Tinsae Holistic School @tinsc Channel on Telegram

Tinsae Holistic School

@tinsc


Tinsae Holistic School (English)

Welcome to Tinsae Holistic School! This Telegram channel, with the username @tinsc, is dedicated to providing a comprehensive and integrated approach to education. Tinsae Holistic School focuses on nurturing the mind, body, and spirit of every student, ensuring they receive a well-rounded education that prepares them for success in all areas of life. Who is Tinsae Holistic School? Tinsae Holistic School is a unique educational institution that values the holistic development of its students. By focusing on not just academics, but also physical, emotional, and spiritual well-being, Tinsae Holistic School ensures that each student receives a truly comprehensive education. What is Tinsae Holistic School? Tinsae Holistic School offers a wide range of educational resources, including articles, videos, and webinars, all aimed at helping students reach their full potential. Whether you are a student looking for guidance on personal growth, a parent seeking holistic education for your child, or an educator interested in implementing holistic practices in the classroom, Tinsae Holistic School has something for you. Join us on this journey towards holistic education and personal growth. Together, we can create a brighter future for the next generation. Follow us on Telegram @tinsc and start your holistic education today!

Tinsae Holistic School

14 Feb, 10:35


Our kindergarten students had a great sports activities with their teachers during assembly time.👇

Tinsae Holistic School

12 Feb, 03:54


ረቡዕ ፣ የካቲት 05 ቀን ፣ 2017ዓ.ም
ለትንሳኤ ሆሊስቲክ ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ
የሶስተኛውን ሩብ ዓመት የትምህርትና የትራንስፖርት ክፍያ እስከ ጥር 30 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደነበረ ይታወቃል። ነገር ግን እስካሁን ድረስ ከፍላችሁ ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች ከቅጣቱ ጋር ከፍላችሁ በአስቸኳይ እንድታጠናቅቁ እያሳወቅን ክፍያ ፈጽማችሁ ደረሰኝ ያላወራረዳችሁ ወላጅዎች የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ከወዲሁ እንድታወራርዱ ማስታወስ እንወዳለን።

በተጨማሪም የየካቲት ወር የትራንስፖርት ክፍያ የሚፈጸመው እስከ የካቲት 05 ቀን ፣ 2017ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ክፍያዉን ከፈጸሙ በኃላ የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ክፍያውን እንድታወራርዱ ማሳሰብ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ
1. ክፍያዉን ሲፈጽሙ በተማሪው ስም ያስገቡ።
2. ክፍያዉን ከፈጸሙ በኃላ የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ክፍያውን ያወራርዱ።
3. የትምህርት ቤት  እና የጥናት ክፍያ የሚፈፀመው አትንሳ ት/ቤት እና የትምህርት ስራዎች ኃ/የ/የግል  ማህበር በሚለው ስም በባንክ ብቻ ሲሆን
ኦሮሚያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፡ 1504871000001 ወይም
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፡ 1000429458122 ነው፡፡ 
4. የትራንስፖርት ክፍያ የሚፈጸመው ደግሞ
ትንሳኤ አሰፋ በሚል ስም
በኦሮሚያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር
C/A 1424151100002 ወይም
በንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር
1000079536141 ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

                           እናመሰግናለን።
                  የት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል

Tinsae Holistic School

04 Feb, 15:05


ውድ ወላጆች ከዚህ ቀደም በላክነው መልዕክት እንዳሳወቅነው የተወመ አደረጃጀትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እሁድ፣ የካቲት  02 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም  አጠቃላይ የወላጆች  ስብሰባ  መጥራታችን ይታወቃል። በመሆኑም በእለቱ የተማሪዎች  የውጤት መግለጫ  ካርድም ስለሚሠጥ ከጠዋቱ 2:30 ላይ በ1ኛ ደረጃ ግቢ እንዲገኙ በአክብሮት ተጠርተዋል።

