Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle) @abuumuawiya Channel on Telegram

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

@abuumuawiya


ከቁርአንና ከሀዲስ ማስረጃ እስከሌለህ
ድረስ አቋም አትያዝ !
ለሁሉም ሰው ሂዳያን ተመኝለት
ሀቅን እንጂ ሰውን አትከተል።
"ሰው በሀቅ ይለካል እንጂ
ሀቅ በሰው አትለካም"!

https://t.me/abuumuawiya
https://t.me/abuumuawiya

ያለዎትን ሀሳብ በዚህ ይጠቁሙኝ
በተለይም ስህተት ከተመለከቱ
በአስቸኳይ ጠቁሙኝ።
@Abumuuawiya
@Abumuuawiya

Abu_Muawiya_As_Selefy (Amharic)

አብደር መወዬ እግዚአብሔር ንጉሥ ኩርናዕ እስከመድሃኒዓለም። ስለሆነ፣ እኛ በመተካት እና በግንባር ውስጥ ከስነስርአት በገንዘብ ወደነት እስከገንዘብህ ድረስ እንዲህ ሲል መሄድ ነው። በቁርአል ላይ ተባብረው ወደ ሀዲስ መሬት እንዲሄዱ፣ በራስን በደረሰ ስራ የሚሰጥበትን ታሪኩን ይመልሱ። ሁሉንም ሰው ሲሆን የሀቅህን እንጌታ አያቋርጥበትም። የሚፈጠር ምኞትም ዝም አለበት። እባኮትን: @Abumuuawiya እና @Abumuuawiya በማስተካከል ያግኙን።

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

13 Feb, 14:06


ሌራ እንግዶቿን ለመቀበል በዝግጅት ላይ...

🌐 t.me/kedrAbuabderehman

ኑ ከመሻይኾቻችን ትክክለኛ እውቀት ተማሩ!

🚥 ሙሉ አድራሻ፦ በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ በስልጦ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በሌራ ከተማ በኢማሙ አህመድ ኢብን ሀንበል መስጂድና መድረሳ

https://t.me/AbuImranAselefy/9824

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

13 Feb, 08:47


🏝 ልዩ ሀገር አቀፍ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም

👉 በአላህ ፈቃድ የዲን ትምህርት ድግስ ከቀን 07/06/2017 የጁመዓ ኹጥባ እና ሶላት ጀምሮ  ለተከታታይ 3 ቀናቶች ተዘጋጅቷል።

 🏞 ቦታ፦ ሌራ ከተማ በኢማሙ አህመድ መስጂድ እና መድረሳ ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል።

🪑 በዝግጅቱ ላይ ከሚገኙ ውድና ብርቅዬ መሻይኾች መካከል፦
🎙 አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ  ያሲን (ከለተሞ)
🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ሀያት (ከወሎ ሐራ)
🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ከኮምቦልቻ)
🎙 አሸይኽ ሙባረክ አልወልቂጢይ (ከቀቤና)
🎙 አሸይኽ አብድል ከሪም (ከኦሮሚያ ጅማ)
🎙 አሸይኽ መህቡብ (ከሳንኩራ)     
🎙 አሸይኽ አህመድ ወሮታ (ከጎንደር)
🎙 አሸይኽ አወል (ከዳሎቻ)

በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት
🎙 አሸይኽ ሁሴይን መሀመድ (ከሳዑዲ አረቢያ)
🎙 አሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን (ከሳዑዲ አረቢያ)
🎙 አሸይኽ ሀሰን ገላው (ከባህር ዳር)
🎙 አሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ከባህር ዳር)

👉 እንዲሁም እንደ ኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ የመሳሰሉ በርካታ ኡስታዞች የሚታደሙበት ደማቅ ፕሮግራም ነው።

👉 ከሚሰጡ ኮርሶች መካከል፦
📚 شُروطُ الصَّلاةِ وَواجِباتُها وَأركانُها
📚 የሶላት መስፈርቶች ማዕዘናቶቿ እና ግደታዎቿ

📝 للشـيخ محمد بن عبد الوهاب النجدي
🎙 በሸይኽ አብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል`ለተሚይ
       
የሀቅ ወዳጆች ሁሉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል እንዳትቀሩብን!

ማሳሰቢያ፦ ሁላችሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና የማታ ልብስ እንዳትዘንጉ።

አላህ ካለ ሩቅ ላላችሁ 𝙡𝙞𝙫𝙚 ላይ እናካፍላችኋለን
         ➘➘➘➘ 
https://t.me/AbuImranAselefy
https://telegram.me/IbnShifa

🔎 ሸር በማድረግ ለሰለፍዮች በሙሉ የማድረስ ሀላፊነታችንን እንወጣ

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

13 Feb, 08:04


🚎 ሀገር አቀፍ ታላቅ የዲን ኮንፈረንስ የፊታችን ጁመአ ጀምሮ በሚደረገው ፕሮግራም ላይ
ከአዲስ አበባ ብቻ መሳተፍ ለምትፈልጉ በነዚህ ስልክ ቁጥሮች በመደወል ፕሮግራም መያዝ ትችላላቹ

ፉሪ ፣ ኬንቴሪ ፣ ሰበታ ለምትገኙ 0941058157

አለም ባንክ ፣ ስልጤ ሰፈር ፣ ቤተል ለምትገኙ +251949435485

መላው አዲስ አበባ ለምትገኙ

+251936985302


👉 ማሳሰቢያ ቀለል ያለ የማደሪያ ልብስ መታወቂያ መያዣቹን አትርሱ

🔴 የመነሻ ሰአት ጁመአ ከቀኑ 3 :00 ይሆናል

https://t.me/medresetulislah

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

05 Feb, 13:58


ታላቅ የምስራች በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ ታላቅ የሙሓደራ ድግስ በአዳማ ከተማ



    እነሆ የፊታችን እሁድ የካቲት 2/2017 በአዳማ ከተማ 03 ቀበሌ በመደረሰቱል ፈትህ ወነስር ልዩ የሙሐደራ እና ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።

     የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች : –

①ታላቁ እና ተወዳጁ ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን ብን ሙሐመድ አስልጢይ (ሀፊዘሁሏህ)

②ተወዳጁ ዳዒ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁሏህ)
  
በአሏህ ፍቃድ ሌሎችም ይኖራሉ

     ፕሮግራሙ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2 : 30 የጀመራል ። 

https://t.me/adama_ahlusuna_weljemea

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

15 Dec, 22:55


👉 አዲስ ኪታብ pdf የገፅ ብዛት 313

عنوان:- الواضح في تيسير منهج السلف الصالح
የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ ገር በሆነ መልኩ ግልፅ ማድረግ
للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ)

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት፣ የምታቀሩም አቅሩት)

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

05 Dec, 20:43


👆👆👆
🔈
#በተቻለ መጠን ከንቱን የማውገዝ ግደታነት

🔶
በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ በቅልጦ  ወረዳ በሾሞ ቀበሌ የተደረገ ሙሐደራ ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

03 Dec, 19:29


መጅሊስ እየፈጠረው ያለው በሱና ወንድሞችና ኮሚቴዎች የጅምላ እስር  በቅበት ከተማ አስተዳደር

✔️ ነገሩ እንዲህ ነው:–
        ራሱን የሀገሪቱ መንግስት አድርጎ የተመለከተው የቅበት ከተማ አስተዳደር መጅሊስ ተብዬ ሰሞኑን በከተማው ውስጥ በምትገኝ ኣንዲት የሰለፊያ መስጅድ ውስጥ ረብሻና ብጥብጥ አለ እያሉ ሰላማዊ በሆነው ጀመዓ መሃከል አለመግበባት እንዲፈጠር ቀሰቀሱ።

