IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር) @ibnunekir Channel on Telegram

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

@ibnunekir


قل عن أخيك" لا أدري لعله خير مني" فلا تقل كما قال إبليس"أنا خير منه"
@ibnunekir309

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር) (Arabic)

مرحبًا بكم في قناة IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር) على تطبيق تيليجرام! هل تبحث عن الإلهام والحكمة؟ إذاً، هذه القناة هي المكان المثالي بالنسبة لك. IBNU NEKIR تقدم لك يوميًا الحكم والأقوال المأثورة التي تساعدك على التفكير والتأمل في الحياة. الاسم الذي يحمل جذورًا عربية وأفريقية يعكس تنوع الثقافات والحضارات التي تجتمع في هذه القناة الرائعة. قم بمتابعة @ibnunekir309 لتكون على اطلاع دائم بآخر التحديثات والمشاركات. كما قال الحكيم: "قل عن أخيك: لا أدري، لعله خير مني، فلا تقل كما قال إبليس: 'أنا خير منه'." انضم اليوم لهذه القناة الرائعة وشارك حكمتك وتأملاتك مع أعضاء آخرين يبحثون عن المعرفة والإيجابية في الحياة. تابعوا #أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري واحصلوا على جرعة يومية من الحكمة والتفاؤل. انضموا اليوم للقناة وشاركوا الحكمة والإلهام مع العالم!

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 17:12


ተጅዊድ 👌💯

እስኪ ሱረቱ'ል ኢኽላስን በሚገርም ተጅዊድ አዳምጡ!

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
🌐 t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 11:16


🌹የቁርኣን ውበት እና ጥበብ በቃላት የሚገለፅ አይደለም!

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
🌐 t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 09:14


🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

አህባቢ አምላካችን አላህ ወደእርሱ እንድንመለስና ልባችንን እንድንፈትሽ በዚህና በመሰል ክስተቶች እየገሰፀን ነው ።በንዝረቱና በመንንቀጥቀጡ ስንዘናጋ ይኸው ሌላ ደውል!።ግን ምን ያህል ልባችን ቢደርቅ ነው እንደዚህ አይነት ክስተቶችን እንኳን እያየን እራሳችንን የማንመረምረውና ለልባችን መፍትሄ የማንፈልገው?እስኪ ከስር በተዘረዘሩት ነጥቦች እራሳችንን መርምረን አቋቋማችንን እናስተካክል።አላህ ያግራልን ይድረስልን።አሚን🤲

❤️የልብ መድረቅ ምልክቶች

🔻 ልቡ የደረቀ ሰው ሐራም መዳፈር ያበዛል።

🔻ወንጀል እየፈፀመ አይደነግጥም።

🔻የሰው ሐቅ መዳፈሩ አያስጨንቀውም።

🔻ዒባዳው ለዛ ያጣል።

🔻 የዒባዳውን አሻራ አይፈትሽም።

🔻ተውበት ከመከጀል ሃጢያት መዳፈር

🔻ዒልም ኑሮት አለመተግበር

🔻ስራን ያለ ኢኽላሰ መስራት

🔻የአላህን ሪዝቅ እየበሉ አለማመሰገን

🔻የአላህን ቀድር አለመውደድና አለመቀበል

🔻የሞተን ሰው እየቀበሩ አለማሰተንተን

❤️የልብ ድርቀት ምክንያቶች

🔻የአላህን ትዕዛዝ መራቅ

🔻ወንጀሎችን ማብዛት

🔻በዱንያ ላይ ልብን ማንጠልጠል

🔻ረዥም ምኞትን መመኘት

🔻 አኼራን ፍፁም መዘንጋት

🔻ቁርአንን አለማንበብና አለመሰማት እንዲሁም አለመተግበር

🔻መጥፎ ጓደኛ መያዝ

🔻በመጥፎ ማህበረሰብ ውሰጥ መኖር

🔻ሞትን መርሳት

❤️የልብ ድርቀት መድኃኒቶች

🔻አላህን አብዝቶ ማውሳት

🔻እስቲግፋር ማዘውተር

🔻ቁርአንን በማስተንተን ማንበብ

🔻ራስን መመርመር እና መተሳሰብ

🔻ከመጥፎ ጓደኞች መራቅ እና ጥሩ ጎደኛ መያዝ።

https://t.me/ibnukedir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 08:40


Tejwid 👌💯

🎙 sheykh Temim Zu'eby

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
🌐 t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 07:13


አዎ የተሻለ ነው!!