የት/ቤቱ አስተዳደር

Tinsae Holistic School

03 Feb, 08:45


ውድ ወላጆች ተማሪዎቻችን በዚህ የመንፈቅ ዓመት እረፍት ወቅት የተለያዩ የሳይንስ የፈጠራ ስራዎችን አዘጋጅተው በመምጣት በቀጣይ በደማቅ ሁኔታ በሚከናወነው የሳይንስ የፈጠራ ስራ ውድድር (Science Fair Competition) ላይ እንዲሳተፉ እንድታበረታቷቸው እየጠየቅን ከዚህ በታች የታጋሩት ቪዲዮዎች  አጋዝ
ስለሚሆኗቸው ቪዲዮዎቹን ለተማሪዎቻችን እንድታሳዩዋቸው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

Tinsae Holistic School

01 Feb, 05:21


ቅዳሜ ፣ ጥር 24 ቀን ፣ 2017ዓ.ም
ለትንሳኤ ሆሊስቲክ ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ
የሶስተኛውን ሩብ ዓመት የትምህርትና የትራንስፖርት ክፍያ እስካሁን ድረስ ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች እስከ ጥር 30 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ክፍያዎች ማጠናቀቅ ያለባቸው መሆኑን እያሳወቅን ክፍያ ፈጽማችሁ ደረሰኝ ያላወራረዳችሁ ወላጅዎች የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ከወዲሁ እንድታወራርዱ ማስታወስ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ
1. ክፍያዉን ሲፈጽሙ በተማሪው ስም ያስገቡ።
2. ክፍያዉን ከፈጸሙ በኃላ የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ክፍያውን ያወራርዱ።
3. የትምህርት ቤት  እና የጥናት ክፍያ የሚፈፀመው አትንሳ ት/ቤት እና የትምህርት ስራዎች ኃ/የ/የግል  ማህበር በሚለው ስም በባንክ ብቻ ሲሆን
ኦሮሚያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፡ 1504871000001 ወይም
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፡ 1000429458122 ነው፡፡ 
4. የትራንስፖርት ክፍያ የሚፈጸመው ደግሞ
ትንሳኤ አሰፋ በሚል ስም
በኦሮሚያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር
C/A 1424151100002 ወይም
በንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር
1000079536141 ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

                           እናመሰግናለን።
                           የት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል

Tinsae Holistic School

06 Jan, 10:39


ሰኞ/ታህሳስ 28 ቀን/2017ዓ.ም

ውድ ወላጆች:-
የጥር ወር የትራንስፖርት ክፍያ የሚከፈለው ከታህሳስ 25 እስከ ጥር 5 ቀን ፣ 2017ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ክፍያዉን ከፈጸሙ በኃላ የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ክፍያውን እንድታወራርዱ ማሳሰብ እንወዳለን።
ማሳሰቢያ
1. ይህ የትራንስፖርት ክፍያ በሩብ አመት ክፍያ የሚከፍሉ ወላጅዎችን አይመለከትም። የትራንስፖርት ክፍያቸውን በወር የሚከፍሉ ወላጅዎችን እንጂ።
2. የትራንስፖርት ክፍያ የሚፈጸመው
     ሀ.በኦሮሚያ ባንክ ትንሳኤ አሰፋ ገሰሰ የሂሳብ ቁጥር C/A 1424151100002 ወይም
    ለ. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: ትንሳኤ አሰፋ ገሰሰ
የሂሳብ ቁጥር
1000079536141 በሚል ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።
                           እናመሰግናለን።
                           የት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል።

Tinsae Holistic School

27 Dec, 17:08


Dear Parents,
Today we held an Academic Contest in Math and English for our grade 6 and 8 students. It was a fantastic opportunity for them to showcase their skills and learn from each other.
Thank you for your continued support of our students' academic growth.

