነቢያት ሁሉ ዐውራ፣የሙላ ከውኑ ጮራ የሆኑት ሰዪዳችን ﷺ ከተሰጡትና፣ከተላቁበት አበይት ስጦታዎች ውስጥ ዒልም መሆኑን ጉልህ ማሳያ ነው።

ወንድሜ በስጋዊ አካልህ ላይ ሐፍረተ ገላ እንዳለው ሁሉ፣ መሀይምነት የአዕምሮህ ዐውራ(ሐፍረት) ነው፤የሙስሊሙ ኡማ እንቅፋት አዋቂዎች ናቸው እያሉ፣እውቀትንና አዋቂያንን በሚያነውሩ ወሬ ሰምተህ ከእውቀት ራስህን አታራቁት፣ሰው ለራቀውና ላላወቀው ነገር ጠላት መሆኑን አትዘንጋ፤ከወዲያና ወዲህ የሚነፍሰው የፊትና ነፋስ እንዳያወዛውዝህ የእውቀትን ግንድ አጥብቀህ ያዝ፣በሰፊ ጥላው ስርም ተጠለል !!!
ከእውቀት ማማ ላይ ዘላለም ለመንገስ፣ከአዋቂዎች ስር እውቀትን ተቋደስ፣ኩራት ሕፍረት ትተህ ነፍስህን አስተናንስ !!!

ገጣሚውም እንዲል :–
عاب التفقه قوم لاعقول لهم
وما عليه إذا عابوه من ضرر

ما ضرّ شمس الضحى وهي طالعة
أن لايرى ضوءها مَن ليس ذا بصر

እውቀት አነውሩ የሆኑ ዐቅለ ባዳ
ነውር ማድረጋቸው እርሱን ምን ሊጎዳ
ብርሃኗን ቢኮንን የተሳነው ማየት
የንጋትን ፀሀይ ፈፅሞ አይጎዳት

___
T.me/hamidabuhamid

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

11 Jun, 13:07


ከትልልቅ ወደ አሏህ መቃረቢያ ስራዎች ውስጥ የሙእሚን ወንድምህ ልብ ውስጥ ደስታን ማስገኘት ነው ::

የኛ ነብይም صلى الله عليه وسلم ከስራዎች ሁሉ በላጩ ምንድነው ተብለው የተጠየቁ ግዜ እንዲህ ብለዋል :-

" ሙእሚን ሙስሊም የሆነ ወንድምህ ልብ ውስጥ ደስታን ማስገባት ,, ወይም እዳውን መክፈልህ ,, ወይም እሱን ምግብ ማብላትህ ነው "
------------------
ዒዱም ከመቃረቡ ጋር በተለያየ ምክንያት ደስታቸው ደፍርሶ ልባቸው ተከፍቶ ዒዱን የሚያሳልፉ ወንድሞችን በቻልነው አቅም ልባቸውን በማስደሰት ወደ አሏህ መቃረባችንን እናጠንክር


እንሳተፍ ውዶቼ :: ሁላችንም የበጎነት ባለቤቶች ነን::

በእነዚህ 👇👇አካውንቶች ድጋፋቹን መላክ ትችላላቹ ::

📍СВЕ = 1000580908587

📍OROMIA = 1000094625077

📍ZEMZEM = 0033646410301

📍አቢሲኒያ = 159300099

📍HIJRA = 1000019190001

☎️ስልክ : 0911449925
0961707090
0964707090

https://t.me/elmeewa

Kedir Al Hadra Official Menzuma&Neshida🥁👏

29 May, 20:54


# ይህን ሐዲስ በልብህ ላይ አኑረው፣ምላሹንም ተዘጋጅበት !!!

مَا مِنِ امْرِئٍ يَخْذُلُ امْرَأً مُسْلِمًا فِي مَوْضِعٍ تُنْتَهَكُ فِيهِ حُرْمَتُهُ، وَيُنْتَقَصُ فِيهِ مِنْ عِرْضِهِ؛ إِلَّا خَذَلَهُ اللهُ فِي مَوْطِنٍ يُحِبُّ فِيهِ نُصْرَتَهُ.
وَمَا مِنِ امْرِئٍ يَنْصُرُ مُسْلِمًا فِي مَوْضِعٍ يُنْتَقَصُ فِيهِ مِنْ عِرْضِهِ وَيُنْتَهَكُ فِيهِ مِنْ حُرْمَتِهِ؛ إِلَّا نَصَرَهُ اللهُ فِي مَوْطِنٍ يُحِبُّ نُصْرَتَهُ.
نبينا ﷺ
“ክብሩ በሚነካበት፣መብቱ በሚጣስበት ቦታ ላይ አንድ ሙስሊም ወንድሙን ከመርዳት የታቀበ ሰው፣የአላህን እርዳታ በሚፈልግበት ቦታ ላይ አላህ ያዋርደዋል

ክብሩ በሚነካበት፣መብቱ በሚጣስበት ቦታ ላይ አንድ ሙስሊም ወንድሙን የረዳ ሰው፣የአላህን እርዳታ በሚፈልግበት ቦታ ላይ አላህ ይረዳዋል”

#ረሱለላህ ﷺ
# አቡ ዳውድ ዘግበውታል