ከደራሲያን እልፍኝ @kederasiyan Channel on Telegram

ከደራሲያን እልፍኝ

@kederasiyan


ከደራሲያን እልፍኝ (Amharic)

ከደራሲያን እልፍኝ የሚደረግን በተመሳሳይ ማስተዳደር እና በላቀ ህዝብ እና ሲኦስትያን እና ሌላ የፍቅር ቤተሰብ ማህበረሰብ አላማ ነው። ከአሮጌ ወዳጆችና አስተዋወቁ ወደ ከደራሲያን እልፍኝ በመመልከት እና በመጠቀም ሌሎችን ከተማ ዋጋ አሰንሃውን ለማሻሻል በማለት ካንተ ስልጣን ብቻ ነህ። አንዳንድ እና በጥሬ የሚባሉ ግንድ እስከዚህ መስራት ላይ ናቸው። በምርጫ ሽᑯቱን እና ፍቅርን ከከተማ ውጪ ማህበረሰብ አላማ ያወራል። አንድ ሲዋጋድ ብዙም ህዝብ እና ባላም ህዝብ ስኡእንን ቻመል በሚሆነው ጥበቃ ከተማህ ከሚ ቤተ ሰብ የሚለየው ወጣት የለም።

ከደራሲያን እልፍኝ

14 Nov, 03:49


📆 Majors, the wait is over!

There was much excitement and many questions, but the coveted date is here!

On November 28 at 12:00 PM UTC, we will launch on OKX. And it’s not the only exchange — we’ll be launching on others too. Don’t worry, and stay tuned!

A task related to OKX is already available in the game. It’s the perfect time to complete it, Major! 📈

By the way, games and tasks are the only ways to earn rankings. This will be the case until the listing.

Didn’t we say November would be hot? ⭐️

ከደራሲያን እልፍኝ

14 Nov, 01:03


ሲዲ ሊያልቅ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ቀርተዋል ፣ ብዙ ዋጋ ሊኖረው ይችላል ተብሎ የተገመተው ሲድ በተለያዩ ትልልቅ ኤክቼንጆች ላይ ሊስት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ታዲያ 1 ሲድ እንኳን ዋጋ ሰላላት እስካሁን ያልጀመራቹት አሁኑ ጀምሩት 15 ቀን እየሰለቻቹ በሰትሰሩ ምናልባት ትካሱ ይሆናል ልፋታቹን

ለመጀመር
t.me/seed_coin_bot/app?startapp=833660916

ከደራሲያን እልፍኝ

08 Nov, 17:14


በነገራችን ላይ እስካሁን ድረስ የairdrop ስራ ቀልድ የሚመስለው ብዙ ሰው አለ....
ነገር ግን እውነታው ከቀልዱ በተቃራኒ ነው....
ብልሆች እየተለወጡበት ነው.....
ለምሳሌ በDogs
እስካሁን እኔ በሰማሁት በኢትዮጵያ እስከ 960$ የሰራ ሰው አለ(ከዛ በላይም ሊኖር ይችላል)።

960×120= 115,200 ብር በጥቂት ጊዜያት ውስጥ.... ሌላ የሰራ ሰው በሰራው ልክ አግኝቷል

አሁንም አልረፈደባችሁም Dogs  ካልሰራችሁ ሁለተኛው dogs የተባለውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊስት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን paws የተሰኘውን airdrop እንዳይቆጫችሁ ካሁኑ ጀምሩ .......🫡

መቼም Dogsን ያየ  pawsን ችላ አይልም.....
ላልጀመራችሁ እነሆ ሊንክ




https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=rnxtpqeG
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

ከደራሲያን እልፍኝ

07 Nov, 11:08


'ሰው የጣለው ሲነሣበት አይወድም'

