የእምነት በር @kiyyaa2929 Channel on Telegram

የእምነት በር

@kiyyaa2929


https://t.me/kiyyaa2129 #የግሩፑ ሕግጋት

1. ስድብ አይፈቀድም፡፡
2. የሌላ ቡድን ማስታወቂያ አይፈቀድም፡፡
3. የግለሰቦችን ምስልና የግል መረጃ መለጠፍ አይፈቀድም፡፡
4. በክርስትና ቤተ እምነቶች መካከል ክርክር አይፈቀድም፡፡
5. ስለ ሃይማኖት እንጂ ስለ ሌላ ጉዳይ ውይይት ማድረግ አይፈቀድም፡፡
6 ግሩፑ የክርስቲያኖች እና የሙስሊሞች የመወያያ ግሩፕ ነው!👈👆

የእምነት በር (Amharic)

በር የክርስቲያን እና ሙስሊሞች መወያያ ግሩፕ ነው! 'የእምነት በር' በላይ የሚያውቁት እና ጽሁፎችን በማግኘት የእምነትን ዕውቂዎችን በመጫን እና መረጃዎችን በማውረድ መዋጮችን ይከተሉልን። ከዝህ ስኮንዶ ትላይ እና መካከለኛ መጠቆም አልቻሉም። የክርስቲያን እና ሙስሊሞች መወያያ የግሩፑ ክርስቶም ለመሆኑ ለመግባት መከታተል የሚለዋጋብን የሊቃውን ማኅበረሰብን እና መሰረትን በመዝማር በጽሁፍ እና በህይወት ከፈተሻል። የሚያስፈልጉበት እና የሚያስፈልጉበት ቆይ።

የእምነት በር

10 Feb, 17:43


አዲስ ነብስ ለክርስቶስ

የእምነት በር

17 Jan, 20:09


በነበር የቀረ ታሪክ አለኝ አሁን ግን ይመስገን የጌታ ነኝ ትለናለች እህታችን

የእምነት በር

16 Jan, 18:53


አንዲት እህታችንን አዳኟን ጌታ ተቀብላ አስጠምቀናታል
እንኳን ጌቲ ረዳሽ ሲስ

የእምነት በር

06 Jan, 18:25


እንኳን አደረሳቹሁ
ሉቃስ 2:11 "ዛሬ በዳዊት ከተማ  
                    መድኃኒት እርሱም
                    ክርስቶስ ጌታ የሆነ
                    ተወልዶላችኋልና።"

"ድንግል ምድር፣ በምድር ላይ ራስ የነበረውን አዳምን  ​​ወለደች ድንግል በሰማያት ላይ ራስ የነበረውን አዳምን ዛሬ ወለደች። የአሮን በትር አበቀለ የደረቀውም እንጨት ፍሬ ሰጠ። ሕፃን የተሸከመውን የድንግል ማኅፀን ነውና ምሥጢሩ ዛሬ ተነግራል(ተገልጧል)"።

#St.Ephraim the Syrian
         Hymns on the Nativity
            hymn 1 paragraph 2

"በዳዊት ከተማ የተወለደው ክርስቶስ ጌታ ነው። ሉቃ 2፡11 እና በእምነት ቃሉን እንድትቀበሉ ብቻ ሳይሆን ከብሉይ ኪዳንም ማረጋገጫን እንድትቀበሉ ክርስቶስ ከመገለጡ በፊት ከአብ ጋር ጌታ እንደሆነ ታውቃላችሁን? ወደ መጀመሪያው መጽሐፍ ዘፍጥረት ሂድ፡ እግዚአብሔር አለ፡- ሰውን በመልካችን ሳይሆን በአምሳሉ እንፍጠር ይላል። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 አዳምም ከተፈጠረ በኋላ ቅዱሱ ጸሐፊ እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔርም ሰውን ፈጠረ። በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው። ሰው የእግዚአብሔር(የአብ) ሥራ ብቻ ሳይሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስም ሥራ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ የመለኮትን ክብር ለአብ ብቻ አልወስንም ወልድንም ጭምር ጨምሯል።"

#St.cyril of Jerusalem
       Catechetical lectures
                 lecture 10:6

የእምነት በር

04 Jan, 15:30


እስልምና 😳😳😳ተበታጠሰ 🤔

የእምነት በር

19 Dec, 15:45


ምዝገባ 👉@VikiOrthodox

የእምነት በር

19 Dec, 02:50


ቁርአን የፈጣሪ ቃል እስልምና የአምላክ መገለጥ እንዳልሆነ የሚያስረዳ አንዲት ነገር ልበላችሁ

ፈጣሪ ሚመለከው ምን ስለሆነ ነው
አምላክ ስለሆነ አምላክ ነው ይመለካል።

ፈጣሪ ሚመለከው ሌላ ፈጣሪ ስላለ እሱን በመቃወ በመከራከር ከሆነ የእሱ አምልኮ የጀመረው ፈጣሪ ተብሎ ሚመለክ ስላለ ነው እንጂ ከመጀመሪያውኑ የነበረ አምላክ ሆኖ አደለም ሀሰተኛ ነው ያስብላል

እና ወደ ነጥቡ ስንገባ 

ክርስትና እውነተኛው የፈጣሪ አምልኮ ያለበት ትክክለኛው ነው እንዴት
የክርስትናው ትምህርት

ኢየሱስ >> ተሰቅሏል ሚለው አልተሰቀለም ሚል እምነት አስተምህሮ ስለነበረ አደለም

እግዚአብሔር ልጅ >> አለው ሚለው እግዚአብሔር ልጅ የለውም የሚል እምነት አስተምሮ ስለነበረ አደለም

ኢየሱስ>> ፍጹም ሰው ፍጽም አምላክ ነው ሚለው ኢየሱስ ፍጹም ሰው አምላክ አደለም ሚል እምነት አስተምህሮ ስለነበረ አደለም

ሥላሴ>> ሚለው ትምህርት ሥላሴ አምላክ አደለም ሚል እምነት አስተምህሮ ስለነበረ አደለም

ከላይ የተጠቀሱት ክርስቲያናዊ ትምህርቶች ከክርስትናው በፊት ስለነበረ እሱን በመቃወም ያለ ሃይማኖት አደለም ልክ ከላይ ፈጣሪ ምን ስለሆነ ይመለካል ብለን እንዳየነው ስለሆነ ነው

እሄ ማለት ደሞ ትክክለኛው የፈጣሪ አስተምሮ ከላይ እንዳየነው እንደዚ👇 ሳይሆን ክርስትና

ፈጣሪ ሚመለከው ሌላ ፈጣሪ ስላለ እሱን በመቃወ በመከራከር ከሆነ የእሱ አምልኮ የጀመረው ፈጣሪ ተብሎ ሚመለክ ስላለ ነው እንጂ ከመጀመሪያውኑ የነበረ አምላክ ሆኖ አደለም ሀሰተኛ ነው ያስብላል
ልክ እንደ ትምህርቱ የፈጣሪ ቃል ትምህርትን እንደዚ👇ስለሆ ነው

ፈጣሪ ሚመለከው ምን ስለሆነ ነው
አምላክ ስለሆነ አምላክ ነው ይመለካል።
በተቃራኒው እስልምና

ኢሳ አልተሰቀለም ሚለው ትምህርታቸው
>> ተሰቅሏል ሚል እምነትም አስተምህሮ ስለነበረ

አላህ ልጅ የለውም ሚለው >> እግዚአብሔር ልጅ አለው ሚል እምነት አስተምህሮ ስለነበረ

ኢሳ አምላክ አደለም ሚለው ኢስላማዊ ትምህርት >> ኢሳ አምላክ ነው ሚል እምነት አስተምህሮ ስለነበረ ነው

ሚገርመው በእስልናው አላህ አምላክ ነው ሚባለው ለራሱ ሥላሴ ሚል አስተምህሮ ስለነበረ ነው እሱን በመቃወም የተነሳ ትምህርት ነው በስነ መለኮት ትምህርትኳም

