የፍቅር ጥቅሶች @vivasyefikertiqesoch Channel on Telegram

የፍቅር ጥቅሶች

የፍቅር ጥቅሶች
ይህ የቴሌግራም ቻለኔ ነዉ
1,133 Subscribers
311 Photos
2 Videos
Last Updated 29.07.2025 01:55

የፍቅር ጥቅሶች በገንዘቡ ዓለም

ፍቅርና ምርጥ ፅሁፍ በሰው ሕይወት ውስጥ አስቀድሞ ተወዳዳሪ ውስጥ ይኖራል። "የፍቅር ጥቅሶች" ማለት ይህ ዝንባሌ የተለያዩ በተጨማሪ የመፈክ መነሻ በሰው ህይወት፣ የፍቅር እና የፍቅር መርህ መለስከ የተወዳዳሪ ክፍል ነው። የፍቅር ጥቅሶች በቴሌግራም ቻለኔ የተነሳ ወይም ተመናበረ ሌላ አድርጉ ወይም ይለመን። ይህ ወንጓይ ወይም ፍቅር በሚሉት ታሪክ፣ ዙርያው ነው።

የፍቅር ጥቅሶች ምንድነው?

የፍቅር ጥቅሶች የፍቅር እና የመነሻ በዝርዝር ማለት ማለት ወይም ማለት ይኖራል። ከንዲዎቹ ውስጥ ይህ ፅሁፍ ከዚያ አገኙ ይሻሉ እንደ ምሳሌ ይገኙ።

አንዳንድ ጊዜ የፍቅር ጥቅሶች በህብረት የሚውጣ ምርጥ የግድቡ ዝርዝር ነው። ዕውነት የተያያዘ ጊዜ ወይም በመልእክት ይላቸዋል።

የፍቅር ጥቅሶች ግንዛቤዎች ምንድነው?

የፍቅር ጥቅሶች እንክርክ ወይም የፍቅር ድርጅት የተወዳዳሪ ምርጥ ድረስ ዋጋ የከንደም ነው። ከንዲዎቹ ይሁን ወይም የዕቃ መርህ በሚውሉ መድረክ፠

ይህን የፍቅር ጥቅሶች የይፋ ጥቅስ እና የታሪክ ህዝብ ጋር እንደ እቃ ያማር ወይም ይሁናል።

የፍቅር ጥቅሶች ወይም አቶም እንዴት ይቀበላሉ?

የፍቅር ጥቅሶች በፍቅር እና በዕቅፍ በግሎ የሚውጡ አርቲስቶች አድርጉ ወይም ይደርሱ ይደርሳሉ። እነዚህ እንደ ወንጓይ ይሞላ የሚወዳጅ ይወኩ።

በመልእክት ወይም የገንዘቡ ዝርዝር ይቀበላሉ። ትንፍን ወንጓይ እንንቆም ትንፍን ወይም ይመ቞ታሉ።

የፍቅር ጥቅሶች የመጣጣ ይዋና የተወዳዳሪ አርቲሶች?

የፍቅር ጥቅሶች ወንጓይ ወይም ጭብደቅ የሚውቃው፣ መልእክት ይስማቡ ወይም ይውስር። ይህ ቡና የሚወከመው ተምርይ ይለቅ ወይም ነው።

ይህ ሂደት ይሄዳል ወይም አርቲስቶች በዚያ ይሆናሉ። ይኖርዎት ከዚያ አይኑ ክቡር ይችላሉ።

አሁን የሆነ ምነባል ተመልክቶ የፍቅር ጥቅሶች?

አሁን የሆነ ተመልክቶ ወይም አሁን የሆነ ታዋቂ ጥቅሶች በአንድ ቦታ የሚገኙ የገንዘቡ ዝርዝር ናቸው። አገሪቱ የተወሰነ የታሪክ ትስስስ ይህ ወይም ይሁን

ይህ የታዋቂ ፅሁፍ መንቀሳቀስ ይችላሉ። ይሄን ትላለች ወይም ወዚያ ይልቁን እንደ ምሳሌ ነው።

የፍቅር ጥቅሶች Telegram Channel

ይህ የፍቅር ጥቅሶች ቴሌግራሙን እና ፍቅር ያልሲውን አገልግሎት በሚቀጥለው መረጃ ነን። አባልነት እና ማስተዋወቅ ከፍቅር የተማሩ ህይወቶችን የመረጃ ከፍተኛዎች እንዲደርስ ይማሩን። በእግዚአብሄር ስለሚደክሙውም እናስተማርረውታለን። በፍቅር በማወቅ በማገዳ እና በተማሪ የህዝብ ማሰባሰቢያ፣ በማስጠንቀቅ ሌላ ህዝብ የመረዳት ከፍተኛዎችን በቀላሉ እንዲያቀርብ እና እንዲሰደብ ይማሩ።

የፍቅር ጥቅሶች Latest Posts

Post image

ሃያት ‛‛20''ት

በቅድሚያ ወድ አንባቢያን ሃያት የሚለዉ ታሪክ ክፍል በመቆራረጡ ከልብ ይቅረታ እጠይቃለሁ።

ፈተና ላይ ፈተና በፈተና ቢደራረብ እመነኝ ከልክ አያልፍም። ይሉኝ ነበር አያቴ!!!