የሠርጉን ፎቶ ለጥፎ ዐየኹት…
ከእኔ ጋር ለመኾን ጥሮ ነበር። በግልጽ ፍቅሩን ዐሳይቶኛል፤ ለምኖኛልም።
እኔ እምቢ አልኩኝ እንጂ…
ልቤን አልሞላልኝም።
ልቤ ላይ ስላልሞላ አልኮራኹበትም፣ ነፍሴም አልተቀበለችዉም።
የሠርጉ ፎቶ ላይ ዐይኔ አልነቀል አለ። ሚስቱን ለብቻ… እሱን ለብቻ እየነጠልኩ አፈጠጥኩበት።
ሚስቱ በጣም ታምራለች! ፎቶዉን የተነሡበት ቦታ እንዴት እንደሚያምር!
እጅግ ብዙ ሰው የተነሱት ፎቶ ሥር ደስታቸዉን ገልጸዋል…
ቀናኹ… ለማንም የማልተነፍሰዉን ቅናት ቀናኹ።
ምን አለ በእሷ ቦታ እኔ በነበርኩ!!!
ለካ እንዲህ ያምራል!
“እንዲህ ሞገሳም ነው?” አልኩ፤
አሁን እሱ፡ ምኑን ለእኔ ያንሳል፧
ዕጣ ፈንታዬ ጨፍኖኝ ካልኾነ በቀር፤ ወይ ለኔ የነበረው ስፍራ ያለውን ነገር እንዳልመለከት ባይረታኝ፤ ዛሬ ሠርጌ ነበር።
የጣልኩትን… የገፋኹትን ሌላ እጅ ላይ ሳየው ቀናኹ።
ልቤ እስኪሸቀሽቀኝ፤ ድብርት እስኪጣባኝ ድረስ ስሜቴ ወረደ፤ ዱካክ ተላፋኝ።
ግን ለምን ቀናኹ?
ቀድሞኝ ስላገባ ይኾን…?
ልቤ የሚያርፍበት ስላላገኘ ይኾን…?
አሠሣዬ በድል ስላልተጠናቀቀ ይኾን…?
ሰው አልፈልግም ያለዉን ሌላ በሚፈልገው እጅ ላይ ሲያዩት ይደብር ይኾን…?
አላውቅም ግን ቀናኹ። ስጦታዬን ይኾን እንደዋዛ የተውኩት? ውሳኔዬን ጊዜ ይመሰክርልኝ ይኾን?
ይሄም ቢኾን ግን ልቤ ከቅናቱ ጋር ታግሎ “መልካም ጋብቻ” ብዬዋለኹ።
By Adhanom Mitiku
@kederasiyan
@kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

05 Nov, 18:05


#paws ስማቹ አጠገብ ይችን እሞጂ 🐾

አሰቀምጡና 5000 ውሰዱ

ያልጀመራችሁ.... Start


https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=i2GUv1Ot

ከደራሲያን እልፍኝ

03 Nov, 16:03


በተጀመረ በጥቂት ቀናት ብዙ ተስፋ የተጣለበት Paws airdrop መነጋገሪያ ሆኗል።

እንደ ብዙ ሰዎች አስተያየት ይሄ Airdrop ብዙ ላይቆይ ይችላል በቀናቶች ውስጥም Verify ተደርጓል።

የተወሰኑ Tasks ስላሉት ብዙ ለማግኘት ያስቸግራል ቢሆንም ብዙ sim በመጠቀም እና invite በማድረግ ብዙ መስራት ትችላላችሁ

ያልጀመራችሁ ጀምሩ ጥሩ እድል ነው



https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=i2GUv1Ot

ከደራሲያን እልፍኝ

01 Nov, 12:09


SEED !

Seed እንደሚታወቀው በ Binance list የመሆን እድሉ 100% ያለቀ ይመስላል ምክኒያቱም Binance lab invest እንዳደረገበት አብዛኛው የ Crypto ዙሪያ ዜናዎች ዘግበውታል

SEED ምንድነው?

- Seed ከ Web3 ፕሮጀክት ጋር የተቆራኘ Gaming እና Social interaction ፕሮጀክት ነው. Airdrop በመሆን በገነባው ፕሮጀክት መሰረት በ November 2024 ለ ተጠቃሚዎች Token ይሰጣል

- Seed Total supply cap 20 ሚልየን ነው, ይህም ፋርም ስታደርጉ ብዙ ቁጥር ለመስራት ትቸገራላችሁ ነገር ግን Active መሆን ከቻላችሁ ጥሩ እድል ነው, በተለይ Bird hunt አድርጎ እዛው ላይ መሸጥ ብዙ ነጥብ እንድትሰበስቡ ያደርጋል

Snapshot እና listing በኖቬምበር መጨረሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል

ለመጀመር



t.me/seed_coin_bot/app?startapp=833660916

ከደራሲያን እልፍኝ

31 Oct, 06:26


የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።

የቱ ጋር መሰለህ?

በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴትን ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።

የቱ ጋር መሰለህ?

የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በዋዛ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ስትዘነጋ ፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።

ትዝ አለህ?

ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።

ያን ጊዜ ተከፋህ!

ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።

ትዝ አለህ?

መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?

ትዝ አለህ?

በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?

ትዝ አለህ?

የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
‘አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ? ‘
ብለህ ስትቆዝም … ?

እንዲያ ነው አይዋ…
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።

ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
‘ኧረ ስከን’ ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!

ከደራሲያን እልፍኝ

30 Oct, 17:33


Paws ኤርድሮፕ ከዶግስ መመሳሰሉ ወይም የብሉም እና የኖትኮይን መስራቾች መደገፋቸው እና ኤርድሮፑን መጠቀማቸው ብቻ ሳይሆን ኤርድሮፑ ብዙም የማይቆይ መሆኑን ብዙዎቻቹ መረዳት መቻል አለባቹ 👋

Paws ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኤርድሮፕ አይደለም ስለዚ ያልጀመራቹ ጊዜያቹን ተጠቀሙበት.....

ከላይ ባለው ምስል መሰረት ታስኮችን ወጥራችሑ ስሩዋቸው.......እስካሁን ካልጀመራችሁ ይኸው ሊንክ





https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=2OIf4vqv
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

ከደራሲያን እልፍኝ

30 Oct, 09:38


🔹ጀምሩት | አዲስ ነው ... ከቻላችሁ Multiple account

✔️አሰራሩን እነግራችኋለው (ገና viral አልሆነም)

✔️first come first serve (በደንብ ስሩት ከአሁኑ)

✔️Error ካላችሁ ደጋግማችሁ reload እያደረጋችሁ ሞክሩት!

✔️ምንም ልፋት የለውም!

✔️NOTCOIN ,DOGS እና HAMSTER በሰራችሁት ልክ ነው Initial coin ሚሰጣችሁ!








https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=2OIf4vqv
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾

ከደራሲያን እልፍኝ

28 Oct, 17:23


‹‹ስለ አምቦውኃው››

--
ከባሌ ጋር ባለትዳር ጓደኞቻችንን ኤልያስና ሕሊናን ልንጠይቅ ቤታቸው ተገኝተናል፡፡

ለዓመታት ትዳራቸው ከመሠረቱ የተናጋ እስኪመስል ክፉኛ ቢነቃነቅም፣ ለረጅም ጊዜ ‹‹በቃ ተለያዩ›› ብለን ብንሰጋም፤ በቅርብ ደውለው  ‹‹እሑድ ቤት ኑ እና ምሳ ብሉ›› ሲሉን ግን ያጠላባቸው ጥቁር ደመና ተገፍፎ ለትዳራቸው አዲስ ፀሃይ የወጣለት መስሎን ደስ አለን፡፡

መስሎን፡፡ ተሳስተን ነበር፡፡

ምሳውስ በደኅና አልፎ ነበር፡፡ ነገር የተበላሸው፣ የዘወትር አጉል ዐመላቸው ያገረሸው፣  ከምሳ በኋላ የሚጠጣ ቀርቦ መጫወት እንደጀመርን ነው፡፡

ባሌ አምቦውኃ ሲጠይቅ፡፡

‹‹ውይ…አምቦውኃ ሳልገዛ ረሳኹ›› አለ ኤልያስ ጭንቅላቱን እያከከ፡፡
ቀጥሎ ‹‹ይቅርታ በናትኽ-›› ብሎ ሳይጨርስ
ባሌ ዘሎ ገባና፣
‹‹ምንም ችግር የለውም፡፡ ምግቡ ጣፍጦኝ ወጥቄ ወጥቄ ነው፡፡ ተወው ውኃውን እጠጣለኹ፡፡›› ሲል ሕሊና ፊት ላይ እንደ ጥይት የምፈራው የውሸት ፈገግታ ተሣለ፡፡

‹‹ብገድልኽ ደስ ይለኛል ግን ሰው ፊት ስለኾንን እተውሃለኹ›› የሚለው ፈገግታዋ፡፡

ሴትና ሚስት አይደለኹ?
ይሄንን ፊት አውቀዋለኹ፡፡
የእሷ ግን ገደብ ጥሶ ያስፈራል፡፡

‹‹አይ ኤልያስ…ያንተ ነገር…ብታስታውሰው ነበር የሚገርመኝ›› አለች ዝቅ ባለና ሰላማዊ በሚመስል ግን እንዳልኾነ በሚያሳብቅ ድምፅ።