እሄ ማለት የእስልምናው ትምህርት መጀመሪያ እንዳየነው 👇 ስለሆነ ነው

ፈጣሪ ሚመለከው ሌላ ፈጣሪ ስላለ እሱን በመቃወ በመከራከር ከሆነ የእሱ አምልኮ የጀመረው ፈጣሪ ተብሎ ሚመለክ ስላለ ነው እንጂ ከመጀመሪያውኑ የነበረ አምላክ ሆኖ አደለም ሀሰተኛ ነው ያስብላል
ክርስትናው ግን እንደዚ👇 ስለሆነ ነው

ፈጣሪ ሚመለከው ምን ስለሆነ ነው
አምላክ ስለሆነ አምላክ ነው ይመለካል።
የኢየሱስ አምላክነት፣ የኢየሱስ መሰቀል፣ እግዚአብሔር ልጅ አለው፣ ሚለውና የሥላሴ እነዚ ትምህርቶች ከክርስትና በፊት ስለነበሩ እነሱን በመቃወም ሳይሆን ማንም ሳያስተምር እውነተኛው አስተምህሮ የፈጣሪያችን ቃል ትምህርት ስለሆነ ነው

እሄ ማለት መጀመሪያ በነበረው የክርስትና አስተምህሮ የነበረው ትምህርት ላይ የሚነሱ ኑፋቄ ሀሰተኛ ትምህርቶች እየተወገዙ እየተለዩ ደኢፍ እየተባሉ ይሄዳሉ እንጂ

እንደ እስለምናው የክርስትና አስተምሮ ስለነበረ እሱን በመቃወም በእሱ ላይ ሚሰጥ ሚመሰረት ትምህርት ከሆነ ማለትም
ፈጣሪ ሚመለከው ሌላ ፈጣሪ ስላለ እሱን በመቃወ በመከራከር ከሆነ የእሱ አምልኮ የጀመረው ፈጣሪ ተብሎ ሚመለክ ስላለ ነው እንጂ ከመጀመሪያውኑ የነበረ አምላክ ሆኖ አደለም ሀሰተኛ ነው ያስብላል
👆 ስለሆነ ነው ነው ያስብላል እስልምናው

ስለዚህ ቁርአን የፈጣሪ ቃል እንዳልሆነ በዚ ይታወቃል ማለት ነው ።

ክርስትና አስተምህሮ እምነት ማለት ግን
ፈጣሪ ሚመለከው ምን ስለሆነ ነው
አምላክ ስለሆነ አምላክ ነው ይመለካል። ክርስትና እንደዚ
ስለሆነ እውነተኛው የፈጣሪ ቃል አምልኮ ትምህርት ክርስትና እንደሆነ ይታወቃል ማለት ነው

“እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።”
  — ሉቃስ 24፥44

“በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”
  — ኤፌሶን 2፥20

ሁሉ ተፈጽሟል በቁርአን አትታለሉ

የነብያት አስተምህሮ እምነት ስላለ እሱን በመቃወም የተመሠረተ እንጂ የነብያት አስተምህሮ ሁኖ አደለም

ክርስትና እምነት የነብያት አስተምህሮ ተከታይ ነኝ ሚል ስላለ እስልምናው በዚ ትምህርት ተቃውሞ የተመሠረተ ሀሰተኛ ሲሆን።
ክርስትናው ግን የነብያት አስተምህሮ ነኝ ሚል ስላለ እሱን በመቃወም የተመሠረተ አደለም ።

እስልምናው ክርስትና ከሌለ የማይኖር ክርስትናውን እምነት በመቃወም የተመሠረተ ሲሆን
ክርስትናው ግን እስልምና ከመኖሩ በፊት የነበረ እምነት ስለሆነ ክርስትናው እውነተኛ ነው

ክርስትና ስላለ እሱን በመቃወም የነሳ ሲሆን  እስልምና ክርስትናው ግን እስልምናው ሳይኖር የነበረ ወደፊትም ሚቀጥል እውነተኛው እምነት አስተምህሮ ነው

ሰይጣን ሰይጣን ነኝ ገሀነብ ሚከታችሁን አስተምህሮ ተቀበሉኝ ብሎ ይመጣል ብላችሁ መቼስ እንማጠብቁ እርግጠኛ ነኝ ንቁ ንቁ ሙስሊሞች የመዳን ቀን ዛሬ ነው

ክርስቲያኖች ለሙስሊም ሼር

የእምነት በር

05 Dec, 22:44


ህዳር 27/2017 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ

👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት

👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር

👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን ሲሰቀል በመሰቀሉ የተገኙት እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው አባታችን #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት ፃድቁ አቡነ #መብአ_ፅዮን በምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

የእምነት በር

01 Dec, 08:45


የመጨመር አመት ኑ በብርሀኑ ተመላለሱ

የእምነት በር

25 Nov, 22:28


አንዱ ሙስሊም ጓደኛዬ

“ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” ኢሳይያስ 9፥6

ይሄ ጥቅስ ምስጢረ ተዋሕዶ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ጌታችን ፍጹም ሰው ዘመን የሚቆጠርለት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተገለጠ እንደመሆኑ መጠን ሕፃን ብሎ ይገልጸዋል። የሰው ልጆችም ወንድ እና ሴት ተብለው በጾታ ይለያሉ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ሲገልጠው ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ብሎ አስቀምጦታል።

ሕፃን ብሎ ሲገልጸው ጾታውንም ወንድ ሲለው ብቻ አንብበን ሌላውን ችላ ካልነው ሰው ብቻ ሊመስለን ይችላል። ይሄ ግን ሙሉ መረዳት እና ከእግዚአብሔር የሆነ መገለጥ አይደለም። ኢየሱስ ሕፃን በመሆን ሰው እንደመሆኑ በየጥቂቱ አድጓል ። ይህ ሕፃን ተብሎ የተገለጠው ከሰዎች እንደ አንዱ ሁኖ በምድር ላይ የተመላለሰው ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል።

አንዱ ሙስሊም ጓደኛዬ ኢየሱስ ለእኔ ብሎ ያደረገውን ሰው እንደመሆኑ የተቀበለውን ነገር እያነሳ ተራበ ተጠማ በማለት ሊያሸማቅቀኝ ሞከረ ። እርሱ ያልተረዳው አንድ ነገር ለማሸማቀቅ ይጠቅሙኛል ብሎ የተጠቀማቸው ቃላት ሁሉ እኔን የሚያኮሩኝ መሆናቸውን አልመገንዘቡ ነው። የእኔ ትምክህት እኮ የኢየሱስ መከራ ነው በቁስሉ እኮ ነው የፈወሰኝ። እርሱ በእኔ በኃጢአተኛው ሳያፍር በደሙ ሊያነጻኝ ሰው የሆነው ወደ ከፍታ ሊያወጣኝ ዝቅ ባለው ንጉሴ አምላኬ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት አፍራለሁ?