        ከዛም ችግሩን ኮሚቴውና የቀበሌ መጅሊስ በውይይት ይፍቱት በሚል ለውይይት ተቀመጡ፣ ተበደልኩ ያለ ሰው አለ ብለው ስለነበረ ኮሚቴዎች ምንድነው? በማለት ጠየቁ፣ ለጥያቄውም መልሱ መስጅዳችን ሰላም ነው፣ ቂርዓትም ስርዓቱን ጠብቆ ቁርዓንንና ሀዲስን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ እንዳለ ተናገሩ።



      ☑️በመቀጠልም ለሚያነሱት እዚህግባ ለማይባለው ወሬ በአግባቡ መልስ ተሰጠ፣ በመቀጠል ለውሳኔ ሁለት ቀን ተብሎ ተሰጠና ዝምምምም ኣሉ እስከ 10 ቀን ከዛም የመጅሊስ አካላት የኔ አመለካከት ብለው የያዙት እቅድ ስላላቸው የሆነ ረብሻን ይፈልጉ ስለነበረ በሰላማዊ ዳዕዋ ላይ የማይክ መቆጣጠሪያ ብሬከር እንዲመልስ ኣንድን ተላላኪ አደረጉ ።

     በዚህ መሃል በጀመዓ ፊት ደዕዋን ለማወክ ሞከረ አስቆመ፣ በነጋታው አስር ከተሰገደ በኋላ መጅሊስ በመነሳት በዛው መስጅድ የመጀመሪያውን ኮሚቴ አውርደናል እያለ  አዲስ ኮሚቴን ማንበብ ጀመረ ።

   በንዲሁ አንዳለ ጀመዓው እድል ስጡን ምንድነው የተፈጠረው? ኮሚቴን መምረጥ ሀላፊነቱ የማን ነው? ብሎ ጥያቄ ለማንሳት እድል ለመስጠት አልፈለገም።


የጀመዓውን ሀሳብ ላለመስማት ቶሎ ብሎ  ጥሶ ወጣ፣ ጀመዓው የናንተው ኮሚቴው እኛን አይወክሉም በማለቱ ነባር ኮሚቴዎችን ፣ ኡስታዞችን እንዲሁም ጀመዓውን ከእሁድ ቀን  ጀምሮ በፖሊስ እስር ቤት እያፈሱ ይገኛሉ።


      ይህ ሁሉ ድርጊት ሲፈፀም ተበዳዩ ኮሚቴና ጀመዓ ሆኖ ሳለ መጅሊስ የሱን አመለካከት በግድ ለማስገባት በሚል ንፁሃን ጀመዓን ለእንግልት እየዳረጉ ይገኛሉ። ለመሆኑ የመጅሊስ ፍላጎት ምን ይሆን??……………








         https://t.me/sadikawol

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

22 Nov, 21:28


ቲቪ አፍሪካና ነሲሀ⁉️

"እንዴ!
እኛም መሀከል ክፍተት አለ ማለት ነው እንዴ!
ሁለቱም ቲቪዎች ላይ ?
እኔ እነዚ እነዚ ላይ ብዙ ልዩነት ያለ አይመስለኝም!
ለማንኛውም" .....

🎙 ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን



https://t.me/abuumuawiya
https://t.me/abuumuawiya
https://t.me/abuumuawiya

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

19 Nov, 18:31


"

ሰዎችን ማስጠቀም እስከቻልክ አስጠቅም

قَالَ رَسُولُ اللَّه ﷺ:

🔹"خيرُ الناسَ أنفعُهُمْ لِلناسِ"

" በጣም ምርጥ ሰው ሰዎችን በጣም የሚጠቅም ነው "

#حسنه العلامة الألباني رحمه الله في

📚 ሰሂሁል ጃሚዕ - رقم: (3289).

ከልብ ሰዎችን ለማገልገል መቆም ወደ ከፍታ የሚያመጠ መንገድ ነው ሰዎች እኔን ያገለግሉኝ እንጂ እኔ ለነሱ አገልጋይ ልሆን አይገባኝም የሚል ስሜት እንዳይኖርህ ።

https://t.me/abuabdurahmen

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

19 Nov, 18:29


#ታላቅ የሙሃደራ ግብዣ በአልከሶ ከተማ
============>

በጣም አጓጊ እና ተናፈቂው የሰለፊዮች የዳዕዋ ድግስ በጣም ተናፈቂ በሆኑት ታላቁ ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ኢብን ያሲን አላህ ይጠብቃቸው!

🏝 ለየት ባለ እና በማረ መልኩ ተደግሶ ይጠብቀናል።

ሌሎችም ውድ ብርቅዬ የሱና ኡስታዞች ይገኙበታል !!
🎙 ኡስተዝ ሸ አወል ከደሎቻ
🎙 ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ከወረቤ
🎙 ኡስታዝ ሲራጅ ሁሴን ከወራቤ
🎙 ኡስተዝ ኢብራሂም ከወረቤ
🎙 ኡሰታዝ ዘይኔ ከቅበት
🎙 አስተዝ አቡ ሙዒን ከአልከሶ
🎙 ኡስተዝ ያሲን ከአልከሶ!!
አላህ ይጠብቀቻው🤲

📅 የፊታችን እሮብ 11/3/2017
ሀርጤይ 👈
ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ አስከ 10:00 ሰዓት

🕌 ቦታ፦ አልከሶ ከተማ ቃልቃል ሃምዛ መስጂድ ከአልከሶ ወደ ወረቤ መውጫ መንገድ ደር በሚገኘው መስጂድ!!!

👉
እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል

ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ለይ
ቀጥ በል

Sher
ሼር
Sher
ሼር

https://t.me/Yalkasoenaakebabiwasalfyochgurup

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

18 Nov, 18:48


ርዕስ፦
« መስለሃና መፍሰዳ በኢስላም»

🎙በሸይኽ አብዱልሃሚድ ሀፊዘሁሏህ

🗓 ሕዳር ‐‐ 08  - 2017 E.C

🕌በአልበያን መድረሳ  -ቡታጅራ-


በሰለፊያ መንገድ ያፅናን


🌎ቡታጅራ፣ ኢትዮጲያ


@Abdul_halim_ibnu_shayk

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

17 Nov, 07:11


https://t.me/abuabdurahmen?livestream=e839619e0eb2bb19d6

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

14 Nov, 14:44


🟢 📚 በኡስታዝ አቡ ሀሳን ሙሐመድ ኪርማኒይ ሀፊዘሁሏሁ ተዓላ

ተቀርተው ያለቁ ከሰላሳ (30) በላይ ኪተቦችን በቀላሉ ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1📚 ኡሱሉ ሰላሳህ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3323

2 📚 ቀዋኢዱል አርባኣ
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3337

3 📚 ሹሩጡ ሶላት
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3304

4 📚 ኡሱሉል ኢማን
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3223

5 📚ሹሩጡ ላ- ኢለሀ ኢለላህ
👇 ሙሉ ደረሰ
አለhttps://t.me/abuumuawiya/4230

6 📚 አርባኡነ ለተሚያህ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/2321

7 📚 ኑሩ ተውሂድ ወዙሉማቲ አሽ-ሺርክ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/4444

8 📚ሰለሱነ ሙላሀዘቲን ዐለል ሙመይዓ
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/YusufAsselafy/1922

9 📚 አቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወልጀማዐህ
👇 ሙሉ ደርስ

https://t.me/abuumuawiya/4490

10 📚 አቂደቱ ጠሓዊያ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/4595

11 📚 ኡሱሉል ኢማን ፊ ደውዒል ኪታቢ ወሱነህ 👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3606

12 📚 አርበኢን ነወዊያህ
ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/4257

13 📚 ሙእተቀዱ ሶሂህ
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3172

14 📚 ኩን ሰለፊያ አለል ጃዳህ
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/2376

15 📚 ፊርቀቱ ነጂያህ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3286

16 📚 ኪታቡ ተውሒድ የሸይኽ ፈውዛን
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/2572

