Mereb Media መረብ ሚዲያ @merebmedia24 Channel on Telegram

Mereb Media መረብ ሚዲያ

@merebmedia24


Welcome to our Channel, Mereb Media - መረብ ሚዲያ We provide daily reliable and trusted information.

Mereb Media መረብ ሚዲያ (Amharic)

እንኳን ደህና መጡ፡፡ ከአብነት እምድ ፈጥነው በከተማ ሚዲያ - Mereb Media - መረብ ሚዲያ የአዲስ የድምጽ መረብ ፕሮግራም እና መረብ አማራጮች አስተናጋጅ በሽታቸው አንዱን፡፡ ይህ እምድ ሚዲያ የተለያዩትን እና የቆዳማዊ መረብ አማራጮችን ሰነድ እንዲረዱ ነው፡፡

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Feb, 08:30


አርሶ አደሩ ይናገራል!

ሙሉውን ይከታተሉ👉

https://youtu.be/KftdHE7DdAU?si=_hgAaq3vh49cwtjk

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Feb, 17:27


የአምባሰሉ አርበኛ በቪዲዮ!

ትግሉ ተጓትቷል ወይስ አልተጓተተም? ለምን?

በሁለት ቢለዋ የሚበሉ ታጋዮች አሉ!

https://www.youtube.com/watch?v=kP31H3I0kaY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Feb, 13:53


እንደምን ዋላችሁ!

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልንና ፌስቡክ ገፅን ተወዳጅታችኋል?

በግምባር የሚገኙ ጋዜጠኞች የሚያዘጋጇቸው መረጃዎች እንዳያልፏችሁ!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

ቴሌግራም👉https://t.me/MerebMedia24

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 17:01


አርሶ አደሩ ይናገራል!

ሙሉውን ተከታተሉ👉

https://www.youtube.com/watch?v=nWFWcxFPXOE&t=1139s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 11:34


አርበኛ ሰለሞን አሊ ከአምባሰል!

ሙሉውን ተከታተሉ👉https://www.youtube.com/watch?v=D6weKgI6R6s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 11:05


የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት  ዕዝ ለበርካታ ወራት ያሰለጠናቸውን አባት አርበኛ ጦር አስመረቀ!

አደረጃጀት የማዘመንና ሠራዊት የማብቃት ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ የሚገኘው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከግንባር ተጋድሎ ጎን ለጎን የሠራዊት ግንባታ አፈፃፀሙን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በትናትናው ዕለትም በጀግናው አርበኛ ማንበግር ንጉስ የተሰየመው ማንበግር ክፍለጦር በቀወት ወረዳ ራሳ ለወራት ያሰለጠናቸውን እርሳስ ግንባር ላይ የሚጥሉ አባት አርበኞችን የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች  በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ባሉት 8 ክፍለጦሮች ጠንካራ መሠረት ያለው ፤ ለህዝብ ነፃነት የሚዋደቅ ታማኝ ሠራዊት በመገንባት አደረጃጀት እየገነባ ተቋማዊነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

ስር ነቀል ለውጥ የትግላችን መዳረሻ ነው!

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 10:29


https://www.youtube.com/watch?v=BEEyUycrIww&t=40s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 09:40


መሃል ደብረብርሃን ከተማ የሚገኘው አገዛዙ ወታደራዊ ካምፕ   በአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር በከባድ ተመታ።
 
እኩለ ሌሊት 7:00 ሰዓት ላይ የአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር አንበሳው ብርጌድ አስራት ሻለቃ በብርጌዱ ዘመቻ መሪ በፋኖ ደረጀ እና በሻለቃዋ መሪ ፋኖ ዳዊት  እየተመራ መሃል ደብረብርሃን አፄ -ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ምድረ ገነት ቀበሌ ሰርጎ በመግባት በአገዛዙ ሰራዊት ካምፕላይ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከ15 በላይ የተደመሰሱ ሲሆን ከ20 በላይ ቁስለኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

በተወሰደው ድንገተኛ ጥቃት የአራዊት ሰራዊቱን ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ለሰዓታት መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን ቁጥራቸው በዉል ያልታወቁ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተበትነው መጥፋታቸውን ማረጋገጥ ሲቻል ቁጥሩ በርከት ያለ ምርኮኛ መኖሩን ለማረገጥ ተችሏል።

ከሰሞኑ ጌትቫ ሆቴል የመንግስት ሰራተኞችን በመሰብሰብ ሙሉ ለሙሉ ፋኖን አጥፍተነዋል በማለት የተናገሩት የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊው በተሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ መግባታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።
     ክብር ለተሰውት!
"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ በሸዋ ሚዲያ እና ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 08:37


የቀድሞው ምስራቅ አማራ የአሁኑ አማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አምሓራ) ፋኖ ከዓመታት በፊት እነ እሸቴ ሞገስን ያወሳበት አጋጣሚ።

አ ር አ ያ ነ ት + ታ ማ ኝ ነ ት + ፅ ና ት + ጀ ግ ን ነ ት=ድል

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 07:51


ብርሸለቆ!

ከብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ በቅርብ ርቀት ከባድ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ!!

ዛሬ ንጋት ላይ በተፈፀመው በዚህ ደፈጣ ጥቃት ከአምስት በላይ የጠላት ዐብይ አህመድ አገልጋይ ወታደሮች መገደላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር አረንዛው ዳሞት ብርጌድ የፍኖተ ዳሞት ሻለቃ ፋኖዎች ዛሬ የካቲት 10/2017 ዓ/ም ንጋት ላይ ከብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ኬላ ላይ በፈፀሙት ሽምቅ ጥቃት በኬላ ጥበቃ ላይ የነበሩ በቁጥር አምስት ፀረ አማራ ኃይሎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን ነው ጣቢያችን ለማረጋገጥ የቻለው።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

17 Feb, 05:05


"ዝናሩም ጥብቅ ነው ትጥቁም አይፈታ:
ማን ይመልሰዋል ዘራፍ ያለ ለታ"

ምሽግ ደርማሾቹ የአርበኛ ተሾመ አበባው ልጆች!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

16 Feb, 19:00


ሰበር ቪዲዮ!

የጎንደር አባት አርበኞች ስለ ድርድሩ ዝምታቸውን ሰበሩ!

ከሰይጣን ጋር ውይይትም ሆነ ድርድር አይታሰብም!

https://www.youtube.com/watch?v=BEEyUycrIww

Mereb Media መረብ ሚዲያ

16 Feb, 17:23


የዳግም ወረኢሉ ክተት ክፍለጦር ዋና አዛዥ ኢንጂነር ናትናኤል አክሊሉ በአዲሱ አደረጃጀት የአማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አምሓራ) ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ም/ኃላፊ ሆኖ ተመድቧል።

ኢ/ር ናትናኤል ድል ለአንተ  እና ለጓዶችህ!

መልካም የስራ ዘመን!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

16 Feb, 15:13


በአምባሰል ወረዳ 022 ጂብጎዶ ቀበሌ ላይ ገዢው የብልፅግና ቡድን የካቲት 06/2017 ዓ/ም በፈፀመው የጀት ድብደባ በአሰቃቂ ሁኔቲ የተገደሉ ሰዎች አ*ስ*ከ*ሬን ከቤቶች ፍርስራሽ ላይ ሲወጣ የሚያሳይ ምስል!

መነሻውን አፋር ሰመራ ከሚገኘው ሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ አየር ማረፊያ (ኤርፖርት) ያደረገው ሚግ 23 በባቲ በኩል አቆራርጦ በመብረር አምባሰል ወረዳ በጂብጎዶ ቀበሌ  ነዋሪዎች ላይ ድብደባ ፈፅሞ እንደነበረ መረብ ሚዲያ በእለቱ መዘገቡ ይታወሳል።

በተጨማሪም በዕለቱ፡ መቆጣጠሪያ ስቴሽናቸውን ደሴ ጦሳ ተራራ ላይ በማድረግ ከኮምቦልቻ አየር ማረፊያ እያረፉ የሚነሱት ሰው አልባ አውሮፕላኖችም በዚሁ አከባቢ ድብደባ ፈፅመው የበርካታ ንፁኋኖችን ህይወት ቀጥፈዋል።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

16 Feb, 14:19


ልዩ ኮማንዶ!

የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌው መኮንን ብርጌድ ላለፉት በርካታ ወራት ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ልዩ ኮማንዶዎች በዛሬዉ ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

ከውጊያው ጎን ለጎን ወታደራዊ ስልጠናውም ተጠናክሮ ቀጥሏል!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

አዲሱን የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጋብዙ።

የፌስቡክ👉 https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 20:18


https://www.youtube.com/watch?v=aq-ULzDD4gg&t=193s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 17:17


ሰበር ዜና

አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) ምዕራብ ወሎ ኮር ዳግም ክተት ወረኢሉ ክፍለጦር 7ለ52 ብርጌድ ንስር ሻለቃ ለገሂዳ ወረዳ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ጀግኖቹ በለገሂዳ ወረዳ የሚገኘውን የአገዛዙን ዙፋን አስጠባቂ ሀይል ካምፕ አድርጎ በተቀመጠበት የለገሂዳ ወረዳ ምክርቤት ግቢና ደፈጣ ብለው በወጡበት አድሱ ጤና ጣቢያ ወይም ማጀቴ በመባል በሚጠራው ቦታ ላይ ዶግ አመድ በማድርግ ጥላትን አንገት አስደፍቶ አዋርዶና አሸማቆ በመውጣት ታላቅ ድል ሰርተዋል::

በተጋድሎው ብዛት ያለው ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን ከአምስት በላይ ቁስለኛን አስተናግዶ በአጠቃላይ ሙትና ቁስለኛዉን ታቅፎ በስነ ልቦናም ተሸማቆ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ሲል የ7ለ52 ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሙሃመድ ሽፈራው ገልጿል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!


ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ- አምሓራ)
የካቲት 1/2017 ዓ.ም

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 16:53


ከአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

፨ ሀምሳ አለቃ ፋኖ ሀይማኖት አፍወርቅ በቅፅል ስሙ ካይሮ በመባል የሚታወቀው ጀግናችን ለጠላት እጄን አልሰጥም በማለት ከጠላት ጋር ተናንቆ ተሰውቷል!!

የካቲት 01/2017 ዓም

፨ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ ጥቅምት10/1974/ዓም ደሮተራ ሰፈር ተወለደ።ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ እድሜው ለትምህርት ሲደረስ በቢቸና ከተማ ሀይሎ ሴዴቅ የመጀመረያ ደረጃ ትምህርቱን በመከታተል ላይ እያለ ወደ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል ሆኖ ትምህርቱን አጠናቀቀ።ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ በመከላከያ ሰራዊት ከ15 አመት በላይ ለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ከአገለገለ በኅላ በቢቸና ከተማ እነማይ ኮሌጅ accounting diploma ተመረቆ በግል ባንክ በጥበቃ ስራ አገልግሏል።ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ በግል ንግድ የግል ባጃጅ እና አባዱላ በመግዛት ቤተሰቡን እየመራ ነበረ።

፨ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ ህዳር 24/2014 ዓም በእነማይ ወርዳ የተመሰረተው የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ መስራች ነበር።በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ ተወልዶ ያደገው ወንድማችን ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወረቅ በአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል አሻራቸውን ካሳርፉ ጥቂት አመራሮች ውስጥ አንዱ ነበር።

፨ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ በአርበኛው ዘመነ ካሴ በሚመራው የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ የትጥቅ ትግል በመሰለፍ የንግድ ባንክ ስራውን በመተው በቢቸና ከተማ ከ166(አንድ መቶ ስልሳ ስድስት) የአንደኛ ዙር የፋኖ አባላትን አሰልጥኖ አስመረቋል።ከተመረቁት ሰልጣኞች ውስጥ 43 (አርባ ሶስት) ምልምል የፋኖ አባላትን በመያዝ ከቢቸና ከተማ የትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ከአማራ ህዝብ ሂሳብ አወራርዳለሁ ካለው የTPLF ሰራዊትን ለመፋለም በሰሜኑ ጦርነት ከቢቸና ከተማ በመነሳት እስከ ደቡብ ወሎ ሀይቅ ከተማ ድርስ በመሄድ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ተሳትፏል።

፨ ጀግናው ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ ከሰሜኑ ጦርነት በኅላ በምስራቅ ጎጃም ዞን ባሉ ወረዳወች በመዘዋወር የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ አደረጃጀት በማገዝ አሻርውን አሳርፏል።ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ በቀድሞው የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ በእነማይ ወርዳ በላይ ብርጌድ በአሁኑ አባ ኮስትር ብርጌድ ውስጥ ጦር አዛዥ፣የአባ ኮስትር ስልጠና መምሪያ፣የአባ ኮስትር ብርጌድ 1ኛ ጠቅል ሻለቃ ጦር አዛዝ በመሆን በወረደው ውስጥ በተደርጉ አውደ ውጊያወች በሙሉ ተሳትፏል።

፨ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ በአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ ልዩ ኮማንዶ ለ6 (ስድስት) ወራት በልዩ ብቃት አሰልጥኖ አስመረቋል።ፋኖ ሀይማኖት አፍወርቅ በአባ ኮስትር ብርጌድ ስልጠና መምሪያ በተሰጠው የስራ ዘረፍ ሀላፊነቱን በብቃት በመወጣቱ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስልጠና መምሪያ ሀላፊ በመሆን እየሰራ ባለበት ሰዓት ጥር 30/2017 ዓም በክፍለ ጦሩ በተሰጠው የስራ ግዳጅ በእነማይ ወረዳ የረዝ ቀበሌ ላይ ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት በተደረገበት ከበባ እና እልህ አስጨረሽ ውጊያ በኅላ እጄን ለጠላት አልሰጥም በማለት ከጠላት ጋር ተናንቆ ለተከበርው የአማራ ህዝብ ውድ ህይወቱን ሰጥቶ አልፏል።ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ ጥር 30/2017 ዓም በእነማይ ወረዳ ዲማ ቅዱስ ጊዮወርጊስ በክብር የትግል ጎዶቹ በተገኙበት ስረዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል።

ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በጀግንነት የተሰዋህው ጓዳችን/ወንድማችን ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ ነፍስህን ከደጋጎች ጋር ያኑርልን!

ከአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የምንገኝ የትግል ጎዶችህ
              ''የጀግና ሞቱ እረፍቱ''
                  ጀግና ይሰዋል!
                  ትግል ይቀጥላል!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 10:11


አገዛዙ ህዝብን መዝረፉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል!

የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከጦርነቱና ዘር ማጥፋቱ ባሻገር የህዝብን ንብረት መዝረፉንና ወደ ድህነት ብሎም ብልፅግና መር ረሃብ ለመፍጠር የሚያደርገዉን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሎበታል::

የአገዛዙ ሰራዊት ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ራያ ቆቦ ልዩ ስሙ ጎለሻ የሚባል ቀበሌ ላይ ከ80 ኩንታል በላይ ማሽላ ህዝቡን በመደብደብ አስገድዶ ዘርፏል:: ለፋኖ ስንቅ ትሰፍራላችሁ በሚል ሰበብ ህዝቡን በጅምላ በመደብደብ ቤት ለቤት እየገባ ከሰማኒያ ኩንታል በላይ ማሽላ በመዝረፍ በኦራል ጭኖ ወደ ቆቦ ከተማ ወስዷል::

ሰራዊቱ በቅርቡ ከዞብል እስከ ዋጃ ባለው ቀጠና በነበረው ከባድ ዉጊያ በአሳምነው እና ሐውጃኖ ክፍለጦሮች ከፍተኛ ኪሳራ ስለደረሰበት ከፋኖ ጋር ሆናችሁ መረጃ ከመስጠት ጀምሮ ደጀን ሆኖ እስከ መዋጋት ደርሳችሗል በሚል ምክንያት ቤት ለቤት እየገባ ዘረፋ ፈፅሟል::

ድል ለአማራ ህዝብ
አማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አምሓራ)

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 09:49


አሳዛኝ ዜና!

በሸዋ ኤፍራታናግድም ወረዳ አገዛዙ በፈፀመው የድሮን ጥቃት የንፁኃኖች ሕይወት አልፏል!

በሁሉም መስክ ኪሳራ አሰያስተናገደ ያለው አሸባሪው የብልፅግና አገዛዝ በተለያየ ወቅት የሚፈፅማቸው ንፁኃንን ዒላማ ያደረጉ የድሮን ጥቃቶች በርካታ ሲቪሊያን ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ገደማ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የፋኖ አባላትና አመራሮች ይኖሩበታል በሚል የተሳሳተ ግምት በኤፍራታና ግድም ዘንቦ ቀበሌ በሰነዘረው የድሮን ጥቃት የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ባደረሰው ጉዳት የንፁኃኖች ህይወት አልፏል።

አገዛዙ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት እናት ከእነ ልጇ ጨምሮ 4 ሲቪሊያን ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ጋር ከ20 በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳትና ውድመት አድርሷል።

የአብይ አህመድ አማራ ጠል አገዛዝ በጋራ ታግለን ልናስወግደው የሚገባ ከባዕድ ወራሪ ያልተለየ አረመኔና ጨካኝ አገዛዝ በመሆኑ በተባበረ ክንድ ሁሉም አማራ በተሰለፈበት መስክ ስርዓቱን ለመቅበር የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

ክብር ለሰማዕታት
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የካቲት 1/2017 ዓ.ም

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 08:06


https://www.youtube.com/watch?v=nWFWcxFPXOE&t=1038s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 05:58


ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ መሪዎች ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለሁ አሉ!

ፕረዝዳንቱ ሰሞኑን በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአፍሪካ መሪዎችን በሚመለከት የሚከተለውን ጥያቄ አንስተዋል፦

<> ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

<> በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ቢሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?

<> በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን  ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

<> የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር  ትጠብቃላችው?

<> በራሳችው  አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን  ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችሁ?

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Feb, 04:17


እንደምን አደራችሁ!

የሳቀ ቀን ይሁንላችሁ!

አማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አምሓራ)!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 19:55


ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት!

የጋይንቱ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በሚመለከት የተናገረው!

"የበላይ ትንፋሽ ዘሜ አባ ግርሻ"

https://www.youtube.com/watch?v=O1oIzi8HlBY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 16:17


"ቄሮነትና  አባገዳነት ወንጀል እንዳልሆነዉ ሁሉ፤ፋኖነትም ክቡር ትውፊት ነው! አዎ አማራ እስከሆንኩ ድረስ፤ እኔም  ፋኖ ነኝ።"

ክቡር አቶ ዮሐንስ ቧያለው!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 15:41


ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይግዛት ዕዝ የተሰጠ ማሳሳቢያ !!

በሸዋ ሁሉም ከተሞችላሉ ኗሪዎች የተሰጠ ማሳሰቢይ!!

1ኛ. ከቀን 01/01/2016 ዓ.ም ጀምሮ ቦታ በኛ በኩል ተቀባይነት የለውም ።

2ኛ. ከቀን 01/01/2016 ዓ.ም ጀምሮከብልፅግናአመራሮች፣ ከሚሊሻ፣ከአድማ ብተና ቤት ቦታ ለሌላም ሀብት ንብረት መግዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

3ኛ. ከብልፅግናአመራሮች፣ከሚሊሻ፣ከአድማ ብተና ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት መከራየትም ማከራየትም አይቻልም።

4.701/01/2016 9.9 ጀምሮ በሊዝ ለሚሸጡመሬቶች እውቅና አንሰጥም ።

5ኛ. በማንኛውም የብልፅግና መስሪያ ቤት የምትሰሩ ስረዕቱ እዲቀጥል የምታደርጉ የስረዕቱ አገልጋዮች ።

ሀ.ከቻላችሁ የአማራ ህዝብን ትግል ተቀላቅላችሁ ታሪካዊ የሆነ ተግባር ስሩ።

ለ. ካልቻላችሁ ከሀላፊነት ለቃችሁ መልቀቃችሁን ለፋኖ ድርጅት አሳውቁ ስረዓቱን ማገልገል ትታችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ ።

ይህን በማያደርጉ ማናቸውም ግለሰቦች ላይ የምኖስደው እርምጃ የማያዳግም መሆኑን እናሳውቃለን ።

ባንዳነት ሞት !!

ፋኖነት አርበኝነትና ነፃነት !!

ድል ለተገፋው ለአማራ ህዝብ!!

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ!!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 13:14


ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት!

የጋይንቱ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በሚመለከት የተናገረው!

"የበላይ ትንፋሽ ዘሜ አባ ግርሻ"

https://www.youtube.com/watch?v=O1oIzi8HlBY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 13:09


ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት!

የጋይንቱ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በሚመለከት የተናገረው!

"የበላይ ትንፋሽ ዘሜ አባ ግርሻ"

https://www.youtube.com/watch?v=O1oIzi8HlBY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 11:55


አማራነት ተመርጦ የመገደያ ካርድ በሆነባት ሀገራችን ኢትዮጵያ አኛ የጤና ሙያተኞች አማራ ሆነን አምርረን እንድንታገል የሚያስገድድ ሁኔታ ላይ እንገኛለን!!!

መርጠን ያልተፈጠርንበት ማንነታችን -አማራነታችን- እንደወንጀል ተቆጥሮ እኛ አማራዎች ሁለንተናዊ ማንነት ተኮር ጥቃት እና የዘር ማጥፋት አዋጅ ከታወጀብን ረጅም ጊዜ ሆኖታል።

ላሳለፍነው ከግማሽ ክፍለ ዘመን ለሚልቅ ጊዜ የዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች በፈጠሩት ሀሰተኛ ትርክት ምክንያት አማራ ለገነባት ሀገር እንደጠላት ተስሎ የዘር ፍጅት እየተፈፀመበት የሚገኝ ሲሆን ሀገሪቱም አማራውን ከሁሉም ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ያገለሉ ፖሊሲዎች እና ህጎች ቀርፃ እንድትተዳደር ተደርጋ ትገኛለች።

ይህ ለረጅም ጊዜ በስውር እና በስልት ሲፈጸም የኖረ የዘር ፍጅት ለማንም ግልፅ በሆነና በማያሻማ መልኩ ላለፉት ስድስት አመታት መጠነሰፊ በሆነ መንገድ ተባብሶ ቀጥሎ ይገኛል።

ይባስ ብሎም ባሳለፍነው አንድ አመት ከስምንት ወራት ዉስጥ በስልጣን ላይ ያለው ፋሽስታዊ መንግሥት ሙሉውን የሀገሪቱን የመከላከያ ሠራዊት እና ሙሉውን የፀጥታ ሀይል በማሠለፍ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከፍቶብን እንገኛለን።

እየተካሄደ ባለው የዘር ማጥፋት ጦርነት በአማራው ላይ የጅምላ ፍጅት እየተካሄደ ሲሆን የሒፖክራትስን ቃለ መሀላ ፈፅመው ያለ አድሎ ሰው መሆንን ብቻ ባማከለ መልኩ ግልጋሎት እየሰጡ ያሉት የጤና ሙያተኞች እንኳን በአማራነታቸው በግፍ ከመሠቃየትና ከመገደል አልተረፉም።

ሰሞነኛው የዶክተር አንዷለም ዳኘ ዘግናኝ ግድያ ለዚህ አንዱ ማሳያ ሲሆን ዶክተሩ በክልሉ ሁለተኛው የጋስትሮ ኢንትሮሎጂ ስፔሻሊስት በመሆኑ ግድያውን እንደ አንድ ግለሠብ ሳይሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በአንዴ እንደተረሸኑ ነው የምንቆጥረው።

ከዚህ ቀደም መሀል አዲስ አበባን ጨምሮ በክልላችን በተለያዩ ቦታዎች የጤና ሙያተኞች  ተደብድበዋል ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል እንዲሁም  በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

በተጨማሪም አለምአቀፋዊ ሙያ የሆነው የጤና ሙያ ቅጥር በሀገራችን አንድ አንድ አካባቢዎች ኦሮምኛ መናገር ባለመቻልህ የማትቀጠርበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሰነባብቷል።

ይህም በመሆኑ እኛ አማራ የጤና ሙያተኞች ህልውናችን እስኪረጋገጥ አማራ ሆነን እንድንታገል የታሪክ አጋጣሚ ግዳጅ ጥሎብናል። ይህ ነባራዊ ሁነት ላይ  ተመስርቼ ውድ የጤና ሙያተኞች በያዝነው የትጥቅ ትግል የናንተ ሚና የማይተካ በመሆኑ ከጎናችን ተሰልፋችሁ ትታገሉ ዘንድ ጥሪየን አቀርባለሁ።

በመጨረሻም በቅርቡ ጂማ ላይ አሸባሪዉ መንግስት ባደረገው ድብቅ ስብሰባና የቀድሞ ባለስልጣናቱን አካቶ ባደረገው ምክክር አሳክቻለሁ ያላቸውን ጉዳዮችን እና የወደፊት እቅዶቹን አዉቀናል።

ስለሆነም ሁላችሁም የትግሉ ሜዳ ላይ ውድ ዋጋ እከፈላችሁ ያላችሁ እንቁ የአማራ ታጋዮች ከህልውናችን የማይበልጡ የመለያያ ነጥቦችን ወደ ጎን በመተው እና ለአማራ ህዝብ፣ ለትግላችን ትልም መሳካትና ለጓዳዊ ዝምድናችን ቅድሚያ በመስጠት ሁሉንም አደረጃጀቶች ያካተተ አንድነትን በመመሥረት የጠላትን እቅድ ቅዠት እናድርገው ስል ልባዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።

ፋኖ ዶ/ር አቡበክር ሰኢድ
(የአማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አምሓራ) የሕክምና ቡድን አመራር)

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 10:02


ሰው ነኝ፡

አማራ ነኝ፡

ኢትዮጵያዊ ነኝ፡

ጋዜጠኛ ነኝ፡

እኔ ዓባይ ዘውዱ ነኝ፡

ላመንኩበት ነገር ዋጋ ለመክፈል የማላቅማማ እሴቶቻችን እንዲከበሩ የምፈልግ እውነትን ፣ አቋም እና መርህን መከተል የምፈልግ እና የምሞክርም ሰው ነኝ እንዲሁም አሁን ላይ ደግሞ የማንነት ፣ የሕሊና እና የፖለቲካ እስረኛ ነኝ (የግፍ እስረኛ ነኝ)

እኔ ንፁህ ሰው ነኝ ፤ የፈፀምኩትም ወንጀል የለም ። በሽብር ሊያስከስሰኝ የሚችል ነገር የለም ፤ እኔ አሸባሪ ስርዓትንና ሽብርተኝነትን ፣ አምባገነንነትን ፣ ፀረ-ህዝብን ፣ ፀረ-ሀገርን ፣ ክህደትን፣ ባንዳነትን፣ የዘር ማጥፋትን (ጄኖሳይድን) አጥብቄ የምቃወም እና እንዳይፈፀም በምችለው መንገድ ሁሉ የማጋልጥ ሰው ነኝ ።

አማራነትን ፣ የአማራ እሴትን እና ታሪክን የሚጠላ ፣ የሚከስ እና የሚወነጅል ስርዓት እና ስሪት በመኖሩ ካልሆነ በስተቀር በሽብር ልከሰስ የምችልበት ሁኔታ የለም ።

ኃላፊነት የማይሰማው ፣ የህግ የበላይነትን የማያከብርና ለማስከበር አቅሙ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱ የሌለው በህዝብ ላይ የአፓርታይድ አገዛዝን የሚያሰፍን ስርዓትና ስሪትን በመታገሌ ነው ግፍ እየተፈፀመብኝ ያለው።

በዚህ አገዛዝ በጠላትነት ተፈርጀ፡ ሞት ታውጆበት በድሮንና በከባድ መሳሪያ በምድር እና በአየር ኃይል ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ በተለይም ለ2 ዓመት ገደማ እየተፈፀመ ያለውን ይፋዊ ጦርነት ልክ እንደ ስርዓቱ አማራን በመፈረጅ ህልውናው አደጋ ውስጥ እንዲገባ አፍና ልሳን በመሆን "አይዞህ በለው ፣ በርታ " እንድለው ምንም እንኳ አገዛዙ አብዝቶ ቢፈልግም በቻለው ሁሉ መከራ ቢያደርስብኝም ላመኑበት ነገር መፅናት ከቀደሙት ሞት አይፈሬ ጀግኖቻችን ልንወርሰው የሚገባ መልካም እሴት - ከመቃብር በላይ አፍ አውጥቶ የሚናገር የማይሞት ታሪክ በመሆኑ ምርጫዬ እሱ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ።

ፍትህን የምጠብቀውም ከተንሸዋረረ አገዛዝና ስርዓት ሳይሆን ፦

(ሀ) ከኃያሉ እግዚአብሔር ፣

(ለ) ከህዝብ /ከትውልድ ፣

(ሐ) ከጊዜ እና

(መ) ከታሪክ መሆኑን አምናለሁ ፡፡

ፍትህ ለሁሉም!

አመሰግናለሁ!

ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ ደመቀ!

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፋሪስ መዝገብ ከተከሰሱት 49ኛተከሳሽ የሆነው ጋዜጠኛ ዓባይ የእምነት ክህደት ቃል በሰጠበት ወቅት የተናገረው።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 09:48


https://www.youtube.com/watch?v=Rwq79jtro5g&t=23s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Feb, 08:17


የአማራ ፋኖ በጎጃም ሀዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር ደጃዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ ስፔሻል ፎርስ አሰልጥኖ አስመረቀ።

የከተማ ኦፕሬሽን እና ሽምቅ እንድሁም መደበኛ የጨበጣ ውጊያ ላይ ልዩ ትኩረት ያደረገ የረጅም ጊዜ ስልጠና ሲወስዱ ከርመው የተመረቁት እነዚህ ጀግኖች ጥይት ቢያልቅባቸው በጉልበት ጠላት መጣል እንድችሉ ተደርገው ነው የሰለጠኑትም ተብሏሎ።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Feb, 19:20


"አርበኛ ዘመነ ካሴ የሽብር ቡድን አመራር አይደለም አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ፋኖ በጎጃም ዋና ሰብሳቢ ነዉ። የአማራ ፋኖ በጎጃም ደግሞ በሽብር የተፈረጀ ድርጅት አይደለም። ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ጋር በስልክ ማዉራት ደግሞ ወንጄል አይደለም።
እኔ የተከሰስኩት ሰነፍ ስለሆንኩ ነዉ። በሰላማዊ መንገድ ከተማ ስለተቀመጥኩ ነዉ  የአባቶቻችንን ነፍጥ አንስቸ ብታገል ኖሮ አልከሰስም ነበር። "

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ንብረት ዛሬ በነበረው የእምነት ክህደት መስጠት ሂደት ላይ የተናገረው ነው።

በተጨማሪም ተከሳሹ ጋዜጠኛ  "በእኔ ላይ ክስ ከቀረበብኝ ውስጥ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው የአማራ ህባዊ ሃይል መሪ ተልእኮ በመቀበል የሚል ሲሆን ሆኖም ግን በክሱ ላይ 6ኛ ተከሳሽ እስክንድር ነጋ የሚል ስለሆነ የአማራ ህዝባዊ ኃይል መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ ስለሆነ የቀረበብኝ ክስ ሐሰት መሆኑን በቂ ማስረጃ ነው" በማለት አስመዝግቧል።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Feb, 15:41


"የደረሰብን ነገር እኛ ስለሆን ችለነው እንጂ ቀላል ሆኖ አይደለም" የአማራ ፋኖ የሕክምና ባለሙያዎች!

