ባወቅነው ቁጥር ስለሱ ብለን የትኛውንም መስዋት እንቀበላለን። ይህንን ምሳሌ እንመልከት ፣🌹
ክፍል 5️⃣✅💙 ቢስሚከ ነህያ💜
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
(አል-ፋቲሐህ - 1)
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
(አል-ፋቲሐህ - 2)
ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤
ታላቁ ሰሀባ አብደላህ ኢብኑ ሑዛፋ (ረ ዐ,) ከእስልምና በፊት ምንም ጥረትም አስተዋፆ አልነበረውም። የአላህ ፍቃድ ሆነና እስልምናን ተቀበለ። ከሰለመ ቡሀላ በምርኮነት በሩም ንጉስ እጅ ወደቀ ንጉሱም ሊገድለው አሰበ። ሃይማኖትህን የምትተው ከሆነ ይህን ያህል ሀብት እሰጥሀለሁ አለው። ሁዘይፋም በአላህ እምላለሁ ሀይማኖቴን እድተው ብለህ ሙሉ ሀብትህን ብትሰጠኝ የምተው አይደለሁም አለው።
ቀጥሎም ሀይማኖትህን ከተውክ ከስልጣኔ አካፍልሀለሁ በማለት ሊያግባባው ሞከረ። ሁዘይፋም በአላህ እምላለሁ የዚህ አለም ስልጣን ለኔ ምንም አይደለም።💪✅አለው።
እንግዳውስ እገድልሀለሁ አለው። ሑዘይፋም የሻህን መስራት ትችላለህ አለው። ንጉሱ ጋሻጀግሬወቹን በቀስት ወጋጉት እና አሰቃዩት ግን አትግደሉት በማለት አዘዛቸው። 😭😭
ከፍተኛ ስቃይ እስኪሰማው ድረስ እጆቹን በቀስት ወጋጉት። ሀይማኖትህን ተው በማለት ጠየቁት በአላህ እምላለሁ አልተውም አላቸው። በቀስቱ እግሩን ወጋጉት አላቸው። በታዘዙት መሰረት እግሩን በቀስት ወጋጉትና ሃይማናትህን ተው አሉት ። በአላህ እምላለሁ አልተውም አላቸው ። ንጉሱ በመቀጠል ሁለት ባልደረቦቹን አምጡና በመርሜል ዘይት በማፍላት እዛ ውስጥ ክተቱዋቸው አለ። ከሱ ጋር የነበረት ሁለት ሙስሊሞች አመጡና አይኑ እያየ በፈላ ዘይት ውስጥ ከተቱዋቸው። አሁንም ጠየቁት ሀይማኖትህን ተው አለበለዚያ -…………………አሉት ወላሂ አልተውም አላቸው 💪🌹
በሉ ውሰዱና ዘይት ውስጥ ክተቱት አላቸው። ሊከቱት ወደ ሜርቤሉ ሲያስጠጉት ፡ታላቁ ሁዘይፋ ( ረ ዐ ) አለቀሰ። ሰወቹ ይህንን ለንጉሱ ነገሩት ። ንጉሱም መልሱት ወዲህ አላቸው ። መልሰው አመጡት። ንጉሱም ማልቀስህ ተነግሮችኛል። አለው ሁዘይፋም አወ አለው ለንጉሱ።
___
የሩም ምድር የሚባለው በግዜው በሰሜኑ የዐረብ ምድር አቅጣጫ አዋሳኝ የነበሩ የዛሬው የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ሀገሮች ናቸው።
____
✍️እግዳውስ ሃይማኖትህን ተው። አለው። ወላሂ አልተውም አለ። እንግዳውስ ለምን አለቀስክ? አለው። በአላህ መንገድ የምሰጠው ነፍስ አንዲት ብቻ መሆኗ ነው ያስለቀሰኝ። በሰውነቴ ላይ ባለው ፀገር ልክ ነፍስ ቢኖረኝና በአላህ መንገድ አንድ በአንድ ብሰጥ እመኝ ነበር። አለው።
✍️አልኸንሳእ ከኢስላም በፊት ሰኸር የሚባል ወንድሟ ሞተና ትእግስት አጥታ በለቅሶ መላውን የአረብ ምድር አዳርሳ ነበር።
ከእስልምና ቡሀላ ደግሞ አራት ልጆቿ ሞቱባት።ፅኑ እምነቷ እጅግ የሚገርም ነበር ። እነሱን መስዋት በማድረግ ክብር እድትጎናፀፍ ላደረጋት አላህ ምስጋና ይሁን። ነበር ያለችው።
በዚህን ግዜ አልኸንሳ ይህን ልትል የቻለሽችው ፈጣሪዋንና አምላኳን ስላወቀች ነው። ስላወቀችው ለፍርዱና ለውሳኔው እጅ ሰጠች። ኢማን እና ኢማን አልባ መሆን ልዩነቱ በጥልፅ የታየበት ክስተት ነበር።
✍️አላህን እናውቃለን። ለምንል ሰወች ደግሞ ምልክት አለው። የላይ ላዩን ብቻ አላህን ማወቅ ማወቅ አይደለም። ማወቅ ሲባል ከሰውነት ጋር በተዋሀደና ከደም ጋር የተቀላቀለ መሆን አለበት።የዚህ አይነቱን ማወቅ ካጣን እንሞታለን። ለምሳሌ ይህቺ ሴት በዚህ በዚህ የአላህን ስም እያስታወሰች ሞተች አለቃየ የሰራይ ነገር ይህን ይህን የአላህን ስም እዳስታውስ ያደርገኛል፡ ፈገግ ባለችልኝ ትንሿ ልጅ ምክንያት ይህ ይህ የአላህ ስም ትዝ ይለኛል። እና የመሳሰሉትን አባባሎች እንመልከት። ማወቅ ማለት ስንል በዚህ መልኩ በአጋጣሚወች ሁሉ የአላህን ሱ ወ )) ስሞች ስናውቅና ስናስታውስ ነው።
✍️ሌላ ምሳሌ አላህ ሱ ወ)) ውሀን የፈጠረው ለሁለት አላማ ነው። ትንሹ እና ትልቁ አላማ ልንለው እችላለን። ትንሹ አላማ ጠጥተነው ጥማችንን እንድንወጣ ነው። ውሀ ጠጥተን አእምሯችን ውሃውን ወደሰጠን አር, ረዛቅ ) ሲሳይ ሰጪ አምላክ የሚወረውረውና ሲሳይን በሰማይ ውስጥ በምትሄደው ውሃ የያዘች ዳመና ላይ ላደረገው አላህ ምስጋና ይሁን። የምንል ከሆነ ወደ ትልቁ አላማ ተሸጋገርን ማለት ነው። ይህም ውሃን ከመፍጠር ጀምሮ አላህን በስሙ በ,አር , ረዛቅ ) እስከማወቅን ይይዛል።……….................…ክፍል… ……6️⃣…ይቀጥላል ✍️
___
✍️((አልኸንሳ በዐረቡ ዓለም ና በኢስላም ታሪክ ስመ ጥር. እንስት ገጣሚ እደነበረች ታሪኳ ያስረዳል። ታሪኳ ና ገድሏን በበርካታ ኢስላማውይ መፅሀፍት ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል))።🌹
__
…