👸ልባም ሴት👸 @libamua Channel on Telegram

👸ልባም ሴት👸

@libamua


ከክፋት የራቀች ለ ፅድቅ የጀገነች

ቅድስና ውበቷ ይልቅ ያደረገች

የገንዘቡ ፍቅር እርሷን ያልበገረ

የውሸቱን ህይወት ልቧ ያባረረ

ዝቅታ ጌጧ ነው እውነት መዋቢያዋ

አትገላለጥም ውድ ነው ገላዋ ...

👸ልባም ሴት👸 (Amharic)

በ👸ልባም ሴት👸 ታሪኩ ከክፋት የራቀች ለ ፅድቅ የጀገነች። የፀሐይ ድንገት እንዴት መፍትሄ ያለበትን ዝማሬን ውስጥ ሲወርድ ሰላም በመሰየህ ነው። ቅድስና ውበቷ ይልቅ ያደረገች። የገንዘቡ ፍቅር እርሷን ያልበገረ። የውሸቱን ህይወት ልቧ ያባረረ። አትገላለጥም ውድ ነው ገላዋ! 🌟🌟

👸ልባም ሴት👸

14 Jan, 09:18


የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ?

👸ልባም ሴት👸

13 Jan, 18:36


🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
ሰበር ዜና በ አጭር ግዜ ተወዳጅነትን የገኙ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ የሚለቀቁ አስተማሪ ና አዝናኝ ቻነሎችን ይ🀄️🀄️👇👇
Free promotion የሚትፈልጉ
Channel ያላችሁ በ @seer_lewi አነግሩኝ 👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

13 Jan, 08:53


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

12 Jan, 17:47


የትኛውች የ tv ቻናል ይመለከታሉ🤔
@free_wave1

👸ልባም ሴት👸

12 Jan, 14:25



🎤የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ???🤔🤔
👇👇👇👇👇
በመዝሙሮቹ የተባረካቹ እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ
➨Wave ለመግባት የምትፈልጉ
👉ከ5K በላይ Subscriber ያላችሁ
📥inbox 👉 @seer_lewi
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

12 Jan, 05:42


🍀ለክርስቲያኖች ብቻ የተከፈተ ቻናል ነው
join ምትለውን ሲነኩ ያገኙታል👇

👸ልባም ሴት👸

10 Jan, 17:27


ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለመንፈሳዊ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ button ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ

👸ልባም ሴት👸

10 Jan, 17:05


ምን ይፈልጋሉ
@free_wave1

👸ልባም ሴት👸

10 Jan, 11:18


🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ
አሁን በዳምጣው የምትሉትን ምራጡ "Join" ያድርጉ 🙏🙏

👸ልባም ሴት👸

10 Jan, 07:53


🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
ሰበር ዜና በ አጭር ግዜ ተወዳጅነትን የገኙ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ የሚለቀቁ አስተማሪ ና አዝናኝ ቻነሎችን ይ🀄️🀄️👇👇
Free promotion የሚትፈልጉ
Channel ያላችሁ በ @seer_lewi አነግሩኝ 👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

08 Jan, 16:23


🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ
አሁን በዳምጣው የምትሉትን ምራጡ "Join" ያድርጉ 🙏🙏

👸ልባም ሴት👸

08 Jan, 16:21


በአዲስ ኪዳን አጢያት የሚሰረየው እንዴት ነው? መልሱን ይሆናል የምትሉትን ይንኩት
@free_wave1

👸ልባም ሴት👸

08 Jan, 09:02


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ አና መዝሙሮችን ያድምጡት ::Wave👉 @seer_LEWI
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲

👸ልባም ሴት👸

07 Jan, 11:23


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን ሊንኮችን ወይም የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ ::

👸ልባም ሴት👸

06 Jan, 09:37


🎅🎄እንኳን አደረሳችሁ 🎄🎅
የገናን በዓል ምስንያት በማድረግ በዓሉን የሚያደምቁላችሁን የክርስቲያን ቻናሎች ልጠቁማችሁ🎅
Wave መግባት ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ @free_wave1

👸ልባም ሴት👸

06 Jan, 06:20


🏑🏑🏑🏑🏑🏹🏑🏑🏑🏑🏑🏑
የ ገና በዓል ፕሮግራሞችን በተለየዩ ቋንቋዎች ለማግኘት  ከታች ያሉትን ቋንቋ መርጣው ይጫኑ እና ፕሮግራሞችን ይከታተላሉ ::Wave👉 @seer_LEWI
🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒

👸ልባም ሴት👸

05 Jan, 06:33


🎅🎄እንኳን አደረሳችሁ 🎄🎅
የገናን በዓል ምስንያት በማድረግ በዓሉን የሚያደምቁላችሁን የክርስቲያን ቻናሎች ልጠቁማችሁ🎅
Wave መግባት ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ @free_wave1

👸ልባም ሴት👸

05 Jan, 05:46


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ አና መዝሙሮችን ያድምጡት ::Wave👉 @seer_LEWI
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲

👸ልባም ሴት👸

04 Jan, 18:02


🏑🏑🏑🏑🏑🏹🏑🏑🏑🏑🏑🏑
የ ገና በዓል ፕሮግራሞችን በተለየዩ ቋንቋዎች ለማግኘት  ከታች ያሉትን ቋንቋ መርጣው ይጫኑ እና ፕሮግራሞችን ይከታተላሉ ::Wave👉 @seer_LEWI
🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒

👸ልባም ሴት👸

04 Jan, 15:33


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ አና መዝሙሮችን ያድምጡት ::Wave👉 @seer_LEWI
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲

👸ልባም ሴት👸

03 Jan, 17:52


🎄አዳዲስ የገና በዓል መዝሙሮች ለማግኘት🎄 መዝሙር የሚለውን ይጫኑ🎄

👸ልባም ሴት👸

03 Jan, 15:24


🏑🏑🏑🏑🏑🏹🏑🏑🏑🏑🏑🏑
የ ገና በዓል ፕሮግራሞችን በተለየዩ ቋንቋዎች ለማግኘት  ከታች ያሉትን ቋንቋ መርጣው ይጫኑ እና ፕሮግራሞችን ይከታተላሉ ::Wave👉 @seer_LEWI
🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒🏒

👸ልባም ሴት👸

03 Jan, 05:51


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ አና መዝሙሮችን ያድምጡት ::Wave👉 @seer_LEWI
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 16:45


🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ
አሁን በዳምጣው የምትሉትን ምራጡ "Join" ያድርጉ 🙏🙏

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 16:07


🎅🎄እንኳን አደረሳችሁ 🎄🎅
የገናን በዓል ምስንያት በማድረግ በዓሉን የሚያደምቁላችሁን የክርስቲያን ቻናሎች ልጠቁማችሁ🎅
Wave መግባት ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ @free_wave1