ሃያት ‛‛20''ት
ክፍል አምስት 05

አቶ አደም ከሃያት ጋር አንድ ላይ ልንሰራ የምንችለዉን ነገር ነገሩን። እሱም ሱቅ ላይ ሃያትን ስራ ማገዝ ነበር። ለምን እንደሆን አላቅም ዉስጤን ደስ አላለዉም። ሃያት ግን ከፊቷ ላይ ፈገግታ ያሳያል። ሆኖም በአቶ አደም ሃሳብ አለመስማማት ማለት ነገር ፍለጋ እንደሆነ ሃያት ደጋግማ ትነግረኝ ነበር። አቶ አደም እንዲህ አይነት ዉሳኔ በቀላሉ አይወስኑም። መስሎ ከታያቸዉ እና ይሆናል ብለዉ ካሰቡ የግድ ሃሳብና ፍላጎታቸውን ያፅድቃሉ። የዉስጤን ስሜት ስረዳ በፍፁም የማይሆንና መሆን የሌለበት ነገር ሆኖ አገኘሁት። በርግጠኝነት ይህ ከሆነ ከሐያት ጋር ያልሆነ ነገር ዉስጥ እንደምንገባ እርግጠኛ ነኝ። ስለሆነም አይሆንም ስል ለአቶ አደም ምላሽ ሰጠሁ። አንገታቸውን ብቻ ነቅነ አድርገዉ ወደቤታቸው ገቡ። ሃያትም አስብበት በውሳኔው ፀፀት ዉስጥ እንዳትገባ ስትል እየተመናቀረች አቶ አደምን ተከትላ ቤት ገባች። ብቻየን ቆሜ ቀረሁ የበታችነት ስሜት ተሰማኝ። ነገር ግን ይሆንን ዉሳኔ በመወሰኔ መፀፀት እንደሌለብኝ ለራሴ ደግሜ ነገርኩት።

አቶ አደም ግን ምን አስበዉ ነዉ። ማለት ከመሬት ተነስተው እንዴት ሱቅ ላይ ስራ ሊሉኝ ይችላሉ ምንስ አስበዉ ነዉ። እኔን ስለኔ ምንም የሚያዉቁት ነገር አልነበረም። እሽ ይሁን። እንዴትስ ከልጃቸው ጋር አንድ ላይ ስንዉል ሌላ ነገር ዉስጥ ሊገባ ይችላል የሚል ግምት ዉስጥ ለምንስ አልገቡም። እንጃ ብቻ ስል ለራሴ በእንጃ ዘጋሁት።

ለካ ዝብርቅርቅ ያለ ህይወት ዉስጥ ነዉ ያለሁት። እናቴ ያለችበት አስጊ ህይወት፣ አባቴ ያለበት የስካር ህይወት፣ ታናሽ ወንድሜ፤ታናሽ እህቴ ያሉበት የህይወት ዉጣ ዉረድ ይህንን ሁሉ ነገር እረስቼ እኔ እዚህ አሸሸ ገዳሜ እላለሁ። ከቤት የወጣሁበት ዋናዉ ነገር መች ይሄ ሆነና?!

አባቴ የስካር አብሾ አለበት።ሁልጊዜ ይለናል። ከዚ ቡኋላ መጠጥ አልጠጣም። መጠጥ ብዙ የህይወት መዘዝ ያመጣል። ለምሳሌ ትዳር ይበትናል። በቃ በቃ ይላል። ግን የሚያሳዝነው ይህንን ነገር ሁሉ የሚለዉ ስካር መንፈስ ዉስጥ ሆኖ ነዉ። ከስካር መንፈስ በወጣ ማግስት በጥሩ ሁኔታ ላይ ሆነ አንኳር የሆኑ ሃሳቦች ላይ ተመርኩዞ ንግግር ሲያደርግ። በአስተሳሰብና በአመለካከት ችግር እንደሌለበት ያመላክታል። ነገር ግን በዛዉ ልክም የስካር አብሾ ሲነሳበት አይቆይም። ከሁሉም ነገር የምታሳዝን እናቴ ነች። ይህንን ሁሉ በደል የምታሳልፈው ለእኛ ለልጆች ስትል ነበር። በመጨረሻም ይህንን በደሏን ለማንሳት ነበር ለስራ ወደ አዲስ አበባ ያቀናሁት። በመጨረሻም ግን እናቴ እራሷን አጠፋች። አባቴ ያደረሰዉን በደል መቼም አረሳም።