ኹላችንም ዝም አልን፡፡

‹‹የኹልጊዜ ፀባይኽ ነው ግዴለሽነት›› ብላ ጨመረች፡፡

ኤልያስ ሶፋው ውስጥ ነቅነቅ አለና ‹‹ዌል…ቢዚ ነበርኩ…›› አለ፡፡

‹‹ቢዚ? ›› ኦምብሬ ቅንድቦቿን ወደ ላይ ሰቅላ ቶሎ መለሰችለት፡፡

‹‹ ምንድነው ቢዚ ያረገኽ በናትህ..ቀኑን ሙሉ ላፕቶፕና ስልክ  እየቀያየሩ መጣድ ነው ቢዚ ያደረገኽ? ….ሠራተኛ ሄዶብኝ ቀኑን ሙሉ ብቻዬን ቤት ሳፀዳ እና ምግብ ስሠራ የዋልኩት እኔ እንኳን ቢዚ ነበርኩ አላልኩም›› አለች ቅድም ከነበረው ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፡፡
‹‹ሕሊና…ሥራ ስሠራ ነበር…አንቺ መቼም ቢሮ ካልተሔደ ቤት የሚደረግ ነገር ሥራ አይመስልሽም..ደግሞ ኹለት ዐይነት የጾም ወጥና ሰላጣ መስራት ነው ቀኑን ሙሉ የሚፈጀው….?  ቢያንስ እኔ ገንዘብ የሚያስገኝ ሥራ እየሠራሁ ነበር…እኔ የምልህ ታሜ…እኔ ጋር ብቻ ነው ወይስ ሁሉም ሚስት እንደዚህ ነገር ፈላጊ ነው..? ››
ቀልድ አስመስሎ የምሩን ነው የተናገረው፡፡

ግንባሩ ላይ ላብ ቸፍ ያለበትን ባሌን ይዤ ብወጣ ደስ ባለኝ ግን ትንፋሽ አልሰጡንም፡፡ ከነ መፈጠራችንም የረሱን ይመስል ቀጠሉ፡፡
‹‹ገንዘቡ ያንተ እንደኾነ ለማውራት መቼም ሰበብ አታጣም…ለሚስትኽና ለልጆችኽ እናት የምታወጣው ገንዘብ ውለታ ይመስልሃል አይደል…ለዚህ ነው አምቦውኃ ገዝተኽ ለመምጣት እንኳን የምትንጠባረረው….ክብርኽ ይነካ ይመስል..››
‹‹ሕሊና….ጨዋታ እንቀይር-››ባሌ ጣልቃ ገባ፡፡

አልሰሙትም፡፡ እኔና ባሌ በጭንቀት እርስ በርስ ተያየን፡፡

‹‹ዌል…ቤት የምትውይው አንቺ ነሽ…ሠራተኛ የለኝም ትያለሽ…በመጡ በሳምንቱ እንሒድየሚሉት ለምንድነው ብለሽ ጠይቂ እስቲ…ዐመልሽ ነው…ዐመልሽ….አሁን አምቦውኃአለመግዛቴ ትልቅ ነገር ኾኖ ነው ሰው ፊት የምትነተርኪኝ››

‹‹ልክ ነኽ፡…ቤት ነው አይደል የምውለው…ሳውና ባዝ ሳደርግ ሜካፕ ስቀባ ነው የምውል የሚመስልኽ አይደል…አንተ ልጆችኽ እንደ ኩስ የምትጥሏቸውን ልብሶች መሰብሰቡ፣ ምግብ መሥራቱ፣ ቤት ማጽዳቱ ሥራ አይደለም አይደል…የንግሥት ሕይወት እኮ ነው ያለኝ…አይደል? ››

‹‹እኔ እንደዛ አላልኩም…እንደለመድሽው ነገር አትጠምዝዢ…የኾነው ኾኖ ሰው እንዴት ለአንድ አምቦውኃ እንዲህ ይሆናል..እንዴት እንዴት ነው ኹሉ ነገር የነገር ወጥመድ የሚኾንልሽ ግን?  መንግሥት ያልመዘገበው ችሎታ ነው…አይደለም እንዴ ሜላት…ነው ወይስ አንቺም እንዲህ አይነት ሚስት ነሽ…ሁሉ ሴት እንዲህ ነው ወይስ የእኔዋ ብቻ ናት….? ››

