አስትሮሎጂ @astrologytube23 Channel on Telegram

አስትሮሎጂ

@astrologytube23


በዚህ ቻናል ➲➫ ☆☆ ኮከቦች ላይ ትኩረት አድርገን የህይወትን ድብቅ ገመና የምናይበት፣ ስለ ሰው ልጅ ባህርያት የምንወያይበት፣ የምንመረምርበት በዋናነት ደግሞ ጊዜን ቀድመን የምንቃኝበትና ➽የዓለም ምስጢራትን ሁሉ የምንዳስስበት እንዲሁም አዝናኝ መረጃዎችን የምናቀርብበት ገፃችን ነው።

➥➥ #ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ሀሳብ
በ @Akiya_a ልታደርሱን ትችላላችሁ።

አስትሮሎጂ (Amharic)

አስትሮሎጂ ከማንኛውንም አስተያየት በቀላሉ ከሚን ቢለው የህይወትን ድብቅ ገመና የምናይበት ጠቃሚ መከላከያና ትኩረት አድርገን ጋር በአገልግሎቱ እንዲሁም በዮሒቃንቕኘቂንጂን መረጃዎች ለማግኘት እና መረጃዎችን ለማግኘት በዓለም መስጠታዊ እና ህወሓት አስተያየት ማዘን የሚሆነው ቻናል ነው። የህይወትን ድብቅ ገመናን እና ከስለ ሰው ልጅ ባህርያት የሚናገር መረጃዎችን በዋናነት መረጃዎችን ከተቀረጸ እና ከመረጃዎች መብትን ለመልኩ ባህርያትን በመጠቀም የምግብ ምስጢራውን ሁሉ እንዳስስበት ቢሆን በቻናሉ ምስጢረን መረጃዎችን እንመለከታለን። በቻናሉ ለማንኛውንም መረጃ ውስጥ ማለፊያ በ @astrologytube23 በመተንከላው ደግሞ በዚህ ቻናሉ ሀሳብ መረጃዎችን አቅርቡ።

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:24


ሰላም 💓ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? ፣ አሁን የጀመርነው ምዕረፍ ወደ ማለቁ እየተዳረሰ ነው፣ ቀጣዩንም መዕራፍ ለመጀመርም እያኮበኮብን እንገኛል፣ በቅርብ ቀን ማለትም ይህ የጀመርነው ሲጠናቀቅ፣ በ ሌላ አዲስ ፕሮግረም #የኮከቦች ጥምረት በሚል ርእስ የእናንተን የውልደት ቀን መሰረት በማድረግ የትኛው ኮከብ ከየትኛው ኮከብ ጋር በትዳር ቢጣመር የተሻለ ይሆናል የሚለውን የእያንዳንዱን የኮከቦች ጥምረትን ከነባህሪያቸው ጋር አያይዘን// ይዘን እንቀርባለን ። ይህን ዝግጅት ከሌሎቹ ለየት ባለ መልኩ 👍 እንደምትወዱት እርግጠኞች ነን። እስከዛ ድረስ አሁን እየለቀቅንው ባለው ፕሮግራም አብረን እንቆያለን ማለት ነው።

ሌላው፦ እስካሁን ለየት ባለ መልኩ ስትደግፉንና ስታበረታቱን ለነበራቹ ከልብ እየመሰገንን፣ ቀጣይም አብራቹን እንድትቆዩ እየጠየቅን፣ ከታች ባለው (👍Like) 👇መስጫ ሳጥን የአብሮነት ማሳያ ድምፃችሁን ስጡን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።

➮መልካም ጊዜ🙏 መልካም አዳር🌚

📱@Akiya_a

🌈 @AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ቶረስ"――――

Sculptor, the money minded

»» Let it rain, let in rain .ቶረሶች እንዴት የዶላርን ቢል ወደ ወፍራም ቼክ መለወጥ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ። ሁሉንም የፋይናንሺያል ስራ ማሳካትና እንዴትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው፣ በረቀቀ መንገድ ተክነውበታል። የዞዳይኩ ፋይናንሺያል ማናጀር ናቸው። የማንንም እሴትና ጊዜ ዝም ብሎ ማበላሸት አይፈልጉም። የጄሚኒ፣ የሊብራ ወይ አኳሪየስ ተፅኖ ካለባቸው በስተቀር፣ ሁሉንም ተረጋግተው መጠበቅ ይችላሉ።

»» ለዚ ማሳያ የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግን ፣ ማየት በቂ ነው፣ the wealthiest younger billionaire person in world ቶረስ ባይሆን እዚ ቦታ መድረስ ትንሽ ይከብደው ነበር። ተረጋግቶና ጠንክሮ መስራትን ይፈልጋሉ፣ ለጉዞ፣ ለደሞዝ፣ ለትርፍ፣ ለበጎ አድራጎት ወይም ለሌላ ጉዳይ ሊሆን ይችላል ብቻ መስራት ይፈልጋሉ። ታጋሽ፣ ተማኝና በእቅድ የሚመሩ ናቸው።

»» በህብረት መስራት ይችላሉ፣ ነገር ግን ጥገኛ መሆን የለባቸውም፣ ለሚያምርና ውብ ለሆነ ነገሮች ጥሩ ግምት አላቸው፣ በውጤታማነት ያምናሉ፣ ውጤት እንዲኖራቸውም ይፈልጋሉ፣ አብዛኞቹ ቶረሶች ቱጃር ናቸው፣ ፈጥነውም ይሁን ዘግይተው የሚፈልጉትን በደንብ ያገኙታል።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ቆራጥ፣ ታታሪ፣ ታማኝ፣ ግትርና ማንኛውንም ከትንሽ እስከ ትልቅ በተሰጣቸው ወሰን ልክ ማጠናቀቅ ይችላሉ።


√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ኢኮኖሚስት፣ አካውንታንት፣ ኢንጂነር፣ ኮምፒተር ፕሮግራመር፣ ቴክኒሺያን፣ የቡድን መሪ፣ ኢንቬስተር፣ የቅንጦት እቃ መሸጫ ቤቶች፣ የህግ ባለሞያ፣ አርክ፣ ሞዴል ፋርመር፣ ሜክ አፕ አርቲስትና የመሳሰሉት ላይ ድንቅ ናቸው

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን ያልተጠና፣ በጀት የሚፈልግና ያለ ፕሮፖዛል መስራት፣ ትልቅ ኪሰራ ውስጥ እንዳይጥላቸው ያሰጋል።
.
.
.ይቀጥላል፣....መልካም አዳር ውዶቼ😘🙏
.
.

ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_aመጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ቪርጎ"――――

The master, eagle eyed

»» ቪርጎዎች እያንዳንዷን ነገር ጥንቅቅ ብለው ስለሚያዩ፣ ቴክኒካል ነገሮችን በደንብ የመስራት ብቃት አላቸው። ሚሰሩትንም ስራ ምርጥ አድርገው መስራት ይፈልጋሉ ምንም እንከን እንዲኖረው አይፈልጉም። ምርታማ ሰዎች ናቸው ማንም ማያየውንና ማይገነዘበውን ነገር ቁልጭ አድርገው ያያሉ።

»» ስራ ላይ አንደኛና ጎበዝ ናቸው፣ መስራት ለነሱ ገንዘብ ማግኛ መንገድ ብቻ ሳይሆን የደስታና ከጭንቀት ነፃ መውጫ መንገዳቸውም ጭምር ነው። ሁሉንም ሰው ማያስጨንቀውን ነገር ያስጨንቃቸዋል፣ ለዚህም ነው እንከን እንደይገኝበት አድርገው ሚሰሩት። ለምሳሌ ደራሲዋን አጋታ ክርስቲን ብናያት፣ ጥንቅቅ ያሉና እንከን ማይገኝባቸውን የወንጀል ድርሰቶቿ ቃዋቂ አድርጓታል።

»» ብዙ ነገሮችን ማስታወስ ይችላሉ፣ ፅዱና ጥንቁቅ ናቸው፣ ስለዚህም ከሌሎች ስራዎች ይልቅ የአግልግሎት(service) ሴክተር ላይ ቢሰማሩ የበለጠ ይሳካላችዋል፣ በዛ ላይ ሪሰርችና ስታቲክስን ቀለል አድርገው ማውጣት ይችሉበታል። ጫጫታና ውዥንብር የበዛባቸው ነገሮች ብዙም አይወዱም።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ጥቃቅን ነገሮችን ማስተካከል ላይ፣ ተንታኝ፣ ትጉ ፣ ስጉና ሚሰሩትንም ስራ በፕሮግራምና፣ እቅድ አውጥተው ነው።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ኤዲተር፣ አካውንታንት፣ ኢንጂነሪንግ፣ ግራፊክስ ዲዛይነር፣ አበባ ሻጭ፣ ስታይሊስት፣ መርማሪ ፖሊስ፣ ዶ/ር፣ ነርስ፣ አስተማሪ፣ ተርጓሚና የመሳሰሉትን መሆን ይችላሉ።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ዝርክርክ ያለ የስራ ኢንቫይሮመንት ሆኖ ብዙ ሰዎች ሚበዙበትና፣ አልምጥ ሰራተኞች ያሉበት ማንኛውም ቦታ።
.
.
.👏ተፈፀመ👏 ከዚ በመቀጠል ቃል በገባነው መሰረት፤ የኮከቦች ጥምረትን የምንቀጥል ይሆናል።
.
.
.እስከዛው መልካም አዳር 🙏 ይሁንላችሁ እያልሁ➮➮ 🦠 ኮሮና ተብሎ ስም የወጣለትን በሽታ ➟➟🇪🇹 ፈጣሪ 🙌 ከኢትዮጲያችን 🇪🇹 ምድር ያጥፋልን🙏
.
.

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23


((End))

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የናንተ ተስማሚ የስራ መስክ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ሊበራ"――――

The socialite, art

»» ምን አይነት ስራ ላይ ውጤማ እሆናለው ብላቹ አስባቹ ነበር? ሊብራዎች ማራኪ፣ የደስደስና ሰውን የመያዝ ብቃት አላቹ፣ ከሰው ጋ በጋራ የመሆን ችሎታቹ ምርጥ የአምባሰደርነትና የመሪ ብቃት እንዳላቹ ያሳያል።

»» የሆነ መስሪያ ቤት ውስጥ ሆናቹ መስሪያ ቤቱ ከደንበኞች ጋ በስልክ ከሆነ ሚገናኘው፣ ቦታው ላይ ከሊብራ የተሻለ ማንም ሊመጥን አይችልም፣ ሊብራዎች የህዝብ እሳቤዎች ናቸው። የሆነ ቦታ ላይ ሊብራዎች ብዙ መቀመጥ ይጨንቃቸዋል፣ የነሱ ምቹ ቦታ ብዙ ሰው ሚያዩበት ቦታ መሆን ነው ያለበት።

»» የአርት ፍቅር አላቸው፣ በተለይ ሙዚቃ ቢሰሙና ቢጫወቱ ይወዳሉ። ማራኪ ፣ ግልፅ፣ ሰዎችን አንድ ላይ ማደራጀትና ጥሩ የስራ አየር መፍጠር ይችላሉ። ባለንስና ሀቅ ያለበት ስራ ነው መስራት ሚወዱት፣ ወግ አጥባቂ የሆነ የስራ ቦታ በጣም ይጠላሉ፣ በተለይ ስሜታቸው እንዲገደብ አይፈልጉም፣ ሚሰማቸውን መግለፅ ይፈልጋሉ፣ እስካመኑበትም ከማንም ሰው ጋ መስማማት ይችላሉ።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ዲፕሎማቲክና አርቲስቲክ መሆናቸው፣ ለውሳኔ ሚከብዱ ነገሮችን የማስቀረት ችሎታ፣ እንዲሁም  በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በብቃት ማለፍና ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋ በቀላሉ መግባባት ይችላሉ ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» አርክቴክት፣ ዲዛይነር፣ ዳኛ፣ አማካሪ፣ ሁሉንም የአርት መስኮች ለምሳሌ ሙዚቃ፣ ትወና፣ ፊልምና፣ ወዘተ። የጉዞ ወኪል፣ ተቆጣጣሪና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» የተለመደ ስራ ሆኖ ምንም ፈጠራ የሌለበትና ነፃ ሆኖ መስራት ሚከብድ እንዲሁም በተፅኖ ውስጥ ተኮኖ ሚሰራ ስራዎች አይመቻቸውም።
.
.
.
.ይቀጥላል፣....መልካም አዳር🙏
.
.

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ፓይሰስ"――――

The dreamer, imaginative

»» ፓይሰሶች የዞዳይኩ ህልመኞች ናቸው፣ መቼም ቢሆን ማለምን አያቆሙም፣ ስለወደፊቱም ሆነ ስለ ማንኛውም ነገር በአይነህሊናውቸው ይስላሉ፣ ብዙዎች ራሳቸውን update እንዳልሆኑ አይነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ነገር ግን ጥሩ የፈጠራ ተነሳሽነት አላቸው።

»» ባህላዊ ነገሮች ላይ ጥሩ ናቸው፣ ሩህሩና ነገሮችንም በአስተዋይነት ስለሚያዩ፣ ፈጠራ የሚጠይቁ ስራዎች ላይ ጎበዝ ናቸው፣ ነገር ግን አደባባይ ላይ፣ በግንዘብ የተጠላለፈና ትልቅ ትኩረት የበዛበት ስራ ባይሰሩ ይመረጣል። ጠንቃቃ ናቸው፣ ነገር ግን የሆነ ግዜ በሀሳብ እልም ሊሉ ይችላሉ።

»» የእንቅልፍ ስራአታቸው፣ ሊለወዎጡ ስለሚችሉ፣ ቤት ውስጥ በነፃነት የሚሰሩ ስራዎች የበለጠ ያነሳሷቸዋል። ፓይሰሶች ውስጣዊ ጥንካሬና ውዥንብር ስላለባቸው ትክክለኛ ፍላጎታቸውንና አውነተኛ አላማቸውን ከሰው ለመሰወር ይገደዳሉ። በስራቸው ከተደሰቱ በደንብ ይሰራሉ፣ ካልሆነ ግን አልምጥ ነው የሚሆኑት። ቶሎ መከፋታቸውን ለመቆጣጠር ከቻሉ፣ አንፀባራቂ ነገር ማምጣት ይችላሉ። በጣም ስሜተ ስስ ስለ ሆኑ ።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ሩህሩህ፣ አስተዋይ፣ ተስማሚ፣ ስሜታዊ፣ ባለ ረዕይና ሀሳባዊ ናቸው፣ በሀሳብ የሚያስቡትንም ነገር ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» አርቲስት፣ ሳይኮሎጂስት፣ ሆስተስ፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ፣ ነርስ፣ ቴራፒስት፣ ፎቶግራፈር፣ ፊልም ሜከር፣ ሙዚቀኛ፣ ሼፍ፣ ኢንጂነሪንግ፣ የማስታወቂያ ባለሞያና የመሳሰሉት።

»»

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ከሰው ጋ የሚያጋጩና የሚያቀያይሙ ከሆነ መቼም አይፈልጉም።
.
.
.
.ይቀጥላል፣.....መልካም አዳር🙏
.
.

ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሱሶቼ ምነው ድምፃችሁ ጠፋብኝ ወይ አስነጥሱ ወይ ላይኳን ግጩን👇

አልያ ሼር፣ ጆይን አድርጉ እናም ደሞ ጓደኞቻቹን ጋበዙ የምን እያዩ ላሽ ነው !!

🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ኤሪስ"――――

The Trailblazer, authoritative

»» ዞዳይክ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ኮኮቦች በጣም ሚሰማቸውን ነገር ብትጠይቋቸው። ኤሪስ መቼም ላላ ያለ ነገር እንደማይወዱ ይነግሯቸዋል። ኤሪሶች ሁሌም በሙሉ ሀይልና በፍክክር ሚሰራ ነገርን ይወዳሉ፣ ከሌሎችም ድፍረትና ጥንካሬ አላቸው። ዶ/ር አቴና እንደሚሉት ከሆነ ከፊታቸው የሆነ ግብ ተቀምጦ ካለ ግቡን በ200% በላይ እንደሚያሳኩት ተናግረዋል።

»» የራሳቸውን ነገር መስራትና በትልቅ ቦታ በሀላፊነት መቀመጥ መፈለግ የኤሪሶች ባህሪ ነው። ለተፈጥሮ ነገሮች ርህራዬ አላቸው። ከማንም በላይ ተራማጅና እቅዶች ቢኖሯቸውም ብዙ ግዜ በደመ ነፍስ አንድ አንድ ስተቶች ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ንቁ ስለሆኑ ኮሚሽን ያለባቸው ስራዎች ላይ አሪፍ ናቸው፣ በተለይ ቦነስ ካለው የበለጠ ይሆናሉ። በድፍረታቸውና ቆራጥነታቸው የህይወት ዘመናችን ጀግኖች ያስብላቸዋል ። ምርጥ ኦፊሰርና፣ ጀግና ተዋጊ ወታደሮች ይዋጣላችዋል።

»» ኤሪሶች ሀሳባዊ  ስራ ነው ሚፈልጉት፣ የሆነ ትንሽ ከበድ ሚል ስራ፣ ዝም ብሎ አይነት ሆኖ መደበርን አይፈልጉም፣ በማርስ የሚመሩት ኤሪሶች ሁሉኑም ነገር ሲጀምሩ፣ በሙሉ ልባቸው ነው። በውድድር ያምናሉ፣ ከግዜም ጋ ቢሆን መወዳደር ይፈልጋሉ። የራሳቸውንም ግዜ አጥብቀው ይፈልጋሉ። ሁሉንም በቅድመ ተከተል ስለማይሰሩ፣ የራሳቸው ነገር ቢኖራቸውና ቢሰሩ ይሻላቸዋል ።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ጉጉት፣ ትጋት፣ ፈጠራ፣ ልባዊ የሆነ ስራን ከኤሪስ ማግኘት ቀላል ነው።  ትላልቅ ነገር ላይ ምርጥ ነገሮችን ያሳያሉ ነገር ግን እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገር ማውጣት አይወዱም።


√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ጄኔራል፣ ኮማንደር፣ ኢንተርፕሬነር፣ ፊልምና ቴሌቪዥን፣ ሽያጭ፣ ስቶክ ሆልደር፣ የመንግስት ባለስልጣን፣ መዝናኛ ላይ፣ አትሌቲክስ፣ ዳንስ፣ አሰልጣኝ፣ አነቃቂ ንግግሮች ላይ፣ CEO፣ ኢንጂነሪንግና የመሳሰሉት ለይ ምርጥ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ተራ የተለመዱና፣ እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገሮች መስራት ያለበት ስራ አይነት አይሆንላቸውም።
.
.
.ይቅጥላል፣....መልካም ቀን
.
.
.

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


ሰላም 🙌 ውድ ቤተሰቦቼ

የናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ካፕሪኮርን"――――

Corporate, The CEO

»» ሁነኛውና የሌላ ኮኮብ ተፅኖ ጎልቶ ማይታይበትን ካፕሪኮርን፣ ማግኘት ከፈለጋቹ፣ በእርግጠኛነት ትልቅ ክብር ያለው ስራ ላይ ወይም ደግሞ ትልቅ ሽልማት ሲጎናፀፉ ተገኛቿላቹ። ካፕሪኮርኖች በሕይወታቸው እንድ ትልቅ ነገር ማግኘት ይፈልጋሉ፣ እሱም ስኬትን። ትልቅ ስኬት ሚገኝበት ስራ ሲያገኙም ትልቅ ሀሴት ነው ሚሰማቸው፣ ያማልላቸዋል። ነገር ግን ስሜታቸውን ያገናዘበ የተወሰነ ፕሮሞሽን ይፈልጋሉ፣ ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ፕሮሞሽን።

»» ትላልቅ ተልኮና ግብ ተሰቷቸው ሚሰሩትን ስራ ይወዱታልም በአስተማማኝ ሁኔታም ይጨርሱታልም። ለምሳሌ የFBI አለቃ J.edgar hoover አስተማማኝ ምሳሌ ነው። ካፕሪኮርኖች ትልቅ ምኞት አላቸው፣ ደስተኛ መሆንንም ከልብ ይፈልጉታል፣ ገደብ ያላቸውና በአቋማቸው ፅኑ ናቸው፣ የፈለገውን ግዜ ይወሰድ አንዴ ከቆረጡ፣ ቆረጡ ነው። ለመለወጥ ይሰራሉ።

»»  ሁሉም በህግና ደንብ ቢሆን ይመርጣሉ፣ ህግና ደንብንም የማክበር ዝንባሌ አላቸው። አሪፍ የቢዝነስ ሀሳቦችን መጀመር ላይ ጎበዝ ናቸው። በአከባቢያቸው ያሉትን ሀሳቦችንም ሆነ ሰዎችንም፣ ወደ አንድ ያመጣሉ።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ጥሩ ምኞት፣ ትልቅ አቅም፣ ታጋሽ፣ በህግ የሚመሩ፣ አካሄድን አዋቂና ተወዳዳሪ አንዲሁም ማንኛውንም ስራ ቢሰጣቸው፣ አሪፍ አድርጎ መስራት ይፈልጋሉ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ፋይናንስ ላይ፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ዶክተር፣ አሰልጣኝ፣ ማናጀር፣ ባንከር፣ የኮምፒተር ባለሙያ፣ ስቶክ ኤክስፐርት፣ ኢንቨስተርና እንዲሁም ጥሩ የፈጠራ ሰው መሆን ይችላሉ። በዛ ላይ ደግሞ ውክልናና ፕላን ላይ ምርጥ ስለሆኑ፣ ሰውን ጥንቅቅ አድርገው ማማከር ስለሚችሉ፣ ኮንሰልታንሲ ላይ አሪፍ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»»   ምንም ጥቅሙ ሳይታወቅ በድፍረት ሚገቡበት ስራም ሆነ ቢዝነስ ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋል።
.
.
.
.ይቀጥላል፣.....💓ውዶችየ ፈጣሪ ለእናንተ ጤና እና ሰላም ፍቅር እና አንድነትን ጨምሮ ጨማምሮ አብዝቶ ይስጥልኝ🙏
.
.