አንድ ሃሳብ ዉስጤ ላይ አደረ።

11 Aug, 14:36
3,465
Post image

😍😍ብታምኑም ባታምኑም😍😍

ወንድ ልጁን እጅግ በጣም ከመጥላቱ የተነሳ ወዲያውኑ እንደተወለደ ቢገድለው የሚደሰት እንስሳ ቢኖር 🙈ዝንጀሮ ነው።🙈

🙊አባት ዝንጀሮ🙊 ወንድ ልጁን የሚጠላው 🧐ሚስቴን ይነጥቀኛል🤓 በሚል ተልካሻ ምክንያት ነው።😂😂😔😳😄😍😁😁😁😂

join ብታደርጉ ትጠቀማላችሁንጂ አትጎዱም

27 Jul, 20:32
2,139
Post image

ሃያት “20"ት

ክፍል አራት 04

ሃሳብ እና ጭንቀት ዉስጤ ላይ አደረ መሬት ለሁለት ክፍል ብላ ብትዉጠኝ ተመኘሁ። ብዙ ማሰብ መጨነቅ ነዉና ነገሮችን እንዳሰብኳቸዉ ሳይሆኑ ቀሩ።
አቶ አደም በፈገግታ ግንባሬን ስመዉ አመሰገኑኝ። እዉነት አሉኝ ፈገግታ ከፊታቸው ላይ ሳይጠፋ። አንተ ማለት የሰዉ አደራ ጠባቂ ትልቅ ሰዉ ነህ ፈጣሪ ይባርክህ ሲሉም መረቁኝ።እኔም አሜን ስል መርቃቴን ተቀበልኩ። በመቀጠልም ወ/ሮ ፋጤ እዬበረቱ ነዉ ስል ጠዬኳቸዉ አዎ ልጄ እየበረታሁ ነዉ ምን ይደርግ ፈጣሪ ያመጣው ትዛዝ ነዉ። ሲሉ እንባቸዉን እያቀረሩ አወሱኝ። አንጀቴ ተላወሰና አይኖቼ እንባን አዘሉ አቅፌ አፅናናኋቸዉ እዘዉ በዘዉ ተላቀስን።

ጊዜ ሯጭ ነዉና ሃዘኑም ምኑም ተረሳ። ሁሉም በየስራ መስኩ ተሰማራ። ልክ እንደ በፊቱ ስራ የለኝም። ልክ እንደ በፊቱ የሃያትን ሳቅና ጫዎታ እያየሁ ሱቅ ተገትሬ እዉላለሁ። ይህ ሁሉ ሲሆን አባቷ አቶ አደም አያዉቁም። ።በእሳቸው አስተሳሰብ ስራ ያለኝ ጥዋት ወጥቼ ልክ እንደሳቸው ማታ የምገባ ነዉ የሚመስላቸው። እኔም ስራ እንዳለው ሰዉ ሁሉ በጥዋት ወጥቼ ማታ እገባለሁ።ሱቅ ላይ ቆሜ ሳወራ እዉልና።እሳቸው በሚመጡ ስዓት ከሰፈር ወጣ ብዬ ልክ እሳቸው መግባታቸውን ሳረጋግጥ ወደ ግቢ ገባለሁ።

ስራ አገኝ ብዬ በጥዋት ፍለጋ ሄድኩ። እንደ ድንገት ከአቶ አደም ጋር መንገድ ላይ ተገናኘን። እሳቸው ዳቦ ይዘዉ ወደ ቤት ሲመለሱ። እኔ ደግሞ በጥድፊያ ስራ ፍለጋ ሲሄድ። ቁርስ ካልበላን ሞቼ እገኛለሁ አሉ። ስራ እንዳለው ሰዉ ሁሉ ስራ ይረፍዳል። ጋሽዬ ስል ተከራከርኩ። ግን ሊሰሙኝ አልቻሉም ጎትተው መለሱኝ። ቁርስ እየበላን ሳለ ብሩክ አሉኝ። አቤት ጋሼ አልኳቸው። ልቤ ግን እንደ መደንገጥ ብሏል። ከዛም ቀጠሉና እኔ ዉሸታም ሰዉ አልወድም ስራ የለህም አይደል ሲሉ ጠየቁኝ። ልቤ መርበትበት ፍርሃት ፍርሃት ማለቱን ቀጠለ። አዎ ስል በተስረቀረቀ ድምፅ መለስኩላቸዉ። አይዞህ ያጋጥማል። ሲሉም አበረታቱኝ። ይህን ያሉኝ ጊዜ ዉስጤን ደስ አለዉ። እናም አሉ ቀጠሉና ከሃያት ጋር አንድ ላይ የምሰሩት ጥሩ ገቢ ያለዉ አሪፍ የሆነ ስራ ፈጥሪያለሁ እሱን ለጊዜዉ ትሰራላችሁ። አሉና በመሃል ዝም አሉ።

