ኡመተ ረሱል @smithhk Channel on Telegram

ኡመተ ረሱል

@smithhk


የአላህ ሰላም እና እዝነት በናንተ ላይ ይውረድ ውድ የአላህ ባሮች
በዚህ #channel ላይ የተለያዩ
ኢስላማዊ አስተምህሮቶች
አስተማሪ ታሪኮች
ቀልዶች እና
ወቅታዊ አሳሳቢ ነገሮችን ወደናንተ እናደርሳለን



ለማንኛውም አስተያየት
@Ummate_resul_bot ይጠቀሙ

ኡመተ ረሱል (Amharic)

ከአላህ ሰላም እና እዝነት በናንተ ላይ ይውረድ ውድ የአላህ ባሮች፡ ለፕተትይውር ፈቃዶች እና አጋለ ታሪኮች ተለዋዋጥሎች፡ ቀልዶች፡ እና ወቅታዊ አሳሳቢ ነገሮች፡ እና እንደናንተ ደርሶናል፡ ለተጨማሪ ዓምለተ ረሱል ያጠቃሙ፡ @Ummate_resul_bot

ኡመተ ረሱል

06 Jan, 17:52


Must Listen! SHARE!

ኡመተ ረሱል

10 Dec, 03:33


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የእጁጅ - ወመእጁጅ

የመጨረሻዉ - ክፍል

ከዚያም በቅፅበት ሁሉም ያእጁጃውያን የራስ ምታት እራሳቸውን ከቁጥጥራቸው ውጭ ያደርጋቸውና በአካሎቻቸው ባሉ ቀዳዳዎች በሙሉ ደም ይፈሳቸው ይጀምራል፡፡ ያእጁጃዉያን ምን እንደገጠማቸው ሳያውቁ በማያውቁት ህመም መታመም ይጀምራሉ፡፡ ከራስ ምታቱ ብዛት ትላልቅ ቋጥኝ እያነሱ እራሳቸውን በመደብደብ ጭንቅላታቸውን እየመቱ ይሞታሉ፡፡ ምድርን በብክለት ካጨማለቋት በኀላ በዚህ አይነት በደካማ ትል ምክንያት አላህ ባጠቃላይ ሁሉንም በድን አድርጎ በየሜዳው ያጋድማቸዋል፡፡ ከያእጁጃውያን የአስክሬን ብዛት የተነሳ ምድር በሙሉ ትሸፈናለች፡፡ ሲሞቱም እርስ በርስ ተደራርበው ምድር  ላየሸ ስንዝር ማሳረፊያ እንኳን አይኖርም ከብዛታቸው የተነሳ ያን ጊዜ ምድር ትርምሷን ታቆምና ፀጥታ ይነግስባታል፡፡ ሁሉም ነገር ረጋ ርምሱም ይቆማል፡፡ ምድር ላይ የፀጥታው መንገስ ያጠራጠራቸው ሙእሚኖችም፦ እስቲ ማን ነው እራሱ መስዋት አድርጎ እነ ያእጁጅ የት እንደደረሱ የሚያጣራው በማለት ሲመካከሩ አንዱ ሙሚን እራሱን መስዋት ለማድረግ ተዘጋጅቶ ምድር ላይ ምን እንደተከሰተ ለማየት ተራራውን ለቆ ሲወርድ ለማመን በሚያስቸግር መልኩ ዗዗ምድር በነዚያ ትላልቅ ፍጥረታት ሬሳዎች ተሞልታ ያይና በተክቢራ እየጮኸ ወደመጣበት በመመለስ አላህ ዱዓቸውን እንደተቀበላቸው በደስታ ይነግራቸዋል፡፡ ያን ጊዜ በየዋሻው ተደብቆ የከረመው ከየምሽጉ ወደዉጭ ብቅ ማለት ይጀምራ፡ ሙዕሚኖች የናፈቁትን አለም ለማየት ሲወጡ ያልጠበቁት ነገር ይመለከታሉ፡፡ ሙዕሚኖች ይህን ሲመለከቱ ምንም  እንከን በያእጁጃውያን መሞት ቢደሰቱም እሬሳቸው ምድርን ሞልቶ መንቀሳቀሻ  በማጣታቸው እጅግ ተጨነቁ፡፡ በድጋሚ አላህ ጋር እጃቸውን በማንሳት ዱዓ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ምድራችንን አፅዳልን እያሉ ይማፀኑም ጀመር፡፡ አላህ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ጌታ ነውና ተዐምሩን የግመል አንገት የሚመስል ትላልቅ ፎችን ወደ ምድር ልኮ እነዚህን ግዙፍ ፍጡሮች ወፎቹ ተሸክመው ከምድር ያርቆቸዋል፡፡ ምድር ላይ ያሉ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሬሳዎች፡ከተነሱ በኀላ ምንም እንኳን ምድር ከቆሻሻው ቢፀዳም ሽታው ግን ሊለቅ አልቻለም፡፡
ዳግም አላህ ምድርን ለማፅዳት ሀይለኛ ዶፍ ዝናብ ያወርድና ምድር ልክ እንደ መስታወት ንፁህ ትሆናለች፡፡ ከዚያም አላህ ሰማይን እንዲያዘንብ ምድርን እንዲያበቅል ያዘዋል፡፡ ምድርም ከተፈጠረ ጀምሮ አብቅሎ ማያውቀውን የእህል አይነት ማብቀል ትጀምራለች፡፡ አንድን ፍሬ ዝም ብለው ያገኙት ነገር ድንጋይ ላይም ቢሆን በሚገርም ሁኔታ አብቅሎ ያገኙት ነበር፡፡ በዛን ጊዜ አንድ የሩማን ፍሬ አንድን ሙሉ ጎሳ ማስተናገድ ይችላል፡፡ በዛን ጊዜ አንዴ የታለበው ወተት ብዞ ሰዎችን ያስጠጣል፡፡ በዛን ጊዜ መጠላላት፣መመቃኘት፣መቀናናት የሚባል ነገር ይጠፋል፡፡ በዛ ዘመን አንዱ ሰው ለሌላው ሰው ብር ቢሰጠው እንኳን ተርፎኛል የት ላስቀምጠው ነው ሚለው፡፡ሀብት በሀብት ላይ ነበር፡፡ ያኔ ምድር ሰላም ትሆናለቾ የሰዎች ልብ እንደፀደዳ ሁላ የእንስሳቱም የአራዊትም ቀልብ ይፀዳል፡፡ አንበሳ ግመል ነብር በግ ምናምን ምንመሸ ሳይተናኳሉ አብረው ይኖራሉ፡፡ ልጆችም ከእባብ ጋር መጫወት ይጀምራሉ፡፡ እባቦቹም አይነኳቸወም፡፡ በዛ ዘመን ምድር ላይ ከኢስላም ሌላ ሀይማኖት አልነበረም፡፡


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

09 Dec, 19:05


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

        ክፍል 1⃣9⃣

በየመንገዶቻቸው....በየተዘጉ ቤቶች......እና በየጫካዎች ያገኙትን የሰው ዘር በማተረማመስ ላይ ይጠመዳሉ፡፡ ይህን ግዜ ሙዕሚኖች በመካከላቸው ዒሳ ዐለይሂ ሰላም ይገኝ ነበርና  አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላህ ለዒሳ ቀደም ብሎ፦ ዒሳ ሆይ!!!የያእጁጅ እና ማእጁጅ ህዝቦች ባንተ የምድር መውረጃ ጊዜ ላይ ይወጣሉ፡፡ ባሮቼም የያእጁጃውያኑን በፍፁም መቋቋም አይችሉም ስለዚህም ሴት ምዕመናትን እና ወንድ ምዕምናኖችን ይዘህ ወደ ማመላክትህ ዋሻ ሂድ በማለት ትዕዛዝ ባስተላለፈበት መሰረት ይዟቸው በዋሻው ይሰወራል፡፡

አላህም ከነዚህ አውሬዎች  ሙእሚኖችን ይሰውራቸውና ያእጁጃውያኑም ምድርን መበከላቸውን አጠናክረው ይቀጥሉታል፡፡ ያእጁጃውያኑ ለዘመናት ከተቃጠሉበት የከርሰ ምድር ቃጠሎ ሲወጡ በየአከባቢው የሚገኙትን ወንዞች....ሀይቆች...ባህር እየጠጡ በማድረቅ ምድርን መዞር ይጀምራሉ፡፡ በዚህ መሀል አንድ ያእጁጃውያኑ ቡድን ከአንድ ሀይቅ እንዳልነበር አድርገው በመጠጣት ያደርቁትና ቀጣዩ ቡድን ሲመጡ፦ እዚህ ጋር የሆነ ሀይቅ አልነበር እንዴ!!! እየተባባሉ ያልፋሉ፡፡ ያእጁጃውያን ምድርን ማተራመሳቸውን ተያይዘውታል፤ጅረቶችን፣ወንዞችን፣ ሀይቆችን፣ ባህሮችን እና ውቅያኖሶችን ምጥጥ አድርገው በመጠጣት ምድሪቱን አድርቀውታል፡፡ ይህን ሁሉ ውሀ ጠጥተው ያልረኩትም ፍጥረቶች በመቀጠል ወደ ጫካዎች፣ ወደየማሳዎች በመትመም አረንጓዴ ነገር የተባለ ምድሪቱ ላይ እንዳይቀር አድርገው ይበላሉ፡፡ የይህንንም ሲያጠናቅቁ ሙሉ በሙሉ የዘመቻቸውን አላማ ወደ ሰው ልጆች በማዞር ሰዎችን ከየተደበቁበት መሸሸጊያ ፈልፍለው በማውጣት እየቆራረጡ መብላት ይጀምራሉ፡፡ ይህን የተመለከቱ ደሰው ዘሮችም መሸሽ ቢሞክሩም የትም መሸሻ አያገኙምና ለክስተቱ እጅ በመስጠት የአውሬዎች እራት ይሆናሉ፡፡  እያንዳንዱ ያእጁጃዊ ያገኘውን ማንኛውም ሰው ሲመለከት ለዘመናት መሹለኪያውን የዘጋብን ይህ ሰው ነው በማለት የሰዎቹን እግር ወደ ታች አድርጎ እጆቹን በመቦጫጨቅ ነበር የሚመገበው፡፡ ይህ ሲሆን ሰው እጅግ ይጮሀል ምድር በማታውቀው አይነት የሰዎች ጩኸት ትጥለቀለቃለች፡፡ ይህ ጩኸት ግን ያእጁጃውያኑን ያዝናናቸው ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰዎችን በመያዝ ያስሩና በእንጨት ላይ አንጠልጥለው በእሳት እየለበለቡ በመቆራረጥ ይመግቧቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ያእጁጃውያኑ ሰውንን በተመገቡ ቁጥር በጥጋብ ፋንታ አላህ ከበፊቱ በላይ ረሀብን ይለቅባቸውና ዳግም ወደ ሌላ ቦታ ይስገበገባሉ፡፡
በዚህ ክስተት ላይ ጨቅላ ህፃናት እንኳን የመትረፍ እድል አያገኙም፡፡ ያእጁጃውያኑ የተንኮላቸው እና የጥመታቸው ብዛት ህፃናቱን በወላጆቻቸው ፊት ከበሉ በኀላ ወላጆቹንም እዚያው ይበሏቸውና የበቀል ስሜታቸውን ያበርዱባቸዋል፡፡ ይህን ጊዜ ከዒሳ ጋር በዋሻው የሚገኙት ሙዕሚኖችም የትርምሱን ሁኔታ እንዲያጣራ አንዱን ይልኩታል፡፡ ወጣ ብሎ ሲመለከት ምድር በደም ተጥለቅልቃ እና በየቦታው በተከመሩ በተከመሩ የሰዎች ጭንቅላት እና አጥንት ተሞልቶ ያገኛታል፡፡ በዚን ጊዜ በፍርሀት ተውጦ ወደመጣበት በመመለስ ሁኔታውን ለተቀሩት ሙዕሚኖች ይተርክላቸዋል.....

.....ይቀጥላል
...

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

08 Dec, 06:48


🚨ታሪካዊ ቀን 📅 2024/12/8

ዲመሽቅ ተከፍታለች አላሁ አክበር

أيتها الأمة العظيمة.... الليلة فُتحت دمشق

من ثمر ربيع العربي


👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

17 Nov, 03:57


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

በቁርዐን የተገለፁት 25 ነብያቶች

1 አደም (አ.ሰ)
2 ኢድሪስ (አ.ሰ)
3 ኑህ (አ.ሰ)
4 ሁድ (አ.ሰ)
5 ሷሊህ (አ.ሰ)
6 ኢብራሒም (አ.ሰ )
7 ሉጥ (አ.ሰ)
8 እስማኤል (አ.ሰ)
9 ኢስሃቅ (አ.ሰ)
10 ያዕቆብ (አ.ሰ)
11 ዩሱፍ (አ.ሰ)
12 አዩብ (አ.ሰ)
13 ሹዐይብ (አ.ሰ)
14 ሃሩን (አ.ሰ)
15 ሙሣ (አ.ሰ)
16 ኢልያሥ (አ.ሰ)
17 ዙልኪፍል (አ.ሰ)
18 ዳዉድ (አ.ሰ)
19 ሡለይማን (አ.ሰ)
20 አልየሠዕ (አ.ሰ)
21ዩኑስ (አለይሂሰላም)
22 ዘከሪያ (አ.ሰ )
23 የህያ (አ.ሰ)
24 ኢሳ (አ.ሰ) እና
25 ሙሐመድ {{ሶለሏሁ አለይሂ ወሠለም}} ናቸዉ::

ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት 25
ታላላቅ ነብያቶች መካከል ደግሞ አምስቱ ዑሉል-ዐዝም {መከራና ስቃይ ታጋሽ} በመባል ይታወቃሉ::

እነሱም
👉1 ኑህ(አ.ሰ)
👉2 ኢብራሂም(አ.ሰ)
👉3 ሙሳ(አ.ሰ)
👉4 ኢሳ(አ.ሰ)
👉5 ነብዩ ሙሐመድ {ሰዐወ} ናቸዉ!!!

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

12 Nov, 04:09


قال رسول الله ﷺ:

إذا عَمِلْتَ سيئةً فأتبِعْهَا حسنةً تَمحُهَا قالَ: قلتُ يا رسولَ الله، أمِنَ الحسَناتِ لا إلهَ إلَّا اللهُ قالَ: هيَ أفضَلُ الحسَنات.