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "አኳሪየስ"――――

Adaptable , The visionary

»» አኳሪየሶች የፈለጉትን የእጣ ካርድ ያንሱ፣ ያገኙትን እጣ እንዳለ ወደፈለጉበት መውሰድ ይችላሉ፣ የሁሉም እጣዎች ጆከር ናቸው። በፈለጉት ሞያ ቢገቡ ነጥሮ መውጣት ይችላሉ፣ ከሕይወታቸው ጠንቅቀው ልምድ  መውሰድ ይችላሉ። ያገኙትንም እውቀት ምንም ሳይሰስቱ ይሰጣሉ፣ በስራ አካባቢ ላይ በጎ አድራጎት ያበረታታሉ፣ ስለ ፍትህና እኩልነትም ይቆማሉ።

»» አዳዲስና ጀብዱ የተሞላበት ነገሮችን ይናፍቃሉ፣ ይወዳሉ እንዲሁም ያልማሉ። በአንድ ወኪል ወይም ማህበር ብቻ መታሰርን ይጠላሉ፣ በዚ አጋጣሚም፣ እድሉን የሚያገኙ ከሆነ ብዙ ስራ ይለዋውጣሉ። ነፃነታቸው ሕይወታቸው ነው፣ ከተለመደ ስራና ነገር ራሳቸውን ማላቀቅ ይፈልጋሉ። ተሞክሮ የማያቅ በማንም ለመስራት የማይገመት ስራ መስራትና መሞክርን ይወዳሉ።

»» ኦርጂናል ናቸው ነገር ግን በሁለት ሐሳብ መሀል ሲሆኑ ይስተዋላል፣ የሆነ ግዜ ላይ ሀይለኛ ሀይልና ፍላጎት ከዛን ደግሞ ቀዝቀዝና ድክም ወደ ማለት ይመጣሉ። ይሄም በገዥያቸው ኡራኖስ ምክንያት ይከሰታል።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ጥሩ ተንታኝ፣ ጎበዝ፣ ፈጠራ ላይ እንዲሁም ጓደኝነትና ከማንም ጋር ተግባብቶ መኖር ይችላሉ፣ ምንም አይነት ሰው ይሁን።


√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» አፕ ዲቨሎፐር፣ ሳይንቲስት፣ የእንስሳት ሀኪም፣ ኢንጂነር፣ ዲዛይነር፣ ሙዚቀኛ፣ የህዋ ተመራማሪ፣ የነፃነት ተከራካሪ፣ ሶሻል ሚዲያ ላይና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ምንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ተለምዷዊ ሆኖ፣ ነፃ ሆኖ ማሰብንም ሆነ ልዩነትን የሚቃወም የስራ ኢንቫይሮመንት  ከሆነ ትዕግስት የላቸውም።
.
.
.ይቀጥላል፣....መልካም ቀን እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ🙏 ፈጣሪ 🇪🇹 ኢትዮጵን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይጠብቅልን🙏
.
.
.

ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠየቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ሳጁታሪየስ"――――

Searching, the sage

»» ሳጁታሪየሶች ነፃነትን አፍቃሪ፣ ከማንኛውም ተፅዕኖ መላቀቅ የሚፈልጉ፣ በሆነ ሳጥን ውስጥ መሆንና ባለፈበት ባህልና ህግ መመራት የሚጠሉ ናቸው። አብረው ከእነሱ ጋር የሚሰሩ ሰዎች እንደ ግሩፕ ብዙ ስኬትን ያስመዘግባሉ፣። በአስተዳደርነት ሆነ በካንፓኒው ባለቤትነት ሚመራው ህግ እያለ ፈታ ያለ የስራ አከባቢ በዙሪያቸው ካለ፣ ፈታ ብለው እየዞሩ ነው መስራትን የሚፈልጉት፣ ከመስሪያ ቤቱ ውጪም ሆነው ሊሆን ይችላል የሚሰሩት።

»» ህግ መስበርና አዲስ ነገርን መፍጠር ላይ ጎበዝ ናቸው። ሀቀኛ፣ በሙሉ ሀይላቸው የሚጠቀሙና የራሳቸውን ፍልስፍና የሚከተሉ ናቸው። ውሳኔ ላይም ፈጣን፣ ተራማጅና ትክክለኛ ናቸው። ብዙ አማኝ ሳጁተሪየሶች አሉ፣ ሲበዛም ተጓዥ ናቸው።

»» ወጣ ያሉ ሲሆኑ፣ ቀልድም ይወዳሉ፣ ይቀልዳሉም። ጥሩ ተወዳጅነትም አላቸው፣ እየሰሩና እያሳዩ ነው የሚሰሩት። ለእያንዳንዱ ነገር ስለማይጨነቁ፣ ስለወደቀች ቆሻሻና ትናንሽ ነገር ላያስተውሉ ይችላሉ። የተለመደ ነገር መስራት ቶሎ ነው ስልችት ሚላቸው። ሁሌም ለወጥ ያለና እድገት ያለው ፍልስፍና ነው የሚፈልጉት።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ለየት ያለ ነገር ማምጣት የሚችሉ፣ ተስፈኛ፣ ቀጥተኛና ነፃነታቸውን በእንቅስቃሴና ራሳቸውን በመግለፅ ዘና የሚሉ እንዲሁም ፈልገው የገቡበትንና የሰሩትን ስራ ምርጥ አድርገው መስራት የሚችሉ ናቸው።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ኢንተርፕሬነርሺፕ ፣ ፓይለት፣ ስፖርት ኢንዱስትሪ፣ ፖሊስ ኦፊሰር፣ ሆስተስ፣ ሚኒስተር፣ የእንስሳት አሰልጣኝ፣ ኤዲተር፣ ህዝብ ግንኙነት፣ አሰልጣኝና ማንኛውንም አይነት ስራ ከጉዞ ጋ በተገናኘ፣ አስተማሪ፣ ዲፕሎማት፣ ፕሮፌሰር፣ ሰባኪ፣ ሪፖርተር፣ ሳይንቲስትና ደላላ መሆን ይችላሉ።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»»   ድግግሞሽ የበዛበት፣ የሙሉ ቀን የቢሮ ውስጥ  ወይም የጠረቤዛ ላይ ስራ  ።
      
.
.
.ይቀጥላል፣......መልካም ቀን🙏
.
.
.

ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ።

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ሊዮ"――――

Follow the Leo, The star

»» ሊዮዎች መስራት የሚፈልጉትን ነገር መስራት ይችላሉ፣ ብዙ ነገር ውስጥም ተሳትፎ ያደርጋሉ፣ ይሳካላቸዋልም። ግርማ ሞገሳም፣ አስተዋይ፣ ደፋር፣ እብድ፣ ፖዘቲፍ ኢነርጂና በመሪነትም ማንንም ማስገረም ይችላሉ፣ እስከሁን አለም ላይ ብዙዎቹ ፕሬስዳንቶችና መሪዎች ሊዮ ናቸው። በሀገራችንም እነ ዶ/ር አብይ አህመድና ኦቦ ለማ መገርሳን መየት እንችላለን።

»» የሚሰሩትንም ስራ በአግባቡና አድሏዊ ባልሆነ መንገድ መስራት ነው የሚፈልጉት፣ ብዙ እቃዎችን ኦርደር በማድረግ፣ ፓርቲዎችን በመውደድና ዘና ማለትን ይወዳሉ፣ በተፈጥሯቸውም ሰው እንዲከተላቸው ማድረግ ይችላሉ፣ የሚሰሩትንም ስራ ያለምንም ተፅኖና ፍራቻ፣ በጥልቅ ተነሳሽነትና ወገንታዊነት ይሰራሉ፣ ሰማይ እንዳሉ ኮኮቦችም የሚፈልጉት ነገር ብዙ ነው፣ በሰሩት ስራም ምስጋናና ክብር እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ። ደፋር ቢሆኑም ውስጥ ውስጡን ፈራ ይላሉ።