Tinsae Holistic School

09 Dec, 06:20


ሰኞ/ህዳር 30 ቀን/2017ዓ.ም

ውድ ወላጆች:-
የታህሳስ ወር የትራንስፖርት ክፍያ የሚከፈለው ከህዳር 25 እስከ ታህሳስ 5 ቀን ፣ 2017ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ክፍያዉን ከፈጸሙ በኃላ የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ክፍያውን እንድታወራርዱ ማሳሰብ እንወዳለን።
ማሳሰቢያ
1. ይህ የትራንስፖርት ክፍያ በሩብ አመት ክፍያ የሚከፍሉ ወላጅዎችን አይመለከትም። የትራንስፖርት ክፍያቸውን በወር የሚከፍሉ ወላጅዎችን እንጂ።
2. የትራንስፖርት ክፍያ የሚፈጸመው
     ሀ.በኦሮሚያ ባንክ ትንሳኤ አሰፋ ገሰሰ የሂሳብ ቁጥር C/A 1424151100002 ወይም
    ለ. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: ትንሳኤ አሰፋ ገሰሰ
የሂሳብ ቁጥር
1000079536141 በሚል ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።
                           እናመሰግናለን።
                           የት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል።

Tinsae Holistic School

05 Dec, 08:11


Grades 5 to 8 Best Students Award of the 1st Quarter in different categories.

Tinsae Holistic School

22 Nov, 16:35


የዛሬው የወተመህ ስብሰባችን አድማሱን በማስፋት በአካል ከኛ ጋር ያልነበሩ አባላትን በኦንላይን ያሳተፈ ነበር።

Tinsae Holistic School

22 Nov, 16:31


ዛሬ ህዳር 13 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም ከወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት (ወተመህ) ጋር ውጤታማ ስብሰባ አድርገናል። በስብሰባችንም የባለፈውን ወር ቃለጉባኤ ገምግመን አጽድቀናል። በባለፈው ወር ስብሰባው ወቅት የተቀበልናቸውን ዝርዝር ተግባራት ክንውን ገምግመናል። እንዲሁም የወተመህን የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አጽድቀናል። በመጨረሻም ወራዊ የምልከታ መርሃ ግብር በማውጣትና ለቀጣይ ስብሰባ እንዲከናወኑ የተለያዩ ተግባራትን በመከፋፈል የዛሬውን ስብሰባ አጠናቀናል። እናመሰግናለን!!

Tinsae Holistic School

15 Nov, 10:41


በዛሬው እለት ተማሪዎቻችን እጅግ አስደናቂ እና ዲሞክራሲያዊ የሆነ ምርጫ ያከናወኑ ሲሆን ከተወዳደሩት ሶስት ፖርቲዎች የዳይመንድ ፓርቲ በአብላጫ ድምጽ ምርጫውን ማሸነፍ ችሏል።

Tinsae Holistic School

27 Oct, 09:49


ውድ ወላጅዎች
ስኖዝ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግል ስራ ማህበር በሶስተኛ ዙር እስከ ጥቅምት 5 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ድረስ ክፍያ ለፈጸሙ ተማሪዎች ያዘጋጀውን ተቀያሪ የደንብ ልብስ ያመጣ በመሆኑ ከነገ ማለትም ሰኞ፣ ጥቅምት 18 ጀምሮ  ከቀኑ 10፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ብቻ ክፍያ የፈጸማችሁበትን  ኦርጂናል ፕሪንት የተደረገ ደረሰኝ በመያዝ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ (ከሞባይል ስልክ ላይ ደረሰኝ የማናይ መሆኑን አስቀድመን ማሳወቅ እንወዳለን)፡፡
ማስታወሻ
 ተማሪዎቹ ቱታውን ለክተው የሚወስዱ በመሆኑ ስትወስዱ አብረው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 ተማሪዎች ተቀያሪ የደንብ ልብሱን መልበስ የሚችሉት በሳምንት ሶስት ቀን (ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ) ብቻ ሲሆን ከነዚህ ቀናት ውጪ ቱታውን መልበስ የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ 
እናመሰግናለን!