ሙሉውን ይከታተሉ👉

https://www.youtube.com/watch?v=KzyFqVq-e3A&t=19s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Feb, 14:53


በስልክ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም በመደወል መከላከያን ማጥቃት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ እንዲመቱት ትዕዛዝ ሰጥቷል የሚል ነው። አቃቤ ህግ ለዚህ ክሴ አስረጅ የሚሆን አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም። የተደወለበትና የጥሪ ተቀባይ ስልክ ቁጥሮች እንዲሁም የትዕዛዝ ተቀባይ ግለሰቦች ማንነት አልቀረበም። በቀረበ የማስረጃ ዝርዝር ላይም በተሰጠው ትዕዛዝ መነሻነት በቋሪትና ደጋዳሞት ወረዳዎች የተጎዱ ሰዎችና ንብረት ዝርዝርም አልቀረበም። የፍሬ ነገር ክርክር ሲደረግ የማቀርበው እንደተጠበቀ ሆኖ የወቅቱ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የፌደራል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን ወደ ክልሉ እንዲገባ የጠየቁት ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ነው። የመከላከያ ሰራዊት ወደ ደጋ ዳሞትና ቋሪት መግባት የሚችለውም ርዕሰ መስተዳደሩ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ በመሆኑ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም አቃቤ ህግ በክሱ ርምጃ ይወሰድበት ብለሃል ያለውን መከላከያ በምን አግባብ ቋሪትና ደጋዳሞት ሊገባ ቻለ የሚል ከባድ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄ የሚያስነሳ  ነው።

የተከበረው ችሎት፤ ክቡራን ዳኞች፤

አቃቤ ህግ በስልክ ትዕዛዝ ሰጥቷል በሚል የሁለት ግለሰቦች ንግግር የያዘ ድምፅ አዳምጨዋለሁ። አቃቤ ህግ በስሜ በተመዘገበ የታወቀ ስልክ ቁጥር ስለመደወሌ፣ የደወልኩበትን ስልክ ቁጥር እና አስተባባሪ ነው ያለውን ግለሰብ ስም አላቀረበም። ለመሆኑ በማስረጃነት ያቀረበው የድምፅ ቅጅ የኔ ስለመሆኑ በምን አረጋገጠ? በምን መሳሪያ መረመረው? ኢትዮጵያ የድምፅ አሻራ መመርመሪያ መሳሪያና በዚህ መስክ የሰለጠነ ባለሙያ የላትም። የት አስመርምሮት? ምን ያህል ፐርሰንት ከእኔ የትኛው ኦሪጅናል ድምፅ ተነፃፅሮ ምስስሎሽ ተገኘበት? እንደ አገርስ የድምፅ ምስስስሎሽ መቁረጫው መቶኛው(cut -off percentage) ምን ያህል ሲሆን ነው ህጋዊ ውጤት የሚኖረው?
እነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው እና የቀረበው የድምፅ ማሰረጃ የእኔ አይደለም እንጅ፤ ቢሆን እንኳን ወንጀል የሚያቋቁም አንዳችም የህግ ጥሰት ግን አላገኘሁበትም።

በመጨረሻም፦ አቃቤ ህግ ያቀረበው የፀና ፈቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ መያዝ ጉዳይ ህጋዊ ፈቃድ ያለኝ፣ የፈቃድ ደብተሩንም ለ8 ወራት ይዘውት ቆይተው የመለሱልኝና ማቅረብ የምችል መሆኔን ለችሎቱ አስታውቃለሁ።

አመሰግናለሁ
አቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Feb, 18:56


ይሄን ልጅ አስታወሳችሁት?

2014 ዓ/ም ወለጋ ላይ ከአንድ ሺ በላይ የአማራ ተወላጆች ሲጨፈጨፉ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነበር" ከዩኒቨርሲቲ ወጥተን የትጥቅ እናድርግ"  በሚል አንድ ተማሪ መድረክ ላይ ቆሞ ሲናገር የተሰማው።

ይህ ተማሪ ሞገስ አባራው ይባላል።የጎንደር ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪ ነበር። በሕግ ትምህርት አምስት ዓመት ሙሉ ተምሮ 3.7 ውጤቱን እንደያዘ የመመረቂያ ፅሁፉን አጠናቆ ተመርቆ ሊወጣ በጣት የሚቆጠሩ ወራቶች ሲቀሩት አገዛዙ በይፋ በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት አወጀ።

ተመራቂ የሕግ ትምሕርት ክፍል ተማሪው በወገኑ ላይ የታወጀውን ጦርነት ዳር ሆኖ መመልከት አልፈለገም። ለምርቃት እያደረገ የነበረውን ሽርጉድ እርግፍ አድርጎ ትቶ፡ ነፍጥ አነሳ።

አሁን ላይ አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) የግዙፉ ላስታ አሳምነው ፅጌ ኮር ቃል አቀባይና የአማራ ፍኖ በወሎ ከፍተኛ አመራር ነው።

ፋኖ ሞገስ አባራው በርሃ ከወረደበት እለት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓትና ደቂቃ ድረስ በፅናት እየታገለ ነው። ነገም የድሉ ባለቤት እሱና ጓዶቹ ናቸው።

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ሕዝብ!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Feb, 18:48


አለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ‼️

ይህ ሚዲያ በአማራ የህልውና ትግል ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለዉ ሚዲያ ቢሆንም ሚዲያው በአገዛዙ ዕጆች በተደጋጋሚ ተዘግቷል።
የተከበራቹህ የአማራ ህልዉና ትግል ደጋፊዎች ይህንን ሚዲያ subscribers ሸር እና ላይክ በማድረግ በየዕለቱ የሚለቀቁ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላቹህ!!!
👇👇👇
https://youtu.be/Bs-EQ49_uqk?si=9s3TWKt0pkYfvhX8

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Feb, 18:01


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) ምዕራብ ወሎ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ መካነሰላም ክፍለ ጦር በመካነሰላም ግንባር ጀብዱ መፈፀሙ ተገለፀ::

ሞት አይፈሬዎቹ የቦረና ሣይንት ጀግኖች በትናንትናው እለት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም የአብይን ጥምር ጦር ሲያበራዩት ውለዋል::

ከመካነሰላም ከተማ ወጣ ብላ በሣይንት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ቢሊ ተብላ በምትጠራው ታዳጊ ከተማ ግንባር በተደረገ እልህ አስጨራሽ ግብግብ በአርበኛ አብነው ታደሰ ምትኩ የሚመራው የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ መካነሰላም ክፍለ ጦር ሰራዊት በጠላት ላይ የኃይል የበላይነት ወስዶ 3 አምቡላንስ አስከሬን ጠላት እንድታቀፍ አድርጓል::

በዚህ ትንቅንቅ አንድ ፋኖ በጀግንነት ሲዋጋ ቆይቶ መስዋዕትነት የከፈለ ሲሆን በአነስተኛ መስዋዕትነት የቦ/ሣይንት አውራጃ ጀግኖች ወሳኝ ወታደራዊ ድል አስመዝግበዋል::

የጦር ሰፈራቸውን ላለመልቀቅ ባደረጉት ትንቅንቅ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ይዞታቸውንም ማስከበር ችለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

"ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን"
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)
ጥር 26/2017 ዓ.ም

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Feb, 07:58


ሰበር ቪዲዮ ከወሎ!

የዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጅ ሕዝቡን አስደመመው!

ከአዲስ አበባ የመጡ እንግዶች ከፋኖ ጋር ሲገናኙ የተቀረፀ!

https://www.youtube.com/watch?v=IrgH-tdXnjc

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Feb, 07:14


አርበኛ ሰለሞን አሊ!

አማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አምሓራ) ልጅ እያሱ ኮር የቤተ አማራ ክ/ጦር ዋና አዛዥ!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Feb, 02:01


ሰበር ቪዲዮ ከወሎ!

የዋርካው ምሬ ወዳጆ ቀኝ እጅ ልክ ልካቸውን ነገራቸው!

ሕዝቡ በተሰበሰበበት አደደባባይ ምን ተፈጠረ?

https://www.youtube.com/watch?v=Rwq79jtro5g

Mereb Media መረብ ሚዲያ

02 Feb, 12:17


የቪዲዮ ስርጭት ከመና መቀጣዋ ተራራ!

ሙሉውን ይከታተሉ

https://www.youtube.com/watch?v=aq-ULzDD4gg&t=206s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

02 Feb, 11:46


የግፍ ጥግ በሜጫ ወረዳ
በቀን 23_05_2017 ዓ/ም የፅንፈኛው የአብይ ወራሪ ሠራዊት  በሰሜን ጎጃም ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ ገሸር ጎጥ በርካታ ንፁሃኖችን ከቤታቸው እያወጡ ከ10በላይ ግለሰቦችን አረሽነዋል
በርካቶችን በጥይት ቁስለኛ አድርገው ደብድበው በሞትና ሽረት ውስጥ ይገኛሉ። ሌላው በትናንትናው ዕለት የቀብር ሥነሥርዓታቸው ላይ የተገኙ ከባህርዳር ለለቅሶ የተገኙ ቤተሠቦች መካከልም አንድ ንፁሃንን በጥይት ደብድበው ገለዋል።
ከእነዚህ  ንፀሃን ውስጥ በጥቂቱ
1ኛ ተመሥገን አለሙ
2ኛ ጥሩዬ ፀጋ
3ኛ ምሥጌፈጠነ
4ኛ በቃሉ ዘመነ
ገሸር ላይ የተቀበሩ ሢሆን ሌሎችን አሥከሬናቸውን ይዞ አልሰጥም ሢል
ድብደባና በቁሥለኛ ያሉ ደግሞ
1ኛ በላይ ቄስመንጌ
2ኛ ምትኬ ጥሌ
3ኛ ፀጋ ሞላ
4ኛ አትርሣው ተፈራ
5ኛ ሙሉ ፈጠነ  የተባሉ ንፁሃን በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ናቸው
በተመሣሣይ  ሙገር ከተማ ላይ የተደበደቡ ቁስለኞች አክመሻል በሚል አንድ የጤና ባለሙያ አፍነው ወደ መሸንቲ ከወሠዷት በሗላ እስካሁን አድራሻዋ አልተገኘም።

የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ህ/ግንኙነት መምሪያ!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

02 Feb, 08:57


በአገዛዙ ጭካኔ የተገደለዉ ዶክተር !!

የጅማ ዩኒቨርሲቲው የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ የቀዶ ጥገናው ስፔሻሊስት ፣ መምህሩና ተመራማሪው ዶ/ር አንዷለም ዳኜ በአገዛዙ መከላከያ ተረሸነ።

ትሁቱ ፣ የሰው ልክ ፣ ቅን ፣ በርካቶችን ከውጭ ሃገር ህክምና የገላገለ ፣ የብዙዎች መድኃኒት ፣ ዕንቁ ተመራማሪና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣  ተመራማሪ እና መምህር  ፤ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር በብልፅግናው መንግስት ወታደሮች ከስራ መልስ ከመኪናው አስወርደው በጥይት ደብድበው ገለውታል።

ዶክተር አንዷለም በባህርዳር ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሰራ አምሽቶ ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተጉዞ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በማሰብ ወደተጠቀሰው ሆስፒታል በማሽከርከር ላይ ሳለ ቆሼ የተባለ ሰፈር ሲደርስ ወታደሮቹ አ ስቁመው ያለርህራሄ የገደሉት።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

02 Feb, 07:59


ሰበር ቪዲዮ ከወሎ!

የዋርካው ምሬ ወዳጆ ቀኝ እጅ ልክ ልካቸውን ነገራቸው!

ሕዝቡ በተሰበሰበበት አደደባባይ ምን ተፈጠረ?

https://www.youtube.com/watch?v=Rwq79jtro5g

Mereb Media መረብ ሚዲያ

01 Feb, 15:36


ተጨማሪ ምስል ግሸን ደብረ ከርቤ!

ጥር 21/2017 ዓ/ም የተከበረው የአስተርዕዮ ማርያም ንግስ በዓል በዳግማዊት እየሩሳሌም ግሸን ደብረ ከርቤ!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
###
አዲሱን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Jan, 05:29


የአማራ ሕዝብ በዚህ መልኩ እየተሰቃየ ነው።

በየወረዳው ተመድበው የነበሩ አምቡላንሶችን መከላከያ ሰራዊቱ ተዘፎ በጦርነት ወቅት ትጥቅና ስንቅ ማመላለሻ እንዲሁም ለከፍተኛ አዛዦቹ መጓጓዣ አድርጓቸዋል።

ሕዝቡ ድንገተኛ የጤና ችግር ሲደርስበት እና ነፍሰጡር እናቶች በምጥ ሲያዙ በቃሬዛ/በወሰካ/ ተሸክሞ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ሕክምና ወዳለበት ቦታ ይጓዛል።

ሕክምና ቦታ ከደረሰ በኋላ፡ ሕክምና ተቋሙ በድሮን ወድሟል፡አንድም መድሃኒት የለውም፡ አልያም የጤና ባለሙያዎቹ ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል ተገድለዋል ወይም ለእስር ተዳርገዋል።

ሙሉውን ይከታተሉ👉https://youtu.be/I-g770WgEJE?si=dYvozRSlMxBEOQuV

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Jan, 04:52


የተከበራችሁ የመረብ ቤተሰቦች!

የመጀመሪያው የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅ ከፀረ አማራ ኃይሎች በተደረገብን ቅንጅታዊ ሪፖርት ምክኒያት ታግዷል።

ስለሆነም አዲስ የፌስቡክ ገፅ ከፍተናል።

ተወዳጁት።ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Jan, 12:31


https://www.youtube.com/watch?v=amxJG6NilrA

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Jan, 10:59


የተከበራችሁ የመረብ ቤተሰቦች!

የመጀመሪያው የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅ ከፀረ አማራ ኃይሎች በተደረገብን ቅንጅታዊ ሪፖርት ምክኒያት ታግዷል።

ስለሆነም አዲስ የፌስቡክ ገፅ ከፍተናል።

ተወዳጁት።ለወዳጅ ዘመድዎ ጋብዙ።

https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Jan, 04:24


"ሰማይ ተደፍቶብኛል፡ የበሬ ቀምበር እንኳን አልተረፈልኝም" በቤታቸው ፍርስራሽ አመድ ላይ ቁጭ ብለው የሚያለቅሱ አባት!

በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ድብኮ ቀበሌ ልዩ ስሙ እንኮይበር በተባለ አከባቢ የአገዛዙ ወታደሮች የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል መኖሪያ ቤቶችን ቤንዚን አርከፍክፈው በእሳት አቃጥለዋል።

በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ጎልማሳ አባት በቅርቡ ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁ ሲሆን፡ የባለቤታቸውን አርባ ለማውጣት ዝክር ሲዘክሩ የተመለከቱት የአገዛዙ ወታደሮች "ፋኖን ልታበሉ ነው" በሚል መኖሪያ ቤታቸውን በእሳት አቃጥለውባቸዋል።

ድርጊቱ የተፈፀመው ጥር 09/2017 ዓ/ም እኩለ ቀን ገደማ ነው። ወታደሮቹ ቤቱ በእሳት ተቃጥሎ እስኪጨርስ ማንም ሰው እሳቱን እንዳያጠፋ ቁጭ ብለው ሲከለክሉ እንደነበርም ተነግሯል።

ሙሉ ቪዲዮውን ተመልከቱ👉
https://www.youtube.com/watch?v=amxJG6NilrA&t=49s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Jan, 04:02


https://youtu.be/FZc8NtRpSJY?si=moSTsoeR2lqZ7pc0

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 19:36


ሰበር ቪዲዮ ከወሎ!

ከባድ የጦር ወንጀል ተፈፀመ!

ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ከስፍራው!

https://www.youtube.com/watch?v=amxJG6NilrA

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 18:34


በባህርዳር ከተማ ዙሪያ የነበረው የአገዛዙ ወታደሮች ምሽግ በፋኖ መሰበሩ ተሰምቷል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር  ስር የሚገኘው ባህርዳር ብርጌድ ዛሬ ጥር 10/2017 ዓ/ም ንጋት ጀምሮ በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህርዳር ከተማ ዙሪያ በወሰደው እርምጃ አንድ ዲሽቃን ጨምሮ ከ56 በላይ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ማርኮ መታጠቁን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

"ብርጌዳችን በከፍተኛ ሁኔታ እራሱን በማደራጀት በዛሬው እለት በክልላችን ውቢቷ ባህርዳር ውስጥ በተለያዩ ቦታወች መሽጎ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ትንቅንቅ በማድረግ ለ3ወር ጠላት ሰፍሮበት የአውንኸራን ምሽግ በመስበር ታላቅ ድል ተቀዳጅተናል" ሲሉ ብርጌዱ በቃል አቀባዩ በኩል አሳውቋል።

በኃያላኑ የጎጃም ፋኖዎች ምሽጉ የፈረሰበት የአገዛዙ ጦር ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ መሣሪያውን እያዝረከረከ ወደ መሀል ከተማዋ ከተማ መፈርጠጡን የጣቢያችን ምንጮች ገልፀዋል።

ፋኖ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጦር ሳይንስ ስልት ተጠቅሞበታል በተባለው በዚህ ኦፕሬሽን
አንድ ዲሽቃ፣ አራት ብሬን ከነ ሙሉ ሸንሸኑ፣ አንድ ስናይፐር፣ 56 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 30 የክላሽ ካዝና ከነ ተተኳሹ ማርኮ መታጠቁን መረብ ሚዲያ ከብርጌዱ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም በቁጥር ለመግለፅ የሚያዳግት በርካታ የጠላት አስክሬን በየቦታው ወድቆ ይገኛል ተብሏል።

በዚህ ኦፕሬሽን በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተሸላሚ የነበረ አንድ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች ኮረኔል ኮረኔል  ተረሽኗል ተብሏል።

በተጨማሪም  በቁጥር ዘጠኝ የጠላት ኃይሎች የተማረኩ ሲሆን በርካቶች ቆስለው ወድቀዋል ነው የተባለው።

ተጨማሪ👉https://www.youtube.com/watch?v=oOt2FfH7JF4

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 18:06


ጎንደር ከተማ በፋኖ ተከባ ውላለች!

በጎንደር ከተማ ዙሪያ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጦርነት እየተካሄደ የዋለ ሲሆን፡ የአገዛዙ ወታደሮች በከተማዋ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የእንቅስቃሴ እገዳ መጣላቸው ተሰምቷል።

በዓሉን ለመታደም በሚመጡ እንግዶች ላይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት በከተማዋ መሽጎ የነበረው የብልፅግና ካድሬ የሚሸሸግበት ስምጥ፣ የሚገባበት ምጥ ጠፍቶታል ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጎንደር መግባታቸውን ተከትሎ ለክፉ ቀን ተብሎ አራት ኪሎ ቅጥር ግቢ ዙሪያ ሲቀለብ የነበረ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቀይ ቦኔት ለባሽ የሪፐብሊካን ጋርድ ወደ ጎንደር ተልኮ በከተማዋ ዙሪያ የሰፈረ ቢሆንም ነገር ግን የራስ አሞራው ውብነህ ልጆች "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ብለው የሳት ዝናብ ሲያዘንቡበት ውለዋል።

ሰማይ የተደፋባቸው የአገዛዙ ወታደሮችም በከተማዋ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸው ታውቋል።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ስር የሚገኙ ፋኖዎች ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅ እያደረጉ መዋላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የራስ አሞራው ውብነህ ልጆች በከተማዋ ዙሪያ በተመረጡና የጠላት ጦር የተከማቸባቸው ቦታዎች ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ማካሄዳቸውን ነው ጣቢያችን ያረጋገጠው።

ለጥምቀት ወደ ጎንደር ያመራችሁ እንግዶች ኦፕሬሽኑ ከጠላት ጋር ብቻ ስለሆነ መደናገጥ አያስፈልግም የሚል መልዕክትም ተላልፏል።

በከተማዋን ዙሪያ ባሉ ተራሮች ሰፍረው በዓሉን ተገን በማድረግ በፋኖ ላይ ትንኮሳ በፈፀሙት የብልፅግና አገልጋይ ወታደሮች ላይ ፋኖ በወሰደው አፀፋዊ እርምጃ በርካታ የሪፐብሊካን ጋርድ እንደ ደረቀ ዛፍ ቅጠል እረግፈዋል።

"አይ ቀይ ቦኔት ብላሽ
አይ ኮማንዶ ብላሽ
አይ መድፍ ብላሽ
ዞሮ አደባየው ፋኖ በክላሽ" በሚል የበዓሉ ታዳሚ ተደምሟል።

ይህ የዛሬው የፋኖ ኦፕሬሽን በአገዛዙ ጥበቃ የሚከናወን ምንም አይነት የአደባባይ በዓል እንደማይኖር ያሳየ ነው ተብሏል።

በተመሣሣይ ፋኖ በየትኛውም ሰዓትና ሁኔታ ማድረግ የፈለገውን ነገር እንዳያካሂድ የሚያግደውና የሚያስቆመውው ነገር እንደሌለ በግልፅ ታይቶበታል ነው ያሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች።

በከተማዋ ዙሪያ ማርፈጃውን የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሰዓት በኋላ ባለው መብረዱ ቢነገርም ነገር ግን የአገዛዙ ወታደሮች ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን አጥምደው በከተማዋ መኃል ከላይ ከታች ሲቅበዘበዙ አምሽተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የአገዛዙ ባለስልጣናት አርፈውበት በነበረው ዶሀ ሆቴል ድረስ ማርፈጃውን ዘልቆ ጥቃት መፈፀም የቻለው ፋኖ፡ የውጊያውን ሁኔታ በራሱ ስልትና ንድፍ እየመራ አርፍዷል ተብሏል።

በተለይ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ እረፋድ አምስት ሰዓት ድረስ ባለው በተከተማዋ ዙሪያ እና በተመረጡ በከተማዋ መኃል ባሉ አከባቢዎች ፋኖ በወሰደው እርምጃ የአገዛዙ ጦር ድንብርብሩ መውጧቱ ነው የተነገረው።

ተጨማሪ👉

https://www.youtube.com/watch?v=oOt2FfH7JF4

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 17:53


"የናዝሬቱ እየሱስ አለምን ያድን ዘንድ ወደ መስቀሉ ያደረሰው ይሁዳ እንጂ ጳጥሮስ ወይንም ከደቀ መዛሙርቱ ሌላኛው አይደለም"  አርበኛ ዘመነ ካሴ!

የአማራ ፋኖ በጎጃም ዋና ሰብሳቢ አረበኛ ዘመነ ካሴ የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ይህ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

አዲስ የተከፈተው ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ👉https://www.facebook.com/share/14tusNR7Kp/

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 17:11


ሰበር ቪዲዮ ከወሎ!

ከባድ የጦር ወንጀል ተፈፀመ!

ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ከስፍራው!

https://www.youtube.com/watch?v=amxJG6NilrA

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 17:09


የተከበራችሁ የመረብ ቤተሰቦች ዝግጅቶቻችን በመረጃ ቲቪ የሚተላለፉበት ሰዓት ተጀምሯል።

ተከታተሉ!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 15:48


በጎንደር ከተማ ዙሪያ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጦርነት እየተካሄደ የዋለ ሲሆን፡ የአገዛዙ ወታደሮች በከተማዋ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የእንቅስቃሴ እገዳ መጣላቸው ተሰምቷል።

በዓሉን ለመታደም በሚመጡ እንግዶች ላይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት በከተማዋ መሽጎ የነበረው የብልፅግና ካድሬ የሚሸሸግበት ስምጥ፣ የሚገባበት ምጥ ጠፍቶታል ተብሏል።

ማርፈጃውን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የአገዛዙ ባለስልጣናት አርፈውበት በነበረው ዶሀ ሆቴል ድረስ ዘልቆ ጥቃት መፈፀም የቻለው ፋኖ፡ የውጊያውን ሁኔታ በራሱ ስልትና ንድፍ እየመራ መዋሉ ታውቋል።በዝርዝር ይዘነዋል።

###

በባህርዳር ከተማ ዙሪያ ፋኖ በወሰደው ልዩ ኦፕሬሽን የኮሎኔልነት ማዕረግ ያለው አንድ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች ወታደራዊ አዛዥ ሲገደል፡ የአገዛዙ ወታደሮች ላለፉት ሦስት ወራት መሽገውበት የነበረው የኮንክሪት ምሽግ በፋኖ ክንድ መደርመሱ ተሰምቷል።

በዚህ ኦፕሬሽን አንድ ዲሽቃን ጨምሮ 56 ክላሽንኮቭ መሣሪያና ሌሎች የቡድን መሣሪያዎች በፋኖ እጅ መግባታቸው ታውቋል።በዝርዝር አካተነዋል።

ዝርዝሩን ይከታተሉ👉https://www.youtube.com/watch?v=oOt2FfH7JF4

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 15:34


ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ የተላለፈ መልዕክት!

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር አደረሳችሁ አደረሰን እያልን፤ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በሚያስተዳድራቸዉ በሁሉም ቀጣናዎች እንዲሁም በተቀሩ አካባቢዎች የምትገኙ ወገኖች ለተቸገሩ በመርዳት እና በመተሳሰብ እንድታሳልፉ እናሳስባለን።

ክብረ በዓሉን ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ በልበ ሙሉነት እና በንቃት እንደምንጠብቀዉ እየገለፅን፤ በሌላ በኩል የግፈኛዉ ወንበር ጠባቂዎች በያዟቸው ጥቂት የከተማ ቀበሌዎች ስር ሆናችሁ ክብረ በዓሉን ለምታከብሩ ህዝበ ከርስቲያን ወንድሞችና እህቶቻችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከግፈኛዉ ስርአት የጭቆና ስቃይ ቀንበር ነፃ እንደምናወጣችሁ እንገልፃለን።

ሕዝባችን የጥምቀት በዓልን በሰላም እንዲያሳልፍ በማሰብም ከአገዛዙ የሚሰነዘር ጥቃት ከሌለ በቀር ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በኩል በዓሉ እስከሚያልፍ ምንም አይነት የተኩስ ጥቃት እንደማንከፍት እና ጥምቀተ በዓሉን ተረጋግታችሁ እንድታከብሩ ስንል እናሳስባለን።

ጥር 10/05/2017 ዓ.ም

አርበኛ ፋኖ መከታው ማሞ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ


የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ👉https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 15:03


https://www.youtube.com/watch?v=oOt2FfH7JF4

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 13:45


የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ዛንበራ ብርጌድ ገንበው ሻለቃ በደጀን ወረዳ ፅድም ጥር 09/2017ዓም ቀበሌ ከሌሊቱ 4:00 ሰዓት ሰረጎ በመግባት በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት ሁለት ሚኒሻ እስከወዳኜው ሲሸኝ ሁለቱን ቁስለኛ አድረገዋል።

፨በሌላ መረጃ በትላንትነው እለት ጥር 09/2017ዓም  የአገዛዙ ሀይል ከደብረወርቅ ከተማ በአባዱላ በመምጣት ኬላ ላይ ያሉ የሶማ ብርጌድ የፋኖ አባላትን ከበባ አድርገው ለመያዝ አስበው የመጡ ቢሆንም በጉዞ ላይ በነበሩ የአገዛዙ ሀይል ላይ ሶማ ብርጌድ በወሰደው የደፈጣ ውጊያ ሁለቱ እስከወዳኘረው ሲሸኙ ቀሪዎቹ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጦል።

፨በእናረጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ድንጃሜ ቀበሌ ጨየ ወንዝ ላይ ሻወር እየወሰዱ በነበሩ የአገዛዙ ሀይልን አንድ ወጣት አንድ ጥቁር ክላሽ ማርኮ ሶማ ብርጌድ ይናጭ ሻለቃን ተቀላቅሏል።

አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!ለአማራ ህዝብ!

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ👉https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 09:15


የባህርዳርና አካባቢው ተጋድሎ !

በዛሬው የባህርዳር ብርጌድ በከፍተኛ ሁኔታ እራሱን በማደራጀት የክልላችን ውቢቷ ባህርዳር ውስጥ በተለያዩ ቦታወች መሽጎ የነበረው የጠላት ሀይል በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ትንቅንቅ በማድረግ ጠላት ለ 3 ወር ሰፍሮበት  የነበረውን የአውንኸራ ምሽግ  በአንበሶች በባህርዳር ብርጌድ ምሽጉን በመስበር በማስለቀቅ አሁን ላይ ጠላት በደረሰበት ከፍተኛ ምት መቋቋም ስላልቻለ  እራሱን ለመትረፍ ወደ ባህርዳር ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል።

  እስካሁኑ ሰዓት ድረስ  የተማረኩ መሳሪያወች
➢1 ዲሽቃ
  ➦ 4  ብሬን ከነ ሸንሸኑ
➦1 ስናይፐር
➢ 56 ክላሽ
➢30 የክላሽ ካዝና ከነ ተተኮሹ
ከጠላት መማረክ የተቻለ ሲሆን  በቁጥር ለመግለፅ በሚያዳግት ሁኔታ  የጠላት አስክሬን በየቦታው ተዘረክርኮ ይገኛል
➢ በሰሜኑ ውጊያ ጊዜ ተሸላሚ የነበረ 1 ኮረኔል  ተረሽኗል
      በተጨማሪም  9 የጠላት ሀይል  በህይወት መማረክ ተችላል አሁንም ወደፊት እየገሰገስን ነው ተጨማሪ ድሎችም ይኖራሉ ...  ለጊዜው ያለው መረጃ ይኸን ይመስላል
አድማ ብተና ፓሊስ እና ሚሊሻ አሁንም ቢሆን ወደ ቀድሞ ማንነታቹህ ተመልሳቹህ ለእውነት እየተዋደቀ ላለው ከፋኖ ጎን እንድትሰለፉ ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር       ባህርዳር ብርጌድ  ቃል አቀባይ ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ ጥሪ አቅርቧል።

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ👉https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Jan, 07:37


https://www.youtube.com/watch?v=Gq8zIIqOhvY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

11 Jan, 19:33


https://youtu.be/KftdHE7DdAU?si=j7bTr59VCLynG7cp

Mereb Media መረብ ሚዲያ

11 Jan, 07:58


ሰበር ቪዲዮ ከጎንደር!

አርሶ አደሩ ከነ ኮማንዶ ሳሚና ከነ አርበኛ ደረጀ ጎን መቆሙን አሳወቀ!

ጠብመንጃውን ይዞ ግልብጥ ብሎ ወጣ!

https://youtu.be/KftdHE7DdAU?si=vEW9sLtfEIicRfmB

Mereb Media መረብ ሚዲያ

11 Jan, 06:15


የወልድያ ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ምክትል አዛዥ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት መፈፀሙ ተነገረ!

ትናንት እና ዛሬ በሦስት የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት መፈፀሙ ነው የታወቀው።

በወልዲያ ከተማ የቀድሞው የሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ አዛዥና የአሁኑ የከተማ አስተዳደሩ ሚሊሻ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ በሆነው በኮማንደር ደርበው መኖሪያ ቤት ላይ ዛሬ ጥር 02/2017 ዓ/ም ረፋድ 3 ሰዓት ላይ የቦምብ ጥቃት መፈፀሙን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በወልድያ ከተማ ጎንደር በር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ልዩ ቦታው ጃይካ ትምርህት ቤት በስተጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት የሚሊሻ ፅ/ቤት ም/ኃላፊው ኮማንደር ደርበው፡ ከዚህ ቀደም በከተማ አስተዳደሩ የ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ እንደነበረ ነው መረብ ሚዲያ ያገኘው መረጃ የሚያመላክተው።

በኃላፊው መኖሪያ ቤት ላይ ዛሬ ጥር 02/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 3:15 ላይ በተፈፀመው የቦንብ ጥቃት፡ የደረሰው ጉዳት በውል ባይታወቅም ነገር ግን የኃላፊው ቤተሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስለመወሰዳቸው ተጠቁሟል።

በመኖሪያ ቤቱ ላይ ዛሬ ማርፈጃውን የቦምብ ጥቃት የተፈፀመበት ኮማንደር ደረበው ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የከተማዋ ነዋሪዎችን በማፈን ከ100 ሺ ብር ጀምሮ ሲቀበል እንደነበር እና ገንዘብ መስጠት ያልቻሉትን ደግሞ የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል ወደ አዋሽ አርባ እና ወደ ሌሎች ማጎሪያ ቤቶች እንዲወሰዱ ሲያስደርግ ነበር ሲሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና!

በወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አበራ መኖሪያ ቤት ላይ በትናንትናው እለት የቦምብ ጥቃት ተፈፅሟል።

ኮማንደር አበራ ከወልድያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ አይሰማ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ ነው የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመው ሲሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀውል።

በከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አበራ መኖሪያ ቤት ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት የደረሰውን ጉዳት እስካሁን በውል ማወቅ አልተቻለም።

በተመሣሣይ በትናንትናው እለት የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈፅሟል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ በሆነው እንስፔክተር አያሌው መኖሪያ ቤት ላይ ነው ትናንት ጥር 01/2017 ዓ/ም የቦምብ ጥቃት የተፈፀመው።

በከተማዋ ልዩ ስሙ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ የቦምብ ጥቃት የተፈፀመበት እንስፔክተር አያሌው፡ በግል ጉዳይ ተካሰው ፍትሕ ለማገኘት ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎችን "የፋኖ ደጋፊ ናቸው ብየ ለከፋ ነገር ሳልዳርጋችሁ ገንዘብ ክፈሉኝ" በሚል በማስፈራራት ከ50ሺ ብር ጀምሮ እስከ 100 ሺ ብር እንደሚቀበል ጠቁመዋል።

እንስፔክተር አያሌው በመኖሪያ ቤቱ ላይ የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመው ሁለት ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው ጥቃት ቀላል ጉዳት ሲያደርስ፡ የከተማዋ ፖሊሶች ተሰባስበው በመጀመሪያው ጥቃት የደረሰውን ጉዳት በመመልከት ላይ ሳሉ ሁለተኛው ጥቃት እንደተፀመባቸው ነው ምንጮቻችን የገለፁት።

በዚህም ከአምስት በላይ የፖሊስ አባላት ቆስለው ወደ ሕክምና ጣቢያ መወሰዳቸው ተነግሯል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አራጌ ይመር በወልድያ ከተማ ጎንደር በር አከባቢ ልዩ ቦታው ከቀበሌ 06 ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ ከሳምንት በፊት የቦምብ ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።

ተጨማሪ👉

https://www.youtube.com/watch?v=5OO4j7d06bE&t=106s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

11 Jan, 05:57


ሰበር ዜና ከጎጃም!

የአርበኛ ዘመነ ካሴ ልጆች ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጡ!