»» ተራ ሰራተኛ ወይም ከመጋረጃ ጀርባ የሚሰሩ ሰዎች አይደሉም፣ አይወዱምም፣ ካልሆነም ስራውን ለቀው ይሄዳሉ። ጭምቱም ሆነ ግልፁ ሊዮ፣ ቶሎ እንዲታወቁና እንዲደነቁ ይፈልጋሉ፣ ሁሉም ሊዮዎች የማዕረግ ስም ይወዳሉ፣ አመራር የመስጠት ፍለጎት በልባቸው ስር የሰደደ ነው ።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ኮንፊደንሳም፣ ተስፈኛ፣ ኢንተርፕሬነር፣ ደግና ሀይለኛ ናቸው፣ መስራት የሚፈልጉትም ስራ የእነሱን የተለያየ ብቃት የሚያሳይ ቢሆን ይመረጣል። እንዲሁም አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችሉበትን።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ኢንተርፕሬነር፣ ፕሬዝዳንት፣ ኢንተርቴይመንት፣ ፖለቲካ፣ ህዝብ ግንኙነት፣ ሴናተር ፣ ሙዚቀኛ፣ CEO ፣ አስተማሪ፣ አስጎብኚ፣ የሪልስቴት ባለቤት፣ ፋሽን ዲዛይነር፣ ሽያጭ፣ ሶሻል ሚዲያና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ጎልተው መውጣት የማያስችላቸው ከሆነ አይመቻቸውም።
.
.
.ይቀጥላል፣....መልካም ቀን🙏
.
.

ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

14 Oct, 05:21


የናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ጄሚኒ"――――

The genius, The magic mind

»»ጄሚኒን እንደፈለገኝ እናገራለው ማለት ይከብዳል፣ ምክንያቱም እናንተ በተናገራቹት ልክ እነሱ አፀፋውን በእጥፍ ይመልሳሉ፣ ሚሉትን አያጡም። ምጡቅ አዕምሮ አላቸው፣ በጣም ውስብስብና ከባድ ሀሳብን በቀላሉ ማስረዳት ይችላሉ፣ የጄሚኒዎች ገዥ ሜርኩሪ አንደበትን ታዛለች፣ ፈጣን አስተማሪና አስተርጓሚ መሆን ይችላሉ፣ ፕሮፌሽናል ናቸው፣ ንግግርም ላይ እንደዛው።

»» ጄሚኒዎችን ደስተኛ ለማድረግ በእውቀት ሚጥለቀልቁበትን ነገር ስጧቸው ወይም አሳዯቸው፣ ነገር ግን ሁለት የተለያየ ባህሪ ስላላቸው፣ ዙሩን ፈጣንና አከባብያዊ ማድረግ አለባቹ፣ አዝጋሚና አሰልቺ ከሆነባቸው  ምንም ሳያቅማሙ ይጠፋሉ፣ ወይም ገሸሽ ያደርጉታል። ጉዞ ያለበት ስራና አከባቢያዊ መስተጋብር ያለበት ስራ ይወዳሉ። በጎ አሳቢና በሙሉ ሀይላቸው ይሰራሉ። ባህላዊ ነገሮችን ከመከተል ይልቅ፣ ራሳቸውን ሚገልፁበትን ነገር ይወዳሉ።

»» የጄሚኒ ሀሳባዊ ስራቸው፣ ፈጣንና በሚገባ አዕምሯቸውን ማሰራት ሚችሉበት ቢሆን ይመርጣሉ። ነገሮችን በፈጣን ሁኔታ መልመድና መስራት ይችላሉ፣ ነገር ግን ከለመዱት ኅላ ሊያዝጋቸው አይገባም። በብዥታ አለምና በእውነተኛ አለም መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያዎቁት ጥረት ማድረግ አለባቸው፣ በሁለት አለማት ድንበር ላይ ከመጥፋት ለመዳን ይጠቅማቸዋል።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ቀልደኛ፣ፈጣን፣ ጎበዝና ተላማጅ ናቸው፣ ነገር ግን ሀሳባቸውን ብዙ ነገር ላይ መጣዳቸው ድብርት ውስጥና ውጤማ ላያደርጋቸው ስለሚችል፣ አንድ ነገር ላይ ብቻ  ትኩረት ቢያደርጉ ምርጥ ነው።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ሚድያና ማስታወቂያ፣ ማርኬቲንግ፣ ጋዜጠኛ፣ ፀሀፊ፣ የቴሌ ኦፕሬተር፣ ረዳት ቴክኒሺያን፣ አስተማሪ፣ አርክቴክት፣ ማሽን ኦፕሬተር፣ ኮሜዲያን፣ ፖሎቲከኛ፣ ቴክኖሎጂ ላይና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ጥብቅና ቁጥጥር ያለበት ስራ ሆኖ፣ ስረው ላይ ደግሞ እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገር እነሱን ሚጠብቅ አይነት ስራ ከሆነ ቶሎ ላጥ ቢሉ ነው ሚሻላቸው።

.
.
.ይቀጥላል፣.......መልካም አዳር🙏
.
.

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

10 Sep, 04:39


ጳግሜን ለይቅርታ

ሰላም ጤና ፍቅር ፀጋ ይሁንልን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ጳጉሜ ገባ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ፈጣሪ በአመት ላይ አመት......365days🌻🌻🌺🌼🌼🌼
በወራት ላይ ወራት .....12months🌓🌹🌷🌺🌺
በሳምንት ላይ ሳምንት.....48weeks🍀🌞❄️🌧⭐️🌟
በቀናት ላይ ቀናት.....365days🌼🌼🌼🌼
በሰዐት ላይ ሰዓት.....8760hours🌃🌃🎈🎀🎈🎀🎈
በደቂቃ ላይ ደቂቃ......21900minutes💌🎊🛍🎁🎈🎀🎁🎀
በሰከንድ ላይ ሰከንድ.....43800seconds🎎🎏📍🎀🎀🎀🎀🎀
ጨምሮ ለዚህ ግዜ ያበቃንን ቸሩ ፈጣሪን ከእግራችን በርከክ ብለን እናመስግነው 🙏🙏🙏

የኔ....ፍቅር💋💋❤️❤️💖🎀🎀
የኔ....ምስኪን😘😘😘😘😘😘😘
የኔ....አሳቢ🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
የኔ....ህይወት👍👍👍👍👍👍👍
የኔ....ሁሉነገር🙏😱🎀💖💞👗💖💗💘

ጓዴ በደስታዬ የተደሰትክ /😄😄 የተደሰትሽ😄😄😄
በሃዘኔ ያዘንክ 😔😔😔😔/ ያዘንሽ😔😔😔😔
ፍቅር 💝💝ስሰጥሽ ፍቅር❤️❤️ የሰጠሽኝ / የሰጠኧኝ
ችግሮቼን የተጋራህ / የተጋራሽ💦🌟🌟
ጓደኞቼ 👩‍❤️‍💋‍👩 💏
እህቶቼ👩‍❤️‍💋‍👩 👩‍❤️‍💋‍👩 👩‍❤️‍💋‍👩
ወንድሞቼ👨‍❤️‍💋‍👨 👨‍❤️‍💋‍👨 👨‍❤️‍💋‍👨
ወዳጆቼ👩‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧👨‍👩‍👧‍👦👨‍👨‍👦👨‍👨‍👧👨‍👦‍👦👩‍👧‍👧👨‍👦