رواه أحمد/٢١٤٨٧

👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

08 Nov, 17:09


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የእጁጅ_ወመእጁጅ

        ክፍል  1⃣8⃣

አሁን ደግሞ ከምድረ ገፅ ወደ ከርሰ ምድር እንሸጋገርና እነዚያ የተዘነጉት ህዝቦች በምን መልኩ ይህን ረጅም ህይወት እንደሚገፉ እንቃኝ
ይህ ድንበር ከተገነባ አንስቶ ያእጁጃውያኑ በሰዎች ዘንድ ፍፁም ተዘንግተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከየትኛውም ህዝብ በላይ በሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ህዝብ ዘንድ በሚገባ ይወሳሉ፡፡ ለነገሩ የሰው ልጅ አስታወሳቸውም ረሳቸውም ምንም አይመስላቸውም፡፡ እነሱ አላማቸው ከዚያ ማጎሪያ ወጥተው የዘጋባቸውን የሰው ዘር ማጥፋት ነው፡፡
በያንዳንዱ ቀን በትዕግስት እና በትጋት የምድርን ቅርፊት ገንጥለው ለመውጣት ይጥራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ዘዉትር ሊከፈትላቸው ትንሽ ሲቀር ነገ የቀረውን እንቆፍርና እንወጣለን በማለት ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ በነጋታው ካቆሙበት ሊጀምሩ መቆፈሪያዎቻቸውን ይዘው ሲመጡም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ቦታውን እንደነበር በማድረግ ዳግም ለልፋት በመዳረግ አሁንም ሊከፍቱ ትንሽ ሲቀራቸው ለቀጣይ ቀን ቀጠሮ በመያዝ ዳግም ትተው ወደየቤቶቻቸው ይበታተናሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ሺህ አመታት ከንቱ ልፋታቸውን ካካፈሰሱ በኀላ የመውጫቸው ቀጠሮ ሲደርስ ድንገት የያእጁጃውያኑ የጦር መሪ በመምጣት የህዝቦቹን ተስፋ አስቆራጭ ተግባር እና ወደ ምድር የመውጣት ጉጉት ሲመለከት የሰው ዘር የሆነ ፍጥረት ተስፋ ሲቆርጥ ወደ ፈጣሪው እንደሚደገፍ ሁላ የጦር መሪውም ለዛሬ በቃ ነገ ኢንሻ አላህ በጠዋት እንከፍተዋለን ይላቸዋል፡፡ በመቀጠልም ለቀጣዩ ቀን ቀጠሮ ይዘው ሁሉም ወደማረፊያቸው በመመለስ ለብዙህ ሺህ አመታት በድካም እና በትግል የደከመ ሰውነታቸውን ለረፍት ያስረክባሉ፡፡
ለሊቱ ሄዶል ሁሉም እንቅልፍ ጥሏቸዋል  ድንገት ከመሀከላቸው አንዱ በለሊት በመነሳት ከየፊናው የሚያንፀባርቀውን የፀሀይ ወጋገን ሲመለከት ጮክ ብሎ፦ ወገኖቼ ሆይ መሹለኪያዎቹ በሙሉ ተከፋፍተዋል፡፡ ወገኖቼ ሆይ!!! ተነሱ ተነሱ እንውጣ በማለት ይጣራል፡፡ ይህን ጊዜ ያ ለቁጥር የሚያዳግት ፍጥረት ከእንቅልፋቸው በመንቃት በግርምት የተከሰተውን ይመለከት ጀመር፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜያቸውን መግደል አይፈልጉምና በየመሹለኪያው እየሾለኩ ወደ ገፀ ምድር መትመም ይጀምራሉ፡፡
በምድሪቱ በተከፈተላቸው የመሹለኪያ መዓት አማካኝነት ከየቀዳዳው የሚሿልኩት እና በምቀኝነት፣ በቅናት፣ በጥላቻ የተወጠሩት ያእጁጃውያንም ምድርን በመሙላት ማጥለቅለቅ ይጀምራሉ፡፡
በየመንገዶቻቸው....በየተዘጉ ቤቶች......እና በየጫካዎች ያገኙትን የሰው ዘር በማተረማመስ ላይ ይጠመዳሉ፡፡ ይህን ግዜ ሙዕሚኖች በመካከላቸው ዒሳ ዐለይሂ ሰላም ይገኝ ነበርና  አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላህ ለዒሳ ቀደም ብሎ፦ ዒሳ ሆይ!!!የያእጁጅ እና ማእጁጅ ህዝቦች ባንተ የምድር መውረጃ ጊዜ ላይ ይወጣሉ፡፡ ባሮቼም የያእጁጃውያኑን በፍፁም መቋቋም አይችሉም ስለዚህም ሴት ምዕመናትን እና ወ
ንድ ምዕምናኖችን ይዘህ ወደ ማመላክትህ ዋሻ ሂድ በማለት ትዕዛዝ ባስተላለፈበት መሰረት ይዟቸው በዋሻው ይሰወራል፡፡

   ...ይቀጥላል
...

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

06 Nov, 12:33


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

                ክፍል  1⃣7⃣

ትውልድ ትውልድን እየተካ ረዥም አመታት ከተቆጠረ በኀላ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ኑህን ዐለይሂ ሰላም በነብይነት ወደ ምድር ነዋሪያን ላከው፡፡
ይሁን እንጂ ህዝቡ መለኮታዊ ትዕዛዛቱን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እስከ መጨረሻቸው በመጥለቅለቅ ሊጠፉ ቻሉ፡፡ ሙዕሚኖች ሲቀሩ፡፡ ምድር አስተናግዳ ማታቀውን ከባድ የጥቃት እንቅስቃሴ በምታስተናግድበት ወቅት እንኳን በከርሰ ምድሩ የሚገኙት ያእጁጃውያኑ ስለ ክስተቱ ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡
አመታት እየተተካኩ ዘመኑ እጅግ ይገሰግስ ጀምሯል በኑህ ዘመን የኖሩ ትውልዶችም ለቀጣዩ ትውልድ ምድርን አስረክበዋል፡፡ የተለያዩ ትውልዶች ምድር ላይ ከመተካካተቸው የተነሳም ያእጁጃውያኑ ጉዳይ ፍፁም ተረስቶ ስማቸውን እንኳን የሚያውቀው ጠፍቷል፡፡ ይሁን እንጂ ያእጁጃውያኑ የታታሪ ሰራተኛን ተስፋ ሰንቀው ምድርን በመበረቃቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡
አሁንም ትውልድ ትውልድን መተካቱን ይዞታል፤ ምድርም አስደናቂ ክስተቶቿን በግሩም መለኮታዊ ትዕዛዝ ማሰተናገዱን ተያይዛዎለች፡፡
ነቢያት እንደ ጉድ ይተካካሉ ነቢያቱ ወደየህዝባቸው በመጡ ቁጥርም ስለያእጁጃውያኑ ሳያወሱ እና ሳያስጠነቅቁም አያልፉም ነበር፡፡ ምድር በነቢያት መፈራረቅ እና በትውልድ መተካካት ረጅም አመታትን ካስቆጠረች በኀላ ተራውን ለነብያት መደምደሚያ ..ለነቢያት ቁንጮ ..ለነቢያቱ ኢማም...ለሰው ልጆች ፈርጡ...ለጌታው ተናፋቂ ለሙሀመድ ኢብን ዐብዱላህ ሰ.ዐ.ወ አሰረክባ የያእጁጃውያኑን የመውጫ ቀገሮ መቃረቡን ለህዝባቸው ያበስሩ ጀመር፡፡
በረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የህይወት ዘመን ከሚፈታተኗቸው ፍጥረታት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አይሁዳውያኑ ረሱል ዘንድ በመምጣት ነብይ የሆነ ሰው ብቻ የሚመልሰውን ጥያቄ ሊጠይቋቸው አስበው ስለ አስሃቡል ካህፍ እና ስለ ዙል ቀርነይን ምንነት እንዲዘረዝሩላቸው ጠየቋቸው፡፡
ለረሱልም ሰ.ዐ..ወ መለኮታዊ ጥቆማ እንዲህ ሲል መጣላቸው ከዙል ቀርነይንም ይጠይቁሀል፡፡ <<በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን አነባለሁ>>በላቸው፡፡
እኛ ለእርሱ ምድርን አስመቸነው፡፡  ለነገሩም ሁሉ መንገድን ሰጠነው፡፡ መንገዱንም ወደ ምዕራብ ተከተለ .......እያለ ይቀጥላል የቁርዐኑ አንቀፅ <<ሱረቱል ካህፍ>><<83-85>>

ይህን አስከትሎ ቀደምት ነቢያት ለህዝቦቻቸው ያስጠነቅቁትም የነቀረውን የያእጁጃውያን ክስተት ረሱል ሰ.ዐ.ወ ለህዝቦቻቸው በመተረክ በመጨረሻው ዘመንም እንደሚወጡም አክለዉ አስጠነቀቁ፡፡
በዚህ ሁኔታ ሀላፊነታቸውን ተወጥተው ዱንያን ትተው ወደዚያኛው አለም ሲሸጋገሩ በረሱላችን ሰ.ዐ.ወ ሞት ምክንያት የነቢያት ድምዳሜው ተፈፀመ፡፡ ትውልድ ትውልድን ይተካ ይዟል ምንም እንኳን ይኸኛው የሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ኡመት ከሌላው ኡመት በተሻለ መልኩ ስለያእጁጃውያኑ እውቀት ቢኖረውም ያሉበትን ግን በቴክኖሎጂ ምጥቀት ተጠቅሞ እንኳን ሊያረጋግጥ አልቻለም፡፡

የሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ኡመቶች በቴክኖሎጂ ምጥቀት ከየትኛውም ኡመት ጋር የማይስተካከሉ ሲሆኑ ቀደምት ኡመቶች ያልሞከሯቸውን ድንቅ ተግባራት በመተግበር አሳክተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ከርሰ ምድር ህዝቦች እንዳያውቁ በምድር በታች የሚከሰተው ከፍተኛ የሆነ እሳተ ገሞራዊ እንቅስቃሴ አግዷቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ምድር በውስጧ አምቃ በያዘቻቸው እና ለቁጥር አዳጋች በሆኑ ፍጥረታት አማካኝነት የምታስተናግደውነሸ ሙቀት  የምታስተነፍስበት ሂደት ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ አላህ ሱ.ወ በሰው ልጆች እና በያእጁጃውያኑ መሀከል የማይደፈር የነበልባል ግድብ በዙል ቀርነይን አማካኝነት አስገድቦ ለጥበቡ መግለጫ በማድረግ ለዘመናት ከሰው ልጆች እይታ  እሱ ብቻ በሚያውቀው ተዐምር ሰውሮታል፡፡ እስቲ አሁን ደግሞ ከምድረ ገፅ ወደ ከርሰ ምድር እንሸጋገር......

   ...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

05 Nov, 04:01


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የእጁጅ - ወመእጁጅ

       ክፍል  1⃣6⃣

በዚህ ሁኔታ የአመፅን ተስፋ ሰንቀው መውጫ ጉድጎዳቸውን ለብዙ ሺህ አመታትን ከቆፀሩ በኀላ እሱን ትተው ሌላ መውጫ መቆፈር ይጀምራሉ፡፡
ምንም እንኳን ከቀላጭ ነበልባሉ ሽሽት ሌላ ቦታ ለመቆፈር ቢሞክሩም ምድሪቱን መውጫ ጫፍ ሲቃረቡ እንደ በበፊቱ የቀላጭ ናዳ ይዘንብባቸዋል፡፡ በዚን ጊዜ ለቁጥር የሚያዳግቱ ያእጁጃውያን ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ የሞቱትንም በጅምላ በማከማቸት ለምግብነት ያዉሉታል፡፡
ምንም እንኳን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ያእጁጃውያን በየሰከንዱ የቀላጩ ሰለባ ሁነው ቢሞቱም ብዛታቸው ግን እጅግ ከመጨመሩ የተነሳ ሬሳውን መመገብ አላጠግብ ብሏቸው በረሀብ ይተራመሳሉ፡፡
ገደብ ያለፈው ስግብግብነታቸው እና የተመሳሳይ ዘራቸውን ስጋ በልነታቸውን አቅላቸውን አስቶ ያዋልላቸዋል፡፡
በየቀኑ የሚበሏቸውን የሙታኑን አጥንትም ከቤት መስሪያነት በተጨማሪ ለመቆፈሪያነትም በመገልገል የምድሪቱን ቁፋሮ ጠበቅ አድርገው ይዘዉታል፡፡

ይሁን እንጂ ምድርን በቆፈሩ ቁጥር ከሆዱ የሚወጣው ቀላጭ መኖሪያዎቻቸውን ያጥለቀልቅ ይዞታል፡፡
ዙል ቀርነይን አላህ ባገራለት እውቀት ተጠቅሞ ዘመናዊያን ያልሞከሩትን ኦክስጅን በሌለበት እሳትን በማንቀልቀል ለረጅም ዘመናት የቆየ ብልህ ንጉስ ነው፡፡
አዎ!!!አላህ የፈቀደ እለት እንጂ ለነዚህ ያእጁጃውያን መውጫ የላቸውም፡፡ የጅልነት ተስፋቸው ይህን የቀላጭ ክምር ጥሰው ሳይወጡ በፊት የንዴት ዛቻዎችን እንዲደረደሩ አድርጓቸዋል፡፡ አንዳንድ ያእጁጃውያንም ከረሀብ ብዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ያብራክ ክፋይ ልጆቻቸውን አጣጥመው መብላት ይጀምራሉ፡፡ የልጆቻቸውን መብላት ያላጠገባቸው ያእጁጃውያን በዙሪያቸው ያለውን ቋጥኝ እና ተራራዎችንም መብላት ይጀምራሉ፡፡

ዙለል ቀርነይን እና ህዝቦቹ ለዘመናት ያሰቃይዋቸው ህዝቦች ላይ የተሳካ ግድብን በመገደባቸው በደስታ ፈንድንቀዋል፡፡አላህ እስከወሰነው ቀን እስከሚወጡ ድረስ ከያእጁጃውያኑ ተንኮል የተገላገሉ ህዝቦችም ለአላህ ምስጋነሠ ሰላት በመስገድ ደስታቸውን ሙሉ አድርገዋል፡፡
ነገር ግን በመሀላቸው ያለው ዘረ ቅይጥ አይጁር በደስታ እና በሀዘን መካከል ነበር የነበረው
ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት አመታትን ታጅበው ጊዜው ይነጉድ ጀመር፡፡ ምድር ሰላማዊ ሆና ህዝቦችዋን ትውልድን በትውልድ መተካቱን ተያይዟቸዋል፡፡
ትውልድ ትውልድን እየተካ ረዥም አመታት  ከተቆጠረ በኀላ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ኑህን ዐለይሂ ሰላም ወደ ምድር ነዋሪያን ላከው፡፡

   .....ይቀጥላል
...