17 📚 ሸርህ ሉመእቱል ኢዕቲቃድ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3123

18 📚 ሸርህ ከሽፉ ሹቡሃት
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/2888

19 📚አቂደቱ ሰለፍ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/2813

20 📚 ተንቢሃት ሙሉ ደርስ
👇
https://t.me/abuumuawiya/4176

21 📚 ሪሳለቱል ሂጃብ
ሙሉ ደርስ 👇
https://t.me/abuumuawiya/4064

22 📚 አቂደቱል ዋሲጢያህ
👇ሙሉ ደርስበ
https://t.me/abuumuawiya/4595

23 📚 ሲፈቱ ሰላት የሸይኽ ኡሰይሚን
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/4691

24 📚 ዶላሉ ጀማአቲል አህባሽ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/4708

25 📚 ኡምደቱል አህካም
ሙሉ ደርስ👇
https://t.me/abuumuawiya/4016

26 📚 አጁዊበቲል ሙፊዳህ
👇ሙሉ ደርስ https://t.me/abuumuawiya/4375

27 📚 አልሀቁል- አውከድ
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3853

28 📚 ፈትሁ ረቡል በሪያ
👇 ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/2682

29📚 ቀዋኢዱል ሙስላ
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/abuumuawiya/3688

30 📚ሀዚሂ ደእወቱና ወአቂደቱና
👇ሙሉ ደርስ
https://t.me/kedrAbuabderehman/6190

31📚 ኢጅቲማእ ጁዩሺል ኢስላሚያ
👇 እየተለቀቀ ያለ ኪታብ
https://t.me/kedrAbuabderehman/6202

ጥንቅር አቡ ያሲር ዩሱፍ ሙዘይን
https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

13 Nov, 17:24


=> ወራቤ ዩኒቨርሰቲ ለተመደባችሁ የ Frershman ተማሪዎች በሙሉ

አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ ወበረካቱህ

📝 ዩኒቨርስቲው የጠራበትን ማስታወቂያ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ
➴➴➴➴
https://t.me/wru_selefy_official_chanel/2224

↪️ በ2017 E.C ወደ ወራቤ ዩኒቨርሰቲ ለfreshman የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የሚዘረዘሩት ተማሪዎች ስለ ጊቢው ሙሉ መረጃ ማለትም፦
- ጊቢ ስትገቡ ዶርማችሁን በማሳየት
- ሙሉ ምዝገባ  በማስጨረስ
- መስጂድ በማሳየት
- በትምህርት ጉዳይ በመርዳት

- በተለያዩ ጉዳዮች በማገዝ  ይተባበሯችኋል።

ችላ ሳትሉ ቀድማችሁ በመደወል አመቻቹ!!!

🍭 አብዱልሃሚድ
📲 +251955290801

🏝 አብዱሯህማን ነስሩ
📲 +251919925562

🏝 አሊ አብደሏህ
📲 +251908098412

🏝 አቡ ዒምራን
📲 +251925221042

🏝 አወል ሰዒድ
📲 +251954169515

🏝 ሙሰፋ አብደላህ (በስልጢኛ ለማናገር)
📲 +251908072703
              O  R
📲 +251937126410

🍭 ኸድር ከማል (በስልጢኛ ለማናገር)
📲 +251960404788

🍭 ነስሩዲን አብደላህ (በስልጢኛ ለማናገር)
📲 +251934364556

🍭 ሀሚድ ዩሱፍ (ለኦሮምኛ ተናጋሪዎች)
📲 +251929227128

N.B እህቶች ደግሞ የእህቶቻችሁን አድራሻ ወንድሞችን በመጠየቅ ማግኘት ትችላላችሁ።

ወይም በሚከተለው ሊንክ በመግባት መጠየቅ ትችላላችሁ!!!
https://t.me/WRU_Student_Bot

🏝 ለተጨማሪ መረጃዎች የሚከተሉትን አድራሻዎች በመቀላቀል መከታተል ትችላላችሁ!!!

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏖 https://t.me/wru_selefy_official_chanel

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

11 Nov, 12:01


ታላቅ_የሙሃደራ_ግብዣ በአዳማ ከተማ
==========================

በጣም አጓጊ እና ተናፋቂው የሰለፊዮች የደዕዋ ድግስ በጣም ተናፋቂ በሆኑ ኡስታዞች ለየት ባለ እና በማረ መልኩ ተደግሶ ይጠብቀናል


🪑ተጋባዥ እንግዶች

1ኛ  ተወዳጁ ኡስታዝ ባሕሩ ተካ ((ሀፊዘሁሏህ)

2 ተወዳጁ ኡስታዝ አቡ ሀመዊየህ ሸምሱ ጉልታ ( ሀፊዘሁሏህ)

3ኛ አቡ አብዲረህማን አብዱልቃዲር ( ሀፊዘሁሏህ)

ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይጠበቃሉ


    📅  የፊታችን እሁድ 08/03/2017

🕌ቦታ አዳማ 01 ቀበሌ በኢብኑ ተይሚያ መስጂድ

ሰዓት ከ 🕰2:30 ጀምሮ እስከ ዙህር

https://t.me/abuabdurahmen

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

07 Nov, 06:58


የኸይር ስራ ፈላጊ እህት ወንድሞቻችን ሆይ፦

ሸሪአችንን "በዚህች ምድር የወንድሙን ወይም የእህቱን እንዲሁም የእህቷን ወይም የወንድሟን ጭንቀት ያስወገደ/ች አላህ በአኸይራህ (በመጪው አለም) የሱን/ሷን ጭንቀት ያስወግድለታል" በማለት በኸይር ስራ አነሳስቷል። በመቀጠል ወደ መልካም ስራ እናመላክታችሁ። እሱም አንድ እህታችን የወንድም እህቶቿን እገዛ ትፈልጋለች።

እህታችን አጢባ ነጋሽ ትባላለች። በወራቤ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን በደረሰባት የልብ ህመም የወራቤ ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ህንድ ሀገር ሄዳ እንዲትታከም ፅፎላታል። ለህክምናውም 2,000,000 [ሁለት ሚሊዮን ብር] ያስፈልጋል ተብላለች። ነገር ግን በግል ህክምናውን ለመከታተል አቅም የሌላት በመሆኑ ከሀያሉ ጌታ ቀጥሎ የናንተን ወንድም እህቶቿን ድጋፍ ትፈልጋለች።

ይህች እህታችን ለበርካታ ጊዚያት በበሽታ እየተሰቃየች መሆኑን ተደጋግሞ እየሰማን ነው። አላህ ሁላችነንም ቤተሰቦቻችነንም እኛንም ከዱንያም ከአኸይራም ችግር ይጠብቀን!  በመሆኑም አላህ የመዋረጃው ቀን ጭንቀት ጊዜ ዘወር እንዲያደርገለት የፈለገ በተቻለው ይርዳት በማለት መልእክቱን ለማላስተላለፍ እንወዳለን።

❝ አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡ ❞

በዚህ መልካም ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ የሚከተሉትን አካውንቶች መጠቀም ትችላላችሁ