ሳላውቅ በድፍረት
አውቄ በስህተት
ያስቀየምኩህ👨
ያስቀየምኩሽ👱‍♀
የጎዳውህ👨👨 የጎዳውሽ👱‍♀👱‍♀

ከልቤ❤️❤️❤️❤️


🙏🙏🙏
🌼🌼🌼🌼
🎀🎀🎀🎀🎀
💝💝💝💝💝💝

በመጠየቅ ከጉልበቴ
በርከክ ብያልለሁ🙇‍♀🙇

ጳጉሜውን
የሰላም💖💖
የፍቅር💝💝
የጤና💞💞
የይቅርታ❤️❤️
ያርግልን

በጣምምም
ከልቤቤቤቤቤ
እወድሃለው👱💋❤️💖
እወድሻለሁ👱‍♀💋❤️💞


ይህንን ለወዳጆቻችን ሼር በማድረግ ጳጉሜን
እናሳልፍ😍😍😍❤️🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼💋💋💋💋💋💋💋💋💋💋😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘

አስትሮሎጂ

22 Aug, 07:24


😋ውድ ተከታዮቼ ዛሬ ሚገርም ነገር ይዤላቹ መጥቻለው 👉👉 *999*1*1*2*3*4*2*1# እዚ ቁጥር ቀጥጣ በመደወል የ4GB የወር Package በነፃ ያግኙ ለምታቁት ሁሉ

አስትሮሎጂ

25 Jun, 19:12


🎈Welcome to Tele Birr Bot
➣ ቴሌ ብር Botን ሲጠቀሙ

📋 ሲመዘገቡ 15.00 ብር Bonus

🎁 በየ 48:00 ሰሀት(2 ቀን) 3.00 ብር ጉርሻ

🔗 ጓደኛ በመጋበዝ 5.00 ብር ያገኛሉ።

TeleBirr Botን ይቀላቀሉ
🔗 https://t.me/TeleBirrProBot?start=Bot5875119

አስትሮሎጂ

20 May, 16:56


የመጨረሻ ክፍል👇

(#የኮከብ_መጠሪያ_ስም_ቪርጎ_ወንድ)

የውልደት ቀን ከነሐሴ 18 እስከ መስከረም 13
⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️

➮»» ይህ ሰው የሚኖረው በተግባራዊና ቁሳዊ ደረጃ ስለሆነ ለረቂቅ የፍቅር ስሜት ያለው ጠቀሜታ ዝቅተኛ ነው፣ በእርግጥ ዋናው ምክንያት አካዳሚ ሊሆን ይችላል፣ ቪርጎዎች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ በፍቅር ይያዛሉ፣ ሆኖም የሮሚዮና ጁልየት አይነት አይደለም፣ ፍቅሩን የሚገልፅበት ዋነኛ መንገዱ ለቤተሰቡ፣ ለጓደኞቹ፣ ለደካሞችና ከእሱ ለሚያንሱ ሰዎች በታማኝነት መልካም አገልግሎት በመስጠት ነው።

➮»» በድራማዊ ትወናና በስሜታዊ ቃል ኪዳን ታጅቦ በእንባ ጎርፍ የሚገለጽ ፍቅር የቪርጎን ስሜት ማቀዝቀዝ ብቻ ሳይሆን አስፈራርቶ ያስሸሸዋል። በእርግጥ ልቡን ለማግኘት መንገዶች አሉ፣ ጠብ ጫሪነት፣ ጉልበተኛ ወይም ወሲበኛ መሆን ከመንገዶቹ አንዱ አይደለም፣ በፍቅር ከብዛት ይልቅ ጥራት ይፈልጋል፣ በጥቂቱም ላይ አሳዛኝ ሁኔታ ሊያጋጥማቸው ይችላል፣ እንዲ አይነት አሳዛኝ የፍቅር ህይወት ሲገጥማቸው ራሳቸውን በከባድ ስራ ያስጠምዱና ከህብረተሰቡ ይርቃሉ፣ ለወደፊትም በጣም ጥንቁቆች ይሆናሉ፣ ቪርጎን በፍቅር የምታጠምድ ሴት እንግዲህ ምን ያህል ታጋሽና ስልታዊ መሆን እንዳለበት ያየሽ ይመስለኛል።

➮»» ከሌሎች ቤተ ባህሪያት ይበልጥ ከወሲብ ታቅበው በቀላሉ መኖር ይችላሉ፣ አሪፍ አእምሮ እና ጠንካራ አካል አጣምሮ የያዘ ነው፣ እውነተኛ ፍቅር ለማቀጣጠል ብዙ ማገዶ ማንደድ ያስፈልጋል፣ ሴት ሲመርጥ በጣም ተጠንቅቆ እና ጊዜ ወስዶ ነው አስተሳሰቡ ጥርት ያለ ነው፣ ዝቅ ያለ የፍቅር ግንኙነት ጨርሶ አይቀበልም።

➮»» የቪርጎን ወንድ ስሜት ለመቀስቀስ ያስቸግራል ፣ ከወሰነ ግን ወሰነ ነው። ቪርጎ ወንድ ከልክ በላይ ባይሆንም በጣም ቀናተኛ ነው ቅናቱን በግልፅ አለማሳየቱ ሊያዘናጋሽ አይገባም ከልኩ ካለፈ ጥሎሽ ላጥ ሊል ይችላል። ቪርጎ ወንድን ስታፈቅሪ አስተሳሰብሽንም ማጥራት ያስፈልግሻል፣ እንዲሁም ጥሩ ልብስ ልበሺ ፣ ፀጉርሽንም በጥሩ ስታይል ተሰርተሽ በንፅህና ያዢ።።
.
.
.
.። ➟➟ #ተፈፀመ ።
.
.
.
.በሌሎች ዝግጅቶች እስክንገናኝ ➮➮ ❤️መልካም ውሎን ከጥሩ ምኞት ጋር ተመኘሁላችሁ🙏
.
ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ


ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

20 May, 16:56


ሳሚ...የናቱ ልጅ ምን አለ በሉ ፤፤፤፤፤
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እንዴት ነህ አንተ ልሙጥ ሽሮ በልተህ የምትውል ህዝብ? ዛሬም "ተምሬ ጥሩ ቦታ ደርሼ..." ምናምን ብለህ ዘመድ ትቀፍላለህ ውይ?
ይገርምሀል ስትመረቅ የሚያጋጥምህን ልንገርህ...

#እልልልልልልል ይባልልሀል (ሶስት F እንደላመጣህ አያውቁማ! 'ጨ' የሚባል ግሬድ አለማምጣትህ ራሱ ኡራኤል ሲረዳህ ነው!)

#ይዞት ይዞት ጦስሽን በሚል ዘፈን የሰፈር ሰው ዘንጦ... ጨፍሮ... ምሳ በልቶ ቀይ ወጥ እያጋሳ Congra ምናምን ብሎ ከመንገድ ላይ የገዛውን photo album በብልጭልጭ ወረቀት ሸፋፍኖ ይሰጥሻል፡፡ (ይዞት ይዞት ጦስሽን...)

#እናቶች እየመጡ ያለቅሳሉ፡፡ ትላንት ሱሪው ላይ ሲሸና የማውቀው ልጅ ዩንቨርስቲ በጠሰ? ምናምን እያሉ ያሳቅቁሀል፡፡ አባቶች በሚዋጋ ፂማቸው እንደ መፅሀፍ እየገላለጡ ይስሙሀል፡፡

#የሰፈር ልጆች ሹክክ ብለው ጠላ ጠጥተው ላጥ ይላሉ፡፡ ካንተ ጋር ማን ይሟዘዛል...