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

🌐 t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 04:59


ትንሽ እንኳ አንደነግጥም አይደል??

መሬት ደጋግማ እየተንቀጠቀጠች ነው። ይህ ከባዱ ማስጠንቀቂያ ነው። መሬት የተንቀጠቀጠችው ውስጧ እንዲህ እንዲያ ስለሆነ የሚለው የሞኝ ትንታኔ ወደ ጎን ትተን ሀሊቁ አላህን እንስማ ወደ እርሱም እንመለስ!

አላህ በቁርዓኑ አመፀኞቹ የነብዩላህ ሷሊህ (ዐሰ) ህዝቦች በመሬት መንቀጥቀጥ እንዴት እንደቀጣቸው ሲገልፅ:

فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ جَٰثِمِينَ
«ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡»  (አል አዕራፍ 7:78)

ወደ አላህ ከመሸሽ ውጭ ምንም አማራጭ የለም። ወንጀላችን ሲበዛ፣ በደል ሲበዛ፣ የተበዳዮች እንባ ሲበዛ የአላህ ቁጣ መምጣቱ የማይቀር ነው። ተውበት በማድረግ ወደ አላህ እንመለስ፣ ሰደቃ በማድረግ የተቸገሩትን እንርዳ፣ የተበዳዮችን ይቅርታ እንጠይቅ፣ መበዳደል ይብቃን፣ ይቺ በሰከንዶች ለምትጠፋ አለም መስገብገብ ይብቃን

ኡማ ቲቪ

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

04 Jan, 04:56


ቅናት አያረጅም!
~
የአዛንና የሶላት ሰዓት አጭር ነው። በጥላቻ ስትሞላ ግን 5ቱ ደቂቃ አምስት ሰዓት ይሆንብሃል። ሰፈራችን ላይ የሱብሕ አዛን 11፡25 አካባቢ ተደረገ። ሶላቱ ደግሞ ሩብ ጉዳይ አካባቢ። ሁሉም ቢደመር 20 ደቂቃ አይሞላም። ከማዶ የሚሰማው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ግን እስካሁን አልተቋረጠም። ይሄ የየሰፈሩ እውነታ ነው። ግን የራስ እንትን አይገማም።

የዚች ሃገር ትልቁ ችግር ቅናት ነው። ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚገፋው አስተማሪ ከክልከላው ጀርባ ያደፈጠው ምክንያቱ ምቀኝነት ነው። ሌላው እንዲሁ ሽፋን ነው። የራሱን ማስለበስ ሲያቅተው። ሌሎች ላይ ይዘምታል። "ለሙስሊሞች ሒጃብ ከተፈቀደ እኛም ነጠላ እንለብሳለን" የሚለው የምቀኛ ሰፈር ልጆች መፈክርም የታወቀው በሽታ ነው፣ ቅናት። "ለሙስሊሞቹ መስገጃ ከተፈቀደ ለኛም መፀለያ ይፈቀድልን" የሚለው የምቀኝነት ልክፍትም የተለመደና ዝነኛ ህመም ነው።

ምቀኝነት እየተጋተ ያደገ አካል አድጎ አርጅቶ፣ በምርኩዝ እየሄደ፣ የሌሎችን ሃገራት ሁኔታ እያየ እንኳ አይለወጥም። እንዲያውም እየባሰበት ይሄዳል። ወደው አይደለም "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም" የሚሉት። በቅናት የገረጣ ፊት በቅባት አይወዛም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 21:01


" ዱአ ያስፈልጋል !! "

" አፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን ሀን ሩካ ወረዳ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ህዝቡን ከመኖሪያ ቤቱ አውጥቶ ሜዳ ላይ እያሰደረው ነው።

በተለያየ ግዜ በጎርፍ አደጋ ሲጠቃ የኖረው የአፋር ህዝብ ዛሬም አላህ ይድረስለት።

ሁሉም ሰው ቤት ውስጥ መተኛት አቁሞ ውጭ በረንዳ ላይ ወጥቶ እየተኛ ነው።

ዱአ ያስፍልጋል !! " - መሀመድ ኢሴ


@tikvahethiopia

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 15:02


እስቲ እንታረቅ❗️

🔅ምድር የሰው ልጆች ሆይ በቃኝ! ከዚህ በላይ አልታገሳችሁም!ከዚህ በላይ እኔ ላይ በሰላም መኖር አትችሉም!  ግፋችሁ በዛ!ከስሬ አድርጌ የዋጋችሁን እሰጣችኋለሁ! እያለች ይመስላልና እስቲ ወደ አላህ እንመለስ!