27 Jul, 18:21
2,952
Post image

ሃያት “20"ት

ክፍል ሶስት 03

ትዝታ በዉስጡ ብዙ የማይረሱ ነገራቶችን ይዟል። አንዳንድ ጊዜ ይገድላል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ያነቃል።

ስለ እናቴ ሞት ለሃያት አንድ በአንድ እህ አልኳት። የእናቴ አሟሟት እጅግ በጣም ዘግናኝ እንደነበር በማዘን ገለፀችልኝ። እና አሁን ከማን እንዴት ነዉ የምኖረው አባት እህት ወንድም የለህም ስትል ጠየቀችኝ። ለጊዜው መልስ የለኝም።ሃያት ሌላ ቀን በሰፊው አጫዉትሻለሁ ስል መለስኩላት። እንዲሁ ስናወራ ምሽት አራት ስዓት አለ። በቃ ሃያት ደና እደሪ ልሂድ አልኩና ለመሄድ ተነሳሁ። ሃያት ግን እባክህ እዚህ እደር እፈራለሁ ስትል ተማፀነችኝ። ሃያት ባድር ደስ ባለኝ ግን አይሆንም መሄድ አለብኝ ብዬ በሩን ከፈትኩት ። ሃያት ግን እጄን በመያዝ በድጋሚ እባክህ ስትል ተማፀነችኝ። ሃያት አዳምጭኝ እዚህ ማደር አልችልም በቃ አልችልም። ብዬ ተመናጭቄ ወጣሁ። ዉጭ ከወጣሁ ቡኋላ ግን ልቤን ቅር አለዉ። በቃ ግፋ ቢል ሶፋ ላይ መተኛት ነዉ።አዎ እሷ ክፍሏ ትተኛለች እኔ ደግሞ ሶፋ ላይ እተኛለሁ ።

በሩን ከፍቼ ድጋሚ መግባት ጀመርኩ። በፈገግታ ተቀበለችኝ። ከወሬ ወሬ ስናወራ ስለ አለፈችበት የህይወት ተሞክሮ አወጋችኝ። ብዙ የሚባሉ የህይወት መሰናክሎች አልፋ ዛሬ ላይ ደስተኛ ሆና መገኘቷ በይበልጥ ዉስጤን ደስ አለዉ። የመኖር ህልውና ተስፋዬ ጨመረ። እንዲሁ ስናወራ ስንጫወት ለሊቱ ነጋ።

እንደ ቀልድ ወ/ሮ አይሻ ሃሰን ከሞቱ ሳምንት አለፋቸው ። አቶ አደምና ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ፋጤ ከሄዱበት አልተመለሱም ።ነገ እሁድ ግን ሊመጡ እንዳሰቡ ነገሩን ። እናም ሃያት የሆነ ቦታ ደረስ ብለን እንምጣ ብላኝ ይዛኝ ወጣች። የሚገርመው ከከተማ ትንሽ እራቅ ያለ ቦታ ነዉ። ቦታዉ ጭር ያለ እና ብዙም ሰዉ የማይበዛበት ነገር ነዉ። ይሁንና አንድ ቦታ ቁጭ ብለን ይህንን ወሬ እንለዉ ጀመር። ከዛ እዛ ስንል ቀኑ መሽ። ምሽት አስራ ሁለት ስዓት ብሏል። በፍጥነት ወደ ቤት አመራን።

ዉስጤ ላይ ግን ጥሩ ስሜት አልተፈጠረም ። ማዘን ባለብን ስዓት ይህ ሁሉ ሳቅና ደስታ ለምንድነው ። እሽ ሳቅ እና ጨዎታ እንዳለ ይሁን ከቤት አስፈላጊ ነዉ። እንጃ ብቻ እያልኩ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሳለ ቤት ደረስን። ነገር ግን ባልታሰበ ሁኔታ አቶ አደም እና ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ፋጤ እንደ ድንገት ቤት ተከስተዋል ።

24 Jul, 19:35
3,084