"በከፋፋዮች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንወስዳለን"

https://www.youtube.com/watch?v=mo36EZCUaMI

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Jan, 20:12


በደብረብርሃን ከተማ ትናንት ለሊቱን ለአጭር ሰዓት የቆየ ከባድ ውጊያ መደረጉ ተገለፀ!

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክ/ጦር ስር የጋተው ብርጌድ ፋኖዎች ደብረብርሀን ከተማ ዘልቀው በመግባት የተሳካ ኦፕሬሽን መፈፀማቸው ነው የተነገረው።

በዚህም በከተማዋ ለአጭር ሰዓታት የቆየ ከባድ ውጊያ የተደረገ ሲሆን በዚህ ውጊያ የአጉዛዙ ወታደሮች የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ማስተናገዳቸው ታውቋል።

በተጠና ሰርጅካል ኦፕሬሽን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የአገዛዙ ኃይሎች፡ በከተማዋ ቤት ለቤት እየዞሩ ፍተሻ ሲያካሂዱ ውለዋል።

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ👉https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Jan, 19:42


የፋኖን ትግል ጠልፎ ለመጣል ተልዕኮ በተቀበሉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰዱ በአርበኛ ዘመነ ካሴ በሚመራው አማራ ፋኖ በጎጃም ስር የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች አስጠነቀቁ።

ወታደራዊ አመራሮቹ ትግሉን ጠልፎ ለመጣልና በፋኖ መኃል ልዩነትን ለመፍጠር ተልዕኮ ተቀብለው በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ትዕግስታችን አልቋል፡ የመጨረሻውን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።በዝርዝር ይዘነዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ያጋጣመውን የእሳት አደጋ የቀሰቀሱት የአገዛዙ ወታደሮች ናቸው ሲል በአርበኛ ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ አስታወቀ!

የነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ድርጅት በዋድላ ወረዳ በ11 ቀበሌዎች የእሳት አደጋ በመቀስቀስ የ154 አርሶ አደሮች የእህል ክምር እንዲወድም ያደረገው መከላከያ ሰራዊቱ ነው ሲል ባወጣው መግለጫ አስነብቧል።በዝርዝር ይዘነዋል።

###

የሰሜን ሸዋ ዞን መቀመጫ በሆነችው ደብረብርሃን ከተማ ትናንት ለሊት የሸዋ ፋኖዎች ዘልቀው በመግባት አስደናቂ ኦፕሬሽን ሲፈፅሙ፡ በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ተሰማርተው በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ደግሞ ከባድ የሆነ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።

የደብረብርሃኑ ሰርጅካል ኦፕሬሽን እጅግ ስኬታማ ነበር የተባለ ሲሆን በርካታ የአገዛዙ ጀበና ሰባሪ ኮማንዶዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ለወስደዋል ተብሏል።

በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳም ህፃናትን ጨምሮ ንፁኋንን ለመጨፍጨፍ ስምሪት ለመውሰድ ተሰባስበው በነበሱ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ነው ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው። በዝርዝር ይዘነዋል።


ተከታተሉ👉https://www.youtube.com/watch?v=mo36EZCUaMI

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Jan, 16:59


ሰበር ዜና ከጎጃም!

የአርበኛ ዘመነ ካሴ ልጆች ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጡ!

"በከፋፋዮች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንወስዳለን"

https://www.youtube.com/watch?v=mo36EZCUaMI

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Jan, 15:44


በዛሬዉ ዕለት ጥር 02/2017 ዓ.ም

በተከታታይ በሽምቅና በደፈጣ ረፍት ያጣው ወራሪ ሠራዊት አርብ ገበያ ከተማን ለቆ ፈርጥጦ ደ/ታቦር ገብቷል።

አብዛኛው የሚሊሻና አድማ ብተና አባላትም የቀረበለትን የምሕረት አዋጅ ተጠቅሞ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ይገኛል።

ጸረ አማራዉ የአብይ አሕመድ ወራሪ ሠራዊት አማራ ስለሆንህ ብቻ ምቹ ጊዜ ጠብቆ ሳይረሽንህ እስከ ጥር 15/2017 ዓ.ም በሠላማዊ መንገድ በየቀጠናው ወደ ሚገኝ የፋኖ አደረጃጀት ምሕረት ግባ!!!

        ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
      አርበኛ ባዬ ቀናዉ

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ👉https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Jan, 15:05


በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ያጋጣመውን የእሳት አደጋ የፈጠረው አገዛዙ ነው ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ አስታወቀ!

በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በ11 ቀበሌዎች የሰብል ክምር ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ተሰምቷል።

በዋድላ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ነው የተገለፀው።

በደረሰው ቃጠሎ አደጋው 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚሆን የእህል ክምር ላይ ጉዳት መድረሱንና ይህም ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ነው የተነገረው።

በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በ11 ቀበሌዎች
ያጋጠመውን የእሳት አደጋ በሚመለከት በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል መግለጫ ያወጣው በአርበኛ ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ የእሳት አደጋውን ያስነሳው የብልፅግና መንግስት መሆኑን ለማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል።

በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ የወደመው የህዝባችን ሰብል በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው የብልፅግናው መንግስት ወታደሮች ናቸው ነው ያለው ድርጅቱ።

የአማራ ፋኖ በወሎ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መግለጫው፡ በዋድላ ወረዳ ጥር 1/2017 ዓ.ም አዳሩን የአገዛዙ ወታደሮች በቀሰቀሱት የእሳት ቃጠሎ የ154 ገበሬዎች የሰብል ክምር የወደመ መሆኑን ገልፆ፡ ብልፅግና ባለፉት ጊዜያቶች በአማራ ህዝብ ላይ መንግስት መር ረሃብና የህክምና አጦት እንደሚፈፅም በበርካታ ዝግ ስብሰባዎች ሲፎክር እንደነበር አስታውሷል።

"የአማራ ህዝብ ላይ በራሱ ሜዳ ጦርነትና ረሃብ ከፍተንበታል በዚህም ካለኛ ፈቃድ እርዳታም ሆነ መድሃኒት እንዳይደርሰው አድርገን እናንበረክከዋለን" በሚል ሲፎክሩ የነበሩት የብልፅግናው መንግስት ምንጣፍ ጎታች ወታደራዊ አዛዦችና የክልሉ አመራሮች የፎከሩትን በህዝባችን ላይ እየፈፀሙት ይገኛሉ ብሏል ድርጅቱ።

ስለሆነም ህዝባችን ይህንን ብልፅግና መር ፀረ አማራ ተግባር በመገንዘብ በሌሎች አካባቢዎች ላይ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፀምበት ነቅቶ እንዲጠብቅና የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድ ሲል በአርበኛ ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መግለጫ መልዕክት አስተላልፏል።

የመረብ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ👉https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Jan, 13:13


የወልድያ ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ምክትል አዛዥ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት መፈፀሙ ተነገረ!

ትናንት እና ዛሬ በሦስት የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት መፈፀሙ ነው የታወቀው።

በወልዲያ ከተማ የቀድሞው የሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ አዛዥና የአሁኑ የከተማ አስተዳደሩ ሚሊሻ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ በሆነው በኮማንደር ደርበው መኖሪያ ቤት ላይ ዛሬ ጥር 02/2017 ዓ/ም ረፋድ 3 ሰዓት ላይ የቦምብ ጥቃት መፈፀሙን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በወልድያ ከተማ ጎንደር በር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ልዩ ቦታው ጃይካ ትምርህት ቤት በስተጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት የሚሊሻ ፅ/ቤት ም/ኃላፊው ኮማንደር ደርበው፡ ከዚህ ቀደም በከተማ አስተዳደሩ የ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ እንደነበረ ነው መረብ ሚዲያ ያገኘው መረጃ የሚያመላክተው።

በኃላፊው መኖሪያ ቤት ላይ ዛሬ ጥር 02/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 3:15 ላይ በተፈፀመው የቦንብ ጥቃት፡ የደረሰው ጉዳት በውል ባይታወቅም ነገር ግን የኃላፊው ቤተሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስለመወሰዳቸው ተጠቁሟል።

በመኖሪያ ቤቱ ላይ ዛሬ ማርፈጃውን የቦምብ ጥቃት የተፈፀመበት ኮማንደር ደረበው ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የከተማዋ ነዋሪዎችን በማፈን ከ100 ሺ ብር ጀምሮ ሲቀበል እንደነበር እና ገንዘብ መስጠት ያልቻሉትን ደግሞ የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል ወደ አዋሽ አርባ እና ወደ ሌሎች ማጎሪያ ቤቶች እንዲወሰዱ ሲያስደርግ ነበር ሲሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና!

በወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አበራ መኖሪያ ቤት ላይ በትናንትናው እለት የቦምብ ጥቃት ተፈፅሟል።

ኮማንደር አበራ ከወልድያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ አይሰማ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ ነው የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመው ሲሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀውል።

በከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አበራ መኖሪያ ቤት ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት የደረሰውን ጉዳት እስካሁን በውል ማወቅ አልተቻለም።

በተመሣሣይ በትናንትናው እለት የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈፅሟል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ በሆነው እንስፔክተር አያሌው መኖሪያ ቤት ላይ ነው ትናንት ጥር 01/2017 ዓ/ም የቦምብ ጥቃት የተፈፀመው።

በከተማዋ ልዩ ስሙ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ የቦምብ ጥቃት የተፈፀመበት እንስፔክተር አያሌው፡ በግል ጉዳይ ተካሰው ፍትሕ ለማገኘት ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎችን "የፋኖ ደጋፊ ናቸው ብየ ለከፋ ነገር ሳልዳርጋችሁ ገንዘብ ክፈሉኝ" በሚል በማስፈራራት ከ50ሺ ብር ጀምሮ እስከ 100 ሺ ብር እንደሚቀበል ጠቁመዋል።

እንስፔክተር አያሌው በመኖሪያ ቤቱ ላይ የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመው ሁለት ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው ጥቃት ቀላል ጉዳት ሲያደርስ፡ የከተማዋ ፖሊሶች ተሰባስበው በመጀመሪያው ጥቃት የደረሰውን ጉዳት በመመልከት ላይ ሳሉ ሁለተኛው ጥቃት እንደተፀመባቸው ነው ምንጮቻችን የገለፁት።

በዚህም ከአምስት በላይ የፖሊስ አባላት ቆስለው ወደ ሕክምና ጣቢያ መወሰዳቸው ተነግሯል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አራጌ ይመር በወልድያ ከተማ ጎንደር በር አከባቢ ልዩ ቦታው ከቀበሌ 06 ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ ከሳምንት በፊት የቦምብ ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።

ተጨማሪ👉
https://www.youtube.com/watch?v=5OO4j7d06bE&t=106s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Jan, 15:11


የቪዲዮ ስርጭት ከወሎ ሰንሰለታማ ተራሮች!

የአማራ ፋኖ በወሎ ወታደራዊ አመራሮች ከመረብ ሚዲያ ጋር!

ሙሉ ቪዲዮውን ይከታተሉ!👉
https://youtu.be/ZykkkLCp2_o?si=r_DuyIxH-JIr4Zp5

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Jan, 08:00


የገና በዓልን በጦር ግምባር/ ቀጥታ በቪዲዮ!


የወሎው ኮሎኔል ፈንታው ከመረብ ሚዲያ ጋር!

https://youtu.be/ZykkkLCp2_o?si=r_DuyIxH-JIr4Zp5

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Jan, 07:00


የልደት በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ለመላው የአማራ ሕዝብ እና ስለ አማራ ሕዝብ ነፃ መውጣት ስትሉ በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ለምትገኙ የትግል ጓዶቻችን እንኳን ለጌታ እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በድልና በፅናት አደረሳችሁ!

የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበትን የሕልውና አደጋ ለመመከት፡ ለዘመናት በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ሲጨፈጭፉትና ሲያስጨፈጭፉት፣ ከቤት ንብረቱ ሲያፈናቅሉት፣ በተጠና ሁኔታ ወግና ባሕሉን ሲበርዙበት፣ ከኢኮኖሚውና ከሌሎች ማህበራዊ ግልጋሎት በአሻጥር ሲያገሉት የነበሩትን ጠላቶቹን አንገታቸውን እየሰበረ፡ የነፃነት ድልን እያበሰረ ይገኛል።

የአማራ ሕዝብ ዛሬ ላይ በክንዱ የሞቱ ደብዳቤን ለመቅደድ፣ በጫንቃው ላይ የወደቀበትን የሞት ቀንበር ለመስበርና በምትኩ የነፃነት ኒሻንን በአንገቱ ላይ ለማጥለቅ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ነው።

በሀገር ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብ በአሁን ሰዓት አቅምና ጉልበት ያለው መሣሪያውን ይዞ ጣቶቹን ከክላሹ ቃታ ሳይለይ በምሽግ ውስጥ እንዳደፈጠ ነው። ወደ ዱር ለመውጣት አቅም ያጠረውም በቤት ውስጥ ሆኖ በዱር ላሉ ልጆቹ ድልን ያቀዳጅ ዘንድ ፈጣሪውን እየተማፀነ ነው።

ከሀገር ውጭ ያለው የአማራ ሕዝብና ሌሎች የትግሉ ደጋፊዎችም ትግሉን በፋይናንስ እና በሌሎች ሀሳብና ምክሮች በመደገፍ ከምሽግ ካለው ታጋይ ባልተናነሰ መልኩ የበኩላቸውን እያደረጉ የሚገኙበት ወቅት ነው።

በዚህ ትግል ሒደት ውስጥ የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበትን የሕልውና አደጋ በውል ተገንዝቦ እንደ ሕዝብ ወጥቶ መታገሉ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም ነገር ግን በትግል ሒደቱ መራር የሆነ ሀዘንን፣ መታረዝና መጠማትን ሊያስተናግድ ግድ ይላል። ያለ ሞት ነፃነት የለምና መስዋዕትነትም የትግሉ አንድ አካል ነው። በዚህ ትግል ሒደት መጨረሻ ላይ ግን ያ ለዘመናት በሕዝባችን ጫንቃ ላይ ተጭኖ የነበረው የሞትና የጭቆና ቀምበር ይሰበራል። ሕዝባችንም የነፃነት አየር ይተነፍሳል።

የመጨረሻውን ሒደት ለማቅረብና የትግል ሂደቱን ለማፍጠን የሁላችንንም ርብርብ ይጠይቃልና እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን በሕብረት እጅ ለእጅ ተያይዘን ልንታገል ግድ የለናል።

እውነተኛ ትግል ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። እውነተኛ ትግል ከእብሪት መላቀቅን ይጠይቃል።እውነተኛ ትግል መጀመሪያ እራስን ማሸነፍን፣ መንደሬነትንና ጎጠኝነትን መስበርን ይጠይቃል። ይሄንን አሟልተን ልክ እንደ ንስር ታድሰን በከፍታው ላይ ለመብረር የሁላችንም የዛሬ አቋም ይሁን።

መልካም በዓል!

የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀቤ!
ታህሳስ 29.2017 ዓ.ም
ድል ለአማራ ሕዝብ!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Jan, 05:49


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ነፃነቱን ለማስከበር በትግል ላይ ለሚገኘው የአማራ ሕዝብና ለአማራ ፋኖ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

ገዢው የብልፅግና ቡድን በአማራ ክልል በአራቱም ክፍላተ ሀገራት የድሮን አሰሳ እያደረገ ይገኛል። ይህንን መረጃ ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ ሕዝባችንን ከእልቂት እንታደግ።

መልካም በዓል!

ከመረብ ሚዲያ ማኔጅመንት ቡድን!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

07 Jan, 04:40


በአማራ ፋኖ በጎጃም ወታደራዊ መምሪያ የልደት በዓልን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 20:35


ክርስቶስ የሰውን ልጆች ሁሉ ለማዳን እደተወለደ ለእኛም ለአማራዎች የፋኖ ትግል ተወልዶልናል !!

ለተከበርከው ታላቁ የአማራ ህዝብ ፣በውጪም በሀገር ቤትም ያላችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፅናት አደረሳችሁ አደረሰን ።

እንደሚታወቀው አሁን ያለንበት ወቅት የአማራ ህዝብ በፋሽስት አምባገነኖች የጥፋት ጦርነት ታውጆበት ፤በዘመኑ አሉ በተባሉ መሳሪያዎች ከምድር እንዲጠፋ በብዙ ተዋናዮች ጅምላ ፍጅት እየተፈፀመበት ይገኛል። ሆኖም እደሚታወቀው ቆራጥ የአማራ ልጆች እንደህዝብ የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ክርስቶስ ራሱ በፈጠራት አለም ውስጥ ለጠፋው ለሰው ልጅ በከብቶች በረት እደተወለደ ሁሉ ፤የአማራ ህዝብ በፈጠራት ሀገር ውስጥ ተሳዳጅና ባይተዋር በመሆኑ ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን የቁርጥ ቀን ልጆች ጫካ ከገቡ ሁለት አመታት ተቆጥረዋል ።

በታሪክ እንዳየነው ክርስቶስ ከውልደት እስከ ስቅለቱ ባሳለፋቸው ዘመናት ውስጥ የተበላሸ ስርዓትን ለመለወጥ ምን ያህል ፈታኝ ዋጋ እደሚያስከፍል ከቅዱስ መፀሀፍ አንብበናል ።

እኛም ይህን በዓል ስናከብር አባቶቻችን የሰጡንን ጠቃሚ እሴቶችን በመጠበቅ ጎጂ የሆኑ የኛን እሴቶች ሊያጠፉ የሚችሉ ባዕድ የሆኑ ልማዶችን በማስወገድ የራሳችንን እምነት (faith) ማስቀጠልና መጠበቅ አማራዊ የትግል ግዴታችን ነው ።

ለዚህም በዓሉን ስናከብር ሊተገበሩ የሚገባቸውን መመሪያዎች እደሚከተለው እገልፃለን።

፩.በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ህዝብና በዓሉን ሊረብሹ የሚችሉ የደስታ ተኩሶች ፣ ከልክ ያለፉ የአልኮል መጠቀምና ማወክ ክልክል ናቸው።

፪.በቅርብ ልምድ የመጡ የገና ዛፍ ፣የገና አባት የሚሉ ከአማራ ሕዝብ ማህበራዊ እሴት ዝምድና የሌላቸውን ባዕድ ባህሎች ከማስፋፋት መቆጠብ።

፫.ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሁሉ ያላችሁ የጎበዝ አለቆች ከህዝባችን ጋር ተባብራችሁ የአካባቢያችሁን ፀጥታውን እድታስከብሩ !!

፬.በዓሉን ስናከብር በየአካባቢው የሚገኙ አቅመደካሞችን በመጠየቅና በመረዳዳት እድናሳልፍ!!

፭.ሁሉም ክፍለጦሮች በማዕከላት ያሉትን የተማረኩ የጠላት ሰራዊት አባላት አቅም በፈቀደ መጠን በዓሉን ደስተኛ ሆነው በጋራ እንዲያሳልፉ  ያሳስባል !!

፮. እንዲሁም በህልውና ትግሉ ውስጥ ሲታገሉ የቆሰሉና የተሰው ፋኖ አባሎችና ቤተሰቦችን በመጠየቅና በማፅናናት እንድታሳልፉ አማራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መልዕክቱን ያስተላልፋል!!

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !!

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ !!

ታህሳስ 2017 ዓ.ም

ሸዋ ፣አማራ ፣ኢትዮጵያ

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 20:33


ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የገና በዓልን አስመልክቶ የተሰጠ የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ!

እንኳንስ የክርስቶስ ኢየሱስ የልደት በዓል ዋዜማ ላይ ሁነን ይቅርና በዘወትር ቀናትም ቢሆን እንዴት ዋላችሁና ከረማችሁ ከአፋችን የማይለይ ብቻ ሳንሆን እግዚአብሄር ይመስገን… ያውም በነገር ሁሉ ብለን ባለቤታችንን እንደምናውቅ አስረግጠን የምንናገር ፍጡር ነን፡፡ ትልቁን ነገር ይዘናል… አለምም በዚህ ያውቀና፡፡

በመሆኑም እንናተ የአማራን ህዝብ ከብሄር ተኮር ጥቃት ለመታደግ በዱር በገደል የምትንከራተቱ፣ በማንነታችሁ ብቻ የእለት ተእለት ሰቆቃና እንግልት የምትቀበሉ፤   ሀብትና ንብረታችሁ ተዘርፉ በየ-ስደት ጣቢያዎች ለምጽዋት ኑሮ የተዳረጋችሁ፤ ግፍና በደል ይብቃ በሚል ሲቃ ስላሰማችሁ በየ እስር ቤት ታጉራችሁ ቁም ስቅል የምታዩ፤ ብሎም ከዛሬ ነገ ምን ይመጣብን ይሆን በሚል በጭንቀትና ስጋት የቀን ጨለማ የዋጣችሁ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ፡፡ የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን ስናስብ በልደቱ ምክንያት ብዙ ሀይማኖታዊና ማህበረሰባዊ ጥያቄዎች እንደሚኖሩ በማስታወስ ነው፡፡ በልደቱ እርቅ፣ ሰላም፣ ቂም-የለሽነትና የመዳን ተስፋ ይዘን ማክበር ይኖርብናል፡፡ በዚህም ለእኛ የትግል ጉዞ ብዙ አስተምሮት ያለዉና መካሪና አቅጣጫ አመላካች አንድምታ ያለው በአል አድርግን እንወስደዋለን፡፡ ክርስቶስ እኛን ያድን ዘንድ ወደ ምድር እንደመጣ ሁሉ እኛም የአማራን ህዝብ ለማዳን ወደ ዱር ገብተናል፡፡

በጌታ የትውልድ ጊዜ የእስራኤል አካል በነበሩ የገሊላና የይሁዳ ክፍለ ሀገራት መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ተጸንሶ በይሁዳ በቤተ-ልሄም ግርግም ሲወለድ በሁለቱ አዉራጃዎች መካከል የነበረዉን አለመግባባት ከንቱ አድርጎ ሽሮታል፡፡
በሌላ በኩል የክርስቶስ ልደት ሰው ከአምላኩ እንደታረቀ የተበሰረበት ብቻ ሳይሆን ከጠላቱ ከዲያብሎስ ለዘላለም እንደተለየ ማሳያ እለትም ነበር፡፡ በአንድ በኩል በሰውና በአምላክ መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ እንደሚፈርስ የተረጋገጠበት የመጀመሪያው የተግባር ምእራፍ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከሰይጣንና ሰራዊቱ ጋር ለዘላለም የሰው ልጅ እንደማይገናኝ የልዩነት ግድግዳ የጸናበት ጊዜም ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሰይጣን ወደ ጥልቁ ሊጣል እንደቀረበ አንዱ የተግባር ማረጋገጫ እለት ነበር፡፡ ለዚህም እኮ ነው ዲያብሎስ በሄሮድስ ልቦና አድሮ ያን ያህል ንጹሀን ህጻናትን እንዲፈጅ ያስደረገው፡፡ ልክ ዛሬ በአብይ አህመድ አድሮ አማራን እንደሚያስጨፈጭፍ ማለት ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል፡፡ ዛሬ ያለንበት ነባራዊ ሀቅ አንድነታችንን እያጠናከርን ብሎም ለዘላለም እንዳይናጋ መሰረት እየጣልን ብቻ ሳይሆን ያለያየንን የፀብ ግድግዳና ግድግዳ መሳይ ነገር እየናድን ጎርባጣውን ገደላ-ገደል ደልዳላ እያደረግን ምቹ የሩር-መለጊያ ሜዳ እየፈጠርን ነው፡፡ በክርስቶስ ልደት በጭራሽ ከሰይጣን ጋር እርቅ እንደሌለ ሁሉ እኛም ከሰው ዘር-አጥፊ ጋር  የሚያገናኘንና የሚያስማማን አጀንዳ እንደሌለ አስረግጠን በድጋሜ እንናገራለን፡፡

ክርስቶስ በሰውና በዲያብሎስ መካከል ያቆመው ግድግዳ በአማራ ህዝብና በአብይ መራሹ መንግስት መካከልም በጽኑ ቁሟል፡፡ ሰይጣን የሰውን ልጅ ሊያጠፋ እንደመጣ ሁሉ አብይ አህመድ አማራን ለማጥፋት ተነስቷል፡፡ ክርስቶስ የሳጥናኤልን መንግስት እንዳፈራረሰ ሁሉ ፋኖም የአብይን መንግስት ያፈራርሰዋል፡፡ ሰላም የሚገኘውም ከሰይጣን በመታረቅ ሳይሆን የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ በጽናት ከፍሎ በማሸነፍ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶስ እስከ መሰቀል መስዋእትነትን የከፈለው፡፡

በሌላ በኩል የገና በአል ለእኛ ትግል የሚያስተምረው ሌላዉ ነገር የወንድማማች ቂምን መሻር ነው፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው እኛን ስለበደለን ይቅርታ ሊጠይቅ ሳይሆን እኛ በዳዮቹን ሊምር ነው ያውም እራሱን አሳልፎ እስከ ሞት ድረስ በመስጠት፡፡ የእኛም ስርአት ይህን የተከተለ መሆን አለበት፡፡

ትናንት ከፋፋዮች ሲለያዩን በገባነው ግጭት የተፈጠረ ብዙ ነገር ይኖራል፡፡ ነገም ከእርቅ በኋላ ያንን በደል ሽረን… እንዳልነበር ቆጥረን በአዲስ መንፈስና ወኔ ወደፊት ልንጓዝ እንጂ እንደ-ከብት የተዋጠን እየመለስን ልናመነዥክ አይደለም፡፡ መከባበር፣ መዋደድ፣ በእኩል መተያየትና ይቅር መባባል በውስጣችን መንገስ ይኖርበታል፡፡ በገና የአጨዋወት ስርአታችንም እኮ “በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ” ሲል እኩል ነን፣ አንድ ነን፣ ይቅር እንባባላለን ብሎም የፍቅር ቀን ነው ብሎ ሲያጠይቅ ነው፡፡ የእኛ የትግል ዘመንም ይሄው ነው፡፡

ህዝባችን ምን ያህል እንደተዋረደ፣ እንደተናቀ፣ እንደተጎሳቀለና ተስፋ የሌለው ፍጡሩ እስኪመስል እንደተገፋ ታውቁታላችሁ፡፡ ነገር ግን ምንም ያልተጠበቀችውንና እንደ ተናቀች የተቆጠረችውን የናዝሬትን ከተማ ኢየሱስ እንዳከበራትና ብዙ ብዙም እንዳደረገላት እኛም በሙሉ ልብ ይህንን የጽልመት ጊዜ እንሻገረዋለን፡፡ በብርሀንም እንተከዋለን፡፡ የግፉ መሙላት፣ የዋይታ መብዛትና የበዳዮች ትእቢት ከፍ ከፍ ማለት ጠላቶቻችን የመውደቅ አፋፍ ላይ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ነው፡፡ ሊነጋ ሲል ይጨልማልና!

    "ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል

  ታህሳስ 28/2017 ዓ/ም
   ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 20:29


ከአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 20:25


ከአማራ ፋኖ በጎንደር የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 20:18


እንኳን ለልደት (የገና) በዓል በጽናት አደረሳችሁ!

ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ መግለጫ!

በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በጽናት አደረሳችሁ! አደረሰን!

ጌታቸን ጽንሰቱ ናዝሬት ውልደቱ በዳዊት ከተማ ቤተልሔም እንደሆነ ሁሉ የእኛም ትግል መነሻ ከየአካባቢው መገፋት፣ መገደል፣ በቃኝ ብሎ የተነሳ አደረጃጀት ቢሆንም መዳረሻች ከአባታቶቻችን ከምኒሊክ ከተማ ስለመሆኑ የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል አንጠራጥርም፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ በሀጢያት የወደቅነውን ወደ ቀደመ ማዕረጋቸን ሊመልሰን እንደመጣ ሁሉ፤ አማራም መዋቅራዊ ጥቃት ተከፍቶበት ባለፉት አስርተ አመታት ሲፈናቀል፣ ሲገደል ማህበራዊ እረፍት ተነስቶ እንዲወድቅ እንዲጠፋ ሲሰራበት፣ ፋኖም አማራን ወደ ቀደመ ክብሩና ማዕረጉ ለመመለስ እየታገለና በድል ጎዳና በሚገኝበት ወቅት እንኳን በጽናት አደረሳችሁ መልዕክት ሲያስተላልፍ ለሰፊው አማራ ሕዝብ ትግሉን ከዳር ለማድረስ ቃል እንደ መግባት ነው፡፡

በዓሉን ስናከብር እየሱስ ክርስቶስ መወለድንና ታሪኩን እያሰብን ለሰው ልጅ ሁሉ ዝቅ ብሎ መከበርን እንዳስተማረን ሁሉ እኛም የፋኖ ሰራዊቶች ለሕዝባችን አንድ ነፍሳችን ለመስጠት እስከ ወጣን ድረስ ሕዝባችን በአከበረና በሚመጥን መልኩ እንድንቅሳቀስ ማሳወቅ እንወዳለን።

በቀጣይ አመት የአማራ ሕዝብን የህልውና አደጋ ቀልበሰን ህልው አደርገን በደስታና በፍቅር እንድናከብረው ሁላችንም ለዛ እንድንተጋ እንደ አማራ ፋኖ በወሎ ጥሪ እናቀርባለን።

ዋርካው ምሬ ወዳጆ
የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 18:39


የመንግስት ወታደሮች በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ አንድ ወጣትን በስለት ቆራርጠው መግደላቸው ተሰማ!

ወታደሮቹ ወጣቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉት የአልኮል መጠጫ ብር ካላመጣህ በሚል ምክኒያት እንደሆነም የሟቹ ቤተሰቦች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ሙጃ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ የነበረ አንድ ወጣት ታህሳስ 22/2017 ዓ/ም ምሽት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ አስከሬኑ ከከተማዋ ዳርጃ ባለ ስፍራ ተጥሎ ተገኝቷል።

ሟቹ ወጣት መንገሻ አያሌው ባለትዳርና የአንድ ሴት እና የአንድ ወንድ ልጆች አባት ሲሆን በወረዳው ባሕልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ውስጥ በተወዛዋዥነት ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር መረብ ሚዲያ የሟቹን ቤተሰቦች በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

ታህሳስ 22/2017 ዓ/ም ምሽት በአገዛዙ ወታደሮች ተይዞ በስለት ተቆራርጦ ነው የተገደለው ተብሏል።

ወታደሮቹ ድርጊቱን በፈፀሙበት ዕለተ ማክሰኞ አመሻሹን ጀምረው በመንገድ ላይ ያገኙትን ሰው እያስቆሙ ጥሬ ገንዘብ፡ የአንገት ሀብል እና የጣት ወርቅ እንዲሁም የእጅ ስልክ ሲዘርፉ ነበር የተባለ ሲሆን፡ በተጨማሪም በየሸቀጣሸቀጥ መደብሮች እየዞሩ "የመጠጫ ብር አምጡ" በሚል ሲቀበሉ ማምሸታቸውን ነው የከተማዋ ነዋሪዎች እና የሟች መንገሻ ቤተሰቦች ለጣቢያችን የገለፁት።

መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦች "ወታደሮቹ ምሽት ላይ በየጎዳናው ያገኙትን ሰው እየዘረፉ ባሉበት ሟች ወጣት መንገሻ አያሌው ከስራ ውሎ ሲመለስ መንገድ ላይ ሲያገኙት ብር እንዲሰጣቸው ጠየቁት፡ እሱም ምንም ብር እንደሌለው ሲነግራቸው፡ እንዴት የለኝም ትላለህ በሚል ከከተማዋ ውጭ በመውሰድ አንገቱ ላይ እና ደረቱ ላይ በተደጋጋሚ በስለት በመውጋት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ጥለውታል" ብለዋል።

"የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ወጣቱን መንገድ ላይ አስቁመው የአልኮል መጠጫ ብር እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት፡ ወጣቱም ከኪሱ ምንም ገንዘብ እንደሌለው ከነገራቸው በኋላ በክላሽ ሰደፍ እየደበደቡ ወደ ከተማዋ ዳርቻ ወሰዱት" ሲሉ በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ የገለፁት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው ሌሎች የአይን እማኞች፡ በበነገታው ማርፈጃውን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ አስከሬኑ ወድቆ አገኘነው" በሚል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የሟቹ ቤተሰቦች የልጃቸውን አስከሬን ስርዓተ ቀብር ከፈፀሙ በኋላ "ይሄንን ነገር ለሚዲያ እንዳታወጡ በሚል" ከወረዳው ካድሬዎች ማስጠንቀቂያ  እንደተሰጣቸው ጨምረው ገልፀዋል።

የሟቹ ቤተሰቦች ከመረብ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ👉

https://youtu.be/YaGw_3imFyU?si=v9pPVkPH_U9pDVd5

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 18:10


ልብ ሰባሪ ድርጊት!

መከላከያ ሰራዊቱ ተስለት ቆራርጠው ገደሉት!

በሰሜን ወሎ ዞን አሰቃቂ ግፍ ተፈፀመ!

https://youtu.be/YaGw_3imFyU?si=v9pPVkPH_U9pDVd5

Mereb Media መረብ ሚዲያ

06 Jan, 17:52


ከአማራ ፋኖ በወሎ ከላስታ አሳምነው ኮር የልደት በዓልን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Jan, 08:50


እንደም አረፈዳችሁ!

