አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku @adhanom05 Channel on Telegram

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

@adhanom05


ነጋ

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku (Amharic)

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku በአማርኛ፣ ከእንግሊዝ አፍሪካ የሚገኝ በእናት ቤተሰብ ማክሰኞ፣ ቅዳሜ፣ አርብሳና ቅዳሜ በተከሰተው የአድኃኖም ቴሌግራም ፕሮግራም የምትኩ ምርጥ የውስጥ አዳዲስ ዝግጅትን በቀላሉ ለመስራት የሚችሉትን አዝናኝ ቪዛን ለመሸጥ በመደበኛው ቀጥሎ በማግኘት እና በፍጥነት በሚከተለው ቪዛን ውስጥ የሚከተለውን ቁልፍ ለመስራት የሚቷሉን ቪዛን አሳይቷል። በአድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku አማርኛ እና አልፈው አልፈው በሆዳችን ይገኛል። የአጠቃላይ ድርጅት ያለውን አዝናኝ ቪዛን ከአድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku ላይ ማዘጋጀት እና ለማግኘት እባኮት ይመዝገቡ።

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

08 Feb, 21:14


ጊዜ ሃያል ነው ። የከበደን ይቀላል ፣ ግራ የገባን መስመር ይይዛል፣ የምንፈራውን ስናየው ሳቅ ይታገለናል።

አሻግረን ብርሃን እናያለን  ፤ጠንክረን እንሰራለን ፤ ያሸነፍን ሲመስለን አንታበይም ፤ በወደቀ ላይ አንፈርድም ፤በትንሽ በትልቁ አንማረርም ፤በረባው ባረባው አንቀደድም  ፤ላለው አናሽቃብጥም ።

ስንገሰፅ እንሰማለን ፤ ቅር ያለንን እናሳያለን ፤ ስንወድ መውደዳችንን አንደብቅም ፤ ስናደንቅ አድንቆታችን ለሚገባው ሰው እንሰጣለን ።

ድክመት ድክመት ላይ አንመሰጥም ፤ ውድቀታችንን ጠቅልለን አናላክክም ፤ ይሉንታ ቢስ አንሆንም ።

ግፍን እንፈራለን ፤ ያዘነ ላይ አንስቅም፤ የጉብዝና ወራታችን ወቅት አንመፃደቅም ።  መስገብገባችንን አደብ አናሲዘዋለን ፤ ውድድራችን ከራሳችን ትላንት ጋ ነው፤  ትግላችን ከህልማችን ጋ ነው።

ከትላንታችን እንማራለን ፤  ታላላቆቻችን እንሰማለን ታላላቆቻችን በምክንያት እንሞግታለን ፤ አድናቆታችን አምልኮት የለበትም ፤  ስኬታችንን በመርሃችን እንለካለን ፤ እራሳችንን እንገዛለን ።

የማይነጋ  ጨለማ የለም... ይነጋል ፣ የጠወለገው ይለመልማል ፣ የጎደለው ይሞላል ።

አሜን  🙏
     Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

08 Feb, 06:50


ትንሽ አምሮውን ያመዋል ። መቼ እንደለመደኝ መቼ እንደለመድኩት አላቅም ። ትልቅ ሰው ነው አጠር ያለ ነው አንገቱን ከመድፋት ብዛት አንገቱ ትንሽ ቁልምም ይላል ቀና ብሎ ሲሄድ አላቅም መሬት እያየ ነው የሚሄደው ...

ሲያየኝ ፈገግ ብሎ ነው ሁሌ ሙሉ ስሜን የሚጠራኝ ። ስምን ቁልምጫ የሚያደርገው ለካ አጠራር ውስጥ ያለው ቃና ነው !

የሆነ ቀን ልብስ ሰጠሁት አንድ ሁለቱን ወስዶ አንድ ሁለቱን ለኔ አይሆንም የወጣት ነው ይሄ ለሌላ ሰው ስጠው ብሎ መለሰልኝ ...

መኪና ይዤ ያየኝ ቀን ፊቱ ላይ ያየሁት ደስታ እና ኩራት አበዛዝ ...የሆነ ቀን መኪናዋን ሸጥኳት ባገኘኝ ቁጥር ለብዙ ግዜ መኪናህስ? መኪናህን አትነዳትም ? መኪናህን አቁመሃት ነው
መኪናህስ ? ጥያቄውን አደባብሼ አልፈዋለሁ

የኮራበትን መኪና ሸጥኩበት ኣ !