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 15:47


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 13:52


👉ምን አይነት ቻናል ይፈልጋሉ? ‽🤔

👉What kind of channel do you want? ‽🤔

👉Chaanaalii akkamii barbaadda? ‽🤔
wave @seer_lewi

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 08:35


🎄ይኤንን የመሰሉ እና ልዩ የገና ጥቅሶች እና ለፕሮፋይል የሚሆኑ picture ለማግኘት ከታች መልካም በዓል የሚለውን ይጫኑ🎄

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 05:19


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን ሊንኮችን ወይም የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ ::

👸ልባም ሴት👸

02 Jan, 04:20


👉ምን አይነት ቻናል ይፈልጋሉ? ‽🤔

👉What kind of channel do you want? ‽🤔

👉Chaanaalii akkamii barbaadda? ‽🤔
wave @seer_lewi

👸ልባም ሴት👸

01 Jan, 07:20


🎅🎄እንኳን አደረሳችሁ 🎄🎅
የገናን በዓል ምስንያት በማድረግ በዓሉን የሚያደምቁላችሁን የክርስቲያን ቻናሎች ልጠቁማችሁ🎅
Wave መግባት ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ @free_wave1

👸ልባም ሴት👸

01 Jan, 07:16


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ አና መዝሙሮችን ያድምጡት ::Wave👉 @seer_LEWI
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲

👸ልባም ሴት👸

01 Jan, 07:00


🎅🎄እንኳን አደረሳችሁ 🎄🎅
የገናን በዓል ምስንያት በማድረግ በዓሉን የሚያደምቁላችሁን የክርስቲያን ቻናሎች ልጠቁማችሁ🎅
Wave መግባት ምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ @free_wave1

👸ልባም ሴት👸

01 Jan, 03:35


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን ሊንኮችን ወይም የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ ::

👸ልባም ሴት👸

31 Dec, 18:38


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ከዚህ በፊት ገና በዓል ለመታሰቢያነት የተዘመሩ መዝሙሮችን ለማግኘት  ከታች ያሉትን ሊንኮችን ወይም የዘማሪዎችን ስም መርጣው ይጫኑ ::

👸ልባም ሴት👸

10 Dec, 05:12


ይህን👆 ስም የምትወዱት

👸ልባም ሴት👸

10 Dec, 04:27


👉ምን አይነት ቻናል ይፈልጋሉ? ‽🤔

👉What kind of channel do you want? ‽🤔

👉Chaanaalii akkamii barbaadda? ‽🤔
wave @seer_lewi

👸ልባም ሴት👸

09 Dec, 19:35


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

29 Nov, 10:43


Day_3

ኃጢአተኛ ፣በደለኛ እንኳን ሆነህ እርሱ በፍፁም ፍቅሩ ወዶሀል:: ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጥቶሀል። ከበዛ እና ከተትረፈረፈ ምህረቱ የተነሳ ኢየሱስ የአንተን ሞት ሞቶልህ ሕይወቱንም ስለአንተ አሳልፎ በመስጠት መውደዱን፣ፍቅሩን በቀራኒዮ ገልጦልሀል:: በምህረቱ ባለጠጋ ወደሆነው ውደ እግዚአብሔር ልትቀርብ ትወዳለህ?

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

👸ልባም ሴት👸

28 Nov, 09:06


#Day_2
ሀጢአተኛ እና በደለኛ ሆነህ እንኳን እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ ፍቅሩ ገለጦልሀል:: የእርሱ ፍቅር አንተ እርሱን እንደወደድከው ሳይሆን እርሱ እንዴት አንተን እንደወደደህ ነው:: የእርሱ ፍቅር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ፣ የማይቀያየር፣ ዘላለማዊ ነው:: ዛሬ እርሱን ሳታውቅ ያለህበት ሁኔታ ላይ እንኳን ብትሆን፣ እርሱን ያልተከተልክ እንኳ ብትሆን እርሱ አንተን አውቆህ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ የሆነ ፍቅሩን ገልጦልሀል:: ላይጠላህ ወዶህል! አንተን ለመውደድ ሀጢአትህ እና በደልህ ያላገደውን እንዲሁ የወደደህን አባት ልትከተል ትወዳለህ?

1 ዮሐንስ 4:10፤ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

👸ልባም ሴት👸

27 Nov, 17:39


⚠️ወንጌልን በአንድነት እናገልግል ለ20 ቀን⚠️ ወንጌልን በሶሻል ሚዲያ አንድ ላይ እናገልግል

ወንጌል የፓስተሮች ወይም የወንጌላውያን ሀላፊነት አይደለም  የእያንዳንዱ የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንጂ


⚠️Profile picture(pp) story በማድረግ ባለን ሶሻል ሚዲያ platform በአንድ ላይ ወንጌልን እንስራ⚠️

👸ልባም ሴት👸

27 Nov, 17:35


ሰላሜ ነህ - አስቴር አበበ
#New_Album

God Loves y'all

👸ልባም ሴት👸

25 Nov, 00:07


#Bereket_Lemma New Song

🚨አንተ አለህበት ወይ ከድሎቴ ቀድሞ
አንተ አለህበት ወይ ትልሃለች ነፍሴ ደግሞ
አንተ አለህበት ወይ እዚያ ነው ምቾቴ
አንተ አለህበት ወይ ነው የነፍሴ ጥያቄ

#አያባብለንም❤️

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

23 Nov, 06:48


ሰላም ወዳጆቼ አንድ ድንቅ ቻናል ላስተዋውቃችሁ ለመንፈሳዊ ህይወታችሁ በጣም የሚጠቅም ስለሆነ ማንም join ሳይል እንዳያልፍ button ነክታችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ

👸ልባም ሴት👸

22 Nov, 20:06


🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ መቀላቀል ያለበት  ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻነል ነው
👇👇👇👇👇 join ያድርጉ
➨Wave ለመግባት የምትፈልጉ
👉ከ5K በላይ Subscriber ያላችሁ
📥inbox 👉 @seer_lewi
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

13 Nov, 17:23


የትኛውች የ tv ቻናል ይመለከታሉ🤔
@free_wave1

👸ልባም ሴት👸

13 Nov, 15:23



🎤የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ???🤔🤔
👇👇👇👇👇
በመዝሙሮቹ የተባረካቹ እና የምትወዱትን ዘማሪ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ
➨Wave ለመግባት የምትፈልጉ
👉ከ5K በላይ Subscriber ያላችሁ
📥inbox 👉 @seer_lewi
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

11 Nov, 08:38


ስሜት ይመጣል፣ ስሜት ይሄዳል!

ማናልባት እንደ ስሜታችን ተለዋዋጭ የሆነ ነገር በሕይወታችን አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ በተለዋዋጭነቱ ከምናውቀው ከአየር ጸባይ በፈጠነ ሁኔታ የሚለዋወጥ ነገር ቢኖር ስሜታችን ነው፡፡

ከእውነታው ስንጀምር . . .