“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ዮሐንስ 1፥29 ምን አልባት ይሄንን ጥቅስ ያየ አንድ ሰው ተገኝቶ ለእኛ ዋጋ ለመክፈል በግ መባሉ ለመታረድ በጎተቱ በችንካር መወጋቱ የመስቀሉን መከራ አይቶ ሰለ ኢየሱስ የባሕርይ አምላክነት ግር ሊለው ይችላል።

ሰለዚህ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደው በግ ሰለተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ በሌላኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተባለውን እስቲ ላካፍላችሁ ፦ " #በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።" (ራእ 17: 14) ሰለ በጉ መጽሐፉ ገና አልጨረሰም " በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። አራቱም እንስሶች አሜን አሉ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ። (ራእ 5:13-14 ) በጉ ለእኔ ሲል በተቀደሰ ፊቱ ላይ ምራቅ ሲተፋበት ሊቶስጥራ ላይ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ሲገረፍ ቀራኒዎ ላይ በአምስቱ ቅንዋት ሲቸነከር ብታይው ተራ በግ እንዳይመስልህ እና እንዳትሳሳት። በጉ በሰማይ እና በምድር ያሉ ፍጥረታትን ሁሉ አምልኮ የሚቀበል የባሕርይ አምላክ ነው። ሰለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን በተለይም አዲስ ኪዳን ስናነብ የአባታችንን ቃል መመሪያ አድርገን እነያዝ።

ሊቁ አባታችን ሄሬኔዎስ እንዲህ በማለት ጽፎልናል ፦ የከበሩ መጻሕፍት ክርስቶስ ሰው እንደሆነ እንደሚነግሩን አምላክም እንደሆነ እነርሱ እንዲሁ ይነግሩናል ግዙፍ እንደሆነ እንደሚነግሩን ረቂቅም እንደሆነም ይነግሩናል ። የእግዚአብሔር ቃልም እንደሆነ እርሱ ራሱም እግዚአብሔር እንደሆነ እንዲሁ ይነግሩናል ።

ሰለዚህም ከኢትዮጵያዊ ሊቅ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጋር ሁነን እንዲህ እንላለን ፦ ነፍስህን ሰጥተህ በጎችህን የተቤዠህ ሊቀ ካህናችን አንተ ነህ ከኃጢአት ንጹሕ የሆንክ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያልክ ሊቀ ካህናታችን አንተ ነህ ለአባትህ ራስህን መሥዋዕት አድርገህ ያቀረብክ ሊቀ ካህናችነን አንተ ነህ አጣኙም ሕይወታችንን ያጣፈጥክ ዕጣኑም አንተ ነህ፡፡ [ውዳሴ መስቀል 2:5]

አቤል ተፈራ በላይ
15/03/2017 ዓ/ም
ወልድያ ወሎ አማራ ኢትዮጵያ

የእምነት በር

23 Nov, 17:36


ሰበር ዜና ደሞ መጣ 😁

የእምነት በር

23 Nov, 17:10


ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)


#ጾመ_ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹#ጾመ_ነቢያት (#የነቢያት_ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹#ጾመ_አዳም (#የአዳም_ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹#ጾመ_ስብከት (#የስብከት_ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹#ጾመ_ልደት (#የልደት_ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹#ጾመ_ፊልጶስ (#የፊልጶስ_ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹#ጾመ_ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡-

ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡

ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

#ማኅበረ_ቅዱሳን

የእምነት በር

23 Nov, 16:24


ነቢያት ቃል ሥጋ ይኾን ዘንድ በናፍቆት የጾሙት ጾም ነው ጾመ ነቢያት ። ይኽም እንዲዋጃቸው ተሰግዎቱን በመናፈቅ የተደረገ ነው ።እኛም ምጽአቱን በመናፈቅ ማራናታ ብለን በንስሐ በከበረው ቅዱስ ቁርባን ተዋሕደን ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌምንና የዋጀንን ጌታ በመጠበቅ ተስፋ ትንሳኤን ገንዘብ እያደረግን በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ በአምልኮተ ቅዳሴ ፣ በፍቅርና በአንድነት ጾሙን እንጹም...ጌታ መንፈስ ቅዱስ የበረከት ፣ ያጣነውን የምናገኝበት ፣ ዲያብሎስን ድል መንሻ ኃጢአትን መደምሰሻ ፣ ኢየሱስን ከእናቱ ጋር የምናይበት ፣ አብ የሚከብርበት ጾም ያድርግልን ........ አሜን!
እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ጾመ ነቢያትን ከቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ስያሜና የአምልኮ ሥርዐት አንጻር አስተንትኖ እናደርጋለን 🥰

የእምነት በር

19 Nov, 15:35


አይቀርም ዛሬ 👌

የእምነት በር

18 Nov, 11:30


እፎይ አካውቱ ተዘግቷል አዘግተውታል እዚ ያላችሁ አዲሱን ኮፒሊክ ፎሎና ሼር ሪፖስት እያረጋችሁ

https://vm.tiktok.com/ZMhtGcmW6/

የእምነት በር

17 Nov, 14:45


ይህ ህመም  ላንተ ምን ጠቀመህ ?🤷‍♂
ይህ ቁስል ከቶ ምን ፀጋ ይጨምርልሃል ?🤷‍♂ የእኔ መፈጠር በህይወት መኖር ለአንተ ከቶ ምን ይፈይድልሃ ?🥰 

መልሱ ምንም በቃ ምንም

አካልህ ቢቆስል ለእኔ 🥰
ደምህ ቢፈስ ለእኔ  🥺
ርቃንህን ቢፈረድብህ ለእኔ 🥺
ብትታመም ጥቅሙ ለእኔ 🥰
ሁሉም ለእኔ ...

የእምነት በር

16 Nov, 12:15


የድሮ ተገልጋይዋ የአሁን አገልጋይዋ

የእምነት በር

14 Nov, 19:10


ርግቧ እናቴ 🥰
ስደተኛዋ ሙሽራ 🥺
ንፅህይቷ እመቤት
ከርታታዋ ኮከብ
የውሃ ማሰሮዋ

.... 🥰🥰🥰

ሰላማዊውን ልጅሽን ተጠምተነዋል ። ጠጥተነው ተመግበነው ከረሐበ ሰላም እንፈወስ ዘንድ ይዘሽልን ነይ ።

አዛኟ እባክሽ ሰላምቻንን ክርሰሰቶስን ይዘሸቸልን ነይ 🥰🥺🥺
“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።”
— መኃልየ. 7፥1

የእምነት በር

14 Nov, 14:46


🔥ትውልድ እየነቃ ነው አዳኙን እያወቀ ነው

የእምነት በር

12 Nov, 15:54


"በሥጋ ያዩት ሰቅለውታል በመንፈስ ያዩት ሰግደው ፣ጌትነቱን መስክረው ፣ አምልከው ድነውበታል"
" የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኾይ እኔ ኃጢአተኛውን ማረኝ አሜን! 🥰"

……………………………………………
ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ወንጌል ይማሩ...!
ይቆየን

የእምነት በር

12 Nov, 12:30


የቅዱሳን አማላጅነት ለምን አስፈለገን ?!!

በዲያቆን ሔኖክ ሀይሌ ❤️❤️❤️🙏

የእምነት በር

12 Nov, 08:38


ኡኡኡኡ ኧረ ተዘረፍን አላህ ሰረቀን 😂

ማስረጃው ያውና 👇

“ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።”
  — ማቴዎስ 19፥24

إِنَّ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ وَلَا يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ الْجَمَلُ فِي سَمِّ الْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُجْرِمِينَ

እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ገነትን አይገቡም፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡
7:40

የእምነት በር

08 Nov, 08:58


https://youtu.be/gI8Ex3yWPyM?si=55bFRJoTAwHsOOYK

የእምነት በር

04 Nov, 07:41


https://youtu.be/gI8Ex3yWPyM?si=ZMOdlAldjoDvJbM8

የእምነት በር

03 Nov, 19:58


ፓስተሩን ገቢ አድርገነዋል
መፅሀፍ ቅዱስ የገባው መቼም ጴንጤ አይሆንም ::

የእምነት በር

03 Nov, 15:50


9ኛ.ሐፍሳ፡- የቀድሞ ባሏ በጦርነት ሲሞት አባቷ ኦማር ቢን አል-ኸጣብ ለኦትማን
ሊድራት ብሎ ኦትማንም ሊያገባት ሲል ሙሐመድ ስለፈለጋት ለእርሱ ተወለት ፡፡

ከአይሻ ጋር ብዙ ጊዜ ይጣሉ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሙሐመድ የፈታት ቢሆንም
በኋላ እንደገና መልሶ አግብቷታል፡፡
Sahih Muslim vol.2 no.2642 p.576; vol.2
no.2833 p.625; vol.2 no.3497 p.761; Abu Dawud vol.2 no.2448 p.675; vol.3
no.5027 p.1402. Ibn-i-Majah vol.3 no.2086 p.258, Sahih Bukhari 7:62:119, Sahih
Bukhari 3:43:648, Sahih Muslim 9:3511

10ኛ.ማይሙና ቢንት ሀሪስ Sahih Muslim 8:3284, Sahih Bukhari 3:29:63, Sahih Bukhari
5:59:559 & Sahih Muslim 24:5248 see also Sahih Muslim vol.1 no.1671,1674,1675 p.368-369;
vol.2 no.1672 p.369, Ibn-i-Majah vol.3 no.2408 p.435; Sunan Nasa’i vol.1 no.809 p.492; vol.2

11ኛ.ዑም ሰላማ፡-
Sahih Muslim 8:3443, Sahih Muslim 4:2007, Sahih Muslim 26:5415, See
also: Al-Muwatta 37 6.5, Sahih Muslim 8:3444, Sahih Muslim 8:3445 & Al-Muwatta 28 4.14

12ኛ.ሂንድ፡-
Sahih Muslim vol.3 no.4251-4254 p.928-929.