ግርማ መኪናውን እኮ ሸጥኩት አልኩት ። ግዴለም ሌላ ግዜ ደሞ ትገዛለህ ብሎ አፅናናኝ

University እየተማርኩ ባገኘኝ ቁጥር
ከአንደኛ አመት ጀመሮ መቼ ነው የምትመረቀው ይለኛል
ከሶስት አመት በኋላ ከሁለት አመት በኋላ በዚህ አመት እያልኩ እነግረው ነበር የሆነ ቀን የመመረቂያችንን እለት ሰምቼ ስለነበር

መቼ ነው የምትመረቀው ሲለኝ
ሃምሌ 15 አልኩት። ለአንድ ለሁለት ወር ከአስራምስት ቀን የሆነ ቢሮ intern ስራ ጀመርኩ ተጠፋፋን ... መግቢያ መውጫዬን ቀየርኩ

ሀምሌ 15 ለምርቃቴ ስጦታ አሽጎ አመጣልኝ
የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ነው እንዲ ይላል

"እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። መዝሙረ ዳዊት 136:1

ለብዙ አመት ከአልጋዬ ፊት ለፊት ሰቅዬው አየው ነበረ

የተሰማኝ ደስታ ፣ኩራት ወደር አልነበረውም ተሰጥቶኝ በዛ ልክ ደስ ያለኝ ስጦታ ጥቂት ነው ።

ግርማ በደረቁ ገንዘብ ስጠኝ አይለኝም ቻርጀር ግዛልኝ፣ ለሬድዮኔ ባትሪ ግዛልኝ ፣የስልኬ ባትሪ አልሰራ አለ ፣እያለ ነው ገንዘብ የሚጠይቀኝ

ስሰጠው ለፍቶ ካስተማረው ታናሽ ወንድሙ የተቀበለ አይነት ነው አቀባበሉ ምስጋና አያበዛም ደረስክልኝ ጎሽ ኑርልኝ ፈገግታ ይሰጠኛል

ካዛንችሳችን እየፈረሰብን የነበረ ሰሞኑ" በቃ ተለያየን አይደል" አለ እንደ ድሮ ሲጠራኝ ፈገግ ብሎ አልነበረም ..ለመጨረሻ ግዜ ያተያየነው ያኔ ነው ።

አሁን ግርማ አርፏል ቀብር አምስት ሰዓት አሉኝ

ፈገግ እያልክ ስለጠራኸኝ ፣
እንደምትወደኝ ስላሳየኸኝ ፣
ቅር ያለክን በስሞታ መልክ ስለምትነግረኝ ፣ በምንም ሆኔታ ውስጥ አይተኸኝ ሰላም ሳትለኝ ስለማታልፍ ። እቤት እመጣለሁ ብለህ በቀጠሮ ስለምትመጣ፣

ችርስ 😪😪

May his soul find eternal peace and everlasting comfort.

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

03 Jan, 10:46


ሦስት የተለያየ ጊዜ የተነቀስኩት ንቅሳት አለ።

የግራ ክርኔ ላይ በላቲን ቋንቋ እንዲህ ይላል 'Veni Vidi Vici' "መጣሁ፣ አየሁ፣ አሸንፌ ሄድኩ" ዓይነት ነው ትርጉሙ። 'university' ተማሪ እያለሁ ነበር የተነቀስኩት ።

ድሮ ሕይወት ማሸነፍ ትመስለኝ ነበር። ዓለምን የማበጃጃት ይመስለኝ ነበር ።

ደርሼ ሳይ ግን እንደሱ አልሆነም!

መጀመሪያ የነቀሰኝ ልጅ ጋር ሄጄ የቀኝ ክርኔ ላይ 'Amor Fati' የሚል ተነቀስኩ፤ ይሄም ላቲንኛ ነው።  "ዕድልን መውደድ" ይሉት ትርጉም አለው። ዕድል ሁሉ የሚወደድ መስሎኝ ነበር።

ምድር ርህራዬ ያላት፤ የምትሰጠው ሁሉ የምንችለውን፤ መስሎኝ ነበር...ግን ዕድል የሚሻሟትም እንደሆነ አየሁ።

ላስታውሰው የማልፈልገውን ሽንፈት ጠጣሁ። እየመረረኝ... እየጎመዘዘኝ...ተጋትኩ።

I stand alone and stumble.