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

01 Nov, 18:40


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የእጁጅ - ወመእጁጅ

        ክፍል 1⃣5⃣

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የእጁጃውያን ሀገር ሰላም ብለው ምድርን ወረረው፡፡ የምታቃጥላቸውንም ፀሀይ አጥፍተው የሰው ልጆችን ገድለው የተቀሩትን ለማሰቃየት ወደ ምድር ሊወጡ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ይሁን እንጂ የጉድጓዱን መሹለኪያ ሲመጡ ዝግ ሆኖ ያገኙትና ሊከፍቱት ሲታገሉም እማይሞከር ሆኖ ያገኙታል
ነገር ግን ያለመታከት ሌት ተቀን ስራቸው ከዚህ ግድብ ጋር መታገል ይሆናል፡፡
ዘዉትር ቀኑን ሙሉ የዚህን ግድብ ግድግዳ ሲቆፍሩ ዉለዉ የሬንጁን ጫፍ ሲደርሱና የተከፈተላቸው መስሏቸው ግር ሲሉ ያኔ በአላህ እገዛ የተገደበው ግድብ የብረት ቅላጭ በላያቸው በመዝነብ ተስፋ ቢስነታቸውን ያሳያቸው ጀመር፡፡
በዚህ ሁኔታ ምድሩ እንዴት ተዘጋብን ??በሚል ጩኸት እና እልህ ያናውጧታል፡፡ ከመካከላቸውም ወገንቼ ምን ያስጮሃችኀል??? አሁን ሰዎች በእኛ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል፡፡
ይሁን እንጂ እኛም በመጨረሻው ሰዐት የምንወጣበት ቀን ይመጣል፡፡
ያቺ ቀን ደርሳ ከታገትንበት የወጣን ቀን ግን የሰው ልጆችን እስከ መጨረሻው እናጠፋቸዋለን፡፡ ምድር ላይም ምንም አይነት አረንጓዴ ነገር እንዳይቀር አድርገን ምድርን ካወደምን እና ባህሮቻቸውንም ካደረቅን በኀላ የሰማይ ነዋሪያንንም(መላዕክት) እንዳልነበሩ አድርገን እንደመስሳቸዋለን፡፡ይቺ ቀን ስትደርስ ስፍር ቁጥር የሌለን ሁነን ከምድር በመፍለቅ ቤቶቻቸውን እናፈራርስባቸዋል፡፡ የሰው ልጆችን እንገድላቸዋለን፡፡ እንደውም ሰዎች የሚፈሩትን ሞትን ራስን እንገድለዋለን...ሰዎችንም በአጠቃላይ ገድለን የተቀሩተን አገልጋዩቻችን እናደርጋቸዋለን፡፡
ከዚያም ወደ ሰማይ ነዋሪያን ፊታችንን በማዞር የቀስት ናዳዎችን እንለቅባቸዋለን፡፡ በቀስት ናዳዎች የማያልቁ ከሆነ እራሳችን ወጥተን እስከ መጨረሻው ከገደልናቸው በኀላ የተቀሩትንም አገልጋዩቻችን በማድረግ ፍጥረተ አለሙን በብቸኝነት እንቆጣጠረዋለን፡፡አይዟቹ ይህ ቀን ቅርብ ነው፡፡ ተስፋ እንዳትቆርጡ መውጫ ቀዳዳ እስክናገኝ ድረስ በያንዳንዱ ሰከንድ ትግላችንን በማጠናከር እንቀጥላለን በማለት አፅናናቸው፡፡

የእጁጃውያኑ በዚህ ሁኔታ ይዛዛታሉ ለሰው ልጅ ያላቸው ጥላቻ እና ምቀኝነት ከበፊቱ ይልቅ ይብስባቸዋል፡፡ ከንዴት እና ብስጭት ብዛት ልባቸው ተቃጥሎ በማለቅ እንደ ቁራጭ ስጋ ትሆናለች፡፡ በዚህ ሁኔታ የአመፅን ተስፋ ይዘው መውጫ ቀደዳቸውን ለብዙ ሺህ አመታት ከቆፈሩ በኀላ እሱን ትተው ሌላ መውጫ መቆፈር ይጀምራሉ፡፡....

  ....ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

31 Oct, 17:16


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

        ክፍል 1⃣4⃣

ልጂቱም ፦ አይጁር እወድሀለሁ ነገር ግን ቤተሰቦቼን ትቼ ካንተ ጋር መውጣት አልችልም አለችው፡፡
አይጁርም፦ እነዚህ እኮ ወገኖቻችን አይደሉም፡፡ አታለውናል፤ ሸውደውናል ስለዚህ አታከራክሪኝ ሁሉንም ነገር ከዚህ ስንወጣ አስረዳሻለሁ አሁን ሰዐት የለንም ፈጥነን እንሂድ፡፡አሁን የገፀ ምድር ነዋሪያን የጉድጎዱን መሹለኪያ ሊዘጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው እንሂድ በማለት እጅግ ለመናት፡፡
ልጂቱም አይጁር ሂድ አንተ፡፡ እኔ ግን አልሄድም አለችው፡፡
አይጁርም እጮኛውን እና ያን በትዕቢት የተሞላ ጉድጓድ ድጋሚ ላያያቸው ለመጨረሻ ጊዜ ትቶት ወጣ፡፡

ይህን ጊዜም ዙል ቀርነይም፦ ምን ገጠመህ ልጄ!!! ብሎ ሲጠይቀው፤ አይጁርም የተከሰተውን በሙሉ ተረከለት፡፡
ይህን ጊዜ ዙል ቀርነይን አይዞህ ልጄ!!!አንተ የመረጥከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ መምራት አትችልም፡ አላህ ብቻ ነው የሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራው፡፡ ተዋት ወደ ፈለገችበት ትሂድ የአላህን ውሳኔ አክብረውም ውደደውም፡፡
ምናልባትም በዚህ ላንተ ብዙ ኸይር ሊኖረው ይችላል በማለት አፅናናው፡፡ አይጁር በዙል ቀርነይን ምክር ልቡ ከተረጋጋ በኀላ ዙል ቀርነይን ከፍተኛ ብዛት ያለውን እንደ ሬንጅ ያለ ነገር በማስጠጋት እንዲቃጠል አዘዘ፡፡
ህዝቡም በተባለው መሰረት ጉድጓዱ ላይ ሬንጁን በማድረግ ያቃጥሉት ጀመር፡፡ በመቀጠልም ጉድጓዱ ላይ በቀለጠው ሬንጁም ላይ የተሰበሰበዉን የብረታ ብረት ጥርቅም እንዲከምሩ አዘዘ፡፡
ይህ ሬንጁ ላይ የከመሩት የብረታ ብረት መዐትም ልክ እንደ ሬንጁ እየቀለጠ መንቀልቀል ሲጀምር በላዩ ከፍተኛ ብዛት ያለውን እና እንደ ተራራ የተከመረውን የነሀስ ጥርቅም ይከምሩት ጀመር፤ ይህን ጊዜ ነሀሱም እንደ ሬንጁ እና እንደ ብረታ ብረቱ ይቀልጥ ጀመር፡፡
በመቀጠልም ድጋሚ ከፍተኛ ብዛት ያለውን ሬንጅ በማምጣት በቀላጮቹ ላይ ይከምሩትም ጀመር፡፡
ሁሉም ሰው ሊየነበው የሚገባ ነው
       
በመጨረሻም እንደ ወንዝ ብዛት ያለ የጭቃ ክምር በላዩ ላይ በመመረግ የከርሰ ምድር ነዋሪዎች ዳግም ፀሀይን እንዳይመለከቱ እና እስከ ቂያማ መቃረቢያ ድረስ ላይወጡ አዳፈኗቸው፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የእጁጃውያን ሀገር ሰላም ብለው ምድርን ወረረው፡፡ የምታቃጥላቸውንም ፀሀይ አጥፍተው የሰው ልጆችን ገድለው የተቀሩትን ለማሰቃየት ወደ ምድር ሊወጡ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡.......

   ...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

30 Oct, 18:04


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

           
ክፍል 1⃣3⃣

ዙል ቀርነይንም፦ ጌታዬ ከሱ የሰጠኝ ሀብት ከናንተ ግብር በላጭ ነው፡፡
ስለዚህ በጉልበት አግዙኝ፡፡ በናንተ እና በነሱ መካከል ብርቱን ግድብ አደርጋለሁ፡፡ የብረትን ትላልቅ ቁራጮች ስጡኝ፡፡ በሁለት ጫፍ መካከልም ባስተካከለ ግዜ አናፉ አላቸው፡፡ ብርቱን እሳት ባደረገ ጊዜ የቀለጠውን ነሀስ ስጡኝ፡፡ በሱ ላይ አፈስበታለሁና አላቸው፡፡ <ሱረቱል ካህፍ95>
ህዝቦቹም ዙል ቀርነይን ባዘዛቸው መሰረት በአካባቢያቸው የሚገኘውን ብረታ ብረት...ነሀስ...ሬንጅ እና የተለያዩ ቀላጭ ነገሮችን ባጠቃላይ በመሰብሰብ ይከምሩለት ጀመር፡፡ ይሁን እንጂ የታቀደውን ያህል ሊሰበስቡ አልቻሉም፡፡
ስለሆነም ዙል ቀርነይን የተለያዩ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ነገዶችን በማስተባበር እጅግ በርካታ እና ለአላማው ማሳኪያ በቂ የሆነ ማቴርያል ማሰባሰብ ቻሉ፡፡ በመቀጠልም ለአላማው ማሳኪያ የተሰበሰበውን ማቴርያል በመያዝ ወደ ጉድጓዱ ዘንድ እንዲኬድ ህዝቡን ባጠቃላይ አዘዘና ጉዞ ወደ ፀሀይ መውጫ ተጀመረ፡፡
የያእጁጃውያኑን መሿለኪያ የጉድጓድ በር መዝጊያ ይሆን ዘንድ ለታቀደው አላማ የተዘጋጀውን ማቴርያል ህዝቡ በንቃት ተሸክሞ የጉድጓዱ ቦታ ላይ ደረሰ፡፡
ህዝቡ አይቶት የማያውቀውን የፅልመት ጉድጓድ በግርምት እና በፍራቻ ዙርያውን ከበው ሲመለከቱ አይጁር እና ጓደኞቹ ግን በክህደት...በበደል...በአመፅ በምቀኝነት...እና በጥላቻ ያሳደጋቸውን ጉድጓድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የስንብት እይታቸውን እያሳረፉ ነበር፡፡
ይህን ጊዜ አይጁር ከከርሰ ምድር በታች የምትገኘውን ልጅ በማስታወስ እሺ ካለች ይዟት ሊወጣ እንቢ ካለችም ለስንብት ለመግባት ወሰነ፤ ይሁን እንጂ ጓደኞቹ ድጋሚ ወደ ገፀ ምድር ላይመለስ ይችላል በሚል እና ጉዳዩ ይታወቅብናል ብለው ከለከሉት፡፡
ምንም እንኳን ወደ ጉድጓዱ ዘልቆ እንዳይገባ ጓደኞቹ አጥብቀው ቢማፀኑትም አይጁር ግን የልጅቱ ነገር አልሆንልህ ብሎት ዙል ቀርነይንን አስፈቀደው፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ የያንተ ጉድጓድ ውስጥ ዳግም መግባት ላንተም ሆነ ለኛ አደጋ ስለሇነ መግባት የለብህም በማለት ከለከለው፡፡
አይጁርም፦ ንጉስ ሆይ ስጋት አይግባህ፡፡ የኔ ጉድጓድ ውስጥ መግባት ለኔም ሆነ እዚህ ለተሰበሰበው ህዝብ ምንም አይነት አደጋ አይደርስም፡፡ ስገባም በጥንቃቄ ነው የምገባው በማለት ያሳምነው ጀመር፡፡ ዙል ቀርነይንም የአይጁር ጉጉት እና ውትወታ ሲመለከት፦ ልጄ ጠንቀቅ ብለህ ግባ በማለት ፈቀደለት፡፡
አይጁር ከመግባቱ በፊት ያእጁጃውያኑ ሁኔታውን እንዳይጠረጥሩ በገፀ ምድሩ ላይ የተሰበሰቡት ህዝቦች ፀጥ ረጭ አሉ፡፡
በመቀጠልም አይጁር በእርጋታ እና በጥንቃቄ ወደ ጉድጓድ ዘልቆ ገባ፡፡ የጉድጓድ ነዋሪያንም ጉድጓዱን በፀጥታ አድምቀውት ነበርና አይጁር በፍፁም ጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ ወደ ልጅቱ ሄደ፡፡
ልክ ልጅቱ እሱን ስትመለከተው እጅግ በመደሰት ወደሱ ገሰገሰች፡፡ ይህን ጊዜ፦ ድምፅሽን ቀንሺ፡፡ ማንም መምጣቴን እንዲያውቅ አልፈልግም አላት፡፡
ልጂቱም፦ አንተ አይጁር ምን አድርገህ ነው ወገኖቻችን ሊገድሉህ ሚፈልጉህ? እኔ ስላንተ ሰግቻለሁ አለችው፡፡
አይጁርም ፦ምንም አትስጊ፡፡ አሁን የመጣሁት ይዤሽ ወደ ገፀ ምድር ልወጣ ነው አላት፡፡
ልጅቶም፦ አይጁር እወድሀለው፡፡ ነገር ግን ወገኖቼን ትቼ ካንተ ጋር መውጣት አልችልም አለችው፡፡

...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

27 Oct, 03:53


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የእጁጅ - ወመእጁጅ

       
 ክፍል 1⃣2⃣

ይሁን እንጂ ይህን ሴራ ኑመይሪድ በድብቅ ተደብቆ እየሰማ  ነበር፡፡ ልክ ይህን እንደሰማ በድንጋጤ ራሱን ሳተ፡፡ ከዛም ኑመይሪድ ከነዚህ ህዝቦች ለማምለጥ በፍጥነት ወደ አይጁር ፍቅረኛ በመገስገስ የተከሰተውን በሙሉ ነገራት እና ተነሺ አኔ ጋር እነአይጁር ወዳሉበት እንሽሽ አላት
ልጅቶም፦ ምንም ቢሆን ሁናታው አሳዝኖት ብታለቅስም ግን ወገኖቼን ትቼ የትም አልሄድም፡፡ አንተ ሂድ....እኔ እዚሁ እቀራለሁ፡፡ ነገር ግን ሚስጥርህን ለማንም አልነናገርም አለች፡፡
ኑመይሪድም ከአይጁጃውያኑ ሽሽት ወደ ምድር ማንም ሳያየው ጉዞ ጀመረ፡፡ በመንገድ ላይ ሳለም፦ አይጁር እውነቱን ነበር እነዚ ህዝቦች እውነትም የተረገሙ ናቸው፡፡ በአይጁር ላይ በፈፀምኩት ክህደት በጣም ተፀፅቻለሁ እያለ ከራሱ ጋር በመነጋገር መንገዱን ቀጠለ፡፡
በመጨረሻም ኑመይሪድ በያእጁጃውያኑእና በሰዎች መሀከል ያለውን ርቀት በማጠናቀቅ ዙል ቀርነይን ቤተ መንግስት ደጅ ላይ ቆሞ አይጁርን ጮክ ብሎ ተጣራ፡፡