የአካውንት ቁጥር
Commercial Bank of Ethiopia
1000036881589

Zamzam Bank
0050265620101

Awash Bank
01425562027700

የአካውንት ስም Hatiba Nagash Aman

ተጨማሪ መረጃ
📱 +251912011954
           ሐጢባ ነጋሽ አማን

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

23 Oct, 13:49


👉   የኢኽዋን መሪዮች የመጅሊስ እንጂ የሀገር መሪዮች አይደሉም ።

     የሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች የስልጣን ጥማት በቀን ቁጭ ባሉበት እንዲቃዡ አድርጓቸዋል ። ቅዠቱ በርግጥ በውስጣቸው ሲያልሙት የነበረ መሆኑን ያመላክታል ። የእነዚህ አካላት የቀን ቅዠት ልክ እንደ አንድ በረንዳ አዳሪ ነው ።  በቀን ጎዳና ላይ ቁጭ ብሎ እርጥብ እሳት ( ጫት) እየበላ የምርቃናው ሙቀት በሁለመናው ሲሰራጭ በምናቡ የመዋኛ ቦታ ፣ ሜዳ ቴኒስ ፣ የልጆች መጫወቻ ባለው በተንጣለለ ጊቢ ላይ በተሰራ ቪላ ውስጥ ራሱን አስቀምጦ በሐሴት ማእበል ሲናወጥ ምርቃናው እንደጠፋበት አምሳያ ነው ።
     እነዚህ የሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች ለስንት አመት ሲመኙት የነበረውን የመጅሊስ ስልጣን ላይ ሲወጡ የተሰማቸው ሙቀት የሰራ አካላታቸውን ሲቆጣጠረው ቁጭ ብለው የሀገር መሪ ሲሆኑ በቀን በተቀመጡበት በምናብ ዐለም ማየት ጀምረዋል ። የሚገርመው ይህ ህዋ ላይ የሚያንሳፍፋቸው ቅዠት ወደ መሬት ለማውረድ ቆርጠው ተነስተው ማስፈራራት ጀምረዋል ።
    ከዚህ በፊት ሐረር ላይ በነበራቸው ጉባኤ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሱ " የስልጣን ግዛት " ውስጥ ሰለፍይ የሚባል ነገር መስማት እንደማይፈልግ በመግለፅ ሰለፍዮች ወደዱም ጠሉም በአሁኑ ሳአት እዚህ ሀገር ላይ ( ኢትዮዽያ ላይ ) የሙስሊሙ መንግስት እሱ መሆኑን አውጇል ።
     ገርሞ ገርሞ ይገርማል ። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንደሚሉት ወይም ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ነው ነገሩ ። ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፣ የሙስሊሞች መሪ ፣  ከዶ/ር አብይ አሕመድ ደግሞ የክርስቲያኖች መሪ  እንዲሆኑና ኢትዮዽያ በሁለት መንግስታት እንድትመራ የተስማሙ ይመስል ። ይህን የሐጂ የቀን ቅዠት በተለይ ኦሮምኛ የምትሰሙ በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ አድምጡ :–
https://drive.google.com/file/d/1VZSVRvGK0tOrUTiP4z7vJXz_Mx28Qqi4/view?usp=drivesdk

     በዚህ ቅዠቱ ላይ በሚገርም መልኩ ሰለፍዮችን ያስፈራራል ። ውሀ ዝም ብሎ ሲሄድ የተኛ ይመስላል እንደሚበላ ሰው አያውቅም የሚል ምሳሌ አምጥቶ ዝም ስላልኩ የማላውቅ አይምሰላችሁ አጠፋችሇለሁ ይላል ።
    እኛ የምንለው መጀመሪያ ዙፋኑን አረጋግጥና ከዛ በኋላ ዛቻውን አምጣ ነው ። አሁንም የምንለው አንተ የአንድ ተቋም መሪ እንጂ የሀገር መሪ አይደለህም ነው ። እንደሙስሊም በቁርኣንና በሐዲስ በሶሓቦች አረዳድ እንደ ሀገር ደግሞ በህገ መንግስቱ ነው የምንመራው ። አንተም እኛም በህገመንግስቱ እኩል ነን ።
     ከኢስላም ሊቃውንቶች ጥበበኛ ንግግር አንዱ " ልኩን ያወቀን አላህ ይዘንለት " የሚል ነው ።
     ይህ የቀን ቅዠት በሱ ላይ ብቻ አላበቃም ዶ/ር ጀይላንም የአሕባሽ ሱፍይና ኢኽዋን ጥምር የሆነው የዑለማእ ፈታዋ ያልተቀበለ ኻሪጅይ ነው ( በመንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ የወጣ ) ነው ብሎ የጓደኛውን የማይጨበጥ ምናብ አጠናክሯል ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
       🔹 ይህ ከላይ ያለው ፁሑፍ ግንቦት 2016 ላይ ተፅፎ የነበር ሲሆን ኢኽዋኖችን በተለይ የመጅሊሱን አመራሮች ያበሳጨ ነበር ። አሁንም የምንለው የኢኽዋን ( የመጅሊስ ) አመራሮች የሙስሊሙ መንግስት አይደሉም ። ኢትዮዽያም በሁለት መንግስት እየተመራች አይደለም ። ነገር ግን ከመንግስት ጋር ሲጠጉ እውነተኛ የሀገር ተቆርቋሪ የህዝቡን ሰላም አስጠባቂ መስለው ከመንግስት ጋር ሲጋጩ ወይም መንግስት ፊት ሲነሳቸው ለግል ጥቅማቸው ህዝቡን ከዳር እስከዳር ቀስቅሰው ሀገር እንዲታመስ የሚያደርጉ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባዮች መሆናቸውን መግለፅ በተለይ ለምስኪኑ ተከታይ በጣም አስፈላጊ ነው ። ታዲያ ከላይ የተጠቀሰውን የሀገር መሪነት የምናብ ስካርና ሰለፍዮችን የማሸማቀቅ ጥማታቸው በፊት ለፊት ሳይሆን በመሰሪ አካሄድ ተግባራዊ ለማድረግ የማይቆፉሩት ጉድጓድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ። ለዚህ ዋነኛ መሳሪያቸው ሰለፍዮችን የሀገር ስጋት የሰላም ፀር እንደሆኑ አደርገው ለመንግስት ባለስልጣናት በማቅረብ ወደ አላማቸው መድረስ ትልቁ ስራቸው አድርገው ይዘውታል ።  ይሁን እንጂ ደመናው በፀሀይ እንደሚገፈፈው ሁሉ እነዚህ አካላት በሰለፍዮች ላይ የሚለጥፉት የስም ማጥፋት ታፔላ ተነስቶ እውነታው ፍንትው ማለቱ አይቀርም ።
     ስሙን ለሰው አወረሰው እንዲሉ ኢኽዋኖች የራሳቸውን ማንነት ለሰለፍዮች በመስጠት ስማቸውን ለማጠልሸት መሞከር በምንም መልኩ የእነርሱን እኛ የሙስሊሙ መንግስት ነን የሚለውን ምኞት አያሳካም ። ለጊዜው ለመንግስት የተሳሳተ ምስል በመስጠት የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ ሊያደርጉ ይችላሉ  ። ነገር ግን ይህ ማለት መንግስትን አዘዙ ወይም  ከመንግስት በላይ ሆኑ ማለት አይደለም ። ይልቁንም ማንነታቸውና ድብቅ አጀንዳቸውን እንዲረዳ ነው የሚያደርጉት ። እንኳን ሀገር የሚመራ መንግስት አንድ የቤት አባ ወራም ቢሆን እገሌ እኮ በጣም አደገኛ ነው ካልከው ከሱ ጋር የነበረውን ግንኙነት ቆም አድርጎ በራሱ መንገድ ማንነቱን ያጣራል ። በመጨረሻም ታማኝነቱና እውነትኝነቱን ሲያረጋግጥ በተቃራኒው ያንተን ድብቅ ፍላጎት ለማወቅ ፊቱን ማዞሩ አይቀርም ።
      በመሆኑም የኢኽዋኖች ሰለፍዮችን የማጠልሸት እንቅስቃሴ ለሰለፍዮች ክብርን እንጂ አይጨምርላቸውም ። ሌላው ኢኽዋኖችና የእንጀራ ልጆቻቸው ሊያውቁት የምንፈልገው ሰለፍዮች በመለኮታዊ ቃል የሚመሩ መሆናቸውና ከማንም ምንም ነገር ቢደርስባቸው በመለኮታዊው የሕይወት መመሪያ የአላህ ቃልና በነብዩ ንግግር መዝነው ተግባራዊ የሚያደርጉት መሆኑን ነው ። በስሜት ፈረስ እየጋለቡ ለግል ጥቃማቸው ወጣቱን ከጎናቸው  አሰልፈው ሀገር የሚያምሱ አይደሉም ። ስለዚህ አትድከሙ ህልማችሁ አይሳካም የአላህ ቃል የበላይ ይሆናል እንላቸዋለን ።
      https://t.me/bahruteka