መረብ ሚዲያ ከተከዜ በርሃ ዙሪያ!

ስለዚች ቅምጥል ጀግና፣ ስለዚች ምሽግ ደርማሽ የክላሽ ጠበብት ጀብዱ አንድ ዝግጅት ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል።በቅርቡ ይጠብቁን!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 20:28


https://www.youtube.com/watch?v=Xs_Mu6U1USI&t=108s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 16:25


ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በደባይ ጥላትገን ወረዳ በተደረገ አውደ ውጊያ ከ100 በላይ የመንግስት ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ!

በወረዳው እየተካሄደ የሚገኘው ውጊያ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፡ የፋኖን ክንድ መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል ማሕበረሰቡን በከባድ መሣሪያ እየደበደበ ነው ተብሏል።

ከታህሳስ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላትገን ወረዳ በናብራ ሚካኤል ቀበሌ እና በአከባቢው በተደረገ ትንቅንቅ የሚሊሻ እና የአድማ ብተና አባላትን ጨምሮ ከ100 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን የአማራ ፋኖ በጎጃም የ8ኛ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ይበልጣል ጌጤ ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

ከታህሳስ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ በጮቄ ተራራ ዙሪያ በሚገኙ ናብራ ሚካኤል፣ ደብረ እየሱስ እና እነሞጨር በተባሉ አከባቢዎች ላይ በተደረገ ከባድ ትንቅንቅ የጎጃም ፍኖ ታልቅ ድል የተቀዳጀ ሲሆን፡ በአንፃሩ ደግሞ የአገዛዙ ኃይል አንገት አስደፊ ሽንፈት እንዳጋጠመው ለማወቅ ተችሏል።

በቀጠናው ላለፉት ቀናት በተደረገ ውጊያ ከተደመመሱ 100 በላይ ወታደሮች በተጨማሪ በቁጥር 20 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣1 ሺ 600 መቶ የክላሽ ተተኳሽ፣ 12 ኤፍ ዋን ቦንብ፣ አንድ ሳጥን ሙሉ የድሽቃ ተተኳሽ እና አንድ ሙሉ የብሬን ሸንሸን በፋኖ እጅ መግባቱን የ8ኛ ክ/ጦር ቃል አቀባዩ ፋኖ ይበልጣል ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

በቀጠናው ከከባባድ መሣሪያዎች ጀምሮ ሌሎች ዘመናዊ መሣሪያዎችን ይዞ ገብቶ የነበረው የአገዛዙ ኃይል ከፋኖ የተሰነዘረበትን አፀፋዊ ጥቃት መቋቋም ባለመቻሉ፣ ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ በደብረ እየሱስ አቆራርጦ ወደ ቁይ መፈርጠጡ ተነግሯል።

የአገዛዙ ኃይል ሲሸሽ በመንገድ ባገኛቸውን ንፁኋኖች ላይ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን፡ በዚህም በአዋበል ወረዳ እነሞጨር ቀበሌ ልዩ ስሙ ደጃ ወንበር አከባቢ ድረስ ሞላ የተባሉ አንድ አርሶ አደርን በስለት ቆራርጦ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደላቸው ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

በተመሣሣይ ይህ ፀረ አማራ ኃይል የእውር ድንብሩን ሲወረውረው በነበረው ከባድ መሣሪያ በናብራ ቀበሌ አንድ የሰባት ዓመት ህፃንን ጨምሮ አዝመራ በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ተገድለዋል ነው የተባለው።

በተጨማሪም በርካታ መኖሪያ ቤቶችን እና ታጭደው ተከምረው የነበሩ የስንዴ ነዶዎች በአገዛዙ ኃይሎች ከባድ መሣሪያ መውደማቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

ትንቅንቁ ዛሬ ታህሳስ 26/2017 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በናብራ ሚካኤል ቀበሌ የቀጠለ ሲሆን፡ በዚህም የፋኖን ክንድ መቋቋም ያልቻለው የብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ ወታደር መድፋ እና ሞርተር ወደ መንደሮች ሲወረውር መዋሉ ታውቋል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ይበልጣል ጌጤ ከመረብ ሚዲያ ጋር ያደረገውን ቆይታ ተከታተሉ👉

https://youtu.be/lAbWYQu6yyw?si=rSAYkW2ZBgQ_5tRy

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 16:24


መረጃ!

የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ የጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር ዛሬ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም ዋንዛዬ አካባቢ የአገዛዙን ወራሪ ሠራዊት ሲረፈርፉት ውለዋል።

ከወረታ፣ ከሐሙሲትና ከባ/ዳር በሦስት አቅጣጫ የጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር አርበኞችን ለማፈን የተንቀሳቀሰን ወራሪ ኃይል በተለምዶ ወላሌ ወይም ጉማራ መገንጠያ ላይ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9:00 የዘለቀ ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲደረግ ውሏል።

በባ/ዳር እና በወረታ መካከል ቀኑን ሙሉ በተደረገው በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ በርካታ የወራሪ ኃይሉ ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

በዚህ ኦፕሬሽን ክፉኛ የተመታው አሸባሪው ሠራዊት የደረሰበትን ቁሳዊ፣ ሰብዓዊና ሥነ ልቡናዊ ሽንፈት ለማወራረድ ጉማራ ከተማ ላይ ንጹሐንን ረሽኖ ወደመጣበት ፈርጥጦ ተመልሷል።

       ኅልውናችን  በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ


የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
         አርበኛ ባዬ ቀናዉ
          ታህሳስ 26/2017 ዓ/ም

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

ቴሌግራም👉 https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 14:00


ሰበር ዜና ከጎጃም!

ከ100 በላይ ወታደር ጮቄ ተራራ ላይ ወድቋል!

ትንቅንቁ ቀጥሏል/ ከባድ መሣሪያ ተማርኳል!

https://youtu.be/lAbWYQu6yyw?si=rSAYkW2ZBgQ_5tRy

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 12:22


በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ፋኖን መቀላቀላቸው ተሰማ!

2 ስናይፐር፣ 11-ጥቁር ክላሽንኮቭ እና 4 ዘመናዊ ምሽግ መደርመሻ ኢነርጋ የያዙ የአየር ወለድ ኮማንዶ አባላት ግፍን ተቃውመው ከነበሩበት አሃድ በመውጣት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን መቀላቀላቸውን መረብ ሚዲያ ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

ቴሌግራም👉 https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 11:40


የድል ዜና

ሳምንት ባስቆጠረው የሸዋ ተጋድሎ የተመታው የአገዛዙ ሠራዊት አስከሬኑን በሁለት ተሳቢ ጭኖ መውጣቱ ተገለፀ።

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ራሳ ግንባር ባለፉት ሳምንታት በተደረገ ከፍተኛ የአውደ ውጊያ ውሎ ክፉኛ የተመታው የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሠራዊት በሁለት ተሳቢ ሙትና ቁስለኛ አስከሬኑን  ይዞ ወደ ሸዋሮቢት ከተማ ገብቷል።

ከታሕሳስ 17 ጀምሮ ከተለያየ አቅጣጫ ያለውን ኃይል አሰባስቦ ቀወት ወረዳ ራሳ ለመግባት በማፉድና ሳላይሽ ተራራ ላይ መሽጎ ወደ ራሳ ለመግባት ሙከራ ያደረገውን ኃይል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ራምቦ ክፍለጦር እና አባት አርበኛ ሠራዊት ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ምሽጉን እስኪለቅ ድረስ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል።

ምሽጉን የለቀቀው የጠላት ሠራዊት መግባት እንደ መውጣት የሚል መስሎት ፤በወታደራዊ ጠበብቶች ውሳኔ የተለቀቀለትን ቦታ አገኘሁ ብሎ ዘው ብሎ ከገባ በኋላ ለ9 ቀናት በከበባ ሲቀጠቀጥ ውሀና ተተኳሽ የሚያቀርበልት ደጀን አጥቶ ከራሳ አርበኞች፣ከራምቦ ክፍለጦር፣ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፋለጦርና በፋኖ ለማ አስማማው የሚመራ የእዙ ተወርዋሪ ሻለቃ  የተረፈው በረሀብና በውሃ ጥም አልቋል።

ይህንን የማያውቀው ቤት ገብቶ መውጫ የጠፋበትን የአገዛዙ ልቅምቃሚ ሠራዊት ለማትረፍ ከኬሚሴ እና ከደብረብረሃን ከተማ ተጨማሪ ሀይል ቢያሰማራም ከደብረብረሃን የተነሳው የጠላት ሠራዊት ጣርማበርና ቀይት ላይ በአስቻለው ደሴ ክፍለ ጦርና በአፄ ዘረያዕቆብ ክፋለጦ(ጣይቱ ብርጌድ)  በደፈጣና በመደበኛ ውጊያ ሲቀጠቀጥ አምሽቷል።

በሌላ በኩል ከኬሚሴ የተነሳውን የጠላት ሀይል የአስቴጎማ ክፍለጦር በወሰደው የደፈጣ እርምጃ በርካታ የጠላት ሀይል እርምጃ የተወሰደበተ ሲሆን  ከደፈጣ የተረፈው አንድ የአገዛዙ ብርጌድ ሸዋሮቢት ከሚገኘው የጠላት ካምፕ ጋር ተሰባጥሮ ሳምንቱን በከበባ ሲቀጠቀጥ የነበረውን ሙትና ቁስለኛ ሰራዊት በዛሬው እለት በሁለት ተሳቢ ለቃቅሞ አውጥቷል።

በጠላት ከፍተኛ ድል የተወሰደበት፤ ከሳምንት በላይ የዘለቀው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የራሳው ግንባር ተጋድሎ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን በጠላት ሀይል ላይ ከፍተኛ የድል የበላይነት እየተወሰደ በርካታና የጠላት ኃይል በምርኮና እጅ በመስጠት ላይ ሲሆን ስርዓቱን ከድተው የሚቀላቀሉ የአገዛዙ ሠራዊት አባላትም ይገኙበታል።

መረጃው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

ቴሌግራም👉 https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 09:13


የቪዲዮ ስርጭት ከወሎ!

አብይ አህመድና ጀሌዎቹ ለፍርድ ይቅረቡ!

ሕዝቡ ምን ይላል?

https://www.youtube.com/watch?v=Xs_Mu6U1USI

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Jan, 08:31


የጮጮሆ አናብስቶች!

እንደምን አረፈዳችሁ!

የመረብ ሚዲያ የፌስቡክ ገፅን ተቀላቅላችኋል ወይ?

https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Jan, 19:48


በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ራሳ ቀጠና ካለፉት ሰባት ቀናት ጀምሮ እየተደረገ ባለው ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ!

በውጊያው ከተገደሉ በተጨማሪ በፋኖ ከበባ ውስጥ ገብተው መንቀሳቀሻ በማጣታቸው በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በረሀብ ሕይወታቸው ማለፉም ነው የተነገረው።

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ራሳ ቀጠና ልዩ ስሙ አሻል/መዲና/ ተብሎ በሚጠራው አከባቢው ካለፉት ሰባት ቀናት ጀምሮ እየተደረገ በሚገኘው ትንቅንቅ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፀረ አማራው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በቀጠናው ካለፉት ሰባት ቀናት ጀምሮ በዘለቀውና አሁንም በቀጠለው ተጋድሎ በፋኖ አፈሙዝ ሙትና ቁስለኛ ከተደረጉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጨማሪ የአከባቢው ዙሪያ ገባ በፋኖ ከበባ ውስጥ በመግባቱ በርካታ ወታደሮች በረሃብ ሕይወታቸው አልፏል ተብሏል።

የራሳ ቀጠና ዙሪያ ገባው በፋኖ ከበባ ውስጥ በመግባቱ የአገዛዙ ወታደሮች ከየትኛውም አቅጣጫ ተጨማሪ ኃይል እና ትጥቅና ስንቅ ማስገባት አልቻሉም የተባለ ሲሆን፡ በዚህም በርካታ ወታደሮች በረሃብ ሕይወታቸው ማለፉን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ም/ኃላፊ ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

የአገዛዙ ወታደሮች በተፈፀመባቸው ከበባ ምክኒያት ባጋጠማቸው ረሀብ ሕይወታቸው ካለፈውና በየጊዜው በሚደርስባቸው ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ ወታደሮች በተጨማሪ በርካቶች ተሰላችተው ከነሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ልፋኖ ለፋኖ እየሰጡ ይገኛሉ ተብሏል።

በተመሣሣይ በዛሬው እለት ከደብረ ሲና በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ሾላ ሜዳ በተባለ አከባቢ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ የአገዛዙ ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰበት የዕዙ ምክትል ቃል አቀባይ ፋኖ ስንታየሁ ደመቀ ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

የገዢው ቡድን  ኃይል የደረሰበትን መራር ሽንፈት ለማካካስ በሚመስል መልኩ ለልዩ ዞኑ አዋሳኝ በሆኑ አከባቢዎች ላይ መድፍ በማጥመድ የሾላ ሜዳ አከባቢን እና ሌሎች በደብረሲና ዙሪያ የሚገኙ የገጠር ቀበሌዎችን ሲደበድብ ማምሸቱ ታውቋል።

የፋኖን ክንድ መቋቋም ያልቻለው ፀረ አማራው የገዢው ቡድን ጦር በሚወረውረው ከባድ መሣሪያ አርሶ አደሮችን እየገደለ እንዲሁም ሰብል እና መኖሪያ ቤቶችን እያወደመ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሕዝብ ግንኙንት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ፋኖ ስንታየሁ ደመቀ ከመረብ ሚዲያ ጋር ያደረገውን ቆይታ ይከታተሉ👉

https://www.youtube.com/watch?v=IMS8PaydR_s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Jan, 19:09


የፋኖ አባሏ የሚሊሻ አባል በሆነው ወላጅ አባቷ ላይ እርምጃ መውሰዷ ተሰማ!

አማራ ፋኖ በጎጃም የ9ኛ(ሳሙኤል አወቀ) ክፍለ ጦር አባል የሆነችው ፋኖ ትግስት ውዱ ዛሬ ታህሳስ 25/2017 ዓ/ም በእነብሴ ሳር ምድር በተደረገ ውጊያ ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ተሰልፎ የነበረው የሚሊሻ አባል የሆነው ወላጅ አባቷ አቶ ውዱን መግደሏን መረብ ሚዲያ  ከአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ለመመልከት ችሏል።

ፋኖ ትዕግስት ወላጅ አባቷ ከሚሊሻ አባልነቱ እንዲለቅ እና ፀረ አማራ የሆነውን የአገዛዝ ስርዓት ከማገልገል እንዲቆጠብ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አሳስባው ነበር የተባለ ሲሆን ነገር ግን ከዚህ ድርጊቱ ሊቆጠብ ባለመቻሉ ዛሬ በተደረገ ውጊያ በገዛ ልጁ መገደሉ ነው ቃል አቀባዩ የገለፀው።

ፋኖ ትዕግስት በጦር ግምባር ከጠላት ጋር ተሰልፎ ያገኘችው ወላጅ አባቷን ከገደለች በኋላ የማረከችውን ክላሽንኮፍ መሣሪያ ለክፍለ ጦሯ ማስረከቧንም መረብ ሚዲያ የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ የሆነው ፋኖ ማርሸት ካሰፈረው ፅሁፍ ለማረጋገጥ ችሏል።

የመረብ ሚዲያ ፌስቡክ ገፅን ይቀላቀሉ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

ቴሌግራም👉 https://t.me/MerebMedia24

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Jan, 17:45


ሰበር ዜና ከሸዋ!

ወታደሩ በረሃብ አለቀ / ከፍተኛ አዛዡ ከበባ ውስጥ ገባ!

ከባድ የሞት ሽረት ትንቅንቅ በሸዋ

https://www.youtube.com/watch?v=IMS8PaydR_s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Jan, 15:15


በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአማራ ፋኖ ራስ ጉና ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ አማኑኤል ሞላ ከመረብ ሚዲያ ጋር ያደረገው ቆይታ!

ሙሉውን ይከታተሉ👉
https://www.youtube.com/watch?v=ctdGGHtxmsU&t=155s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Jan, 09:03


"አርበኛ ውባንተ ሞተ ያለው ማነው፡
ያ ምሽግ ደርማሹ ሞተ ያለው ማነው፡
ዛሬም ከጉድጓዱ እንደታጠቀ ነው"

የዛ የጦሩ ገበሬ፣ የዛ የጦሩ ጠቢብ፡ የመውዜሩ ዳኛ፣ የምሽጉ ንጉስ፣ የእርሳሱ ሎሌ የሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ እስትንፋኖሶች ካለፉት አራት ጀምሮ የጠላት ጦርን የእምብርክክ ሲነዱት ሰንብተዋል።

"እረ አንተ ጎንደሬ እንዴትስ አድርገህ ተኩሰሀል ይሆን:
አለቅን አለቅን አለ ጠላት በራዲዮን" ነው ነገሩ።

በህግ ማስከበር ስም በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀው በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ የበላይነት የሚዘወረው የአገዛዝ ስርዓቱ ወታደሮች፡ " እርጎ መስሎሽ ከእርሾ ጥልቅ" እንዲሉ አበው ፋኖን አፍናለሁ ብለው በጉና ቀጠና የገቡ ቢሆንም፡ ነገር ግን በሕይወት ተርፎ መውጣት አባይን በማንኪያ ጨልፎ እንደማድረቅ ሆኖባቸው ቀርቷል።

"ወይ መድፍ ብላሽ ወይ ድሮን ብላሽ፡
ወይ ሞርተ ብላሽ ወይ ታንክ ብላሽ፡
ሲደመስሰው ፋኖ በክላሽ።

የውቤ ልጆች ጎራው እያሉ፡
የጉና አርበኞች ጎራው እያሉ፡
ጉና ሰማይ ስር የጠላትን ጦር ሲዎቁት ዋሉ" ብሏል የጠላት ጦር ተቆላልፎ ተቆላልፎ ሲወድቅ የተመለከተ ያገሬው ሰው።

ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክ/ጦር ስር የሚገኙት ፀያይም አናብስቱ የእስቴ ደንሳ ብርጌድ አባላት እና ኃያላኑ የሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ፋኖዎች በጋራ በመሆን በጉና ቀጠና ሸንበቆች፣ ዘምባራ፣ ሾለክት፣ ለበጥ፣ ማሸንት፣ ሊባኖስ፣ አፎጠን፣ መንቆላት፣ ጥናፋ፣ ሩፋኤል፣ ገና መምቻ፣ ዘንጨፍ እና ቁስቋም በተባሉ ቦታዎች ላይ የጦር አውድማ ጥለው የጠላትን ወታደር ሲያበራዩት መሰንበታቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ያለፉት ቀናት በሸምበቆች ቀበሌ በተደረገ ትንቅንቅ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ጦር እንደ ደረቀ የዛፍ ቅጠል የረገፈ ሲሆን፡ አርሶ አደሩ ቀብር ምሶ አፈር በማልበስ ፋታ አጥቷል ተብሏል።

በዚህ ስፍራ አሁንም በርካታ የጠላት አስከሬን በየአርሶ አደሩ ማሳ ወድቆ የሰማይ አሞራ እና የዱር አራዊት እየተራኮተበት መሆኑንም መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በተመሣሣይ እነዚኸው ምሽግ ደርማሾቹ የአርበኛ ውባንተ አባተ ልጆች፡ ሙትና ቁስለኛን ለማንሳት በሆድ አደር ሚሊሻና አድማ ብተና መሪነት ወደ ቀጠናቸው የገባውን አንድ ኦራል እና አንድ አይሱዙ ኤፍ ኤስ አር ሙሉ የአገዛዙን ጦር ወደ አመድነት ሲቀይሩት አፍታ አልፈጀባቸውም ተብሏል።

በዚህ ስፍራ የጠላት ዐብይ አህመድ ጦር፡ በወገን ኃይል ከበባ ውስጥ ገብቶ በአፈሙዝ አለንጋ መገረፍ ሲጀምር "እባካችሁ አድኑኝ" በሚል ትጥቁን እየጣለ በየአርሶ አደሩ መኖሪያ ቤት ለመደበቅ የሚሯሯጠውን ወታደር ለተመለከተ ትዕንግር ነበር ይላሉ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ሁንታውን ሲያስረዱ።

ደብረታቦር ከተማ ተቀምጠው ውጊያውን ሲመሩ የነበሩ የአገዛዙ የጦር መኮነኖች ወታደራቸው የፋኖ አፈሙዝ ሲሳይ ሆኖ ሲቀርባቸው ጊዜ በብስጭት "እናንተናችሁ ቀላል ነው እያላችሁ ያስበላችሁን" በሚል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የወረዳና የዞን ሚሊሻ አስተባባሪዎችን መረሸናቸው ተሰምቷል።

የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች የጦር መኮነኖቹ በሚሊሻ አስተባባሪዎቹ ላይ የወሰዱት እርምጃ ብቻ አልበቃቸውም፡ በየቀጠናው ገብቶ የነበረው ወታደራቸውን ጤና ጣቢያዎችን እያወደመ፡ መድሃኒቶችን እየዘረፈ፡ የጤና ባለሙያዎችን እየገደለነ እና እያሰረ እንዲወጣ ማድረጋቸው ታውቋል።

በአርበኛ ባየ ቀናው በሚመራው አማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክ/ጦር ስር የእስቴ ደንሣ ብርጌድ ቃል አቀባዩ ፋኖ ማረው ክንዱ ከመረብ ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ይከታተሉ👉
https://youtu.be/tHuXuXAfwyQ?si=9Z6J-r73mu3-UbQ3

Mereb Media መረብ ሚዲያ

03 Jan, 08:27


https://www.youtube.com/watch?v=fj1KXvWTVDQ&t=3s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 18:10


ሰበር ዜና!

በመሀል ሣይንት ዴንሳ ከተማ በተደረገ ውጊያ 10 የሚደርሱ የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከ20 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸው ታወቀ!

በደቡብ ወሎ ዞን የመሀል ሣይንት ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ዴንሳ ከተማ ውስጥ ከትናንት ህዳር 15/2017 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ ዛሬ ሙሉ ቀን በተደረገ ውጊያ 10 የሚደርሱ የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ በቁጥር 21 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለው ወደ ሆፒታል መወሰዳቸውን መረብ ሚዲያ የከተማዋ ነዋሪዎችን እና ጥቃቱን የፈፀመው በአማራ ፋኖ በወሎ አማራ ሳይንት መቅደላ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የአትሮንስ ብርጌድ አመራሮችን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

ውጊያው የተደረገው በከተማዋ ልዩ ስሙ ዶሮ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኝ የአገዛዙ ወታደሮች ካምፕ ላይ ሲሆን በዚህም የፋኖ አባላቱ ትልቅ ድል መቀዳጀታቸውን ነው ለጣቢያችን የገለፁት።

"እስካሁን ባለው 10 የሚዱርሱ ወታደሮች ተገድለዋል። በቁጥር 21 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል" ሲል ከመረብ ሚዲያ የወሎ ወኪል ጋር በነበረው ቆይታ የገለፀው በክ/ጦሩ የአትሮንስ ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ ኃይለማርያም መላክ፡ አሁንም ከወደቁበት ያልተነሱ ቁስለኛ የአገዛዙ ወታደሮች መኖራቸውንና ውጊያውም መቀጠሉን ተናግሯል።

ቃል አቀባዩ አክሎም የአገዛዙ ኃይሎች የኛን ክንድ መቋቋም ሲያቅታቸው  እንደለመዱት በንፁኋን ላይ የበቀል ጥቃት ሊፈፅሙ ስለሚችሉ የአከባቢው ማህበረሰብ ጥንቃቂ እንዲያደርግ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

ሙሉ ዜናውን በቪዲዮ ተከታተሉ👉https://youtu.be/_KEkIDurZvo?si=EkMOfJ-yPDjeq7tH

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 18:02


ሰበር የድል ዜና ከወሎ!

ከራያ ቆቦ ተኩለሽ እስከ መሀል ሣይንት ዴንሳ ከተማ!

ወታደራዊ አዛዦቹ ተገደሉ /ካምፑ ተቃጠለ!

https://youtu.be/_KEkIDurZvo?si=EkMOfJ-yPDjeq7tH

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 15:43


ነፍጠኛ እየመጣብህ ነው ተነስ ዝመት በሚል በምስራቅ ሐረርጌ በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያ መወሰዳቸው ተሰማ!

የአማራ ሕዝብ ወንድማችን እንጂ ጠላታችን አይደለም፡ ልጆቻችን ለማነው የሚዘምቱት የሚል ጥያቄ ያነሱ ወላጆች ድብደባ እና እስር እንደተፈፀመባቸውም ታውቋል።

ገዢው የብልፅግና ቡድን "ነፍጠኛ እየመጣብህ ነው ተነስ ዝመት፡ አባይን ሳይሻገር እዛው ባለበት እናስቀረው" በሚል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች በርካታ ወጣቶችን አፍሶ ወደ ሁርሶ እና ጦላይ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች መውሰዱን የመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ወጣቶቹ ታፍሰው የተወሰዱት በዞኑ ስር ባቢሌ፣ ጃርሶ፣ ጪናቅሰን፣ ኮምቦልቻ እና ኤረር በተባሉ ወረዳዎች  ሲሆን የወጣቶቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስመለስ እስከ 100 ሺ ብር ተጠይቀዋል ነው የተባለው።

በጅምላ ታፍሰው ከሚወሰዱት ወጣቶች መካከል ዕድሜያቸው 13 እና 14 ዓመት የሆነ ታዳጊዎችም ይገኙበታል ሲሉ ከመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በባቢሌ ወረዳ ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ወደ ጦላይ እና ሁርሶ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ በጅምላ ከታፈሱ በኋላ በባቢሌ ወረዳ ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለቀናት እንዲቆዩ የሚደረጉት ምን አልባት ልጆቻቸው ወደ ውትድርና እንዳይሄዱ የሚፈልጉ እስከ 100 ሺ ብር ከፍለው ማስለቀቅ የሚችሉ ወላጆች ካሉ እስኪመጡ ድረስ ለመጠበቅ ሲሆን፡ ወላጆቻቸው የተጠየቀውን የገንዘብ መጠን መክፈል ያልቻሉ ወጣቶች ከቀናት በኋላ ወደ ማሰልጠኛ ይወሰዳሉ ነው የተባለው።

ከላይ በተጠቀሱት በዞኑ ስር በሚገኙ ወረዳዎች "ነፍጠኛ መጣብህ ሊያጠፋህ ነው፣ እዚህ ቁጭ ብለህ ከሚገድልህ ተነስ ታጠቅ፣ አባይን ሳይሻገር እዛው ሄደን እናጥፋው፣ ዘላለም እንዳይነሳ እንስበረው" በሚል በመንቶርቦ የታገዘ የመንግት ፀጥታ ኃይሎች ጭምር የሚያስተባብሩት ቅስቀሳ በሰፊው እየተካሄደ እንደሚገኝም ነው ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን የገለፁት።

በተጨማሪም "ይህ የአገዛዝ ስርዓት የኦሮሞ ነው፡ ስለዚህ ሁሉም የኦሮሞ ሕዝብ ስርዓቱን ከመፍረስ ሊታደገው ይገባል" በሚል ቅስቀሳ እንደሚካሄድም ነው የተገለፀው።

"ነፍጠኛ የምትሉት የአማራን ሕዝብ ነው።እሱ ደግሞ ወንድማችን እንጂ ጠላታችን አይደለም፡ ልጆቻችን ለማነው የሚዘምቱት?" የሚል ጥያቄ ያነሱ ወላጆች ድብደባ እና እስር እንደተፈፀመባቸውም ነው ነዋሪዎቹ ከመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት።

ዘገባውን በቪዲዮ ተከታተሉ👉
https://www.youtube.com/watch?v=6wg9d41oVfE

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 15:13


በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ወደ ሚዲያ አውጥተሻል በሚል ለእስር የተዳረገችው የማህበረሰብ አንቂዋ መስከረም አበራ ከሦስት ሳምንት በፊት ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት እንደተፈረደባት ተሰምቷል።

የቅጣት ውሳኔው በፍርድ ቤት ሲገለጽ መስከረም አበራ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ያላት “በኮምፒውተር ተጠቅማ በህብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ክስ ነው።

ከዚህ ቀደም ያቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮቹ በአግባቡ ያልታዩልኝ ስለሆነ ከዚህ ችሎት ፍትህ አልጠብቅም፤ እናንተ ተገቢ ነው የምትሉትን ቅጣት ወስኑ፤ ከዚህ በኋላ በችሎት አልገኝም ብላ ገልፃ እንደነበር ነው ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት።

###
ቻናሉን ተወዳጁ👉https://www.youtube.com/@itsmeageri

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 14:42


የአመራር ሽግሽግ ተደረገ!

የአርበኛ, ደራሲ እና ጋዜጠኛ አሰግድ መኮንን የእጅ ሥራ ውጤት የሆነው ይኩኖ ዓምላክ ክፍለጦር የአመራር ሽግሽግ ማድረጉን አስታውቋል።

###
ቻናሉን ተወዳጁ👉https://www.youtube.com/@itsmeageri

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 14:05


የእሳት ፖለቲካው እንደቀጠለ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ወር ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ሦስተኛ ዙር የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የዛሬው በአራዳ ክ/ከተማ ውቤ በረሃ(ደጃች ውቤ ሰፈር) ላይ ነው።

###
ቻናሉን ተወዳጁ👉https://www.youtube.com/@itsmeageri

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 13:11


ሰበር ዜና!

በምስራቅ ሐረርጌ ከባድ ፍጥጫ ተፈጥሯል።

መንግስት "ነፍጠኛ መጣባችሁ ተነሱ ዝመቱ" ሲል ሕዝቡ ደግሞ "ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም" ብሏል።

በዚህም በርካታ የዞኑ ነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊት ተደብድበዋል።ገሚሶቹ ታስረዋል።

ገዢው ቡድን በሞንተርቦ ታግዞ "ነፍጠኛ አባይ ማዶን ሳይሻገር ተነሱ እዛው ካለበት ሂደን እናጥፋው" በሚል ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑ ነው የታወቀው። ሕዝቡም ይሄን ቅስቀሳ ተቃውሟል። ፍጥጫው አይሏል።

ዘገባውን ተከታተሉ👉
https://www.youtube.com/watch?v=6wg9d41oVfE

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 12:18


ከራሳቸው አንደበት!

<ምርኮኛ የመራቸው ምርኮኞች> ከተሰኘው ፕሮግራማችን የተወሰደ።

ሙሉውን👉https://www.youtube.com/@itsmeageri

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 11:03


በባሶና ወራና ወረዳ ካሲማ በተባለ ቀበሌ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁኋን ወገኖች ሲጎዱ አንድ የትምህርት ተቋም ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተሰማ!

ገዢው የብልፅግና ቡድን ትናንት ህዳር 15/2017 ዓ/ም አመሻሹን በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ባሶና ወራና ወረዳ ልዩ ስሙ ካሲማ በተባለ ቀበሌ ላይ በፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በርካታ ንፁኋን ወገኖች ሲጎዱ፡ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በአከባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ሚዲያ ክፍል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በንፁኋኖች ላይ ከደረሰው ጉዳት እና በትምህርት ተቋሙ እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶቹ ላይ ከደረሰው ውድመት በተጨማሪ በርካታ የቤት እንስሳቶችም መገደላቸው ነው የታወቀው።

ፀረ አማራው የብልፅግና ቡድን ከሰሞኑ በመላው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተለየ ሁኔታ የሰው አላባ አውሮፕላን ድብደባ እየፈፀመ ሲሆን፣ ሕዝቡ አንድ ቦታ ላይ ከመሰባሰብ እንዲታቀብና እንዲጠነቀቅ የሸዋ ዕዝ በሚዲያ ክፍሉ በኩል ጥሪ አቅርቧል።

***
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 10:50


በአጠቃላይ በዚህ በሁለት ቀን ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦርን ማጥቃት አለብኝ ብሎ የተንቀሳቀሰው የ74ኛ ክፍለ ጦር የምርኮኛው የጁላ ጦር እና ያሳደግነው ውሻ አድማ ብተና ብሎም ሚኒሻ ያሰበው አልሳካ ብሎት እየተቅበዘበዘ ይገኛል።
ጠላት በዛሬው እለት ብቻ በደብረ ኤልያስና በደንበጫ እንዲሁም ማቻክል ወረዳ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ሙትና ቁስለኛ እየተቀየረ ነው።

ጠላት የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦርን በትር መሸከም አልቻለም፣ሊሸከምም አልቻለም ምክኛቱም በክፍለ ጦራችን ውስጥ ያለው ጦር በስነ ምግባር፣በጀግንነት፣በአማራነት ፍቅር የተቃኘ የመሪውን ትዛዝ የሚያከብር ፤አመራር ለአመራርም በእጅጉ መከባበርና በመርህ የሚመራ ለአማራነት ትግል ተስፋ የተጣለበት ጦርም አመራርም ያለው ክፍለ ጦር ስለሆነ።

ሞገስና ክብር ለአማራነት ሲሉ በየ አውደ ውጊያው ለሚዋደቁ ጀግና የአማራ ፋኖ ልጆች!!