አይጁርም የኑመይሪድን ጥሪ ሰምቶ ሲወጣ የቤተ መንግስቱ ጥበቃዎች ቀድመውት በመውጣት ከበውት አገኛቸው፡፡
አይጁርም ኑመይሪድን የከበቡትን ጥበቃዎች እንዲተዉት ቢነግራቸውም ቋንቋውን ሊረዱት ባለመቻላቸው በጭራሽ ሊረዱት አልሞከረም፡፡

በመጨረሻም ዙል ቀርነይን መጥቶ ጥበቃዎቹ እንዲለቁት በማድረግ ኑመይሪድ ከአይጁር ጋር ወደ ቤተ መንግስት በመዝለቅ ጓደኞቹን ተቀላቀለ፡፡
ኑመይሪድም ለአይጁር፦ ወንድሜ ይቅር በለኝ!!!አለው፡፡
አይጁርም ለምንድነው ይቅርታ ማደርግልህ?? አለው፡
ኑመይሪድም፦ስለፈፀመው ክህደትና ተንኮል ክህደት እና ተንኮል በሙሉ በመንገር ከርሰ ምድር ላይ ስለታሰበው ሴራ ዘረዘረለት፡፡
አይጁርም፦ ምንም አይደል ወንድሜ ሁሉም ሰው ይሳሳታል፡፡ ነገር ግን አንተ እኔ ላይ መጥፎ ጥርጣሬን በልብህ አሳደርክ ፤ ቢሆንም አላህ መልካሙን መንገድ ይመራህ ዘንድ ይቅር ብዬሀለው አለው፡፡
በመቀጠልም ዙል ቀርነይን ከየ ክፍለ አለሙ የመጡትን ዑለማኦች እንዲሰበስቧቸው ባዘዘው መሰረት ሁሉም ተሰበሰበ፡፡
ዙል ቀርነይንም ለተሰበሰቡት ዑለማኦች ሁሉንም ነገር ዘርዝሮ ካስረዳቸው በኀላ፦ እነሱ እኛን ለመዉረር ወስነዋል፡፡ የኛ ውሳኔስ ምንድነው መሆን ያለበት በማለት አማከራቸው፡፡
ዑለማኦቹም፥፦ ክቡር ንጉስ ሆይ!!! ውሳኔው ያንተ ነው አላህም ያግዘናል አሉት፡፡
ንጉሱም ፦ ለአይጁር ነገ በአላህ ፍቃድ የጉድጓዱን ቦታ ታሳየኛለህ አለው፡፡
አይጁርም፦ በአላህ ፍቃድ አሳይሀለው ንጉስ ሆይ!!! በማለት የዛሬውን ስብሰባ ለነገ ቀጠሮ አጠናቀዉት ተበታተኑ፡፡
በሁለተኛው ቀን ዉሎሸ ቀርነይንም አይጁርን እና ኡለማኦችን አስከትሎ የያእጁጃውያን መሽለኩያ ጉድጓድ ለመመልከት ጉዞ ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም በሁለት ትላልቅ ተራራዎች መካከል ጉድጓዱን አገኙት፡፡
አይጁርም፦ ንጉስ ሆይ ምን ለማድረግ ወሰንክ? አለው፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ ""የበደለውንማ ወደፊት እንቀጣዋለን፡፡ ከዚያም ወደ ጌታው ይመለሳል፡፡ ብርቱንም ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
አይጁር ይህን ሲሰማ፦ በዙል ቀርነይን አምላክ አምኛለሁ አለ፡፡

ዙል ቀርነይንም ተዟዙሮ ጉድጓዱን ከተመለከተ በኀላ ብዙ አሰበና፦ ኑ እንመለስ መፍትሄውን አግኝቻለሁ በማለት ሁሉንም ይዞ ወደ ህዝቡ ተመለሰ፡፡
በሚቀጥለውም ቀንመሸ ዙል ቀርነይን ለቁጥርየሚያስቸግረውን ህዝቡን በመሰብሰብ፦ ህዝቦቼ ሆይ እነኚህን ያእጁጃውያን ልንዋጋቸው አንችልም፡፡ ብንዋጋቸውም እነሱን በፍፁም መቋቋም አንችልሞ አላቸው፡፡
ህዝቡም ፦ ዙል ቀርነይን ሆይ ያእጁጅ እና መእጁጅ በምድር ላይ አበላሺዎች ናቸውና፤ በእኛ እና በእነሱ መካከል ግድብን ታደርግልን ዘንድ ግብርን እናድርግልህን??? በማለት ጠየቁት፡፡ <ሱረቱል ካህፍ 94>
ዙል ቀርነይንም፦........

...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

26 Oct, 03:55


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

          ክፍል 1⃣1⃣

ህዝቡም፦ ያሳለፉትን ጊዜ እና ወንጀል አላህ ይቅር ይበላቸው"በማለት በአንድ ድምፅ ተናገሩ፡፡ ህዝቡ የሚናገረውን ዙል ቀርነይን ለዘረ ቅይጦቹ ይተረጉምላቸውም ነበር፡፡ ከዚያም ዙል ቀርነይንም "የበደለውንማ" ወደ ፊት እንቀጣዋለን፡፡ ከዚያም ወደ ጌታው ይመለሳል፡፡ ብርቱንም ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
ያመነ ሰው ኸይር ስራ የሰራ ፤ለርሱ በምንዳ በኩል ጀነት አለችው፡፡ ለርሱም ከትዕዛዛችን ገርን ነገር እናዘዋለን፡፡አላቸው.......

ህዝቡም አንተ ንጉስ ሆይ ምን ያማረ ንግግር ነው የተናገርከው በማለት በንግግሩ በመደሰት ተስማሙ፡፡
እነሱ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ኑመይሪድ በነአይጁር ላይ ያበጀውን የሴራ መረብ ሊዘረጋ ወደ ጉድጓዱ በመዝለቅ ነው፡፡ ልክ ከከርሰ ምድር ዘልቆ የእጁጃውያኑን እንደተገናኘም ወሬውን በጉጉት ጠየቁት፡፡
ኑመይሪድም፦ የአይጁር መክዳት መክዳት አንሶ አብረዉኝ የወጡት ወጣቶችም ክህደትን መርጠው እዚዪው ቀርተዋል ብሎ ነገራቸው፡፡
ባለ ስልጣናቱም ፦ ምንድነው የምትለው ኑመይሪድ???ለአይጁር ያለህ ጥላቻ ገፋፍቶህ እንዳይሆን ይህን ያልከው ሁሉንም ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ አይጁር ይህን አያደርግም አሉት፡፡
.....ኑመይሪድን አይደለም ወገኖቼ እኔን በድላችሁኛል፡፡ ለአይጁር የማይገባውን እምነት አሸክማችሁት እናንተን እና አማልክቶቻችሁን በመርገም የማያዳግም እርምጃ ሊወስዱባችሁ ከሰዎች ጋር እየተመካከረላችሁ ነው አላቸው፡፡ በዚህ ስብስብ ውስጥ የጦር አዛዣቸውም ነበርና እስኪ እዛ የተፈፀመውን ነገር ንገረን አሉት፡፡
ኑመይሪድም ከአይጁር የሰማዉን እና ከዙል ቀርነይን የሰማውን በዝርዝር ነገራቸው፡፡
በዚን ጊዜ የጦር አዛዡም አመንካቸው አለው???
ኑመይሪድም፦በፍፁም አለ
የጦር አዛዡም ይህን ሚስጥር ለማንም እንዳታወራ በኔ እና ባንተ መካከል ይቅር የምንወስነውን እስክንወስን ድረስ በማለት ቃል አስገባው፡፡
የጦር አዛዡም ትላልቅ ባለስልጣናትን ብቻ ዝግ ስብሰባ በማድረግ አይጁር የሚስጥራችንን እውነታ እና ዘረ ቅይጦች የማን ዘሮች እንደሆኑ አውቆብናል፡፡ በሱ ማወቅ የተነሳ ሌላ ዘረቅይጦች እውነታውን እንዳያቁ ሰግቻለሁ፡፡ ይህን ጉዳይ ደግሞ በአሁን ጊዜ ከኑመይሪድ ሌላ ማንም አያውቅም፡፡ ኑመይሪድም ከርሰ ምድር ውስጥ ላሉት ዘረቅይጣውያን ሚስጥሩን፡እንዳያጋልጠው ሰግቻለሁ፡፡ ስለዚህም እኔ ዘንድ ጥሩ መፍትሄ አለ መፍትሄውም፦ወሬው ከነምንጩ እንዳይሰራጭ ኑመይሪድ ሊወገድ ሊገደል ይገባል በመቀጠልም ብዙ እና ጠንካራ ወታደሮችን የምድረ ገፅ ነዋሪያንን በለሊት ከከበብናቸው በኀላ ምድር ላይ ያለውን በሙሉ እንወርሳለን፡፡ በማለት ሀሳቡን አቀረበ፡፡

ባለስልጣናቱ በሙሉ በጦር አዛዣቸው ሀሳብ ከተስማሙ በኀላ የጦር አዛዡም ሰራተኛውን በመጥራት የኑመይሪድን ሰውነት በሰይፍ ቆራርጦ በሙታን ማከማቻ ክፍል እንዲያስገባ አዘዘዉ፡፡
ይሁን እንጂ ይህን ሴራ ኑመይሪድ.....

...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

25 Oct, 11:56


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ -ወመእጁጅ

         ክፍል  🔟

ዙል ቀርነይንም ይህን ድምፅ በሰማ ጊዜ ከቤተ መንግስት ወደ ዉጭ ወጣ
አይጁርም ይህን ጉዳይ ለኔው ተወው በማለት ወደ ውጭ ሊመለከት ወጣ፡፡ አይጁርን ከርቀት የተመለከቱት ዘረ ቅይጠጦቹ ያእጁጃውያንም ልክ አይጁርን ከርቀት እንዳዩት ወደ አይጁር መሄድ ጀመሩ፡፡
አይጁርም ምንም ከይነት ተንኳል ከመፈፀም ተቆጠቡ፡፡ ይኸዉ እኔ እንደምታዩኝ በጥሩ ሁኔታ ነው ያለሁት እኚህ ህዝቦች እኛ እንደጠረጠርናቸው ሳይሆን እጅግ ደጋግ ህዝቦች ናቸው፡፡ በሚገባ ተንከባክበውኝ ጥሩ ረፍትም አሳርፈውኛል፡፡

ወንድሞቼ ሆይ!!! እኛ ተታለናል ህዝቦቻችን እጅግ በድለውናል፡፡ በማለት ሁኔታውን ግልፅ ያደርግላቸው ጀመር፡፡ ዙል ቀርነይን በቅርብ ሆኖ ሁኔታውን እየተከላከለ ነው ሰዎች ከርቀት እያዩ ነው፡፡
ይህን የአይጁር ንግግር የሰሙትም ዘረ ቅይጦች አይጁር ምን ሁነሀል??? ምንስ አግኝተህ ነው፡፡ እንዲህ ማሰባያህን ያጣሀው ምን አግኝተህ ነውእንዲ ህዝቦችህን ልትረግም የደረስከው አሉት፡፡
አይጁርም፦ አዎ ምንኛ የተረገሙ ህዝቦች ናቸው በናንተ ቀኔ እና በመሰሎቻችን በፈፀሙት ተግባር አላህ ይርገማቸው፡፡ በማለት ንግግሩን ቀጠለና ከዙል ቀርነይን የሰማውን ታሪክ በሚገባ ተረከላቸው፡፡
በመቀጠልም አይጁር ጎደኞቹን ገለል ያለ ቦታ ወሰዶ ለማናገር ፈልጎ የሚከሰተውን ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ ዙል ቀርነይንን ባስፈቀደው መሰረተሰ ዙል ቀርነይንም ቤተ መንግስቴት እንዲገቡ ፈቅዶ ለአይጁር እና ጎደኞቹ እምነት እና መረጋጋት እንዲኖራቸዉ ምግብ እና መጠጥ አዘዘ፡፡
በዚህ ሁኔታም አይጁር ለጎደኞቹ ወገኖቻቸው ምን ያህል እንዳታለሏቸው ሰውነታቸውም እንዴት መቀየር እንደቻሉ እና ስለማያዉቁት ሚስጥር በአጠቃላይ ነገራቸው፡፡

የአይጁርም ጓደኞችም እንዲህ አይነት መረጃ አይጁር በማግኘቱ እጅግ ተደነቁ፡፡ ይሁን እንጂ በመካከላቸው ኑመይሪድ የተባለ አይጁርን የማይወድ ዘረ ቅይጥ ነበርና የአይጁር ንግግር ሊዋጥለት አልቻለም፡፡ (አይጁር የሚወዳትን ልጅ ኑመይሪድም ይወዳታል ስለዚህ ኑመይሪድ ደግሞ በቅናት አይጁርን አይወደውም፡፡)
ኑመይሪድም የአይጁርን ንግግር በሚገባ በመሸምደድ ለያእጁጃውያኑ ነግሮ ሊያስገድለዉ ወሰነና ሌሎቹ ዘረ ቅይጦች በአይጁር ንግግር ሙሉ በሙሉ ሲያምኑ ኑመይሪድ ግን ሸር አስቦ ዝም አለ፡፡
አይጁርም በንግግሩ መደምደሚያ ላይ፦ ወንድሞቼ እዚሁ ቀርተን ከደጋግ ወገኖቻችን ጎን በመቆም እነዚያን አመፀኛ እና ትዕቢተኛ ህዝቦችን ልንበቀል ይገባል አላቸው፡፡
ጓደኞቹም በአይጁር ንግግር ሙሉ በሙሉ ሲስማሙ ነገሩ ሁሉ ያልተመቸው ኑመይሪድ ግን ዝምታን መረጠ፡፡ ይህን የኑመይሪድ ዝምታ የተመለከተው አይጁርም፦ ምን ሁነሀል ኑመይሪድ!!! ከኛ እዚህ መቅረት አትፈልግም አለው?
ኑመይሪድም፦ከናንተ መቆየት እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ወደ የእጁጃውያኑ በመሄድ በኛ እዚህ መሆን ሌላ ነገር እንዳይጠረጥሩ በውሸት አስረድቻቸው መምጣት አለብኝ፡፡ ሲለው አይጁርም በኑመይሪድ ልብ ያለውን እርኩስነት በመረዳት ወደ ፈለገበት እንዲሄድ ዝም አለው፡፡
ዘረ ቅይጦች በዚህ ሁኔታ በመወያየት ላይ ሳሉ ድንገት ዙል ቀርነይን በያእጁጃውያኑ ቋንቋ፦ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን ብሎ ገባ፡፡
ሰላምታውን በመመለስ እና እንዴት የሰው ልጅ የኛን ቋንቋ ያወራል?? በማለት እጅግ ደነገጡ፡፡ይሁን እንጂ አይጁር ስለ ዙል ቀርነይን ወደር ያለፈ ደግነት በማውራት ጓደኞቹን ያረጋጋም ጀመር፡፡
በመሀል ዙል ቀርነይን አይጁርን በማቋረጥ አይጁር ሆይ ተወኝ እስቲ ስለ አላህ ጥቂት ላዉራላቸው በማለት ንግግሩን ጀመረ፡፡ በጥሩ ሁኔታ ስለሁሉም ክስተት ካስረዳቸው እና ስለ አላህም ከገለፀላቸው በኀላ ዘረ ቅይጦችን ወደ ህዝቦቹ ዘንድ በማውጣት፦ ህዝቦቼ ሆይ!!!እነዚህ ያእጁጃውያኑ ያታለሉብን ልጆቻችን ናቸው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሀን እንምራቸው ወይስ ጠመው እንዲቀሩ እንተዋቸው፡፡ በማለት ንግግሩን ጀመረ....

..ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

24 Oct, 03:52


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

         ክፍል  9⃣

ይህን ጊዜ አይጁር በመገረም ዙል ቀርነይንን እየተመለከተ፦ ስለ ህዝቦቼ የምታቀዉ አለ ሲል ጠየቀው???
ዙል ቀርነይንም ልጄ አንተ ከምታቀው በላይ ስለህዝቦችህ እኔ አውቃለው በማለት ንግግሩን ከጀመረ በኀላ ስለያእጁጃውያን በሚገባ በማስረዳት እናቱንም ከምድረ ገፅ ጠልፈዋት እሱን ዘረቅይጥ እንደወለደችና በመቀጠልም እንደገደሏት ነገረው፡፡
አይጁርም፦ በፍፁም አያደርጉትም ህዝቦቼ በእናቴ ላይ ይህን አያደርጉትም  አለው፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ ለምንድነው ቅርፅህ ከተቀሩት ያእጁጃውያን የሚለያየው በማለት ጠየቀው፡፡
አይጁርም፦ ህዝቦቻችን በኛ ዘመን የሰውነት ቅርፃችን እንዲስተካከል ለአማልክቶቻቸው እርድ  ፣ ቁርባን፣ ስለት እና የመሳሰሉትን አቅርበው ነበርና አማልክቶቹ ተቀብለው ነው ቅርፄን የተስተካከለው አለው፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ ልጄ ህዝቦችህ ዋሽተውሀል፡፡ ከፈለክ እኔ  ማረጋገጫ ልንገርህ፤ ህዝቦችህ  እሳትን ስትመለከት ራስህን ትስታለህ አላሉህም???በማለት ጠየቀው፡፡

አይጁርም አአዎ ብለውኛል ልክ ናቸውም እሳትን ባየሁ ጊዜ እራሴን ስቻለሁ አለ፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ በፍፁም !! ይህ ሊሆን የቻለው አንተ ከልጅነትህ ጀምሮ በዚያ ፍራቻ ታንፀህ ስላደክ ነው በማለት ነገረው፡፡
አይጁርም እንዴት በማለት ጠየቀ፡፡
በዚን ጊዜ ዙል፡ቀርነይንም ወታደሮቹን በመጣራት እሳት እንዲያመጡ አደረገ፡፡ አይጁርም እሳቱን ሲያይ መንቀጥቀጥ ጀመረ ከዛም ምንድነው ቆይ ልትገድለኝ ትፈልጋለህ በማለት ጮኸ፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ ልጄ አትፍራ ምንም አይጎዳህም፡፡ እሳት በእጅህ ካልነካሀው አያቃጥልህም፡፡፡ በድፍረት ወደ እሳቱ ተመልከት    ተመሳስሎብህ ነው እንጂ ምንም አይጎዳህም አለው፡፡
አይጁር ይህን ጊዜ በፍራቻ እሳቱንመመልከት ጀመረ፡፡ ይሁን እንጂ አይጁር እንዳሰበው መጥፎ ነገር አልተከሰተም፡፡
አይጁርምለዙል ቀርነይንን እባክህ ተወኝ ውጭ ልውጣና የሚሆነውን ልመልከት ወይም ግደለኝና ከዚ ጭንቅ ልገላገል አለው፡፡
ዙል ቀርነይንም፦በፍፁም ልጄ ምንም ነገር አልተከሰተብም እኔም ምንም አልሆንኩም  እሳቱም እየተቃጠለ ነው አለው በመቀጠልም ልጄ ከህዝቦችህም ቢሆን በአላህ ያላመፀናና ያመነ አላህንም ያመለከ ከእሳት ይድናል፡፡ ልጄ ሆይ አላህ አንዱ እና  ብቸኛው ሲሆን የሰው ልጆችንም እኩል አድርጎ ነው የፈጠራቸው፡፡በአላህ ፍራቻ እንጂ ማንም ከማንም አይበላለጥም፡፡

"የሰው ልጆች በሙሉ ጌታ በሆነው በአንዱ አላህ አምኛለሁ ፡፡ ከሱ ሌላ የሆነን አካል ከከርሰ ምድርመሸ ሆነ በገፀምድር የማመልከው የለም" በል የቃል ኪዳን ግባ በማለት ዳዕዋ አደረገለት፡፡
ይህን ንግግር አይጁር በሰማ ጊዜም በቀልቡ የራህመት ሰኪናን አላህ ረጨለት፡፡አይጁርም ንግግሩን ከሰማ በኀላ በዚህ ጉዳይ ትንሽ ላስብበት ትንሽ ሰዐት ብቻዬን ተወኝ አለው፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ አረፍ በል ልጄ ተመልሼ እመጣለሁ በማለት ትቶት ሄደ፡፡

ከዚያም አይጁር ብቻውን ሆኖ ከራሱ ጋር መነጋገር ጀመረ ህዝቦቼ እውነት ነው እኔን አታለውኛል!!!በዚህ ጠማማ እና ቀጣፊ ንግግራቸወሸ ስንቱንስ እንደኔ አጣመዉታል፡፡
እናቴን ጠለፏት ከወለደችላቸም በኀላ ገድለው ጣሏት፡፡ እኔ ደግሞ የእናቴን ጎሳዎች ልበቀል እዚህ መጣለሁ  ውይ ጥፋቴ!!!
ምኘው የዛሬዋን የጥፋት እና የፀፀት ቀን ሳላይ በሞትኩ በዚህ ሁኔታ አይጁር ራሰሱን በመውቀስ ላይ ሳለ ከወደ ውጭ በኩል ከፍተኛ ደሰዎቾ ጫጫታና ትርምስ ተሰማውና ባለበት ተረጋጋ፡፡
ዙል ቀርነይንም ይህን ድምፅ በሰማ ጊዜ  ከቤተ መንግስት...... ..

...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

23 Oct, 07:28


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

       ክፍል 8⃣

ለዙል ቀርነይን፦ አንተ ማነህ!!! እኔ የት ነዉ ያለሁት! እያለ ማዉራት ጀመረ።
ይሁን እንጂ ዙል ቀርነይን የአይጁርን ንግግር አይረዳምና በጥሩ ሁኔታ መሆኑን እንዲገነዘብ ብቻ እጁን በአይጁር ራስ በማሳረፍ አሻሸው፡፡

በመቀጠልም ዙል ቀርነይን ወታደሮቹን ለአይጁር ምግብ እናመጠጥ እንዲያቀርቡለት አዘዛቸው፡፡ አይጁርም የቀረበለትን ምግብ እየተመገበ ማን ነዉ ይሄ ሰዉ እንዲ ሚንከባከበኝ በማለት እያሰላሰለ የቀረበለትን ምግብ መመገብ ጀመረ፡፡
ምግቡን በልቶ እንዳጠናቀቀም ዙል ቀርነይን እንዲያርፍ በእጁ ካመላከተዉ በኀላ አይጁር አረፍ ሲል ዙል ቀርነይንም ከጎኑ ተቀመጠ፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉም በድንገት  ከቤተ መንግስት ሰዉ በመምጣት የሀገሩ ዑለማዎች  እንደመጡና የመግባት ፍቃድም እንደሚጠይቁ ነገረዉ፡፡ ይህን ጊዜ ዙል ቀርነይን አይጁርን እንዲተኛ በእጁ አመላክቶት ወደ እንግዶቹ በመሄድ የእንኳን  ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርጎላቸዉ ክስተቱን ከመጀመሪያዉ እስከ መጨረሻው ተረከላቸዉ የንጉሱ ገዳይ እና የያእጁጃዉያኑ ወጣትም እዚህ እንደሚገኝ አክሎ ነገራቸዉ፡፡
በመቀጠልም፦ ስለዚህ ፍጥረታት የምታዉቁት ነገር ምን አለ በማለት ጠየቃቸው፡፡
በመካከላቸዉም አንድ እጅግ በእድሜ የገፋና በእዉቀትም የበለፀጉ አዛዉንት  ነበሩና እንዲህ በማለት ንግግራቸዉን ቀጠሉ፡፡
አንተ መልካም ንጉስ ሆይ!! እነሱ የእጁጅ እና ማእጁጅ የሚባሉ ነገዶች ሲሆኑ እጅግ አላህን በማምለክ ጥሩ የአላህ ባሮች ነበሩ፡፡
በመሀከላቸዉም ያጁስ እና ማጁስ የተባሉ ከሀዲያን እና ድግምተኛ ወንድማማቾችም ነበሩ፡፡
ያጁስ የተባለው፦ድግምቱን ተጠቅሞ ህዝቦቹን ወደ ፀሀይ አምልኮ በመጥራት ለተከታዩችም ግዙፍ የሆነ ቤተ አምልኮ  ገንብቶ በኩፍር ጎዳና አንቧቧቸዉ፡፡
ማጁስ የተባለዉ ደግሞ  የወንድሙን መመለክ እና  በህዝቡ አንደበትም መቀደስን ሲመለከት ቅናት በልቡ አደረበትና የተቀሩትን ህዝቦች እሳትን እንዲያመልኩ ጥሪ

አዛዉንቱ ንግግራቸውን ቀጥለዋል፦ በዚህ ሁኔታ ከፊሎቹ የፀሀይ አምላኪ ሆነዉ ከፊሎቹ የእሳት አምላኪ ሲሆኑ የተቀሩት ጥቂቶቹ ደግሞ በኢማናቸዉ ላይ ፀኑ፡፡
የነዚህ በኢማን መፅናት እረፍት የነሳቸዉ ያጁሳዉያን እና ማጁሳውያን አንድ ላይ በመተባበር በሙእሚኖቹ የድግምት ናዳዎችን ያዘንቡባቸዉ ጀመር፡፡ ይሁን እንጂ ሙእሚኖቹ የድግምቱ መደጋገም ከኢማናቸዉ ፍንክች አላደረጋቸዉም ነበር፡፡
በመጨረሻም የሙእሚኖቹን ልጆች በወላጆቻቸው ፊት እያረዱ ወደ ኩፍር ቢያስገድዷቸዉም እምነታቸዉ ይበልጥ መጠንከር ሲጀምር በዘመኑ የነበሩትን ሙእሚኖች ባጠቃላይ በእሳት አቃጥለዉ ደመሰሷቸዉ በማለት ሽማግሌዉ ንግግራቸዉን  ሳይጨርሱም ዙል ቀርነይንም፦ ከዚያስ ምን ተከሰተ? በማለት ጠየቃቸዉ፡፡
እሳቸዉም፦ "ከዚያማ አላህ የእርግማንን አይነት ካወረደባቸዉ በኀላ ከሰዉ ዘር ባጠቃላይ የተገለሉ በማድረግ ጨለማን መቀመጫቸዉ....እሳትን ደግሞ መደንበሪያቸዉ ......ሰውነታቸው ደግሞ ቅርፅ አልባ አድርጎ ፀሀይ ሰውነታቸዉን ቀነካ ቁጥር እንዲያቃጥላቸዉ ወሰነባቸው፡፡ በማለት ነገሩት
ዙል ቀርነይንም ግራ በመጋባት፦እንዴት ይህ ሊሆን ይችላል? በሰሞኑ እኮ 10-11የሚሆኑት ወደ ምድር ወጥተዉ ከኛም ተቀላቅለው ነበር፡፡ ግን ፀሀይ ሲያቃጥላቸው አላየንም ሲል ጥያቄ አቀረበ?
አዛውንቱም ይህማ በጭራሽ አይሆሆንም፡፡ እስቲ እናንተ ዘንድ ያገታችሁትን ወጣት አይጁር አሳዩኝ ብለው ጠየቁ፡፡
ከዚያም ዙል ቀርነይን እና አዛውንቱ ወደ አይጁር ክፍል ሄዱ፡፡ በእንቅልፍ ላይ ያለዉን አይጁርን ሲመለከቱት ይህ እንኳን ያእጁጃዊ አይደለም፡፡ ግን ዘረ ቅይጥ ነው አሉ፡፡
ዙል ቀርነይን ይሄ ወጣት የተያዘ እለት ሰዎች ይዘው በወጡት የጧፍ ብርሀን ምክንያት እራሱን ስቶ ነበር አላቸው፡፡
አዛውንቱም አይ ተመሳስሎበት ነው፡፡ ያእጁጃዉያኑ በብርሀን ሲያስፈራሩት ሴላደጉ ነው፡፡ አሉት
ዙል ቀርነይንም ገባኝ ግን ቋንቋቸው ሊገባኝ አልቻለም አላቸው፡፡
አዛውንቱም እኔ ስለማቀው አስተምርሀለው አሉት፡፡
በመቀጠልም ዙል ቀርነይን ወደተቀሩት ኡለማዎች ዘንድ በመሄድ የሚከተለውን ጊዜያዊ አዋጅ አፀደቀ፡፡
1.እነዚየያን ሰዎች ለምንም  አይነት ፀብ አንጋብዛቸውም ምክንያቱም በብልሀት ሆነ በጉልበት ከኛ ይበልጣሉና፡፡
2.ከክህደታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማድረግ፦ ጥሪያችንን ካልተቀበሉ ውሳኔው የኛ ይሆናል፡፡ በማለት ትዕዛዙን ካስተላለፈ በኀላ የመጡት ኡለማኦች ተስማምተው፦ ይህ ጉዳይ መቋጫውን ሳያገኝ ወደ ሀገሮቻችን አንመለስም አሉ፡፡
ዙል ቀርነይንም በመቆየታቸው የተሰማውን ደስታ ገሐፆላቸው ለሦስት ቀናት ግን ከአዛውንቱ ማሳለፍ እንደሚፈልጉ ነግሯቸው ቋንቋቸውን ለመማር ከአዛውንቱ ጋር ሆነ፡፡ 
አይጁር በክፍሉ ሆኖ ሳለ በወታደሮቹ በሚመጣለት ምግብ እና መጠጥ በጣም በመገረም ለምንድነው እነዚን ህዝቦች ያለ ምክንያት የምጠላቸው???
እነዚ ህዝቦች መጥፎ ቢሆኑ እኮ ለንጉሳቸው በቀል ሲሉ ጭንቅላቴን ይቆርጡት ነበር፡፡
ስለዚህ
ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት ቀጥልቀት ማሰብ ይኖርብኛል በማለት ከራሱ ጋር አወራ፡፡
ዙል ቀርነይንም ለተከታታይ ቀናት ቋንቋቸውን በሚገባ ከአዛውንቱ ከተማሩ በኀላ አይጀጁር የተኛበት ክፍል በመግባት አይጁርን በተማረው ቋንቋ ሰላም ባንተ ላይ ይሁን አለው፡፡
አይጁርም በድንጋጤ ዙል ቀርነይንን እያየ፦ ይህ ያእጁጃዊ ነዉ ወይስ አይደለም፡፡ በማለት እያሰበ ሰላምታውን መለሰለት፡፡
ዙል ቀርነይንም፦ ልጄ ሆይ ከአላህ ሌላ ማን አለ?እሱ እኮ አንዱ እና ብቸኛው ነው፡፡ ወገኖችህም እኮ አላህን በብቸኝነት አምላኪ ነበሩ፤ በመጨረሻም የማይጠቅምን ነገር አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ አለው
ይህን ጊዜ አይጁር በመገረም ዙል ቀርነይንን እየተመለከተ፦ስለ ህዝቦቼ ምታቀው አለ ሲል  ጠየቀው፡፡