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

17 Oct, 09:52


የበላይነት በፅናት እንጂ በብዛት አይደለም ።

በአሁኑ ጊዜ ኢኽዋኖች ብዛትና አቅም ስላላቸው ከእርነሱ ማስጠንቀቅ ይከብዳል ይላሉ ። እነዚህ ሰዎች ውስጣቸው ያለው ሱና ደክሞባቸው በራሳቸው ጊዜ የተሸነፉ ናቸው ። ምክንያቱም አላህ ዓለምን ከጨለማ ያወጣው በአንድ ነብዩ ነው ። ዐለሙ አቅም በነበራቸው ከሀዲያን ተጥለቅልቆ ሳለ ።
ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሞቱ ጊዜ አብዛኛው ኢማን ሰርፆ ወደ ልቡ ያልገባ የገጠሩ ህዝብ ወደ ኩፍር ሲመለስ ዲኑ የተጠበቀው በአቡ በከር ፅናት ነበር።
የሙዕተዚላዎችም ቁርዓን ፉጡር ነው የሚለው ፈተና በኢማሙ አሕመድ ፅናት ተወግዶ አላህ ሱናን የበላይ አደረገው ። ይህ እንግዲህ ሙዕተዚላዎች ከነበራቸው አቅም ጋር ነው ።
እነደዚሁ አላህ ሱናን በሸይኹል ኢስላም ፅናት ከሞንጎሊያዎች ፣ ከሺዓዎች ፣ ከአሻዒራና አምሳዮቻቸው ፈተና ጠብቆታል ።
አሁንም በሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሀብ ፅናት ዱኑን እንዴት ህያው እንዳደረገው ለአሁኑ ትውልድ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው። ታድያ እነዚህ ሰዎች ብዙ ሆነው ሳይሆ ተዓምር የሰሩት በአላህ እርዳታ ታግዘው በነበራቸው ፅናት ነው ።
እኛም በሱና ላይ ፀንተን ለሱና ዘብ ከቆምን የአላህ ርዳታ ታክሎበት ሱናን የበላይ ማድረግ እንችላለን ሜዳ ውስጥ ሳንገባ ተሸናፊ አንሁን ።

https://t.me/bahruteka

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

11 Oct, 10:49


احذر أن تكون ثناء منشورا وذنبا مستورا ..!!

https://t.me/abuumuawiya

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

11 Oct, 05:22


🔷 ለዲን እውቀት ተማሪዮች

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያላች ጡላበል ዒልሞች በሀገር አቀፉ ኮንፈረስ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉና መምጣት ከቻላችሁ የመግቢያ ትኬት ወንድሞቻችሁ ሊያመቻቹላችሁ ቃል የገቡ መሆኑን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ። በመሆኑም አንድም የዲን እውቀት ተማሪ በትኬት እጦት ምክንያት እንደማይቀር ለመግለፅ እንወዳለን ። ነገር ግን በሚማሩባቸው መሻኢኾች በኩል መምጣት የሚኖሩባቸው መሆኑን እናሳውቃለን ።

http://t.me/bahruteka

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

11 Oct, 04:49


🔷አንጀት አራሽ ቅስቀሳ......!!

በኢትዮጵያ አህሉ ሱንና ኢስላማዊ ማህበር አዘጋጅነት የፊታችን እሑድ ጥቅምት 03 በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚካሄደው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ለሰደቃ የተደረገ ቅስቀሳ።



🎙 أستاذ أبو حسان محمد بن بركا  السلطي السلفي المشهور بكرماني حفظه الله تعالى

🎙 ኡስታዝ አቡ ሀሳን ሙሐመድ በረካ (ኪርማኒይ) አላህ ይጠብቃቸው!

1000 650 550 718
ሙህዲን ሳሊህ እና ዩሱፍ ከድር...


🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝙜𝙧𝙪𝙥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/conference1447
https://t.me/conference1447
https://t.me/conference1447

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

10 Oct, 16:32


     👉 የምቀኝነትን እሳት የሚያጠፋው የተመቀኙበት አካል ብቻ ነው ።

   ውድ እህትና ወንድሞች ለፕሮግራሙ ከሚያስፈልገን ወጪ 1/3ኛው እንኳን አልተሸፈነም ። የተሸጠው ትኬት ወደ 600 አካባቢ ነው ። ለአዳራሽ ኪራይ 810 ሺህ ብር ነው የሚያስፈልገው ። ለዛሬ ነበር እንደምንም ለምነን ወደ ጠዋት ዞሮልናል ። በህልሜም እንዲህ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር ።
      ትልቁ ስራ የመንግስት ፈቃድ ነበር ። በጣም በሚያስደስት ሁኔታ መንግስት ለሱናው ማህበረሰብ እውቅና ሰጥቶ ከላይ እስከታች ያለው የፀጥታው መዋቅር የሚገርም ትብብር ሲያደርግ እኛ በዚህ ደረጃ ስንሆን ደስ አይልም ።
     ሌላው ለተውሒድ ዳዕዋ ሰፊ ቦታ ተከራይቶ ወጪውን ለመሸፈን ትኬት መሸጥን ለምኖ ለመክበር ታስቦ የተሰራ ለማስመሰል የሚሯሯጡ አካላት እስኪ እናንተ ለምናችሁ አላማችሁን አሳኩ ነው የምንለው ።
     የምቀኝነትን እሳት የተመቀኙበት አካል ካልሆነ ከምቀኛው ውስጥ የሚያጠፋው የለም ። ውስጥ ውስጡን እያቃጠለ ያጠፋዋል እንጂ ። የተመቀኙበት አካል ግን ለምቀኛው መልካም በመስራት የውስጡን እሳት ሊያጠፋለት እንደሚችል አላህ ነግሮናልና አላህ ሂዳያ ይስጣቸሁ ከማለት ውጪ የምንሰራላቸው መልካም ነገር የለንም ።

http://t.me/bahruteka

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

10 Oct, 13:38


مِن أعجبِ العجاب وجودُ مَن يَدَّعُوْنَ أنهم مِن أهل السنة والجماعة وهم يُحَارِبُونَ السلفيين أَشَدَّ المُحاربةِ وأمواتٌ على أهل البدعة نسأل اللهَ السلامة والعافية.

وترى أمثال هؤلاء الخبثاء يَسْعَونَ لِإِسقاطِ علماءِ السنة وَدَعوتِهِم وتشويه سُمعَتِهِم بشتى الطرق،تارة بِسَبِّهِم وتارة بالكذب عليهم وتارة بِوَصفِهِم بِغُلاة التجريحِ أو حدادية أو متشددين وتارة بقولهم: إنهم مُتسرعون.

فكل هذا أتوا به وابتكروه لكي يُنفروا الناس عن الدعوة السلفية عن دعوة الحق. وهم يسعون لإماتة الدعوة السلفية وأهلها أشدَ السعي.

يا أيها المغرور! إلى متى؟ ومتى تفيق؟

أنت تَسْكُتُ عن دُعَاةِ الفتنة دُعاةِ الإخوان المفلسين ودعاة أفراخ هؤلاء المفلسين ولا تُحَذِّرُ عَنهم وهم يتلاعبون على الدعوة السلفية وأهلها ويؤيدن البدع وأهلها وَتَتَكَلَّمُ عَلى عُلماءِ السُّنَّةِ ودُعاةِ السنة وَتُحارِبُهم وتُحذِّرُ منهم وَتُنَفِرُّ النَّاسَ عنهم ؟! أَيُّ دينٍ هذا؟! فسبحان من خلق مثل هؤلاء.

