Yekatit 23 SPS @yek23sps Channel on Telegram

Yekatit 23 SPS

@yek23sps


Official school channel

Yekatit 23 SPS (English)

Welcome to the official Telegram channel of Yekatit 23 Senior Secondary School, also known as Yekatit 23 SPS. This channel, with the username @yek23sps, is dedicated to providing latest updates, announcements, and important information related to the school. Yekatit 23 SPS is a prestigious institution known for its academic excellence, diverse student body, and supportive community. With a long-standing history of producing successful graduates, the school is committed to providing a well-rounded education that prepares students for the future. On this channel, you will find notifications about upcoming events, exam schedules, parent-teacher meetings, and other important news. Whether you are a current student, parent, alumni, or simply interested in learning more about the school, this channel is the go-to source for all things Yekatit 23 SPS. Stay connected with us on @yek23sps to stay informed and engaged with the school community. Join us in celebrating our achievements, sharing memories, and staying up-to-date on everything happening at Yekatit 23 SPS. We look forward to connecting with you on this official school channel!

Yekatit 23 SPS

05 Jan, 16:41


#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

@tikvahethiopia

Yekatit 23 SPS

03 Jan, 15:42


እንኳን ደስ አላችሁ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በቀን 22/04/2017ዓ.ም  በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በሁሉም የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች  ጥያቄና መልስ ዉድድር ተካሂዷል፡፡  በዚሁም የት/ቤታችን ተማሪዎች ከፍተኛ ውድድር በማድረግ ደረጃ ውስጥ ገብተዋል ።።
በቂ ዝግጅት በማድረግ ከዚህ በላይ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን ማፍራት እንደሚቻል ተስፋ ሰጭና አበረታች ውጤት ውጤት ነው። በርቱ ....
በማህበራዊ ሳይንስ 12ኛ ክፍል
1ኛ. ሲምቦ ደረጃ➡️ከቅ/ዩሃንስ 2ኛ ደረጃ
2ኛ. ቢፍቱ መሀመድ➡️ከአስኮ ፕሮግረስ 2ኛ ደረጃ
3ኛ. ብሌን ጌታቸው➡️ከየካቲት 23 2ኛ ደረጃ
በተፈጥሮ ሳይንስ 12ኛ ክፍል
1ኛ. የአብስራ ደምሰው➡️ከቅ/ዩሃንስ 2ኛ ደረጃ
2ኛ. ሪሀና ሂክማ➡️ከራዲካል 2ኛ ደረጃ
3ኛ. መቅደላዊት ጌታቸው➡️ከባሽዋም 2ኛ ደረጃ 
በመጨረሻም ለአሸናፊ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል፡፡

Yekatit 23 SPS

03 Jan, 15:26


G-11 Economics worksheet 2017

Yekatit 23 SPS

03 Jan, 15:04


it for tomorrow Tutorial class. Try to do it before coming to school.

Yekatit 23 SPS

28 Dec, 16:46


G-11 Economics worksheet 2017

Yekatit 23 SPS

28 Dec, 15:42


Share 'WORK SHEET FOR GRADE 9th 2017ETC.doc'

Yekatit 23 SPS

27 Dec, 16:59


FURAD ECON WORKSHEET G-12

Yekatit 23 SPS

27 Dec, 12:43


ስማችሁ የተዘረዘረው የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ማመልከቻ ፎርም ያልሞላቸው መሆኑ ሪፖርት ተደርጎልናል። ስለሆነም እስከ ሰኞ 21/4/17 ዓ/ም ድረስ ካልተመዘገባችሁ ሃላፊነቱን ት/ቤቱ የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ።

Yekatit 23 SPS

27 Dec, 12:38


THIS WORKSHEET IS FOR TOMMOROW TUTORIAL CLASS. PLS TRY TO DO IT BEFORE COMING TO SCHOOL.