13ኛ.ሳና ቢንት አስማ (2ኛ ስሟ አል-ነሻት)፡- al-Tabari vol.9 p.135-136, al-Tabari
vol.39 p.168.

14ኛ.ዘይነብ ቢንት ኩዛይማ፡- Sunan Nasa’i vol.1 64 p.129, al-Tabari vol.7 p.150, alTabari vol.39 p.163-164 and al-Tabari vol.9 p.138

15ኛ. ሀብላ፡- al-Tabari vol.39 p.166

16ኛ. አስማ ቢንት ኖማን (ከጋብቻ በኋላ በፍቺ የተሰናበተች)፡-
Bukhari vol.7 book 63
no.181 p.132, al-Tabari vol.10 p.190, al-Tabari vol.39 p.190.

17ኛ.ግብፃዊቷ ማሪያህ (በጦር ምርኮ የተያዘች)፡-
Sahih Muslim vol.4 footnote 2835.
p.1351, al-Tabari vol.9 p.141, al-Tabari vol.39 p.193.

18ኛ.ሪይሃና ቢንት ዛይድ
(በጦር ምርኮ የተያዘች)፡- al-Tabari vol.8 p.39. See also alTabari vol.9 p.137, 141.

19ኛ.ዑም ሻሪክ ጋዚያህ ቢንት ጃቢር (ከጋብቻ በኋላ በፍቺ የተሰናበተች)፡-
al-Tabari
vol.9 p.139, Ibn Sa’d in Tabaqat, 8 p.110-112

20ኛ.2ኛዋ ማይሙና፡- she gave herself to Mohammed as a wife. Mohammed did
not accept her, but gave her to a poor Muslim.
Sahih Muslim vol.2 footnote 1919.

21ኛ.3ኛዋ ዘይነብ፡-
al-Tabari vol.39 p.165

22ኛ.ካውላህ ቢንት አል-ሁዳይል
(በጦር ምርኮ የተያዘች)፡- al-Tabari vol.9 p.139, alTabari vol.39 p.166

23ኛ.ሙላይካህ ቢንት ዳውድ (ከጋብቻ በኋላ በፍቺ የተሰናበተች)፡-
al-Tabari vol.8
p.189, al-Tabari vol.39 p.165

24ኛ.አል-ሻንባ ቢንት አምር (ከጋብቻ በኋላ በፍቺ የተሰናበተች)፡-
al-Tabari vol.9 p.136

25ኛ.አል-አሊያህ
(ከጋብቻ በኋላ በፍቺ የተሰናበተች)፡-
al-Tabari vol.39 p.188, alTabari vol.9 p.138.

26ኛ.አምራህ ቢንት ያዚድ፡- Ibn-i-Majah vol.3 no.2054 p.233 vol.3 no.2030 p.226,
al-Tabari vol.39 p.187

27ኛ.ራሂማ አል-አሚን
(ከጋብቻ በኋላ በፍቺ የተሰናበተች)፡-
al-Tabari vol.39 p.187

28ኛ.ቁቲይላህ ቢንት ቃይስ (ከመሐመድ በፊት የሞተች)፡- al-Tabari vol.9 p.138-139

29ኛ.ሳና ቢንት ሱፈያን፡- al-Tabari vol.39 p.188

30ኛ.ሻራፍ ቢንት ኸሊፋህ፡- al-Tabari vol.9 p.138

ከ 30ዎቹ በተጨማሪ ደግሞ ሙሐመድ ይፋዊ በሆነ መንገድ ባያገባቸውም የቤት
ሰራተኛ ሆነው ለዝሙትም ይጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ ሴቶች በሐዲሱ ላይ
ተጠቅሰዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

1ኛ. ሳልማህ፡-
Abu Dawud vol.3 no.3849 p.1084

2ኛ. ማይሙና፡- Ibn-i-Majah vol.3 no.2531 p.514; Abu Dawud vol.1 no.457 p.118

3ኛ. ስሟ በውል ያልታወቀ ሲሆን ሙሐመድ ከተጠቀመባት በኋላ ማህሚያህ
አል- ዙባይዲ ለተባለ ተከታዩ በሽልማት ሰጥተዋል፡፡
al-Tabari vol.8 p.151

4ኛ. አሁንም ስሟ በውል ያልታወቀች የሙሐመድ ቅምጥ ሆና ሳለ በድብቅ ከሌላ ሰው
ስትማግጥ ተይዛ የተፈረደባት ሰራተኛ በአቡ ዳውድ ሐዲስ ላይ ተጠቅሳለች፡፡ Abu
Dawud vol.3 no.4458 p.1249

5ኛ.ሙሐመድ ገላውን ታጥበው የነበረች አንዲት የጥቁር ቆንጆ ሠራተኛ ነበረችው፡፡ Abu Dawud vol.1 no.332 p.87

6ኛ. ዑም አይማን፡- al-Tabari vol.39 p.287.

የእምነት በር

03 Nov, 15:50


ሰላሳ ስድስቱ የነብዩ ሙሐመድ ሚስቶች

1ኛ.ከድጃ፡- መሐመድ የሲራራ ነጋዴ በነበረ ሰዓት የእርሷም ሀብታም ነጋዴ ባሏ
ስለሞተባት ለንግዷ ሥራ ስትል በ15 ዓመት የምትበልጠውን የ25 ዓመቱን
መሐመድን በ40 ዓመቷ በ595 ዓ.ም አግብታቸዋለች፡፡ መሐመድም ‹‹በእኔ ዘመን ካሉ
ሴቶች ሁሉ ምርጧ እርሷ ናት›› በማለት አሞካሽተዋታል፡፡ (Sahih Bukhari 4:55:642,
See also: Sahih Bukhari 5:58:163 Sahih Muslim 31:5965)
ከድጃ ቀድመው ከሞቱ
ሁለት ባሎቿ 3 ልጆች ወልዳ ነበር፡፡
ለሙሐመድም 2 ወንዶችና 4 ሴቶች ልጆችን
ወልዳለት ነበር ነገር ግን ሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ሁለት ዓመት እንኳን ሳይሞላቸው
ነው የሞቱት፡፡ አባቷን ኸዋይሊድ ቢን አሳድ ቢን ጋብቻውን ቀድመው በጽኑ
ስለተቃወሙ አባቷን በማታለል ነበር መሐመድን ያገባችው፡፡ በሐዲሱ ላይ ብዙ ቦታ
ተጠቅሳለች፡፡ (Sahih Muslim 31:5972, Sahih Bukhari 5:58:164, Sahih Bukhari
5:58:165, Sahih Bukhari 7:62:156, Sahih Bukhari 8:73:33, Sahih Bukhari 7:93:576,
Sahih Muslim 31:5971, Sahih Bukhari 5:58:167, Sahih Muslim 31:5968, Sahih Muslim 31:5970, Sahih Bukhari 9:93:588, See also: Sahih Bukhari 5:58:168, Sahih Bukhari 3:27:19 & Sahih Muslim 31:5967)