ሦስተኛው እንደ ድሮ ንቅሳቴ ብዙ ሰው በማይረዳው ላቲንኛ አይደለም። በቲሸርት ስሆን በሚታይ መልኩ ተነቀስኩ። የማወሳስበው ነገር የለኝም። ለማጨስ ውሰጥ ለውስጥ አልሄድም። ሱቁ ጋር ነው ሲጋራዬን የምለኩሰው፤ ማንንም ለማስደመም ቃላት አላሳምርም። የጉብዝናዬን ወራት አልተርክም።
. . .

ለሦስተኛ ጊዘ ተነቀስኩ...

'Tired soul' ይላል።

'መሸነፍን ቆዳ ላይ ማሳል ምን ጥቅም ይሰጣል?' አለኝ ።

"ማሸነፍንስ ቆዳ ላይ ማሳል ምን ጥቅም አለው?" አልኩት።

'ጥሩ ጊዜ ሲመጣልህ፤ ንቅሳቱ ክፉ ነገርህን እንዳያስታውስህ ነው!' አለኝ።
  
አላመንኩትም!

ስንቴ ወድቄ እጅ እንደ ሰጠሁ አላወቀም። መውደቅን ማመን ካላስፈላጊ መጋጋጥ እንደሚያድን አላወቀም ። መውደቅን ማመን ካላስፈላጊ ትግል እንሚያድን አያውቅም።

ይልቅ...

እንዴት እንደወደኩ በጠይቀኝ  ... !!
       ©   Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

29 Dec, 07:27


አባቴ መጠጥ ወዳጅ ነው... ግን ሰክሮ የረበሸበትን አንድም ቀን አላስታውስም። ሲጠጣ ትንሽ ፈነሽነሽ ያለ ፊት ያሳየናል፣ በየመሃሉ ስማችንን እየጠራ...

'አጠፋሁ? ' ይላል ...

'ተመስገን!' ይላል ....

አደጉልኝ እያለ፥ ይወዱኛል እያለ፥ ጠጅ መጠጫ አላጣሁም፥ ሚስቴ ትወደኛለች፥ እያለ ነው መሰለኝ...!

አምሽቶ ከገባ ዘው አይልም፤ እናቴን "ዓለም ሆዴ ልግባ ?" ብሎ ነው። እናቴን ያከብራታል። ይወዳታል። ለኹለት አመት ከስድስት ወር የአልጋ ቁራኛ ሁናበት ታውቃለች። ጨቅላ ነበርኩ፤ ሌሎቹም ከኔ ብዙ አይበልጡም ነበር ...

እናቴ "እኔ ከታመምኩት በላይ ተጎሳቁሎ፤ ልብሱ ላዩ ላይ አልቆ ነው ያስታመመኝ" ትላለች።

እንደሚወዳት አሳይቷታል ፣እንደምትወደው ሲገባ ሲወጣ እየተንከባከበች አሳይተዋለች ።

"መርቀኝ እለዋለሁ..."

'እንደኔ የምትወድህ እኔ እንደምወዳት ዓይነት ሚስት ይስጥህ፤ ፍቅር ካለ ኑሮ ብዙ አይከብድህም። ስታጠፋ ከታረምክ ህይወት አታሸንፍህም።' ይላል።

መርቀኝ እንጂ ስለው።

'ደስ ብሎህ ኑር' ይላል ። ጌታዬ ለኔ እንደራራው ይራራልህ ይለኛል ።

"ትወደኛልህ እንዴ" ስለው።

ዝም ብሎ በስስት እያየኝ 'ጅል ነህ እንዴ?' ይላል።

ከዚህ ቤተሰብ ተወልደን እንዴት ፍቅር አያንበረክከንም ታድያ!?
©Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

08 Dec, 11:37


ጠብቀኝ ብቻ ነበር ያለቺኝ ....

ተሸበርኩ ፣ ግርግር ፈጠርኩ ፣ ትንሽ ብቻ ጠብቀኝ ያለቺኝ አይመስልም ነበር።

ከመጠበቅ ጋር ጥሩ ትዝታ የለኝም .....!

ወንድሜ እቤት ጠብቀኝ እንዳትወጣ ብሎኝ ወደ ውጪ ወጣ የሆነ ነገር ይዞ ነበር መሰለኝ እቃ ለመቀበል ይመስለኛል ።

ቆየ ....