Tinsae Holistic School

16 Oct, 05:21


Incorporating regular physical exercise into your routine can lead to significant improvements in both physical and mental health. Whether through structured workouts, sports, or everyday activities, the benefits of staying active are profound and far-reaching, contributing to overall well-being and quality of life.

Tinsae Holistic School

16 Oct, 05:20


Morning Physical exercise with our PE teacher,Ms.Situme.Thank You!!

Tinsae Holistic School

15 Oct, 04:30


Part 2

ጉልበተኛነት (bullying) የሚደርስባቸውን ልጆች ለመርዳት ምን እናድርግ?


▪️ስሜታቸውን ያዳምጡ 👂👂

👉🏼ልጅዎ ፍርድን ሳይፈሩ ሀሳባቸውን እና ስሜታቸውን እንዲገልጹ እርዱዋቸው።

ለምሳሌ፡ ልጅህ ትምህርት ቤት ስለመሄድ መጨነቅ እንደሚሰማው ከተናገረ፣ “እንደዚህ አይነት ስሜት መሰማት ሊያጋጥም እንደሚችል መንገርና ስሜታቸው ትክክል እንደሆነ ማረጋገጥና ቀስ ብሎ ማዳመጥ ያስፈልጋል።

👉🏼ልጅዎ ብቻቸውን እንዳልሆኑ እና በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እነሱን ለመደገፍ አብራችዋቸው እንዳላቹ ይወቁ።

▪️መረጃን መሰብሰብ

👉🏼ስለ ጉልበተኝነት (bullying) ምን እንደተፈጠረ በደንብ ለማወቅ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።ት/ቤት የተፈጠሩ ነገሮች ካሉ መጠየቅ

ምሳሌ፡ ዉሎዋቸውን መጠየቅ ፣በምሳ ሰአት/ ክፍል ዉስጥ ምን ተፈጠረ? ማን ተሳተፈ፣ እና ይህ ምን ያህል ጊዜ ይከሰታል?
ጓደኛቸው ማን እንደሆነ? ............

▪️የመቋቋሚያ ስልቶችን ያስተምሩ

♦️ልጆች ጠበኛ ሳይሆኑ ስሜታቸውን በልበ ሙሉነት እንዲገልጹ ማስተማር።

♦️ልጅዎ ስለ ጉልበተኛው(bullying)  ምን እንደሚሰማቸው ለመግለጽ የ"እኔ" መግለጫዎችን እንዲጠቀም ያበረታቱ።
ለምሳሌ፡ “እነዚያን ነገሮች ስትሉኝ አዝኛለሁ።”

♦️አንዳንድ ጊዜ, በጣም ጥሩው ምላሽ እራሳቸውን ከሁኔታዎች ማራቅ ነው.
   ለምሳሌ፡ በቡድን እያሾፈባቸው ከሆነ፣ ልጅዎ እንዲህ ሊል ይችላል፣ “የዚህ አካል መሆን አልፈልግም፣” እና በልበ ሙሉነት መሄድ።

♦️ልጅዎ መጨናነቅ ሲሰማቸው ከጓደኞቹ፣ ከአስተማሪዎች ወይም ከቤተሰብ ጋር እንዲገናኝ ያበረታቱ።
   ለምሳሌ፡ ለአስተማሪ፣ አንዳንድ ልጆች እያስጨነቁኝ ነው፣ እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም።”“እርዳታ እፈልጋለሁ ሊሉ ይችላሉ።

♦️ጭንቀት ወይም ብስጭት ሲሰማቸው ልጅዎ እራሱን ለማረጋጋት ዘዴዎችን ያስተምሩ።
   
   ለምሳሌ፡ የመተንፈስ ልምምዶች፣ እንደ ጥልቅ ትንፋሽ ለአራት ጊዜ መተንፈስ በአስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲረጋጉ ይረዳቸዋል።