2ኛ.ሳውዳ ቢንት ዛማ፡-ወፍራምና ቀርፋፋ ቢጤ ስለነበረች ሌሎቹ የሙሐመድ ሚስቶች ይንቋት ነበር፡፡
Sahih Bukhari 2:26:740, Sahih Muslim 7:2958, See also: Sahih Bukhari 2:26:741.
የመጀመሪያ ባሏ አል-ሳክራን ቢን አምር ቢን አብድ ሻምስ (al-Sakran
b. ‘Amr b.Abd Shams) ወደ አቢሲኒያ ከሄደ በኋላ የክርስትናን እምነት
ተቀብሎ በዚያው ነው የሞተው፡፡ “Sauda’s ex-husband, al-Sakran b. ‘Amr b. ‘Abd
Shams became a Christian in Abyssinia and died there.” al-Tabari vol.9 p.128.
ሳውዳ ዕድሜዋ እየገፋ ሲመጣ ሙሐመድ ሊፈቷት ሲል እርሷ ጋር የሚያድርበትን
ተራ ለአይሻ አሳልፋ ስለሰጠች እንዳትፈታ ሆናለች፡፡ Sahih Bukhari 3:47:766, See
also: Sahih Bukhari 3:48:853, Sahih Muslim 8:3451, Sahih Muslim 8:3452 & AlTabari (Arabic source; translated by Mutee’a Al-Fad

3ኛ.አይሻ፡- የአይሻን ታሪክ በገጽ---ላይ አይተነዋል፡፡ ከሁሉም ሚስቶቻቸው እጅግ
ይወዷት የነበረች ሕጻን ሚስታቸው ናት፡፡ Sahih Bukhari 5:57:114, /Sahih Bukhari
4:55:623

4ኛ.ዘይነብ ቢንት ጃህሽ፡- ቀድሞ ባራህ ትባል ነበር፣ ሙሐመድ ነው ይህን አዲስ ስም ያወጣላት፡፡ ይህቺ ሴት ሙሐመድ ያሳደገው የዛይድ ሚስት የነበረች ቢሆንም ሙሐመድ ግን በሴራ ልጁን እንዲፈታት ካስደረገ በኋላ ወዲያው ነው ያገባት፡፡ ሙሐመድ ይህንን
ኢሰብአዊ ድርጊት በፈጸሙ ጊዜ ‹‹ያሳደኩትን የዛይድን ሚስት ስለማግባቴ የቁርአን
ጥቅስ ከሰማይ ወርዶልኛል›› በማለት ለሰራው ኃጢአት አላህን ሽፋን አድርገው
ተጠቅመውበታል፡፡ ይህንንም ድርጊት ቁርአኑ (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33፡36-38) እና
ሐዲሱ በግልጽ ዘግበውታል፡፡ Sahih Bukhari 9:93:516, Sahih Bukhari 6:60:310

5ኛ.ሳፊያ፡- ሙሉ ስሟ ሳፊያ ቢንት ሁያይ ትባላለች፡፡ ከአይሁድ ወገን ስትሆን
በካይባር ጦርነት ወቅት ሙሐመድ በጦር ማርከውና አስገድደው ነው ያገባት፡፡ በሐዲሱ ላይ እንደተዘገበው ኪናን የተባለውን ወጣት ባሏን አሰቃይተው እንዲሞት ካደረገ
በኋላ እርሷን ወዲያውኑ ወደ መኝታው ድንኳን ይዘዋት ሄደው አብረዋት ያደረው ፡፡
ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ አባቷን ሁያይንና ወንድሟን ከሌሎች አይሁዶች ጋር በሰይፍ
እንዲሰየፉ አድርገዋቸዋል፡፡ Sahih Bukhari 1:8:367 see also: (Bukhari vol.2 book 14
ch.5 no.68 p.35; vol.4 book 52 ch.74 no.143 p.92; vol.4 book 52 ch.168 no.280
p.175 and al-Tabari vol.39 p.185.)

6ኛ.ፋጢማ፡- ይህችኛዋ የሙሐመድ ሚስት ፋጢማ አል-ዳሀክ ቢን ሱፈያን ወይም
ፋጢማ አል-ኪላቢያህ እየተባለች ትጠራለች፡፡ al-Tabari vol.9 p.39, al-Tabari vol.39
p.186.
ነገር ግን ሌላ ፋጢማ የምትባል የሙሐመድ ሴት ልጅ አለች፡፡ ቀጥሎ ባሉት
ሐዲሶች ላይ የተጠቀሰችው ልጁ ፋጢማ ናት፡፡ Bukhari 1:5:278, Bukhari
4:53:396, Ibn-i-Majah vol.1 no.465 p.255 and Sunan Nasa’i vol.1 no.228 p.224; vol.1
no.417 p.307.
ሙሐመድ የልጁን ባል ዓሊን ‹‹ከልጄ ሌላ አንድ ሴት እንኳ
እንዳታገባ›› በማለት ለሌሎች ተከታዮቹ እስከ 4 ሚስት ድረስ አግቡ ብለው
በቁርአኑ የደነገገውን በወለዳት ልጁ ሲሆን ግን ሌላ ሴት እንዲደረብባት ፈጽሞ
አልፈለገም፡፡
ዓሊም እንደታዘዘው ሌላ ሴት ሳይደርብ የኖረ ቢሆንም ሙሐመድ ከሞተ
በኋላ ግን በጦርነት ማርኮ ያመጣትን ራቢያ የተባለች ቆንጆ ሴት አግብቷል፡፡ Ibn-iMajah vol.3 no.1998-1999 p.202-204, al-Tabari vol.11 p.66, Bukhari 3:34:302 &
Bukhari 4:53:325.

7ኛ.ጁዋይሪያህ፡- ሙሐመድ የባኑ ሙስጣሊቅ ጎሳዎችን ድንገት የጂሃድ ወረራ አድርገው
በጦር ምርኮነት ወስደው ነው ያገቤት፡፡ እርሷን ከመውሰዱ በፊት ግን ሙሳፊ ቢን
ሳፍዋን የተባለውን ባሏን እንዲገደል አድርገዋል ፡፡
Sahih Bukhari 3:46:717, Sahih
Muslim 19:4292, al-Tabari vol.9 p.133, Bukhari vol.3 book 46 ch.13 no.717 p.432 &
Sahih Muslim vol.2 no.2349 p.520.
ጁዋይሪያህ በጣም ውብ ሴት ስለነበረች
ሙሐመድም በውበቷ ተማርከው ‹‹አንቺ እኔን ካላገባሽ ዘመዶችሽን በባርነት
እገዛቸዋለሁ›› ብሎ ስላስገደዳት ነው አግብታው ለመኖር የተስማማችው በምርኮ
የያዘባትን አንድ መቶ የጎሳ አባላቶዎቿን ከእስር እንደሚለቅላት ከተደራደረ በኋላ
ነበር፡፡ ያገባችው

8ኛ.ዑም ሀቢባ፡- ከመጀመሪያ ባሏ ከዑቤይዱላህ ጋር ሆነው ወደ አቢሲኒያ ከተላኩት ሰዎች ውስጥ አንዷ የነበረች ሲሆን እርሷ ከተመለሰች በኋላ
ሙሐመድን ማግባቷን ባሏ ሲሰማ ወደ ክርስትና እምነት ተቀይሯል፡፡
al-Tabari vol.39
p.177. see also Sahih Muslim vol.2 no.3413 p.739; vol.2 no.2963 p.652; Sahih Muslim vol.2 no.1581 p.352; vol.2 no.3539 p.776 Ibn-i-Majah vol.5 no.3974 p.302.