.....ይቀጥላል
...

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

22 Oct, 18:07


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የእጁጅ - ወመእጁጅ

      ክፍል 7⃣

አይጁር እዚያዉ ተወልዶ ባደገበት ጉድጓዳዊት መንደር ላይ ከልጅነቱ አንስቶ እስከ ወጣትነቱ የሚወዳት እና የምትወደዉ አንዲት እንስት አለች፡፡
ዛሬ ግን ለተልዕኮዉ ማሳኪያ ራሱን መስዋት አድርጎ ሊወጣ ስለሆነ የሷ ነገር አልሆን ብሎት ሊሰናበታት ሄደ፡፡

የመለያየት እንባ በፊቱ እያሳያት ልጅቶን ሲሰናበታት ምንም እንኳን ትቷት እንዳይሄድ ብትለምነዉም አለመመለሱን አረጋግጦ ግን እንደሚመለስ ቃል ገብቶላት የከርሰ ምድሩን ትቶ ወደ ምድር መጡ፡፡
ልክ ወደ ገፀ-ምድር ብቅእንዳሉም እንደቀደመዉ ጊዜ ሰዐት ማባከን አልፈለጉምና በፍጥነት ወደ ንጉሱ ቤተ-መንግስት በማቅናት የአጭር ሰዓት ስለላ ካደረጉ በኀላ በመግቢያው የሚያገኙትን የቤተ-መንግስቱን ጥበቃዎች ቀለል ባለ መልኩ እየገደሉ በማለፍ በጥቂት ሰዐታት ንጉሱ ዘንድ ደረሱ፡፡
ል ክ ንጉሱ ዘንድ እንደገቡም አይጁር በቀል በጠማው እጁ ንጉሱን በሀይል በመምታት ራሱን  እንዲስት ኬደረገው በኀላም ንጉሱን ተሸክመዉት ከከተማዉ በማዉጣት በከተማዉ መግቢያ ላይ አንገቱን በመቁረጥ አንጠለጠሉት፡፡
የንጉሱን አንገት በከተማዉ መግቢያ ላይ ካንጠለጠሉ በኀላ የተቀረዉን የሰዉነት ክፍሉን ተሸክመዉ በመጓዝ ላይ ሳሉ በድንገት አንዲት አሮጊት አየቻቸውና ሰፈሩን በጩኸት አናጋችው፡፡
ይህን ጩኸት የሰማዉም የመንደሩ ነዋሪ በሙሉ ከየቤቱ ይዞ  የወጣው እንደ ጧፍ ያለ እሳትም አከባቢዉን በማሸብረቅ የያእጁጃዉያንን ሁኔታ ቀያየረው፡፡
በዚህ ሁኔታአይጁር ከዙሪያው ያለዉን ብርሃን መቋቋም ሲያቅተው  እራሱን በመሳት መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ጓደኞቹ ምንም እንኳን ሊያነሱት ቢጣጣሩም ባለመቻላቸው የንጉሱን ቅሪት ስጋ ተሸክመዉ አይጁርን በማያውቀው መንደር ትተው ሸሹ፡፡
የከተማይቱ ህዝብ እጅግ ተሰበሰበ፡፡
ሊገድሉትም አስበው ተዘጋጁ በመሀል አንዱ ሰውዬ፦ከምንገድለዉ ዙል ቀርነይን ዘንድ እንዉሰደዉ በማለት ተናገረ
ዙል ቀርነይን አይቶት የማያውቀውን ፍጡጡር በሰው ታጅቦ ቤቱ ሲገባለት፦ማን ነዉ ይህ ሰዉ በማለት ጠየቀ፡፡  ህዝቡም ከያእጁጃዉያን  አንዱ እንደሆነና መሬት ላይ ወድቆ እንዳገኙትም አክለዉ ነገሩት፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉም ድንገት ከወደ ውጭ በኩል "ንጉስ ሞተ "የሚል ጩኸት ተሰማ፡፡ ህዝቡም እጅግከመረበሹ አይጁር ነው የገደለዉ እሱንም ካልገደልን ብሎ ተነሳ፡፡
ይህን ጊዜ ዙል ቀርነይንም ብልህ ነበረና አይ መገደል የለበትም ምን አልባት ለስለላ ይጠቅመናል በማለት አሳመናቸው፡፡
የየክልሉ አስተዳዳሪዎችም ለነዋሪዎቻቸው የንጉሱን መሞት አወጁ፡፡ ህዝቡም ያለ ንጉሱ መቆየት እንደማይፈልግ በመግለፅ ዙል ቀርነይንን ንጉስ አድርገው ሾሙት፡፡
ህዝቡም ተሰብስቧ ዙል ቀርነይን ተሸክመው ወደ ቤተ መንግስት  በማስገባት በንግስና ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡
ዙል ቀርነይንም ልክ ዙፋኑ ላይ እንዳረፈም አይጁርን እንዲያቀርበቡት አዘዘ፡፡ የቤተ መንግስቱ ወታደሮችም ዙል ቀርነይንም ቤት ተጋድሞ የነበረዉን አይጁርን በማምጣት ባተ መንግስት ዉስጥ ካስገቡት በኀላ ቀዙል ቀርነይን ትዕዛዝ በአንድ ክፍል በማስገባት በጠንካራ ቁልፍ ቆልፈውበት ትተዉት ወጡ፡፡

በመቀጠልም ዙል ቀርነይን አይጁር ወዳለበት ክፍል በመግባት ወታደሮቹ የህክምና መሳሪያዎች እንዲያመጡለት ካደረገ በኀላ ማንም ያለሱ ፍቃድ ወደ ክፍሉ ዘልቆ እንዳይገባ አስጠንቅቆ ገብቶ በሩን ዘጋው፡፡
ወታደሮቹም:-ንጉስ ሆይ እንዳይተናኳልህ እንሰጋለን ሲሉት ፤ ዙል ቀርነይንም አላህ አብሮኝ ነዉና በሱ እመካለው አላቸው፡፡
ዙል ቀርነይንም እራሱን ከሳተዉ አይጁር ጎን በመቀመጥ ቁስለቱ ላይ መድሀኒት ሲያደርግለት የመድሃኒቱ ስሜት አይጁርን አነቃው፡፡ አይጁር ነቅቶ በድካም የዛለውን ራሱን አዟዙሮ ያለበት ሲያይ የድንጋጤ ስሜት እንዳይሰማው ዙል ቀርነይን እጁን በአይጁር ራስ ላይ በማሳረፍ እና ዉሀ በእጁ አድርጎ በማጠጣት አረጋጋው፡፡
አይጁርም ራሱን ካረጋጋ በኀላ ለዙል ቀርነይን፦ አንተ ማነህ  እኔ የት ነዉ ያለሁት እያለ ማዉራት ጀመረ፡፡

...ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

21 Oct, 04:11


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

         ክፍል6⃣

የያእጁጃውያኑ ንጉስም እነ አይጁርን ሲመለከት.........

አይጁር እና ግብራበሮቹ ወደኀላ እና ወደ ፊት እያዩ ጉድጓዱን ዘልቀው ከገቡ በኀላ ህዝቦቻቸዉን በጉጉት ፊቶቻቸው ቀልቶ አገኟቸው፡፡
ያእጁጃዉያን ንጉስም እነ አይጁርን ሲመለከት ወደነሱ በመንደርደር ስለክስተቱ ጠየቃቸው፡፡
ዘረ ቅይጦቹም የተከሰተውን በዝርዝር ተርከውለት የሳዱንንም መገደል አክለዉ ነገሩት፡፡ ይህን ግዜ ንጉሱ በንዴት አይኖቹ ደም መሰሉ፡፡
ከትላልቅ የጦር አዛዦች እና ባለስልጣናት መመካከር አለብኝ ብሎ አንድ ስብሰባ በማዘጋጀት ሁሉንም ባለስልጣናት ጠራቸው፡፡ ሁኔታዉን በሰሙ ጊዜም በንዴት እና በዛቻ ስብሰባውን በማወክ የሰው ዘሮችን ለመበቀል ቀን ቆርጠወሸ ስብሰባውን አጠናቀቁ፡፡
ይሁን እንጂ እነሱ በጉልበታዊ ሴራቸዉ ሲመፃደቁ እና እርስ በርስ ሰዉ ልጆች ላይ ሲዛዛቱ የሰዉ ልጆች ተወካይ የሆነዉ ዙል ቀርነይን ግን የሁኔታዉ ነገር አሳስቦት አላህን መማፀን ጀመረ፡፡
ዙል ቀርነይነ ምን ማድረግ እንዳለበት ብዙ ካሰላሰለ በኀላም በምዕናቡ አንድ ነገር ብልጭ አለለት፡፡
ከነዚህ ያእጁጃውያን ጋር በግልፅ ተወያይተን በመሀከላችን ያለዉን ችግር አንፈታም !!!በአላህ ላይ የሚያጋሩትን አቁመው ወደ አላህ አምልኮ እንዲዞሩ ማናደርጋቸው፡፡

ይሄ ሀሳብ ዙል ቀርነይንን ማረከው
ንጉሱ ዘንድ በመሄድ ለመወያየት ወስኖ አደረ፡፡
አይነጋ የለምና ልክ ሌሊቱ ነግቶ ጎህ ሲቀድ ዙል ቀርነይን ከቤቱ ወጥቶ ወደ ቤተ-መንግስት አመራ፡፡

ዙል ቀርነይንም  ንጉሱ ጋር ሲደርስ ቆም በማለት ንጉስ ሆይ እነዚህን ፍጡሮች ቀድመን ለምን አናወያያቸዉም? ?ምናልባትም ከክህደታቸዉና ኤና ከአመፃቸዉ ሊመለሱ ይችላሉ"" ሲል አማከረዉ፡፡
ንጉሱም-ዙል ቀርነይን ሆይ ከንደዚህ አይነት ፍጥረታት ጋር ውይይት ማድረግ መፍትሄ ያመጣል ብለህ ታስባለህ ብሎ ጠየቀው?
ዙል ቀርነይንም አዎን ንጉስ ይህን ነገር ለኔ ተወዉ፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር እንድታደርግልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ምታደርግልኝም በሁሉም አገር ያሉ ዑለሞች እንዲሰበሰቡና ከነሱ ጋርም ሰፋ ያለ ዉይይት ማድረግ አለብኝ፡፡ ስለዚህ ሁሉንም ዑለሞች ሰብስብልኝ አለው፡፡
ንጉሱም በዙል ቀርነይን ሀሳብ በመስማማት በየሀገሩ ያሉ አስተዳዳሪዎች ጋ የሀገራቸዉነሸ ዑለማ እንዲልኩ እና ስለ ጉዳዩም በመናገር በአስቸኳየይ እንዲቀርቡ ደብዳቤውን ላከ፡፡

ዙል ቀርነይን እና ንጉሱ ምንም እንኳን በጠላቶቻቸዉ መሀከል ያለዉን ችግር ለመፍታት በመሯሯጥ ላይ  ቢሆኑመሰ ከከርሰ ምድር በስተ ጀርባ ግን  ሴራ እየተሸረበ ነበር፡፡
አይጁር ኤና ሁለቱ ጓደኞቹ አንድ ሰይጣናዊ እቅድ በመንደፍ ለእቅዱ ማስፈፀሚያ ይሆን ዘንድ እና ለሴራዉ መጀመሪያም እንዲሆን በመጀመሪያ የንጉሱን አንገት በመቀንጠስ በከተማይቱ መግቢያ ላይ ለማንጠልጠል ወደ ምድር ለመዉጣት ተስማሙ፡፡አይጁር እዚያዉ ተወልዶ ባደገበት ጉድጓዳዊት መንደር ላይ ከልጅነቱ አንስቶ እስከ ወጣትነቱ የሚወዳት እና የምትወደዉ አንዲት እንስት አለች፡፡
ዛሬ ግን ለተልዕኮዉ ማሳኪያ ራሱን መስዋት አድርጎ ሊወጣ ስለሆነ የሷ ነገር አልሆን ብሎት ሊሰናበታት ሄደ፡፡