‹‹እኛ ብንሔድ ይሻላል›› ብዬ ተነሣኹና የባሌን እጅ ጎትቼ ልነሣ ስል፣
ሕሊና ቅድም ያልነበራትን በትሕትና የረሰረሰ ፊት ሠርታ አጠገቤ ቆመችና-
‹‹ሜሉ በእናትሽ አትሒዱ…ይቅርታ…ይሄ ነው የኔ ኑሮ…ኤልያስ ይቅርታ ጠይቃት…ቤትኽ ጠርተኽ ሰው ትሳደባለኽ…? ›› አለችው እያየችው፡፡

ይሄን ጊዜ ባሌ ተነሥቶ ቆመና፤
‹‹ግዴለም…እናንተም ጉዳያችኹን ለብቻችኹ ጨርሱ›› ብሎ ይዞኝ መውጣት ስንጀምር ወደ ቀልቡ የተመለሰው ኤልያስ ሮጥ ብሎ ተከተለን እና የባሌን ትከሻ ይዞ -
‹‹ይቅርታ ›› እንዳለው ተያይዘን ወጣን፡፡

መኪናችን ውስጥ እንደገባን ባሌ ዞር ብሎ ዐየኝና
‹‹ጥፋቱ የእኔ ነው፤ አምቦውኃውን ባልጠይቅ ይሄ ኹሉ ነገር አይመጣም ነበር›› አለኝ፡፡

እጁን ያዝ አደረግኩና ‹‹የኔ ማር፣ ጠባቸው ስለ አምቦውኃው አልመሰለኝም፡፡ ›› አልኩት፡፡

ሕይወት እምሻው

@kederasiyan
@kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

27 Oct, 11:45


እንደልጅ ኩርፊያዋን ትረሳልኛለች፣ ትስቅልኛለች፣
እንደ ልጅ ነው የምታምነኝ፤ ስታምነኝ እንቅፋት መትቷት የምታውቅ አትመስልም ፣ የትም ቦታ ነይ ስላት ትመጣልኛለች፤  እሺ አባባሏ ካንተ ጋ ከኾነ የትስ ቢሆን
የሚል ይመስለኛል    ።

ሕልሜን ስነግራት አሰማሟ እረፍት ይሰጣል ፣  ዐይኗ ላይ ያለው መውደድ ያበረታኛል ።

እወድሻለሁ ስላት እንዴት የማላውቀውን ነገርከኝ፤ ብላ የደስታ ፈገግታ ያበራውን ፊት ታሳየኛለች

ፍቅር ያበረታል
        Adhanom Mitiku

@kederasiyan
@kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

24 Oct, 19:31


https://t.me/major/start?startapp=533058018

👑 Join me in @Major game and earn $MAJOR token soon!
⭐️ 750 rating bonus for you.
⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.

ከደራሲያን እልፍኝ

20 Oct, 14:19


በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ  አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። ገና በሩን ከመዝጋቴ  ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ  አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።  "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ሰው ፣ አህያ ወይም  የተናኘ  ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው"  አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ  ፍቅረኛው ናት) "እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ  ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ  እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ  ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች።  መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ  መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ  የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ  ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣  የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው!.
@kederasiyan
@kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

16 Oct, 19:48


‘ደረጃ የሌለው መሰላል’
ይሄ የሀገሬ ሰው’ኮ...
ደረጃ የሌለው መሰላል አወጣጥ ያውቃል፣
አንዱን እርከን ረግጦ ሲያልፍ ነቅሎ ጉያው ይከትተዋል።
ደግሞ ቀጣዩን ይረግጠዋል፣
ነቅሎ ጉያው ይከትተዋል።
እንዲህ እንዲያ እያለ ዘልቆ፥ ከዝና በላይ ይወጣል፣
ከጥቅምም በላይ ይሰፍራል፡
እንደኮራ እንደተዝናና ቃል ሳይናገር ይሞታል።
በቀብሩም ሥርዐት ላይ ...
ደግ...
ለሰው አሳቢ...
ለተቸገረ ደራሽ...
የሚል የሕይወግ ታሪክ ወግ ይፋ ይነበብለታል።
ከቀን በኋላም ገንኖ ሐውልቱ ገዝፎ ይታያል።
ያም የደረጃ እርከን እንጨት መቃብር አጥሩ ይኾናል።
እንግዲህ ተከታይ ትውልድ
በአንጋፋው ሐበሻ መንገድ
ደረጃ በሌለው መሰላል ጥበብ ፍለጋ ተሰደድ

