🎁 የሻዕባን ልዩ ማስታወሻ
ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
እንደሚታወቀው መልካም ስራችን በአሱር ወቅት፣ በየ ሳምንቱ ወደ አላህ ይሄዳል ይህ ሁሉም ተድምሮ በዚህ በሻእባን ወር ላይ ይወጣል። ወሩን አስደንጋጭ የሚያደርገውም ይሄ ነው። ይሄ ማለት ያለፈው ረመዳን በዚህ ወር ነው ሚወጣው፣ ሃጅ ያደረግነውም፣ሶደቃችን አሁን ነው የሚወጣው። ለዚህም ነው ነብያችን ይሄንን ወር አብዘሃኛውን እንደፆሙት የተነገረው። ሰራዎቸም ፆመኛ ሁኜ እንዲወጡልኝ ፈልጌ ነው ብለዋል። እናታችን አይሻ እንደዘገበችው የአላህ መልእክተኛ ከረመዳን ውጭ እንደ ሸእባን የበለጠ ወሩን የፆሙት ወር የለም ብለዋል። ትልቁም ትኩርታቸው በዚህ ወር ስራችን ወደ አላህ ስለሚወጣ ነው።
የተከበራችሁ ወንድም እህቶቸ በዚህ ወር ውስጥ በድብቅም በግልፅም፣ ትንሽም ይሁን ትልቅ መጥፎም መልካምም ስራዎቻችን ናቸው የሚወጡት። ስለዚህ አንዘናጋ ባለፈው ወንጀላችን ከአላህ ጋር ልንታረቅና የወደፊቱንም ህይወታችንን ለማስተካከል ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል። ልንዘናጋ አይገባም ለነብያችን እንኳ አላህ ምን እንዳላቸው እንመልከት
وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ
ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ እያላቸው ነው።
ሽእባን ማለት የረመዳን መዘጋጃ ነው። ይሄን ወር ነፍሳችንን ልናዘጋጅበት፣ ከወንጀል ልንርቅበት፣ልንፆም፣ዚክር ልናበዛ፣ለይል ልንቆም፣ ያበላሸናቸውን ነገሮች ልናስተካክልበት ይገባል። ያሲሆን ረመዳንንም መጠቀም እንችላለን። ነፍስያችንን ማሰልጠኛ የሆነ ወር ነው።
የሻእባን አጋማሽ ሲሆን አላህ(ሱብሃነወተአላ)ለግርማ ሞገሱ ለክብሩ በተገባው መልኩ ወደሰማ አዱንያ ይወርድና ባሮችን በሙሉ ይምራቸዋል። ሁለት ሰዎች ሲቀሩ ብለዋል ነብያችን
አንደኛ በአላህ የሚያጋራ የሚያሻርክ ነው። መሽሪክን አላህ አይምረውም። እንደማይምርም አላህ አጠንክሮ ተናግሯል። ሁለተኛ ሁለት የተጣሉ ሰዎችን አይምራቸውም። ሱብሃናልህ! የነዚህን ሰዎች ሰራቸውን እስኪታረቁ ድረስ አቆዩት፣ አታምጡት ይላል አላህ ሱብሃነ ወተዓላ። እስካልታረቅን ደረስ አላህ ምህረተን ይይዝብናል ማለት ነው። ይሄም መሆኑ ለዛ ለታላቅ ለራህመት ወር ለረመዳን እንድንዘጋጅ ነው።
ነብያችን(ሰለላሁአለይሂ ወሰለም)ታላቅ ወር ነው ርመዳን መጣላችሁ እያሉ ሶሃቦችን ያበስሯቸው ነበር። በውስጧም ያለች አንድ ውድ ለሊት አለች ኸይሯን ያገኝ ኸይራን በሙሉ አግንቷል።ኸይሯን የተነፍገ ደግሞ ኸይርን የተባለን ነገር ተነፍጓል አሉ። ለዚህ የተከበረ ወር ዝግጅት የሚደረገው በሸእባን ወር ውስጥ ነው። ስለዚህ ረመዳን ሊመጣ ትንሽ ቀናት ነው የቀረው። ስራችንም ወደ አላህ ይወጣል ሲባል ሊያስደነግጠን ይገባል ምን ያክል ነው መልካም ስራችን መጥፎ ስራችንስ ምን ያክል ነው የሚለው ሊያስጨንቀን ይገባል። ምን ያክሉ ነው አላህን በመታዘዝ የተሞላው ምን ያክሉስ ነው በመጥፎ ነገር የተሞላው። ራሳችንን እንፈትሽ። ኢስቲግፋር ተውበት እናድርግ። ወላሁ አእለም
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል
🚨ሼር ሼር ሼር እናድርገው! ብዙ ሰው ሚዘናጋበት ወር ነው።