ስሜታዊ ፍጥረቶች የመሆናችንን፣ ስሜታችን ደግሞ በየጊዜው (አንዳንዴም በየሰዓቱ) እንደሚቀያየር፣ የስሜታችንን መቀያየር ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር እንደማንችል እና የስሜቶቻችን ጉዳይ ችላ ካልን የፍጻሜያችንን ሁኔታ እንደሚነካው እናስታውስ፡፡ 

በየጊዜው፣ እንደሰማነው፣ እንዳየነውና በዙሪያችን እንዳለው ሁኔታ የሚነካውንና የሚለዋወጠውን ስሜታችን በተገቢው መልክ ለመያዝና የወደፊት ሕይወታችንን እንዳያበላሽ ከፈለግን የሚከተሉት ልምምዶች ይጠቅሙናል፡፡

1.  ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ሃሳብን አለመለዋወጥ፡፡
አንድ ጥሩም ሆነ መጥፎ ስሜት ሲሰማን፣ ፈጥነን የሃሳብ ለውጥ ከማድረግ መቆጠብ ስሜት ከሚያመጣው ጫና ራሳችንን እንድንጠብቅ ያግዘናል፡፡

2.  ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ዓላማን አለመለዋወጥ፡፡
ስሜታችን ጥሩ ሆነም መጥፎ ከዓላማችን ለይተን ማየትና ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ማንኛውም ስሜት እያለ ዓላማችንን መከታተላችንን መቀጠል ስኬታማ ሰዎች ያደርገናል፡፡ 

3. ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት አለመዋወጥ፡፡
ስሜቴ ጥሩ በሆነና መጥፎ በሆነ ቁጥር ከሰዎች ጋር ያለኝን ግንኙነት የሚነካው ከሆነ የተበላሸ ማሕበራ ሕይወትና የሕይወት አቅጣጫ ውስጥ መግባቴ አይቀርም፡፡

ስሜት ሲመጣና ሲሄድ የያዝነውን ትክክለኛ ሃሳብ ይዘን እንቀጥል፤ ዓላማችንን ይዘን እንዝለቅ፤ ከሰዎች ጋር ያለንን ጤናማ ግንኙነት ይዘን እንኑር፡፡ 

https://t.me/Dreyob
@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

10 Nov, 18:04


ፅናት ያስፈልግሀል!

አንተን ከምትፈልገው ነገር የሚያገናኝህ የአላማ ፅናት ነው፤ በህይወት የሚያሸንፈው ብርቱ የሆነ ወይ አስተዋይ (Smart) የሆነው አይደለም፤ ውስጡ ላመነበት ነገር እስከ መጨረሻው የሚጓዝ ነው።

ወዳጄ ኑሮ ሊያደክምህ፣ ነገሮች ሊሰለቹህ፣ ህይወት ተደደጋሚ ልትሆን ትችላለች፤ የደስታን ጥግ ማየት ከፈለክ ግን ላመንክበት ጉዳይ መኖር ጀምር
ከዛ በአላማህ ፅና!


#ዛሬ_የተባረኩት_

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

08 Nov, 11:12


ተጋብዛችኋል❤️

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

06 Nov, 10:50


13ቱ የደስተኛ ትዳር ህይወት ወርቃማ ህጎች


1) እርስ በእርስ ሚስጥር አትደባብቁ። ግልፅ ሁኑ።

2) የትዳር አጋራችሁ ሲናገር በጆሮ ብቻ ሳይሆን ትኩረት ሰጥታችሁ በልባችሁም አድምጡ።

3) ከቤት ስትወጡ አንዳችሁ ለሌላኛው መልካም ምኞት ተለዋወጡ። ውላችሁ ስትገናኙም አንዳችሁ የሌላኛውን የውሎ ሁኔታ ተጠያየቁ።

4) አንዳችሁ የሌላውን ስህተት ይቅር ተባባሉ። ስህተት እየቆጠራችሁ ቂም አትቋጥሩ። አትውቀሱ። ያለፈውን መጥፎ ገጠመኝ ማውራት አቁሙና በአሁኑና በወደፊቱ ተስፋችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ። ጥሩ ለነበረው ጊዜና ድርጊት ደግሞ አመስግኑ።

5) ምግብ ስትበሉ አብራችሁ በአንድ ሰሀን(ትሪ) ተመገቡ። በቂ ምክንያት ከሌለ በቀር ለየብቻ አትተኙ። አብራችሁ ተኙ።

6) በየሳምንቱ መጨረሻ አብሮ ጊዜ ለማሳለፍና ለመዝናናት የቤተሰብ ጊዜ መድቡና አብራችሁ አሳልፉ።

7) በመከላካችሁ ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ ማንንም ሰው ጣልቃ አታስገቡ።

8) እውነኛ ፍቅር በጣም ውድና ጥቂት መሆኑንና እንደ ትዳር አጋራችሁ በደስታም ሆነ በመከራ ጊዜ የሚያፈቅራችሁና አብሯችሁ የሚወጣና የሚወርድ ሰው ላታገኙ እንደምትችሉ አስታውሱ።

9) የምትቃወሙት ነገር ሲኖር በፍቅር አስረዱ። በምታስረዱበት ጊዜም ረጋ ብላቹ አውሩ። አንዳንዴም ዝም ማለትን ተማሩ።

10) የማታደርጉትን ቃል አትግቡ። የገባችሁትን ቃል ግን አክብሩ።

11) አንዳችሁ ሌላኛውን አክብሩ። ደካማ ጎኑን ምክንያት አድርጋችሁ አትናቁ። የሚሻሻል ደካማ ጎን ካለው እንዲያሻሽል አግዙ። የማይለወጠውን ደካማ ጎን ደግሞ ተቀበሉ።

12) የትዳር አጋራችሁ ባስከፋችሁ ወይም ፍላጎታችሁን ባላሟላላችሁ አልያም ከትዳር አጋራችሁ በአንድ ነገር የሚልሻ ሰው ባያችሁ ጊዜ ሁሉ ሌላ ሰው አትመኙ። ምኞት ማመንዘርን ፀንሳ ዝሙትን ትወልዳለች። ዝሙት ደግሞ የምድሩንም የሰማዩንም ቤት የሚያፈራርስ ፈንጅ መሆኑን አትርሱ።

13)  አንዳችሁ ሌላችሁን ለማስደሰትና ኑሯችሁን ለመለወጥ ሌት ከቀን ጠንክራችሁ ስሩ። በዚህ በካፒታሊዝም ዘመን ጥሩ ገቢ ወይም በቂ ሀብት የሌለው ትዳር እያደር ግጭት፣ ሀዘንና መከፋት የሚነግስበት መድረክ መሆኑን አትርሱ።

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

04 Nov, 18:25


👸ልባም ሴት👸 pinned «ሴቶች፦ መልካቸውን፣ቁመናቸውን፣የሰውነት፣ቅርፃቸውን  እያሳዩ በአለማዊ ስታይል፣በአለማዊ አለባበስ፣ቅጥ ባጣ አኳኋን photoቸውን በየሶሻል ሚዲያው ሲለጥፉ... ፨የወንዶችን ትኩረት ለመሳብ፣ ፨ቆንጆ ነሽ ለመባል፣ ፨የውበት ዳር ለመባል፣ ፨ wow ለመባል፣ ፨gorgeous ለመባል፣ ፨cute, sexy, hot ለመባል፣ ፨ ልዩ ነሽ ለመባል፣ ፨ ውበትሽ ያስበረክካል ለመባል፣ ፨ሰውነትሽ ያምራል ለመባል፣ ፨ከሌሎች…»

👸ልባም ሴት👸

04 Nov, 18:23


ሴቶች፦ መልካቸውን፣ቁመናቸውን፣የሰውነት፣ቅርፃቸውን  እያሳዩ በአለማዊ ስታይል፣በአለማዊ አለባበስ፣ቅጥ ባጣ አኳኋን photoቸውን በየሶሻል ሚዲያው ሲለጥፉ...