ጩኸት ስሰማ ወጣሁ ግርግር አለ ግርግሩን እየገላለጥኩ ሳይ ወንድሜ ነው ። ወግተውት እያጣጣረ ... ሲያቃስት ደረስኩ .....ሆስፒታል ሳይደርስ ሞተ

እጮኛዬ ትንሽ ግዜ ስጠኝ ብላኝ እየጠበኳት መሞሸሯን ሰማሁ "እንኳን ደስ አለሽ አልኳት" ምን ይሰማት ይሆን? ትስቅ ይሆን? አሳዝናት ይሆን? ትሸልል ይሆን? ፀፀት ይሰማት ይሆን? ብቻ ያመመኝ መጠበቄ ነበር ።

አጎቴ ሁለት አመት ጠብቀኝ እኔ ያለሁበት አገር እወስድሃለሁ ለመኖር ህልምህን ለማሳካት ምቹ ነው ብሎኝ በአንድ አመት ከአስር ወር በኋላ ጠፋ ...ድምፁን ሰምተን አናውቅም

ጠብቀኝ ስባል እፈራለሁ .....

መጠበቄን ለመርሳት እርምጃ እቆጥራለሁ፣ ኮሚቴ አዋቅራለሁ ፣ የድሮ ህንድ ፊልም አያለው ፣ ድሮ አስረኛ ክፍል ስለህልሙ የነገረኝን የክላሴን ልጅ እንዴት ሆንክ ለማለት ስልኩን አፈላልጋለሁ ...በዚህ ሁሉ መሃል እየጠበኩ እንደሆንኩ ልቤ አይዋሽልኝም ።

ቁስላችን አይሞትም ይቀበራል እንጂ ።
©Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

07 Dec, 20:15


ጠንካራ መስያት ነው ። የምታየው ብቻ መስያት ነው ። ለሷ ያለኝ ቦታ ያሳየኋት እና የነገርኳት ብቻ መስሏት ነው።

ሌላም ሰው እኔ ያልኳትን ብሏት ዋሽቷት ስላገኘችው፤ ቃልም፣ ተግባርም ማመን አቁማ ነው ።

ስታገኘኝ 'Dead inside' የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት መልበሴን አላስታወሰችውም ።ሳቄ የቲሸርቴን መልዕክት ከልሎት ነበር ።

የማያቁኝ፣ ያልሰሙኝ የሰጡአት አስተያየት ልቧን ተጭኖት ነው ። የተሰበረ ሁሉ የሚጠገን መስሏት ነው ። ጊዜ ሁሌ አዳኝ መስሏት ነው ።

ከልጅነቴ ጀምሮ የሚራራልኝ አልነበረም!!

ልጅ እያለሁ:-

አባቴ ይወደኝ ነበር ። አንድ ነገር ሳይዝልኝ ቤት አይገባም ፣ ሳያጫውተኝ አይተኛም። መንገድ ስንሄድ እሽኮኮ ያደርገኝ ነበር ። ላገኘው ሁሉ "ልጄ ነው" ይል ነበር። ዘና ያለ ነው ፣ ሙዚቃ ይወዳል፣ ተጫዋችም፣ ዝምተኛም ፣ ሳቂታም፣ ኮስታራም ነበር ።

ከእናቴ ጋር ብዙ ግዜ ቢጨቃጨቁም ፤ ሁለቱም ይወዱኝ ነበር ። ፍቅር አሰጣጣቸው ለየቅል ነው ። ሰው ለሚወደው የሚሰጠው የሚችለውን ሁሉ ነው ።

የሆነ ቀን ፀባቸው ከሮ ፍርድቤት ቆሙ ። ይዘውኝ ሄዱ። የሚያወሩት ስለ መለያየት፣ ስለተቆራጭ ምናምን ነበር።

አይን አይኔን እያየ "አላምናትም፤ ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም" አለ ። አላመንኩም : ውሸቴን ነው ይላል ብዬ ጠበኩት ህይወት እንደዚ አይነት ቀልድ እንደማታውቅ አላቅም ነበር ።

ልጄ አይደለም ካለኝ በኋላ የተወራውን መስማት አልተቻለኝም ።

"ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም " ያለው ፊቱ ፣ ሁኔታው ድምፁ ፤ እርግጠኝነቱ ከልቤ አልጠፋ አለ።
እናቴ እጄን ይዛ ወደ ቤት ተመለስን ።

አደባባይ ላይ "ልጄ አይደለም" ያለኝ ከሰጠኝ ፍቅር ሁላ ስለበለጠብኝ ውስጤ ደነገጠብኝ ።

የሚታይ ነው የሚሰማ መታመን ያለበት ??