🔅እርሱ ይቅር እንዲለን እኛም ይቅር እንባባል/አውፍ እንባባል!

🔅አላህ እንዲታረቀን እስቲ እኛም እንታረቅ!

  🔅 መሪና ባለስልጣኖቻችንም
በየቦታው  እየፈሰሰ ያለውን ደምና የተበዳይ እምባን ለማስቆም ከመቼውም በላይ ጥረት ያድርጉ!

🔅ምድር እንደወትሮዋ ቀጥ ብላ እንድትቆምና ያለ ስጋት እንድንኖርባት ግፍና በደልን ከምድራችን ላይ እናስቁም።

🔅የዛሬ የጁሙዓ ልዩ ዱዓችን ላይም የሀገራችን የሰላምና ፍትህ ጉዳይ ላይ ይበልጥ ያተኮረ ብናደርገው መልካም ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ጁሙዓ ረጀብ 3/1446 ዓ.ሂ

ዛዱል መዓድ

🔹🔸🔹🔸🔹🔸

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 12:27


25/4/2017 በገቢ ረሱ ዞን ዱላሳ ወረዳ ሰጋንቶ ቀበሌ ደግም በመሬት መንቀጥቀጥ የወጣው እሳት ያአላህ....."

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 12:27


ታፍኖ ሲንቀጠቀጥ የከረመው መሬት እየተነፈሰ ይመስላል። አላህ ይዘንልን አላህ ይጠብቀን።

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 12:26


" የጁምዓ ኹጥባ "
√ አጭሯ የዱንያ ጉዞ
√ ወይራ ( ሰልማነል ፋሪስ መስጅድ)
√ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ( ማሜ)

√ ዛሬ  ከምሽቱ 02:00 ጀምሮ  በነሲሓ ቲቪ ይከታተሉ።

🗓 ታህሳስ 25 - 2017
🗓  ረጀብ 03 - 1446
============
ነሲሓ ቲቪ
እስላማዊ እውቀት ለሁሉም!

📡 Nilesat /11545 / V / 27500

@nesihatv

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 11:46


ትምህርት ያለ ሒጃብ
---------------------------------
#በሸይኽ_ሙሓመድ_ሓሚዲን_ዶ/ር
#ከፈትዋ_ፕሮግራም_የተወሰደ

@daewa_tv
📡 Nilesat
★★★★★
Frequency:- 11636
Symbol rate:- 27500
Polarization:-Vertical
★★★★★

Follow us on social media!👇👇👇
Youtube: https://www.youtube.com/@daewa_tv
facebook: https://www.facebook.com/daewa.tv
Telegram: https://t.me/daewa_tv

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 10:51


👌መሳጭ ቲላዋ!

🎙ሸይኽ ዐብዱል ወዱድ ሐኒፍ

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

🌐 https://t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 05:52


ሸህ አህመድ ደግ አደረጉ¡ ማብራት ከለለ መደርደሪያ ማድረጉ ነው ሚሻለው¡
= t.me/AbuSufiyan_Albenan

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 05:51


ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ ተውበት ለማድረግ ሰፊ ጊዜ አለን ብለው ገመቱ። ከዚያም እነርሱ በተዘናጉበት ሰአት ድንገት ሞት ያዘቻቸው።

ኢላሂ ከሞት በፊት ተውበተን ነሱሓን ወፍቀን።

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 05:43


ማራኪ ግብዣ ነውና ተጋበዙ!

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
🌐 t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

03 Jan, 05:43


🎙الشيخ محمود علي البنا

Tilawa 👌

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
🌐 t.me/ibnunekir

IBNU NEKIR (ኢብኑ ነኪር)

02 Jan, 11:44


ውሮ ተልዕኮ ያላት ይመስላል¡

ሰላራችን ለራሱ ኹሹዕ ጎድሎታል እንኳን ይህ ተጨምሮበት!