(ነቢይ መኰንን)

https://t.me/kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

09 Oct, 18:57


ሐዘንሽ አመመኝ
ደበበ ሰይፉ

ውል አልነበረንም የፍቅር ቀጠሮ
ቃልም አላኖርንም በወግ ተቀምሮ፤
እኔ አንቺን እንዳላይ
አንቺ እኔን እንዳታይ አምባችን ተቃጽሮ
ዕጣችን ተካሮ፤
ቀለምሽ ከዐይኔ አሻራሽ ከጣቴ ባይጠፋ ተማትሮ
(እትብት እምብርት ሁኖ እንዲኖር ደድሮ)
ይኸው አካሄደን በድንገት ዘንድሮ።
የገጽሽ ብርሃን ቢጠይም ፀዳሉ
ድምፅሽ ቢቀጥንብኝ ቢሠልልብኝ ቃሉ
ወዘናሽ ቢማስን ዛሬ ያለውሉ
በእጆችሽ ጨበጠኝ ሐዘንሽ ሥዕሉ
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጀንበር ነሽ አበባ ሕይወት ተስፋ ዘቦ
ፋሲካ ዕንቁጣጣሽ ማኅሌተ ገንቦ
ብዬ ያወደስኩበት ታዘበኝ ዘመኔ የትላንታት ቀኔ
ዛሬ ሊጮህብኝ ቅኔ እንዳይደል እውኔ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
የገደል ማሚቶን ታዘብኳት ተኝታ
በጩኸትሽ ማየል አኩርፋና ታክታ
ላንቃዋ ይታየኛል ደም ለብሶ ደም ጐርሶ
ቃልሽ ያለፈበት በጭንቅ ተለውሶ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጽጌሬዳይቱ ንቦችሽ አለቁ ሰዎችሽ ደቀቁ
ጨፌ ላይ ተኝተው ባድማ ላይ ነቁ፤
ዐዋይን ሰማኋት ስታለቅስ በይፋ
ከጐጆሽ ስትወጣ ትቢያዋን አራግፋ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
አላውቅልሽ ብዬ አታውቂልኝ ብዬ
እምነትሽን ጥዬ ፍቅርሽን ገድዬ
አኩርፌሽ ስቀመጥ ያው እንደ ባላንጣ
ይኸው ነጭ ማተብሽ ሊያስታርቀን መጣ፤
ሐዘን ነው ውበትሽ ውበት ነው ፍቅርሽ
ብርሃን - ጥለት አልቦ ከል ነጠላሽ
ዐይኔን የገለጠው ጥቁር ጨለማሽ፤…
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
-----------------
ግንቦት 1966ዓ.ም.

@kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

08 Oct, 18:02


አንዳንዴ....

የራስን ህመም ደብቆ
ማከም የሰው በሽታ፣
የውስጥን ጩኸት አምቆ
ማድመጥ  ሌላ ኮሽታ፣
ሆኖ አለመገኘት
የተናገሩትን ቃል፣
ውስጥን እያበገነ
ከላይ ከላይ ያስቃል!!

#ኤዶምገነት
https://t.me/kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

08 Oct, 18:02


ያንድ ምሽት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤

ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ  ዘበት፤

የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥

የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤

ለካ ሰው ቢማር፥   
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ;:
https://t.me/kederasiyan

ከደራሲያን እልፍኝ

08 Oct, 10:13


‹‹ዋለለ››
-----
(ክፍል ሁለት)

-------------------

ለብቻችን ሆነን ለማውራት ስንፈልግ ስንፈልግ የምናዘወትረውና ሰው የማይበዛበት ካፌ ቀጠርኩት፡፡

ቦታውን የመረጥኩት በነገርኩት ነገር ቢናደድ እንኳን ቤት ውስጥ ስላልሆንን እንደ አባትና እናቴ ወይ እንደልቡ እንዳያንባርቅብኝ ያግደዋል፣ ግን ደግሞ ሰው ስለማይበዛበት በማናውቃቸው ሰዎች ፊት ገመናችንን ለማስጣት አንገደድም ብዬ ነው፡፡ 

ብዬ ነበር፡፡

ግን ያላሰብኩት ሆነ፡፡

ቀድሜው ደርሼ ትንሽ እንደጠበቅኩት ሰማያዊ ሱፍ ግጥም አድርጎ ለብሶ መጣ፡፡
ግራ ተጋባሁ፡፡
አማን ሰርግ ወይ የስራ ኢንተርቪው ከሌለበት ሱፍ መልበስ ሞቱ ነው፡፡ 
ምን ተገኘ?
በእሱ አለባበስ ተገርሜ ሳላበቃ ገና ከመቀመጡ ለወትሮው ትእዛዛችንን ተቀብለው ለብቻችን የሚተዉን አስተናጋጆች ባልተለመደ ሁኔታ ወዲህ ወዲያ ውር ውር እያሉ ሲመለከቱን ይበልጥ ግራ ተጋባሁ፡፡

ምንድነው?