ድል ለአማራ ህዝብ

አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ

የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ቃል ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

***
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Nov, 10:50


የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የውጊያ ውሎ!!

ለሁለት ሳምንት የዘለቀው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ውጊያ ብልፅግናዊ ስርዓቱን ወንበር ያነቃነቀ ሆኖ ተመዝግቧል።
በስራ መደራረብና በውጊያ ምክንያት በየቦታው የተደረጉትን የድል ዜናዎች በዚህ ሁለት ቀን ወደ ተመልካቹ ህዝባችን ባለማድረሳችን ይቅርታ እየጠየቅን በሁለት ቀን ውስጥ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ያደረገውን ውጊያ እንደሚከተለው ነው።

~~በ14/03/2017ዓም በደንበጫ ወረዳ ዋድ እገባለሁ ያለውን የጠላት ኃይል ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ከመሬት ሲቀላቅለው ውሎ የኮሬኔል ማዕረግ እና የሻለቃ ማዕረግ ያላቸው የጠላት አመራሮች ተደምስሰዋል።ኮረኔል መሐመድ አሊ የሚባል የመከላከያ አመራር በዚህ ውጊያ ከእነ አጃቢዎቹ ተደምስሷል።
~~በ15/03/2017ዓም በአራት ቦታዎች ላይ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር አባል ብርጌዶች ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጎል።ድልም ተቀዳጅቷል።

በዚህ ቀን ውጊያ ያደረጉ ብርጌዶች

፩, የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ~~በየደገራ
፪, የበላይ ዘለቀ ብርጌድ~~ በየከባቢት
፫, የቀስተ ደመና ብርጌድ~~በአንገታም፣እመንባ
፬, በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ~~በአስናውዝ ወይም በለቅለቂታና ከባቢ እና የሳባ

~~የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድን አጠቃለሁ ያለው ኃይል ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን ቢይዝም በታምር የሚፈልገውን ቦታ ሊይዝ አልቻለም።በየቀኑ በመቶዎች እያራገፈ ዳግም ከየቦታው እየለቀመ የሚያመጣው የጠላት ኃይል በነበልባሎቹ ፋኖዎች ከመርገፍ ውጭ አንድ ግብ ማሳካት አልቻለም።

በዚህ ስምንተኛ ቀኑን በያዘው ውጊያ የኮረኔል ማዕረግ፣የሻለቃ ማዕረግ፣የሻምበል ማዕረግ፣ያላቸው የመከላከያ አመራሮችና ወረዳውን እድሜ ልካቸውን በባንዳነት ሲያስበሉ የነበሩ የፖሊስ አመራሮችና የአድማ ብተና አመራሮች በቀጠለው ውጊያ ዶግ አመድ ሆነዋል።
በውጊያው በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ተተኳሾችም ተማርከዋል።
ውጊያው ዛሬም በየዘለቃ ቀጥሏል።አናብስቶቹ የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ የፋኖ አባላት በጡሀቱ ተነስተው እየለበለቡት ይገኛሉ።

~~በትናንትናው እለት በበላይ ዘለቀ ብርጌድ የጠላት ኃይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ ተመልሷል።
ከአማኑኤል ከተማ ተነስቶ ወደ ግራ ቅዳምን እገባለሁ ያለው የጠላት ወንበዴ ቡድን የከባቢት ላይ በተደረገ ውጊያ ሶስት አምቡላንስ ሬሳ ጭኖ ሲመለስ ፣ሶስት ምርኮኛ አስረክቦ ተመልሷል።
ግራ ቅዳምን መያዝ ግን የህልም ሩጫ ሆኖበት ቀርቷል።በዚህ የተበሳጨው የአብይ አህመድ አውዳሚ አራዊት ከአስራ ሁለት ጊዜ በላይ ሞርታር በመወርወር የግራ ቅዳምን ንፁን ሲገድልና ቤት ሲያፈርስ ውሏል።በዚህ ውጊያም በርካታ ተተኳሽ ተማርኳል።ውጊያው ዛሬም እንደቀጠለ ይገኛል።
~~በትናንትናው እለት ከደብረ ማርቆስም ፣ከአማኑኤልም ከሌላም ቦታ ተውጣጥቶ ደብረ ኤልያስ ወረዳ እገባለሁ ያለው የብርሐኑ ጁላ አራዊት ሰራዊት በአንገታምና በእመንባ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ውሏል።
አስራ ስድስት ሺ ሰራዊት ለሰሚው ግራ በሆነ መልኩ ዶግ አመድ አርገው የብርሐኑ ጁላን ጦር ያሽመደመዱት የቀስተ ደመና ብርጌድ የፋኖ አባላት ደብረ ኤልያስን ከጠላት ነፃ አድርገው ማስተዳደር ከጀመሩ እነሆ አመት ከሶስት ወራቸው ነው።እስካሁን ጠላት ገብቶ ሳምንት የማይቀመጥባት ዝነኛዋ ወረዳ ደብረ ኤልያስ አሁንም ታሪክ እየተሰራባት ነው።

የእነ ዮፍታሔ ንጉሴ የትውልድ ቀዬ የሆነው ደብረ ኤልያስ ወረዳ ዛሬም በልጆቹ ታሪክ እየተፃፈ ነው።ከደብረ ማርቆስም ከአማኑኤልም ተነስቶ በባንዳዎች እየተመራ እመንባ አንገታም ቢደርስም ከትናንት እስከ ዛሬ አንገቱን እየተቀላ ጠላት እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው።

ወደፊት መግፋት የሚታሰብ አልሆነም።አሁንም ፔምፒኤ እንዲሁም ዙ23 እየተሸከመ ቢመጣም ጠላት የፋኖን በትር መሸከም አልቻለም።ሬሳ እያመላለሰ የዋለው የጁላ ጦር እመንባ ጊዮርጊስ ተወሽቆ ቤተክርስቲያኑን አለቅም ብሎ ለውጊያ ከማስቸገር ውጭ ሌላ አንዳች የፈየደው ነገር የለም።

ጠላት ሲሸነፍ ቤተክርስቲያን መሸሸግ የሁልጊዜ ተግባሩ ነው።ፋኖ ቤተክርስቲያንን አይመታም በሚል የጁላ ጦር ዱላው ሲበዛበት ወደ ቤተክርስቲያን ነው የሚወሸቀው።አሁንም የብርሐኑ ጁላ ጦር እና ካድሬ አመራር የምፍራቁን በር እየገነጠለ እየገባ የተወሸቀው እዛው እመንባ ጊዮርጊስ ነው።

~~በትናንትናው እለት የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ የፋኖ አባላት በአስናወንዝ እና በለቅለቂታ ከባቢ ጠላትን እንደ ጨጓራ ሲያራግፈው ውሎ የአድማ ብተና አመራሮችንና የከባድ መሳሪያ ተኳሾችን ሲያጣ ጠላት እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደመጣበት ፈርጥጧል።
አንድ ክፍለ ጦር የሚሆን ኃይል ከደብረ ማርቆስ አውጥቶ በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድን መደምሰስ አለብኝ ብሎ ቢንቀሳቀስም ክንደ ነበልባሎቹ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በሶስት አቅጣጫ አሰፍስፎ የመጣውን ወንበዴ ቡዱን እንደ አመጣጡ ግንባር ግንባሩን ሲቀጥፉት ውለዋል።

በሜካናይዝድ የታጀበው የአብይ ወንበዴ ቡድን ለደብረ ማርቆስ ከተማ ስጋት የሆነብኝ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ነው በማለት ሁለት ዙ 23 እና አንድ ፔምፒኤ አሰልፎ አራት ጊዜ ተጨማሪ ኃይል ከማርቆስ ቢያስወጣም የአስናወንዝን ተሻግሮ ቸርተከል መግባት አድለም ማሰብ አልቻለም።ይዞት የመጣው ሞርተር፣ዙ 23፣ ፔምፒኤ፣ድሽቃ የያዘውን ጥይት ቢተኩስ ፋኖ መሬት ካነጠፈ ወይ ፍንክች ፀጥ እረጭ።

ጠላት አንድ እርምጃ ሲራመድ ነበልባሎቹ ቅንድቡን ሲላጩት ተመልሶ ወደ ኃላ ይሮጣል።በዚህ የተበሳጨው የጠላት ኃይል አዋጊ ስልኩን አንስቶ ወደ ደብረ ማርቆስ ኃይል ይጨመረኝ ጥያቄ አቀረበ ፣መልሱ ግን ባለህ ተዋጋ ሌላ ኃይል የለኝም የሚል መልስ ነበር።
በዚህ ውጊያ የየደረና ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን በሞርታር በመደብደብ ቤተክርስቲያን ከሚሳለሙ ምዕመናን አንድ ሰው አቁስሏል።የዚህን ቤተክርስቲያን መመታት የተመለከቱት የፋኖ ኃይሎች እንደገና ወኔያቸው ጨምሮ በተደረገ ውጊያ ቅዲስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ለመታደግ እና የአማራን ህዝብ ለመታደግ በተደረገ ውጊያ ሶስት ወንድማማቾች ታሪክ ሰርተው ተሰውተዋል።ክብርና ሞገስ ለጀግኖቻችን ይሁን።

ውጊያ ሲበዛበት መሸሸጊያ ያደርጋታል፣ውጊያው የቀለልኝ ሲመስለው ደግሞ በሞርታር የሚደበድባት ቅድስት ቤተክርስቲያን የዚህ እምነት የለሽ ስርዓት እንደ አማራ ህዝብ እንድትጠፋ የተፈረደባት ሐይማኖት ናት።
ድል መቀዳጀትን እና ጠላትን እረፍት ነስቶ ጠዝጥዞ ፣ነዝንዞ ማስወጣት የሚል መርህ የሚከተለው የበረኸኛው ጅበላ መተራ ብርጌድ አንድ ኦራል፣ሁለት ፒካፕ፣አንድ አምቡላንስ ሬሳ አስነስቶ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ፤ጠላት ቸርተከልን መያዝ አድለም ዳግመኛ ማሰብ እንዳይችል አድርጎ መልሶ ልኮታል።

በዚህ የተበሳጨውና ከማርቆስ ተነስቶ ወደ ደብረ ኤልያስ እገባለሁ ያለው የአብይ ቡድን እመንባ ጊዮርጊስ ላይ ቤተክርስቲያን በመግባቱ ምክኛት የቀስተ ደመና ብርጌድ ከቦ ስለያዘው እሱን ለማስለቀቅ ወደ እመንባ አቀና።

ጎዛምን ወረዳን ለቆ የወጣው ኃይል ቀስተ ደመናን እመታለሁ ብሎ ለሊቱን ሙሉ ሲያግዘው ቢያድርም የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ጠላት የደብረ ኤልያስ ወረዳን ሲወር ከምናይ የደሳለው መላኩ እና የሽመልስ ስማቸው  አፅም እሾህ ሁኖ ቢወጋን ይሻላል ብለው ከአንደኛው ወረዳ ወደ ሌላኛው ወረዳ በእሳት ወራውርት ተወርውረው አሁን በዚህ ሰዓት ከቀስተ ደመና ብርጌድ ጋር በመሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ የወሸቀውን ጠላት እንደ ቅጠል እያረገፉት ይገኛሉ።

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 20:52


የአገዛዙ ኃይሎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ታዳጊዋ ቃሊም ከተማ ላይ በፈፀሙት የመድፍ ድብደባ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አረሶ አደሮች ተገድለዋል።

የሟቾቹ  ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መረብ ሚዲያ በስፍራው ተገኝቶ ቀረፃ አካሂዷል። እናቶች ሀዘናቸውን መቋቋም ከበዳቸው።  ቪዲዮ ይመልከቱ👉

https://youtu.be/HX4D4jijRFU?si=ch9RpqMgfExHZBS-

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 17:19


"ሰልጥነን እንታገላለን እየታገልን እንሰለጥናለን"

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር #ሃይለማርያም ማሞ ብርጌድ ለተከታታይ አምስት ወራት ያህል ያሰለጠናቸውን ልዩ የኮማንዶ አባላት በድምቀት አስመርቋል።

የምርቃት ፕሮግራሙ ህዳር 14/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በሸዋ ቡልጋ ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ የተካሔደ ሲሆን በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የከሰም ክፍለጦር ከፍተኛ አመራሮች፣የሀይለማርያም ማሞ የብርጌድ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

በዕለቱ በተማራቂዎች ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ፋኖ ደጉ ተስፋዬ "የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያዊነቱ ደሙን ያፈሰሰ አጥንቱን የከሰከሰ ፣ሀገር ገንብቶ ያስረከበ ባለውለታ ህዝብ ቢሆንም አሁን ላይ እንዲጠፋ የተፈረደበት፣በየቦታው የሚታረድ ፣ሰርቶ እንዳይበላ የተደረገ፣የሞት ድግስ የተደገሰለት እጁ አመድ አፋሽ የሆነ ህዝብ ስለሆነ ይህንን የሴራ ወጥመድ የምንበጥሰው በልኩ ስንነቃ፣አንድ ሆነን ስንታገል ፣ታጥቀን ስንፋለም ብቻ ስለሆነ ሳንወድ በግድ ተገፍተን እየታገልን እንገኛለን" ብለዋል። እንዲሁም  "የምንታገለው በትክክለኛና በተጠና የትግል መስመር፣መነሻችንን እና መድረሻችንን ለይተን የምናቅ በስንቅም በትጥቅም ፣በእውቀትም በክህሎትም የተደራጀን ከቲም እስከ ዕዝ ተቋም ገንብተን የምንታገል የምናታግል ጀግንነትን ከአባቶቻችን ፅናትን ከማንነታችን የወረስን እኛ አማራዊያን ነን" ያሉት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለአስተዳደር ዋና ሳጅን እሸቱ ተክለ ሚካኤል "ለወጣንለት የህልውና ትግል ታምነን እንሰራለን" ብለዋል።


   ድል ለአማራ ፋኖ
     ድል ለአማራ ሕዝብ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ  ህዝብ ግንኙነት ክፍል

***
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 14:04


የአገዛዙ ኃይሎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ታዳጊዋ ቃሊም ከተማ ላይ በፈፀሙት የመድፍ ድብደባ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አረሶ አደሮች ተገድለዋል።

የሟቾቹ  ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መረብ ሚዲያ በስፍራው ተገኝቶ ቀረፃ አካሂዷል። እናቶች ሀዘናቸውን መቋቋም ከበዳቸው።  ቪዲዮ ይመልከቱ👉

https://youtu.be/HX4D4jijRFU?si=ch9RpqMgfExHZBS-

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 13:02


የአገዛዙ ወታደሮች ያ ባበላቸው፣ ባጠጣቸው፣ ቁስላቸውን ባጠበላቸው የአማራ አርሶ አደር ላይ የሚወረውሩት ከባድ መሣሪያ ነው።

(ምስል፦ አማራ ፋኖ በወሎ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)

***
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 11:51


ቀጥታ ከጎንደር!

የቪዲዮ ስርጭት ከጉና ተራራ ስር!


ሴት አርበኞች ከመረብ ሚዲያ ጋር!

https://www.youtube.com/watch?v=-onn_2FMAoU

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 11:31


ቀጥታ ከጎንደር!

የቪዲዮ ስርጭት ከጉና ተራራ ስር!


ሴት አርበኞች ከመረብ ሚዲያ ጋር!

https://www.youtube.com/watch?v=-onn_2FMAoU

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 11:14


https://www.youtube.com/watch?v=I1xdbTzl65c&t=12s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 07:45


የአድማ  ብተና አባሉ ኑዛዜ!

"በጥቅም ተሸውጄ እናቶቼ ላይ ተኮስኩ"

ሙሉውን ይከታተሉ👉https://www.youtube.com/watch?v=cb0YQGJcH6w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

23 Nov, 05:29


ምርኮኛ ልጆቻቸው በሰላም ወደ ቤታቸው የተሸኙላቸው የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለፋኖ ምስጋና አቀረቡ!

በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ የስርዓቱ አገልጋይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተማርከው በፋኖ እጅ ይገኛሉ።

ፋኖ እነዚህ ምርኮኛ ወታደሮችን የአለም አቀፍ የምርኮኛ አያያዝ ሕገ ደንብን ባከበረና አማራዊ እሴትን በጠበቀ መልኩ ተንከባክቦ እንደያዛቸው የመረብ ሚዲያ የግምባር ዘጋቢዎች በተንቀሳቀሱበት ቀጠና ለመመልከት ችለዋል።

ከምርኮኛ ወታደሮች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ "ይህ ስርዓት የኦሮሞ ስርዓት ነው።እንዳይፈርስ መታደግ አለባችሁ" በሚል ፕሮፓጋንዳ ተታለው መከላከያ ሰራዊትን እንደተቀላቀሉ ይናገራሉ።

የፋኖ አባላቱም በፈቃደኝነት አላማቸውን ተጋርተው ከእነሱ ጋር ለመቀላቀል የፈለጉ ምርኮኛ ወታደሮችን የተሀዲሶ ስልጠና በመስጠት እንዲቀላቀሏቸው ያደረጉ ሲሆን፡ ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ የፈለጉትን ደግሞ የትግሉን አላማ በማስረዳትና የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈን በሰላም የሚሄዱበትን ቀጠና በማመቻቸት እየሸኙ ይገኛሉ።

ከነዚህ መካከል በወሎ ቀጠና እየተካሄደ ባለው ውጊያ ከ2016 ዓ/ም መጨረሻዎቹ ወራት ጀምሮ የተማረኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ የሚፈልጉ ምርኮኛ ወታደሮች የሚሄዱበትን ሰላማዊ ቀጠናና የመጓጓዣ ወጪ በፋኖ ተሸፍኖላቸው የተሸኙ ሲሆን፡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሰላም መቀላቀላቸውንም አሳውቀዋል።

ልጆቻቸው ከሞት ተርፈው በሰላም የመጡላቸው በወለጋ፣ በሸዋ፣ በቦረና እና በሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች የሚገኙ የምርኮኛ ወታደር ወላጅ የሆኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለፋኖ ምስጋና ማቅረባቸውን ነው መረብ ሚዲያ የፋኖ አመራሮችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።

በፋኖ ከተማረከ በኋላ የመጓጓዣ ወጭ ተሸፍኖለት የተሸኘ ልጇን በሰላም ያገኘች በምዕራብ ሸዋ አምቦ ከተማ ነዋሪ የሆነች አንዲት እናት ምርኮኛ ልጇ ይዞት በነበረው የፋኖዎች አድራሻ መሠረት ስልክ በመደወል "ልጄን ዳግመኛ እንደወለዳችሁት ነው የምቆጥረው። ይህ አካሄዳችሁ ትግላችሁ ሀቅ እንዳለው የሚያስመሰክር ነው። የእውነት አምላክ ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ነው የፋኖ አመራሮቹ ለጣቢያችን የገለፁት።

ምርኮኛ ልጃቸው በሰላም ወደ ቤቱ የተመለሰላቸው ሌላኛው በቄለም ወለጋ ደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ አባት "ልጄ በፋኖ መማረኩን ስሰማ አለቀስኩ።ምክኒያቱም እኛ በቀበሌ ስብሰባም፡ በኦቢኤንና በኦኤሜን ቴሌቪዥንም የሚነገረን ፋኖ ገዳይና አራጅ ነው በሚል ነው። አሁን ግን የትግላችሁን ሀቀኝነት አረጋግጣችሁልኛል። ዋቃ(አምላክ) ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምርኮኛ ልጆቻቸው በሰላም ወደቤታቸው መሸኘታቸውን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አርሲ አከባቢን ጨምሮ በጉጂ፣ በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ እና በሌሎች የክልሉ አከባቢዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ተመሣሣይ የምስጋና መልዕክት ማስተላለፋቸውን ነው የፋኖ አመራሮቹ ለመረብ ሚዲያ የወሎ ወኪል የገለፁት።

ዜናውን በቪዲዮ ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ👉https://youtu.be/5wPqehlsVr4?si=Q1lK4ditacqMD-m8

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Nov, 17:17


ሰበር ቪዲዮ ከጎንደር!

የአድማ ብተና አባሉ ሕዝቡን በይፋ ይቅርታ ጠየቀ!

"እናቶቼ ላይ ተኮስኩ/ወንድሞቼ ላይ ጨከንኩ"

https://www.youtube.com/watch?v=cb0YQGJcH6w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Nov, 15:42


ወሎ ቤተ-አምሐራ

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ረፍት መንሳቱና መፈናፈኛ ማሳጣቱ ብሎም በደፈጣ ተዳክሞ ሲገኝ በመደበኛ ዉጊያ መደምሰስና መማረኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ዞብል አምባ ክፍለጦር ካለው ሰራዊት 1ኛ ሻለቃ እና በፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ልዩ ዘመቻ ዛሬ ህዳር 13/2017 ዓ.ም በጋራ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ጥቃቱ ከቆቦ ከተማ በምዕራብ ተኩለሽ መስመር ከ4-5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተፈፀመ ሲሆን በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ዉጊያ ወደ መደበኛ አድጎ ጠላት በርካታ ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ ቆቦ ከተማ ፈርጥጧል:: የደፈጣ ጥቃቶቹ ከከተሞች በቅርብ ርቀት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ጠላትም በበርካታ ጥቃቶች ተሰላችቶ ወደ ፋኖ እየኮበለለ ይገኛል::

ራያ ቆቦ ተኩለሽ የገባው ጠላትም መሉ ለሙሉ ከበባ ዉስጥ ገብቶ ረሽንና ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዳይደርሰው ሆኖ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ሲል የዞብል አምባ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሃብተማርያም መንበሩ ገልፇል::

በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የዞብል አምባ ክፍለጦር አመራሮች እና የልዩ ዘመቻ አዛዡ ፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) ገልፀዋል::

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 13/2017 ዓ.ም

***
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 16:10


የአማራ ፋኖ በወሎ ከፍተኛ አመራሮች ከመረብ ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቆይታ!

ከአንድ ሰዓት በኋላ በመረጃ ቲቪ ላይ በሚኖረን የስርጭት ሰዓት ይከታተሉ።

ሙሉ ቪዲዮውን በዩቲዩብ ለመመልከት ለምትፈልጉ ሊንኩን ይጫኑ!
https://www.youtube.com/watch?v=MugA0WEHhdY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 14:44


ሰበር ዜና!

በአምቦ ሜዳ ከተማ እና በሊቦ ከምከም መካከል ግራጫ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው የብልፅግና ፓርቲ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ታወቀ!

በደፈጣ ጥቃቱ የቆሰሉና ህይወታቸው ያለፈ ወታደሮችን አንስታችሁ ተሽከርካሪ ላይ ጫኑ ባሉ ለጥቂት ከጥቃቱ በተረፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና አናነሳም ባሉ በአከባቢው ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሁለት አርሶ አደሮች መገደላቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

በደቡብ ጎንደር ዞን ዛሬ ሕዳር 11/2017 ዓ/ም ማርፈጃውን በበርካታ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ከአምቦ ሜዳ ከተማ ወደ ሊቦ ከምከም እየተጓዙ የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች በተለምዶ ግራጫ ወይም አቦ ገዳም ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ሲደርሱ የደፈጣ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው መረብ ሚዲያ በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር ቃል አቀባይ የሆነው ፋኖ መልካሙ ጣሴን ዋቢ በማድረግ ከሰዓታት በፊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ማስነበቡ አይዘነጋም።

በደፈጣ ጥቃቱ በኦሮሞ ብልፅግና የበላይነት ለሚዘወረው የአገዛዝ ስርዓት አገልጋይ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ቆስለው ለሕክምና ወደ አዲስ ዘመን ከተማ መወሰዳቸው ታውቋል።

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ወታደሮችን በቁጥር አራት አምቡላንሶች ወደ ሕክምና ጣቢያ ሲያመላልሱ ማርፈዳቸውን ነው የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ የገለፁት።

እድል ቀንቷቸው ከደፈጣ ጥቃቱ ለጥቂት የተረፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአከባቢውን ነዋሪዎች ሰብስበው በጥቃቱ የተገደሉ የጓዶቻችንን አስከሬንን ተሽከርካሪ ላይ ጫኑ የሚል ትዕዛዝ የሰጡ ቢሆንም ነገር ግን ነዋሪዎቹ አንተባበርም በማለታቸው በዚህ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ አርፍዷል።

በግጭቱ እስካሁን ባለው ሁለት አርሶ አደሮች ህይወታቸው ማለፉ የታወቀ ሲሆን፣ በርካታ አረጋውያን እናቶችም ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ሲሉ ጣቢያችን ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ሁኔታውን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ውጊያዎች በፋኖ የሚገደሉ የመከላከያ ሰራዊትና የአድማ ብተና አባላት አስከሬንን የሰው ልጅ ክቡር ነው በሚል ከወደቀበት እያነሳን ስርዓተ ቀብራቸውን ፈፅመን ነበር ያሉት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ነገር ግን የቀበራችሁትን የመንግስት ወታደር ብዛት ለሚዲያ ተናግራችኋል በሚል ግድያ እና ድብደባ እንዲሁም እስራት ተፈፅሞብናል ብለዋል።

በዚህ ምክኒያት ከፋኖ ጋር በሚደረግ ውጊያ ለሚጎዱ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአድማ ብተናና የሚሊሻ አባላት ምንም አይነት ትብብር አናደርግም ሲሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ከመረብ ሚዲያ የጎንደር ወኪል ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

ቪዲዮውን ይመልከቱ👉 https://www.youtube.com/watch?v=aCRT52zoZ-k

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 14:06


ሰበር ዜና!

አምቦ ሜዳ አከባቢ ፋኖ በፈፀመው ደፈጣ ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ተሰምቷል።

በጥቃቱ የተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮችን አስከሬን አንሱ ባሉ ከጥቃቱ በተረፉ ወታደሮች እና አናነሳም ባሉ የአከባቢው ነዋሪዎች መካከል ግጭት የተቀሰቀሰ ሲሆን በዚህም ሁለት አርሶ አደሮች መገደላቸው ተሰምቷል።

ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=aCRT52zoZ-k

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 13:45


ሰሜን ወሎ ሲሪንቃ!

ስሪንቃ ከተማ ላይ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በጅምላ ታፍሰው እርሻ ልማት ወደ ሚገኘው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ወታደር ካምፕ ተወስደዋል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የደሴ ቅርንጫፍ ጋዜጠኞችና የካሜራ ባለሙያዎች እንዲሁም የፋናና የኤቢሲ፣ የመከላከያ ቴሌቪዥን የቀረፃ ባለሙያዎችም በስፍራው እንደተገኙ ነው ለመረብ ሚዲያ የደረሰው መረጃ የሚያመላክተው።

በስራ ላይ እንዳሉ ጅምላ ታፍሰው የታሰሩ ወጣቶችን ምርኮኛ ናቸው በሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ቀረፃ ሊካሄድ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ የወሎ ወኪል ገልፀዋል።

(ምስል፦ ከማህደር)
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 11:20


https://www.youtube.com/watch?v=MugA0WEHhdY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 10:44


ከባድ የደፈጣ ጥቃት ከሊቦከምከም በቅርብ ርቀት!

በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ከአምቦ ሜዳ በቅርብ ርቀት ግራጫ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከባድ የሆነ የሽምቅ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።

በጥቃቱ በርካታ የብልፅግና ፓርቲ መከላከያ ሰራዊት አባላት የተገደሉ ሲሆን ቁስለኞች ለሕክምና ወደ አዲስ ዘመን እየተወሰዱ መሆኑን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ከጥቃቱ የተረፉት ወታደሮች የአከባቢው ነዋሪ አስከሬን እና ቁስለኛ እያነሳ በተሽከርካሪ እንዲጭን ያዘዙ ቢሆንም፡ ነገር ግን ሕዝቡ "የጓዶቻችሁን አስከሬን ከወደቀበት አንስተን በተሽከርካሪ ከጫንላችሁ በኋላ መረጃ ታወጣላችሁ በሚል ምክኒያት ልክ እንደዚቀደሙ ትገድሉናላችሁ"በሚል አንተባበርም ብሏል።

በዚህም በአከባቢው ውጥረት መንገሱ ነው የተሰማው።

መረጃውን ለመረብ ሚዲያ ያደረሰው በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ነው።

(ምስል፦ የክ/ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ መልካሙ ጣሴና ጓዶቹ)

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 08:36


https://www.youtube.com/watch?v=kZZ_V1JOCk0

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Nov, 06:17


የዞብል አናብስቶች!

ዱር ቤቴ ካሉ እንሆ ዓመታትን አስቆጥረዋል።

ከሕወሓት ወረራ ጀምሮ የምሽግ ድንጋይ ነው ትራሳቸው።

ስለ አማራ ሕዝብ ሕልውና ሲሉ አበባው ዕድሜያቸውን፣ ወጣትነታቸውን እየገበሩ ይገኛሉ።

ድል ለእናንተ ይሁን!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Nov, 17:12


ሰበር ዜና!

በደምበጫ ወረዳ ለሁለት ቀናት በተደረገ ውጊያ ከአንድ ሬጅመንት በላይ የገዢው ቡድን ጦር መደምሰሱ ተሰማ!

በተመሣሣይ ዛሬ እኩለ ቀን ገደማ በደምበጫ ከተማ በተፈፀመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በቁጥር አምስት ንፁኋን ወገኖች መገደላቸው ታውቋል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የደምበጫ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ደምበጫ ከተማ እና ዳባ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ትናንት ህዳር 09/2017 ዓ/ም ማለዳ የተጀመረው ውጊያ ዛሬ እስከ እኩሉ ቀን የቀጠለ ሲሆን በዚህም 220 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ ከ50 በላይ የሚሆኑት ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአማራ ፋኖ በጎጃም የ6ኛ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መምህር ታደገ ይሁኔ ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

ትናንት ከማለዳው ጀምሮ እስከ አመሻሹ ድረስ በደምበጫ ከተማና በዙሪያዋ እንዲሁም ዳባ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተደረገ ውጊያ በቁጥር 170 የገዢው ብልፅግና ፓርቲ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ በተመሣሣይ በዛሬው እለት በዚኸው ቀጠና በቁጥር 50 ወታደሮች ተገድለዋል፣ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ሲል ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ የገለፀው የክ/ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ መምህር ታደገ፡ በሁለት ቀናት ብቻ በድምሩ ከአንድ ሬጅመንት በላይ የአገዛዙ ጦር መደምሰሱን አረጋግጧል።

በውጊያው ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ የአገዛዙ ወታደሮች በተጨማሪ አንድ ዙ 23 የወደመ ሲሆን፡ በቁጥር 800 የብሬንና የክላሽንኮቭ መሣሪያ ተተኳሽ በፋኖ እጅ መግባቱንም ቃል አቀባዩ ለጣቢያችን ገልጿል።

አገዛዙ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ በሚመስል መልኩ በዛሬው እለት በደምበጫ ከተማ የድሮን ጥቃት የፈፀመ ሲሆን በዚህም ህፃናትን ጨምሮ እስካሁን ባለው  አምስት ንፁኋን ሰዎች መገደላቸው ሲታወቅ በርካቶች ቆስለዋል ነው የተባለው።

ሀገር እየገዛሁ ነው የሚለውና በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የበላይነት የሚዘወረው የአገዛዝ ስርዓት በጦር ግምባር ከፋኖ የሚሰነዘርበትን አፀፋዊ ጥቃት መቋቋም ባለመቻሉ፡ በዚህም ሰው አልባ አውሮፕላን፣ መድፍ እና ሌሎች ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም በንፁኋን ወገኖች ላይ የሚፈፅመው አሰቃቂ ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉን መረብ ሚዲያ ከየአከባቢው ያሰባሰበው መረጃ ያመላክታል።

የውጊያውን ዝርዝር በቪዲዮ ይከታተሉ!👉
https://www.youtube.com/watch?v=G3GwWZrjzDQ&t=357s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Nov, 13:33


የአገዛዙ ኃይሎች በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ ላይ በርካታ ንፁኋን ሰዎችን መግደላቸው ተሰማ!

የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ትናንት ህዳር 09/2017 ዓ/ም በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ አሰም ስላሴ፣ ኳንቻ አቦ  እና አከና ጂፊ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ በርካታ ንፁኋን ሰዎችን መግደላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የአገዛዙ ኃይሎች አማራ ፋኖ በጎጃም በ3ኛ ክ/ጦር ስር በሚገኙት ከዘንገና፣ከኤፍሬም አጥናፉ እና ከስሜነህ ደስታ ብርጌድ ፋኖዎች በኩል የተሰነዘረባቸውን አፀፋዊ ጥቃት መቋቋም ባለመቻላቸው ነው የፈሪ ዱላቸውን በንፁኋን ላይ ያሳረፉት ሲሉ ለመረብ ሚዲያ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በዚህም ህፃናትን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልተለየ በርካታ ንፁኋን ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል።

"የብልፅግና ፓርቲ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከፋኖ የተሰነዘረባቸውን ጥቃት መቋቋም ባለመቻላቸው ወደ ኋላ ሲሸሹ <የእናንተ ወንድሞች፣ የእናንተ ልጆች ናቸው የመቱን> በሚል በመንገድ ያገኟቸው ንፁኋን ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እረሽነዋል።አንዳንዶቹንም ለከባድ ጉዳት ዳርገዋቸዋል" ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የጤና ባለሙያ ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

በተጨማሪም እነዚኸው ሞራልና ህሊናቢስ የገዢው ቡድን ወታደሮች አከባቢውን በዙ23 እና በሌሎች ከባድ መሣሪያዎች በመደብደብ በመኖሪያ ቤቶች እና በሰብል ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸው ነው የታወቀው።

በተመሣሣይ በዚኸው ወረዳ ከሁለት ቀናት በፊት በጃንጉታ ጊዮርጊስ ቀበሌ ላይ የአገዛዙ ወታደሮች በሚሊሻና አድማ ብተና መንገድ መሪነት "የፋኖ ወላጆች ናችሁ፣ የፋኖ እህትና ወንድም ናችሁ" በሚል ምክኒያት በርካታ ነዋሪዎች መደብደባቸውን ለጣቢያችን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ሙሉ ዜናውን ይከታተሉ👉
https://www.youtube.com/watch?v=d3JRVMoAAjY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

19 Nov, 06:38


እንደምን አረፈዳችሁ!

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ በወሎ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ያደረገውን ቆይታ ዛሬ ምሽት መረጃ ቲቪ ላይ በሚኖረን ከትግል ሜዳ በተሰኘው ፕሮግራማችን ይጠብቁን!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Nov, 20:48


የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ጦር በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ አሰም ስላሴ፣ ኳንቻ አቦ  እና አከና ጂፊ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ በርካታ ንፁኋን ሰዎችን መግደሉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የአገዛዙ ወታደሮች ንፁኋኑን በአሰቃቂ ሁኔታ የረሸኑት ከፋኖ የተሰነዘረባቸውን አፀፋዊ ጥቃት መቋቋም ባለመቻላቸው ወደ ኋላ እየሸሹ በነበረበት ወቅት ነው ሲሉም የአይን እማኞች ለጣቢያችን ገልፀዋል።ዝርዝሩን ይዘናል።

***
በተሽከርካሪ ተሳፍረው ከቆቦ ከተማ ወደ ወልድያ አቅጣጫ እየተጓዙ የነበሩ የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች አራዱም አከባቢ በሚገኘው ጎሊና ወንዝ ላይ ሲደርሱ በተፈፀመባቸው ደፈጣ ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ተሰማ!


በተመሣሣይ

በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ጮቢ በር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የመሸገው የጠላት ኃይል ላይ በተፈፀመ ድንገተኛ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ በርካቶች ደግሞ ከነ መሣሪያቸው መማረካቸው ታውቋል።በዝርዝር ይዘነዋል።

***
በአማራ ሳይንት ወረዳ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አንድ የትምህርት ተቋም ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተሰማ!

ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ጥቃቱ በተፈፀመበት አከባቢ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችም መውደማቸው ነው የታወቀው።

በዚህም መኖሪያ ቤታቸው የወደመባቸው ነዋሪዎች ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው ሜዳ ላይ መውደቃቸውንም ተሰምቷል።በዝርዝር ይዘነዋል።

የሦስቱንም ዝርዝር መረጃ በቪዲዮ ይከታተሉ👉
https://www.youtube.com/watch?v=d3JRVMoAAjY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Nov, 18:30


ራያ ቆቦ፣ ወልድያ ዙሪያ፣ ጎጃም አገው ምድር!


ሰበር የድል ዜና በዚህ ምሽት!

https://www.youtube.com/watch?v=d3JRVMoAAjY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Nov, 16:46


በአማራ ሳይንት ወረዳ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አንድ የትምህርት ተቋም ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተሰማ!

ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ጥቃቱ በተፈፀመበት አከባቢ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችም መውደማቸው ነው የታወቀው።

በአማራ ሳይንት ወረዳ 024 ቀበሌ ዋሮ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ ህዳር 09/2017 ዓ/ም ማርፈጃውን በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የትምህርት ተቋሙ ሙሉ በሙሉ መውደሙን የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

"የድሮን ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅትም ይሁን ከዛ በፊት በነበረው ጊዜ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ምንም አይነት የፋኖ ኃይል የለም፣ አልነበረም" ሲሉ ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ "ገዢው የብልፅግና ቡድን በህግ ማስከበር ስም የአማራን ሕዝብ ከነማህበራዊ ተቋሟቱ ማውደምን እንደ ትልቅ ስኬት ስለሚቆጥረው የአየር ጥቃት ፈፅሞብናል" ብለዋል።

በትምህርት ተቋሙ ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሃፍና ቤተ ሙከራ ክፍሎች እንዲሁም የመምህራንና የትምህርት ቤቱ አሰተዳደር አካላት ቢሮዎች መውደማቸው ነው የተገለፀው።

በጥቃቱ ከትምርት ተቋሙ በተጨማሪ በአከባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ውድመት የደረሰ ሲሆን፡ በዚህም መኖሪያ ቤታቸው የወደመባቸው ነዋሪዎች ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው ሜዳ ላይ መውደቃቸውንም የአይን እማኞች ለመረብ ገልፀዋል።

ሀገር እየገዛሁ ነው የሚለውና በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የበላይነት የሚዘወረው የአገዛዝ ስርዓት በህግ ማስከበር ስም በአማራ ክልል ምንም አይነት የታጠቀ የፋኖ ኃይል በማይገኝባቸው የሐይማኖት ተቋማት፣ የትምህርት እንዲሁም ሌሎች ታሪካዊና ማሕበራዊ ተቋማት ላይ የሚፈፅመው የከባድ መሣሪያ ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉን መረብ ሚዲያ ከየአከባቢው ያሰባሰበው መረጃ ያመላክታል።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

18 Nov, 14:50


በተሽከርካሪ ተሳፍረው ከቆቦ ከተማ ወደ ወልድያ አቅጣጫ እየተጓዙ በነበሩ የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!

ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ህዳር 09/2017 ዓ/ም ንጋት ላይ በቆቦ ከተማ እና ሮቢት መካል በምትገኘው አራዱም ተብላ በምትጠራው አከባቢ ልዩ ቦታው ጎሊና ወንዝ ላይ ሲሆን በዚህም በርካታ ወታደሮች እስከ ተሽከርካሪያቸው በእሳት ተቃጥለው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈው በርካታ ወታደሮች በተጨማሪ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኛ ወታደሮች ከስድስት በላይ በሚሆኑ በባለ ሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ሕክምና ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን፡ ቀሪዎቹ ወታደሮችም አጋጣሚውን ተጠቅመው ከአሃዳቸው እየከዱ ማሽላ ለማሽላ አቆራርጠው መጥፋታቸውን መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ በወሎ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ደፈጣ ጥቃቱን የፈፀመው አማራ ፋኖ በወሎ ካላኮርማ ክፍለጦር መሆኑንም ሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ለጣቢያችን በላከው አጭር መግለጫ ጠቅሷል።

በአርበኛ ዘውዱ ዳርጌ የሚመራው ካላኮርማ ክፍለጦር ሰሞኑን ከራያ ቆቦ አራዱምና መንጀሎ እስከ ጎብየ በርካታ ተጋድሎዎችን እያደረገ መሰንበቱም ነው የተገለፀው።
(ምስል፦ ከማህደር)

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

14 Nov, 11:51


ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ቃሊም ቀበሌ!

የገዢው ቡድን ወታደሮች በትናንትናው እለት ቃሊም ቀበሌ ላይ በፈፀሙት ከ50 ጊዜ በላይ የመድፍ ድብደባ ህይወቱ ያለፈው የሦስት ልጆች አባት የሆነው የሟች አርሶ አደር ወዳይ ጎበዜ ስርዓተ ቀብር ላይ የተወሰዱ ምስሎች።

አንድ አርሶ አደር ሕይወቱ ማለፉንና ህፃናትና አዛውንቶችን ጨምሮ ጤፍ አጨዳ ላይ የነበሩ በርካታ አርሶ አደሮች መቁሰላቸውን እንዲሁም ቁስለኞች ወደ ህክምና ጣቢያ እንዳይወሰዱ የአገዛዙ ወታደሮች የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ማገዳቸውን መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

14 Nov, 08:14


የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች በምስራቅ ጎጃም በእነማይ ወረዳ በሚገኘው የቅኔ ተማሪዎች መፍለቂያ በመባል የሚታወቀው ታላቁ የዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ፍቅር እስከ መቃብር ሙዚየምን በዚህ መልኩ አውድመውታል።

እነዚህ ሞራልና ስርዓት የለሽ ፀረ አማራ የሆኑ የአገዛዙ ወታደሮች የቅኔ ዩኒቨርስቲ በመባል በሚታወቀው የታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ገዳም ንብረት በሆነው ፍቅር እስከ መቃብር ሙዚየም ላይ የእሳት ውድመት ማድረሳቸውን እንዲሁም ቤት ለቤት እየዞሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ከእጅ ስልክ ጀምሮ ጥሬ ገንዘብ እና ሌሎች ጌጣጌጦችን መዝረፋቸውን በሚመለከት መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ በጎጃም የ8ኛ ክ/ጦር ቃል አቀባይ የሆነው ፋኖ ይበልጣል ጌቴን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ አይዘነጋም።

(ምስል፦ በአገዛዙ ወታደሮች የወደመው የፍቅር እስከ መቃብር ሙዚየም)
***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

13 Nov, 11:36


ሰሜን ወሎ ቃሊም!

አንድ አርሶ አደር ሕይወቱ አልፏል።ህፃናትና አዛውንቶች ጨምሮ ጤፍ አጨዳ ላይ የነበሩ በርካታ አርሶ አደሮች ቆስለዋል።ወደ ሕክምና ጣቢያ እንዳይወሰዱ መከላከያ ሰራዊቱ ከቃሊም ወደ ወልድያ መግቢያ ላይ ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ አግዷል። ቁስለኞችን በምታዩት መልኩ በወሰካ(ቃሬዛ) እና በሰው ታዝለው ወደ ወልድያ እየተወሰዱ ነው።

ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት ቃሊም ላይ ማርፈጃውን የመድፍ እና የቢኤም ድብደባ ሲፈፀም እንደነበር መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።

ወልድያ ከተማ ማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካው ላይ የተጠመደው ከባድ መሣሪያ ነው በንፁኋን ላይ ጥቃት ሲፈፅም ያረፈደው።

ከ50 በላይ የመድፍ እና የቢኤም ቅምቡላ ተወርውሯል።

***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

13 Nov, 07:00


በቃሊም እና በአከባቢው ከባድ የሆነ የመድፍ ድብደባ እየተፈፀመ ነው!

ዛሬ ህዳር 04/2017 ዓ/ም ጧት ከ2:30 ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በቃሊም እና በዙሪያው የመድፍ ድብደባ እየተፈፀመ እንደሚገኝ የመረብ ሚዲያ የወሎ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

በወልድያ ከተማ ማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የተጠመደው መድፍ ቃሊምና አከባቢውን እየደበደበ ሲሆን፡ ጥቃቱ መፈፀም ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከ30 በላይ የሚሆን የመድፍ ቅምቡላ መወርወሩን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል።

ጥቃቱ እየተፈፀመ ያለው በአርሶ አደሮች መኖሪያ ቤት ላይ ነው ሲሉ ለመረብ ሚዲያ የወሎ ዘጋቢዎች የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በጥቃቱ በርካታ መኖሪያ ቤቶች በእሳት እየጋዩ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

(ምስል፦ ከማህበራዊ ሚዲያ)
***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

12 Nov, 17:03


ሰበር ቪዲዮ ከጎንደር!

ሕዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት ቁጣውን ገለፀ!

ቀጥታ ስርጭት ከስፍራው!

https://www.youtube.com/watch?v=dQh9o5elVk0

Mereb Media መረብ ሚዲያ

12 Nov, 16:15


"ዘመነን እርምጃ ወስደንበታል" ብልፅግና ከሁለት ሳምንት በፊት

"ፎቶው ላይ ነው ወይ እርምጃ የወሰዳችሁት" ሕዝቡ😁

***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Nov, 18:29


በምስራቅ ጎጃም ዞን በተደረገ ውጊያ 21 የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 59 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ!

በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ ሉማሜ ከተማ እና በባሶሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ ላይ ዛሬ ህዳር 01/2017 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ እኩለቀን ገደማ በተደረገ ውጊያ 21 የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ በድምሩ 59 የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ሲገደሉ ከ20 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን የአማራ ፋኖ በጎጃም የሀዲስአለምአየሁ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መምህር እንደሰው ታምሩ ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

በባሶሊበን ወረዳ ስር በምትገኘው የጁቤ ከተማ ሰፍረው በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ዛሬ ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ጀምሮ የተከፈተው ጥቃት እስከ እኩለቀን የዘለቀ ሲሆን በዚህም በፀረ አማራ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት መድረሱ ነው የታወቀው።

የጁቤ ከተማ ላይ በተካሄደው ውጊያ 23 የመከላከያ ሰራዊት፣ 21 የሚሊሻ እና አራት የአድማ ብተና እንዲሁም ሦስት የፖሊስ አባላት በድምሩ 51 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ 16ቱ ቁስለኛ መሆናቸውን ነው የክ/ጦር ቃል አቀባይ ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ የገለፀው።

በዚህ ውጊያ ሙትና ቁስለኛ ከሆኑት የአገዛዙ ወታደሮች በተጨማሪ 15 የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችና ከ200 በላይ ተተኳሾች በፋኖ እጅ መግባታቸው ተነግሯል።

በተመሣሣይ በአዋበል ወረዳ ሉማሜ ከተማ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ጀምሮ በተወሰደ እርምጃ ስምንቱ ሲገደሉ፡ ከአምስት በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን ነው ፋኖ መምህር እንደሰው ለጣቢያችን የገለፀው።

የዛሬው ኦፕሬሽን በእኛ እቅድ የተመራና እጅግ ስኬታማ ነበር ሲል ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ የገለፀው ቃል አቀባዩ፡ የጠላት ኃይልን አከርካሪ የሰበርንበትና ወታደራዊ የትጥቅ አቅማችንን ያሟላንበት አውደ ውጊያ ነው ብሏል።

ዝርዝሩን በቪዲዮ ተከታተሉ👉https://www.youtube.com/watch?v=KFnPZ86Lsaw

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Nov, 18:11


ሰበር ዜና!

የጁቤ ከተማ ላይ በተካሄደው ውጊያ 23 የመከላከያ ሰራዊት፣ 21 የሚሊሻ እና አራት የአድማ ብተና እንዲሁም ሦስት የፖሊስ አባላት በድምሩ 51 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ 16ቱ ቁስለኛ መሆናቸውን አማራ ፋኖ በጎጃም የሀዲስ አለም አየሁ ክ/ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መምህር እንደሰው ለመረብ ሚዲያ ገልጿል።

በተመሣሣይ በአዋበል ወረዳ ሉማሜ ከተማ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ጀምሮ በተወሰደ እርምጃ ስምንቱ ሲገደሉ፡ ከአምስት በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን ነው ፋኖ መምህር እንደሰው ለጣቢያችን የገለፀው።

እንሆ ዝርዝሩን በቪዲዮ!
https://www.youtube.com/watch?v=KFnPZ86Lsaw

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Nov, 15:37


ሰበር ዜና!

ብልፅግና ፓርቲን አልደገፉም በሚል የከተማዋ ነዋሪዎችን በጅምላ እንዲታሰሩና እንዲገደሉ ሲያደርጉ ነበር የተባሉት የራያ የቆቦ ከተማ ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ ባልታወቁ አካላት መገደላቸው ተሰማ!

በሰሜን ወሎ ዞን የራያ የቆቦ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው የቆቦ ከተማ ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ደርቤ በለጠ፡ ዛሬ ህዳር 01/2017 ዓ/ም ረፋድ 4 ሰዓት ገደማ ላይ ካልታወቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

አቶ ደርቤ ብልፅግና ፓርቲን አይደግፉም ብለው የጠረጠሯቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ፋኖ ናቸው በሚል ሰበብ በጅምላ እንዲታሰሩና በእስር ቤት ውስጥ እንዳሉም አሰቃቂ ግፍ እንዲፈፀምባቸው ሲያስደርጉ ነበር ብለዋል መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች።

ግለሰቡ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ተደጋጋሚ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸው ነበር የተባለ ሲሆን፡ ነገር ግን ከገዢው ብልፅግና ፓርቲ ጋር ወግነው በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙት ግፍና በደል በመቀጠሉ ዛሬ ህዳር 01/2017 ዓ/ም ረፋድ 4 ሰዓት ገደማ ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ነው የታወቀው።

በብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊው ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ በከተማዋ ወጣቶች በጅምላ ታፍሰው መታሰራቸውንም ለጣቢያችን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

አቶ ደርቤ በለጠ ባልታወቁ አካላት መገደላቸውን ተከትሎ የከተማና የወረዳ አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የዞኑ አመራሮች የተሰማቸው ሀዘን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ማስፈራቸውን መረብ ሚዲያ ለመመልከት ችሏል።

ከነዚህ መካከል የዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ሙስጦፋ "ወንድሜን አብሮ አደጌን "ለአማራ ህዝብ እንታገላለን  በሚሉ የህዝብን መሪ በሚገሉ ጽንፈኞች ተነጠቅን" የሚል መልዕክት ያሰፈሩ ሲሆን በተመሣሣይ የቆቦ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ይርጋ ወዳጆ በበኩላቸው ሀዘናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

ዛሬ ለተገደሉት አቶ ደርቤ በለጠ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ሀዘናቸውን የገለፁት የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ሙስጦፋ ሙሀመድ፡ እሳቸውም በተመሣሣይ ያለፈው ዓመት ግምቦት 21 ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ በወልድያ ከተማ ልዩ ስሙ ጎማጣ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንዳሉ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሞባቸው እንደነበር የአሁኑ የመረብ ሚዲያ መስራቾችና የቀድሞው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ጋዜጠኞች በዕለቱ መዘገባቸው አይዘነጋም።

***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Nov, 13:49


የአገዛዙ ወታደሮች በመካነሰላም ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ደፍረፋራ ቀበሌ ላይ 14 ጊዜ በፈፀሙ የሞርተር ጥቃት በንፁኋን እና በሀይማኖት ተቋማት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተነገረ!

የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች በደቡብ ወሎ ዞን ከመካነሰላም ከተማ አስተዳደር በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ 012 ደፍረፋራ ተብሎ በሚጠራ ገጠራማ ቀበሌ ላይ ትናንት ጥቅምት 30/2017 ዓ/ም በፈፀሙት 14 ጊዜ የሞርተር ጥቃት በቀበሌዋ ነዋሪዎች እና በደፍረፋራ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በቤት እንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተጎጂዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

በጥቃቱ እስካሁን የታወቀ አንድ አርሶ አደር ህይወቱ ያለፈ ሲሆን አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ በርካታ ንፁኋኖች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ነው ያሉት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአከባቢው ነዋሪዎች።

የአገዛዙ ወታደሮች በንፁኋኖች ላይ የሞርተር ጥቃቱን የፈፀሙት በዛው በአከባቢው ልዩ ስማቸው መቅደላ እና ሰኞ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ከፋኖ ጋር ባደረጉት ውጊያ ከባድ የሆነ የሰውና የንብረት ኪሳራ የደረሰባቸው መሆኑን ተከትሎ ነው ብለዋል ከመረብ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአከባቢው ነዋሪዎች።

ትናንት ከንጋት ጀመሮ እስከ አመሻሹ ከመካነ ሰላም ከተማ በግምት በ10 km ርቀት ገደማ ላይ በሚገኙት መቅደላና ሰኞ ተብለው በሚጠሩት ቀበሌዎች በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ መብረቅ ክ/ጦር ስር የክፍለ ጦሩ ተወርዋሪ ሻለቃዎችና የመካነሰላም አባይ ሸለቆ ብርጌድ ፋኖዎች በጋራ በመሆን በአገዛዙ ወታደር ላይ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ ከፍተው መዋላቸው ታውቋል።

በዚህ ውጊያ ከፋኖ አንድ አባል ብቻ ሲቆስል ከአገዛዙ ወታደሮች ግን ከ15 በላይ የሚሆኑት ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል የተባለ ሲሆን፡ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ ወታደራዊ ሬሽንን ጨምሮ ሌሎች የመሣሪያዎችም በፋኖ መማረካቸውን መረብ ሚዲያ ከክፍለ ጦሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጋራ በመሆን ካምፕ መስርተው ለበርካታ ወራት ሲኖሩባቸው የነበሩት መቅደላ እና ሰኞ ቀበሌዎች በአሁን ሰዓት በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባታቸው ታውቋል።

የአገዛዙ ወታደሮች በወረዳው መቅደላ እና ሰኞ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ የደረሰባቸውን ሽንፈት ተከትሎ ምንም አይነት የፋኖ ኃይሎች በለሉበት ደፍረፋራ ቀብሌ ነዋሪዎች ላይ ከ14 ጊዜ የሞርተር ጥቃት ፈፅመዋል ሲሉ ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት ተጎጂዎቹ፡ በዚህም ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበረ አንድ አርሶ አደር ሲገደል፡ አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ በርካታ የቀበሌዋ ነዋሪዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጥቃቱ የደፍረፋራ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዳት የደረሰባት ሲሆን፡ በርካታ የቤት እንስሳቶችም ተገድለዋል ነው የተባለው።

የአገዛዙ ወታደሮች በደፍረፋራ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ጥቃቱን ሲፈፅሙ የነበሩት ልዩ ስሙ እናሪት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ባጠመዱት ሞርተር መሆኑንም ነው ጣቢያችን ለማረጋገጥ የቻለው።

ስለ ጥቃቱ በቪዲዮ መመልከት ከፈለጉ ሊንኩን ይጫኑ👉
https://www.youtube.com/watch?v=G3Mb1flwBzQ

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Nov, 12:10


ሰበር ዜና ከመካነሰላም!

ትንቅንቁ ቀጥሏል/ ወታደሩ ሽሽት ላይ ነው!

የፋኖን ክንድ መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ወታደር 14 ጊዜ የሞርተር ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።

በጥቃቱ አንድ አርሶ አደር ሲገደል ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው የደፍረፋራ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጉዳት እንደደረሰባት መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የአገዛዙ ወታደር በንፁኋኖች ላይ  ይህን ጥቃት የፈፀመው በርካታ አባሎቹ በፋኖ ስለተገደሉበትና ተሽከርካሪዎቹን ጨምሮ የጦር መሣሪያዎቹ ስለተማረኩበት ነው ተብሏል።

በመካነሰላም ከተማ ዙሪያ በሚገኙ አከባቢዎች እየተደረገ ያለው ትንቅንቅ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፡ የአገዛዙ ወታደሮችም ህይወታቸውን ለማትረፍ ሽሽት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

እንሆ ሙሉ ዝርዝሩን ያድምጡ👉
https://www.youtube.com/watch?v=G3Mb1flwBzQ

Mereb Media መረብ ሚዲያ

10 Nov, 04:14


እንደምን አደራችሁ!

"ሀገራችን ጎንደር  ደምቢያና አርማጭሆ፡
ቦታውም ያስፈራል እንኳን ጥይት ጮሆ"

***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

09 Nov, 19:01


ዶክተር አቡበክር በስራ ላይ

ሙሉ ቪዲዮውን ይከታተሉ!
https://www.youtube.com/watch?v=cAfp-sK_G_E

Mereb Media መረብ ሚዲያ

09 Nov, 15:26


መረብ ሚዲያ ዋግኽምራ ሰቆጣ ላይ!

"አባ መረብ ኃይሌ፡ ኃይሌ አባ ይባስ፣
አጨደው ከመረው ወቃው እንደገብስ"

የሕዝብ ድምፅ የሆነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ዛሬ ምሽት ከ2 ሰዓት ጀምሮ  በመረጃ ቲቪ በሚኖረው ፕሮግራም የኃይሉ ከበደ ልጆች ጋር ያደረገውን ሙሉ ቆይታ ለእናንተ ለተመልካቾቹ ያቀርባል።

በዛሬው ዝግጅታችን በምዕራፍ የተከፋፈሉ የተለመዱ አራት ፕሮግራሞቻችንን እናቀርባለን።እነርሱም፦

1ኛ፦ ከትግል ሜዳ (ከፋኖ አመራሮችና አባላት ጋር የተደረገ ቆይታ)

2ኛ፦ ሕዝቡ ምን ይላል? (በትግሉ ዙሪያ የሕዝቡ ሀሳብና አስተያየት፣ የሕዝቡ ጥያቄዎችና በአገዛዙ የደረሰበት ግፍ ይቀርብበታል)

3ኛ፦ ምርኮኛ የመራቸው ምርኮኞች (በፋኖ የተማረኩ የአገዛዙ ወታደሮች ጋር የሚደረግ ቆይታ)

4ኛ፦ ከጀግኖች አምባ (ስለ አማራ ሕዝብ ነፃነት ሲሉ በክብር የተሰው ጀግኖች ታሪክ፣ አስደናቂ ጀብዶች እና ሌሎች የግምባር ገጠመኞች በትረካ መልክ ይቀርቡበታል)

እንዳያመልጣችሁ!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

09 Nov, 14:07


ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ከላስታ ላሊበላ ግምባር!

ዶ/ር አቡበክር ሰኢድ ከጓዶቹ ጋር በስራ ላይ!

https://www.youtube.com/watch?v=cAfp-sK_G_E

Mereb Media መረብ ሚዲያ

09 Nov, 07:37


እንደምን አረፈዳችሁ!

ከወሎ ሰማይ ስር!

የአማራ ፋኖ በወሎ የአሳምነው ኮር አዛዥ አርበኛ ወንድሙ ማሩ እና በኮሩ ስር የተከዜ ክ/ጦር አዛዡ ኮማንዶ ዘላለም።
***
የግምባር ቪዲዮዎችን ብቻ ስትፈችጉ አዲሱን የመረብ ዩቲዩብ ቻናል ይወዳጁ https://www.youtube.com/@MerebEntertainment-u9w

Mereb Media መረብ ሚዲያ

09 Nov, 06:28


https://www.youtube.com/watch?v=bhTF3tDj3aY&t=2s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Nov, 19:09


ቀጥታ ከቦረና ገነቴ!

የወግዲው ምሽግ ሲደረመስ የነበረው ሁኔታ!

ዝምተኛው የጦር ጠበብት ሳጅን አደም አሊ የፈፀመው አስደማሚ ገድል!

https://www.youtube.com/watch?v=Im2N0Dv9u24&t=230s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Nov, 15:29


"ማን ያመጣልኛል?
ከሳይንት ነጭ ጤፍ ከቦረና ስንዴ፡
አሰሱን ገሰሱን አልበላ አለ ሆዴ" ነው ስንኙ ሲቋጠር።

በዛሬው ዝግጅታችን ከጀግኖቹ እና ከቆንጆዎቹ ምድር ከወሎ ቤተ አማራ ሰማይ ስር በምዕራቡ በኩል መሀል ሳይንት ወረዳ አቅንተን በወረዳው ውስጥ ከአንዲት አነስተኛ መንደር ስለወጣውና ሞት አይፈሬው ሳይንቴ ተብሎ ስለሚጠራው እንቁ ሰማዕት፡ ማንነትና ጀግንነት እናወጋችኋለን።

በቅፅል ስሙ ቆቁ ተብሎ የሚጠራው የዛሬው ባለታሪካችን እንቁ ጀግና፡ ከጉልበቱ በርከክ፡ ከሰደፉ ቀና አድርጎ የተኮሰ ጊዜ የጠላት ኃይል ሰማይ ይደፋበታ፣ የሚይዘው የሚጨብጠው ይጠፋዋል፣ የሚሸሸግበት ምጥ፣ የሚጠለልበት ስምጥ ያጣል ይባላል። ጀግናው ጥይት አያባክንም።አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት ነው የተኩስ መርሁ። በውጊያ ወቅት እሱ የገደላቸውን የጠላት ኃይል ብዛት ለማወቅ የያዘውን ካዝና መቁጠር በቂ ነው ይላሉ አብረውት ከምሽግ ውለው ሲያድሩ የነበሩ ጓዶቹ።

ይህ የኛ ዘመን አብሪ ኮከብ፣ ይህ የኛ ትውልድ ፋኖስ የክብር ሞት ሸማ ከመጎናፀፉ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በተደጋጋሚ በተተኮሰበት ጥይት በተመታ አካሉ የሚፈሰውን ደም በአንድ እጁ ለማስቆም እየታገለ፡ በሌላኛው እጁ በያዘው ክላሹ ደግሞ ከምሽግ ምሽግ እየተወናጨፈ የጥይት ናዳ በጥላቶቹ ግምባር ላይ ሲያርከፈክፍ ነበር።

ይህ የዘመኔ ጀግና የገበሬ ጦር እየመራ ከ400 በላይ የጠላት ኃይል በተሰለፈበት በአንድ ምድርን ቃጤ ባደረገ ውጊያ መሀል እየተዋጋና እያዋጋ ባለበት መሃል እንዴት የክብር ሞትን እንደሞተ በሰፊው እናጫውታችኋለን።

አብራችሁን ቆዩ
****

"ሳይንት አፋፉ ላይ የተሰራ ቤት
ግድግዳው ጠብመንጃ ክዳኑ ጥይት" ሲባል እንደምንሰማው፡ የሳይንት ሰው ቤቱም፣ የቤቱ ክዳኑም ጥይት ስለሆነ የከፋው ቀን፡ ፍትህ ተጓደለ ብሎ ያሰበ ቀን ከቤቱ ግድግዳ የደበቀውን መሳሪያ ፈልፍሎ መዥረጥ ያደርግና ዱር ቤቴ ይላል።
የዛሬው ባለታሪካችንም የነዚህ ዘር ነው።

ፋኖ ሀብታሙ ደረበው ይባላል። ወይም በቅፅል ስሙ ቆቁ እያሉ ይጠሩታል የትግል ጓዶቹ።

የትግል ጓዶቹና አብሮ አደጎቹ ቆቁ የሚል ቅፅል ስም ያወጡለት አንድ ጥይት አልሞ ተኩሶ ጎን ለጎን እየበረሩ የነበሩ ሁለት ቆቆችን አንገት በመበጠሱ የተነሳ ነው።

"አይኑ መነጽር ጠብመንጃው ሆዳም
ነጭ ሰው ገዳይ ደባልቄ ካዳም"
የተባለለት የቦረና ሳይንት አውራጃ ስመጥር አርበኛ የነበረ የማይጨው ዘማች ጀግናን ታሪክ የደገመው ፋኖ ሀብታሙ ደርበው፡ "የዚህ ልጅ አይንማ አጉሊ መነጽር ነው" እስኪባልለት ድረስ በተደጋጋሚ አልሞ ተኳሽነቱን አስመስክሯል::

ወፍ በሰማይ እየበረረች አስቀራታለሁ ብሎ ከተኮሰ በብርሀን ፍጥነት ያስቀራታል ሲሉ የአይን እማኞች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

ይህን ያህል አልሞ ተኳሽ እና አንገት በጣሽ የሆነው የት እና እንዴት ተምሮ ነው ልትሉ ትችላላችሁ ነገር ግን ቦታውና አገሩ መቼም መሀል ሳይንት መሆኑን አትርሱ።

ይህ አካባቢ ወንድ ልጅ ሲወለድ ተኳሽ እና አራሽ አንደፋራሽ እንዲሆን በማለት ተፈጥሮም የምታሽቃሽጥበት አካባቢ ነው::

ከመግቢያችን ላይ:-
"ማን ያመጣልኛል?
ከሳይንት ነጭ ጤፍ ከቦረና ስንዴ
አሰሱን ገሰሱን አልበላ አለ ሆዴ"
የሚለውን ስንኝ መጥቀሳችን ያለ ነገር አይደለም።
ቀጠናው የጤፍ እና ስንዴ ምድር እንድሁም የአልሞ ተኳሾች እርስተ ጉልት ነው።

"እወቀረዋለሁ ጥርሴን በጥይት፡
የጀግና ልጅ ሀገር አማራ ሳይንት" ሲሉ ያንጎራጉራሉ የአከባቢው ኮበሌዎች።

ሀገር ምድሩ ጀግና እና እህል ማብቀል ያውቃል። ወትሮውንስ የአማራ እናት መች ነጥፋ ታውቅና?