ለምን ይዘውኝ ሄዱ ? ፣ እማኝ ባለበት ስካድ ማየት እኔን ከማበላሸት ውጪ ምን ይጠቅማል ?? ያን ቀን አባት አልባ ሆኜ ተመለስኩ ።

ዘግኖ ባዶ ማግኘት ህይወት ውስጥ አዲስ አይደለም !!
© Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

06 Dec, 16:33


አባቴ ጥቁር ነበር ፊቱ አይፈታም። ወታደር ነበር መቶ አለቃም ነበር ። ፀጉር ጥቅጥቅ ያለ ነበር ። አናፂ ነበር ። ብዙ አያወራም ነበር ።

ይወደኝ ነበር ። ያለውን ብር አውጥቶ ሱሪ ጥልፍልፍ ጫማ አቡወለድ ይገዛልኛል ። አታጨማልቀው ይሉት ነበር ። መቶኝ አያውቅም ።

ከጁ ሲጋራ ከእጁ እኔ አልጠፋም ነበር ። ሲጋራ ሽታው አባቴን ስለሚያስታውሰኝ ሲጋራ እወዳለሁ ። ሲጋራ አጤሳለሁ ።

አባቴ ኮስተር እንዳለ ነበር ውለታ የሚውለው ። አኮሰታተሩ አዲስ ሰው አያቀርብም ። የቀረበው ሁሉ ግን ይወደዋል ። ዝናብ ይወድ ነበር ። ፀሃይ ከረረ ብሎ አይነጫነጭም ብርድ ነው ሙቀት ነው እያለ ስለ አየር ሁኔታው አያብራራም ። ከተፈጥሮ ጋ ሲጨቃጨቅ ሰምቼው አላቅም ።

አባቴን እወደዋለሁ ። አይኑ ላይ የማየው ቸርነት እና ፍቅር የትም ስፍራ የትም ፊት ላይ አይቼው አላውቅም ። ምንም ነገር ለኔ ከሆነ ሲሳሳ አይቼ አላውቅም ። አለም ላይ ብቸኛ እንድበልጠው የሚፈልገው አባቴ ነው ።

አባቴ ሲናፍቀኝ ፎቶውን አያለሁ ኮቱን እለብሳለሁ ። ያለኝን አስታውሳለሁ ። ሳላማርር እናፍቀዋለሁ ። ከተፈጥሮ ጋር ሳልጨቃጨቅ ያወረሰኝን መልካምነት እኖረዋለሁ ።

መልኬን እምወደው ስለማምር አይደለም እሱን ስለምመስል ነው። አምሳያዬ ሶስት ቀን ብሎኝ ያውቃል ። እሱ እወዳቸዋለሁ ያለኝን ሰዎች ሁሉ እወዳቸዋለሁ ።
ናፈቀኝ .....ማግኘት የሌለበት ናፍቆት ደስ አይልም መሰለኝ ።

© Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

06 Dec, 16:32


Channel photo updated

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

06 Dec, 16:29


እያወራን ነው ከባሌ ጋር ። እሱ አልጋው ላይ ጋደም ብሏል አልጋው ጠርዝ ላይ ቢጃማዬን ለብሼ ቀሚሴን እስከጉልበቴ ገልቤ በእጄ የቆነጠርኩትን ግሪሲሊን ጉልበቴን፣ ጭኔን ፣ ቁርጭምጭሚቴን ... እየቀባባሁ ነው።

ከላይ ነጭ ፓካውንት፣ ከስር ቱታ ለብሶ አንዴ ስልኩን አንዴ TVውን ያያል። Televisionኑ የትዝታ ዘፈን ያስመለክታል። ዘፈኑ የድሮ ቢሆንም በአዲስ ክሊፕ አዲስ ቆንጆ ድምፅ ያለው ልጅ እየዘፈነው ነው ።

🎼🎼🎼🎼

ሞት አደላድሎኝ አፈር ካልተጫነኝ
ቃሌን አላጥፈውም ካንቺ ጋር ነዋሪ ነኝ
ውበትሽ ኩራዜ ይበራል ከቤቴ
ጠረንሽ ፈውሴ ነው የፍቅር እመቤቴ
ሞት አደላድሎኝ አፈር ካልተጫነኝ ቃሌን አላጥፈውም 🎶🎶