ግራ መጋባቱ ሳይለቀኝ ሰላም ካልኩት በኋላ ራሴን ወንበሩ ላይ አመቻችቼ እንዲህ አልኩት፤

‹‹አማንዬ ስማኝማ…የማናግርህ ትልቅ ጉዳይ አለ ግን ሳልጨርስ እንዳታቋርጠኝ እ?››

በቃኝ ስልህ እንዳትጮህ፣ እንዳትናደድ ማለቴ ነበር፡፡

ገና የምለውን ነገር ሳይሰማ ፊቱ በደስታ እያበራ፣ ‹‹ሄዋንዬ እሺ ወዳንቺ እንሄዳለን ግን መጀመሪያ ልነግርሽ የጓጓሁለት ነገር ስላለ ሳልፈነዳ በፊት እኔ ልቅደም?›› አለኝ፡፡

ምንድነው?

‹‹ምን…ምንድነው ምታናግረኝ?›› አልኩ፡፡
አዲስ መጫወቻ እንደተገዛለት ህጻን ልጅ እየቦረቀ፣
‹‹የማወራሽ ትልቅ ነገር አለ›› አለኝ፡፡

ጌታ ሆይ!

‹‹ቪዛውን ሰጡህ?›› አልኩት አዎ ካለኝ እንዴት አድርጌ በቶሎ ማርሽ እንደምቀይር እያሰብኩ፡፡
‹‹አዎ ግን ስለ እሱ አይደለም የማናግርሽ!›› አሁንም ጥርሶቹ በሙሉ እስኪታዩኝ እየሳቀ፡፡

ስለ እሱ አይደለም?

እኔ የሚለኝን ነገር ለመረዳት ስባዝን የሚከተሉት ነገሮች በቅደም ተከተል ሆኑ፡፡

1ኛ- ቅድም ሲተራመሱ የነበሩት አራት አስተናጋጆች  40 ኢንች ቲቪ የሚያህል ፍቅር ስንጀምር የተነሳነው ሰልፊ ፎቶ ያለበት ኬክ እየተንገዳገዱ ተሸክመው መጡ፡፡
2ኛ- ቤስት ፍሬንዱ  በትልቅ ስልኩ የሚሆነውን ሁሉ እየቀረጸና በጫት አረንጓዴ የሆኑ ጥርሶቹን ፈልቅቆ እያሳየ አጠገቤ መጥቶ ከነስልኩ መሽከርከር ጀመረ፡፡
3ኛ- ዛሬ እንለያይ ልለው የቀጠርኩት ቦይፍሬንዴ መሬት ላይ በግራ እግሩ ተንበርክኳል፡፡ በቀኝ እጁ ቀይ፣ ከፋይና ተከፍታ ቀለበት የያዘች ሚጢጢ ሳጥን ወደ ፊት አንከርፍፎ፡፡

ቀለበት! ባለ ፈርጥ የቃልኪዳን ቀለበት፡፡
እኔ ወንበሩ ላይ እንደተለሰነ  ሰው በተቀመጥኩበት ‹‹ታገቢኛለሽ?›› ብሎ ጠየቀኝ፡፡

ያን ጊዜ ነው የወንዲ ማክ
“ታገቢኛለሽ ወይ” ሙዚቃ በካፌው ስፒከሮች ያለቅጥ ያንባረቀው፡፡

ዘፈኑ፣
‹‹ውዴ…እኔና አንቺ ለዚህ ቀን እንደርሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ?›› ብሎ በንግግር ሲጀምር፣
ክው አልኩ፡፡  ህእ! አስቤ አላውቅማ!
ዝም ብዬ በተቀመጥኩበት ጓደኛው መቅረጹን ሳያቆም መጥቶ በግድ ጎትቶ አስነሳኝና የተንበረከከው አማን ፊት አቆመኝ፡፡

ቁልቁል ሳየው እንዲህ ብሎ ቀጠለ፡፡
‹‹ሄዋንዬ፣ ካናዳ ሄደን አዲስ ሕይወት እንድንጀምር እፈልጋለሁ፡፡ ቀለበት እንሰር፤ እንጋባና አብረን እንሂድ፡፡ እንውለድ፤ እንክበድ፡፡ ታገቢኛለሽ?››
ጌታ ሆይ!