♦️ለራስ ያላቸውን ግምት የሚያሳድጉ እና ከጉልበተኝነት(bullying)  የሚያዘናጉ በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ወይም እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍን ያበረታቱ።
ለምሳሌ፡  ስፖርት፤ስዕል፤ሙዚቃ

♦️ልጅዎ ሃሳባቸውን እና ስሜታቸውን ለመግለጽ ጆርናል እንዲይዙ ይምከሩ።
   ለምሳሌ፡ ስለ ቀናቸው መጻፍ ይችላሉ፣ አዎንታዊ ልምዶችን እና ማንኛውንም የጉልበተኝነት (bullying)  ክስተቶችን ጨምሮ፣ ይህም ስሜታቸውን እንዲያካሂዱ
ይረዳቸዋል።

♦️ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ከአስተማሪዎች፣ አማካሪዎች ወይም የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ጋር ስለሁኔታው ይነጋገሩ። ለምሳሌ፡ መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ ያለውን መረጃ በመያዝ ፣ ለትምህርት ቤቱ አማካሪ፣ “ልጄ ከክፍል ተማሪዎች ጉልበተኝነት (bullying)  እየደረሰበት ነው፣ እና ይህን እንዴት መፍታት እንደምንችል መወያየት እፈልጋለሁ።”

♦️በልጅዎ የአእምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረ የአእምሮ ጤና ባለሙያ ማማከር !!

በልጅዎ ህይወት ውስጥ የወላጅ መገኘት ወሳኝ ነው። ግልጽ ግንኙነትን ያበረታቱ እና ሁልጊዜ ለእርዳታ ወደ እርስዎ መምጣት እንደሚችሉ ያሳውቋቸው። በእነዚህ እርምጃዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ፣ ልጅዎ የጉልበተኝነት (bullying)  ፈተናዎችን በብቃት እንዲዳስስ መርዳት ይችላሉ።

ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው (ጠቅላላ ሀኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ)

Tinsae Holistic School

14 Oct, 17:30


Part 1

ጉልበተኝነት(bullying)

ጉልበተኝነት(bullying)  ማለት በአንድ ልጅ  ወይም በቡድን የሚደረግ ተደጋጋሚ እና ሆን ተብሎ የሚደረግ  ጥቃት ወይም የማስፈራራት ተግባር ነው። ይህም በመምታት ፣ በመጥፎ ቃል፣ የተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም ሊሆን ይችላል። ዓላማው ብዙውን ጊዜ ተጠቂውን ልጅ ለመጉዳት፣ ለመቆጣጠር ወይም ከነሱ በታች እንዲሆን  ለማድረግ ነው።

በልጆች መካከል በጣም የተለመዱት የጉልበተኝነት(bullying) ዓይነቶች

1. የቃል ጉልበተኝነት (Verbal Bullying)
•  በተደጋጋሚ ስም መጥራት፣ ማሾፍ ወይም አዋራጅ አስተያየቶችን መስጠት።ይህ ብዙውን ጊዜ በትምህርት ቤት ውስጥ በጣም ይታያል።
2. ማህበራዊ (ግንኙነት) ጉልበተኝነት(Social (Relational) Bullying)
•  እኩዮችን ከቡድኖች ማግለል፣ ስለነሱ ወሬ ማሰራጨት ወይም ጓደኝነትን መጠቀም።
•  ይህ ብዙ ጊዜ በሴት ልጆች መካከል የተለመደ ነው፣ በተለይ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ስለሚያነጣጠር ጎጂ ሊሆን ይችላል።

3. አካላዊ ጉልበተኝነት (Physical Bullying)
•  መምታት፣ መግፋት ወይም ሌላ አይነት አካላዊ ጥቃት።

4. የሳይበር ጉልበተኝነት (Cyberbullying)
•  እንደ ማህበራዊ ሚዲያ፣ የጽሑፍ መልእክት ወይም ጨዋታ ባሉ ዲጂታል መድረኮች ላይ ይታይል።
•  በልጆችና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መጨመር ጋር ተያይዞ በጣም እየጨመረ ነው።