قال الله تعالى: {{وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنْسِ وَالْجِنِّ يُوحِي بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ زُخْرُفَ الْقَوْلِ غُرُورًا ۚ وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ مَا فَعَلُوهُ ۖ فَذَرْهُمْ وَمَا يَفْتَرُونَ (١١٢) وَلِتَصْغَىٰ إِلَيْهِ أَفْئِدَةُ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ وَلِيَرْضَوْهُ وَلِيَقْتَرِفُوا مَا هُمْ مُقْتَرِفُونَ}} سورة الأنعام.

📚📚 قال فضيلة الشيخ العلامة ربيع بن هادي المدخلي – حفظه الله تعالى وختم له بالحسنى – :

"كل ما وصفوا به أهل السنة هم برآء منه ولا يلحقهم شيء منه، وإنما هو من افتراءات وأكاذيب أهل البدع ؛ فإنهم لِخُلُوِّ أَيدِيْهِم مِنَ الْحُجَجِ وَالْبَراهِيْنِ التي يجابهون بها أهل السنة يَلْجَئُونَ إلى الكَذِب.

وهذا حال أهل البدع في كل زمان ومكان لا يستطيعون محاربة أهل السنة إلا بالإشاعات الكاذبة والافتراءات الظالمة، وهذا موجود الآن على وجه أقبح وأشد في محاربة أهل السنة .

"...أَهلُ البدعِ الآن من أكذب الناس حتى إنهم قد يَفُوقون الكفار في الكذب،

الروافض والأحزاب الضالة المنحرفة فيهم من الكذب والافتراء ما لا يعلمه إلا الله.

وكم كالوا من التهم والسباب والتشنيعات لأهل السنة في هذا العصر، ولا سيما قد ساعدتهم وسائل، مثل الوسائل الإعلامية التي استغلوها في حرب أهل السنة؟!

حَربُ أَهلِ السنةِ وَاللهِ حَربٌّ لِلإسلامِ نفسِه، وَإن تستروا به وتلحفوا به فإنهم يحاربون الإسلام؛ لأن أهل السنة على كتاب الله وعلى سنة رسول الله في عقائدهم ومناهجهم وأخلاقهم وأعمالهم، فهؤلاء يحاربونهم من أجل هذه العقائد والأخلاق والأعمال التي استمدوها من كتاب الله ل ومن سنة رسول الله ﷺ!". اهــــــ [المجموع ٢ / ٣٣١].


ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺟﻌﻠﻨﺎ ﻫﺎﺩﻳﻦ ﻣﻬﺘﺪﻳﻦ، ﻏﻴﺮ ﺿﺎﻟﻴﻦ ﻭﻻ ﻣﻀﻠﻴﻦ، ﺳﻠﻤﺎ ﻷﻭﻟﻴﺎﺋﻚ، ﻭﺣﺮﺑﺎ ﻋﻠﻰ ﺃﻋﺪﺍﺋﻚ، ﻧﺤﺐ ﺑﺤﺒﻚ ﻣﻦ ﺃﺣﺒﻚ، ﻭﻧﻌﺎﺩﻱ ﺑﻌﺪﺍﻭﺗﻚ ﻣﻦ ﺧﺎﻟﻔﻚ.
اللهم أرنا الحق حقا وارزقنا اتباعه
وأرنا الباطل باطلا وارزقنا اجتنابه
وارزقنا الثبات على الحق حتى نلقاك برحمتك يا أرحم الراحمين.

🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

قَــال رَسُـــــولُ اللهِ
صلى الله عليه وسلم:
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹 "...وَالكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ" رواه مسلم🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በአሏህ ፍቃድ የተለያዩ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ።👇👇👇👇👇👇👇👇


አቡ ኑዐይም - Sultan Hassen
ይህ የአቡ ኑዐይም ሱልጣን ሐሰን ቻናል ነው
https://t.me/abunueaymsultanhassen

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

09 Oct, 19:17


ምስጋና መግለጽን ይመለከታል

የኢትዮዽያ አህሉሱና ኢስላማዊ ማህበር አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ ጥቅምት 3/2017 የሚያካሂደው ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረስ እንዲሳካ ከቀልጣፋ አገልግሎት ጋር ከፍተኛ ትብብር ላደረጉለት:–
➡️ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት
➡️  ለሰላምና አስተዳደር ቢሮ
➡️  ለመረጃና ደህንነት ዋና ቢሮ
➡️  ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና
➡️  ለአ/አ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
     በራሱና በሱናው ማህበረሰብ ስም ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል ።

የኢትዮዽያ አህሉሱና ኢስላማዊ ማህበር
https://t.me/alateriqilhaq/5140

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

09 Oct, 17:11


🔷የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር አጭር መልዕክት
=========================

በኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀውና በአይነቱ ልዩ የሆነው  ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ፣ አዲስ አበባ ላይ ይታወቃል።
ስለሆነም የእሁድ ስለተዘጋጀው የሚሊኒየም ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍረንስ በተመለከተ በተከበሩ ሸይኽ ሐሰን ገላው ሀፊዞሁሏህ እና ኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ የሰጡት አጭር መልእከት።

በተጨማሪም:- በአሏህ ፍቃድ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መሻይኾች፤ ኡስታዞች፣ ዱዓቶች፣ ይኖራሉ።

ቀን:- ጥቅምት 3/2017

ቦታ:- በሚሊኒየም አዳራሽ (ቦሌ ኤርፖርት አጠገብ)

ከአቅም በላይ በሆነ ኡዙር ምክናየትበአካል የማትገኙ የተላለፉ ጠቃሚ መልዕክቶችን በባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ የቀጥታ ስርጭት (online) በአሏህ ፍቃድ የሚተላለፍ ይሆናል ስለሆነም አስፈላጊዉን ዝግጅት አድርጋችሁ ለወዳጅ ዘመድዎ፣ ለጓደኛዎ፣ለስራ ባልደረባዎ በመጋበዝ ጠብቁን።

የኮንፈረንሱ መሪ ሀሳብ:-
'' ዲናችንን ማወቅ፣ መተግበርና ማስተማር'' በሚል

የመግቢያ ትኬትዎን ቶሎ ከእጅዎ ያስገቡ!

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

09 Oct, 14:00


🔷   ሰበር የምስራች

         የታላቁ ኮንፈረንስ ቀንና ቦታ 

በኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀውና በአይነቱ ልዩ የሆነው  ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ፣ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።
ቀን:- ጥቅምት 3/2017
ቦታ:- በሚሊኒየም አዳራሽ
(ቦሌ ኤርፖርት አጠገብ)

የኮንፈረንሱ መሪ ሀሳብ:-
ዲናችንን ማወቅ፣ መተግበርና ማስተማር

የመግቢያ ትኬትዎን ቶሎ ከእጅዎ ያስገቡ!

የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

08 Oct, 06:38


በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ

የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “ዲናችንን ማወቅ መተግበርና ማስተማር”

🏝 የኢትዮጵያ አህለ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ታላቅ ሀገር ቀፍ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጥቅምት ላይ   በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አስቧል።
ለዚህ ፕሮግራም የአዳራሽ ኪራይ፣ ለተሳታፊዎች ሻይ ቡና ፣ ለዑለማዎች ትራንስፖርትና ማረፊያ ወዘተ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት 1000 ብር ነው።

🔹 ስለሆነም ትኬት በአካል መግዛት ለምትፈልጉ፦
➡️  አል ኢስላሕ መድረሳ
➡️  ዳሩ ሱና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🔹በባንክ አካውንት ለምትጠቀሙ
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000650550718
          ሙሒዲን ሳሊሕ እና ዩሱፍ ኸድር

   የኢትዮዽያ አህሉ ሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

05 Oct, 18:21


#አዲስ_መፅሐፍ
👉 በ ቅ ር ብ ቀን

አንድ ሰው ከሰለፍያህ የሚወጣው መቼ ነው?❞ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ በዘመናችን ለተከሰቱ ፊትናዎች መፍትሔ የሚሆን ወሳኝ ኪታብ ነው።

📝 ዝግጅት፦ የተከበሩ ሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን ኢማም አቡ ጦልሃ አል`ወሎውይ አላህ ይጠብቃቸው!

📨 ለማንኛውም ጥቆማ ➴➷➴
https://t.me/AbuImranAselefybot
                ➚➶➹ ብቅ ይበሉ

🏝 የኪታቡ pdf በሸይኹ ቻናል እና በሌሎችም ቻናሎች በቅርቡ ይለቀቃል።
➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

05 Oct, 18:20


https://t.me/abuabdurahmen?livestream=09b3d6456fec97960a

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

03 Oct, 23:09


አዲስ የተጠናቀቁትን 7 ኪታቦችን ጨምሮ በሸይኽ አቡዘር ሀሰን አላህ ይጠብቃቸው ከ35 በላይ ዱሩሶች በቅደም ተከተል ያለበት ሊንክ ነው።

1ኛ የኡሱሉ ሰላሳ (ሰላሰቱል ኡሱል)
👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/46

2ኛ  የ አርባዒን ሓዲስ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/74

3ኛ ኪታቡ አት– ተውሒድ  ሊሸይኽ ሙሀመድ  ብን አብደል ወሃብ
👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/190

4ኛ  "አዕላሙ ሱና "ሙሉ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/275

5ኛ  ሸርሁ ሱና ሊል በርበሃሪይ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/340

6ኛ  አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/530

7ኛ  መንዙመቱል ሙቀዲመቱ አል ጀዘሪይ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/578

8ኛ  ቱህፈቱል አጥፋል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/603

9ኛ  መስዓለቱ ዑዝር ቢል ጀሕል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/811

10ኛ  ሙቀዲመቱ ኡሱሉ ተፍሲር
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/847

11ኛ አነ—ሕዉል ሙስተጧብ ክፍል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/932

12ኛ አነ—ሕዉል ሙስተጧብ ክፍል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1032

13ኛ አል መውሪዱል ዓዝቡ ዙላል 
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1205

14ኛ አል አቂደቱል አጡሓዊያህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1262

15ኛ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1292

16ኛ አል በራሂኑል ሙረሰዓህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1389

17 አል አቂደቱል ዋሲጢየህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1448

18 ቡሉጉል መራም ሚን አዲለቲል አህካም
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1452

19 በሰዎች ላይ የ "አል-ጀርህ እና አት-ተዲል" ኢማሞች ንግግር በኢጅቲሃድ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በመረጃ ላይ የተመሰረተ ነው።
أقوال أئمة الجرح والتعديل في الرجال من باب الإخبار لا من باب الإجتهاد
ለኸድር ኬሚሴ የተሰጠ ምላሽ
ሙሉ ደርስ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1815

20  የኪታቡ ስም = "ኪታቡ አት– ተውሒድ  ሊሸይኽ ሙሀመድ  ብኑ አብደል ወሃብ "ሙሉ ደርስ" ከአል ቀውሉል  ሙፊድ ማብራሪያ ጋር
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1880

21 መሳኢሉ አል-ጃሂሊያ مسائل الجاهلية
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1993

22 መንሃጁል-አንቢያእ منهج الأنبياء
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2027

23 ከሽፉ አሽ-ሹቡሃት
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2133

24 መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2165

25 አል ኡሱሉ አስሰላሳህ (አዲስ)
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2229

26 ቀዋዒዱል አልአርበዓህ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2257

27 አል ቀሲደቱ ላሚያህ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2263

28 የالدرة المضية ሙሉ ደርስ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2273

29 የ نخبة الفكر ሙሉ ደርስ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2303

30 ኢጅማዑል ኡለማዕ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2327

31 አርበዑነ-ነወውያህ (አዲስ)
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2452


32ኛ መንዙመቱበይቁኒይ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2505

33ኛ ቀሶሱሱከር ነዝሙ ኑኽበቲል ፊከር
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2520

34ኛ ቀሲደቱ ገዘልያህ ፊ አልቃቢ አልሀዲስ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2555

35ኛ አል
ወረቃት
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2559

36ኛ ተስሂል
ጡሩቃት ፊነስሚል ወረቃት
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2618

37ኛ ነዝሙል ቀዋኢድል ፊቅሂያህ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2679

38ኛ አል˙ከሊማቱል ሂሳን ፊ′በያኒ ዑሉዊራህማን
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2712

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

02 Oct, 12:02


🔷 ወንድማዊ ምክር

በአንድ የዋትሳፕ ወይም ሌላ ግሩፕ ላይ ለምትሳተፉ ወንድና ሴት ሙእሚኖች ። የዚህ አይነቱ በአንድ ግሩፕ ላይ መሰባሰብ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ሁኔታ ነው ። እሱም በሚከተለው መልኩ ከሆነ ነው :–
-- ስለ ዲናዊ ጉዳይ ለመነጋገር ።
-- ከዲናዊ ጉዳይ ውጪ አላስፈላጊ የሆኑ ወሬዎች ከሌሉ ።
-- ሴቶች ሃሳባቸው አጠር ባለ መልኩ ማስተላለፍ ከተቻለ ሴት መሆናቸው እንዳይታወቅ ቢያደርጉ ይመረጣል ።
-- በየ ሀሳቡ እየገቡ ታዕሊቅ አለማድረግ ።
-- በግል ወይም በውስጥ መስመር አለ መፃፃፍ ። ለሸሪዓዊ ጉዳይ ከሆነ የሚፃፈው ነገር ማንም ሰው ሊያየው የሚችል ሆኖ ምንም አይነት ወደ ሌላ የሚወስድ ነገር የሌለ ከሆነ ።
-- ምንም አይነት የፈገግታ ምልክት ወይም ሌላ አይነት ተቃራኒ ፆታን የሚስብ ነገር አለመጠቀም ።
-- የሳቅ ምልክት የሆኑ ፊደሎችን አለመላክ ።
-- በምንም መልኩ በቅላፄ ወይም በለሰለሰ ድምፅ አለ ማናገር ።
-- በተሳትፎ ላይ የወንዶችን እይታ ለመሳብ የሚደረግ ነገር እንዳይኖር ማድረግ ።
እነዚህና የመሳሰሉትን ገደቦች ተጠብቆ ነው መሆን ያለበት ።
ከመሆኑም ጋር በጣም የተመረጠውና የሚወደደው ሴቶች በሴቶች ግሩፕ ወንዶችም በወንዶች ግሩፕ ለብቻ ብቻ መሆኑ ነው ።
በአሁኑ ጊዜ ለቁርኣን ተብለው የሚከፈቱ ግሩፖች የፈሳድ ምንጭ እየሆኑ እንደሆነ ብዙ እህቶች እየተናገሩ ነው ። ሴቶች ቁርኣን መቅራት ያለባቸው በሴቶች ነው ። ምክንያቱም በቁርኣን ድምፅን ማሳመር አስፈላጊ ስለሆነ ። አንዲት ሴት ለአጅ ነብይ ወንድ ድምፇን እያሳመረች መቅራት አይፈቀድላትም ። የሴት ልጅ ድምፅ አውራ ነው የሚሉ ዑለሞች እንዳሉ የሚታወቅ ነው ። በዚህ ላይ ቅላፄና ማሳመር ሲጨመር የሚመጣውን ፊትና ማሰብ አይከብድም ።
የሚገርመው የቁርኣን ግሩፕ ተብሎ ወንድና ሴት መሰብሰቡ ነው ። የዚህኛው ፊትና በጣም የከፋ ነው የሚሆነው ። እህቶችም እያማረሩ ያሉት ለቁርኣን ተብሎ ተከፍቶ በውስጥ መስመር እያስቸገሩን ለመቅራት አልቻልንም እያሉ ነው ።
ይህ ጉዳይ በጣም ለሱና የቀረቡ ጠንካራ የሚባሉ እህትና ወንድሞች የተፈተኑበት ጉዳይ ነው ። በመሆኑም እህቶች አላህን ፈርታችሁ ከእንደዚህ አይነት ግሩፕ ውጡ ። የዚህ አይነት ግሩፕ የምትከፍቱ ወንድሞች ከአህን ፍሩ ከማለት ውጪ የሚባል ነገር የለም ።
ንፁህ የሆነው ሸሪዓ የመጣው ወደ ፊትና ( መፍሰዳ ) የሚያደርሱ መንገዶችን ለመዝጋት ነው ።
እኔ አልፈተንም የሚል የተፈተነ ሰው ብቻ ነው ።
ስለዚህ ይህንን ጉዳይ በቀላሉ ማየት በራስ ዲን ላይ መጫወት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል ።
ለደርስና ለሙሀደራ የሱና ወንድሞች ቻናሎች ስላሉ በግሩፕ አንድ ላይ ለመሆን የሚያስገድድ ነገር መኖሩ በደንብ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው ።
አላህ መልካሙን ሰምተው ከሚከተሉት ያድርገን