የእምነት በር

03 Nov, 10:17


ይህን ወንድም ፎሎ አድርጎት እሚገርም ወንድም ነው😍

  👇


“https://www.tiktok.com/@a..l..r..a..e..d?_t=8qv24nMJGTY&_r=1

የእምነት በር

03 Nov, 10:17


ይደመጥ

የሙሐመድ ሰሀባ አሊ ከእስልምና የወጡትን
በእሳት አቃጠላቸው 😥

የእምነት በር

31 Oct, 07:37


እነኾም አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ወረደ
(ትንቢተ ዳንኤል ፬፣፲፫)

በመጋቤ ብሉይ መምህር መክብብ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ማኅበረ ተዋሕዶ ዘ-ኦርቶዶክስ
ደቂቃው //56፡26//

Enehom And Kidus Tebaki Kesemay Werede
(Tnbite Daniel 4፡13)
Be Megabe Bluy Memhr Mekbib
Lememhrachn Kale Hiywet Yasemaln
MAHBERE TEWAHDO ZE-ORTHODOX
👉👂👂👈
https://youtube.com/@kiyyaa2129?si=6uVcGXZyd58PhbCS
የዩቲዩን ቻናል👆

የቴሌግራም ቻናል👆

የእምነት በር

31 Oct, 07:36


የምሥጢረ ሥላሴ ምሥጢር
ከባለፈው የቀጠለ
በመምህር ፈቃዱ ሳህሌ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ማኅበረ ተዋሕዶ ዘ-ኦርቶዶክስ
ደቂቃው //34፡26//

Ye Mstire Slase Mstir
Kebalefew Yeketele
Be Memhr Fekadu Sahle
Lememhrachn Kale Hiywet Yasemaln
MAHBERE TEWAHDO ZE- ORTHODOX*
👉🏼👂🏼👂🏼👆🏼https://youtube.com/@kiyyaa2129?si=6uVcGXZyd58PhbCS

የዩቲዩብ ቻናል👆

የእምነት በር

31 Oct, 02:36


ሰዎች ላይ እንዳልፈርድ ምን ላድርግ?
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

የእምነት በር

29 Oct, 03:47


ለፈሪው ኡስታዝ አድርሱ 😂

የእምነት በር

28 Oct, 17:35


​​ሥርዓተ ቅዳሴ

ቅዳሴ ማለት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለየ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ ሰጠ ማለት ነው። ሥርዓት ማለት ደግሞ ሠርዐ፡ ሠራ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው። ትርጉሙ ሕግ: ደንብ አሠራር ማለት ነው። በአንድ ላይ አድርገን ስናነበው የምሥጋና ሥርዓት ማለት ነው የሚመሰገነው  ደግሞ እግዚአብሔር ነው።

ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡

ቅዳሴ፡-
• በሰማይ የሚገኘውን ሥርዓት በምድር መተግበር ነው።
• ቅዱስ ቁርባን የሚቀርብበት እግዚአብሔርን የምናመልክበት ሥርዓት ነው።
• በደስታ የምናከናውነው እግዚአብሔርን የምናመልክበት ጸሎት ነው።
• ቅዳሴ አባቶች ካህናት እና ምእመናን ያሳተፈ የምሥጋና ሥርዓት ነው። ስለዚህ ዘወትር ለቅዳሴና ለመንፈሳዊ ትምህርት ትኩረት ልትሰጡ ይገባል።

ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲቆናት በመቀደስ ምእመናን ደግሞ በማስቀደስ  ይሳተፋሉ ከሁሉ በላይ አምላካችን የሚገኝበት እመቤታችን ቅድስት ማርያም የምትገኝበት መላእክት የሚገኙበት ሁሉም ቅዱሳን እንደተሰጣቸው ክብር የሚገኙበት ጸሎት ነው ስለዚህ ስናስቀድስ ብዙ በረከት እናገኝበታለን።

በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ መሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?

አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ፤ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ተሟልተው ይገኙበታል። እዚህንም 5ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

1. የቁርባን መስዋዕት፡-
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ጸሎት ነው። ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል።

2. የከንፈር መስዋዕት፡-
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡

3. የመብራት መስዋዕት፡-
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሠጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህውም ጌታችን ጨለማ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡

4. የዕጣን መስዋዕት፡-
የዕጣን ጸሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል። ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ ወደ ሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል።

በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያለውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡

5. የሰውነት መስዋዕትነት፡-
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል። በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡

ይህ የጸሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦
1. የዝግጅት ክፍል
2. የንባብና የትምህርት ክፍል
3. ፍሬ ቅዳሴ፦ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው። እነዚህም፡-
3.1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
3.2. ቅዳሴ እግዚእ
3.3. ቅዳሴ ማርያም
3.4. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
3.5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
3.6. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
3.7. ቅዳሴ ባስልዮስ
3.8. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
3.9. ጎርጎርዮስ ካልእ
3.10. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
3.11. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
3.12. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
3.13. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
3.14. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ

- የጌታችን በዓል ከሆነ (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጳጉሜ እሑድ ቀን ከዋለች ሰንበት (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

የእምነት በር

28 Oct, 09:46


ሴት ልጅ በእስልምና 😥😥😥

የእምነት በር

27 Oct, 15:12


omg 🥺 ኧረ ጭካኔዉ
ክርስቲያን መሆን ሚፈልግም አንድ ሙስሊም በዚ ሁኔታ ነዉ እንዳይድን ሚደረገዉ በነፍሳቸዉ ላይ ወሰነዉ ጌታን የተቀበሉት በቤቱ ያፅናቸዉ አስልምና ግን እንደዚ ነዉ ነፃነትን ሚጨቁነዉ እዉነተኛዉ አምላክ ብዙ አምላክ ተብለዉ በነፃ ፍቃዳቸዉ ያመለኩትን በአለማችን ላይ ምንም ያላለ የነፃ ፍቃድ አምላክ ነዉ እስልምና በአለም ያለዉን የሚታየዉን ነፃ ፍቃድ አምላክ አዉነታ የተቃረነ ስለሆነ አላህ አምላክ አደለም ሊሆንም አይችል ሀኖም አያቅም

የእምነት በር

27 Oct, 15:10


ውይይት


የሙሐሙድ ግፍ 😥

ቤተሰቦቾን ገሎ
ባሎን በጋለ ብረት አቃጥሎ ገሎ


በ3ኛው ቀን አገባት 😥

ይደመጥ

የእምነት በር

27 Oct, 08:03


ቅድስት ሥላሴ አንድ መለኮት(ባህሪ) ስላለ እንዲሁም አንድ መለኮታዊ ፈቃድ ነው ያለው።
       #አብ አምላክ ነው
       #ወልድም አምላክ ነው
       #መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው። ሶስቱም አካላት አምላክ መባላቸው ሶስት አማልክት ናቸው አያስብልም ምክንያቱም ሶስቱም አካላት ከአንዱ መለኮት የተነሳ አንድ አምላክ ነው።ልክ እንደዚሁም አንድ #ፈቃድ ነው ያላቸው።
     #አብ ፈቃድ አለው
     #ወልድም ፈቃድ አለው
     #መንፈስ ቅዱስም ፈቃድ አለው።ሶስት ፈቃድ አላቸው ማለት አይደለም። በቅድስት ሥላሴ አስተምሮ አንድ መለኮታዊ ፈቃድ/Divine will/ነው ያለው ስለሆነ አንድ ባህሪ እንዳላቸው ሁሉ አንድ ፈቃድ ነው ያለው።
ስለዚህ የአብ ፈቃድ የወልድም የመንፈስ ቅዱስም ነው።የወልድ ፈቃድ የአብም የመንፈስ ቅዱስም ነው።የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የወልድም የአብም ፈቃድ ነው።

#ቅዱስ_አምብሮስ
"እንግዲህ፡— ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አንድ አምላክ ብቻ አለ ። ዘዳግም 6:13 አንድ አምላክ የአብና የወልድና የመንፈስ ቅዱስ መለኮት አንድ ስላለ እንጂ ኃጢአተኛው ሰባሊዮስ እንዳለው አብና ወልድ አንድ አካል ናቸው በማለት አይደለም ። አንድ መለኮት ባለበት ግን #አንድ_ፈቃድ አንድ ዓላማ አለ"[1]