ጉልበተኝነት (bullying) የሚያስከትለው ጉዳት

1.  ስሜታዊ ተፅእኖዎች:
•  ከፍተኛ ጭንቀት
•  ዝቅተኛ በራስ መተማመን እና ለራስ ከፍ ያለ ግምት
•  የብቸኝነት ስሜት መጨመር

2.  አካላዊ ተፅእኖዎች:
•  ራስ ምታት, የሆድ ህመም እና ሌሎች ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ምልክቶች
•  የእንቅልፍ መዛባት

3.  የአካዳሚክ ተፅእኖዎች:
•  በትምህርት መቀነስ
•  ከትምህርት ቤት መቅረት መፈልግ
የረጅም ጊዜ ተፅእኖዎች:
•  ቀጣይነት ያለው የአእምሮ ጤና መታወክ
•  ግንኙነቶችን ለመፍጠር መቸገር
•  የአደንዛዥ ዕፅ የመጠቀም እድል መጨመር

Tinsae Holistic School

14 Oct, 11:42


ከ9ኛ - 11ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በሙሉ፡፡
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM ትምህርት ለመማር ለምትፈልጉ አዲስ ተመዘገቢ ተማሪዎች እንዲሁም ለነባር ስቴም ተማሪዎች በሙሉ ::
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM ትምህርት
1. Level 1: Basic Science Courses
2. Level 2: Engineering Courses
3. Level 3: STEM Innovation Project
የሚያስተምር ሲሆን የSTEM ትምህርት ከጥቅምት 23/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር ቅዳሜ የስቴም ትምህርት ስልጠና መርሃ ግብር ያዘጋጀ ስለሆነ ለመማር ፍላጎት ያላቹህ አዲስ ተመዘገቢ ተማሪዎች እንዲሁም ለነባር ስቴም ተማሪዎች ከመስከረም 21/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ደርስ በሌቭል 1 ለምትመዘገቡ (ከ 9ኛ እስከ 11ኛ ደረጃ ተማሪዎች)
• 2016 ዓ.ም ሪፖርት ካርድ (ውጤት) ኮፒ
• ከምትማሩበት ትምህርት ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ
• የትምህርት ቤት መታወቂያ ኮፒ
• የወላጅ/አሳዳጊ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ እና የስልክ ቁጥር በማዘጋጀት እንዲሁም
1. በሌቭል 2 ለምትመዘገቡ፡ በሌቭል 1 ስትማሩ ያገኛቹሁት የምስክር ወረቀት ኮፒ እና አማካኝ ወጤታቹሁን እና
2. በሌቭል 3 ለምትመዘገቡ፡ በሌቭል 2 ስትማሩ ያገኛቹሁት የምስክር ወረቀት ኮፒ እና አማካኝ ወጤታቹሁን በዚህ ጎግል ቅጽ ላይ (https://forms.gle/dTnV8QvLSzVd43Ve9) በመሙላት እንድትመዘገቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ማሳሰቢያ፡-
1. ምዝገባው በዚህ ጎግል ቅጽ ላይ ብቻ ስለሆነ (https://forms.gle/dTnV8QvLSzVd43Ve9) ለመማር ለሚፈልጉ አዲስ ተመዘገቢ እንዲሁም ነባር ተማሪዎች እንዲመዘገቡ እና መረጃ እንዲደርሳቸው የቴልግራም አድራሻችንን (https://t.me/aastustemcenter) እንዲቀላቀሉን እንድትነግሩልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
2. ቅጹ ላይ ስትመዘገቡ የግል e-mail አድራሻ ሊጠይቃቹህ ይችላል።

Tinsae Holistic School

13 Oct, 15:36


ውድ ወላጅዎች/ ህጋዊ አሳዳጊዎች

ነገ ማለትም ሰኞ፣ ጥቅምት 4 ቀን፣ 2017 ዓ.ም 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን ፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበር በመሆኑ ትናንሽ ሰንደቅ አላማ ያላቸው ተማሪዎች ይዘው ይመጡ ዘንድ በአክብሮት እየጠየቅን በተጨማሪም የኬጂ/ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ የሰንደቅ አላማ ቀለም ያላቸውን ፊኛዎች እያውለበለቡ ይመጡ ዘንድ እንጠይቃለን።

እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር

Tinsae Holistic School

13 Oct, 11:38


Communication Book
1.  Parents must check this book daily.

