✅ በሽታው እንዴት ይከሰታል?
የጨጓራ በሽታ በሚከተሉት መነሻ መንስኤዎች አማካይነት ይከሰታል:-
🍓 በኢንፌክሽን
🍓 የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በተደጋጋሚ ወይም በብዛት በመውሰድ
🍓 የአልኮል መጠጦችን በብዛት መጠጣት
🍓 ጭንቀት ወይም ውጥረት
🍓 በሃሞት ፈሳሽ ምክንያት
🍓 በአውቶኢሚውን ችግሮች ወይም በሽታዎች
🍓 ሲጋራ በማጨስ
🍓 በዕድሜ መግፋት እና
🍓 ጨጓራን ለሚያስቆጡ ወይም ለሚያበሳጩ ነገሮች ለረጂም ጊዜ በመጋለጥ የጨጓራ በሽታ ሊከሰት ይችላል።
✅ ተጨማሪ መንስኤዎች
🍓 የጨጓራ ባክቴሪያ (ኤች. ፓይሎሪ (H.pylori))
ኤች. ፓይሎሪ የጨጓራ ባክቴሪያ ሲሆን፤ በጨጓራ ንፍጣማ ግድግዳዎች ላይ ይኖራል ወይም ይቀመጣል።
በጊዜ ህክምና የማናደርግ ከሆነ፤ ወደ ጨጓራ ቁስለት ያመራል፤ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ የጨጓራ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል።
🍓 ፐርኒሺየስ አኒሚያ
ፐርኒሺየስ አኒሚያ የደም ማነስ ዓይነት ሲሆን፤ ቫይታሚን ቢ12 ለመፍጨት እና ለመምጠጥ የሚያገለግል የተፈጥሮ ንጥረ-ነገር በጨጓራ ውስጥ በማይኖርበት ጊዜ ይከሰታል።
🍓 የሃሞት መፍሰስ
ሃሞት (Bile) ከሀሞት ከረጢት (Bile Duct) ወደ ጨጓራ ተመልሶ በሚፈስበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል።
🍓 በባክቴሪያ እና በቫይረሶች
በባክቴሪያዎች እና በቫይረሶች በሚፈጠር ኢንፌክሽን አማካይነት የጨጓራ በሽታ ሊከሰት ይችላል።
✅ የጨጓራ ህመም ምልክቶች
የጨጓራ በሽታ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው (ከሰው ሰው) የሚለያዮ ሲሆን፤ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ዓይነት የበሽታው ምልክት ላይታይባቸው ይችላል።
በጣም የተለመድና በብዙ በሽተኞች ላይ የሚስተዋሉ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:-
🍏 ማቅለሽለሽ
🍏 የሆድ ህመም
🍏 የሆድ መነፋት
🍏 ማስመለስ
🍏 የምግብ አለመፈጨት
🍏 በምግብ ሰዓት አካባቢ ወይም ማታ ላይ የማቃጠል ስሜት ወይም ግሳት
🍏 ስቅታ ወይም ስርቅታ
🍏 የምግብ ፍላጐት መቀነስ
🍏 ደም የቀላቀለ ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ትውከት
🍏 ጥቁር ቀለም ወይም መልክ ያለው ሠገራ የተለመዱ ምልክቶች ናቸው።
✅ የበሽታው ምርመራ ምን ይመስላል?
አንድ ሰው የጨጓራ በሽተኛ መሆኑ እና አለመሆኑ በሚከተሉት የህክምና ዘዴዎች ይረጋገጣል:-
🍑 የደም ምርመራ | Blood Test
የተለያዮ የደም ምርመራዎች የሚሰሩ ሲሆን፤ ከእነዚህ ምርመራዎች ውስጥ የቀይ ደም ሴሎች መጠን ቆጠራ እና ሄሞግሎቢን ይገኙበታል።
እነዚህ ምርመራዎች የሚደረጉት የደም ማነስ እንዳለብን ለማረጋገጥ ነው።
በተጨማረም የጨጓራ ባክቴሪያ (H.pylori) እና ፐርኒሺየስ የደም መነስ (Pernicious Anemia) እንዳለብን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ይሠራል።
🍑 የሠገራ ምርመራ | Stool Test
ይህ ምርመራ የሚደረገው በዓይነ ምድራችን ውስጥ ደም እንዳለ ለማረጋገጥ ሲሆን፤ የጨጓራ በሽታ አንድ ምልክት ነው።
በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያ ምርመራ ይደረግለታል።
🍑 ኢንዶስኮፒ | Endoscopy
ኢንዶስኮፒ ቀጭን ቱቦ ወደ ጨጓራ ውስጥ ማስገባት ሲሆን፤ ይህ ቱቦ በመጠን ትንሽ የሆነ ካሜራ አለው።
በጉሮሮ ውስጥ እስከ ጨጓራ ወይም ከርስ ድረስ በመክተት የጨጓራ ግድግዳዎችን ለማየት ይጠቅማል።
ይህ ምርመራ የጨጓራ መቅላት፣ እብጠትና ቁስለት መኖሩን ለማረጋገጥ ይረዳናል።
በተጨማሪም ትንሽ የጨጓራ ቁራጭ ናሙና በመውሰድ ለበለጠ ምርመራ (ለፓቶሎጂ ምርመራ) ወደ ላቦራቶሪ ይላካል።
✅ የሚወሰድ መከላከያዎች እና መድሃኒቶች
የሚከተሉት በጨጓራ በሽታ ህክምና ላይ ይካተታሉ:-
🧅 የጨጓራ አሲድ መጠንን ለመቀነስ ፀረ አሲድ (Anti Acid) ወይም ሌሎች መድሃኒቶችን መውሰድ።
🧅 ትኩስና ቅመማ ቅመም ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ።
🧅 በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የጨጓራ በሽታ ፀረ ባክቴሪያ እና የጨጓራ አሲድ ምርትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ያታዘዙለታል።
🧅 በፐርኒሺየስ የደም ማነስ የተከሰተ የጨጓራ በሽታ ከሆነ ቫይታሚን ቢ12 እንዲወስድ ይደረጋል።
🧅 የጨጓራ ማቃጠልን የሚያስከትሉ ምግቦችን መውሰድ ወይም መመገብ ማቆም።
በመጨረሻም የጨጓራ ህመምን የሚቀሰቅሱ ወይም የሚያስነሱ ምክንያቶችን ለይተን ማወቅና እነዚህ ቀስቃሽ ነገሮች ባለመጠቀም ከህመሙ በቀላሉ ማገገም ይቻላል።
በተጨማሪም በጨጓራ በሽታ የተያዙ ሰዎች ህክምና ከጀመሩ በኋላ በፍጥነት ከህመማቸው ያገግማሉ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
⬇️ Join and Share ⤴️👇
╔═══════════╗
🟢 @fikrtena1 🔴
🟢 @fikrtena1 🔴
╚═══════════╝
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