.....ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

20 Oct, 03:51


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

         ክፍል 5⃣

አጥንቱን ሰብሰብ በማድረግ የሰው ዘርን በበቀል እና በጥላቻ እየተመለከቱ ሸሹ፡፡ ከሞት የተረፉትም ወታደሮች ንጉሱ ዘንድ በመሄድ የተከሰተውን ነገሩት ንጉሱም በንዴት ይህ ጉዳይ ዙል ቀርነይን አውቆል አላቸው!!! ወታደሩም፦ አልሰማም ጌታዬ አለው፡፡ ንጉሱም ፀሀፊውን በማስጠራት ለአስቸኳይ ጉዳይ  በፍጥነት እንዲመጣ ለዙል ቀርነይን  ደብዳቤ እንዲፅፍ ነገረው፡፡
ዙል ቀርነይን እጅግ አላህን የሚፈራ ባሮችም ነበር፡፡ ዙል ቀርነይን አላህ በሰጠው ችሎታ በተለያዩ ሀገራዊ  ጉዳዩች ላይ ጣልቃ በመግባት የማበጀትም ልምድ አለው፡፡ የንጉሱን ደብዳቤ የያዘውም ወታደር በፍጥነት ወደ ዙል ቀርነይን ቤት ሄዶ ሲመለከት የዙል ቀርነይን በር በከተማው ነዋሪ ተሞልቶ በተመለከቱት ክስተት ምክንያት ጩኸት እና ጋጋት አናውጦት አገኘው፡፡ ወታደሩም ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ከንጉሱ ያመጣውን ደብዳቤ ለዙል ቀርነይን አስረከበ፡፡ ዙል ቀርነይንም ደብዳቤውን ካነበበ በኀላ ወደ ህዝቡ በመውጣት እናንተ ሰዎች ሆይ አሁን የተመለከታችኀቸው ሰዎች ያእጁጅ እና መእጁጅ ሲሆኑ በድሮ ዘመን ምድርን በብክለት አበላሽተውትም ነበር፡፡ ስለዚህ እናንተ ውስጣቹ በኢማን ይሞላ ብለው መከሮቸው፡፡ በኢማን መተሳሰርና በአላህ መመካት እጅግ ሀይልን ይሰጣልና፡፡ ክህደት በልባችሁ እንዳይገባ ያለፉት ህዝቦች እንደጠፉት እናንተም እስከ መጨረሻችሁ እንዳትጠፉ አላቸው፡፡ በበሩ የተሰበሰቡትም የከተማው ነዋሪ ይህንን የዙል ቀርነይን ንግግር ሲሰሙ ኢማን በልባቸው ላይ ሰከነ፡፡
ዙል ቀርነይንም ንጉሱ ዘንድ ሄደ አይጁር እና ጓደኞቹም ንጉሳቸውን ለማግኘትም ክስተቱን ለመንገርም ወደ ከርሰ ምድር ገቡ 

ዙል ቀርነይንም ቤተ መንግስት እንደገባ ስለሁኔታው ጠየቀው፡ ዙል ቀርነይንም እነዚህ ፍጥረታት ስላሳለፉት ታሪክ ነግሮት የትኛውም ነብይ ስለነሱ ሳያነሳ እንደማያልፍም ጨምሮ ነገረው፡፡ በዚን ጊዜ ንጉሱም፦ አንተ ዓሊም ሆይ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል ሲል አማከረው፡፡ ዙል ቀርነይንም፦   ትንሽ ቀን ስጠኝ ላስብበት አለው፡፡ ንጉሱም ጉዳዩ አስቸኳይ ነው 3 ቀን ሰጥቼሀለው አስብና መልሱን በፍጥነት አሳውቀኝ ህዝቡ እንደሆነ ፍራት ላይ ነው ብለው ተለያዩ፡፡ ዙል ቀርነይንም ቤቱ በመሄድ አላህን እየሰገደዱዓ እያደረገ ይህን ክስተት ከህዝቡ ላይ እንዲያነሳ ይማፀነው ጀመር፡፡

አይጁር እና  ግብራ በሮቹ ወደኀላ እና ወደ ፊት እያዩ ጉድጓዱን ዘልቀው ከገቡ በኀላ ህዝቦቻቸው በጉጉት ሲጠብቆቸው አገኟቸው፡፡ የያእጁጃውያኑ ንጉስም እነ አይጁርን ስመለከት.........

.....ይቀጥላል
.....

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

19 Oct, 04:00


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

   የእጁጅ - ወመእጁጅ

             ክፍል 4⃣

      የባሪያ ነጋዴውም በፈረሰኛው ሀሳብ ተስማምቶ የዘረ ቅይጥ ወጣቶቹን ሂሳብ ለፈረሰኛው ከፍሎ ወደ ባሪያዎቹ አቀላቀላቸው፡፡
በመቀጠልም ወደ ሽያጭ ቦታ ሁሉንም በመውሰድ ላይ ሳለ ድንገት ዞር ሲል ከያእጁጃውያኑ አንዱ የውሻ ስጋ ሲበላ አየው፡፡ እጅግ በመደናገጥ፦ አንተ ሰው ምን እያደረክ ነው ምንስ እየበላህ ነው ብሎ ጠየቀው፡፡ ግን ያእጁጃውያኑ ምንም አይነት መልስ ሳይሰጠው በእጁ የያዘውን ስጋ እየበላ መጓዝ ቀጠለ፡፡ ነጋዴውም ቢያናግራቸውም መልስ ሲያጣ(ያልመለሱለትም የነሱ ቋንቋ ስለሚለያይ ነበር)፡፡ ይህን ሁኔታቸውን ሲያይ ፈረሸኛው ሸውዶኛል ዱዳ እና መስማት የተሳናቸውን ነው የሸጠልኝ ስለዚህ እሱም ሌላ ሰውን ሸውዶ በርካሽም ቢሆን ለመሸጥ ወሰነ፡፡ በመቀጠልም ይህ ነጋዴ ዘረ ቅይጦችን ለገበያ አውጥቶ ገዢ እየተጣራ ሳለ ከነዚህ መሀከል ሳዱን የተባለውን ዘረ ቅይጥ የሚገዛ ሸማች መጣና ሂሳቡን ከፍሎ ነጥሎ ሊወስድ ሲል እንቢ አለ፡፡ ይህን ጊዜ የገዢው አገልጋዩች በጉልበት ሊወስዱት ሲል ዘረ ቅይጦቹ ጣልቃ በመግባት መሄድ እንደማይችል በተግባር አሳዩቸው፡፡ የባሪያ ነጋዴውም፦ ምን እዪደረጋችሁ ነው ምን ሆናችሆል በማለት አንቧረቀባቸው፡፡ የነጋዴው ጩኸት ያናደደውም ሳዱን ነጋዴውን በሀይል አንዴ ጭንቅላቱን ሲመታው በቅፅበት ወድቆ ሞተ፡፡ ገበያውም እጅግ ታወከ ተረበሸ ከቤተ መንግስት አንድ ወታደር መቶ ሳዱንን ለመውሰድ ሲሞክር ሊንቀሳቀስ አልቻለምና ሌላ ሀይል ከቤተ መንግስት ለማስመጣት ተገደደ፡፡ አይጁር ሳዱንን ባደረገው ነገር ክፉኛ ተበሳጭቶል ፡፡ ምክንያቱም ሚስጥራቸው ሊደረስባቸው ይችላልና፡፡ በሳዱን እጅም ካቴና አስገብተው ይዘዉት ሄዱ፡፡ የባሪያ ነጋዴው ቢሞትም እንኳን ባሪያዎቹን የሚቆጣጠር ነበርና የተቀሩት እንዳይሄዱ ከለከሏቸው፡፡ ይሁን እንጂ ሸሽተው ሳዱንን በመከተል ሄደው ከአይናቸው እስኪሰወር ድረስ ይከታተሉት ነበር፡፡ ወታደሮቹም ሳዱንን ንጉሱ ዘንድ  አቅርበውት የሆነውን ነገሩት

ንጉሱም ስሙን ከየት እንደመጣ ደጋግሞ ቢጠይቀዉም ከንቀት ውጭ መልስ አልሰጠውም ንጉሱም ተናዶ ከቤተ መንግስት ውጭ ህዝብ እያየ አንገቱ እንዲቆረጥ ወሰነ፡፡ ወታደሮቹም ትዕዛዙን ለመፈፀም የሳዱንን አንገት በሰይፍ ሰነዘሩበት ዬሁን እነንጂ ከጭረት እና ጥቁር ደም ከመፍሰስ ውጭ ምንም አልተጎዳም ነበር፡ ይህን የተመለከተው ወታደርም በድንጋጤ በሀይል ድጋሚ ሰነዘረ፡፡ በዚህ ምት አንገቱ ባይቀነጠስም ነፍሱ ግን ከአካሉ ተቀነጠሰች ሳዱንም ወደቀ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አይጁር እና ግብራበሮቹ እየተመለከቱ  ነበር፡፡ በመጨረሻም ከመሀከላቸው አንዱ ፈንጠር ብሎ በመሄድ ሳዱንን ወደ ገደለው ወታደር በመሄድ በእጁ አንገቱን ይዞ ቀነጠሰው፡፡ ይህን ሲመለከቱ  የአካባቢው ሰዎች እና ወታደሮች መሸሽ ጀመሩ፡፡ ሁሉም ሲሸሹ ዘረ ቅይጦቹ ወደ ጓደኛቸው ሬሳ በመሄድ ስጋውን በመብላት ሀዘናቸውን ይገልፁ ጀመር፡፡ ያእጁጃውያኑም የጓደኛቸውን ስጋ በልተው እንዳጠናቀቁም አጥንቱን ሰብስበው ....

      ----ይቀጥላል
---

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

18 Oct, 03:01


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

     የእጁጅ _ ወመእጁጅ

            ክፍል 3⃣

አስራአንዱ ዘረ ቅይጦችም አይጁርን በማስቀደም ለረጅም አመታት በከርሰ ምድር ታጉረው የነበሩት ፍጥረታት ለመጀመሪያ ጊዜ ከከርሰ ምድር ወደ ገፀ ምድር ብቅ አሉ ።
ልክ ከምድር ወጥተው የመጀመሪያ እይታቸውን ወደ ፍጥረተ አለሙ ሲያደርጉ ሁሉም በግርምት ተዋጡ። አዲስአለም...፤ንፁህ አየር የምትሞቅ  ፀሀይ ወ.ዘ.ተ ይህ ሁሉ በግርምት ማዕበል ውስጥ አቁሞ አዋለላቸው። ምክንያቱም ምድር ውስጥ ተወልደው ምድር ውስጥ ያደጉ ፍጥረታት ናቸው እና ይህ አለም ለነሱ ድንቅ እና አዲስ ነው።
በማያውቁት አለም ላይ ድንገት መከሰታቸው በአግራሞት መስጧቸው እርስ በርስ ማውራታቸውን ትተው ዙሪያቸውን ግራ በመጋባት መልኩ ይቃኛሉ። ከዚያም ወደ ሰዎች መንደር ጉዞ ጀመሩ። በጉዞዋቸው ላይም ሰዎችን ሲመለከቱ በንቀት እና እጅግ በጥላቻ በተሞላ መልኩ ይመለከቷቸዋል።
ምክንያቱም እነዚህ ዘረ ቅይጥ ወጣቶቹ ከቅድመ አያቶቻቸው አንስቶ እየሰሙ ያደጉት የሰው ዘር ባጠቃላይ ለነሱ ጠላቶች እንደሆኑ ነውእንጂ በእናቶቻቸው ሰው መሆናቸውን አያውቁም ነበር።
ይህን ሁኔታቸውን የተመለከተው ብልሁ አይጁርም አብረውት ላሉት ዘረ ቅይጥ ወጣቶች፦"ወገኖቼ ሆይ እነዚህ በላይኛው ምድር የሚኖሩት የሰው ዘሮች ለኛ እጅግ ጠላቶቻችን መሆናቸውን ታውቃላችሁ።
ማንነታችንን ካወቁ ተራ በተራ ነው የሚቆራርጡን ፤ስለዚህም ማንነታችሁ ላይ እጅግ ተጠንቀቁ። በውስጣችሁ ያለውን ጥላቻ ግልፅ አታሳይዋቸው ። እኛ ላይ ሀላፊነት የጣሉ እና የኛን መልስ በጉጉት የሚጠብቁ ህዝቦች አሉና በብልሀት እንንቀሳቀስ"በማለት ምክር ሰጣቸው።
አይጁር በትኩረት ወደ ሰው ልጆች አለባበስ እና ቋንቋ ሲመለከት ካደገበት ቋንቋ እና የአለባበስ ወግ እጅግ ይለያያል'ና፤ እራሱ እና አብረውት ያሉ ወጣቶችን እንደ ዱዳ ሁነዉ ወደ ህዝቡ ለመቀላቀል ወሰነ።
ይህን ሀሳብ ለጓደኞቹ አቅርቦ በማስማማት በምን መልኩ ወደ ከተማ ገብተው ከሰው ዘሮች መቀላቀል እንዳለባቸው ሲወያዩ ድንገት በአቅራቢያ ከሚገኘው ተራራ በኩል አዋራ እያስነሳ ወደነሱ የሚቀርብ እንግዳ ነገረ ተመለከቱ።
ይሁን እንጂ የሰው ልጆች ነበሩና ወደ ዘረ-ቅይጦች መጠጋት ጀመሩ።ይህን ግዜ አይጁር እና ግብራበሮች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወደቁ። የሰው ዘሮች  ሚስጥራቸውን አውቀውባቸው ሊያጠፏቸው እንደሚመጡም በመገመት ክስተቱትን በትዕግስት መከታተል ጀመሩ።ፈረሰኞቹ(የሰው ዘሮችም) በፍጥነት ወደ ዘረ ቅይጦቹ ወጣቶች  በመድረስ እነማን ናችሁ ፡፡፡፡ከየትነው ወደየት ነው ወ.ዘ..ተ አሏቸው
ይሁን እንጂ የፈረሰኞቹ ንግግር ለዘረ ቅይጦቹ ምንም ማይገባቸው ቋንቋ ነውና ዝምታን መልስ አደረጉላቸው። ፈረሰኞቹ በተደጋጋሚ ጥያቄውን ቢያቀርቡላቸውም ያእጁጃውያን  ሊመልሱላቸው ባለመቻላቸው ከፈረሰኞቹ ዋናቸው የሆነው ያእጁጃውያኑ እንዲገደሉ አዘዘ። (ያእጁጃውያን መሆናቸውን ማንም አያውቅም)  ይህን ጊዜ ከፈረሰኞቹ አንደኛው ለአዛዡ አለቃቸው "ከምንገላቸው ወደ ባሪያ ገበያ አውጥተን  እንሽጣቸው" በማለት ሹክ አለው።
አዛዡም በጓደኛው ሀሳብ ተስማምቶ  ወደ ባሪያ ገበያ ያእጁጃዉያኑን ይዘው ጉዞ ጀመሩ። ወደ ገበያው እንደ ደረሱም የፈረሰኞቹ አዛዥም የባሪያ ነጋዴዎችን በማስጠራት ለሽያጭ ያዘጋጃቸውን (ዘረ ቅይጥ) ወጣቶች አቀረበላቸው።
የባሪያ ነጋዴውም በግርምት ወጣቶቹን እየተመለከተ እና በተክለ ሰውነታቸው እየተገረመ፦ ከየት ነው ያመጣሀቸው? የየት
ሀገር ነዋሪ ናቸው በማለት አዛዡን ፈረሰኛ ጠየቀው፡፡
የፈረሰኞቹ አዛዥም በቁጣ" ከየትም ይምጡ ከየት አንተ አይመለከትህም፡፡ ትገዛለህ ወይስ ለሌላ ልሽጣቸው አለው።
የባሪያ ነጋዴውም በፈረሰኛው ሀሳብ ተስማምቶ የዘረ ቅይጥ ወጣቶቹን ሂሳብ ከፍሎ ወደ ባሪያዎቹ አቀላቀላቸው ፡፡በመቀጠልም ይህ የባሪያ ነጋዴ ዘረ ቅይጦቹን  ለገበያ አውጥቶ ገዢ እየተጣራ ሳለ ከነዚህ ዘረ ቅይጦች አንደኛውን ነጥሎ የሚገዛ ሸማችመጣና ሂሳቡን ከፍሎ ነጥሎ ልወስድ ሲል............