#ቅዱስ_ባስልዮስ
"እኔን ያየ አብን አይቷል; የዮሐንስ ወንጌል 14:9 የመለኮት ባሕርይ ውህደትን አይቀበልምና፥ ወይም መልክን አይደለም፤ ነገር ግን #የፈቃዱ በጎነት፣ ከዋናው ነገር ጋር #አንድ ሆኖ ፣ ተመሳሳይ እና እኩል ሆኖ የሚታየው፣ ወይም ይልቁኑ በአብ ውስጥ እንደ ወልድ ነው።
ስለዚህም አብ በወልድ በኩል መፍጠሩ የአብ ፍጽምና የጎደለው አለመሆኑን ወይም የወልድን ኃይል እንደ ደካማ አድርጎ የሚያሳይ ሳይሆን #የፈቃዱን_አንድነት እንደሚያመለክት እውነተኛው ትምህርት በሁሉም አቅጣጫ ተገልጧል"[2]

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ገባሬ_መንክራት
"ሁሉም አካላት አንድ ተፈጥሮ አንድ ባሕርይ #አንድ_ፈቃድ ናቸው እና ቅድስት ሥላሴ ይባላሉ  እነዚህም ደግሞ በሕይወት የሚኖሩ ናቸው፥ በሦስት አካላት አንድ ባሕርይ እና አንድ ዝርያ ናቸው"[3]

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ
" ፈቃዴን አላደርግም በእኔና በአንተ ዘንድ ያለውን እንጂ ከእኔ ሌላ ማንም የለምና አንድ መለኮት እንዳለን እንዲሁ #አንድ_ፈቃድ አለን"[4]

[1]#St.Ambrose of Milan
   on the Christian faith book 2 chapter 10:86
[2]#St.basil the Great
    on the holy spirit chapter 8:21
[3]#St.Gregory_Thaumaturgus
       on the trinity
[4]#St.Gregory of Nazianzen
   Fourth theological oration (oration 30)

የእምነት በር

25 Oct, 18:46


https://youtu.be/e-oeNxwuu-I?si=G4HaFf_f0PzvUpCE

የእምነት በር

24 Oct, 09:50


"እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው"
ዮሐ5:39
ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ
ክፍል አንድ
https://t.me/orthodoxawitewahdo
ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ወንጌል ይማሩ...!

የእምነት በር

23 Oct, 07:05


🖋  ውይይት


የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
    ሱራ 9:5⃣

[[እናቴ ከእስልምና ከወጣች እገላታለሁ ]]

[[ልጄ ከእስልምና ቢወጣ እገለዋለሁ]]

[[እፎይ እና እሙ ሙርተድ መገደል አለባቸው]]

        🙆 ሌሎችም እርሶች የተዳሰሰበት

ወንድም እፎይ
ወንድም ሳሚ
ወንድም ሰላም ለኩሉ
ወንድም RD
ወንድም ክርስትያን
እኅት እሙ ሙርተድ
        🆚
ሙስሊሙ < Ziyad
ሙስሊሙ <ያሲን
ሙስሊሙ <Amir
ሙስሊሙ < አህመድ

ሌሎችም ሙስሊሞች የተገኙበት

ግሩም ውይይት 😍

የእምነት በር

22 Oct, 12:33


🖋ውይይት

ወንድም እፎይ
ወንድም ጄምዲ
ወንድም ክርስቲያን
ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር 🖋

ከእስልምና የወጣ ይገደላል🙆

እኔ አንተን ባገኝህ እገልሃለሁ አለው 👈

ሌሎችም እርሶችንም የተዳሰሰበት ውይይት
ይደመጥ

የእምነት በር

22 Oct, 12:32


አረ የሙስሊሞች ፈተና በዛ🤯

ለሴጣን አልጋ የማዘጋጀት እዳ ተጥሎባቸው ሲያሳዝኑ ለነገሩ ወንድሞቻቸው ናቸው ለካ😁😁


Jabir b. 'Abdullah reported that Allah's Messengor (ﷺ) said:There should be a #bedding for a #man. a bedding for his #wife and the third one for the #guest, and the #fourth one is #for the #Satan.

"ጃቢር ቢ.  አብደላህ እንደዘገበው ፦ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንደዚህ አሉ ፦ #በማንኛዉ ጊዜ አንድ አልጋ #ለቧል አንድ #ለሚስት አንድ #ለእንግዳ አንድ #ለሸይጣን መኖር አለበት። "

حَدَّثَنِي أَبُو الطَّاهِرِ، أَحْمَدُ بْنُ عَمْرِو بْنِ سَرْحٍ أَخْبَرَنَا ابْنُ وَهْبٍ، حَدَّثَنِي أَبُو هَانِئٍ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا عَبْدِ الرَّحْمَنِ، يَقُولُ عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهُ ‏ "‏ فِرَاشٌ لِلرَّجُلِ وَفِرَاشٌ لاِمْرَأَتِهِ وَالثَّالِثُ لِلضَّيْفِ وَالرَّابِعُ لِلشَّيْطَانِ ‏"‏ ‏.‏

Reference : Sahih Muslim 2084 In-book reference : Book 37, Hadith 67
USC-MSA web (English) reference : Book 24, Hadith 5190  (deprecated numbering scheme)

የእምነት በር

22 Oct, 08:45


ዳግም የተወለድኩበት 5 ኛ አመት ልደቴ ዛሬ ነው

የእምነት በር

15 Oct, 15:45


ኡስታዜ ሙስሊሞች በሐጅ ጊዜ ራሶቻቸውን ሚላጩት ለምንድነው
በጠቅላላ ምስራቃዊያን ማለትም ቻይናውያን ሕንዳውያን
ጣዖቶቻቸውን ሚያመልኳቸው ራሶቻቸውን በመላጨት ወይም በማሳጠር ነው
ለምሳሌ የቻይና ቡድሂዝም መነኩሴዎች ራሶቻቸውን ይላጫሉ
የህንድ ሂንዱይዝም ጣዖት አምላኪዎች
ራሶቻቸውን ተላጭተው ታዕዋፍ ያደርርጋሉ ወይም ጣዖቶቻቸውን ይዞራሉ
ይህም ከእስልምና አራት ሺህ አመታት በፊት የነበረ ስርዓተ አምልኳቸው ነው

ሙሐመድ ራስን ተላጭተው ወይም አሳጥረው ካዕባን መዞር በቀጥታ የኮረጀው ከሂንዱዝምና ከቡድሂዝም ነው

ታዲያ ሱራ 48:27 ራሶቻችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁም የተከበረውን መስጊድ ግቡ የሚለውን የቁርአን አንቀጽ ከአላህ ተቀብለውት አይደለም ነው ምትለኝ

አዎ በትክክል
ነብዩ ከዬትኛውም የሰሙትን ትረካ አላህ ገለፀልኝ እያሉ ያልተማሩትን ያጭበረብሩ ነበር እንጂ ምንም አይነት ከፈጣሪ የሰሙት ቃል የላቸውም