Yekatit 23 SPS

26 Dec, 08:18


Share chemistry worsheet for G-11 in 2017.doc

Yekatit 23 SPS

25 Dec, 17:25


ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 16/4/17 ዓ.ም  በየካቲት 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 11ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ትምህርቶች ላይ በሁለቱ ክበባት አስተባባሪነት የተዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር  ተካሄደ።

Yekatit 23 SPS

17 Dec, 15:35


ቀን 8/4/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች
በ2017 ዓ.ም በየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከነገ 9/4/2017 ዓ.ም ጀምሮ ኦንላይን ፎርም የሚሞላ በመሆኑ በ9/04/2017 ዓ.ም የ12-01 ተማሪዎች በሙሉ ከ9 -11 ሠዓት ስለምትሞሉ እና ፎቶም ት/ቤት ስለምትነሱ የተስተካከለ ዩኒፎርም(የደንብ ልብስ) ለብሳችሁ እና ፀጉራችሁን አስተካክላችሁ እንድትገኙ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ት/ቤቱ

Yekatit 23 SPS

11 Dec, 09:50


ለመ/ራን በሙሉ፦
በ2016ዓ.ም ክረምት ላይ በተሰጠው ት/ት እና ምዘና መሠረት 70% እና በላይ ውጤት ያስመዘገባችሁ የእንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክና የኬሚስትሪ መምህራን በሙሉ   የተላከላችውን ሠርተፊኬት  በመያዝ የመ/ራን ልማት ም/ር/መ ተወካይ መምህር ስለሺ ታደሠ ጋር እስከ ሐሙስ 03/04/17 ዓ.ም ሪፖርት  እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Yekatit 23 SPS

10 Dec, 13:50


ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ/ም የየካቲት 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የስርዓተ ፆታ ክበብ " የሴቶችን ጥቃት ዝም አልልም " በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ አከበረ፡፡ በዝግጅቱ ላይ የክበቡ አባል ተማሪዎችና መምህራን አዝናኝና ቁምነገር መልዕክት ያላቸውን ግጥሞች፣ መነባንብ እና የጥያቄና መልስ ውድድሮችን በማካሄድ ተሳታፊ ተማሪዎችና መምህራን  በሴቶች ጥቃት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል ንቅናቄ መፍጠር ችለዋል፡፡

Yekatit 23 SPS

02 Dec, 13:15


የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጤና ኤች አይቪ ኤድስና ስነ-ተዋልዶ ክበብ ቀኑን በማስመልከት ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መልእክቶችና ስነፅሁፋዊ ሥራዎች አቅርበዋል ::


በ 2023 የወጣ መረጃ  በዓለም አቀፍ ደረጃ 39.9 ሚሊዮን አዋቂዎችና 1.4 ሚሊዮን የሚደርሱ እድሜያቸው ከ 0- 14 እድሜ ክልል የሚገኙ ሕፃናት ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው እንደሚገኝና ከ 630 ሺ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን በቫይረሱ ያጡ መሆናቸውን ያመላክታል ::


የዘንድሮው ዓለም ኤድስ ቀን " ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ መከላከል አገልግሎት ለሁሉም " በሚል መሪ ቃል  ተከብሮ ውሏል ::



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et 
Email;- [email protected]    
Instagram: - https://www.instagram.caeb/

Yekatit 23 SPS

02 Dec, 10:18


በየካቲት 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የጤና፣ ፀረኤችአይቪ እና ስነተዋልዶ ክበብ አስተባባሪነት ለ 38ኛ ጊዜ የሚከበረው  የዓለም ኤድስ ቀን ዛሬ ሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ/ም  በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይ ከት/ቤቱ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች በተጨማሪ የአ/አበባ ት/ቢሮ ሃላፊዎች እና የአ/ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ የስራ ሒደት አስተባሪ እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት  ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው  ለተማሪዎች እና ለት/ቤቱ ማህበረሰብ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Yekatit 23 SPS

29 Nov, 16:34


ማስታወቂያ
በት/ቤታችን ቅዳሜ ቅዳሜ የማጠናከሪያ ት/ት የምትማሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በነገው እለትም ማለትም 21/03/2017 ዓ.ም በተለመደው አግባብ የማጠናከሪያ ትምህርቱ የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ት/ቤቱ