  ------ይቀጥላል
------


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

17 Oct, 04:38


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

       ያእጁጅ - ወማእጁጅ

        ክፍል 2⃣

  ይህን ጊዜ ትላልቅ የያእጁጆች የጎሳ መሪዎች ሰብሰብ በማለት ከምድር ታች ብርሃን በማይኖርበት ሰዎች በማይደርሱበት የራሳቸውን ከተማ ለመመስረት ተስማሙ፡፡
በመጨረሻም ምድርን እየሰነጠቁ በመግባት እና ከተማዎቻቸውን በመቆርቆር የተደራጀ የጦር ሰራዊትንም አቋቁመው አፄዎችንም ሾሙ።
እነዚህ የያእጁጅ ነገዶችም ከመሬት ውስጥ ያለውን የፅልመት ህይወታቸውን ለረጅም አመታት ከገፉ በኀላ ከእለታት አንድ ቀን ለአንድ ትልቅ ጉዳይ ንጉሳቸው ዘንድ ባለስልጣኑ ተሰበሰበ።
በስብሰባው ውስጥም በላይኛው የመሬት ክፍል ለሚኖሩ ሰዎች የተዘጋጁ የተለያዩ ሴራዎች ቢካተቱም መጨረሻ ላይ ግን የረዥም አመት እቅድ በመንደፍ አንድ  ውሳኔ ላይ ደረሱ።
ይህ በንዲህ እንዳለም በላይኛው የምድር ክፍል ከሚኖሩት የሰው ዝርያዎች ሴቶችን ብቻ እየነጠሉ በመጥለፍ ወደ ታች እያስገቡ በመቀጠለም የጠለፉትን ሴቶች በማስረገዝ እና የእርግዝና ግዜያቸውን አጠናቀው ሲወልዱ ያእጁጆቹ ህፃኑን እራሳቸው ጋር በማስቀረት እናቲቱን ቆራርጠው ከከርሰ ምድር አውጥተው በሳጥን አድርገው ይጥሏታል።
ይህን ዘግናኝ ተግባር በመተግበር በዚህ ሁኔታ ለረጅም አመታት ከዘለቁ በኀላ ከላይኛው የምድር ክፍል ከመጡት ሴቶች የተወለዱት ልጆች በቅርፅ ከነዚያ በመለያየት የራሳቸውን ትኩረት መሳብ ጀመሩ።
ከነዚህ ቅይጦች(በናታቸው ሰው ባባታቸው ያእጁጅ) መሀከልም አይጁር የተባለ እጅግ ብልህ እና ጠንካራ ወጣት ይገኝበታል።
ይህ ወጣት ከብልሀቱ እና ከጥንካሬው የተነሳ በትላልቅ የያእጄጃውያን ባለ-ስልጣናት እና የጦር መሪዎች ዘንድ የተወደደ ነበር ።

ይህ ወጣት ወደ ፊት ለታቀደውም የሰዎች ጦርነት ትልቅ አስተዋፅዕ ያደርጋል ብለውም ይጠብቃሉ።
ከእለታት አንድ ቀን እነዚህ የያእጁጅ ዝርያዎች ከከርሰ ምድር በሚገኘው ቤተመንግስት ውስጥ ባለ-ስልጣኖቻቸው እና የጦር መሪዎቻቸው ወደ መሬት ለመውጣት እና በሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት የሰው ዘርን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ብሎም የሰማይ ነዋሪያንንም ለመደምሰስ ትልቅ ስብሰባ አካሄዱ።
በዚህ የባለ-ስልጣኑ ስብሰባ ላይም አይጁር የተባለው(ዘረ-ቅይጥ) ወጣት ነበረና እንዲህ ሲል እሱም ሀሳቡን አቀረበ:-"እኛ(ያእጁጃውያን) ለረጅም አመታት በከርሰ ምድር ታጉረን ኑረናል።
የሰው ዘር እኛን ከመርሳታቸው ባሻገር ታሪካችንን ሳይቀር ዘንግተዋል። ስለዚህም በደፈናው ለጦር ከመውጣታችን በፊት የሰው ልጆች የደረሱበትን የጦር ስልጣኔ አቅም መሰለል ይጠበቅብናል'ና ፤ስለሆነም ከኛ ውስጥ የሰው ልጆችን በመልክ የሚመሳሰሉ ወጣቶቻችንን መልምለን እኔንም ጨምሮ ለስለላ ከከርሰ ምድር እንድንወጣ ላኩን'
ባለ ስልጣኑ እና የጦር አዛዦቹ በሙሉ በአይጁር ሀሳብ እጅግ በመደነቅ የተልዕኮውን ሀላፊነት  ሙሉ በሙሉ ለሱ ሰጥተዉት የወጣቶቹንም ምልመላ ራሱ አንዲያካሄድ ሾሙት።
በመቀጠልም አይጁር እንደ ራሱ ያሉ ዘረ ቅይጥ አስር ወጣቶችን በመመልመል ተልዕኮዋቸውን በሚገባ አስረድቷቸው ጉዞ ወደ መውጫ በር አቀኑ....

     __ ይቀጥላል_


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

16 Oct, 05:47


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀
    
   ያእጁጅ - ወማእጁጅ

        ክፍል 1⃣

  አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ አደምን ወደ ምድር አውርዶት ዝርዪቹ መባዛት ሲጀምሩ በጎሳና  ነገድ ከፋፈላቸው::
በግዜው እጅግ በርካታ ከነበሩ  ነገዶች መካከል ግን በባህሪም በይዘትም በብዛትም ለየት ያሉ ነገዶች ነበሩ::
እነዚህ ነገዶች የሰውነት ቅርፃቸው ሰው መሆናቸውን እስኪያጠራጥር ድረስ እጅግ ውጥንቅጡ የወጣ ነው:: ይሁን እንጂ ህልውናቸው
እንደኛው ሰው ናቸው::
ከነገሩ ጅምር አንስቶ ብርሃን አይወዱም "ጨለማን ከመውደዳቸው የተነሳ ለጨለማ ውዳሴ እና ቅዳሴ ያደርጉለታል:: ከሌላ የሰው  ዝርያዎች ጋርም በፍፁም አይስማሙም:: ይህ ገለልተኝነታቸው በማህበራዊ ኑሮዋቸው ላይ ተፅዕኖ ከመፍጠሩም ባሻገር አንዱ የሌላኛውን ጎሳ እንኳን ትዳር እንዳይመሰርቱ በማድረግ እርስ በርስ እንዲዘዋወጁ አስገድዶቸዋል::
*ማንነታቸው
የእጁጅ እና መእጁጅ
ከኑህ ዘመን ትንሽ ቀደም ብሎየነበሩ ነገዶች ሲሆኑ:እጅግ ግዙፍ እና  ጥንካሬያቸው በዘመኑ ከነበሩ ግዙፍ ሰዎች ጋር እንኳን አይስተካከልም ነበረ::
የያእጁጅ እና መእጁጅ ነገዶች ወደ ሶስት ጎሳዎች ይከፋፈላሉ:-
1ኛ:- እጅግ ግዙፍ እና ረጃጅም( ልክ እንደ ባህር ዛፍ)ሲሆኑ ቁመታቸው ረጃጅም
2ኛ:- መካከለኛ ቢሆኑም አንዱ
ከአንዱ ማይበላለጡ ናቸው
3ኛ:- እነዚህ ደግሞ ጆሮዋቸው እጅግ ትላልቅ ና ግዙፍ ከመሆኑ የተነሳ መተኛት ሲፈልጉ እንኳን አንደኛውን ጆሮዋቸዉን ያነጥፋትና የላይኛውን ደግሞ እንደ ብርድ ልብስ ይለብሱታል::
እነዚ 3ተኛ ላይ የተጠቀሱት ጎሳዎች ከፍተኛ የሆነ የመራባት ባህሪ ሲኖራቸው ኢብን አባስ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ረሱል ሰለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም :* ከነዚያ ጎሳ አንድ አባት 1000 ልጆችን ሳይወልድ አይሞትም* በማለት ገልፀውልናል:- በዚህ ሁኔታ እነኚህ ነገዶች በሰው ልጅ ዐቅል ለማስተዋል በማይመች መልኩ ከዚያ  ሩቅ ዘመን አንስቶ እስካሁንም በከፍተኛ ፍጥነት በመዋለድ እና በመባዛት ላይ ይገኛሉ::በዘመኑ ይኖሩ የነበሩ የተቀሩ የሰው ዘሮችም እነዚህ ነገዶች የሚሰሩትን ዘግናኝ ተግባር ሲመለከቱ ይሸሹ  ነበር::
አብዛኛውን ጊዜ ከነዚህ ነገዶች ሰው ሲሞት እንደተቀሩት የሰው ዝርያዎች በመቃብር ከመቅበር ይልቅ ሰብሰብ ብለው ምንም ሳያስቀሩ በመብላት አጥንቶችን እያጠራቀሙ ቤቶችን  ይገነቡበታል::
ከነሱ ውስጥ የተከበረ የሚባለውም ሌባ እና ነፍስ ገዳይ ሲሆን - ቋንቋቸውም ከተቀረው የሰው ዝርያዎች ከያእጁጅ እና መእጁጅ ነገዶች እራሳቸውን ከባድ ማራቅን ያርቁ ጀመር::
ይህን ጥላቻ የተመለከቱትም የያእጁጅ እና ማእጁጅ ነገዶችም ለተቀሩት የሰው ልጆች የጥላቻ አፀፋ መልሳቸውን በዘግናኝ ተግባራቸው ይመልሱ ጀመር::
በመጀመሪያ ያእጁጆች ለተንኮላቸው ማስፈፀሚያ ይሆን ዘንድ አንድ የተበቃይ ቡድን በማደራጀት ወደ ሰዎች መንደር እየላኩ ህፃናቱን በመግደልና አንገታቸውን እየቆረጡ በየደጁ ማስቀመጥ ጀመሩ:: (ይህ እነሱ ከሚፈፀሙት ትንሹ ተግባራቸው ነው::)በመቀጠልም እነዚህ ነገዶች የሰው ዘርን ከነአካቴው ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የረጅም ጊዜ እቅድ በመንደፍ እቅዳቸውን እውን  ማድረግ ጀመሩ:: እቅዳቸውም:- ወንዱ ካገኛት ሴት ሁሉ በመገናኘት (ከእህቱ ከእናቱ ከልጁ) ብቻ ልጆች ለመውለድ ከሁሉም ጋር እየተገናኘ ዘር ማባዛት ነው::
እቅዳቸውም እውን ይሆን ጀመር ቁጥራቸው የመጠንን ድንበር አለፈ፤ ምድርን እጅግ ወረሯት። ብዛታቸውን ካረጋገጡ በሆላም አጎራባች መንደር ላይ የሚገኙትን የሰው ዝርያዎች እንደ በግ እያረዱ መብላት ጀመሩ። ይህንን ክስተት የሰሙ ከባድ የህዝብ ብዛት፡ያላት እና ራቅ ባለ ስፍራ የሚኖሩ የሰው ዘሮችም ለብቀላ ወደነዚህ ነገዶች በመትመም በአላህ እርዳታ ከፍተኛ የሆነ ውግያ ተዋግተው ያእጁጆችን ለጉዳት ዳረጓቸው::
ይህን ግዜም ትላልቅ የያእጁጆች የጎሳ መሪዎች ሰብሰብ በማለት ከምድር ታች ብርሀን በማይኖርበት.... ፤ሰዎች በማይደርሱበት የራሳቸውን ከተማ ለመመስረት ተስማሙ።

       _ _  ይቀጥላል_


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://t.me/smithhk

ኡመተ ረሱል

14 Oct, 12:49


ጭንቅላት አምኖ ማይቀበለው እንኳን ለመኖር ለማየት የሚከብድ  እሄ ትዕይንት አዳሩን በ አል አቅሳ ሆስቢታል  የተከሰተ ነው።
ህፀናት ይይደረሱልኝ ጥሪ አሰሙ እዛ ያሉ እናቶች ማንም ሊደርስላቸው አልቻለም ሁሉም ከነሂወታቸው ታቀጠሉ ።

እዛ የሌሌ ስሜቱን፣ህመሙን ምንም ቢሆን አይረዳም
ያ ሁላ የህፃንት ለቅሶና የሴቶች ጩኋት ምድርን እያንቀጠቀጠ ነው። ነገር ግን
ከድንጋይ በላይ የደረቁ ልቦችን ያልቀሰቀሰ ትዕይንት።

ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِىَ كَٱلْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةًۭ

Credit:STRONG_IMAN

👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

09 Oct, 17:20


🤲

👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

09 Oct, 04:00


🍁የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ🍁

👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

08 Oct, 03:55


🍁የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ🍁

Zad Islamic Channel ይቀላቀሉ👇

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

07 Oct, 20:00


🍁የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ🍁

👉@ZadIslamicChannel✔️

ኡመተ ረሱል

07 Oct, 14:47


🤲

👉@ZadIslamicChannel✔️