፨የወንዶችን ትኩረት ለመሳብ፣
፨ቆንጆ ነሽ ለመባል፣
፨የውበት ዳር ለመባል፣
፨ wow ለመባል፣
፨gorgeous ለመባል፣
፨cute, sexy, hot ለመባል፣
፨ ልዩ ነሽ ለመባል፣
፨ ውበትሽ ያስበረክካል ለመባል፣
፨ሰውነትሽ ያምራል ለመባል፣
፨ከሌሎች ሴቶች በልጦ ለመገኘት፣ ፨ከንቱ ፉክክር፣
፨ሙገሳን ለመቀበል፣
፨አድናቆትን ፍለጋ፣
ይዜምልሽ? ይዘመርልሽ?እጣን ይታጠንልሽ? ምን ይደረግልሽ?የክብርን ጌታ ሸፍኖ ለክብር ሽሚያ! ከእግዚአብሔር ጋር ውድድር ለሙገሳ ውድድር፣ ለመወደድ ውድድር፣
ራስን ማምለክ፣ ትኩረት ወደ ራስ፣24ሰዓት መስታወት ፊት፣ ለፀሎት ጊዜ የለም፣ ለመንፈሳዊነት ጊዜ የለም ጊዜሽ ራስሸን በከንቱነት በማሽሞንሞን ያልፋል።
ጣዖትነት፣ዘማዊነት፣ ከሚያዩሽ ሁሉ ጋር መዳራት፣ ራስወዳድነት ትምክህት፣ ኩራት፣ ትዕቢት የልብ እብሪት፣ ከኔ ውጪ ሰው የለም ባይነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከል፣ ራስን ማታለል ነው፣ ወሸት ነው።

የእግዚአብሔር መልክ የለሽም የአለምን መልክ ይዘሻል role modelሽ የአለም ዝነኞች፣ celebrityዎች ስታይልሽ የአለም፣ ንግግርሽ ከtiktok፣ አረማመድሽ ከፊልም ኮፒ፣
የክርስቶስ ነኝ ትያለሽ የክርስቶስ መልክ የለሽም፣ ስናይሽ እንዴት ክርስቶስን ባንቺ እንይ?
ስናይሽ አዲሱ ሱሪሽ ነው ሚታየው፣ ስናይሽ አዲሱ lipstick  ነው ሚታየው፣ ስናይሽ የፀጉርሽ ስታይል ነው ሚታየው፣ ስናይሽ ከፍ አርጎ እያስቆነነ የሚያራምድሽ heel ጫማ ነው ሚታየው፣ ስናይሽ ጡትሽና እምብርትሽ ነው ሚታየው፣ ስናይሽ ወርቅና ብርሽ ነው ሚታየው ስናይሽ በውጫዊ መሽሞንሞን ማጌጥሽ ነው ሚታየው፣ ስናይሽ ባንቺና በአለም ምንም ልዩነት የለም፣ የሴትነት ወጉ፣ ጭምተኝነቱ የለብሽም፣ እግዚአብሔር ስለሚለው ግድ የለሽም።
ፈሪሃ እግዚአብሔር የለብሽም፣ ወንድሞች ባንቺ ይስታሉ፣
እህቶች አንቺን ለመምሰል ሲሉ ያልሆኑትን ለመሆን ይጥራሉ።

ምሳሌ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል፤ በጎዳናዋ አትሳት።
²⁶ ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤ እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው።
²⁷ ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፤ ወደ ሞት ማጀት የሚወርድ ነው።
እግዚአብሔር ስለስንቱ ነፍስ ይጠይቅሽ ይሆን?

እግዚአብሔር መሸንገል አይቻልም አይንን የሰራ እሱ ያያል፣ ጆሮን የሰራ እሱ ይሰማል። በልብሽ ያለውን አመፅ ያያል።
ለነፍሳት ርህራሄ ማጣትሽን ያውቃል።

****
ሁሉም ውሸት ነው፤ ሁሉም ከንቱ ነው፤ ራስን ማታለል ነው። አንቺ የውበት ዳር አይደለሽም። ልብሽ በኩራት አይበጥ እግዚአብሔር ከድንቅ ውበቱ ቆንጥሮ ሰጠሽ እንጂ ውበቱን አልጨረሰብሽም።
ይህም ካንቺ ምስጋና ስለሚገባው እንጂ በርሱ ላይ አመፀኛ እንድትሆኚ አይደለም።
ሰዎች ትኩረታቸው ወዳንቺ ሲሆን ተጠንቀቂ፣ ሰዎች ሲያሞግሱሽ ወዮልሽ!!
የእግዚአብሔርን ክብር መሻማት፦ ለሄሮድስ አልጠቀመም።
ትዕቢት ለናቡከደነፆርም አልጠቀመም።
**** 

ልብሽን ለእግዚአብሔር አስገዢ። እግዚአብሔር ልብን እንደሚያይ እናውቃለን ለዛም ነው ልብሽ ለእግዚአብሔር መገዛት ያለበት። ልብሽ ለእግዚአብሔር ከተገዛ ሁለንተናሽ ይገዛል።

የእግዚአብሔር ስርዓት የታመነ ነው፤
አላዋቂን ጥበበኛ ያደርጋል። መዝ 19:7

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

03 Nov, 18:57


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

👸ልባም ሴት👸

03 Nov, 09:59


ክርስቲያን የሆነ ሁሉ መቀላቀል ያለበት  ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻነል
👇👇👇👇👇 join ያድርጉ

👸ልባም ሴት👸

02 Nov, 07:58


"ሚስቴ የእኔ ምርጫ ጉዳይ ሳትሆን ...

አንድ ቀን አንድ የስነ-ልቦና መምህር ወደ ክፍል ገብቶ ተማሪዎቹን "ዛሬ ጌም ብንጫወት ምን ይመስላችኋል አላቸው?"