2.  Homework is given daily, and it is serious. Families should help students with the homework, but they should not do for the child.

3. Parents must sign after they have seen the homework is done properly.

4. It is the responsibility of the family to closely follow the student and communicate actively with the teacher and the school.

5.  Parents must sign the book daily to indicate that they have read all messages and helped the child to complete the homework.

6. We encourage all families to communicate with the teacher by writing their comments, ideas, and suggestions in the book.

7. Being an active parent is the best way to ensure your child’s success.

8. Make sure that your child's Handwriting is getting improved time to time.

9. Letters and slips should not be removed from this book.

10. Do your best in all things.

Thank You!
The School Administrator

የወላጅ ት/ቤት መገናኛ መጽሐፍ ተማሪዎችን ለመከታተል ዋና መሣሪያ ናቸው፡፡
1. ወላጆች ይህን መጽሐፍ በየቀኑ ማየት አለባቸው ።

2.  የቤት ስራ በየቀኑ ይሰጣል፤ እናም  ትኩረት ያስፈልገዋል። ቤተሰቦች ተማሪዎቻቸውን የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ መርዳት አለባቸው:: ልጅን ተክቶ መሰራት ግን ተማሪዎችን ውጤታማ አያደርግም፡፡

3. ወላጆች የቤት ስራው በትክክል መሰራቱን ካዩ በኋላ መፈረም አለባቸው።

4. ተማሪውን በቅርበት መከታተል እና ከመምህሩ እና ከትምህርት ቤቱ ጋር በንቃት መነጋገር የቤተሰብ ሃላፊነት ነው።

5. ወላጆች ሁሉንም መልዕክቶች እንዳነበቡ እና ተማሪው/ዋ የቤት ስራውን እንዲያጠናቅቅ እንደረዱት/እንደረዷት ለማሳየት በየቀኑ መጽሐፉን  ማየትና መፈረም አለባቸው።

6. ሁሉም ቤተሰቦች አስተያየቶቻቸውን፣ሀሳቦቻቸውንና ምክረ ሃሳቦቻቸውን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በመጻፍ ከመምህሩ/ከመምህሯ ጋር እንዲገናኙ እናበረታታለን።

7.ንቁ ወላጅ መሆን የልጅዎን ስኬት ለማረጋገጥ ምርጡ መንገድ ነው።

8. የልጅዎ የእጅ ፅሑፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሉን አጥብቀው ይከታተሉ።

9. ደብዳቤዎች እና መልዕክቶች ከዚህ መጽሐፍ ጋር እንደተያያዙ መገኘት አለባቸው፡፡

10. በሁሉም ነገር የላቀውን ነገር አድርጉ።

የት/ቤቱ አስተዳደር

Tinsae Holistic School

12 Oct, 17:46


ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት(ወተመህ) ጋር ውጤታማ ስብሰባ አድርገናል።በስብሰባችንም የ2016ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ገምግመናል።እንዲሁም የወተመህ የ2017ዓም ዕቅድና ዝርዝር ተግባራትን በመለየትና የክፍያ ጭማሪን ተከትሎ ተቋሙ ያደረጋቸውን ዝርዝር ማሻሻያዎችን ተቋሙ ለወተመህ አቅርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።በመጨረሻም የሐምሌ 19 ቀን 2016ዓም ቃለጉባኤ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ የዛሬውን ስብሰባ አጠናቀናል።እናመሰግናለን!!