  http://t.me/bahruteka

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

02 Oct, 05:43


#አስፈላጊ_ኪታብ
📖
📖📖📖📖

🔎 የኪታቡ ርዕስ፦ ➷➴➷
📚  حُكْمُ التَّصْوِيرِ وَالفِيدِيو.
📚 «የቀረፃ እና ተንቀሳቃሽ ምስል ፍርድ»

📝 ዝግጅት፦ ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸው

📷🤳 በፎቶ እና ቪድዮ ዙሪያ መሰረታዊ እውቀት የሚገኝበት ወሳኝ ስራ ነው።

👌ጉዳዩ በዘመናችን ያለ እና ልናውቀው የሚገባ በመሆኑ በትኩረት አንብቡት


👉 በአግባቡ አንብበን ለመረዳት አንችልም በማለት መሳቀቅ የለም! ምክንያቱም ሸይኹ ራሳቸው በቅርቡ በደርስ መልክ ያቀርቡታል። ማስታወቂያውን ጠብቁ!

➷➷➷➷➷
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/10970

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

02 Oct, 05:43


#አስደሳች_ዜና
=========>

ቀደም ሲል حُكْمُ التَّصْوِيرِ وَالفِيدِيو «የቀረፃ እና ተንቀሳቃሽ ምስል ፍርድ» በሚል ርዕስ በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸውና በአረብኛ ተዘጋጅቶ የቀረበው አስፈላጊ ኪታብ አሁን ደግሞ አረብኛ በአግባቡ ለማይገነዘቡ እና ሀሳቡን በዝርዝር ማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ የኪታቡ አዘጋጅ ሸይኽ አቡ ዘር በደርስ መልክ ለመስጠት ፕሮግራም ይዘዋል።

🏝 ደርሱ የሚሰጠው በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሲሆን በመላው አለም የምትገኙ ደግሞ በቀጣዩ የሸይኽ አቡ ዘር የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

🏝 https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

=> ደርሱ የሚሰጥበት ቀን
🕛 ዘወትር ጁምዓ እና ቅዳሜ ከኢሻ ሶላት  በኋላ ይሆናል።

📮 ኪታቡን print በማድረግ መከታተል የምትፈልጉ ለprint የሚመች pdf ይለቀቅላችኋል።

በኪታቡ ዙሪያ ያገኛችሁት ክፍተት ካለ ወይም ጥቆማ ወይም ማንኛውም ሀሳብ ለመስጠት
➷➴➷
https://t.me/AbuImranAselefybot

ለተጨማሪ ትምህርቶች
➴➷➴➷➴
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/10971

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

01 Oct, 15:04


📢 አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ
       ======>
          【የመልካም ስራ ጥሪ!】

↪️ ውድና የተከበራችሁ የሱና እህቶችና ወንድሞቻችን እንሆ ነገ ማክሰኞ እህታችንን ካለችበት ህመም ለመታደግ በተከፈተው ግሩፓችን ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልክ የደዕዋ የኒያና የገቢ ፕሮግራም አለን።

🪑ተጋባዥ እንግቻችን፦

🎙 ኡስታዛችን አቡ ሀሳን ሙሀመድ ኪርማኒይ حفظه الله تعالى

 ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ሰዓት
ከምሽቱ 03:00:00 በኢትዮ

እስከዛው በቻልነው ያክል የእህታችንን እንባ እናብስላት። በመነየ፣ ገቢ በማድረግ አድ (ሰዎችን ወደ ግሩፑ በመጋበዝ)፣ ሼር በማድረግ እና ከምንም በላይ በዱዓችሁ አስታውሷት እስከዛሬ የነየትን ገቢ በማድረግና አሁንም ነይታችሁ ገቢ ማድረግ ምትችሉም ገቢ በማድረግ እህታችንን ካለችበት ህመም እንታደጋት እናም በተለይ የቻናል ባለቤቶችና ባለ ግሩፖች ሸር በማድረግ አግዙን።ባረከላሁ ፊኩም!


👉 ወደ ግሩፑ ለመግባት ይችን ነካ ያድርጉ
📱👇👇👇👇👇
https://t.me/ye_selefiyoch_eht

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

30 Sep, 05:37


📢 አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ
       ======>

          【የመልካም ስራ ጥሪ!】

↪️ ውድና የተከበራችሁ የሱና እህቶችና ወንድሞቻችን 
እንሆ የፊታችን ጁሙዓ እህታችንን ካለችበት ህመም ለመታደግ በተከፈተው ግሩፓችን ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልክ የደዕዋ የኒያና የገቢ ፕሮግራም አለን

🪑ተጋባዥ እንግዶቻችን፦
🎙 ኡስታዝ አቡል በያን ኑራዲስ አልቡታጀሪይ አላህ ይጠብቀውና!
↪️ «ርዕስ በሰዓቱ ይገለፃል»

🎙 ኡስታዛችን አቡ ሀሳን ሙሀመድ ኪርማኒይ ቡኻሪ አላህ ይጠብቅልንና!
↪️ «ርዕስ በሰዓቱ ይገለፃል

🎙እንዲሁም ሌሎችም እንግዶች ይኖሩናል ኢንሻአሏህ!

 ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ሰዓት
ከምሽቱ 03:00:00 በኢትዮ

እስከዛው በቻልነው ያክል የእህታችንን እንባ እናብስላት። በመነየ፣ ገቢ በማድረግ አድ (ሰዎችን ወደ ግሩፑ በመጋበዝ)፣ ሼር በማድረግ እና ከምንም በላይ በዱዓችሁ አስታውሷት እስከዛሬ የነየትን ገቢ በማድረግና አሁንም ነይታችሁ ገቢ ማድረግ ምትችሉም ገቢ በማድረግ እህታችንን ካለችበት ህመም እንታደጋት እናም በተለይ የቻናል ባለቤቶችና ባለ ግሩፖች ሸር በማድረግ አግዙን።ባረከላሁ ፊኩም!


👉 ወደ ግሩፑ ለመግባት ይችን ነካ ያድርጉ
📱👇👇👇👇👇
https://t.me/ye_selefiyoch_eht

3,459

subscribers

329

photos

181

videos