#የምትወድህ ልጅ ከሳሪስ የማታ ገበያ ከአንዱ ጥግ (ክንዴ ቡቲክ) ብልጭልጭ ሸሚዝ ገዝታ ትሰጥሀለች፡፡ ከዛ ፍቅሯ ያንዘፈዝፍሀል... አረፋ ትደፍቃለህ... ቻው ስትልህ የመሳቀቅ አይነት እሩብ ከንፈርህን ስማህ ውልቅ ትላለች (የድግሱን ወጥ አፏ ላይ እንዳለ ትቀምሳለህ... ጨው የለውም!)

#ቤተሰብ እየመጣ እንደ ብርቅዬ እንስሳ ብብቱ ስር እየከተተህ ፎቶ ይነሳል፡፡

#የፍቅር ጓደኛሽ የቱርክ ሱፍ አድርጎ ይመጣና ሲንጎማለል ሲንቀዠቀዥ እዩኝ እዩኝ ሲል ሸሚዙን አልጫ ወጥ ይነካውና እንደ ዱር ዝንጀሮ በንዴት ደረቱን ይደበድባል (ይሄ ዝርክርክ ትያለሽ በሆድሽ)

#ጠይቆሽ እምቢ ብለሽው... ለምኖ... ለምኖ... ለምኖ... ተንፈራፍሮ... ተንጀላጅሎ... እምቢ ብለሽው ስምሽን ያጠፋብሽን ልጅ ጥግ ላይ ተቀምጦ ጭንቅላት የሚያክል ጉርሻ ሊጎርስ ሲል ትተያያላቹ፡፡ በአይንሽ ታናግሪዋለሽ (ውጣ!) ላሽ ሲል አጠገብሽ ያለው ምስኪን ሊግጣት ጥግ አስይዞ የነበረችውን አጥንት አንስተሽ ትወረውሪያለሽ! ሶስት ሰው ይቆስላል፡፡

#አስቀያሚ ናቸው ያልካቸው የሰፈር ቺኮች የሌለ ፏ ብለው ይመጡና የመቶ ብር አንገት ሀብል ያደርጉልሀል፡፡ ትሳሳትና አንዷን ስትጠቅስ "ይሄ ቅሌታም" ምናምን እያሉ ዝንብ እንደወረረው ሰው ይጠቋቆሙብሀል፡፡ የእናትህን ስጋ ወጥ እየበሉ፡፡

#የእናትህ መረዳጃ እድር አባላት ድርቅ ብለው አገልግል እሰሩልን ይላሉ፡፡
~
~
~
እመነኝ ድንቁ ሀበሻ አዲስ ነገር ተመኝቶ እንጂ ያገኘ ቀን ጥሞት አያውቅም! ይሄ ሁሉ ግርግር ላንተ እንዳልነበር ይገባሀል፡፡ ምንም እንዳልሆንክ ይገባሀል፡፡
ለራስህ የሰጠኸው ግምት በሰው መሰብሰብና መበተን የሚወሰን ከሆነ ተበልተሀል ወዳጄ!

#U_will_face_reality_soon!
#ነኝ_ብለሽ_ያሰብሽውን_እንጂ_ነሽ_ያሉሽን_አይደለሽም! ሳቢታ;;

Sher us, join👇
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

🌈 @Akiya_a

አስትሮሎጂ

20 May, 16:56


😘ውድ የ አስትሮሎጂ ቲውብ ቤተሰቦቻችን➮ የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???➟)))) በሚል ርእስ እንደቀደመው ሁሉ የስራ ባህሪያቶቻችሁን በውልደት ቀናችሁ መሰረት የተተነበየውን ትንበያ በቅደም ተከተል ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ። አብራችሁኝ ሁኑ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ስኮርፒዮ"――――

the soulful,  midheaven

»» ስኮርፒዮዎች ሁሉንም ነገር በጥልቅና እውቀት በተሞላበት ነገር መጠን ማወቅ ይፈልጋሉ፣ ነገሮችንም አስፍተው ነው የሚያዩት፣ የሰዎችን ችግር መረዳትና ድጋፍ ማደረግ ላይም ጎበዝ ናቸው፣ በዚህም ቋሚ ተማኝነትና የረጅም ግዜ ጓደኝነትን ይፈጥራሉ። ዶ/ር ፓራኪሶ እንደሚሉት ከሆነ ፣ ስኮርፒዮዎች የቴራፒስት እውቀት ስላላቸው የሰውን የውስጥ ችግር መረዳት እንደሚችሉም  ይናገራሉ።

»» በዛ ላይ የሌሎችን ሚስጥር መጠበቅ ላይ ጎበዝ ናቸው፣ እንደው በአጠቃላይ ስኮዎች ምን አይነት ስራ የሚወዱ ይመስላቹዋል? በቦንብ የቆሰለን ሰው የሚረዱ? ወይስ ውስብስብ ቀዶ ጥገናዎችን በስኬት የሚያደርጉ? እመኑኝ ስኮዎች በየትኛውም የስራ ዘርፍ ላይ ቢሆን ትፈልጓቸዋላቹ፣ እስከ ጥግ ትኩረት አድርጎ መስራትን ያውቁበታል።

»» ነገር ግን አጠገባቸው አታንዣቡ፣ ነፃነትንና የሰራተኞቻቸውን እምነት ይፈልጋሉ፣ ግለኝነታቸውም እንዲጠበቅላቸው ይፈልጋሉ፣ ይሄ ማለት ከእነሱ ፍቃድ ውጪ ማንም ሰው ስራቸውን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ አይፈልጉም።


√√ ጥሩ እሴቶች

»» ታታሪ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው፣ እምቅ ብቃትና ቆራጥነት፣  እንዲሁም ብዙ ግዜ ሰውን ሳይጠብቁ ይሰራሉ። ነገር ግን በጣም የሚጓጓለት ነገር ቢሆን  ይመርጣሉ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ሳይኮሎጂስት፣ ህግ አዋቂ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሰራተኛ፣ መርማሪ ፖሊስ፣ አስተማሪ፣ ሳይንቲስት፣ ሳርጂዮን፣ ፊዚስት፣ ፖሎቲከኛ፣ ፀሐፊ፣ ቴራፒስት፣ ዶክተርና እንዲሁም አስትሮሎጂና አንድ አንድ ጥበባት ላይ ጎበዝ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ትልቅ እውቀት ሳይኖራቸው የሚሰሩት ስራና ሳያምኑበት የሚገቡበትን ነገር መስራት ስኬታማ አያደርጋቸውም።

               
.
.ይቀጥላል፣.......... መልካም ቀን🙏
.
.
.
.