ምን አይነት ጌም እንደሆነ ሲጠይቁት፣ እሱን አብረን እናየዋለን አለና ከመካከላችሁ አንድ ፈቃደኛ ተማሪ እፈልጋለሁ አለ። አንድ ተማሪ እጅ አወጣና ጌሙ ተጀመረ።

መምህር:- "ሰላሳ በህይወትህ የምትወዳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ፃፍ!" አለው።

ተማሪው:- ከቤተሰቦቹም፣ ከሩቅ ዘመዶቹም፣ ከጓደኞቹም እያለ የሰላሳ ሰው ስም ፃፈ።

መምህር:- "አሁን ከፃፍካቸው ውስጥ ብታጣቸው ግድ የማይሰጥህን አምስት ሰዎችን ስም ሰርዝ" አለው።

ተማሪውም አምስት ስም ሰረዘ ሰረዘ።
መምህሩ:- "አሁን ደግሞ የአስር ሰዎችን ስም ሰርዝ አለው"።

እንዲህ እንዲህ እያለ የአራት ሰዎች ስም ቀረው(የእናቱ፣ የአባቱ፣ የልጁና የሚስቱ)
መምህር:- "ከነዚህ ከ4ቱ ሰዎች ሁለቱን ሰርዝ አለው።"

ተማሪው: በከፍተኛ የሀዘን ስሜት ተውጦ የወላጆቹን ስም ሰረዘ።

መምህር:- "አሁን የቀሩህ ሁለት ሰዎች ሚስትህና ልጅህ ናቸው ከሁለቱ አንዱን አስቀርተህ አንደኛቸውን ሰርዝ አለው።"

ተማሪ:- በሃዘን እያነባ የልጁን ስም ሰረዘ። ተማሪዎቹ በሁኔታው ግራ ተጋብተው መጨረሻውን ለማወቅ ጓጉተዋል።

መምህር:- "ሚስትህ ብትሞት ሌላ ሚስት ማግባት ትችላለህ፣ እንዴት ከወላጆችህና ከልጅህ አብልጠህ ሚስትህን መረጥካት?" ሲል ጠየቀው።

ተማሪውም:- "ወላጆቼን አጥብቄ ብወዳቸውም እድሜያቸው ገፍቷልና በሞት ትተውኝ ይለዩኛል። ልጄም በፍቅር ተንሰፍስፌ ባሳድገውም ሲያድግ ጥሎኝ ወደሚስቱ ይሄዳል። በህይወት እስካለሁ ድረስ መቸም ቢሆን የማትለየኝ ሚስቴ ናት። ሚስቴ የኔ የምርጫ ጉዳይ ሳትሆን ስጦታዬ ናትና ለዛ ነው እሷን ያልሰረዝኩት" ብሎ መለሰ።

አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች በመልሱ ተደስተው አጨበጨቡለት። መምህሩም አብሮ አጨበጨበለት! እኔም ታሪኩን ስሰማ እጀን ከፍ አድርጌ አጨበጨብኩለት!

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

28 Oct, 07:21


👸ልባም ሴት👸 pinned «💖 የእጮኝነት ጥያቄ ሲቀርብ ምን ማድረግ ይኖርብሻል ? 👉 ከሁሉ አስቀድሞ በጉዳዩ ላይ በእግዚአብሔር ፊት መፀለይ ። ቢቻል ሁኔታዎች ከተመቻቹ በፆም ፀሎት በእግዚአብሔር ፊት መቆየት ። ፆም ፀሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ያስችላል ። ውሳኔ ለመወሰን ከቃሉ አንፃር መወሰን ይገባል ። በፀሎት ቆይታ በኋላ ነገሩ የጌታ ፈቃድ መሆኑን እና አለመሆኑን በሚከተሉት በሁለት በተከፈሉ ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ…»

👸ልባም ሴት👸

28 Oct, 07:21


💖 የእጮኝነት ጥያቄ ሲቀርብ ምን ማድረግ ይኖርብሻል ?

👉 ከሁሉ አስቀድሞ በጉዳዩ ላይ በእግዚአብሔር ፊት መፀለይ ።

ቢቻል ሁኔታዎች ከተመቻቹ በፆም ፀሎት በእግዚአብሔር ፊት መቆየት ። ፆም ፀሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ያስችላል ።

ውሳኔ ለመወሰን ከቃሉ አንፃር መወሰን ይገባል ።

በፀሎት ቆይታ በኋላ ነገሩ የጌታ ፈቃድ መሆኑን እና አለመሆኑን በሚከተሉት በሁለት በተከፈሉ ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ የልብ ምስክርነት በአንዱ በማረጋገጥ ወደ ቀጣዪ ምዕራፍ መሸጋገር ይቻላል ።

💔 ነገሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርሱ ዋና ዋና ምልክቶች ፦

Ⓐ የልብ መታወክ እና መረበሽ
Ⓑ የልብ ፈቃደኝነት ማጣት
Ⓒ ጠያቂውን የመቀበል የአዕምሮ ፈቃደኝነት ማጣት
Ⓓ ወደ ፊት ከጥያቄው ጋር በሚመሠረተው ጋብቻ ተስፋ ማጣት
Ⓔ ስለ ጠያቂው ማሰብም አለመፈለግ
Ⓕ ጠያቂውን ዳግመኛ ለማግኘት አለመፈለግ
Ⓖ የጥያቄውን መልካምም ሆነ ደካማ ጎን ለመቀበል ፈቃደኝነት ማጣት እና የመሳሰሉት ሲሆኑ

🤮 በፀሎት በጌታ ፊት በቆየሽባቸው ጊዜያት እነዚህ ስሜቶች በልብሽ ከተሰማሽ ወደሚቀጥለው የቅርርብ ሂደቶች መግባት አስፈላጊ አይደለም ።  ለእጮኝነት ለጠየቀሽ ሰው ፍቃደኛ አለመሆንሽን አስታውቂ ።

ነገሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርሱ ዋና ዋና ምልክቶች ፦

Ⓐ የልብ ማረፍ እና ሰላም
Ⓑ ፍፁም የሆነ የልብ ፈቃደኝነት
Ⓒ የጨያቂውን ጉድለት እንኳን ለመቀበል የሚያስችል ቁርጠኝነት
Ⓓ ስለ ጠያቂው ደጋግሞ በማሰላሰል በልብ ውስጥ የሚፈጠር የደስታ ስሜት
Ⓔጠያቂው ጥያቄውን ባቀረበ ጊዜ የተናገረበትንና የተጠቀመበትን ቃላት ደጋግሞ በማሰላሰል የሚሰማ የልብ ደስታ
Ⓕ የቀጠሮው ቀን ደርሶ ለቀረበው ፈቃደኝነትን ለመግለጽ መናፈቅ
Ⓖ ነገሩን እግዚአብሔር ከግብ እንዲያደርሰው ደጋግሞ የመፀለይ ፍላጎትና ሸክም በልብ ውስጥ መሰማት
Ⓗ ለጠያቂው ማዘን ፥ መራራትና ለጎደሎት ነገሮች ማሰብ መጀመር  እና የመሳሰሉት ሲሆኑ

🥰 እነዚህ ምልክቶች በልብሽ ከተሰማሽ ወደ ሚቀጥለው ዙር ለመሄድ  አንድ ሰው ሚስጢር የሚጠብቅ ማማከርና  እና ስለጠያቂው የማወቅና እና የማጣራት  ሂደት እንዲረዳ ማድረግ ።

👉ጠያቂውን የሚመለከቱ ማጣራት ያለብሽ ፦

1.በሰፈሩ እና በቤተሰቡ ያለው ምስክርነት
2. የስራው ቦታ ያለው ምስክርነት
3.በቤተክርስቲያን ያለው ምስክርነት

በእነዚህ ሶስት አቅጣጫ ስለ እሱ በርካታ ነገሮችን ማወቅ ያስችልሻል ።

👉ማጣራት እና ማወቅ ያለብሽ ምንድነው ?