አን ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ ዓንሁማ ቓለ ኣለማዮ ቐዲመ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ መከ አመረ አስኻበሁ አን የጡፉ ቢልበይቲ ወቢሰፋ ወመርዋ ሱም የኺሉ ወየኽሊቑ አው ዩቕሲሩ
حَدَّثَنَا مُحَمَّدُ بْنُ أَبِي بَكْرٍ، حَدَّثَنَا فُضَيْلُ بْنُ سُلَيْمَانَ، حَدَّثَنَا مُوسَى بْنُ عُقْبَةَ، أَخْبَرَنِي كُرَيْبٌ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ لَمَّا قَدِمَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مَكَّةَ أَمَرَ أَصْحَابَهُ أَنْ يَطُوفُوا بِالْبَيْتِ، وَبِالصَّفَا وَالْمَرْوَةِ، ثُمَّ يَحِلُّوا، وَيَحْلِقُوا أَوْ يُقَصِّرُوا‏.‏
ኢብኑ አባስ እንደተረከው፡- ነብዩ ( ሶ.ዐ.ወ) ወደ መካ በመጡ ጊዜ ሶሓቦቻቸውን በካዕባ ዙሪያ እና በሶፋ እና በመርዋ መካከል ጠዋፍ እንዲያደርጉ፣ ኢህራም እንዲጨርሱ እና ፀጉራቸውን እንዲላጩ ወይም እንዲያሳጥሩ አዘዙ
Sahih al-Bukhari 1731

ለቐድ ሰደቐ አላሁ ረሱለሁ እሩእየ ቢልኻቒ ለተድኹሉነል መስጂደል ሐራመ ኢንሻኣላሁ አሚኒይነ ሙኸሊቒይነ ሩኡሰኩም ወሙቐሲሪይነ ላ ተኻፉነ ፈአሊመ ማ ለም ተእለሙ ፈጀኣለ ሚን ዱኒ ዛሊከ ፈትኸ ቐሪበ
لَّقَدْ صَدَقَ اللَّهُ رَسُولَهُ الرُّؤْيَا بِالْحَقِّ ۖ لَتَدْخُلُنَّ الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ إِن شَاءَ اللَّهُ آمِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمْ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَ ۖ فَعَلِمَ مَا لَمْ تَعْلَمُوا فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتْحًا قَرِيبًا
አላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡
አገር የመክፈት ምዕራፍ الفتح 48:

የእምነት በር

14 Oct, 06:49


ቁርዓን ብረት ከሰማይ ነው የወረደው ይላችኋል ሃቢቢ እና ሃቢብቲሞች ምን እሱ ብቻ ኧረ በግ እና ፍየልም ከሠማይ ናተው ይላል 🤥🤭

ሱራ 57 ÷25
لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَلِيَعْلَمَ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ وَرُسُلَهُ بِالْغَيْبِ ۚ إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٌ

መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደእነርሱ አወረድን፤ #ብረትንም_በውስጡ_ብርቱ_ኀይልና_ለሰዎች_መጠቃቀሚያዎች_ያልሉበት_ሲኾን_አወረድን፡፡ (እንዲጠቀሙበት) አላህም ሃይማኖቱንና መልክተኞቹን በሩቅ ኾኖ የሚረዳውን ሰው ሊያውቅ (ሊገልጽ አወረደው)፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡

👉ስለ እንስሳት ደግሞ

خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ الْأَنْعَامِ ثَمَانِيَةَ أَزْوَاجٍ ۚ يَخْلُقُكُمْ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ خَلْقًا مِّن بَعْدِ خَلْقٍ فِي ظُلُمَاتٍ ثَلَاثٍ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ الْمُلْكُ ۖ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ

ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ #ለእናንተም_ከግመልና_ከከብት_ከፍየል_ከበግ_ስምንት_ዓይነቶችን(ወንድና_ሴት)_አወረደ፡፡ በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ (ሙሉ) መፍጠርን ይፈጠራችኋል፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ስልጣኑ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡

የእምነት በር

12 Oct, 10:48


እውነት ነው አዎ እውነት ነው

እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው

ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባህሪ አምላክ ብለን ስናምነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የአማልክት አምላክ ነው

በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅነው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በኃይል በሥልጣን የተካከለ
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ እርሱ ጌታ ነው

ሥጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው

ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁ ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በዓለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ

የእምነት በር

12 Oct, 08:30


ሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ አለን?

ሙስሊሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ሙሐመድ አለ
ብለው ለሚያነሶቸው

መልስ
በወንድም አኬ 🆚በወንድም ዮሐድ

እሚገርመው ሙሐመድ ሽታውም አልተገኘም 😋

የእምነት በር

12 Oct, 08:28


እኛም ደስ ብሎናል እግዚአብሔር ይመስገን 🥰🥰

“ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።”
— 2ኛ ዮሐንስ 1፥9

“ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።”
— ዮሐንስ 10፥16🥰🥰

የእምነት በር

09 Oct, 18:20


በነበር የቀረ ታሪክ አለኝ አሁን ግን ይመስገን የጌታ ነኝ ትለናለች እህታችን እንኳን ጌታ ረዳሽ

የእምነት በር

08 Oct, 19:37


#የያዕቆብ_ሌሊት ያድርግልን ማለት ምን ማለት ነው?

መጀመሪያ ያዕቆብ ማነው!?
ቅዱስ ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ ማለትም የአባታችን የአብርሃም የልጅ ልጅ ነው።
የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ርብቃን አገባ ርብቃም መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራትምና አባታችን ይስሐቅ ስለ ሚስቱ እግዚአብሔርን ለመነ እግዚአብሔርም ተለመነው ርብቃ ሚስቱም ፀነሰች።

ልጆቹም በሆዷ ውስጥ ይገፋፉ ነበር ርሷም እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።

እግዚአብሔርም እንዲህ አላት ሁለት ወገኖች በማህፀንሽ ናቸው ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።

ትወልድ ዘንድ ዘመኗ በተፈፀመ ጊዜም እነሆ በማህፀኗ #መንታ ነበሩ።
በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ ሁለንተኛውም ጠጉር ለብሶ ነበር ስሙም #ዔሳው ተባለ።
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም #ያዕቆብ ተባለ።

አባታቸው ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበር
እናታቸው ርብቃ ግን ያዕቆብን አብልጣ ትወደው ነበር

ስለዚህም አባታቸው ይስሐቅ በሸመገለ ጊዜ በጣም አርጅቶ ነበርና ለሚወደው ልጁ ሊባርከው (ሊመርቀው) አሰበ። ነገር ግን እናታቸው ርብቃ የዔሳውን ምርቃን ለያዕቆብ በመምከር የዔሳውን በረከት አስወሰደችበት።

ዔሳውም በጣም ተናዶ ወንድሙ ያዕቆብን ለመግደል ወሰነ በረከቱን ወስዶበታልና።

እናቱ ርብቃም ይህ የታላቁ ልጇ የዔሳውን ቃል ደረሰላት ታናሹንም ልጇን ያዕቆብንም አስጠርታ እነሆ ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ይፈቅዳል። ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነስና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድለት ጥቂት ቀናት በዚያው ተቀመጥ ብላ አሳመነችው። ያዕቆብም እሺ ብሎ መንገዱን ጀመረ። ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሄደ።

ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከእርሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።

ሕልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደረሰ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበርና።

እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኘህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጥሃለሁ

ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምስራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ የምድርም አህዛብ ሁሉ ባንተ በዘርህም ይባረካሉ።

እነሆም እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ ወደዚችም ምድር እመልስልሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።

ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነስቶ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ። ፈራ እንዲህም አለ ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው።

ያዕቆብም ማልዶ ተነሳ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው በበላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።

ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያንች ስም ሎዛ ነበረ።

ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥

ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል።

ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአስር እጅ አነዱን እሰጥሃለሁ። ብሎ ቃል ገባ።

✝️ ስለዚህም እኛም #የያዕቆብ_ሌሊት ያድርግልን የምንባባለው እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳን መላእክቱ ከእኛ ጋር እንዲያድርና ጥሩ የሰላም እንቅልፍ እንዲያስተኛን ቅዱሳን መላእክትን በሕልማችን እንዲያሳየን ከመጥፎ ህልም እንዲጠብቀን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን ከመጥፎ አጋንንት እንዲጠብቀን #የያዕቆብ_ሌሊት ይሁንልን እንላለን።
ለበለጠ ኦሪት ዘፍጥረት (26-30) አንብቡት

Mule Ze Kdst Ldeta