ከባድ ወጥመድ ውስጥ ገባሁ፡፡ ለዚያውም በቪዲዮ የሚቀረፅ ወጥመድ ውስጥ፡፡

ዘፈኑ ሲሟሟቅ፣ ካፌው ውስጥ የነበረው ጥቂት ሰው ሁሉ ወደ እኛ ሲመለከት፣ የከበቡን አስተናጋጆች (ታሪካችንን ያውቁት ይመስል) እያሽቃበጡ ሲያጨበጭቡ፣ ጓደኛው ብዙ እንደተከፈለው የቪዲዮ ባለሙያ እየዞረን ሲቀርጽ፣ አማን አይን አይኔን ሲያየኝ እንደ መንቃት ይባስ ደነዘዝኩ፡፡

ልቤና መንፈሴ ዋለለ፡፡
ምን ባደርግ ይሻለኛል?
እምቢ ብዬ እዚህ ሁሉ ሰው ፊት ላዋርደው…ቅስሙን ልስበረው?
ቲክቶክ ላይ ሊለቀቅ የሚችል ቪዲዮ ላይ ‹‹እምቢ አላገባህም!›› ልበለው?
ወይስ በይሉኝታ እሺ ብዬው ራሴን የባሰ ማጥ ውስጥ ልክተት?

‹‹እ….ታገቢኛለሽ?›› አለ ደግሞ በልምምጥ፡፡

በተበታተነ ሃሳቤ መሃል አማንን አተኩሬ አየሁት፡፡

በድንገት ፊት ለፊቴ ተንበርክኮ ‹‹አግቢኝና ካናዳ ልውሰድሽ›› የሚለው ልለየው ያቀድኩት ቦይፍሬንዴ ብቻ እንዳልሆነ ተከሰተልኝ፡፡

ፊት ለፊቴ የተንበረከከው የማይደገምና ብዙዎች የሚመኙት፣ ብዙዎች መስዋእትነት የሚከፍሉለት፣ ንብረት ሸጠው የሚገዙት ታላቅ ከዚች ሃገር የማምለጥ እድል ነው፡፡
ስራ ለመሄድ የታክሲ ወጪዬን እንኳን የማይሸፈን አስር ሺህ ብር ደሞዝ እየተቀበልኩ እየኖርኩ እንዲህ ያለውን ታላቅ እድል እምቢ ብዬ ብገፋ የእግዜርን ዐይን መውጋት አይሆንም?

እምቢ ብለው፣ እማዬ ቆዳዬን ነው የምትገፈው፡፡
ጓደኞቼ እብድ ነሽ ይሉኛል፡፡ የአማን ዐይኖች ያረፉባት የልብ ጓደኛዬ ደግሞ ይሄንን እድል ብታገኝ ከመቀበል አልፋ ለማንኛውም ብላ (ለቀብድ እንዲሆን ) መንታ ታረግዝለት ነበር፡፡

ስለዚህ እሺ ልለው ወሰንኩ፡፡

ነገር ግን አማንን አግብቼ ካናዳ ብሄድ መንገድ የለመዱ አይኖቹ ሌሎች ሴቶችን ሲቃኙ፣ ጓደኞችና ኳስ ጨዋታን ደጋግሞ ከእኔ ሲያስቀድም፣ ከእሱ በስተቀር ሌላ ሰው በማላውቅበት ሃገር በብቸኝነት ሲያቆራምደኝ ታየኝና  ‹‹እሺ›› የምትለዋ ቃል ከንፈሬን አልፋ መውጣት አቃታት፡፡

ቢሆንም እሺ አልኩት፡፡

የከበበን ሰው ሁሉ በሆታ ሲያጅበን፣ ካናዳን ከመርገጤ ታናሽ እህቴን ቶሎ ወስጄ እንደምፈታው እያሰብኩ ነበር፡፡

Hiwot Emshaw
https://t.me/kederasiyan

1,382

subscribers

22

photos

5

videos