# ክርስቲያን መሆኑን
# ከዚህ በፊት ጋብቻ ያለመመስረቱን
# ሌላ እጮኛ ያለመያዙን
# የስራ እና የትምህርት ደረጃ
#  ዕድሜውን
# የጤንነት ሁኔታ
# ወቅታዊ የቅድስና እና መንፈሳዊ ሕይወቱን
# ማህበራዊ ህይወቱን  እና ወዘተ ...

🌹 እነዚህን ማጣራቶች ከተደረጉ በኋላ በማጣራት ሂደት ውስጥ የተገኙት ውጤቶችን ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር በማየት ውጤቱ ከእግዚአብሔር ጋብቻ ተኮር ፈቃድ የማይፃረር ከሆነ የቀጠሮው ቀን ከመድረሱ አስቀድሞ ወደ ውሳኔ መድረስ ተገቢ ነው ።
ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ !!!

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

26 Oct, 16:51


የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ?

👸ልባም ሴት👸

26 Oct, 16:18


👉ምን አይነት ቻናል ይፈልጋሉ? ‽🤔

👉What kind of channel do you want? ‽🤔

👉Chaanaalii akkamii barbaadda? ‽🤔
wave @seer_lewi

👸ልባም ሴት👸

25 Oct, 20:30


👉ምን አይነት ቻናል ይፈልጋሉ? ‽🤔

👉What kind of channel do you want? ‽🤔

👉Chaanaalii akkamii barbaadda? ‽🤔
wave @seer_lewi

👸ልባም ሴት👸

25 Oct, 20:25


የድሮ ቆየት ያሉ የ አልበም መዙሙሮች

👸ልባም ሴት👸

13 Oct, 22:25


  እጮኝነት

ክርስቲያን የፍቅር ግንኙነት መጀመር ያለበት ከክርስቲያን ጋር ብቻ ነው ። እጮኛ መሆን ያለበት ጌታ አየሱስን የተቀበለ መሆን አለበት ።

እጮኝነት ብዙ ከማውራት ብዙ መፀለይ መልካም ነው ።

ጥሩ አፍቃሪ ፍቅረኛውን አልጋ ከመጋበዝ ይልቅ መንፈሳዊ ነገር የሚጋብዝ ነው ።

ጥሩ አፍቃሪ የሚባለው በቅድሜያ የራሱን ህይወት ከጌታ ጋር ያጠነክርና ፍቅረኛውንም ህይወት ለማጠንከር የሚሰራ ነው።

አጮኝነት ሊቀር ስለሚችል እዩልኝ እዩልኝ አያስፈልግም ።

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

13 Oct, 22:24


📘📘📘"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን  ይቀበላል ።
ምሳ 18:22

👸ልባም ሴት👸

10 Oct, 16:02


ሃምሳ በመቶው ሃላፈነታችሁን አትዘንጉ! 

ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞች፣ በተለይም ለባለትዳሮች . . .

ዛሬም ደግሜ ላስታውሳችሁ፣ እውነተኛ ፍቅር ማለት አንድ ሰው ሙሉ ስለሆነ መውደድ ማለት አይደለም፡፡ በተቃራኒው እውነተኛ ፍቅር ማለት አንድን ሰው ስለወደድነው ሙሉ ወደመሆን እንዲያድግ መቀበልና መደገፍ ማለት ነው፡፡

በፍቅር ወይም በትዳር አጋራችሁ ላይ የምትመለከቱት “ጎዶሎ” ሁኔታ (አለባስ፣ አመለካከት፣ አለማወቅ፣ የግንኑነት ብቃት ጉድለት …) ሊሻሻል የሚገባው እንደሆነ ካመናችሁ ለውጡ እንዲመጣ የማድረጉ ሃምሳ በመቶው ሃላፊነት የእናንተም ጭምር እንደሆነ አትዘንጉ፡፡ አጋራችሁማ ቀድሞውኑ ያንን ማድረግ ቢችል ኖሮ ባደረገው ነበር፡፡ የፍቅር አጋራችሁ የሚችለውን ያህል አድርጎ እዚህ ደርሷል፡፡ አሁን ደግሞ “አጋር” እና “ደጋፊ” አገኘሁ ብሎ ለማገዝና ለመታገዝ ራሱን ሰጥቷል፡፡

አጋራችሁ ያለበትን ጉድለት በየጊዜው በመጠቀም በንግግርና በንቀት አእምሮን መደብደብ አጥፍቶ ከመጥፋት እርምጃ ተለይቶ አይታይም፡፡ ስለዚህ አጋራችሁ ያቃተው ነገር ካለ፣ “አትችልም” በማለት ከመደብደብ ይልቅ እንዲችል ማገዝ … አጋራችሁ የማታውቀው የእውቀት ዘርፍ ካለ፣ አለማወቋን እያነሱ ስነልቦናዋን ከማጥቃት ይልቅ እንድታውቅ መደገፍ …

አጋራችሁ ስትለብስ “የማያምርባት” ልብስ ካለ የሚያምርባትን ልብስ በመግዛት እንዲያምርባት  ማድረግ … የጎበዞችና በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች ልምምድ ነው!