"ክሊፑ ላይ ያለችው ልጅ የድሮ እጮኛዬን ትመስላለች።" አለ ፈገግ እያለ አፈጋገጉ እንደናፈቀችው አይነት ነው ።

ስቀብጥ ይሁን ስጃጃል፣ ወይም የጎጆ እና የትዳር ቀመር ስላልገባኝ የድሮ ፍቅረኛው ስላላት ልጅ ጠየኩት ።

ትክዝ እንደማለት አለና ሲያፈጥበት ከነበረው የሙዚቃ ክሊፕ አይኑን ነቅሎ ሲነካካው የነበረውን ስልክ አስቀመጠው ።

"እወዳት ነበር በጣም ። ስትናፍቀኝ ብንጣላም እኔ ካላሁበት ብትርቅ ፣ አላገኝህም ብትልም የትም ሄጄ አያት ነበር ...ስታኮርፈኝ የበለጠ ማግኘት እፈልግ ነበር...።" ሳቅ ነገር አለ ።

"እሷ ላይ ከቻቻ ነበርኩ ! ቀልድ ትችላለች ፣ ኩርፊያዋም፣ አሳሳሟም፣ አደናነሷ ፣ አስተቃቀፏ፣ ግልፅነቷን እወደው ነበር .... ደስስ ትላለች" ደማቅ ፈገግታ ፈገግ አለና "ናይል እኮ እብድ ነገር ነች " አለ ።

"አለ ኣ ደስ የምትል እብድ : ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሳልፈናል... " እያለ እየተመሳሰጠ ያለ ይሉኝታ አብራራልኝ ።

የእሷን እሩብ ያህል እንደማይወደኝ አይነት ነው ሁኔታው ። ላየሁት.. ላሳየኝ ማረጋገጫ ይሰጠኛል፣

ከትላንት ዛሬ አይበልጥም?

ለምኖ ላገባት ለልጆቹ እናት ይሄ ይነገራል ? ፣ የልጆች እናትስ እኔ የጠየኩትን ትጠይቃለች? ፣

የተጠየቀ ነው በሃላፊነት መመለስ ያለበት ? ወይስ ጠያቂው ነው ተጠያቂ ??

ስንት ጥልፍልፍ መንገድ አብረን መጣን አይደል? ፣ስንት የሃሳብ ዳገት ተጓዝን አይደል ?፣ የተሸከምነው የወጣነው የወረድነው የግዜ መዓት ትንሽ ይሉኝታ እንኳን እንዴት አልወለደበትም ?፣

ለጎጇችን ብዙ ገንዘብ ስለሚያመጣ ነው?፣ ዘመዶቿ አቅም የላቸውም ቢከፋት አትሄድም ብሎ ነው?፣ ወልዳለች ፈላጊ የላትም ብሎ ነው ?፣ ስለማይወደኝ ስለሚሰማኝ ስሜት ግድ ስለሌለው ነው ?፣

አይውደደኝ እንዴት አያከብረኝም ?፣

እውነት የሆነ ሁሉ ይነገራል ?፣ ሳይሰክር ሳንጣላ ሳላናድደው እንደዚህ ግዴለሽ እንዴት ይሆናል ?!፣
ይሉኝታና ብስለት ካልከለለን ልባችን ያባውን፣ ያደረግነውን ሁሉ ፣ የተሰማንን ሁሉ ቢወራ መች ኑሮ ፡ጎጆ ይመሰረታል?

ብቻ አመመኝ ...አለመወደድ በመላ አካሌ ተርመሰመሰ ማምለጫ የሌለው ህመም ተላወሰኝ ... እንደዋዛ የማይተው ሰው ሲወጋ ህመሙ ይለያል !!

የተሰማኝ ህመም እንዳልታመን ፣ እንዳልወደው፣ እንዳልጠነነቅለት ሊያደርገኝ የገፋኝ መሰለኝ ።

የቱ ጋ ነው የወጋኝ ?!

ቁስሉ ያልታየ ህመም ለመታከም ምቹ አይደለም !!

© Adhanom Mitiku

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

06 Dec, 16:28


Channel photo updated

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

06 Dec, 16:19


Channel name was changed to «አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku»

አድኃኖም ምትኩ -Adhanom Mitiku

12 Sep, 15:08


Channel created