የክብር መስዋዕቱ ፋኖ ሀብታሙ ደርበው ወይም በቅፅል ስሙ ቆቁ ተወልዶ ያደገው ከጀግኖች እና ቆንጆዎቹ ምድር ከወሎ ቤተ አማራ ሰማይ ስር በምዕራቡ በኩል መሀል ሳይንት ወረዳ ውስጥ በአንዲት አነስተኛ መንደር ነው።

ይህ ውሽንፍር ጀግና የልጅ ሽፈራው ገርባው ምትክ ነው በሚል የሀገር ሽማግሌዎች ሲናገሩ ይደመጣሉ።

"ሶማ ጎራ ሆኖ ሽፈራው ቢያገሳ
ወታደሩ ሁላ ቁና ቁና ፈሳ"
የተባለለት ልጅ ሽፈራው ገርባው ገና በ17 አመቱ በላይ ዘለቀን ተከትሎ ጫካ የገባ የልጅ አርበኛ ሲሆን፡ የጋሜ ጦር የሚባለውን የታዳጊዎች ጦር እየመራ የአንጋቾች አለቃ ሆኖ ከሶማ እስከ ጉበያ በርሀ ደማቅ ታሪክ ሰርቶ በማለፉ የስጋ ወንድሙ በላይ ዘለቀ ጋር በታሪክ ይወሳል።

አባ ቀስቶ እጅጉ ዘለቀም የዚህ ወርቃማ ትውልድ አካል ሲሆን እነ በላይ ዘለቀና ሽፈራው ገርባው ጋር ጣልያንን መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ነበር።

"እጅጉ ባይቆስል ሽፈራው ባይሞት
ማን ይወጣው ነበር የሶማን ዳገት"
ሲባል አልሰማችሁምን?

ልጅ ሽፈራው ገርባው "ሞት አይፈሬው" የሚል ቅጽል ስም እንደነበረውም የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ::

ሞት አይፈሬው ፋኖ ሀብታሙ ደርበው፡ ልጅ ሽፈራው ገርባውን የመሰለ የልጅ አርበኛን ነው ሲሉ የአምባው ነዋሪዎችና የአከባቢው ታሪክ አዋቂዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ያመሳጠሩትም ከዚህ የተነሳ ነው።

"ሰነፍ አረፍቆ እንቅልፉን ይጥገበው
የነቃው ይበቃል ቃሉን ያነገበው"
እንዲል ባለቅኔው፡ ፋኖ ሀብታሙ ገና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳለ ቀድሞ ነቅቶ ብልጽግናን በመቃወም ነበር ከመንግስት ጋር ፍጥጫውን የጀመረው።

በብልጽግና ዘመን የመጀመሪያው የሆነው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ ሽር ጉድ ሲባል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ የመራጮች ቅስቀሳ ፕሮግራም ባካሄደበት ወቅት ይህ ጀግና የፓርቲው መለያ ምልክት የሆነው የእጅ ሰዓት የታተመበትን ወረቀት ኮፍያው ላይ ሰክቶ በደቡብ ወሎ ዞን መሀል ሳይንት ወረዳ ቆተት ቀበሌ ውስጥ ወደምትገኘው ማክሰኝት ገበያ በመሄድ ብልጽግና ፀረ አማራ ስለሆነ እንዳትመርጡ በማለት መቀስቀስ ጀመረ ሲሉ የዚህን ጀግና ድፍረት እና ንቃት አብሮ አደጎቹ ያወጋሉ።

ለተከታታይ ማክሰኞዎች እሱ ከገበያ አይጠፋም፡ ኮፍያው ላይ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን የምርጫ ምልክት የያዘች ነጭ ወረቀት ሰክቶ ብልፅግና ፓርቲ እንዳይመረጥ ገበያተኛውን በየሳምንቱ ሲቀሰቅስ የነበረ ጀግና መሆኑን የሚያውቁት ይናገራሉ።

ይህንን የተመለከተ አንድ የፓሊስ አባል፡ ፋኖ ሀብታሙን አስቆመውና "በሕግ ትፈለጋለህ" በማለት ሊይዘው ይሞክራል፡ በዚህ ጊዜ ወጣቱ ፋኖ ሀብታሙ "ማን ማንን ይይዛል? አንተ ፈሳም" ብሎ ፖሊሱን በአንድ ቡጢ ከዘረረው በኋላ የፖሊስ መለዮ ኮፍያውን መንጥቆት እልም አለ።  የፖሊስ አባሉ ያለ ኮፍያ ቀረ።

የፖሊስ ከባላቱ ከዚያን ቀን ጀምሮ ይህን ጀግና  ማሳደድ ጀመሩ። ደፍሮናል ብለው በጥብቅ ይፈልጉትና ያፈላልጉት ጀመር።

ይህ ጀግና ለመንግስት ስጋት ሆነ። ብልፅግና ፓርቲን ከወጣቱ ልብ ፋቀው። የፓርቲው የምርጫ ምልክት የሆነችው አምፓል ተቃጠለች። ወጣቱ ብልፅግናን ላለመምረጥ ወሰነ። ምንም እንኳን ገዢው ፓርቲ በምርጫው ማግስት ኮሮጆ ቢገለብጥም፡ ጀግናው ሀብታሙ ግን ይህ ፀረ አማራ የሆነ የአገዛዝ ስርዓት እንዳያንሰራራና በአጭር እንዲቀር ለማድረግ ገና ያኔ በጧቱ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።

ይህ ወጣት በሰሜኑ ጦርነትም ከአከባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን የምዕራብ ወሎ ቀጠና ለሕወሓት ወራሪዎች የእሳት እረመጥ እንዲሆንባቸው አድርጓል።

ከሰሜኑ ጦርነት ማግስት ከመሀል ሳይንት ወረዳ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት የተወጣጣ ሁለት ጋንታ ኃይል ዋጩ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ የፋኖ ሀብታሙ ደርበውን ከበውት ነበር።

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Nov, 15:29


ፋኖ ሀብታሙ ግን የዋዛ አይደለም።ያን ልክ እንደ እሳት ቶን የሚጋረፈውን ክንዱን አቀመሳቸው። ከጉልበቱ በርከክ ብሎ፡ እንደጣት ቀለበት ከእጁ የማይለየውን ክላሹን ያንደቀድቀው ጀመር።

የፖሊስና ሚሊሻ አባላቱ ብርክ ውስጥ ገቡ።አልቻሉም። የገጠሙት ከአንድ ፋኖ ሀብታሙ ጋር ብቻ ሳይሆን አምስት ሺ ሰራዊት ጋር መስሎ እስኪታያቸው ድረስ ከላይ ከታች እየተወረወረ አጣደፋቸው።

መንጋው ተሽመደመደ። በዚህ መሀል የፖሊስና ሚሊሻ አባላቱ የተከፈተባቸውን አፀፋዊ ምት መቋቋም ባለመቻላቸው አንድ ሰላማዊ ሰው ገድለው፡ የራሳቸውን ሙትና ቁስለኛ መሸከም እስኪከብዳቸው ድረስ ከዋጩ ቀበሌ ወደ ቆተት እግሬ አውጪኝ ፈረጠጡ።

በወጣቱ ጀግንነት የአምባው ሰው ተደመመ። እናትህ መንታ ትውለድ ብለው አዛውንቶች ጭምር መረቁት። ይህንን ጀግንነቱን ያስተዋሉ የሃገሩ ኮበሌዎች
"የሳይንቶች ዘር የዋጩ ጥሪት፡
ልቡ ድፍን ነው እንደ መድሀኒት"
ሲሉ ስንኝ ቋጠሩለት።

ፀረ አማራው የብልፅግና ፓርቲ በሕግ ማስከበር ስም ሕዝቡን ለመጨፍጨፍ አለኝ የሚለውን የጦር መሣሪያ ይዞ ይፋዊ ጦርነት ሊጀምር በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ወራቶች በቀሩት ሰሞን፡ ይህ ትንታግ ውሽንፍር ጀግና ለአንድ ጉዳይ ወደ መካነሰላም ከተማ አከባቢ ባቀናበት ወቅት የወረዳው የፀጥታ ኃይሎች ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት የቡድን መሣሪያ ጭምር አጥምደው በድንገት አፈኑት። ወጣቱ በጠላት እጅ ወድቆም እየፎከርና እየሸለለ ነበር። ወደ እስር ቤት ተወሰደ። ጥፋተኛ ተብሎ ተፈረደበት።

የብልፅግና ቡድን በህግ ማስከበር ስም የአማራ ተወላጅ የሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎችን በአጭር ለመቅጨት፣ ነፍሰጡር ሴቶችና እናቶችን ለመቅጠፍ፣ አዛውንቶችን ለመግደል ብሎም አማራን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያቀደውን የጦርነት ፕሮጀክት በይፋ ጀመረ።

የአማራ ሕዝብም የታወጀበትን መንግስት መር ጦርነት ለመመከት በዱር በገደሉ ይዋደቅ ጀመር።

በዚህ ሁኔታ በአርበኛ አብነው ታደሰ የሚመራው የመካነሰላም አባይ ሸለቆ ፋኖ በ2015 ዓ/ም ክረምት ላይ መካነሰላም ከተማ የሚገኘው የምዕራብ ወረዳዎች ማረሚያ ቤትን ሰብሮ በወቅታዊ ጉዳይ የታሰሩትን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞችን ብቻ መርጦ አስፈታ።

በፋኖ ተጋድሎ ከእስር ከተፈቱት መካከል ያ የዋጮው ውሽንፍር፡ ያ ከሰማይ ወፍ ያረግፋል የሚባልለት አልሞ ተኳሹ ፋኖ ሀብታሙ ደርበው አንዱ ነበር።

ፋኖ ሀብታሙ ከእስር ከተፈታ በኋላ ቤተሰቦቹን ሊጠይቅ ሄደ።ከቤተሰቦቹ ጋር ሁለትና ሦስት ቀናት ከተጫወተ በኋላ ክላሹን መዞ ብድግ አለ።

በሁኔታው ግራ የተጋቡ ቤተሰቦቹም "የት ልትሄድ ነው?" ሲሉ ጥያቄ አነሱ። እሱም "ወደ መካነሰላም ነው። ነፃ ያወጡኝ ወንድሞቼ ጋር ሆኜ እኔም አማራን ነፃ አወጣለሁኝ" የሚል አጭር ቃል ሰቷቸው አንድግራ ክላሹን እያወዛወዘ ደንቆሮ ወንዝን ተሻግሮ በመጓዝ የመካነሰላም ብርጌድን ተቀላቀለ።

የፋኖ አዛዦች ቆቁ ዝነኛ ጀግና እና አልሞ ተኳሽ መሆኑን ስለሚያውቁ ወዲያው ጋንታ መሪ አደረጉት።

ከጠላት የብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ ወታደሮች ጋር በተደረገ ተደጋጋሚ ውጊያ ላይ፡ ፋኖ ሀብታሙ ወይም በቅፅል ስሙ ቆቁ የፊት መስመር አጥቂ ሆኖ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ፡ አጃኢብ የሚያስብሉ በርካታ ጀብዶችን ፈፀመ።

ቆቁ በተሰለፈበት አውደውጊያ ሁሌም ድል አለ።ምክኒያቱም ቆቁ በስፍራው ስላለ።

በቆቁ ኢላማ ስንት የጠላት ኃይል እንደተፈጀ ለማወቅ ቆቁ ስንት ጋዝና ጥይት ይዞ ገባ፡ ይዞት ከገባው ጥይትስ ምን ያህሉ ብቻ ቀረ የሚለውን ብቻ መቁጠር ነው ይላሉ አብረውት ከምሽግ ውለው የሚያድሩ የትግል ጓዶቹ።

ቆቁ ጥይት አያባክንም። አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት ነው የሱ የተኩስ መርህ።አንድ ይተኩሳል አንድ ይጥላል።አንዳንዴም በለስ ሲቀናው በአንድ ጥይት ሁለት ሶስቱን ጠላት አነባብሮ ያጋድመዋል።ከዚህ ውጪ የፋኖ ሀብታሙ ጥይት መሬት አታርፍም።በጠላቶቹ ግምባር ላይ እንጂ።

በዚህ ጀግንነቱ የመካነሰላም ብርጌድ ዋና አዛዡ አርበኛ አብነው ታደሰ ስለ ቆቁ አውርቶ አይጠግብም። እንደ ልጁ ነው የሚሳሳለት።

መስከረም 30/2016 ዓ/ም በደቡብ ወሎ ዞን  መካነሰላም ዙሪያ ገጠር ወረዳ ውስጥ አደሬ ቆቦ የሚባል ቦታ ላይ እነ ቆቁ ከጥምር ጦሩ ጋር ገጠሙ::

ቆቁ የገበሬውን ጦር እየመራ ዋናውን መንገድ ይዞ ወደ መካነሰላም ከተማ መገስገስ ጀመረ።

ሌሎች የብርጌዱ ፋኖዎችም ከእሱ ቡድን በስተግራ ባለ ግምባር ወደ ከተማ በመጠጋት ላይ ነበሩ።

ፋኖ ቆቁ በተሰለፈበት አደሬ ቆቦ ላይ ምድር ቃጤ ሆነች።

ቆቁ የሚመራቸው አባት አርበኞች፡ መሪያቸው በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ከምሽግ ምሽግ እየተራመዱ በጠላይ ላይ የእሳት ዶፍ ያዘንቡ ጀመር።

እነዚህ አርሶ አደሮች ከምሽግ ምሽግ ሲወረወሩ ላየ ሰው፡ የማርሻል አርትን ከጦር ሳይንስ ጋር አዋህደው ለበርካታ ዓመታት ስልጠና የወሰዱ ልዩ ኮማንዶዎች ናቸው እንጂ መቼም እነዛ እጃቸው ከሞፈርና ከቀንበር ተላቆ የማያውቀው አፈር ገፊ አርሶ አደሮች ናቸው አይልም።

ተርብ ናቸው። አንዳንዴ ሳንጃ ነቅለው ጠላት ካለበት ምሽግ ተወርውረው ይገቡና በሳንጃ ይሞሻለቃሉ። ሞትን አይፈሩም።ምክኒያቱም መሪያቸው ያ ሞት አይፈሬው የሚባለው የልጅ ሽፈራው ገርባው ፈለግ ተከታይ የሆነው ፋኖ ሀብታሙ ነውና።

በውጊያው በዚህ ግምባር ብቻ ከ80 በላይ የሚሆን የአገዛዙ ወታደር የአሞራ ስንቅ ሆነ።

በርካታ የሆኑ ቁስለኛ የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላትም በየምሽጉ ወድቀው ድረሱልኝ የሚል የሲቃ ድምፅ ያሰሙ ጀመር።

ማዘዣቸውን ደሴ ያደረጉት የጠላት ጦር አዛዦችም ተጨማሪ ኃይል በላይ በላይ ይልካሉ።

የፋኖን ጦር እያዋጋ ያለው ፋኖ ቆቁ "አይዟችሁ፣ አማራ አይሸሽም፡ አይዟችሁ ይሄን ፈሳም ሰራዊት እንበትነዋለን" እያለ አብረውት ያሉትን ተዋጊዎች ያጀግናል።

ፋኖ ቆቁ ውጊያውን ከመምራት ጎን ለጎን እሱም ደጀን ቦታ ይዞ ይተኩሳል።እንደለመደው በያዘው ክላሽ እነዛን የአገዛዙ ወታደሮችን እሳት መሀል ጥዶ ያማስላቸው ገባ። በዚህ ውጊያ ፋኖ ቆቁ ሦስት ካዝና ጥይት ጭጭ አድርጎ ጨርሷል።

የቆቁ ጥይት መሬት ጠብ አትልም የጠላት ግምባር ላይ እንጂ። አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት ነው መርሁ። አንድ ካዝና 30 ፍሬ ይይዛል። ቆቁ ሦስት ካዝና ጨርሷል። የተመታውን የጠላት ኃይል ብዛት መደመሩን ለአንባቢዎቻችን እንተወው።

የጠላት ኃይል በየደቂቃዎቹ ልዩነት ደሴ ለሚገኘው ማዕከል በመገናኛ ራዲዮን እየደወለ አለቅን፣ አለቅን እያለ ሪፖርት ያደርጋል። አዛዦቻቸውም ከባባድ መሣሪያ እያስታጠቁ ተጨማሪ ኃይል ይልኩላቸዋል። ግን ጠብ ያለ ውጤት የለም።ድል እንደ ሰማይ እራቃቸው።

የጠላት ኃይል አንድ ነገር አሰበ።የገበሬ ጦር በዚህ ልክ የከፋብን መሪው ኃይለኛ በመሆኑ ነው በሚል ያለ የለለ ኃይሉን ሰብስቦ የተኩስ አቅጣጫውን ቆቁ ወደ ሚገኝበት ምሽግ መተኮስ ጀመረ።

ፋኖ ቆቁ ቀደም ብሎ በተተኮሰ ጥይት ቆስሎ ነበር። የሚደማውን ደም ለማስቆም በአንድ እጁ አፍኖ ይዞ በሌላኛው እጁ በያዘው ክላሽ ያራውጠው ጀመር።

የጠላት ተኩስ እሱ ወዳለበት አቅጣጫ አረበበ። ፋኖ ቆቁ በድጋሚ የቆሰለ ቢሆንም ነገር ግን ከመጤፍ አልቆጠረውም። ደሙን እያዘራ እስከ መጨረሻዋ ህቅታው አንገት ላንገት ተናነቀ።

በመጨረሻም ከጠላት የተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ቆቁ ካለበት ምሽግ በቅርብ ርቀት ወደቀ። ፍንጥርጣሪው ክፉኛ ጎዳው።

ውጊያው አልቆመም የገበሬው ጦርም ከምሽግ ምሽግ እየተወረወረ የጠላት ኃይል ላይ ከባድ የጥቃት ናዳ ያዘንባል።

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Nov, 15:29


በስተመጨረሻም ፋኖ ቆቁ በሰውነቱ ላይ ባረፈበት ተደጋጋሚ ጥይት መንቀሳቀ አቃተው። ብዙ ደም ፈሰሰው። በዚህ ሁኔታ እያለ "አይዟችሁ፣ አማራ አይሸሽም፣ አማራ አያፈገፍግም፣ አይዟችሁ!" ይል ነበር በተደጋጋሚ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ የክብር ሞትን ሸማ ተቀዳጀ።

ይህ የኛ ትውልድ አብሪ ኮከብ፣ ይህ የዘመናችን ልጅ ሽፈራው ገርባው፣ ይህ የነፃነት ፋና ወጊ እስከ እለተሞቱ፣ እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ለአማራ ህዝብ ታምኗል። በመጨረሻም "አማራ አይሸሽም፣ አማራ አይሸነፍም" የምትለዋን ቃል ደጋግሞ በመናገር መስዋዕትነትን ተቀብሏል።

አዎ።አማራ አይሸነፍም።
አዎ።አማራ አይሸሽም።

ምክኒያቱም ለነፃነቱ የተገበረለትን ዋጋ ያውቃል እና።

ስለተከፈለለት የደም ዋጋ አይደለም ሕዝቡ ዛፍ ቅጠሉ፣ ተራራ ገደሉ፣ ጋራ ሸንተረሩ በሚገባ ያውቃሉ።

አዎ።አማራ አይሸነፍም።
አዎ።አማራ አይሸሽም።

የጀግናውን ገድል በቪዲዮ ለመከታተል ይሄን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 👉
https://www.youtube.com/watch?v=7CAGzhL9pI4

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Nov, 13:45


https://www.youtube.com/watch?v=bhTF3tDj3aY

Mereb Media መረብ ሚዲያ

08 Nov, 07:51


https://www.youtube.com/watch?v=u8aeiDuEhtY&t=309s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 18:31


ጀግና እናስተዋውቃችሁ!

ጠቋር ደባልቄ ይባላል።

አብራራው ተኳሹ አርበኛ ጠቋር ደባልቄ፣ ከትናንት እስከ ዛሬ የምሽጉ ጌታ እንደሆነ አለ። በፀረ አማራው የአገዛዝ ስርዓት ስለ ሚገደሉ ህፃናት፣ ስለሚደፈሩ ልጃገረዶች፣ ስለሚገደሉ እናቶችና አዛውንቶች፣ በድሮን ስለሚጨፈጨፉ ታዳጊ ተማሪዎችና በከባድ መሣሪያ ስለሚወድሙ የሀይማኖት ተቋማት ሲል ጣቶቹ ከሱኪ ጥይቱ ሳይነቀሉ ዛሬም የምሽጉ ንጉስ፣ አሁንም የምሽጉ ጌታ ነው።

"እልም ካለው ጫካ እልም ካለው ዱር፡
ሲነጋገር ያድራል ከመውዜሩ ጋር" የሚለው ስንኝ ለሱና ለጋዶቹ  የተቋጠረ ነው።

ይህ ልበ ሙሉ ጀግና የእስልምና እምነት ተከታይ ነው። ምድር ቃጤ በሆነበት ውጊያ መሀል ቢሆንም ሰዓቱ ከደረሰ የዝሁር፣ የፈጅር፣ የአሱር፣ የኢሻና የመግሪብ ስግደት ዝንፍ አይልበትም። አማራን ልበ ሙሉ አድርጎ የፈጠረ አላህ ምስጋና ይገባዋል ነው የእሱ የዘውትር ንግግሩ።

ከምሽግ ምሽግ ሲወረወር ያየው ሰው ይህ የሰው ፍጡር ብቻ ሳይሆን የአዕዋፍ ዝርያም አለበት ሊል ይችላል።በዚህ ዘንካታ ቁመቱ ሲምዘገዘግ ከንፋስ ይቀድማል። ሱኪውን አቀባብሎ በርከክ ካለ የጠላቱን አናት ሳይበሳ አይነሳም።እሱንም በአንድ ጥይት ብቻ።

የሕወሓት ወራሪዎች በአማራ ሕዝብ ላይ በይፋ የመጀመሪያዋን ጥይት ካጮሁበት ዕለት ጀምሮ  እስከ አሁኑ ኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ቡድን ወረራ ድረስ እጁ ከክላሹ ምላጭ፡ አናቱ ከምሽግ ድንጋይ ትራስ ተለይቶ አያውቅም። ገና ለአማራ ሕዝብ የነፃነት ፀሀይ ፍንትው ብላ እስክትወጣ ድረስም ዛሬም ዱር ቤቴ እንዳለ ነው።

በሁለተኛው ዙር የሰሜኑ ጦርነት ወቅት በውጊያ መሃል ተቆርጦ ቀርቶ 40 ቀንና ለሊት በርሃ ላይ የዱር ፍሬ እየበላ ብቻውን የሕወሓት ወራሪዎችን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል።

ስለ ቀድሞው የምስራቅ አማራ ፋኖ አድባር፣ የአሁኑ የአማራ ፋኖ በወሎ የምድር ድሮን፡ አርበኛ ጠቋር ደባልቄ፣ አባ ሸጋ፣ አባ መላ፣ የሱኪው ጠበብት፡ የፅናት ተምሳሌት ከትናንት እስከ ዛሬ ስለከፈለው ዋጋ፡ ስለነገ ቁርጠኝነቱም ጥቂት እናወጋችኋለን።

አብራችሁን ቆዩ።
****
https://www.youtube.com/watch?v=kfhtQUVqTy8

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 18:03


ቪዲዮው ተለቀቀ!

https://www.youtube.com/watch?v=kfhtQUVqTy8&t=13s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 17:11


ቪዲዮው ተለቀቀ!

https://www.youtube.com/watch?v=kfhtQUVqTy8

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 16:23


https://www.youtube.com/watch?v=n5RF6pV1IAU

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 15:36


አርበኛ ጠቋር ደባልቄ!

የዋርካው ምሬ ወዳጆ ቀኝ እጅ!

ከትናንት እስከ ዛሬ ያደረገው ትንቅንቅ ለወደፊቱ ትግል ስላለው ቁርጠኝነት ከደቂቃዎች በኋላ ይጠብቁን!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 14:57


በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በ24 ሰአት ውስጥ ሁለት ቦታዎች ላይ የድሮን ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ!

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋት ቀጠና ቀወት ወረዳ ልዩ ስሙ የለን ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ዛሬ ጥቅምት 26/2016 ዓ/ም ማለዳ የድሮን ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን በዚህም ህፃናትን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

በተመሣሣይ ትናንት አመሻሹን በዚኽው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አንጎለላ ጠራ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ነው ለጣቢያችን የደረሱ መረጃዎች የሚያመለክቱት።

ገዢው የብልፅግና ቡድን በተለይ ንፁኋንን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሁም የትምህርት፣ ግብርና፣ የሀይማኖትና ሌሎች የመሠረተ ልማት ተቋማትን ታሳቢ ያደረገ የአየር ድብደባ እየፈፀመ ይገኛል።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 13:49


https://www.youtube.com/watch?v=1AFB_oePPMg

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 13:37


አማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ በሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ የሚመራው መብረቅ ክፋለጦር ስር በፋኖ ጌትነት አበበ የሚመራው የክፋለ ጦሩ ተወርዋሪ ቃኝ ቡድንና በአበጀ የሚመራው አሳምነው ፅጌ ብርጌድ እና እያሱ ክፋለጦር አይሻ ሰይድ ሻለቃ በጋራ በመሆን አስገራሚ ውጊያ በማድረግ ድል ተቀዳጅተዋል።

ትናንት ጥቅምት 25/2017 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰአት ገደማ የተጀመረ ውጊያ በጠላት ኃይል ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሷል።

በተመሣሣይ በዛሬው ዕለት ከንጋት 12 ሰአት የተጀመረው ውጊያ እስከ እኩለ ቀን ገደማ በቆየ ውጊያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ፣ አድማ ብተና እንዲሁም ሚሊሻ እና ፖሊስ ሙትና ቁስለኛ ሆነው ተመልሰዋል።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 13:04


ሰበር ዜና
ወሎ ቤተ-አምሃራ

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ሙጃ ከተማን ተቆጣጥሮ በርካታ ድሎችን ተቆናፀፈ::

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ዛሬ ጥቅምት 26/ 2017 አ.ም ማለዳ ላይ በተጀመረ መደበኛ ዉጊያ በቀላል መስዋዕትነትና ባጭር ሰአት ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ፖሊስ ጣቢያዉንና የተለያዩ የጠላት መሰረት የሆኑ ቦታዎችን ሰብሮ በመግባት በርካታ ድሎችን ተጎናጽፏል::

የጠላት ቁልፍና መሰረት የሆነዉን ወታደራዊ ቦታ የሰሜን ወሎ ዞን ጊዳን ወረዳን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የአማራ ፋኖ በወሎ በዛሬው እለት ደግሞ የከተማ መቀመጫው የሆነችዉን ሙጃ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ ጠላት ላይ ከባድ ዉጊያ በመክፈት በርካታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በመማረክ ሰብአዊና ቁሳቂ ኪሳራ አድርሶበታል::

በኮማንዶ ዘላለም የሚመራው ተከዜ ክ/ጦር በሻለቃ ብርሃን የሚመራው ጥራሪ ክ/ጦር እንዲሁም ከማረጉ ተማረ ክ/ጦር በፋኖ ምስጋን የሚመራ ሻለቃ በአጠቃላይ በላስታ አሳምነው ኮር ስር ያሉ ግዳጁ ላይ አሃዶቻቸዉን ያሳተፉ ክፍለጦሮች ናቸው:: ከዚህ በተጨማሪ በፋኖ ካሳ አበበ የሚመራው ሃውጃኖ ክፍለጦርና በፋኖ ጌታሁን ሲሳይ የሚመራው አሳምነው ክፍለጦርን ጨምሮ ከሁሉም አሃዶች የተውጣጡ ሻለቆች በጋራ የፈፀሙት ግዳጅ ነው::

ከጠላት ኪሳራ አኳያ
1. እስካሁን በቁጥር ያልታወቀ በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል::
2. ሁለት የጠላት መኪና የተቃጠለና አንድ የጠላት ዲሽቃ ከጥራሪ ክፍለጦር መካናይዝድ ቡድን በተወነጨፈ ሞርታር ሙሉ ለሙሉ ወድሟል::
3. ብልፅግና የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የሚጠቀማቸዉ የቢሮ ሰነዶች ከምንፈልጋቸው ዉጭ ያሉት ፖሊስ ጣቢያዉን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል::

ምርኮን በተመለከተ
1. ጥራሪ ክ/ጦር 22 ከላሽ አንድ ጂመስሪ በምርኮ አግኝታለች::
2. ተከዜ ክ/ጦር ከአስር በላይ ከላሾችን በምርኮ አግኝታለች::
3. ከ20 በላይ  ሆድ አደር ሚሊሻ ተማርኳል::
4. የአሳምነው እና ሃውጃኖ ክፍለጦር አሃዶች ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ የነፍስ ወከፍ ክላሽ ማርከዋል::
ሌላው አስገራሚ ነገር የተከበበዉን የጠላት ሃይል ለማዉጣት ከድልብ በኩል የመጣው ዙ23 የራሱን ወገን መትቷል: ይህ የሆነው ደግሞ ፋኖዎች በጥበብ የነበሩበትን ቦታ ለቀው ለጠላት ቦታዉን በመስጠታቸዉ ነው። በዚህም ዙ23ቱ የራሱን ወገን በርካታዉን ጨፍጭፎታል።
• መሐል ሳይንት
የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ክንፍ የሆነው አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ጀብዱ መፈፀሙ ተገልጿል::

የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር አካል የሆነው በመቅደላ ወረዳ የሚንቀሳቀሰው በፋኖ በለጠ ምትክ የሚመራው ሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ባንዳዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል::

አድማ ብተና ጋር ተጠርንፈዉ የነበሩ የብልፅግና ባንዳዎች ጤፍ ሊያሳጭዱ  አስፈቅደው ወደ ቤተሰብ እንደመጡነው  እርምጃ የወሰድንባቸዉ ሲል የሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ገልጿል።  ደጋግመን ጥሪ አድርገን ስለነበር ጥሪያችንን ሳይቀበሉ በመቅረታቸውና ወደወጡበት ማህበረሰብ ተመልሰው የመምጣት ፍላጎት ስለሌላቸው  የማያደግም እርምጃ ለመውሰድ ተገደናል ሲል ብርጌዱ አክሎም ገልጿል።

በሌላ ምእራብ ወሎ ኮር ተጋድሎ መሃል ሳይንት ወረዳ ደንሳ ከተማ ዛሬ አዳሩን ማለትም ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ለአንድ ቡድን አገዛዙና ለሆዳቸው አድረው ህዝባቸውን ሲጨፈጭፉና ሲያስጨፈጭፉ የከረመው ሆድ አምላኩ የሆኑ ሚሊሻዎች አዳሩን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው አድረዋል። በርካታ የጠላት ሃይልም ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል:: የህልዉና ተጋድሎው እስከ ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ጥቅምት 26/2017 አ.ም

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 11:53


አሳዛኝ ዜና!

45 የሚዱርሱ ንፁኋን በድሮን ጥቃት መገደላቸው ተሰማ!

አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ አገዛዝ ስርዓት በጎጃም ደቡብ አቸፈር ወረዳ በታዳጊዋ ዝብስት  ከተማ ዛሬ ጥቅምት 26/ 2017 ዓ/ም ማርፈጃውን በፈፀመው የድሮን ጥቃት 43 ንፁኋን በጅምላ መገደላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በተጨማሪም ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል።

በድሮን ጥቃቱ ከተገደሉ እና ከቆሰሉ ንፁኋኖች በተጨማሪ አንድ የጤና ተቋምና የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችም መውደማቸው ነው የተሰማው።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

05 Nov, 06:09


ምሽግ ደርማሾቹ!

የእብናት፣ የደጋ መልዛ፣የበለሳ፣የአምቦ ሜዳ፣ የደብረታቦር፣ የአይሣና የክምር ድንጋይ ተራሮች ስለነዚህ ምሽግ ደርማሽ ሴት ፋኖዎች አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ።

ከምሽግ ምሽግ ሲወረወሩ ያየ ሰው እነዚህ የሰው ዝርያ ብቻ አይደሉም ቢል አይፈረድበትም። ቁጡ፣ ሱሩፍ፣ አራስ ነብር ናቸው ቦንብ ነካሾች።

ሻለቃ አስቻለው ደሴን/ገብርየ/ በነዚህ ታጋዮች ልብ ውስጥ ታገኙታላችሁ።ምን አለፋችሁ እራሱ አስቻለው ደሴ ዳግም ተፈጥሮ ነው።

የመረብ ሚዲያ ዘጋቢዎች እነዚህ ታጋዮች በሚገኙበት በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ እቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር አስቻለው ደሴ ብርጌድ ባለበት ቀጠና አቅንተዋል።

እነዚህ የዘመናችን እቴጌ ጣይቱዎች፣ እነዚህ የዘመናችን አብሪ ኮኮቦች፣ እነዚህ የዘመናችን የነፃነት ፋና ወጊዎች እያደረጉት ስላለው ተጋድሎ መረብ ሚዲያ በመረጃ ቲቪ ባለው የስርጭት ጊዜ ዛሬ ምሽት ከ2 ሰዓት ጀምሮ ይመልከቱ።

አምልጧችሁ ኋላ እንዳትቆጩ!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Nov, 14:17


ሰበር ዜና!

ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዡ በፋኖ ተያዘ!

ወታደራዊ ሚስጥሩን ዘረገፈው

https://www.youtube.com/watch?v=WFqA13fycVQ

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Nov, 14:08


https://www.youtube.com/watch?v=WFqA13fycVQ

Mereb Media መረብ ሚዲያ

04 Nov, 10:01


ደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት እና በመናመቀጣዋ ወረዳ መካከል የሚገኘው እምብስ በር!

በአንድ ጀምበር ከ100 በላይ የጠላት ኃይል የተደመሰሰበት ምሽግ!

ቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ከስፍራው👉

https://www.youtube.com/watch?v=-vM8MAS6tV0

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 19:21


https://www.youtube.com/watch?v=5lAXmcQAp34

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 18:39


https://www.youtube.com/watch?v=DnhF62kC5hM&t=41s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 17:08


ሰበር ዜና!

ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት አብይ አህመድን ልክ ልኩን ነገረው!

የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሏል።በቪዲዮ ይከታተሉ!

https://www.youtube.com/watch?v=5lAXmcQAp34

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 17:02


ዝክረ ሰማዕት!

የአማራ ፋኖ በወሎ ጄነራል አሳመነዉ ጽጌ ኮር ስር የሚገኘው የእሸተ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበረዉ ሻለቃ ሰማኝ አማረ የ40ኛ ቀን መታሰቢያ መርሐግብር ተካሂዷል::

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 16:58


የምዕራብ ወሎ ኮር ምስረታን በተመለከተ ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም

የአማራ ፋኖ በወሎ ካሉት ክፍለ ጦሮች መካከል ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ በኩል የሚንቀሳቀሱት 3 ክፍለ ጦሮች በአንድ ወታደራዊ ኮር እንዲታቀፉ መደረጉን ድርጅታችን እየገለጸ:-

1.  የንጉሥ ሚካኤል አሊ ክፍለ ጦር፣

2. የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣

እና

3. ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር

ቀጠናዊ የክፍለ ጦር ለክፍለ ጦር ግንኙነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል ግዳጅ የመፈጸም አቅማቸውን ማሳደግ እና የትግሉን ዙር ማክረር እንዲችሉ ማድረግ በማስፈለጉ የተነሳ በቀጠናው ያሉት እነዚህ 3 ክፍለ ጦሮች በአማራ ፋኖ በወሎ ስር ምዕራብ ወሎ ኮር በሚል ስያሜ ተደራጅተዋል::

ለዕዝ ሰንሰለት ስምረት እና ለአስተዳደራዊ አመችነት ሲባል ክፍለ ጦሮችን በኮር የማደራጀት እንቅስቃሴ ከተጀመረ የሰነበተ ሲሆን የአማራ ፋኖ በወሎ በያዘው እቅድ መሰረት የምዕራቡን ክፍል በኮር የማደራጀት ስራውን በዛሬው እለት አጠናቋል::

የምዕራብ ወሎ ኮር ከደሴ እስከ ሳይንት ጫፍ በሽሎ ወንዝ ድንበር ድረስ የሚያካልል የፋኖ ሀይልን ያቀፈ ሲሆን የአፄ ቴዎድሮስ አጽመ እርስት ከሚገኝበት መቅደላ አምባ እስከ ጌታው ሸህዬ ሀገር ደገር የሚዘረጋ ግዙፍ ኮር ነው:: ከሸዋ ድንበር በቶ እና ወለቃ ወንዞች እስከ ጎንደር ድንበር በሽሎ ወንዝ እንድሁም የጎጃም እና ወሎ መዘያየሪያ የሆነው አባይ ወንዝ ድልድይ ድረስ የሚወነጨፍ የፋኖ ሀይል በኮሩ ስር የተሰበሰበ ሲሆን የኮሩ መስራች የሆኑት 3 ክፍለ ጦሮች ያቀፏቸው ብርጌዶች፣ ሻለቃዎች እና ሻምበሎች ከምዕራብ ወሎ ቀጠና ባሻገር ወደ ጎንደር፣ ጎጃም እና ሸዋ በመወርወር ግዳጅ መወጣት እንደሚችሉ ተደርገው የተደራጁ መሆናቸውን እየገለፅን የቀጠናው ፋኖዎች ወንዝ ተሻግረው እና ጎራ ዙረው ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችላቸውን ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ጭምር በቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው ስም ሰይመው ለሰማዕተ ጓዳችን እና ወንድማችን ማስታወሻ የሚሆን የተቋም ሀውልት እንዲቆምለት ማድረግ ተችሏል::

የምዕራብ ወሎ ኮርን በዋና ሰብሳቢ/ዋና አዛዥ የሚመራው ስመጥሩው አርበኛ ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ሲሆን በጥብቅ ወታደራዊ ዲስፕሊን የታነፀ እና ግዳጅ የመፈፀም ብቃቱ አኩሪ መሆኑ የተረጋገጠ ሰራዊትን ያቀፈ ኮር ነው:: አርበኛ ሳጅን አደም አሊ ጋር ኮሩን በመምራት ትግሉን ወደተሻለ ምዕራፍ ያሸጋግራሉ ተብለው የታመነባቸው የኮሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ስም እና ኃላፊነት ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ለታጋይ ሰራዊታችንና ለህዝባችን ይፋ የምናደርግና የምናሳውቅ ይሆናል::

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ጥቅምት 21/2017 ዓ/ም

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 13:20


አንዲት የአዕምሮ ህመምተኛን ጨምሮ የአንድ ቤተሰብ አባላት ያለቁበት የከባድ መሣሪያ ድብደባ!

መረብ ሚዲያ በሟቾቹ ቀብር ስነ ስርዓት ላይ ተገኝቶ የሚከተለውን ምስል አስቀርቷል።

https://www.youtube.com/watch?v=-Ci16fs1HPo
ሙሉውን ማየት ከፈለጋችሁ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 12:22


እናጅሬ መሀል አደባባዩ ላይ ተገማሸሩበት!

አስደማሚው የፋኖ ተግባር!


https://www.youtube.com/watch?v=r2qZkK4OdpM

Mereb Media መረብ ሚዲያ

31 Oct, 06:53


እንደምን አረፈዳችሁ!

የምርኮኞች የቁርስ ሰልፍ
###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 21:14


https://www.youtube.com/watch?v=EyxsFpoUhS4&t=24s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 20:19


https://www.youtube.com/watch?v=Z8_lRWEkD00&t=26s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 20:00


https://www.youtube.com/watch?v=OzUAfj9mBG4&t=99s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 19:42


https://www.youtube.com/watch?v=Iwif9Klgsck&t=56s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 18:59


እንደምን አመሻችሁ!

ወ/ሮ ሃገሬ ዮሀንስ ትባላለች!

ባለቤትሽ ፋኖ ነው በሚል ከጥቅምት 10/2017 ዓ/ም ጀምሮ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፊጥራ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ትገኛለች።

የታሰረችው ወ/ሮ ሃገሬ ብቻ ሳትሆን የሁለት ዓመት ህፃን ልጇም አባትሽ ፋኖ ነው በሚል ከእናቷ ጋር ለእስር መዳረጓን መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከነ ህፃን ልጇ የታሰረችውን ወ/ሮ ሃገሬን ቤተሰብ እንዳይጠይቃት እነዚኸው የገዢው ቡድን ወታደሮች መከልከላቸው ነው የታወቀው።

በተመሣሣይ በዚኸው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እነዋሪ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ መደሰት ገዛኸኝ፡ ባለቤትሽ ፋኖ ነው በሚል ከጥቅምት 03/2017 ዓ/ም ጀምሮ በእነዋሪ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደምትገኝ ጣቢያችን ከሳምንት በፊት መዘገቡ አይዘነጋም።

ባለቤትሽ ያለበትን ጠቁሚ የሚል ጥያቄ ስናቀርብልሽ "ያለበት ጠፍቷችሁ አይደለም፡ ይዞ ማምጣት አቅቷችሁ እንጂ?" የሚል ምላሽ ሰተሻል በሚል ምክኒያት የሚሊሻና የፖሊስ አባላቱ እየተፈራረቁ ድብደባ እንደፈፀሙባት በወቅቱ መረብ ሚዲያ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስነብቦ ነበረ።

የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ በሚል ጨቅላ ህፃናትን ጨምሮ ነፍሰጡር ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በአገዛዙ ወታደሮች እየታደኑ በየቀኑ ለእስር የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከመጠን በላይ ማሻቀቡን ነው መረብ ሚዲያ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ የቻለው።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 17:11


ቀጥታ ከጦር ግምባር!

የእስልምና እምነት ተከታዩ የመከላከያ ሰራዊት አባል አፈሙዙን አዞረ!

"ወላሂ አማራ ያሸንፋል፡ አይዟችሁ በርቱ" ይህ ከወንድሞቼ ጋር አልገጥምም ብሎ ወደ ራሱ አባሎች አፈሙዙን  ያዞረው የመከላከያ ሰራዊት አባል ከመሰዋቱ በፊት የተናገረው የመጨረሻ ቃል ነው።

ይህን በወሎ ግምባር የተፈፀመ ከባድ ተጋድሎ ተከታተሉ👉

https://www.youtube.com/watch?v=EyxsFpoUhS4

Mereb Media መረብ ሚዲያ

30 Oct, 15:43


https://www.youtube.com/watch?v=J4fX7oqP-EM&t=37s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

27 Oct, 18:49


https://www.youtube.com/watch?v=lPfUXHFFtjI

Mereb Media መረብ ሚዲያ

27 Oct, 16:12


ትናንት መረብ ሚዲያ በላስታ ወረዳ የ3 ዓመት ህፃን ልጇ በጀርባዋ አዝላው እየተጓዘች እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ስለተገደለባት እናት መዘገቡ አይዘነጋም።

እናት በደረሰባት ከባድ ሀዘን የተነሳ የአዕምሮ መቃዎስ ገጥሟታል።

እንሆ ቪዲዮ!

https://www.youtube.com/watch?v=lPfUXHFFtjI&t=376s
ሙሉውን ማየት ከፈለጋችሁ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

27 Oct, 11:25


ይሄንን ጉድ ያላየ ሰው ይኖር ይሆን?

ሁሉም አማራ ሊያየው የሚገባ ቪዲዮ!

https://www.youtube.com/watch?v=lPfUXHFFtjI&t=376s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

26 Oct, 19:20


https://www.youtube.com/watch?v=Z8_lRWEkD00

Mereb Media መረብ ሚዲያ

26 Oct, 13:15


ይች እናት ስቅስቅ ብላ የምታለቅሰው የ3 ዓመት ከ3 ወር ህፃን ልጇ በአሰቃቂ ሁኔታ በመከላከያ ሰራዊት ተገድሎባት ነው።

የሚያሳዝነው ደግሞ ህፃኑ የተገደለው በተባራሪ ጥይት ወይንም በስህተት አይደለም። ሆን ተብሎ ታስቦና ታቅዶበት የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዦች ከበላይ አመራሮቻቸው ጋር በመገናኛ ራዲዮን ትዕዛዝ ተቀብለው የፈፀሙት ድርጊት ነው።

ህፃኑ የተገደለው እናቱ ትከሻ ላይ ሳለ ነው።እናቱ ልጇን ለማትረፍ በወገቧ አዝላ እየሸሸች በነበረበት የመከላከያ ሰራዊት የድሽቃ ምድብተኞች አነጣጥረው ኢላማቸው ውስጥ ካስገቡ በኋላ ህፃኑን ከእናቱ ወገብ ላይ እንዳለ አንገቱን በመምታት ቅንጭላቱ ለብቻ ተገንጥሎ እንዲወድቅ አድርገውታል።

መረብ ሚዲያ ይህ የሚያስነብባችሁ ፅሁፍ ሆሊውድ ወይንም ቦሊውድ ውስጥ ስለተሰራ አንድ ሆረር ፊልም አይደለም። ይልቁንስ በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ወደብየ ቀበሌ ላይ የአገዛዙ ወታደሮች ስለ ፈፀሙት አሰቃቂ ግፍ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው፦

በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ ወረዳና አይና ቡግና ወረዳ ስር በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ከመስከረም 20/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሚሊሻና አድማብተናን ጨምሮ በገዢው ቡድን ወታደሮች እና በፋኖ መካከል ከባድ ውጊያ ይካሄዳል።

የአገዛዙ ወታደሮች ገና ውጊያው ከመጀመሩ ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ የኔትዎርክና የመብራት አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርገው፣ ከባባድ መሣሪያዎችን ካፍ እንስከደገፉ ታጥቀው ነው ወደ ውጊያው የገቡት።

ወታደሮቹ ከተቻለ የላስታ አሳምነው ኮር አመራሮችን መግደል፡ ካልተቻለ ፅንፈኛ ብለው የሚጠሩት የፋኖ ሰራዊትን አከርካሪ መስበር የሚል ተልዕኮ ነበር የተሰጣቸው።

ነገ ግን እንዳሰቡት አልሆነላቸውም። በሚሊሻና አድማብተና መንገድ መሪነት የፋኖን አከርካሪ ሊሰብሩ የገቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ በእጅ አዙር የነሱ አከርካሪ ተሰበረ። እነዛ የአሳምነው ልጅ እያሉ ከምሽግ ምሽግ የሚወረወሩት የላስታ ፋኖዎች ዙሪያውን ከበው የጥቃት ናዳ አወረዱባቸው።

የመከላከያ ሰራዊቱ ከፋኖ የተሰነዘረባቸውን አፀፋዊ ምት መቋቋም አልቻሉም። ተጨማሪ ኃይል በተደጋጋሚ ከወደ ላሊበላና ግዳን አቅጣጫ ቢያስመጡም ነገር ግን የፋኖ ክንድ የሚቀመስ አልሆነም። የሻምበልና መስመራዊ የጦር መኮነኖችን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። ነገሩ እንዳሰቡት ስላልሆነ ሙትና ቁስለኛቸውን በአራትና አምስት አይሱዙ ጭነው ወደ መጡበት መመለስ ጀመሩ።

ወታደሮቹ ወደ መጡበት ሲመለሱ ህፃናትና አዛውንቶችን ጨምሮ በመንገድ ያገኟቸውን ንፁኋን እየገደሉ እንዲሁም ከፊሎቹን ምርኮኛ ናቸው በሚል እያሰሩ አንዲት ቀበሌ ላይ ደረሱ። ይቺ ቀበሌ በላስታ ወረዳ ስር የምትገኝ ሲሆን ስሟም ወደብየ ወይም ጨበርጣይ በመባል ትጠራለች።

በዚህ ከታች ባለው ምስል ላይ ስታለቅስ ያያችኋት እናት በጧት ተነስታ ለልጇ የሚሆን ምግብ አብስላ ከመገበች በኋላ ጦርነቱ እየተፋፋመ በመምጣቱ ከባድ መሣሪያ ሲወረወር ልጄን እንዳይመታብኝ በሚል የ3 ዓመት ከ3 ወር ህፃን ልጇን በአንቀልባ አዝላ ለጊዜው ጦርነት ወደለለበት ቀጠና ሽሽት ትጀምራለች።  በዚህ ጊዜ ነበር እነዛ በአማራ ጥላቻ የሰከሩ የአንድ ፓርቲ ወንበር አስጠባቂ ከሆኑ የአገዛዙ ወታደሮች ጋር ፊት ለፊት የተገጣጠመችው።

ወታደሮቹ አስቆሟትና ወዴት እየሄደች እንደሆነ ጠየቋት።እሷም እየሸሸች መሆኑ ነገረቻቸውና መንገዷን ቀጠለች።

ይህኔ መገናኛ ራዲዮን የያዘ አንድ ወታደራዊ አዛዥ ለድሽቃ ተኳሹ በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው። ድሽቃ ተኳሹም ተሸክሞት የነበረውን ድሽቃ ከመቅፅበት መሬት ላይ አስቀምጦ ገጣጠመና ጥይት አቀባበሎ ልጅ አዝላ ወደ ምትሸሸው እናት አነጣጠረ።

ልጅ ያዘለችው እናት ግራ ቀኟን ዞር ዞር እያለች እያየች የደመነፍሷን ትሮጣለች። ድሽቃ ተኳሹ ለረዢም ሰከንዶች አነጣጥሮ ሲያበቃ ሁለት ጊዜ አከታትሎ ተኮሰ ወደ ምትሸሸው እናት። ሊያገኛት አልቻለም። እንደገና ቦታ አመቻችቶ አነጣጠረና ሦስተኛ ጥይት ተኮሰ።

ሦስተኛዋ ጥይት ልክ እንደ መጀመሪያዋና ሁለተኛዋ ጥይት አልሳተችም።  በእናቱ ጀርባ ታዝቶ የነበረው የ3 ዓመት ከ3 ወር ህፃን አንገት ላይ ተወርውራ ተሰካች።

ይህኔ ወታደራዊ አዛዡን ጨምሮ ድሽቃውን ከበው ቆመው የነበሩት ወታደሮች በፉጨትና በደስታ ጩኸት አከባቢውን አናወጡት። "ብራቮ!...ብራቮ የኛ ልጅ፣ ምርጥ ተኳሽ፣ ጀግናችን" እያሉ ድሽቃ ተኳሹን በደስታ ይጨብጡት ጀመር።

እናት አሁንም እየሮጠች ነው።ልጇን ከነፍሰበላዎች ልትታደግ። ልጇ አድጎ ለቁም ነገር እንዲደርስ ከነዚህ ፀረ ህፃናት፣ ከእነዚህ አውሬዎች ልትሰውረው ነፍሷ እስክትወጣ እያለከለከች ትሮጣለች።

በመሃል ድንገት ጎኗን ቀዘቀዛት። ከድካሜ የተነሳ ላብ አልቦኝ ይሆናል ብላ ዝም አለች። ነገር ግን በአንድ ጎኗ ብቻ ሳይሆን በሌላኛው ጎኗም ይቀዘቅዛት ጀመር። እጇን ሰደደች። ጎኗን ዳበስ ዳበስ አድርጋ እጇን ስታይ በደም ተጨማልቋል። ያየችውን ማመን አቃታት።

ልጇን ጠራችው...አይሰማም። ደጋግማ ጠራችው። ፀጥ። ምላሽ የለም። ያ ስትሮጥ አይዞሽ እማመይ እኔ አብርልሻለው አይመቱሽም እያለ በልጅ አፉ እየተኮላተፈ ሲያወራት የነበረው ልጇ አሁን ስትጠራው አልሰማት አለ።

ሰውነቷ ተንቀጠቀጠቀጠ።እጆቿ ተሳሰሩ።የአንቀልባውን መቋጠሪያዎች መፍታት ከበዳት።ጣቶቿ ተሳሰሩ።

እንደምንም ብላ እየየተንቀጠቀጠች አንቀልባውን ፈታችና በጀርባዋ ያዘለችውን ልጇን አውርዳ ስታይ እራሷን ስታ ወደቀች። ቅንጭላቱ ተቆርጦ ወድቋል።ህፃኑ ከመገደሉ በፊት በጣቶቹ የጨበጣትን ከጭቃ የተሰራች መጫወቻ አሁንም እንደጨበጣት ነው። እናት አካሉ ከሁለት የተከፈለ አስከሬን ታቅፋ ጀርባዋ በደም እንደተለወሰ እራሷን ስታ ወድቃለች።

በቅርብ ርቀት ከኋላዋ ይከተሉ የነበሩ የአከባቢዋ ነዋሪዎች እሩጠው ደረሱ። እናቲቱ አለመመታቷን ካረጋገጡ በኋላ ተቆርጦ የወደቀውን የህፃኑን ቅንጭላት ፍለጋ ገቡ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የወታደሮቹ ፉጨትና የደስታ ሆይ ሆይታ አልበረደም። "ብራቮ!...ብራቮ የኛ ልጅ ብራቮ! ፣ ምርጥ ተኳሽ ነህ!፣ አምበሳ የኛ ልጅ፣  ጀግና" እያሉ ድሽቃ ተኳሹን ያሞካሹታል።

መረብ ሚዲያ የሟችን እናት ለመጠየቅ ባቀናበት ወቅት የተመለከተው በልጇ ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት የተነሳ አዕምሮዋ ተቃውሷል።

አንዳንዴ ከቤት ትወጣና የሟች ልጇን ስም እየተጣራች "እረ ና መሽቷል። ናልኝ ልጄዋ አባው እንዳይበላህ። ና የሚበላ እንድሰጥህ፣ ና ስትጫወት  ጭቃ ስለነካህ ገላህን እንዳጥብህ፣ ናልኝ መኩሪያየ" ትላለች።

አንዳንዴ ደግሞ ትንሽ ቀልቧ መለስ ሲልላት እንዲህ ስትል ታለቅሳለች "እሸሽጋለሁ ብየ ልጄን ለአውሬዎቹ አሳልፌ ሰጠሁ። አትፍረድብኝ ሲሸሹ አይቼ ነው ልጄ፡ መኩሪያየ ልጄ፡ ጠበቃየ ልጄ፡ ወግ ማዕረጌ ልጄ"

"ጨከኑብህ ልጄ፡ እኔማ ልሸሽግህ ነበር፡ ልብማ ከነዛ ክፉዎች ልደብቅህ ነበር፡ አመለጥከኝ ልጄ፣ ለአውሬዎቹ አሳልፌ ሰጠሁህ ልጄ፣ እረ ወዴት ልሂድ ሰማይ ተደፋብኝኮ" እያለች መንታ መንታውን እያነባች፣ ደረቷን እየደቃች ታለቅሳለች።

ገዢው የብልፅግና ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመው ካለው ግፍና መከራ መካከል ይህ ቀላሉና ትንሹ ግፍ ነው።

መረብ ሚዲያ ከሃዘንተኛዋ እናት ጋር ያደረገውን ቆይታ ዛሬ ምሽት መረጃ ቲቪ ላይ በሚኖረን የስርጭት ሰዓት ይጠብቁን!

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Oct, 19:31


ሰበር ዜና!

በወሎ የሚገኙ የፋኖ አዛዦችን ለማስገደል ከመንግስት አካላት ተልዕኮ ተቀብሎ በጦር ግምባር የተገኘ አንድ የደህንነት አባል በፋኖ እጅ ከፈንጅ ተያዘ!

መረብ ሚዲያ በስፍራው ተገኝቶ በፋኖ እጅ ከፈንጅ የተያዘውን የደህንነት አባል በቪዲዮ ቀርፆታል።ይከታተሉ!
https://www.youtube.com/watch?v=Iwif9Klgsck

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Oct, 14:22


በትናንትናው እለት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተከታታይ አምስት ጊዜ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከተገደሉት ንፁኋኖች መካከል አንዱ የሆነው ህፃን ዳዊት መካሽ ይህ ነው።

የ6 ዓመቱ ህፃን ዳዊት መካሽ ትናንት በይፋት ቀጠና ራሳ አከባቢ በተፈፀመው የድሮን ጥቃት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ክፍል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

#Dawit_Mekash
#AmharaGenocide

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Oct, 10:57


እንደምን ዋላችሁ!

የጁመአ ሶላት በጦር ግምባር!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Oct, 10:29


ታላቅ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ለአማራና የአማራ ደጋፊዎች በሙሉ!

ጨፍጫፊው እና ፋሺስቱ የአብይ አህመድ አንባገነን አገዛዝ: በአማራ ህዝባችን ላይ
ጦርነት በማወጅ፣ በአሁኑ ሰዓት በሰውአልባ፣ በጦር አውሮፕላን እና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ: የሚፈፀመውን የጅምላ ዘር ጭፍጨፋ በመቃወም በመላዉ ዓለም ለወገኖቻችን ድምፅ ለመሆን!

ሰልፉ የሚደረግባቸው የዓለም ከተሞች ፣

1. Berlin, Germany: Oct 18
2. Indianapolis, USA: Oct 25
3. ⁠Denver,USA: Oct 28
4. ⁠Seattle, USA: Nov 7
5. ⁠Frankfurt, Germany: Nov 9
6. ⁠Paris, France: Nov 9
7. ⁠Stockholm, Sweden: Nov 9
8. ⁠Queensland, Australia: Nov 9
9. ⁠Chicago, USA: Nov 9
10. ⁠London, UK: Nov 10
11. Washington, D.C., USA: Nov 10
112. Pretoria, South Africa: Nov 10
13. Minnesota, USA: Nov 10
14. Brussels, Belgium: Nov 10
15. Geneva, Switzerland: Nov 12
16. Oslo, Norway: Nov 23

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Oct, 06:31


አንዲት የአዕምሮ ህመምተኛን ጨምሮ የአንድ ቤተሰብ አባላት ያለቁበት የከባድ መሣሪያ ድብደባ!

መረብ ሚዲያ በሟቾቹ ቀብር ስነ ስርዓት ላይ ተገኝቶ የሚከተለውን ምስል አስቀርቷል።

https://www.youtube.com/watch?v=-Ci16fs1HPo
ሙሉውን ማየት ከፈለጋችሁ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!

Mereb Media መረብ ሚዲያ

25 Oct, 05:38


እንደምን አደራችሁ!

ላስታ...በአሸተን ተራሮች አናት!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 19:17


https://www.youtube.com/watch?v=-Ci16fs1HPo&t=76s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 16:10


ይሄንን ጉድ ተመልከቱ!

በመድፍ ያለቁ የአንድ ቤተሰብ አባላት የቀብር ስነ ስርዓት ሲፈፀም የተቀረፀ ቪዲዮ!


"አብይ አህመድ ልጄን በላት"/ የሟች ቤተሰቦች ኡኡታ!...

ቀጥታ ስርጭት በቪዲዮ!

https://www.youtube.com/watch?v=-Ci16fs1HPo&t=50s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 13:15


"በለው በለው ሲል ነው የወንድ ልጅ ሞቱ
ሴትም ትገላለች ከረጋ መሬቱ"

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 11:44


የመርካቶው እሳት አደጋ ከመከሰቱ ሁለትና ሦስት ቀናት በፊት አንድ የኦሮሞ አክቲቪስት ከተናገረው የተወሰደ ድምፅ!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 09:40


ወሎ ቤተ- አምሃራ
የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው ተጋድሎ

በአርበኛ ፋኖ ጌታሁን ሲሳይ የሚመራው አሳምነው ክፍለጦር ወልድያ ዙሪያ እያደረገ ያለው ተጋድሎ የቀጠለ ሲሆን ባህር ዳር መውጫ አፍሪኬር አካባቢ ጠላት ኬላ የሚያደርግበት ቦታ ላይ ደፈጣ በማድረግ የተለመደዉን ክንዳቸዉን አቅምሰዉታል::

በጥቃቱ ጠላት አምስት ሙትና ስድስት ቁስለኛ ያነሳ ሲሆን በወልድያና በሳንቃ በኩል ሁለት ዙ23 በማምጣት በዘፈቀደ እየተኮሰ ሲሆን ቃሊም መግቢያ አቦ ቤተ-ክርቲያን አካባቢ ሁለት እናቶችን በከባድ ሁኔታ አቁስሎ የነበረ ሲሆን አንደኛዋ እናታችን አርፋለች::

አሁን ላይ ወደመጣበት የሸሸ ሲሆን ወልድያ ከተማ ተረጋግቶ መቀመጥና ስራ መስራት ስላልቻለ ራያ አላማጣ ያስቀመጠዉን ተጠባባቂ ቀይ ቆብ ለባሽ ፈርጣጭ ሰራዊቱን ዛሬ ያስገባ መሆኑን አረጋግጠናል:: ተጋድሎዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ምንጭ፦ የአማራ ፋኖ በወሎ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 08:48


ታላቅ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ!
በ16 ከተሞች!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

22 Oct, 06:40


ድምፅ አልባው ሚሳኤል!

በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር አዛዥ አርበኛ ተሾመ አበባው!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

21 Oct, 12:48


አማራ ፋኖ በጎጃም!

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

21 Oct, 08:32


እንደምን አረፈዳችሁ!

ሕዝቡ ምን ይላል?

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Oct, 19:43


አዛውንቱ አርበኛ ፖለቲካን በዚህ ልክ ብጥር አድርገው ይተነትኗታል ብሎ ማን ያምናል? ይገርማል!

👉ድንቅ ትንታኔ ከአባታዊ ምክር ጋር

👉የትግሉን መነሻና መድረሻ ጥንቅቅ አድርገው የተገነዘቡ

👉የጥላትን ሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ የሚንድ ሃሳብ የሰነዘሩ

የአምባሰሉ አርበኛ ከመረብ ሚዲያ ጋር የሚገርም ቃለመጠይቅ አድርገዋል። ተከታተሉ#እንዳያመልጣችሁ!

https://www.youtube.com/watch?v=XoW-SNtcY1Y&t=139s

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Oct, 18:16


የጎፍ ክ/ጦር ተመሰረተ!

ደሴ ከተማ ዙሪያን ጨምሮ ከወረኢሉ እስከ አልብኮ ወረዳ እንዲሁም እስከ ዳዋ ጨፋ/ልዩ ዞኑ/ ድረስ የሚንቀሳቀስ በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ስር የጎፍ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው አንድ ክ/ጦር መመስረቱን የክ/ጦሩ አመራሮች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

<የጎፍ> በደሴ እና በኮምቦልቻ(ከኮምቦልቻ በቅርብ ርቀት) መካከል የሚገኝ በደን የተሞላ ተራራማ ስፍራ ነው።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Oct, 17:47


የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ተጨማሪ ኃይል ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ለማስግባት ዙ- 23፣ BM-107፣ ዲሽቃና ሞርታር ይዞ በሄሊኮፍተር የታገዘ እንቅስቃሴ ሢያደርግ ውሏል።

ከወደ ባሕር ዳር እየመጣ የነበረውን ኃይል ለመቀበል ከደብረ ታቦር ወደ አለም በር የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ጦር ላይ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጥምረት ደፈጣ ጥቃት ፈፅመውበታል።

አለም በርና ዙሪያ ገባው ላይ በተፈፀመው ደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፡ የደብረ ታቦር ሆስፒታል በዚህ ሠዓት በቁስለኛ ወታደሮች ተጨናንቋል።

በተጨማሪም አንድ የጦር አዛዥ እንደቆሰለና በደብረ ታቦር ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ አረጋግጠናል።

ሕልውናችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን❗️

የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Oct, 17:29


★አገዛዙ በንፁሃኖች ላይ ግፍ ፈፀመ

የ8 ንፁሀን ወጣቶች የግፍ ሞትና የ450 ወጣቶች እስራት የብልፅግናው አሳፋሪ ተግባር በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

    የሽንፈት ማሳያ ጥጉን ፣የውርደት ካባውን ተከናንቦ የሚደናበረው የብልፅግናው መንግስት የቀን ስራ በመስራት የእለት እንጀራቸውን ለመብላት ከየአቅጣጫው የመጡ  ከ1000 በላይ ወጣቶችን ሰብስቦ የጅምላ ግድያ ሙከራ አድርጎ ሳይሳካለት 450 ወጣቶችን በአንድ ክፍል ውስጥ በጅምላ ያሰረው ልጓም የለሹ የብልፅግናው ወንበር ጠባቂ ቡድን ማንነቱን በይፋ ገልፇል።

    ራሱን ጥምር ጦር እያለ የሚጠራው የአማራ ሚሊሻ ፣የአማራ ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ከተማ የሚገኙ  ለቀን ስራ የመጡ እና የከተማው ወጣት ነዋሪዎችን ቁጥራቸው ከ1000 በላይ የሚሆኑትን   ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ  ለአስቸኳይ ስብስባ ትፈለጋላችሁ በሚል የማስፈራሪያ ጥሪ በአንድ አዳራሽ ሰብስበው የአገዛዙ አረመኔዎች የጅምላ ጭፍጨፋውን የአፈፃፀም እቅድ በማሴር ላይ ሳሉ በጉዳዩ ግራ የተጋቡት ወጣቶች ባነሱት የግልፀኝነት ጥያቄ "ገድለን ሳንጨርሳችሁ ማን ተንፍሱ አላችሁ?" በሚል የአገዛዙ ሹማምንቶች በሰጡት ትዕዛዝ በተፈፀመ የግድያ ተኩስ 8 ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን 450 ወጣቶች ከሞት አምልጠው በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ በጅምላ ታስረው ይሰቃያሉ። ቀሪዎቹ አምልጠው ከከተማው በመውጣት ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

    ይህንን  አሳፋሪ ተግባር አይደለም የአንዲት ሉአላዊት አገር መሪ ነኝ ከሚል መንግስት ይቅርና በአለም አቀፍ ደረጃ አሉ የሚባሉ አሸባሪዎች እንኳን ፈፅመውት የማያውቁት ወራዳ ተግባር ነው።

    አሁንም እንላለን በየከተማው ቁጭ ብለህ እንደ መስዕዋት በግ ልትታረድ የተዘጋጀህ የማረጃ ቢለዋህ ሲሞረድ ድምፁን እየሰማህ ቁጭ ያልክ የአማራ ወጣት ሆይ በየአካባቢህ የሚገኘውን የአማራ ፋኖ አደረጃጀት በመቀላቀል ይህን ፀረ አማራ ስርዓት በቃኝ ልትል ይገባል።


  ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
     ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

Mereb Media መረብ ሚዲያ

20 Oct, 16:31


"የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተሰጠው 2ኛው ዙር ስልጠና!

ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ "ስልጠናው ለቀጣይ የሀገራዊ ብልጽግና ጉዞው አጋዥ የሆኑ ገንቢ ሀሳቦችን በግብዓትነት የወሰድንበት ነው" ሲሉ ቃል በቃል ተናግረዋል።

###
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም 👉https://t.me/MerebMedia24

ፌስቡክ👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61564373210803

10,418

subscribers

1,385

photos

124

videos