ማንኛውንም አስተያየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

20 May, 16:56


የናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

――――  "ካንሰር"――――

Caring, the mystic

»» ካንሰሮች ስሜታዊ ናቸው፣ እንዲሁም በቀላሉ የሰውን ልብ፣ አዕምሮና ውስጣዊ ፍላጎት መረዳት ይችላሉ። የሕይወት ነገር ለነሱ በጣም ወሳኝ ነው፣ በተለይ ደግሞ ቤተሰብን በተመለከተ፣ እንዴትና ደስተኛ ቤተሰብ መምራት እንዳለባቸው ይጨነቃሉ፣ በዚህ እሳቤም ምን አይነት ስራ ቢሰሩ ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው ጠንቅቅው ያውቃሉ፣ ያጤናሉ።

»» ምርጥ ሼፍ ናቸው፣ ምግብ ይጣፍጥላቸዋል፣ የአንድ ሬስቶራንት ወይ ሆቴል ማናጀር ቢሆኑ ማንንም ደንበኛ አጠረግርገው መሳብ ይችላሉ፣ በተፈጥሯቸው ተፈጥሮ ነገሮች ይስባቸዋል፣ እንደ ነርሲንግ፣ የህፃነትና የአዛውንቶችን ክትትልና እንክብካቤ ሚፈልጉ ነገሮች ላይ ይችሉበታል።

»» በጎ አድራጎትና መደራጃ ማህበራት ላይም እንደዛው፣ ለምሳሌ ንግስት ዲያና( የዊሊያምና ሀሪ ልጅ) አንጀት ምትበለ ልዕልት እንደነበረች ማስታወስ እንችላለን፣ ጥሩ መካሪና ተከላካይ ናቸው። እንዴትና ምን ያህል ገንዘብ ተጠቅመው አንድን ስራ መጀመር እንዳለባቸው ያዎቃሉ፣ ሲኖራቸው ሁሌም ደስተኛ ናቸው፣ የሚሰሩትም ወይ ለዝና ወይ ደግሞ ራሳቸውን ለማሳወቅ አይደለም፣ ጀስት መስራት ስላለባቸው ነው። ከአላማቸውም ማንም አያዘናጋቸውም፣ ከሚፈልጉትም ነገር እንደዛው።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» አሳቢ፣ ታጋዥ፣ ስሜታዊ፣ ፈጣሪ፣ ትጉ እንዲሁም ሰውን ማፅናናት ይችሉበታል።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ሪል ስቴት፣ ዲዛይነር፣ ሳይኮሎጂስት፣ አስተማሪ፣ ቴራፒስት፣ ሁምን ሪሶርስ፣ የህግ ባለሞያ፣ ወታደር፣ CEO ፣ አማካሪ፣ ባንከር፣ ሼፍ፣ ፀሀፊ፣ አዋላጅ ፣ ፋርማሲስት፣ ሞግዚት፣ ባለ ስልጣንና የመሳሰሉትን ቢሆኑ የበለጠ ስኬታማ ይሆናሉ።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» የተነጠለ ስራ ሆኖ ኦቨርሳይት ሚበዛበት ስራ።

.
.
.
.ይቀጥላል፣..... መልካም አዳር🙏
.

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23

አስትሮሎጂ

20 May, 16:56


(#የኮከብ_መጠሪያ_ስም_ሊዮ_ወንድ)

የውልደት ቀን ከሀምሌ 17 እስከ ነሃሴ 17
⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥⚡️💥

➮»» ሊዮ ወንድ የሚገኘው ህዝብ በተሰበሰበበት፣ የሰው አይን በበዛበት ባደባባይ ጣፋጭ ንግግር ሲያደርግ እንጂ በበረሃ ሲጠወልግ አይደለም።ጣፋጭነቱን ግን በባዶ አየር ላይ አይረጭም፣ ሁል ግዜ ተደራሲ ይኖረዋል፣ የሊዮ ምስጢር ይሄ ነው፣ ተደራሲ ሁኚ፣ አድናቂው ሁኚ፣ ለፍቅር ጨዋታ የተጋና የተባ ነው። ቀልብሽ ካረፈበት አድንቂው፣ አሞግሽው፣ አክብሪው።

➮»» ሊዮ ያለ ፍቅር መኖር አይችልም፣ ፍቅር ቢሉሽ ፍቅር መሰለሽ፣ እንደ ጣኦት መመለክ ነው ሚፈልገው፣ ከዚያ ካነሰ ሞቱን ይመርጣል ለገንዘቡም አይሳሳም፣ በውድ ስጦታዎች ያጥለቀልቅሻል፣ በደስታ ያስፈነድቅሻል።

➮»» ግን በአካልም፣ በመንፈስሽና በአእምሮሽ የሱ ነሽ፣ ምን አይነት ልብስ መልበስ እንዳለብሽ፣ ፀጉርሽን እንዴት መሰራት እንደሚኖርብሽ፣ የትኛውን መፃፍ እንደምታነቢና ከነማን ጋር እንደምትውዪ ሁሉ ሚመርጥልሽ እሱ ነው፣ ይቀናል። ማራኪ መሆንሽን አሳምሮ ያውቃል፣ የሌላ ሰው ማረጋገጫ አያስፈልገውም። ሊዮ የበደለውን ሰው ያነጥፈዋል፣ ባህሪው ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ያንቺ ትብብር ያስፈልገዋል፣ የጋለ ስሜቱን ከአሳማኝ ምክንያት ጋር እያስታረቅሽ ልታጓጊው ይገባል፣ የሱን ስሜት ለማረጋጋት አንቺ ራስሽ መራጋጋት ይኖርብሻል፣ የተራጋጋሽ ካልሆንሽ የፍቅር ህይወታቹ የጦርነት አውድማ መሆኑ ነው።

➮»» ስራ ሊኖርሽ አይገባም፣ ሊዮ ባልሽ ፈፅሞ አይፈቅድልሽም፣ ስራሽ እሱ ነው ፣ ሊዮ ባልሽ ልክ እንደ ንጉስ ደግ ይሆንልሻል፣ ቤተሰቦችሽን ይረዳልሻል፣ የሚፈልገውን አክብሮትና ሙገሳ ካገኘ ለልገሳው ወሰን የለውም፣ አንቺን ከያዘ ቧላ እንደገና ወደ መምረጥ አይገባም።

➮»» ወደ ግልፅ ጨረታ ቦታም ባይሄድ ይሻላል፣ ከሰው በላይ ዋጋ የመስጠት ፍላጎቱ ብልጭ ይልበትና ገንዘቡን ይዘራው ይሆናል፣ የፈጠራ ችሎታ እንዳላቸው ሁሉ የመቆመር እና ጨረታ የማሸነፍ አመልም አለባቸው። ሁሉም ሊዮዎች የእጅ ብልሀት አላቸው፣ እቤት ውስጥ ከሬድዮ እስከ ቴሌቪዥን ሲበላሽ ያድሳሉ።

➮»» ሊዮዎች ማንኛውንም የፓርቲ ግብዣ ህይወት ይዘሩበታል፣ ባፀፋውም ይታዩበታል፣ ይከበሩበታልም፣ ሊዮን የሚፈልገው የሚያገኘ ነው፣ አያያዙንም ያቅበታል።

➮»» ከጋብቻ በፊት በፍቅር ወዳጅነት በተቀራረባቹበት ወቅት ታማኝሽ እንዲሆን ከፈለግሽ የፍቅር ጥማቱን በደንብ አርኪለት፣ ባይኑ መቀንዘሩ ግን አይቀርም፣ አይንህን ቅጣ ከምትይው ውበትን ሲያደንቅ አብረሽ ብታደንቂ ታስገርሚዋለሽ፣ ውበትን አየ ብላ ፍቅረኛው ስትለየው ሊዮ ወንድ ይገረማል፣ያዝናል እንዲሁም ይጎዳልም።

➮»» ልጆቹን ከሱ አታስበልጪ፣ ወደ ልጆችሽ አድልተሽ ለሱ የምትሰጪው ትኩረት ካነሰ ችግር ይፈጠራል፣ በስሩ ያሉ ሰዎችን የማዘዝና በነሱም የመፈቀር ፍላጎቱ ከፍ ያለ ነው።
.
.
.
.
.የቀጣይ ወር ትንበያ ይቀጥላል....
.
.
.
.
.🙏ሰላም እደሩልኝ🙏
.
.
ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Akiya_a መጠያቅ ትችላላቹ


ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ
🌈 @AstrologyTube23
@AstrologyTube23