Yekatit 23 SPS

03 Nov, 07:22


22/02/2017 ዓ/ም

ማስታወቂያ
ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች
በ2016 ዓ.ም የ12 ክፍል ተማሪዎች የሆናችሁ በሙሉ የትምህርት ማስረጃ /ትራንስክሪብት/  እና የውጤት ካርድ  የምትወስዱበት የመጨረሻ ቀን ሰኞ 25/02/2017 ዓ.ም  ከ3:00-4:30 ሰዓት ብቻ በመሆኑ በዚህ ቀን በሰዓቱ መጥታችሁ እንድትወስድ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Yekatit 23 SPS

01 Nov, 16:29


22/02/2017 ዓ/ም

ማስታወቂያ
ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች
የነገ ቅዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት በአብዛኛው መምህራን ስልጠና እና ማህደረ ተግባር ምዘና ስራ መደራረብ ምክንያት የማይኖር መሆኑን እየገለፅን በቀጣይ ሳምንት የሚቀጥል እንደሆነ እናሳውቃለን ።

Yekatit 23 SPS

01 Nov, 03:24


የትምህርት ማስረጃ ለጠፋባችሁ ፣ ለተበላሸባችሁ እና
ለተለያያ የትምህርት ማስረጃ አገልግሎት ፈላጊዎች

Yekatit 23 SPS

19 Oct, 09:34


ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 09/2017 ዓ/ም የካቲት 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የት/አመራር እና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች  በ 2017 ዓ.ም የእንግሊዝኛ እና የሒሳብ ትምህርት  ውጤት  ለማሻሻል በተዘጋጀው ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ  ውይይት አደረጉ።
በውይይቱ ላይም የተማሪዎች ስነምግባርና ውጤትን ለማሻሻል የተቀመጡ የመምህራንና የተማሪዎች ስነምግባር መመሪያዎች ሙሉ  በሙሉ በመተግበር የተጠያቂነት ስርዓት ማስፈንና የተጠናከረ የማጠናከሪያ ትምህርት መጀመር እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል ።

Yekatit 23 SPS

14 Oct, 07:57


04/02/2017 ዓ/ም
የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትናችሁ የሪሞዲያል ውጤት አምጥታችሁ የፊልድና የዩኒቨርስቲ ምርጫ ያልሞላችሁ ተማሪዎች ዛሬ 4/2/17 እና ነገ 05/2/17 በት/ቤት እየተገኛችሁ መሙላት ጠምትችሉመሆኑን እያሳወቅን በወቅቱ ያልሞላችሁ ተማሪዎችን ሃላፊነት የማንወስድ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

Yekatit 23 SPS

09 Oct, 16:26


29/01/17 ዓ/ም
የ2016 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትናችሁ የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የመስክ እና ዩኒቨርስቲ ምርጫ ለመሙላት ሊንኩ እየሠራ ስላልሆነ መስራት ሲጀምር የምናሳውቅ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን ።

Yekatit 23 SPS

07 Oct, 19:08


እንኳን ደስ አላችሁ!!

የካቲት 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት  በ2016ዓ.ም ለ 3ኛ ጊዜ ባስፈተነው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጣ ተማሪ የሱፍ አዲብ
523/600  በማስመዝገብ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በ27/01/2017ዓ.ም   የታብሌት እና የምስጋና የምስክር ወረቀት   ሽልማት ተበርክቶለታል ። ለዚህ ውጤት መምጣት  ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራችሁ  መምህራንና የትምህርት ባለድርሻ አካላትና የተማሪው ወላጆችን እንኳን ደስ አላችሁ  ለማለት እንወዳለን ።

Yekatit 23 SPS

27 Sep, 07:35


ለክርስትና   እምነት  ተከታዮች  በሙሉ
እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
BAGA AYYANA MASQALAA NAGAAN GEESSANI!

የካቲት 23 አጠቃላይ  2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Yekatit 23 SPS

21 Sep, 12:25


ዛሬ መስከረም 11/2017 ዓ/ም የወላጆች ውይይት መድረክ በከፊል