የአጋራችሁ ለመለወጥ መፈለግ የእሱ (የእሷ) ሃምሳ በመቶ ሃላፊነት ሲሆን፣ እናንተ አጋራችሁን ለመለወጥ የምታደርጉት ድጋፍና መዋጮ ደግሞ ሌላኛውን ሃምሳ በመቶ ይይዛል፡፡

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

10 Oct, 15:46


🥰 የጥሩ የፍቅር ወይም የትዳር ጓደኛ  ምልክቶች
😍🥰🥰😍

➢ ብዙ ሴቶች እና ወንዶች ፍቅር የሚሉት አፍላነት የወለደውን ስሜታቸውን  ነው::

➢ ይሄንን አፍላነት አምነው ወደትዳር ሲገቡ በሴቶች ላይ የከፋ የስነልቦና ጉዳት ይደርሳል ።

➢ አንድን ሰው ከመሬት ተነስተን ልናፈቅረው አንችልም:  አንዳች የሚማርከን ነገር ሊኖር ይገባል:  ያ ነገር ደሞ ከአካላዊ ገፅታ እና ከአንደበት ቃላት የዘለለ መሆን አለበት::

➢ ከአንድ ወንድ ሊማርክሽ የሚገባው ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ማንነቱ አይተሽ መሆን አለበት ለምሳሌ የሚከተሉት የጥሩ አፍቃሪ ጥቂት ምልክቶች ናቸው ።

➢ከነዚህ ምልክቶች በተቃራኒ የሆነን ወንድ ወይም አብረሺው ስትሆኚ ለነገ ተስፋ የማይሰማሽ ፍርሃት የሚሞላሽን ወንድ አፈቅረዋለሁ ብትይ ይሄ የወጣትነት ስሜት እንጂ ፍቅር አይደለም።

ከጥሩ ፍቅር  ወይም የትዳር ጓደኛ ምልክቶች ውስጥ የተወሰኑትን እነሆ ፦

# ላንቺ እውነተኛ አክብሮት እንክብካቤ ሊኖረው ይገባል ።

# ከጋብቻ በፊት ለሚፈፀም ወሲብ የማይገፋፋሽ መሆን አለበት።

# ሁሌም ያንቺን ደስታ የሚፈልግ ባንቺ ደስታ ሀሴት የሚያደርግ መሆን አለበት።

# የሚያዳምጥሽ እና ሃሳብሽን የሚያከብር መሆን አለበት ።

# ሁሌም በራስ መተማመንሽን የሚገነባ ፤ የሚደግፍሽ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንሽ እንዲሰማሽ የሚያደርግ መሆን አለበት።

# ካንቺ ጋር በቂ ጊዜ የሚያሳልፍ የማይዋሽ ፤ስለወደፊታችሁ በግልፅ ካንቺ ጋር የሚያቅድ  መሆን አለበት።

# እያንዳንዱ ንግግሩ ከተግባሩ ጋር መግጠም አለበት ።

# ከቤተሰቡ እና ከ ጓደኞቹ ጋር ከሆነ ጊዜ በኃላ ሊያስተዋውቅሽ ይገብል።

# በግልፅ ካንቺ ጋር ለመታየት እጅ ለእጅ ለመያያዝ ማፈር የለበትም ።

# አንዳንድ ነገሩን እና አቋሙን ላንቺ ሲል መተው እና መሰዋት መቻል አለበት

# በሂወትሽ በሚገጥም ሃዘን ጊዜ ልክ እንዳንቺ ሆኖ ሲያዝን እና ሲያፅናናሽ ማየት አለብሽ ።

ባንቺ እምነት ሊኖረው ይገባል
______
@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

08 Oct, 12:37


🚨 ኢየሱስ እኮ ይወድሻል!

ምናልባት ብዙ ሰዎች ላይወዱሽ, ስላንች መልካም ነገርን ላይናገሩ ይችላሉ ምናልባት በአንዳንድ ምክንያቶች አንቺ ራስሽ ራስሽን ጠልተሽ ሊሆን ይችላል የኔ እህት ግን አንድ ለዘለዓለም የማይለወጥን እውነት ልንገርሽ ምንም ሁኚ ምንም በየትኛውም ድካም ውስጥ ልትሆኚ ትችያለሽ ኢየሱስ ግን ይወድሻል ፍቅሩ የተዛባውን ነገርሽን መቀየር ይችላል ብቻ አንቺ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት ቅረቢ።

Join and Share
@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

06 Oct, 18:03


ስወዳቹ ይህን መልክት👆👆 እስከ መጨረሻው አንብቡት 👸🥰

👸ልባም ሴት👸

06 Oct, 18:02


👸ልባም ሴት👸 pinned «👰ልባም ሴት!  👑 “ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።”   — ምሳሌ 31፥10 ➽ መልካም ሴት ብቻ ሳይሆን መልካም ሚስትም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ሰዎች ገንዘብ ስላላቸው ቆንጆ ሴት ማግባት ይችሉ ይሆናል። ልባም ሴትን ግን በገንዘባቸው ማግኘት አይችሉም። ትዳር ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል። ገንዘብ ግን መልካም ትዳርን ሊያመጣ አይችልም። የልባምነት ጠባይ ምንድነው?…»

👸ልባም ሴት👸

06 Oct, 18:01


👰ልባም ሴት!  👑

“ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።”
  — ምሳሌ 31፥10

➽ መልካም ሴት ብቻ ሳይሆን መልካም ሚስትም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ሰዎች ገንዘብ ስላላቸው ቆንጆ ሴት ማግባት ይችሉ ይሆናል። ልባም ሴትን ግን በገንዘባቸው ማግኘት አይችሉም። ትዳር ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል። ገንዘብ ግን መልካም ትዳርን ሊያመጣ አይችልም። የልባምነት ጠባይ ምንድነው? የልባም ሴት መገለጫዋ ምንድነው?

😍 1. ታማኝ ናት!

“የባልዋ ልብ ይታመንባታል፥ ምርኮም አይጐድልበትም።”
  — ምሳሌ 31፥11

➽ ባሏ ልቡን ጥሎ ያርፍባታል። የምታደርገውንና የምትወስነውን ታውቃለች። በሌሎች ምክር አትስትም። ብቻዋን አትወስንም። ለመስማት ስፋት አላት። የሰማችውን ሁሉ ግን አታምንም። የምታደርገውን ሁሉ አትናገርም። የጀመረችውን መልካም ነገር ትጨርሳለች። ክፉውን ነገር ታቋርጣለች። ባልዋ ምርኮ የማይጎድልበት ከሆነ ከምርኮ በፊት ትግልና ድል አለ። በኑሮ ውስጥ ያለውን ትግል በቆራጥነት ታግዘዋለች። ችግርን አታደንቅም። ከትዕግሥት በኋላ ተስፋዋን ትወርሳለች። ኃላፊነትን መሸከም ትችላለች። ምሥጢር ጠባቂ፣ እውቀት ፈላጊ ናት።

😍 2. መልካምነቷ አይለወጥም!

“ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም።”
  — ምሳሌ 31፥12

➽ ወደ ኑሮ ከገባች በኋላ የጠባይ ለውጥ አይታይባትም። መልካምነቷ ሥራ ሳይሆን ሕይወት ነው።  ሁልጊዜ አንድ አይነት ማንነት አላት። የምታደርገውን የምታደርገው ለእግዚአብሔር ክብር ለራሷ ደስታ እንጂ ለሰው ብላ አይደለም። ክፉ ቢደረግባት እንኳ በሰው መለወጥ ታምናለች እንጂ የድካም ዘመንን ጠብቃ አትበቀልም።

😍 3. ባለሙያ ናት!

"የበግ ጠጕርና የተልባ እግር ትፈልጋለች፥ በእጆችዋም ደስ ብሎአት ትሠራለች። እርስዋ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ ከሩቅ አገር ምግብዋን ትሰበስባለች።"
               -ምሳሌ.31፥13-14

➽ ራሷን ትችላለች። የባሏ የአቅም ጥገኛ ለመሆን አትፈልግም። በዓለም ላይ መናናቅን ራስ ያለ መቻል እንደሚያመጣው ትረዳለች። አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችን ታቋቁማለች። በበግ ጠጉር ስጋጃውን ፣ ምንጣፉን፣ ብርድ ልብሱን ትሰራለች። በተልባ እግር ለስላሳ ልብስ ፣ ነገስታት የሚለብሱትን ታዘጋጃለች። መጪውን ዘመን በመገመትም ቤተሰቡ እንዳይራብ ምግብን ከአገራቱ ታሰባስባለች። የእጇ ጥበብ ቦርሳዋን ስለሚሞላው ጤፉን ከአድአ፣ በርበሬውን ከማረቆ፣ ማሩን ከማሻ፣ ቅመሙን ከኦሞ.........ታስመጣለች።ዠ

😍 4. ቤቷን በትክክል ታስተዳድራለች!

“ገና ሌሊት ሳለ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለገረዶችዋም ተግባራቸውን ትሰጣለች።”
  — ምሳሌ 31፥15

➽ ንቁ ናት። በጊዜ ተኝታ ማልዳ ትነቃለች። የቀኑ ኃይል ያለው ማለዳ ላይ መሆኑን ትገነዘባለች። ወንድ እንደ ልጅ እንክብካቤ ፈላጊ መሆኑን ትገነዘባለች። የቀኑን የሥራ ዝርዝር ለሠራተኞችዋ ትሰጣለች። ቤቱን አትለቀውም። ቤቷን ታውቀዋለች።  ሠራተኞችም የሚያከብሯት ሙያና ትጋት ካላት እንደሆነ ትረዳለች። ለቀኑ ከተፈቀደው ውጭ ሠራተኞቿን በሥራ አትጎዳም። ሲያርፉ አትበሳጭም። ሰው መሆናቸውን ትገነዘባለች።

😍 5. ቆራጥ ናት!

" እርሻንም ተመልክታ ትገዛለች፤ ከእጅዋም ፍሬ ወይን ትተክላለች። ወገብዋን በኃይል ትታጠቃለች፥ ክንድዋንም ታበረታለች። ንግድዋ መልካም እንደ ሆነ ትመለከታለች፤ መብራትዋ በሌሊት አይጠፋም።" -ምሳ.31፥16-18

➽ ይህቺ ሴት እውቀቷ ከፍ ያለ ነው። ስለ አፈር አይነት ስለሚያበቅለው ፍሬ በቂ ግንዛቤ አላት። እርሻን ስትገዛ ተመልክታ እንጂ ተስገብግባ አይደለም። በቂ የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ባለሙያ ናት። የከበረ ፍሬ ወይን በመትከል ሀብቷን ከፍ ታደርጋለች። ቆራጥ ናት። ፈተናዎች አያቆሟትም። ስለ ችግሮች ዜማ አታወጣም። በችግሮች ውስጥ የድል ዝማሬ ታዘጋጃለች። አልችልም ባይነትን ታሸንፋለች። አንድ አይነት ሥራ ላይ ችክ አትልም። መልካም ካልሆነ ትቀይራለች። ሱቆች ቢዘጉ በሌሊት እንግዳ ቢመጣ የመጠባበቂያ ኑሮ አላት። አታፍርም። ድስት አጥባ አትተኛም።

😍 6. ድሆችን ትረዳለች!

“እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች።”
  — ምሳሌ 31፥20

➽ ሌባ ማለት ርቦት የሚሰርቅ ብቻ ሳይሆን ኖሮት የማይሰጥ መሆኑን ትገነዘባለች። ይህቺ ሴት በአገራችን ወጪን የመጋራት እቅድ ሳይመጣ ተሜ ሲለምን እንጀራ አጥፋ የምትሰጥ፣ ድሆችን በጨለማ ሄዳ የምትጎበኝ ናት። እዚህ የደረሰችው በእግዚአብሔር ቸርነት መሆኑን ትገነዘባለች። ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ትሸጉጣለች። የወደፊት የልጆቿን መውደቂያ እያሰበች መልካምን ታቆያለች።

😍 7. ባሏን ታስከብረዋለች!

"ለቤትዋ ሰዎች ከበረዶ ብርድ የተነሣ አትፈራም፥ የቤትዋ ሰዎች ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና።  ለራስዋም ግብረ መርፌ ስጋጃ ትሠራለች፤ ጥሩ በፍታና ቀይ ግምጃ ትለብሳለች። #ባልዋ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ በበር የታወቀ ይሆናል።"  -ምሳሌ.31፥21-23

➽ ለክረምት የሚሆነው ልብስ በሥርዓት ይቀመጣል። ወቅቱ ሲደርስ ይወጣል።  ራሷን የምትጥል አይደለችም። የተመረጠ ትለብሳለች።  አለባበሷ ሴትነቷን የሚያከብር እንጂ የሚያራቁት አይደለም። ባልዋንም ታለብሰዋለች። በእርሱ አለባበስ ሚስቱ ትደነቃለች። የአደባባይ የወንዶች ድል የሴቶች ድብቅ ጸሎት መሆኑን ታስመሰክራለች። በዚህ ሁሉ ልባምነቷ ባልዋና ልጆቿ ሳይቀር ያመሰግኗታል። የግፍና የስንፍና እንጀራ ትጸየፋለችና ለእርቅ ትፈለጋለች።

🙏ባልዋም ሲያመሰግናት፦
" መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፥ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ። ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት፥ ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።"  -ምሳሌ.31፥28-31

➽ በውበቴ ልመስገን አትልም። ራሷን ራሷ አልሰራችምና ውበት ለምስጋና አያበቃም። እንዲሁ ልደነቅ አትልም። ሥራዋ ግን ያስደንቃታል። የዚህ ሁሉ ጨዋነትና ትጋት መሠረቱ እግዚአብሔርን መፍራትዋ ነው።

"ልባም ሴትነት በውሳኔ የሚገኝ እንጂ ለጥቂቶች የተሰጠ የማይደገም ጸጋ አይደለም"

@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

04 Oct, 19:04


👸ልባም ሴት👸 pinned an audio file

👸ልባም ሴት👸

04 Oct, 03:42


🚨 እስቲ ይህንን ትምህርት ስሙ
ከብዙ ነገር ትድናላችሁ።
የምትወዷቸው ከሆነ ብያንስ ለአምስት እህቶቻቹ Share አድርጋቹ የነገ ህይወታቸውን አድኑ🙏

Join and Share
@libamua
@libamua
@libamua

👸ልባም ሴት👸

04 Oct, 03:35


(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2 )
=====================
21፤ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል።
22፤ ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።
...
24፤ የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።

#ለጌታሽ_የምትጠቅሚ_ሁኚ🙏